YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በታሪኩ ሁለተኛ ከፍተኛ የተባለለትን የመድን ሽፋን በ2 ባቡሮችና 12 ፉርጎዎች ላይ ለደረሰ ጉዳት ከፍሏል።የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ነፃነት ለሜሳ የ95.1 ሚሊዮን ብር ቼክ ለኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር(EDR) ሀላፊ አቶ ጥላሁን ሳርካ አስረክበዋል።

ምንጭ: ፎርቹን
@YeneTube @FikerAssefa
ታህሳስ 3 ቀን በዋልታ ቴሌቪዥን የፌስ ቡክ ገጽ ላይ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤልን በተመለከተ ከተቋሙ እዉቅና ዉጭ የተሰራጨውን የሀሰት ዜና ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ሰባት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡የፌራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የተደራጁና ልዩ ልዩ ወንጀሎች ዳይሬክተር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ጋር በመሆን ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ቅርበት ባላቸው እና ሌሎች ቀጣይ የምርመራ ስራዎችን እያካሄደ እንዳለ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጥፋት ፈፅመዋል ባላቸው 77 ተማሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

በዩኒቨርሲቲው የጥፋት አላማን አንግበው ሲንቀሳቀሱ ነበሩ ያላቸው ጥቂት ተማሪዎች ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዲታወክ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።በመሆኑም የዩኒቨርሲቲውን አጠቃላይ ህልውና ጭምር አደጋ ውስጥ በመክተት የጥፋት ተልዕኮ ሲያከናውኑ ቆይተዋል ነው ያለው።ተማሪዎቹ ከጥፋታቸው እንዲመለሱና እንዲታረሙ ተደጋጋሚ ምክርና ጊዜ የተሰጣቸው ቢሆንም ከጥፋታቸው ሊታረሙ አለመቻላቸውንም ገልጿል።

በመሆኑም የዩኒቨርሲቲውን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለማስቀጠል፥ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዲስተጓጎል ምክንያት ሆነዋል ባላቸው 77 ተማሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ነው የገለጸው። እርምጃ ከተወሰደባቸው ተማሪዎች መካከል ሁለቱ ሙሉ ለሙሉ ሲሰናበቱ፥ 75 ተማሪዎች ደግሞ ለሁለት ዓመት ከትምህርት ገበታቸው ታግደዋል። በተጨማሪም ሁለት መምህራን ተማሪዎችን በማስኮብለል ድርጊት ላይ ተሳትፈው በመገኘታቸው የደመወዝ ቅጣትና የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።

ተማሪዎቹ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስተጓጎል የተለያዩ እንቅፋቶች ከመፍጠር አንስቶ በተደራጀ ሁኔታ ሠላማዊ ተማሪ ላይ ጥቃት በማድረስ፣ ህገወጥ ሠልፍ በማደራጀት እና ትምህርት እንዳይካሄድ የማሸማቀቅ እና የማስፈራራት ተግባር ሲፈጽሙ ነበር ተብሏል፡፡በተያያዘም የብሔር ግጭት የሚቀሠቅሱ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ንግግሮች ማድረግ፣ በህገወጥ ሠልፍ የዩኒቨርሲቲው ንብረት ላይ ውድመት ማድረስም ተማሪዎቹ የተሳተፉበት ህገ ወጥ ድርጊት መሆኑም ተገልጿል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በዋልታ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሀሰተኛ ዘገባ በማሰራጨት የተጠረጠሩ #ሰባት ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

በዋልታ ቴሌቪዥን ማህበራዊ ሚድያ ላይ “የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ባልታወቀ ሁኔታ ተገደሉ” የሚል የሀሰት መረጃ ሰርተዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደባቸው መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ጋር በመሆን እያጣራ ባለው በዚህ ወንጀል ከድረ ገፁ ስራ ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት ያላቸው፣ የድረ ገፁ የይለፍ ቃል ያላቸውን እና በኃላፊነት ደረጃ የሚጠረጠሩ ሰባት ተጠርጣሪዎችን መያዙን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ የተደራጁ እና ልዩ ልዩ ወንጀሎች ዳይሬክተር ኮማንደር አበራ ቡሊና ገልፀዋል።

ዳይሪክተሩ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የሀሰተኛ ወሬው እንዴት ሊሰራጭ እንደቻለ ምርመራ ሲደረግ መቆየቱን ጠቁመው ከጉዳዩ ጋር ቅርበት አላቸው ተብሎ የተጠረጠሩ ወደ ሰባት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ብለዋል።

Via:- EBC
@YeneTube @Fikerassefa
ዛሬ በቡሌሆራ ዩኒቨርስቲ የተከሰተ ግጭትን ተከትሎ፣ የፀጥታ ሀይሎች ተኩስ ከፍተው አንድ ተማሪ ሲገድሉ 3 ተማሪዎችን አቁስሏል። ሟች ተማሪ ናትናዔል መንግስቱ የ3ኛ አመት የሲቪል ኢንጅነሪንግ ተማሪ ነበር።

Via:- ELU / YeneTube
@YeneTube @Fikerassefa
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጥፋት ፈፅመው በተገኙ 77 ተማሪዎች ተማሪዎች ላይ ዛሬ እርምጃ ወሰድኩ አለ፡፡

@YeneTube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
Breaking

ኢራን የዩክሬን የመንገደኞች አውሮፕላንን በስህተት መትታ መጣሏን አመነች።

@YeneTube @FikerAssefa
ኢራን የዩክሬን የመንገደኞች አውሮፕላንን በስህተት መትታ መጣሏን አመነች።

የኢራን ጦር ባወጣው መግለጫ የዩክሬኑ የመንገደኞች አውሮፕላን "ሆነ ተብሎ አለመመታቱን" ገልጿል።

በኢራን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ የተነበበው የጦሩ መግለጫ፤ አውሮፕላኑ በኢራን አብዮታዊ ጥበቃ አቅራቢያ በሚገኙ የደህንነት ሥፍራዎች እየበረረ ስለነበረ ''በሰዎች ስህተት" ተመትቶ ስለመጣሉ ተነግሯል።
በመግለጫው የመንገደኞች አውሮፕላኑ ተመቶ ለመውደቁ ኃላፊነት የሚወስዱት ተጠያቂ ይሆናሉ ተብሏል።

ከዚህ ቀደም የአሜሪካ፣ ካናዳ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ዩክሬን እና ኢራቅ መንግሥታት አውሮፕላኑ በስህተት በሩሲያ ሰራሽ ሚሳኤል ተመትቶ ስለመውደቁ መረጃው አለን ማለታቸው ይታወሳል።

ምዕራባውያኑ መንግሥታት ይህን ይበሉ እንጂ፤ ትናንት የኢራን ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ኃላፊ አሊ አቤደዛዱህ "አውሮፕላኑ በምዕራብ አቅጣጫ ከአየር ማረፊያ ተነስቶ መብረር ከጀመረ በኋላ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ወደ ቀኝ ዞሮ ተመልሶ ለማረፍ እየመጣ ሳለ ነው የተከሰከሰው" በማለት ማስተባበያ ሰጥተው ነበር።

ኃላፊው ጨምረውም የዓይን እማኞች አውሮፕላኑ አየር ላይ ሳለ በእሳት ተያይዞ ማየታቸውን ገልጸዋል።

ከቴህራን እንደተነሳ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በተከሰከሰው አውሮፕላን ላይ ተሳፍረው የነበሩት 178 ሰዎች በሙሉ አልቀዋል።

Via:- BBC
@YeneTube @Fikerassefa
የሃረማያ ዩኒቨርሲቲ 239 የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ

በሃረማያ ዩኒቨርሲቲ የሃረር የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ ያሰለጥናቸውን 239 የህክምና ዶክተሮች ዛሬ አስመርቋል

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሃረሪ ክልል ርዕሰ-መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋና ሌሎች የክልልና የፌዴራል የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 56 የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።
Via:- ኢዜአ
@YeneTube @Fikerassefa
ኢዜማ በሀዋሳ ህዝባዊ ስብሰባው ተጀምሯል
ስብሰባ ቦታ ሳውዝ ስታር ሆቴል

@YeneTube @Fikerassefa
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ
በዛሬው ቀን 221 የሕክምና ዶክተሮችን በድህረ-ምረቃ፣ ስፔሻሊቲ በተለያዩ የህክምና ዘርፎች በአጠቃላይ 394 ተማሪዎች እያስመረቀ ይገኛል፡፡
@YeneTube @Fikerassefa
#Update ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ሰኞ ይጀምራል ተብሎ የነበረው የአንደኛ ሴሚስተር ፈተና ጊዜ ወደ እሮብ (06/05/2012) ተለውጧል።

@Yenetube @FikerAssefa
የምርጫ ቦርድ በሁለት ረቂቅ መመሪያዎች ላይ ጥር 9 ምክክር ሊያደርግ ነው

የአትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በሁለት ረቂቅ የምርጫ መመሪያዎች ላይ ጥር 9 ቀን 2012 ዓ.ም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመምከር ግብዓት ለማሰባሰብ ማቀዱን አስታውቋል።

ውይይት የሚደረግባቸው ሁለቱ ረቂቅ መመሪያዎች የመገኛኛ ብዙሃን እና የጋዜጠኞች የምርጫ አዘጋገብ “ስነምግባር እና አሰራር ረቂቅ መመሪያ የመጀመሪያው ሲሆን ሌላኛው መመሪያ ደግሞ የስነ ዜጋ እና የመራጮች ትምህርት ፍቃድ አሰጣጥ እና ስነ ምግባር ለመደንገግ የወጣው ረቂቅ መመሪያ ነው።

ቦርዱ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ፀድቆ በወጣው አዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና ቁጥር 1133/2011 መሰረት የተሰጡትን ሀላፊነትና ግዴታን ለመወጣት እንዲያስችለው የተለያዩ መመሪያዎች በማርቀቅ ላይ እንደሚገኝም ጠቁሟል፡፡

Via:- EPA
@YeneTube @Fikerassefa
የአፋር እና የአማራ ክልል ሕዝቦች የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት መድረክ በሠመራ ከተማ እየተካሄደ ነው። በውይይት መድረኩ ከሁለቱ ክልል ሕዝቦች የተውጣጡ ከ500 በላይ የሃይማኖት አባቶች፣ ምሁራን እና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

Via:- elu
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በ17 የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ እገታ ተፈጽሟል መባሉን ተከትሎ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ለታ ተስፋዬ የሰጡት ማብራሪያ

Via:- EBC
@YeneTube @Fikerassefa
በታገቱት ተማሪዎች ዙሪያ ከጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ምንም አይነት መግለጫ አይሰጥም ተባለ

በምዕራብ ኦሮሚያ አንድ ወር ከሁለት ሳምንት በፊት ስለታገቱት 17 የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጉዳይ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ዛሬ ጥር 2/2012 ከምሽቱ 12 ሰአት ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ(ዶ/ር) ለአዲስ ማለዳ የተናገሩ ቢሆንም የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ፕሬስ ሴክሬታሪ ባልደረባ ሔርሜላ ሰለሞን በተባለው ቀን ምንም አይነት መግለጫ እንደማይሰጥ ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ።

ሔርሜላ አያይዘውም በቀጣይ ሳምንት መግለጫው ሊሰጥ እንደሚችል አስታውቀዋል።

ምንጭ:- አዲስ ማለዳ
@YeneTube @Fikerassefa