ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
#ዋሂድ_የቤተክርስቲያን_ባለውለታ!

በ'ወንጌላዊ' አማን ገረመው
29/04/2013ዓ.ም
(የገና ስጦታዬ ነው)

(እባክዎን እስከመጨረሻው የማያነቡት ከሆነ አይጀምሩት)
++++++++++++++

የእስልምና ዘብና ጠበቃ ነን ከሚሉ የሀገራችን ሙስሊም አቃቢያን መካከል የሚመደብ ነው፡፡ -ዋሂድ ዑመር፡፡ የክርስትናን ገፅታ ያበላሻሉ ብሎ በማሰብ በተለያዩ ክርስቲያናዊ ርዕሶች ላይ በሚፅፋቸው ጽሑፎች በብዙዎቻችን ዘንድ የሚታወቀው ዋሂድ ከእርሱ በፊት እርሱ በተሰማራበት የጥብቅና አገልግሎት ከተሰማሩ የሀገራችን ሙስሊም ፀቃቤያን የሚለየው አንድ ነገር አለ፡፡ እርሱም፦ ከብዙዎቹ ሙስሊም ፀሀፊያንና ዐቃቢያን በተለየ መልኩ ለሙግቶቹ መፅሀፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፃፈባቸውን የግሪክና የዕብራይስጥ ቋንቋዎች እንደ ማስረጃ መጠቀሙ ነው፡፡

ይህ የዋሂድ አዲስ አካሄድ ደግሞ ለእኛ ለክርስቲያኖች አንድ ነገር ይነግረናል፡፡ ይኸውም የእስልምናው የዐቅብተ-እምነት አገልግሎት በአንድ ደረጃ ከፍ ማለቱን፡፡ ስለሆነም ከዚህ በኻላ መፅሀፍ ቅዱስን ብቻ ይዞ መንገድ ላይ መጮህ እንደ እብድ ያስቆጥር እንደሆን እንጂ ፍሬ የማፍራቱ ጉዳይ ግን ወደ አጠራጣሪ ደረጃ ያደገ ይመስላል፡፡ እንደከዚህ ቀደሙም በ'ኢየሱስ ያድናል!' ስብከት ብቻ 'የምንሸውደውም'(ትምህርተ-ጥቅስ ውስጥ ያስገባሁት ትክክል ባልሆነ መልኩ እንዳይተረጎም መሆኑ ይሰመርበት) ትውልድ እያለፈ የመጣ ይመስላል፡፡ እንዴት እንደሚያድንም የሚጠይቅ ትውልድ መጥቷልና፡፡

'ቲዮሎጂ መማር ደረቅ ያደርጋል!' ፤ 'በገለጠ ሳይሆን በመገለጥ ነው!' ፤ ........ ወዘተ የሚሉ ደናቁርት አገልጋዮቻችንም ገለባ ትምህርታቸው የሚፈተንበት ሰዓት በደጅ ያለ ይመስላል፡፡ ክርስትና ከጭፈራና ከጩኸት የሚላቀቅበት ጊዜም ላይ ደርሰናል፡፡ ቲዮሎጂ መማርም ወደአደጉት ሀገራት የመሄድን ያህል በሽሚያ የሚሆንበትም ሰዓት በቅርብ ሆኗል፡፡ ለወንጌል አገልግሎት የተቋቋሙ ድርጅቶችም(ministries) ቢሆኑ ዙሩ የከረረ መሆኑን ተገንዝበው በዕውቀት የሰለጠኑ አገልጋዮችን የማያፈሩ ከሆነና አሁንም በቀደመው አዙሪታቸው ለመሾር የሚፈቅዱ ከሆነ ያለምንም ጥርጥር የሚወድቁበት ጉድጓድ የተቆፈረላቸው መሆኑን የሚገነዘቡበት ሰዓት ላይ ደርሰናል፡፡

ምን እያልክ ነው? እያልኩ ያለሁትማ ግልጥ ነው፡፡ የእስልምናው ዐቅብተ-እምነት ዘምኗል ነው የምለው፡፡ እያልኩ ያለሁትማ ግልጥ ነው፡፡ ቤ/ክያን መፅሀፍ ቅዱስን ከማንበብ እልፍ ብሎ ግሪክና ዕብራይስጥ እየጠቀሰ የሚያስተምር ትውልድ እየመጣላት(ይቅርታ እየመጣባት) ነው እያልኩ ነው፡፡ እያልኩ ያለሁትማ ግልጥ ነው፡፡ቤ/ክያን ህንፃ ግንባታዋን ገታ አድርጋ ትውልድ ግንባታዋን ካልጀመረች ወደኻላ መቅረቷ የማይቀር ነው እያልኩ ነው፡፡ እያልኩ ያለሁትማ ግልጥ ነው፡፡ ቤ/ክያን ከእንቅልፏ ነቅታ ለዘመኑ የሚመጥን ትውልድ ካልገነባች ልጆቿ ሊበሉ ነው እያልኩ ነው፡፡ - ግልጥ ነው!!!
--------------------------------
ታዲያ ይህ እንዴት ሆኖ ነው ዋሂድን ባለውለታ የሚያሰኘው ነው ያላችሁኝ? ያሰኘዋል እንጂ!! ዋሂድማ ባለውለታችን ነው፡፡ እንዴት? ከሆነ ጥያቄያችሁ ደግሞ እነ ዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌና እነ ዘላለም መንግስቱን ጨምሮ ሌሎችም እነርሱን የመሠሉ ጥቂት የቤ/ክያን አገልጋዮች ጨጓራቸው እስኪላጥ ድረስ ወደ ቃሉ እንመለስ፣ ቤተስኪያን ለዐቅብተ-እምነት ትኩረት ትስጥ፣ ዝላዩ ይብቃን፣....ወዘተ ሲሉ ጆሮ አልሰጥ ያለችው ቤተስኪያን አሁን እድሜ ለዋሂድና ለተማሪዎቹ ሳትወድ በግዷ የምትሰማበት ጊዜ መጥቷል፡፡

በለብ ለብ ስብከት ተጠጋግነው የከረሙ ልጆቿ የግሪክ ዕውቀት የተቀመጡበት ሲናድ፣ የተጣፈ ክርስትናን የደረተው ምዕመን ለጥያቄው በቂ ምላሽ አጥቶ ማጣፊያው ሲያጥረው፣ መድረክ ያጣበበው መንጋ ቀስ በቀስ እየሰለመ ስፍራውን ሲለቅ፣ የአሸባሪዎች ዛቻ መቆሚያ መቀመጫ ሲያሳጣት፣.......ወዘተ ያኔ ዶክተርዬ ማረን? ዘልሽዬ ይቅር በለን? የምትልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡ በግዷ ትነቃለች፡፡ በሳር አልማር ብላለችና በአሳር ትማራለች፡፡

ስለሆነም ዋሂድ እግዚአብሄር እንደ ልምጭ እየተጠቀመበት ያለ ባለውለታችን ነው ማለት ነው(አራት ነጥብ)

@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@