YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ኢትዮ-ቴሌኮም 47 ድርጅቶች ላይ እርምጃ ወሰደ

ኢትዮ-ቴሌኮም 47 ድርጅቶች ላይ እርምጃ ወሰደ
ከሞባይል ተጠቃሚው ፈቃድና ፍላጎት ውጪ አጭር የጽሑፍ መልዕክትን በመላክ ሲያማርሩ ነበር የተባሉ 47 ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን ኢትዮ-ቴሌኮም አስታወቀ፡፡

ኩባንያው የአጭር መልዕክት አገልግሎት ላይ ደንበኞች ለረጅም ጊዜ ቅሬታ ሲያቀርቡ እንደነበር ገልጿል፡፡

''አጭር ቁጥር በመጠቀም የሚሰጡ የመልዕክት አገልግሎቶች በህብረተሰቡ ፈቃድ ላይ ብቻ የተመሰረቱ መሆን አለባቸው'' ያለው ኢትዮ ቴሌኮም ያለፈቃድ ይልኩ የነበሩትን ድርጅቶች መዝጋቱን አክሏል፡፡

በዐጭር የፅሑፍ አገልግሎት ጠቃሚ መልዕክቶች እንደሚተላፉም እረዳለሁ ያለው መንግሥታዊው ተቋም አገልግሎቶቹን በህብረተሰቡ ፈቃድ ላይ ብቻ ተመስርተው እንዲሰጡ ቁጥጥር እያደረግሁ ነው ብሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት 310 ድርጅቶች ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር በመተባበር በአጭር ቁጥር የጽሁፍ መልዕክት አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ይታወቃል።

Via:- አሀዱ ራዲዮ
@YeneTube @Fikerassefa
ለጅማ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በሙሉ!
……………………………………………………….
ውድ ተማሪዎቻችን ከዚህ ቀደም እንደገለጽንው ምዝገባችሁ የሚፈጸመው ጥቅምት 1ዐ እና 11 መሆኑን እያስታወስን፤ የ12ኛ ክፍል አድሚሽን ቁጥራችሁን በማስገባት የተመደባችሁበትን ካምፓስ፣ መኝታ ክፍል እና መመገቢያ አዳራሽ ባላችሁበት ሆናችሁ የምታውቁበትን ሲስተም (https://placement.ju.edu.et ) ላይ በመግባት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን፤ ለምዝገባ የሚረዳችሁን ፎቶግራፍ ሲስተሙ ላይ አስቀድማችሁ ማስገባት እንደምትችሉ እንገልጻለን፡፡

Via:- ጂማ ዩንቨርስቲ
@YeneTube @Fikerassefa
ደብዳቤው ወደ ምርጫ ቦርድ ተልኳል!!

የሲዳማ ክልል ጥያቄ ላይ የሚደረገው ሪፍረንደም በህዳር 03/03/2012 ይደረጋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም የክልሉ መንግስት እና የዞኑ አስተዳደር ማሟላት ያለበትን ቅድመ ሁኔታ በጊዜ ባለሟሟላቱ የሪፍረንደሙ ጊዜ ወደ ህዳር 10 መዘዋወሩን ምርጫ ቦርድ ትላንት በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።ከማረዘምያ ምክንያቶች አንዱ የነበረው የደቡብ ክልል ምክር ቤት ህዝበ ውሳኔው የሚካሄድባቸውን ቀበሌዎች ቁጥር እና ካርታ በጊዜ ገቢ አለማድረጉ ነው ተብሎ የነበረ ሲሆን ትላንት ማታ በደቡብ ክልል እና በሲዳማ ተወካዮች በተደርገ እልህ አስጨራሽ ክርክር ብኋላ የቀበሌዎቹን ቁጥር የያዘ ሰነድ ወደ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ጥዋት ተወስዷል። 598 የምርጫ ቀበሌዎች ያሉ ሲሆን ደብዳቤውን ይዘው ያመሩት የዞኑ አስተዳዳሪ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ እና የዞኑ አፈጉባኤ ናቸው።

ምንጭ: ማለዳ ሚድያ
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ተጨማሪ አንድ ቢሊዮን ዶላር የቀጥተኛ በጀት ድጋፍ ‹‹ልታገኝ ትችላለች››

ኢትዮጵያ ተጨማሪ አንድ ቢሊዮን ዶላር የቀጥተኛ በጀት ድጋፍ ከአለም ባንክ ማግኘቷ እርግጥ እንደሆነ የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዢ ይናገር ደሴ ከብሉም በርግ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ አስታውቀዋል።ባለፈዉ በጀት አመት 1ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ቀጥተኛ በጀት ድጋፍ ኢትዮጵያ ማግኘቷ የሚታወስ ሲሆን በወቅቱም አገሪቷ እንድታሟላ የተሰጧትን ግቦች በየአመቱ ካሳካች ተጨማሪ ድጋፍ እንደምታገኝ በአለም ባንክ ቃል እንደተገባላቸዉ ይናገር ተናግረዋል። በዚህ አኳያ፤ ኢትዮጵያ ያለችበት ደረጃ አመርቂ መሆኑን አውስተዋል።

Via አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የሀዘን መግለጫ! ተማሪ አሌክሳንደር ተስፋዬ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከ 2004 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት የመጨረሻ ዓመት የህክምና ተማሪ ሆኖ የqualification ፈተና ለመፈተን በዝግጅት ላይ በነበረበት ወቅት፤ ማለትም በቀን 02/02/2012 ዓ.ም ምሽት ላይ በደረሰበት ከፎቅ ላይ የመውደቅ ድንገተኛ አደጋ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ሕይወቱን ለማትረፍ ከፍተኛ ርብርብ…
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአንድ ተማሪ ህይወቱ አለፈ

ተማሪ አሌክሳንደር ተስፋዬ የተባለ የስድስተኛ አመት የህክምና ተማሪ ጥቅምት 2 ቀን 2012 ምሽት ላይ ከፎቅ ላይ ወድቆ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡

ተማሪው ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ሕይወቱን ለማትረፍ ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም ሕይወቱ ማትረፍ እንዳልተቻለ፣ የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ግኙኝነትና የኮሚኒኬሽን ዳይይክተር ወ/ሮ አርማዬ አሰፋ ተናግረዋል፡፡

ከተማሪው ሞት ጋር ተያይዞ እስካሁን ምንም አይነት መረጃ እንዳልተገኘና ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራውን እያካሄደ ይገኛል ተብሏል፡፡
ተማሪ አሌክሳንደር በአሁኑ ወቅት የመጨረሻ ዓመት የህክምና ተማሪ ሆኖ የqualification ፈተና ለመፈተን እየተዘጋጀ እንደነበረ ወ/ሮ አርማዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
ተማሪዉ ስርአተ ቀብሩ በአዲስ አበባ በትላንትናው እለት ተፈጽሟል፡፡

Ethio FM
@Yenetube @FikerAssefa
የኦዲፒ ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን እያካሄደ ነው!

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።ማእከላዊ ኮሚቴው ስብሰባውን በአዲስ አበባ ከተማ ነው በማካሄድ ላይ የሚገኘው። የኦዲፒ ማእከላዊ ኮሚቴ በስብሰባውም የፓርቲውን እና የክልሉን መንግስት የስራ አፈፃፀም በመገምገም አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል።በዚህም ኮሚቴው የነበሩ ጥንካሬዎችን እና ድክመቶችን በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ነው የተባለው።እንዲሁም ማእከላዊ ኮሚቴው በወቅታዊ ሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ተጠቁሟል፡፡የኦዲፒ ማእከላዊ ኮሚቴ በስብሰባው የፓርቲው የውስጥ አንድነት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሪፎርምንም በአጀንዳ መያዙን ተነግሯል።ከዚህ በተጨማሪም ማእከላዊ ኮሚቴው እንደ ሀገር እና እንደ ክልል የተጀመሩ ለውጥ እንቅፋቶችን በመለየት አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን በማግኘታቸው ደስታቸውን በመግለፅ ስጦታ አበረከቱላቸው፡፡

ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ሽልማቱን የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር እና የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ አባላቱን በመወከል አበርክተዋል፡፡በዚህ ወቅት አቶ ለማ ባደረጉት ንግግር ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተበረከተው ሽልማት ለኢትዮጵያ ህዝብ ትግል እውቅና የሰጠ ነው ብለዋል፡፡

Via Fana
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የሴቶች እኩልነት እና ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት በመስራት ላይ መሆኗ በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ትዝታ ሙሉጌታ ተናገሩ።

አምባሳደሯ በህንድ ኒው ደልሂ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የዩቨርሲቲ ምሁራንና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት በተሳተፉበት እና በተመድ የዘላቂ ልማት እና በኮርፖሬት ማህብራዊ ሀላፊነት ላይ ባተኮረ ጉባኤ ላይ ነው ይህ ያሉት።
በዚሁ ወቅት እንዳሉትም፥ በመንግስት አስተዳደር ውስጥ የሴቶች ተሳትፎን ከፍ በማድረግ እና በትምህርት ገበታ ላይ መገኘት የሚገባት ሴት ሁሉ እንድትገኝ በማስቻል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት እየሰራች ነው።

አምባሳደሯ በተለይም መንግስት ሴቶች በእኩልነት የተካተቱበት የፌደራል መንግስት ካቢኔ መገንባት መቻሉንም ለአብነት ጠቅሰዋል።
የአረንጓዴ ኢኮኖሚ በመገንባቱ ረገድም ሀገሪቱ ከውሃ፣ ንፋስ እና ፀሃይ ሀይል በማመንጨት ጥረት እያደረገች መሆኑን በማንሳት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን በምሳሌነት አንስተዋል።

በተጨማሪም በቅርቡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አነሳሽነት በአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ በአንድ ቀን ብቻ 350 ሚሊየን ችግኝ በመትከል በረሃማነትን ለመከላከል የተከናወነውን ተግባር አንስተዋል።

Via:- FBC
@YeneTube @Fikerassefa
ሀዋሳ ዩንቨርስቲ አንደኛ አመት አጠቃላይ ኦረንቴሽን ስለሚሰጥ በተመዘገባችሁበት አደራሽ እንድትገኙ ያሳስባል።

@YeneTube @Fikerassefa
በጅቡቲ ድንበር በኩል አልፈው የገቡት ታጣቂዎች ዜጎቹ ላይ ጥቃት ለመፈጸም #ቦምብን_ጨምሮ_ከባድ መሣሪያዎችን መጠቀማቸውም ታውቋል፡፡


ኢትዮጵያና ጅቡቲ ድንበር አቅራቢያ በአፋር ክልል አፈምቦ ወረዳ ልዩ ስሙ ኦብኖ በተባለ ሥፍራ የታጠቀ ቡድን ባደረሰው ጥቃት፣ 16 ንፁኃን ዜጎች መገደላቸውና ወደ 30 የሚጠጉት ዜጎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱ ታወቀ፡፡

ጥቃቱ የተፈጸመው ጥቅምት 1 ቀን 2012 ዓ.ም. ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ጀምሮ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በጥቃቱም ከሰው ሕይወት መጥፋት በተጨማሪ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ከብቶችና ግመሎች በታጠቀው ቡድን መዘረፋቸውን እንዲሁም በርካታ ፍየሎች መገደላቸውን የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በጅቡቲ ድንበር በኩል አልፈው የገቡት ታጣቂዎች ዜጎቹ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ቦምብን ጨምሮ ከባድ መሣሪያዎችን መጠቀማቸውም ታውቋል፡፡ በዚህም እንደ አርፒጅ ላውንቸር፣ ስናይፐር እንዲሁም ተቀጣጣይ ነገሮችን መጠቀማቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡፡

በጥቃቱም የአራት ወር ሕፃንን ጨምሮ 16 የሚሆኑ ንፁኃን ዜጎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ በተጨማሪም 28 የሚሆኑ ቁስለኞች ወደ ጂቡቲ ሆስፒታል የተላኩ ሲሆን፣ ወደ መቐለና አዲስ አበባ የተላኩ ቁስለኞች መኖራቸውን ታውቋል፡፡
ከጥቃቱ በኋላ በአፋር ክልል የተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ሰላማዊ ሠልፍ ተደርጓል፡፡

በተጨማሪም በቅርቡ ወደ አገር ውስጥ የገባውና በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የአፋር ሕዝቦች ፓርቲ ጥቃቱን አውግዟል፡፡ የፌዴራል መንግሥት ይኼንን አረመኔያዊ ድርጊት በንፁኃን አርብቶ አደሮች ላይ የፈጸመውን ኃይል በማጣራት ሕጋዊ ዕርምጃ እንዲወስድበት የጠየቀው ፓርቲው፣ በንፁኃን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት መንግሥት እንዲስያቆም አሳስቧል፡፡

Via :- Reporter
@YeneTube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ ሶስት ሰዎች ወንዝ ውስጥ ገብተው መሞታቸው ተገለጸ፡፡

የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ አቶ ስለሺ ተስፋዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በከተማዋ በትላንትናው እለት ሶስት ሰዎች በወንዝ ውስጥ ገብተው ህይወታቸው አልፏል፡፡የመጀመርያ የሞት አደጋ የደረሰው በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት ኮካ የመዝናኛ ስፍራ ላይ በሚገኝው ወንዝ ውስጥ ሲሆን እድሜው በግምት 35 አመት የሆነ ወጣት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡

ሁለተኛው የሞት አደጋ የደረሰው ደግሞ በአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት ጨሬ መድሀኒአለም አካባቢ እድሜው 30 ዓመት የሆነው ወጣት ወንዝ ውስጥ ገብቶ ህይወቱ አልፏል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የሞት አደጋዎች ምክንያት ሟቾች ወንዙን ለመሻገር፣ለመዋኘትና ለሌሎች አገልግሎቶች እንደሆነ በአካባቢዉ ነዋሪዎች ቢጠቀስም ፖሊስ ክስተቱን በመመርመር ላይ እንደሆነ ተገልጿል።

ሶስተኛው የሞት አደጋ የደረሰው ደግሞ በቦሌ ክፍለ ከተማ ሀሰን ኮንስትራክሽን አካባቢ አንድ ግለሰብ በፈሳሽ ማስወገጃ ውስጥ ገብቶ እንደሞተ ነው ኮሚሸኑ ያስታወቀው፡፡

በተያያዘ ዜና በትላንትናው እለት በከተማዋ አራት የእሳት አደጋዎች መከሰቱን ኮሚሽኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

አደጋዎች የደረሱት በጉለሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ ስድስት ፖሊስ ጣበያ አካባቢ በሚገኝው የኩኪስ ማምረቻ እና መሸጫ ቤት የተከሰተ የእሳት አደጋ ነው፡፡

ሁለተኛው አደጋ የደረሰው ደግሞ እዛው ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት ሲሆን ሶስተኛ አደጋ የደረሰው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሰፈረ ሰላም ጭማድ ተብሎ በሚጠራው ባለቤትነቱ የሸበሌ ትራንስፖርት የሆነ ጋራዥ ላይ የተከሰተ የእሳት አደጋ ነው፡፡

አራተኛው አደጋ የደረሰው በአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ጨፌ ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

በነዚህ አደጋዎች ሳብያም በግምት 2 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ ተገልጿል።

Via:- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa
በድሬዳዋ ከተማ አዲስ የተቃዋሚ ፓርቲ ተመሰረተ።ለሶማሌ ሕዝብ ነጻነትና ዴሞክራሲ እንደሚታገል ያስታወቀው አዲሱ ፓርቲ ቅንጅት ለዴሞክራሲና ለነጻነት ይሰኛል። የፓርቲው መስራች ጉባዔ እስከስኞ ድረስ ይቀጥላል ተብሏል። ፓርቲው ዋና መቀመጫውን በጅግጅጋ እንደሚያደርግና በድሬዳዋና አዲስ አበባም ቅርንጫፎች እንደሚኖሩት ገልጿል።

ምንጭ:VOA
@YeneTube @FikerAssefa
400 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት በእስር ላይ የነበሩ 400 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል።

በዛሬው እለት ወደ ሃገራቸው የተመለሱት ኢትዮጵያውያን ቀይ ባህርን አቋርጠው ሲጓዙ በሳዑዲ ዓረቢያ የፀጥታ ሀይል ተይዘው በእስር ላይ የቆዩ ናቸው ተብሏል።

ኢትዮጵያውያኑ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ዮሃንስ ሾዴ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የዛሬዎቹን ተመላሾች ጨምሮ በበጀት ዓመቱ ባለፉት 3 ወራት 32 ሺህ 890 ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ ሀገራት ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን በመከተል በተለያዩ ሃገራት የሚኖሩና መሰል ችግር ያጋጠማቸውን ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ፈቃድ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል።

Via:- FBC
@YeneTube @Fikerassefa
⬆️በሀዋሳ ከተማ በመናኸሪያ ክ/ከተማ በርካታ የሺሻ ቁሳቁሶች ተያዙ አስጠቃሚ ቤቶችም ታሸጉ፡፡

ይህ የሆነው ከህብረተሰቡና ከፖሊስ ጋር በተደረገ ቅንጅታዊ አሰራር መሆኑን የሀዋሳ ከተማ አሰተዳደር የህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መልካሙ ተፈራ አስታውቀዋል፡፡

ከህብረተሰቡ በተሰጠ ጥቆማና በፖሊስ ክትትል የተከናወነው ይህ ተግባር የህብረተሰቡን ሰላምና
ደህንነት ለማስጠበቅ ሲባል በሁሉም ክ/ከተማ ተመሳሳይ ኦፕሬሽኖችን የተጠናከረ መልኩ እየተከናወነ እንደሚገኝም ነው አቶ መልካሙ የገለፁት፡፡

ለህብረተሰቡ ሰላም እና ደህንነት እንዲሁም ለወጣቱ መልካም አርአያ ሊሆኑ የሚችሉ ተመሳሳይ የቅንጅት ስራዎች በሁሉም ክፍለ ከተሞች እየተደረጉ ያሉ ውይይቶች ስለመኖራቸውም የጽ/ቤት ሀላፊው አስረድተዋል።

አብዛኞቹ የሺሻ ማጬሻ ቤቶች በትምህርት ቤት አቅራቢያ እና በመኖሪያ መንደሮች ውስጥ መሆናቸው ጉዳቱን የከፋ እንዳደረገውም ነው አቶ መልካሙ ለዝግጅት ክፍላችን የገለፁት።

Via:- ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር
@YeneTube @Fikerassefa
⬆️አፋር ክልል የኢፌዲሪ መከላከያ ገብቷል #የማጣራት ስራ እንዲሁም #የማረጋጋት ስራ ይሰራል ተብሎ ይጠበቃል።

@YeneTube @Fikerassefa
በአፋር ክልል አፋምቦ ወረዳ ታጣቂዎች በንጹሃን ላይ የፈጸሙትን ጥቃት የሚያጣራ ቡድን ወደ ሥፍራው ልኬያለሁ- ብሏል ሰላም ሚንስቴር፡፡ የ17 ሰዎች ያህል ሕይወት የጠፋበት ጥቃት ግን ከተፈጸመ ዛሬ 5ኛ ቀኑን ይዟል፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማን ከሃላፊነት እንዳነሷቸው ነግረዋቸዋል፡፡

በምትካቸው አዳነች አቢቤን እንደሚተኩም ከ3 ቀናት በፊት ለታከለ ገልጸውላቸዋል አዳነች የኦሕዴድ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የፌደራሉ ገቢዎች ሚንስትር ናቸው፡፡

ታከለ ለምን ከሃላፊነት እንደተነሱ አልታወቀም፡፡

በሌላ ዜና፣ ኢሕዴግን #የማዋሃድ ሃሳብ የኦሕዴድ/ኦዴፓን ሥራ አስፈጻሚ #ለሁለት ከፍሎታል፡፡ ዛሬ የተሰበሰበው ማዕከላዊ ኮሚቴው በዚሁ ጉዳይ ላይ ጭምር ይመክራል፡፡

ምንጭ :- አዲስ እስታንዳርድ - ትርጉም ዋዜማ
@YeneTube @FikerAssefa
የህወሓት መግለጫና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ምላሽ!

የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት የፕሬስ ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ለህወሀት መግለጫ በሰጡት ምላሽ “በህወሓት የወጣው መግለጫ ለውጡ ከመጣላት ሳይሆን ከመጣበት ሕዝብን የማይወክል አካል የወጣ ነው። ለዚህም ምክንያቱም መግለጫውን ያወጣው ቡድን በለውጡ ምክንያት የተቋረጠበት ጥቅም መኖሩንና የነበረው ግፍ እንዲመለስ መመኘቱ ነው። ህወሓት የኢህአዴግን የውህደት እንቅስቃሴ አስመልክቶ በመግለጫው ያሰፈረውም ለዓመታት ሲያንፀባርቀው ከነበረው አቋም የተለየ ነው።"

Via VOA Amharic
@YeneTube @Fikerassefa
የአማራ ክልል ደኅንነትና የጸጥታ ካውንስል የጋራ መግለጫና ውሳኔዎች!

በማዕከላዊ እና በምዕራብ ጎንደር ዞኖች፣ በጎንደር ከተማ እንዲሁም በቅማንት ብሔረሰብ አስተዳድር ማንነትን ሽፋን በማድረግ ባለፉት አምስት ዓመታት የዘለቀው የጸጥታ መደፍረስ ለሰው ህይዎትና ለንብረት ጥፋት ምክንያት ሆኖ መቀጠሉ የሚታወስ ነው፡፡ የክልሉ መንግስት ህግና ሥርዓትን በተከተለ አኳኋን ለተነሱ የማንነት ጥያቄዎች የቅማንት ብሔረሰብን ጨምሮ ምላሽ መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡ ለተነሱ የማንነት ጥያቄዎችና መልሶች ቅሬታ ያቀረበ ኃይል፣ ቡድንና ማኅበረሰብ ህግና ሥርዓትን በተከተለ መንገድ ሀሳባቸውን፣ ጥያቄያቸውንና ቅሬታቸውን አቅረበው መስተናገድ እየተቻለና ለዚህም በርካታ ዕድሎች ብሎም ጊዜያት ተሰጥተው እያለ በሃይል ፍላጎትን ለማሳካት መሞከር ጸረ ህገ መንግስትና የለዬለት ጸረ ሰላም ተግባር መሆኑ በግልጽ ሊታወቅ ይገባል፡፡

ሙሉ መግለጫ👇👇👇👇

https://telegra.ph/Amhara-10-16

@YeneTube @FikerAssefa
📌መረጃ ከምንጩ

ዛሬ ከቀኑ 3:00 ላይ የውሀ ሚኒስትራችን ለሁሉም ሚኒስትሮች ስለ አባይ ግድብ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሏል። ማብራሪያ የሚሰጡበት ቦታ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር።

የመንግስት ሚዲያዎች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል። ተጨማሪ መረጃዎች ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዘ እንደደረሰን የምናደርሳችሁ ይሆናል።

@YeneTube @Fikerassefa