YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በጅቡቲ ድንበር በኩል አልፈው የገቡት ታጣቂዎች ዜጎቹ ላይ ጥቃት ለመፈጸም #ቦምብን_ጨምሮ_ከባድ መሣሪያዎችን መጠቀማቸውም ታውቋል፡፡


ኢትዮጵያና ጅቡቲ ድንበር አቅራቢያ በአፋር ክልል አፈምቦ ወረዳ ልዩ ስሙ ኦብኖ በተባለ ሥፍራ የታጠቀ ቡድን ባደረሰው ጥቃት፣ 16 ንፁኃን ዜጎች መገደላቸውና ወደ 30 የሚጠጉት ዜጎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱ ታወቀ፡፡

ጥቃቱ የተፈጸመው ጥቅምት 1 ቀን 2012 ዓ.ም. ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ጀምሮ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በጥቃቱም ከሰው ሕይወት መጥፋት በተጨማሪ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ከብቶችና ግመሎች በታጠቀው ቡድን መዘረፋቸውን እንዲሁም በርካታ ፍየሎች መገደላቸውን የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በጅቡቲ ድንበር በኩል አልፈው የገቡት ታጣቂዎች ዜጎቹ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ቦምብን ጨምሮ ከባድ መሣሪያዎችን መጠቀማቸውም ታውቋል፡፡ በዚህም እንደ አርፒጅ ላውንቸር፣ ስናይፐር እንዲሁም ተቀጣጣይ ነገሮችን መጠቀማቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡፡

በጥቃቱም የአራት ወር ሕፃንን ጨምሮ 16 የሚሆኑ ንፁኃን ዜጎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ በተጨማሪም 28 የሚሆኑ ቁስለኞች ወደ ጂቡቲ ሆስፒታል የተላኩ ሲሆን፣ ወደ መቐለና አዲስ አበባ የተላኩ ቁስለኞች መኖራቸውን ታውቋል፡፡
ከጥቃቱ በኋላ በአፋር ክልል የተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ሰላማዊ ሠልፍ ተደርጓል፡፡

በተጨማሪም በቅርቡ ወደ አገር ውስጥ የገባውና በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የአፋር ሕዝቦች ፓርቲ ጥቃቱን አውግዟል፡፡ የፌዴራል መንግሥት ይኼንን አረመኔያዊ ድርጊት በንፁኃን አርብቶ አደሮች ላይ የፈጸመውን ኃይል በማጣራት ሕጋዊ ዕርምጃ እንዲወስድበት የጠየቀው ፓርቲው፣ በንፁኃን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት መንግሥት እንዲስያቆም አሳስቧል፡፡

Via :- Reporter
@YeneTube @Fikerassefa