ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.9K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነጥብ ሁለት
“የእሳትን ዘበኞች”
ሙፈሲሪን በሐዲስ ላይ በተገኘው ሪዋያህ “ማሊክ” የጀሃነም እሳት ዘበኛ መሆኑን ገልፀዋል፤ ይህም ዘገባ በሐዲስ ላይ ማሊክ የእሳት ዘበኛ መሆኑ ቁልጭ ባለ መልኩ ተጠቅሷል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 59 , ሐዲስ 47:
ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ “በሌሊት ላይ ሁሉት ሰዎች ወደ እኔ ሲመጡ አየሁኝ፤ ከእነርሱ አንዱ እንዲህ አለ፦ ያ እሳት የሚያይዝ “ማሊክ” ሲሆን “የእሳት ዘበኛ” ነው፤ እኔ ጂብሪል ነኝ፣ ይህ ሚካኤል ነው قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ رَأَيْتُ اللَّيْلَةَ رَجُلَيْنِ أَتَيَانِي قَالاَ الَّذِي يُوقِدُ النَّارَ مَالِكٌ خَازِنُ النَّارِ، وَأَنَا جِبْرِيلُ، وَهَذَا مِيكَائِيلُ ።

ምን ትፈልጋላችሁ? ማሊክ የእሳት ዘበኛ መሆኑ ከታወቀ ከአሥራ ዘጠኝ የእሳትንም ዘበኞች አንዱ ነው፤ የእሳትንም ዘበኞች በቁጥር አሥራ ዘጠኝ ሲሆን ከእነርሱ መካከል የልኡካኑ ቡድን አለቃ ማሊክ ነው፦
74:30-31 በእርሷም ላይ አሥራ ዘጠኝ “ዘበኞች” አሉባት፤ አመጠኞች በገሀነም ስቃይ ውስጥ በእርግጥ ዘውታሪዎች ናቸው። የእሳትንም ዘበኞች፣ “መላእክት” እንጅ ሌላ አላደረግንም፤ ቁጥራቸውንም፣ ለነዚያ ለካዱት መፈተኛ እንጅ አላደረግንም፤

ስለዚህ የእሳት ሰዎች “ማሊክ ሆይ!” ያሉት የእሳት ዘበኛ የሆነውን መልአክ ሲሆን “ጌታህ” ያሉት ደግሞ የመላእክት ጌታ የሆነውን አላህ ነው፤ ሆን ብሎ በአላህ ላይ ውሸት መዋሸትና ይህ እውነት ሲመጣ ያስተባበለ ሰው በዳይ ነው፤ ለከሃድያን መኖሪያ ገሃነም ነው፦
39:32 በአላህ ላይም ከዋሸ እውነቱንም በመጣለት ጊዜ ከአስተባበለ ሰው ይበልጥ በላይ በዳይ ማን ነው? በገሀነም ውስጥ ለከሐዲዎች መኖሪያ የለምን?

መደምደሚያ
ድምዳሜዬን በአንድ ማነፃፀሪያ የባይብል ሙግት ልደምድም፤ “ሞሎክ” ወይም “መለክ” מֹלֶךְ ትርጉሙ “ንጉሥ” ማለት ነው፤ ይህ ስም የከነዓን እና የአሞናውያን ጣኦት ስም ነው፤ ይህ ጣዖት የተበጀለት ማንነት የእሳት መልአክ እንደሆነ ስለሚያምኑ ከነዓናውያን በእሳት እንዳይቀጣቸው የበኩር ልጃቸው በሄኖም ሸለቆ ላይ “ቶፌት” ማለትም የእሳት ምድጃ” ሰርተው መስዋዕ ያቀርቡለት፣ ይሰግዱለትና ያመልኩት ነበር፦
ዘሌዋውያን 18፥21 ከዘርህም “ለሞሎክ” לַמֹּ֑לֶךְ በእሳት አሳልፈህ አትስጥ፥ የአምላክህንም ስም አታርክስ፤ እኔ ያህዌህ ነኝ።
ዘሌዋውያን 20፥2 ደግሞ የእስራኤልን ልጆች እንዲህ በላቸው፦ ከእስራኤል ልጆች ወይም በእስራኤል ዘንድ ከሚቀመጡ እንግዶች ማናቸውም ሰው ዘሩን “ለሞሎክ” לַמֹּ֖לֶךְ ቢሰጥ ፈጽሞ ይገደል፤ የአገሩ ሕዝብ በድንጋይ ይውገረው።
አሞጽ 5:26 ለራሳችሁም የሠራችኋቸውን ምስሎች፥ “የሞሎክን” ድንኳንና የአምላካችሁን የሬፋን ኮከብ አነሣችሁ።
ራእይ14፥18 “”በእሳትም ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ”” ከመሠዊያው ወጥቶ ስለታም ማጭድ ያለውን፦ ዘለላዎቹ ፈጽመው በስለዋልና ስለታሙን ማጭድህን ስደድና በምድር ያለውን የወይን ዛፍ ዘለላዎች ቍረጥ ብሎ በታላቅ ድምፅ ጠራ።

አሞጽ 5:26 ላይ “ሞሎክ” מֹלֶךְ ተብሎ የተቀመጠውን ግሪክ ሰፕቱአጀንት”LXX” ላይ “ባሲለዩስ” βασιλεύς ብለውታል፤ ትርጉሙም “ንጉሥ” ማለት ነው፤ ልብ አድርግ “ሞሎክ” ወይም “መለክ” מֹלֶךְ ቃሉና ትርጉሙ አንድ ነው ማለት ቃሉና ትርጉሙ የወከለው ሃሳብ አንድ ነው ማለት አይደለም፤ ምክንያቱም ይህ ስም ለጣኦቱ የተፀውኦ ስም ቢሆንም ለፈጣሪ ግን የባህርይ ስም ሆኖ ተገልፃል፤ ታዲያ ፈጣሪ የከነዓን እና የአሞናውያን ጣኦት ነውን? እንደማትሉኝ ግልፅ ነው፤ ፈጣሪ ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር “ንጉሥ” ነው፤ እርሱ ታላቅ ንጉሥ ነው፦
መዝሙር 74፥12 ያህዌህ ግን ከዓለም አስቀድሞ “ንጉሥ” מֶ֖לֶךְ ነው፥
መዝሙር 95፥3 ያህዌህ ታላቅ አምላክ ነውና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ ታላቅ “ንጉሥ” מֶ֖לֶךְ ነውና።
መዝሙር 47፥2 ያህዌህ ልዑል ግሩምም ነውና፥ በምድር ሁሉ ላይም ታላቅ “ንጉሥ” מֶ֖לֶךְ ነውና።
መዝሙር 47፥7 ያህዌህ ለምድር ሁሉ “ንጉሥ” מֶ֖לֶךְ ነውና፤

ከላይ ያለውን የቁርአን ሃሳብ በዚህ ስሌት ተረዱት።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ለዲያብሎስ እርድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

22፥34 *ለሕዝብም ሁሉ ወደ አላህ መስዋዕት ማቅረብን ደነገግን፡፡ ከቤት እንስሳት በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ብቻ ያወሱ ዘንድ አዘዝናቸው፡፡ አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ ታዘዙ*፡፡ وَلِكُلِّ أُمَّةٍ جَعَلْنَا مَنسَكًا لِّيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّن بَهِيمَةِ الْأَنْعَامِ ۗ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا

“መንሠክ” مَنسَك ማለት “መስዋዕት” ወይም “ሥርዓተ ሃይማኖት” ማለት ሲሆን “ሀድይ” هَدْي ማለት “የእርድ እንስሳ” ማለት ነው፤ ይህም እርድ ጊደር፣ በግ፣ ፍየል፣ ጥጃ፣ ግመል ነው፤ ይህ ለአላህ የሚቀርበው መስዋዕት “ቁርባን” ይባላል፤ “ቁርባን” قُرْبَان የሚለው ቃል “ቀርረበ” قَرَّبَ ማለትም “አቀረበ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መቃረቢያ” “አምሃ” “እጅ መንሻ” ማለት ነው፤ አምላካችን አላህ ለሕዝብም ሁሉ ወደ እርሱ መስዋዕት ማቅረብን አዟል፦
22፥34 *ለሕዝብም ሁሉ ወደ አላህ መስዋዕት ማቅረብን ደነገግን፡፡ ከቤት እንስሳት በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ብቻ ያወሱ ዘንድ አዘዝናቸው፡፡ አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ ታዘዙ*፡፡ وَلِكُلِّ أُمَّةٍ جَعَلْنَا مَنسَكًا لِّيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّن بَهِيمَةِ الْأَنْعَامِ ۗ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا

ይህ ሆኖ ሳለ ግን በባይብል ላይ መስዋዕት ለሁለት ምንነቶች እንዲቀርብ ታዟል፤ አንዱ ለፈጣሪ ሲሆን ሁለተኛው ለዲያብሎስ ነው፦
ዘሌዋውያን 16፥8 አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፥ *አንዱን ዕጣ ለያህዌህ ሌላውንም ዕጣ ለዐዛዝኤል*።

ዕብራይስጡ፦
וְנָתַן אַהֲרֹן עַל-שְׁנֵי הַשְּׂעִירִם, גֹּרָלוֹת--גּוֹרָל אֶחָד לַיהוָה, וְגוֹרָל אֶחָד לַעֲזָאזֵל.
ዐረቢኛው፦
وَيُلْقِي هَارُونُ عَلَى التَّيْسَيْنِ قُرْعَتَيْنِ: قُرْعَةً لِلرَّبِّ وَقُرْعَةً لِعَزَازِيل
ኢንግሊሹ፦
"There he shall draw lots, using two stones, one marked *"for the LORD"* and the other *"for Azazel*."(Good News Translation)

ሁለት ፍየል እጣ ይጣልበታል፤ አንዱ ለያህዌህ ሁለተኛ ለዐዛዝኤል ነው፤ ተርጓሚዎች "ዐዛዝኤል" የሚለው ቃል "መለቀቅ" " የምድረ-በዳ ፍየል" እያሉ ትርጉሙን ሊያዛቡ ቢፈልጉም የዕብራይስጡ "ዐዛዝኤል" עֲזָאזֵל የዐረቢኛው "ዐዛዚል" عَزَازِيل ብሎ በግልጽ አስቀምጦታል፤ "ዐዛዝኤል" ታዲያ ማን ነው? የጥንት ሆነ የአሁን የባይብል ማብራሪያዎች ጋኔን ነው ብለው አስቀምጠውታል፤ ይህ ጋኔን ስሙ በመጽሐፈ ሄኖክ ላይ ከሃያ አንዱ አጋንንት አስረኛው ጋኔን ዐዛዝኤል ነው፦
ሄኖክ 19፥10-12 *የእነዚያ የአጋንንት ስማቸው እንደዚህ ነው*፦
አለቃቸው ስማዝያ፣ ሁለተኛውም አርስጢኪፋ ነው፣ ሥስተኛውም አርሚን ነው፣ አራተኛውም ኮክብኤል ነው። አምስተኛውም ጡርኤል ነው፣ ስድስተኛውም ሩምያል ነው፣ ሰባተኛውም ዳንኤል ነው፣ ስምንተኛውም ምቃኤል ነው፣ ዘጠነኛውም በራቃኤል ነው፣ *አስረኛውም "አዛዝኤል" ነው*፣ አስራ አንደኛውም አርማሮስ ነው፣ አስራ ሁለተኛውም በጠርያል ነው*።
ሄኖክ 3፥10 *በዐዛዝኤል ሥራና ትምህርት ምድር ሁሉ ጠፋች፤ የሰውን ሁሉ ኃጢአት በእርሱ ጻፍበት አለው*።
ሄኖክ 15፥7 *በአዛዝኤል ይፈረድበታል፤ በወገኖችሁ ሁሉ፤ በመላእክት ጌታ ስም ባላመኑ በሰራዊቱም ሁሉ ይፈረድባቸዋል*።

ዐዛዝኤል በግዕዝ ትውፊታዊ አጠራሩ "ሳጥናኤል" ይባላል፤ ከሥነ-አምክኖ አንጻር እስቲ እዩት አንዱ ለፈጣሪ ሁለተኛው ለመለቀቅ ወይም ለምድረ-በዳ ፍየል ይገበርለት እንበልና፤ ለምንስ ለመለቀቅ ወይም ለምድረ-በዳ ፍየል ይገበራል? ከያህዌህ በስቀር ለሌላ የሚሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ ተብሏል እኮ፦
ዘጸአት 22፥20  *ከያህዌህ በቀር ለአንዳች አምላክ የሚሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ*።

ከአንዱ አምላክ ውጪ ለሌላ ማንነትና ምንነት መስዋዕት መሰዋት ይህንን ያክል ከባድ ወንጀል ከሆነ እንግዲያውስ ለሳጥናኤል የፍየል መስዋዕት አቅርብ የሚለውን የብርዘት ውጤት ትታችሁ ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ብቻ እንድትሰዉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፤ ሙስሊም መስዋዕቱ ለፈጠረው ብቻ ነው፦
6፥162 *«ሶላቴ፣ "መስዋዕቴም"፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው»* በል፡፡ قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኒፋቅ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥145 *መናፍቃን በእርግጥ ከእሳት በታችኛው አዘቅት ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱም ረዳትን አታገኝላቸውም*፡፡ إِنَّ الْمُنَافِقِينَ فِي الدَّرْكِ الْأَسْفَلِ مِنَ النَّارِ وَلَن تَجِدَ لَهُمْ نَصِيرًا

"ኒፋቅ" نِفَاق የሚለው ቃል "ናፈቀ" نَافَقَ ማለትም "ነፈቀ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ኑፋቄ" ወይም "ምንፍቅና" አሊያም "አስመሳይነት" ማለት ነው፤ "ኑፋቄ" የሚለው የግዕዝ ቃል "ነፈቀ" ማለትም "ከፈለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ክፍልፍል" ወይም "አራጥቃ" ማለት ነው፤ ዓመት ለሁለት ስንከፍለው ስድስት ወሩ "መንፈቅ" ይባላል።አለቃ ኪዳነ-ወልድ ክፍሌ ገፅ 645።

ኒፋቅ በውስጥ ኩፍር በውጪ ኢማን የሆነ ሁለት አይነት ገጽታ ያለው ነገር ነው፤ ኒፋቅ ያለበት ግለሰብ ደግሞ በነጠላ "ሙናፊቅ" مُنَٰفِق ሲባል በብዜት "ሙናፊቁን" مُنَٰفِقُون ወይም "ሙናፊቂን" مُنَٰفِقِين ይባላል፤ በአማርኛችን "መናፍቅ" "መናፍቃን" ማለት ነው። አላማቸው ኡማውን መከፋፈልና መበታተን ነው፦
63፥7 *እነርሱ እነዚያ ፡- «አላህ መልክተኛ ዘንድ ላሉት ሰዎች እስከሚበታተኑ ድረስ አትቀልቡ» የሚሉ ናቸው፡፡ የሰማያትና የምድር ድልቦችም የአላህ ናቸው፡፡ ግን መናፍቃን አያውቁም*፡፡ هُمُ الَّذِينَ يَقُولُونَ لَا تُنفِقُوا عَلَىٰ مَنْ عِندَ رَسُولِ اللَّهِ حَتَّىٰ يَنفَضُّوا ۗ وَلِلَّهِ خَزَائِنُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَلَـٰكِنَّ الْمُنَافِقِينَ لَا يَفْقَهُونَ

ውጪአቸው አማኝ ነው ውስጣቸው ግን ክህደት አለ፤ ወደ ሶላትም በቆሙ ጊዜ ታካቾች ስዎችን የሚያሳዩ ኾነው ይቆማሉ፤ አላህን እና እነዚያን ያመኑትን ያታልላሉ፤ የማያውቁ ሲኾኑ እራሳቸውን እንጅ ሌላን አያታልሉም፤ ወደ ቁርኣንና ወደ ሐዲስ አይመጡም፦
4፥142 *መናፍቃን አላህን ያታልላሉ፡፡ እርሱም አታላያቸው ነው፡፡ ወደ ሶላትም በቆሙ ጊዜ ታካቾች ስዎችን የሚያሳዩ ኾነው ይቆማሉ፡፡ አላህንም ጥቂትን እንጅ አያወሱም*፡፡ إِنَّ الْمُنَافِقِينَ يُخَادِعُونَ اللَّهَ وَهُوَ خَادِعُهُمْ وَإِذَا قَامُوا إِلَى الصَّلَاةِ قَامُوا كُسَالَىٰ يُرَاءُونَ النَّاسَ وَلَا يَذْكُرُونَ اللَّهَ إِلَّا قَلِيلًا
2፥8 *ከሰዎችም «በአላህና በመጨረሻው ቀን አምነናል» የሚሉ አሉ፤ እነርሱም አማኞች አይደሉም*፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يَقُولُ آمَنَّا بِاللَّهِ وَبِالْيَوْمِ الْآخِرِ وَمَا هُم بِمُؤْمِنِينَ
2፥9 *አላህን እና እነዚያን ያመኑትን ያታልላሉ፤ የማያውቁ ሲኾኑ እራሳቸውን እንጅ ሌላን አያታልሉም*፡፡ يُخَادِعُونَ اللَّهَ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَمَا يَخْدَعُونَ إِلَّا أَنفُسَهُمْ وَمَا يَشْعُرُونَ
3፥167 *እነዚያንም የነፈቁትን* እና ለእነርሱ «ኑ፤ በአላህ መንገድ ተጋደሉ፤ ወይም ተከላከሉ፤» የተባሉትን ሊገልጽ ነው፡፡ «መዋጋት መኖሩን ብናውቅ ኖሮ በተከተልናችሁ ነበር» አሉ፡፡ *እነርሱ ያን ጊዜ ከእምነት ይልቅ ወደ ክህደት የቀረቡ ናቸው፡፡ በልቦቻቸው የሌለውን በአፎቻቸው ይናገራሉ፡፡ አላህም የሚደብቁትን ዐዋቂ ነው*፡፡ وَلِيَعْلَمَ الَّذِينَ نَافَقُوا ۚ وَقِيلَ لَهُمْ تَعَالَوْا قَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ أَوِ ادْفَعُوا ۖ قَالُوا لَوْ نَعْلَمُ قِتَالًا لَّاتَّبَعْنَاكُمْ ۗ هُمْ لِلْكُفْرِ يَوْمَئِذٍ أَقْرَبُ مِنْهُمْ لِلْإِيمَانِ ۚ يَقُولُونَ بِأَفْوَاهِهِم مَّا لَيْسَ فِي قُلُوبِهِمْ ۗ وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا يَكْتُمُونَ
4፥61 ለእነርሱም፡- *«አላህ ወደ አወረደው ቁርኣን እና ወደ መልክተኛው ኑ» በተባሉ ጊዜ መናፍቃን ከአንተ መሸሽን ሲሸሹ ታያቸዋለህ*፡፡ وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ تَعَالَوْا إِلَىٰ مَا أَنزَلَ اللَّهُ وَإِلَى الرَّسُولِ رَأَيْتَ الْمُنَافِقِينَ يَصُدُّونَ عَنكَ صُدُودًا
2፥14 *እነዚያንም ያመኑትን በተገናኙ ጊዜ «አምነናል» ይላሉ፡፡ ወደ ሰይጣኖቻቸውም ባገለሉ ጊዜ «እኛ ከእናንተ ጋር ነን፤ እኛ በእነርሱ ተሳላቂዎች ብቻ ነን»* ይላሉ፡፡ وَإِذَا لَقُوا الَّذِينَ آمَنُوا قَالُوا آمَنَّا وَإِذَا خَلَوْا إِلَىٰ شَيَاطِينِهِمْ قَالُوا إِنَّا مَعَكُمْ إِنَّمَا نَحْنُ مُسْتَهْزِئُونَ

የመናፍቃን ቅጣቱ ከእሳት በታችኛው አዘቅት ውስጥ ናቸው፦
4፥145 *መናፍቃን በእርግጥ ከእሳት በታችኛው አዘቅት ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱም ረዳትን አታገኝላቸውም*፡፡ إِنَّ الْمُنَافِقِينَ فِي الدَّرْكِ الْأَسْفَلِ مِنَ النَّارِ وَلَن تَجِدَ لَهُمْ نَصِيرًا
9፥68 *መናፍቃንንና መናፍቃትን፣ ከሓዲዎችንም አላህ የገሀነምን እሳት በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ ቃል ገብቶላቸዋል፡፡ እርሷ በቂያቸው ናት፡፡ አላህም ረግሟቸዋል፡፡ ለእነርሱም ዘውታሪ ቅጣት አላቸው*፡፡ وَعَدَ اللَّهُ الْمُنَافِقِينَ وَالْمُنَافِقَاتِ وَالْكُفَّارَ نَارَ جَهَنَّمَ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ هِيَ حَسْبُهُمْ ۚ وَلَعَنَهُمُ اللَّهُ ۖ وَلَهُمْ عَذَابٌ مُّقِيمٌ
የሙናፊቅ ምልክቶች ሦስት ናቸው፦ ሲናገር ይዋሻል፣ ሲያምኑት ይከዳል፣ ቃል የገባውን ያፈርሳል፦
 ኢማም ቡኻሪይ  መጽሐፍ 55, ሐዲስ 12
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው ነብዩ"ﷺ" ሲናገሩ፦ *"የሙናፊቅ ምልክቶች ሦስት ናቸው፦ ሲናገር ይዋሻል፣ ሲያምኑት ይከዳል፣ ቃል የገባውን ያፈርሳል*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ آيَةُ الْمُنَافِقِ ثَلاَثٌ، إِذَا حَدَّثَ كَذَبَ، وَإِذَا اؤْتُمِنَ خَانَ، وَإِذَا وَعَدَ أَخْلَفَ ‏.‏

ነጥብ አንድ
"ሲታመን ይከዳል"
አምላካችን አላህ አማና ሲጣልብን አማናችን መወጣት እንዳለብን እንዲህ ይነግረናል፦
4፥58 *አላህ አደራዎችን ወደ ባለቤቶቻቸው እንድታደርሱ ያዛችኋል*፡፡ በሰዎችም መካከል በፈረዳችሁ ጊዜ በትክክል እንድትፈርዱ ያዛችኋል፡፡ አላህ በርሱ የሚገሥጻችሁ ነገር ምን ያምር! አላህ ሰሚ ተመልካች ነው፡፡ إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُكُمْ أَن تُؤَدُّوا الْأَمَانَاتِ إِلَىٰ أَهْلِهَا وَإِذَا حَكَمْتُم بَيْنَ النَّاسِ أَن تَحْكُمُوا بِالْعَدْلِ ۚ إِنَّ اللَّهَ نِعِمَّا يَعِظُكُم بِهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ سَمِيعًا بَصِيرًا
8፥27 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህንና መልክተኛውን አትክዱ፡፡ *አደራዎቻችሁንም እናንተ እያወቃችሁ አትክዱ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَخُونُوا اللَّهَ وَالرَّسُولَ وَتَخُونُوا أَمَانَاتِكُمْ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
23፥8 *እነዚያም እነርሱ ለአደራዎቻቸው እና ለቃል ኪዳናቸው ጠባቂዎች*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ
70፥32 *እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውን እና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ

ነጥብ ሁለት
"ሲናገር ይዋሻል"
ሙስሊም ከዋሸ ቀኑ ተበላሸ ይላል ያገሬ ሰው፤ አንድ ሙናፊቅ "አባይ" "ቀላማጅ" "ዋሾ" "በጥራቃ" "ውሸታም" "ሐሰተኛ" "ወሽከታ" ነው፤ አምላካችን አላህ፦ "ሐሰትንም ቃል ራቁ" "ትክክለኛንም ንግግር ተናገሩ" ብሎ ያዘናል፦
22፥30 ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ፡፡ *ሐሰትንም ቃል ራቁ*፡፡ فَاجْتَنِبُوا الرِّجْسَ مِنَ الْأَوْثَانِ وَاجْتَنِبُوا قَوْلَ الزُّورِ
33፥70 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ *ትክክለኛንም ንግግር ተናገሩ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَقُولُوا قَوْلًا سَدِيدًا

ኢንሻላህ በክፍል ሁለት ይቀጥላል...

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኒፋቅ

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥145 *መናፍቃን በእርግጥ ከእሳት በታችኛው አዘቅት ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱም ረዳትን አታገኝላቸውም*፡፡ إِنَّ الْمُنَافِقِينَ فِي الدَّرْكِ الْأَسْفَلِ مِنَ النَّارِ وَلَن تَجِدَ لَهُمْ نَصِيرًا

ነጥብ ሦስት
"ቃል ገብቶ ያፈርሳል"
ቃል ገብቶ ማፍረስ ከመሃላ አይተናነስም፤ አምላካችን አላህ፦ "በቃል ኪዳኖች ሙሉ" ይለናል፦
5፥1 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በቃል ኪዳኖች ሙሉ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَوْفُوا بِالْعُقُودِ ۚ
23፥8 *እነዚያም እነርሱ ለአደራዎቻቸው እና ለቃል ኪዳናቸው ጠባቂዎች*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ
70፥32 *እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውን እና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ
17፥34 የየቲምንም ገንዘብ የብርታቱን ጊዜ እስኪደርስ ድረስ በዚያች እርሷ መልካም በኾነች ኹኔታ እንጂ አትቅረቡ፡፡ *በኪዳናችሁም ሙሉ፤ ኪዳን የሚጠየቁበት ነውና*፡፡ وَلَا تَقْرَبُوا مَالَ الْيَتِيمِ إِلَّا بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ حَتَّىٰ يَبْلُغَ أَشُدَّهُ ۚ وَأَوْفُوا بِالْعَهْدِ ۖ إِنَّ الْعَهْدَ كَانَ مَسْئُولًا

ነገር ግን ይህ ምልክት የሚታይበት ሁሉ ሙናፊቅ ላይሆን ይችላል፤ ግን መናፍቅ የሚያሰኘው ጉዳይ ነብያችን"ﷺ" እንዲህ ይነግሩናል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 116
ዐብዱላህ ኢብኑ ዐምር"ረ.ዐ." እንደነገረን የአላህ መልክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፡- *“አራት ነገሮች ያሉበት ሰው ግልጽ መናፍቅ ሆኗል፤ ከአራቱ ውስጥ አንዱ ያለበት ሰው ደግሞ እስኪተወው ድረስ ከኑፋቄ ከፊሉ ጠባይ አለበት ማለት ነው፤ አራቱ ነገሮች፡- ሲታመን ይከዳል፣ ሲናገር ይዋሻል፣ ቃል ገብቶ ያፈርሳል፣ ሲሟገት ያስተባብላል*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ أَرْبَعٌ مَنْ كُنَّ فِيهِ كَانَ مُنَافِقًا خَالِصًا وَمَنْ كَانَتْ فِيهِ خَلَّةٌ مِنْهُنَّ كَانَتْ فِيهِ خَلَّةٌ مِنْ نِفَاقٍ حَتَّى يَدَعَهَا إِذَا حَدَّثَ كَذَبَ وَإِذَا عَاهَدَ غَدَرَ وَإِذَا وَعَدَ أَخْلَفَ وَإِذَا خَاصَمَ فَجَرَ ‏"‏ ‏

ነጥብ አራት
"ሲሟገት ያስተባብላል"
መናፍቃን የአላህ አንቀጾች ግልጾች ኾነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ መከራከር ይወዳሉ፦
45፥25 *አንቀጾቻችንም ግልጾች ኾነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ ክርክራቸው* «እውነተኞች እንደ ኾናችሁ አባቶቻችንን አምጡ» *ማለት እንጅ ሌላ አልነበረም*፡፡ وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ آيَاتُنَا بَيِّنَاتٍ مَّا كَانَ حُجَّتَهُمْ إِلَّا أَن قَالُوا ائْتُوا بِآبَائِنَا إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ
10፥95 *ከእነዚያም የአላህን አንቀጾች ከአስተባበሉት አትሁን፡፡ ከከሳሪዎቹ ትሆናለህና*፡፡ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِ اللَّهِ فَتَكُونَ مِنَ الْخَاسِرِينَ
4፥107 *ከነዚያም እራሳቸውን ከሚበድሉት ላይ አትከራከር*፤ አላህ ከዳተኛ ኀጢአተኛ የሆነን ሰው አይወድምና። وَلَا تُجَادِلْ عَنِ الَّذِينَ يَخْتَانُونَ أَنفُسَهُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ خَوَّانًا أَثِيمًا

ነጥብ አምስት
"በጥቂት አለመብቃቃት"
በጥቂት መብቃቃትን የአማኞች ባህርይ ነው፤ በጥቂት አለመብቃቃት የመናፍቃን ባህርይ ነው፦
ኢማም ቡኻሪይ: መጽሐፍ 70, ሐዲስ 22
አቢ ዑመር”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ሙዕሚን በአንድ አንጀት ይመገባል፤ ካፊር ወይም ሙናፊቅ በሰባት አንጀት ይመገባል*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّ الْمُؤْمِنَ يَأْكُلُ فِي مِعًى وَاحِدٍ، وَإِنَّ الْكَافِرَ ـ أَوِ الْمُنَافِقَ فَلاَ أَدْرِي أَيَّهُمَا قَالَ عُبَيْدُ اللَّهِ ـ يَأْكُلُ فِي سَبْعَةِ أَمْعَاءٍ ‏”‌‏.

ሙዕሚን በአንድ አንጀት ይመገባል ማለት ሲበላ በቢሥሚላህ ስለሚጀምር በረካ አለው፣ ያጣቅመዋል እና ይብቃቃል ማለት እንጅ አንድ ነው አንጀቱ ማለት አይደለም። በተጨማሪም ካፊር ወይም ሙናፊቅ በሰባት አንጀት ይመገባል ማለት በቢሥሚላህ ስለማይጀምር በረካ የለውም፣ አያጣቅመውም እና አይብቃቃም ማለት እንጅ ሰባት ነው አንጀቱ ማለት አይደለም። ይህ “መዕነዊይ” ማለትም “ፍካሬአዊ” አነጋገር እንጂ “ሒስሲይ” ማለትም “እማሬአዊ” አይደለም።
ነጥብ ስድስት
"ቁርአንን የሚቀራ ሙናፊቅ"
ቁርአንን የሚቀራ ሙናፊቅ ልክ እንደ አሪቲ ነው፤ ሽታው ያውዳል ጣዕሙ ግን ይመራል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 6 , ሐዲስ 288,
ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *“ቁርአንን የሚቀራ አማኝ ምሳሌው ልክ “እንደ” ትርንጎ ነው፤ ሽታው ጥሩ ነው ጣዕሙም ጥሩ ነው። ቁርአንን የማይቀራ አማኝ ደግሞ ልክ እንደ ተምር ነው፤ ሽታ የለውም ጣዕም ግን አለው። ቁርአንን የሚቀራ ሙናፊቅ አምሳያው ልክ እንደ አሪቲ ነው፤ ሽታው ያውዳል ጣዕሙ ግን ይመራል። ቁርአንን የማይቀራ ሙናፊቅ ደግሞ ልክ እንደ እንቧይ ነው ሽታ የለውም፤ ጣዕሙም መራራ ነው”* عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْمُؤْمِنُ الَّذِي يَقْرَأُ الْقُرْآنَ وَيَعْمَلُ بِهِ كَالأُتْرُجَّةِ، طَعْمُهَا طَيِّبٌ وَرِيحُهَا طَيِّبٌ، وَالْمُؤْمِنُ الَّذِي لاَ يَقْرَأُ الْقُرْآنَ وَيَعْمَلُ بِهِ كَالتَّمْرَةِ، طَعْمُهَا طَيِّبٌ وَلاَ رِيحَ لَهَا، وَمَثَلُ الْمُنَافِقِ الَّذِي يَقْرَأُ الْقُرْآنَ كَالرَّيْحَانَةِ، رِيحُهَا طَيِّبٌ وَطَعْمُهَا مُرٌّ، وَمَثَلُ الْمُنَافِقِ الَّذِي لاَ يَقْرَأُ الْقُرْآنَ كَالْحَنْظَلَةِ، طَعْمُهَا مُرٌّ ـ أَوْ خَبِيثٌ ـ وَرِيحُهَا مُرٌّ ‏”

ኒፋቅ በሁለት ይከፈላል፤ አንደኛው ኒፋቁል አስገር ሲሆን ይህ ባህርይ ያለበት ሙናፊቅ ባይሰኝም ግን ከላይ የተዘረዘሩት የታመኑት ጊዜ መካድ፣ ሲናገሩ መዋሸት፣ ቃል ገብቶ ማፍረስ፣ ቀጠሮን ማዛባት፣ ሲከራከር ማስተባበል ናቸው።
ሁለተኛው ኒፋቁል አክበር ሲሆን ይህ ሰው ሙናፊቅ ይባላል፤ የትልቁ ኒፋቅ ምልክቶች የአላህን መልእክተኛ ማስተባበል፣ የተቀበሉትን መልእክት በከፊሉ ማስተባበል፣ እሳቸውን መጥላት፣ መልእክታቸውን መጥላት፣ በኢስላም ዝቅ ማለት መደሰት፣ የኢስላም የበላይነትን መጥላት ናቸው ወዘተ ናቸው። ሙናፊቅ ማለት የሚችለው አላህ ብቻ ነው። ምክንያቱም ኒፋቅ ልብ ላይ ያለ በሽታ ነው፦
4፥63 *እነዚህ እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው፤ እነርሱንም ተዋቸው፤ ገሥጻቸውም፤ ለእነርሱም በራሳቸው ውስጥ ስሜት ያለውን ቃል ተናገራቸው*። ﺃُﻭﻟَﺌِﻚَ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﻌْﻠَﻢُ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻣَﺎ ﻓِﻲ ﻗُﻠُﻮﺑِﻬِﻢْ ﻓَﺄَﻋْﺮِﺽْ ﻋَﻨْﻬُﻢْ ﻭَﻋِﻈْﻬُﻢْ ﻭَﻗُﻞْ ﻟَﻬُﻢْ ﻓِﻲ ﺃَﻧْﻔُﺴِﻬِﻢْ ﻗَﻮْﻟًﺎ ﺑَﻠِﻴﻐًﺎ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ
3፥118 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *ከእናንተ ሌላ ምስጢረኛን አትያዙ፤ ማበላሸትን አይገቱላችሁም፤ ጉዳታችሁን ይወዳሉ፥ ጥላቻይቱ ከአፎቻቸዉ በእርግጥ ተገለጸች። ልቦቻቸዉም የሚደብቁት ይበልጥ ትልቅ ነዉ*። ልብ የምታደርጉ እንደሆናችሁ ለእናንተ ማብራራያዎችን በእርግጥ ገለጽን። يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا بِطَانَةً مِّن دُونِكُمْ لَا يَأْلُونَكُمْ خَبَالًا وَدُّوا مَا عَنِتُّمْ قَدْ بَدَتِ الْبَغْضَاءُ مِنْ أَفْوَاهِهِمْ وَمَا تُخْفِي صُدُورُهُمْ أَكْبَرُ ۚ قَدْ بَيَّنَّا لَكُمُ الْآيَاتِ ۖ إِن كُنتُمْ تَعْقِلُونَ

አላህ የቀልብ በሽታ ከሆነው ከኒፋቅ ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ቅጥፈት ይብቃ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥105 *ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ብቻ ናቸው፤ እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው*፡፡ إِنَّمَا يَفْتَرِي الْكَذِبَ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ۖ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَاذِبُونَ

ግብጻዊ ቄስ ዘካሪያስ ሁልጊዜ ለሚቀጥፈው ቅጥፈት ምላሽ ሲሰጠው እየተገለባበጠ ኢስላምን የሚያጠለሽበት ጥላሸት ለመፈለግ ቀን ከሌሊት ይዳክራል፤ ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ብቻ ናቸው፤ እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው፦
16፥105 *ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ብቻ ናቸው፤ እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው*፡፡ إِنَّمَا يَفْتَرِي الْكَذِبَ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ۖ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَاذِبُونَ

ከቀጠፈው ቅጥፈት አንዱ ነብያችንን"ﷺ" ከሬሳ ጋር ተራክቦ እንዳደረጉ አድርጎ መቅጠፉ ነው፤ ወሊ-አዑዝቢሏህ እኔ ለደገሙት ቃል ሰቀጠጠኝ፤ ህሊናውን ለሸጠ ሰው እና ሃሰትን ለተከናነበ ሰው ይህን ማድረግ ውስጡን ሰላም አይሰጠውም፤ እስቲ የሚያነሳቸውን ሐዲሳት እንመልከት፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 23, ሐዲስ 98
አነሥ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ሴት ልጅ የቀብር ሥርአት ላይ ነበርን፤ የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" በመቃብር አቅራቢያ ተቀምጠው ዓይኖቻቸው በእንባ ሞልተው አየዋቸው፤ እርሳቸውም፦ "ከመካከላችሁ በዚህ ሌሊት ከሚስቱ ጋር ተራክቦ ያላደረገ አለን? አሉ፤ አቡ ጠልሓህም፦ "እኔ አለሁ" ብሎ መለሰ፤ እርሳቸውም፦ "ወደ መቃብሯ ውረድ" አሉት፤ እርሱም ወደ መቃብሯ ወረዶ ቀበራት*። عَنْ أَنَسٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ شَهِدْنَا بِنْتَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَرَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم جَالِسٌ عَلَى الْقَبْرِ، فَرَأَيْتُ عَيْنَيْهِ تَدْمَعَانِ فَقَالَ ‏"‏ هَلْ فِيكُمْ مِنْ أَحَدٍ لَمْ يُقَارِفِ اللَّيْلَةَ ‏"‌‏.‏ فَقَالَ أَبُو طَلْحَةَ أَنَا‏.‏ قَالَ ‏"‏ فَانْزِلْ فِي قَبْرِهَا ‏"‌‏.‏ فَنَزَلَ فِي قَبْرِهَا فَقَبَرَهَا‏.‏

ከመነሻው እዚህ ሐዲስ ላይ እከሌ ከሬሳ ጋር ወሲብ ፈጸመ የሚል ሽታው እንኳን ቢፈለግ የለም፤ ውሸት ሲጋለጥ ከዚህ ይጀመራል።
ሲቀጥል "ኔክሮፊሊያ"Necrophilia" ማለት ከሬሳ ጋር የሚደረግ ተራክቦ ነው፤ በኢስላም አይደለም ከሞተ ሰው ይቅርና በቁም ካለ ሰው ጋር ተራክቦ ለማድረግ ኒካሕ ይወጅባል። እስቲ ሁለተኛውን ሐዲስ እንመልከት፦
ከንዙል ዑማል 242218
ኢብኑ አባስ እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" አሉ፦ *"የጀነትን ልብስ እስከምትለብስ ልብሴን አለበስኳት፤ በመቃብሯ ውስጥ አብሬ ተጋደምኩኝ፤ ምናልባት የመቃብሩ ጫና ይቀንሳል ብዬ፤ ለእኔ ከአቡ ጠሊብ በኃላ ከአላህ ፍጥረት በላጭ ናት። ነብዩም"ﷺ" ይህንን ያሉት የዐሊይ እናት ስለሆነችው ስለፋጢማ ነበር*።
"ከንዙል ዑማል" كنز العمال ማለት "የሰናይ ገባሪ ጥሪኝ" ማለት ነው፤ ዐሊ ኢብኑ ዐብዱል ማሊክ አል-ሂንዲ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 1517 ድህረ-ልደት ያዘጋጀው ሐዲስ ነው፤ ይህ ሐዲስ ከመነሻው ደኢፍ ነው።
ሲቀጥል የዐሊይ እናት ለነብያችን"ﷺ" አክስት ናት፤ ከአክስት ጋር አይደለም ሞቷ ወሲብ ይቅርና በቁምም ከአክስት ጋር ጋብቻ ክልክል ነው፦
4፥23 እናቶቻችሁ፣ ሴት ልጆቻችሁም፣ እኅቶቻችሁም፣ *አክስቶቻችሁም፣ የሹሜዎቻችሁም፣* የወንድም ሴቶች ልጆችም፣ የእኅት ሴቶች ልጆችም፣ እነዚያም ያጠቡዋችሁ እናቶቻችሁ፣ ከመጥባት የኾኑትም እኅቶቻችሁ፣ የሚስቶቻችሁም እናቶች፣ እነዚያም በጉያዎቻችሁ ያሉት የእነዚያ በእነርሱ የገባችሁባቸው ሚስቶቻችሁ ሴቶች ልጆች፣ *ልታገቧቸው በእናንተ ላይ እርም ተደረጉባችሁ*፡፡ حُرِّمَتْ عَلَيْكُمْ أُمَّهَاتُكُمْ وَبَنَاتُكُمْ وَأَخَوَاتُكُمْ وَعَمَّاتُكُمْ وَخَالَاتُكُمْ وَبَنَاتُ الْأَخِ وَبَنَاتُ الْأُخْتِ وَأُمَّهَاتُكُمُ اللَّاتِي أَرْضَعْنَكُمْ وَأَخَوَاتُكُم مِّنَ الرَّضَاعَةِ وَأُمَّهَاتُ نِسَائِكُمْ وَرَبَائِبُكُمُ اللَّاتِي فِي حُجُورِكُم مِّن نِّسَائِكُمُ اللَّاتِي دَخَلْتُم بِهِنَّ فَإِن لَّمْ تَكُونُوا دَخَلْتُم بِهِنَّ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ وَحَلَائِلُ أَبْنَائِكُمُ الَّذِينَ مِنْ أَصْلَابِكُمْ وَأَن تَجْمَعُوا بَيْنَ الْأُخْتَيْنِ إِلَّا مَا قَدْ سَلَفَ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا

የአባት እህት ሹሜ ስትባል የእናት እህት አክስት ትባላለች፤ ሲሰልስ "በመቃብሯ ውስጥ አብሬ ተጋደምኩኝ" اضْطَجَعَ معها في قبرها ማለት "ወሰብኩኝ" "ተራከብኩኝ" ብሎ የተረጎመላችሁ ማን ነው? "አድጠጀዐ" اضْطَجَعَ ማለት "ተኛ" ማለት እንጂ "ወሰበ" አሊያም "ተራከበ" ማለት አይደለም። ይህ ዐረቢኛው ባይብል ላይ ኤልሳዕ ከሕፃኑ ጋር የተኛውን ለማመልከት አገልግሎት ላይ ውሏል፦
2 ነገሥት 4፥34 መጥቶም በሕፃኑ ላይ *ተኛ*፤ አፉንም በአፉ፥ ዓይኑንም በዓይኑ፥ እጁንም በእጁ ላይ አድርጎ *ተጋደመበት*፤ የሕፃኑም ገላ ሞቀ። ثُمَّ صَعِدَ وَاضْطَجَعَ فَوْقَ الصَّبِيِّ وَوَضَعَ فَمَهُ عَلَى فَمِهِ وَعَيْنَيْهِ عَلَى عَيْنَيْهِ وَيَدَيْهِ عَلَى يَدَيْهِ

"ተኛ" የሚለው ቃል "አድጠጀዐ" اضْطَجَعَ ነው፤ ታዲያ ኤልያስ ከሕጻኑ ጋር ወሲብ አደረገ ማለት ነውን? አዎ ካላችሁን ነብዩ ኤልሳዕ ግብረ ሰዶማዊ ነው ልትሉ ነው? ምክንያቱም ሕጻኑ ወንድ ሕጻን ነውና፤ አይ "ተወሰበ" "ተራከበ" ለሚለው ቃል "ነከሐ" نَكَحَ እንጂ "አድጠጀዐ" اضْطَجَعَ አይደለም ካላችሁ እንግዲያውስ ቅጥፈታችሁን እዚህ ጋር ይብቃ። ምነው በተመሳሳይ ሙሴ ከአባቶቹ ጋር በመቃብር እንደሚተኛ እግዚአብሔር ነግሮታል፤ ኢዮብም ሰው ከአጥንቱ ጋር በመቃብር እንደሚተኛ ተናግሯል፤ ኢሳይያስም ነብርም ከፍየል ጠቦት ጋር ይተኛል ብሏል፦
ዘዳግም 31፥16 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ እነሆ፥ *ከአባቶችህ ጋር ትተኛለህ*፤ وَقَال الرَّبُّ لِمُوسَى: «هَا أَنْتَ تَرْقُدُ مَعَ آبَائِك
ኢዮብ 20፥11 አጥንቶቹ ብላቴንነቱን ሞልተዋል፤ ነገር ግን *ከእርሱ ጋር በመሬት ውስጥ ይተኛል*። عِظَامُهُ مَلآنَةٌ قُوَّةً وَمَعَهُ فِي التُّرَابِ تَضْطَجِعُ.
ኢሳይያስ 11፥6 ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋር ይቀመጣል፥ *ነብርም ከፍየል ጠቦት ጋር ይተኛል*፤ فَيَسْكُنُ الذِّئْبُ مَعَ الْخَرُوفِ وَيَرْبُضُ النَّمِرُ مَعَ الْجَدْيِ وَالْعِجْلُ

ሰው በመሬት ውስጥ "ይተኛል" ለሚለው ቃል የወደፊት ግስ የተጠቀመበት "ተድጠጂዑ" تَضْطَجِعُ ሲሆን የእርሱ አላፊ ግስ "አድጠጀዐ" اضْطَجَعَ ነው፤ እና ሰው አፈር ውስጥ ወሲብ ያረጋል ማለቱ ነውን? እረ "መተኛት" ሲባል ተራክቦ ወይም ወሲብ ማለት አይደለም ካላችሁ እንግዲያውስ ቅጥፈት ይብቃ! ከላይ ያለውን ደኢፍ ሐዲስ በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት። አላህ ሂዳያህ ይስጣችሁ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አብ እና ኢየሱስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ዮሐንስ 8፥26 *የላከኝ እውነተኛ ነው እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ*፤ አላቸው።

ኢየሱስን የላከው አብ ነው፤ ኢየሱስ ከአብ እየሰማ የሚናገር ማንነት ነው፤ ኢየሱስ ወደ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ከእግዚአብሔር መጥቶ መጽሐፍን ተቀብሏል፦
ራእይ 5፥7 *መጥቶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠ ከዚያ ከቀኝ እጁ መጽሐፉን ወሰደው*።
ራእይ 19፥4 *በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለእግዚአብሔር፦ አሜን፥ ሃሌ ሉያ እያሉ ሰገዱለት*።

በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው አብ እና ከአብ መጽሐፉን የወሰደው ኢየሱስ ይለያያሉ፤ ኢየሱስ በአብ ፊትይመሰክራል፦
ማቴዎስ 10፥32 ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ *እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ*፤

መስካሪው ኢየሱስ የሚመሰክረው በአብ ፊት መሆኑ አብ እና ኢየሱስ ሁለት የተለያዩ ማንነቶች መሆናቸውን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፤ ኢየሱስ ከአብ "ጋር" በሚል መስተዋድድ ተለይቷል፦
ራእይ 3፥21 *እኔ ደግሞ ድል እንደ ነሣሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፥ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ*።

ኢየሱስ አባቴ ከሚለው ማንነት "ጋር" በሚል መስተዋድድ ተለይቷል፤ አማኝ "ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጣል" ማለት አማኙ እና ኢየሱስ በማንነት እንደሚለያዩ ሁሉ ኢየሱስ እና አብ በማንነት ይለያያሉ፤ አብም ወልድን በቀኜ ተቀመጥ አለው፦
ሐዋ. ሥራ 2፥34 *ጌታ ጌታዬን፦ ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ፥ አለው*፤ he saith himself, The *LORD* said unto my *Lord*, Sit thou on my right hand,(KJV)

ትልቁ ጌታ"LORD አብ ትንሹን ጌታ"Lord" ወልድን በቀኜ ተቀመጥ ብሎ ሲያናግረው ተመልከቱ፥ አብ ኢየሱስን ጌታ አደረገው፦
ሐዋ. ሥራ 2፥36 *ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው* የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።

አብ ማለት ኢየሱስ ውስጥ ያለው የኢየሱስ መንፈስ ቢሆን ኖሮ ኢየሱስ አብን ነው ለአብ በእጁ አደራ የሰጠው? የማይመስል ነገር፦
ሉቃስ 23፥46 *ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ፦ "አባት ሆይ፥ መንፈሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ" አለ። ይህንም ብሎ መንፈሱን ሰጠ*። And when Jesus had cried with a loud voice, he said, Father, into thy hands I commend my *spirit*: and having said thus, he gave up *the spirit*. (KJV)

ስለዚህ ኢየሱስ ከአብ ተለይቶ እራሱን የቻለ የራሱን መንፈስ ነበረው፤ መንፈሱ ይታወክ እና ያዝን ነበር፤ አብ ነበር ሲያዝንና ሲታወክ የነበረው? ኢየሱስ፦ ስለ እኔ የሚመሰክር ሌላ ነው፤ እርሱም የላከኝ አብ ነው ብሏል፦
ዮሐንስ 5፥31-32 *እኔ ስለ እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ምስክሬ እውነት አይደለም፤ ስለ እኔ የሚመሰክር ሌላ ነው፥ እርሱም ስለ እኔ የሚመሰክረው ምስክር እውነት እንደ ሆነ አውቃለሁ*።
ዮሐንስ 8፥18 *ስለ ራሴ የምመሰክር እኔ ነኝ፥ የላከኝም አብ ስለ እኔ ይመሰክራል*።

አብን "እኔ ነኝ" ሳይሆን ያለው "ሌላ ነው" ብሎ ተናግሯል፤ ሌላ ነው እያለ እራስክ ነህ ማለት ቂልነት ነው፤ አብ ኢየሱስን "አንተ" እያለ ሲያናግረው ኢየሱስም አብን "አንተ" እያለ ያናግረው ነበር፤ "እኔ" "አንተ" እርሱ" ማንነትን ያሳያል፦
ማርቆስ 1፥10 የምወድህ ልጄ *አንተ* ነህ፥ *በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ*።
ዮሐንስ 17፥13 *አሁንም ወደ አንተ እመጣለሁ*፤

"ወደ" የሚለው መስተዋድድ በሁለት ማንነቶች መካከል የምንጠቀምበት ነው፤ ይህ ሁሉ ጥቅስ እየተዥጎደጎደ ኢየሱስ እራሱ የላከ አብ ነው ማለት ኢየሱስ በሰዎች ላይ ሚስጥር እየተመሳጠረ እና ድራማ፣ ተውኔት፣ ቁማር እየተጫወተ ነበር ብሎ መሳደብ ነው፤ ሰዎች ነን፤ እኛ በሌጣው እንኳን አንብበን ሊገባን በሚችል ቋንቋ ኢየሱስ እና አብ ሁለት ማንነቶች እንደሆኑ እንረዳለን። አብ ደግሞ አንዱ አምላክ ሲሆን ከአንዱ በቀር አምላክ የለም። ኢየሱስ በአንዱ አምላክ እና በሰዎች መካከል ያለ ሰው ነው፦
1 ቆሮንቶስ 8፥4 *ከአንዱም በቀር ማንም አምላክ* እንደሌለ እናውቃለን።
1 ጢሞቴዎስ 2፥5 *አንድ አምላክ አለና፥ በአምላክ እና በሰዎች መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ*፥ እርሱም *ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው*፤ For there is *one God*, and *one mediator* between God and men, *the man* Christ Jesus; (KJV)

ከላይ የጠቀስናቸው ጥቅሶች ለሃዋርያት ቤተ ክርስቲያን በተለምዶ ኦንልይ ጂሰስ ለሚባሉት እራስ ምታት ናቸው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ከእኛ እንደ አንዱ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

14፥52 *ይህ ቁርኣን ለሰዎች ገላጭ ነው፡፡ ሊመከሩበት፣ በእርሱም ሊያስጠነቅቁበት፣ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት እና የአእምሮ ባለቤቶችም ሊገሰፁበት የተወረደ ነው*፡፡ هَـٰذَا بَلَاغٌ لِّلنَّاسِ وَلِيُنذَرُوا بِهِ وَلِيَعْلَمُوا أَنَّمَا هُوَ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ وَلِيَذَّكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ

ቁርኣን ከወረደበት አንዱ ፈጣሪ አላህ አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት ነው፦
14፥52 *ይህ ቁርኣን ለሰዎች ገላጭ ነው፡፡ ሊመከሩበት፣ በእርሱም ሊያስጠነቅቁበት፣ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት እና የአእምሮ ባለቤቶችም ሊገሰፁበት የተወረደ ነው*፡፡ هَـٰذَا بَلَاغٌ لِّلنَّاسِ وَلِيُنذَرُوا بِهِ وَلِيَعْلَمُوا أَنَّمَا هُوَ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ وَلِيَذَّكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ

ይህ የአንድ አምላክ እሳቤ በመለኮታዊ ቅሪት እንዲህ ተቀምጧል፦
ዘዳግም 6፥4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ *አምላካችን ያህዌህ አንድ ያህዌህ ነው*። שְׁמַע, יִשְׂרָאֵל: יְהוָה אֱלֹהֵינוּ, יְהוָה אֶחָד.

ያህዌህ አንድ ያህዌህ ሲሆን እርሱ ሌሎችን ማንነቶችን ጨምሮ፦ "ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ" ብሏል፦
ዘፍጥረት 3፥22 *ያህዌህ አምላክም አለ፦ *እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ*፤ וַיֹּאמֶר יְהוָה אֱלֹהִים, הֵן הָאָדָם הָיָה כְּאַחַד מִמֶּנּוּ, לָדַעַת, טוֹב וָרָע; וְעַתָּה פֶּן-

"እንደ አንዱ" እና "እኛ" ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን ነጥብ በነጥብ ጥርስና ምላሱን እየነቀስን እናየዋለን፦

ነጥብ አንድ
"እንደ አንዱ"
"ከ-አሐድ" כְּאַחַ֣ד ማለት "እንደ አንዱ"as one of" ማለት ነው፤ ያ ማለት በከፊል መመሳሰልን ያሳያል፦
1ኛ ሳሙኤል 17፥36 *እኔ ባሪያህ “አንበሳ እና ድብ” መታሁ፤ ይህም ያልተገረዘው ፍልስጥኤማዊ የሕያውን አምላክ ጭፍሮች ተገዳድሮአልና “ከእነርሱ እንደ አንዱ” ይሆናል*። גַּם אֶת-הָאֲרִי גַּם-הַדֹּב, הִכָּה עַבְדֶּךָ; וְהָיָה הַפְּלִשְׁתִּי הֶעָרֵל הַזֶּה, כְּאַחַד מֵהֶם, כִּי חֵרֵף, מַעַרְכֹת אֱלֹהִים חַיִּים.

"ከ-አሐድ ሜሄም" כְּאַחַד מֵהֶם ማለት "ከእነርሱ እንደ አንዱ"as one of them" ማለት ሲሆን ፍልስጥኤማዊ ጎልያድ በዳዊት በመገደል ደረጃ “እንደ አንበሳ እና ድብ” ይሆናል ማለት ነው እንጂ ጎልያድ አውሬ ይሆናል ማለት አይደለም፣ “እንደ” የሚለው ተውሳከ-ግስ የተወሰነን መመሳሰል ለማመልከት የሚገባ ነው፣ ልክ እንደዚሁ አደም መልካምና ክፉ በማወቅ እንደ እንደ እነርሱ ሆኗል፤ ለዛ ነው "ከ-አሐድ ሜንሁ" כְּאַחַ֣ד מִמֶּ֔נּוּ ማለትም "ከእኛ እንደ አንዱ"as one of us" የሚለው፤ ያህዌህ ታዲያ ማንን ጨምሮ ነው "እኛ" የሚለው?

ነጥብ ሁለት
"እኛ"
ያህዌህ "እኛ" የሚለው ማንን ጨምሮ ነው የሚለው ለመረዳት እዚሁ ዐውድ ላይ አዳም ከእኛዎቹ እንደ አንዱ የሚሆነው "መልካምንና ክፉን ለማወቅ" እንደሆነ ይሰመርበት፤ እዛው ዐውድ ላይ አዳም ቢበላ "እንደ አማልክትም መልካምንና ክፉን የሚያውቁ" እንደሆነ ተነግሯል፦
ዘፍጥረት 3፥5 ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ *“እንደ አማልክትም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ"* ያህዌህ ስለሚያውቅ ነው እንጂ። כִּי, יֹדֵעַ אֱלֹהִים, כִּי בְּיוֹם אֲכָלְכֶם מִמֶּנּוּ, וְנִפְקְחוּ עֵינֵיכֶם; וִהְיִיתֶם, כֵּאלֹהִים, יֹדְעֵי, טוֹב וָרָע.

የግዕዙ ዕትም፦
ዘፍጥረት 3፥5 *“ዘይቤ ከመ ኢትኩኑ አማልክተ ወኢታምሩ ሠናየ ወእኩየ”*

የኢንግሊሹ ዕትም፦
For God doth know that in the day ye eat thereof, then your eyes shall be opened, and *ye shall be as gods, knowing good and evil*.(KJV)

ግሪክ ሰፕቱአጀንት”LXX”፦
ዘፍጥረት 3፥5 ᾔδει γὰρ ὁ Θεός, ὅτι ᾗ ἂν ἡμέρᾳ φάγητε ἀπ᾿ αὐτοῦ, διανοιχθήσονται ὑμῶν οἱ ὀφθαλμοὶ καὶ ἔσεσθε ὡς *θεοί*, γινώσκοντες καλὸν καὶ πονηρόν.

የግዕዙ ዕትም ላይ "አማልክት" ብሎ እንዳስቀመጠው አስተውል፤ "ኤሎሂም" כֵּֽאלֹהִ֔ים ማለት "አማልክት" ማለት ነው፤ ይህ ቃል ለነጠላ ማንነት ወይንም ለብዙ ማንነት ይውላል፤ እዚህ አንቀጽ ላይ ግን ለብዙ መባሉን በግሪክ ሰፕቱጀንት ላይ “ቴኦ” θεοί ማለትም "አማልክት" ብሎ በብዙ ቁጥር አስቀምጦታል፤ ልብ አድርግ የቴኦ ነጠላ “ቴኦስ” Θεὸς ነው፤ "ቴኦስ" ብሎ በነጠላ አለማስቀመጡ ለብዙ ማንነቶች መሆኑን ያሳያል፤ በኢንግሊሹም ደግሞ በብዙ ቁጥር “gods" መባሉን አስተውል። በብሉይ ደግሞ ብዙ ቦታ አማልክት የተባሉት መላእክት ናቸው፦
መዝሙር 97፥7 *"አማልክትም” כֵּֽאלֹהִ֔ים ሁሉ ስገዱለት*።
መዝሙር 104፥4 *“አማልክትን” כֵּֽאלֹהִ֔ים መንፈስ የሚያደርግ፥*
መዝሙር 8፥5 *“ከአማልክትን” כֵּֽאלֹהִ֔ים እጅግ ጥቂት አሳነስኸው*፤
መዝሙር 103፥20 የቃሉንም ድምፅ የምትሰሙ *“አማልክቱ” כֵּֽאלֹהִ֔ים ሁሉ ያህዌህን ባርኩ*።
መዝሙር 138፥1 *"በአማልክት כֵּֽאלֹהִ֔ים ፊት እዘምርልሃለሁ*።

ስለዚህ አዳም ዛፉን ሲበላ መልካም እና ክፉውን በማወቅ እንደ መላእክት ከሆነ ያህዌህ ደግሞ መልካምና ክፉ ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ የሚለው እነዚህን አማልክት ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው፦
ሆሴዕ 12፥4 *በጕልማስነቱም ጊዜ “ከአምላክ” ጋር ታገለ፤ “ከመልአኩም” ጋር ታግሎ አሸነፈ፤ አልቅሶም ለመነው። በቤቴልም አገኘው፥ በዚያም “ከእኛ” ጋር ተነጋገረ*።

ያዕቆብ የተነጋገረው ከመልአኩ ጋር እና ከያህዌህ ጋር ነው፤ ያህዌህ መልአኩን ጨምሮ "ከእኛ" እንዳለ አንባቢ ልብ ይለዋል። አይ ያህዌህ እኛ የሚለው ሥላሴን ያሳየል ከተባለ ዕውዱ ላይ ስለ ሥላሴ የሚያሳይ ሃይለ-ቃል ፈልቅቆ ማሳየት ይጠበቅባችኃል፤ ወይም ይህ አንቀጽ ስለ ሥላሴ ያወራል ብሎ የተናገረ ነብይ ወይም ሐዋርያ ጠቅሳችሁና አጣቅሳችሁ መሞገትና መሟገት ይጠበቅባችኃል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ዒድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

79፥40-41 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ *ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡ وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَىٰ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ

“ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፤ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል፤ ነብያችን”ﷺ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻና ብቻ ናቸው፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ : መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” በሁለቱ በአል በኢደል አደሐ እና ኢደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ ‏.

ታዲያ በየዓመቱ የሚከበረው ሥስተኛው በዓል መውሊድ ምንድን ነው? አዎ ይህ ድብን ያለ ቢድዓ ነው፤ ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው።
ሲጀመር ነብያችን”ﷺ” የተወለዱበት ሳምንት እንጂ የተወለዱበት ቀን በሐዲስ አልሰፈረም።
ሲቀጥል አላህም እና መልእክተኛው መውሊድ አክብሩ አላሉም።
ሢሰልስ ነቢያችን”ﷺ” የተወለዱበትን ቀን ከቀደምት ሰለፎች ማለትም ሶሐባህ ወይም ታቢኢይ አሊያም አትባኡ ታቢኢይ ያከበረ የለም።
ስለዚህ መውሊድ በቁርኣንና በሐዲስ አሕካሙ ካልተቀመጠ እና አይ የፈለግነውን በዲኑ ላይ እንጨምራለን ከሆነ ቢድዓ ነው፤ ሑክም የአላህ እና የመልክተኛ ብቻና ብቻ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 53, ሐዲስ 7
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ማንኛውም ሰው ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ فِيهِ فَهُوَ رَدٌّ ‏”‌‏.‏

“ከትእዛዛችን” የሚለው ይሰመርበት። አንድ ነገር ፈርድ ነው፣ ሙስተሐብ ነው፣ ሙባሕ ነው፣ መክሩህ ነው፣ ሐራም ነው ማለት የሚቻለው ከአላህ እና ከመልእክተኛ ትእዛዝ ሲመጣ ብቻና ብቻ ነው፦
3፥32 *አላህን እና መልክተኛውን ታዘዙ*፡፡ ብትሸሹም አላህ ከሓዲዎችን አይወድም» በላቸው፡፡ قُلْ أَطِيعُوا اللَّهَ وَالرَّسُولَ ۖ فَإِن تَوَلَّوْا فَإِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْكَافِرِينَ
4፥80 *መልክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ፡፡ ከትእዛዝም የሸሸ ሰው አያሳስብህ*፡፡ በእነርሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አልላክንህምና፡፡ مَّن يُطِعِ الرَّسُولَ فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ ۖ وَمَن تَوَلَّىٰ فَمَا أَرْسَلْنَاكَ عَلَيْهِمْ حَفِيظًا

“ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም” የሚለው የነብያችን”ﷺ” ንግግር ይሰመርበት፤ ማንኛውም መመሪያ ቁርአን እና የነብያችን”ﷺ” ሐዲስ ላይ ይገኛል፤ አላህን የሚወድ መልእክተኛውን ይከተላል፤ አላህም፦ “መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፤ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ” ብሎናል፦
3፥31 *በላቸው፡- አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ “ተከተሉኝ*፤ አላህ ይወዳችኋልና፤ ኀጢኣቶቻችሁንም ለእናንተ ይምራልና፤ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው” قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ ٱللَّهَ فَٱتَّبِعُونِى يُحْبِبْكُمُ ٱللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَٱللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ ፡፡
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ ፡፡
ጥሩ ቢድዓ ካለ የሌሎችን ነብያት ልደት ለምን አይከበርም? ለምሳሌ “ገና” የዒሳ ልደት አይከበርም? ነብያችን”ﷺ” ወሕይ የመጣላቸው ቀን፣ ያረፉበት ቀን ወዘተ እየተባለ ልክ እንደ ኦርቶዶክስ ሰላሳውም ቀን ለምን አይከበርም? ይህ ደግሞ ዲኑን ያባሻል። አይ ዝንባሌአችን ደስ ያለውን መልካም ነገር በዒባዳህ ላይ እናካትት ማለት ዲኑ ሙሉ ነው የሚለንን አምላካችን አላህን እየተቃረንን ነው፦
5፥3 *ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ*፡፡ ጸጋዬንም በእናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡ الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا

“ነፍስያ” نفسيه ማለትም “የራስ ዝንባሌ” ጌታችን የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ነው፤ ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም፦
12፥53 ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ *ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና*፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡ وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ
6፥164 በላቸው እርሱ የሁሉ ጌታ ሲኾን ከአላህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን *ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም*፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا

ቢድዓ፣ ኩርፍ፣ ሽርክ እና ኒፋቅ ምንጫቸው ዝንባሌ ነው፤ ብዙ ጊዜ ሰርጎ-ገብ የሆኑት ቡድንተኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ጠርዘኝነት መነሻቸው ዝንባሌ ነው፤ አንድ ሙስሊም ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፦
79፥40-41 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ *ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡ وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَىٰ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ

አላህ ከነፍሲያ ከሚመጣ ዝንባሌ ጠብቆን፤ እርሱንና መልእክተኛው ባስቀመጡልን ሑክም የምንመራ ያድርገን አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የቁርኣን ልኬት

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

41፥42 *ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፤ ጥበበኛ ምስጉን ከኾነው ጌታ የተወረደ ነው*፡፡ لَّا يَأْتِيهِ ٱلْبَٰطِلُ مِنۢ بَيْنِ يَدَيْهِ وَلَا مِنْ خَلْفِهِۦ ۖ تَنزِيلٌۭ مِّنْ حَكِيمٍ حَمِيدٍۢ

"አል-ተቅዪሥ" التقييس ማለት "ልኬት"Standardization" ማለት ነው፤ ቁርኣን በወረደበት ጊዜ ዐረቦች የተለያየ "ለህጃህ" لهجة ማለትም "ዘዬ"dialect" ነበራቸው፤ እነርሱም፦ "ቁሬይሽ" "ሁድኸይል" "ጠቂፍ" "ሃዋዚን" "ኪናነህ" "ተሚን" "የመኒ" የመሳሰሉት ነበሩ፣ እነዚህ ዘዬዎች የአነባነብ ሥርአታቸው ላይ "ተሽኪል" تَشْكِيل ማለትም "አናባቢ ድምጽ"Vowelling mark" ይለያያሉ፤ ይህም ልዩነት በማጥበቅና በማላላት፣ በመጎተትና በመጠቅለል የቃሉን መልእክት የተለያየ ትርጉም እንዲኖረው ሊያደርግ ይችላል። ለምሳሌ በአገራችን፦
"ገና" ብለን "ገ" ሆሄን ስናጥብቀው "ልደት" ማለት ሲሆን ስናላላው "መዘግየት" የሚል ትርጉም ይኖረዋል።
"የማይገባው" ብለን "ገ" ሆሄን ስናጥብቀው "ብቃት" ማለት ሲሆን ስናላላው ደግሞ "መረዳት" የሚል ትርጉም ይኖረዋል።
"የማይረዳኝ" ብለን "ዳ" ሆሄን ስናጥብቀው "ሃሳቤን የማይገባው" ማለት ሲሆን ስናላላው "የችግሬ መፍትሄ የማይሆን" የሚል ትርጉም ይኖረዋል።
"ዋና" ብለን "ዋ" ሆሄን ስናጥብቀው "ዐብይ" ማለት ሲሆን ስናላላው "መዋኘት" የሚል ትርጉም ይኖረዋል። እንዲሁ በዐረቢኛ ለምሳሌ፦
"አሊም" أَلِيم የሚለው በመነሻ ላይ በሃራካ "ሀምዛህ" ا ፈትሓህ "አ" أ አድርገን ስንቀራ "ህመም" ማለት ሲሆን "ዐሊም" عَلِيم የሚለውን በመነሻ ላይ በሃረካ "ዐይን" ع ፈትሓህ "ዐ" عَ አድርገን ስንቀራ ደግሞ "ዐዋቂ" ማለት ነው፡፡
"ከፈረ" كَفَرَ የሚለውን በግንድ ላይ በሃረካ "ፋ" ف ፈትሓህ "ፈ" فَ አድርገን ስንቀራ "ካደ" ማለት ሲሆን “ከፈረ” كَفَّرَ የሚለውን በግንድ ላይ በሸዳ "ፋ" ف ተሽዲድ ፈትሓህ "ፍፈ" فَّ አድርገን ስንቀራ "ሸፈነ" ማለት ነው።
"ነዘለ" نَزَلَ የሚለውን በግንድ ላይ በሃረካ "ዛል" ز ፈትሓህ "ዘ" زَ አድርገን ስንቀራ "ወረደ" ማለት ሲሆን "ነዘለ" نَزَّلَ የሚለውን በግንድ ላይ በሸዳ "ዛል" ز ፈትሓህ ተሽዲድ ፈትሓ "ዝዘ" زَّ አድርገን ስንቀራ "አወረደ" ማለት ነው። ብዙ ናሙና ማቅረብ ይቻል ነበር፤ ግን ይህ በቂ ነው፤ ይህ ሙግት የሥነ-አናባቢ ጥናት"orthography" ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ነው።

ሌላው "አብጀድ" أَبْجَد ማለትም "ተነባቢ ፊደላት"consonant" ላይም ልዩነት አላቸው፤ ድምጽ ያላቸው ሐርፎች 28 ሲሆን "አሊፍ" ا ደግሞ "አጫዋች ፊደል"stretch letter" ነው፤ በጥቅሉ 29 ሐርፎች ሲሆኑ በመካከላቸው ስናነባቸው የሚቀጥኑ ሐርፎች 19 ሲሆኑ "ተርቂይቅ" تَرْقِيْقٌ ይባላሉ፣ የሚወፍሩ ሐርፎች ደግሞ 7 ሲሆኑ "ተፍኺይም" تَفْخِيْمُ ይባላሉ፣ የሚወፍርና የሚቀጥኑ ሐርፎች ደግሞ ሁለት ሲሆኑ አንደኛው "ሯ" ر በፈትሓህ እና በደማ ሲቀራ ይወፍራል፤ በከስራ ሲቀራ ይቀጥናል። ሁለተኛ "ላም" ل በለፍዙል ጀላላ ማለትም በአላህ ስም ላይ ሲቀራ ይወፍራል፤ በሌሎች ላይ ሲቀራ ይቀጥናል።
በእነዚህ ተነባቢ ፊደላት ላይ "ኑቅጧህ" نُقْطَة‎ ማለትም "ነጥብ" ያላቸው 16 ሐርፎች "ሙአጀማ" ሲባሉ ነጥብ የሌላቸው 14 ሐርፎች ደግሞ "ሙሃመላ" ይባላል፣ አንዷ ሐርፍ "ያ" ي ደግሞ ሁለቱንም ናት።
ሐርፎች በመነሻ ቅጥያ"Prefix" ላይ፣ በግንድ"stem" ላይ እና በመዳረሻ ቅጥያ"Suffix" ላይ ቅርጻቸው ሲቀያየር "ረሥም" رَسْم ይባላል።
ይህ ሙግት የሥነ-ተናባቢ ጥናት"Typography" ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ነው።
ይህ እንዲህ በእንዲህ እያለ ቁርኣን በቁሬይሽ ዘዬ ወረደ፤ ሌሎች ሁድኸይል፣ ጠቂፍ፣ ሃዋዚን፣ ኪናነህ፣ ተሚን፣ የመኒ ወዘተ ከዚህ ዘዬ ወስደው ሲጠቀሙ በማጥበቅና በማላላት፤ በማቅጠንና በማወፈር በትርጉም ላይ ልዩነት አመጣ፤ ይህ ልዩነት ከዐረብ ውጪ ላሉት መከፋፈል አመጣ፤ ይህንን ልዩነት የታዘበው የነብያችን"ﷺ" ሰሃቢይ ሑደይፋህ ኢብኑል-የማን በወቅቱ ኸሊፋህ ለነበረው ለዑስማን በመናገር በቁሬይሽ ዘዬ አንድ የጋራ ልኬት እንዲደረግ ተደርጓል፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 9
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ *"የሻም ሕዝብ እና የኢራቅ ሕዝብ አርመንያን እና አዛርባጃንን ለማሸነፍ ጦርነት ባደረጉ ጊዜ ሑደይፋህ ኢብኑል-የማን ወደ ዑስማን ሲመጣ የሻም እና የኢራቅ ሕዝቦች በቂርኣት ዘዬ ላይ ሲለያዩ ፈራ፤ ከዚያም ሑደይፋህም ለዑስማን፦ "የምእመናን አሚር ሆይ! ይህንን ዑማህ ታደግ፤ ስለ መጽሐፉ ከዑማህ በፊት ልክ የሁዲ እና ነሳራህ እንደተለያዩት እንዳይለያዩ። ከዚያም ዑስማንም ለሐፍሷህ፦ "የቁርኣን መሷሒፍ ላኪልኝ፤ በጥሩ ሙስሐፍ ካዘጋጀን በኃላ መሷሒፉን እመልስልሻለው" ብሎ ላከባት፤ ሐፍሷህም ለዑስማን ላከችለት፤ ከዚያም ዑስማን ለዘይድ ኢብኑ ሳቢት፣ ለዐብደሏህ ኢብኑ አዝ-ዙበይር፣ ለሠዒድ ኢብኑል ዓስ እና ለዐብዱ አር-ረሕማን ኢብኑል ሓሪስ ኢብኑ ሂሻም ከመሷሒፍ እንዲገለብጡ አዘዛቸው፤ ዑስማንም ለሦስቱ የቁሬይሽ ሰዎች፦ "ምናልባት በአገለባበጡ ከዘይድ ኢብኑ ሳቢት ጋር ያልተስማማችሁበት ነጥብ ካለ በቁሬሽ ዘዬ ጻፉት፤ ቁርኣን በእነርሱ ዘዬ ነው የወረደው፤ ከዚያም በእነርሱ ዘዬ አደረጉ። ብዙ ሱሑፎችን ገለበጡ፤ ዑስማንም የቁርኣንን መሷሒፍ ለሐፍሷህ መለሰላት። ከዚያም ዑስማንም ለሁሉም ሙስሊም አውራጃ እነርሱ ከገለበጡት ከላከ በኃላ ማንኛውም ሌሎች የቁርኣን እደ-ክታባት ሆኑ ግልባጮች ተቃጠሉ*። أَنَّ أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ، حَدَّثَهُ أَنَّ حُذَيْفَةَ بْنَ الْيَمَانِ قَدِمَ عَلَى عُثْمَانَ وَكَانَ يُغَازِي أَهْلَ الشَّأْمِ فِي فَتْحِ إِرْمِينِيَةَ وَأَذْرَبِيجَانَ مَعَ أَهْلِ الْعِرَاقِ فَأَفْزَعَ حُذَيْفَةَ اخْتِلاَفُهُمْ فِي الْقِرَاءَةِ فَقَالَ حُذَيْفَةُ لِعُثْمَانَ يَا أَمِيرَ الْمُؤْمِنِينَ أَدْرِكْ هَذِهِ الأُمَّةَ قَبْلَ أَنْ يَخْتَلِفُوا فِي الْكِتَابِ اخْتِلاَفَ الْيَهُودِ وَالنَّصَارَى فَأَرْسَلَ عُثْمَانُ إِلَى حَفْصَةَ أَنْ أَرْسِلِي إِلَيْنَا بِالصُّحُفِ نَنْسَخُهَا فِي الْمَصَاحِفِ ثُمَّ نَرُدُّهَا إِلَيْكِ فَأَرْسَلَتْ بِهَا حَفْصَةُ إِلَى عُثْمَانَ فَأَمَرَ زَيْدَ بْنَ ثَابِتٍ وَعَبْدَ اللَّهِ بْنَ الزُّبَيْرِ وَسَعِيدَ بْنَ الْعَاصِ وَعَبْدَ الرَّحْمَنِ بْنَ الْحَارِثِ بْنِ هِشَامٍ فَنَسَخُوهَا فِي الْمَصَاحِفِ وَقَالَ عُثْمَانُ لِلرَّهْطِ الْقُرَشِيِّينَ الثَّلاَثَةِ إِذَا اخْتَلَفْتُمْ أَنْتُمْ وَزَيْدُ بْنُ ثَابِتٍ فِي شَىْءٍ مِنَ الْقُرْآنِ فَاكْتُبُوهُ بِلِسَانِ قُرَيْشٍ فَإِنَّمَا نَزَلَ بِلِسَانِهِمْ فَفَعَلُوا حَتَّى إِذَا نَسَخُوا الصُّحُفَ فِي الْمَصَاحِفِ رَدَّ عُثْمَانُ الصُّحُفَ إِلَى حَفْصَةَ وَأَرْسَلَ إِلَى كُلِّ أُفُقٍ بِمُصْحَفٍ مِمَّا نَسَخُوا وَأَمَرَ بِمَا سِوَاهُ مِنَ الْقُرْآنِ فِي كُلِّ صَحِيفَةٍ أَوْ مُصْحَفٍ أَنْ يُحْرَقَ‏.‏

ይህ ትልቅ መርሃ-ግብር ነው፤ የነብያችን"ﷺ" ባልደረቦች ከቁርኣን ውጪ ከነብያችን"ﷺ" የሚሰሟቸው የቁርኣን ማብራሪያዎችን እና ዱዓዎችም በራሳቸው በሚጽፏቸው ቁርኣን ላይ ከግርጌ፣ከራስጌ፣ ከፊት እና ከኃላ ይጽፉ ነበር፤ ይህ ጽሑፍ ለመጪው ትውልድ የቁርኣን ሱራ ተደርጎ እንዳይወሰድ ከላይ ከተጠቀሱ ችግሮች ጋር አብሮ ተቃጥሏል፤ ለምሳሌ የኡበይ ኢብኑ ከዐብ ቁኑት ነው፤ "ቁኑት" قنوت‎ ማለት "በየትኛውም ጊዜና ቦታ ላይ በሙስሊሞች ላይ ግፍ ወይም በደል ከደረሰ በሶላት ሩኩዕ በኋላ ኢማሙ የሚያደርገው ዱዓ ነው" የኡበይ ሁለት ቁኑት ቁኑቱል ኸል እና ቁኑቱል ሀፍድ ናቸው፦
አሥ-ሡዩጢ አል-ኢትቃን ፊ ዑሙል ቁርኣን: መጽሐፍ 1, ቁጥር 227
ቁኑቱል ኸል
*አላህ ሆይ! አንተን ብቻ እንለምናለን፤ አንተ ብቻ ይቅርታህ እንጠይቃለን፤ እናመሰግንሃለን፤ አናስተባብልህም፤ አንተን ከሚያምጹ እንለያለን እንለያያለን*። اللَّهُمَّ إِنَّا نَسْتَعِينُكَ وَنَسْتَغْفِرُكَ وَنُثْنِي عَلَيْكَ وَلَا نُكْفُرُكَ وَنَخْلَعُ وَنَتْرُكُ مَنْ يَفْجُرُكَ
ቁኑቱል ሀፍድ
*አላህ ሆይ! አንተን ብቻ እናመልካለን፤ ሶላትም ሡጁድም ለአንተ ነው፤ እሾትም ወደ አንተ ነው፤ የአንተን ምህረት ተስፋ እናደርጋለን፤ የአንተ ከባድ ቅጣት ከሃድያንን ልትቀጣበት ያለው ቅጣት እንፈራለን*። اللَّهُمَّ إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَلَكَ نُصَلِّي وَنَسْجُدُ وَإِلَيْكَ نَسْعَى وَنَحْفِدُ نَرْجُو رَحْمَتَكَ وَنَخْشَى عَذَابَكَ إِنَّ عَذَابَكَ بِالْكُفَّارِ مُلْحَقٌ.

እነዚህ ቁኑቶች ዱዓዎች ሆነው ሳሉ ሱራዎች ናቸው የሚል ተሟጋች ካለ ከሐዲስ ወይም ከሰሃባዎች ከተገኘ ሪዋያህ መረጃ ማቅረብ ይጠበቅበታል፤ ያለበለዚያ ግን የሚሽነሪዎችን አርቲ ቡርቲ ይዞ መነታረክ መደዴ የቡና ወሬ ነው። ኢንሻላህ በክፍል ሁለት ስለ ዐብደሏህ ኢብኑ መሥዑድ እና በእርሱ ዙርያ እንዳስሳለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የቁርኣን ልኬት

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

15፥9 *እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን*፡፡ إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ

ከቁሬይሽ ዘዬ ውጪ ያሉበት ሙስሐፎች እና የቁርኣን ማብራሪያዎችን እና ዱዓዎችም በራሳቸው በሚጽፏቸው ቁርኣን ላይ ከግርጌ፣ከራስጌ፣ ከፊት እና ከኃላ ያሉባቸው ሙስሐፎች ተሰብስቦ ከመቃጠሉ በፊት ዐብደሏህ ኢብኑ መሥዑድ ይህንን ልኬት አልቀበለም ነበር፦
 ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3387
አዝ-ዙህሪ እንደተረከው፦ *"ዑበይዱልላህ ኢብኑ ዐብደላህ ኢብኑ ኡትባህ ለእኔ እንደነገረኝ፤ ዐብደሏህ ኢብኑ መሥዑድ ዘይድ ኢብኑ ሣቢት ያዘጋጀውን ሙስሐፍ አልወደደውም ነበር፤ እርሱም፦ "የሙስሊም ዑማህ ሆይ! በዘይድ ኢብኑ ሣቢት የተዘጋጀውን ሙስሐፍ እና አመራሩን አትቀበሉ። በአላህ ይሁንብኝ እኔ ኢስላምን ስቀበል በካፊ አብራክ ውስጥ ነበረ፤ የኢራቅ ሕዝብ ሆይ! ከእናንተ ጋር ያለውን ሙስሐፍ ያዙት፤ እነርሱም ደበቁት። አላህ በእርግጥም እንዲህ አለ፦ "ነገርንም የሚደብቅ ሰው በትንሣኤ ቀን በደበቀው ነገር ተሸክሞ ይመጣል" 3፥161 ስለዚህ ከደበቀው ሙስሐፍ ጋር አላህን ይገናኛል፤ አዝ-ዙህሪ እንደተናገረው፦ "የነብዩ"ﷺ" ተወዳጅ ሰሃባዎች የዐብደሏህ ኢብኑ መሥዑድን አመለካከት አልወደዱትም የሚል ለእኔ የተላለፈ ነው*። قَالَ الزُّهْرِيُّ فَأَخْبَرَنِي عُبَيْدُ اللَّهِ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُتْبَةَ أَنَّ عَبْدَ اللَّهِ بْنَ مَسْعُودٍ كَرِهَ لِزَيْدِ بْنِ ثَابِتٍ نَسْخَ الْمَصَاحِفِ وَقَالَ يَا مَعْشَرَ الْمُسْلِمِينَ أُعْزَلُ عَنْ نَسْخِ كِتَابَةِ الْمُصْحَفِ وَيَتَوَلاَّهَا رَجُلٌ وَاللَّهِ لَقَدْ أَسْلَمْتُ وَإِنَّهُ لَفِي صُلْبِ رَجُلٍ كَافِرٍ يُرِيدُ زَيْدَ بْنَ ثَابِتٍ وَلِذَلِكَ قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ يَا أَهْلَ الْعِرَاقِ اكْتُمُوا الْمَصَاحِفَ الَّتِي عِنْدَكُمْ وَغُلُّوهَا فَإِنَّ اللَّهَ يَقُولُ ‏:‏ ‏(‏ وَمَنْ يَغْلُلْ يَأْتِ بِمَا غَلَّ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ‏)‏ فَالْقُوا اللَّهَ بِالْمَصَاحِفِ ‏.‏ قَالَ الزُّهْرِيُّ فَبَلَغَنِي أَنَّ ذَلِكَ كَرِهَهُ مِنْ مَقَالَةِ ابْنِ مَسْعُودٍ رِجَالٌ مِنْ أَفَاضِلِ أَصْحَابِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم

እርሱ ኢስላምን ሲቀበል ዘይድ በአባቱ አብራክ ሆኖ ገና አለመወለዱ አጥጋቢ ምክንያት አልነበረም። ይህንን አይነት አመለካከት ከራስ ወዳድነት የመነጨ ስለነበር ተወዳጅ ሰሃባዎች አልወደዱለትም። ነገር ግን በተቃራኒው ሚሽነሪዎች የዐብደላህ ሙስሐፍ ላይ 111 ሱራህ ብቻ ያየዘ ነው" ይላሉ፤ ነገር ግን የዐብደላህ ሙስሐፍ ላይ 111 ሱራህ ብቻ እንደነበረ እና ሱረቱል ፋቲሐህ፣ ሱረቱል ፈለቅ እና ሱረቱ አን-ናስን እንደማያካትት የሚያሳይ የሐዲስ መረጃ የለም።
ነገር ግን በነብያችን"ﷺ" ጊዜ ሁለቱ ሱራዎች ሱረቱል ፈለቅ እና ሱረቱ አን-ናስ ለዱዓ አገልግሎት ላይ ስለሚውሉ ዐብደላህ ኢብኑ መሥዑድ ሙዐወዛት የቁርኣን ክፍል አይደሉም ብሎ ሲናገር ኡበይ ኢብኑ ከዕብም የአላህን መልእክተኛን"ﷺ" ስለ እነርሱ ጠይቋቸው እርሳቸውም፦ "እነርሱ ወደ እኔ ተወርዶልኛል፤ የቁርኣን ክፍል አርገን እንቀራዋለን" ብለውታል፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4977
ዚር ኢብኑ ሑበይሽ እንደተረከው፦ *ኡበይ ኢብኑ ከዕብን፦ "አቢ ሙንዚር ሆይ! ወንድምህ ዐብደላህ ኢብኑ መሥዑድ፦ ሙዐወዛት የቁርኣን ክፍል አይደለም" ይላል ብዬ ጠየኩት፤ ኡበይ ኢብኑ ከዕብም፦ "የአላህን መልእክተኛ"ﷺ" ስለ እነርሱ(ሙዐወዛት) ጉዳይ ጠየኳቸው፤ እርሳቸውም፦ "እነርሱ(ሙዐወዛት) ወደ እኔ ተወርዶልኛል፤ የቁርኣን ክፍል አርገን እንቀራዋለን" አሉኝ። ስለዚህ የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዳሉት እኛም እንላለን*። عَنْ زِرٍّ، قَالَ سَأَلْتُ أُبَىَّ بْنَ كَعْبٍ قُلْتُ يَا أَبَا الْمُنْذِرِ إِنَّ أَخَاكَ ابْنَ مَسْعُودٍ يَقُولُ كَذَا وَكَذَا‏.‏ فَقَالَ أُبَىٌّ سَأَلْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ لِي قِيلَ لِي‏.‏ فَقُلْتُ، قَالَ فَنَحْنُ نَقُولُ كَمَا قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم‏.‏

ከዚያ በሓላ ዐብደላህ ኢብኑ መሥዑድ እነዚህ ሁለት ሱራዎች ላይ ምንም አይነት ቅሬታ እንደነበረው የሚያሳይ የሐዲስ መረጃ የለም። ገና ለገና በነብያችን"ﷺ" ጊዜ ሁለቱ ሱራዎች የቁርኣን ክፍል አይደሉም ብሏልና በዑስማን ኸሊፋነት ጊዜ ዘይድ ኢብኑ ሣቢትን ስለተቃወመ ሁለቱን ሱራህ ስለማይቀበል ነው ማለት ምንጭ አልባና ሰነድ አልባ ስሁት ሙግት ነው።
ዋናው ነጥብ እሺ እርሱ አልተቀበለም እንበል የአሐድ ዘገባ እኮ ቁርኣን ላይ ተቀባይነት የለውም፤ “አሐድ” آحاد ማለት አንድ ዘገባ በአንድ ሙስኒድ ከተተረከ ትረካው “አሐድ” ይባላል፤ ነገር ግን ቁርኣን በሙተዋቲር ብቻ ነው ተቀባይነት ያለው፤ “ሙተዋቲር” مُتَواتِر ደግሞ አንድ ዘገባ ከአንድ ኢስናድ ማለትም ሰንሰለት በላይ በጀመዓ የሚደረግ ዘገባ ነው።
“አል-ሙዐወዘተይን” الْمُعَوِّذَتَيْن የሚባሉት ሁለቱ ሱራዎች ሱረቱል ፈለቅ እና ሱረቱ አን-ናስ ሲሆኑ የሲሕር ማክሸፊያ ሆነው መውረዳቸውን የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ከመነሻው ነግረውናል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 6 , ሐዲስ 319:
*የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ ዛሬ ምን አስደናቂ አንቀጾች ዛሬ ወርደዋል፤ ይህም ብጤአቸው ታይቶ አያውቅም! እነርሱም፦ “በል «በተፈልቃቂው ጎህ ጌታ እጠበቃለሁ” እና በል «በሰዎች ፈጣሪ እጠበቃለሁ» ናቸው*። قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ أَلَمْ تَرَ آيَاتٍ أُنْزِلَتِ اللَّيْلَةَ لَمْ يُرَ مِثْلُهُنَّ قَطُّ ‏{‏ قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ الْفَلَقِ‏}‏ وَ ‏{‏ قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ النَّاسِ‏}‏ ‏”‏
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." ሱረቱል ፈለቅና ሱረቱ አን-ናስ ነብያችን"ﷺ" ሚቀሩት ሱራዎች መሆናቸውን መስክራለች፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 31, ሐዲስ 3529
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *ነብዩ"ﷺ" ሲታመሙ ሙዐወዛትን ማለትም ሱረቱል ፈለቅና ሱረቱ አን-ናስ ይቀሩ ነበር*። عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ كَانَ إِذَا اشْتَكَى يَقْرَأُ عَلَى نَفْسِهِ الْمُعَوِّذَات
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 80, ሐዲስ 16
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *መቼም ቢሆን የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ወደ አልጋ ሲሄዱ እጃቸውን እያወዛወዙ በተመሳሳይ ጊዜ ሙዐወዛትን ማለትም ሱረቱል ፈለቅና ሱረቱ አን-ናስ ይቀሩ ነበር*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم كَانَ إِذَا أَخَذَ مَضْجَعَهُ نَفَثَ فِي يَدَيْهِ، وَقَرَأَ بِالْمُعَوِّذَاتِ،

ሱረቱል ፋቲሐህ በዐብደላህ ኢብኑ መሥዑድ ሙስሐፍ ላይ አልነበረም የሚለው ምንም አይነት ኢስናድ የሌለው ዲቃላ ንግግር ነው፤ ሱረቱል ፋቲሐህ በቁርኣን ውስጥ ታላቂቱን ሱራህ እና የቁርኣን እናት ተብላ የምትታወቅ ሱራ እንደሆነ በቁና ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል፤ ግን ጊዜና ቦታ ላለማጣበብ ይህ በቂ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 57
ዐብደላህ ኢብኑ ሙገፈል እንደተረከው *በመካ ውድቀት ቀን የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” በሴት ግመል ላይ ሆነው ሱረቱል ፋቲሐህን ይቀሩ ነበር*። حَدَّثَنَا حَجَّاجُ بْنُ مِنْهَالٍ، حَدَّثَنَا شُعْبَةُ، قَالَ أَخْبَرَنِي أَبُو إِيَاسٍ، قَالَ سَمِعْتُ عَبْدَ اللَّهِ بْنَ مُغَفَّلٍ، قَالَ رَأَيْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَوْمَ فَتْحِ مَكَّةَ وَهْوَ يَقْرَأُ عَلَى رَاحِلَتِهِ سُورَةَ الْفَتْحِ‏.‏
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 28
አቢ ሠዒድ ኢብኑ ሙዐላ እንደተረከው *ሶላት ላይ ሆኜ ነብዩ”ﷺ” ጠሩኝ፤ ነገር ጥሪያቸውን አልመለስኩላቸውም፤ በኃላ ላይ፦ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ሶላት ላይ ነበርኩኝ” አልኩኝ፤ እሳቸውም፦ አላህ፦ “(መልእክተኛው) በጠራችሁ ጊዜ ለአላህ እና ለመልክተኛው ታዘዙ”8፥24 አላለምን? ከዚያም፦ “በቁርኣን ውስጥ ታላቂቱን ሱራህ ላስተምርህን? እርሷም፦ “ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው የምትለዋ የሚደጋገሙ የሆኑ ሰባት ሱረቱል ፋቲሐህን እና ታላቁ ቁርኣንን ተሰጠኝ*። عَنْ أَبِي سَعِيدِ بْنِ الْمُعَلَّى، قَالَ كُنْتُ أُصَلِّي فَدَعَانِي النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم فَلَمْ أُجِبْهُ قُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ إِنِّي كُنْتُ أُصَلِّي‏.‏ قَالَ ‏”‏ أَلَمْ يَقُلِ اللَّهُ ‏{‏اسْتَجِيبُوا لِلَّهِ وَلِلرَّسُولِ إِذَا دَعَاكُمْ‏}‏ ثُمَّ قَالَ أَلاَ أُعَلِّمُكَ أَعْظَمَ سُورَةٍ فِي الْقُرْآنِ قَبْلَ أَنْ تَخْرُجَ مِنَ الْمَسْجِدِ ‏”‌‏.‏ فَأَخَذَ بِيَدِي فَلَمَّا أَرَدْنَا أَنْ نَخْرُجَ قُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ إِنَّكَ قُلْتَ لأُعَلِّمَنَّكَ أَعْظَمَ سُورَةٍ مِنَ الْقُرْآنِ‏.‏ قَالَ ‏”‌‏{‏الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ‏}‏ هِيَ السَّبْعُ الْمَثَانِي وَالْقُرْآنُ الْعَظِيمُ الَّذِي أُوتِيتُهُ ‏”‌‏.‏
15፥87 *ከሚደጋገሙ የኾኑን ሰባትን እና ታላቁንም ቁርኣን በእርግጥ ሰጠንህ*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَاكَ سَبْعًا مِّنَ الْمَثَانِي وَالْقُرْآنَ الْعَظِيمَ

የሚደጋገሙ ሰባት አንቀጾች ሱረቱል ፋቲሓህ ነው፤ ምክንያቱም ሱረቱል ፋቲሓህ ሰባት አናቅጽ አላት፤ በተጨማሪም ነብያችን”ﷺ” ነግረውናል፤ ይህቺ ሱራህ በቁርኣን ውስጥ ታላቂቱ ሱራ ብትባልም ከቁርኣን “ወ” وَ ማለትም “እና” በሚል መስተጻምር መለየቱ ሱረቱል ፋቲሓህ የቁርኣን እናት ማለት መሰረት መሆኗን ያሳያል፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3415 
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *አል-ሐምዱሊሏህ የቁርኣን እናት፣ የመጽሐፉ እናት እና ሰባት የተደጋገሙ ናት*። عَنِ ابْنِ أَبِي ذِئْبٍ، عَنِ الْمَقْبُرِيِّ، عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْحَمْدُ لِلَّهِ أُمُّ الْقُرْآنِ وَأُمُّ الْكِتَابِ وَالسَّبْعُ الْمَثَانِي ‏”

የሚያጅበው ነገር ቁርኣን ላይ ችግር እንዳይኖር አላህ በነብያችን”ﷺ” ሰሃባዎች ዘመን ሁሉን ነገር አስተካክሎታል፤ ቁርኣን እንደ በፊቶቹ መጽሐፍት ከፊቱና ከኃላው ሰዎች ውሸት እንዳይጨመሩበት የዓለማቱ ጌታ ይጠብቀዋል፦
41፥42 *ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፤ ጥበበኛ ምስጉን ከኾነው ጌታ የተወረደ ነው*፡፡ لَّا يَأْتِيهِ ٱلْبَٰطِلُ مِنۢ بَيْنِ يَدَيْهِ وَلَا مِنْ خَلْفِهِۦ ۖ تَنزِيلٌۭ مِّنْ حَكِيمٍ حَمِيدٍۢ
15፥9 *እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን*፡፡ إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የቁርኣን አነባነብ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

73፥4 ወይም በእርሱ ላይ ጨምር፤ *ቁርኣንንም በተርቲል ማንበብን አንብብ*፡፡ أَوْ زِدْ عَلَيْهِ وَرَتِّلِ الْقُرْآنَ تَرْتِيلًا

“ቁርኣን” قُرْءَان የሚለው ቃል “ቀረአ” قَرَأَ ማለትም “አነበበ” ወይም “አነበነበ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “መነባነብ”recitation” ማለት ነው፤ የቁርኣን "አነባነብ" ደግሞ "ቂራኣት" قـِراءات ይባላል፤ አምላካችን አላህ በጂብሪል ለነብያችን"ﷺ" ቁርኣንን አስቀርቷቸዋል፦
87፥6 *ቁርኣንን በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም*፡፡ سَنُقْرِئُكَ فَلَا تَنسَىٰ
75፥18 *ባነበብነውም ጊዜ ንባቡን ተከተል*፡፡ فَإِذَا قَرَأْنَاهُ فَاتَّبِعْ قُرْآنَهُ

"እናስነብብሃለን" ለሚለው የገባው "ሠኑቅኡሪኡከ" سَنُقْرِئُكَ ሲሆን "ባነበብነው" ለሚለው ደግሞ "ቀረእናሁ" قَرَأْنَاهُ ነው፤ ይህ የሚያሳየው የአላህ ንግግር መነባነብ መሆኑን ነው፤ አምላካችን አላህ ይህንን ቁርኣን ወደ ነብያችን"ﷺ" ያስቀራው በተርቲል ነው፦
25፥32 እነዚያ የካዱትም «ቁርኣን በእርሱ ላይ ለምን በጠቅላላ አንድ ጊዜ አልተወረደም?» አሉ፤ *እንደዚሁ በእርሱ ልብህን ልናረጋ በተርቲል አነበብነው*፡፡ وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْلَا نُزِّلَ عَلَيْهِ الْقُرْآنُ جُمْلَةً وَاحِدَةً ۚ كَذَٰلِكَ لِنُثَبِّتَ بِهِ فُؤَادَكَ ۖ وَرَتَّلْنَاهُ تَرْتِيلًا

"ረተልናሁ" رَتَّلْنَاهُ ማለት "አነበብነው" ማለት ሲሆን "ተርቲል" تَرْتِيل ማለት "የአነባነብ ስልት"manner of recitation" ማለት ነው፦
73፥4 ወይም በእርሱ ላይ ጨምር፤ *ቁርኣንንም በተርቲል ማንበብን አንብብ*፡፡ أَوْ زِدْ عَلَيْهِ وَرَتِّلِ الْقُرْآنَ تَرْتِيلًا

እዚህ አንቀጽ ላይ "አንብብ" ለሚለው የገባው "ረተል" رَتَّلْ ሲሆን በተርቲል መቅራትን ያመልክታል፤ ይህ የአቀራር ስልት ወደ ነብያችን"ﷺ" የወረደው በሰባት አይነት የአቀራር ስልት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 13
ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ጂብሪል ለእኔ በአንድ ሐርፍ አቀራር ይቀራልኝ ነበር፤ ከዚያም እኔ በሌላ ሐርፍ እንዲያስቀራኝ ጠየኩት፤ በተደጋጋሚ ስጠይቀው በሰባት አሕሩፍ በመቅራት ጨመረልኝ*። أَنَّ ابْنَ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ حَدَّثَهُ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ أَقْرَأَنِي جِبْرِيلُ عَلَى حَرْفٍ فَرَاجَعْتُهُ، فَلَمْ أَزَلْ أَسْتَزِيدُهُ وَيَزِيدُنِي حَتَّى انْتَهَى إِلَى سَبْعَةِ أَحْرُفٍ ‏"‌‏.‏
"ሐርፍ" حَرف ማለት ቋንቋዊ ትርጉሙ "ፊደል" ማለት ሲሆን እዚህ ዐውድ ላይ ግን "የአነባነብ ስልት"mode of recitation" ማለት ነው፤ ምክንያቱም "አቅረአኒ" أَقْرَأَنِي ማለትም "ይቀራልኝ" የሚል ሃይለ-ቃል ስላለ፤ የሐርፍ ብዙ ቁጥር "አሕሩፍ" أَحْرُف ነው፤ ይህ የቁርኣን አነባነብ ልዩነት ከአላህ በጂብሪል ለነብያችን"ﷺ" የተወረደ ሲሆን ይህንን ልዩነት በነብያችን"ﷺ" ዘመን በአንድ የቁሬሽ ዘዬ በነበሩት በዑመር ኢብኑል ኸጧብ"ረ.ዐ." እና በሂሻም ኢብኑ ሐኪም"ረ.ዐ." መካከል በነበረው የቂራኣት ልዩነት ማየት ይቻላል፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 14
ዑመር ኢብኑል ኸጧብ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" በሕይወት እያሉ ሂሻም ኢብኑ ሐኪም"ረ.ዐ." ሱረቱል ፉርቃንን ሲቀራ ሰማሁት፤ የእርሱ አቀራር የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ለእኔ ባልቀሩልኝ በተለየ በሌላ ሐርፍ ሲቀራ ሰማሁት፤ በሶላቱ ላይ እያለ ወደ እርሱ ዘልዬ ነበር፤ ነገር ግን ንዴቴን መቆጣጠር ነበረብኝ፤ ሶላቱን በጨረሰ ጊዜ በአንገቱ ዙሪያ ከላይ ያለውን ልብስ አውልቄ በእርሱ ያዝኩትና፦ "እኔ ይህንን እኔ የሰማሁትን ማን ነው ያስተማረህ? ብዬ ስለው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ብሎ መለሰልኝ፤ እኔም፦ "ከአንተ በተለየ ለእኔ የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ባስተማሩኝ ትዋሻለህ አልኩት፤ ከዚያም ወደ የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" አመጣሁት፤ ከዚያም፦ "ለአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ይህንን ሰው ሱረቱል ፉርቃንን እርሶ ባላስተማሩኝ ሐርፍ ሲቀራ ሰማሁት፤ የአላህ መልእክተኛም"ﷺ"፦ "ልቀቀው፤ ሂሻም ሆይ! ቅራ አሉት፤ ከዚያም እኔ በሰማሁበት ሐርፍ ሲቀራ ሰማሁት፤ የአላህ መልእክተኛም"ﷺ"፦ "በዚህ ሐርፍ ለእኔ ተወርዶልኛል፤ ዑመር ሆይ! ቅራ አሉኝ፤ እኔ እሳቸው ባስተማሩኝ ቀራሁኝ፤ እርሳቸውም፦ "ለእኔ በዚህ ሐርፍ ተወርዶልኛል፤ ቁርኣንን በሰባት ሐርፎች እንድቀራ ተወርዶልኛል፤ ስለዚህ የትኛውንም የሚቀላችሁን ቅሩት*። سَمِعَا عُمَرَ بْنَ الْخَطَّابِ، يَقُولُ سَمِعْتُ هِشَامَ بْنَ حَكِيمٍ، يَقْرَأُ سُورَةَ الْفُرْقَانِ فِي حَيَاةِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَاسْتَمَعْتُ لِقِرَاءَتِهِ فَإِذَا هُوَ يَقْرَأُ عَلَى حُرُوفٍ كَثِيرَةٍ لَمْ يُقْرِئْنِيهَا رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَكِدْتُ أُسَاوِرُهُ فِي الصَّلاَةِ فَتَصَبَّرْتُ حَتَّى سَلَّمَ فَلَبَّبْتُهُ بِرِدَائِهِ فَقُلْتُ مَنْ أَقْرَأَكَ هَذِهِ السُّورَةَ الَّتِي سَمِعْتُكَ تَقْرَأُ‏.‏ قَالَ أَقْرَأَنِيهَا رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم‏.‏ فَقُلْتُ كَذَبْتَ فَإِنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَدْ أَقْرَأَنِيهَا عَلَى غَيْرِ مَا قَرَأْتَ، فَانْطَلَقْتُ بِهِ أَقُودُهُ إِلَى رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَقُلْتُ إِنِّي سَمِعْتُ هَذَا يَقْرَأُ بِسُورَةِ الْفُرْقَانِ عَلَى حُرُوفٍ لَمْ تُقْرِئْنِيهَا‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ أَرْسِلْهُ اقْرَأْ يَا هِشَامُ ‏"‌‏.‏ فَقَرَأَ عَلَيْهِ الْقِرَاءَةَ الَّتِي سَمِعْتُهُ يَقْرَأُ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ كَذَلِكَ أُنْزِلَتْ ‏"‌‏.‏ ثُمَّ قَالَ ‏"‏ اقْرَأْ يَا عُمَرُ ‏"‌‏.‏ فَقَرَأْتُ الْقِرَاءَةَ الَّتِي أَقْرَأَنِي، فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ كَذَلِكَ أُنْزِلَتْ، إِنَّ هَذَا الْقُرْآنَ أُنْزِلَ عَلَى سَبْعَةِ أَحْرُفٍ فَاقْرَءُوا مَا تَيَسَّرَ مِنْهُ ‏"‌‏.‏

እንግዲህ ይህንን ሰባት የአነባነብ ስልት ከነብያችን"ﷺ" በዋነኝነት ያስተላለፉ ሰሃባዎች ዑበይ ኢብኑ ከዐብ፣ ዘይድ ኢብኑ ሣቢት፣ ዐብደሏህ ኢብኑ መሥዑድ፣ አቡ አዝ-ዘርዳ፣ ዐሊ ኢብኑ አቡ ጧሊብ፣ አቡ ሙሳ አልሻሪ፣ ዑስማን ኢብኑ አፋን ናቸው።
በሰባቱ አነባነብ ስልት የተላለፈ ሪዋያህ ደግሞ፦
1ኛ. ቃሪ ከመዲና ናፊ ኢብኑ አብ ሲሆን ቂራአቱ የተላለፈው ደግሞ ከዑበይ ኢብኑ ከዐብ ነው።
2ኛ. ቃሪ ከመካ ኢብኑ ከሲር ሲሆን ቂራአቱ የተላለፈው ደግሞ ከዘይድ ኢብኑ ሣቢት ነው።
3ኛ. ቃሪ ከደማስቆ አቡ አምር ሲሆን ቂራአቱ የተላለፈው ደግሞ ከዐብደሏህ ኢብኑ መሥዑድ ነው።
4ኛ. ቃሪ ከባስራ ኢብኑ አምር ሲሆን ቂራአቱ የተላለፈው ደግሞ ከአቡ አዝ-ዘርዳ ነው።
5ኛ. ቃሪ ከኩፋ አሲም ኢብኑ አብ ሲሆን ቂራአቱ የተላለፈው ደግሞ ከዐሊ ኢብኑ አቡጣሊብ ነው።
6. ቃሪ ከኩፋ ሃምዛ ኢብኑ ሲሆን ቂራአቱ የተላለፈው ደግሞ ከአቡ ሙሳ አልሻሪ ነው።
7. ቃሪ ከኩፋ አል-ኪሳኢ ሲሆን ቂራአቱ የተላለፈው ሃቢብደግሞ ከዑስማን ኢብኑ አፋን ነው።

"ሪዋያህ" رِواية ማለት "መስተጋብ" "ስንክሳር" "transmission" ማለት ነው፤ ይህ በሙተዋቲር የተላለፈው ሰንሰለት የሃፍሥ ሪዋያ፣ የወርሽ ሪዋያ፣ የቃሉን ሪዋያ፣ የዱሪ ሪዋያ፣ የሂሻም ሪዋያ፣ የሩህ ሪዋያ እና የባዚ ሪዋያ ሲባል ሲሆን ከአላህ በጂብሪል የተወረደ ግህደተ-መለኮት እንጂ ሰዎች የፈጠሩት ልዩነት አይደለም። ኢንሻላህ በክፍል ሁለት ስለነዚህ ጤናማ ልዩነቶች እንዳስላለን....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የቁርኣን አነባነብ

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

25፥32 እነዚያ የካዱትም «ቁርኣን በእርሱ ላይ ለምን በጠቅላላ አንድ ጊዜ አልተወረደም» አሉ፡፡ *እንደዚሁ በእርሱ ልብህን ልናረጋ ከፋፍለን አወረድነው፤ ቀስ በቀስ መለያየትንም ለየነው*፡፡ وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْلَا نُزِّلَ عَلَيْهِ الْقُرْآنُ جُمْلَةً وَاحِدَةً ۚ كَذَٰلِكَ لِنُثَبِّتَ بِهِ فُؤَادَكَ ۖ وَرَتَّلْنَاهُ تَرْتِيلًا

የቁርኣን አነባነቡ ጤናማ የኢዕራብ ልዩነት አለው፤ “ኢዕራብ” إﻋﺮﺍﺏ ማለት “ሙያ”case” ማለት ሲሆን ይህ ሙያ “ፈትሐህ” فَتْحَة “ከስራህ” كَسْرَة “ደማህ” ضَمَّة በሚባሉ አጭር አናባቢ ሐርፎች ላይ ያገለግላሉ።
በፈትሐህ የሚያገለግለው ሙያ “መንሱብ” منصوب ማለትም ተሳቢ ሙያ”accusative case” ይባላል።
በከስራህ የሚያገለግለው ሙያ “መጅሩር” مجرور ማለትም አገናዛቢ ሙያ”genitive case” ይባላል።
በደማ የሚያገለግለው ሙያ ደግሞ “መርፉዕ” مرفوع ማለትም ባለቤት ሙያ”nominative case” ይባላል።
እዚህ ድረስ ከተግባባን ለናሙና ያክል ሁለት ሁለት ሪዋያዎችን ማየት እንችላለን፦
30፥54 *አላህ ያ "ከደካማ" ፍትወት ጠብታ የፈጠራችሁ ነው*፡፡ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن ضَعْف
ሱነን አቢ ዳውድ: መጽሐፍ 32, ሐዲስ 10
ዐብደሏህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ ዐጢያህ ኢብኑ ሠዕድ አል-ዐውፍፊይ እንዳለው፦ *"እኔ ለዐብደሏህ ኢብኑ ዑመር "አላህ ያ "ከደካማ"ደዕፍ" ፍትወት ጠብታ የፈጠራችሁ ነው"* ብዬ ቀራሁለት፤ እርሱም፦ *"ከደካማ"ዱዕፍ"*
አለ፤ *አንተ ለእኔ እንደቀራኸው እኔም ለአላህ መልእክተኛ ቀርቻለው፤ እኔ አንተን እንዳስያዝኩህ እርሳቸው እኔን አስይዘውኛል"*። عَنْ عَطِيَّةَ بْنِ سَعْدٍ الْعَوْفِيِّ، قَالَ قَرَأْتُ عَلَى عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُمَرَ ‏{‏ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَكُمْ مِنْ ضَعْفٍ ‏}‏ فَقَالَ ‏{‏ مِنْ ضُعْفٍ ‏}‏ قَرَأْتُهَا عَلَى رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم كَمَا قَرَأْتَهَا عَلَىَّ فَأَخَذَ عَلَىَّ كَمَا أَخَذْتُ عَلَيْك
የዱሪ ቂሪኣት "ዷድ" ض ፈትሐህ "ደ" ضَ በሚል ሪዋያህ "ደዕፍ" ضَعْف ብሎ ሲቀራው፤ የቃሉን ቂሪኣት ደግሞ "ዷድ" ض ደማህ "ዱ" ضُ በሚል ሪዋያህ "ዱዕፍ" ضُعْف ተብሎ ይቀራዋል።
እንቀጥል፦
11፥46 አላህም፦ «ኑሕ ሆይ! እርሱ ከቤተሰብህ አይደለም፤ *እርሱ መልካም ያልሆነ ሥራ ነው*። قَالَ يَا نُوحُ إِنَّهُ لَيْسَ مِنْ أَهْلِكَ ۖ إِنَّهُ عَمَلٌ غَيْرُ صَالِح
ሱነን አቢ ዳውድ: መጽሐፍ 32, ሐዲስ 15
ኡሙ ሰለማህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦
*"ሻህር ኢብኑ ሐውሸብም አለ፦ "እኔም ኡሙ ሰለማህን የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዴት አድርገው ነው "እርሱ መልካም ያልሆነ"ገይሩ" ሥራ ነው" የሚለውን ይህንን አንቀጽ የሚቀሩት? እርሷም፦ "እርሱ መልካም ያልሆነ"ገይረ" ሥራ ነው" ብለው ነው የሚቀሩት አለች*። عَنْ شَهْرِ بْنِ حَوْشَبٍ، قَالَ سَأَلْتُ أُمَّ سَلَمَةَ كَيْفَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم صلى الله عليه وسلم يَقْرَأُ هَذِهِ الآيَةَ ‏{‏ إِنَّهُ عَمَلٌ غَيْرُ صَالِحٍ ‏}‏ فَقَالَتْ قَرَأَهَا ‏{‏ إِنَّهُ عَمِلَ غَيْرَ صَالِحٍ ‏}‏

የሂሻም ቂሪኣት "ሯ" ر ደማህ "ሩ" رُ በሚል ሪዋያህ "ገይሩ" غَيْرُ ብሎ ሲቀራው፤ የባዚ ቂሪኣት ደግሞ "ሯ" ر ፈትሐህ "ረ" رَ በሚል ሪዋያህ "ገይረ" غَيْرَ ተብሎ ይቀራዋል።
እንቀጥል፦
1፥4 *የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው*፡፡ مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ

የሃፍሥ ቂሪኣት "ሚም" م ፈትሐህ ያ ስኩን "ማ" مَا በሚል ሪዋያህ ሁለት ሃረካህ ስቦ "ማሊክ" مَالِك ብሎ ሲቀራው፤ የወርሽ ቂሪኣት ደግሞ "ሚም" م ፈትሐህ "መ" مَ በሚል ሪዋያህ አንድ ሃረካህ ስቦ "መሊክ" مَلِك ተብሎ ይቀራዋል።
እንቀጥል፦
1፥6 *ቀጥተኛውን "መንገድ" ምራን*፡፡ اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ

የሃፍሥ ቂሪኣት "ሷድ" ص ከስራህ
"ሲ" صِ በሚል ሪዋያህ "ሲሯጥ" صِرَٰط ብሎ ሲቀራው፤ የወርሽ ቂሪኣት ደግሞ "ሢን" س ከስራህ "ሢ" سِ በሚል ሪዋያህ "ሢሯጥ" ِسِرَٰط ተብሎ ይቀራዋል።
እንቀጥል፦
5፥6 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወደ ሶላት በቆማችሁ ጊዜ ፊቶቻችሁን፣ እጆቻችሁንም እስከ ክርኖች እጠቡ፡፡ ራሶቻችሁንም በውሃ አብሱ፤ *"እግሮቻችሁንም" እስከ ቁርጭምጭሚቶች እጠቡ*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِذَا قُمْتُمْ إِلَى ٱلصَّلَوٰةِ فَٱغْسِلُوا۟ وُجُوهَكُمْ وَأَيْدِيَكُمْ إِلَى ٱلْمَرَافِقِ وَٱمْسَحُوا۟ بِرُءُوسِكُمْ وَأَرْجُلَكُمْ إِلَى ٱلْكَعْبَيْنِ

የዱሪ ቂሪኣት "ላም" ل ፈትሐህ
"ለ" لَ በሚል ሪዋያህ "አርጁ'ለ'ኩም" أَرْجُلَكُمْ ብሎ ሲቀራው፤ የሩህ ቂሪኣት ደግሞ "ላም" ل ከስራህ "ሊ" لِ በሚል ሪዋያህ "አርጁ'ሊ'ኩም" أَرْجُلِكُمْ ተብሎ ይቀራዋል።
እንቀጥል፦
8፥128 *ከጎሳችሁ የሆነ ችግራችሁ በእርሱ ላይ ጽኑ የሆነ፣ በእናንተ እምነት ላይ የሚጓጓ፣ በምእምናን ላይ ርኅሩኅ አዛኝ የኾነ መልክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ*፡፡ لَقَدْ جَاءَكُمْ رَسُولٌ مِّنْ أَنفُسِكُمْ عَزِيزٌ عَلَيْهِ مَا عَنِتُّمْ حَرِيصٌ عَلَيْكُم بِالْمُؤْمِنِينَ رَءُوفٌ رَّحِيمٌ

የሂሻም ቂሪኣት "ፋ" ف ደማህ
"ፉ" فُ በሚል ሪዋያህ "አን'ፉ'ሢኩም" أَنْفُسِكُمْ ብሎ ሲቀራው፤ የባዚ ቂሪኣት ደግሞ "ፋ" ف ፈትሐህ "ፈ" فَ በሚል ሪዋያህ "አን'ፈ'ሲኩም" أَنْفَسِكُم ተብሎ ይቀራዋል።
እንዲህ አይነት ጤናማ የኢዕራብ ልዩነት ከዓለማቱ ጌታ ከአላህ የተወረደ እንጂ ነብያችን"ﷺ" ሆኑ ሶሐባህ ወይም ታቢኢይ አሊያም አትባኡ ታቢኢይ የፈለሰፉት አይደለም። አምላካችን አላህ እራሱ በተርቲል እንደለየው ይናገራል፦
25፥32 እነዚያ የካዱትም «ቁርኣን በእርሱ ላይ ለምን በጠቅላላ አንድ ጊዜ አልተወረደም» አሉ፡፡ *እንደዚሁ በእርሱ ልብህን ልናረጋ ከፋፍለን አወረድነው፤ ቀስ በቀስ መለያየትንም ለየነው*፡፡ وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْلَا نُزِّلَ عَلَيْهِ الْقُرْآنُ جُمْلَةً وَاحِدَةً ۚ كَذَٰلِكَ لِنُثَبِّتَ بِهِ فُؤَادَكَ ۖ وَرَتَّلْنَاهُ تَرْتِيلًا

መደምደሚያ
አንድ ሰው ያምሃል? ስትቱት አንተም ያምሃል ካላችሁ ህመምተኛ መሆኑን አምኗል ማለት ነው፤ ባይብል የሰው ቃል ገብቶበታል ስትሏቸው እረ በፍጹም በማለት ፋንታ ቁርኣንም እንደዛው ሲሉ ባይብል የሰው ቃል መግባቱን ያረጋግጥሏችኃል፤ እከክልኝ ልከክልህ ነው። የሚገርመው የባይብል ልዩነት የፈጠሩት ለምሳሌ የአዲስ ኪዳን ልዩነትን ያመጣው ፈጣሪ ወይም ኢየሱስ አሊያም ሐዋርያት ሳይሆን ከዚያ በኃላ ያሉት ናቸው፤ ዛሬ ያሉት 5800 ቀዳማይ የግሪክ እደ-ክታባት ኢየሱስ ካስተማረ ከሥስት መቶ አመት በኋላ የተዘጋጁ ናቸው፦ ሳይናቲከስ ጥራዝ 330 ድህረ-ልደት"AD"፣ ቫቲካነስ ጥራዝ 350 ድህረ-ልደት"AD"፣ አሌክሳንድሪየስ ጥራዝ 400 ድህረ-ልደት"AD"፣ ኤፍሬማይ ጥራዝ 450 AD ላይ የተዘጋጁ ናቸው፣ እሩቅ ሳንሄድ በሳይናቲከስና በቫቲካነስ መካከል 3,036 የትርጉምና የቃላት ልዩነት አላቸው፣ በማቴዎስ ወንጌል 656 ልዩነት፣ በማርቆስ ወንጌል 567 ልዩነት፣ በሉቃስ ወንጌል 791 ልዩነት፣ በዮሐንስ ወንጌል 1022 ልዩነት አላቸው። ዋቢ መጽሐፍ ይመልከቱ፦
Bart D. Ehrman, The Text of the New Testament: Its Transmission, Corruption and Restoration, (Oxford University Press, 2005), p. 147.

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም