ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.3K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ሥነ-ፅንስ

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

31:34 አላህ የሰዓቲቱ እውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው፤ ዝናምንም ያወርዳል፤ #በማሕፀኖችም #ውስጥ #ያለን #ሁሉ #ያውቃል

“ደረጃ ሁለት”
“ዐለቃ”
“ዐለቃ” عَلَقَة አንስታይ ሲሆን “ዐለቅ” عَلَق ደግሞ ተባእታይ ነው፤ ትርጉሙም “አልቅት”leech” ወይም “የረጋ ደም”blood-clot” ማለት ነው፤ ይህን የፅንስ ሁለተኛው ደረጃ ከሚታይ አልቅት ከሚባል የባህር ትል”insect” እና ከረጋ ደም ጋር ስለሚመሳሰል ነው፤ ወደዚህ ሂደት ለመምጣት በህዋሳት ውህደት ወቅት “ክሮሞሶም”Chromosomes” ከአንዱ ለጋሽ ወላጅ ወደሌላው ለጋሽ ወላጅ ይተላለፋል፤ እያንዳንዱ ተሣታፊ ህዋስ የለጋሾችን ግማሽ ክሮሞሶም ይይዛል፤ የአባት ክሮሞሶም ግማሽ 23% የእናት ክሮሞሶም 23% ተገናኛተው 46% ይዋሃዳሉ ማለት ነው፤ ተወራሽ የዘር ምልክቶች በምፃረ-ቃል “ዲ-ኤን-ኤ”(DNA) ወይም በዝርዝር “ዲኦክሲሪቦ ኒውክሊክ አሲድ”(deoxyribonucleic acid) በመባል በሚታወቀው በክሮሞሶሞች ውስጥ የሚገኝ ንጥረ-ነገር ውስጥ ሰፍረው ይገኛሉ። ክሮሞሶሞች “በጥንድ” ሆነው በሚገኙበት ጊዜ “ዳይፕሎይድ”(diploid) ይባላሉ፤ ክሮሞሶሞች በነጠላ ግዜ “ሃፕሎይድ”(haploid) ይባላሉ፤ በዚህ ሂደት አንድ ሴል የነበረው የወንድ የዘር ህዋስ ከሴት የእንቁላል ህዋስ ጋር ከተዋሐደ በኃላ 2, 4, 8, 16, 32, 64 እያለ በቲሪልየን ብዜት በ 21 ቀን የረጋ ደም”blood-clot” የሚለው ደረጃ ይጀምራል፤ ይህንን ደረጃ አምላካችን አላህ እንዲህ ይለናል፦
22:5 እላንተ ሰዎች ሆይ! ከመቀስቀስ፣ በመጠራጠር ዉስጥ እንደ ሆናችሁ አፈጣጠራችሁን ተመልከቱ፤ እኛም ከአፈር ፈጠርናችሁ ከዚያም ከፍቶት ጠብታ፣ ከዚያም “ከረጋ ደም” عَلَقَةٍ ፣ ከዚያም ከቁራጭ፣ ስጋ ፍጥረትዋ ሙሉ ከኾነችና ሙሉ ካልሆነች ችሎታችንን ለእናንተ ልንገልጽላችሁ ፈጠርናችሁ፤
40:67 እርሱ ያ ከአፈር፣ ከዚያም ከፍትወት ጠብታ፣ ከዚያም “ከረጋ ደም” عَلَقَةٍ፣ የፈጠራችሁ ነው።
96:1-2 አንብብ በዚያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም፤ ሰውን “ከረጋ ደም” عَلَقٍ በፈጠረው ጌታህ ስም።

ከፍትወት ህዋስ ወደ የረጋ ደም የሚሄድበት ሂደት እና ደረጃ ለማመልከት “ሱምመ” ثُمَّ “ከዚያም” የሚል መስተፃምር ይጠቀማል፤ ከዚህ ከተቀላቀለው የፍትወት ህዋስ ሁለት ዓይነቶችን ወንድና ሴትን ይመጣል፦
75፥36-39 ሰው ስድ ሆኖ መትተውን ይጠረጥራልን? የሚፈስስ ከሆነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን? “ከዚያም” ثُمَّ “የረጋ ደም” عَلَقَةً ሆነ፤ ሰው አድርጎ ፈጠረውም፤ አስተካከለውም። “ከእርሱም” ሁለት ዓይነቶችን “ወንድና ሴትን” አደረገ።

“የዘረ-መል ጥናት”(Genetic) እንደሚያስተነትነው የተባእት ክሮሞሶም ‘XY’ ሲሆን የእንስት ክሮሞሶም ደግሞ ‘XX’ ነው፤ ከወንድ ‘Y” መጥቶ ከሴት ‘X’ ከመጣ ሽሉ የአባቱን ፆታ በመያዝ ወንድ ይሆናል፤ ከወንድ ‘X” መጥቶ ከሴት ‘X’ ከመጣ ሽሉ የእናቱን ፆታ በመያዝ ሴት ይሆናል፤ ልብ አድርግ የወንድ ክሮሞሶም ‘XY’ ሲሆን የሴት ክሮሞሶም ደግሞ ‘XX’ መሆኑ ማለቴ ነው፤ የዘረ-መል ጥናት ይህንን ከማወቁ በፊት አላህ ለመልእክተኛው ይህንን የሩቅ ነገር ሚስጥር አሳውቋል፦
ኢማም ቡሃሪ መጽሐፍ 60 , ቁጥር 4 :
وَأَمَّا الشَّبَهُ فِي الْوَلَدِ فَإِنَّ الرَّجُلَ إِذَا غَشِيَ الْمَرْأَةَ فَسَبَقَهَا مَاؤُهُ كَانَ الشَّبَهُ لَهُ، وَإِذَا سَبَقَ مَاؤُهَا كَانَ الشَّبَهُ لَهَا ‏”‌‏.‏
የአላህ መልክተኛ አሉ፦ የልጆች ከወላጆቻቸው መመሳሰል እንዲህ ነው፤ ተባእት ከሚስቱ ጋር ተራክቦ ሲያደርግ የእርሱ ከተለቀቀ ህፃኑ እርሱን ይመስላል፤ የእንስት ከተለቀቀ ደግሞ ህፃኗ እርሷን ትመስላለች።

እውነት ነው፤ አላህም ከወንድ ክሮሞሶም ‘XY’ ወንድን እና ከሴት ክሮሞሶም ‘XX’ ደግሞ ሴትን በምድር ላይ ፈጥሮ የበተነ ነው፤ ይህም የሁለቱ አስተዋእፆ የአባት ክሮሞሶም ግማሽ 23% የእናት ክሮሞሶም 23% ተገናኛተው 46% ሲሆኑ ነው፦
4:1 እላንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ(ከአዳም) የፈጠራችሁን፣ ከእርስዋም መቀናጆዋን(ሔዋንን) የፈጠረውን፣ #ከእነርሱም ብዙ “ወንዶችን” እና “ሴቶችን” የበተነውን፣ ጌታችሁን ፍሩ።
49፥13 እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ “ከወንድ እና ከሴት ፈጠርናችሁ”፡፡ ኢንሻላህ ይቀጥላል…..

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም