YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአሊባባ መስራች ጃክ ማ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን በምርምር ለማግኘ $14 ሚሊዮን ዶላር ለቻይና ለምርምር ተቋማት ረድቷል:: $144 ሚሊዮን ዶላር ለቻይና የምርመራ ቁሳቁስ መግዣና ለህክምና መድቧል::

የፊት ማስክ 1 ሚሊዮን ለጃፓን: 1 ሚሊዮን ለኢራን: 1.8 ሚሊዮን ማስክና 800ሺህ ቁሳቁስ ለአውሮፓ ረድቷል:: ለአሜሪካ ለመርዳት ቃል የገባው 1 ሚሊዮን ማስክ እና 800 ሺህ ቁሳቁስ እየተጠበቀ ነው:: አሁን ደግሞ ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ! እናመሰግናለን!

ሌሎችም ከያሉበት በገንዘብ: በቁሳቁስ: በሙያቸውም ሆነ በጸሎታቸው ይህንን እጅግ ክፉ ግዜ ለማልፍ ተጨባጭ ድጋፍ ለአገራቸውና ለወገናቸው እንደሚያደርጉ ይጠበቃል::

Via:- Fistum Arega
@Yenetube @Fikerassefa
#ቁጥሩ_4_ደርሷል

አዲስ 3 ኮሮና ቫይረስ ያለበት ግለሰብ እንዳለ የኢትዮጵያ ጤና ሚንስትር አሁን በላከው መግለጫ አስታውቋል ።

ሁለቱ ጃፓናዊያን ሲሆኑ የ44 አመት እና 47 እድሜ መሆናቸውም ተገልጷል። አንዱ ደሙ ኢትዮጵያ ዜጋ ሲሆን 42 አመት መሆን ተገልጷል።
@YeneTube @Fikerassefa
#ቁጥሩ_4_ደርሷል_ኢትዮጵያ

አዲስ 3 ኮሮና ቫይረስ ያለበት ግለሰብ እንዳለ የኢትዮጵያ ጤና ሚንስትር አሁን በላከው መግለጫ አስታውቋል ።

ሁለቱ ጃፓናዊያን ሲሆኑ የ44 አመት እና 47 እድሜ መሆናቸውም ተገልጷል። እንዲሁም አንዱ ደሙ ኢትዮጵያ ዜጋ ሲሆን 42 አመት መሆን ተገልጷል።

@YeneTube @Fikerassefa
በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 4 ደርሷል ኢትዮጵያ

-ከጃፓናዊ ጋር ንክኪ አላቸው ተብሎ የተጠረጠሩት ቁጥር 117 ደርሷል እነዚህ ሰዎች በለይቶ ማቆያ የቅርብ ክትትል እየተደረገባቸው ይገኛል።

-ከነዚህ ምርመራ ከተወሰደላቸው እና የቅርብ ንኪኪ ካላቸው ግለሰቦች መሃከልም ሶስት ግለሰብ በቫይረሱ ተይዘዋል። ከነዚህም ውስጥ ሁለቱ የ44 አመት የ47 አመት ጃፓናዊ ዜጋ ሲሆኑ አንደኛውን ደግሞ የ42 አመት ኢትዮጵያዊ ነው።

-ሁሉም የአዲስ አበባ ውስጥ የሚሰሩ እና እና ቫይረስ ከተገኘበት የመጀመሪያ ግለሰብ ጋር የቅርብ ንኪኪ የነበራቸው ናቸው።

@Yenetube @Fikerassefa
በኮሮናቫይረስ ተጠርጥሮ ከአምቡላንስ ያመለጠው ወጣት ያደረገው ምንድን ነው?

ይህንን ለማጋራት በ ኢሜይል ይህንን ለማጋራት በ ፌስቡክ ይህንን ለማጋራት በ ትዊተር ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ

አንድ ከሳዑዲ አረቢያ የተመለሰ ግለሰብ የኮሮናቫይረስ ምልክት ታይቶበት ተጠርጥሮ ወደ ለይቶ ማቆያ በአምቡላንስ በሚወሰድበት ጊዜ አምልጦ ወደ ትውልድ መንደሩ በመመለስ ላይ ሳለ በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ በቁጥጥር ስር መዋሉን የወረዳው የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ለቢቢሲ አስታወቀ።

ቢቢሲ ስለግለሰቡ ከአካባቢው ነዋሪዎች ባደረገው ማጣራት ነዋሪነቱ እዚያው ለጋምቦ ወረዳ ተወልዶ ያደገ ወጣት ሲሆን በሕገ ወጥ መንገድ ከአንድ ወር በፊት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለሥራ ተጉዞ የነበረ መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል።
ነገር ግን በስደት ለአንድ ወር ከቆየ በኋላ በሳዑዲ አረቢያ ፖሊስ ተይዞ ወደ ኢትዮጵያ መላኩን የወረዳው ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌትነት አበባው ተናግረዋል።

በመሆኑም ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በተደረገለት ምርመራ የኮሮናቫይረስ ምልክትቶች ስለታዩበት በአምቡላንስ ወደ ለይቶ ማቆያ ቦታ ሲወሰድ አምቡላንሱን ሰብሮ በማምለጥ እዚያው አዲስ አበባ ወደሚገኘው የእህቱ ቤት እንዳመራ ኃላፊው ይናገራሉ።

ይህ መቼ እንደሆነ ቀኑን ለማወቅ እንዳልቻሉ አቶ ጌትነት ገልጸው፤ ትናንት ከፌደራል ጤና ጥበቃ ተደውሎ የአካባቢው ተወላጅ የሆነው ግለሰብ በኮሮናቫይረስ ተጠርጥሮ እንደነበርና ለይቶ ማቆያ ከመግባቱ በፊት እንደጠፋ እንደተነገራቸውና ክትትል እንዲያደርጉ መረጃ እንደደረሳቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል።

ከዚህ በኋላም የአካባቢው ባለስልጣናት ከቅዳሜ ምሽት ጀምሮ ወደ አካባቢው የሚመጡ መኪኖች ላይ ፍተሻ በማድረግ ግለሰቡን ለማግኘት ክትትል ሲያደርጉ ቆይተዋል።

አቶ ጌትነት እንዳሉት የግለሰቡን ወንድም አብሯቸው እንዲሆን በማድረግ በመኪና ከሚጓዙ መንገደኞች መካከል ተፈላጊውን ለመለየት ጥረት ማድረጋቸውን አመልክተው ዛሬ [ዕሁድ] ጠዋት 5 የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችን ከፈተሹ በኋላ ስድስተኛው ላይ ተጠርጣሪው መገኘቱን ገልጸዋል።

ከተፈላጊው ግለሰብ ጋርም ከአዲስ አበባ ጀምሮ ወደ ትውልድ መንደሩ ለማድረስ የተጓዘው የእህቱ ባልም አብሮት መገኘቱን ተነግሯል።
ክስተቱን የበለጠ ውስብስብ ለማድረግም ከአዲስ አበባ ቀጥታ ወደ ሚፈልገው ቦታ የሚያደርሰው ትራንስፖርት ከመያዝ ይልቅ በተለያዩ ከተሞች ላይ እየወረደ መጓጓዣውን ሲቀይር እንደነበር ተገልጿል።

በዚህም መሰረት ከክትትሉ ለማምለጥ በሚልም ኮምቦልቻ፣ ደሴና ጉጉፍቱ የሚባሉ ከተሞች ላይ ወርዶ መኪና መቀየሩንና መጨረሻ ላይም ጉጉፍቱ ላይ በሳይንት መኪና ሲጓዝ ለጋምቦ ላይ መያዙን ኃላፊው አረጋግጠዋል።

ግለሰቡና አብሮት የነበረው የእህቱ ባለቤት በትራንስፖርት አብረዋቸው ከተጓዙት ሰዎች ባሻገር ከሌሎች ጋር እንዳይገናኙ በማድረግ በለይቶ ማቆያ ውስጥ በመሆን ምርመራና ክትትል ወደሚያገኙበት ወደ አዲስ አበባ ክትትሉ ሲያደርጉ በነበሩት የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሠራዊት አባላት ታጅበው እንዲሄዱ ተደርጓል።
ግለሰቡ ተሳፍሮበት በነበረው ውስጥ የነበሩት ወደ 60 የሚደርሱ ሰዎች ምርመራ ተደርጎ ውጤት እስኪታወቅ ድረስ ድንኳን ተዘጋጅቶ ለብቻቸው እንዲቆዩ እንደሚደረግም አቶ ጌትነት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ከዚህ ባሻገር ግን በተለያዩ ከተሞች ውስጥ ከተሳፈረባቸው መኪኖች ላይ አብረውት የተጓዙትን መንገደኞች ለማወቅ አስቸጋሪ መሆኑን ገልጸው፤ የግለሰቡ የምርመራ ውጤት ቀጣይ መወሰድ ያለበትን እርምጃ የሚወስን መሆኑን የአካባቢው ባለስልጣናት አመልክተዋል።

Via:- BBC
@YeneTube @Fikerassefa
#ኬንያ

ኬንያ ቫይረሱን ካለባቸው ሀገራት የሚመጣን ሰው ወደ ኬንያ እንደማይገባ አስታውቃለች እንዲሁም መግባት የሚችሉት ኬንያዊያን ብቻ ነው የሚገቡትም እነሱም ለ14 ቀን ለይቶ ማቆያ እንደሚገቡ አስታውቋል።

@Yenetube @Fikerasssefa
ጋና - አንድ ተማሪ በኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ከተገኘ ብኃላ

- ዩንቨርቲዎቿን ዘግታለች

- ሀይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች እንዳይደረጉ መልክት ተላልፏል

- ማንኛውም ስፓርታዊ እንቅስቃሴዎች እንዳይደረጉ ተውስናል

- ተማሪዎች ወደ ካምፓስ እንዳይሄዱ ተነግሯቸዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
አስም አለቦት? ካለቦት በጥንቃቄ ያንብቡት

አስም እና ኮሮና ቫይረስ አስም ታካሚዎች በኮሮና ቫይረስም ሆነ በሌሎች የመተንፈሻ አካልን በሚያጠቁ ቫይረሶች ከተያዙ የአስም በሽታ መቀስቀስ (ትንፋሽ ማጠርና ደረትን የሚጫን ስሜት) ሊገጥማቸው ይችላል፡፡ ይህም አደገኛ ሊሆን ይችላል፡፡

ስለዚህም አስም ታካሚዎች የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ማድረግ ይገባቸዋል!

1.አለመደናገጥ

2.ስሜት ቢኖርም ባይኖርም በየዕለቱ መወሰድ ያለበቸውን የአስም መቆጣጠርያ መድሃኒቶች (Controllers) በአግባቡ መውሰድ

እነዚህን መውሰድ አስም እንዳይቀሰቀስ ወይም ከተቀሰቀሰም በከፍተኛ ደረጃ እንዳይቀሰቀስ ይረዳል።

3.የማረጋግያ (Reliever) መድሃኒትዎን በሁሉም ጊዜና ቦታ ከእርስዎ አይለይ - በተለይም ሳልቡታሞል (ቬንቶሊን).

4.በቫይረሱ ላለመጠቃት መሰረታዊ የመከላከያ መንገዶችን በአግባቡ መተግበር:-

ሀ. እጆችን ሁልጊዜ መታጠብ

ለ.እጅ መጨባበጥና ሌሎች አካለዊ ንክኪዎችን ማስቀረት።

ሐ.ባልታጠበ እጅ አይን፣ አፍንጫ እና አፍን አለመንካት መ.ከታመመ ሰው ጋር በቅርበት ብዙ ጊዜ አለማሳለፍ፣ መጠቀምያ ቁሶችን አለመጋራት

5.የአስም ስሜቶችዎ የሚባባሱ ከሆነ ኃኪሞትን ማማከር

6."አዲስ" ሳል ወይም "አዲስ" ትኩሳት ከተሰማዎት እና/ወይም በቫይረሱ እንደተጠቁ ከጠረጠሩ ወድያውኑ የፊት መሸፈኛ ማስክ ማድረግ፣ ራሶትን መለየትና ኃኪሞትን ማማከር


ለሚመለከተው ሰው Forward አድርጉ
@Yenetube @Fikerassefa
Afaan oromoo Version⬇️

Asmii qabduu? Yoo qabaattan of eeggannoon dubbisaa.

Asmii fi vayrasii koronaa
Yaalamtoonni asmii fi vayrasii koronaanis ta'ee vayrasoonni qaamolee hargansuu miidhaniin yol qabaman dhukkuba asmii namatti kaasuu( hafuurri hanqachuu fi laphee ykn qomatti nama ulfaachuun) isaan muudachuu ni danda'a.

Kanaaf yaalamtoonni asmii of eeggannoo kanaa gadii gochuu qabu.
1. Nahuu ykn sodaachuu dhiisuu

2 fedhiin jiraatus/ jiraachuu yoo baates qoricha asmii too'atan(controllers) seeraan fudhachuu hin dhiisinaa.
Kana gochuun asmiin akka isinitti hin kaane yoo ka'es akka sadarkaa olaanaa irra hin geenye ittisa.

3 Qorichi isinirraa laaffisu (reliever) bakkaa fi yeroo kamittuu isinirra akka adda hin baane.
4 vayrasichaan hunamuu irraa karaalee of eeggannoo seeraan hordofuu.

A. Harka yeroo hundaa dhiqachui.

B. Harka walfuudhuufi wol tuttuqqaa kamiinuu dhiisuu.

C. Harka hin dhiqanneen ijaan
funyaan tuttuquu dhiisuu.
D. Nama dhibamutti dhiyaatanii yeroo hedduu dabarsuu dhiisuu.

E. Meshaalee wojjiin fayyadamuu dhiisuu.

5. Mallattooleen asmii yoo hammaataa dhufan ogeessa fayyaa haasofsisuu.

6. Qufaan/ hoo'i haaraan yoo isinitti dhagayamee ykn vayrasiidhaan qabamuu yoo shakkitan yerooma san haguuggi fuulaa godhachuufi qophaatti of baasuu.


Nama ilaallatuuf forward godhaa!"
@Yemetube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ ተጨማሪ ሶስት አዲስ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ነው የተገኘው ይሁን እንጂ #አንጋፋው ጋዜጠኛ #ጌጡ_ተመስገን አራት ተጨማሪ አዲስ በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተዋል ብሏል።

ከ27 ደቂቃ በፊት Edit እንዲያደርገው መልክት ልከናል።

መልስ የለም 🙌
#ይመለከተኛል
#ያገባኛል
ጣልያን ህመሟ ብሶባታል!!

በጣልያን ዛሬ ብቻ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ሰው ቁጥር 3,590 መሆኑ ተነግሯል ይህ በእንዲህ እንዳለ በኮሮና ቫይረስ ዛሬ ብቻ የሞቱት 368 ነው እንዲሁም በአጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 24,747 ሲደርስ የሟቾች ቁጥር ደግሞ 1809 ደርሷል።

@Yenetube @Fikerassefa
ኮሮና ቫይረስ ተጠቂ እና ሞት ብዙ የተመዘገበባቸው ሀገራት ዛሬ ብቻ

➡️ጣልያን :- 3590 አዲስ ታማሚ : 368 ሰው ዛሬ ሞቷል።

➡️ጀርመን :- 1632 አዲስ ታማሚ : 4 ሰው ዛሬ ሞቷል።

➡️ስፔን :- 1452 አዲስ ታማሚ : 96 ሰው ዛሬ ሞቷል።

➡️ኢራን :- 1209 አዲስ ታማሚ : 113 ሰው ዛሬ ብቻ ሞቷል።

➡️ፈረንሳይ :- 924 አዲስ ታማሚ : 36 ሰው ዛሬ ብቻ ሞቷል።
@Yenetube @Fikerassefa
አሜሪካ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባትን ልትሞክር ነው

አሜሪካ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባትን በሙከራ ደረጃ ዛሬ መስጠት እንደምትጀምር አስታወቀች፡፡

የአሜሪካ ባለስልጣናት እንዳስታወቁት፣ዛሬ የሚሰጠዉ የሙከራ ክትባት በ45 ፈቃደኛ ሰዎች ላይ የሚከናወን ሲሆን ክትባቱ ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንደማያደርስ ነዉ የተነገረዉ፡፡

ምርምሩን የሀገሪቱ ታላላቅ የጤና ተቋማት/የአሜሪካ ብሄራዊ ጤና ተቋም፣ዋሽንግተን ሄልዝ ሪዘርች ኢንስቲትዩት፣ NIH and Moderna Inc እና ሌሎችም በጋራ ሲያካሂዱ መቆየታቸዉን ኤ ፒ ጽፏል፡፡

ሀገራት የመከላከያ ክትባቱን በእጃቸዉ ለማስገባት ከፍተኛ እሽቅድምድም ላይ በሆኑበት በዚህ ሰዓት አሜሪካ ወደ ማረጋገጫ ሙከራ ተሸጋግራለች፡፡

በዋናነትም ክትባቱ የመከላከል አቅሙ ዘለቄታዊ እንዲሆን ብዙ ጥረት መደረጉንም ዘገባዉ ጠቁሟል፡፡

የሀገሪቱ የጤና ባለሙያዎች ግን አሁንም በስራዉ እርካታ እተሰማቸዉ እንዳልሆነ እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡

ለኮቪድ 19/ኮሮና ቫይረስ ፍቱን የሆነ ክትባትን በጥራትና በብዛት አምርቶ ለዓለም ህብረተሰብ ለማቅረብ ከአንድ ዓመት እስከ አንድ አመት ተኩል የሚሆን ጊዜን ይጠይቃል ብለዋል፡፡

ኢኖቪዮ ፋርማስቲዩካልስ የተባለ ተቋምም እንዲሁ በግሉ በቻይናና ደቡብ ኮሪያ ምርምር ሲያደርግ መቆየቱንና ድካሙ አወንታዊ ዉጤት በማስገኘቱ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ሙከራየን አደርጋለሁ እያለ ነዉ፡፡

የኤን-አይ-ኤች ዓለም ዓቀፍ ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት ዶር አንቶኒ ፋዉሲ እንደሚሉት ክትባቱ ለጊዜያዊ መፍትሄም ቢሆን ተስፋ ሰጭ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

እርሳቸዉም ቢሆን ክትባቱ በሰዎች ላይ የጎንዮሽ ጉዳት እንዳያደርስና ለብዙሃኑ ተደራሽ ለማድረግ ተጨማሪ ጥናትን ይጠይቃል ባይ ናቸዉ፡፡

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም ክትባቱ በቶሎ መሰጠት እንዲጀመር ግፊት እያደረጉ መሆኑ ነዉ ተገለጸዉ፡፡

በአሜሪካ በአሁኑ ወቅት በኮሮና ቫይረስ ከ50 በላይ ሰዎች ሲሞቱ 3 ሽህ የሚሆኑት ደግሞ ተጠቅተዋል፡፡

Via:- Ethio FM
@Yenetube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ያሉ ትምህርት ቤቶች ላልሰተወሰነ ቀን በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት ሊዘጉ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በጉዳዩ ላይ መንግስት ዛሬ መግለጫ ይሰጣል።
Via:- Tsefay Getnet
@Yenetube @Fikerassefa
ምክር ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ :-

- እድሜያችሁ ከ60 አመት በላይ ከቤት ባትወጡ ይመከራል

- አስም ያለባችሁ በጭራሽ ከቤት አትውጡ

- ወጣተችም ህዝብ የተሰበሰበበት አከባቢ ማዘውተር ቀንሱ

- እጃችን ሳትታጠቡ በፍፁም አይናችሁን : ጆራችሁን : አፊንጫችሁን እንዲሁም አፋችሁን አትንኩ❗️

- እጃችሁን ታጠቡ❗️ እጃችሁን ታጠቡ ❗️

ጠቃሚ መረጃዎች ከምንጊዜው በተለየ በቻናላችን ያገኛሉ ከቤት መውጣት አይጠበቅቦትም

🌄 :- Zeamanuel
@Yenetube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Harka keenya saamumaan dhiqachuun kornavaayrasii irraa if haa eegnu
#COVID19
#SafeHands

Via Jawar Mohammed
@Yenetube @Fikerassefa
ምርጫ ቦርድ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ሰራተኞቹ ለዛሬ ከቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ አደረገ። መስሪያ ቤቱ ከውሳኔው ላይ የደረሰው ለቦርዱ ቴክኒካዊ ድጋፍ ከሚሰጡ የውጭ ሀገር ባለሙያዎች መካከል አንድ ግለሰብ የቫይረሱ ምልክቶች ስለታዩበት ነው።

Via:- Election 2012
@Yenetube @Fikerassefa
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በትምህርት ቤቶች እንዳይስፋፋ የቅድመ ጥንቃቄ ስራ እየሰራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ወይዘሮ ሐረጓ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ቫይረሱ በትምህርት ቤቶች እንዳይስፋፋ ትምህርት ቤቶች ከጤና ተቋማት ጋር በትብብር እየሰሩ መሆኑን ነግረውናል።

እስካሁን ባለው መረጃ ቫይረሱ ከአዲስ አበባ ውጪ አልተከሰተም ያሉን ወይዘሮ ሐረጓ ተማሪዎች እና መምህራን ከቫይረሱ እራሳቸውን እንዲጠብቁ በትምህርት ሚኒስቴር ቴሌዥን እና በትምህርት በሬድዮ ፕሮግራሞች እያስተማርን ነው ብለዋል።

በቫይረሱ ስርጭት ሳቢያ ትምህርት ቤቶች ሊዘጉ ይችላሉ? በሚል ላነሳንላቸው ጥያቄም አሁን ላይ ትምህርት ቤቶችን መዝጋት የሚያስገድድ ሁኔታ የለም ይሁንና መንግስት በቀጣይ ውሳኔ ይሰጥበታል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

Via:- Ethio FM
@Yenetube @FikerAssefa