YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሴቶች አልባሣት እና ኮስሞቲክስ ማዘዝ ምትፈልጉ ገፃችን ላይ ያገኛሉ ከታች ባለው ሊንክ መርጠው ይላኩልን

የአውሮፓ ስታዳርድ
Imported from England
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFW3ZmuRfJiwNyWX7g
ኒውዮርክ ታይምስ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎችን ጠቅሶ ያወጣው ዘገባ:

"የኢትዮጵያው ገዢ ፓርቲ የሶሻል ሚድያ ንግግሮች ራሱን እንዲደግፉ ለማድረግ ሰዎችን ቀጥሮ ያሰራል/ያሰራ ነበር።"

Via:- elias meseret
@YeneTube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክትን በይፋ አስጀመሩ።በቻይና መንግሥት ድጋፍ የሚገነባው የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።

ምንጭ:ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የሩስያ ልዑክ ጎንደርን እየጎበኘ ነው

የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክስርቲያን የውጪ ጉዳይ ኃላፊዎችና የሩሲያ የሚዲያ አባላትን ያካተተ የአገሪቱ ልዑክ ጎንደርን እና በውስጧ የሚገኙ ቅርሶችን እየጎበኙ ነው።
ዘጠኝ የሚደርሱት የልዑካን ቡድኑ አባላት ዛሬ ረፋድ ላይ ደብረ ብርሃን ሥላሴን እና የዓፄ ፋሲል አብያተ-መንግሥትን ጎብኝተዋል።

ለሁለት ቀናት በጎንደር ከተማ በሚኖራቸው ቆይታም የአብነት ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በኢትዮጵያ ብቸኛ የሆነውን የባታ ደብረ ኃይል ወደብረ ጥበብ ባሕታ ለማሪያም ካቴድራል የአቋቋም ትምህርት ቤትን ይጎበኛሉ፡፡
በጎንደር ከተማ የሚገኙ የመንበረ መድኃኒዓለም እና የቁስቋም ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያንንም እንደሚጎበኙ ታውቋል።

ምንጭ፡- አብመድ
@YeneTube @Fikerassefa
በአውሮፓውያኑ 2030 የሴት ልጅ ግርዛትን ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ከእስካሁኑ በሰባት እጥፍ ፍጥነት መስራት ያስፈልጋል ተባለ፡፡

አሁን ባለው ፍጥነት ግን ኢትዮጵያ በዘላቂ የልማት ግቦች የሴት ልጅ ግርዛትን በ2030 ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት ያቀደችውን ማሳካት እንደማትችል ተነግሯል፡፡

አምሬስ ኸልዝ አፍሪካ ድንበር ተሻጋሪ የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቆም በአምስት የምስራቅ አፍሪካ አገራት መካከል የተገባውን ቃል ኪዳን አስመልክቶ ከባለድርሻዎች ጋር እየተወያየ ነው፡፡
በውይይቱ የተገኙት የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ ኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቆም የተገባውን ቃል ኪዳን ለመፈፀም እየሰራች ነው ብለዋል፡፡

ይሁንና ከአንዱ አገር ወደ ሌላው እየተዘዋወሩ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት የሚፈፅሙትን ለማስቆም በርካታ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

ኬኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ታንዛኒያና ኢትዮጵያ ስምምነቱን ፈራሚ አገራት ሲሆኑ ኬኒያ ዋነኛዋ የድንበር ተሻጋሪ የሴት ልጅ ግርዛት የሚፈፀምባት አገር መሆኗ ተጠቅሷል፡፡
ከአራቱ የምስራቅ አፍሪካ አገራት በርካቶች ወደ ኬኒያ በመሄድ የሴት ልጅ ግርዛትን ይፈፅማሉ ተብሏል፡፡

የአገራቱ የህግና የቁጥጥር ሁኔታ የተለያየ መሆን፣ የዋጋ ዝቅተኝነትና ሌሎች ምክንያቶች ለድንበር ተሻጋሪ የሴት ልጅ ግርዛት መበራከት ምክንያት መሆናቸው ተነግሯል፡፡

በተለይም በአገራቸው ድርጊቱን መፈፀም የሚያስከትለውን ህጋዊ እርምጃ በመሸሽ ኬኒያን የሚጎበኙት ቁጥር በርካታ ናቸውም ተብሏል፡፡
በአምስቱ የምስራቅ አፍሪካ አገራት ከ48 ሚሊዮን በላይ ሴቶች በተለያየ ጊዜ የሴት ልጅ ግርዛት የተፈፀመባቸው ናቸው መባሉን ከውይይቱ ሰምተናል፡፡

Via:- Shager FM
@YeneTube @Fikerassefa
ጅቡቲ ወደብ ላይ ተከማችቶ ለመንፈቅ ያህል ፀሀይ ሲፈራረቅበት የቆየው ከውጭ ተገዝቶ የመጣ ስንዴ በቅርቡ ወደ ሃገር እንዲገባ ስምምነት ላይ መደረሱ ተሰማ፡፡

የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ድርጅትም ለማጓጓዣ መኪና ለመመደብ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡ለገበያ ማረጋጊያ የተገዛው ስንዴ አንዴ የማጓጓዣ ችግር አለ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ነቀዝ ታይቶበታል በሚል ሰበብ ከፍተኛ ሙቀት ባለበት የጅቡቲ ወደብ ላይ ተከማችቶ ፀሀይ ሲቀጠቅጠው መክረሙን ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል፡፡አሁን ወደብ ላይ የቀረው 2 ሺህ 300 ሜትሪክ ቶን ስንዴ ነቀዝ ታይቶበት ከሆነ በድጋሜ ታክሞ በቅርቡ ወደ ሃገር እንዲገባ በገዥው በኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ድርጅትና ከውጭ ባስገባው በፕሮሚሲንግ ኢንተርናሽናል መካከል ስምምነት ላይ መደረሱን ከሁለቱም ወገን ሸገር አረጋግጧል፡፡

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
ከቦሌ መስቀል አደባባይ ወደ የሚወስደው መንገድ ፍላሚንጎ አከባቢ ( ኢግዚብሽን ማዕከል ጀርባ) እሳት አደጋ ተነስቷል አሁን እሳት አደጋ መኪኖች ደርሰዋል ለማጥፍት እየተረባረቡ ነው።

እንዲሁም እየጣለ ያለው ዝናብ እያገዛቸው ይገኛል።

📌ምን ያህል ውድመት አስከተለ የሚለሁን የሚመለከተውን አካል አናግረን እንቀርባለን።

Via:- Ab Kaza #YeneTube
@YeneTube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
የሴቶች አልባሣት እና ኮስሞቲክስ ማዘዝ ምትፈልጉ ገፃችን ላይ ያገኛሉ ከታች ባለው ሊንክ መርጠው ይላኩልን

የአውሮፓ ስታዳርድ
Imported from England
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFW3ZmuRfJiwNyWX7g
የአዲስ አበባ አስተዳደር በከባድ ጭነት ተሸከርካሪዎች በከተማዋ እንዳይንቀሳቀሱ ጥሎት የነበረውን ማሻሻሉን ካፒታል አስነብቧል፡፡ ማንኛውም የጭነት መጠን ያለው የጭነት ተሸከርካሪዎች ቅዳሜ ቅዳሜ በቀን ብቻ እንዲንቀሳቀሱ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ የትራፊክ ፍሰትን ለመቀነስ ሲባል አስተዳደሩ እገዳውን የጣለው በሐምሌ ነበር፡፡

-ዋዜማ
@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የጥብቅና ፈቃድ መስጫ ፈተና የለመፈተን ምዝገባ ጊዜ ማራዘሙን ከላይ በፎቶ በሚታየው ማስታወቂያ አሳውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የፑሽኪን አደባባይ ጎፋ ማዞሪያ -ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታን በዛሬ መስከረም 20/2012 በይፋ አስጀምራል።

ፕሮጀክቱ 3 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ርዝመትና ከ30 እስከ 45 ሜትር የሚሆን የጎን ስፋት ያለው ሲሆን የመንገድ ግንባታውን ቻይና ፈርስት ሀይ ዌይ ኢንጂነሪንግ የተባለ የስራ ተቋራጭ የሚያከናውነው መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ገልጿል።

@YeneTube @Fikerassefa
የወልድያ-ቆቦ መንገድ በደለል ምክንያት መዘጋቱ ተገለፀ!

ከወልዲያ ቆቦ የሚወስደው ዋና የአስፓልት መንገድ በጎርፍ ምክንያት በተደጋጋሚ የሚዘጋ ነው። ዛሬም በጣለው ዝናብ ከቀላል እስከ ከባድ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ አልቻሉም። መንገዱ የተዘጋው ከተራራማ ቦታዎች የሚወርድ ደለልን መከላከል የሚያስችል ደጋፊ የግንብ አጥር ባለመኖሩ ነው። በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮምቦልቻ መንገድ ዝርጋታ ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ተስፋዬ ‹‹ችግር በተፈጠረባቸው አካባቢዎች የመንገድ ጠረጋ እየተከናወነ ነው፤ በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት ደግሞ ከሰባት ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ የጎርፍ መከላከያ ደጋፊ ግንብ ይሠራል›› ብለዋል፡፡ የጎርፍ መከላከያ ደጋፊ ግንቡ ከደሴ ዋጃ ያለውን መንገድም ተመሳሳይ ችግር እንዳይገጥመው ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የወልድያ ቆቦ መንገድ ከአዲስ አበባ በደሴ-ወልድያ-ቆቦ- መቀሌ የሚገባ ነው፡፡ መንገዱ ክልል ከክልል የሚያገናኝና በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የሚተዳደር ነው፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
የኢሬቻ በዓል ኤግዚቢሽንና ባዛር በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ትናንት ተከፍቷል።

በዚሁ የግብይት መርሃ ግብር ልዩ ልዩ አልባሳት ፣ መዋቢያ ባህላዊ ቁሳቁሶች ፣ ጌጣጌጦችና ሌሎችም ምርቶች ቀርበው ግብይት እየተካሄደ ይገኛል።
@YeneTube @Fikerassefa
የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ

በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢህአዴግና የኦዲፒ ሊቀ መንበር እና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የኦዲፒ ምክትል ሊቀ መንበርና የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀ መንበር አቶ ሌንጮ ለታን ጨምሮ በርካታ በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ተሳትፈዋል።

https://telegra.ph/Oromo-10-01
በአንዋር መስጅድ ዙርያ እሳት ተነስቶ የነበረ ሲሆን አሁን በቁጥጥር ስር መዋሉ ታውቋል!

Via Abdurahim Ahmed/Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
🤩🤩🤩🤩የምስራች 🤩🤩🤩

በአ.አ በቀላሉ የማይገኙ ፤ ወደ12ሺ ሰዓቶች እና ቦርሣዎች ለትዛዝ ፤ ከ 1ሺ በላይ እቃዎች በ እጃችን መርጠው ይዘዙን ወደ ክልልም እንልካለን
ከታች ባለው ሊንክ ይጎብኙን
👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAENXyUTam6WMV6_hmg
ዕረፍት ላይ የከረመው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመጭው ሰኞ ይከሰፈታል ሲሉ አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ መናገራቸውን ፋና ብሮድካስት ዘግቧል፡፡ ምክር ቤቱ በ5ኛ ዐመቱ፣ የሀገር ዐቀፍ ምርጫው እና ሕዝብና ቤቶች ቆጠራው በሕጉ መሠረት መከናዎናቸውን የመከታተል ሥራ ይጠብቀዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የጠ/ሚሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን መኖርያ ግቢ ውስጥ በቅርቡ ተከስቶ የነበረው ችግር ምንድን ነበር?ማረጋገጥ የቻልኩት ጉዳይ ቢኖር የዛሬ ሳምንት ማክሰኞ ለሊት ለእሮብ አጥቢያ ከለሊቱ 10:30 ላይ ግርግር ተፈጥሮ ነበር:

- ግቢው ውስጥ አራት መንግስት የመደባቸው ጥበቃዎች ነበሩ፣ ነገር ግን የወ/ሮ ጠይባ መኪና ተሰባብሮ በዛውም ላፕቶፕ እንደተወሰደ ተነግሮኛል። ነገር ግን ሁኔታው ዘረፋ ብቻ ይሁን ወይስ ሌላ በሀላፊዋ ላይ ያነጣጠረ እንደነበር ገና እየተጣራ ነው ተብሏል።

- አራቱ ጠባቂዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ተብሏል። ሌላው የተረዳሁት ነገር ይህ ሁኔታ ሲከሰት በግቢው ውስጥ አራት ሌሎች መኪናዎች እንደነበሩ እና ሰበራ እና ዘረፋ የተደረገበት ሀላፊዋ የሚጠቀሙበት መኪና ብቻ መሆኑን ነው።ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችም ከመኪናው ስር ትናንት እንደተገኙ ተነግሮኛል።

-Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa