#Humanright #HRW
በየአመቱ ዲሴምበር 10 ተከብሮ የሚውለውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ቀንን ምክንያት በማድረግ ምክክሩ እንደሚካሄድ ሰምተናል፡፡ኮሚሽነሩ ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ለሸገር እንደተናገሩት፣ ኮሚሽኑ ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሚያዘጋጀው ምክክር ወቅታዊው የሰብአዊ መብት አያያዝን በተመለከተ በምሁራን ለውይይት መነሻ የሚሆን ጥናት ይቀርባል፡፡ችግሮቹም ተነቅሰው ከተዘረዘሩ በኋላ የመፍትሄ ሀሰብ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል ብለውናል፡፡
በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝ እንዲሻሻል የተጉ ኢትዮጵያውያንም እውቅና እንደሚሰጣቸው ሰምተናል፡፡በየአመቱ ዲሴምበር 10 ተከብሮ የሚውለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ቀን መነሻው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አማካኝነት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ ሰነድ የፀደቀበት እለት ነው፡፡የዘንድሮው የዓለም የሰብአዊ መብት ቀን ለ71ኛ ጊዜ የሚከበር ነው፡፡
Via:- Sheger FM
@Yenetube @Fikerassefa