የ2012 የትምህርት ዘመን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት #የተረጋገጠ
ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች የሚያመሩ ተማሪዎች
I. የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን ዋናውን እና ሁለት ኮፒዎች፣
• የ8ኛ ክፍል (ሚኒስትሪ) ሰርተፊኬት
• የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሰርተፊኬቶች
• ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የተማራችሁበትን ትራንስክሪፕት
II. 8 ፓስፖርት ሳይዝ ፎቶ ግራፍ (የቅርብ ጊዜ)
III. አንሶላ እና ብርድ ልብስ
IV. የስፖርት አልባሳት (ጫማን ጨምሮ)
** ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች የሚኖራቸውን ቆይታ ሰላማዊ ለማድረግ የተማሪ ወላጆች ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር የዋስትና ውል እንዲገቡ መደረጉ ይታወቃል።
ስለዚህ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዎቹ በሚሄዱበት ወቅት ወላጆቻቸው የተፈራረሙበትን ሰነድ ይዘው እንዲገኙ ዩኒቨርሲቲዎቹ ጠይቀዋል። ተማሪዎቹ ሰነዶቹን ከየሚኖሩበት ወረዳ መውሰድ ይችላሉ።
ተጨማሪ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ሲጠሩ ተከታትለን የምናሳውቃችሁ ሲሆን ከታች የተዘረዘሩት ቀናት ላይ የጊዜ ለውጥ ካለም ለውጡን የምናሳውቃችሁ ይሆናል።
Via:- EBC
@YeneTube @Fikerassefa

YeneTube
የእነብርጋዲዬር ጀኔራል ተፈራ ማሞ ጉዳይ ለጥቅምት 12 ቀን ተቀጠረ፡፡ የእነብርጋዲዬር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የምርመራ ጉዳይ ላይ የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፖሊስ ምርመራ ቡድን የጠየቁት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ይግባኝ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዛሬ ረፋድ ባስቻለው ችሎት የመርማሪ ቡድኑ የጠየቀውን የተጨማሪ ቀጠሮ ይግባኝ ውድቅ አደርጓል፡፡…
#update
ዛሬም ችሎቱ በዝግ የታየ ሲሆን፣ የፍርድቤቱን ድርጊትየተቃወሙ የባህርዳር ነዋሪዎች ሰልፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።ፖሊስ ተቃውሞ በሚያሰማው ህዝብ ላይ አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ ላይ ይገኛል።
Via ELU
@YeneTube @FiketAssefa

ጎንደር ታች አርማጭሆ❗️
በማዕከላዊ ጎንደር ታች አርማጭሆ የሚገኙ ነዋሪዎች ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ድንገት ወደ አካባቢው እየመጡ በሚፈፅሙት ጥቃት እና አልፎ አልፎ እየታየ ባለው የተደራጀ ዘረፋ አማካኝነት ከአንድ ሺ አምስት መቶ በላይ የሚሆኑ ሰዎች መኖሪያ አካባቢያቸውን በመተው ተፈናቅላዋል፡፡
እምሩ ባንተይሁን የተባሉ አንድ የወረዳው ነዋሪ ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት ከቅርብ ግዜ ወዲህ የተለመዱ እየሆኑ የመጡት እነዚህ ተግባሮች በነዋሪው ዘንድ ከፍተኛ ስጋት የፈጠሩ ሲሆን አራት የተለያዩ ሰብሎችን የያዙ መኪኖችም ሰብላቸው ተዘርፎ መኪናዎቹ መገኘታቸውንም ይናገራሉ፡፡
Via:- አዲስ ማለዳ
@YeneTube FikerAssefa

የምርጫ ቦርዱ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሊያደርጉ የነበረው ውይይት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ!
የኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች በቅርቡ በፀደቀው የምርጫ አዋጅ ላይ ሊያደርገው የነበረው ውይይት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ተገለፀ፡፡
ውይይቱ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና በስነ-ምግባር አዋጁ እንዲሁም በቦርዱ የአደረጃጀት ለውጥ ላይ ሊካሄድ የታሰበ ነበር። ሆኖም አዋጁ ከአሁን ቀደም ባደረግናቸው ውይይቶች የተነሱ የማሻሻያ ሃሳቦች ሳይካተቱ የፀደቀ ነው ያሉት ፓርቲዎቹ የውይይቱ መካሄድ ተገቢነት የለውም በሚል ተቃውመውታል።
ቦርዱ ስምምነት ላይ ሳይደረስ መፅደቁን አለመከላከሉ ተዓማኒነቱን ጥያቄ ውስጥ ሊከተው እንደሚችልም ነው ፓርቲዎቹ ያስታወቁት። በጉዳዩ ላይ ሲከራከሩ የቆዩት ፓርቲዎቹ ውይይቱን ላልተወሰነ ጊዜ አራዝመው ተለያይተዋል። ፓርቲዎቹ በጋራ ምክር ቤታቸው በኩል መወያየት ጀምረዋል።
Via :- ኢቢሲ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን ከችጉንጉኒያ ወረርሽ ስጋት ለመታደግ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡
በከተማው ለወራት በዘለቀውና ከ35 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ያጠቃው ወረርሽኙ ከእረፍት እየተመለሱ ባሉ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ላይም ስጋት መፍጠሩ ተገልጿል፡፡የቺኩንጉኒያን ወረርሽኝን ለመከላከል በተማሪዎች አገልግሎት መስጫ ስፍራዎች መድሃኒት መረጨቱን የድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ማሞ ለአሐዱ ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡በድሬዳዋ ከአንድ ቤት ከ2-4 ሰዎች በወረርሽኙ እንደተያዘ የተገለጸ ሲሆን መንግስት ጉዳዩን በአጽኖት እንዲመለከተው የህክምና ባለሞያዎች እየጠየቁ ነው፡፡ከድሬዳዋ የጤና ቢሮ ጋር በመተባበር የድሬ የበጎ ፍቃድ የህክምና ባለሞያዎች ማህበር ወረርሽኙን ለመግታት የህክምና ዘመቻ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
Via Ahadu Radio
@YeneTube @FikerAssefa

የጤና ሚኒስቴር የተቋሙን አዲሱን መለያ አርማና መሪ ቃል አስተዋወቀ:: የጤና ሚኒስቴር የተቋቋመበትን ዓላማናግብ ለህብረተሰቡ በቀላሉ ለማድረስ ይቻለው ዘንድ አዲስ መለያ ዓርማና መሪ ቃል በማዘጋጀት በዛሬው ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ይፋ አድርጓል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የጠ/ሚ ፅ/ቤት እስራኤል የሚገኙ ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳይ...
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ እስራኤል የሚገኙ ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደሃገራቸው መመለስን ጉዳይ አስመልክቶ ከቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋር ያደረጉት ውይይት የለም ሲሉ የጠ/ሚ ፅህፈት ቤት ምንጮች ገልፁልኝ ሲል የአሜሪካ ድምፅ ዘግቧል።
የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር በዋቢነት የጠቀሰው 'The Times Of Israel' /ዘ ታይምስ ኦፍ ኢስራኤል/ “የኢትዮጵያው መሪ ኤርትራውያን ስደተኞችን ወደሃገራቸው በመመለሱ ሂደት ዕገዛ ለማድረግ ተስማምተዋል” ሲል ነው ሰሞኑን የዘገበው።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ፅህፈት ቤት ምንጮች እንዳሉት ግን የስደተኞችን ወደሃገራቸው የመመለስ ጉዳይ እንዲያውም በሁለቱ መሪዎች ውይይት አልተነሳም ።
#VOAAmharic

⬆️
ሰኔ 15 ጀነራል ሰአረ መኮንን ላይ ግድያ እንደፈፀመ የተጠረጠረው ጠባቂ መንቀሳቀስ እና መናገር እንደጀመረ መረጃ ደርሶኛል!
መረጃው እንደሚጠቁመው ግለሰቡ በአሁን ሰአት በአራት የፌደራል እና አራት መከላከያ አባላት ጥበቃ ተደርጎለት ህክምና እየተከታተለ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ንግግር ማድረግ እና እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምሯል ተብሏል። ሌላው ከዚህ ጋር አብሮ የደረሰኝ መረጃ ግለሰቡ በግድያው ቀን በነበረው ተኩስ አንድ አይኑን አጥቷል። አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ የተባለው ይህ የጀነራሉ ጠባቂ ሰኔ 15 ግድያውን እንደፈፀመ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር እንዳለ ይታወቃል። የመንግስት አካላትም በወቅቱ ይህ ግለሰብ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት ሰንዝሮ ነገር ግን ቆስሎ በህይወት እንደተረፈ በወቅቱ ገልፀው ነበር። ተጨማሪ መረጃ ለመጠየቅ የፌደራል ፖሊስ ደውዬ ነበር። ነገር አሁን ላይ ምንም ተጨማሪ መረጃ የለም፣ ሲኖር ለህዝብ ይፋ ይደረጋል የሚል መልስ ብቻ አግኝቻለሁ።
Via Elias Meseret

ሻለቃ አስቻለው ለከፈተው ተኩስ በተወሰደ አጸፋ ህይወቱ ማለፉን ፖሊስ ለአብመድ ተናገረ።ግለሰቡ ሰኔ 15 ላይ በተፈፀመው የከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና የፖሊስ አባላት ግድያ ተጠርጥሮ በህግ ሲፈለግ መቆቱንም ፖሊስ አስታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በቴክኒክ ችግር ወደተነሳበት አየር ማረፊያ ተመልሶ ለማረፍ ተገደደ!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET908 የበረራ መስመር ዲአስ ሴኔጋል - ማሊ ባማኮ - አዲስ አበባ የሆነው ቦይንግ 767-300 አውሮፕላን ከሴኔጋል ዲአስ ከተነሳ በኋላ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ወደተነሳበት አየር ማረፊያ ለማረፍ መገደዱን አየር መንገዱ ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።አየር መንገዱ አውሮፕላኑ ምን አይት የቴክኒክ ችግር እንደገጠመው ግልጽ ባያደርግም አጀንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው ከሆነ፤ ከአውሮፕላኑ ሞተሮች አንዱ እሳት በመያዙ 90 ሰዎችን አሳፍሮ የነበረው አውሮፕላን በፍጥነት ተመልሶ እንዲያርፍ ተደርጓል።
የሴኔጋል ኤርፖርቶች ቃል አቀባይን ጠቅሶ ኤኤፍፒ እንደዘገበው የአውሮፕላኑ አብራሪ ተመልሶ ለማረፍ ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ ነው አውሮፕላኑ እንዲያረፍ የተደረገው።የሴኔጋል መገናኛ ብዙሃን አውሮፕላኑ አየር ላይ የቆየው ለ10 ደቂቃዎች ብቻ መሆኑን ጨምረው እየዘገቡ ነው።አየር መንገዱ መንገደኞቹ በመጉላላታቸው ይቅርታ በመጠየቅ ሁሉም ተሳፋሪዎች በተለዋጭ በረራዎች ጉዟቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቋል።
Via BBC

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛው መርሐ ግብር አዲስ ለተመደባችሁ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ
እንኳን ለ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያልን አዲስ አንደኛ ዓመት ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያና የመመዝገቢያ ቀን ጥቅምት 04 እና 05 ቀን 2012 ነው፤
- በተጠቀሱ ቀናት ለምዝገባ የሚያስፈልጉ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ስርተፊኬት፣ የስፖርት ትጥቅ፣ ትራንስክሪፕት ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም አራት ጉርድ ፎቶግራፍ በመያዝ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት በአካል ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ እናስታውቃለን፡፡ከዚህ በፊት Withdrawal ሞልታችሁ የወጣችሁና በRe-admission የምትገቡ ተማሪዎች ከላይ በተጠቀሱት ቀናት እንድታመለክቱ እናስታውቃለን።
ማሳሰቢያ
- ከተገለጸው ጊዜ ቀድመውም ሆነ ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
-ዲላ ዩኒቨርሲቲ

በአጣዬው ግጭት፣የሰሜን ሸዋ ዞንና የኦሮሞ ብሔር አስተዳደር ውዝግብ
የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር«አጣየን ለማጥቃት የተዘጋጀ እና የተደራጀ ኃይል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ውስጥ አለ» ይላል።በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ደግሞ በዞኑ የተደራጀና የታጠቀ ኃይል ፈፅሞ የለም ባይ ነው።ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በሰሜን ሸዋ ዞን አጣየ አካባቢ በተፈጠረው ግጭት 8 ሰዎች መገደላቸውና 13 መቁሰላቸው ተነግሯል፡፡ሰሞኑን በአማራ ክልል አጣዬ አካባቢ የተፈጠረው አለመረጋጋት ምክንያት፣« የአማራ ክልል በተለይም የሰሜን ሸዋ ዞን እንዳይረጋጋ የሚፈልጉ ኃይሎች ናቸው» ሲል የሰሜን ሸዋ ዞን የፀጥታ መምሪያ አስታውቋል። የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር፣« አጣየን ለማጥቃት የተዘጋጀ እና የተደራጀ ኃይል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ውስጥ አለ»ይላል።በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ደግሞ በዞኑ የተደራጀና የታጠቀ ኃይል ፈፅሞ የለም ባይ ነው።ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በሰሜን ሸዋ ዞን አጣየ አካባቢ በተፈጠረው ግጭት 8 ሰዎች መሞታቸውና 13 መቁሰላቸውን አመራሮቹ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡
-DW

ኢ/ር ታከለ ኡማ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የታክሲ አገልግሎት (ኤታስ) ከሚሰጡ 13 ተቋማት ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
በዋነኛነት የከተማ አስተዳደሩ በቅርቡ የኤታስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲከተሉት ባወጣው መመሪያ ዙሪያ እና የትራንስፖርት ሴክተሩን በዘላቂነት ዘመናዊ ለማድረግ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከኤታስ እና ሶፍትዌር ማበልፀጊያ ተቋማት ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡የኤታስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማቱ በከተማ አስተዳደሩ ረቅቆ በቅርቡ ይፋ የሆነው መመሪያ ቴክኖሎጂው ላይ ምንም ተፅዕኖ እንደሌለው ተናግረዋል፡፡
ተቋማቱ ህጉን እንደማይቃወሙ እና ለተፈፃሚነቱ ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡ኢ/ር ታከለ ኡማ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የትራንስፖርት አሰጣጥ በከተማዋ ውስጥ እንዲስፋፋ ፍላጎቱ ነው ብለዋል፡፡ በከተማዋ ውስጥ ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ የሚረዱ ሌሎች ተጨማሪ ቴክኖሎጂዎችን ለሚያመጡ በራቸው ክፍት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይነትም የከተማ አስተዳደሩ የተቀላጠፈ እና ህዝቡን የሚጠቅም መመሪያ ቀርጾ በከተማዋ ውስጥ ያለውን የትራንስፖርት እጥረት ለመቅረፍ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡በመጨረሻም የኤታስ ተቋሞቹ በከተማዋ ውስጥ የታክሲ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ ተሽከርካሪዎች ያረጁ በመሆናቸው የከተማ አስተዳደሩ ተሽከርካሪዎቹን በአዲስ በመተካቱ ሂደት ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Via Mayor Office