YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፀደቀ!

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባው በዛሬው እለት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ አድርጓል።ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው ከውጪ ጉዳይና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም በተባባሪነት ከህግ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርምሮ ያቀረበለትን የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ተመልክቷል።በዚህም የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር የሀገርንና የህዝብን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ እንዲሁም የዜጎችን እና የህዝቦችን መብትና ደህንነት ለማስከበር አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ መዘጋጀቱ ተነግሯል...


https://telegra.ph/regulation-01-09
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ችግር ፈጥረዋል ባላቸው 51 ተማሪዎች ላይ እርምጃ ወሰደ

ችግር ፈጥረዋል ባላቸው 51 ተማሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የጅማ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።

ትምህርት እንዲስተጓጎል ፍላጎት ባላቸውና ሁኔታዎችን በመጠቀም ችግር የፈጠሩ 51 ተማሪዎች በመለየት ሕግ የማስከበር እርምጃ መውሰዱን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል፡፡
ለ31 ተማሪዎች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሲሆን 20 ተማሪዎች ላይ ከ1 ዓመት እሰከ ሙሉ በሙሉ ከትምህርት መርሐ-ግብር ማገድ የሚደርስ የዲሲፕሊን ቅጣት እርምጃዎችን መውሰዱ ተገልጿል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዩኒቨርሲቲዉ ባደረገዉ ሰፊ ግምገማ 28 የጥበቃ አባላትን በጡረታ እና 29 ደግሞ ለይቶ ከጥበቃ ሥራ እንዳሰናበተ ነው የተገለፀው።

ተልዕኮውን ለማሳካት በተለያዩ የአስተዳደር ደረጃዎች ላይ ያሉ ኃላፊዎችን በአዳዲስ ሰዎች በመተካት የተቋም ለውጥ ሂደቱን እያንቀሳቀሰ ይገኛልም ተብሏል።

ከተቋማዊ ለውጥ ሂደቱ ጋር በተገናኘ በአስተዳደር እና ተማሪዎች አገልግሎት ዙርያ የምክትል ፕሬዝዳንት እና የ3 ዳይሬክተሮች እንዲሁም በሌሎች ዘርፎችም የ3 ኃላፊዎችን ለውጥ አድርጓል፡፡

Via:- EBC
@YeneTube @Fikerassefa
በ$5000 ዶላር አነስተኛ ስራ መጀመር እቅድ ካሎት በTony Elumelu Foundation ላይ አፕላይ በማድረግ አሸናፊ ለሆኑ ቡድኖች #5000 ዶላር እንደሚሰጥ አስታውቋል።

ከዚህ በፊት የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ይሳተፉበታል ነገር ግን ከኢትዮጵያ ታሳታፊዎች አነስተኛ ናቸው።

-ይህንን ሊንክ በመጠቀም እቅዶን ለፋውንዴሽኑ ይላኩ⬇️

#Share
http://tefconnect.com
አቶ ትግስቱ አወሉ ከፌዴራሊስት ሃይሎች ፎረም ራሳቸውን ማግለላቸወን አስታወቁ።

አቶ ትግስቱ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፤ የፌዴራሊስት ሃይሎች በሚል የተሰባሰበው ሃይል ህወሓት ዳግም የበላይነቱን ለመመለስ የሚያደርገው ጥረት አካል ነው።

እንደ አቶ ትግስቱ ገለጻም፤ ይህ ፎረም የኢትዮጵያን ህዝብ ዳግም ለማስለቀስ ያለመ ነው።

ህወሓት የብልጽግና ፓርቲ አሃዳዊ ነው የሚለው የብሄር ብሄረሰቦችን ቀልብ ለመሳብና የስብስቡ አካል ለማድረግ ነው ያሉት አቶ ትግስቱ፤ የፎረሙ አላማና አካሄድ የህወሓትን የበላይነት ለመመለስ ያለመ በመሆኑ ራሳቸውን ከፎረሙ ምክትል ሰብሳቢነት ጭምር ማግለላቸውን አስታውቀዋል።

Via:-EPA
@YeneTube @Fikerasssefa
ይፍጠኑ

የሃምሳ ፐርሰንት ተጨማሪ የአየር ሰዓት ቦነስ በኀፃ የሚሰጥበት የመጨረሻው ቀን ነገ ነው።

ቦነሱን ለማግኘት በውጭ ሃገር ከሚኖር ወዳጅ ዘመድ የአየር ሰዓት በ remit.et ያስሞሉ።

ለምሳሌ የመቶ ብር የአየር ሰዓት ውጭ ሃገር ከሚኖር ወዳጆ በ remit.et ሲላክሎት ኢትዮ ቴሌኮም ሃምሳ ብር ጨምሮ በድምሩ የመቶ ሃምሳ ብር አየር ሰዓት ወዲያውኑ ይሞላሎታል።
__
In partnership with Ethio Telecom

ቻናላችንን በመቀላቀል በየጊዜው የሚኖረንን የካርድ ስጦታ ይቀበሉ @remiteth
ከ4 ሚሊየን 485 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ሃሺሽ መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።

ሃሺሹ በተሽከርካሪ ተጭኖ ከሻሸመኔ ወደ ኬንያ በመጓጓዝ ላይ እያለ በሀዋሳ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በጪጩ ጉምሩክ ጣብያ ጥሶ ለማለፍ ሲሞክር መያዙ ተገልጿል።
የመኪናው አሽከርካሪ ለፍተሻ ተባባሪ ባለመሆኑ ተረኛ ፌደራል ፖሊስ ጎማውን በጥይት
በመምታት በቁጥጥር ስር መዋሉም ተገልጿል።

የተያዘው ሃሺሽም በተገቢው መንገድ እንዲወገድ ለሚመለከተው አካል ገቢ መደረጉን ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Via:- addis Maleda
@YeneTube @Fikerassefa
የሀድያ ዞን ምክር ቤት የሀድያ ብሔር በክልል የመደራጀት ጥያቄዉን የክልሉ ምክር ቤት ባለማስፈጸሙ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ይግባኝ አቀረበ፡፡

@YeneTube @Fikerassefa
የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ውይይት ያለስምምነት ተጠናቀቀ!

ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በአዲስ አበባ ሲያካሂዱት የቆዩት የሶስትዮሽ ውይይት ያለስምምነት ተጠናቋል።የሶስትዮሽ ውይይቱ መጠናቀቁን ተከትሎ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ውይይቱ ያለስምምነት የተጠናቀቀው ግብፅ የግድቡን የውሃ ሙሌት በተመለከተ አዲስ ሃሳብ ይዛ በመቅረቧ መሆኑን ተናግረዋል።

ትናንት በተጀመረው አራተኛው ዙር የሶስቱ ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች ስብሰባ ግብፅ ግድቡ ከ12 እስከ 21 ዓመት እንዲሞላ የሚል አዲስ ሀሳብ ማቅረቧ ተገልጿል።ኢትዮጵያ በበኩሏ ይህን ሃሳብ በማንኛውም መልኩ እንደማትቀበል መግለጿን ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።ሶስቱ ሀገራት ከዚህ በፊት የህዳሴው ግድብ በ7 ዓመት ውስጥ እንዲሞላ ስምምነት ላይ ደረሰው የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

በቀጣይም የሶስቱ ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች የእስካሁኑን የሶስትዮሽ ስብሰባ ሂደት ሪፖርት ለሀገራቱ መሪዎች የሚያቀርቡ ይሆናል።በተጨማሪም ሚኒስትሮቹ የፊታችን ሰኞ ወደ ዋሽንግተን በማምራት የአለም ባንክ ፕሬዚዳንት እና የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሃላፊ በተገኙበት በተካሄዱት አራት የቴክኒክ ስብሰባዎች ዙሪያ ገለፃ ያደርጋሉ።በዚህ ውይይት ላይም የሶሰቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሚገኙ መሆኑ ተመላክቷል።

ምንጭ:ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
Breakng news...


176 ሰዎችን አሳፍሮ ሰጓዝ የነበረውና ንብረትነቱ የዩክሬን የሆነው አውሮፕላን በስህተት ተኩሳ የጣለቸው ኢራን ነች ሲል የአሜሪካ የዜና ወኪል ዘግቧል።

አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ሀላፊ 'ሲቢኤስ' ለተባለው የዜና ድርጅት አሉት እንደተባለው ከሆነ ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን በኢራን ሚሳኤል ነው ተመትቶ ወደቀው።

ዩክሬን ቀደም ብላ አውሮፕላኑን እንዲከሰከስ ያደረገው ከኢራን የተተኮሰ ሚሳኤል ሊሆን እንደሚችል ግምት አስቀምጣ የነበረ ሲሆን ኢራን ግን ሊሆን አይችልም በማለት አጣጥላው ነበር።


ሲቢኤስ የጠቀሳቸው ከፍተኛ የደህንነት ሀላፊ አውሮፕላኑን ያጠቁ የሁለት ሚሳኤሎች ድምጽ ከተሰማ በኋላ ሌላ ተጨማሪ ሶስተኛ ሚሳኤል እንደተከተለ ከሳተላይት የተገኘ መረጃ ይጠቁማል።

በሌላ በኩል 'ኒውስዊክ' በበኩሉ አንድ የፔንታጎን ከፍተኛ ሀላፊና የኢራቅ የደህንነት አባልን ጠቅሶ እንደዘገበው የዩክሬኑ አውሮፕላን ተመትቶ የወደቀው ሩሲያ ባመረተችው 'ቶር' በሚባል ሚሳኤል ነው።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ትናንት ባስተላለፉት መልእክት ''ከዚህ አውሮፕላን ጋር በተገናኘ ጥርጣሬ አለኝ። የሆነ ሰው ስህተት ሳይሰራ አይቀርም'' ብለው ነበር።

የዩክሬን ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ አውሮፕላን ቴህራን ከሚገኘው ኢማም ኮሜይኒ አውሮፕላን ማረፊያ ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ነው የተከሰከሰው።
አውሮፕላኑ ጉዞውን ወደ ዩክሬን ዋና ከተማ ኪዬቭ አድርጎ ነበር የተነሳው።

Via:- ቢቢሲ
@Yenetube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
Forwarded from YeneTube
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEO_AwEACCqYXy4L9A. 👈🏾👈🏾👈👈👈 🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄
የተከበራችሁ የ SHOPIA®️ ቤተሰቦች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዐል በሰላም አደረሳችሁ ❤️ እያልን በዐሉን ምክንያት በማድረግ ከ 25/04/12(ቅዳሜ) ጀምሮ ለ 3 ተከታታይ ቀናት በቻናላችን በኩል በሚሸጡ ሁሉም ዕቃዎች ላይ 5-15%⬇️ ቅናሽ አድርገናል።🤗
🎉🛍 ይግዙ በዕድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ ቅናሹ የሚቆየው እስከ በዐሉ ዋዜማ ድረስ ብቻ ነው🎁🛒

🎅🎄🎅🎄🎅🎄🎅🎄🎅🎄🎅
⭐️ መልካም የገና በዐል ⭐️
⭐️ SHOPIA ⭐️
🎅🎄🎅🎄🎅🎄🎅🎄🎅🎄🎅👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEO_AwEACCqYXy4L9A
Forwarded from YeneTube
🎊እንኳን አደረሳችሁ🎉
ፈረስ ለበዓሉ ስጦታዎችን አዘጋጅቶላችኋል 🎁🎁🎁

አንድ ሙክት በግ እና ሁለት ዶሮዎች አዘጋጅቶላችኋል

ከዚህ ሽልማት አሽናፊ ለመሆን

ፈረስ ይዘዙ እና የሄዱበትን ሂሳብ ስክሪን ሻት አድርገው ይላኩልን @FCS6090


ደንብና ግዴታዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ።
Forwarded from TARGET MARKETS ®
Perfumes 👇👇👇👇👇
100 ml 👇👇👇👇👇👇
ALL AVILABLE NOW🔥🔥🔥
Contact @kiru04
0931607806

Miss dior-1100 birr
Miss dior-1500
Poison girl dior-1500 birr
Ysl manifesto-1100 birr
YSL-1100 birr

ALL AVILABLE NOW🔥🔥🔥
Contact @kiru04
0931607806
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEPkyxEP1snCoAkFGw
ዶ/ር አሚር አማን ከፍተኛ አማካሪ ሆነው ተሾሙ

በአሜሪካዊው ባለሀብት ዋረን ቡፌት ከ56 አመት በፊት የተመሰረተውና በሴቶች ወሊድና ፅንስ ክትትል አለም ላይ ያለትርፍ በሚሰራው ሱዛን ቶምፕሰን ቡፌት ፋውንዴሽን በተባለ ተቋም የቀድሞ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን ከፍተኛ አማካሪ ሆነው መሾማቸውን ማረጋገጡን ጋዜጠኛ ተስፋዬ ጌትነት ዘግቧል ። ፋውንዴሽኑ ዋና ቢሮ አሜሪካ ግዛት ባለቸው ኔቤሪስካ ኦማሃ ከተማ ውስጥ ይገኛል።

ምንጭ:- ጋዜጠኛ ተስፋዬ ጌትነት
@YeneTube @Fikerassefa
የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶ በኢራን የተከሰከሰው አውሮፕላን በሚሳኤል ተመቶ ስለመውደቁ መረጃዎች ደርሰውናል አሉ፡፡

ምእራባዊያን መሪዎች ረቡዕ እለት በቴህራን የተከሰከሰው የዩክሬን የመንገደኞች አውሮፕላን፤ በኢራን ሚሳኤል ተመቶ መውደቁን #ማስረጃዎች_ያሳያሉ_እያሉ ነው፡፡

የካናዳና የእንግሊዝ መሪዎች 176 ሰዎች ለሞቱበት አደጋ የተሟላ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ እቅርበዋል፡፡

አደጋው የተከሰተው ኢራን በኢራቅ የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ የሚሳኤል ጥቃት ከፈጸመች ከሰዓታት በኋላ ነበር፡፡

ከዚህ ከመነሳትም የአሜሪካ ብዙሃን መገናኛዎች አውሮፕላኑ ከአሜሪካ ለአጸፋ እርምጃ የተላከ የጦር አውሮፕላን መስሏት ኢራን በስህተት መታዋለች ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

የአሜሪካ የደህንነት ባለስልጣናትም አውሮፕላኑ በሩሲያ ሰራሽ ሚሳኤል መመታቱን ተናግረዋል፡፡

አደጋውን ተከትሎ ኢራን የመረጃ ሳጥኑን ለአሜሪካም ሆነ ለአምራች ድርጅቱ ቦይንግ አልሰጥም ብትልም፤ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሞሃመድ ጃቫድ ዛሪፍ በአደጋው ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ቦይንግን መጋበዛቸው ተሰምቷ፡፡

በአደጋው ከኢራን ቀጥሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎቿን ያጣችው ካናዳ ስትሆን 63 ዜጎቿ ሞተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶ አውሮፕላኑ በኢራን የአየር መቃወሚያ ሚሳኤል መመታቱን የሚያመላክቱ መረጃዎች ከተለያዩ ምንጮች እየደረሷቸው መሆኑን ገልጸው፤ይህም በስህተት የተፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የቱሩዶና ሃሳብ አጠናክረው ከሌሎች በአደጋው ዜጎቻቸውን ካጡ ሃገራት ጋር በቅርበት እጠሰሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ኢራን በበኩሏ ውንጀላውን ውድቅ ውድቅ ማድረጓን #ቢቢሲ_ዘግቧል፡፡

ምንጭ:- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa
በአውስትራሊያ የተከሰተው እሣት 240 ሺ ሰዎች ርቀው እንዲሸሹ ማድረጉ ተነግሯል፡፡

የአውስትራሊያ ባለሥልጣናት ሩብ ሚሊዮን ህዝብ በአስቸኳይ ካለበት ሥፍራ ለቅቆ ይርቅ ዘንድ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

በአውስትራሊያ የተነሣው እሣት በሙቀት መጠኑ መጨመር እየታገዘና በሃይለኛ የነፋስ ወጀብ እየተራገበ በምሥራቃዊ የሀገሪቱ ጠረፍ ያገኘውን ሁሉ እየበላ በመገሥገስ ላይ መሆኑም ነው የሚነገረው፡፡

በመላው አውስትራሊያ የሙቀት መጠን ከ40 ዲግሪ ሴልሺየስ መዝለሉንም ነው የሚገልፁት፡፡

ከ240 ሺ በላይ ህዝቦች በአሥቸኳይ ሥፍራቸውን ለቀው ይሸሹ ዘንድ የማስጠንቀቂያ ትዕዛዝ ተላልፎላቸዋል፡፡

Via:- ዘ-ቴሌግራም / አሐዱ
@YeneTube @FikerAssefa