YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
17ቱ የደንቢዶሎ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች የት ገቡ ? ዛሬ ከታፈኑ 50ኛ ቀናቸው ነው!!

በማህበራዊ ሚዲያዎች ፖስት ስታደርጉ ይህንን hashtag ተጠቀሙ⬇️

#BringBackOurStudents #ReleaseTheStudents #BringBackOurStudents #ReleaseTheStudents #BringBackOurStudents #ReleaseTheStudents
መንግስት በታገቱት የደንቢ ደሎ ዪንቨርሲት ተማሪዎች አጥጋቢ ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ በኦሮሚያ ክልል የሚማሩ የአማራ ተማሪዎች ወደቦታቸው እንዲመለሱ አደርጋለው ሲል የአማራ ወጣቶች ማህበር አሳሰበ፡፡

የአማራ ወጣቶች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አስናቀ መንገሻ ለአሐዱ እንደተናገሩት ከሁለት ወራት በፊት በደንቢዶሎ ዩንቨርስቲ 17 የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች የታገቱ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል 40ሺ የሚሆኑት ደግሞ ከትምህርት ገበታቸው መፈናቀላቸውን አንስተዋል::

መንግስት በታገቱ ተማሪዎች ላይ አፋጣኝ ምላሽ የማይሰጥና ሀላፊነቱን የማይወጣ ከሆነ በሁሉም የኦሮሚያ ክልል ዩንቨርሲቲዎች የሚማሩ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች ወደየቤታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ በቅርቡ መግለጫ እንደሚሰጥ የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ አስናቀ ተናግረዋል፡፡

#Bringbackourstudents

Via:- Ahadu radio
@YeneTube @Fikerassefa