"ይህንን ደንብ አንቀበለውም፣ ከፍርድ ቤት እገዳ ለማስወጣት ሂደት ላይ ነን" የራይድ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ሳምራዊት ፍቅሩ በትናንት ምሽቱ "
ልዩ መረጃ-- ከኤልያስ ጋር" ፕሮግራም ላይ ቀርባ ከተናገረችው
የአ/አ ትራንስፖርት ቢሮ አዲስ የኤሌክትሮኒክስ ታክሲ ስምሪት ህግ እንዳወጣ ትናንት አስታውቋል። በዚህም መሰረት አሽከርካሪዎች ወደታክሲ ስራ መሰማራት የሚችሉት በኮድ 1 ነው ብሏል። በተጨማሪም ቢጫ ወይም ሰማያዊ እና ነጭ የታክሲ ቀለም እንዲቀቡም ይደረጋል ብሏል። ለራይድ ድጋፍ እንዲሆን #IStandWithRide የሚል ሀሽታግ ትዊተር ላይ በስፋት ሼር እየተደረገ ነው፣ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አበበ አበባየሁ ጨምሮ። በዚህ ጉዳይ ላይ የራይድ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ሳምራዊትን በቀጥታ ስልክ አናግሬአት ነበር። ስትመልስም:
"ሲጀመር የትራንስፖርት ቢሮው ይህን መመሪያ ማውጣት ይችላል ወይ የሚለው ላይ ጥያቄ አለ፣ ምክንያቱም እኛ የቴክኖሎጂ ድርጅት ስለሆንን የሚመለከተው የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ነው። በእኛ እምነት የትራንስፖርት ቢሮው ይህ ስልጣን የለውም። ሲቀጥል በRide ስር ከ 6,000 በላይ አባላት አሉ፣ የሚጎዱት እነዚህ ሰዎች ጭምር ናቸው። ይህ መመሪያ ሲወጣ እኛን ማሳተፍ ነበረበት። ሌላው ቀርቶ ረቂቁን እንኳን አላየነውም። በአጠቃላይ ይህንን ደንብ አንቀበለውም፣ ከፍርድ ቤት እገዳ ለማስወጣት ሂደት ላይ ነን። በሌለ infrastructure አንድን ድርጅት እዚህ ማድረስ ቀላል አልነበረም። ይህንን ሁሉ ስራ ሰርተን እዚህ ስንደርስ appreciate መደረግ ነበረብን። በትራንስፖርት ቢሮ የተደረገው ግን እኛን የሚቃረን ነው።
እንደዚህ አይደረግም! ይህ ፈፅሞ መቆም ያለበት ነገር ነው። ይብቃ! ወጣቱ ይስራ! ሀገሪቱንም ያሳድግ! በዚህ አጋጣሚ ኢንጅነር ታከለ እና አቶ እንዳወቅ እየደገፉን ነው ያሉት። (የአ/አ ትራንስፖርት ቢሮው) ዶ/ር ሰለሞን ግን ትንሽ ቆም ብለው አስበው ከእኛ ጋር ቢሰሩ ጥሩ ነው። ብዙ ልምድ አለን። ምን አልባት ልምድ የላቸውም ብለው አስበው ከሆነ ተሳስተዋል።"
Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa

የባህር ዳር ቀጥታ የአበባ ጭነት አገልግሎት ተቋረጠ።
አምስት የአበባ አምራች ኩባንያዎች ከባህር ዳር ወደ ተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት በሳምንት ኹለት ቀናት 30 ቶን አበባ ለማቅረብ የሚያደርጉት የቀጥታ በረራ መቋረጡን የአበባ አምራች ኩባንያዎቹ አስታወቁ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራው የተቋረጠው አቅርቦቱ በመቀነሱ ነው ብሏል።የጣና ፍሎራ የእርሻ ልማት አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ ክንዳለም ፀጋዬ፣ የአበባ ልማቱ በዓመት 58 ሚሊዮን ዘንግ በማምረት ከ40 ሚሊዮን እስከ 48 ሚሊዮን ዘንግ ወደ ውጭ ሀገር በመላክ ከመቶ ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ እያስገባ መሆኑን ገልጸው፣ ይሁን እንጂ አምስት አበባ አምራች ድርጅቶች በሳምንት ኹለት ቀን 30 ቶን አበባ ለማቅረብ በተስማማነው መሰረት ሥራ ብንጀምርም ሦስቱ ድርጅቶች በገቡት ቃል መሰረት ማቅረብ ባለመቻላቸው የባህር ዳር ቀጥታ ጉዞው መቋረጡንና ይህም በድርጅቶቹ ላይ መስተጓጎል መፍጠሩን ተናግረዋል።
ምንጭ: አዲስ ማለዳ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የቀድሞ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ማህበር ተዎካዮችን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
የቀድሞ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ማህበር አባላት ካካበቱት ሙያ እና ልምድ አንፃር በቀጣይ በዘርፉ ሃገራዊ አቅም መሆን በሚችሉበት ጉዳዮች ዙሪያ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ጋር ተወያይተዋል።
#DPMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ማህበር አባላት ካካበቱት ሙያ እና ልምድ አንፃር በቀጣይ በዘርፉ ሃገራዊ አቅም መሆን በሚችሉበት ጉዳዮች ዙሪያ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ጋር ተወያይተዋል።
#DPMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
ቃና ቴሌቭዥን በአንድ ጉዳይ ሁለቴ ልከሰስ አይገባም አለ!
የሸማቾች ጥበቃ እና ውድድር ባለሥልጣን አስተዳደራዊ ችሎት ቃና ቴሌቪዥንን ጨምሮ ሶስት ተከሳሾች አሳሳች የጥርስ ሳሙና ማስታወቂያ አሰራጭተዋል በሚል ቅጣት መጣሉን ተከትሎ ድርጅቶቹ ለባለስጣኑ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኝ አሉ። አሳሳች ነው የተባለውን የጥርስ ማስታወቂያ ያዘጋጀው ቢ ሚዲያ እና አሰራጩ ቃና ‹‹ከዚህ ቀደም የብሮድካስት ባለስልጣን ማስታወቂያውን እንድናቆም ባዘዘን መሰረት አቁመናል ይህንን ጉዳይ የመመልከት ስልጣንም የብሮድካስት ባለስልጣን በመሆኑ የተወሰነው ውሳኔ አግባብነት የለውም›› ሲሉ አቤቱታቸውን አሰምተዋል።

የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ከቀናት በፊት ጋምቤላ ውስጥ የተገደሉትን 2 የእርዳታ አቅራቢ ድርጅት ሰራተኞችን በተመለከተ አፋጣኝ ፍትህ እንዲሰጣቸው አሳስቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በABH ላይ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ መልካም ሥም ከማንሳት እንዲቆጠብ እግድ ተጣለበት።
የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የኤ ቢ ኤች (ጥምረት ለተሻለ ጤና) ሰርቪስስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል አማካሪ ድርጅትን መልካም ሥም ከማንሳት እንዲቆጠብ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እግድ እንደጣለበት የመዝገብ ግልባጩ አስነብቧል፡፡በመዝገብ ቁጥር 241863 በ 02/01/2012 ዓ.ም የወጣው መዝገብ ግልባጭ እንደሚያመላክተው፤ ኤጀንሲው የአማካሪ ድርጅቱን መልካም ሥምና ዝናን በማንሳት ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጋር አያይዞ ለመገናኛ ብዙሃን ሲሰጥ የነበረው መረጃ አግባብነት የለውም።
ድርጊቱም በድርጅቱ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ኤጀንሲው የዚህ ዓይነት መሠል ተግባር እንዳይፈጽም ወይም የድርጅቱን መልካም ሥም ማንሳት እንዲያቆሙ የእግድ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ከሳሽ አማካሪ ድርጅቱ እንዲሁም ተከሳሾች ኤጀንሲውና አምስት የሥራ ኃላፊዎቹ የሆኑበት ይህ መዝገብ የግራ ቀኙን አቤቱታና ምላሽ እንደተስተናገደ አብራርቷል።
ምንጭ: ኢፕድ

❤1
በባሕር ዳር ከተማ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ተያዘ።
በባህር ዳር ከተማ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ መያዙን የአማራ ክልል አድማ ብተና 2ኛ ሻለቃ 1ኛ ሻምበል ምክትል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ታለማ ዳኛ አስታወቁ።ምክትል ኢንስፔክተሩ ለአብመድ እንደተናሩት በ20 ጆንያዎች የተቋጠረ 497 ሽጉጥ እና ወደ 46 ሺህ የሚገመት ጥይት በባሕር ዳር ከተማ ተይዟል።የጦር መሳሪያው ከብሔራዊ መረጃ ደህንነትና ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሠረት ከነዳጅ ጋር ተቀላቅሎ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ በገባ የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴ ውስጥ ሲጓጓዝ ነው የተያዘው።
ከትናንት ምሽት ጀምሮ በተደረገ ክትትልም መሳሪያው ባሕር ዳር ከተማ ጣና ክፍለ ከተማ መያዙን ተናግረዋል። አሽከርካሪው ለማምለጥ ሙከራ አድርጎ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ያስታወቁት ምክትል ኢንስፔክተር ታለማ፥ ነዳጁ ከባሕር ዳር አልፎ የሚሄድ እንደነበርና ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያውን ከቦቴው ለማውጣት የሚያገለግል ብረት በተሽከርካሪው ውስጥ መገኘቱን ገልጸዋል።በተያያዘ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በታች አርማጭሆ ወረዳ በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 3 ሺህ 555 የብሬን ጥይት ተይዟል።
ምንጭ: ፋና

ከንቲባዎችና ከፍተኛ የጸጥታ አካላት ታስረዋል!!
በኦሮሚያ ክልል በወለጋ፣ በጉጂና በቦረና እንዲሁም በአንዳንድ የሐረርጌ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ የኦነግ ታጣቂዎች እና ለታጣቂዎች ስንቅ እና መረጃ አቀብላችኋል የተባሉ በርካታ ግለሰቦች ተይዘው በምርመራ ላይ መሆናቸውን የክልሉ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ታዬ ደንደአ ለአዲስ ማለዳ አረጋገጡ።እንደታዬ ገለፃ፣ ተጠርጣሪዎችን የመያዝና የማሰር እንቅስቃሴዎች በክልሉ አንዳንድ ዞኖች እንደነበሩ ጠቅሰው፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ በተለይ በአራቱም የወለጋ ዞኖች እና በጉጂ የሚገኙ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ከንቲባዎችና ከፍተኛ የጸጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።

በኦሮሞ ባህል ማዕከል ለፎሎዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
የዘንድሮው የእሬቻ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅደመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የአባገዳዎች ህብረት አስታውቋል፡፡በተለይ በሆራ ፊንፊኔ የሚከበረው የእሬቻ በዓል በሰላም ና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲከበር ቄሮ ና ፎሌዎች ድርብ ሀላፊነት አለባቸው ነው የተባለው፡፡የአባ ገዳዎች ህብረት ክለለፎሌዎች፣ ለቄሮና ቀሬ በኦሮሞ ባህል ማዕከል ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡
Via OBN

ማስታወቂያ!!
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በ2012 ዓ.ም ትምህርት ዘመን በህክምና /Medicine/ ለመማር ያመለከታችሁ የፅሑፍ ፈተና የሚሰጠው እሁድ መስከረም 11, 2012 ዓ.ም ከ 3:00 ሰዓት ጀምሮ ሲሆን ፈተና የሚሰጥበት ቦታ በመድኃኒያለም መሰናዶ ትምህርት ቤት (ከሆስፒታሉ ከ300-350ሜተር ወደ አስኮ የሚወስደው መንገድ ላይ ያለ ትምህርት ቤት) እና ሆሊ ሰቪየር (ከሆስፒታሉ ከ200-250ሜትር ወደ አስኮ የሚወስደው መንገድ ላይ ያለ ትምህርት ቤት) ነው፡፡
📌 የተመደባችሁበትን ትምህርት ቤት እና የመፈተኛ ክፍል ለማወቅ በኮሌጁ ድረ-ገፅ https://sphmmc.edu.et እና በፌስቡክ facebook.com/sphmmc/ በመግባት ቅዳሜ 11, 2012 ዓ.ም ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
📌 ለፈተና የሚቀርብ አመልካች ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ወይም 12ኛ ክፍል የተፈተነበት/የተፈተነችበት ፎቶ ያለው የመፈተኛ ካርድ ይዞ መምጣት አለበት/አለባት፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ሪጅስትራር ጽሕፈት ቤት

ኢትዮ ቴሌኮም የሲ.ዲ.ኤም.ኤ አገልግሎት ሊያቆም ነው።
ኢትዮ ቴሌኮም የኢንተርኔት አገልግሎት ለመስጠት ሲጠቀምበት የነበረውን የሲ.ዲ.ኤም.ኤ ኔትወርክ የደንበኞቼን ፍላጎት አላሟላልኝም በማለት በሶስት አመት ውስጥ አገልግሎቱን ከገበያ ለማስወጣት እየሠራ እንደሚገኝ አስታወቀ።
የገመድ አልባ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የ2ጂ እና 3ጂ የኢንተርኔት አገልግሎትን ለማቅረብ የሚያገለግለው ሲ.ዲ.ኤም.ኤ ፍጥነት እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ተከትሎ በተንቀሳቃሽ ስልኮች እና የገመድ የኢንተርኔት አገልግሎት ይተካል ሲሉ የቴሌኮሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ጨረር አክሊሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም በሲ.ዲ.ኤም.ኤ የኔትወርክ መሰረተ ልማት ላይ ምንም ዓይነት ማስፋፊያ የማያደርግ መሆኑን ተከትሎ በሃገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የሲ.ዲ.ኤም.ኤ ተጠቃሚዎች ከአገልግሎት ጥራት ጋር በተያያዘ ችግር እንዳይገጥማቸው በማሰብ ነው በሂደት አገልግቱን ለማቆም የወሰነው።
Via:- AddisMaleda
@YeneTube @Fikerassefa

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተወካዮችና ከኢትዮጵያ እስልምና መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ጋር ዛሬ መስከረም 7 ቀን 2012 ጠዋት ተገናኝተው ተወያዩ:: አባላቱ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታይ እህትና ወንድሞቻቸውን ለማክበር ከመስቀል በዓል በፊት በሚደረግ ጽዳት ላይ ለመሳተፍ ያላቸውን ፍላጎት ገልፀዋል::
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል በወባ በሽታ የአምስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እንዳስታወቀው በወባ በሽታ የተያዙ ሰዎች የወባ በሽታ እንዳያዛቸው ባለማወቃቸው እና ወደ ሕክምና ጣቢያ ባለመድረሳቸው ለሕልፈት እየተዳረጉ ነው፤ በመረጃው መሠረትም የአምስት ሰዎች ሕይወት በወባ በሽታ ምክንያት አልፏል፡፡
የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የወባ በሽታ መርሀ ግብር አማካሪ አቶ ፀሐይ ተዋበ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ የወባ በሽታ ስርጭት ጎልቶ የሚታይባቸው ሁለት ወቅቶች አሉ፡፡ የበልግ ዝናብን ተከትሎ አነስተኛ የወባ ስርጭት ከሚያዝያ እስከ ሰኔ አጋማሽ ባሉት ወራት ውስጥ ይከሰታል፤ ዋናው የወባ በሽታ መስፋፊያ ወቅት ደግሞ የክረምቱን መውጣት ተከትሎ ከመስከረም እስከ ሕዳር መገባደጃ ባሉት ወራት ነው፡፡
Via AMMA

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ጥንታዊ ቤቶችን ለማደስ 10 ሚሊዮን ብር መመደቡን የከተማዋ የባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡ ከሚታደሱት ቤቶች መካከል የሸህ ሆጀሌ ቤተመንግስትና የአዲስ አበባ የመጀመሪያው ከንቲባ የወልደጻድቅ ጎሹ ጥንታዊ ቤት ተጠቃሽ ናቸው ተብሏል፡፡
@YeneTube @Fikerassefa
@YeneTube @Fikerassefa
መቀመጫውን ስዊዘርላንድ ያደረገው ‹‹ተስፋ አይ ኤል ጂ›› የተሰኘ ድርጅት በስዊዘርላንድ ‹‹ስታንዳርድ›› የቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ማዕከል በኢትዮጵያ የመገንባት እቅድ እንዳለው ይፋ አደረገ፡፡
‹‹ተስፋ አይ ኤል ጂ›› በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ጀማሪዎችን በተለያየ መልክ ለመደገፍ የሚያችለውን ስምምነት ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር ተፈራርሟል፡፡
ድርጅቱ በስዊዘርላንድ የቴክኖሎጂ ጀማሪዎችን የቴክኖሎጂ ሃሳቦቻቸውን ከመነሻ ጀምሮ ወደ ገበያ እስኪገቡ ድረስ የተለያዩ ድጋፎችን የሚያደርግ ነው፡፡
በኢትዮጵያም የቴክኖሎጂ ጀማሪዎች የፈጠራ ሃሳቦቻቸው እንዲዳብሩ የቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ስልጠና መስጠት፣ ለፈጠራ ባለሙያዎች ስራዎቻቸው ወደ ምርት እንዲገቡ የገንዘብ ድጋፍ የማድረግ፤ የንግድ እቅድ አሰራር ስልጠና እና የቴክኖሎጂ ልምድ ልውውጥ ማድረግ የስምምነቱ አካል ነው፡፡
ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክሎጂ ሚኒስት ዴኤታ ጀማል በከር እና ‹‹ተስፋ አይ ኤል ጂ›› ፕሬዝዳንት ዳዊት ተስፋየ ተፈራርመዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው ጀማል በከር ስምምነቱ የኢትዮጵያ መንግስት የያዘውን የቴክኖሎጂ ዘርፍ የስራ እድል ፈጠራን እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡
‹‹ተስፋ አይ ኤል ጂ›› የስዊዘርላንድ የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ከኢትዮጵያ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በማስተሳሰር በጋራ እንዲሰሩ የማድረግ እቅድ እንዳለውም ማስታወቁን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፡፡
ምንጭ:- EPA
@Yenetube @Fikerassefa

3 የከፍተኛ ደረጃ የማዕድን ማምረት ፈቃዶች ተሰጡ።
የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች የማዕድናት ፍለጋ ለማካሄድ ፈቃድ ለጠየቀውና የፈቃድ መውሰጃ መስፈርቶችን አሟልቶ ለቀረበው አባይ ኢንደስትሪ ልማት አክሲዮን ማኅበር 3 የከፍተኛ ደረጃ ማዕድን ማምረት ሰጥቷል፡፡ስምምነቱን በፈቃድ ሰጪው መ/ቤት በኩል የፈረሙት ክቡር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሲሆኑ በባለፈቃዶቹ በኩል ደግሞ የፈቃድ ወሳጅ ኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ናቸው፡፡ኩባንያው ፈቃድ ያገኘው በአማራ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ አካባቢዎች ሲሆን የከፍተኛ ደረጃ ሸክላ አፈር፣ የከፍተኛ ደረጃ ላይም ስቶን ማዕድን እንዲሁም የከፍተኛ ደረጃ የጅፕሰም ማዕድን ያመርታል፡፡
ምንጭ: የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር

የጣሊያን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዘረኝነትን ለመታገል ብቁ አለመሆኑ ተገለፀ!!
በጣሊያን ሴሪ ኤ ኢንትር ሚላን ከካግላሪ ጋር በነበረው ጨዋታ የካግላሪ ደጋፊዎች በሮሚዮ ሉካኩ ላይ የዘረኝነት ጥቃት ሰንዝረዋል በሚል የቀረበባቸዉን ክስ የጣሊያን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውድቅ አድርጎታል፡፡
የካግላሪ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች በሉካኩ ላይ የዘርኝነት ጥቃት ስለመሰንዘራቸው በቂ ማስረጃ አለማግኘቱን የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ የዳኝነት ክፍል አስታውቋል፡፡
በመሆኑም በደጋፊዎችም ሆነ በክለቡ ላይ ማንኛዉንም ቅጣት ለማስተላለፍ በቂ ማስረጃ አላገኘሁም ማለቱ ተሰምቷል፡፡
በእለቱ ጨዋታ የተወሰኑ የካግላሪ ደጋፊዎች የፕላስቲክ ጠርሙሶችን ወደ ሜዳ በመወርወራቸው ግን የ5 ሺህ ዩሮ ቅጣት መተላለፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በአውሮፓ የእግር ኳስ የፀረ ዘረኝነት ተቋም በበኩሉ ዉሳኔዉን ኢፍትሃዊና አለማዉን የሳተ በሚል ተቃዉሞታል፡፡
በጣሊያን እግር ኳስ ዘረኝነት ስር መስደዱን የገለፁት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ፒየራ ፓዋር የሀገሪቱ እግር ኳስም ሆነ የእግር ኳሱ የዳኝነት ስርዓት በስፖርቱ ያለዉን ዘረኝነት ለመታገል ብቁ አይደለም ብሏል፡፡
ለአብነትም በሊጉ በተደጋጋሚ በጥቁር ተጫዋቾቸ ላይ እየደረሰ ያለዉን የዘረኝነት ጥቃት ማቆም አለመቻሉን ጠቅሷል፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ

⬆️⬆️
ተማሪዎች ውጤታቸውን መሰረት በማድረግ የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን ማስተካከል እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️⬆️
ተማሪዎች ውጤታቸውን መሰረት በማድረግ የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን ማስተካከል እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በአፍሪካ ከሚገኙ ምርጥ አለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች 13ኛ ደረጃ ተሰጥቶታል።
ዩንቨርስቲው ይህን ደረጃ ያገኘው U.S. News and WORLD REPORT EDUCATION ከተባለ ተቋም ሲሆን በአካዳሚክ ጥናትና ምርምር ባስመዘገበው ውጤት እና በልሂቃን በተሰጠ ድምፅ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል።