YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from YeneTube
💥💥School Of American English💥💥

ይምጡ እኛ ጋር የተለያዩ #ቋንቋዎችን ተምረው ይመለሳለሁ!!

#እንግሊዝኛ #ቻይንኛ
#ጀርመንኛ #ጣልያንኛ
#አረብኛ አንቱታን በአተረፉ መምህራኖቻችን እናስተምሮታለን።

በተጨማሪ ለሰራተኞች የጊዜ እጥረት ላለባቸው በግል እንዲሁም ቅዳሜ እና እሁድ እናስተምሮታለን።

📌ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 1ኛ ፎቅ
📌ጎላጎል ህንፃ ስድስተኛ 6ኛ ፎቅ
📌ፒያሳ የገበያ መዐከል

ከላይ የተጠቀሱት ህንፃዎች ላይ እንገኛለን 0921309530 ይደውሉ
በተጨማሪ መረጃ ⬆️ ፎቶውም ላይ ይመልከቱ።
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ 💥

BLUE Brand Solutions

Blue Brand Solutions brought you the latest
📌Technologies(smartphones,Laptops)

📌 Men's and women's clothing👔

📌 Human hair 🙆‍♀

📌Musical instruments

📌Mens and Women's Perfume

Contact; @sherlockseller @Nah22
Call us
+251947896322&+251945421100

ቻናላቸውን ተቀላቅለሁ ይመልከቱ⬇️
https://tttttt.me/blueelec
Macbook Pro😍 15.4" 256GB SSD Intel Core i7 9th Gen 2.60 GHz 16GB Touch Bar - Space
Call now🏃‍♂+251912894363
Or via ZenachBrands1
Join our channel 😍😍@ZenachBrands for more items
ማስታወቂያ💥

Buy and Order Quality clothes we will bring any orders from USA 🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸 in 8 to 15 days
for more info: @order_us1_inbox
0911073577 (abrsh)
👉tops 👚
👉Demin👖
👉Dress 👗
👉underwear 👙
👉T- shirt 👕
For more 👇🏾👇🏾👇🏾join the chanal
👉🏻 https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFeEeXHsZxR6KmWVxA

🏠location: medihanialem mall, 3rd floor , 306
በትግራይ ክልል 'እየተባባሰ የመጣው' በሴቶች ላይ የሚፈፀም ፆታዊ ጥቃት የሚያወግዝ ሰልፍ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ያሉ እንስቶች፣ በመንግስት ወገን ሰልፍ እንዳያደርጉ ክልከላ እንደገጠማቸው ገለፁ፡፡ ሴቶቹ ግን ሰልፉ እሁድ ይደረጋል እያሉ ነው፡፡

Via ሚሊዮን ሃ/ስላሴ
@YeneTube @FikerAssefa
ታከለ ኡማና ሌሎች ሹማምንት ከስልጣናቸው ለምን ይነሳሉ?

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና ሌሎች ሹማምንት ከስልጣናቸው ይነሳሉ። ዋዜማ ራዲዮ ባለስልጣናቱ የሚነሱበት ምክንያት ምንድ ነው? በሚል የነበሩትን ሂደቶች ተመልክቷል። አንብቡት👇👇👇👇

https://telegra.ph/Takele-10-17

@YeneTube @FikerAssefa
ሀዋሳ ዩንቨርሲቲ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ኦሬንቴሽን እየተሰጠ ይገኛል በጠዋቱ መረሀ ግብር ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪች ኦሬንቴሽን እየተሰጠ ሲሆን ከሰዐት ላይ (7:30) ላይ ለማህበረሰብ ሳይንስ ኦሬንቴሽን ይሰጣል።

🎯ተማሪዎች ኦሬንቴሽን የሚሰጥበት አደራሽ መገኘት እንዲሁም መከታተል ግዴታችሁ ነው።
@YeneTube @Fikerassefa
የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ይጀመራል።

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 5ኛ የስራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ይጀመራል።የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 8 ቀን 2012 ዓ.ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል።ምክር ቤቱ በዚህ መደበኛ ስብሳበው የክልሉ የ2012 በጀት ዓመት አጠቃላይ ዕቅድ ላይ ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።በተጨማሪም በክልሉ ስራ አስፈፃሚ፣ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የዋና ኦዲተር የ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት ረቂቅ እድቅ ዙሪያ ተወያይቶ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።ከዚህ ባለፈም ምክር ቤቱ የፍርድ ቤቶች አደረጃጀት፣ የዳኝነት የአገልግሎት ክፍያ፣ የዳኞች ጉባኤ ሥልጣን እና ተግባር ለመወሰን ተሻሽለው የወጡ ረቂቅ አዋጆችን ጨምሮ 5 የተለያዩ አዋጆችን መርምሮ ከተወያየ በኋላ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
በአፋር ክልል ዋና ከተማ ሰመራ ሰላማዊ ሰልፍ እየተደረገ ይገኛል።

በቅርቡ የተከሰተው ግድያ በማውገዝ ሰላማዊ ሰልፍ በአፋር ክልል ለከተሞች እየተደረገ ይገኛል።
@YeneTube @Fikerassefa
በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት የተገነባው ትምህርት ቤት ተመረቀ፡፡በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት አማካኝነት የተገነባው የሎዛ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታው ተገባድቦ ዛሬ ተመርቋል፤ የመማር ማስተማር ሥራውንም ጀምሯል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
የሶፍኡመር ዋሻ በ‘UNESCO’ የአለም ቅርስነት ለማስመዝገብ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡

የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ከበደ ዴሲሳ ለኦቢኤን እንደገልፁት በ ‘UNESCO’ በጊዚያዊ የአለም ቅርሰነት ተመዝግቦ የቆየውን የሶፍኡመር ዋሻ ሙሉ ለሙሉ ለማስመዝገብ የሚያስፈልጉ መረጃዎች ሁሉ ተሟልቷል፡፡ከድርጅቱ በተላኩ ባለሙያዎች ዋሻው ተጎብኝቶ ፤ አስፈላጊው ጥናት መደረጉን ምክትል ሀላፊው ተናግረዋል፡፡

Via OBN
@YeneTube @FikerAssefa
ማረሚያ ቤቶች የማምረቻ ኢንዱስትሪዎችን እንዲያቋቁሙ የሚፈቅድ ሕግ ተረቀቀ!

ባሳለፍነው ሳምንት መስከረም 29/2012 ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የፌደራል ማሪሚያ ቤት ረቂቅ አዋጅ የማረሚያ ቤት አስተዳደርን ወደ ኮሚሽን እንዲያድግ እና ተጨማሪ ዘጠኝ ሥልጣኖች እንዲኖሩት ያቀረበ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል ታራሚዎችን በሥራ ላይ ለማሰማራት የሚያስችሉ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎችን እንዲያቋቁም ሥልጣን የሚሰጥ ነው።በተጨማሪም የማሰልጠኛ ተቋማት እንዲኖሩት፣ ለፖሊሶች የጋራ መኖሪያ ካምፖችን እንዲገነባ እና የውስጥ ገቢዎቹን ለመንግሥት ገቢ ማድረጉ ቀርቶ ከበጀት ውጪ ላሉ ሥራዎች እንዲያውል የሚሉት የተወሰኑት ናቸው።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
በጭልጋ ቁጥር 1 ወረዳ በተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ተፈጸመ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት እንደሆነ ተገለጸ፡፡

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ ቁጥር 1 ወረዳ ‹ቡሆና› በተባለው አካባቢ በተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ተፈጽሟል የሚል መረጃ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተሠራጨ ነው፡፡ አብመድ ጉዳዩን ለማጣራት ባደረገው ጥረት ግን ‹‹ከመተማ ወደ ጎንደር ሲጓዝ የነበረ ሚኒባስ ቡሆና አካባቢ በከባድ መሳሪያ ተመትቷል›› በሚል የተሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን ከአካባቢው ባገኘው መረጃ አረጋግጧል፡፡የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደርና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳኘው በለጠ ባለሙያዎችን ቦታው ድረስ በመላክ አረጋግጠናል በማለት ለአብመድ እንደገለጹት በአካባቢው መስከረም 18 ቀን 2012 ዓ.ም ከተከሰተው ጥቃት ውጭ የተፈጸመ ሕገ ወጥ ድርጊት (ጥቃት) የለም፡፡

‹‹በአካባቢው አሁን አንጻራዊ ሠላም አለ፤ ጥምር የፀጥታ ኃይሉም ተቀናጅቶ እየተንቀሳቀሰ ነው፤ የትናንቱ መግለጫ ደግሞ በኅብረተሰቡ ዘንድ መረጋጋት እንዲፈጠር አድርጓል›› ብለዋል አቶ ዳኘው፡፡ ትናንት ምሽት በተሰጠው መግለጫ ልክ የፀጥታ ኃይሉ አካባቢውን አስተማማኝ ሠላም የሠፈነበት ለማድረግ እንዲሰራ ነዋሪዎች እያሳሰቡ መሆኑንም ነው አቶ ዳኘው ያመለከቱት፡፡ኅብረተሰቡ ዛሬ የተፈጸመ ጥቃት አለመኖሩን አውቆ የተረጋጋ መደበኛ ሕይወቱን እንዲመራ ያሳሰቡት መምሪያ ኃላፊው በማኅበራዊ ሚዲያ ኃላፊነት በጎደለው መንገድ የቆዬ መረጃ እየለቀቁ ሕዝቡን ማደናገር እንደማይገባም አስገንዝበዋል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
በመዲናዋ ከሚገኙ ወረዳዎች ግማሽ ያህሉ የዲጂታል መታወቂያ እየሰጡ ነው።

በአዲስ አበባ ከሚገኙ ወረዳዎች ግማሽ ያህሉ የዲጂታል መታወቂያ እየሰጡ መሆናቸውን የከተማው ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ በኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በተለይ ለኢቲቪ እንደተናገሩት በከተማዋ ካሉ 121 ወረዳዎች 62ቱ የዲጂታል መታወቂያ እየሰጡ ናቸው፡፡አገልግሎቱ የሚሰጠው በቴሌኮም ኔትወርክ እገዛ እንደመሆኑ የዚህ መሰረተ ልማት ጥራትና ተደራሽነት ጉድለት የዲጂታል መታወቂያው በሁሉም የከተማዋ አስተዳደር እንዳይሰጥ እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል አቶ ዮናስ፡፡ከዚህ ባሻገር የሰው ሀይል እጥረት፣ ስራውን ማስፈጸሚያ በቂ ቢሮ ያለመኖር እና ለሰራተኞች የሚከፈል ደመወዝ አናሳ መሆኑ አገልግሎቱን በመዲናዋ ሙሉ ለሙሉ ለመተግበር ችግር መፍጠሩን ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ: ኢቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
አየር መንገዱ በጀመረው የኤሌከትሮኒክስ ቪዛ 200 ሺህ መንገደኞች ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤሌክትሮኒክስ ቪዛ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ተከትሎ 200 ሺህ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል።የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2017 ሰኔ ወር ላይ ጀምሮ ለደንበኞቹ የኤሌክትሮኒክስ ቪዛ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ይታወቃል።ይህን ተከትሎም የተለያዩ ሀገራት ቱሪስቶች ከየትኛውም የአለም ክፍል ሆነው በአገልግሎቱ በመጠቀም በቀላሉ ወደ ሀገሪቱ መግባት ችለዋል።

በዚህ መሰረትም አግልግሎቱ ስራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ ከ217 ሀገሮች በአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሆኑ 200 ሺህ ቱሪስቶች ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል። አገልግሎቱ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ ጥቅም ከማስገኘቱ ባለፈ ቱሪዝምን በማስተዋወቅ እና በንግድና ኢንቨስትመንት ሀገሪቱን ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም ተናግረዋል።ከዚህ ባለፈም በፍጥነት እያደገ ያለው የአየር መንገዱ ዓለም አቀፋዊ ተደራሽነት በሀገሪቱ ካለው የሆቴል አገልግሎት ጋር ተቀናጅቶ ኢትዮጵያን ተመራጭ የኮንፈረንስ እና ቱሪዝም መናኸሪያ እንደሚያደርጋት ታምኖበታል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
ከአንድ ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ከመኪና ውስጥ ሰርቀው ለመማምለጥ ሙከራ ያደረጉ ሶስት ተጠርጣሪዎች በሕ/ሰቡ እና በፖሊስ ጥምረት ተያዙ ::


ጥቅምት 4 ቀን 2012 ዓ/ም የግል ተበዳይ ሚስተር ፒን ላፊ ላንግ የተባሉ የሚንግ ሲያ ስትሮንግ ማሽነሪ ማኑፋክቸሪንግ ኃ.የተ የግ›ማህበር ባለቤት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ከሚገኘው አዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ 1.2 ሚሊየን ብር አውጥተው በኮድ 2 ቢ 23934 አ.አ ቪትዝ መኪናቸው ገንዘቡን ጭነው ሲሄዱ ተጠርጣሪዎቹ ደግሞ በኮድ 2 ቢ 01156 አ.አ ቪትዝ መኪና የግል ተበዳይ መኪናቸውን አቁመው ምሳ ለመብላት ወደ ሆቴል በገቡለት አጋጣሚ ተጠርጣሪዎቹ የመኪናውን መስታወት በመስበር መኪናው ውስጥ የነበረውን ሙሉ ሻንጣ ብር ይዘው በተሸከርካሪያቸው ለማምለጥ ሙከራ ሲያደርጉ የግል ተበዳይ ባሰሙት ይድረሱልኝ ጥሪ ተጠርጣሪዎቹ ከነ እግዝቢቱ በህ/ሰቡና በፖሊስ ክትትል በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ረዋንዳ ጉሊት ቻይና ገበያ አካባቢ በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን የጉዳዩ መርማሪ ዋ/ሳጅን ተረፈ ይጥና ገልፀዋል ፡፡

የግል ተበዳዩ ንብረታቸው በቁጥጥር ስር በመዋሉ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀው ሕብረተሰቡና ፖሊስ ላደረገላቸው ከፍተኛ ትብብር ምስጋናቸው የላቀ መሆኑን ከዝግጅት ክፍላችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል ፡፡በመጨረሻም መሰል ወንጀሎች በአ/አበባ ከተማ መበራከታቸውን የተናገሩት የጉዳዩ መርማሪ ዋ/ሳጅን ተረፈ ይጥና ሕብረተሰቡ ከፍተኛ መጠን ያሏቸውን ገንዘቦች በጥሬ ከመያዝ ይልቅ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶችን በመጠቀም ከወንጀል ድርጊቶች አራሳቸውን መከላከል እንዳለባቸው መርማሪው በመልክታቸው ገልፀዋል ፡፡

Via Addis Ababa Police Commission
@YeneTube @FikerAssefa
b47c-2c4b-4ea2-8747-8611a0441536.m4a
1.7 MB
መደበኛ ባልሆነ መንገድ፣ በተለያዩ አካባቢዎች በራሳቸው የፖሊስን ስራ በመከወን የሚንቀሳቀሱ ወጣቶችን ከዚህ በኋላ እንደማይታገስ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ተናገረ፡፡የፖለቲካ አመራሩም ለግጭት ምክንያት የሚሆኑ ንግግሮችን አቁሞ ህዝቡን ካረጋጋ ፖሊስ የዜጋውን ደህንነት ለመጠበቅ አይቸገረም ብሏል፡፡

Via sheger
@YeneTube @FikerAssefa