YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ግብፅ ከአሜሪካ ባደረገችው የተናጠል ውይይት ታላቁ የኅዳሴ ግድብ ውኃ የሚሞላበትና የሚተዳደርበት ሕግጋት እና አሰራር ምን መሆን እንዳለበት አገራቸው ማስረዳቷን የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አሕመድ ሐፌዝ ገልጸዋል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ አዲሱ የመሬት ልኬታ/ካዳስተር/ በተካሄደባቸው አካባቢዎች የእርሻ መሬት ግብር ክፍያ የተቀየረና የተጨመረ ተደርጎ የሚነሳው ስህተት መሆኑን ገለፀ፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዳደር መምሪያና የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ በጋራ በመሆን የአርሶ አደሩ የገጠር መሬት ይዞታ አዲስ የመሬት ልኬት /ካዳስተር/ከተሰራ በኋላ የገጠር መሬት መጠቀሚያና የእርሻ ስራ ግብር ላይ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ንጉሴ እንደገለፁት ፤የገጠር መሬት መጠቀሚያና የእርሻ ስራ ስራ ገቢ ግብር በክልሉ ምክር ቤት አዋጅ ህዳር 2001 ዓ.ም በጸደቀው መሰረት በአርሶ አደሩ መሬት ልክ እንዲከፍል ተደርጎ እየተሰራበት ቆይቷል፡፡

የአርሶ አደሮች የገጠር መሬት ይዞታ የግብር ክፍያ በምግብ ዋስትና የተያዙና ያልተያዙት በስተቀር ልዩነት እንደሌለው ገልጸው ፤በጥማድ 30 እና 40 ብር እንዲከፍሉ ሲደረግ ቆይቷል፤ አሁንም ይህ አሰራር እንደቀጠለ ያለና ያልተቀየረ ሲሆን ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት በአንዳንድ አካባቢዎች ከግንዛቤ ማነስ ሊሆን በሚችል የአርሶ አደሩ የመሬት መጠቀሚያ ግብር የተቀየረና የተጨመረ ተደርጎ የሚነሳው ስህተትና ልዩነት አለመደረጉን ገልፀዋል፡፡

ምንጭ: የሰሜን ሸዋ ዞን ኮሚኒኬሽን መምሪያ
@YeneTube @FikerAssefa
የቤኒሻንጉል ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ‹‹ቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ›› የተሰኘ አዲስ ፓርቲ ለመመሥረት በዝግጅት ላይ የነበሩ 10 ግለሰቦች ላይ የእስር ማዘዣ በማውጣት ሰብሳቢውን ጨምሮ አራት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አዋለ። የፓርቲዉ ምክትል ሰብሳቢ ጌታሁን መርጋ፣ የሕግ ባለሙያ የሆኑት ጌታቸዉ ወድሻ፣ የድርጅት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጉዮ ፈረደን (ዶ/ር) ሐሙስ ታኅሳስ 30/2012 መታሰራቸውን የቦሮ ፓርቲ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ ዮሐንስ ተሰማ ተናግረዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
"ጋዜጠኞቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ደብዳቤ ይዘው ስላልተገኙ ነው" የአሶሳ ፖሊስ

ዋና ኢንስፔክተር እስማኤል፤ ሁለቱ ጋዜጠኞች የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይትን ለመዘገብ ከኤጀንሲው አዲስ አበባ ቅርንጫፍ መላካቸውን እንደነገሯቸው ጠቅሰው፤ ጋዜጠኞቹ ወደ አሶሳ ሲመጡ ደብዳቤ ባለመያዛቸው እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስለ ሁለቱ ጋዜጠኞች ወደ ክልሉ መምጣት የሚያውቀው ነገር ባለመኖሩ መታሰራቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮ-ቴሌኮም ንብረት የሆኑ በርካታ የስልክ ገመዶችን ከነ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገፀ፡፡

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንዳስታወቀው ጥር 15 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ መርካቶ ጋዝ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለበርካታ ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች አገልግሎት የሚሰጡ እና ከመሬት ውስጥ ተቆፍረው የወጡ የስልክ ገመዶችን አከማችተው የተገኙ 2 ተጠርታሪዎች በፖሊስ አባላት ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በተመሳሳይ በክ/ከተማው መርካቶ ኢትዮጵያ ዳቦ ቤት ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ አንድ ተጠርጣሪ በመሬት ውስጥ የተቀበሩ ንብረትነቱ የኢትዮ ቴሌኮም የሆኑ የስልክ ገመዶችን ቆፍሮ እያወጣና እየቆረጠ ሰርቆ ለመውሰድ ሲሞክር በፖሊስ አጋዥ ሃይሎች እጅ ከፈንጅ ሊያዝ መቻሉን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ወንጀሉን ሲፈፅሙ የነበረው በሌሊቱ ክፍለ ጊዜ መሆኑን ያስታወሰው ፖሊስ መምሪያው በአሁኑ ወቅት ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡የመሰረተ ልማት አውታሮች የህብረተሰቡን የዕለት ተዕለት መረጃ ግንኙነት ያቀላሉ፡ ለሀገራች የኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ ሚና ያላቸው የህዝብ ሀብት ስለሆኑ ፖሊስ ወንጀሉን ለመከላከል የሚያደርገው ጥረት ህብረተሰቡ በነቃ ተሳትፎ እንዲያግዝ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

Via Addis Ababa Police Commission
@YeneTube @FikerAssefa
ለፌዴራል መንግስት ከተመደበው 240,179,459,024 ብር ላይ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ (ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ለተጠሪ ተቋማትና ለ45ቱ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት) 20.15% ድርሻ ይይዛል፡፡

Photo:የአጠቃላይ በጀቱ ክፍፍል
Via MoSHE
@YeneTube @FikerAssefa
ሰርግዎን በቅርቡ ለመሰረግ አስበዋል?
እንግድያውስ የዲኮሩን ስራ በእኛ ላይ ይጣሉት

💥LEAD DECOR

በባህላዊ እና ዘመናዊ መልኩ ዝግጅትዎን እናስውባለን::
➡️ለሠርግ
➡️ለመልስ
➡️ለልደት
➡️ለስብሰባ አዳራሽ
እንዲሁም
ለልዩ ልዩ ዝግጅቶች

0912672317, 0920315163 ደውለው ያነጋግሩን

ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት ቻናላችንን ይቀላቀሉ⬇️
https://tttttt.me/LeadDecor
LADIES BOOK NOW👇 👇👇👇👇

Contact @kiru04
0931607806
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEPkyxEP1snCoAkFGw
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የበረሃ አንበጣ የኢትዮጵያ ደቡባዊ አካባቢዎች ደርሷል

ለወራት ሰሜን ኢትዮጲያን ሲያስጨንቅ የከረመው የበረሃ አንበጣ አሁን ፊቱን ወደ ደቡብ አካባቢ ያዞረ ይመስላል። የደቡብ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳንኤል ዳምጠዉ በክልሉ የአንበጣ መንጋ በስፋት መከሰቱን ለዶቼ ቨለ (DW) አረጋግጠዋል።

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa
የትንባሆ ዋጋ አሁን ካለበት ዋጋ ሦስት ዕጥፍ ቢጨምር በትንባሆ ምክንያት የሚደርሰውን እና እየደረሰ ያለውን ጉዳት እስከ 40 በመቶ እንደሚቀንሰው የኢትዮጵያ ምግብ፣ መድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።

Via:- ኢትዮ ኤፍ ኤም /Addis Maleda
@YeneTube @Fikerassefa
ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 2ሽሕ ኹለት መቶ 25 ግብር ከፋዮችን ኦዲት በማድረግ ሊሰወር የነበረ 7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ማስቀረት እንደተቻለ በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርሀኑ አበበ ተናገሩ።

Via:- አዲስ ማለዳ
@YeneTube @Fikerassefa
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ የበረከት ስምዖንን እና ታደሠ ካሳን 2 መከላከያ ምስክሮች መስማቱን የአማራ ብዙኻን መገናኛ ዘግቧል፡፡ በነገው ችሎት ሌሎች ምስክሮች ይቀርባሉ፡፡ ለምስክርነት የተጠሩት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን፣ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ገዱ አንዳርጋቸው እና የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም መቼ እንደሚቀርቡ አልታወቀም፡፡

Via:- wazema
@YeneTube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
 ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ
 በድረ ገፁ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ዕቃዎቹን ወይም አገልግሎቱን መሸጥ ይችላል።
 ከ2700 በላይ ዕቃዎችና አገልግሎቶች
@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com
 0953707070
Samsung CURVED UHD TV
55 7 SERIES NU7300 SMART TV
BRAND NEW
INBOX 📩 @CloudMultiTrading2 📩
በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የተፈጠረው ስምምነት በሰላም እጦት ለተቸገሩት እፎይታን የሰጠ ጉዳይ በመሆኑ ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ በኩል ክፍፍል ሊኖር አይገባም ሲሉ የቫቲካኑ ጳጳስ ፍራንሲስ ተናገሩ። ጳጳሱ በቫቲካን የሚገኘው የኢትዮጵያ ካቶሊክ ኮሌጅ 100ኛ ዓመት ምስረታ በዓል ላይ ተገኝተዋል።

Via:- ኢትዮ ኤፍ ኤም
@YeneTube @Fikerassefa
ሐና ዩሐንስ የጋብቻ ቀለበት በድብቅ አደረገች።

የዘመን ድራማ ተዋንያኗ እና የእንተዋወቃለን የቴቪ ፕሮግራም አዘጋጇ ሐና ዩሃንስ ባሳለፍነው ሳምንት በድብቅ የጋብቻ ቀለበት እንዳረገች ኢትዮፒካሊን ዘግቧል። እንደ ኢትዮፒካሊክ ዘገባ ከሆነ በቀለበት ስነ-ስርዓቱ ላይ ከልጇ በስተቀር የተገኝ ሰው አልነበረም።

ሐና በዘጠነኛው ለዛ ሽልማት ላይ በተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ምርጥ የሴት ተዋናይት ተብላ መሸለሟ ይታወሳል።

Via:- AccessAddis
@YeneTube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ ከትራፊክ አደጋ ጋር በተያያዘ በየቀኑ በአማካኝ 13 ሰዎች ህይወታቸው እንደሚያለልፍ የኢፌዲሪ ትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

Via:- ኢቢሲ
@YeneTube @Fikerassefa
የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ አስራ ሰባት የአስተዳደር ሠራተኞችን በግምገማ ከስራቸው አባረረ

የዩኒቨርስቲው የዓለም አቀፍ እና ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደቻሳ ጋንፉሬ ለዶይቸ ቬለ (DW) በስልክ እንደገለፁት ዩኒቨርስቲው የመማር ማስተማር ሥራውን እንዳያከናውን ያጋጠመውን እክል ተከትሎ እያካሄደ ባለው የሠራተኞች ግምገማ ከዲስፕሊን ግድፈት ጋር በተያያዘ አስራ ሰባት የአስተዳደር ሠራተኞች ከሥራቸው እንዲባረሩ ወስኗል።

ኃላፊው እንዳሉት በአስተዳደር ሠተኞች ላይ በተካሄደው ግምገማ አንድ ሠራተኛ ከደረጃው ዝቅ ብሎ እንዲሠራ ተወስኗል። በዩኒቨርሲቲው ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት የተጀመረው ግምገማ ቀጥሎ የአካዳሚክ ክፍሉ ሠራተኞች በመገምገም ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

የድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ከሁለት ሳምንት በላይ ያቋረጠውን መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ ለማስጀመር ቀደም ሲል በተማሪ ማደርያ ክፍሎች፤ በመመገቢያና ሌሎች አካባቢዎች ነበሩ ያላቸውን ችግሮችን ለመፍታት እና የተቋሙን አገልግሎት ምቹ የማድረግ ሥራ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑንም አቶ ደቻሳ አስረድተዋል።

ዩኒቨርስቲው በተቋረጠው ትምህርት ሳቢያ የባከኑ የትምህርት ጊዜያትን ለማካካስ የሚቻልበት ዕቅድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን እና በቅርብ ቀናት የተቋረጠው ትምህርት ለማስጀመር እቅድ እንዳለው አስታውቀዋል።

በዩኒቨርሲቲው በትምህርት ዓመቱ በተማሪዎች በተነሱ ግጭቶች ሳቢያ ሁለት ተማሪዎች ሕይወት ማለፉና ሌሎች ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱ የሚታወስ ነው። ምክንያቱ በውል አይገለፅ እንጂ ባሳለፍነው ሳምንት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶ/ር ያሬድ ማሞ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር በተፃፈ ደብዳቤ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርጓል።

ምንጭ:- DW
@YeneTube @Fikerassefa
የሁለት ሳምንት አስክሬን አስነሳለሁ ያለችው 'አማኝ' በገንዘብ ተቀጣች!

በኦሮሚያ ክልል ቦሰት ወረዳ ወለንጪቲ ከተማ ከሞተ ሁለት ሳምንት የሆነውን የሁለት ወር ህፃን "ከሞት እንዳስነሳ ራዕይ ታይቶኛል" በማለት መቃብር ያስቆፈረችው 'አማኝ' በማጭበርበር መቀጣቷን ፖሊስ ለቢቢሲ ገልጿል።
ህጻኑ ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ከሞተ በኋላ ራዕይ ታይቶኛል ያለችው ሴት፤ የህጻኑን እናት እና አንዲት ሌላ ሴት በመያዝ ወደ መቃብር ሥፍራ በመሄድ ቆፍረው ማውጣታቸውን የቦሰት ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ዋና አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ካሰኝ ደምሴ ገልጸዋል። ''ግለሰቧ እንደ ለቅሶ ደራሽ በመሆን ወደ እናት ቤት በመሄድ ልጅሽ አልሞተም፤ በሕይወት ነው ያለው፤ ከሞት እንዳስነሳውም ራዕይ ታይቶኛል" ትላታለች። መቃብር ሥፍራም ሄዳ ጸሎት ማድረግ እንደምትፈልግ ትነግራታለች። እናትም እውነት መስሏት ተያይዘው ወደ መቃብር ሥፍራው ሄደዋል።

https://telegra.ph/bbc-01-14
🛑 Breaking 🛑

የኦሮሚያ ክልል ከእገታ የተለቀቁ ተማሪዎች #በእጄ ናቸው አለ

ከእገታ ተለቀቁ የተባሉ ተማሪዎችን ዛሬም እንዳላገኙ ቤተሰቦች ቢናገሩም የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ከእገታው የተለቀቁት ተማሪዎች አሁን #በመንግሥት_እጅ መሆናቸውን ለቪኦኤ ተናግረዋል።

የእገታውን ተግባር የፈፀሙት ራሳቸውን ሸኔ ብለው የሚጠሩ ቡድኖች ናቸው ሲሉ ኮሎኔል አበበ ተናግረዋል።

Via:- Addis Maleda / VOA
@YeneTube @FikerAssefa