YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from YeneTube
@kiru04
+251 931607806
➡️የሌለን የለም ብቻ ነው!
JOIN 👇 ብለው ቤተሰብ ይሁኑ ። 👇

@onlinesaleandbuy
@onlinesaleandbuy
@onlinesaleandbuy

https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFBAc0Ri5bEWs7J4TQ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ፖሊስ ደበደበኝ ፤ አንገላታኝ የሚል አቤቱታ ቀርቦልን አያውቅም” የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር

ከትናንት በስቲያ አንድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ባልደረባ እጁ በካቴና የታሰረ ግለሰብን ሲደበድብ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማኅበራዊ ሚዲያ መሰራጨቱን ተከትሎ ብዙዎች በፖሊስ ስለደረሰባቸው ድብደባና እንግልት ገጠመኛቸውን እያጋሩ ነው። ቢቢሲ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዘላለም መንግስቴ ቀጣዮቹን ጥያቄዎች አንስቷል።

ቢቢሲ፡ ፖሊሶች የሕዝብ አገልጋይ ስለመሆናቸው ምን ዓይነት ስልጠና ነው የሚሰጣቸው?

አቶ ዘላለም፡ በዋናነት የስልጠና ችግር አይደለም። በዚህ ዓመት አዲስ ለውጡን ተከትሎ ለሁሉም ፖሊስ የአገልጋይነት ስልጠና ሰጥተናል። አገልጋይ የሆነ የፖሊስ ማኅበረሰብ ለመፍጠር፣ አገልግሎታችንም የፖሊስ ስምሪታችንም ሕዝብን የሚያገለግል፣ የሚያከብር፣ ፖሊስ የሚፈራ ሳይሆን የሚከበር እንዲሆን የሚያስችል ሰነድ ቀርጸን ያለንን ፖሊስ በሙሉ አሰልጥነናል። ከአንድም ሁለቴ፣ ሦስቴ። ይህንን ስልጠና እታች ኮሚኒቲ ፖሊስ ድረስ ጭምር አውርደነዋል።

ቢቢሲ፡ ስልጠናው የተሰጠው ለቀደሙት ፖሊሶች ጭምር ነው ለአዲሶች ብቻ?

አቶ ዘላለም፡ ለሁሉም ነው። አሁን ያለውን አመለካከት የሰው ፖሊስ የመፈራት፣ ፖሊስ ሲያይ ከመሸማቀቅ ስሜት እንዲወጣና ዜጎችን የምናገለግል፤ ለዚህም ቃለ መሀላ ፈጽመን፣ ይሄንን ዩኒፎርም ለብሰን የወጣን መሆናችንን እንዲገነዘቡት የሚያደርግ ስልጠና አዘጋጅተን እየሰጠን ነው። ነገር ግን በሽግግር ጊዜ ላይ መሆናችን ልብ ሊባል ይገባል። ትናንት የታየው ያልተገባ ተግባር ከአንዳንድ ፖሊሶች የግል ባህሪ የሚመነጭ ፤ ተቀባይነት የሌለው የግለሰቦች ችግር ነው። ልጆቹ አዲስ በመሆናቸው የአገልጋይነት ስሜት ገና ወደ ውስጣቸው ያልገባና ያልተቀበሉት ሊሆን ይችላል። በእነዚህ ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ወስደን የማጣራት ሥራ ጀምረናል። ይሄ እንጂ የፖሊስ የመዋቅሩ፣ የአስተሳሰብም፣ አጠቃላይ የአገልጋይነት ስሜትን ያለመቀበል ነገር አይደለም።

ቢቢሲ፡ ቀደም ካሉት ዓመታት ጀምሮ ያለው እውነታ ሰው ፖሊስ እኔን ሊጠብቀኝ፣ ሊያገለግለኝ ነው የተሰማራው ብሎ ሳይሆን ፖሊስ የመፍራት ነገር ነው ያለው። በፖሊሶች በኩልም አለቃህ ነኝ የምልህን ታደርጋለህ የሚል አመለካከት ነው ያለው። ይህን አመለካከት ለመቀየር ስልጠናው ምን ያህል ረድቷል ይላሉ?

አቶ ዘላለም፡ ሽግግሩ ገና አንድ ዓመት አልሞላውም። ያ አስተሳሰብ ረዥም ጊዜ የቆየ ነው። ከዛ አስተሳሰብ በአንድ ጊዜ ሁሉንም ነገር ጨርሶ ሁሉም ትክክለኛውን አመለካከት ይዞ ይወጣል ማለት በጣም ይከብዳል። ጊዜ የሚወስድ ነገር ነው ቢሆንም ግን ረዥምም ጊዜ ሳንወስድ በአጭር ጊዜ የምንቀይረው ነው የሚሆነው።

ቢቢሲ፡ ለእንደዚህ አይነት ተግባር ምን አይነት የሥነ ምግባር (ማረሚያ) ቅጣት ነው የሚወሰደው?

አቶ ዘላለም፡ የነገርኩሽ 'ጄነራል' [ጠቅለል ባለ መልኩ] ነው። በዚህ ዓመት ያጋጠመን ይህ ነው።

ቢቢሲ፡ እናንተ ወደ አመራር ከመጣችሁ በኋላ በአንድ አመት ውስጥ አጋጥሞ አያውቅም?

አቶ ዘላለም፡ በማኅበራዊ ሚዲያ ያልወጡ፣ እኛ እርምጃ የወሰድንባቸው የተለያዩ የዲሲፒሊን [የሥነ ምግባር] ግድፈቶች አሉ።

ቢቢሲ፡ ምን እርምጃ ተወሰደ?

አቶ ዘላለም፡ የተለያየ ነው። በወንጀል የሚሳተፍም ካለ እንደ ወንጀል መጠኑ በሕግ እንዲጠየቅ፣ የስነምግባር ችግር ያለበት እንዲሁም ሃላፊነቱን ያልተወጣም እንዲጠየቅ አድርገናል። ችግሮች ያየንባቸውን በየደረጃው ከላይ እስከታች የማስተካከያ እርምጃ ወስደናል።

ቢቢሲ፡ ተደብድቦ ወይም በፖሊስ በደል ደርሶበት ወደ እናንተ ለአቤቱታ መጥቶ የሚያውቅ ሰው አለ?

አቶ ዘላለም ፡ በፍጹም። ሪፖርት ካላችሁ ቢሯችን 24 ሰዓት ክፍት ነው። በተለይም ከፖሊስ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ የምንታገሰው ነገር የለም።

ቢቢሲ፡ በትላንቱ ድርጊት ላይ የተሳተፉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ባልደረቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ጉዳያቸው እየታየ መሆኑ ተሰምቷል። እውነት ነው?

አቶ ዘላለም፡ እርምጃ ወስደናል።

ቢቢሲ፡ የተወሰደው እርምጃ ምንድን ነው?

አቶ ዘላለም፡ የተለያየ እርምጃ አለ። ፖሊስ የውስጥ አሠራር አለው። አንድ የፖሊስ አባል ያልተገባ ድርጊት ሲፈጽም [የሚቀጣበት ደንብ] ሥርዐት አለው። የትኛውም መሥሪያ ቤት እንዳለው ማለት ነው። [ፖሊሶቹን] ከሥራ ውጪ አድርገን፣ ጉዳዩን በሕግ ጥላ ሥር እንዲያዝ አድርጎ የማጣራት ሥራ እየሠራን ነው።

ቢቢሲ፡ ስለዚህ ሁለቱ የፖሊስ ባልደረቦች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ናቸው ማለት ነው?
አቶ ዘላለም፡ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ፣ እንዲጣራና እንዲመረመር ውሳኔ ተሰጥቷል። ይህን የሚከታተሉ ከታች ያሉ የሥራ ኃላፊዎች አሉ። እነሱ የደረሱበትን ነገር በእኛ ፖሊስ ኮምኒኬሽን በኩል አቅርበናል። ይሄ ነው የተወሰደው እርምጃ።

ቢቢሲ፡ የፖሊስ ባልደረቦቹ ምን ዓይነት ቅጣት ሊጠብቃቸው ይችላል?

አቶ ዘላለም፡ ጥፋቱ እኮ ገና ይታያል የሚጣራ ነው። በፖሊስ ባልደረቦቹ ላይ የደረሰ ጉዳት ካለ ለምሳሌ አንደኛው ፖሊስ ተመቷል አብጧል የሚል ነገር አለ። ስለዚህ ፖሊሶቹ ወደዚህ የገቡት በስነምግባር ችግር ነው? የግለሰብ ችግር ነው ወይስ በእነሱ ላይ የተፈፀመ ጥቃት አለ? የሚሉት ነገሮች ሁሉ ታይቶ ነው ውሳኔ ላይ የሚደረሰው።

BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ሰላማችን የሁላችን ለሁላችን !!

የጥልቅና የረጅም ታሪክ ባለቤቷ ኢትዮጵያ ብዙ የሚነገርላት እሴተ ብዙ ሀገር ናት፡፡ የሰው ዘር መገኛ ከመሆኗም በላይ የአፍሪካውያን የእኩልነትና የነፃነት ተምሳሌት መሆኗም ከፍ ብሎ የሚጠቀስ ማንነቷ ነው፡፡ 


አያት ቅድመ አያቶቻችን ሀገሪቱ ሰላሟ ተጠብቆ በፍቅር፣በአንድነትና በአብሮነት ኖረው ታላላቅ ገድል የመስራታቸውን ያህል ይህ ትውልድም እንደትናንቱ ለሰላም፣ ለፍቅር፣ ለልማትና ለእኩልነት እጅ ለእጅ በመያያዝ ሌላ ገድል መድገም የግድ በሆነበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡ 


ተጨማሪ ለማንበብ 👇
https://telegra.ph/PeaceYeneTube-08-28
የጫት ማሳን ለጤና ጠቃሚ በሆኑ ሰብሎች ለመተካት እየተሰራ መሆኑ ታውቋል፡፡

በባሕር ዳር ከተማ አስተዳድር ለእርሻ ከሚውለው 15 ሺህ ሄክታር ውስጥ 1 ሺህ 300 ሄክታሩ በጫት የተሸፈነ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ⬇️
https://telegra.ph/Chaw-YeneTube-08-28
የ50 ዓመት ጓደኛሞቹ የ2 ሚሊየን ዶላር ሎተሪን ተጋርተዋል

ለ50 ዓመታት የዘለቀ ጓደኝነት ያላቸው ካናዳውያን የ2 ሚሊየን ዶላር የሎተሪ እጣን ለሁለት መጋራተቸው የብሪትሽ ኮሎምቢያ ሎተሪ አስተዳደር አስታውቋል።

ሱዛን ሁክ እና ማርታ ኤምሲካለም የተባሉ ካናዳውያን ጓደኛሞች ናቸው የሎተሪ እጣውን ለሁለት የተጋሩት።
በጀመመሪያ የሆነውን ማመን ተስኖን ነበር ያሉት ጓደኛሞቹ፥ ሁለቱም በጋራ የሎተሪ አሸናፊ መሆናቸው እንዳስደሰታቸው አስታውቀዋል።
ባገኙት ገንዘብም ኑሯቸውን ማመቻቸት እና የተለያ ጉዞዎችን በማድረግ ዓለምን የመጎብኘት እቀድ እንዳላቸው አስታውቀዋል።
ምንጭ፦ www.upi.com/Odd
@YeneTube @
መካኒሳ የሚገኘው የአዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካ በ750 ሚሊ ሊትር በሰዓት 9,000 ጠርሙሶች፣ በ330 ሚሊ ሊትር 11,000 ጠርሙሶች እንደሚያመርት ተናግረዋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
ለሐጅ የሄዱ ምዕመናንን ጨምሮ 180 ኢትዮጵያውያን በጂዳ በቁጥጥር ሥር ዋሉ።

ለሐጅ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ወደ መካ የተጓዙ ምዕመናንን ጨምሮ ለተጓዦች የምሥጋና አቀባበል ዝግጅት ያደረጉ 180 ኢትዮጵያውያን፣ ባለፈው ሳምንት በሳዑዲ ዓረቢያ ጂዳ ከተማ የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡በእንዲህ ዓይነት ሃይማኖታዊ ጉዞዎች ላይ መሰባሰብና ማመስገን የተለመደ መሆኑን በመጠቆም ክስተቱን ለሪፖርተር ያስረዱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ዮሐንስ ሸዴ፣ በሥፍራው የተሰባሰቡ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸውን ሰዎች ጨምሮ ሁሉም በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ በዕለቱ በጂዳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ጉዳዩን በመከታተል፣ 70 የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወዲያውኑ እንዲፈቱ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡ አሥር ያህል ተጓዦችና ሌሎች ታሳሪዎችም በተከታታይ ቀናት እንዲፈቱ መደረጋቸውንም አክለዋል፡፡‹‹እስከ 100 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን እስካሁን በቁጥጥር ሥር ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ፈቃድ የሌላቸው በመሆናቸው ከሳምንት በኋላ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ይደረጋል፤›› ሲሉ አቶ ዮሐንስ አስረድተዋል፡፡ከዚህ ውጪ ተጓዦችን ከነዋሪዎች ጋር ያገናኘው ስብሰባ ከማኅበራዊ ሚና የዘለለ ሌላ ዓላማ አልነበረውም ሲሉ አክለዋል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
#NewsAlert

ደቡብ ክልል ምክር ቤት አዲስ የክልል ፕሬዘዳንት ሊሾም ነው።

ደቡብ ክልል ምክር ቤት አርብ ነሐሴ 24/2011 በሚያካሒደው ስብሰባ ከሰኔ19/2010 ጀምሮ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙትን ሚሊዮን ማቲዎስን ከስልጣናቸው በማንሳት በሌላ አዲስ ርዕሰ መስተዳደር እንደሚተካ ረቡዕ ነሐሴ22/2011 የወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ በፊት ገፁ አስነብቧል። ሚሊዮን ማቲዎስ ከርዕሰ መስተዳደርነታቸው በመነሳትም የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የዲሞክራሲ ማዐእከል ምክትል አስተባባሪ ሆነው በሚንስትር ማዕረግ እንደሚያገለግሉ ተሰምቷል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ቦሌ ፍሬንድሺፕ ሆቴል ፊት ለፊት ያለ ባዶ ቦታ ላይ የተደራጁ ወጣቶች የመኪና ማቆሚያ አገልግሎት ይሰጣሉ። ቦታው ላይ መኪና አቁመው ሄደው ሲመለሱ መኪናቸው የተዘረፉ ሰዎች ቁጥር ግን እየጨመረ ነው። ጠንቀቅ በሉ!

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
ሻሸመኔ ⬆️
ወራዊ የማብራት ክፍያ ለመክፈል ብንሄድም በአግባቡ እያስተናገዱን አይደለም ሲሉ ለመክፈል የሄዱ ግለሰቦች ለየኔቲዩብ ጠቁመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ክልል ምክር ቤት አዲስ ፕሬዚዳንት ይሾማል!!

ከአሁን ቀደም የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉት #አቶ_መለስ_ዓለሙ፣ ለክልሉ ምክር ቤት በፕሬዚዳንትነት ሊሾሙ እንደሚችሉ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

አቶ መለስ በአሁኑ ወቅት በሚኒስትር ማዕረግ የኢሕአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ማዕከል ምክትል ዋና አስተባባሪ በመሆን በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ
https://telegra.ph/Debub-YeneTube-08-28
ከቱሪዝም የተገኘው ገቢ ቅናሽ አሳየ!!

በ2011 የበጀት ዓመት ኢትዮጵያን የጎበኙ ቱሪስቶች ቁጥር አንድ መቶ ሺህ ገደማ ቅናሽ በማሳየት 849 ሺህ ሆኖ መመዝገቡን እና ከእነዚህ ጎብኚዎች የተገኘውም ገቢ በአራት መቶ ሚሊዮን ዶላር ቀንሶ 3.1 ቢሊዮን ዶላር አንደሆነ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። በተጠናቀቀው ዓመት ይገኛል የተባለው የውጪ ምንዛሬ 5.1 ቢሊዮን ዶላር ቢሆንም ሚኒስቴር መሥርያ ቤቱ ማሳካት የቻለው ግን 62 በመቶ ብቻ ነው። በበጀት ዓመቱ 1.5 ሚሊዮን ገደማ ጎብኚዎችን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ከአጠቃላይ እቅዱ ከግማሽ በላይ አለመሳካቱን የሚኒስቴሩ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ተወካይ ታሪኩ ነጋሽ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
መንግሥት በፓርላማ እንዲፀድቅ የተደረገውን ዓለም አቀፍ የትምባሆ ኮንቬንሽን በመጣሱ ቅሬታ ቀረበበት።

መንግሥት ተስማምቶ የፈረመውንና በኋላም በፓርላማ ያፀደቀውን የዓለም የትምባሆ ቁጥጥር ኮንቬንሽንና ኮንቬንሽኑን ለማስፈጸም በፓርላማው የወጣውን የምግብና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ የሚጥስ ተግባር እየፈጸመ መሆኑን፣ የትምባሆ ቁጥጥር ተሟጋች የሲቪክ ተቋማት አስታወቀ፡፡ የሕግ ጥሰቱን በፈጸሙ የመንግሥት ተቋማት ላይም ወቀሳቸውን ሰንዝረዋል፡፡ የገቢዎች ሚኒስትር ለትምባሆ አምራች ድርጅቱ የሰጠው የፕላቲንየም የዕውቅና ሽልማት ትምባሆ አምርቶ መሸጥ መልካም ተግባርና አዋጭ ተደርጎ በማኅበረሰቡ ዘንድ እንዲቆጠር ያደረገ መሆኑን በመጥቀስ ድርጊቱን አውግዘዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ህገወጥ መድኃኒቶች፣ አደንዛዥ ዕፆችና አልሚ ምግቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ግምታቸው ከ208 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ ህገወጥ መድኃኒቶች፣ አደንዛዥ ዕፆችና አልሚ ምግቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡በኦሮሚያ እና በሱማሌ ክልል የጤና ተቆጣጣሪዎች በሱቆችና መድኃኒት ቤቶች ላይ በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ከ181,060 ብር በላይ የሚገመት ህገወጥ መድኃኒቶች፣ አደንዛዥ ዕፆችና አልሚ ምግቦች አገልግሎት ላይ ከመዋላቸው በፊት በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል፡፡

ምንጭ: ኢቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
አሜሪካ ሰራሹ ተአምረኛው መድሀኒት አገራችን ገባ በ ቀናት ውስጥ ከ መላጣነት ወደ ማበጠሪያ ተጠቃሚነት ይዞራሉ
100% በተግባር የታየ ፀጉር እና ፂም ማሳደጊያ 🔽USA🇺🇸 አሁኑኑ ያናግሩን @Fabulousss
በተጨማሪም በተለያዩ አማራጮችየቀረቡ የዉፍረት መቀነሻ ቀበቶዎች, [Human hair ] +ለ እስፖርታዊ እንቅስቃሴ ገንቢ የሆኑ ፕሮቲኖች (protein shake), በተለያየ ምክንያት ለመጣ ጠባሳ ማጥፊያ የሚሆኑ ትሪትመንቶችን ከኛ ያገኛሉ፡፡
+251991203033
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEpoRsmLNv7NNj3K_g
Forwarded from HEY Online Market
Iphone_7_( 32 GB)
#BigDiscount
Color : Rose gold
and Matte black
Storage: 32 GB
Price : # 9,999 birr

Contact us
0953964175
0925927457
0956111111
በጋምቤላ ፈቃድ የሌላቸው 11 የውጭ ኮሌጆች ተገኙ።

ከየት እንደመጡ ያልታወቁ 11 ሕገወጥ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በጋምቤላ ክልል ሲያስተምሩ እንደተደረሰባቸው፣ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ኤጀንሲው ከተለያዩ ግለሰቦች በደረሰው ጥቆማ መሠረት ወደ ክልሉ ተንቀሳቅሶ የለያቸው እነዚህ 11 ተቋማት በድኅረ ምረቃና በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ተማሪዎችን እየተቀበሉ እንደሚያስተምሩ ለሪፖርተር የገለጹት፣ የኤጀንሲው የኮሙዩኔኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ታረቀኝ ገረሱ ናቸው፡፡ከኤጀንሲው ፈቃድ ሳያገኙ ሊያስተምሩ የተገኙት 11 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በአገር ውስጥ የማይታወቁና እንግዳ መጠሪያ ያላቸውና ከውጭ የገቡ እንደሆኑ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

‹‹በተደጋጋሚ በደረሰን ጥቆማ መሠረት ለማጣራት ወደ ክልሉ ስናመራ የጠበቅነው አንድ ተቋም ብቻ ነበር፡፡ ስንደርስ ግን 11 ሆነው አገኘናቸው፡፡ በወቅቱ ምንም ማድረግ ስላልቻልን ለክልሉ መንግሥት ስለሁኔታው በማስረዳት የክልሉን ነዋሪዎች ከሕገወጦች እንዲጠብቅ ደብዳቤ ጻፍን፤›› የሚሉት አቶ ታረቀኝ፣ ለክልሉ ደብዳቤ ከተጻፈ ስድስት ወራት የተቆጠረ ቢሆንም ምንም ዓይነት ምላሽ ለኤጀንሲው አለመድረሱን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሄዱ 30ሺህ ዜጎች ህጋዊ ፍቃድ ተሰጣቸው!

ከዚህ ቀደም በህገ ወጥ መንገድ ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሄዱ 30ሺህ ኢትዮጵያውያን ባሉበት ሀገር ላይ ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ እንደተሰጣቸው የሰራተኛ ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴር መስርያቤቱ ዛሬ ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የመጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ባደረገው የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የሰራተኛ ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንዳሉት ከሀገራቱ ባለስልጣናት ጋር በተደረገ ግንኙነት መሰረት በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሄዱ 30ሺህ ዜጎች ህጋዊ ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል፡፡

እንደ ዶክተር ኤርጎጌ ገለፃ ከዚህ በፊት በሀገወጥ መንገድ ለሄዱት ዜጎች የተሰጠው ህጋዊ ፈቃድ ቢያስደስታቸውም ከዚህ በኋላ በሀገ ወጥ መንገድ ለሚሄዱ ዜጎች ምንም አይነት ምህረት እንደማይደረግና ሲያዙም ቀጥታ ወደ ሀገር ቤት እንደሚመለሱ ተናግረዋል፡፡

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
የዳይመንድ ሊግ ነገ በዙሪክ የመጀመሪያ 16 አሸናፊዎች ይሸልማል።

ነገ በስዊትዘርላንድ ዙሪክ ከተማ በሚደረገው የ1500 ሜትር የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ገንዘቤ ዲባባ እና ኔዘርላንዳዊቷ ሲፋን ሐሰን ይፎካከራሉ።

በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነችው ሲፋን በአንድ ማይል የተደረገ ውድድር በ4 ደቂቃ 12 ሰከንድ ከ33 ማይክሮ ሰከንድ ጨርሳ ክብረ ወሰን ማስመዝገቧ አይዘነጋም። በዳይመንድ ሊግ የማጠናቀቂያ ውድድር ሲፋን የበረታ ፉክክር የሚገጥማት ከገንዘቤ ዲባባ ነው።

ገንዘቤ የ1500 ሜትር ክብረ ወሰን ባለቤት ነች። ገንዘቤ በሮም በ1500 ሜትር የተካሔደውን ውድድር በ3 ደቂቃ 56 ሰከንድ ከ28 ማይክሮ ሰከንድ አሸናፊ መሆኗ አይዘነጋም።

ገንዘቤ እና ሲፋን በሞሮኮዋ ራባት ከተማ በተመሳሳይ ርቀት ተገናኝተው አስደናቂ ውድድር አድርገዋል። በወቅቱ ውድድሩን ገንዘቤ በአንደኝነት ስታጠናቅቅ ሲፋን በሁለተኝነት ጨርሳለች።


በነገው ዕለት ከሚደረጉ ውድድሮች መካከል ሰለሞን ባረጋ፣ ኃይሌ በቀለ እና ዮሚፍ ቀጀልቻ በ5000 ሜትር የሚያደርጉት አጓጊ ነው። ከዚህ ቀደም ባደረገው ውድድር 12 ደቂቃ 43 ሰከንድ 02 ማይክሮ ሰከንድ ውድድሩን ያጠናቀቀው ሰለሞን ባረጋ ከአገሩ ልጆች የሚያደርገውን ፉክክር በበላይነት ይጨርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

Via:- Dw
@YeneTube @FikerAssefa
ቺኩንጉንያ ወረርሽኝ በድሬዳዋ ችሎት እስከማስተጓጎል ደርሷል ተባለ።

የችኩንጉንያ በሽታ በወባ መሰል ትንኝ የሚዛመት ሲሆን የሰውነት መገጣጠሚያ አካልን ከአቅም በታች የማድረግና የአፍ ምሬት እንደሚፈጥር ይነገራል፡፡ ራስ ምታትና ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት የበሽታው ተጨማሪ ምልክቶች ናቸው፡፡

በድሬደዋ ከተማ በወረርሽኝ መልክ የተከሰተውን ይህ በሽታ እየተስፋፋ መምጣቱን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከድሬዳዋና አካባቢዋ ነዋሪዎች አረጋግጧል፡፡

ነዋሪዎቹ እንዳሉትም ለቫይረሱ ተጋላጭ በሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ ያተኮረ ሥራ እየተሰራ ቢሆንም ወረርሽኙ ከቀን ወደ ቀን እየተስፋፋ ነው ብለዋል።

በዚህ ወረርሽኝ የተጠቁ ዜጎች ቁጥር ከ15 ሺህ በላይ መድረሱ እየተገለጸ ይገኛል።

አወድ አህመድ የተባሉ የ07 ቀበሌ ነዋሪ እንደተናገሩት “ስርጭቱ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ነው የከተማው ጤና ቢሮ የመከላከያ መንገዶቹን በተመለከተ የሚሰጠው መረጃም አናሳ ነው” ብለዋል፡፡

“በከተማዋ ከ60 ዓመት በላይ ስኖር እንዲህ አይነቱን በሽታ አይቼ አላውቅም መንግስት አንድ ነገር ያድርግ” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

በህፃናት ላይ በስፋት ባይታይም በሌሎቹ የዕድሜ ክፍሎች ወረርሽኙ በስፋት እየተስተዋለ መሆኑንመ ተናግረዋል ነዋሪዎቹ፡፡

ወረርሽኙን ተከትሎ በከተማዋ ያልተስተጓጎለ የስራ ዘርፍ የለም የሚሉት ነዋሪዎቹ ዳኞችም በዚህ በሽታ ተጠቅተው ችሎት መስተጓጎሉን ሰምተናል፡፡

መንግስት ለበሽታው ተገቢው ትኩረት አልሰጠውም ያሉት ነዋሪዎቹ የችግሩን አሳሳቢነት ግምት ውስጥ -ና በቃ ሚኒሠትረ ትኩረት መስጠት አለበት በለዋለ፡፡

በከተማዋ ያሉ የጤና ተቋማት በዚህ ወረርሽኝ የተጠቁ ህመምተኞችን በመርዳት የተጠመዱ ሲሆን መረጃ ለብዙሃን መገናኛዎች እንዳትሰጡ ተብለናል በሚል ተጨማሪ መረጃዎችን ሊሰጡን አልቻሉም።

የከተማዋ ነዋሪዎች ላነሱት ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡን የከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ ሀላፊዎችን ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም መረጃ ሊሰጡን አልቻሉም።

Via:- Ethio FM
@YeneTube @FikerAsseda