YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ማስታወቂያ 💥

BLUE Brand Solutions

Blue Brand Solutions brought you the latest
📌Technologies(smartphones,Laptops)

📌 Men's and women's clothing👔

📌 Human hair 🙆‍♀

📌Musical instruments

📌Mens and Women's Perfume

Contact; @sherlockseller @Nah22
Call us
+251947896322&+251945421100

ቻናላቸውን ተቀላቅለሁ ይመልከቱ⬇️
https://tttttt.me/blueelec
ማስታወቂያ💥

Buy and Order Quality clothes we will bring any orders from USA 🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸 in 8 to 15 days
for more info: @order_us1_inbox
0911073577 (abrsh)
👉tops 👚
👉Demin👖
👉Dress 👗
👉underwear 👙
👉T- shirt 👕
For more 👇🏾👇🏾👇🏾join the chanal
👉🏻 https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFeEeXHsZxR6KmWVxA

🏠location: medihanialem mall, 3rd floor , 306
የማስታወቂያ ሰዓት!!!
ጤና ይስጥልኝ! ክብራት እና ክቡራን የYeneTube ቤተሠቦች፡፡ ጥራታቸውን የጠበቁ የተለያዩ የሴት እና የወንድ አልባሳትን ከቱርክ በማስመጣት ለእርሶ እናቀርባለን፡፡ በአሁን ሰዓት ትዕዛዝ እየተቀበልን ስለሆነ ከታች ባለው ሊንክ ቻናላችንን በመቀላቀል እርሶ ያሻዎትን ይዘዙን በ 1 ሳምንት ውስጥ እናደርስሎታለን፡፡
እናመሠግናለን፡፡

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEa9jhKpu8JbbDsYLQ

☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

ትዕዛዝ ለመስጠት በዚህ ያዋሩን @Hode40

ወይም ይደውሉ +251940407900
ማስታወቂያ💥

Red frames😍 are ready for computer 😎⭕️💻 and sun light we also work 🙁 prescribed lenses call now @+251912894364 or inbox🏃‍♂ via @ZenachBrands1
የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ አዲስ ለሚገነባው የፓርላማ ህንፃ 370 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገባች!

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ መንግሥት ኢትዮጵያ ለምታስገነባው አዲስ የፓርላማ ህንፃ 370 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል መግባቱን አስታውቋል።

በቅርቡ ለህዝብ ክፍት የሆነው የቤተመንግስት እድሳት እና ግንባታን ወጪም የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በ5 ቢልዮን ብር መሸፈኗ ይታወሳል።

Via ኢ.ፕ.ድ

@YeneTube @Fikerassefa
ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ግብጽ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር እያደረገች ያለችውን ጥረት ለመመከት የተሻለ ሀገራዊ አንድነት በመፍጠር እና ጠንካራ ኢኮኖሚን በመገንባት ላይ መሰራት እንደሚገባ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ገለፁ።
@YeneTube @FikerAssefa
#አትልፉ ብዙዎች ከሀዋሳ እንዲሁም ከሲዳማ ዞን ምርጫ ለማስፈፀም ምርጫ ቦርድ ያወጣሁን ማስታወቂያ አይተው ወደ አዲስ አበባ ለመመዝገብ ቢመጡም ምርጫ ቦርድ በአጠቃላይ የደቡብ ክልል ተወላጅ አላስተናግድም ብሏል። ስለዚህ የደቡብ ክልል ተወላጆች ህዳር 3 ለሚካሄደው ሪፈረንደም ምርጫ ማስፈፀም ስለ #ማትችሉ አትልፉ!!

@YeneTube @Fikerassefa
አርባምንጭ⬆️

የአርባምንጭ ከተማ ኗሪዎች ጠቅላይ ሚኒስተሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ ባገኙት የሰላም ኖቭል ፕራይስ ሽልማት በመደሰት በዛሬዋ ዕለት ሰልፍ ከማድረግ ይልቅ በጠቅላይ ሚኒስተሩ አነሳሽነት ቀደም ሲል #የተተከሉ ችግኞችን #በመንከባከብ እያሳለፉ ነው!!

@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ከአዲስ አበባ ጅቡቲ የቀን ምልልሱን ወደ ሶስት ጊዜ ከፍ ሊያደርግ ነው።

የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር አክስዮን ማህበር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው ከአዲስ አበባ ጅቡቲ ወደብ ድረስ በቀን ሁለት ጊዜ የእቃና የሰው ትራነስፖርት አገልግሎት እየሰጠ ነው።

ማህበሩ ገቢውን ለማሳደግ ከያዝነው ዓመት ጥር ወር አነስቶ የቀን ምልልሱን ወደ ሶሰት ጊዜ ለማሳደግ የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑን ዋና ስራ አስኪያጁ ኢንጂነር ጥላሁን ሳርካ ተናግረዋል።

የአገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ፣የሃይል መቆራረጥ እና የቴክኒክ ብልሽቶች የባቡር ፕሮጀክቱን እየፈተኑት ነውም ብለዋል።

የባቡር ፐሮጀክቱ በቀን 60 ሚሊዮን ብር በማግኘት ላይ ሲሆን የምልልስ መጠኑን በመጨመር ዓመታዊ ገቢውን ወደ 100 ሚሊዮን ዶላር ወይም ሶስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ መታቀዱንም ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

752 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መስመር በሰዓት 120 ኪሎ ሜትር የሚጓዝ ሲሆን ለግንባታው 3.4 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ተደርጎበታል።

Via:- ethio Fm
@YeneTube @FikerAssefa
አሜሪካ ቱርክ ላይ ማዕቀብ ጣለች!

አሜሪካ ቱርክ በሶሪያ ድንበር ላይ እየወሰደችው ላለው የጦር ጥቃት ምላሽ ሁለት የቱርክ ሚኒስትር መሥሪያ ቤቶችንና ሶስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ ጣለች።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለቱርኩ አቻቸው ጣይብ ኤርዶጋን ስልክ የደወሉ ሲሆን፣ የስልክ ልውውጡም በፍጥነት ተኩስ የሚቆምበት ላይ እንደነበር ምክትል ፕሬዝዳንቱ ማይክ ፔንስ ተናግረዋል።ማይክ ፔንስ አክለውም ወደ ቱርክ " በተቻለ ፍጥነት" እንደሚሄዱ ተናግረዋል።የሶሪያ ጦር ወደ ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል የገባ ሲሆን፣ ይህም በቱርክ ከሚረዱ አማፂያን ተግዳሮት ገጥሞታል።የሶሪያ ጦር ወደ አካባቢው የተሰማራው እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ የአሜሪካ አጋር ከነበረው በኩርዶች ከሚመራው ጦር ጋር ከተደራደረ በኋላ ነው።

ምንጭ: ዋልታ
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመንግሥት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የደንብ ልብስ ለማሠራት ያወጣውን ጨረታ ካሸነፉት 18 ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የፍቅር ሌዘርና ጋርመንት ኢንዱስትሪ ሥራ አስኪያጅና ባለቤት፣ ከጥራት በታች የሆነ ጨርቅ ከውጪ አምጥተዋል በሚል የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ከተማ አስተዳደሩ ውሉን በማቋረጥ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
የሸጎሌ የአውቶብስ ዲፖ ተመርቆ ተከፈተ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ555 ሚሊዮን ብር ያስገነባው የሸጎሌ የአውቶብስ ዲፖ ተመርቆ ተከፍቷል። የተመረቀው ዲፖ በዘመናዊ መንገድ የተገነባ ሲሆን ምቹ የአውቶብስ ማቆያ፣ ዘመናዊ የጥገና ማዕከል፣የአውቶብሶችን ውጪ አካል የቀለም መቀባት አገልግሎትን የሚሰጥ እንደዚሁም የአውቶብስ እጥበት እና የነዳጅ ማደያ አገልግሎቶች የሚሰጡበት ቦታዎች አሉት ተብሏል።ዲፖው 212 አውቶብሶችን ማቆም የሚችል እና ከ250 እስከ 300 ለሚሆኑ አውቶብሶች በተመቻቸ ሁኔታ የእጥበት እና የጥገና አገግሎቶችን የሚሰጥ መሆኑ ተነግሯል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ የሚታየውን የትራንስፖርት እጥረትን ለመቅረፍ ዘመናዊ የአውቶብሶች አገልግሎትን ለኅብረተሰቡ ለመስጠት የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑንም አስታውቋል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን ስያሜውን የመቀየር ፍላጎት እንደሌለው አስታወቀ።

የእግር ኳስ ቡድኑ ምክትል ፕሬዝዳንትና የጎንደር ከተማ አስተዳደር የባሕል ቱሪዝም፣ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አስቻለው ወርቁ በጉዳዩ ላይ ለአብመድ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ከመጀመሩ ቀደም ብሎ በርካታ ውዝግቦች እየተስተዋሉበት ነው። ፋሲል ከነማን ጨምሮ ሌሎች ቡድኖች የስያሜ ለውጥ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማሳሰቡ አንደኛው የውዝግብ ምንጭ ሆኗል።የቡድኑ ምክትል ፕሬዝዳንት እንደተናገሩት ፋሲል ከነማ ስም የመቀየር ፍላጎት የለውም። የእግር ኳስ ቡድኑ የብሔር፣ የከተማ ወይም የአካባቢ ሳይሆን ሀገራዊ ስያሜ እንደተሰጠው በመግለጽ ‹ፋሲል ከነማ› እና ‹ዓፄዎቹ› የሚለው ስያሜ በሌሎች ላይ ምንም ዓይነት ችግር እንደማይፈጥርም አቶ አስቻለው አስታውቀዋል። የተወሳሰቡ ችግሮች በነበሩበት ባለፈው የውድድር ዘመን ቡድኑ ያሳዬውን ስፖርታዊ ጨዋነት ያስታወሱት ምክትል ፕሬዝዳንቱ ‹‹ስያሜ የሚያስቀይር አሳማኝ ምክንያት የለም›› ብለዋል፡፡ከ50 ዓመታት በላይ በዚህ ስያሜ ሲጠራ የኖረን ቡድን ዘንድሮ ለምን ስም ማስቀየር እንዳስፈለገ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ግልጽ ሊያደርግ እንደሚገባም ጠይቀዋል።

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
የኢፌዴሪ አየር ኃይል 166 አብራሪና ቴክኒሻን ሰልጣኞችን አስመረቀ!

የኢፌዴሪ አየር ኃይል አካዳሚ በበረራና በቴክኒሺያንነት ያሰለጠናቸውን 166 ሰልጣኞችን አስመረቀ፡፡ከተመራቂዎቹ መካከል 17ቱ አብራሪዎች ሲሆኑ 149 የሚሆኑት ደግሞ የበረራ ቴክኒሺያን ናቸው፡፡የአየር ኃይሉ ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ይልማ መርዳሳ አየር ኃይሉ በምርምርና በቴክኖሎጂ ሽግግር የሚያደርጋቸውን የአቅም ግንባታ ስራዎች ማሰደጉን እንደሚቀጥል በምረቃው ላይ ተናግረዋል፡፡አየር ኃይሉ በዛሬው ዕለት ያስመረቃቸው ሰልጣኞችም የአየር ኃይሉን የግዳጅ አቅሙ ያሳድገዋል ብለዋል፡፡አየር ኃይሉ ራሱን ለማዘመንና በተሻለ ቁመና ላይ እንዲገኝ ለጥናትና የምርምር ስራዎች ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
ህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን እስከ ሞት የሚያስቀጣ የህግ ማዕቀፍ እየተጠናቀቀ ነው!

ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን፣ የድንበር ማሻገርና በሰው መነገድ ወንጀሎችን መቆጣጠር ያስችላል የተባለውና እስከሞት የሚያስቀጣ አንቀጾችን ያካተተ ጠንከር ያለ የህግ ማዕቀፍ እየተጠናቀቀ መሆኑን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ፡፡በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱሉ በተለይ ለኢቢሲ እንደተናገሩት በርካታ አምራች ወጣቶች በደላሎችና በህገ ወጥ ድንበር አሻጋሪዎች ለእንግልት፣ ለስቃይ እንዲሁም ለሞት እየተዳረጉ በመሆኑ ወንጀሉን ለመቆጣጠር የሚያስችል ጠንካር ያለ የህግ ማዕቀፍ አስፈልጓል፡፡በወንጀል ድርጊቱ በርካታ ወጣቶች የአካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊና አልፎም የህይወት መጥፋት እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡

በሀገራቸው መስራትና ማምረት የሚችሉ በርካታ ወጣቶች በደላሎችና ህገ ወጥ ድንበር አሻጋሪዎች ተጠቂ በመሆናቸው ለጉዳዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑም አክለዋል፡፡ረቂቅ አዋጁ ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ተገቢ ቅጣት እንዲያገኙ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል፡፡ረቂቅ አዋጁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ለህግና ፍትህ ዴሞክራሲያዊ ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም ለሴቶች፣ወጣቶችናማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ ቀርቧል ተብሏል፡፡ጉዳዩ አስከፊና አሳሳቢ መሆኑን ተከትሎ ከሚቀርቡትና ቶሎ ከሚጸድቁት የህግ ማዕቀፎች ውስጥ ቅድሚያ እንዲያገኝ ተደርጓል ብለዋል፡፡

ወንጀሉ በሃገር ውስጥና በውጭ ሃይሎች በቅንጅት የሚሰራ በመሆኑ ችግሩን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ድንበር አካባቢ ካሉ ጎረቤት አገራት ጋር በቅንጅትና በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ እንደተደረሰ አቶ ዝናቡ ገልጸዋል፡፡ችግሩንም በዘላቂነትለመፍታት የህግ ማዕቀፎች ማዘጋጀቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ህብረተሰቡ ላይ ለውጥ ማምጣጥት የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ላይ እና የስራ አድል ፈጠራ ላይ በስፋት መስራት እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡ወጣቱ በሃገሩ ሰርቶ የሚለወጥበት፣ሃብት ንብረት የሚያፈራበት ምቹ ሁኔታ መፍጠር ላይ ትኩረት መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡በዚህ ወንጀል ድርጊት የሚሳተፉ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ከጸጥታ ሃይሉ ጎን ለጎን የህብረትሰቡ ትብብር፣ የወንጀሉ ተጎጅ አካላት ተባባሪ መሆን ወሳኝ ነውም ነው የተባለው፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
በአፋር ክልል ከሰሞኑ የተፈጸመው ጥቃት የታቀደና በውጭ ኃይሎች የተደገፈ እንደነበር የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ ሙሐመድ ለአብመድ እንዳስታወቁት ጥቃት አድራሾቹ የተደራጁና የሶማሌ ላንድ የሠሌዳ ቁጥር ያለው ተሽከርካሪ የሚጠቀሙ ነበሩ፡፡ቅዳሜ ከሌሊቱ 9፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ አፋንቦ ወረዳ ሰንጋ የሚባል መንደር በተፈጸመው ጥቃት የ17 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ በርካቶች መቁሰላቸውንና እንስሳትም መዘረፋቸውን ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡
ጥቃት የተፈጸመበት መንደር ከጂቡቲ ድንበር 35 ኪሎ ሜትር አካባቢ ርቀት የሚገኝ መሆኑን ያመለከቱት አቶ አህመድ በጥቃቱ ሕጻናትና ሴቶች ክፉኛ ሰለባ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡

በአንዳንድ የመገናኛ ብዙኃን ጥቃቱ የተፈጠረው በግጦሽና ውኃ ምክንያት በአፋርና ኢሳ ጎሳዎች መካከል የተፈጠረ እያስመሰሉት መሆኑን ያመለከቱት አቶ አህመድ ‹‹ጥቃቱ ፈጽሞ የአፋርና የኢሳ ጎሳዎች አይደለም›› ብለዋል፡፡
በጥቃቱ የተሳተፉት ኃይሎች ‹‹የሶማሌ ላንድ ሰሌዳ ያለው ተሽከርካሪ ተጠቅመዋል፤ የአልሸባብ ወታደሮች የሚለብሱትን የፊት መሸፈኛና ጥቁር አርማም ተጠቅመዋል›› ብለዋል፡፡ ‹‹የአፋር ሕዝብ በሕይወት የመኖር መብቱ ሊረጋገጥለት ይገባል›› ያሉት ኃላፊው ጥቃቱ የመጀመሪያ አለመሆኑንም አመልክተዋል፡፡ ከአራት ወራት በፊት መሰል ጥቃት ተፈጽሞ እስከ አምስት ሰዎች ሕይወት በዚሁ አካባቢ ማለፉንም ነው ያስታወሱት፡፡ ከመጀመሪያው ጥቃት ጋር በተያያዘ ስድስት ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው እየተጣራ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡
አካባቢው ከዚህ ቀደም የኮንትሮባንድ ንግድ መተላለፊያ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡

አካባቢው ኔትወርክ የማይሠራበትና የመሠረተ ልማት እጥረት ያለበት መሆኑ ጥቃቱን በፍጥነት ለመከላከልም ሆነ ቁስለኞችን ለማጓጓዝ አስቸጋሪ እንደነበርም አመልክተዋል፡፡የአካባቢውን ሠላም ለማረጋገጥ የፌዴራሉ መንግሥት ልዩ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባው ያሳሰቡት አቶ አህመድ ‹‹የሀገር መከላከያ ሠራዊት ወደ አካባቢው አልተሠማራም›› ብለዋል፡፡የተፈጸመውን ጥቃት ለማውገዝ በአፋር ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ዛሬ ሰልፎች መካሄዳቸውንም አስታውቀዋል፡፡ አቶ አህመድ እንደተናገሩት አዋሽ አርባ፣ አፋምቦ እና ገዋኔ ላይ ሠልፎች ተካሂደዋል፡፡ የአፋር ሕዝብ ደኅንነት እንዲረጋገጥም ሰልፈኞቹ መጠየቃቸውን አመልክተዋል፡፡

ምንጭ: አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa
አፋር ⬆️

"በውጪ ወረራ ሀይል ለሚሞተው ንፁሀን የአፋር ህዝቦች ፍትህ እንሻለን"

በአፋር ክልል በተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል።

@YeneTube @Fikerassefa