YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ወምበራ ወረዳ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ዙሪያ ዛሬ የወምበራ ወረዳ መግለጫ ሰጧል።
በመግለጫው መሰረት:-

📌8 ሰዎች እንደሞቱና የሁለት ሰዎች አስከሬን እስከ አሁን እንደተገኘ

📌ተጨማሪ የሟቾችን አስከሬን ለማግኘት የማጣራት ስራ እየተሠራ እንደሆነ

📌33 የሚሆኑ የማህበረሠብ ክፍሎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ መደረጉ ተገልጿል።


በተጨማሪም 14ሰዎች እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም።

ምንጭ:- ELU / ወምበራ ወረዳ
@Yenetube @Fikerassefa
የኮሮና ቫይረስ ክስተትን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከቻይና የሚመጡ መንገደኞች ላይ የአየር ማረፊያ ላይ ምርመራ (screening) ማረግ ጀምራለች!

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ እስካሁን 581 የቫይረሱ ተጠቂዎች በአለም ዙርያ የተለዩ ሲሆን ከዚህ ውስጥም 571ዱ ቻይና ውስጥ ይገኛሉ።

"የቅድመ-ጥንቃቄ ስራዎችን ስንሰራ የቆየን ሲሆን አሁን የቦሌ አየር ማረፊያ ላይ ከቻይና የሚመጡ መንገደኞችን screen ማረግ ጀምረናል። እስካሁን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች የሉም፣ ነገር ግን ከዉሀን ከተማ የመጡ መንገደኞች ላይ ክትትል እያደረግን ነው" ያሉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ ናቸው።

በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አምስት የቻይና ከተሞች በሳምንት 35 በረራዎችን ያደርጋል።

ምንጭ:- Elias Meseret
@YeneTube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ2012 ማብቂያ በጃፓን፣ ቶኪዮ ለሚካሄደው ኦሎምፒክ የሚደረጉ ዝግጅቶችን ለማስተባበር ከተቋቋመ ብሔራዊ ኮሚቴ ጋር ተወያይተዋል። ብሔራዊ የኦሎምፒክ ኮሚቴው ለጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ ዝግጅታቸውን ባብራሩብተ ወቅት፣ ዓላማቸው ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን ለውድድር መላክ ብቻ ሳይሆን፣ በድል እንዲመለሱም ማገዝ እንደ ሆነ አስታውቀዋል።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
በዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ፌስቡክ ገጽ ላይ የትግራይ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ደብረ ጺዮን ገብረ ሚካዔል ሕይወታቸው አልፏል የሚል ሐሰተኛ መረጃ ያሰራጩ 3 ሠራተኞቼን ሙሉ በሙሉ ከሥራ አሰናብቻለሁ- ብሏል ድርጅቱ፡፡ 1 አመራር ከሃላፊነት ተነስተው በዝቅተኛ ሥራ መደብ የሠራሉ፤ ሌሎቹ ወደ ሥራቸው ይመለሳሉ፡፡ በእስር የቆዩ 7 ሠራተኞች ደሞ በ4 ሺህ ብር ዋስ ከትናንት ወዲያ ተፈተዋል፡፡ ዘገባው ሁሉንም ሠራተኞች በስም አልጠቀሰም፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
17ቱ የደንቢዶሎ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች የት ገቡ ? ዛሬ ከታፈኑ 50ኛ ቀናቸው ነው!!

በማህበራዊ ሚዲያዎች ፖስት ስታደርጉ ይህንን hashtag ተጠቀሙ⬇️

#BringBackOurStudents #ReleaseTheStudents #BringBackOurStudents #ReleaseTheStudents #BringBackOurStudents #ReleaseTheStudents
1
አዲስ ለተቋቋመው የተማሪዎች ምገባ ኤጀንሲ 23 በተለያዩ ሙያዎች ላይ የተሰማሩ የቦርድ አባላትም ተመርጠዋል። አባላት ሆነው የተመረጡት:-

1. ወ/ሮ አለምጸሃይ ጳውሎስ - ሰብሳቢ
2. ወ/ሮ የፍሬዓለም ሽባባው - ም/ሰብሳቢ
3. ወ/ሮ አምለሰት ሙጬ
4. አቶ ስኩር ካርዲን
5. አቶ አበበ ባልቻ
6. ዶ/ር በድሉ ዋቅጂራ
7. ወ/ሮ ሮማን ታፈሰወርቅ
8. አቶ ጥላሁን ጉግሳ
9. አቶ ያሬድ ሹመቴ
10. አቶ አማን ፍሰሃጽዮን
11. አቶ ፍትህ ቶላ
12. ዶ/ር ፍሬህይወት ገ/ህይወት
13. አቶ ጌጡ ተመስገን
14. ቀሲስ ሙሉቀን ብርሃኑ
15. ዶ/ር መሳይ ገ/ማርያም
16. ዶ/ር ፈቃዱ ሙሉጌታ
17. አቶ በላይ ካሳ
18. አቶ ሰለሞን መንገሻ
19. ዶ/ር ታረቀኝ ታደሠ
20. ሐዋሪያ ዮሐንስ ግርማ
21. ዶ/ር ቤቴልሄም ደረጀ
22. ወ/ሮ ዘኒት ት ይመር
23. ወ/ሮ ሜቲ ታምራት ናቸው፡፡
ቦርዱ በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ ህፃናትና ወጣት ተማሪዎች በምግብና በትምህርት ግብዓት አቅርቦት ችግር ከትምህርት ገበታ ውጪ እንዳይሆኑ የማስተባበርና የመከታታተል ኃላፊነት ይኖረዋል፡፡

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መመለሳቸውን ቀጥለዋል

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለማስጀመር ለተማሪዎቹ የአስተላለፈውን ጥሪ ተከትሎ ዛሬ ጥር 15/2012 ዓ.ም ለግቢው ፀጥታና ደህንነት በተዘጋጀው ካሜራ የተማሪዎቹ ፎቶ እየተወሰደና በአዲስ ሲስተም ተማሪነታቸው እየተረጋገጠ ከጧቱ ጀምሮ ተማሪዎቹ ወደ ግቢ መግባታቸውን ቀጥለዋል፡፡ በቀጣይ ቅዳሜና እሁድ ሁሉም ተማሪ ተጠቃሎ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡

በተያያዘ ሁኔታ በፍጥነት ሠላማዊ የሆነ ትምህርታቸውን ለመጀመር እንደጓጉ ወደ ግቢ ከገቡ ተማሪዎቹ ለመረዳት ችለናል፡፡ ትምህርት ጥር 18/2012 ዓ.ም እንደሚጀመር ማስታወቃችን ይታወሳል፡፡

Via:- ድሬደዋ ዩንቨርስቲ
@Yenetube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
#ለሰባ_አመታት_ተደብቆ_ሳይታተም_የቆየ_መፅሐፍ
#የስኬት_ፍልስፍና

ሰይጣን እንዴት ከስኬታማ ህይወት ወደኋላ እንደሚያስቀረን የሚያሳይ አነጋጋሪ መፅሐፍ!!

ይህ አነጋጋሪ መፅሐፍ ከተዘጋጀ በኋላ የህዝብ ቁጣ ሊቀሰቅስ ይችላል ተብሎ ለ 70 ዓመታት ሳይታተም ተደብቆ ኖሯል፡፡ የጨለማው አለም ገዢ ሰይጣን የተናዘዘው ኑዛዜ ከ70 ዓመት በኋላ በዚህ መጽሐፍ ሲወጣ ግን በመላው አለም መነጋገሪያ ሆነ!!

መፅሐፉ ሰይጣን ስኬታማና ትርጉም ያለው ህይወት እንዳንመራ እንዴት አዕምሯችንን እንደሚቆጣጠረውና አስተሳሰባችንን እንደሚያበላሸው በማሳየት በንቃት እንድናሸንፈው ይረዳናል!!!

***

“ናፖሊዮን ሂል ህይወቱ ካለፈ ከብዙ አስርት አመት በኋላ እንኳን እስከዛሬም ጥላው የከበደ አሜሪካ አሉኝ ከምትላቸው አሳቢዎች አንዱ ነው፡፡ ለዘመኑ አንባቢ እንዲመጥን ተደርጎ በሻሮን ሌስተር የቀረበው ይህ ድንቅ መጽሐፍ ዲያብሎስ እንዴት አንድን ሰው ከስኬት ጐዳና እንደሚያስወጣው ቁልጭ አድርጎ ያሳያል!!”
ስቲቨ ፌርብስ
የፎርብስ መጽሄት ዋና አዘጋጅ

“ይህ ዘመን ተሻጋሪ ስራ ትክክለኛ ጊዜው ደርሶ ታተመ ማለት ነው፡፡ እንዴት ድንቅ ነው!”
ሐርቬይ ማኬይ
የከፍተኛ ሽያጭ መፅሐፍት ደራሲ

በየመፅሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል!
Forwarded from YeneTube
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
Forwarded from YeneTube
Samsung Galaxy A10s
2019 Model Phone
Brand New Packed &
Original with Full Accessories
6.2inch screen size
32GB Storage
13MP camera 1080HD
4000mAh battery capacity
Dual Sim Slot

📩 @CloudMultiTrading 📩
📞 0944182119 📞

@CloudTrading @CloudTrading
ዋሺንግተን ዲሲና በአካባቢው የሚኖሩ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት የኢትዮጵያ መንግሥት በተለይ በደቡብና ምዕራብ ኦሮምያ ያደረሰዋል የሚሉትን ጥቃት በመቃወም በትናንትናው ዕለት ሰልፍ ወጥተዋል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ!

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 5ኛ ዘመን 18ኛ ዙር መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ።በመቐለ ከተማ ምክር ቤት አዳራሽ እየተካሄደ ያለው ጉባዔ ለቀጣዮቹ አምስት ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል። ምክር ቤቱ የክልሉ ሥራ አስፈጻሚ አካላትን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸምን ጨምሮ በ21 ረቂቅ ዓዋጆችና ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

ከእነዚህ መካከል ዳግም ወረዳዎችን ለማደራጀት የወጣውን ረቂቅ ዓዋጅ ጨምሮ፥ የከተሞችና የወረዳዎች የስራ አፈጻጸምን፣ የመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ረቂቅ ዓዋጆችን መርምሮ እንደሚያጸድቅም ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል።በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና በዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ላይም ውይይት ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአን ጠቅሶ የዘገበው ፋና ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
ቻይና ውስጥ አንድ ዶክተር ኮሮና ቫይረስ ታማሚውን በማከም ላይ ሳለ በቫይረሱ ተጠቅቶ መሞቱ ተሰምቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
የሆንግ ኮንግ ማራቶን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እንደማይካሄድ ቷውቋል። በሆንግ ኮንግ በቫይረሱ የተጠቃ አንድ ሰው ብቻ ቢሆን በስጋት ምክንያት ማራቶኑ እንደማይካሄድ ታውቋል።

#coronavirus
@Yenetube @Fikerassefa
በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ አዛዥ ሌ/ጄነራል ጌታቸው ጉዲና ከሀላፊነታቸው ተነስተው የምህንድስና ዋና መምሪያ ሀላፊ ሆነው መሾማቸውን ሰምተናል። ሌ/ጄነራል ድሪባ መኮንን የሰሜን ዕዝ ኣአዛዥ ሆነው እንደሚሾሙ ይጠበቃል።

ምንጭ:- ELU
@yenetube @Fikerassefa
Confirmed coronavirus cases:

- China

- US

- France

- Japan

- South Korea

- Taiwan

- Singapore

- Thailand

- Australia

- Nepal

- Vietnam

- Hong Kong

- Macau

- Malaysia
@YeneTube @Fikerassefa
የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጉዳይ አሁንም ተጨባጭ መረጃ አልተገኘበትም፡፡

የመታገታቸው ዜና ከተሰማበት ኅዳር 24/2012 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎቹ ስላሉበት ሁኔታ ግልጽ መረጃ አልተገኘም፡፡ መጀመሪያ አካባቢ አልፎ አልፎ በአጋቾቹ የእጅ ስልኮች ከወላጆቻቸው ጋር ይገናኙ እንደነበር ከእገታ ያመለጠችዋ ተማሪም ሆነ ወላጆች መናገራቸው ይታወሳል፡፡ አሁን ላይ ግን የትና በምን ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ መረጃ የለም፡፡ የፌዴራል መንግሥቱ ከታገቱት ውስጥ 21 ተማሪዎች ስለመለቀቃቸው መረጃ ቢሰጥም ተማሪዎቹ ከወላጆቻቸው ጋር አልተገናኙም፤ በየትኛውም ቦታ ስለመታዬታቸውም መረጃ አልተገኘም፡፡

ይህ ደግሞ ጥያቄው ጎላ ባሉ መላምቶች እንዲቀጥል አድርጎታል፡፡ መገናኛ ብዙኃኑም፣ ወላጆችም፣ ኅብረተሰቡም ይጠይቃል፤ «ተለቀቁ የተባሉት ተማሪዎች የት አሉ?» በማለት፡፡ መጀመሪያ ላይ ታገቱ የተባሉት 17 በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች ናቸው፡፡ መንግስት ደግሞ 21 መለቀቃቸውንና ቀሪ ስድስት ተማሪዎችን ደግሞ በከፍተኛ ጥንቃቄ በሚደረግ ክትልል ለማስለቀቅ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ መግለጫ ሰጠ፡፡ ከዩኒቨርሲቲው ጋር ተደረገ በተባለ ማጣራት ደግሞ ከ17ቱ መካከል ተማሪዎቼ ናቸው ያላቸው 12ቱን ብቻ ነው፡፡ አሁንም ሌላ አወዛጋቢ መረጃ፡፡

ቁጥራቸው የቱንም ያህል ይሁን ደብዛቸው ከጠፋ 52 ቀናት የሆናቸው ተማሪዎች ያሉበት ሁኔታ በግልጽ አለመታወቁ ግን አሁንም አሳሳቢ ጥያቄ ሆኗል፡፡ አካባቢው የተሰማራው ኮማንድ ፖስት ጉዳዩን እያጣራ እንደሆነ ከመናገር ያለፈ የተለዬ መረጃ መሥጠት አልቻለም፡፡ ከፌዴራል ፖሊስ እና ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተቋቋመ ቡድን ከሰሞኑ ወደ አካባቢው አምርቶ ጉዳዩን ለማጣራት እንደሞከረ፤ ነገር ግን ተማሪዎቹ ስላሉበት ሁኔታ ተጨባጭ መረጃ ሳያገኝ እንደተመለሰ አብመድ ባደረገው ማጣራት አረጋግጧል፡፡በቀጣይም ፌዴራል ፖሊስ በመነሻነት ያገኘውንና ሌሎች መረጃዎችን በማካተት ተማሪዎቹ ያሉበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ እንደሚሠራ ነው የሚጠበቀው፡፡

ትልቅ ተስፋ ተጣለበት ፍንጭ ይገኛል የተባለው ግን ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ሲጀምር ነው፡፡ አሁን ላይ 800 የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው ግቢ ውጭ እንደሆኑ ታውቋል፡፡ትምህርት ሲጀመር ምናልባትም ከታገቱት ተማሪዎች ውስጥ የተለቀቁ ካሉ እና ለመማር ከሄዱ ስለሁኔታው ግልጽ መረጃ ይገኛል ተብሎ ነው የትምህርት መጀመሩ ጉዳይ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት፡፡በአካባቢው የተንቀሳቃሽ ስልክ ኔትወርክ ባለመሥራቱ ትምህርት መቼ እንደሚጀምር መረጃ ለማግኘት አልተቻለም፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
#የመጨረሻ_የሆነው_ባይብል_ኮድ_3_በገበያ_ላይ_ዋለ!

#በአንድ_ምሽት_ሽያጭ_ብቻ_ሪከርድ_የያዘ_መጽሐፍ!!

ቁጥር 3 ባይብል ኮድ፡-

*ስለ አርማጌዶን መቅረብና ዓለምን ከጥፋት የማዳን ቁልፍ በኮድ ስለመቀመጡ…

* አሜሪካኖች የሚኮሩበትና አለም የሚያደንቀው ዝነኛው የስለላ ድርጅት ሲ.አይ.ኤ በቸልተኝነት በርካታ ከባባድ ስህተቶችን እንደሚሰራ…

*በዓለም ላይ ያሉ መሪዎች ስለሚገደሉበት ቦታ፣ ስለሚገድሏቸው ሰዎች ስም…

*ስለ እያንዳንዳችን ዕጣ ፈንታ እንዲሁም በኮድ ተፅፎ ስለሚገኘው ሚስጥራዊ ቁልፍና በአለም ላይ ስለተከናወኑና ወደፊት ስለሚከናወኑ ድርጊቶች ሁሉ በስም፣ በቀን፣ በቦታ ሳይቀር ከዛሬ ሶስት ሺ ዓመት በፊት…

#በመፅሐፍ_ቅዱስ_ውስጥ_በኮድ_ተቀምጧል!!

ቁጥር 3 ባይብል ኮድ ኮዶቹን እየፈታ ያስገርመናል፡፡

‹‹#ይህ_መፅሐፍ_እውነትነቱ_በዘመናዊ_ሳይንስ_የተረጋገጠለት_ተአምር_ነው››

በየመፅሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🦗🦗🦗 ሀዋሳ 🦗🦗🦗🦗

ሀዋሳ የአንበጣ መንጋ ተከስቷል ነዋሪዎች የአንበጣ መንጋውን ለማባረር ጭስ በማጬስ እንዲሁም ድምፅ በመፍጠር የእንበጣ መንጋውን ለማባረር ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ።

Video - ( YeneTube / Yisak )
@YeneTube @Fikerassefa