ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.9K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
አልተበረዘምን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

መግቢያ
ሚሽነሪዎች አምላካችን አላህ በተከበረው ቃሉ ስለራሱ በሶስተኛ መደብ “የአላህ ቃላት መለወጥ የላትም” ብሎ የሚናገረው ንግግር ለቀድሞቹ መጽሐፍት ላለመበረዝ ማስረጃ ነው ብለው መሪ ሙግት ሲያቀርቡ ለጊዜው የሚያስኬድ ቢመስልም አበሳና አሳር ውስጥ እራሳቸውን እያስገቡ መሆኑ እሙን ነው፤ ምክንያቱም የቀድሞ መጽሐፍት ለመለወጣቸው በዋዛ ፈዛዛ ሊታዩ ያማይቻሉ አንቀፆች ስላሉ፤ ለምሳሌ፦”የአላህን ቃል የሚሰሙና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ “”የሚለውጡት” ሲኾኑ” ይላልና፤ ይህንን መረጃ ሲያገኙ ደግሞ እንደ ግጭትና ተቃርኖ ለማየት ይሞክራሉ፤ እኛ የምንለው ሙሾና ፌሽታ አብረው አይሔዱም ነው፤ ግራም ነፈሰ ቀኝ ሲጀመር “መለወጥ” የሚለው ቃል ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ ሀሳብና ትርጉም አለው ማለት አይደለም፤ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጒም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው፤ ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው ሐሳብ መታየት ያለበት።
ሲቀጥል የቁርአን ቅኝት የሆነው የአረብኛው ቃል “ተህሪፍ” تحريف, እና “ተብዲል” تَبْدِيل የአማርኛችን ጥበት ሁለቱንም “መለወጥ” ይበለው እንጂ ስሜቱ አንድ አይነት አይደለም፤ ይህንን ለመረዳት ጉባኤ ሆነ ሱባኤ አያስፈልግም ወደ ቁርአኑ ዘው ብሎ መግባት ብቻ ነው፦
ነጥብ አንድ
“ተህሪፍ”
“ተህሪፍ” تحريف, ማለት “ብርዘት” ማለት ሲሆን በመለወጥ የሚደረግ ብርዘት ሲሆን ይህ ጉዳይ አላህ በቃሉ ይነግረናል፦
2:75 ከነሱ የኾኑ ጭፍሮች “የአላህን ቃል የሚሰሙና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ “የሚለውጡት” يُحَرِّفُونَهُ ሲኾኑ ለናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?
4:46 ከነዚያ ይሁዳውያን ከሆኑት ሰዎች “ንግግሮችን” ከሥፍራዎቹ “የሚለውጡ” يُحَرِّفُونَ አሉ፤
5:13 ቃልኪዳናቸውንም በማፍረሳቸው ረገምናቸው፤ ልቦቻቸውንም ደረቆች አደረግን፤ “ቃላትን” ከቦታዎቻቸው “ይለውጣሉ” يُحَرِّفُونَ ።

የመጸሐፉ ሰዎች አይሁድና ክርስቲያኖች ቃሉን የለወጡት የአላህ ቃልን ከሰው ቃል ጋር በመቀላቀል መጨመርና የአላህ ቃል በመደበቅ አፖክራፋ አድርጎ መቀነስ ነው፦
3:71 የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! “እዉነቱን በዉሸት” ለምን *ትቀላቅላላችሁ*? “እዉነቱንም” እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን *ትደብቃላችሁ*?

“እውነት” የተባለው ከአላህ የወረደው ኪታብ፦
34:48 ፦ጌታዬ “እውነትን” ያወርዳል፤ ሩቅ የኾኑትን ሚስጢሮች ሁሉ ዐዋቂ ነው በላቸው።

“ውሸት” የተባለው ደግሞ መጽሐፉን በእጆቻቸው ፅፈው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ብለው የቀጠፉት ጭማሬ ነው፦
2:79 ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው፡፡

የነቢያችን ቅርብ ባልደረባ ኢብኑ ዓባስ”ረ.አ.” የሱረቱል በቀራ 2:79 አንቀጽ ሲፈስረው፦
ኢማም ቡሃሪ ቅጽ 3, መጽሃፍ 48, ቁጥር 850:
ኢብኑ አባስ ሲናገር፦ ሙስሊሞች ሆይ ለምን የመጽሐፉ ሰዎችን ትጠይቃላችሁ? በተመሳሳይ መጽሐፋችሁ ከአላህ ዘንድ ለነቢዩ የተወረደው ወቅታቂ ንግግርና የምትቀሩት እያለ? መጽሐፋ አልተበረዘምን? አላህ ለእናንተ የመጽሐፉ ሰዎች በእጆቻቸው በርዘው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» እንደሚሉ አውርዷል።
حَدَّثَنَا يَحْيَى بْنُ بُكَيْرٍ، حَدَّثَنَا اللَّيْثُ، عَنْ يُونُسَ، عَنِ ابْنِ شِهَابٍ، عَنْ عُبَيْدِ اللَّهِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُتْبَةَ، عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ يَا مَعْشَرَ الْمُسْلِمِينَ، كَيْفَ تَسْأَلُونَ أَهْلَ الْكِتَابِ، وَكِتَابُكُمُ الَّذِي أُنْزِلَ عَلَى نَبِيِّهِ صلى الله عليه وسلم أَحْدَثُ الأَخْبَارِ بِاللَّهِ، تَقْرَءُونَهُ لَمْ يُشَبْ، وَقَدْ حَدَّثَكُمُ اللَّهُ أَنَّ أَهْلَ الْكِتَابِ بَدَّلُوا مَا كَتَبَ اللَّهُ وَغَيَّرُوا بِأَيْدِيهِمُ الْكِتَابَ، فَقَالُوا هُوَ مِنْ عِنْدِ اللَّهِ، لِيَشْتَرُوا بِهِ ثَمَنًا قَلِيلاً أَفَلاَ يَنْهَاكُمْ مَا جَاءَكُمْ مِنَ الْعِلْمِ عَنْ مُسَاءَلَتِهِمْ، وَلاَ وَاللَّهِ مَا رَأَيْنَا مِنْهُمْ رَجُلاً قَطُّ يَسْأَلُكُمْ عَنِ الَّذِي أُنْزِلَ عَلَيْكُمْ. 
ነጥብ ሁለት
“ተብዲል”
“ተህሪፍ” تحريف, ማለት ቃልና መልዕክትን መለወጥ መሆኑን አይተን ነበር፤ “ተብዲል” تَبْدِيل ማለት ደግሞ “ማስቀየር” ነው፤ ተብዲል የንግግርን ሃሳብ፣ የውሳኔ ቃል እና የተስፋ ቃል ማስቀየርን ያመለክታል፤ አላህ የተናገረውን የውሳኔ ቃል አሊያም የትንቢትና የተስፋ ቃል ማንም ማስቆም አሊያም ማስቀረት እንደማይችል አላህ በቃሉ ይናገራል፦
6:115 “”የጌታህም ቃላት እውነተኛና ትክክለኛ ስትኾን “ተፈጸመች”፡፡ ለቃላቱ ለዋጭ የለም” لَا مُبَدِّلَ፡፡ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡
10:64 ለእነሱ በቅርቢቱ ሕይወትም በመጨረሻይቱም “ብስራት” አላቸው፤ “”የአላህ ቃላት “መለወጥ የላትም*لَا تَبْدِيلَ ፤ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡
6:34 ከበፊትህም መልክተኞች በእርግጥ ተስተባበሉ፡፡ በተስተባበሉበትም ነገርና በተሰቃዩት ላይ እርዳታችን እስከመጣላቸው ድረስ ታገሱ፡፡ “”የአላህንም ንግግሮች *ለዋጭ የለም*وَلَا مُبَدَِّ፡፡

በተለይ “ተፈጸመች” እና “ብስራት” የሚሉት ቃላት የሚበሰርን እና የሚፈጸም ቃልን እንጂ በቀድሞ መጽሐፍት የተናገረውን መልእክት አያመለክትም፣ ኢማም ጦበራኒ ለሱረቱል አንአም 6፡115 የሰጡት ማብራሪያ እንዲህ ይላል፦
‹‹ለቃላቱ ለዋጭ የለም የሚለው ቃል አላህ በእርሱ መጽሀፍ ውስጥ ጉዳዩ ይከሰታል ብሎ ለመተግበሩ የሰጠው ቃል በጊዜው ከመተግበር ማንም አያግደውም እሱ እነደተናገረው ይፈጸማል ማለት ነው››
ኢማም ቁርጡቢም ተመሳሳይ ሀሳብ ያዘለ ማብራሪያቸውን እንዲህ ሲሉ ይገልጻል፦
‹‹ አልራሚኒ እንዳስተላለፉት አቡ ቀታዳ እንዲህ ይላሉ፡-ለኣላህ ፍርድ ምንም ለዋጭ የለውም የመጽሀፉ ሰዎች እንዳደረጉት ቃላቱን አንድ ሰው እንኳ ቢቀይረው የአላህ እውነተኛ ቃል ግን ከመፈጸም ወደ ኋላ አይልም የተለወጠው ቃል የሚፈጸመውን ቃል መለወጥ አይችልም፡፡››

ይህ የውሳኔ ቃል “ከሊማቱል-ከውኒያህ” ሲባል “ከሊማቱ አሽ-ሸርዒያህ” ደግሜ ወሕይ ነው፤  እንደው ሙግቱን ጠበብ ለማድረግ “ለቃላቱ ለዋጭ የለም” የሚለው ሃረግ መልእክቱን ነው ብንል እንኳን “ለቃላቱ ለዋጭ የለም” የሚለው የቀድሞ መጽሐፍትን ሳይሆን ቁርአንን ብቻና ብቻ ነው አራት ነጥብ። ምክንያት ከተባለ ማስረጀው ይኸው፦

18:27 ከጌታህም መጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፤ “ለቃላቶቹ ለዋጭ የላቸውም” لَا مُبَدِّلَ፤

“ኢለይከ” إِلَيْكَ “ወደ አንተ” የሚል ነጠላ ተውላጠ-ስም ነቢያችንን ብቻ የሚያመለክት ሲሆን ወደ እርሳቸው የተወረደው የተስፋ ቃላት ለማመልከት ደግሞ “ኢለይ” إِلَيْ “ወደ” በሚል መስተዋድድ ተጠፍንጓል፣ ወደ ነብያችን ደግሞ የወረደው ቁርአን ብቻ ነው።
ተህሪፍ እና ተብዲል በመንስኤ ሆነ በውጤት ሁለት ለየቅል የሆኑ ቃላት እና እሳቦት ናቸውና የተነሳችሁበት ስሁት የሆነ ሙግት ስህተትና ግድፈት ነው ብዬ ስል ምፀታዊ ተምኔት ሳይሆን እርምት እና ትምህርት እንድትወስዱበት ነው። አይ ሌሎችንም መጽሐፍት ያመለክታል የሚል ተሟጋች ካለ ያቀረብነውን ሙግት የሚያስተባብልበት የአውድ፣ የቋንቋ፣ የሰዋስው ሙግት ጠቅሶና አጣቅሶ ማቅረብ ይጠበቅበታል። ስለዚህ “የአላህ ቃል መለወጥ የላትም” የሚለው ሃረግ የቀድሞ መጽሐፍት ላለመለወጣቸው ማስረጃ ሊሆን አይችልም።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የቁርኣን አሻሻር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥106 *ከአንቀጽ ብንለውጥ ወይም እርሷን ብናስረሳህ ከእርሷ የሚበልጥን ወይም ብጤዋን እናመጣለን*፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መኾኑን አታውቅምን? مَا نَنسَخْ مِنْ آيَةٍ أَوْ نُنسِهَا نَأْتِ بِخَيْرٍ مِّنْهَا أَوْ مِثْلِهَا ۗ أَلَمْ تَعْلَمْ أَنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

በሥነ-ጽሑፍ ጥናት "ተሕሪፍ" تَحريف ማለት "ብርዘት"corruption" ማለት ሲሆን አንድ ጽሑፍን የሚበርዘው "በራዥ" ደግሞ "ሙተሐሪፍ" تَدْعُونَ ይባላል፤ ቁርኣን የአላህ ንግግር ነው፤ በእርሱ ንግግር ላይ ጂብሪል፣ ነብያችን"ﷺ" ሶሐባዎች፣ ታቢኢይዎች፣ አትባኡ ታቢኢይዎች በእርሱ ንግግር ላይ የጨመሩት ወይም የቀነሱት አንዳችም ንግግር የለም። ቁርኣን የመጨረሻው ግህደተ-መለኮት ነው። ከነብያችን"ﷺ" በኃላ የሚመጣ ነቢይ፣ የሚወርድ ወሕይ፣ የሚላክ መልእክተኛ ስለሌለ ይህንን ቁርኣን አላህ ካወረደው በኃላ ፍጡራን እንዳይጨምሩበትና እንዳይቀንሱበት የሚጠብቀው እራሱ የዓለማቱ ጌታ አላህ ነው፦
15፥9 *እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን*፡፡ إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا ٱلذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ
41፥42 *ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፤ ጥበበኛ ምስጉን ከኾነው ጌታ የተወረደ ነው*፡፡ لَّا يَأْتِيهِ ٱلْبَٰطِلُ مِنۢ بَيْنِ يَدَيْهِ وَلَا مِنْ خَلْفِهِۦ ۖ تَنزِيلٌۭ مِّنْ حَكِيمٍ حَمِيدٍۢ

ይህንን ከተረዳን ዘንድ በቁርኣን "ነሥኽ" የሚባል እሳቤ አለ፤ “ነሥኽ” نسخ ማለት “ሽረት”abrogation” ማለት ሲሆን ይህም ሽረት ሁለት ክፍል አለው፤ አንደኛው ክፍል “ናሢኽ” ناسخ ማለትም “ሻሪ አንቀጽ”Abrogator verse” ሲሆን ሁለተኛው “መንሡኽ” منسوخ ማለትም “ተሻሪ አንቀጽ”Abrogated verse” ነው፦
2፥106 *ከአንቀጽ ብንለውጥ ወይም እርሷን ብናስረሳህ ከእርሷ የሚበልጥን ወይም ብጤዋን እናመጣለን*፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መኾኑን አታውቅምን? مَا نَنسَخْ مِنْ آيَةٍ أَوْ نُنسِهَا نَأْتِ بِخَيْرٍ مِّنْهَا أَوْ مِثْلِهَا ۗ أَلَمْ تَعْلَمْ أَنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
16፥101 *በአንቀጽም ስፍራ አንቀጽን በለወጥን ጊዜ አላህም የሚያወርደውን ዐዋቂ ነው*፡፡ «አንተ ቀጣፊ እንጂ ሌላ አይደለህም» ይላሉ፡፡ በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡ وَإِذَا بَدَّلْنَا آيَةً مَّكَانَ آيَةٍ ۙ وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا يُنَزِّلُ قَالُوا إِنَّمَا أَنتَ مُفْتَرٍ ۚ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ

ይህንን እሳቤ ምሁራን "አን-ናሲኽ ወል መንሱኽ" الناسخ والمنسوخ ይሉታል፤ ይህ ሽረት በቁርኣን ሕጉን ታሳቢና ዋቢ ያረደገ ሲሆን የማህበረሰቡትን ዕድገትና የአስተሳሰብ ደረጃ፣ የጊዜውን ቅድመ-ተከተል እና ዘመነ-መግቦት”dispensation” ያማከለ ነው፣ ይህም “ተከታታይ ግህደተ-መለኮትን”progressive revelation” እሴት እና ግብአት ነው፤ አላህ የሕጉን አንቀጽ በሌላ የሕግ አንቀጽ የመሻሩ ሂደት በሁለት ይከፈላል፤ ይህንን ነጥብ በነጥብ በአጽንዖትና በአንክሮት ማየት ይቻላል፦
ነጥብ አንድ
"ነሥኹል ሑክም"
“ሑክም” حُكْم ማለት "ሕግ" ማለት ሲሆን "መትን” مَتن ማለት ደግሞ "ጥሬ-ቃል" ማለት ነው፤ "ነሥኹል ሑክም" ማለት "ሕግ" ተነሥኾ ግን "ጥሬ-ቃል" የማይነሠኽበት ማለት ነው፤ ለምሳሌ ተሻሪ አንቀጽ ይህ አንቀጽ ነው፦
2፥240 *እነዚያ ከእናንተ ውስጥ የሚሞቱ ሚስቶችንም የሚተዉ፤ ለሚስቶቻቸው ከቤታቸው የማይወጡ ሲኾኑ ዓመት ድረስ መጠቀምን ኑዛዜን ይናዘዙ፡፡ በፈቃዳቸው ቢወጡም በሕግ ከታወቀው ነገር በነፍሶቻቸው በሠሩት በእናንተ በሟቹ ዘመዶች ላይ ኃጢኣት የለባችሁም አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው*፡፡ وَالَّذِينَ يُتَوَفَّوْنَ مِنكُمْ وَيَذَرُونَ أَزْوَاجًا وَصِيَّةً لِّأَزْوَاجِهِم مَّتَاعًا إِلَى الْحَوْلِ غَيْرَ إِخْرَاجٍ ۚ فَإِنْ خَرَجْنَ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ فِي مَا فَعَلْنَ فِي أَنفُسِهِنَّ مِن مَّعْرُوفٍ ۗ وَاللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٌ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4530
ኢብኑ አዝ-ዙበይር እንደተረከው፦ *"እኔም ለዑስማን ኢብኑ ዐፋል"ረ.ዐ."፦ " እነዚያ ከእናንተ ውስጥ የሚሞቱ ሚስቶችንም የሚተዉ.."2፥240 ስለዚህ ይህ አንቀጽ በሌላ አንቀጽ ተሽሯል፤ ለምንድን ነው የምትጽፈው ወይም የምትተወው? ዑስማንም፦ "የወንድሜ ልጅ ሆይ! እኔ ከቦታው ምንም ነገር አለውጥም" አለው*። قَالَ ابْنُ الزُّبَيْرِ قُلْتُ لِعُثْمَانَ بْنِ عَفَّانَ ‏{‏وَالَّذِينَ يُتَوَفَّوْنَ مِنْكُمْ وَيَذَرُونَ أَزْوَاجًا‏}‏ قَالَ قَدْ نَسَخَتْهَا الآيَةُ الأُخْرَى فَلِمَ تَكْتُبُهَا أَوْ تَدَعُهَا قَالَ يَا ابْنَ أَخِي، لاَ أُغَيِّرُ شَيْئًا مِنْهُ مِنْ مَكَانِهِ‏.‏

አላህ መትኑን ከሚነሥኸው ውጪ ሰዎች የመነሠኽ ሥልጣን እንደሌላቸው ይህ ሐዲስ ያሳያል፤ "ኢብዳል" إبـدال ማለት "ምትክ"replacement" ማለት ሲሆን የተተካበት ሻሪ አንቀጽ ደግሞ ይህ አንቀጽ ነው፦
4፥12 *ለእናንተም ሚስቶቻችሁ ከተዉት ንብረት ለእነርሱ ልጅ ባይኖራቸው ግማሹ አላችሁ፡፡ ለእነሱም ልጅ ቢኖራቸው ከተዉት ሀብት ከአራት አንድ አላችሁ፡፡ ይህም በእርሷ ከሚናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከዕዳ በኋላ ነው፡፡ ለናንተም ልጅ ባይኖራችሁ ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ ለሚስቶች ከአራት አንድ አላቸው፡፡ ለእናንተም ልጅ ቢኖራችሁ ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ ከስምንት አንድ አላቸው ይህም በርሷ ከምትናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከዕዳ በኋላ ነው፡፡ ወላጅም ልጅም የሌለው በጎን ወራሾች የሚወርስ ወንድ ወይም ሴት ቢገኝ ለእርሱም ለሟቹ ወንድም ወይም እኅት (ከእናቱ በኩል ብቻ የኾነ ቢኖር ከሁለቱ ለያንዳንዳቸው ከስድስት አንድ አላቸው፡፡ ከዚህም ከአንድ የበዙ ቢኾኑ እነርሱ በሲሶው ተጋሪዎች ናቸው፡፡ ይህም ወራሾችን የማይጎዳ ኾኖ በእርሷ ከሚናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከዕዳ በኋላ ነው፡፡ ከአላህም የኾነን ኑዛዜ ያዛችኋል፡፡ አላህም ዐዋቂ ቻይ ነው*፡፡ وَلَكُمْ نِصْفُ مَا تَرَكَ أَزْوَاجُكُمْ إِن لَّمْ يَكُن لَّهُنَّ وَلَدٌ ۚ فَإِن كَانَ لَهُنَّ وَلَدٌ فَلَكُمُ الرُّبُعُ مِمَّا تَرَكْنَ ۚ مِن بَعْدِ وَصِيَّةٍ يُوصِينَ بِهَا أَوْ دَيْنٍ ۚ وَلَهُنَّ الرُّبُعُ مِمَّا تَرَكْتُمْ إِن لَّمْ يَكُن لَّكُمْ وَلَدٌ ۚ فَإِن كَانَ لَكُمْ وَلَدٌ فَلَهُنَّ الثُّمُنُ مِمَّا تَرَكْتُم ۚ مِّن بَعْدِ وَصِيَّةٍ تُوصُونَ بِهَا أَوْ دَيْنٍ ۗ وَإِن كَانَ رَجُلٌ يُورَثُ كَلَالَةً أَوِ امْرَأَةٌ وَلَهُ أَخٌ أَوْ أُخْتٌ فَلِكُلِّ وَاحِدٍ مِّنْهُمَا السُّدُسُ ۚ فَإِن كَانُوا أَكْثَرَ مِن ذَٰلِكَ فَهُمْ شُرَكَاءُ فِي الثُّلُثِ ۚ مِن بَعْدِ وَصِيَّةٍ يُوصَىٰ بِهَا أَوْ دَيْنٍ غَيْرَ مُضَارٍّ ۚ وَصِيَّةً مِّنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَلِيمٌ

"በአንቀጽም ስፍራ አንቀጽን በለወጥን ጊዜ አላህም የሚያወርደውን ዐዋቂ ነው" የሚለው ይህንን እሳቤ ዋቢ ያደረገ ነው፦
16፥101 *በአንቀጽም ስፍራ አንቀጽን በለወጥን ጊዜ አላህም የሚያወርደውን ዐዋቂ ነው*፡፡ «አንተ ቀጣፊ እንጂ ሌላ አይደለህም» ይላሉ፡፡ በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡ وَإِذَا بَدَّلْنَا آيَةً مَّكَانَ آيَةٍ ۙ وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا يُنَزِّلُ قَالُوا إِنَّمَا أَنتَ مُفْتَرٍ ۚ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ
ነጥብ ሁለት
"ነሥኹል መትን"
"ነሥኹል መትን" ማለት "ሕግ" ተነሥኾ ግን "ጥሬ-ቃል" የሚነሠኽበት ማለት ነው፤ "ኢብታል" إبـتال ማለት "ማንሳት"nullification" ማለት ሲሆን አምላካችን አላህ ጥሬ ቃሉ በማንሳት ይነሥኸዋል፦
2፥106 *ከአንቀጽ ብንለውጥ ወይም እርሷን ብናስረሳህ ከእርሷ የሚበልጥን ወይም ብጤዋን እናመጣለን*፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መኾኑን አታውቅምን? مَا نَنسَخْ مِنْ آيَةٍ أَوْ نُنسِهَا نَأْتِ بِخَيْرٍ مِّنْهَا أَوْ مِثْلِهَا ۗ أَلَمْ تَعْلَمْ أَنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
87፥6 *ቁርኣንን በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም*፡፡ سَنُقْرِئُكَ فَلَا تَنسَىٰ
87፥7 *አላህ ከሻው በስተቀር*፡፡ እርሱ ግልጹን የሚሸሸገውንም ሁሉ ያውቃልና፡፡ إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۚ إِنَّهُ يَعْلَمُ الْجَهْرَ وَمَا يَخْفَىٰ

ነብያችን"ﷺ" ከሚወርድላቸው አንቀጽ ምንም አይረሱም አላህ ከሻው በስተቀር፤ “አላህ ከሻው በስተቀር” ማለት አላህ አንድን አንቀጽ በማስረሳት በሌላ አንቀጽ ከመለወጥ በስተቀር ማለት ነው፤ "ብናስረሳህ" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ለዛ ነው የተነሰኹ አናቅጽ ሐዲስ ላይ የምናገኘው፤ ለምሳሌ አንድ ናሙና ማየት ይቻላል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 5, ሐዲስ 264:
አል-በረራዒ ኢብኑ ዓዚብ እንደተረከው፦ *“በሶላቶች እና በአስር ሶላት ላይ ተጠባበቁ” ይህ አንቀፅ ወርዶ ነበር፤ አላህ እስከሻው ድረስ እንቀራው ነበር፤ ከዚያም *አላህ ነሠኸውና፦ “በሶላቶች በመካከለኛይቱም ሶላት ላይ ተጠባበቁ፡፡ ታዛዦች ኾናችሁም ለአላህ ቁሙ” የሚለውን አንቀፅ አወረደ*። عَنِ الْبَرَاءِ بْنِ عَازِبٍ، قَالَ نَزَلَتْ هَذِهِ الآيَةُ حَافِظُوا عَلَى الصَّلَوَاتِ وَصَلاَةِ الْعَصْرِ ‏.‏ فَقَرَأْنَاهَا مَا شَاءَ اللَّهُ ثُمَّ نَسَخَهَا اللَّهُ فَنَزَلَتْ ‏{‏ حَافِظُوا عَلَى الصَّلَوَاتِ وَالصَّلاَةِ الْوُسْطَى‏}‏

ሶሐባዎችም መትኑ የተነሠኸውን አንቀጾች አላህ እስከ ነሠኸው ድረስ በቂራኣታቸው ውስጥ አያካትቱም ነበር፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4481
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *"ዑመር"ረ.ዐ." አለ፦ " የእኛ ምርጥ ቃሪእ ኡበይ ነው፤ የእኛ ምርጥ ዳኛ ዐሊይ ነው፤ ሆኖም ግን የዑበይን አንዳንድ ንግግር እንተወው ነበር፤ እርሱም፦ "ከአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ከምሰማው ምንም አልተውኩም፤ አላህ እንዳለው ከሚረሳው በቀር፦ "ከአንቀጽ ብንለውጥ ወይም እርሷን ብናስረሳህ"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ قَالَ عُمَرُ ـ رضى الله عنه ـ أَقْرَؤُنَا أُبَىٌّ، وَأَقْضَانَا عَلِيٌّ، وَإِنَّا لَنَدَعُ مِنْ قَوْلِ أُبَىٍّ، وَذَاكَ أَنَّ أُبَيًّا يَقُولُ لاَ أَدَعُ شَيْئًا سَمِعْتُهُ مِنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَقَدْ قَالَ اللَّهُ تَعَالَى ‏{‏مَا نَنْسَخْ مِنْ آيَةٍ أَوْ نَنْسَأْهَا‏}‏

አምላካችን አላህ አንቀጹን ሽሮ ከሚያስረሳው በቀር ሰዎች በግላቸው የቁርኣንን አንቀጽ የቀነሱበት የጨመሩበት የለም። ለነብያችን"ﷺ" የሚወርደው ቁርኣን ብቻ ሳይሆን ሐዲሱል ቁድስ እና ሐዲሱል ነበውይም ጭምር ነው፤ ነብያችን"ﷺ" በዐቂዳህ እና በፊቅህ ነጥብ ላይ የሚናገሩት ወሕይ ነው፦
53፥4 *እርሱ ንግግሩ የሚወርረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም*፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْيٌ يُوحَىٰ
ከወረዱት አንዱ ልክ እንደ ሱረቱል በቀራህ እርዝመት እና ክብደት ያለው ምእራፍ ነበር፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 12, ሐዲስ 156
አቡ ሐርብ ኢብኑ አቢይ እንደተረከው፦ *"አል-ኢሥወድ ከአባቱ አግኝቶ እንዲህ አለ፦ አቡ ሙሳ አል-ዐሻሪይ የበስሯ ቃሪእዎችን ልኮ አስጠራ፤ እነርሱም መጡ፤ በቁጥር ሦስት መቶ ይሆናሉ፤ ቁርኣንን ቀሩ*፤ ከዚያም እንዲህ አለ፦ *"እናንተ ከበስሯ ነዋሪዎች በላጮች ናችሁ፤ ምክንያቱም ከእነርሱ መካከል ቃሪእዎች ናችሁ፤ ስለዚህ መቅራታችሁን ቀጥሉ፤ ነገር ግን ይህንን እወቁ! ከእናንተ በፊት ለረጅም ጊዜ በመቅራታችሁ ልባቸው እንደ ደነደነባቸው ልቦቻችሁ እንዳያደነድነው። አንድ ምእራፍ በርዝመቱና በክብደቱ ከሱረቱል በራትን(በቀራህ) የሚያክል እናነብ ነበር። ነገር ግን "የአዳም ልጅ በወርቅ የተሞላ ሸለቆ ቢኖረው ኖሮ፣ እንደ እርሱ ዓይነት ሌላ ሁለት ሸለቆ ለመያዝ ይፈልጋል፤ የአዳም ልጅም ሆዱን የሚሞላለት አፈር እንጂ ሌላ ነገር አይደለም" ከሚለው በቀር እኔ ረስቼዋለሁ*። عَنْ أَبِي حَرْبِ بْنِ أَبِي، الأَسْوَدِ عَنْ أَبِيهِ، قَالَ بَعَثَ أَبُو مُوسَى الأَشْعَرِيُّ إِلَى قُرَّاءِ أَهْلِ الْبَصْرَةِ فَدَخَلَ عَلَيْهِ ثَلاَثُمِائَةِ رَجُلٍ قَدْ قَرَءُوا الْقُرْآنَ فَقَالَ أَنْتُمْ خِيَارُ أَهْلِ الْبَصْرَةِ وَقُرَّاؤُهُمْ فَاتْلُوهُ وَلاَ يَطُولَنَّ عَلَيْكُمُ الأَمَدُ فَتَقْسُوَ قُلُوبُكُمْ كَمَا قَسَتْ قُلُوبُ مَنْ كَانَ قَبْلَكُمْ وَإِنَّا كُنَّا نَقْرَأُ سُورَةً كُنَّا نُشَبِّهُهَا فِي الطُّولِ وَالشِّدَّةِ بِبَرَاءَةَ فَأُنْسِيتُهَا غَيْرَ أَنِّي قَدْ حَفِظْتُ مِنْهَا لَوْ كَانَ لاِبْنِ آدَمَ وَادِيَانِ مِنْ مَالٍ لاَبْتَغَى وَادِيًا ثَالِثًا وَلاَ يَمْلأُ جَوْفَ ابْنِ آدَمَ إِلاَّ التُّرَابُ ‏

የአደም ልጆች በወርቅ ሸለቆ የሚለው የነብያችን"ﷺ" ንግግር እንጂ የአላህ ንግግር አይደለም፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 81, ሐዲስ 28
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ *"የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" አሉ፦ "የአዳም ልጅ በወርቅ የተሞላ ሸለቆ ቢኖረው ኖሮ፣ እንደ እርሱ ዓይነት ሌላ ሁለት ሸለቆ ለመያዝ ይፈልጋል፤ የአዳም ልጅም አፉን የሚሞላለት አፈር እንጂ ሌላ ነገር አይደለም፤ አላህ ወደ እርሱ የሚመለሱት ይቅር ይላል*። قَالَ أَخْبَرَنِي أَنَسُ بْنُ مَالِكٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لَوْ أَنَّ لاِبْنِ آدَمَ وَادِيًا مِنْ ذَهَبٍ أَحَبَّ أَنْ يَكُونَ لَهُ وَادِيَانِ، وَلَنْ يَمْلأَ فَاهُ إِلاَّ التُّرَابُ، وَيَتُوبُ اللَّهُ عَلَى مَنْ تَابَ ‏"‌‏.‏

ይህ ንግግር ነብያችን"ﷺ" በተናገሩበት ጊዜ ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." "ከቁርኣን ይሁን አይሁን ዐላወቀም ነበር" ብሏል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 81, ሐዲስ 26
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ "የአዳም ልጅ በወርቅ የተሞላ ሸለቆ ቢኖረው ኖሮ፣ እንደ እርሱ ዓይነት ሌላ ሁለት ሸለቆ ለመያዝ ይፈልጋል፤ የአዳም ልጅም በዐይኑ ፊት አፉን የሚሞላለት አፈር እንጂ ሌላ ነገር አይደለም፤ አላህ ወደ እርሱ የሚመለሱት ይቅር ይላል" ኢብኑ ዐባስም፦ "ይህ ንግግር ከቁርኣን ይሁን አይሁን ዐላውቅም ነበር" አለ*። حَدَّثَنِي مُحَمَّدٌ، أَخْبَرَنَا مَخْلَدٌ، أَخْبَرَنَا ابْنُ جُرَيْجٍ، قَالَ سَمِعْتُ عَطَاءً، يَقُولُ سَمِعْتُ ابْنَ عَبَّاسٍ، يَقُولُ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ لَوْ أَنَّ لاِبْنِ آدَمَ مِثْلَ وَادٍ مَالاً لأَحَبَّ أَنَّ لَهُ إِلَيْهِ مِثْلَهُ، وَلاَ يَمْلأُ عَيْنَ ابْنِ آدَمَ إِلاَّ التُّرَابُ، وَيَتُوبُ اللَّهُ عَلَى مَنْ تَابَ ‏"‌‏.‏ قَالَ ابْنُ عَبَّاسٍ فَلاَ أَدْرِي مِنَ الْقُرْآنِ هُوَ أَمْ لاَ‏.

ያ ማለት ከቁርኣን አይደለም ማለት ነው፤ ዑበይ"ረ.ዐ." ይህ ንግግር ሱረቱል ተካሱር የቁርኣን ሱራህ እስከሚወርድ ድረስ ከቁርኣን ሱራህ ነው ብለን እናስብ ነበር" ብሏል፤ ያ ማለት የቁርኣን ሱራህ አይደለም ማለት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 81, ሐዲስ 27
ኢብኑ ሠዕድ እንደተረከው፦ *"ኢብኑ አዝ-ዙበይር በመካህ ሚንበር ላይ ሆኖ ኹጥባህ ሲሰጥ ሰማሁት፤ እንዲህም አለ፦ "እናንተ ሰዎች ሆይ! ነብዩ"ﷺ"፦ "የአዳም ልጅ በወርቅ የተሞላ ሸለቆ ቢኖረው፣ እንደ እርሱ ዓይነት ሌላ ሁለተኛ ሸለቆ ለመያዝ ይፈልጋል፤ ሁለተኛ ቢሰጠው ሌላ ሦስተኛ ሸለቆ ለመያዝ ይፈልጋል፤ የአዳም ልጅም ሆዱን የሚሞላለት አፈር እንጂ ሌላ ነገር አይደለም፤ አላህ ወደ እርሱ የሚመለሱት ይቅር ይላል" እያሉ ሲናገሩ ነበር። ዑበይም አለ፦ "ይህ ንግግር "በብዛት መፎካከር ጌታችሁን ከመገዛት አዘነጋችሁ"102፥1 የሚለው ሱራህ እስከሚወርድ ድረስ ከቁርኣን ነው ብለን እናስብ ነበር*። حَدَّثَنَا أَبُو نُعَيْمٍ، حَدَّثَنَا عَبْدُ الرَّحْمَنِ بْنُ سُلَيْمَانَ بْنِ الْغَسِيلِ، عَنْ عَبَّاسِ بْنِ سَهْلِ بْنِ سَعْدٍ، قَالَ سَمِعْتُ ابْنَ الزُّبَيْرِ، عَلَى الْمِنْبَرِ بِمَكَّةَ فِي خُطْبَتِهِ يَقُولُ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَقُولُ ‏ "‏ لَوْ أَنَّ ابْنَ آدَمَ أُعْطِيَ وَادِيًا مَلأً مِنْ ذَهَبٍ أَحَبَّ إِلَيْهِ ثَانِيًا، وَلَوْ أُعْطِيَ ثَانِيًا أَحَبَّ إِلَيْهِ ثَالِثًا، وَلاَ يَسُدُّ جَوْفَ ابْنِ آدَمَ إِلاَّ التُّرَابُ، وَيَتُوبُ اللَّهُ عَلَى مَنْ تَابَ ‏"‌‏.‏
Ubbay ibn Ka'ab said "We considered this as a saying from the Qur'an untill the Sura፦ 'The mutual rivalry for piling up of worldly things diverts you..' (102.1) was revealed."

ስለ ነሥኽ ያለው እሳቤ በግርድፉና በሌጣው ይህንን ይመስላል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሥነ-ፅንስ

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

31:34 አላህ የሰዓቲቱ እውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው፤ ዝናምንም ያወርዳል፤ #በማሕፀኖችም #ውስጥ #ያለን #ሁሉ #ያውቃል

መግቢያ
ሥነ-ፅንስ ጥናት ኢምብሪዮሎጂይ”Embryology” ሲባል “ኢምብሮ” ἔμβρυον “ያልተወለደ” እና “ሎጂአ” λογία, “ጥናት” ከሚል ሁለት የግሪክ ቃል የተዋቀረ ነው፤ ይህንን ፅንስ እናቱ ማህፀን ውስጥ በሚፈልገው መልኩ የሚቀርፀው አንዱ አምላክ አላህ ነው፦
3:6 እርሱ ያ “በማሕፀኖች” ዉሰጥ እንደሚሻ አድርጎ “የሚቀርጻችሁ” ነዉ፤ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፤

ይህ ፅንስ ማህፀን ውስጥ እንዴት እንደሚፈጠር ሙሉ እውቀት ያለው የዓለማቱ ጌታ አላህ ብቻ ነው፦
31:34 አላህ የሰዓቲቱ ዕውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው፤ ዝናምንም ያወርዳል፤ “በማሕፀኖችም ውስጥ ያለን ሁሉ ያውቃል”፤
53:32 ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜ እናንተም በእናቶቻችሁ “ማሕፀኖች” ውስጥ ሽሎች በሆናችሁ ጊዜ እርሱ በእናንተ ሁኔታ “አዋቂ” ነው።
13:8 አላህ ሴት ሁሉ የምታረግዘውን ያውቃል፤ “ማሕፀኖችም የሚያጐድሉትን የሚጨምሩትንም፥ ያውቃል”፤ ነገሩም ሁሉ እርሱ ዘንድ በልክ የተወሰነ ነው።

በማሕፀኖችም ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቀ አምላክ የሥነ-ፅንስ እውቀት ወደፊት እንደሚያሳየና እንደሚያሳውቀን ለማመልከት፦ “በራሶቻችሁ ውስጥ ያሉትም ታምራት ወደፊት ያሳያችኋል፤ ታውቁታላችሁ” በማለት ቃል ገብቷል፦
41፥53 እርሱም ቁርአን እውነት መሆኑ ለነርሱ እስከሚገለጽላቸው ድረስ፣ በአጽናፎቹ ውስጥ እና #በራሶቻቸውም ውስጥ ያሉትን #ታምራቶቻችንን በእርግጥ #እናሳያቸዋለን፤ ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ መሆኑ አይበቃቸውምን?
27:93 ምስጋና ለአላህ ነው፤ #ታምራቶቹን #ወደፊት #ያሳያችኋል#ታውቁታላችሁ በላቸው።

አላህ ይህንን እውቀት በራሳችን አካላት ከማሳየቱ በፊት በቁርአን አንድ ሽል በማህፀን ውስጥ እንዴት የተለያየ ደረጃዎችን”stages” እንደሚያሳልፍ በተከበረ ቃሉ ይነግረናል፦
23:12 በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው፤ ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ “የፍትወት ጠብታ” النُّطْفَةَ አደረግነው፤ ከዚያም ጠብታዋን “የረጋ ደም” عَلَقَةً አድርገን ፈጠርን፤ የረጋውንም ደም “ቁራጭ ሥጋ” مُضْغَةً አድርገን ፈጠርን፤ ቁራጯንም ሥጋ “አጥንቶች” عِظَامًا አድርገን ፈጠርን፤ አጥንቶቹንም ሥጋን لَحْمًا አለበስናቸው፤ ከዚያም “ሌላ ፍጥረትን” خَلْقًا آخَرَ አድርገን “አስገኘነው” أَنْشَأْنَاهُ፤ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ፡፡
ደረጃ አንድ
“ኑጥፋህ”
የአንድ ሽል በማህፀን ያለው የመጀመሪያ ደረጃ “ኑጥፋህ” نُّطْفَة ነው፤ “ኑጥፋህ” ማለት “የፍትወት ጠብታ” ሲሆን ይህም የተባእት ዘር ህዋስ” sperm cell” እና የእንሥት እንቁላል ህዋስ”egg cells” ነው፤ እነዚህ የፍትወት ጠብጣዎች በሥነ-ፅንስ ምሁራን “ፍናፍንት”hermaphroditic” በመባል ይታወቃሉ፤ አላህ ስለዚህ የፍትወት ጠብታ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ይለናል፦
53:45-46 እርሱም ሁለቱን ዓይነቶች ወንድና ሴትን ፈጠረ። “ከፍትወት ጠብታ” نُطْفَةٍ በማኅፀን ውስጥ በምትፈስ ጊዜ፤
80:19 “ከፍትወት ጠብታ” نُطْفَةٍ ፈጠረው መጠነውም።
16:4 ሰውን “ከፍትወት ጠብታ” نُطْفَةٍ ፈጠረው፤ ከዚያም እርሱ ወዲያውኑ ትንሣኤን በመካድ ግልጽ ተከራካሪ ይሆናል።
35:11 አላህም ከአፈር፣ ከዚያም “ከፍትወት ጠብታ” نُطْفَةٍ ፈጠራችሁ፤
36:77 ሰውየው እኛ “ከፍቶት ጠብታ” የፈጠርነው መሆናችን አላወቀምን?
40:67 እርሱ ያ ከአፈር፣ ከዚያም “ከፍትወት ጠብታ” نُطْفَةٍ ፣ ከዚያም ከረጋ ደም፣ የፈጠራችሁ ነው።

የሴት ልጅ ማህፀን ዘር በሚዘራበት “እርሻ” ሲመሰል፤ የእንሥት ማህፀን ላይ ላይ የሚገናኘው የተባእት ዘር ህዋስ ደግሞ ገበሬ እርሻ ላይ በሚዘራው “ዘር” ተመስሏል፤ ምክንያቱም አንድ ገበሬ እርሻው ላይ ከዘራ በኃላ ዘሩ ዳብሮ ለፍሬ የሚበቃው በእርሻ ውስጥ እንደሆነ ሁሉ አንድ ተባእትም አንድ እንስት ማህፀን ውስጥ ዘሩን ተገናኝ ሆኖ ከዘራ በኃላ ሂደቱ ሁሉ ተከናውኖ ለፍሬ የሚበቃው ማህፀን ውስጥ ነው፦
2:223 ሴቶቻችሁ ለእናንተ “እርሻ” ናቸው፤ እርሻችሁንም በፈለጋችሁት ኹኔታ ድረሱ፤ ለነፍሶቻችሁም መልካም ሥራን አስቀድሙ፤ አላህንም ፍሩ፤ እናንተም “”ተገናኝዎቹ”” መኾናችሁን ዕወቁ፡፡
56:57-59 እኛ ፈጠርናችሁ፤ አታምኑምን? “በማኅፀኖች “የምታፈሱትን አያችሁትን”? እናንተ ትፈጥሩታላችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎቹ ነን።
56:63-64 “የምትዘሩትንም አያችሁን”? እናንተ ታበቅሉታላችሁን? ወይስ እኛ አብቃዮቹ ነን?
32:7-8 ያ የፈጠረውን ነገር ሁሉ ያሳመረው፣ የሰውንም ፍጥረት ከጭቃ የጀመረው፥ ነው፤ ከዚያም “ዘሮቹን”፣ ከተጣለለ “ከደካማ ውሃ” ያደረገ፣ ነው።
77:20-21 “ከደካማ ውሃ” አልፈጠርናችሁምን? “በተጠበቀ መርጊያ በማሕፀን ውስጥም” አደረግነው፤

አላህ በማህፀን ያለውን የመጀመሪያ ደረጃ ሰው እንዴት የተባእት ዘር ህዋስ እና የእንሥት እንቁላል ህዋስ ፍናፍንት ሆኖ ተቀላቅሎ እንደሚፈጠር ቀድሞውኑ በማሕፀኖችም ውስጥ ያለንውን ሁሉ አዋቂ አምላክ መሆኑን ለእኛ ለማሳየት “አምሻጅ” أَمْشَاج “ቅልቅል”mixture” በማለት ይናገራል፦
76:2 እኛ ሰዉን በሕግ ግዳጅ የምንሞክረዉ ስንሆን፥ “ቅልቅሎች” أَمْشَاجٍ ከሆኑ “የፍትወት ጠብታ” نُطْفَةٍ ፈጠርነዉ፤ ሰሚ ተመልካችም አደረግነዉ። ኢንሻላህ ይቀጥላል…..

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሥነ-ፅንስ

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

31:34 አላህ የሰዓቲቱ እውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው፤ ዝናምንም ያወርዳል፤ #በማሕፀኖችም #ውስጥ #ያለን #ሁሉ #ያውቃል

“ደረጃ ሁለት”
“ዐለቃ”
“ዐለቃ” عَلَقَة አንስታይ ሲሆን “ዐለቅ” عَلَق ደግሞ ተባእታይ ነው፤ ትርጉሙም “አልቅት”leech” ወይም “የረጋ ደም”blood-clot” ማለት ነው፤ ይህን የፅንስ ሁለተኛው ደረጃ ከሚታይ አልቅት ከሚባል የባህር ትል”insect” እና ከረጋ ደም ጋር ስለሚመሳሰል ነው፤ ወደዚህ ሂደት ለመምጣት በህዋሳት ውህደት ወቅት “ክሮሞሶም”Chromosomes” ከአንዱ ለጋሽ ወላጅ ወደሌላው ለጋሽ ወላጅ ይተላለፋል፤ እያንዳንዱ ተሣታፊ ህዋስ የለጋሾችን ግማሽ ክሮሞሶም ይይዛል፤ የአባት ክሮሞሶም ግማሽ 23% የእናት ክሮሞሶም 23% ተገናኛተው 46% ይዋሃዳሉ ማለት ነው፤ ተወራሽ የዘር ምልክቶች በምፃረ-ቃል “ዲ-ኤን-ኤ”(DNA) ወይም በዝርዝር “ዲኦክሲሪቦ ኒውክሊክ አሲድ”(deoxyribonucleic acid) በመባል በሚታወቀው በክሮሞሶሞች ውስጥ የሚገኝ ንጥረ-ነገር ውስጥ ሰፍረው ይገኛሉ። ክሮሞሶሞች “በጥንድ” ሆነው በሚገኙበት ጊዜ “ዳይፕሎይድ”(diploid) ይባላሉ፤ ክሮሞሶሞች በነጠላ ግዜ “ሃፕሎይድ”(haploid) ይባላሉ፤ በዚህ ሂደት አንድ ሴል የነበረው የወንድ የዘር ህዋስ ከሴት የእንቁላል ህዋስ ጋር ከተዋሐደ በኃላ 2, 4, 8, 16, 32, 64 እያለ በቲሪልየን ብዜት በ 21 ቀን የረጋ ደም”blood-clot” የሚለው ደረጃ ይጀምራል፤ ይህንን ደረጃ አምላካችን አላህ እንዲህ ይለናል፦
22:5 እላንተ ሰዎች ሆይ! ከመቀስቀስ፣ በመጠራጠር ዉስጥ እንደ ሆናችሁ አፈጣጠራችሁን ተመልከቱ፤ እኛም ከአፈር ፈጠርናችሁ ከዚያም ከፍቶት ጠብታ፣ ከዚያም “ከረጋ ደም” عَلَقَةٍ ፣ ከዚያም ከቁራጭ፣ ስጋ ፍጥረትዋ ሙሉ ከኾነችና ሙሉ ካልሆነች ችሎታችንን ለእናንተ ልንገልጽላችሁ ፈጠርናችሁ፤
40:67 እርሱ ያ ከአፈር፣ ከዚያም ከፍትወት ጠብታ፣ ከዚያም “ከረጋ ደም” عَلَقَةٍ፣ የፈጠራችሁ ነው።
96:1-2 አንብብ በዚያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም፤ ሰውን “ከረጋ ደም” عَلَقٍ በፈጠረው ጌታህ ስም።

ከፍትወት ህዋስ ወደ የረጋ ደም የሚሄድበት ሂደት እና ደረጃ ለማመልከት “ሱምመ” ثُمَّ “ከዚያም” የሚል መስተፃምር ይጠቀማል፤ ከዚህ ከተቀላቀለው የፍትወት ህዋስ ሁለት ዓይነቶችን ወንድና ሴትን ይመጣል፦
75፥36-39 ሰው ስድ ሆኖ መትተውን ይጠረጥራልን? የሚፈስስ ከሆነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን? “ከዚያም” ثُمَّ “የረጋ ደም” عَلَقَةً ሆነ፤ ሰው አድርጎ ፈጠረውም፤ አስተካከለውም። “ከእርሱም” ሁለት ዓይነቶችን “ወንድና ሴትን” አደረገ።

“የዘረ-መል ጥናት”(Genetic) እንደሚያስተነትነው የተባእት ክሮሞሶም ‘XY’ ሲሆን የእንስት ክሮሞሶም ደግሞ ‘XX’ ነው፤ ከወንድ ‘Y” መጥቶ ከሴት ‘X’ ከመጣ ሽሉ የአባቱን ፆታ በመያዝ ወንድ ይሆናል፤ ከወንድ ‘X” መጥቶ ከሴት ‘X’ ከመጣ ሽሉ የእናቱን ፆታ በመያዝ ሴት ይሆናል፤ ልብ አድርግ የወንድ ክሮሞሶም ‘XY’ ሲሆን የሴት ክሮሞሶም ደግሞ ‘XX’ መሆኑ ማለቴ ነው፤ የዘረ-መል ጥናት ይህንን ከማወቁ በፊት አላህ ለመልእክተኛው ይህንን የሩቅ ነገር ሚስጥር አሳውቋል፦
ኢማም ቡሃሪ መጽሐፍ 60 , ቁጥር 4 :
وَأَمَّا الشَّبَهُ فِي الْوَلَدِ فَإِنَّ الرَّجُلَ إِذَا غَشِيَ الْمَرْأَةَ فَسَبَقَهَا مَاؤُهُ كَانَ الشَّبَهُ لَهُ، وَإِذَا سَبَقَ مَاؤُهَا كَانَ الشَّبَهُ لَهَا ‏”‌‏.‏
የአላህ መልክተኛ አሉ፦ የልጆች ከወላጆቻቸው መመሳሰል እንዲህ ነው፤ ተባእት ከሚስቱ ጋር ተራክቦ ሲያደርግ የእርሱ ከተለቀቀ ህፃኑ እርሱን ይመስላል፤ የእንስት ከተለቀቀ ደግሞ ህፃኗ እርሷን ትመስላለች።

እውነት ነው፤ አላህም ከወንድ ክሮሞሶም ‘XY’ ወንድን እና ከሴት ክሮሞሶም ‘XX’ ደግሞ ሴትን በምድር ላይ ፈጥሮ የበተነ ነው፤ ይህም የሁለቱ አስተዋእፆ የአባት ክሮሞሶም ግማሽ 23% የእናት ክሮሞሶም 23% ተገናኛተው 46% ሲሆኑ ነው፦
4:1 እላንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ(ከአዳም) የፈጠራችሁን፣ ከእርስዋም መቀናጆዋን(ሔዋንን) የፈጠረውን፣ #ከእነርሱም ብዙ “ወንዶችን” እና “ሴቶችን” የበተነውን፣ ጌታችሁን ፍሩ።
49፥13 እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ “ከወንድ እና ከሴት ፈጠርናችሁ”፡፡ ኢንሻላህ ይቀጥላል…..

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሱረቱል ፋቲሓህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

15፥87 *ከሚደጋገሙ የኾኑን ሰባትን እና ታላቁንም ቁርኣን በእርግጥ ሰጠንህ*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَاكَ سَبْعًا مِّنَ الْمَثَانِي وَالْقُرْآنَ الْعَظِيمَ

አምላካችን አላህ “ሙርሲል” مُرْسِل ማለትም “ላኪ” ነው፤ ነብያችን”ﷺ” ደግሞ “ረሱል” رِسَالَة ማለትም “መልክተኛው” ናቸው፤ እንዲሁ ቁርኣን የአላህ “ሪሳላ” رِسَالَ ማለትም “መልእክት” ነው።
የመልእክቱ “ሙአለፍ” مؤلف ማለትም “አመንጪ”author” አምላካችን አላህ ሲሆን፤ ነብያችን”ﷺ” ደግሞ የመልእክቱ “ሙራሲል” مراسل ማለት “አስተላላፊ”reporter” ናቸው፤ አምላካችን አላህ ለነብያችን”ﷺ”፦ “ቁል” قُلْ ማለትም “በል” በሚል ትዕዛዛዊ ግስ ያዛቸዋል፦
112፥1 *በል «እርሱ አላህ አንድ ነው*፡፡ قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ
13፥30 እንደዚሁ ከበፊትዋ ብዙ ሕዝቦች በእርግጥ ያለፉ ወደኾነችው ሕዝብ እነርሱ በአልረሕማን የሚክዱ ሲኾኑ ያንን *ወደ አንተ ያወረድነውን ቁርኣን በእነርሱ ላይ ታነብላቸው ዘንድ ላክንህ፡፡ «እርሱ አልረሕማን ጌታዬ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ በእርሱ ላይ ተጠጋሁ፡፡ መመለሻዬም ወደ እርሱ ብቻ ነው» በላቸው*፡፡ كَذَٰلِكَ أَرْسَلْنَاكَ فِي أُمَّةٍ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهَا أُمَمٌ لِّتَتْلُوَ عَلَيْهِمُ الَّذِي أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ وَهُمْ يَكْفُرُونَ بِالرَّحْمَـٰنِ ۚ قُلْ هُوَ رَبِّي لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ وَإِلَيْهِ مَتَابِ

“ወደ አንተ ያወረድነውን ቁርኣን በእነርሱ ላይ ታነብላቸው ዘንድ ላክንህ” የሚለው ሃይለ-ቃል ቁርኣንን አውራጅና ነብያችንን”ﷺ” ላኪው አላህ እራሱ “በል” ማለቱን እንረዳለን፤ በመቀጠል እዛው አንቀጽ ላይ “ቁል” قُلْ ብሎ መናገሩ በራሱ “በል” የሚለው ማንነት አላህ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፤ በተጨማሪም “በልን” ወደ ነብያችን”ﷺ” የሚጥለው እራሱ እንደሆነ ይናገራል፦
73፥5 *እኛ በአንተ ላይ ከባድ ቃልን እንጥላለንና*፡፡ إِنَّا سَنُلْقِي عَلَيْكَ قَوْلًا ثَقِيلًا

እዚህ አንቀጽ ላይ “ቃል” ለሚለው የተቀመው ቃላት “ቀውል” قَوْل ሲሆን “ቁል” قُلْ ከሚል ትዕዛዛዊ ግስ የመጣ ነው፤ ስለዚህ “በል” እያለ የሚያስነብባቸው እራሱ አላህ ነው፤ ሱረቱል ፋቲሓህ የሚደጋገሙ ሰባት አንቀጾች ናት፤ ምክንያቱም ሱረቱል ፋቲሓህ ሰባት አናቅጽ አላት፤ በተጨማሪም ነብያችን”ﷺ” ሱረቱል ፋቲሓህ የሚደጋገሙ ሰባት አንቀጾች ናት ብለው ነግረውናል፦
15፥87 *ከሚደጋገሙ የኾኑን ሰባትን እና ታላቁንም ቁርኣን በእርግጥ ሰጠንህ*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَاكَ سَبْعًا مِّنَ الْمَثَانِي وَالْقُرْآنَ الْعَظِيمَ
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 28
አቢ ሠዒድ ኢብኑ ሙዐላ እንደተረከው *ሶላት ላይ ሆኜ ነብዩ”ﷺ” ጠሩኝ፤ ነገር ጥሪያቸውን አልመለስኩላቸውም፤ በኃላ ላይ፦ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ሶላት ላይ ነበርኩኝ” አልኩኝ፤ እሳቸውም፦ አላህ፦ “(መልእክተኛው) በጠራችሁ ጊዜ ለአላህ እና ለመልክተኛው ታዘዙ”8፥24 አላለምን? ከዚያም፦ “በቁርኣን ውስጥ ታላቂቱን ሱራህ ላስተምርህን? እርሷም፦ “ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው የምትለዋ የሚደጋገሙ የሆኑ ሰባት ሱረቱል ፋቲሐህን እና ታላቁ ቁርኣንን ተሰጠኝ”*። عَنْ أَبِي سَعِيدِ بْنِ الْمُعَلَّى، قَالَ كُنْتُ أُصَلِّي فَدَعَانِي النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم فَلَمْ أُجِبْهُ قُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ إِنِّي كُنْتُ أُصَلِّي‏.‏ قَالَ ‏”‏ أَلَمْ يَقُلِ اللَّهُ ‏{‏اسْتَجِيبُوا لِلَّهِ وَلِلرَّسُولِ إِذَا دَعَاكُمْ‏}‏ ثُمَّ قَالَ أَلاَ أُعَلِّمُكَ أَعْظَمَ سُورَةٍ فِي الْقُرْآنِ قَبْلَ أَنْ تَخْرُجَ مِنَ الْمَسْجِدِ ‏”‌‏.‏ فَأَخَذَ بِيَدِي فَلَمَّا أَرَدْنَا أَنْ نَخْرُجَ قُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ إِنَّكَ قُلْتَ لأُعَلِّمَنَّكَ أَعْظَمَ سُورَةٍ مِنَ الْقُرْآنِ‏.‏ قَالَ ‏”‌‏{‏الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ‏}‏ هِيَ السَّبْعُ الْمَثَانِي وَالْقُرْآنُ الْعَظِيمُ الَّذِي أُوتِيتُهُ ‏”‌‏.‏
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3415
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *አል-ሐምዱሊሏህ የቁርኣን እናት፣ የመጽሐፉ እናት እና ሰባት የተደጋገሙ ናት*። عَنِ ابْنِ أَبِي ذِئْبٍ، عَنِ الْمَقْبُرِيِّ، عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْحَمْدُ لِلَّهِ أُمُّ الْقُرْآنِ وَأُمُّ الْكِتَابِ وَالسَّبْعُ الْمَثَانِي ‏”
ሱረቱል ፋቲሓህ ላይ ከሚሽነሪዎች የሚነሳው ጥያቄ “ቀጥተኛውን መንገድ ምራን“ የሚለው የአላህ ንግግር ከሆነ አላህ ማንን ነው ምራን የሚለው? የሚል ነው፤ መልሱ "ቀጥተኛውን መንገድ ምራን" እኛ እንድንል ለእኛ ያለው ነው፤ ይህንም "ቁል" قُلْ የሚል ትዕዛዛዊ ግስ "ሙስተቲር" ْمُسْتَتِر ማለትም "ህቡዕ-ግስ"headen verb" ሆኖ የመጣ ነው፦
1፥6 *ቀጥተኛውን መንገድ ምራን*፡፡ اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ

"ኢህዲና" اهْدِنَا ማለትም "ምራን" ብዙ ቁጥር ሲሆን ይህ ባለቤት ግስ አማኞችን ያመለክታል፤ ተሳቢው ግስ ደግሞ መሪውን ያመለክታል፤ ስለዚህ "ቁሉ" قُلُوا የሚለው ሙስተቱር ሆኖ የመጣ ነው፤ ለምሳሌ በሱረቱል በቀራህ 2፥187 ላይ "ከተበ" كَتَبَ ማለትም "ጻፈ" የሚለውን ወደ ኢንግሊሽ ሲቀየር "He wrote" ነው፣ "He" ደግሞ ወደ ዐረቢኛ "ሁወ" هُوَ ማለትም "እርሱ" ነው፤ "ሁወ" هُوَ የሚለው "ከተበ" كَتَبَ ላይ ሚስተቲር ሆኖ የመጣ ነው፤ "ቁል" ወይም "ቁሉ" ተደብቀው በሙስተቲር የሚመጡበት ብዙ ቦታ ነው፦
11፥2 *አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ፤ እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስጠንቃቂ እና አብሳሪ ነኝ*፡፡ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ ۚ إِنَّنِي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ቁል" የሚለው የለም፤ ያ ማለት "አስጠንቃቂ እና አብሳሪ ነኝ" የሚለው አላህ ነው ማለት ቂልነት ነው፤ ምክንያቱም "ሚንሁ" مِّنْهُ የሚል ሃይለ-ቃል አለ፤ "ሚን" مِّن ማለት "ከ" ሲሆን መስተዋድድ ነው፤ በሚን ላይ "ሁ" هُ ማለት "እርሱ" የሚል ተሳቢ አለ፤ "እርሱ" የተባለው ላኪ አላህ ነው "አስጠንቃቂ እና አብሳሪ ነኝ" የሚሉት ደግሞ የተላኩት ነብያችን"ﷺ" ናቸው፦
35፥24 *እኛ አብሳሪ እና አስጠንቃቂ አድርገን በእውነቱ ላክንህ*፡፡ إِنَّا أَرْسَلْنَاكَ بِالْحَقِّ بَشِيرًا وَنَذِيرًا
7፥188 *እኔ ለሚያምኑ ሕዝቦች አስጠንቃቂ እና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም» በላቸው*፡፡ قُل لَّا أَمْلِكُ لِنَفْسِي نَفْعًا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۚ وَلَوْ كُنتُ أَعْلَمُ الْغَيْبَ لَاسْتَكْثَرْتُ مِنَ الْخَيْرِ وَمَا مَسَّنِيَ السُّوءُ ۚ إِنْ أَنَا إِلَّا نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ
"በል" ሳይል በአንድ አንቀጽ ላይ በውስጠ ታዋቂነት "እኔም በእናንተ ላይ ጠባቂ አይደለሁም" ይልና፤ ሌላ አንቀጽ ላይ "እኔም በእናንተ ላይ ጠባቂ አይደለሁም በል" የሚል ይጠቀማል፦
6፥104 *እኔም በእናንተ ላይ ጠባቂ አይደለሁም*፡፡ وَمَا أَنَا عَلَيْكُم بِحَفِيظٍ
6፥66 *በላቸው፡- «በእናንተ ላይ ጠባቂ አይደለሁም፡፡»* قُل لَّسْتُ عَلَيْكُم بِوَكِيلٍ

"በል" ሳይል በአንድ አንቀጽ ላይ በውስጠ ታዋቂነት "እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ" ይልና፤ ሌላ አንቀጽ ላይ "እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ በል" የሚል ይጠቀማል፦
6፥163 *«ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም በማጥራት ታዘዝኩ፡፡ እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ»*፡፡ لَا شَرِيكَ لَهُ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا أَوَّلُ الْمُسْلِمِينَ
39፥11 *በል* «እኔ አላህን ሃይማኖትን ለርሱ ያጠራሁ ኾኜ እንድግገዛው ታዘዝኩ፡፡ قُلْ إِنِّي أُمِرْتُ أَنْ أَعْبُدَ اللَّهَ مُخْلِصًا لَّهُ الدِّينَ
39፥12 *«የሙስሊሞችም መጀመሪያ እንድኾን ታዘዝኩ፡፡»* وَأُمِرْتُ لِأَنْ أَكُونَ أَوَّلَ الْمُسْلِمِينَ

ይህንን ከተረዳን ሱረቱል ፋቲሓህ ላይ "አንተን" ብለው በሚሉት ላይ "በል" ሳይል ሌላ አንቀጽ ላይ "አንተ በል" የሚል ይጠቀማል፦
3፥26 *በል*፡- «የንግስና ባለቤት የኾንክ አላህ ሆይ! ለምትሻው ሰው ንግሥናን ትሰጣለህ፡፡ ከምትሻውም ሰው ንግሥናን ትገፍፋለህ፡፡ የምትሻውንም ሰው ታልቃለህ፡፡ የምትሻውንም ሰው ታዋርዳለህ፡፡ መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ በችሎታህ ነው፤ *"አንተ"* በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና፡፡ قُلِ اللَّهُمَّ مَالِكَ الْمُلْكِ تُؤْتِي الْمُلْكَ مَن تَشَاءُ وَتَنزِعُ الْمُلْكَ مِمَّن تَشَاءُ وَتُعِزُّ مَن تَشَاءُ وَتُذِلُّ مَن تَشَاءُ ۖ بِيَدِكَ الْخَيْرُ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

በተጨማሪም ነብያችን"ﷺ" በሐዲስ ላይ ሱረቱል ፋቲሓን የሚለው የአላህ ባሪያ ወደ አላህ መሆኑን በግልጽ እና በማያሻማ መልኩ ነግረውናል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 4 ሐዲስ 41
አቢ ሁረይራ"ረ.ዐ" እንደተረከው *ነብዩ"ﷺ" አሉ፦ "የቁርአን እናት ሳያነብ የሰገደ ሰው ሶላቱ ጎዶሎ ነው"* አንድ ሰው ለአቢ ሁረይራ፦ "ከአሰጋጁ በኋላ ብንሆንም እንኳን"? አለው፤ እርሱም አለ፦ "ለራስህ አንብብ ምክንያቱም ነብዩ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁና፦ *"ኃያሉና የተከበረው አላህ እንዲህ ብሏል፦ "ሶላትን በእኔ እና በባሪያዬ መካከል ለሁለት ከፍየዋለሁ እናም ባሪያዬየጠየቀውን ያገኛል*፤ ባሪያው፦ *"ምስጋና ለአላህ ይገባውየዓለማት ጌታ ለኾነው" ሲል አላህ፦ "ባሪያዬአመሰገነኝ" ይላል*፤ ባሪያው፦ *"እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ" ሲልደግሞ አላህ፦ "ባሪያዬአሞገሰኝ’ ይላል*፤ ባሪያው፦ *"የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው" ሲል አላህ፦ ባሪያዬ አላቀኝ" ይላል*፤ ባሪያው፦ *"አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን" በሚል ግዜ አላህ፦ "ይህ በእኔ እና
በባሪያዬ መካከል ነው እናም ባሪያዬ የጠየቀውን ያገኛል" ይላል*፤ ባሪያው፦ *"ቀጥተኛውን መንገድ ምራን የእነዚያን በእነርሱ ላይበጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን" በሚል ግዜ ደግሞ አላህ፦ "ይህ ለባሪያዬ ነው፤ እናም ባሪያዬየጠየቀውን ያገኛል" ይላል*፡፡ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ مَنْ صَلَّى صَلاَةً لَمْ يَقْرَأْ فِيهَا بِأُمِّ الْقُرْآنِ فَهْىَ خِدَاجٌ - ثَلاَثًا - غَيْرُ تَمَامٍ ‏"‏ ‏.‏ فَقِيلَ لأَبِي هُرَيْرَةَ إِنَّا نَكُونُ وَرَاءَ الإِمَامِ ‏.‏ فَقَالَ اقْرَأْ بِهَا فِي نَفْسِكَ فَإِنِّي سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏"‏ قَالَ اللَّهُ تَعَالَى قَسَمْتُ الصَّلاَةَ بَيْنِي وَبَيْنَ عَبْدِي نِصْفَيْنِ وَلِعَبْدِي مَا سَأَلَ فَإِذَا قَالَ الْعَبْدُ ‏{‏ الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ‏}‏ ‏.‏ قَالَ اللَّهُ تَعَالَى حَمِدَنِي عَبْدِي وَإِذَا قَالَ ‏{‏ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ‏}‏ ‏.‏ قَالَ اللَّهُ تَعَالَى أَثْنَى عَلَىَّ عَبْدِي ‏.‏ وَإِذَا قَالَ ‏{‏ مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ‏}‏ ‏.‏ قَالَ مَجَّدَنِي عَبْدِي - وَقَالَ مَرَّةً فَوَّضَ إِلَىَّ عَبْدِي - فَإِذَا قَالَ ‏{‏ إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ‏}‏ ‏.‏ قَالَ هَذَا بَيْنِي وَبَيْنَ عَبْدِي وَلِعَبْدِي مَا سَأَلَ ‏.‏ فَإِذَا قَالَ ‏{‏ اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ * صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلاَ الضَّالِّينَ‏}‏ ‏.‏ قَالَ هَذَا لِعَبْدِي وَلِعَبْدِي مَا سَأَلَ ‏"‏ ‏.‏ قَالَ سُفْيَانُ حَدَّثَنِي بِهِ الْعَلاَءُ بْنُ عَبْدِ الرَّحْمَنِ بْنِ يَعْقُوبَ دَخَلْتُ عَلَيْهِ وَهُوَ مَرِيضٌ فِي بَيْتِهِ فَسَأَلْتُهُ أَنَا عَنْهُ ‏.‏

በዚህ መልኩ መረዳት ካልቻላችሁ አንድ ናሙና ከባይብል ላቅርብ፦ ዮሐንስ 20፥17 ኢየሱስም፦ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፦ እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ *ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው* አላት።

ወደ አምላኩ አራጊው ኢየሱስ ሆኖ ሳለ "ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው" ሲላት አራጊዋ መቅደላዊት ማርያም ሆና ነውን? አይ "ይላል" በይ ለማለት ተፈልጎ ነው ከተባለ "ይላል" የሚለውን የት አለ? በውስጠ-ታዋቂነት ይኖራል ከሆነ መልሱ እንግዲያውስ ሱረቱል ፋቲሐህንም በዚህ መልኩ መረዳት ይቻላል። ያለበለዚያ አራጊዋ መቅደላዊት ማርያም ትሆናለች።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሥነ-ፅንስ

ክፍል ሶስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

31:34 አላህ የሰዓቲቱ እውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው፤ ዝናምንም ያወርዳል፤ #በማሕፀኖችም #ውስጥ #ያለን #ሁሉ #ያውቃል

ደረጃ ሶስት
“ሙድጋ”
“ሙድጋ” مُضْغَة ማለት “ቁራጭ ስጋ”embryonic lump” ወይም “የታኘከ ስጋ”chewed gum” ማለት ሲሆን ልክ ጥርስ እንዳረፈበት ስጋ የሚመስልበት የፅንስ ደረጃ ነው፤ ይህን ደረጃ ለማመልከት “ሱምሙ” ثُمَّ “ከዚያም” የሚል መስተፃምር ከመጠቀም ይልቅ “ፈ” فَ “ም” የሚል ቅፅበታዊ መስተፃምር ይጠቀማል፤ ምክንያቱም 21-24 ቀናት የረጋ ደም ጊዜ ሲሆን 24ኛ ቀን ላይ በቅፅፈት የታኘከ ስጋ ቅርፅ ይጀምራል፤ በዚህ ጊዜ “”ፍጥረትዋ ሙሉ ካልሆነች”” ጅማት፣ አንጀት፣ ስስ ጡንቻ፣ ስስ የደም ስር ወዘተ ስለሚፈጠሩ ነው፦
22:5 እላንተ ሰዎች ሆይ! ከመቀስቀስ፣ በመጠራጠር ዉስጥ እንደ ሆናችሁ አፈጣጠራችሁን ተመልከቱ፤ እኛም ከአፈር ፈጠርናችሁ ከዚያም ከፍቶት ጠብታ፣ ከዚያም ከረጋ ደም፣ ከዚያም ከቁራጭ ስጋ مُضْغَةٍ “”ፍጥረትዋ ሙሉ ከኾነችና ሙሉ ካልሆነች”” ችሎታችንን ለእናንተ ልንገልጽላችሁ ፈጠርናችሁ፤
23:12 በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው፤ ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ “የፍትወት ጠብታ” አደረግነው፤ ከዚያም ጠብታዋን “የረጋ ደም” አድርገን ፈጠርን፤ የረጋውን”ም” ደም “ቁራጭ ሥጋ” مُضْغَةً አድርገን ፈጠርን፤

“ፍጥረትዋ ሙሉ የሆነች” ቁራጭ ሥጋ በአምተኛው ደረጃ ላይ ይመጣል፤ ይህንን ለማመልከት “ከመፍጠር በኋላ ሙሉ መፍጠርን ይፈጥራችኋል” ይላል፦
39:6 በእናቶቻችሁ ማህፀኖች ውስጥ፣ በሦስት ጨለማዎች ውስጥ፣ “ከመፍጠር በኋላ ሙሉ መፍጠርን ይፈጥራችኋል”፤

ሶስት ጨለማ የተባሉት፦ ሆድ፣ ማህፀንና የእንግዴ ልጅ ናቸው።

ደረጃ አራት
“ዐዝም”
“ዐዝም” عَظْم በነጠላ ሲሆን “ዒዛም” عِظَام ደግሞ በብዜት ነው፤ ትርጉሙም “አፅም”skeleton” ወይም “አጥንት”bone” ማለት ነው፤ ከ 24-35 ቀናት የቁራጭ ስጋ ሂደት ሲሆን ከመቅፅበት 35ኛው ቀን የደም ዝውርውር፣ የነርቭ ሥርዓት፣ አፅም ወዘተ የሚፈጠርበት ሂደት ነው፤ ይህን አጭር ጊዜ ለማመልከት “ፈ” فَ “ም” የሚል ቅፅበታዊ መስተፃምር ይጠቀማል፦
23:12 በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው፤ ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ “የፍትወት ጠብታ” አደረግነው፤ ከዚያም ጠብታዋን “የረጋ ደም” አድርገን ፈጠርን፤ የረጋውንም ደም “ቁራጭ ሥጋ” አድርገን ፈጠርን፤ ቁራጯን”ም” ሥጋ “አጥንቶች” عِظَامًا አድርገን ፈጠርን፤
ደረጃ አምስት
“ለህም”
“ለህም” لَحْم ማለት “ስጋ” ማለት ሲሆን ይህ ስጋ ጠንካራ ጡንቻ ያለው ስጋ ነው፤ ከ 35-38 ቀናት የአጥንት ሂደት ሲሆን ከመቅፅበት በ 38ኛው ቀን ልብ፣ አንጎል፣ ቆዳ፣አይን፣ አፍንጫ ወዘተ የሚፈጠርበት ሂደት ነው፦
23:12 አጥንቶቹንም “ሥጋን” لَحْمًا አለበስናቸው፤

በዚህ ጊዜ ሩህ ይነፋል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 46, ሐዲስ 1:
ዓብደላህ ኢብን መስዑድ እንዲህ አለ። እውነት ተናጋሪ እና እውነት የተነገራቸው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፦
إِنَّ أَحَدَكُمْ يُجْمَعُ خَلْقُهُ فِي بَطْنِ أُمِّهِ أَرْبَعِينَ يَوْمًا نُطْفَةً، ثُمَّ يَكُونُ عَلَقَةً مِثْلَ ذلِكَ، ثُمَّ يَكُونُ مُضْغَةً مِثْلَ ذلِكَ، ثمَّ يُرْسَلُ إلَيْهِ الْمَلَكُ فَيَنْفُخُ فيهِ الرُّوحَ، وَيُؤمَرُ بأرْبَعِ كَلِمَاتٍ: بِكَتْبِ رِزْقِهِ وَأَجَلِهِ وَعَمَلِهِ وَشَقِيٌّ أوْ سَعِيدٌ.
እያንዳንዳቹህ በእናቱ ሆድ ውስጥ ፍጥረቱ ይሰበሰባል፤ አርባ ቀን የፍትወት ጠብታ ይሆናል፤ ከዛም በተመሳሳይ የረጋ ደምን ይሆናል፤ ከዛም በተመሳሳይ የታኘከን ስጋ ይሆናል፤ ከዛም መልአክ ይላክና ሩሕ ይነፋበታል፤ መልአኩም አራት ነገሮች ላይ ይታዘዛል፦ ሲሳዩን፣ ፍጻሜውን፣ ስራውን፣ የተከፋ ወይንም ደስተኛ መሆኑን እንዲጽፍ ይታዘዛል።

ደረጃ ስድስት
“ነሽአ”
“ነሽአ” نَّشْأَة የሚለው ቃል “አንሸአ” أَنشَأَ “አስገኘ” ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን “ግኝት”production” ማለት ነው፤ አላህም “አንሸናሁ” أَنْشَأْنَاهُ “አስገኘነው” ይለናል፤ ይህም ፅንስ እስከ መወለድ ጊዜ ያለው ሽልን የሚያመለክት ሲሆን “ሌላ ፍጥረትን” ይለዋል፤ በዚህ ጊዜ ከንፈር፣ ጥፍር፣ ፀጉር ወዘተ የሚገኘበት ጊዜ ነው፤ ይህን እረጅም ደረጃ ለማመልከት “ሱምሙ” ثُمَّ “ከዚያም” የሚል መስተፃምር ይጠቀማል፦
23፥12 ከዚያም “ሌላ ፍጥረትን” خَلْقًا آخَرَ አድርገን “አስገኘነው” أَنْشَأْنَاهُ ፤ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ፡፡

መደምደሚያ
አላህ ከራሳችን ጥንድ እንድንረካ መፍጠሩ፣ በመካከላችን መተዛዘንና ፍቅር መኖሩ በመርካትም ማህፀን ውስጥ የሚፈሱት የፍትወት ጠብታ ሰው መሆኑ ለሚያስውሉ ሕዝቦች ከአስደናቂ ታምራቶቹ ተጠቃሽ ነው፦
30:21 ለእናንተም ከራሳችሁ “ጥንዶችን” أَزْوَاجًا “mates” ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፤ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ “ታምራቶቹ” آيَاتِهِ ነው፤ በዚህ ውስጥ ለሚያስውሉ ሕዝቦች “ታምራቶች” አሉ።

ይህንን ታምር አላህ በሥነ-ፅንስ እውቀት በራሳችን ያሉትን የአላህ ታምራት በዘመናችን አሳይቶናል፤ ከዚህ የሚበልጥ ምን መታደል አለ? ምስጋና ሁሉ ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ይሁን፦
41፥53 እርሱም ቁርአን እውነት መሆኑ ለነርሱ እስከሚገለጽላቸው ድረስ፣ በአጽናፎቹ ውስጥ እና #በራሶቻቸውም ውስጥ ያሉትን #ታምራቶቻችንን በእርግጥ #እናሳያቸዋለን፤ ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ መሆኑ አይበቃቸውምን?

ዋቢ መጽሐፍት ይመልከቱ፦
1. The Developing Human ( Prof. Keith Moor & Prof. T. Persaud) Edition 6 – 1998
2. Clinical Anatomy . By Richard Snell ( 3ed edition) published in 1986 – Little, Brown
3. A Scientist’s Interpretation of References to Embryology in the Quran (Prof. Keith Moor) Journal of the Islamic Medical Association, 1986: vol.18, Page 15-16

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የቁርአን ሱራህ

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

መግቢያ
“ሱራህ” سُورَة የሚለው ቃል ትርጉሙ “ምዕራፍ” ወይም “ክፍል” አሊያም “ደረጃ” ማለት ነው፤ ቁርአን ሱራህ እንዳለው አላህ በቁርአን 10 ጊዜ ያነሳዋል፣ ለናሙና ያክል ውስን ጥቅሶችን ብንመለከት፦
24:1 ይህች ያወረድናትና የደነገግናት “ሱራ” سُورَةٌ ናት፣
2:23 በባሪያችንም ላይ ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትኾኑ ከብጤው አንዲትን “ምዕራፍ” بِسُورَةٍ አምጡ፡፡
10:38 በእውነትም «ቀጣጠፈው » ይላሉን «ይህ ከሆነ መሰሉን አንዲት “ሱራ” بِسُورَةٍ አምጡ፡፡
11፥13 ይልቁንም «ቀጣጠፈው» ይላሉን፡- «እውነተኞች እንደሆናችሁ ብጤው የሆኑን ዐስር የተቀጣጠፉ “ሱራዎች” سُوَرٍ አምጡ፡፡
9፥64 መናፍቃን በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ነገር የምትነግራቸው “ሱራ” سُورَةٌ በእነርሱ ላይ መውረዷን ይፈራሉ፡፡

ቁርአን 114 ሱራዎች ሲኖሩት ለ 13 ዓመት 86 ሱራዎች የወረዱት በመካ ሲሆን ለ 10 ዓመት ደግሞ 28 ሱራዎች የወረዱት በመዲና ነው፣ አላህ ቁርአንን በሱራህ ከፋፍሎ ያወረደው ልብህ በማርጋት ለማንበብ እንዲመች ነው፦
17:106 ቁርአንንም በሰዎች ላይ ሆነህ ታነበው ዘንድ “ከፋፈልነው” ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው ።
25:32 እነዚያ የካዱትም፦ ቁርአን በርሱ ላይ ለምን በጠቅላላ አንድ ጊዜ አልተወረደም? አሉ፤ እንደዚሁ በእርሱ ልብህን ልናረጋ “ከፋፍለን” አወረድነው ፤ ቀስ በቀስ “መለያየትም” ለየነው።
3፥3 መጽሐፉን በአንተ ላይ “ከፋፍሎ” በእውነት አወረደ፡፡

አንድ ሱራህ ከሌላው ሱራህ የሚለየው በተስሚያህ ማለትም “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” በሚል ቃል ነው፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 2, ቁጥር 398
ኢብኑ አባስ እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ ሁለት ሱራዎች አይለያዩ በመካከላቸው “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” የሚለው ቃል ወደ እርሳቸው ቢወርድላቸው እንጂ።
قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم لاَ يَعْرِفُ فَصْلَ السُّورَةِ حَتَّى تُنَزَّلَ عَلَيْهِ ‏{‏ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ ‏}‏ ‏
96፥1 አንብብ በዚያ ሁሉን “በፈጠረው ጌታህ ስም”፡፡

እያንዳንዱ ሱራህ ሲጀምር በተስሚያህ ነው ከአንድ ሱራህ በስተቀር፤ ይህም ሱራህ ሱረቱ አት-ተውባህ ነው፤ 9ኛው ሱራህ ተስሚያህ ባይኖርም ሱረቱ አን-ነምል 27፥30 ላይ ይደግመዋል፤ ይህም ሱረቱ አት-ተውባህ የቁጣ ሱራህ ሆና ብትዘለልም የዘጠኝ ድምር የሆነችው ሱረቱ አን-ነምል ላይ ይገኛል፤ 2+7=9 ይሆናል፦
27፥30 «እርሱ ከሱለይማን ነው፡፡ እርሱም “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በኾነው”፡፡

ኦሪት፣ መዝሙራት፣ የነቢያት መጽሐፍት ጸሐፊዎቻቸው ባልሆኑ ሰዎች ቢከፋፈሉም ባይብል ግን በምእራፍ የተከፋፈለው ከ 1244 AD እስከ 1248 AD እቴቨን ላንቶን በሚባል ሰው ነው፤ ከዚያም ባሻገር የመጽሐፍቱን ስም የዳቦ ስም አድርገው በሰው ስም የሰየሙት ነብያት ሳይሆኑ ታሪክ ጸሐፊዎች ናቸው፤ የቁርአን ሱራህ ስም ግን ከመለኮት በጂብሪል ወደ ነብያችን የተላለፈ ነው፤ ይህን ከነብያችን ንግግር ለናሙና ማቅረብ ይቻላል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 6, ሐዲስ 311
ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ “”ከሱረቱል ከህፍ”” መጀመሪያ አስር አናቅፅ ያፈዘ ማንኛውም ከደጃል ይጠበቃል።
أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ مَنْ حَفِظَ عَشْرَ آيَاتٍ مِنْ أَوَّلِ سُورَةِ الْكَهْفِ عُصِمَ مِنَ الدَّجَّالِ ‏”‏
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 21, ሐዲስ 33
ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ “ሱረቱል ያሲንን” በሟቻችሁ ላይ ቅሩ።
قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ اقْرَءُوا ‌‏ يس عَلَى مَوْتَاكُمْ ‏”

የቁርአን ሱራህ እያንዳንዱ ስም በውስጡ ይገኛል ከሶስት ሱራዎች በስተቀር፤ እነርሱም፦ ሱረቱል ኢኽላስ፣ ሱረቱል አንቢያ እና ሱረቱል ፋቲሃ ናቸው፤ እነዚህ ሱራዎች ውስጣቸው ባለው ትርጉም ተሰይመዋል፤ ሌላው 111 ሱራዎች ስማቸው በውስጣቸው ይገኛል፤ ዝርዝሩን ኢንሻላህ በክፍል ሁለት ይዤ እቀርባለው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የቁርአን ሱራህ

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

የቁርአን ሱራህ እያንዳንዱ ስም በውስጡ ይገኛል ከሶስት ሱራዎች በስተቀር፤ እነርሱም፦ ሱረቱል ኢኽላስ፣ ሱረቱል አንቢያ እና ሱረቱል ፋቲሃ ናቸው፤ እነዚህ ሱራዎች ውስጣቸው ባለው ትርጉም ተሰይመዋል፤ ሌላው 111 ሱራዎች ስማቸው በውስጣቸው ይገኛል፤ ይህንን ዝርዝር እንመልከት፦

“በቀራህ”
“በቀራህ” بَقَرَةٌ ማለት “ላም” ወይም “ጊደር” ማለት ሲሆን ሁለተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
2፥68 «ለኛ ጌታህን ጠይቅልን፤ እርሷ ምን እንደኾነች ዕድሜዋን ያብራራልን» አሉ፡፡ «እርሱ እርሷ ያላረጀች ጥጃም ያልኾነች በዚህ መካከል ልከኛ የኾነች *ጊደር* بَقَرَةٌ ናት ይላችኋል፤

“ዒምራን”
“አለ-ዒምራን” َءَالَ عِمْرَٰنَ ማለት “ኢያቄም” ማለት ሲሆን የማርያም አባት ስም ነው፤ *የዒምራንንም ቤተሰብ* ማለት ነው፤ ይህም ሶስተኛው ሱራህ ሲሆን ይህ ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
3፥33 አላህ አደምን፣ ኑሕንም፣ የኢብራሂምንም ቤተሰብ፣ *የዒምራንንም ቤተሰብ* وَءَالَ عِمْرَٰنَ በዓለማት ላይ መረጠ፡፡

“ኒሳእ”
“ኒሳእ” النِّسَاءَ ማለት “ሴቶች” ማለት ሲሆን አራተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
4፥4 *ሴቶችንም* النِّسَاءَ መህሮቻቸውን በደስታ ስጡ፡፡ ለእናንተም ከእርሱ አንዳችን ነገር ነፍሶቻቸው ቢለግሱ መልካም ምስጉን ሲኾን ብሉት፡፡

“ማኢዳህ”
“ማኢዳህ” مَائِدَةً ማለት “ማእድ” ወይም “ገበታ” ማለት ሲሆን አምስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
5፣112 ሐዋርያት፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! ጌታህ በእኛ ላይ ከሰማይ *ማእድን* مَائِدَةً ሊያወርድልን ይችላልን» ባሉ ጊዜ አስታውስ፡፡ «ምእመናን እንደ ኾናችሁ አላህን ፍሩ» አላቸው፡፡

“አንአም”
“አንአም” أَنْعَٰمٌۭ ማለት *”የቤት እንስሳ”* ማለት ሲሆን ስድስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
6፥138 በሐሳባቸውም ይህች እርም የኾነች *”ለማዳ እንስሳ”* أَنْعَٰمٌۭ እና አዝመራ ናት፡፡ የምንሻው ሰው እንጂ ሌላ አይበላትም፡፡

“አዕራፍ”
“አዕራፍ” الْأَعْرَافِ ማለት *”ኮረብታ”* ማለት ሲሆን ሰባተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
7፤46 በመካከላቸውም ግርዶሽ አልለ፡፡ *በአዕራፍም* الْأَعْرَافِ ላይ ሁሉንም በምልክታቸው የሚያውቁ ሰዎች አልሉ፡፡ የገነትንም ሰዎች ሰላም ለናንተ ይኹን በማለት ይጣራሉ፡፡ እነርሱም የሚከጅሉ ሲኾኑ ገና አልገቧትም፡፡

“አንፋል”
“አንፋል” الْأَنفَالِ ማለት *”ምርኮ”* ማለት ሲሆን ስምንተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
8:1 *ከምርኮ* الْأَنفَالِ ይጠይቁሃል፡፡ «የዘረፋ ገንዘቦች የአላህና የመልክተኛው ናቸው፡፡» ስለዚህ አላህን ፍሩ፡፡ በመካከላችሁ ያለችውንም ኹኔታ አሳምሩ፡፡ አማኞችም እንደኾናችሁ አላህንና መልክተኛውን ታዘዙ በላቸው፡፡

“ተውባህ”
“ተውባህ” تَوْبَة ማለት *”ፀፀት”* ወይም “ንስሃ” ማለት ሲሆን ዘጠነኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
2፥102 ሌሎችም በኃጢአቶቻቸው የተናዘዙ መልካም ሥራንና ሌላን መጥፎ ሥራ የቀላቀሉ አልሉ፡፡ አላህ “ከእነሱ ጸጸታቸውን” يَتُوبَ عَلَيْهِمْ ሊቀበል ይከጀላል፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
ዩኑስ”
“ዩኑስ” يُونُسَ ማለት የአላህ ነብይ ሲሆን አስረኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
10:98 ያመነችና እምነትዋ የጠቀማት ከተማ ለምን አልኖረችም ግን *የዩኑስ* يُونُسَ ሕዝቦች ባመኑ ጊዜ በቅርቢቱ ሕይወት የውርደትን ቅጣት ከእነሱ ላይ አነሳንላቸው፡፡ እስከ ጊዜም ድረስ አጣቀምናቸው፡፡

“ሁድ”
“ሁድ” هُودُ ማለት የአላህ ነብይ ሲሆን አስራ አንደኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
11:53 አሉ፡- «*ሁድ* هُودُ ሆይ! በአስረጅ አልመጣህልንም፡፡ እኛም ላንተ ንግግር ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው አይደለንም፡፡ እኛም ለአንተ አማኞች አይደለንም፡፡

“ዩሱፍ” ”
ዩሱፍ” يُوسُفُ ማለት የአላህ ነብይ ሲሆን አስራ ሁለተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
12:4 *ዩሱፍ* يُوسُفُ ለአባቱ፡- «አባቴ ሆይ! እኔ ዐስራ አንድ ከዋክብትን ፀሐይንና ጨረቃንም በሕልሜ አየሁ፡፡ ለእኔ ሰጋጆች ሆነው አየኋቸው» ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡

“ረዕድ”
“ረዕድ” الرَّعْدُ ማለት *ነጎድጓድም* ማለት ሲሆን አስራ ሶስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
13 ፣13 *ነጎድጓድም* الرَّعْدُ አላህን በማመስገን ያጠራል፡፡ መላእክትም እርሱን ለመፍራት ያጠሩታል፡፡

“ኢብራሂም”
“ኢብራሂም” إِبْرَاهِيمُ ማለት የአላህ ነብይ ሲሆን አስራ አራተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
14፣35 *ኢብራሂምም* إِبْرَاهِيمُ ባለ ጊዜ አስታውስ «ጌታዬ ሆይ! ይህንን አገር (መካን) ጸጥተኛ አድርገው፡፡ እኔንም ልጆቼንም ጣዖታትን ከመገዛት አርቀን፡፡

“ሂጅር”
“ሂጅር” الْحِجْرِ ማለት *የሸለቆ ስም* ሲሆን አስራ አምስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
15: 80 *የሒጅርም* الْحِجْرِ ሰዎች መልክተኞቹን በእርግጥ አስተባበሉ፡፡

“ነሕል”
“ነሕል” النَّحْلِ ማለት *ንብ* ማለት ሲሆን አስራ ስድስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
16፣68 ጌታህም ወደ *ንብ* النَّحْلِ እንዲህ ሲል አስታወቀ «ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ቤቶችን ያዢ፡፡

“ኢስራእ”
“ኢስራእ” أَسْرَىٰ ማለት *ጉዞ* ማለት ሲሆን አስራ ሰባተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
17፣1 ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጊድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ ሩቁ መስጊድ በሌሊት ውስጥ “ያስኼደው” أَسْرَىٰ ጌታ ጥራት ይገባው፡፡ ከተዓምራቶቻችን ልናሳየው አስኼድነው፡፡ እነሆ እርሱ አላህ ሰሚው ተመልካቺው ነው፡፡

“ከህፍ”
“ከህፍ” الْكَهْفِ ማለት *ዋሻ* ማለት ሲሆን አስራ ስምንተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
18:9 *የዋሻው* الْكَهْفِ እና የሰሌዳው ባለቤቶች ከተዓምራቶቻችን ሲሆኑ ግሩም መሆናቸውን አሰብክን?

“መርየም”
“መርየም” مَرْيَمَ ማለት “የኢሳ እናት” ስትሆን አስራ ዘጠነኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
19፣16 በመጽሐፉ ውስጥ *መርየምንም* ከቤተሰቧ ወደ ምሥራቃዊ ስፍራ በተለይች ጊዜ አውሳ፡፡

“ጧሃ”
“ጧሃ” طه ማለት ከሃያ ዘጠኙ ሃርፎች አንዱ ሲሆን ሃያኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
20:1 ጠ.ሀ. *ጧሃ* طه

ኢንሻላህ ይቀጥላል….

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የቁርአን ሱራህ

ክፍል ሶስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

“ሐጅ” حَجِّ ማለት “ጉብኝት” ማለት ሲሆን ሃያ ሁለተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
22፥27 አልነውም፡- በሰዎችም ውስጥ *በሐጅ* بِالْحَجِّ ትዕዛዝ ጥራ፡፡

“ሙዕሚኑን”
“ሙዕሚኑን” الْمُؤْمِنُونَ ማለት “ምዕመናን” ወይም “አማኞች” ማለት ሲሆን ሃያ ሶስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
23፣1 *ምእምናን* الْمُؤْمِنُونَ ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ)፡፡

“ኑር”
“ኑር” نُورُ ማለት “ብርሃን” ማለት ሲሆን ሃያ አራተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
24፣35 አላህ የሰማያትና የምድር *አብሪ* نُورُ ነው፡፡

“ፉርቃን”
“ፉርቃን” الْفُرْقَانَ ማለት “እውነትን ከሃሰት መለያ” ማለት ሲሆን ሃያ አምስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
25.1 ያ *ፉርቃንን* الْفُرْقَانَ በባሪያው ላይ ለዓለማት አስፈራሪ ይኾን ዘንድ ያወረደው አምላክ ክብርና ጥራት ተገባው፡፡

“ሹዐራህ”
“ሹዐራህ” وَالشُّعَرَاءُ ማለት “ባለ ቅኔዎችንም” ማለት ሲሆን ሃያ ስድስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
26፣224 *ባለ ቅኔዎችንም* وَالشُّعَرَاءُ ጠማማዎቹ ይከተሉዋቸዋል፡፡

“ነምል”
“ነምል” النَّمْلِ ማለት “ባለ ቅኔዎችንም” ማለት ሲሆን ሃያ ሰባተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
27፣18 *በጉንዳንም* النَّمْلِ ሸለቆ በመጡ ጊዜ አንዲት ጉንዳን «እናንተ ጉንዳኖች ሆይ! ወደ መኖሪያዎቻችሁ ግቡ፡፡ ሱለይማንና ሰራዊቱ እነርሱ የማያውቁ ሲኾኑ አይሰባብሩዋችሁ» አለች፡፡

“ቀሶስ”
“ቀሶስ” الْقَصَصَ ማለት “ባለ ቅኔዎችንም” ማለት ሲሆን ሃያ ስምንተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
28፣25 ከሁለቱ አንደኛይቱም ከሐፍረት ጋር የምትኼድ ሆና መጣችው፡፡ «አባቴ ለእኛ ያጠጣህልንን ዋጋ ሊሰጥህ ይጠራሃል» አለችው፡፡ ወደእርሱ በመጣና ወሬውን በእርሱ ላይ *በተረከለትም* الْقَصَصَ ጊዜ «አትፍራ ከበደለኞቹ ሕዝቦች ድነሃል» አለው፡፡

“ዓንከቡት”
“ዓንከቡት” الْعَنكَبُوتِ ማለት “ሸረሪት” ማለት ሲሆን ሃያ ዘጠነኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
29፣41የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን (ጣዖታትን) የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች *ሸረሪት* الْعَنكَبُوتِ ብጤ ነው፡፡ ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡

“ሩም”
“ሩም” الرُّومُ ማለት “የጣሊያን ሀገር ስም” ሲሆን ሰላሳኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
30፣2 *ሩም* الرُّومُ ተሸነፈች፡፡

“ሉቅማን”
“ሉቅማን” لُقْمَانَ ማለት “የጻድቅ ስም” ሲሆን ሰላሳ አንደኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
31 :12 ለ*ሉቅማንም* لُقْمَانَ ጥበብን በእርግጥ ሰጠነው፡፡

“ሰድጃህ”
“ሰድጃህ” سُجَّدًا ማለት “ሰጋጆች” ሲሆን ሰላሳ ሁለተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
32:15 በአንቀጾቻችን የሚያምኑት እነዚያ በእርሷ በተገሰጹ ጊዜ *ሰጋጆች* سُجَّدًا ሆነው የሚወድቁትና እነርሱም የማይኮሩ ሆነው በጌታቸው ምስጋና ተጎናጽፈው የሚያወድሱት ብቻ ናቸው፡፡

“አሕዛብ”
“አሕዛብ” الْأَحْزَابَ ማለት “ህዝብ” ወይም “ክፍፍል” ማለት ሲሆን ሰላሳ ሶስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
33፥20 መናፍቆች *አሕዛብን* الْأَحْزَابَ አልኼዱም ብለው ያስባሉ፡፡

“ሰበእ”
“ሰበእ” لِسَبَإٍ ማለት “ሳባ” ማለት ሲሆን “የአገር ስም” ነው፤ ሰበእ ሰላሳ አራተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
34:15 *ለሰበእ* لِسَبَإٍ በመኖሪያቸው በእውነት አስደናቂ ምልክት ነበራቸው፡፡ ከግራና ከቀኝ ሁለት አትክልቶች ነበሯቸው፡፡

“ፋጢር”
“ፋጢር” فَاطِرِ ማለት “ፈጣሪ” ማለት ሲሆን ሰላሳ አምስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
35፣1 ምስጋና ሰማያትንና ምድርን *ፈጣሪ* فَاطِرِ ፣ መላእክትን ባለ ሁለት ሁለት፣ ባለ ሶስት ሶስትም፣ ባለ አራት አራትም ክንፎች የኾኑ መልክተኞች አድራጊ ለኾነው አላህ ይገባው፡፡
“ያሲን”
* ያ ሲን* يس ማለት ከሃያ ዘጠኙ ሃርፎች ውስጥ ሲሆኑ ሰላሳ ስድስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
36:1 * ያ ሲን* يس

“ሷፋት”
“ሷፋት” َٱلصَّٰٓفَّٰت ማለት “መሰለፍ” ማለት ሲሆን ሰላሳ ሰባተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
37፥1 መሰለፍን وَٱلصَّٰٓفَّٰتِ በሚሰለፉት፡፡

“ሷድ”
“ሷድ” ص ማለት ከሃያ ዘጠኙ ሃርፎች ውስጥ ሲሆን ሰላሳ ስምንተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
38፡1 ሷድ* ص የክብር ባለቤት በሆነው ቁርኣን እምላለሁ

“ዙመር”
“ዙመር” الَّذِينَ ማለት “ጭፍሮች” ማለት ሲሆን ሰላሳ ዘጠነኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
39 :73 እነዚያም ጌታቸውን የፈሩት የተከፋፈሉ *ጭፍሮች* الَّذِينَ ኾነው ወደ ገነት ይንነዳሉ፡፡

“ጋፊር”
“ጋፊር” غَافِرِ ማለት “መሓሪ” ማለት ሲሆን አርባኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
40:3 ኀጢአትን *መሓሪ* غَافِرِ ፣ ጸጸትንም ተቀባይ፣ ቅጣተ ብርቱ፣ የልግስና ባለቤት ከኾነው (አላህ የወረደ ነው)፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ መመለሻው ወደርሱ ብቻ ነው፡፡

“ፉሲለት”
“ፉሲለት” فُصِّلَتْ ማለት “የተብራሩ” ማለት ሲሆን አርባ አንደኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
41።3 አንቀጾቹ *የተብራሩ* فُصِّلَتْ የኾነ መጽሐፍ ነው፡፡ ዐረብኛ ቁርኣን ሲኾን ለሚያውቁ ሕዝቦች (የተብራራ) ነው፡፡

“ሹራ”
“ሹራ” شُورَىٰ ማለት “መመካከር” ማለት ሲሆን አርባ ሁለተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
42:38 ለእነዚያም የጌታቸውን ጥሪ ለተቀበሉት፣ ሶላትንም ላዘወተሩት፣ ነገራቸውም በመካከላቸው *መመካከር* شُورَىٰ ለኾነው ከሰጠናቸውም ሲሳይ ለሚለግሱት፡፡

“ዙኽሩፍ”
“ዙኽሩፍ” َزُخْرُفًا ማለት “የወርቅ ጌጥንም” ማለት ሲሆን አርባ ሶስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
43:35 *የወርቅ ጌጥንም* وَزُخْرُفًا ባደረግንላቸው ነበር፡፡ ይህም ሁሉ የቅርቢቱ ሕይወት መጣቀሚያ እንጅ ሌላ አይደለም፤ ጠፊ ነው፡፡ መጨረሻይቱም አገር በጌታህ ዘንድ ለጥንቁቆቹ ናት፡፡

“ዱኻን”
“ዱኻን” ِدُخَانٍ ማለት “ጭስ” ማለት ሲሆን አርባ አራተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
44:10 ሰማይም በግልጽ *ጭስ* بِدُخَانٍ የምትመጣበትን ቀን ተጠባበቅ፡፡

“ጃሢያህ”
“ጃሢያህ” جَاثِيَةً ማለት “ተንበርካኪ” ማለት ሲሆን አርባ አምስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
45:28 ሕዝብንም ሁሉ *ተንበርካኪ* جَاثِيَةً ኾና ታያታለህ፡፡ ሕዝብ ሁሉ ወደ መጽሐፏ ትጥጠራለች፡፡ «ዛሬ ትሠሩት የነበራችሁትን ነገር ትመነዳላችሁ» ይባላሉ፡፡

“አሕቃፍ”
“አሕቃፍ” لْأَحْقَافِ ማለት “አሸዋማ የቦታ ስም ነው”፤ አሕቃፍ አርባ ስድስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
46: 21 የዓድንም ወንድም ሁድን ሕዝቦቹን *በአሕቃፍ* بِالْأَحْقَافِ ባስጠነቀቀ ጊዜ አውሳለቸው፡፡

“ሙሐመድ”
“ሙሐመድ” مُحَمَّدٍ “ሰላዋቱል ረቢ አለይሂ ወሰላም” የነብያት መደምደሚያ ናቸው፤ “ሙሐመድ” አርባ ሰባተኛው ሱራህ ሲሆን ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
47:2 እነዚያም ያመኑ፣ በጎዎችንም የሠሩ፣ *በሙሐመድ* مُحَمَّدٍ ላይም የወረደው እርሱ ከጌታቸው ሲኾን እውነት ስለ ኾነ ያመኑ ከእነርሱ ላይ ኃጢአቶቻቸውን ያባብሳል፡፡ ኹኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል፡፡

“ፈትህ”
“ፈትህ” فَتْحًا ማለት “መክፈት” ማለት ሲሆን አርባ ስምንተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
48፣1 እኛ ላንተ ግልጽ የኾነን *መክፈት* فَتْحًا ከፈትንልህ፡፡

“ሑጁራት”
“ሑጁራት” الْحُجُرَاتِ ማለት “ክፍሎች” ማለት ሲሆን አርባ ስምንተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
49:4 እነዚያ *ከክፍሎቹ* الْحُجُرَاتِ ውጭ ኾነው የሚጠሩህ አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡

“ቃፍ”
“ቃፍ” ማለት ከሃያ ዘጠኙ ሃርፎች ውስጥ ሲሆን ሃምሳኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
50:1 *ቃፍ* ق በተከበረው ቁርአን እምላለሁ፤

ኢንሻላህ ይቀጥላል…

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም