ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.1K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ተራዊህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

“ዒባዳህ” عِبَادَة ማለትም “አምልኮ” አላህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኝባቸው ሥስት ሸርጦች ኢማን፣ ኢኽላስ እና ኢቲባዕ ናቸው። “ኢቲባዕ” إتباع የሚለው ቃል “አትበዐ” أَتْبَعَ “ተከተለ” ከሚለው የመጣ ሲሆን “መከተል” ማለት ሲሆን ያለ ኢቲባዕ ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም። ኢቲባዕ ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው ብቻ ዒባዳህን መፈጸም ነው፦
7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ*፤ اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ
6፥106 *ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን ተከተል* ፡፡ اتَّبِعْ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ

“ተከተሉ” የሚለው ቃል “ኢተቢዑ” اتَّبِعُوا ሲሆን “ኢቲባዕ” إتباع ማለት እንግዲህ ከአላህ ወደ ነብያችን”ﷺ” የተወረደውን ብቻ መከተል ነው፤ ወደ ነብያችን”ﷺ” የተወረደው ደግሞ ቁርኣን እና ሰሒህ ሐዲስ ነው።

“ቢድዓ” بدع ደግሞ “በደዐ” بدع ማለትም “ፈጠረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ኢብቲዳዕ” ابتداع ማለትም “ፈጠራ” ማለት ነው፤ ቢድዓ የኢቲባዕ ተቃራኒ ነው። ቢድዓ ማለት ከአምስቱ አሕካም ውጪ አዲስ ፈጠራ ማለት ነው፤ ስለ ቢድዓ ነብያችን”ﷺ” እንዲህ ይሉናል፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 53, ሐዲስ 7
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ማንኛውም ሰው ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም"* عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ فِيهِ فَهُوَ رَدٌّ ‏”‌‏.‏
ሡነን ነሣኢ : መጽሐፍ 19, ሐዲስ 23
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሑጥባቸው ላይ እንደተናገሩት፦ *“አላህ የመራውን ማንም አያጠመውም፤ አላህ ያጠመመውን ማንም አያቀናውም። ከንግግር ሁሉ በላጩ የአላህ መጽሐፍ ነው፤ ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነው። ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው*። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ فِي خُطْبَتِهِ يَحْمَدُ اللَّهَ وَيُثْنِي عَلَيْهِ بِمَا هُوَ أَهْلُهُ ثُمَّ يَقُولُ مَنْ يَهْدِهِ اللَّهُ فَلَا مُضِلَّ لَهُ وَمَنْ يُضْلِلْهُ فَلَا هَادِيَ لَهُ إِنَّ أَصْدَقَ الْحَدِيثِ كِتَابُ اللَّهِ وَأَحْسَنَ الْهَدْيِ هَدْيُ مُحَمَّدٍ وَشَرُّ الْأُمُورِ مُحْدَثَاتُهَا وَكُلُّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلُّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ وَكُلُّ ضَلَالَةٍ فِي النَّارِ .

ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ከሆነ ካየን ቢድዓ የሚያራምድ ማንኛውም ሰው “ሙብተዲዕ” مبتدئ ይባላል።
ይህንን ለቅምሻ ያክል በወፍ በረር ካየን ዘንዳ ሚሽነሪዎች፦ "ተራዊህ" تراويح‌‎ ማለትም "በረመዳን የሌሊት ሶላት" ነብያችን"ﷺ" የማያውቁትና ያልሰሩት ነው ብለው ለሚቀጥፉት ቅጥፈት ምላሽ መስጠት ግድ ይላል፤ ስለ ተራዊህ ከነብያችን"ﷺ" ሱና በቁና ማቅረብ ይቻላል፦
ኢማም ቡኻርይ: Book 31, Hadith 4
የነብዩ"ﷺ" ባልተቤት ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" በረመዳን ሌሊት ይጸልዩ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، رضى الله عنها زَوْجِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم صَلَّى وَذَلِكَ فِي رَمَضَانَ‏.‏
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 31, ሐዲስ 1
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ስለ ረመዳን እንደተናገሩት፦ *"ማንም በረመዳን ሌሊት በእምነት እና ከአላህ ወሮታ አገኛለው ብሎ ተስፋ አድርጎ ከቆመ ያለፈው ወንጀሉ ሁሉ ይቅር ይባልለታል"*። أَنَّ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ لِرَمَضَانَ ‏ "‏ مَنْ قَامَهُ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ ‏"‌‏.‏

አምላካችን አላህ፦ "መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፤ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ" ስላለን ተራዊህ መልእክተኛው የነገሩን ነገር ስለሆነ ቢድዓ አይደለም፦
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የእግዚአብሔር ልጅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

18፥4 *እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው*፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا

ክርስቲያኖች ኢየሱስ "የእግዚአብሔር ልጅ" ነው ይላሉ፤ "ልጅ" ማለት ምን ማለት ነው? ስንላቸው፦ "አብን አህሎና መስሎ ከአብ “ባህርይ ዘእም-ባህርይ አካል ዘእም-አካል” ማለትም ከባህርይው ባህርይ ወስዶ ከአካሉ አካሉን ወስዶ ተወለደ" ይሉናል። እረ ከሰማናቸው፦ “አምላክ ዘእም-አምላክ ማለትም ከአምላክ የተገኘ አምላክ" ይሉናል። ከእዚህ እሳቤ ቁርኣን በተቃራኒው፦ "አላህ ወለደ" ያሉ በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፤ አላህ አልወለደም፤ አልተወለደምም፤ እንደውም አላህ ቁርኣን ካወረደበት ምክንያት አንዱ እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት ነው፦
37፥152 ፦ *“አላህ ወለደ” አሉ፤ እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው*፡፡ وَلَدَ اللَّهُ وَإِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ
112፥3 *አልወለደም፤ አልተወለደምም*፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ
18፥4 *እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው*፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا

ይህንን የቁርኣን እሳቤ ካየን ዘንዳ ባይብል ላይ እግዚአብሔር አባት መባሉ "አገኚ" ወይም "ፈጣሪ" በሚል ፍካሬአዊ ቃል መጥቷል፦
ሚልክያስ 2፥10 ለሁላችን *”አንድ አባት”* ያለን አይደለምን? *አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን*?
ዮሐንስ 8፥41 *አንድ አባት* አለን *እርሱም እግዚአብሔር ነው*፡ አሉት።
ኤፌሶን 4፥6 ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር *አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ*።

ለምሳሌ መላእክት መናፍስት ተብለዋል፤ እግዚአብሔር የመናፍስት አባት ነው። መናፍስቱ መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፦
ዕብራውያን 12፥9 እንዴትስ ይልቅ *ለመናፍስት አባት* አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን?
ዕብራውያን 1፥14 *ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?*
ኢዮብ 38፥7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ *የእግዚአብሔርም ልጆች* ሁሉ እልል ሲሉ፥

መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት ያለ እናት እና ያለ አባት ስለፈጠራቸው እንደሆነ ቅቡል ነው፤ አዳምም የእግዚአብሔር ልጅ ተብሏል፦
ሉቃስ 3፥38 የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥ *የእግዚአብሔር ልጅ*።
አዳም የእግዚአብሔር ልጅ የተባለው ያለ እናት እና ያለ አባት ስለፈጠረው እንደሆነ እሙን ነው፤ ታዲያ ያለ አባት በእናት ብቻ የተፈጠረው ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ቢባል ምን ይደንቃል? ከማርያም ተጸንሶ የተወለደው ሰው መሆኑን አንርሳ፦
ሉቃስ 1፥35 ስለዚህ ደግሞ *ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል*።
ገላትያ 4 ፥4 ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ *እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ*፤

ማርያም የወለደችው መለኮትን ሳይሆን ሰው ብቻ ነው፤ ያም ሰው የእግዚአብሔር ልጅ መባሉ ፈጣሪ ያለ አባት ከእርሷ መፍጠሩን ያሳያል። አይ እግዚአብሔር ኢየሱስን ወለደው ይሉናል፦
መዝሙር 2፥7 ትእዛዙን እናገራለሁ፤ *እግዚአብሔር አለኝ። አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ “ወለድሁህ”*።
ዕብራውያን 1:5 ከመላእክትስ። *እግዚአብሔር አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ “ወልጄሃለሁ”*፥ (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ጭራሽ ይህ ጥቅስ “ዛሬ” የምትለዋ ቃል መነሻ ጊዜን ታመለክታለች፣ ይህም የኢየሱስ መፈጠር በጊዜ ውስጥ መሆኑን ያሳያል፤ ሲቀጥል "ወለደ" የሚለው በግሪኩ “ጄኑስ” γένος ማለት “ፈጠረ” ሲሆን አይሁዳውያን አምላክ ፆታ ስለሌለውን “መወለድ” መፈጠር ነው ብለው ያምናሉ፤ ምክንያቱን ተራራ እንደተወለደ ስለሚናገር፤ ያ ማለት ተራራ ተሰራ ማለት ነው፦
መዝሙር 90:2 *”ተራሮች ሳይወለዱ”* γεννήθηκαν፥
አሞፅ 4:13 እነሆ፥ *”ተራሮችን የሠራ”*፥

ተራሮች "ሳይወለዱ" የሚለው ይሰመርበርበት፤ ተራራ ይወለዳል እንዴ? ስንል መልሱ "ይወለዳል" የሚለው እማራዊ ቃል “ይሰራል” ማለት ነው፤ በተመሳሳይ “ወለደ” ማለት “ፈጠረ” ማለት መሆኑን “የወለደህን አምላክ” የሚለው ቃል “የፈጠረውን አምላክ” በሚል ተለዋዋጭ ቃል መምጣቱ ነው፦
ዘዳግም 32፥18 *የወለደህን አምላክ ተውህ*፥ NIV
ዘዳግም 32፥15 ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፤ *የፈጠረውንም አምላክ ተወ*፤ NIV

"ይሽሩ" የእስራኤላውያን የቁልምጫ ስም ነው፤ አምላክ እስራኤላውን "ወለደ" ወይስ "ፈጠረ" ? አይ ፈጣሪ ጾታ ስለሌለው በእማሬአዊ ቃል ወለደ ማለት ሳይሆን በፍካሬአዊ ቃል ፈጠረ ለማለት ነው ከተባለ እንግዲያውስ ከላይ ያለውንም በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት። አንዳንድ ቂሎች "መወለድ" ከአብ "መውጣት" ነው ይላሉ፤ ምነው መንፈስ ቅዱስ ከአብ የሚወጣ ነው ትሉ የለ እንዴ? ለምን መንፈስ ቅዱስን የአብ ልጅ አትሉትም? አይ "መውጣት" ማለት "መስረጽ" ነው ካላችሁ ለምንስ ወልድን ከአብ የሰረጸ ነው አትሉትም? ምክንያቱም ወልድም ከአብ የወጣ ነው ስለሚል፤ አይ መውጣት መላክ ማለት ነው ካላችሁ ጥሩ። ካልሆነ ልጅ ማለት፦ "አብን አህሎና መስሎ ከአብ ባህርይ ዘእም-ባህርይ አካል ዘእም-አካል ማለትም ከባህርይው ባህርይ ወስዶ ከአካሉ አካሉን ወስዶ ተወለደ፤ አምላክ ዘእም-አምላክ ማለትም ከአምላክ የተገኘ አምላክ" ካላችሁ ይህንን እሳቤ አይደለም ቁርኣን ባይብላችሁም አይደግፋችሁ። በዚህ ስሌት ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፦
19፥35 *ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል*፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
2፥116 *አላህም ልጅ አለው አሉ፡፡ ከሚሉት ጥራት ተገባው፡፡ አይደለም በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ሁሉም ለእርሱ ታዛዦች ናቸው*፡፡ وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ وَلَدًۭا ۗ سُبْحَٰنَهُۥ ۖ بَل لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۖ كُلٌّۭ لَّهُۥ قَٰنِتُونَ
2፥117 ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ *ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን» ነው፤ ወዲያውም ይኾናል*፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ፍቅር

በዓለም ላይ ትልቁ ቁጥር ሴንቲሊዮን"Centillion" ነው፤ ባለ ስድስት መቶ ዜሮ የያዘ ነው። ይህንን ትልቅ ቁጥር ግን ከፊት ለፊቱ አንድ"1" ቁጥር ብትነሳ እነዚያ ሁሉ ዜሮ ሆነው ይቀራሉ። ከፊት ለፊት ዕውቀት፣ ጥበብ፣ ማስተዋል፣ ሃብት፣ ውበት ወዘተ ቢደረደሩም ከፊታቸው እንደ አንድ ቁጥር "ፍቅር" ከሌለ እንዚህ ሁሉ ዜሮ ናቸው። ፍቅር የሁሉ ነገር መነሻ ነው። ዓለማችን ሥርአቷን ጠብቃ በመሰሳብ እንዳትዛነፍ ያረጋት ይህ የፍቅር ሕግ ስበት"gravity" ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ኸምር

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥219 *አእምሮን ከሚቃወም መጠጥና ከቁማር ይጠይቁሃል፡፡ «በሁለቱም ውስጥ ታላቅ ኃጢኣትና ለሰዎች ጥቅሞች አሉባቸው፡፡ ግን ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ነው» በላቸው*፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ ۖ قُلْ فِيهِمَا إِثْمٌ كَبِيرٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ وَإِثْمُهُمَا أَكْبَرُ مِن نَّفْعِهِمَا

ከሚሽነሪዎች የሚሰነዘሩ ጥያቄዎች አብዛኛውን አርቲ ቡርቲና ቶራ ቦራ ናቸው፤ “አስካሪ መጠጥ በኢስላም ይፈቀዳል” የሚል ጥራዝ ነጠቅ መረጃ ይነዛሉ። ጠይቆ ከስሩ በአጽንኦትና በአንክሮት መረዳት የእናት ነው፤ “ነገርን ከስሩ ውሃን ከጡሩ” ይላል ያገሬ ሰው።
እስቲ ስለ ኸምር ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እናስተንትን፤ “ኸምር” خَمْر ማለት “ወይን ጠጅ” ማለት ሲሆን ከዘምባባ እና ከወይን ፍሬ የሚሰራ ጠጅ ነው፦
16፥67 *ከዘምባባዎች እና ከወይኖችም ፍሬዎች እንመግባችኋለን፡፡ ከእርሱ ጠጅን እና መልካም ምግብንም ትሠራላችሁ፡፡ በዚህም ውስጥ ለሚያስቡ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አለ*፡፡ وَمِن ثَمَرَاتِ النَّخِيلِ وَالْأَعْنَابِ تَتَّخِذُونَ مِنْهُ سَكَرًا وَرِزْقًا حَسَنًا ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّقَوْمٍ يَعْقِلُونَ

አላህ ከዘንባባ እና ከወይን ፍሬ ማብቀሉ በእርግጥ ታምር አለበት፤ ከዚህም ሰው በሰናይ መልካም ምግብ ማለትም ጭማቂ ሲሰራ በተቃራኒው እኩይ የሆነውን አስካሪ ጠጅን ይሰራል፤ “ዛሊከ” ذَٰلِكَ ማለትም “በዚህም” የተባለው አመልካች ተውላጠ-ስም”demonstrative pronoun ከበፊቱ ያለው “ሁ” هُ ማለትም “እርሱ” የተባለው ተሳቢ ተውላጠ-ስም”objective pronoun” የሚያመለክት ነው፤ ይህም “እርሱ” የተባለው ፍራፍሬው ነው፦
16፥11 *በእርሱ ለእናንተ አዝመራን፣ ወይራንም፣ ዘምባባዎችንም፣ ወይኖችንም፣ ከፍሬዎችም ሁሉ ያበቅልላችኋል፤ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ታምር አለ*። يُنبِتُ لَكُم بِهِ الزَّرْعَ وَالزَّيْتُونَ وَالنَّخِيلَ وَالْأَعْنَابَ وَمِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ዛሊከ” ذَٰلِكَ የተባለው የአዝመራን፣ የወይራንም፣ የዘምባባዎችንም፣ የወይኖችንም ፍራፍሬ ነው፤ ተጨማሪ አናቅጽ፦ 6፥99 13፥3 ይመልከቱ። ፍራፍሬ ሲቆይ ስኳርነቱ ወደ አሲድ ይቀየርና ያሰክራል፤ ይህ ሂደት በሥነ-ምርምር ጥናት ቆምጣጣነት”Fermentation” ይባላል፤ አሊያም ጌሾና ብቅል ሲቀላቀልበት ያሰክራል። ይህ ሂደት በሥነ-ምርምር ጥናት ፓስቸራዜሽን”Pasteurization” እና ኒዩትራላይዜሽን”Neutralization” ይባላል፤ ቢራ ፣ ቮድካ፣ ውስኪ የመሳሰሉት የዛ ውጤት ናቸው። ይህ ኣስካሪ መጠጥ አልኮልነት ሲኖረው የሰውን ህይወት በእጅጉ ይጎዳል፤ ነገር ግን በተፈጥሮ ሰውነታችን ውስጥ አልኮል ስላለ አልኮል ለጎደለው ሰውነት ጥቅም አለው፣ ከዚያም ባሻገር ጊዜአዊ ደስታ አለው። ነገር ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። አምላካችን አላህ ስለዚህ ጉዳይ እንዲህ ይለናል፦
2፥219 *አዕምሮን ከሚቃወም መጠጥ እና ከቁማር ይጠይቁሃል፡፡ «በሁለቱም ውስጥ ታላቅ ኃጢኣት እና ለሰዎች ጥቅሞች አሉባቸው፡፡ ግን ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ነው» በላቸው*፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ ۖ قُلْ فِيهِمَا إِثْمٌ كَبِيرٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ وَإِثْمُهُمَا أَكْبَرُ مِن نَّفْعِهِمَا

ቁማር ጥቅሙ ገንዘብ ቢሆንም የሰው ሃቅ ነውና ታላቅ ኃጢኣት ነው። አስካሪ መጠጥ ጥቅሙ ጊዚያዊ ደስታ ቢሆንም አዕምሮን የሚያደንዝና ለጥል፣ ለጥላቻ፣ ለዝሙት፣ ለጣዖት አምልኮ የሚዳርግ፤ ከሰላትና አላህ ከማውሳት የሚያዘናጋ እኩይ ነገር ስለሆነ ከሸይጧን ነው፦
5፥90 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሚያሰክር መጠጥ ቁማርም ጣዖታትም አዝላምም ከሰይጣን ሥራ የኾኑ እርኩስ ብቻ ናቸው፡፡ እርኩስን ራቁትም ልትድኑ ይከጀላልና*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّمَا الْخَمْرُ وَالْمَيْسِرُ وَالْأَنصَابُ وَالْأَزْلَامُ رِجْسٌ مِّنْ عَمَلِ الشَّيْطَانِ فَاجْتَنِبُوهُ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
5፥91 *ሰይጣን የሚፈልገው በሚያሰክር መጠጥና በቁማር በመካከላችሁ ጠብንና ጥላቻን ሊጥል፤ አላህን ከማውሳት እና ከስግደትም ሊያግዳችሁ ብቻ ነው፡፡ ታዲያ እናንተ ከእነዚህ ተከልካዮች ናችሁን ተከልከሉ*፡፡ إِنَّمَا يُرِيدُ الشَّيْطَانُ أَن يُوقِعَ بَيْنَكُمُ الْعَدَاوَةَ وَالْبَغْضَاءَ فِي الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ وَيَصُدَّكُمْ عَن ذِكْرِ اللَّهِ وَعَنِ الصَّلَاةِ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّنتَهُونَ

ነብያችንም”ﷺ” በሐዲስ ላይ አስካሪ መጠጥ መጠጣት ከልክለዋል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 36, ሐዲስ 81
ዐብደላህ ኢብኑ ቡረይዳህ አባቱ እንዳለው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ *በኮዳ በስተቀር ከነቢድ የሚዘጋጅ ነገር እንዳትጠጡ ከልክያችሁ ነበር፤ ግን አሁን በሁሉም ሰፍነግ መጠጣት ትችላላችሁ። ነገር ግን አስካሪ መጠጥ እንዳትጠጡ*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ بُرَيْدَةَ، عَنْ أَبِيهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ نَهَيْتُكُمْ عَنِ النَّبِيذِ إِلاَّ فِي سِقَاءٍ فَاشْرَبُوا فِي الأَسْقِيَةِ كُلِّهَا وَلاَ تَشْرَبُوا مُسْكِرًا ‏”‏

“ነቢድ” نَّبِيذ ማለት ከዘምባባ እና ከወይን ፍሬ የሚጠጣ ጭማቂ ነው፤ ይህ ሃላል ሲሆን ይህ ጭማቂ ከሁለት ቀናት አሊያም ከሦስት ቀናት በኃላ “ሙሥኪር” مُسْكِر ወይም “ሠከር” سَكَر ማለትም “አስካሪ”intoxicant” ይሆናል፤ ይህንን መጠጣት ሃራም ነው፤ አይደለም ኸምር ጠጪው ይቅርና ቀጂውን፣ ሻጩንም፣ ገዢውንም፣ ጨማቂውን፣ አስጨማቂውን፣ ተሸካሚውን እና የሚሸከሙለትንም ሁሉ ተጠያቂዎች ናቸው፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 27, ሐዲስ 6: 
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር”ረ.ዐ.” እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “አላህ ኸምርን ጠጪውን፣ ቀጂውን፣ ሻጩንም፣ ገዢውንም፣ ጨማቂውን፣ አስጨማቂውን፣ ተሸካሚውን እና የሚሸከሙለትንም ሁሉ ረግሟቸዋል” أَنَّهُمَا سَمِعَا ابْنَ عُمَرَ، يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ لَعَنَ اللَّهُ الْخَمْرَ وَشَارِبَهَا وَسَاقِيَهَا وَبَائِعَهَا وَمُبْتَاعَهَا وَعَاصِرَهَا وَمُعْتَصِرَهَا وَحَامِلَهَا وَالْمَحْمُولَةَ إِلَيْهِ ‏”‏

በዱኒያህ ያለው ኸምር አስካሪ እና ሃምራ ከሆነ ታዲያ በጀነት ያለው ኸምር ምንድን ነው? ኢንሻላህ ይህንን ነጥብ በክፍል ሁለት እንዳስሳለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኸምር

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

32፥17 ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ *”የተደበቀላቸውን ጸጋ ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም”*፡፡ فَلَا تَعْلَمُ نَفْسٌ مَّا أُخْفِيَ لَهُم مِّن قُرَّةِ أَعْيُنٍ جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

“ጀነት” جَنَّة የሚለው ቃል እራሱ “ጀነ” جَنَّ ማለትም “ተሰወረ” ወይም “ተደበቀ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ድብቅ” ወይም “ስውር” ማለት ነው፤ በጀነት ውስጥ ያለው ለሙስሊሞች የተደበቀላቸውን ፀጋ ደግሞ ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም፦
32፥17 *"ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን ጸጋ ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም”*፡፡ فَلَا تَعْلَمُ نَفْسٌ مَّا أُخْفِيَ لَهُم مِّن قُرَّةِ أَعْيُنٍ جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

አላህ በሐዲሰል ቁድሲይ ላይ የጀነት ፀጋ አይን አይቶት፣ ጆሮ፣ ሰምቶት፣ ልብ አስቦት የማያውቅ ለባሮቹ ያዘጋጃት እንደሆነች ነግሮናል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 123:
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ ነብዩ”ﷺ” እንዲህ ብለው አሉ፦ *"አላህም እንዲህ አለ፦ እኔ ለደጋግ ባሮቼ አይን አይቶት የማያውቅ፣ ጆሮ ሰምቶት የማያውቅና በሰው ልቦና ውል ብሎ የማያውቅ ጸጋን አዘጋጅቻለው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ قَالَ اللَّهُ أَعْدَدْتُ لِعِبَادِي الصَّالِحِينَ مَا لاَ عَيْنٌ رَأَتْ، وَلاَ أُذُنٌ سَمِعَتْ، وَلاَ خَطَرَ عَلَى قَلْبِ بَشَرٍ ‏”

ታላቁ ሰሓቢይ ዐብደሏህ ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ” እንዲህ ይላሉ፦ *"በጀነት ውስጥ ካሉ ነገሮች ዱንያ ውስጥ ምንም የለም ግን ከስሞች መመሳሰል በስተቀር”* (ተፍሲሩ አጥ-ጦበሪይ)

ስለዚህ በጀነት ውስጥ ያሉትን አላህ ለባሮቹ ያዘጋጃቸው ፀጋዎች አይን አይቶት፣ ጆሮ፣ ሰምቶት፣ ልብ አስቦት የማያውቅ ነገር ከሆነ ሙዝ፣ ዘንባባ፣ ወይን፣ ተምር የመሳሰሉት የስም መመሳሰል እንጂ ቅርጽና ይዘቱ፣ ጥፍጥናውና ጣእሙ ከዚህ ዓለም ጋር አንድ አይደለም፤ ይህን አምላካችን አላህ ሲናገር፦
47፥15 *የዚያች ጥንቁቆች ተስፋ የተሰጧት ገነት "ምሳሌ" በውስጧ ሺታው ከማይለወጥ ውሃ ወንዞች ጣዕሙ ከማይለውጥ ወተትም ወንዞች ለጠጪዎች ሁሉ ጣፋጭ ከኾነች የወይን ጠጅም ወንዞች፤ ከተነጠረ ማርም ወንዞች አሉባት፤ ለእነሱም በውስጧ ከፍሬዎች ሁሉ በያይነቱ ከጌታቸው ምሕረትም አላቸው*። مَّثَلُ الْجَنَّةِ الَّتِي وُعِدَ الْمُتَّقُونَ ۖ فِيهَا أَنْهَارٌ مِّن مَّاءٍ غَيْرِ آسِنٍ وَأَنْهَارٌ مِّن لَّبَنٍ لَّمْ يَتَغَيَّرْ طَعْمُهُ وَأَنْهَارٌ مِّنْ خَمْرٍ لَّذَّةٍ لِّلشَّارِبِينَ وَأَنْهَارٌ مِّنْ عَسَلٍ مُّصَفًّى ۖ وَلَهُمْ فِيهَا مِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ وَمَغْفِرَةٌ مِّن رَّبِّهِمْ ۖ كَمَنْ هُوَ خَالِدٌ فِي النَّارِ وَسُقُوا مَاءً حَمِيمًا فَقَطَّعَ أَمْعَاءَهُمْ
2፥25 *ከእርሷ ከፍሬ ዓይነት ሲሳይን በተመገቡ ቁጥር ፍሬዎችዋ ስለሚመሳሰሉ «ይህ ያ ከአሁን በፊት የተገመብነው ነው» ይላሉ፡፡ እርሱንም ተመሳሳይ ኾኖ ተሰጣቸው*፡፡ ۖ كُلَّمَا رُزِقُوا مِنْهَا مِن ثَمَرَةٍ رِّزْقًا ۙ قَالُوا هَـٰذَا الَّذِي رُزِقْنَا مِن قَبْلُ ۖ وَأُتُوا بِهِ مُتَشَابِهًا ۖ وَلَهُمْ فِيهَا أَزْوَاجٌ مُّطَهَّرَةٌ ۖ وَهُمْ فِيهَا خَالِدُونَ

"መሰል" مَثَل ማለት "ምሳሌ" ማለት ሲሆን እዚህ ላይ የተዘረዘሩት ውሃ፣ ወተት፣ የወይን ጠጅም፣ ማር፣ ፍሬዎች "ምሳሌ" ናቸው፤ ምክንያቱም የዚህ ዓለም ውሃ ሲቆይ ይሸታል፣ ወተት ሲቆይ ረግቶ ይቀየራል፣ ማርና ወይንም ጥፍጥናው ይሰለቻል፤ ነገር ግን የጀነት ውሃ፣ ወተት፣ የወይን ጠጅም፣ ማር፣ፍሬዎች ግን የተለየ ነው፤ የዚህ ዓለም ወይን ከቆየ ይቆመጥጥና ያሰክራል፤ እራስምታት ያመጣል፤ ከዚያም መጥፎ ንግግር ሰው እንዲናገር ያደርጋል፣ በመቀጠልም ወንጀልም ያሰራል። ነገር ግን የጀነት ወይን ጠጅ አያሰክርም፣ ራስምታት የለውም፣ ውድቅ ንግግር እና ወንጀልም አያሰራም፤ ምክንያቱም ምንም አልኮል የሌለበት "ንጹህ" የሆነ ነው፦
56፥19 *ከእርሷ የራስ ምታት አያገኛቸውም፤ አይሰክሩምም*። لَّا يُصَدَّعُونَ عَنْهَا وَلَا يُنزِفُونَ
37፥47 *በእርሷ ዉስጥም ራስ ምታት የለባትም። እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም*። لَا فِيهَا غَوْلٌ وَلَا هُمْ عَنْهَا يُنزَفُونَ
52፥23 *በውስጧ መጠጥን ይሰጣጣሉ፤ በውስጧ ውድቅ ንግግር እና ወንጀልም የለም*። يَتَنَازَعُونَ فِيهَا كَأْسًا لَّا لَغْوٌ فِيهَا وَلَا تَأْثِيمٌ
76፥21 *ጌታቸውም ንጹህ የሆኑን መጠጥ ያጠጣቸዋል*። رَبُّهُمْ شَرَابًا طَهُورًا

"ንጹህ" የሚለው ቃል "ጠሁር" طَهُور ሲሆን ይህም ከአልኮልነት ነጻ የሆነ የተጣራ ወይን ነው፦
83:25 *ተጣርቶ ከታተመ ጠጅ ይጥጠጣሉ*። يُسْقَوْنَ مِن رَّحِيقٍ مَّخْتُومٍ

ይህም ንጹህ ወይን መበረጃው "ካፉር" كَافُور "ዘንጀቢል" زَنجَبِيل "ተሥኒም" تَسْنِيم ነው፦
76፥5 በጎ አድራጊዎች፥ *መበረዣዋ ካፉርው ከሆነች ጠጅ ይጠጣሉ*። إِنَّ الْأَبْرَارَ يَشْرَبُونَ مِن كَأْسٍ كَانَ مِزَاجُهَا كَافُورًا
76፥17 በእርሷም *መበረዣዋ ዘንጀቢል የሆነችን ጠጅ ይጠጣሉ*። وَيُسْقَوْنَ فِيهَا كَأْسًا كَانَ مِزَاجُهَا زَنجَبِيلًا
83፥27 *መበረዣውም ከተሥኒም ነው*። وَمِزَاجُهُ مِن تَسْنِيمٍ

"እሺ የማያሳክር ወይን ከሆነ እንዴት ጀነት ውስጥ ወይን ይኖራል?" ብለው ሚሽነሪዎች ይሞግታሉ፤ ምነው በእናንተ መንግሥተ-ሰማይ ውስጥ የሚበላ ዛፍ እና የሚጠጣ ወይን የለም እንዴ? አንብቡት፦
ማቴዎስ 26፥29 *ነገር ግን እላችኋለሁ፥ በአባቴ መንግሥት ከእናንተ ጋር አዲሱን ወይን ፍሬ እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ ከዛሬ ጀምሬ ከዚህ ከወይን ፍሬ አልጠጣም*። But I say unto you, I will not drink henceforth of this fruit of the vine, until that day when I drink it new vine with you in my Father's kingdom.
ራእይ 2፥7 *ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ*።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የዓኢሻ”ረ.ዓ.” ቤት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

9፥33 የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋት ይፈልጋሉ፤ አላህም ከሓዲዎች ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን መሙላትን እንጅ ሌላን አይሻም፡፡

መግቢያ
መቼም ሚሽነሪዎች የኢስላም ብርሃን በምን እናጠልሸው ብለው ከተነሱ ጊዜያት አለፉ፤ የኢስላምን መሰረትና ውቅር፣ ዋልታና ማገር፣ ጥልቀትና ስፋት፣ ድርና ማግ በቅጡ ያልተረዱ ስለሆኑ መደበኛ በሆነ መርሃ-ግብርና መዋቅር ከመማር ይልቅ ጎግል ላይ በሰፈረው የተለቃቀመ ጥራዝ-ነጠቅ መረጃ ድምዳሜ ላይ ሲደርሱ ማየት እጅጉን ያማል፣ አንዱ ሚሽነሪ፦ ነብያችንን”ﷺ” የዓኢሻ”ረ.ዓ.” ልብስ ሲለብሱ እና ከእርሷ ጋር ተራክቦ ሲያደርጉ ብቻ ነው ወህይ የሚወርድላቸው ብሎ በትክክል እንኳን ማንበብ የማይችለውን ጩቤ ጥቅስ ጠቅሶ የጨባራ ለቅሶ እና ተስካር የሆነው ውሃ የማይቋጥ ሙግት ሲሟገተኝ ነበር፤ ይህ ስሁት የሆነ ሙግት ሳይርቅ በቅርቡ ሳይደርቅ በእጥቡ ሳይቃጠል በቅጠል እንደሚባለው ከመነሻው አከርካሪውን መመታት አለበት፤ እስቲ ሐዲሱን እንመልከት፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 51 , ሐዲስ 16:
ሂሻም ኢብኑ ኡርዋህ ከዓኢሻ”ረ.ዓ.” እንደተረከው….የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ለኡሙ ሰላማ”ረ.ዓ.” በአይሻ ጉዳይ አታስቸግሪኝ፤ ወላሂ ከማናቸውም ሴቶች ልብስ ውስጥ ወህይ አይመጣልኝም “ከአይሻ ልብስ በስተቀር አሏት”፤ فَقَالَ لَهَا ‏”‏ لاَ تُؤْذِينِي فِي عَائِشَةَ، فَإِنَّ الْوَحْىَ لَمْ يَأْتِنِي، وَأَنَا فِي ثَوْبِ امْرَأَةٍ إِلاَّ عَائِشَةَ ‏”‌‏ ።

ምን ያህል ቅጥፈት እንዳለ ተመልከቱ፤ እዚህ ሐዲስ ላይ የዓኢሻ”ረ.ዓ.” ልብስ ለበሱ የሚል የት አለ? ከዓኢሻ”ረ.ዓ.” ጋር ተራክቦ ሳደርግ የሚል የት አለ? ወህይ የሚመጣልኝ ከአይሻ ልብስ ውስጥ ብቻ ነው የሚል የት አለ? ይህ ሁሉ ገለባ ሂስ ነው፤ ነብያችን ወህይ የሚመጣላቸው በተለያየ ሁኔታ ቢሆንም ከሌሎች ባለቤቶታቸው ይልቅ የዓኢሻ”ረ.ዓ.” ቤት እያሉ ብቻ ነው ወህይ የሚመጣላቸው ማለት “ይልቅ” የሚለው ማነፃፀሪያ ከሴቶቹ ጋር እንጂ አጠቃላይ አይደለም፤ “ሠውብ” ثَوْب የሚለው ቃል በብዙ ይመጣል፦
“ሂጃብ” حِجَاب “መጋረጃ”፣
“ፊራሽ” فِرَٰش ምንጣፍ”፣
“ሊሃፍ” لِحَاف “ፍራሽ”
“በይት” بَيْت “ቤት”
“ሊባሥ” لِبَاس “ልብስ” በሚል ይመጣል፤ ይህንን በተለያዩ ነጥቦች ማየት ይቻላል፦

ነጥብ አንድ
“ሊሃፍ”
“ሊሃፍ” لِحَاف የሚለው ቃል “ፍራሽ” ማለት ሲሆን “ከአይሻ ልብስ በስተቀር” የሚለው “ከአይሻ ፍራሽ በስተቀር” በሚለው መጥቷል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 62 , ሐዲስ 122:
ኡሙ ሰላማ ሆይ በአይሻ ጉዳይ አታስቸግሪኝ፤ ወላሂ ከማናቸውም ሴቶች ፍራሽ ውስጥ ወህይ አይመጣልኝም “ከአይሻ ፍራሽ በስተቀር” “‏ يَا أُمَّ سَلَمَةَ لاَ تُؤْذِينِي فِي عَائِشَةَ، فَإِنَّهُ وَاللَّهِ مَا نَزَلَ عَلَىَّ الْوَحْىُ وَأَنَا فِي لِحَافِ امْرَأَةٍ مِنْكُنَّ غَيْرِهَا ‏”‌‏.‏ ፤

ነጥብ ሁለት
“በይት”
“በይት” بَيْت ማለት “ቤት” ሲሆን “ከአይሻ ልብስ በስተቀር” የሚለው “ከአይሻ ቤት” በሚለው መጥቷል፤ ቤት የሚከፋፈለው በመጋረኛ ስለሆነ “ሠውብ” የሚለው በሌላ ሪዋያ ላይ “በይት” بَيْت “ቤት” በሚል መጥቷል፦
ኢማሙ አህመድ መጽሐፍ 6 ሐዲስ 293
የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ ኡሙ ሰላማ ሆይ በአይሻ ጉዳይ አታስቸግሪኝ፤ ወላሂ ከማናቸውም ሴቶች ቤት ውስጥ ወህይ አይመጣልኝም ከአይሻ ቤት በስተቀር፤ رسول الله صلى الله عليه و سلم ثم قال يا أم سلمة لا تؤذيني في عائشة فإنه والله ما نزل على الوحي وأنا في بيت امرأة من نسائي غير عائشة ።

ነጥብ ሶስት
“ሊባሥ”
“ሊባሥ” لِبَاس ማለት ትርጉሙ “ልብስ” ማለት ሲሆን “ሠውብ” ማለት “ሊባሥ” ነው ብንል እንኳን “ልብስ” የሚለው ቃል ሁልጊዜ ሱሪን፣ ቀሚስን፣ ጃኬትን ብቻ ሳይሆን የሚያመለክተው መጠለያን፣ መከለያ፣ መሸሸጊያ ለማመልከት ይመጣል፤ አምላካችም አላህ ለምሳሌ ሴት የወንድ ልብስ ናት ወንድ የሴት ልብስ ነው ይለናል፦
2፥187 በጾም ሌሊት ወደ ሴቶቻችሁ መድረስ ለእናንተ ተፈቀደላችሁ፡፡ እነርሱ ለእናንተ “ልብሶች” ናቸው፤ እናንተም ለእነርሱ “ልብሶች” ናችሁ أُحِلَّ لَكُمْ لَيْلَةَ ٱلصِّيَامِ ٱلرَّفَثُ إِلَىٰ نِسَآئِكُمْ ۚ هُنَّ لِبَاسٌۭ لَّكُمْ وَأَنتُمْ لِبَاسٌۭ لَّهُن ፡፡

መቼም ልብስ የሚለውን አንዱ የአንዱ መሸሸጊያ ማለት እንጂ አንዱ የአንዱ ጃኬት ወይም ቀሚስ አሊያም ሱሪ ማለት ነው የሚል ቂል የለም፤ አላህ ሌሊትን ልብስ አደረገ፤ ያ ማለት “መጠለያ” ማለት ነው፦
25:47 እርሱም ያ ለእናንተ “ሌሊትን” ልብስ፣ እንቅልፍንም ማረፊያ ያደረገ፤ ቀንንም መበተኛ ያደረገላችሁ ነው وَهُوَ ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيْلَ لِبَاسًۭا وَٱلنَّوْمَ سُبَاتًۭا وَجَعَلَ ٱلنَّهَارَ نُشُورًۭا ።
78:10 ሌሊቱንም ልብስ አደረግን وَجَعَلْنَا ٱلَّيْلَ لِبَاسًۭا ።

ይህንን ካየን ነብያችን”ﷺ”፦ “ከማናቸውም ሴቶች ልብስ ውስጥ ወህይ አይመጣልኝም ከዓኢሻ”ረ.ዓ.” ልብስ በስተቀር” ሲሉ ከዓኢሻ”ረ.ዓ.” ፍራሽ ወይም ቤት ማለታቸው እንደሆነ እሙንና ቅቡል ነው እንጂ ቃላትን ማንሸዋረር እና ማውረግረግ አይቻልም። እንዴት የአንድ ሴት ልብስ ውስጥ አንድ ወንድ ቃል በቃል ሊገባስ ይችላል? ይህ ሆን ተብሎ ድርቅና አላህ በትንሣኤ ቀን በዚያ በእርሱ ትወዛገቡበት በነበራችሁት ሁሉ በመካከላችሁ ይፈርዳል፦
18፥68-69 ቢከራከሩህም «አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡ አላህ በትንሣኤ ቀን በዚያ በእርሱ ትወዛገቡበት በነበራችሁት ሁሉ በመካከላችሁ ይፈርዳል፡፡

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ቁርአንን አያስተነትኑምን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 ቁርኣንን አያስተነትኑምን? ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ *ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ ٱلْقُرْءَانَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ ٱللَّهِ لَوَجَدُوا۟ فِيهِ ٱخْتِلَٰفًۭا كَثِيرًۭا

ቁርአን ከወረደበት ምክንያት አንዱ የአዕምሮ ባለቤቶች አንቀፁን እንዲያስተነትኑ ነው፦
38:29 ይህ ወደ አንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፤ አንቀጾቹን *እንዲያስተነትኑ* እና *የአዕምሮ ባለቤቶችም* *እንዲገሰጹ* አወረድነው كِتَٰبٌ أَنزَلْنَٰهُ إِلَيْكَ مُبَٰرَكٌۭ لِّيَدَّبَّرُوٓا۟ ءَايَٰتِهِۦ وَلِيَتَذَكَّرَ أُو۟لُوا۟ ٱلْأَلْبَٰبِ ፡፡

ቁርአን የዓለማቱ ጌታ የአላህ ንግግር ነው፤ አላህ እውነተኛ አምላክ ስለሆነ የሚናገረው ንግግር እርስ በእርሱ አይጋጭም፣ አይቃረንም፣ አይፈለስም፣ አይጣረስም፤ አይ እርስ በእርስ ይጋጫል የሚል ሃያሲ ካለ ግን አንተንትኖ ማምጣት አለበት የሚል ተግዳት”Falsification test” ያቀርባል፦
4፥82 ቁርኣንን አያስተነትኑምን? ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ *ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ ٱلْقُرْءَانَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ ٱللَّهِ لَوَجَدُوا۟ فِيهِ ٱخْتِلَٰفًۭا كَثِيرًۭا

እኛ ሙስሊሞሽ ለሚሽነሪዎች ልዩነት የሚመስሏቸው ጉዳዮች ቁርአን የወረደበትን ቋንቋ፣ሰዋስው እና አውድ ካለመረዳት የሚመጣ ጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት ነው የሚል ሙግት አለን፤ ጭራሽ በሂስ የሚቀርቡት አንቀፆች በአፅንኦትና በአንክሮት ከተጠና የቁርአን ታምር ነው፤ ይህንን ነጥብ በጥራዝ ጠለቅ ዕውቀት እናስተንትን፦
39፥71 እነዚያ የካዱትም የተከፋፈሉ ጭፍሮች ኾነው ወደ ገሀነም ይነዳሉ፡፡ በመጧትም ጊዜ *ደጃፎችዋ ይከፈታሉ*፡፡ وَسِيقَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِلَىٰ جَهَنَّمَ زُمَرًا ۖ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُوهَا فُتِحَتْ أَبْوَٰبُهَا

የጀሃነም ደጆች “ይከፈታሉ” የሚለው ቃል ላይ “ፉቲሐት” فُتِحَتْ ሲሆን መነሻው ላይ “ወ” و የሚል ቃል የለውም፤ ግን የጀነት ደጆች “የተከፈቱ” የሚለው ቃል ግን “ወፉቲሐት” وَفُتِحَتْ ሲሆን “ፉቲሐት” በሚለው ቃል ላይ “ወ” የሚል መነሻ ቅጥያ አለ፦
39፥73 እነዚያም ጌታቸውን የፈሩት የተከፋፈሉ ጭፍሮች ኾነው ወደ ገነት ይንነዳሉ፡፡ በመጧትም ጊዜ *ደጃፎችዋ “የተከፈቱ”* ሲኾኑ፤ وَسِيقَ ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوْا۟ رَبَّهُمْ إِلَى ٱلْجَنَّةِ زُمَرًا ۖ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُوهَا وَفُتِحَتْ أَبْوَٰبُهَا

እስቲ ይህ “ዋው” و የሚለው ቃል”ፉቲሐት” በሚለው ቃል ላይ የሌለበትን ምክንያት እናስተንትን፤ ገሃነም ሰባት ደጆች አሏት፦
15፥43-44 «ገሀነምም ለእርሱና ለተከተሉት ለመላውም በእርግጥ ቀጠሯቸው ናት፡፡ وَإِنَّ جَهَنَّمَ لَمَوْعِدُهُمْ أَجْمَعِينَ «ለእርሷ *ሰባት ደጃፎች* አሏት፡፡ ለየደጀፉም ሁሉ ከእነሱ የተከፈለ ፋንታ አለ፡፡ لَهَا سَبْعَةُ أَبْوَٰبٍۢ لِّكُلِّ بَابٍۢ مِّنْهُمْ جُزْءٌۭ مَّقْسُومٌ
39፥71 እነዚያ የካዱትም የተከፋፈሉ ጭፍሮች ኾነው ወደ ገሀነም ይንነዳሉ፡፡ በመጧትም ጊዜ *ደጃፎችዋ* ይከፈታሉ፡፡ وَسِيقَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِلَىٰ جَهَنَّمَ زُمَرًا ۖ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُوهَا فُتِحَتْ أَبْوَٰبُهَا

ቀጥሎ “ዋው” و የሚለው ቃል”ፉቲሐት” በሚለው ቃል ላይእናስተንትን ያለበትን ምክንያት ፤ ጀነት ስምንት ደጆች አሏት፦
7፥40 እነዚያ አንቀጾቻችንን ያስተባበሉ ከእርሷም የኮሩ ለእነርሱ *የሰማይ ደጃፎች አይከፈቱላቸውም*፡፡ ግመል በመርፌ ቀዳዳ እስከሚገባም ድረስ *ገነትን አይገቡም*፡፡ እንደዚሁም አጋሪዎችን እንቀጣለን፡፡ إِنَّ ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا وَٱسْتَكْبَرُوا۟ عَنْهَا لَا تُفَتَّحُ لَهُمْ أَبْوَٰبُ ٱلسَّمَآءِ وَلَا يَدْخُلُونَ ٱلْجَنَّةَ حَتَّىٰ يَلِجَ ٱلْجَمَلُ فِى سَمِّ ٱلْخِيَاطِ ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلْمُجْرِمِينَ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 59 , ሐዲስ 67:
ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ጀነት ስምንት ደጃፎች አሏል*፤ ከእነርሱ አንዷ ስሟ አር-ረይያን ፆመኛ እንጂ ሌላ አይገባባትም። عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ فِي الْجَنَّةِ ثَمَانِيَةُ أَبْوَابٍ، فِيهَا باب يُسَمَّى الرَّيَّانَ لاَ يَدْخُلُهُ إِلاَّ الصَّائِمُونَ ‏”‌‏
ነጥቡ ያለው እዚህ ጋር ነው፤ ቁርአን ላይ ሰባት ቁጥር ተነግሮ ስምንት ቁጥር ከመጣ ሰባት ላይ ዋው የለውም ግን ስምንት ላይ ዋው አለ፤ ምሳሌ አንድ፦
18፥22 በሩቅ ወርዋሪዎች ሆነው በጥርጣሬ «ሦስት ናቸው፤ አራተኛቸው ውሻቸው ነው» ይላሉ፡፡ «አምስት ናቸው፤ ስድስተኛቸው ውሻቸው ነውም» ይላሉ፡፡ «ሰባት ናቸው፤ *ስምንተኛቸውም* ውሻቸው ነው» ይላሉም፡፡ سَيَقُولُونَ ثَلَٰثَةٌۭ رَّابِعُهُمْ كَلْبُهُمْ وَيَقُولُونَ خَمْسَةٌۭ سَادِسُهُمْ كَلْبُهُمْ رَجْمًۢا بِٱلْغَيْبِ ۖ وَيَقُولُونَ سَبْعَةٌۭ وَثَامِنُهُمْ كَلْبُهُمْ ۚ

“ወ” የሚል ቃል “ሳሚን” ثَامِن ማለትም “ስምንተኛ” በሚል ቃል ላይ መጥቷል፤ “*ወ*ሳሚኑሁም” وَثَامِنُهُمْ ። ነገር ግን “ሠብዐቱን” سَبْعَةٌ ማለትም “ሰባተኛ” በሚለው ቃል ላይ ግን አልመጣም፤ ምሳሌ ሁለት፦
69፥7 ተከታታይ በኾኑ ሰባት ሌሊቶች *እና ስምንት* መዓልቶች ውስጥ በእነርሱ ላይ ለቀቃት፡፡ سَخَّرَهَا عَلَيْهِمْ سَبْعَ لَيَالٍۢ وَثَمَٰنِيَةَ أَيَّامٍ حُسُومًۭا فَتَرَى ٱلْقَوْمَ فِيهَا صَرْعَىٰ كَأَنَّهُمْ أَعْجَازُ نَخْلٍ خَاوِيَةٍۢ

“ወ” የሚል “ሰማኒን” ثَمَٰنِين ማለትም “ስምንት” በሚል ቃል ላይ መጥቷል፤ “ወሰማኒየታህ” وَثَمَانِيَةَ ። ነገር ግን “ሠብዐ” سَبْعَ ማለትም “ሰባት” በሚለው ቃል ላይ ግን አልመጣም። “ዋው” እዚህ ጋር አርፉል አጥፍ ሳይሆን ዋው ሙተና ነው፤ ዋው ሁልጊዜ መነሻ ቅጥያ ላይ ሆኖ ሲመጣ አያያዥ መስተጻምር ነው ተብሎ አይደመደምም፤ ለምሳሌ “ወላሂ” وَٱللّٰهِ እንላለን፤ እዚህ ጋር “ወ” و የሚለው “ቢ” بِا በሚል ሲመጣ “ቢላህ” بِالله “በአላህ” እንደማለት ነው። አንድ ቃል ሁልጊዜ አንድ ትርጉም ይኖረዋል ማለት አይደለም፤ ለምሳሌ “ለው” َلَوْ ማለት “ቢሆን”if” ሲሆን “ኢን” إِن በሚል ይመጣል። ለናሙና ያክል ሌላ ሰዋስው ከቁርኣን ብንመለከት ለምሳሌ “ላ” َلَا የሚለው ቃል ብዙ ትርጉም ይኖረዋል፦
1ኛ. “ላ” የሚለው ቃል ለቀድ” َلَقَدْ ማለትም “እርግጥ” የሚል ሆና ትመጣለች፤ ለምሳሌ፦
70፥40 በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡ فَلَآ أُقْسِمُ بِرَبِّ ٱلْمَشَٰرِقِ وَٱلْمَغَٰرِبِ إِنَّا لَقَٰدِرُونَ

2ኛ. “ላ” የሚለው ቃል “ማ” مَا ማለትም “አፍራሽ ቃል” ሆና ትመጣለች፤ ለምሳሌ፦
4፥71 «ሦስት ናቸው» አትበሉም፡፡ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ

ስለዚህ ዋው መጀመሪያ ስለ ጀሃነም በተጠቀሰው አንቀፅ ላይ አለመኖሩ እና ሁለተኛው ስለ ጀነት በተጠቀሰው አንቀፅ ላይ መኖሩ ያለው ጥበብ በአጋጣቢ የሆነ ሳይሆን አላህ የጀሃነም ደጆች ያላቸው ውርደት የሚያመለክ ሲሆን የጀነት ደጆች ደግሞ ያላቸውን ክብር ያሳያል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
በሕይወትም እስካለሁ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥31 *በየትም ስፍራ ብሆን ብሩክ አድርጎኛል፡፡ በሕይወትም እስካለሁ ሶላትን በመስገድ ዘካንም በመስጠት አዞኛል*፡፡ وَجَعَلَنِي مُبَارَكًا أَيْنَ مَا كُنتُ وَأَوْصَانِي بِالصَّلَاةِ وَالزَّكَاةِ مَا دُمْتُ حَيًّا

ዒሳ ኢብኑ መርየም፦ "በሕይወትም እስካለሁ ሶላትን በመስገድ ዘካንም በመስጠት አዞኛል" ማለቱ "አሁን ዘካን ሰለማይሰጥ በሕይወት የለም ሞቷል ወይም በሰማይ በሕይወት ካለ እዛ ዘካ እየሰጠ ነው ወይ?" ብለው ስሁታን ተሟጓቾች ብዙ ጊዜ አድሮ ቃሪያና ከርሞ ጥጃ በመሆን ይጠቅሳሉ፤ ይህንን የሚጠይቁት አለስልሶና አቅለስልሶ ለመንቀፍ እንጂ ለመረዳት አይደለም፤ ይህ ደግሞ እያነቡ እስክስታ ነው፤ እዚህ አንቀጽ ላይ ሰው ብርቱ ብረት ከንቱ! የሚያስብል ስሙር ሙግት እንሞግት እስቲ፦
19፥31 *በየትም ስፍራ ብሆን ብሩክ አድርጎኛል፡፡ በሕይወትም እስካለሁ ሶላትን በመስገድ ዘካንም በመስጠት አዞኛል*፡፡ وَجَعَلَنِي مُبَارَكًا أَيْنَ مَا كُنتُ وَأَوْصَانِي بِالصَّلَاةِ وَالزَّكَاةِ مَا دُمْتُ حَيًّا

"በየትም ስፍራ" ማለት በምድርም በሰማይም አላህ ዒሳን ብሩክ አድርጎታል፤ ቀጥሎ "እስካለው" የሚል ሃይለ-ቃል "ዱምቱ" دُمْتُ ሲሆን ይህም ቃል "በእስራኢል ልጆች መካከል እስካለ ድረስ" መሆኑን ለማመልከት በሌላ አንቀጽ ተጠቅሷል፦
5፥117 «በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ *"በውስጣቸውም እስካለሁ ድረስ" በእነርሱ ላይ ”ምስክር” ነበርኩ*፡፡ *”በወሰድከኝም” ጊዜ አንተ በእነርሱ ላይ *”ተጠባባቂ”* ነበርክ*፡፡ አንተም በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ ነህ፡፡» مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ ۚ وَكُنتُ عَلَيْهِمْ شَهِيدًۭا مَّا دُمْتُ فِيهِمْ ۖ فَلَمَّا تَوَفَّيْتَنِى كُنتَ أَنتَ ٱلرَّقِيبَ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنتَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍۢ شَهِيدٌ

"ዱምቱ" دُمْتُ ማለትም "እስካለው" ድረስ የሚለው ሃይለ-ቃል በምድር ላይ ያለውን ቆይታ ያመለክታል፤ ምክንያቱም ቀጥሎ ያለው "በወሰድከኝ ጊዜ" የሚለው ሃይለ-ቃል ወደ ሰማይ መወሰዱን ስለሚያመለክት "እስካለው" የሚለው ሃይለ-ቃል በምድር ላይ በሕይወት እያለ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፤ ስለዚህ በሕይወት በምድር ላይ እያለ ሶላትን በመስገድ ዘካንም በመስጠት አሳልፏል፤ አላህ ወደ ሰማይ በወሰደው ጊዜ ግን የዘካ አገልግሎት ይቆማል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኢኽላስ እና ሪያዕ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

76፥9 *«የምናበላችሁ ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው፡፡ ከእናንተ ዋጋንም ማመስገንንም አንፈልግም*፡፡ إِنَّمَا نُطْعِمُكُمْ لِوَجْهِ اللَّهِ لَا نُرِيدُ مِنكُمْ جَزَاءً وَلَا شُكُورًا

ነጥብ አንድ
"ኢኽላስ"
“ዒባዳህ” عِبَادَة ማለትም “አምልኮ” አላህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኝባቸው ሥስት ሸርጦች አሉ፤ እነርሱም፦ አንደኛ “ኢማን” إِيمَٰن ሁለተኛ “ኢኽላስ” إخلاص ሦስተኛ “ኢቲባዕ” إتباع ናቸው። “ኢኽላስ” إخلاص ማለት ከእዩልይና ስሙልኝ እና ከሙገሳና ወቀሳ ነጻ ሆኖ ለአላህ ውዴታ ተብሎ የሚነየት መተናነስ፣ ማጎብደድ፣ ማሸርገድ እና ማጥራት ነው፣ እነዚያም የጌታቸውን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ አምልኳቸውን የፈጸሙ ለእነርሱ መጨረሻይቱ ምስጉን አገር አለቻቸው፦
13፥22 እነዚያም *የጌታቸውን ውዴታ ለመፈለግ የታገሱ፣ ሶላትንም አዘውትረው የሰገዱ፣ እኛ ከሰጠናቸው ሲሳይም በምስጢርም ኾነ በግልጽ የመጸወቱ፣ ክፉውንም ነገር በበጎ የሚገፈትሩ ናቸው*፡፡ እነዚያ ለእነርሱ መጨረሻይቱ ምስጉን አገር አለቻቸው*፡፡ وَالَّذِينَ صَبَرُوا ابْتِغَاءَ وَجْهِ رَبِّهِمْ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَأَنفَقُوا مِمَّا رَزَقْنَاهُمْ سِرًّا وَعَلَانِيَةً وَيَدْرَءُونَ بِالْحَسَنَةِ السَّيِّئَةَ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ عُقْبَى الدَّارِ

ፊትን የሚያጨፈግግን ብርቱ ቀን ከአላህ የሚፈራ ሙስሊም ከሰው ዋጋ እና ምስጋና ፈልጎ ሳይሆን የሚያደርገውን ሁሉ ለአላህ ውዴታ ብሎ ያደርጋል፦
76፥9 *«የምናበላችሁ ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው፡፡ ከእናንተ ዋጋንም ማመስገንንም አንፈልግም*፡፡ إِنَّمَا نُطْعِمُكُمْ لِوَجْهِ اللَّهِ لَا نُرِيدُ مِنكُمْ جَزَاءً وَلَا شُكُورًا
76፥10 *«እኛ ፊትን የሚያጨፈግግን ብርቱ ቀን ከጌታችን እንፈራለንና» ይላሉ*፡፡ إِنَّا نَخَافُ مِن رَّبِّنَا يَوْمًا عَبُوسًا قَمْطَرِيرًا

ኢኽላስ ያለው ሙስሊም ምሳሌ በተስተካከለች ከፍተኛ ስፍራ ላይ እንዳለች አትክልት፣ ብዙ ዝናብ እንደነካት ፍሬዋንም እጥፍ ኾኖ እንደሰጠች፣ ዝናብም ባይነካት ካፊያ እንደሚበቃት ብጤ ነው፦
2፥265 *የእነዚያም የአላህን ውዴታ ለመፈለግና ለነፍሶቻቸው እምነትን ለማረጋገጥ ገንዘቦቻቸውን የሚለግሱ ሰዎች ምሳሌ በተስተካከለች ከፍተኛ ስፍራ ላይ እንዳለች አትክልት፣ ብዙ ዝናብ እንደነካት ፍሬዋንም እጥፍ ኾኖ እንደሰጠች፣ ዝናብም ባይነካት ካፊያ እንደሚበቃት ብጤ ነው*፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡ وَمَثَلُ الَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُمُ ابْتِغَاءَ مَرْضَاتِ اللَّهِ وَتَثْبِيتًا مِّنْ أَنفُسِهِمْ كَمَثَلِ جَنَّةٍ بِرَبْوَةٍ أَصَابَهَا وَابِلٌ فَآتَتْ أُكُلَهَا ضِعْفَيْنِ فَإِن لَّمْ يُصِبْهَا وَابِلٌ فَطَلٌّ ۗ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

በዓለም ላይ ትልቁ ቁጥር መቼም ሴንቲሊዮን ነው፤ እርሱም ባለ ስድስት መቶ ዜሮ የያዘ ነው፤ ይህንን ትልቅ ቁጥር ግን ከፊት ለፊቱ አንድ ቁጥር ብትነሳ እነዚያ ሁሉ ዜሮ ሆነው ይቀራሉ እንጂ ዋጋ የላቸው። እንደዚሁ ልግስና፣ ዕውቀት፣ ሰማዕትነት፣ ጥበብ፣ ማስተዋል፣ ሃብት፣ ውበት ወዘተ... ቢደረደሩም ከፊታቸው እንደ አንድ ቁጥር "ኢኽላስ" ከሌለ እንዚህ ሁሉ ዜሮ ናቸው። ኢኽላስ ያለው ሙስሊም "ሙኽሊስ" مُخْلِص ማለትም "አጥሪ" "ምርጥ" ይባላል፦
40፥14 *አላህንም ከሓዲዎች ቢጠሉም ሃይማኖትን ለእርሱ "አጥሪዎች" ኾናችሁ ተገዙት*፡፡ فَادْعُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُون
37፥40 *ግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ቅጣትን አይቀምሱም*፡፡ إِلَّا عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ
38፥82 እርሱም አለ፦ *"በአሸናፊነትህ ይኹንብኝ፤ በመላ አሳስታቸዋለሁ"*፡፡ قَالَ فَبِعِزَّتِكَ لَأُغْوِيَنَّهُمْ أَجْمَعِينَ
38፤83 *"ከእነርሱ ምርጥ የኾኑት ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ"*፡፡ إِلَّا عِبَادَكَ مِنْهُمُ الْمُخْلَصِينَ

"ሙኽሊሲን" مُخْلِصِين የሙኽሊስ ብዙ ቁጥር ነው፤ ሸይጧን ቃል የገባው ከአላህ ባሮች ሙኽሊሲን የሚባሉትን ላለማሳሳት ነው፤ ሙኽለሲን በአላህ መንገድ የሚለግሱ፣ መመጻደቅንና ማስከፋትን የማያስከትሉ ሲሆኑ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፤ በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነርሱም አያዝኑም፦
2፥262 *እነዚያ ገንዘቦቻቸውን “በአላህ መንገድ የሚለግ ከዚያም የሰጡትን ነገር “መመጻደቅንና ማስከፋትን የማያስከትሉ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነርሱም አያዝኑም*፡፡ الَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ثُمَّ لَا يُتْبِعُونَ مَا أَنفَقُوا مَنًّا وَلَا أَذًى ۙ لَّهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُون

ኢንሻላህ በክፍል ሁለት ስለ ሪያዕ እንቀጥላለን.....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አትሁን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

28፥86 *መጽሐፉ ወደ አንተ መወረዱን ተስፋ የምታደርግ አልነበርክም፡፡ ግን ከጌታህ ችሮታ ተወረደልህ፡፡ ለከሓዲዎችም በፍጹም ረዳት አትኹን*፡፡ وَمَا كُنتَ تَرْجُو أَن يُلْقَىٰ إِلَيْكَ الْكِتَابُ إِلَّا رَحْمَةً مِّن رَّبِّكَ ۖ فَلَا تَكُونَنَّ ظَهِيرًا لِّلْكَافِرِينَ

አምላካችን አላህ ስለ ነብያችን"ﷺ" አለመጠራጠር እና ማመን ሲናገር፦
2፥285 *መልክተኛው ከጌታው ወደ እርሱ በተወረደው አመነ*፡፡ آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِ

ይህ አንቀጽ በቂ ነው፤ ሌላ ጥቅስ ላይ አምላካችን አላህ ለነብያችን"ﷺ"፦ "ወደ አንተም ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትሆን" ይላል፤ "ብትሆን" ማለት እና "ነህ" ማለት በይዘም ሆነ በአይነት፤ በመንስኤም ሆነ በውጤት ሁለት ቃላት እና ትርጉም ናቸው፦
10፥94 *ወደ አንተም ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትሆን እነዚያን ከአንተ በፊት መጽሐፉን የሚያነቡትን ጠይቅ*፡፡ እውነቱ ከጌታህ ዘንድ በእርግጥ መጥቶልሃል፡፡ *ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን*፡፡ فَإِن كُنتَ فِي شَكٍّ مِّمَّا أَنزَلْنَا إِلَيْكَ فَاسْأَلِ الَّذِينَ يَقْرَءُونَ الْكِتَابَ مِن قَبْلِكَ ۚ لَقَدْ جَاءَكَ الْحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْمُمْتَرِين

"ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን" ማለት "ከተጠራጣሪዎቹም ነህ" ማለት አይደለም። ይህንን ሃይለ-ቃል ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት የሚቀጥለውን አንቀጽ እንመልከት፦
10፥95 ከእነዚያም የአላህን አንቀጾች *ከአስተባበሉት አትሁን*፡፡ ከከሳሪዎቹ ትሆናለህና፡፡ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِ اللَّهِ فَتَكُونَ مِنَ الْخَاسِرِينَ

"ከአስተባበሉት አትሁን" ማለት አስተባብለካል ማለት ሳይሆን ምክርና ማስጠንቀቂያ ነው፤ አውዱ ይቀጥልና "ከአጋሪዎቹም አትሁን" ይላል፤ ያ ማለት አጋርተሃል ማለት አይደለም፦
10፥105 ፊትህንም ወደ ቀጥታ ያዘነበልክ ስትሆን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ *ከአጋሪዎቹም አትሁን*፡፡ وَأَنْ أَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

በለይለቱል ኢስራእ ወል ሚራጅ ነብያችን"ﷺ" ሙሳን ከማግኘታቸው በፊት እንደሚያገኙት አምላካችን አላህ ሲናገር፦ "እርሱን ከመገናኘትህም በመጠራጠር ውስጥ አትሁን" ብሏል፦
32፥23 ሙሳንም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ *እርሱን ከመገናኘትህም በመጠራጠር ውስጥ አትሁን*፡፡ ለእስራኤል ልጆችም መሪ አደረግነው፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ فَلَا تَكُن فِي مِرْيَةٍ مِّن لِّقَائِهِ ۖ وَجَعَلْنَاهُ هُدًى لِّبَنِي إِسْرَائِيلَ

ሙሳን እንደሚያገኙት አውቀው ተጠራጥረው ሳይሆን አትሁን ምክር እና ማስጠንቀቂያ እንጂ እርሱን ከመገናኘት በመጠራጠር ውስጥ ነበሩ የሚለውን እንደማይይዝ ሁሉ በተመሳሳይም "ከአስተባበሉት አትሁን" "ከአጋሪዎቹም አትሁን" "ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን" ማለት ምክርና ማስጠንቀቂያ እንጂ "አስተባባይ" "አጋሪ" "ተጠራጣሪ" ነበርክ የሚል ፍቺ አይኖረውም። መዲና ላይ የነበሩት አይሁዳውያን ከመካዳቸው በፊት አላህ፦ "የመጀመሪያ ከሓዲ አትሁኑ" ብሏቸዋል፦
2፥41 ከእናንተ ጋር ያለውን የሚያረጋግጥ ሆኖ ባወረድኩትም እመኑ፡፡ *በእርሱም የመጀመሪያ ከሓዲ አትሁኑ*፡፡ وَآمِنُوا بِمَا أَنزَلْتُ مُصَدِّقًا لِّمَا مَعَكُمْ وَلَا تَكُونُوا أَوَّلَ كَافِرٍ بِهِ

"የመጀመሪያ ከሓዲ አትሁኑ" ማለት ክደው ነበር ማለት ሳይሆን እንዳይክዱ ምክርና ማስጠንቀቂያ እንደሆነ ሁሉ ከላይ ያለው ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን የሚለው ሃይለ-ቃል ይህንን ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው። "ለከሓዲዎችም በፍጹም ረዳት አትኹን" ማለት እረዳት ሆነው ነበር ማለትን ያስይዛልን? በፍጹም። ነብያችን"ﷺ" መጽሐፉ ወደ እርሳቸው መወረዱን ተስፋ የሚያደርጉ አልነበሩም፤ መጽሐፉም ምን እንደኾነ የሚያውቁ አልነበሩም፤ ግን ከጌታህ ችሮታ ተወረደላቸው፤ እሳቸው ወደ ቀጥተኛው መንገድ የሚመሩ ሆነው ሕይወታቸውን አሳልፈዋል እንጂ አንድም ቀን በቁርኣን አስተባብለው፣ በመልእክቱ ተጠራጥረው እና በአላህ ላይ አጋርተው አያውቁም፦
28፥86 *መጽሐፉ ወደ አንተ መወረዱን ተስፋ የምታደርግ አልነበርክም፡፡ ግን ከጌታህ ችሮታ ተወረደልህ፡፡ ለከሓዲዎችም በፍጹም ረዳት አትኹን*፡፡ وَمَا كُنتَ تَرْجُو أَن يُلْقَىٰ إِلَيْكَ الْكِتَابُ إِلَّا رَحْمَةً مِّن رَّبِّكَ ۖ فَلَا تَكُونَنَّ ظَهِيرًا لِّلْكَافِرِينَ
42፥52 እንደዚሁም ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲኾን መንፈስን አወረድን፡፡ *መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም*፡፡ ግን መንፈሱን ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው፡፡ *አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ*፡፡ وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ رُوحًا مِّنْ أَمْرِنَا ۚ مَا كُنتَ تَدْرِي مَا الْكِتَابُ وَلَا الْإِيمَانُ وَلَـٰكِن جَعَلْنَاهُ نُورًا نَّهْدِي بِهِ مَن نَّشَاءُ مِنْ عِبَادِنَا ۚ وَإِنَّكَ لَتَهْدِي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ

ተጠራጥረው ቢሆን ኖሮ "ነህ" የሚል ቃል ይጠቀም ነበር፤ ነገር ግን "ነህ" የሚለውን የሚጠቀመው ለአሉታዊ ብቻ ነው፤ "አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ" "በቀጥታም መንገድ ላይ ነህ" "ከመልክተኞቹ ነህ" የሚል ነው፤ ለናሙና ያክል ይህ በቂ ነው፦
68፥4 *አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ*፡፡ وَإِنَّكَ لَعَلَىٰ خُلُقٍ عَظِيمٍ
36፥4 በቀጥታም መንገድ ላይ ነህ፡፡ عَلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ
2፥252 *እነዚህ አንቀጾች በእውነት በአንተ ላይ የምናነባቸው ሲኾኑ የአላህ አንቀጾች ናቸው፤ አንተም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነህ*፡፡ تِلْكَ آيَاتُ اللَّهِ نَتْلُوهَا عَلَيْكَ بِالْحَقِّ ۚ وَإِنَّكَ لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ
36፥3 *አንተ በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነህ*፡፡ إِنَّكَ لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አማላጅ ማን ነው?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

34፥23 *ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም*፡፡ وَلَا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ عِندَهُ إِلَّا لِمَنْ أَذِنَ لَهُ

“ሸፋዐህ” شَفَٰعَهማለት “ምልጃ” ማለት ሲሆን ምልጃ ሥስት ማንነቶችን ያቅፋል፤ እነርሱም፦ አንደኛው የሚማለደው ተማላጅ፣ ሁለተኛው የሚማለድለት ተመላጅ እና ሥስተኛው የሚማልደው አማላጅ ናቸው፤ አላህ የሁሉም ነገር ፈጣሪና አስተናባሪ በመሆኑ የሚማለድ ተማላጅ ነው፤ ከፍጡሮቹ መካከል ደግሞ እርሱ የፈቀደላቸው ፍጡሮቹ ደግሞ ተመላጆች እና አማላጆች ናቸው። ይህ ሦስቱ ሂደት “ምልጃ” ሲባል ይህ የምልጃ ፈቃድ የአላህ ብቻ ነው፦
39፥44 *”ምልጃ በሙሉ የአላህ ብቻ ነው፤ የሰማያትና የምድር ሥልጣን የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ከዚያም ወደ እርሱ ትመለሳላችሁ”* በላቸው፡፡ قُل لِّلَّهِ الشَّفَاعَةُ جَمِيعًا ۖ لَّهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ ثُمَّ إِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
34፥23 *ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም*፡፡ وَلَا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ عِندَهُ إِلَّا لِمَنْ أَذِنَ لَهُ
20፥109 *በዚያ ቀን ለእርሱ አልረሕማን የፈቀደለትን እና ለእርሱም ቃልን የወደደለትን ሰው ቢኾን እንጅ ምልጃ አንድንም አትጠቅምም*፡፡ يَوْمَئِذٍ لَّا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ إِلَّا مَنْ أَذِنَ لَهُ الرَّحْمَـٰنُ وَرَضِيَ لَهُ قَوْلًا

ነጥብ አንድ
“አማላጅ”
“ሸፊዕ” شَفِيع ማለት “አማላጅ” ማለት ሲሆን በአላህ ፈቃድ የሚያማልዱት መላእክት፣ ነቢያት፣ ሙዑሚን ናቸው፤ ለምሳሌ መላእክት፦
53፥26 *በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች ሊማለዱለት ለሚሻው እና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም*፡፡ وَكَم مِّن مَّلَكٍ فِي السَّمَاوَاتِ لَا تُغْنِي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا إِلَّا مِن بَعْدِ أَن يَأْذَنَ اللَّهُ لِمَن يَشَاءُ وَيَرْضَىٰ
21፥28 በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ *ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም*፡፡ እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው፡፡ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يَشْفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ارْتَضَىٰ وَهُم مِّنْ خَشْيَتِهِ مُشْفِقُونَ

“ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም” የሚለው ሃይለ-ቃል መላእክት ለአማንያን እንደሚያማልዱ ያሳያል፤ ሌላው አማላጆች አላህ ቃል ኪዳን የገባላቸው ነብያት ናቸው፦
19፥87 *አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ሰው ቢኾን እንጂ ማማለድን አይችሉም*፡፡ لَّا يَمْلِكُونَ الشَّفَاعَةَ إِلَّا مَنِ اتَّخَذَ عِندَ الرَّحْمَـٰنِ عَهْدًا
2፥255 *ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው?* مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِندَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ
33፥7 *ከነቢያትም የጠበቀ ኪዳናቸውን ከአንተም፣ ከኑሕም፣ ከኢብራሒምም፣ ከሙሳም እና ከመርየም ልጅ ከዒሳም ጋር በያዝን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከእነርሱም የከበደን ቃል ኪዳን ያዝን*፡፡ وَإِذْ أَخَذْنَا مِنَ النَّبِيِّينَ مِيثَاقَهُمْ وَمِنكَ وَمِن نُّوحٍ وَإِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ ۖ وَأَخَذْنَا مِنْهُم مِّيثَاقًا غَلِيظًا
ነጥብ ሁለት
“አማላጅ የለም”
ከላይ በግልፅና በማያሻማ መልኩ አላህ የፈቀደለት አማላጅ እና የሚማለድለት ተመላጅ ሰው እንዳለ ተቀምጧል፦
10፥3 *ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፡፡ እነሆ! አላህ ጌታችሁ ነውና አምልኩት፤ አትገሰጹምን?* مَا مِن شَفِيعٍ إِلَّا مِن بَعْدِ إِذْنِهِ ۚ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ

“ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት “አንድም አማላጅ የለም” ነገር ግን “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ”።
ነገር ግን ጣዖታውያን ቁሬሾች ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፤ “እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ፤ እነዚህም በትንሳኤ ቀን፦ “እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአላህ ተጋሪዎች ናቸው የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም” ይባላሉ፦
10፥18 *ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፤ “እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ*፡፡ وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُمْ وَيَقُولُونَ هَـٰؤُلَاءِ شُفَعَاؤُنَا عِندَ اللَّهِ
6፥94 *እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአላህ ተጋሪዎች ናቸው የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም፤ ግንኙነታችሁ በእርግጥ ተቋረጠ፡፡ ከእናንተም ያ ያማልደናል የምትሉት ጠፋ* ይባላሉ፡፡ وَمَا نَرَىٰ مَعَكُمْ شُفَعَاءَكُمُ الَّذِينَ زَعَمْتُمْ أَنَّهُمْ فِيكُمْ شُرَكَاءُ ۚ لَقَد تَّقَطَّعَ بَيْنَكُمْ وَضَلَّ عَنكُم مَّا كُنتُمْ تَزْعُمُونَ

እነዚያ ጣዖታውያን በአላህ ሌላ የሚያጋሩትን ጣዖታት፦ “አማላጆቻችን ናቸው” ይበሉ እንጂ ለእነርሱ ወደ አላህ የሚያማልድ አማላጅ የላቸው፦
6፥51 *እነዚያንም ከእርሱ ሌላ ረዳት እና አማላጅም የሌላቸው ሲኾኑ ወደ ጌታቸው መስሰብሰብን የሚፈሩትን ይጠነቀቁ ዘንድ በእርሱ በቁርኣን አስጠንቅቅ*፡፡ وَأَنذِرْ بِهِ الَّذِينَ يَخَافُونَ أَن يُحْشَرُوا إِلَىٰ رَبِّهِمْ ۙ لَيْسَ لَهُم مِّن دُونِهِ وَلِيٌّ وَلَا شَفِيعٌ لَّعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ
40፥18 *ለበዳዮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም*፡፡ مَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ حَمِيمٍ وَلَا شَفِيعٍ يُطَاع
32፥4 *ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት እናም አማላጅም ምንም የላችሁም፤ አትገሰጹምን?* مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُون

“አትገሰጹምን” የሚለው ያልተገሰጹትን በዳዮች ነው፤ “ለበዳዮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም” የሚለው ይሰመርበት፤ “ማ ለኩም ሚን ዱኒሂ ሚን ወሊይ” مَا لَكُمْ مِنْ دُونِهِ مِنْ وَلِيٍّ ማለትም “ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም” ማለት ሲሆን ከአላህ ውጪ በጀነት ለመጥቀምና በጀሃነም ለመቅጣት የሚችል ማንም እረዳት የላቸውም፤ “ሚን ዱኒሂ” مِنْ دُونِهِ ማለትም “ከእርሱ ሌላ” የሚለው ተሳቢ ተውላጠ-ስም ከሰዋስው አንፃር አላህ ብቻ በመጥቀምና በመጉዳት ረዳት መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፦
18፥26 *ለእነርሱ ከእርሱ በቀር ምንም ረዳት የላቸውም፤ በፍርዱም አንድንም አያጋራም*። أَبْصِرْ بِهِ وَأَسْمِعْ ۚ مَا لَهُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا يُشْرِكُ فِي حُكْمِهِ أَحَدًا

አንቀጹ ላይ፦ “ወላ ሸፊዒን” وَلَا شَفِيعٍ ማለት “እና አማላጅም የላችሁም” ማለት ሲሆን ከመጀመሪያው ሀረግ ለመለየት “ወ” وَ የሚል መስተዋድድ ይጠቀማል፤ ያ ማለት “በተጨማሪም አማላጅም የላችሁም” ማለት ነው፤ “ላ” لَا የሚለው “ሐርፉ ነፍይ” አፍራሽ ቃል ነው፤ ስለዚህ በመጀመሪያው ሀረግ ላይ “ማ” مَا የሚለው “መስደሪያ” አፍራሽ ቃል ሆኖ ገብቶ በተጨማሪ በሁለተኛው ሃረግ ላይ “ላ” لَا የሚለው አፍራሽ ቃል መደገሙ ጣኦታውያን ጣኦቶቻቸውን ወደ አላህ በማማለድ ያቀርቡናል ብለው የሚናገሩላቸውን ጣኦታት አማላጆች አለመሆናቸውን ለማሳየት “አማላጅ የላችሁም” በማለት ዘግቶታል፤ ለእነርሱም ከሚያጋሩዋቸው አማላጆች አይኖሯቸውም፦
30፥13 *ለእነርሱም ከሚያጋሩዋቸው አማላጆች አይኖሯቸውም*፤ وَلَمْ يَكُن لَّهُم مِّن شُرَكَائِهِمْ شُفَعَاءُ

ስለዚህ “አማላጅም ምንም የላችሁም” ማለት “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ካልሆነ በቀር እናንተ ከምታጋሯቸው የሚያማልድ አንድም አማላጅ የለም” ማለት ነው እንጂ በአላህ ፈቃድ የሚያማልዱ አማላጆች የሉም ማለት አሊያም አላህ አማላጅ ነው ማለት አይደለም። ከአላህ ሌላ ከቅጣት ሊያድናቸው የሚችል ረዳት የላቸውም፤ እንዲሁ ቅጣት እንዳይቀጡ ወደ አላህ የሚያማልዱ አማላጅ የላቸውም ማለት ነው። ሙፈሲሮችም በዚህ መልኩ ነው ተረድተው ያስቀመጡት:-
ተፍሲሩል ኢብኑ ከሲር 32፥4
*”ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም” ማለት “እርሱ ብቻ ሉአላዊ የሁሉንም ጉዳዮች ተቆጣጣሪ፣ የሁሉም ነገር ፈጣሪ፣ ሁሉን ነገር አድራጊ ነው፤ ከእርሱ ሌላ ፈጣሪ የለም” ማለት ነው። “እናም አማላጅም ምንም የላችሁም” ማለት “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም” ማለት ነው*።
( ما لكم من دونه من ولي ولا شفيع )
أي : بل هو المالك لأزمة الأمور ، الخالق لكل شيء ، المدبر لكل شيء ، القادر على كل شيء ، فلا ولي لخلقه سواه ، ولا شفيع إلا من بعد إذنه .

መላእክት፣ ነቢያት፣ ሙዑሚን ያማልዳሉ ማለት እና እኛ ወደ ፍጡራን በሌሉበት መለማመን፣ መጠየቅ እና መጸለይ ይለያያል፤ ወደ ፍጡራን በሌሉበት መለማመን፣ መጠየቅ እና መጸለይ ሺርክ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ዱዓ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

1፥5 አንተን ብቻ እናመልካለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ ፡፡

“ዱዓ” دُعَآء የሚለው ቃል በቁርአን 22 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን ትርጉሙ “ልመና” “ጥሪ” “ፀሎት” የሚል ፍቺ ሲኖረው ለአንዱ አምላክ የሚቀርብ መጎባደድ፣ መተናነስ፣ ማሸርገድ፣ መለማመንን ያሳያል፣ ዱዓ በቀውል ከሚደረጉ የአምልኮ አይነት አንዱ ነው፣ አብዛኛው ሰው ወደ ፍጡራን ዱዓ ያደርጋል፤ ነገር ግን ፍጡራን ወደ እነርሱ የሚደረግላቸው ዱዓ እስከ ቂያማ ቀን አያቁም ዝንጉዎች ናቸው፣ በቂያማ ቀን ግን ያንን ዱዓ ሰምተው እንደማያውቁ ይመሰክሩባቸዋል፣ በሰው ልብ ያለውን የሚያውቅ፣ የሁሉንም ልመና በአንድ ጊዜና በተለያየ ቦታ አይቶና ሰምቶ የሚመልስ አንዱ አምላክ አላህ ብቻ ነው፦
2:186 ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ ፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ፡፡ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በእኔም ይመኑ፤ እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡
40፥60 ጌታችሁም አለ «ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና፡፡ እነዚያ እኔን ከማምለክ የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ وَقَالَ رَبُّكُمُ ٱدْعُونِىٓ أَسْتَجِبْ لَكُمْ ۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِى سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ ፡፡
60:1 እኔ የምትደብቁትንና የምትገልጹትን የማውቅ ስሆን ወደነርሱ በፍቅር ትመሣጠራላችሁ፤
34:11 እኔ የምትሠሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነኝና።

መለመን፣ መጎባደድ፣ ማሸርገድ፣ መተናነስ አላህን ብቻ ነው፤ እነዚያም ከእርሱ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱም፦
7፥197 እነዚያም ከእርሱ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱም وَٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا يَسْتَطِيعُونَ نَصْرَكُمْ وَلَآ أَنفُسَهُمْ يَنصُرُونَ ፡፡
1፥5 አንተን ብቻ እናመልካለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ ፡፡

የሚገርመው አጋሪዎች ዱዓ በማድረግ ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው የሚይዙት አላህ፦ “ባሮቼ” የሚላቸውን መላእክትንና ነቢያትንም ነው፦
18፥102 እነዚያ የካዱት *ባሮቼን ከእኔ ሌላ አማልክት አድርገው መያዛቸውን* የማያስቆጣኝ አድርገው አሰቡን? እኛ ገሀነምን ለከሓዲዎች መስተንግዶ አዘጋጅተናል أَفَحَسِبَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ أَن يَتَّخِذُوا۟ عِبَادِى مِن دُونِىٓ أَوْلِيَآءَ ۚ إِنَّآ أَعْتَدْنَا جَهَنَّمَ لِلْكَٰفِرِينَ نُزُلًۭا ፡፡
3:80 “መላእክትንና ነቢያትንም አማልክቶች አድርጋችሁ እንድትይዙ” ሊያዛችሁ አይገባዉም፤ እናንተ ሙስሊሞች ከሆናችሁ በኋላ በክሕደት ያዛችኋልን?
43:19 “መላክትን እነርሱ የአልረሕማን ባሮች” የሆኑትን ሴቶች አደረጉ፤ ሲፈጠሩ ነበሩን? መመስከራቸው በርግጥ ትጻፋለች፤ ይጠየቃሉም።
38:45 “ባሮቻችንንም” ኢብራሂምን፣ ኢስሐቅንና ያዕቆበንም፣ የኅይልና የማስተዋል ባለቤቶች የኾኑን አውሳላቸው፡፡

አንድ ሰው አንድ ነገር አምላክ አርጎ ያዘ ማለት አምላክ ብሎ መጥራት ብቻ ሳይሆን አምላክ አድርጎ መያዝም ነው፣ ያ ማለት ለአምላክ የሚሰጠውን የአምልኮ ክፍል ለሌላ ማንነት ሆነ ምንነት መስጠትን ያመለክታል፤ ለምሳሌ አንድ ሰው ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ ያዘ ማለት ፍላጎቱን አምላኬ ብሎ ጠራ ማለት ሳይሆን ለአምላክ የሚሰጠውን የአምልኮ ክፍል ለፍላጎቱ ቅድሚያ ሰጠ ማለት ነው፦
25:43 ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ የያዘውን اتَّخَذَ ሰው አየህን? አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትሆናለህን?

ሰዎች ከአላህ ሌላ አማልክትን ለእነርሱ መከበሪያ እንዲኾኑዋቸው ቢይዙም የትንሳኤ ቀን እነዚያ ዱዓ ሲደረግላቸው የነበሩት አካላት ከአምላኪዎች ተቃራኒ በመሆን አምልኮ እንዳልተቀበሉ ይክዳሉ፦
19፥81-82 *ከአላህም ሌላ አማልክትን* ለእነርሱ መከበሪያ እንዲኾኑዋቸው *ያዙ* وَٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ ءَالِهَةًۭ لِّيَكُونُوا۟ لَهُمْ عِزًّۭا ፡፡ ይከልከሉ፤ *ማምለካቸውን በእርግጥ ይክዷቸዋል፡፡ በእነሱም ላይ ተቃራኒ ይኾኑባቸዋል* كَلَّا ۚ سَيَكْفُرُونَ بِعِبَادَتِهِمْ وَيَكُونُونَ عَلَيْهِمْ ضِدًّا ፡፡
28:62-63 አላህ የሚጠራባቸውንና እነዚያ ተጋሪዎቼ ትሏቸው የነበራችሁት የት ናቸው የሚልበትን ቀን አስታውስ፤ እነዚያ በእነርሱ ላይ ቃሉ የተረጋገጠባቸው ይላሉ «ጌታችን ሆይ! እነዚህ እነዚያ ያጠመምናቸው ናቸው፡፡ እንደጠመምን አጠመምናቸው፡፡ ከእነርሱ ወደ አንተ ተጥራራን፡፡ *”እኛን ያመልኩ አልነበሩም”*፡፡
አላህ እነርሱን እና ከአላህ ሌላ የሚያመልኳቸውንም የሚሰበስብባቸውን እና እናንተ እነዚህን ባሮቼን አሳሳታችሁን ወይስ እነርሱው መንገድን ሳቱ? ብሎ ይጠይቃቸዋል፦
25፥17-18 እነርሱን እና ከአላህ ሌላ የሚያመልኳቸውንም የሚሰበስብባቸውን እና *«እናንተ እነዚህን ባሮቼን አሳሳታችሁን ወይስ እነሱው መንገድን ሳቱ?» የሚልበትን ቀን* አስታውስ፡፡ «ጥራት ይገባህ፤ ከንተ ሌላ ረዳቶችን ልንይዝ ለእኛ ተገቢያችን አልነበረም፡፡ ግን *እነርሱንም አባቶቻቸውንም መገንዘብን እስከተዉ ድረስ* አጣቀምካቸው፡፡ ጠፊ ሕዝቦችም ኾኑ» *”ይላሉ”*፡፡

ዱዓ በቀውል ከሚደረጉ የአምልኮ አይነት አንዱ ነው፣ ሰውን በአካል ማየት፣ መስማት፣ መናገር እስከቻለ ድረስ ማነጋገሩ ተፈጥሯዊ ነው፣ ነገር ግን የሚያይበት አይን፣ የሚሰማበት ጆሮ፣ የሚናገርበት አፍ በሞት ጊዜ ስለሚፈራርሱ አይሰማም፣ አይናገርም፣ አያይም። በክርስትና ማለትም ካቶሊክ፣ ኦርቶዶክስና አንግሊካል ለምሳሌ ወደ ማርያም ጥሪ፣ ልመና፣ መተናነስ፣ መጎባደድ ይደረጋል፣ ይህ አይን ያፈጠጠና ጥርስ ያስገጠጠ ሃቅ ነው፣ ታዲያ ማርያም ይህን ዱዓ ትሰማለች ወይ? አይ ከተባለ ለምን ወደ ማርያም ዱዓ ይደረጋል? አዎ ትሰማለች ከተባለ በምኗ? ሰውን የምትገናኝበት ህዋሳቷ አፈር ሆኖ የለ እንዴ? በሰው ልብ ያለውን መለኮት ካልሆነች እንዴት ታውቃለች? ከአላህ ሌላ ማንነት ሆነ ምንነት መለማመን፣ መጎባደድ፣ መተናነስ፣ መጥራት ሽርክ ነው፦
46:5 እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልስለት ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّن يَدْعُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَن لَّا يَسْتَجِيبُ لَهُۥٓ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ وَهُمْ عَن دُعَآئِهِمْ غَٰفِلُونَ ::

“መን” مَنْ የሚለው አንፃራዊ ተውላጠ ስም “ማንነት” ያላቸውን ኑባሬ ሲያመለክት፤ እነዚህ የአላህ ባሮች ዱዓን አይሰሙም፤ የሚጠሯቸው እንደ እነርሱ አላህን አምላኪዎች ናቸው፦
7:194 እነዚያ ከአላህ ሌላ *የምትጠሯቸው እንደ እናንተ አምላኪዎች ናቸው*፤ እውነተኞችም እንደሆናችሁ ጥሩዋቸው እና ለእናንተ ይመልሱላችሁ አይችሉም إِنَّ ٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ فَٱدْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا۟ لَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ ።

እነዚህን የአላህ ባሮች ቅርፅ አበጅተው ቢለማመኑም እነርሱና የተለማመኗቸው ጣኦታት እጣ ፋንታ የገሃነም ማገዶ መሆን ነው፦
21፥98 እናንተ ከአላህ ሌላ የምታመልኳቸውም የገሀነም ማገዶዎች ናችሁ፡፡ እናንተ ለእርሷ ወራጆች ናችሁ إِنَّكُمْ وَمَا تَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ حَصَبُ جَهَنَّمَ أَنتُمْ لَهَا وَٰرِدُونَ ፡፡

“ኢነኩም” إِنَّكُمْ “እናንተ” የሚለው ሁለተኛ መደብ ላይ ያሉት ሙሽሪኮች ሲሆኑ ከዓለማቱ ጌታ ከአላህ ሌላ የሚያመልኳቸው ጣዖታትም የገሃነም ማገዶዎች ናቸው፤ “ማ” َمَا የሚለው አንፃራዊ ተውላጠ-ስም አቅል የሌላቸውን ጣኦታት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፤ አቅል ያላቸውን ማንነቶች “መን” مَّن የሚል አንፃራዊ ተውላጠ-ስም የሚጠቀመው፤ ግን እዚህ አንቀፅ ላይ “ማ” የሚል አንፃራዊ ተውላጠ-ስም መጠቀሙ አቅል የሌላቸውን ጣኦታት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፤ ይህ የሰዋስው ሙግት ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው። በተጨማሪም ሌላ አንቀፅ ላይ የጀሃነም መቀጣጠያ ማገዶ ድንጋይ መሆናቸው ተገልጿል፦
66፥6 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *እራሳችሁን እና ቤተሰቦቻችሁን* መቀጣጠያዋ *ሰዎች እና ደንጋዮች* ከኾነች *እሳት ጠብቁ* يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ قُوٓا۟ أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًۭا وَقُودُهَا ٱلنَّاسُ وَٱلْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَٰٓئِكَةٌ غِلَاظٌۭ شِدَادٌۭ لَّا يَعْصُونَ ٱللَّهَ مَآ أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ ፡፡
2፥24 ይህንን ባትሠሩ ፈጽሞም አትሠሩትምና ያችን *”መቀጣጠያዋ ሰዎችና ድንጋዮች”* የኾነችውን እሳት ተጠበቁ፤ ለከሓዲዎች ተደግሳለች፡፡ فَإِن لَّمْ تَفْعَلُوا۟ وَلَن تَفْعَلُوا۟ فَٱتَّقُوا۟ ٱلنَّارَ ٱلَّتِى وَقُودُهَا ٱلنَّاسُ وَٱلْحِجَارَةُ ۖ أُعِدَّتْ لِلْكَٰفِرِينَ

ስለዚህ ለፍጡራን ዱዓ የምታደርጉ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደሆነች ቃል ኑ፤ ይህም ቃል አላህ አንድ አምላክ ነውና ከአላህ ሌላን ላናመልክ፤ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን *ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጐ ላንይዝ ነዉ፦
3:64 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደሆነች ቃል ኑ፤ እርሷም አላህን እንጅ ሌላን ላናመልክ፤ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን *ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጐ ላንይዝ ነዉ*፤ በላቸዉ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ማለደ እና አማለደ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ሮሜ 8፥34 *ይልቁንም* የሞተው፥ ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ *የሚማልደው* ἐντυγχάνει ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።

ሮሜ8፥33 ላይ የግዕዙ ባይብል ላይ፦ “ወይትዋቀሥ በእንቲአነ” ይለዋል፤ “ይትዋቀስ” የሚለው ግስ “ተዋቀሠ” ማለትም “ተከራከረ” “ተሟገተ” ከሚል ስርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “የሚከራከር” “የሚሟገት” የሚል ፍቺ አለ፤ ያ ነጥብ ስለገባቸው አንድምታው ላይ፦ “ስለ እኛ ይከራከራል” ብሎ አስቀምጠውታል፤ አንዳንድ እትሞች ግሪኩን እና ግዕዙን መሰረት ያላደረገ፦ “ስለ እኛ የሚፈርደው” ብለው ተርጉመውታል፤ ይህ ከሁለት አንጻር እንደሆነ ይናገራሉ፤ አንደኛ ማማለድ የፍጡር ባህርይ ስለሆነ፤ ሁለተኛ ዐውዱ ስለ ፍርድ ስለሚያወራ ይላሉ። ግን ዐውዱ ስለ ፍርድ ይናገራል ወይ? እስቲ እንየው፦
ሮሜ 8፥31 እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ *ማን ይቃወመናል?*
ሮሜ 8፥33 እግዚአብሔር የመረጣቸውን *ማን ይከሳቸዋል*? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ *የሚኰንንስ ማን ነው?*

ዐውዱ ላይ ስለማንም ፈራጅነት አያወራም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል? መልሱ ማንም።
እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? ማንም።
እግዚአብሔር ካጸደቀ የሚኰንንስ ማን ነው? ማንም።
ስንጠቀልለው፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማንም አይቃወመንም።
እግዚአብሔር ከመረጠ ማንም አይከስም።
እግዚአብሔር ካጸደቀ ማንም አይኮንንም።
ይህ ነው መልእክቱ። እከሌ ያጸድቃል ይኮንናል የሚል ሃይለ-ቃል በአንቀጹ ላይ የለም። ቀጥሎ አንቀጹ፦
ሮሜ 8፥34 *ይልቁንም* የሞተው፥ ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ *የሚማልደው* ἐντυγχάνει ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።

ይህ ጥቅስ በግልጽና በማያሻማ መልኩ ኢየሱስ አማላጅ መሆኑ አስቀምጧል፣ ምክንያቱም “ዴ” δὲ ማለትም “ይልቁንም”moreover” የሚል ለይ መስተጻምር በመጠቀም ስለ ኢየሱስ አማላጅነት ይናገራል፣ “የሚማልደው” የሚለው የግሪኩ ቃል “ኢንትይንች” ἐντυγχάνει ሲሆን የሚፈርደው እያሉ ለሚቀያይሩት ሰዎች ማምለጫ መንገድ የላቸውም፣ “ኢንትይንች” ἐντυγχάνει የሚለው ቃል ግስ ሲሆን “ኢንቲአኖ” ἐντυγχάνω ማለትም “አማለደ” ከሚለው ስርወ-ቃል የመጣ ነው፣ አሁን ምን ይዋጣቸው ኢየሱስ አያማልድም ለሚሉ? ማጠናከሪያ ተመሳሳይ ቃላት፦
ዕብራውያን 7፥25 ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል፣ ስለ እነርሱም *ሊያማልድ* ἐντυγχάνειν ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ።

ሰዎች ወደ እግዚአብሔር የሚመጡት በክርስቶስ ነው ካለን፣ እግዚአብሔር ተማላጅ ነው ማለት ነው፣ በክርስቶስ ወደ እግዚአብሔር ለሚመጡት ሰዎች ደግሞ ክርስቶስ ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ይለናል፣ “ሊያማልድ” የሚለው የግሪኩ ቃል “ኢንቲቻኔን” ἐντυγχάνειν ሲሆን አሁንም “ኢንቲአኖ” ἐντυγχάνω “አማለደ” ከሚለው ስርወ-ቃል የመጣ ነው፣ አሁን ምን ይዋጣቸው ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው ለሚሉት? ይህ ነጥብ የገባው ሊቀ-ጠበብት ዘሪሁን ሙላቱ በአንድ ጥያቄና መልስ መርሃ-ግብር ላይ፦ “የሚማልድ” ማለት እና “የሚያማልድ” ማለት ይለያል፤ ወይም “ማለደ” ማለት እና “አማለደ” ማለት ይለያያል ብሏል።
ልዩነቱን ሲያስቀምጥ፦ “ማለደ” ማለት “ፈረደ” ማለት ሲሆን “አማለደ” ማለት ደግሞ “ለመነ” ማለት ነው” ብሏል፤ ይህ የቃላት ጨዋታ የትኛውም የአማርኛ ሆነ የግዕዝ ሙዳየ-ቃላት ላይ ማለትም አለቃ ታዬ፣ አለቃ ኪዳነ ወልድ፣ አለቃ ከሳቴ ብርሃን ሙዳየ-ቃላት ላይ ይደግፈውም፤ የጠበብት አለቃ የተባለው ይህ ሰው በመሰለኝና በደሳለኝ የተናገረውን የቃላት ጨዋታ ይህ ጥቅስ ድባቅ ያስገባዋል፤ “የሚማልድ” ማለት “የሚፈርድ” ማለት ከሆነ “የሚማልዱኝ” ማለት “የሚፈርዱኝ” ማለት ነውን? ትርጉም አይሰጥም፦
ሶፎንያስ3፥10 ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ *የሚማልዱኝ*፥ የተበተኑት ሴቶች ልጆቼ፥ ቍርባኔን ያመጡልኛል።

ማለደ” ማለት “ፈረደ” ማለት ከሆነ ስለ ዓመፀኞችም “ማለደ” ማለት ስለ ዓመፀኞችም “ፈረደ” ማለት ነው? ስለ ዓመፀኞችም ከፈረደማ ወንጀል ተባባሪ ሆነ፤ ባይሆን ስለ ታዛዦችም ፈረደ መባል ነበረበት፦
ኢሳይያስ 53፥12 ስለ ዓመፀኞችም *”ማለደ”*።

ማለደ” ማለት “ፈረደ” ማለት ከሆነ እነዚህን ጥቅሶች እንዴት ትረዳዋለክ? ሙግትክ ውሃ የማያነሳና የማይቋጥር ስሁት ሙግት ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 16:38 የሮሜ ሰዎች እንደሆኑ በሰሙ ጊዜ ፈሩ መጥተውም *ማለዱአቸው* ።
የሐዋርያት ሥራ 25:3 ወደ ኢየሩሳሌምም እንዲያስመጣው *ማለዱት*።

ማለደ ማለት ፈረደ ማለት ነው ብሎ መሞገት የቋንቋ ሙግት መረጃ የሌለው እና ጉንጭ አልፋ ንትርክ ብቻ ነው። ኢየሱስ አማላጅ ከሆነ ደግሞ ተማላጅ የሚሆነው እግዚአብሔር ነው። ፊሽካው ተነፋ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ተነጥሎ ፍጡር ይሆናል።
ኢየሱስ ተማላጅ ነው የሚል ባይብል ላይ የለም ፣ ከሌለ ደግሞ ክርስቶስ እግዚአብሔር አይደለም ማለት ነው፣ እግዚአብሔር ወደ እግዚአብሔር ይጸልያልን? አይጸልይም የጸለየው ፍጡር ነው፦
ሉቃስ 6፥12 ሌሊቱንም ሁሉ *ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ*።

እግዚአብሔር እግዚአብሔርን ቀባውን? እግዚአብሔርን ማንም አይቀባውም፤ የተቀባው ፍጡር ነው፦
ሐዋርያት ሥራ 10፥38 *እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው*፥

እግዚአብሔር ለእግዚአብሔር የበላይ ነውን? በፍጹም፤ እግዚአብሔር የፍጡራን የበላይ ነው፦
1ኛ ቆሮ 11፥3 *የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ* ልታውቁ እወዳለሁ።

እግዚአብሔር የእግዚአብሔር ነውን? በፍጹም፤ ሁሉን የእርሱ እንጂ እርሱ የማንም አይደለም፦
1ኛ ቆሮ 3፥23 *ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው*።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ማሻረክ ነውን?

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥36 *አላህንም አምልኩ፡፡ በእርሱም ምንንም አታጋሩ*፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا

አምላካችን አላህ በእርሱ አምልኮ ላይ ምንንም ነገር ማንም እንዳያጋራ ከልክሏል፦
6፥151 *«ኑ፤ ጌታችሁ በእናንተ ላይ እርም ያደርገውን ነገር ላንብብላችሁ» በላቸው፡፡ «በእርሱ ምንንም ነገር አታጋሩ*፡፡ قُلْ تَعَالَوْا أَتْلُ مَا حَرَّمَ رَبُّكُمْ عَلَيْكُمْ ۖ أَلَّا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا
4፥36 *አላህንም አምልኩ፡፡ በእርሱም ምንንም አታጋሩ*፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا

ብዙ አንቀጾች ላይ “ እኔን ብቻ አምልኩኝ” እያለ በመጀመሪያ መደብ ተናግሯል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ *”እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ”*፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ

ይህ እንዲህ በእንዲህ እያለ በተቃራኒው ሚሽነሪዎች፦ "አላህ መልእክተኛውን ነብያችን”ﷺ” ከራሱ ጋር አሻርኮታል" ብለው ውሃ የማያነሳ ስሁት ሙግት ያቀርባሉ፤ ለዚህም እንደመነሻ የሚያነሷቸው አናቅጽ አምላካችን አላህ ብዙ አንቀጾች ላይ፦ "አላህ እና መልእክተኛው ታዘዙ" "አላህ እና መልእክተኛው እመኑ" "አላህ እና መልክተኛውም ነገርን በፈረዱ ጊዜ" ማለቱን ነው፤ እውን እነዚህ ዓረፍተ-ነገር ወደዚያ ድምዳሜ ላይ ያደርሳሉን? እስቲ የሚጠቅሷቸውን ጥቅሶች በሰላ እና በሰከነ አይዕምሮ እንመልከታቸው፦

ነጥብ አንድ
"ታዘዙ"
አምላካችን አላህ ብዙ አንቀጾች ላይ "አላህን እና መልክተኛውን ታዘዙ" ይላል፦
3፥32 *«አላህን እና መልክተኛውን ታዘዙ*፡፡ ብትሸሹም አላህ ከሓዲዎችን አይወድም» በላቸው፡፡ قُلْ أَطِيعُوا اللَّهَ وَالرَّسُولَ ۖ فَإِن تَوَلَّوْا فَإِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْكَافِرِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ፦ "አላህን ታዘዙ" ማለት የአላህ ንግግር የሆነውን ቁርአን መመሪያ አድርጉ ማለት ነው፤ "መልእክተኛው ታዘዙ" ማለት ነብያችን”ﷺ” በሐዲስ የተናገሩትን መመሪያ አድርጋችሁ ያዙ ነው፤ "ታዘዙ" ማለት "አምልኩ" ማለት አይደለም፤ "አዕብዱ" اعْبُدُوا ማለት "አምልኩ" ማለት ሲሆን "አጢዑ" أَطِيعُوا ማለት ደግሞ "ታዘዙ" ማለት ነው፤ እዚህ ጥቅስ ላይ የመጣው "አጢዑ" ለአሚሮችም አገልግሎት ላይ ውሏል፦
4፥59 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *አላህን ታዘዙ፣ መልክተኛውን እና ከእናንተም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَأُولِي الْأَمْرِ مِنكُمْ

"የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ" ስለተባለ የስልጣን ባለቤቶችን መታዘዝ አላህ ላይ ማጋራት ነውን? በፍጹም! "ታዘዙ" ማለት "አምልኩ" ማለት ቢሆን ኖሮ ኑሕ ሹዕይብ፣ ዒሣ የመሳሰሉት መልእክተኞች "ታዘዙኝ" ባላሉ ነበር፦
71፥3 «አላህን ተገዙት፣ ፍሩትም፣ *ታዘዙኝም" በማለት አስጠንቃቂ ነኝ፡፡ أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاتَّقُوهُ وَأَطِيعُونِ
26፥179 «አላህንም ፍሩ፤ *ታዘዙኝም*፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ
43፥63 «አላህንም ፍሩ፤ *ታዘዙኝም*፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ

እናማ ቁርኣኑ የሚለው፦ "አላህን ብቻ ታዘዙ" ነው፤ ብለው አሁንም ይሞግታሉ፦
22፥34 *አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ ታዘዙ*፡፡ ለአላህ ተዋራጆችንም አብስራቸው፡፡ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا ۗ وَبَشِّرِ الْمُخْبِتِين

እውነት ነው፤ እዚህ አንቀጽ ላይ “ታዘዙ” ለሚለው ቃል የተቀመጠው “አሥሊሙ” أَسْلِمُوا ሲሆን “አሥለመ” أَسْلَمَ ማለትም “ታዘዘ”፣ “ተገዛ”፣ ” አመለከ” ከሚል ግስ የመጣ ነው፤ ይህ ቃል ለአላህ ብቻ የሚውል ቃል ነው፤ "አጢዑ" ከሚለው ጋር በቃላትም አይመሳሰልም። “አሥሊሙ” ግን “ሙሥሊም” مُسْلِم ለሚለው ቃል ትእዛዛዊ ግስ ነው፤ አላህ ለኢብራሂም “አሥሊም” أَسْلِمْ ማለትም “ታዘዝ” ብሎ ሲለው እርሱም ለዓለማት ጌታ “አሥለምቱ” أَسْلَمْتُ ማለትም “ታዘዝኩ” አለ፦
2፥131 ጌታው ለእርሱ *”ታዘዝ”* ባለው ጊዜ መረጠው፡፡ ለዓለማት ጌታ *”ታዘዝኩ”* አለ፡፡ إِذْ قَالَ لَهُۥ رَبُّهُۥٓ أَسْلِمْ ۖ قَالَ أَسْلَمْتُ لِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

“ኢሥላም” إِسْلَٰم ደግሞ የሙስሊም ሃይማኖቱ ሲሆን "መታዘዝ" መገዛት" "ማምለክ" ማለት ነው፤ አላህ፦ "ሁላችሁም በመታዘዝ ውስጥ ግቡ" የሚለን፤ “መታዘዝ” ለሚለው ቃል የገባው “ሲልም” سِّلْم መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፦
2፥208 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *ሁላችሁም በመታዘዝ ውስጥ ግቡ*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱدْخُلُوا۟ فِى ٱلسِّلْمِ كَآفَّةًۭ
ነጥብ ሁለት
"ፍርድ"
“አል-ሐከም” الحَكَم ከአላህ ስሞች አንዱ ሲሆን ትርጉሙ “ፈራጅ ወይም ዳኛ” ማለት ሲሆን “ሁክም” حُكْم ማለትም "ፍርድ" ደግሞ የእርሱ ባህርይ ነው፤ አምላካችን አላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ፈራጅ ነው፤ በፍርዱ ቀን ፍርዱ የእርሱ ብቻ ነው፤ እርሱ የፍርዱ ቀን ባለቤት ነው፤ በዚያ ቀን በፍርዱ ማንንም አያጋራም፦
95፥8 *አላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ፈራጅ አይደለምን? ነው*፡፡ أَلَيْسَ اللَّهُ بِأَحْكَمِ الْحَاكِمِين
10፥109 ወደ አንተም የሚወረደውን ተከተል፡፡ *አላህም በእነርሱ ላይ እስከሚፈርድ ድረስ ታገስ፡፡ እርሱም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነው*፡፡ وَاتَّبِعْ مَا يُوحَىٰ إِلَيْكَ وَاصْبِرْ حَتَّىٰ يَحْكُمَ اللَّهُ ۚ وَهُوَ خَيْرُ الْحَاكِمِينَ
1፥4 *የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው*፡፡ مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ
6፥62 *ከዚያም እውነተኛ ወደ ኾነው ጌታቸው ወደ አላህ ይመለሳሉ፡፡ ንቁ! ፍርዱ ለእርሱ ብቻ ነው*፡፡ እርሱም ከተቆጣጣሪዎች ሁሉ ይበልጥ ፈጣን ነው፡፡ ثُمَّ رُدُّوا إِلَى اللَّهِ مَوْلَاهُمُ الْحَقِّ ۚ أَلَا لَهُ الْحُكْمُ وَهُوَ أَسْرَعُ الْحَاسِبِينَ
18፥26 ለእነርሱ ከእርሱ በቀር ምንም ረዳት የላቸውም፡፡ *በፍርዱም አንድንም አያጋራም*፡፡ مَا لَهُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا يُشْرِكُ فِي حُكْمِهِ أَحَدًا

አምላካችን አላህ የፈራጆች ሁሉ ፈራጅ ሲሆን በዱኒያህ ግን ለሁሉም ነብያት ማለትም ለሉጥ፣ ለዩሱፍ፣ ለሙሳ፣ ለዳውድ፣ ለሱለይማን ወዘተ የሚፈርዱበት ፍርድ ሰቷቸዋል፦
21፥74 *ሉጥንም ፍርድንና ዕውቀትን ሰጠነው*፡፡ وَلُوطًا آتَيْنَاهُ حُكْمًا وَعِلْمًا
12፥22 *ጥንካሬውንም በደረሰ ጊዜ ፍርድን እና ዕውቀትን ሰጠነው*፡፡ እንደዚሁም መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡ وَلَمَّا بَلَغَ أَشُدَّهُ آتَيْنَاهُ حُكْمًا وَعِلْمًا ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ
28፥14 ብርታቱንም በደረሰና በተስተካከለ ጊዜ *ፍርድ እና ዕውቀትን ሰጠነው*፡፡ እንዲሁም መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ وَلَمَّا بَلَغَ أَشُدَّهُ وَاسْتَوَىٰ آتَيْنَاهُ حُكْمًا وَعِلْمًا ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ
21፥79 *ለሱለይማንም ትክክለኛይቱን ፍርድ አሳወቅነው፡፡ ለሁሉም ፍርድ እና ዕውቀትን ሰጠን*፡፡ فَفَهَّمْنَاهَا سُلَيْمَانَ ۚ وَكُلًّا آتَيْنَا حُكْمًا وَعِلْمًا

አላህ ለሁሉም ፍርድ እና ዕውቀትን እንደሰ ለነብያችንም"ﷺ" ቁርኣንን እና ሱናው ፍርድ አድርጎ ሰጥቷል፦
5፥49 *በመካከላቸውም አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ*፡፡ وَأَنِ احْكُم بَيْنَهُم بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ
5፥42 *ብትፈርድም በመካከላቸው በትክክል ፍረድ፤ አላህ በትክክል ፈራጆችን ይወዳልና*፡፡ وَإِنْ حَكَمْتَ فَاحْكُم بَيْنَهُم بِالْقِسْطِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ

"ፈራጆች" የሚለው ቃል ይሰመርበት፤ ስለዚህ ለነብያችን”ﷺ” በመታዘዝ እና ለአላህ በመገዛት ፍርድን በዱንያህ እንቀበላለን፤ "አላህ እና መልክተኛውም ነገርን በፈረዱ ጊዜ" የሚለው ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ እንጂ በፍርድ ቀን ስለሚፈረደው ፍርድ በፍጹም አይደለም፦
24፥51 *የምእምናን ቃል የነበረው ወደ አላህ እና ወደ መልክተኛው በመካከላቸው ሊፈርድ በተጠሩ ጊዜ፦ "ሰማን እና ታዘዝንም" ማለት ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا كَانَ قَوْلَ الْمُؤْمِنِينَ إِذَا دُعُوا إِلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ لِيَحْكُمَ بَيْنَهُمْ أَن يَقُولُوا سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا
33፥36 *አላህ እና መልክተኛውም ነገርን በፈረዱ ጊዜ ለምእምናንና ለምእምናት ከነገራቸው ለእነርሱ ምርጫ ሊኖራቸው አይገባም! የአላህንና የመልክተኛውንም ትእዛዝ የጣሰ ሰው ግልጽ የሆነን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ*፡፡ وَمَا كَانَ لِمُؤْمِنٍ وَلَا مُؤْمِنَةٍ إِذَا قَضَى اللَّهُ وَرَسُولُهُ أَمْرًا أَن يَكُونَ لَهُمُ الْخِيَرَةُ مِنْ أَمْرِهِمْ ۗ وَمَن يَعْصِ اللَّهَ وَرَسُولَهُ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَالًا مُّبِينًا

"የአላህንና የመልክተኛውንም ትእዛዝ" የሚለው ይሰመርበት፤ "ትእዛዝ" የሚለው "ፍርድ" በሚል ተለዋዋጭ ቃል እንደመጣ ልብ በል፤ ስለዚህ ይህ ከማጋራት ጋር አንዳች ግንኙነት የለውም። ኢንሻላህ በክፍል ሁለት የተቀረውን ነጥብ እንጨርሳለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ማሻረክ ነውን?

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥36 *አላህንም አምልኩ፡፡ በእርሱም ምንንም አታጋሩ*፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا

ነጥብ ሦስት
“እመኑ”
አምላካችን አላህ፦ “በአላህ እና በመልክተኛው እመኑ” ብሏል፤ በእርሱ እና በመልክተኛው ያላመነም ሰው ለእርሱ እሳትን አዘጋጅቷል፦
57፥7 *በአላህ እና በመልክተኛው እመኑ*፡፡ آمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ
48፥13 *በአላህ እና በመልክተኛው ያላመነም ሰው እኛ ላከሓዲዎች እሳትን አዘጋጅተናል*፡፡ وَمَن لَّمْ يُؤْمِن بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ فَإِنَّا أَعْتَدْنَا لِلْكَافِرِينَ سَعِيرًا

አላህ በነብያችን”ﷺ” “እመኑ” ያለው ለእኛ ብቻ ሳይሆን በዒሣ ዘመንም ለሐዋርያት፦ “በእኔ እና በመልክተኛዬ እመኑ” ብሏል፦
5፥111 ወደ ሐዋርያትም *«በእኔ እና በመልክተኛዬ እመኑ»* በማለት ባዘዝኩ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى الْحَوَارِيِّينَ أَنْ آمِنُوا بِي وَبِرَسُولِي

እረ እንደውም ቁርኣን ሲወርድም፦ “በአላህ እና በመልክተኞቹም እመኑ” ብሏል፤ በሁሉም መልእክተኞ ለካዱት ሰዎች እሳት ተዘዛግቶላቸዋል፦
4፥171 *በአላህ እና በመልክተኞቹም እመኑ*፡፡ فَآمِنُوا بِاللَّهِ وَرُسُلِه
3፥79 *በአላህ እና በመልክተኞቹም እመኑ*፡፡ فَآمِنُوا بِاللَّهِ وَرُسُلِه
11፥27 *ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከእሳት ወዮላቸው*! فَوَيْلٌ لِّلَّذِينَ كَفَرُوا مِنَ النَّارِ

ስለዚህ “እመኑ” ማለት “አምልኩ” ማለት አይደለም፤ “እመኑ” ማለት ማሻረክ ቢሆን ኖሮ “በአላህ እና በመልክተኞቹም እመኑ” በማለት ሁሉንም መልእክተኞ ያካትት ነበርን? ይህ ሥነ-አመክኖአዊ ተፋልሶ”logical fallacy” ነው።

መደምደሚያ
አምላካችን አላህ የነገረን፦ “በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህ አትታዘዛቸው” በማለት ነው፤ ይህን መመሪያ የተቀበለ ሙስሊም ይባላል፤ እርሱ ስለ ሙስሊም ሲናገር፦ “በእኔ ምንንም የማያጋሩ ኾነው ያመልኩኛል” በማለት ነው፦
29፥8 *ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህ አትታዘዛቸው*፡፡ وَإِن جَاهَدَاكَ لِتُشْرِكَ بِي مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ فَلَا تُطِعْهُمَا
24፥55 *በእኔ ምንንም የማያጋሩ ኾነው ያመልኩኛል*፡፡ ከዚያም በኋላ የካደ ሰው እነዚያ እነርሱ አመጸኞች ናቸው፡፡ يَعْبُدُونَنِي لَا يُشْرِكُونَ بِي شَيْئًا ۚ وَمَن كَفَرَ بَعْدَ ذَٰلِكَ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْفَاسِقُونَ

ከፈጣሪ ጋር አብረው የተጠቀሱ አካላት ማሻረክ ከሆነ እኛም በተራችን ከባይብል ጥያቄ እንጠይቃለን፤ ሳኦል ከእግዚአብሔር ጋር እና በሚል መስተጻምር ተያይዟል፦
1ሳሙ 12፥3 እነሆኝ *በእግዚአብሔር እና “በመሲሑ” מְשִׁיח֗וֹ ፊት መስክሩብኝ* የማንን በሬ ወሰድሁ?
1ሳሙ 12፥5 እርሱም፦ በእጄ ምንም እንዳላገኛችሁ *እግዚአብሔር እና “መሲሑ” מְשִׁיח֗וֹ ዛሬ በእናንተ ላይ ምስክሮች ናቸው* አላቸው፤

“ፊት” በሚል በነጠላ ስም እና በአያያዥ መስተጻምር ሳኦል ከእግዚአብሔር ጋር ስለተቀመጠ ሳኦል አምላክ ነውን? የእስራኤል ጉባኤውም ሁሉ ራሳቸውንም አዘንብለው ለእግዚአብሔር እና ለንጉሡ ለዳዊት ሰገዱ፦
1ኛ ዜና መዋዕል 29፥20 ጉባኤውም ሁሉ የአባታቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ባረኩ፥ ራሳቸውንም አዘንብለው *”ለእግዚአብሔር እና ለንጉሡ ሰገዱ”*።

“ሰገዱ” በሚል በነጠላ ግስ እና በአያያዥ መስተጻምር ዳዊት ከእግዚአብሔር ጋር ስለተቀመጠ ዳዊት አምላክ ነውን? እግዚአብሔርን እና ንጉሡን ሰለሞንን ፍራ ተብሎ በአንድ መደብ ተቀምጧል፦
ምሳሌ 24፥21-22 ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔርን እና ንጉሥን *”ፍራ”*፥ ከዓመፀኞችም ጋር አትደባለቅ። *”መከራቸው”* ድንገት ይነሣልና፤ *”ከሁለቱ የሚመጣውን”* ጥፋት ማን ያውቃል?

“ፍራ” በሚል በነጠላ ግስ እና በአያያዥ መስተጻምር ሰለሞን ከእግዚአብሔር ጋር ስለተቀመጠ ሰለሞን አምላክ ነውን? የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር እና በሙሴ አመኑ፦
ዘጸአት 14፥31 ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ፥ *በእግዚአብሔርም በባሪያውም በሙሴ አመኑ*።

“አመኑ” በሚል በነጠላ ግስ እና በአያያዥ መስተጻምር ስለተቀመጠ ሙሴ አምላክ ነውን? በእግዚአብሔር እመኑ በነብያትም እመኑ ተብላል፦
 2ኛ ዜና 20፥20 *በአምላካችሁ በእግዚአብሔር እመኑ*፥ ትጸኑማላችሁ፤ *በነቢያቱም እመኑ*፥ ነገሩም ይሰላላችኋል አለ።
ዮሐንስ 14፥1 *በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ*።

“በእግዚአብሔር እመኑ” ማለት እግዚአብሔር ላኪ መሆን እመኑ ማለት ሲሆን “በነቢያቱም እመኑ” ማለት ደግሞ ነብያት ተላኪ መሆናቸውን እመኑ ማለት ነው።
በዚህ አጋጣሚ እግዚአብሔር እና ኢየሱስ በሁለት መደብ ብዙ ጊዜ መቅረባቸው ማሻረክ እንዳልሆነ እግረ-መንገዴን ጠቁሜ ልለፍ፦
መዝሙር 2፥2-3 የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም *በእግዚአብሔር እና በመሢሑ* ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ፦ *ማሰርያቸውን እንበጥስ፥ ገመዳቸውንም* ከእኛ እንጣል።

እግዚአብሔር እና ኢየሱስ “ማሰሪያቸው” “ገመዳቸው” በሚል እንጂ “ገመዱ” ማሰሪያው” በሚል አለመቅረቡ ሁለት የተለያዩ ህልውናዎች መሆናቸውን ያሳያል፦
ራእይ 21፥22 *ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እና በጉ መቅደስዋ ናቸውና*።

“ናቸው” እንጂ “ነው” አለመሆኑ ሁሉንም የሚገዛ አንድ ጌታ አምላክ እና ኢየሱስ ሁለት የተለያዩ ህልውናዎች መሆናቸውን ያሳያል፦
2 ተሰሎንቄ 2፥17 ራሱ *ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና የወደደን በጸጋም የዘላለምን መጽናናት በጎንም ተስፋ የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን* ልባችሁን *ያጽናኑት* በበጎም ሥራና በቃል ሁሉ *ያጽኑአችሁ*።

“ያጽናኑት” “ያጽኑአችሁ” የሚሉት የብዜት ግስ ኢየሱስ እና እግዚአብሔር ሁለት የተለያዩ ህልውናዎች መሆናቸውን ያሳያል። ብዙ ማቅረብ ይቻል ነበር ግን ይህ በቂ ነው። በሰፈሩት ቁና መስፈር ይሉሃል እንደዚህ ነው።

 ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም