YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የዓለም የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በካፒቴን አምሳለ ጓሉ አብራሪነት ከአዲስ አበባ የተነሳው አውሮፕላን በዋሺንግተን ዳላስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በደረሰበት ወቅት ሞቅ ያለ አቀባበል ጠብቆታል።

Via VOA
@YeneTube @FikerAssefa
ባይብል ኮድ

ስለ እያንዳንዳችን ዕጣ ፈንታ ጨምሮ በአለም ላይ ያሉ መሪዎች ስለሚገደሉበት ቦታ፣ ስለሚገድሏቸው ሰዎች ስም…

በአለም ላይ ስለተከናወኑ ነገሮችና ወደፊትም ስለሚከናወኑ ነገሮች ሁሉ በስም፣ በቀንና በቦታ ሳይቀር ከዛሬ ሶስት ሺ አመት በፊት…

በየቤታችን በሚገኘው መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ በኮድ ተቀጧል!!

በአንድ ምሽት ሽያጭ ብቻ ሪከርድ የያዙት ባይብል ኮድ ቁጥር 1፣ ቁጥር 2 እና የመጨረሻው ቁጥር 3 ኮዶቹን እየፈቱ ያስደምሙናል፡፡

ሶስቱንም መጽሐፎች በየመፅሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኟቸዋል፡፡
@teklutilahun
ግራ አጋቢው ዘመን
አዲስ መፅሐፍ በገበያ ላይ

የወባ ትንኞችን ከመግደል ሀሳቦችን ወደ መግደል፤
ከስራ አጥነት ወደ ስራ አልባነት እያመራን ነው… ምን ይሻላል?

ግራ አጋቢው ዘመን መፅሐፍ መፍትሄ አለው፡፡

መፅሐፉ እንዴት ከጀግንነት ወደለየለት ብሔርተኝነት፣
ከኃይማኖተኝነት ደግሞ ወደ ሽብርተኝነት እያመራን እንዳለን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ መጨረሻችንስ?

መልሱ ግራ አጋቢው ዘመን መፅሐፍ ውስጥ ይገኛል፡፡

እንኳን ወደ ግራ አጋቢው ዘመን መፅሐፍ ግራ ተጋብተው መጡ!!

የእውነት ይሄ መፅሐፍ አስተሳሰባችሁን ያሰፋዋል!!

በየመፅሀፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል!!
Forwarded from YeneTube
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEmpJPx72XxnzEFGQg

🔖እናስተዋዉቅዎ! AmAzON BrAnD® ገበያ
ሱቅ ለሱቅ መሄድ ሳይጠበቅቦት ባሉበት ቦታ ሆነው ውስን እቃዎችን በማይታመን ዋጋ ሚገኙበትን ማወቅ ይፈልጋሉ እንግዲያውንስ ይሄን የቴሌግራም ቻናላችንን ሊንክ በመጫን የፈለጉትን ይምረጡ ይዘዙ
.
ብራንድ ጫማዎች የወንድም የሴትም
ብራንድ ልብሶች የወንድም የሴትም
ብራንድ ሸሚዞች ቲሸርቶች
ብራንድ ቱታዎች ሹራቦች እንዲሁም ጃኬቶች በወንድም በሴትም
ብራንድ ቦርሳዎች
የእጅ ጌጣጌጦች
ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
ሀገር ውስጥ ውስን የሆኑ መዋብያ እቃዎች ሽቶዎች
.
እንዲሁም በግል የቴሌግራም አካውንት ማዘዝ የምትፈልጉ እቺን ሊንክ በመጫን ያናግሩን @KALID67 እንዲሁም በስልክ ቁጥራችን +251954833467 ደውለው ይዘዙን
.
በተጨማሪም አዲስ አበባ ለምትገኙ ደንበኞቻችን ይዘዙን ያሉበት ድረስ እናመጣለን ክፍለ ሀገር ለምትገኙ ደንበኞቻችን ባዘዙን በ48ሰአት ውስጥ በፖስታ ቤት ወይም በሹፌር እናደርሳለን ታማኝነት መገለጫችን AmAzON BrAnD® ገበያ
online shopping is always a good idea!!
Forwarded from HEY Online Market
Acer predator (i7, 9th gen)
Ram: 16 GB
Hard disk: 1tb+256gb ssd
Graphics: 6 GB NVDIA Graphix 1660ti
Price : 55,500 birr

Acer predator (i7, 8th gen)
Ram: 16 GB
Hard disk: 256gb ssd
Graphics: 6 GB NVDIA Graphix
Price : 47,500 birr

Contact us @heymobile
0953964175
0925927457
0910695100
በሜክሲኳዊዉ የአደንዛዥ እጽ ዝዉዉር እና የወንጀለኛ ቡድን መሪ ኤል ቻፖ ስም አዲስ የቢራ ብራንድ መሰየሙን የኤል ቻፖ ሴት ልጅ አስታወቀች፡፡

የቢራዉ ስያሜ “El Chapo 701” 701 ቁጥር የተመረጠዉ እ.ኤ.አ በ2009 ኢል ቻፖ የአለማችንን 701ኛ ቱጃሩ ሰዉ ነዉ ሲል የሀብታሞችን ዝርዝር የሚያወጣዉ ፎርብስ ማሳወቁን ተከትሎ ነዉ፡፡ቢራው 4% የአልኮል ይዘት ያለዉ ሲሆን በ355 ሚ.ሊ ጠርሙስ ቀርቧል፡፡

በሰሜንና ደቡብ አሜሪካ በግለሰቦች ስም ቢራ ማቅረብ የተለመደ ሲሆን በአርጀንቲና የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች በፓርቲያቸዉ ስም የቢራ ብራንድ አላቸዉ፡፡አንዱ የፓርቲ አባል የሌላኛዉን ፓርቲ የቢራ ብራንድ አይጠጣም።

Via:- ብስራት ራዲዮ
@Yenetube @Fikerassefa
በቻይና በኮሮና ቫይረስ የተጠረጠሩ ሰዎች ያረፉበት ሆቴል ተደርምሶ አራት ሰዎች ሞቱ

በቻይና ፉጃን ግዛት ኳንጁ ከተማ ሺንጃ የተባለ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ተደርምሶ በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥረው በሆቴሉ ህክምና ሲያገኙ ከነበሩ ሰዎች አራት ሰዎች ትናንት ቅዳሜ ለሊት እንደሞቱ ቢቢሲ ዘግቧል።
የመጀመርያ ደረጃው አየታደሰ የነበረው ይሄ ሆቴል 71 ሰዎች የነበሩት ሲሆን 47ቱን ከፍርስራሹ ማውጣት ተችሏል።

80 ክፍሎች ያሉት ይሄ ሆቴል ከሁለት አመት በፊት ስራ የጀመረ ሲሆን በቅርቡ በቻይና በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ሆቴሉ በበሽታው ለተጠረጠሩ ሰዎች ማረፍያና ማከሚያ ሆኗል።

Via:- Tesfay Getnet / BBC
@Yenetube @Fikerassefa
ኢራቅ ከኢራን ጋር ያለኝን ግንኙነት እንዳቋርጥ አሜሪካ ጫና እያደረገችብኝ ነዉ ብላለች፡፡

የቀድሞዉ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር አዴል-አብዱል-ማህዲ እንዳሉት፣ሀገራቸዉ ከኢራን ጋር ሽብርተኝነትን ለመከላከልና በቀጠናዉ የተረጋጋ ሰላም እንዲፈጠር መስራት ትፈልጋለች፡፡

ይሁንና ሀገሪቱ ይህን እንዳታደርግ በአሜሪካ ጫና እየተፈጠረባት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ማህዲ እንደሚሉት፣በመካከለኛዉ ምስራቅ ለሚፈጠር ቀዉስ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ የአሜሪካ ተጽዕኖ እንዳለበት ለፕሬስ ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

ቀደም ሲል ኢራንና ኢራቅ የዳኢሽ ታቅፊር ታጣቂ ቡድንን ለመደምሰስ በጋራ ለመስራት ሲንቀሳቀሱ አሜሪካ ኢራን በኢራቅ እየተገነባ ያለዉን ሰላም እየናደች ነዉ በሚል ስትወነጅል እንደነበር አይዘነጋም፡፡

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
ሰበር ዜና❗️የመግደል ሙከራ ከሸፈ

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሀምዱክ ላይ የመግደል ሙከራ ተሞክሮባቸው መክሸፉን የሀገሪቱ ሚዲያዎች በመዘገብ ላይ ናቸው።

የተደረገው ሙከራ በመኪና ላይ በተጠመደ ቦንብ እንደሆነም ሚዲያዎች ዘግበዋል።

BREAKING: Sudan's PM Abdalla Hamdok survives assassination attempt in Khartoum - state TV.

@Yenetube @Fikerassefa
የኮሮና ተሕዋሲ ወደ ኢትዮጵያ ቢገባ የካ ኮተቤ ሆስፒታል ሌሎች ሥራዎች አቁሞ ሕክምና እንደሚሰጥ ዶ/ርሊያ ታደሰ ተናገሩ። «በዚህ ሆስፒታል የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በማሟላት ባለሙያዎችን በማሰልጠን ሥራዎች እየተሰሩ ነው» ብለዋል።

Via:- Eshete Bekele
@Yenetube @Fikerassefa
በምዕራብ #ኦሮሚያ ሕገወጥ ድርጊቶችን ለማስቆም እየተወሰደ ባለው እርምጃ፣ በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ የቆዩ የ-#ኦነግ #ሸኔ አባላት እጃቸውን እየሰጡ እና እየተያዙ ነው ተብሏል፡፡

Via:- Sheger FM
@Yenetube @Fikerassefa
"አብሮነት ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት" (አብሮነት) የተሰኘው በኢዴፓ፣ ኢሃን እና ኅብር ኢትዮጵያ የተቋቋመ ቅንጅት ለምርጫው በጋራ ለመወዳደር የሚያስችለውን የስምምነት ሰነድ በመፈራረም ለኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ አስገባ

@Yenetube @Fikerassefa
#OMN ትናንት በኦኤምኤን የተላለፈን መልዕክት እየመረመረ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን መንግስት የሃሳብ ነጻነት በዴሞክራሲያዊ መንገድ እንዲያድግ የፖለቲካ ምህዳሩን ቢያሰፋም አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ፈር እየለቀቁ እንደመጡ መመልከቱን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጿል።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንደሰን አንዷለም እንዳሉት፥ ተቋሙ በሁሉም ዘርፍ የሚዲያ ነጻነት እንዲረጋገጥና የዴሞክራሲ ግንባታ ሂደቱን ለማገዝ ኢ ፍትሀዊ ሀሳቦች ሲተላለፉ በተለያየ መንገድ ለመፍታት እየጣረ ነው።

ባለፉት ስድስት ወራትም ለ49 የመገናኛ ብዙሃን ግብረ መልስ መሰጠቱን ጠቅሰው፥ ለአራት መገናኛ ብዙሃን ደግሞ የማስጠንቀቂያ መልዕክት በስልክና በደብዳቤ እንዲደርሳቸው ተደርጓል ብለዋል።

በሂደቱ የተወሰኑ ለውጦች ቢታዩም ከህገ መንግስቱም ሆነ ከብሮድካስት ባለስልጣን አዋጅ ተጻራሪ በሆነ መንገድ የሚጓዙ መገናኛ ብዙሃን መኖራቸውንም አንስተዋል።

አያይዘውም ባለስልጣኑ ከአንድነት ይልቅ ልዩነት ላይ ያተኮሩ እና ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ መገናኛ ብዙሃንን እንደማይታገስ አስረድተዋል።

ከዚህ አንጻርም ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩና ቁርሾ የሚፈጥሩ ሃሳቦችን በሚያስተላልፉ መገናኛ ብዙሃን ላይ በአዋጁ መሰረት እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምርም ተናግረዋል።
ትናንት በኦ ኤም ኤን የህዝቦችን አንድነት የሚሸረሽርና ቁርሾን የሚፈጥር መልዕክት ሙሉ ተንቀሳቃሽ ምስል ባለስልጣኑ እንደደረሰውም ገልጸዋል።

አሁን ላይ መልዕክቱ በባለሙያዎችና አመራሮች እየተገመገመ ሲሆን፥ በአጭር ጊዜ መረጃውን በማጥራት ውጤቱ ይፋ እንደሚደረግም አውስተዋል።

በማጣራት ሂደት ውስጥ የሚገኙ ውጤቶች የሚያስጠይቁ ሆነው ከተገኙም እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ መቃ ቀበሌ በተለምዶ ስጋጦሬ እየተበለ ከሚጠራው አካባቢ በቀን 27/06/2012ዓ.ም ከሱዳን ወደ ጎንደር ነዳጅ ጭኖ ሲጎዝ የነበረ አንድ የነዳጅ ማመላለሻ ቦቲ የኋላ ተሳቢው ላይ እሳት የተነሣበት በመሆኑ በወቅቱ በቲውን ሲያሽከረክር የነበረው ሹፌር ሾልቶውን ነቅሎ ያዳነው ቢሆንም የኋላ ተሣቢው ግን ከነጫነው ነዳጅ ሙሉ በሙሉ በሳት ተቃጥሏል፡፡

የነዳጅ ቦቲውን መኪና ሲያሽከረክር የነበረው አሽከርካሪ ሹፌርም በወቅቱ ለተገኙት የፅጥታ ሀይል እና ለትራፊክ ፖሊስ እንደገለፅው ለቦቲው ተሣቢ መቃጠል ምክንያቱ ጓማው በመሞቁ የተነሳ ወደሳት መቀየሩ ነው፡፡ ብሏል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ በወቅቱ ከተቃጠለው ቦቲ ነዳጅ ለመቅዳት ሙከራ ያደረገ አንድ በ13 እድሜ የሚገመት ህፃን ለሞት ተዳርጓል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ከኮሮናቫይረስ መተላለፊያ መንገዶች አንዱ በእጅ መጨባበጥ መሆኑን ተከትሎ በርካቶች የየራሳቸውን ሰላምታ መለዋወጫ መንገድ እየፈበረኩ ነው።

በሽታው የመነጨባት ዉሃን ነዋሪዎች ሰላምታ የሚለዋወጡት በእግር ሆኗል። በርካታ የዓለም መሪዎች ደግሞ በክርን መገጫጨትን መርጠዋል። የእስራኤል ፕሬዝደንት ኔታኒያሁ እንደ ሕንዶች 'ናማስቴ' ብንል ነው የሚሻለው ብለዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ደግሞ ፎቶ ላይ እንደተመለከተው ዓይነት ሰላምታ ይዘው ብቅ ብለዋል።

ምንጭ፡ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር/ቢቢሲ
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሀምዱክ ደህ ነኝ ሲሉ በቲውተር ገፃቸው ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል።
@YeneTube @Fikerassefa
እንግሊዝ በፈቃደኝነት በኮሮና ቫይረስ ተይዞ እራሱን ለክትባት ላዘጋጀ ሰው 130 ሺህ ብር እሸልማለሁ አለች።

በለንደን ያለ አንድ የጤና ፈጠራ ኩባንያ ለዓለማችን ገዳይ ለሆነው ለኮሮና ቫይረስ መድሃኒት በመቀመም ላይ መሆኑን አስታውቋል።

ኩባንያው ለዚህ የምርምራ ስራው እንዲያግዘው በጎ ፈቃደኞችን በመመልመል እና በዚህ ቫይረስ በማስያዝ ከዚያ በዚሁ ኩባንያ የተፈበረኩ የክትባት መድሃኒቶችን ለመወጋት ዛሬ ማስታወቂያ አውጥቷል።

ዴይሊ ሜይል እንደዘገበው ከሆነ ኩባንያው በዚህ ስራ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ለሆኑ ሰዎች 3 ሺህ 500 ዩሮ ወይም ከ130 ሺህ ብር በላይ እንደሚከፍል አስታውቋል።

ይህ ኩባንያ ለዚህ ምርምር 24 ሰዎችን እንደሚፈልግ ያስታወቀ ሲሆን በጎ ፈቃደኞችን እንደሚያገኝ ተስፋ እንዳለው ገልጿል።

እንግሊዝ ለቫይረሱን ለመከላከል ከ46 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ገንዘብ የበጀተች ሲሆን እስካሁን 273 ሰዎች በዚህ ቫይረስ ሲያዙ 3 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።

Via:- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa