YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶ በኢራን የተከሰከሰው አውሮፕላን በሚሳኤል ተመቶ ስለመውደቁ መረጃዎች ደርሰውናል አሉ፡፡

ምእራባዊያን መሪዎች ረቡዕ እለት በቴህራን የተከሰከሰው የዩክሬን የመንገደኞች አውሮፕላን፤ በኢራን ሚሳኤል ተመቶ መውደቁን #ማስረጃዎች_ያሳያሉ_እያሉ ነው፡፡

የካናዳና የእንግሊዝ መሪዎች 176 ሰዎች ለሞቱበት አደጋ የተሟላ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ እቅርበዋል፡፡

አደጋው የተከሰተው ኢራን በኢራቅ የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ የሚሳኤል ጥቃት ከፈጸመች ከሰዓታት በኋላ ነበር፡፡

ከዚህ ከመነሳትም የአሜሪካ ብዙሃን መገናኛዎች አውሮፕላኑ ከአሜሪካ ለአጸፋ እርምጃ የተላከ የጦር አውሮፕላን መስሏት ኢራን በስህተት መታዋለች ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

የአሜሪካ የደህንነት ባለስልጣናትም አውሮፕላኑ በሩሲያ ሰራሽ ሚሳኤል መመታቱን ተናግረዋል፡፡

አደጋውን ተከትሎ ኢራን የመረጃ ሳጥኑን ለአሜሪካም ሆነ ለአምራች ድርጅቱ ቦይንግ አልሰጥም ብትልም፤ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሞሃመድ ጃቫድ ዛሪፍ በአደጋው ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ቦይንግን መጋበዛቸው ተሰምቷ፡፡

በአደጋው ከኢራን ቀጥሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎቿን ያጣችው ካናዳ ስትሆን 63 ዜጎቿ ሞተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶ አውሮፕላኑ በኢራን የአየር መቃወሚያ ሚሳኤል መመታቱን የሚያመላክቱ መረጃዎች ከተለያዩ ምንጮች እየደረሷቸው መሆኑን ገልጸው፤ይህም በስህተት የተፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የቱሩዶና ሃሳብ አጠናክረው ከሌሎች በአደጋው ዜጎቻቸውን ካጡ ሃገራት ጋር በቅርበት እጠሰሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ኢራን በበኩሏ ውንጀላውን ውድቅ ውድቅ ማድረጓን #ቢቢሲ_ዘግቧል፡፡

ምንጭ:- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa
የዓለም ባንክ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ 12 ቢሊየን ዶላር እርዳታ ለመስጠት ቃል ገባ

የዓለም ባንክ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ትግል ውስጥ ያሉ አዳጊ አገራትን ያግዝ ዘንድ የ12 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገብቷል።

ዓለም ባንክ ገንዘቡን የሚሰጠው በብድር፣ በእርዳታና በቴክኒክ ድጋፍ መልክ ሲሆን፣ ባንኩ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የዓለም መሪዎች ኮሮና ቫይረስ ኢኮኖሚያቸውን እንዳያሽመደምድ ብርቱ ዝግጅት ለማድረግ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ ነው።

ኮሮና ቫይረስ የአገራቱ ኢኮኖሚዎች ላይ የሚያስከትለው መቀዛቀዝ አገራትን ችግር ውስጥ ሊከት እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

ይህ የዓለም ባንክ እርዳታ አገራት የኮሮና ቫይረስን ስርጭት በመከላከል ረገድ የጤና አገልግሎት ስርዓቶቻቸውን እንዲያጠናክሩና ቫይረሱ የሚያሳድረውን ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ ለመቀነስ ከግል ዘርፍ ጋር እንዲሰሩ ለማስቻል ነው ተብሏል።
"ለማድረግ እየሞከርን ያለነው የቫይረሱ ስርጭት እንዲገታ ነው" ብለዋል የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማልፓስ።

ዓለም ባንክ እንዳስታወቀው እርዳታውን በቅድሚያ የሚሰጠው በጣም ድሃ ለሆኑ አገራትና ለቫይረሱ ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ለሆኑ አገሮች ነው።
ኮሮና ቫይረስ በ70 አገራት ላይ እንደተሰራጨ የሚታወቅ ነው።

ዓለም ባንክ ቃል የገባው ገንዘብ ግማሽ ያህሉ ከባንኩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ኮርፖሬሽን የሚገኝ ሲሆን አራት ቢሊየን የሚሆነው ደግሞ ቀደም ሲል ከነበሩ ፈንዶች ተዘዋውሮ የሚመጣ እንደሆነ ተገልጿል።

እስካሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ 92 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን 80 ሺህ የሚሆኑት የተመዘገቡት ቻይና ውስጥ ነው። በሌላ በኩል ሶስት ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ የሞቱ ሲሆን በተመሳሳይ ብዙዎቹ መሞታቸው የተመዘገበው በቻይና ነው።

በዛሬው እለት 38 ሰዎች በቻይና መሞታቸው የታወቀ ቢሆንም የቻይና መንግሥት እንቅስቃሴን የሚገቱ ጥብቅ እገዳዎችን በመጣሉ ካለፉት ጥቂት ሳምንታት ወዲህ አዳዲስ በኮሮና ቫይረስ የመያዝ ሪፖርቶች ቀንሰዋል እየተባለ ነው ሲል #ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

Via:- BBC /Walta
@YeneTube @Fikerassefa
ህንድ በኮሮና ቫይረስ ሟቾች ቁጥር በአለም አራተኛ ሀገር ሆናለች
ይህም ሀገሪቱን ከአሜሪካ ብራዚል እና ሜኪስኮ ቀጥሎ አራተኛዋ ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር የተመዘገበባት ሀገር ያደርጋታል።

በሃገሪቱ እስካሁን በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ምክንያት 47 ሺ 033 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን የተጠቂዎች ቁጥርም 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ደርሷል፡፡

ጆንሆፕስኪንስ ዩኒቨርስቲ ባወጣው መረጃ መሰረት በህንድ በቀን ከ66 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ይያዛሉ።

አንዳንድ ባለሙያዎች ለቫይረሱ በስፋት መሰራጭት የሃገሪቱ የህዝብ ቁጥር ብዛት ከፍተኛ ሚና አለው ሲሉ ስጋታቸውን መግለጻቸውን #ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @Fikerassefa
በአሜሪካ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ ሪፐብሊካኖች በተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ ወንበር አሸንፈዋል።

በምርጫው ሪፐብሊካኖች እስካሁን የምክር ቤቱን መቀመጫ ለመቆጣጠር የሚያስፈልጋቸውን 218 ወንበሮች አግኝተዋል ነው የተባለው።

ሪፐብሊካኖች ተጠባቂውን የካሊፎርኒያ 27ኛ አውራጃ ምርጫ ማይክ ጋርሺያ ማሸነፋቸውን ተከትሎ አብዛኛውን የምክር ቤት መቀመጫ ማሸነፍ መቻላቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በምርጫው በየግዛቶቹ የተሰጡ ድምፆች ተቆጥረው ያላለቁ ሲሆን ሪፐብሊካኖቹ ከ435ቱ መቀመጫዎች ከ218 እስከ 223 መቀመጫዎች እንደሚያሸንፉ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም የዴሞክራቷን ተወካይና የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲን ለመተካት ኬቨን ማካርቲ ዕጩ መሆናቸውን #ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa