"የማራቶን ሯጮቹ ላይ የተላለፈው እገዳ አይደለም" ዱቤ ጂሎ
የኢትዮጵያ የማራቶን ውድድር ሯጮች ላይ ምንም አይነት የእገዳ ውሳኔ እንዳልተላለፈ ከአትሌቶቹ ጋር ካታር የሚገኙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክትር ዱቤ ጂሎ ለቢቢሲ ተናገሩ።በካታር ዶሃ እየተካሄደ ባለው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በማራቶን ውድድር ላይ የተሳተፉት አትሌቶች ለቀጣዮቹ ሦስት ወራት እረፍት አድርገው እንዲያገግሙ እንጂ እገዳ አለመሆኑን ገልጸዋል።ውሳኔው ከ42 ኪሎሜትሮች በላይ በሚሮጥበት ከባድ በሚባለው የማራቶን ውድድር ላይ የሚሳተፉ ሯጮችን ጤንነትና ደህንነት ለመጠበቅ የሚወሰድ ተቀባይነት ያለው እረፍት ነው ብለዋል ዱቤ ጅሎ።
አትሌቶች የሦስት ወራት የማገገሚያ ጊዜ እንዲያገኙ ማድረግ በዓለም አቀፍ የውድድር ሕግና ደንብ ውስጥ ተቀባይነት ያለውና በሌሎችም ሃገራት የሚሰራበት እንደሆነ አመልክተዋል። ለሦስት ወራት ከውድድር እርቆ የሚወሰደው እረፍት ሁሉንም በማራቶን ውድድር የተሳተፉ አትሌቶችን የሚመለከት መሆኑን የጠቀሱት የቴክኒክ ዳይሬክተሩ፤ በተለይ በዶሃ ያለው ከባድ ሙቀት ላይ ለተወዳደሩ አትሌቶች እረፍቱ በጣም አስፈላጊያቸው ነው ብለዋል ለቢቢሲ።ባለፈው አርብ ሌሊት በተካሄደው የሴቶች ማራቶን ላይ ተሳታፊ የነበሩት ኢትዮጵያዊያን ሯጮች በነበረው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ውድድሩን አቋርጠው መውጣታቸው የሚታወስ ሲሆን እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ በርካቶችም ለማቋረጥ ተገደው ነበር።
Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa

በድሬዳዋ አስተዳደር ግጭት 22 ተጠርጣሪዎች ታሰሩ።
ሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ በተቀሰቀሰው ግጭት ከፊትም ሆነ ከጀርባ ሆነው የነዋሪዎችን ደኅንነት አደጋ ላይ የጣሉ ማንኛውንም የመንግሥት አመራር፣ የፀጥታ አስከባሪ፣ በዋናነትም ፀረ ሰላም ሆኖ እራሱን ያደራጀ ቡድንም ሆነ ግለሰብ በንፁሐን ነዋሪዎች ሕይወት ላይ በመቆመር የቆሸሹ እጆችን ሰብስቦ ለህግ እንደሚያቀርብ የአስተዳደሩ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። በጸጥታ አካላት በተተኮሰ ጥይት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ሦስት መድረሱን አዲስ ማለዳ ከድሬደዋ ነዋሪዎች የተገኘው መረጃ ያመለክታል። በግጭቱ በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን እና በውል ያልታወቀ ንብረት መዘረፉን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።
ምንጭ: አዲስ ማለዳ

በሆራ ፊንፊኔና በሆራ አርሰዴ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን መወጣት እንዳለበት የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከኦቢኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል፡፡
በሀገሪቱ በተገኘው ድል የኦሮሞ ህዝብ ሀሳቡን፣ ፍላጎቱንና ማንነቱን በነፃነት መግለፅ ችሏል ብለዋል፡፡
ኢሬቻ የሰላም ና የምስጋና በዓል ነው ያሉት ዶ/ር አብይ በዓሉን ለፖለቲካ አላማ ማዋል ተገቢ አይደለምም ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እርስ በርስ መማማር አለባቸው የኦሮሞ ህዝብ ለሌሎች የሚያስተምረው በርካታ ባህል፣ታሪክ ና እሴቶች አሉት ሌላውም እንዲሁ ያለውን እሴት በማስተማር በመደማመጥ በጋራተቀራ አንድነትን ማጠናከር ይኖርበታል ብለዋል፡፡
Via:- OBN
@Fikerassefa @YeneTube

ምርጫ ቅስቀሳ - ሲዳማ
ቦርዱ የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ቅስቀሳ ከጥቅምት 18 እስከ 22 ድረስ እንደሚካሄድ አስታወቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ክልልነት ህዝበ ውሳኔ አፈጻጸም መርሃ ግብር ላይ ለውጥ መደረጉን በዛሬው እለት አስታውቋል።.
በሲዳማ ክልልነት ህዝበ ውሳኔ አፈጻጸም መርሃ ግብር መሰረት የቅስቀሳ ጊዜ ከመስከረም 23 እስከ መስከረም 28 2012 ዓ.ም በሚል ታቅዶ እንደነበረ ይታወሳል።
ነገር ግን የህዝበ ውሳኔ ቅስቀሳው የመራጮች ምዝገባ ከሚደረግበት ጊዜ ጋር የተቀራረበ ቢሆን ይሻላል በሚል ስለታመነበት የቅስቀሳ መርሃ ግብሩ ከጥቅምት 18 እስከ ጥቅምት 22 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት እንዲሆን ማሻሻያ መደረጉን አስታውቋል።
ቦርዱ በአፈጻጸም ጉዳዮች የተነሳ የሚኖሩ የቀናት ለውጥና መሸጋሸጎችን ወደፊትም ይፋ የሚያደርግ መሆኑን ነው የገለፀው።
Via:- FBC
@YeneTube @Fikerassefa

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገዛቸውን 100 አውቶብሶች ለአንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት አስረከበ።
የርክክብ ስነ ስርዓቱ በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በተገኙበት በመስቀል አደባባይ ተከናውኗል።
ዛሬ ወደ ስምሪት የገቡት 100 አውቶብሶች ሁሉም አሽከርካሪዎች እና ረዳቶቸውም ሴቶች መሆናቸውንም ገልፀዋል።
Via:- FBC
@YeneTube @Fikerassefa
የርክክብ ስነ ስርዓቱ በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በተገኙበት በመስቀል አደባባይ ተከናውኗል።
ዛሬ ወደ ስምሪት የገቡት 100 አውቶብሶች ሁሉም አሽከርካሪዎች እና ረዳቶቸውም ሴቶች መሆናቸውንም ገልፀዋል።
Via:- FBC
@YeneTube @Fikerassefa
የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ጥቅምት ወር ላይ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ እንደሆነ ተገለፀ፡፡
የምክር ቤቱ አባላት በአፍሪካ በሚያደርጉት ጉብኝት ከአዲስ አበባ ባሻገር የደቡብ ሱዳንን ጁባ ከተማ እንደሚጎበኙ ተነግሯል፡፡
የመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በጥቅምት 12 እና 13 በአዲስ አበባ በሚያደርገው ቆይታውም ከአፍሪካ ህብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት እና ከአጋር አካላት ጋር ዓመታዊ ምክክር እንደሚያደርግ ተመልክቷል፡፡
በማግስቱም ምክር ቤቱ በመንግስታቱ ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር ኬሊ ክራፍት ጋር በመሆን በጁባ ጉብኝት እንደሚያደርግ ይጠበቃል ተብሏል፡፡
በዚህም በአገሪቱ ጉዳዮች ላይ በተቀመጡ የውይይት አጀንዳዎች ላይ ምክክር እንደሚደረግ ነው የተነገረው፡፡
ምክር ቤቱ አፍሪካ የሚያደርገውን ጉብኝት ካጠናቀቀ በኋላም በኒውዮርክ በሚያደርገው ስብሰባ በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ እንዲሁም በኮሶቮ ጉዳይ ላይ ውይይት እንደሚያደርግ ተጠቁሟል፡፡
ምንጭ፦ ሽንዋ
@Yenetube @Fikerassefa

የጃፓን ተመራማሪዎች ሰው ሰራሽ ደም መስራታቸውን አስታወቁ
በጃፓን ተመራማሪዎች ቤተ ሙከራ የተሰራው ሰው ሰራሽ ደም የትኛውም የደም አይነት ላላቸው ታማሚዎች ሊውል እንደሚችልም ተገልጿል፡፡
ሰው ሰራሹ ደም ከኦክስጅን ተሸካሚ የቀይ የደም ሴሎች ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ደም እንዲረጋ የሚያስችል ፕላቲሌትን ያዘለ መሆኑም ታውቋል፡፡
ሰው ሰራሹ ደም በ10 ከፍተኛ የደም መፍሰስ ባጋጠማቸው ጥንቸሎች ላይ ተሞክሮ የስድስቱን ህይወት ለመታደግ ተችሏዕል፡፡
ደሙ ከተፈጥሮአዊው ደም ጋር ተቀራራቢ ይዘት እንዳለውም ተገልጿል፡፡
ምንጭ፡- ደይሊ ሜል

በእነብርጋዴር ተፈራ ማሞ ጉዳይ የተጠየቀው የጊዜ ቀጠሮ ይግባኝ ላለፉት 2 ወራት ውሳኔ ሳያገኝ ዛሬም በዝግ ችሎት ለመስከረም 27 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠው፡፡
ከሰኔ 15 ቀን፣ 2011 ዓ.ም የባህር ዳሩ ጥቃት ጋር በተያያዘ የእነ ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ሲመለከት የነበረው ባህር ዳር ወረዳ ፍረድ ቤት የተጠርጣሪዎችን ምርመራ አጠናቅቆ ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ እንደማስፈልግ በማመልከት ሐምሌ 29 ቀን፣ 2011 ዓ.ም የ15 ቀናት የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቅዶ ፋይሉን ዘግቶ ለባህር ዳርና አካባቢው ፍርድ ቤት መላኩ ይታወሳል።
ኾኖም ቀሪ የምርመራ ሥራዎች አሉኝ በማለት መርማሪ ቡድኑ ለባሕርዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ጠይቆ ሲከራከር ቆይቷል፡፡ የባህር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ነሐሴ 22 ቀን፣ 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት የባህር ዳር ወረዳ ፍርድ ቤት የወሰነውን ውሳኔ በማፅደቅ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ኤስፈልግም በሚል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
የመርማሪ ቡድኑ ጉዳዩን ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በማቅረብ የጊዜ ቀጠሮ ይግባኙ እንደፈቀድለት ቀደም ሲል ይግባኝ ጠይቋል፡፡
ዛሬ ለጋዜጠኞች ዝግ የሆነው የፍርድቤት ውሎን አስመልክተው ከተጠርጣሪ ጠበቆች አንዱ ለዶይቼ ቬለ (DW) በስልክ እንደተናገሩት ጉዳዩን ዛሬ 5 ዳኞች በተሰየሙበት ማብራራታቸውንና ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ይሰጥ ወይስ አይሰጥ በሚለው ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ለመስከረም 27 ቀን፣ 2012 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል፡፡
የባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ፍርድ ቤት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ኤስፈልግም በማለት መዝገቡን ዘግቶ ወደ ባህርዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የላከው ሐምሌ 29 ቀን፣ 2011 ዓ.ም ነበር፡፡
Via:- DW

ለ21 ዓመታት በኔዘርላንድ ተደብቆ የነበረው ኢትዮጵያ ንብረት የሆነው ዘውድ ወደ ኢትዮጵያ ሊመለስ ነው።የ18ኛው ክፍለ ዘመን ዋጋ የማይገዛው ድንቅ ቅርስ የተባለለት እና ከ21 ዓመታት በፊት ተሰርቆ ወደ ኔዘርላን በማምራት ተደብቆ የነበረው ዘውድ ለኢትዮጵያ ተላልፎ ሊሰጥ ነው።
ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ግጭትና ሁከት የሚፈጥሩ ያላቸውን ሃይሎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ የአማራ ክልል አስጠነቀቀ።
ክልሉን ወደ ግጭትና ሁከት እንዲገባ እየሰሩ ያሉ አካላትና ጽንፈኛ መገናኛ ብዙሃን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ የአማራ ክልል የሰላምና ደህንነት ቢሮ አስጠነቀቀ።የቢሮ ሀላፊው አቶ አገኘሁ ተሻገር፤ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ ባለፉት ዓመታት ተነስቶ የክልሉ መንግስትና ምክር ቤቱ ተገቢ ምላሽ ሰጥቷል። ይሁን እንጂ በምላሹ ያልተካተቱ ቀበሌዎች አሉ በሚል ከኮሚቴዎቹ አባላት ቅሬታ ይነሳል። ባልተስማሙበት ጉዳይ ጥያቄ ማንሳት ተገቢነት ያለው ቢሆንም ፅንፈኛ ሃይሎች ከኋላ ሆነው ሁከት እንዲፈጠር በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት ጉዳዩ በተሳሳተ መንገድ እንዲሄድ እያደረጉ ነው ያሉት የቢሮ ሃላፊው፤ ልዩነቱን የሚጠቀሙበት ሀይሎች የአማራ ክልል ተረጋግቶ እንዳይቀጥል ከጽንፈኛ ሃይሎች ጋር ትስስር ፈጥረዋል ብለዋል።
እነዚህ ሃይሎች ከኋላ በመሆን ስልጠና በመስጠት፣ ትጥቅ በማስታጠቅና ገንዘብ በማቅረብ የተለያዩ የሽብር ስራ እንዲሰሩ እያደረጓቸው እንደሆነና ዓላማውም ክልሉን ማተራመስ እንደሆነም ገልፀዋል።እንደ አቶ አገኘሁ ገለፃ ከኋላ ሆነው በሚደግፏቸው ሀይሎች የክልሉ ፖሊስና ተራ የመከላከያ ወታደር የማይታጠቃቸውን እንደ ስናይፐር፣ መትረየስና ሌሎች መሳሪያዎችን ታጥቀዋል። እነዚህ ሃይሎች አማራን ለማዳከም የተፈጠሩ ናቸው። በጽንፈኛ ኮሚቴዎች በመታገዝ መንገድና ተቋማትን በመዝጋት፣ ሰው በመግደል፣ የመንግስትን ስራ በማስተጓጎል ክልሉን ወደ ችግር ለመክተት እየሰሩ ይገኛሉ።
ምንጭ: ኢፕድ

የቻግኒ-ግልገል በለስ-ጃዊ መንገድ በአፈር መንሸራተት ተዘጋ!
ከቻግኒ ግልገል በለስ ጃዊ እና ሕዳሴ ግድብ በሚወስደው መንገድ የካር ተራራ ተደርምሶ በትራንስፖርት አግልግሎት ላይ መስተጓጓል ተፈጥሯል ። የካር ተራራ ተደርምሶ መንገዱን በመዝጋቱ ተሽከርካሪዎች በቅብብሎሽ አግልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ከቻግኒ ግልገል በለስ ጃዊ እና ሕዳሴ ግድብ በሚወስደው መንገድ በተደጋጋሚ ብልሽት የሚደርስበት እና ዘላቂ መፍትሔ የሚያስፈልገው መሆኑን ደግሞ የግልገል በለስ የትራፊክ ቁጥጥርና ውሳኔ ሰጪ ባለሙያ ምክትል ሳጅን ፍቅሬ ኦጄ ተናግረዋል፡፡ የተደረመሰውን አፈር ለማንሳት እና መንገዱን ለመክፈት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ባለሙያው ተናግረዋል፡፡
ምንጭ:Geepa

View From Arada የሚለውን መጣጥፋቸውን በእንግሊዝኛዉ ፎርቹን ጋዜጣ ለዓመታትና ሌሎች መጣጥፎችንም በአማርኛ ሲያስነብቡ የነበሩት አቶ ግርማ ፈይሳ በ78 ዓመታቸው በቤልጂየም ብራሰልስ አረፉ!
Via:-Tamiru Tsige
@YeneTube @Fikerassefa
Via:-Tamiru Tsige
@YeneTube @Fikerassefa
ተጨማሪ የፌዴራል መንግስት የስራ ቋንቋዎች እንዲኖሩ ለማድረግ እየተሰራ ነው -ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተጨማሪ የፌዴራል መንግስት የስራ ቋንቋዎች እንዲኖሩ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (OBN) ጋር ባደረጉት ቆይታ ተጨማሪ የፌዴራል መንግስት የስራ ቋንቋዎች እንዲኖሩ ለማድረግ ጥናት መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ይህ ተግባራዊ መሆን ያለበት ጥናትና እውቀትን መሰረት አድርጎ መሆን እንዳለበት የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አፋን ኦሮሞን ጨምሮ ሌሎች ቋንቋዎችን የፌዴራል መንግስት የስራ ቋንቋዎች ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

መንገዱን ስቶ የተገለበጠ መኪና የስድስት ሰዎችን ሕይወትን ቀጠፈ ተሳፋሪዎች ላይ ግን ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ፖሊስ አስታውቋል፡፡
መንገዱን ስቶ የተገለበጠ መኪና እግራቸውን በመታጠብ ላይ የነበሩ ስድስት ሰዎች ሕይወት እንዲያልፍ ምክንያት መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን እናርጅ እናውጋ ወረዳ ፈለገ ዛቸና ቀበሌ ዛሬ ጥዋት 4፡00 ላይ ነው አደጋው ያጋጠመው፡፡ከባሕር ዳር ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ መለስኛ የሕዝብ ማመላለሻ (ኤፍ ኤስ አር) ተሽከርካሪ መስመሩን ስቶ በመገልበጡና እግራቸውን በመታጠብ ላይ የነበሩ ስድስት ሰዎች ላይ በመውደቁ የስድስቱም ሕይወት እንዲያልፍ ምክንያት ሆኗል፡፡
የምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ዋና ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው እንደገለጹት በመኪናው ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች ግን ምንም ጉዳት አልደረሰባቸውም፡፡ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሆነና አሽከርካሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑንም ዋና ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው ተናግረዋል፡፡መረጃውን ያደረሰን ጋሻዬ ጌታሁን ነው፡፡
Via AMMA

የፍል ውሃና አካባቢው የልማት ተነሺዎች ለ13 ዓመታት ሲያነሱት የነበረው የይዞታ ማረጋገጫ ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱ ተገለፀ።
ከፍል ውሃና አካባቢው በልማት ተነሺ የነበሩ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በቦሌ ክፍለ ከተማ ሲ ኤም ሲ አካባቢ አልታድ የመኖሪያ ሰፈር ቤት ተሰጥቷቸው ይኖሩ ነበር፡፡ነገር ግን የልማት ተነሺዎቹ የይዞታ ማረጋገጫ የነበራቸው በመሆኑ እንደ ቀበሌ ቤት እየከፈልን መኖር የለብንም በማለት ቅሬታ ሲያቀርቡ ነበር፡፡በዛሬው ዕለትም እነዚህ የልማት ተነሺዎች ለ13 ዓመታት ሲያነሱት የነበረው የይዞታ ማረጋገጫ ጥያቄ የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ምላሽ አግኝቷል፡፡በዚህ መሰረት 1 ሺህ 300 የሚሆኑ አባዎራዎች እያንዳንዳቸው የይዞታ ማረጋገጫ እንደተሰጣቸው የከተማዋ ቤቶች አስተዳድር ልማት ቢሮ ሃላፊ ኢንጂነር ሰናይት ዳምጠው ተናግረዋል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማም የከተማ አስተዳደሩ በህብረተሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ምንጭ: ፋና

Forwarded from YeneTube
🤩🤩🤩🤩የምስራች 🤩🤩🤩
በአ.አ በቀላሉ የማይገኙ ፤ ወደ12ሺ ሰዓቶች እና ቦርሣዎች ለትዛዝ ፤ ከ 1ሺ በላይ እቃዎች በ እጃችን መርጠው ይዘዙን ወደ ክልልም እንልካለን
ከታች ባለው ሊንክ ይጎብኙን
👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAENXyUTam6WMV6_hmg

የኦሮሞ ፓርቲዎች ጋር በአንድ ፓርቲ ጥላ ስር ተሰባስቦ እስከመሥራት ድረስ መዘጋጀታቸውን አቶ በቀለ ገርባ ገለፁ።
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ገዢው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን ጨምሮ ከተለያዩ የኦሮሞ ፓርቲዎች ጋር በአንድ ፓርቲ ጥላ ስር ተሰባስቦ እስከመሥራት ድረስ መዘጋጀታቸውን ገለጡ። «ተመሳሳይ ዓላማና ተልዕኮ ይዘን እስከተነሳን ድረስ ወደ አንድነት እና ወደ አንድ ፓርቲ እንዳንመጣ የሚከለክለን ነገር የለም» ሲሉም ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ገዢው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ባለበት ትናንት ባደረጉት ስምምነት በጋራ ለመሥራት መፈራረማቸው ተገልጧል። የኦሮሞ አመራርን በአንድ ጥላ ስር የሚያሰባስብ (ጋዲሳ ሆገንሳ ኦሮሞ) የተባለ ኮሚቴም ተመስርቷል። የኮሚቴው መሪ በትናንቱ የፊርማ ስምምነት ከጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ ጋር የታደሙት መከላከያ ሚንሥትሩ ለማ መገርሳ መኾናቸው ተገልጧል።
-ዶይቸ ቬሌ

70 የፖለቲካ ድርጅቶች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በምርጫ ሕጉ ላይ ተቃውሟችን ካልሰማልን ከጥቅምት 5-6 ርሃብ አድማ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ የፓርቲዎቹ የጋራ ኮሚቴ ዛሬ በሰጠው መግለጫ፣ በተሻሻለው የምርጫና ፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጆች ላይ ተቃውሞውን ቢያቀርብም ሰሚ እንዳላገኘ መግለጹን ሸገር ዘግቧል፡፡ ያላግባብ የታሰሩ ዜጎች እንዲፈቱም ጠይቋል፡፡ ምላሽ ካልተገኘ፣ መጠነ ሰፊ የሕዝብ ፊርማ ድጋፍ እናሰባስባለን ሲል አክሏል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የባህርዳርና አካባቢዋ ፍርድቤት የእነ ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ለማየት ለመስከረም 27 ቀጠረ። የዛሬው ችሎት በዝግ የታየ ሲሆን፣ ችሎቱን ለመታደም የተገኘው ህዝብ በፍርድቤቱ ድርጊት አንጻር ተቃውሞውን አሰምቷል።
Via Ethiopia live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
Via Ethiopia live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
#FakeNewsAlert
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ሰራተኞች የእድገት መሰላልና የደሞዝ ስኬል ማሻሻያ ተደረገ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
Via Elias Meseret