YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በሚቀጥሉት ሁለት ቴክኒካዊ ስብሰባዎች ለታላቁ የኅዳሴ ግድብ የውሐ አሞላል እና አስተዳደር ቴክኒካዊ ሕግጋት እና መመሪያዎች ለማዘጋጀት ተስማሙ።

ሶስቱ አገሮች በዋሽንግተን ካደረጉት ግምገማ በኋላ በአሜሪካ ግምዣ ቤት በኩል ባወጡት የጋራ መግለጫ በግድቡ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ስለሚችል የድርቅ ሁኔታ ብያኔ ለመስጠት እና ድርቅን ለመከላከል ሊወሰዱ የሚችሉ እርምጃዎችን በሚቀጥሉት ሁለት ስብሰባዎች ለመለየት ተስማምተዋል። ሶስቱ አገሮች ከስምምነቱ የደረሱት በምኒስትሮች ደረጃ በዋሽንግተን ባደረጉት ሁለተኛ ስብሰባ ነው። ቀጣዮቹ ሁለት የባለሙያዎች ስብሰባዎች በአዲስ አበባ እና በኻርቱም ይደረጋሉ። ሕግጋት እና መመሪያዎቹ በወንዙ አመታዊ የፍሰት እና ከታላቁ የኅዳሴ ግድብ የሚለቀቅ የውሐ መጠን መሰረት ድርቅን ለመከላከል የሚያስችሉ እርምጃዎችን ያካትታሉ።

ምኒስትሮቹ ባወጡት የጋራ መግለጫ መሰረት የኅዳሴ ግድቡ የውሐ አሞላል እና አስተዳደር የሚወስኑትን ቴክኒካዊ ሕግጋት እና መመሪያዎች ኢትዮጵያ ተግባራዊ ታደርጋለች። ምን አልባት በማንኛውም አመት ሊኖር እንደሚችል ተለዋዋጭ የአየር ጠባይ ሁኔታ (hydrological conditions) ሶስቱ አገሮች ሊያስተካክሏቸው እንደሚችሉ ተገልጿል። ምኒስትሮቹ በመጪው ጥር 13 ቀን 2020 የአዲስ አበባ እና የኻርቱም ቴክኒካዊ ስብሰባዎችን ውጤት ለመገምገም በዚያው በዋሽንግተን ይገናኛሉ። የሶስቱ አገሮች የዋሽንግተን ውይይት ከቀደሙት አኳያ ሲመዘን አሜሪካ እና የዓለም ባንክ ከታዛቢነት የዘለለ ሚና እንዳላቸው ይታያል።

Via Sheger Tribune
@YeneTube @FikerAssefa
በኒውዝላንድ የፈነዳ እሳተ ጎመራ አምስት ሰዎችን ሲገድል ከ30 በላይ በሚሆኑት ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ፡፡

ከዋና ከተማዋ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ዋካሪና በተሰኘ ቦታ ላይ የፈነዳው እሳተ ጎመራ በርካቶች ላይ ጉዳት ማድረሱ ተነግሯል፡፡በሃገሪቱ የሚገኘው ዋይት አይስ ላንድ ኮረብታ ላይ የፈነዳው እሳተ ጎመራ የ 5 ሰዎችን ህይወት ማሳጣቱን የአገሪቱ ባለስልጣናት ለሮይተርስ ተናግረዋል።

ይሁንና የአይን እማኞች ግን የሟቾች ቁጠር 13 መድረሱን ለዚሁ ሚዲያ ተናግረዋል፤።ከ30 በላይ ሰዎች ደግሞ በፍንዳታው ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተነግሯል፡፡

እሳተ ጎመራው ከመፈንዳቱ አስቀድሞ 50 ጎብኝዎች አካባቢውን ሲጎበኙ እንደነበር የተነገረ ሲሆን የቻይና፤አውስትራሊያ፤ማሌሸዢያ፤የአሜሪካና የሌሎችም ሃራ ጎብኝዎች በስፍራው ላይ ነበሩ ተብሏል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም መቀመጫውን ኡጋንዳ ያደረገው ዲፌንድ ዲፌንደርስ የተሰኘ የሰብአዊ መብት ድርጅት ለሰብአዊ መብት ጉዳይ ለከፈላችሁት ዋጋ ክብር ይገባችኋል ብሎ በ71ኛው የሰብአዊ መብት ቀን ዋዜማ አመስግኖአቸዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
Today Exchange Rate
#BusinessView #CBE
#Humanright #HRW

በየአመቱ ዲሴምበር 10 ተከብሮ የሚውለውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ቀንን ምክንያት በማድረግ ምክክሩ እንደሚካሄድ ሰምተናል፡፡ኮሚሽነሩ ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ለሸገር እንደተናገሩት፣ ኮሚሽኑ ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሚያዘጋጀው ምክክር ወቅታዊው የሰብአዊ መብት አያያዝን በተመለከተ በምሁራን ለውይይት መነሻ የሚሆን ጥናት ይቀርባል፡፡ችግሮቹም ተነቅሰው ከተዘረዘሩ በኋላ የመፍትሄ ሀሰብ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል ብለውናል፡፡

በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝ እንዲሻሻል የተጉ ኢትዮጵያውያንም እውቅና እንደሚሰጣቸው ሰምተናል፡፡በየአመቱ ዲሴምበር 10 ተከብሮ የሚውለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ቀን መነሻው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አማካኝነት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ ሰነድ የፀደቀበት እለት ነው፡፡የዘንድሮው የዓለም የሰብአዊ መብት ቀን ለ71ኛ ጊዜ የሚከበር ነው፡፡

Via:- Sheger FM
@Yenetube @Fikerassefa
የደቡብ ክልል ምክር ቤት አንድ አመት ልሞላው ጥቂት ቀናት ለቀረው የወላይታ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ በአጭር ጊዜ ውሰጥ ምላሸ ካልሰጠው ጉዳዩን ወደ ፌዴሬሸን ም/ቤት እንዲወሰድ የቀረበለትን አጀንዳ የወላይታ ዞን ም/ቤት በሙሉ ድምፅ አፀደቀ።

የወላይታ ዞን ምክር ቤት አራተኛ ዙር ሰባተኛ ዓመት አንደኛ አስቸኳይ ጉባኤ በጠራው ስብሰባ ያወጣው የአቋም መግለጫ።

👇👇👇👇

https://telegra.ph/Wolaita-12-10
የ19 ሀገራት የተለያየ መጠን ገንዘብ በህገ ወጥ መንገድ ከሃገር ሊወጣ ሲል በቁጥጥር ስር ዋለ!

በቀን 27/03/2012 ከድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ኤርፖር ወደ ጅቡቲ የሚጓዘዉ መንገደኛ ፍፁም ባለተለመደ መልኩ የተለያዩ 19 ሀገራትን ገንዘብ ይዞ ከአገር ሊወጣ ሲል እጅ ከፍንጅ ተይዟል፡፡ከድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ኤርፖር ወደ ጅቡቲ ለመጓዝ አቶ እስማኤል አህመድ ኡስማን የተባለ ግለሰብ ላይ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኤርፖረት መቅ/ጣቢያ ሰራተኞች በተደረገ ፍተሻ የ19 ሀገራት የተለያየ መጠን የመገበያያ ገንዘቦችን በመያዝ በህገወጥ መንገድ ከሀገር ለማስወጣት ሲሞክር በጉምሩክ ሰራተኞች ተይዞ ገቢ የተደረገ ሲሆን ግለሰቡም ተይዞ ምርምራ እየተደረገበት ይገኛል፡፡

Via Ministry of Revenue
@YeneTube @FikerAssefa
የኖቤል ሰላም ሽልማት አሰጣጥ ስነ-ስርዓት ዛሬ ማክሰኞ ኅዳር 30 ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች መከታተል ይችላሉ:

bit.ly/2P1qZvM & nobelprize.org

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በሚገኙ ት/ቤቶች የሚማሩ ሴት ተማሪዎች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እንዲሰራጩ በሚያስችልበት ሁኔታዎች ዙሪያ ኢ/ር ታከለ ኡማ በጉዳዩ ላይ ከሚሰሩ የበጎ ፍቃድ ማህበራት ጋር ተነጋገሩ፡፡

በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ለሴቶችና ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆኑ መጸዳጃ ቤቶችን መገንባት በሚቻልበት ዙሪያም ውይይት ተደርጓል፡፡የከተማ አስተዳደሩ ለሴቶች የወር አበባ ንጽሕና መጠበቂያ ዋጋ መናር ምክንያት የሆኑ የህግና የአስተዳደር ጉዳዮችን በመፈተሽ እንዲሁም ቀጥተኛ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው በተለይም ለተማሪዎች መድረስ የሚችል ተግባራዊ ስራ በቅርቡ የሚጀምር መሆኑን ኢ/ር ታከለ ኡማ በፌስቡክ ገፃቸው ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡

እነዚህ ድጋፎች ታዳጊ ሴቶች በወር አበባ ምክኒያት ከትምህርት እስከ መቅረት የሚያደርሱ ችግሮችን ለመፍታትና የሴቶች የትምህርት ተሳትፎን ማሳደግ ላይ የሚሰሩ ሰራዎች አካል ናቸው፡፡ከቁሳቁስ አቅርቦት በተጨማሪ የወር አበባን በተመለከተ ለታዳጊ ሴቶችና ለተለያዩ የማህበረሰብ አካላት በየትምህርት ቤቶቹ ተከታታይ የሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች የሚሰሩ ይሆናል፡፡

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት ተቀበሉ።

@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠ/ሚ አብይ አህመድ የሰላም ሎሬት ሽልማት ሲቀበሉ።

@YeneTube @FikerAssefa
ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በኖርዌይ፣ ኦስሎ የኖቤል የሰላም ሽልማታቸውን ከተቀበሉ በኋላ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፡-

📌 የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ ለሰጠኝ እውቅና አመሰግናለሁ፡፡
📌 ለኢትዮ-ኤርትራ የሰላም ስምምነት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሰላም ቁርጠኝነት ወሳኝ ነበር፡፡
📌 ይህንን ሽልማት የአፍሪካ ህዝቦችና የዓለም ህዝቦችን ወክዬ ነው የምቀበለው፡፡
📌 ከ20 ዓመታት በፊት በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት የሬድዮ ኦፕሬተር ነበርኩ፡፡
📌 ጦርነቱ በርካታ ቀውሶችን አስከትሎ ነበር፡፡
📌 በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ለሁለት አስርት ዓመታት ሰላም አልነበረም፤ ሰዎች ተለያይተዋል፤ በርካታ ሰራዊት በሁለቱ አገራት ድንበር ላይ መሽጎ ነበር፡፡
📌 ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆንኩ በኋላ የሁለቱ አገራት ህዝቦች ልዩነት መቆም እንዳለበት ወሰንኩ፡፡
📌 ሁለቱ አገራት ጠላቶች እንዳልሆኑ ይልቁንስ ድህነት የጋራ ጠላታችን እንደሆነ አውቀን ለአገራቱ እና ለቀጠናው ብልፅግና መስራት ጀመርን፡፡
📌 መደመር አገር በቀል ሀሳብና የጋራ ብልጽግና ላይ ያተኮረ ፍልስፍና ነው፡፡
📌 የመደመር ጽንሰ ሀሳብ እንደ ዘር ውስጤ የበቀለው በኦሮሚያ ክልል በምትገኝ የትውልድ መንደሬ በሻሻ ውስጥ ነው፡፡
📌 በመደመር ጽንሰ ሀሳብ ውስጥ እኛና እነሱ የሚባል ነገር የለም፡፡
📌 ኢትዮጵያውያን በአንድነት በመቆማችን ለዓመታት ነፃ አገር ሆነን ቆይተናል፡፡
📌 የአፍሪካ ቀንድ የአሸባሪዎች ቀጠና እንዲሆን አንፈልግም፣ የሰላም ቀጠና እንጂ፡፡
📌 ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሰላም ላይ ኢንቨስት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
📌 ለዴሞክራሲ ግንባታ መንገድ ዘርግተናል፤ በቅርቡ ነፃና ፍትሓዊ ምርጫ እናካሂደለን፡፡
📌 ለሁሉም ዜጎቿ እኩልነት መረጋገጥ አብረውኝ እንዲሰሩ ለኢትዮጵያውያን ጥሪ አቀርባለሁ፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ባንክ የአክሲዮን ሽያጩን ለአንድ ወር አራዘመ።

ባንኩ በድረገጹ እንዳስታወቀው የአክስዮን ሽያጩ አስከ ሕዳር 30 ቀን ቢሆንም በህዝብ ጥያቄ መሰረት የመሸጫ ጊዜውን እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን አስታውቋል።ከስድስት ወር በፊት የአክስዮን ሽያጩን የጀመረው አማራ ባንክ አክስዮን መሸጥ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ30 ሺህ በላይ ግለሰቦችና ድርጅቶች በአክሲዮን ግዥ ተሳትፈዋል።በአስካሁኑ ሂደትም ከ 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ አክሲዮን በካሽ መሸጡን አስታውቋል

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በየመንገዱ የስልክ ስክሪን ማጠንከሪያ ተብሎ አገልግሎት ላይ እየዋለ ስላለው ፈሳሽ የሚያውቀው ነገር አለመኖሩን የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለሥልጣን አስታወቀ። ናኖ ቴክኖሎጂ በውስጡ በርካታ ነገሮችን እንደሚይዝና ጠንከር ያለ ምርመራ የሚያስፈልገው ነገር እንደሆነም ባለስልጣኑ አስታውቋል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ በሚል በአማርኛ የሚታወቀው እና በትግርኛ ምህፃሩ ዴምህት ራሱን አክስሞ ከህወሓት ጋር በመዋሃድ ለመታገል መወሰኑን አስታወቀ፡፡ የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ ህወሓት በበኩሉ የዴምህትን ውሳኔ አድንቋል፡፡

ምንጭ:ዶቼ ቬለ
@YeneTube @FikerAssefa
የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በፍርድ ቤት ለመሞገት ተሰናድቻለሁ- ብሏል የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ኅብረት፡፡ ኅብረቱ የመንግሥት ተቋማት ሃላፊነታቸውን አንዲወጡ ግፊት እያደረገ ነው፡፡ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተፈጸመባቸው አካባቢዎችም መረጃዎችን እየሰበሰበ እንደሆነ ሸገርን ጠቅሶ ዋዜማ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
CHINESE CLASS WILL BEGIN ON Dec 17,2019. SCHEDULE1:
Tuesday, Thursday and Saturday from evening 6:00pm-7:30 pm and SCHEDULE 2:
Saturday(in the noon 3:pm-6pm) and Sunday(in the morning 9am-12am)
Duration: 2-6 months

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
Forwarded from YeneTube
💥ማስታወቂያ💥
PUMA (GV SPECIAL)

📎ORIGINAL

Size 40-41-42-43

📌 Made in Vietnam
📌 Price 2200 birr
📌 With delivery
📌 በ 5 አይነት ከለር
📞 0912732493

ቴሌግራም ለማግኘት ሊንኩን ተጭነው ይቀላቀሉን👇👇
@Hkaeg