ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ማጠቃለያ
ነብያችን”ﷺ” ወደ መካ ሲገቡ በካዕባህ የሚመለኩ 360 ጣዖታትን ሰባብረዋል፤ ያስቀሩት አንድም ጣዖት የለም፤ አል-ሐጀሩል አስወድ ከ 360 ጣዖታት መካከል ነበር የሚለው ዲስኩር የሚሽነሪዎች ቅጥፈት እንጂ የታሪክ ሆነ የሥነ-ቅርስ መረጃ የለም፤ ሐጀሩል አስወድ መጉዳትንና መጥቀምን የማይችልና የአላህን ቤት መዞር የሚጀመርበት መነሻ ነጥብ እንጂ አምልኮ የሚቀበል አይደለም። ይህንን ከሐዲስ መረዳት ይቻላል፦
ኢማም ቡሃሪ መጽሐፍ 25, ሐዲስ 83:
ዑመር ወደ ሃጀሩል አስወድ ቀረቦ ሳመውና፦ አውቃለው #አትጠቅምም #አትጎዳም ነብዩ”ﷺ” ሲስሙህ ባላይ ኖሮ አልስምህም ነበር።
عَنْ عُمَرَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّهُ جَاءَ إِلَى الْحَجَرِ الأَسْوَدِ فَقَبَّلَهُ، فَقَالَ إِنِّي أَعْلَمُ أَنَّكَ حَجَرٌ لاَ تَضُرُّ وَلاَ تَنْفَعُ، وَلَوْلاَ أَنِّي رَأَيْتُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يُقَبِّلُكَ مَا قَبَّلْتُكَ‏.‏

ሃጀሩል አስወድ መስማት፣ መናገር፣ ማየት፣ ማወቅ የማይችል ህያው ያልሆነው ነገር ነውና አይጠቅምም አይጎዳም፣ የማይጠቅምና የማይጎዳ ነገር አይመለክም፤ የሚመለከው መጥቀና መጉዳት የሚችለው የሰማያትና የምድር ጌታ ብቻ ነው፦
13:16 የሰማያትና የምድር ጌታ ማን ነው? በላቸው፤ አላህ ነው በል፤ #ለነፍሶቻቸው #ጥቅምንም #ጉዳትንም የማይችሉን ረዳቶች ከእርሱ ሌላ ያዛችሁን? በላቸው፤
19፥42ለአባቱ ባለ ጊዜ አስታውስ «አባቴ ሆይ! “የማይሰማን” እና “የማያይን” ከአንተም ምንንም “የማይጠቅምህን” ለምን ታመልካለህ?
19፥48 እናንተንም “ከአላህ” ሌላ “የምታመልኩትንም እርቃለሁ፤ ጌታዬንም አመልካለሁ፤ ጌታዬን በማምለክ የማፍር አለመኾኔን እከጅላለሁ፡፡

ከአላህ ሌላ የሚመለክ እንደሌለ ለማሳየት አላህ እራሱ በመጀመሪያ መደብ፦ “እኔንም ብቻ አምልኩኝ ” በማለት ይናገራል፦
29:56 እላንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፤ እኔንም ብቻ #አምልኩኝ فَاعْبُدُونِ ።

የፈጣሪ ሃቅ አምልኮ፣ መለማመን፣ ስለት መሳል፣ መስገድ ወዘተ ነው፤ ይህንን ሃቅ ከመሳም ጋር ማምታታት የለብንም፤ ሲጀመር “መሳም” የመውደድ መገለጫ እንጂ በራሱ መውደድ አይደለም፤ ምክንያቱም ሳንስማቸው የምንወዳቸው ሰዎች ስላሉ፤ ሲቀጥል “መሳም” የፈጣሪ ሃቅ አይደለም፤ ፈጣሪ አይሳምምና፤ ሲሰልስ “መሳም” የፍጡራን መብት ነው፤ አንድ ሰው አባቱን ሳመ ማለት አመለከ ማለት አይደለም፤ አንድ ሰው በእግር ኳስ አሸንፎ ዋንጫ ቢስም አመለከ አይባልም፤ ለሃጅሩል አስወድ አምልኮ፣ መለማመን፣ ስለት መሳል፣ መስገድ ወዘተ ቢቀርብ ኖሮ ይህ ማሻረክ ወይም ባእድ አምልኮ ይሆን ነበር፤ ነገር ግን ይህ ፈፅሞ ሽርክ ነው፤ በኢስላም በድንጋይና በድንጋይ ላይ የሚደረግ አምልኮ “ኑሱብ” نُصُب እና “አዝላም” أَزْلَٰم ሲባል በአላህ ላይ ማሻረክ የሆነ አመፅ ነው፦
5:90 እላንተ ያመናችሁ ሆይ! የሚያሰክር መጠጥ፣ ቁማርም፣ “አንሳብ” وَالْأَنْصَابُ “አዝላምም”* بِالْأَزْلَامِ ከሰይጣን ሥራ የሆኑ እርኩስ ብቻ ናቸው፤ እርኩስን ራቁትም ልትድኑ ይከጀላልና።
5:3 ለኑሱብ” النُّصُبِ የታረደው *በአዝላምም* بِالْأَزْلَامِ ዕድልን መፈለጋችሁ በእናንተ ላይ እርም ተደረገ ይሃችሁ “አመፅ” ነው።

ወሒድ የንጽጽር ማህደር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ነጥብ ሁለት
“ኢሥባት”
“ኢሥባት” إثبات ማለት “ማፅደቅ” ሲሆን አውንታዊ ቃል ነው፤ ይህም አውንታዊ ቃል፦ “ኢለ ሏህ” إِلَّا اللَّهُ “ከአላህ በቀር” ብለን ስንል አንዱን አምላክ በብቸኝነትና በእውነት ልናመልከው የምናፀድቅበት ነው፤ አንዱ እምላክ አላህ ነገሮችን ካለመኖር ወደመኖር የፈጠረ፣ የሚያሞት ህያው የሚያደርግ፣ መጥቀምና መጉዳት የሚችል፣ ሁሉን የሚያውቅ፣ ሁሉን የሚያይ፣ ሁሉን የሚሰማና በእኔነት የሚናገር ነው፦
1. “ሁሉን የፈጠረ ነው”
46:4 #ከአላህ ሌላ የምታመልኳቸው አያችሁን? ከምድር ምንን እንደ #ፈጠሩ# አሳዩኝ ወይም በሰማያት ለእነርሱ መጋራት አላቸውን?
50:38 ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ #ፈጠርን፡፡
49:13 እላንተ ሰዎች ሆይ እኛ ከወንድና ከሴት #ፈጠርናችሁ፤ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፤

2. “የሚያሞት ህያው የሚያደርግ ነው”
30:40 አላህ ያ የፈጠራችሁ፣ ከዚያም ሲሳይን የሰጣችሁ፣ ከዚያም #የሚያሞታችሁ#፥ ከዚያም #ሕያው# የሚያደርጋችሁ ነው፤ ከምታጋሩዋቸው ጣዖታት ውስጥ ከዚኻችሁ አንዳችን የሚሠራ አልለን?
44:8 ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ #ሕያው ያደርጋል#፣ #ያሞታልም፣ ጌታችሁ፣ የመጀመሪያ አባቶቻችሁም ጌታ ነው።

3. “መጥቀምና መጉዳት የሚችል ነው”
20:89 ወደ እነነሱ ንግግርን የማይመልስ ለእነርሱም #ጉዳትንና #ጥቅምን የማይችል መሆኑን አያዩምን?
10:106 ከአላህም በቀር #የማይጠቅምንና #የማይጎዳን አታምልክ፡፡ ብትሠራም አንተ ያንጊዜ ከበደለኞቹ ትሆናለህ» ተብያለሁ” በላቸው፡፡
5:76 ከአላህ ሌላ ለእናንተ #መጉዳትንና #መጥቀምን የማይችልን ታመልካለህን? በላቸው፤

4. “ሁሉን የሚያውቅ ነው”
60:1 #እኔ የምትደብቁትንና የምትገልጹትን #የማውቅ ስሆን ወደ እነርሱ በፍቅር ትመሣጠራላችሁ፤
64:4 በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል፤ የምትደብቁትንም የምትገልጡትንም ያውቃል አላህ በልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነው።

5. “ሁሉ ተመልካች ነው”
34:11 #እኔ የምትሠሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነኝና።
57፥4 #አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው።

6. “ሁሉን የሚሰማ ነው”
2:186 ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ #እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በእኔም ይመኑ፤ እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡
9:103 ለእነርሱም ጸልይላቸዉ፤ ጸሎትህ ለእነርሱ እርካታ ነዉና አላህም “ሰሚ” ዐዋቂ ነው።

7. “እኔነት ያለው ተናጋሪ ነው”
21:92 “#እኔም” ጌታችሁ #ነኝ እና “አምልኩኝ”።
2:160 እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ #እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ #ነኝ፡፡

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም