YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
መንግስት በደቡብ አፍሪካ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አስፈለጊውን ጥበቃ እንዲያደርግላቸውም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ ጠይቀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ በኢትዮጵያ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር የሆኑትን Mr.Ndumiso Ndima Ntshinga ዛሬ ነሐሴ 30 ቀን 2011 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው አነጋግረዋል።
ክብርት ሚኒስትር ዴኤታ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያና በደቡብ አፍሪካ መካከል ያለውን የጠበቀ ታሪካዊ ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እየተስራ መሆኑን ገልጸዋል::ሰሞኑን ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ የሌሎች አፍሪካ አገር ዜጎች ላይ በደረሰው ጥቃትና የንብረት ዝርፊያ በእጅጉ ማዘናቸውን ገልጸዋል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ክቡር ፕሬዝደንት ሰርል ራማፎሳ ያስተላለፉት መልዕክት አበረታች መሆኑንና በጉዳዩ የተሳተፉ ጥፋተኞች ለህግ እንደሚቀርቡ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ምንጭ: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
@YeneTube @FikerAssefa
በጋምቤላ ክልል በዛሬው ዕለት ሁለት የግብረ-ሰናይ ድርጅት ሰራተኞች ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን የአይን እማኞች እና የክልሉ መንግሥት ሰራተኛ ተናገሩ።

በጋምቤላ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰራተኛ የሆኑ አንድ የአይን እማኝ እንዳሉት ሰራተኞቹ የተገደሉት “ዊኜል” ከተባለ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ለመድረስ ጥቂት ሲቀራቸው ነው። ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉት የተ.መ.ድ. ሰራተኛ «ዛሬ በኢታንግ መስመር ዊኜል ወደተባለ [መጠለያ] ሲሔዱ፤ ሁለት ግብረ-ሰናይ ድርጅት ሰራተኞች ተገድለዋል። እኛው ጋ የሚሰሩ የሌላ ተቋም ሰራተኞች ማለት ነው» ሲሉ ተናግረዋል።

አክሽን አጌይንስት ኸንገር (Action Against Hunger) የተባለ ዓለም አቀፍ ተቋም ተቀጣሪ ናቸው የተባሉት ሁለት ሰዎች «ወደ ኢታንግ ከሚወስደው መንገድ ተገንጥለው ወደ ስደተኞች መጠለያለው ለመግባት ወደ ስድስት ኪሎ ሜትር ሲቀራቸው» በታጣቂዎች መገደላቸውን የአይን እማኙ አብራርተዋል።የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪ ባለሙያ በበኩላቸው በአካባቢው አንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ንብረት የሆነ ተሽከርካሪ ጥቃት እንደተፈጸመበት አረጋግጠዋል።

«የሆነ መኪና መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት መኪና ተመቷል። አክሽን አጌይንስት ኸንገር የሚባል አለ። ሁለት ሰው ሞቷል» ያሉት የጋምቤላ ፕሬስ ሴክሬታሪ ባልደረባ አንድ አሽከርካሪ እና የመስክ ሰራተኛ መገደላቸውን ለዶይቼ ቬለው ዘጋቢ ዓለምነው መኮንን ተናግረዋል።“ዊኜል” የተባለው የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ኢታንግ ከተባለው የኑዌር ዞን ከተማ 6 ኪሎ ሜትር ያህል ይርቃል። በጋምቤላ ክልል ወደ 400 ሺሕ ገደማ ደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞች ይገኛሉ። በርካታ የግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ለስደተኞች እገዛ ለማቅረብ በአካባቢው ይንቀሳቀሳሉ።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ቡና ካሳዬ አራጌን የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የአዴፓ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል አመራሮችን ጨምሮ በየክልሉ ያሉ የፓርቲው የዞንና ወረዳ አደረጃጀት አመራሮች ለስብሰባ ወደ ባህር ዳር መጠራታቸውን ሰምተናል ስብሰባው መች እንደሚጀምርና የስብሰባው አጀንዳ ምን እንደሆነ መረጃ ስናገኝ እናቀርባለን።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ተጠባባቂ ዋና ጸሐፊ ተሰየመለት።

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትና ጸሐፊ በመሆን እያገለገሉ የነበሩት አቶ እንዳልካቸው ስሜ ኃላፊነታቸውን በመልቀቃቸው፣ የንግድ ምክር ቤቱ ቦርድ አቶ ውቤ መንግሥቱን በተጠባባቂ ዋና ጸሐፊነት መሰየሙ ተገለጸ፡፡ያልተጠበቀ ነው የተባለው የዋና ጸሐፊው የሥራ መልቀቂያ ጥያቄን አዎንታዊ መልስ ካገኘ በኋላ፣ የንግድ ምክር ቤቱ ቦርድ በአቶ እንዳልካቸው ምትክ አቶ ውቤን በተጠባባቂ ዋና ጸሐፊነት ሰይሟል፡፡ ተሰናባቹ ዋና ጸሐፊም ለአዲሱ ዋና ጸሐፊ ኃላፊነታቸውን ያስረክባሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡

ምንጭ:ሪፖርተር
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
HAPPY NEW YEAR!
RJ SHOES presents to you all the latest,variety and catchy brand shoes.
We have all kind of shoes for adults and kids with a fairly affordable price.
👉Adress:-Addis ababa(Gerji mebrat haile)
👉Phone:-+251900628132
:-+251911859997
👉We have a 2 days return policy.
👉Flexible Shoe order with Customers Desire.
👉Delivery to Regional distincts
👉We Are Trustworthy and Best suited for Customers wish.
To Join us on telegram click here👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAE3CCBtJE8NBy8ZShA
Forwarded from YeneTube
አሜሪካ ሰራሹ ተአምረኛው መድሀኒት አገራችን ገባ በ ቀናት ውስጥ ከ መላጣነት ወደ ማበጠሪያ ተጠቃሚነት ይዞራሉ
100% በተግባር የታየ ፀጉር እና ፂም ማሳደጊያ 🔽USA🇺🇸 አሁኑኑ ያናግሩን @Fabulousss
በተጨማሪም በተለያዩ አማራጮችየቀረቡ የዉፍረት መቀነሻ ቀበቶዎች, [Human hair ] +ለ እስፖርታዊ እንቅስቃሴ ገንቢ የሆኑ ፕሮቲኖች (protein shake), በተለያየ ምክንያት ለመጣ ጠባሳ ማጥፊያ የሚሆኑ ትሪትመንቶችን ከኛ ያገኛሉ፡፡
+251991203033
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEpoRsmLNv7NNj3K_g
Forwarded from HEY Online Market
🔶💻HP _Core_i5
Model : elitebook 840
Condition: excellent
Screen :14”
Hard disk : 1tera (1000gb)
Ram : 8gb
Battery: >3hrs - 5hrs
Price 11,900br

Contact US
0953964175
0925927457
0956111111
@HEYOnlinemarket
Forwarded from Brands
🤩🤩🤩🤩የምስራች 🤩🤩🤩

በአ.አ በቀላሉ የማይገኙ ፤ ወደ12ሺ ሰዓቶች እና ቦርሣዎች ለትዛዝ ፤ ከ 1ሺ በላይ እቃዎች በ እጃችን መርጠው ይዘዙን ወደ ክልልም እንልካለን
ከታች ባለው ሊንክ ይጎብኙን
👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAENXyUTam6WMV6_hmg
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በጠዋት ውሎው ከኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ተወካይ ከዲ/ን ዳንኤል ክብረት ጋር ተወያይቷል።

ከጥቂት እረፍት በኋላም ብፁአን አባቶች ለውሳኔ ተመልሰው ወደ ጉባኤው ገብተዋል።

- በአሁኑ ሰአትም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውይይት እያደረገ ይገኛል
@YeneTuve @FikerAssefa
ሚኒስቴሩ የወጪ ንግድ ኮንትራት ክህደት በሚፈጽሙ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ


የወጪ ንግድ ኮንትራት ክህደት በሚፈጽሙ ነጋዴዎች ላይ የንግድ ፈቃድ እስከ ማገድ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በ2012 በጀት ዓመት የወጪ ንግዱ የተሻለ ገቢ እንዲያስገኝ የሀገሪቱን አቅም መነሻ ያደረገ እቅድ ተዘጋጅቶ የቁጥጥርና አመራር ስርዓት ተዘርግቶለት እየተሰራ መሆኑን በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ ማስፋፊያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ተናግረዋል፡፡

በሚደረገው ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል በትክክል የተቀመጠውን ህጋዊ አሰራር ተከትለው የሚሰሩ ነጋዴዎችን በመለየትና በመደገፍ በህገ-ወጥ ተግባር ተሰማርተው በሚገኙ እና የገቡትን የኮንትራት ውል በሚክዱ ነጋዴዎች ላይ የንግድ ፈቃድ እስከ ማገድ የሚደርስ እርምጃ ይወሰዳልም ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር፣ ህገ-ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድን በመከላከል እንዲሁም የወጪ ንግድ ምርቶች የግብይት ማዕከላትን አሰራር በማቀላጠፍ ህጋዊ ለሆነው የንግዱ ማህበረሰብ ምቹ ሁኔታ ይፈጠራልም ብለዋል፡፡

አምባሳደር ምስጋኑ አያይዘውም በተለይ በአስገዳጅነት በምርት ገበያ የሚያልፉ ቡና፣ ሰሊጥ፣ ነጭ ቦሎቄ፣ ቀይ ቦሎቄ፣ አኩሪ አተር፣ ማሾ እና ኑግ ምርቶች የኮንትራት አስተዳደር ስርዓት ተዘርግቶላቸው ነጋዴዎች በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ በሚሆኑበት አሰራር ውስጥ እንዲያልፉ ይደረጋል ብለዋል፡፡

በወጪ ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች የገንዘብ ትርፍ ከማግኘት በተጨማሪ ለውጭ ምንዛሪ ግኝትና ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት የሚሰሩ መሆኑን አውቀው በታማኝነት መስራት አለባቸው ሲሉም ማሳሰባቸውን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
በሰባት ቀናት ብቻ የ840 ሰዎችን የዓይን ብርሃን መመለስ እንደተቻለ ተገለጸ፡፡

ለ 25ኛ ጊዜ በተደረገ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ከ16 ሺህ በላይ ሰዎች ማየት እንደቻሉ ተገልጿል፡፡በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና እየተሰጠ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ዓይነ ስውራን እንደሚኖሩ በዘርፉ ላይ የተሰራ ጥናት ያመላክታል፡፡ 3 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ የእይታ ደረጃቸው ዝቅተኛ እንደሆነ ነው ጥናቱ የሚያሳየው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉ ታክሞ መዳን በሚችል የዓይን ሞራ ግርዶሽ ምክንያት በሚፈጠር ዓይነ ስውርነት ብርሃናቸውን ያጡ ናቸው፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
የዓድዋ በዓልን በተመለከተ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ሰዎች እውቅና ሊሰጣቸው ነው

የአድዋ ድልን በሚመለከት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ለማንኛውም አገር ዜጎች እውቅና ሊሰጥ ነው። እውቅናና ሽልማት የሚሰጣቸው በአደዋ ድል በዓል ላይ መልካም ተግባር ላከናወኑ እና የድል በዓሉ ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ አስተዋጽዖ ላበረከቱ ሰዎች መሆኑ ተገለጸ፡፡

ቢአርሲ አስጎበኚ ድርጅት ዛሬ በእንጦጦ ተራራ ላይ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ለዓድዋ ድል በዓል አስተዋጽዖ ላበረከቱ ሰዎች እውቅና ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል።

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢሻው በላይ እንዳሉት አድዋ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላው ጥቁር ህዝቦች ድል በመሆኑ አድዋን ለመዘከር ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተሰባሰቡ ሰዎች በፈረስ ወደ አድዋ ያቀናሉ ብለዋል።

በአድዋ ድል የፈረሶች ውለታ አይዘነጋም ያሉት ዳይሬክተሩ ያንንም ለመዘከር ነው ጉዞው በፈረስ የሚደረገው ያሉት ሃላፊው የጥንት አባቶቻችንን ታሪክ ለማውሳትና የከፈሉትንም መስዋእትነት ለማሰብ ጉዞው በፈረስ እንዲሆን የተወሰነው ብለዋል።

የሽልማቱ ስለአድዋ ድል በዓል ማንኛውንም አይነት ተሳትፎ ያደረጉ የየትኛውም አገራት ሰዎች የሚበረከት ስጦታ መሆኑም ተነግሯል፡፡

Via:- EPA
@YeneTube @FikerAssefa
#Update

ደቡብ አፍሪካ ከቅርብ ወራት ወዲህ ተከታታይ የጥላቻ ጥቃቶችን እያስተናገደች ሲሆን፣ በዚህም ሳቢያ ከሳምንት በፊት የታክሲ አሽከርካሪ፣በመጋቢት ደግሞ በደርባን በሚገኙ የውጭ ዜጎች ሱቆች ላይ በተፈጸመ ጥቃት 3 ሰዎች ተገድለዋል።

#Southafrica #xenophobia
@YeneTube @FikerAssefa
ኤቶዮጵ በተሰኘው መፅሐፉ የምናውቀው ደራሲና ሐኪም ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ አዲስ የወጎችና ግጥሞች መፅሐፍ "አንድ ሐገር-ቢያ ቶኮ" ነገ ለአንባቢያን ይቀርባል!

መፅሐፉ ነገ ጷግሜ 1 ከ11 ሰኣት ጀምሮ በሐገር ፍቅር ቲያትር ቤት የሚመረቅ ሲሆን ዋጋው 100 ብር ብቻ ነው።
ከቅዳሜ ጀምሮ በሁሉም የአዲስ አበባ መፅሐፍት ቤቶችና አዟሪዎች እጅ ላይ ያገኙታል። መፅሐፉ የተወሰኑ እንግሊዘኛ ግጥሞችንም እንዳካተተ ገጣሚው አሳውቆኛል ሲል ኤልያስ መሰረት አስታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
60 ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች የአውሮፓ ኅብረት ነጻ የትምህርት ዕድል አገኙ።

አዲስ አበባ ኢዜአ ነሃሴ 30/2011 የአውሮፓ ኅብረት ለ60 ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች የኢራስመስ ሙንደስ ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጠ።በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት ልዑክ ዕድሉን ካገኙ ጥቂት ተማሪዎች ጋር በመሆን ዛሬ የመሸኛ መርኃ-ግብር በቅጥር ግቢው አዘጋጅቷል።ተማሪዎቹ ለመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተለያዩ 12 የአውሮፓ ኅብረት አገራት በመዘዋወር ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በተለያዩ የትምህርት መስኮች ይከታተላሉ።በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ተመራቂዎቹ ቢያንስ ሁለትና ሦስት አገራት በመዘዋወር የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉ ነው የተገለጸው።

ምንጭ :ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያውያን ሀገር አቀፍ ንቅናቄ (ኢሀን) «የኢትዮጵያ ሕዝብና የኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያሳስባቸው ሁሉ ለሽግግር መንግሥት መቋቋም» ግፊት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ።

ንቅናቄው በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ በሰጠው መግለጫ በኢትዮጵያ ላይ «ያንዣበበው ክፉ ድባብ ለመቀልበስ»፤ የአገሪቱን «ሕልውና ታድጎ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመሸጋገር ሁሉን አቀፍ የሽግግር መንግሥት ማቋቋም ቀዳሚ መፍትሔ ነው» ብሏል። የሽግግር መንግሥት መመስረት «ጣጣው ብዙ ነው። በፍላጎት ደረጃ ካላችሁ ያንን ነገር መፍጠር በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ እጅግ ከባድ እና ውስብስብ እንደሆነ እናምናለን» ያሉት የድርጅቱ ሊቀ-መንበር አቶ ይልቃል ጌትነት «ግን ሌላ ምርጫ የለም» ብለዋል።

ኢትዮጵያ ውስብስብ የጸጥታ፣ የፖለቲካ እና የኤኮኖሚ ችግሮች እንደገጠሟት የገለጸው ኢሀን «ተደራራቢ እና የሀገርን ሕልውና የሚፈታተኑ» ያላቸውን ችግሮች «በመፍረስ ላይ ባለው ኢሕአዴግ ብቻ ይፈታል ብሎ መዘናጋት ከባድ ሀገራዊ ስህተት» ይሆናል ብሏል። ችግሮቹን ለመፍታት የኢትዮጵያ መንግሥት «አስቸኳይ ሁሉን አቀፍ ሀገራዊ የውይይት መድረክ እንዲያመቻች» ንቅናቄው ጥሪ አቅርቧል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ቤተክህነት እንዲቋቋም አንፈቅድም ብሏል መባሉን አስተባበሉ፡፡

አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጉዳዩን አስመልክተው ለኦ ኤም ኤን በሰጡት አስተያየት፤ የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ቤተክህነት እንዲቋቋም አንፈቅድም ብሏል ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መሰረተቢስ ወሬ ነው ብለዋል፡፡አቶ ሽመልስ ሁለቱ ወገኖች ልዩነታቸውን በዉይይት እንዲፈቱ ነው የተናገርኩት ነው ያሉት፡፡

"የኦሮምያ ቤተ ክህነት የሚባለው የማይታሰብ ጉዳይ ነውና እኛም አንፈቅድም የሀገርን አንድነት የሚፈታተን ጉዳይ እንደመንግስት መቸውኑ ተቀባይነት አይኖረውም በማለት ዛሬ በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ መንግሥትን ወክለው እየተሳተፉ የሚገኙት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዚደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል” ሲል የEOTC TV ጋዜጠኛው ዲ/ን ኃይሉ ዘግቧል የተባለውን ምክትል ፕሬዝዳንቱ የማደናገሪያ ወሬ ነውም ብለዋል፡፡

መንግስት ለምን በሃይማኖት ጉዳይ ውስጥ ገብቶ በስብሰባ ላይ ተሳተፉ ተብለው ለተጠየቁ ጥያቄም መልስ ሲሰጡ በውይይቱ ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘው እንደሆነ ገልፀው፤ ምክረሀሳብ ከማቅረብ የዘለለ ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡
የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ቤተክህነት ለማቋቋም እየተንቀሳቀሱ ያሉት፤ ምእመናን በቋንቋቸው እንዲያመልኩ ላመስቻል ነው በማለት ይሞግታሉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የቤተክህነቱ መቋቋም በቤተክርስትያኗ ውስጥ ስር የሰደደ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ያስችላል ይላሉ፡፡አላማችን ሌላ ስኖዶስ ማቋቋም አይደለምም በማለት በተደጋጋም ተናግረዋል፡፡ይሁንና የቤተክህነቱን መቋቋም በአዎንታዊነት ያልተቀበሉ አካላት እርምጃውን ተቀውመዋል፡፡
ሁለቱ ወገኖች በጉዳዩ ላይ የሚሰጡትን አስተያየት ተከታትለን የሚናቀርብ ይሆናል፡፡

ምንጭ:OMN
@YeneTube @FikerAssefa
ደቡብ አፍሪካ በናይጄሪያ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ዘጋች።

ደቡብ አፍሪካ በናይጄሪያ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ለመዝጋት የተገደደችው በደቡብ አፍሪካ ናይጄሪያውያን ላይ እየደረሰ ባለው ጥቃት ምክንያት በናይጄሪያ ኤምባሲዋ ላይ የአፀፋ ጥቃት በመሰንዘሩ ነው።ባለፈው ሳምንት እሁድ የጀመረው በሌላ አፍሪካ ሃገራት ዜጎች ላይ ያነጣጠረው ጥቃት እስከ ዛሬዋ እለት ድረስ ቀጥሎ የብዙዎች ንብረት ተዘርፏል፤ ወድሟልም።የናይጀሪያ መንግሥት ጥቃቱን ያወገዘው ሲሆን የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም በበኩላቸው ድርጊቱ አሳፋሪ እንደሆነ ተናግረዋል።

ናሌዲ ፓንዶር “በውጭ ሀገራት ዜጎች ላይ እየደረሰ ባለው ጥቃት እንዲሁም በንብረታቸው መውደም ከፍተኛ ሀዘን ተሰምቶናል” ማለታቸውን የሀገሪቱ ሚዲያ ኤስኤቢሲ ዘግቧል።በናይጄሪያ መዲና አቡጃ የሚገኘውን የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ለመዝጋት የተገደዱት በኤምባሲው በሚሰሩ ሰራተኞች ላይ ማስፈራሪያና ዛቻ ከደረሰባቸው በኋላ እንደሆነ ሚኒስትሯ ለሮይተርስ ተናግረዋል።

ምንጭ፡ ቢቢሲ
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ጉባዔ ተቀምጧል፡፡ በጉባዔው የመንግሥት ሃላፊዎች መገኘታቸው ተሰምቷል፡፡ ጉባዔው በኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ነን ባሉ አካላት ላይ እንደሚወያይ ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሃፊ ትናንት ምሽት ለዋዜማ ተናግረዋል፡፡ አቡነ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን እስከወዲያኛው አትደግፋቸውም ብለዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ ከመንግሥት ጋር የሚኖራት ቀጣይ ግንኙነት እና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የደረሱባት ጥቃቶች እና የመንግሥት ምላሽም ጉባዔው መወያያ አጀንዳዎች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa