YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from HEY Online Market
HP Probook
Core i7(6th generation )

Screen :15.6 inch
Storage : 1Tera (1000 GB)
Ram : 8GB
Battry: 5hours
Price :16,500 birr

0953964175
0925927457
0910695100
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ከዳውሮ ዞን ነዋሪዎች ጋር ለመወያየት ተርጫ ከተማ ገብተዋል!

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከዳውሮ ዞን ነዋሪዎች ጋር ለመወያየት ተርጫ ከተማ ገብተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅድሚያ በከተማዋ ስታዲየም ለተሰበሰበው ነዋሪ መልዕክት የሚያስተላልፉ ይሆናል።
በመቀጠለም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከዞኑ ነዋሪዎች ተወካዮች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ከ አምስት ሚሊዮን በላይ የመተንፈሻ አካላት ጭንብሎች ሊገዙ ነው!

የዓለም ስጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ በሽታ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ለሚደረገው የመከላከል ሥራ ተጨማሪ ከ5 ሚሊዮን በላይ የመተ ንፈሻ አካላት ጭንብሎች እንደሚገዙ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በተጨማሪ በ30 የየብስ ትራንስፖርት መዳረሻ የድንበር ኬላዎች ላይ በሽታውን ለመከላከል የሚያስችል የቁጥጥር ሥራ እየተደረገ መሆኑን ገለጸ፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ የውጭ ሀገራት ተጓዦች ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡባቸው ይችላሉ በሚባሉ 30 የየብስ ትራንስፖርት መዳረሻዎች እና የድንበር አካባቢዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ የሙቀት ልየታ ቁጥጥር እየተካሄደ ይገኛል። የድንበር ቁጥጥሮቹ በዋነኛነት በክልሎች የሚከናወን ሲሆን፣ በፌዴራል ደረጃ የድጋፍ ሥራ እየተከናወነ ነው።

እንደ ዶክተር ኤባ ገለጻ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ የበሽታው ስርጭት ከታወቀበት ጥር 15 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ከ431ሺ በላይ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ በየብስና በአውሮፕላን ገብተዋል።
ከእነዚህ ውስጥ 220 ሺ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በኩል የገቡ ሲሆን፣ የተቀሩት 211 ሺህ ሰዎች ደግሞ ከቦሌ ውጪ በሚገኙ በየብስ ተጓጉዘው የገቡ መሆናቸው ታውቋል። በመሆኑም ልክ እንደ አየር ማረፊያው ሁሉ በድንበር እና በተለያዩ ኬላዎች ላይ ጥብቅ የኮሮና ቫይረስ ቁጥጥር ተደርጓል። ይህም በሽታው ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ቦሌ ሞርኒንግ ስታር ሞል አካባቢ ያለ የእናት ባንክ ጥበቃ ሰራተኞች እርስ በርሳቸው ተጋደሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም ከአይን እማኞች እንዳረጋገጡት ከደቂቃዎች በፊት የእናት ባንክ ጥበቃ ሰራተኞች እርስ በርስ ተጣልተው ሶስት ሰዎች ሞተዋል።

አሁን ላይ ፖሊስ በስፍራው ደርሶ በማረጋጋት ላይ ይገኛል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከዳውሮ ነዋሪዎች ጋር በነበራቸው ውይይት፣ ድህነት እንዴት መከፋፈልን እንደሚያስከትል እና በአሁኑ ሰዓት የሚያስፈልገው ጀግንነት በአንድነት ሆኖ ታላቁን የሕዳሴ ግድብ ማጠናቀቅ እና ኢትዮጵያን ከራሷ አልፎ ለጎረቤቶቿ የኃይል ምንጭ ማድረግ እንደ ሆነ ተናግረዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እስካሁን ላሳኳቸው ምዕራፎች አድናቆታቸውን ገልጸዋል። በተለይም ሴት የውይይቱ ተሳታፊዎች፣ ሴቶችን ከፍ በማድረግ እና ወደፊት በማምጣት የሚታወቁ መሪ እንደ ሆኑ ተናግረዋል።ከተነሱት ዐበይት ጉዳዮች መካከል የውኃ አቅርቦት፣ ከከተሞች ዕድገት ሁኔታ ጋር የሚመጣጠን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እና የተጀመሩ የመንገድ ግንባታዎች መጠናቀቅ ይገኙበታል።

በተጨማሪም፣ የዳውሮ ቅርሶች እንዲመዘገቡ ደማድረግ እንቅስቃሴ እንዲጀመር፣ የኦሞ ሸለቆ እሴቶች ላይ የሚያተኩር ጥናት እና ምርምር እንዲካሄድ እና የቀርከሃ ኢንደስትሪ ተፈጥሮ ለሥራ ዕድል እንዲውልም ተጠይቋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለተነሱት ጉዳዮች ምላሽ ሲሰጡም፣ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያው እና በቅርቡ የሚጀመረው የ10 ዓመት ብሔራዊ ዕቅድ ቁልፍ ይዘቶች በዳውሮ ነዋሪዎች የተነሱትን ጥያቄዎች በተሟላ መልኩ ለመመለስ የሚያስችል አካሄድ እንዳላቸው ተናግረዋል።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ሞርኒንግ ስታር ሞል በሚገኘው እናት ባንክ ዶ/ር ጀንበር ተፈራ ቦሌ ቅርንጫፍ ሲሰሩ በነበሩ ሦስት የጥበቃ ሠራተኞች መካከል በተፈጠረ ለጊዜው መነሻ ምክንያቱ ባልታወቀ ጸብ የሦስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ዛሬ የካቲት 28 ቀን 2012 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት አካባቢ በሦስቱ የጥበቃ ሠራተኞች መካከል በተፈጠረው ያለመግባባት አንደኛው የጥበቃ ሠራተኛ በያዘው ክላሽን-ኮቭ ጠብመንጃ ሁለት የጥበቃ ጓዶቹን ህይወት አጥፍቶ የራሱንም ህይወት አጥፍቷል፡፡

ሟቾች ዕድሜያቸው ከ30 አስከ 35 ዓመት የሚገመቱ ጎልማሶች ሲሆኑ የጉዳዩን መነሻ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

Via Addis Ababa Police Commission
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብጽ ከህዳሴዉ ግድብ ጋር ተያይዞ ያላቸዉን ልዩነት በመነጋገር እንዲፈቱ የአፍሪካ ህብረት አሳሰበ፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳፋቂ ማህማት፣በሱዳን ሲያደርጉት የነበረዉን የሶስት ቀናት ጉብኝት ሲያጠናቅቁ እንዳሉት፣ተፈጥሯዊ ሀብቶቻችን የዕድገት እንጂ የግጭት መንስኤ ሊሆኑብን አይገባም ብለዋል፡፡ሙሳፋቂ ማህማት ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሃምዶክ ጋር ባደረጉት ዉይይትም ሶስቱንም ሀገራት ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ ተነጋግረዉ ልዩነቶቻቸዉን እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

የዋሽንግተኑ ድርድር ተስፋ የተጣለበት እንደነበር ጠቅሰዉ ይህ ዳር ባይደርስም ግን አሁንም ሀገራቱ መነጋገር እንደሚገባቸዉ ነዉ ያስታወቁት፡፡ሱዳንን በተመለከተ ባደረጉት ንግግራቸዉ፣ሀገሪቱ በመልካም የሽግግር ሂደት ላይ እንደምትገኝ ጠቅሰዉ የተዳከመዉን ኢኮኖሚዋን እንዲያገግም ለማድረግ ግን ዓለም አቀፋ ማህበረሰብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡አብደላ ሃምዶክ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በሱዳን ፖለቲካዉን ከማከም ባሻገር ኢኮኖሚዉ እንዲነቃቃ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ መባሉን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የገቢዎች ሚኒስቴር ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን (March 8) ምክንያት በማድረግ ግምታቸው አምስት ሚሊዮን ብር የሚሆን በህገወጥ ንግድና የግብር ግዴታን ባለመወጣት የተወረሱ የተለያዩ አልባሳት በሴቶች ለሚመሩ እና ለችግር የተጋለጡ ሴቶችና ህፃናት የሚረዱ የተለያዩ በጎ አድራጎት ድርጅቶች በዛሬው ዕለት ድጋፍ አድርጓል፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ድጋፉን ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ተወካዮች ባስረከቡበት ወቅት እንኳል ለአለም ሴቶች ቀን በሠላም አደራሳችሁ የሚል መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ሴቶች የእኩልትና የፍትሃዊነት ችግሮችን ለመፍታት የተጀመረ ቀን መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዛሬው ዕለት ድጋፍ የተደረገላቸው ድርጅቶች ፈለገ አረጋዊያን መርጃ ድርጅት፣ የተቀናጀ ቤተሰብ ድርጅት፣ ባቡን ኸየር በጎ ድርጅት እንዲሁም ከተለያዩ አካባቦዎች ተፈናቅለው በአዲስ አበባ ዙሪያ ላሉ ወገኖች መሆኑ ተውቀዋል፡፡

ምንጭ:የገቢዎች ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
የሀ ዲጂታል አርት ኤክስፒሪያን በአሁኑ ሰአት በደማቅ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ይገኛል ያልተካፈላችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች እንድትሳተፉ እንመክራለን።

@Yenetube @Fikerassefa
የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ኦሮሚያ ወለጋ ዞኖች ውስጥ የኦነግ ሸኔ አባላት እየፈጸሙት ያለውን ህገ ወጥ ድርጊት ለማስቆም ከምን ጊዜውም በላይ የተጠናከረ እርምጃ እየወሰድል ነው ብሏል።

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ጋላን በስፍራው እየተወሰደ ያለውን እርምጃ አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ መንግስት ልክ እንደከዚህ ቀደሙ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ የተደራጀ የህግ የበላይነት ማስከበርን ያለመ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ተናግረዋል።ምክትል ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው የኦነግ ሸኔ አባላት በአካባቢው ላይ በንፁሃን ዜጎች፣ በፖሊስ አባላት እና በውጭ ሀገራት ዜጎች ላይ ግድያ መፈፀማቸውን ነው ያነሱት።ከዚህ ባለፈም አባላቱ እያደረሱት ባለው ጥፋት በርካታ ንፁሃን ዜጎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውንም አመልክተዋል።

በሴቶች ላይ አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ በርከት ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንም በመፈፀም ላይ ይገኛሉም ብለዋል።ፖሊስ እስካሁን እየወሰደ ያለው እርምጃ አባላቱ ከፈፀሙት ድርጊት ጋር ተመጣጣኝ ያልሆነ ዝቅተኛ መሆኑን ነው ያስረዱት።አሁን ላይ የህግ የበላይነትን ለማስከበር የክልሉ ፖሊስ ከአካባቢው ህብረተሰብ ፣ ከፌደራል ፖሊስ እና ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን በቅንጅት የተጠናከረ እና የተደራጀ እርምጃ መውሰድ ጀምሯል ብለዋል።

የኦነግ ሸኔ አባላትን በሎጀስቲክ እና በሌላ መልኩ ድጋፍ እየደረጉ ያሉ ግለሰቦች እና ቡድኖች መኖራቸውን በመግለፅም እነዚህ አካላትን በተመለከተ ፖሊስ ጥናት እያደረገ መሆኑንና የጥናቱን ውጤት ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ነው የገለፁት።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
ኢዜማና ኦፌኮን ጨምሮ 6 የፖለቲካ ድርጅቶች ላቀረቡት አቤቱታ ምርጫ ቦርድ የመንግስት ኃላፊዎችን ምላሽ ተቀበለ!

ኢዜማና ኦፌኮን ጨምሮ ከስድስት የፖለቲካ ድርጅቶች ለቀረቡ አቤቱታዎች የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ማብራሪያና ምላሽ እንዲሰጡ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያሳሰበ ሲሆን፤ በዚህ መሰረት ምላሾቹን ትናንትና ከትናንት በስቲያ ሲቀበል ውሏል፡፡ለቦርዱ አቤቱታ ያቀረቡት ድርጅቶች፡- የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ)፣ የኢትዮጵያ ዜጐች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ኦሮሚያ ብሔራዊ ፓርቲ (ኦብፓ)፣ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ)፤ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና የጌድዮ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ጌህዴድ) መሆናቸው ታውቋል፡፡

በዶ/ር አረጋዊ በርሄ የሚመራው ትዴፓ፤ በትግራይ ክልል አባላቶች ላይ እስር፣ ማስፈራራትና የቢሮ መዘጋት ችግር እንደገጠመው ሲያመለክት፤ ኢዜማ በበኩሉ፤ ህዝባዊ የህዝባዊ ስብሰባዎች መሰናክል በጐንደርና በደብረ ብርሃን እንዳጋጠመው አቤቱታ አቅርቧል፡፡ኦፌኮ በበኩሉ፤ የአባላት እስርና ማስፈራራት እንደደረሰበት በብ/ጀነራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦብፓ ደግሞ የአባላት እስራት፣ የቢሮ መዘጋት፣ ታፔላ መነቀልና አባላት ማስፈራራት አጋጥሞኛል ብሏል፡፡ኦነግ ደግሞ የፓርቲ መመስረቻ ፊርማ መነጠቅ አጋጥሞኛል፤ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎችም አባላቶቼ ታስረውብኛል ሲል አቤቱታውን ማቅረቡ ታውቋል፡፡

የጌድኦ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት በበኩሉ፤ የፓርቲ ምስረታ ማሟያ ፊርማ የማሰባሰብ ሂደት መደናቀፍ ገጥሞኛል ማለቱን የምርጫ ቦርድ መረጃ ያመለክታል፡፡የፓርቲዎቹን አቤቱታ የተቀበለው ምርጫ ቦርድም፤ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ያላቸው አካላት የካቲት 26 እና 27 ቀን 2012 ዓ.ም በቀረቡባቸው ስሞታዎች ላይ ምላሻቸውን እንዲያቀርቡ ጠይቋል፡፡

የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መስተዳድር፤ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መስተዳድር፣ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንና የኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ የዝዋይ (ባቱ) ከተማ ፖሊስ ምላሽ እንዲያቀርቡ የተጠየቀ ሲሆን፤ ቦርዱ ትላንትና ከትናንት በስቲያ ምላሻቸውን ሲያቀርቡ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

ምንጭ: አዲስ አድማስ
@YeneTube @FikerAssefa
በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ትናንት የኮሮና ተሕዋሲ ከተገኘባቸው 13 ሰዎች 2ቱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የአገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዳለው ተሕዋሲው የተገኘባቸው 13ት ሰዎች በሙሉ ከሌላ አገር የተጓዙ ናቸው።

የጤና ጥበቃ ምኒስትር ድዔታ ዶክተር ሊያ ታደሰ መረጃው እንደደረሳቸው አረጋግጠው ጉዳዩን እየተከታተሉ መሆኑን ገልጸዋል። የአረብ ኤሚሬቶች የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር «ሁሉም ለ24 ሰዓታት ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ» ብሏል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል የሚገኘው እና 18 ሺሕ ገደማ ኤርትራውያን የሚኖሩበት ሕንፃፅ የስደተኞች መጠለያ ሊዘጋ መሆኑ በኢትዮጵያ መንግሥት እንደተነገራቸው በዚያው የሚኖሩ ስደተኞ ተናገሩ።

በመጠለያው የሚኖሩ ስደተኞች በአስር ቀናት ውስጥ ሕንፃጽ መጠለያን እንዲለቁ በኢትዮጵያ ስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር ባለፈው ሐሙስ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ለዶይቼ ቬለ አስረድተዋል። በመጠለያ ጣቢያው የሚኖረው ሐዱሽ ታደለ «እዚህ ያለ ስደተኛ በምንም ተዓምር የማይቀበለው ነገር ነው» ሲል ተናግሯል።

የትግራይ ክልል መንግስት ኤርትራውያን ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ፣ የተቋቋሙ የስደተኞች መጠልያ ጣብያዎች እንዲዘጉ መንግስታት "እያሴሩ ነው" ሲል ሲከስ ቆይቷል፡፡ የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል 45ኛ ዓመት የህወሓት ምስረታ የካቲት 11 በሚከበርበት ወቅት ባደረጉት ንግግር "ማነኛውም ሐይል" የኤርትራ ስደቸኞች መጠለያ ጣብያዎች መዝጋት አይችልም ሲሉ ገልፀው እንደነበረ ይታወሳል፡፡

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from Bruh Club
Last day of @yehadigitalart Festival … we hope to see you there.

Augmented Reality ማለት ምስል/ፖስተርን ወደ ተንቀሳቃሽ 2D-3D ሞዴል በመቀየር ልዩ ሰራዎችን ማየት የሚያስችል የጥበብ ዘርፍ አይነት ነው።

በዚህ አመት የሀ ዲጅታል አርት ላይ ያሉትን 10 Augmented Reality ስራዎች ለመመልከት የሚያስፈልጉት ከታች ያሉት 3 የAndroid App ብቻ ናቸው

1. Dede/Beth Molla art works
2. Dot Advertising
3. Yeha digital art poster

የተጠቀሱትን App ከቴሌግታም ቻናላችን https://tttttt.me/yehadigitalart ላይ ዳውንሎድ በማድረግ ወይንም በእለቱ ከአዘጋጆች እና አርቲስቶች በXender በመቀበል እና ስልክ ላይ በመጫን አስደናቂ ስራዎቹን በቀላሉ መመልከት ይችላሉ።
ኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብጽ ከህዳሴዉ ግድብ ጋር ተያይዞ ያላቸዉን ልዩነት በመነጋገር እንዲፈቱ የአፍሪካ ህብረት አሳሰበ፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳፋቂ ማህማት፣በሱዳን ሲያደርጉት የነበረዉን የሶስት ቀናት ጉብኝት ሲያጠናቅቁ እንዳሉት፣ተፈጥሯዊ ሀብቶቻችን የዕድገት እንጂ የግጭት መንስኤ ሊሆኑብን አይገባም ብለዋል፡፡

ሙሳፋቂ ማህማት ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሃምዶክ ጋር ባደረጉት ዉይይትም ሶስቱንም ሀገራት ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ ተነጋግረዉ ልዩነቶቻቸዉን እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

የዋሽንግተኑ ድርድር ተስፋ የተጣለበት እንደነበር ጠቅሰዉ ይህ ዳር ባይደርስም ግን አሁንም ሀገራቱ መነጋገር እንደሚገባቸዉ ነዉ ያስታወቁት፡፡

ሱዳንን በተመለከተ ባደረጉት ንግግራቸዉ፣ሀገሪቱ በመልካም የሽግግር ሂደት ላይ እንደምትገኝ ጠቅሰዉ የተዳከመዉን ኢኮኖሚዋን እንዲያገግም ለማድረግ ግን ዓለም አቀፋ ማህበረሰብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

አብደላ ሃምዶክ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በሱዳን ፖለቲካዉን ከማከም ባሻገር ኢኮኖሚዉ እንዲነቃቃ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ መባሉን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል፡፡

Via:- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa