YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሸጎሌ የአውቶብስ ዲፖ ተመርቆ ተከፈተ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ555 ሚሊዮን ብር ያስገነባው የሸጎሌ የአውቶብስ ዲፖ ተመርቆ ተከፍቷል። የተመረቀው ዲፖ በዘመናዊ መንገድ የተገነባ ሲሆን ምቹ የአውቶብስ ማቆያ፣ ዘመናዊ የጥገና ማዕከል፣የአውቶብሶችን ውጪ አካል የቀለም መቀባት አገልግሎትን የሚሰጥ እንደዚሁም የአውቶብስ እጥበት እና የነዳጅ ማደያ አገልግሎቶች የሚሰጡበት ቦታዎች አሉት ተብሏል።ዲፖው 212 አውቶብሶችን ማቆም የሚችል እና ከ250 እስከ 300 ለሚሆኑ አውቶብሶች በተመቻቸ ሁኔታ የእጥበት እና የጥገና አገግሎቶችን የሚሰጥ መሆኑ ተነግሯል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ የሚታየውን የትራንስፖርት እጥረትን ለመቅረፍ ዘመናዊ የአውቶብሶች አገልግሎትን ለኅብረተሰቡ ለመስጠት የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑንም አስታውቋል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን ስያሜውን የመቀየር ፍላጎት እንደሌለው አስታወቀ።

የእግር ኳስ ቡድኑ ምክትል ፕሬዝዳንትና የጎንደር ከተማ አስተዳደር የባሕል ቱሪዝም፣ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አስቻለው ወርቁ በጉዳዩ ላይ ለአብመድ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ከመጀመሩ ቀደም ብሎ በርካታ ውዝግቦች እየተስተዋሉበት ነው። ፋሲል ከነማን ጨምሮ ሌሎች ቡድኖች የስያሜ ለውጥ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማሳሰቡ አንደኛው የውዝግብ ምንጭ ሆኗል።የቡድኑ ምክትል ፕሬዝዳንት እንደተናገሩት ፋሲል ከነማ ስም የመቀየር ፍላጎት የለውም። የእግር ኳስ ቡድኑ የብሔር፣ የከተማ ወይም የአካባቢ ሳይሆን ሀገራዊ ስያሜ እንደተሰጠው በመግለጽ ‹ፋሲል ከነማ› እና ‹ዓፄዎቹ› የሚለው ስያሜ በሌሎች ላይ ምንም ዓይነት ችግር እንደማይፈጥርም አቶ አስቻለው አስታውቀዋል። የተወሳሰቡ ችግሮች በነበሩበት ባለፈው የውድድር ዘመን ቡድኑ ያሳዬውን ስፖርታዊ ጨዋነት ያስታወሱት ምክትል ፕሬዝዳንቱ ‹‹ስያሜ የሚያስቀይር አሳማኝ ምክንያት የለም›› ብለዋል፡፡ከ50 ዓመታት በላይ በዚህ ስያሜ ሲጠራ የኖረን ቡድን ዘንድሮ ለምን ስም ማስቀየር እንዳስፈለገ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ግልጽ ሊያደርግ እንደሚገባም ጠይቀዋል።

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
የኢፌዴሪ አየር ኃይል 166 አብራሪና ቴክኒሻን ሰልጣኞችን አስመረቀ!

የኢፌዴሪ አየር ኃይል አካዳሚ በበረራና በቴክኒሺያንነት ያሰለጠናቸውን 166 ሰልጣኞችን አስመረቀ፡፡ከተመራቂዎቹ መካከል 17ቱ አብራሪዎች ሲሆኑ 149 የሚሆኑት ደግሞ የበረራ ቴክኒሺያን ናቸው፡፡የአየር ኃይሉ ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ይልማ መርዳሳ አየር ኃይሉ በምርምርና በቴክኖሎጂ ሽግግር የሚያደርጋቸውን የአቅም ግንባታ ስራዎች ማሰደጉን እንደሚቀጥል በምረቃው ላይ ተናግረዋል፡፡አየር ኃይሉ በዛሬው ዕለት ያስመረቃቸው ሰልጣኞችም የአየር ኃይሉን የግዳጅ አቅሙ ያሳድገዋል ብለዋል፡፡አየር ኃይሉ ራሱን ለማዘመንና በተሻለ ቁመና ላይ እንዲገኝ ለጥናትና የምርምር ስራዎች ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
ህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን እስከ ሞት የሚያስቀጣ የህግ ማዕቀፍ እየተጠናቀቀ ነው!

ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን፣ የድንበር ማሻገርና በሰው መነገድ ወንጀሎችን መቆጣጠር ያስችላል የተባለውና እስከሞት የሚያስቀጣ አንቀጾችን ያካተተ ጠንከር ያለ የህግ ማዕቀፍ እየተጠናቀቀ መሆኑን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ፡፡በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱሉ በተለይ ለኢቢሲ እንደተናገሩት በርካታ አምራች ወጣቶች በደላሎችና በህገ ወጥ ድንበር አሻጋሪዎች ለእንግልት፣ ለስቃይ እንዲሁም ለሞት እየተዳረጉ በመሆኑ ወንጀሉን ለመቆጣጠር የሚያስችል ጠንካር ያለ የህግ ማዕቀፍ አስፈልጓል፡፡በወንጀል ድርጊቱ በርካታ ወጣቶች የአካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊና አልፎም የህይወት መጥፋት እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡

በሀገራቸው መስራትና ማምረት የሚችሉ በርካታ ወጣቶች በደላሎችና ህገ ወጥ ድንበር አሻጋሪዎች ተጠቂ በመሆናቸው ለጉዳዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑም አክለዋል፡፡ረቂቅ አዋጁ ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ተገቢ ቅጣት እንዲያገኙ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል፡፡ረቂቅ አዋጁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ለህግና ፍትህ ዴሞክራሲያዊ ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም ለሴቶች፣ወጣቶችናማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ ቀርቧል ተብሏል፡፡ጉዳዩ አስከፊና አሳሳቢ መሆኑን ተከትሎ ከሚቀርቡትና ቶሎ ከሚጸድቁት የህግ ማዕቀፎች ውስጥ ቅድሚያ እንዲያገኝ ተደርጓል ብለዋል፡፡

ወንጀሉ በሃገር ውስጥና በውጭ ሃይሎች በቅንጅት የሚሰራ በመሆኑ ችግሩን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ድንበር አካባቢ ካሉ ጎረቤት አገራት ጋር በቅንጅትና በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ እንደተደረሰ አቶ ዝናቡ ገልጸዋል፡፡ችግሩንም በዘላቂነትለመፍታት የህግ ማዕቀፎች ማዘጋጀቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ህብረተሰቡ ላይ ለውጥ ማምጣጥት የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ላይ እና የስራ አድል ፈጠራ ላይ በስፋት መስራት እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡ወጣቱ በሃገሩ ሰርቶ የሚለወጥበት፣ሃብት ንብረት የሚያፈራበት ምቹ ሁኔታ መፍጠር ላይ ትኩረት መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡በዚህ ወንጀል ድርጊት የሚሳተፉ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ከጸጥታ ሃይሉ ጎን ለጎን የህብረትሰቡ ትብብር፣ የወንጀሉ ተጎጅ አካላት ተባባሪ መሆን ወሳኝ ነውም ነው የተባለው፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
በአፋር ክልል ከሰሞኑ የተፈጸመው ጥቃት የታቀደና በውጭ ኃይሎች የተደገፈ እንደነበር የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ ሙሐመድ ለአብመድ እንዳስታወቁት ጥቃት አድራሾቹ የተደራጁና የሶማሌ ላንድ የሠሌዳ ቁጥር ያለው ተሽከርካሪ የሚጠቀሙ ነበሩ፡፡ቅዳሜ ከሌሊቱ 9፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ አፋንቦ ወረዳ ሰንጋ የሚባል መንደር በተፈጸመው ጥቃት የ17 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ በርካቶች መቁሰላቸውንና እንስሳትም መዘረፋቸውን ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡
ጥቃት የተፈጸመበት መንደር ከጂቡቲ ድንበር 35 ኪሎ ሜትር አካባቢ ርቀት የሚገኝ መሆኑን ያመለከቱት አቶ አህመድ በጥቃቱ ሕጻናትና ሴቶች ክፉኛ ሰለባ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡

በአንዳንድ የመገናኛ ብዙኃን ጥቃቱ የተፈጠረው በግጦሽና ውኃ ምክንያት በአፋርና ኢሳ ጎሳዎች መካከል የተፈጠረ እያስመሰሉት መሆኑን ያመለከቱት አቶ አህመድ ‹‹ጥቃቱ ፈጽሞ የአፋርና የኢሳ ጎሳዎች አይደለም›› ብለዋል፡፡
በጥቃቱ የተሳተፉት ኃይሎች ‹‹የሶማሌ ላንድ ሰሌዳ ያለው ተሽከርካሪ ተጠቅመዋል፤ የአልሸባብ ወታደሮች የሚለብሱትን የፊት መሸፈኛና ጥቁር አርማም ተጠቅመዋል›› ብለዋል፡፡ ‹‹የአፋር ሕዝብ በሕይወት የመኖር መብቱ ሊረጋገጥለት ይገባል›› ያሉት ኃላፊው ጥቃቱ የመጀመሪያ አለመሆኑንም አመልክተዋል፡፡ ከአራት ወራት በፊት መሰል ጥቃት ተፈጽሞ እስከ አምስት ሰዎች ሕይወት በዚሁ አካባቢ ማለፉንም ነው ያስታወሱት፡፡ ከመጀመሪያው ጥቃት ጋር በተያያዘ ስድስት ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው እየተጣራ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡
አካባቢው ከዚህ ቀደም የኮንትሮባንድ ንግድ መተላለፊያ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡

አካባቢው ኔትወርክ የማይሠራበትና የመሠረተ ልማት እጥረት ያለበት መሆኑ ጥቃቱን በፍጥነት ለመከላከልም ሆነ ቁስለኞችን ለማጓጓዝ አስቸጋሪ እንደነበርም አመልክተዋል፡፡የአካባቢውን ሠላም ለማረጋገጥ የፌዴራሉ መንግሥት ልዩ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባው ያሳሰቡት አቶ አህመድ ‹‹የሀገር መከላከያ ሠራዊት ወደ አካባቢው አልተሠማራም›› ብለዋል፡፡የተፈጸመውን ጥቃት ለማውገዝ በአፋር ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ዛሬ ሰልፎች መካሄዳቸውንም አስታውቀዋል፡፡ አቶ አህመድ እንደተናገሩት አዋሽ አርባ፣ አፋምቦ እና ገዋኔ ላይ ሠልፎች ተካሂደዋል፡፡ የአፋር ሕዝብ ደኅንነት እንዲረጋገጥም ሰልፈኞቹ መጠየቃቸውን አመልክተዋል፡፡

ምንጭ: አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa
አፋር ⬆️

"በውጪ ወረራ ሀይል ለሚሞተው ንፁሀን የአፋር ህዝቦች ፍትህ እንሻለን"

በአፋር ክልል በተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል።

@YeneTube @Fikerassefa
የምዝገባ ቀን በ2012 ዓ/ም በመቐለ ዩኒቨርስቲያችን ለተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች በሙሉ!

ወደ ዩኒቨርስቲያችን የተመደቡ አዲስ ተማሪዎች ቅበላ ከጥቅምት 14-16 2012ዓ/ም መሆኑን እየገለፅን፣ ከሁሉም የሃገራችን ክፍሎች ለሚመጡ ውድ ተማሪዎቻችን በፍቅር ለመቀበል ዝግጅታችን ጨርሰናል።ወደ መቐለ በምትመጡበት ግዜ ከመናሃሪያዋች እና ከአሉላ አባነጋ ኤርፓርት አውቶብሶቻችን ተማሪዎችን ወደ ግቢዎች ያደርሳሉ!
ወደ መቐለ ከመምጣታችሁ በፊት ሁሉም ተማሪ ከዛሬ ጀምሮ

📌 ወደ ድረገፃችን www.mu.edu.et በመግባት eStudent የሚል ማስፈንጠርያ ክሊክ ማድረግ፣
📌 በeStudent ድረገፅ Apply Here በሚል ቅፅ የ12ኛ መልቀቅያ ፈተና የምዝገባ ቁጥር (Registration number) በማስገባት፣ ሲስተሙ በሚሰጣችሁ መመርያ መሰረት እንድትመዘገቡ እንሳሳስባለን፡፡

ማሳሰብያ፡
በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስተር መመርያ መሰረት መሟላት ያለባቸውን ፎርሞች አሟልታችሁ እንድትመጡ እነዲሁም አምና በአንደኛ እና ሁለተኛ ሰሚስተር በሪአድሚሽን ተቀባይነት ያገኛችሁ ተማሪዎች ከአዲስ ተማሪዎች ጋር ወደ ግቢ እንድትገቡ እናሳስባለን፡፡

ምንጭ: መቐለ ዩኒቨርሲቲ
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ ተጀምሮ የነበረው የወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድ ከኹለት ሳምንት በፊት እንዲቆም ተደረገ። ፈንዱ የቆመበት ምክንያትም እስካሁን በተዘዋዋሪ ፈንዱ የተሰጠውን ገንዘብ ለመለየት እንደሆነ ከተማ አስተዳደሩ ቢገልፅም ወጣቶች ግን ቅሬታቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።

ከፈንዱ ተጠቃሚ ለመሆን ከሚጠብቁ ወጣቶች መካከል በ2011 በሲቪል ኢንጂነሪንግ የተመረቀው ዳዊት ተስፋዬ እንደሚለው “መንግሥት ተደራጅተን እንድንሠራ የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም ባለፈ ገንዘብ ድጋፍ እንደሚደርግልን ተነግሮን የሚጠበቁብንን ነገሮች በሙሉ አቅማችን አሟልተን፤ ከአንድ ወር በላይ እንደጠበቅን እና በተለይም በውድ ዋጋ የመሥሪያ ቦታ ተከራይተን ከፍተኛ ወጪ ላይ ብንሆንም ፈንዱ ግን ሊለቀቅልን አልቻለም” ሲል ለአዲስ ማለዳ ተናግሯል።
@YeneTube @Fikerassefa
የታላቁ ቤተ-መንግስት የመኪና ማቆሚያ ግንባታ በይፋ ተጀመረ::

ኢ/ር ታከለ ኡማ የመኪና ማቆሚያ ግንባታውን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

በ 10ሺ ካ.ሜ ላይ የሚያርፍ እና 1 ሺ መኪኖችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችለው ይህ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ቦታ አራት ቤዝመንቶች ይኖሩታል፡፡

ግንባታው በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል፡፡

የመኪና ማቆሚያው በቅርቡ ክፍት ለተደረገው ታላቁ ቤተ-መንግስትን ለመጎብኘት ለሚመጡ ጎብኚዎች የመኪና ማቆሚያነት የሚውል ነው፡፡

Via:- mayor office
@YeneTube @Fikerassefa
አዲስ አበባ በእስር ላይ ያሉ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) አመራሮችና አባላት በርሀብ አድማ ላይ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

አንዳንዱቹ ባጋጠማቸው የከፋ የጤና ችግር ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለኤትዩ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡ከሰኔ 15ቱ ግድያ ጋር በተያያዘ በመፈንቅለ መንግስት እና በጸረ ሽብር ክስ ተጠርጥረው የተያዙት 23 አባላቱ ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ በርሀብ አድማ ላይ መሆናቸውን ዶ/ር ደሳለኝ ተናግረዋል፡፡በርሀብ አድማው ከተካፈሉት አብዛኞዎቹ የጤና ችግር ገጥሟዋል፡፡

የእስሩ ሁኔታ ከፍተኛ ዛቻ እና ማስፈራሪያ አለበት የሚሉት ታሳሪዎቹ ከፓሊስ አባላት እንግልት ይደርሰብናል በማለት አድማ ማደረጋቸውን ዶ/ር ደሳለኝ ገልጸዋል፡፡በአባሎቻችን ላይ ስለሚደርሰው በደልና ግፍ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አንስቶ እስከ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪዎች ድረስ ድምጻችንን ብናሰማም ጠብ የሚል ለውጥ እንዳላገኙም ዶክተር ደሳለኝ ተናግረዋል።ዶ/ር ደሳለኝ መንግስት ለጉዳዩ በቂ ትኩረት እንዲሰጥም አሳስበዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ 💥

BLUE Brand Solutions

Blue Brand Solutions brought you the latest
📌Technologies(smartphones,Laptops)

📌 Men's and women's clothing👔

📌 Human hair 🙆‍♀

📌Musical instruments

📌Mens and Women's Perfume

Contact; @sherlockseller @Nah22
Call us
+251947896322&+251945421100

ቻናላቸውን ተቀላቅለሁ ይመልከቱ⬇️
https://tttttt.me/blueelec
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ💥

Buy and Order Quality clothes we will bring any orders from USA 🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸 in 8 to 15 days
for more info: @order_us1_inbox
0911073577 (abrsh)
👉tops 👚
👉Demin👖
👉Dress 👗
👉underwear 👙
👉T- shirt 👕
For more 👇🏾👇🏾👇🏾join the chanal
👉🏻 https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFeEeXHsZxR6KmWVxA

🏠location: medihanialem mall, 3rd floor , 306
Forwarded from YeneTube
የማስታወቂያ ሰዓት!!!
ጤና ይስጥልኝ! ክብራት እና ክቡራን የYeneTube ቤተሠቦች፡፡ ጥራታቸውን የጠበቁ የተለያዩ የሴት እና የወንድ አልባሳትን ከቱርክ በማስመጣት ለእርሶ እናቀርባለን፡፡ በአሁን ሰዓት ትዕዛዝ እየተቀበልን ስለሆነ ከታች ባለው ሊንክ ቻናላችንን በመቀላቀል እርሶ ያሻዎትን ይዘዙን በ 1 ሳምንት ውስጥ እናደርስሎታለን፡፡
እናመሠግናለን፡፡

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEa9jhKpu8JbbDsYLQ

☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

ትዕዛዝ ለመስጠት በዚህ ያዋሩን @Hode40

ወይም ይደውሉ +251940407900
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ💥

Red frames😍 are ready for computer 😎⭕️💻 and sun light we also work 🙁 prescribed lenses call now @+251912894364 or inbox🏃‍♂ via @ZenachBrands1
የረሀብ አድማው ተራዘመ!!

70 የፖለቲካ ድርጅቶች ጥቅምት 5 እና 6 ሊያደርጉት የነበረውን የረሃብ አድማ ተራዘመ፡፡ድርጅቶቹ እንዳሉት ከሆነ አድማውን ያራዘሙት በአገሪቱ በተፈጠረው አለመረጋጋት ምክንያት ሁሉም ፖለቲከኞች ወደ አዲስ አበባ መምጣት ባለመቻላቸው ነው፡፡በመሆኑም የረሃብ አድማው ተሳታፊዎች ጥቅምት 25 እና 26/2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ አራት ኪሎ አደባባይ ተሰብስበው አድማውን እንደሚያደርጉ ሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

በሰላማዊ የረሀብ አድማ ተቃውሞ ላይ ለሚያጋጥሙ የጤና ችግሮች የመንግሥትም ሆነ የግል የጤና ተቋማት ባለሙያዎችን በመመደብ ህዝባዊ ኃላፊነትን እንዲወጡ ሲሉ ከወዲሁ የጠየቁት ፖለቲከኞቹ የ2 ቀን አድማው በአደባባዩ ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽት 12 ሰዓት የሚካሄድ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ፖለቲከኞቹ የረሃብ አድማ ለማድረግ የወሰኑት ነሐሴ 18 ቀን 2011 የጸደቀው የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና ምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ሲረቅ ያቀረብናቸው ሃሳቦች አልተካተቱም በሚል እንደነበር ይታወሳል፡፡

Via አሐዱ ቴሌቪዥን
@YeneTube @FikerAssefa