ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነጥብ አንድ
“ነፍይ”
“ነፍይ” نفي ማለት “አፍራሽ” ሲሆን አሉታዊ ቃል ነው፤ ይህም አሉታዊ ቃል፦ “ላ ኢላሃ” لَا إِلَٰهَ “ሌላ አምላክ የለም” ብለን ስንል ማንኛውንም ጣኦታት ውድቅ የምናደርግበት ነው፤ በቁርአን ከአላህ ውጪ የሚደረግ ባዕድ አምልኮ “ጣኡት” لطَّاغُوتِ ፣ “አውሳን” أَوْثَٰن እና “አስናም” أَصْنَام ይባላሉ፣ “አውሳን” ማለት ከድንጋይ ተቀርፀው አምልኮ ለሚቀርብላቸው ሲሆን፤ “አስናም” ደግሞ ከእንጨት፣ ብር፣ ነሐስ ተሰርተው አምልኮ ለሚቀርብላቸው ነው። እነዚህ ጣኦታት ከዓለማቱ ጌታ ሌላ የሚመለኩ ምንነትና ማንነት ናቸው፤ እጅጉን ከዓለማቱ ጌታ ከአላህ ተለይተው ተቀምጧል፦
1. “ጣኡት”
2:256 #በጣዖትም لطَّاغُوتِ የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፡፡
4:76 እነዚያ ያመኑት ሰዎች፣ በአላህ መንገድ ይጋደላሉ፤ እነዛ የካዱትም #በጣዖት لطَّاغُوتِ መንገድ ይጋደላሉ፤
16:36 በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን አምልኩ #ጣዖትንም لطَّاغُوتِ ራቁ፤ በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፤

2.”አውሳን”
29:17 ከአላህ ሌላ የምታመልኩት #ጣዖታትን أَوْثَانًا ብቻ ነው፤ ውሸትንም ትቀጣጥፋላችሁ፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምታመልኩአቸው ለእናንተ ሲሳይን ሊሰጧችሁ አይችሉም፤
29:25 ኢብራሂም አለም፦ ከአላህ ሌላ #ጣዖታትን أَوْثَانًا አማልክት የያዛችሁት በቅርቢቱ ሕይወት በመካከላችሁ ለመዋደድ ብቻ ነው፤ ከዚያም በትንሣኤ ቀን ከፊላችሁ በከፊሉ ይክዳል፤ ከፊላችሁም ከፊሉን ይረግማል፤ መኖሪያችሁም እሳት ናት፤ ለእናንተም ከረዳቶች ምንም የላችሁም።

3. “አስናም”
6:74 ኢብራሒምም ለአባቱ ለአዘር «#ጣዖታትን أَصْنَامًا አማልክት አድርገህ ትይዛለህን እኔ አንተንም ሕዝቦችህንም በግልጽ መሳሳት ውስጥ ኾናችሁ አያችኋለሁ» ባለ ጊዜ አስታውስ.
21:57 በአላህም ስም እምላለሁ ዟሪዎች ሆናችሁ ከኼዳችሁ በኋላ #ጣዖቶቻችሁን أَصْنَامًا ተንኮል እሰራባቸዋለሁ፣ አለ።
14:35 ኢብራሂምም ባለ ጊዜ አስታውስ ፦ ጌታዬ ሆይ! ይህንን አገር ጸጥተኛ አድርገው፤ እኔንም ልጆቼንም #ጣዖታትን أَصْنَامًا ከማምለክ አርቀን፤

ነጥብ ሁለት
“ኢሥባት”
“ኢሥባት” إثبات ማለት “ማፅደቅ” ሲሆን አውንታዊ ቃል ነው፤ ይህም አውንታዊ ቃል፦ “ኢለ ሏህ” إِلَّا اللَّهُ “ከአላህ በቀር” ብለን ስንል አንዱን አምላክ በብቸኝነትና በእውነት ልናመልከው የምናፀድቅበት ነው፤ አንዱ እምላክ አላህ ነገሮችን ካለመኖር ወደመኖር የፈጠረ፣ የሚያሞት ህያው የሚያደርግ፣ መጥቀምና መጉዳት የሚችል፣ ሁሉን የሚያውቅ፣ ሁሉን የሚያይ፣ ሁሉን የሚሰማና በእኔነት የሚናገር ነው፦
1. “ሁሉን የፈጠረ ነው”
46:4 #ከአላህ ሌላ የምታመልኳቸው አያችሁን? ከምድር ምንን እንደ #ፈጠሩ# አሳዩኝ ወይም በሰማያት ለእነርሱ መጋራት አላቸውን?
50:38 ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ #ፈጠርን፡፡
49:13 እላንተ ሰዎች ሆይ እኛ ከወንድና ከሴት #ፈጠርናችሁ፤ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፤

2. “የሚያሞት ህያው የሚያደርግ ነው”
30:40 አላህ ያ የፈጠራችሁ፣ ከዚያም ሲሳይን የሰጣችሁ፣ ከዚያም #የሚያሞታችሁ#፥ ከዚያም #ሕያው# የሚያደርጋችሁ ነው፤ ከምታጋሩዋቸው ጣዖታት ውስጥ ከዚኻችሁ አንዳችን የሚሠራ አልለን?
44:8 ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ #ሕያው ያደርጋል#፣ #ያሞታልም፣ ጌታችሁ፣ የመጀመሪያ አባቶቻችሁም ጌታ ነው።

3. “መጥቀምና መጉዳት የሚችል ነው”
20:89 ወደ እነነሱ ንግግርን የማይመልስ ለእነርሱም #ጉዳትንና #ጥቅምን የማይችል መሆኑን አያዩምን?
10:106 ከአላህም በቀር #የማይጠቅምንና #የማይጎዳን አታምልክ፡፡ ብትሠራም አንተ ያንጊዜ ከበደለኞቹ ትሆናለህ» ተብያለሁ” በላቸው፡፡
5:76 ከአላህ ሌላ ለእናንተ #መጉዳትንና #መጥቀምን የማይችልን ታመልካለህን? በላቸው፤

4. “ሁሉን የሚያውቅ ነው”
60:1 #እኔ የምትደብቁትንና የምትገልጹትን #የማውቅ ስሆን ወደ እነርሱ በፍቅር ትመሣጠራላችሁ፤
64:4 በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል፤ የምትደብቁትንም የምትገልጡትንም ያውቃል አላህ በልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነው።

5. “ሁሉ ተመልካች ነው”
34:11 #እኔ የምትሠሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነኝና።
57፥4 #አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው።

6. “ሁሉን የሚሰማ ነው”
2:186 ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ #እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በእኔም ይመኑ፤ እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡
9:103 ለእነርሱም ጸልይላቸዉ፤ ጸሎትህ ለእነርሱ እርካታ ነዉና አላህም “ሰሚ” ዐዋቂ ነው።

7. “እኔነት ያለው ተናጋሪ ነው”
21:92 “#እኔም” ጌታችሁ #ነኝ እና “አምልኩኝ”።
2:160 እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ #እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ #ነኝ፡፡
አላህ እና ጣዖታት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

መግቢያ
አንድን እምነት ለማመን ቅድሚያ ስለዚያ እምነት በቂ እውቀት ይጠይቃል፤ በመሃይምነት እውር ድንብር የሆነ ፀለምተኛ እምነት መከልተል በኢስላም አይሰራም፦
17፥36 ለአንተም በእርሱ #እውቀት #የሌለህን ነገር #አትከተል

የእውቀት መጀመሪያ ደግሞ የፈጠረንን ፈጣሪያችንን ማወቅ ነው፤ በኢስላም የመጀመሪያው እርምጃ “ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩ” ማመን ሳይሆን “ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩን” ማወቅ ነው፦
47:19 እነሆ “ከአላህ ሌላ አምላክ” لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ አለመኖሩን #እወቅ

“ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ” لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ “ከአሏህ በቀር ሌላ አምላክ የለም” ማለት ነው፣ ጣኦታትን የምንክድበት፣ ከአላህ ሌላ በሃቅ ሊመለክ የሚችል አምላክ አለምኖሩን የምናምንበት ቃለ-ምስክርነት ነው፦
2:256 ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ፡፡ #በጣዖትም “የሚክድ” እና #በአላህ “የሚያምን” ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፡፡
39:17 እነዚያም #ጣዖትን “የሚያመልኳት” يَعْبُدُوهَا ከመሆን የራቁ ወደ #አላህም የዞሩ ለእነርሱ #ብስራት አላቸው፤ ስለዚህ ባሮቼን አብስር ።
43፥26-27 ኢብራሂምም ለአባቱ እና ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ “እኔ ከምታመልኩት ሁሉ #ንጹሕ ነኝ፤ ከዚያ #ከፈጠረኝ #በቀር #አላመልክም እርሱ በእርግጥ ይመራኛልና”።
16:36 በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ “#አላህን #አምልኩ #ጣዖትንም #ራቁ” በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፤

ይህ ቃለ-ምስክርነት በቁርአን “ጠንካራን ዘለበት” ይባላል፦
31:22 እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ ፊቱን وَجْهَهُ ወደ አላህ የሚሰጥም يُسْلِمْ ሰው፣ #ጠንካራ #ገመድ بِالْعُرْوَةِ በእርግጥ ጨበጠ፤ የነገሩም ሁሉ ፍጻሜ ወደ አላህ ነው።
2:256 በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን #ጠንካራ #ዘለበት بِالْعُرْوَةِ በእርግጥ ጨበጠ፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡

ይህ ቃለ-ምስክርነት ሁለት ማዕዘናት አለው፤ አንደኛው ነፍይ ሲሆን ሁለተኛ ኢሥባት ነው፤ ይህንን እሳቤ ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
“ነፍይ”
“ነፍይ” نفي ማለት “አፍራሽ” ሲሆን አሉታዊ ቃል ነው፤ ይህም አሉታዊ ቃል፦ “ላ ኢላሃ” لَا إِلَٰهَ “ሌላ አምላክ የለም” ብለን ስንል ማንኛውንም ጣኦታት ውድቅ የምናደርግበት ነው፤ በቁርአን ከአላህ ውጪ የሚደረግ ባዕድ አምልኮ “ጣኡት” لطَّاغُوتِ ፣ “አውሳን” أَوْثَٰن እና “አስናም” أَصْنَام ይባላሉ፣ “አውሳን” ማለት ከድንጋይ ተቀርፀው አምልኮ ለሚቀርብላቸው ሲሆን፤ “አስናም” ደግሞ ከእንጨት፣ ብር፣ ነሐስ ተሰርተው አምልኮ ለሚቀርብላቸው ነው። እነዚህ ጣኦታት ከዓለማቱ ጌታ ሌላ የሚመለኩ ምንነትና ማንነት ናቸው፤ እጅጉን ከዓለማቱ ጌታ ከአላህ ተለይተው ተቀምጧል፦
1. “ጣኡት”
2:256 #በጣዖትም لطَّاغُوتِ የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፡፡
4:76 እነዚያ ያመኑት ሰዎች፣ በአላህ መንገድ ይጋደላሉ፤ እነዛ የካዱትም #በጣዖት لطَّاغُوتِ መንገድ ይጋደላሉ፤
16:36 በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን አምልኩ #ጣዖትንም لطَّاغُوتِ ራቁ፤ በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፤

2.”አውሳን”
29:17 ከአላህ ሌላ የምታመልኩት #ጣዖታትን أَوْثَانًا ብቻ ነው፤ ውሸትንም ትቀጣጥፋላችሁ፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምታመልኩአቸው ለእናንተ ሲሳይን ሊሰጧችሁ አይችሉም፤
29:25 ኢብራሂም አለም፦ ከአላህ ሌላ #ጣዖታትን أَوْثَانًا አማልክት የያዛችሁት በቅርቢቱ ሕይወት በመካከላችሁ ለመዋደድ ብቻ ነው፤ ከዚያም በትንሣኤ ቀን ከፊላችሁ በከፊሉ ይክዳል፤ ከፊላችሁም ከፊሉን ይረግማል፤ መኖሪያችሁም እሳት ናት፤ ለእናንተም ከረዳቶች ምንም የላችሁም።

3. “አስናም”
6:74 ኢብራሒምም ለአባቱ ለአዘር «#ጣዖታትን أَصْنَامًا አማልክት አድርገህ ትይዛለህን እኔ አንተንም ሕዝቦችህንም በግልጽ መሳሳት ውስጥ ኾናችሁ አያችኋለሁ» ባለ ጊዜ አስታውስ.
21:57 በአላህም ስም እምላለሁ ዟሪዎች ሆናችሁ ከኼዳችሁ በኋላ #ጣዖቶቻችሁን أَصْنَامًا ተንኮል እሰራባቸዋለሁ፣ አለ።
14:35 ኢብራሂምም ባለ ጊዜ አስታውስ ፦ ጌታዬ ሆይ! ይህንን አገር ጸጥተኛ አድርገው፤ እኔንም ልጆቼንም #ጣዖታትን أَصْنَامًا ከማምለክ አርቀን፤
ጣዖት እና አምልኮ

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡

ነጥብ አንድ
“ጣኡት”
ከአላህ ውጪ የሚደረግ ማንኛውም ባዕድ አምልኮ “ጣጉት” لطَّاغُوتِ ይባላል። በተለይ ይህም ጣኡት በሁለት ይከፈላል፤ አንዱ “አውሳን” أَوْثَٰن ሲሆን ሁለተኛው “አስናም” أَصْنَام ነው፤ “አውሳን” ማለት ከድንጋይ ተቀርፀው አምልኮ ለሚቀርብላቸው ሲሆን፤ “አስናም” ደግሞ ከእንጨት፣ ብር፣ ነሐስ ተሰርተው አምልኮ ለሚቀርብላቸው ነው፤ እነዚህ ሁለቱም በቁርአን ተጠቅሰዋል፦
1.”አውሳን”
29:17 ከአላህ ሌላ የምታመልኩት #ጣዖታትን أَوْثَانًا ብቻ ነው፤ ውሸትንም ትቀጣጥፋላችሁ፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምታመልኩአቸው ለእናንተ ሲሳይን ሊሰጧችሁ አይችሉም፤
29:25 ኢብራሂም አለም፦ ከአላህ ሌላ #ጣዖታትን أَوْثَانًا አማልክት የያዛችሁት በቅርቢቱ ሕይወት በመካከላችሁ ለመዋደድ ብቻ ነው፤ ከዚያም በትንሣኤ ቀን ከፊላችሁ በከፊሉ ይክዳል፤ ከፊላችሁም ከፊሉን ይረግማል፤ መኖሪያችሁም እሳት ናት፤ ለእናንተም ከረዳቶች ምንም የላችሁም።

2. “አስናም”
6:74 ኢብራሒምም ለአባቱ ለአዘር «#ጣዖታትን أَصْنَامًا አማልክት አድርገህ ትይዛለህን እኔ አንተንም ሕዝቦችህንም በግልጽ መሳሳት ውስጥ ኾናችሁ አያችኋለሁ» ባለ ጊዜ አስታውስ.
21:57 በአላህም ስም እምላለሁ ዟሪዎች ሆናችሁ ከኼዳችሁ በኋላ #ጣዖቶቻችሁን أَصْنَامًا ተንኮል እሰራባቸዋለሁ፣ አለ።
14:35 ኢብራሂምም ባለ ጊዜ አስታውስ ፦ ጌታዬ ሆይ! ይህንን አገር ጸጥተኛ አድርገው፤ እኔንም ልጆቼንም #ጣዖታትን أَصْنَامًا ከማምለክ አርቀን፤

እነዚህ ጣኦታት ከዓለማቱ ጌታ ሌላ የሚመለኩ ምንነትና ማንነት ናቸው፤ እጅጉን ከዓለማቱ ጌታ ከአላህ ተለይተው ተቀምጧል፤ እነዚህን ጣዖታት የሚክድና አንዱን አምላክ አላህ በብቸኝነት ለማምለክ የሚያምን መልካም ዘለበትን ይጨብጣል፤ አላህ በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን አምልኩ ጣዖትንም ራቁ በማለት መልክተኛን ልኳል፦
2:256 #በጣዖትም لطَّاغُوتِ የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፡፡
4:76 እነዚያ ያመኑት ሰዎች፣ በአላህ መንገድ ይጋደላሉ፤ እነዛ የካዱትም #በጣዖት لطَّاغُوتِ መንገድ ይጋደላሉ፤
16:36 በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን አምልኩ #ጣዖትንም لطَّاغُوتِ ራቁ በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፤
39፥17 እነዚያም “#ጣዖታትን” ﺍﻟﻄَّﺎﻏُﻮﺕَ የሚግገዟት ከመሆን የራቁ ወደ አላህም የዞሩ ለነርሱ ብስራት አላቸው፤

የእነዚህ ጣዖታት እጣ ፋንታ የገሃነም ማገዶ መሆን ነው፦
21፥98 እናንተ ከአላህ ሌላ የምታመልኳቸውም የገሀነም ማገዶዎች ናቸው፡፡ እናንተ ለእርሷ ወራጆች ናችሁ إِنَّكُمْ وَمَا تَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ حَصَبُ جَهَنَّمَ أَنتُمْ لَهَا وَٰرِدُونَ ፡፡

“ኢነኩም” إِنَّكُمْ “እናንተ” የሚለው ሁለተኛ መደብ ላይ ያሉት ቀዳማይ ተደራስያን ቁረይሾች ሲሆኑ ከዓለማቱ ጌታ ከአላህ ሌላ የሚያመልኳቸው 360 ጣዖታትም የገሃነም ማገዶዎች ናቸው፤ “ማ” َمَا የሚለው አንፃራዊ ተውላጠ-ስም አቅል የሌላቸውን ተመላኪዎች ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፤ አቅል ያላቸውን ማንነቶች “መን” مَّن የሚል አንፃራዊ ተውላጠ-ስም የሚጠቀመው፤ ግን እዚህ አንቀፅ ላይ “ማ” የሚል አንፃራዊ ተውላጠ-ስም መጠቀሙ አቅል የሌላቸውን ተመላኪዎች ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፤ ይህ የሰዋስው ሙግት ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው። በተጨማሪም ሌላ አንቀፅ ላይ መቀጣጠያ ማገዶ ድንጋይ መሆናቸው ተገልጿል፦
66፥6 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ قُوٓا۟ أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًۭا وَقُودُهَا ٱلنَّاسُ
2፥24 ይህንን ባትሠሩ ፈጽሞም አትሠሩትምና ያችን *”መቀጣጠያዋ ሰዎችና ድንጋዮች”* የኾነችውን እሳት ተጠበቁ፤ ለከሓዲዎች ተደግሳለች፡፡ فَإِن لَّمْ تَفْعَلُوا۟ وَلَن تَفْعَلُوا۟ فَٱتَّقُوا۟ ٱلنَّارَ ٱلَّتِى وَقُودُهَا ٱلنَّاسُ وَٱلْحِجَارَةُ ۖ أُعِدَّتْ لِلْكَٰفِرِينَ