ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.3K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
2ኛ. ቀስ በቀስ በተለያየ ጊዜ" “ተርቲል” ترتيل
በመቀጠል ከሰማኢ ዱንያ ወደ ነቢያችን ቀልብ ቀስ በቀስ በጨረቃ አቆጣጠር ለ 23 ዓመት ወረደ፣ ይህ አወራረድ የሚጀምረው ከሱረቱል ዐለቅ 96.1-5 ሲሆን የሚጠናቀቅ ደግሞ በሱረቱል በቀራህ 2.281 ላይ ነው፣ ይህን አላህ ሲናገር፦
17:106 ቁርአንንም በሰዎች ላይ ሆነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፤ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው وَنَزَّلْنَاهُ ።
25:32 እነዚያ የካዱትም፦ ቁርአን በርሱ ላይ ለምን በጠቅላላ አንድ ጊዜ አልተወረደም? አሉ፤ እንደዚሁ በርሱ ልብህን ልናረጋ፣ ከፋፍለን አወረድነው ፤ ቀስ በቀስ መለያየትም ለየነው።
25:1ያ ፉርቃንን በባሪያው ላይ፣ ለዓለማት አስፈራሪ ይሆን ዘንድ፣ ያወረደው አምላክ ፣ ክብርና ጥራት ተገባው።
2:97 ለጂብሪል ጠላት የኾነ ሰው በቁጭት ይሙት በላቸው፡፡ እርሱ ቁርኣኑን ከበፊቱ ለነበሩት መጻሕፍት አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና፡፡

አወረድነው የሚለው ቃል "ነዝዘልናሁ" وَنَزَّلْنَاهُ ሲሆን ቀስ በቀስ መውረድን ፍንትውና ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፤ ይህ የስነ-ቋንቋ ሙግት ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው፤ ህም የሆነበት ምክንያት የሰዎችን ጥያቄና የአስተሳሰብ ደረጃ ዋቢ ያደረገ ነው፦
25:33 በጥያቄም አይመጡብህም እውነተኛውን መልስ፣ መልካምን ፍች የምናመጣልህ ብንኾን እንጅ።
2:189 ከለጋ ጨረቃዎች መለዋወጥ "ይጠየቁሃል"፡፡
5:4 ለርሱ ምን እንደተፈቀደላቸው ይጠይቁሃል፤ በላቸው፦
17:85 ከሩሕም ይጠይቁሃል፤
20:105 ከጋራዎችም ይጠይቁሃል፤ በላቸው፦
18:83 ከዙልቀርነይንም ይጠይቁሃል፤
7:187 ከሰአቲቱ መቼ እንደምትረጋ እንደምትመጣ ይጠይቁሃል፤
2:215 ምንን ለማንም እንደሚለግሱ ይጠይቁሃል፡፡
2:219 አእምሮን ከሚቃወም መጠጥና ከቁማር ይጠይቁሃል፡፡
2:220 ከየቲሞችም ይጠይቁሃል፡፡
2:222 ከወር አበባም ይጠይቁሃል፡፡

ማጠቃለያ
መጽሐፉ የሚነበብ ቃል እንጂ የተጻፈ ወረቀት እንዳልሆነ የምናውቀው አላህ ወደ ነብያችን”ﷺ” በወረቀት የተጻፈን መጽሐፍ አለማውረዱን መናገሩ ነው፦
6:7 በአንተም ላይ #በወረቀት #የተጻፈን #መጽሐፍ #ባወረድን እና #በእጆቻቸው #በነኩት #ኖሮ እነዚያ የካዱት ሰዎች «ይህ ግልጽ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም» ባሉ ነበር፡፡

በተጨማሪም በነብያችን”ﷺ” ልብ ላይ የወረደው ወረቀት ሳይሆን መነባነብ መሆኑ ነው፤ መቼም ወረቀት ልብ ላይ ይቀመጣል የሚል ቂል ካልሆነ በስተቀር ይኖራል ብዬ አላስብም፦
2:97 ለጂብሪል ጠላት የኾነ ሰው በቁጭት ይሙት በላቸው፡፡ እርሱ ቁርአኑን ከበፊቱ ለነበሩት አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን በአላህ ፈቃድ #በልብህ ላይ #አውርዶታልና፡፡
26:192-194 እርሱም ቁርአን በእርግጥ ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡ እርሱን ታማኙ መንፈስ አወረደው፤ ከአስጠንቃቂዎቹ ትኾን ዘንድ #በልብህ ላይ #አወረደው፡፡

ቁርአን ብዙ አንቀፆች ላይ “ኪታብ” كِتَٰبِى “መጽሐፍ” ተብሏል፤ ይህ ቁርአን “መጽሐፍ” የተባለው በብራና፣ በሰሌን፣ በስስ ድንጋይ፣ በሰሌዳ፣ በበግ አጥንት፣ በዘንባባ ቅርፊት ፣ በቴምር ቅጠል፣ በከብት ቆዳ በመሳሰሉት 40 በሚያክሉ በእነ አቡበከር፣ ኡመር፣ ኡስማን፣ አሊ፣ ዙበይር፣ ኡበይ፣ ሙአዊያህ፣ ዘይድ ኢብኑ ጣቢት በተፃፈ ጊዜ ሳይሆን ከዓለማቱ ጌታ በመውረዱ ነው፦
46:2 #የመጽሐፉ #መውረድ አሸናፊ ጥበበኛ ከሆነው አላህ ነው ::

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም