ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.3K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ጣዖት እና አምልኮ

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡

ነጥብ አንድ
“ጣዖት”
በዕብራይስጥ “ኤሊል” אֱלִיל ማለት “ምስል”፣ “ቅርፅ”፣ “ጣዖት” ማለት ሲሆን በግሪክ ደግሞ “ኤዶሎን” εἴδωλον ነው፤ ትርጉሙ ተመሳሳይ የሙሴ አምላክ ለሙሴ “”ለእናንተ ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ፣ የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፣ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም”” ብሎ ተናግሯል፦
ዘሌዋውያን 26፥1 እኔ ያህዌህ አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ #ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።
ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር #የማናቸውንም #ምሳሌ#የተቀረጸውንም #ምስል ለአንተ አታድርግ፤ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም፤

የሙሴ አምላክ ይናገራል እንጂ መልኩን ይህንን ይመስላል ብሎ በወንድ ሽማሌዎች ቅርፅና ምስል ማቅረብ እጅግ ወንጀል ነው፦
ዘዳግም 4፥15-18 ያህዌህ በኮሬብ በእሳት ውስጥ ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ #መልክ ከቶ #አላያችሁምና እጅግ ተጠንቀቁ፤ እንዳትረክሱ፥ #የተቀረጸውን #ምስል #የማናቸውንም ነገር #ምሳሌ#በወንድ ወይም #በሴት #መልክ የተሠራውን፥ በምድር ላይ ያለውን የእንስሳን ሁሉ ምሳሌ፥ በሰማይም በታች የሚበርረውን የወፍን ሁሉ ምሳሌ፥ በምድርም ላይ የሚሽከረከረውን ሁሉ ምሳሌ፥ ከምድርም በታች በውኃ ውስጥ የሚኖረውን የዓሣን ሁሉ #ምሳሌ #እንዳታደርጉ

በተለይ የሥላሴ ሁለቱ አባላት ካልታዩ በሽማግሌ ሰዎች መመሰሉ ምን አይነት ጣራ የነካ ወንጀል ነው? ከእስራኤል ልጆች ዙርያ ያሉት ህዝቦች ጣዖታቶቻቸው የወርቅና የብር፥ የሰው እጅ ሥራ ናቸው። አፍ አላቸው አይናገሩምም፤ ዓይን አላቸው አያዩምም፤ ጆሮ አላቸው አይሰሙምም፤ አፍንጫ አላቸው አያሸትቱምም፤ እጅ አላቸው አይዳሰሱምም፤ እግር አላቸው አይሄዱምም፤ በጕሮሮአቸውም አይናገሩም ነበር፤ ይህ ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉና የሚመኩ የሚያሳፍ ነበር፦
መዝሙር 115፥4-7 የአሕዛብ ጣዖታቶች የወርቅና የብር፥ የሰው እጅ ሥራ ናቸው። አፍ አላቸው አይናገሩምም፤ ዓይን አላቸው አያዩምም፤ ጆሮ አላቸው አይሰሙምም፤ አፍንጫ አላቸው አያሸትቱምም፤ እጅ አላቸው አይዳሰሱምም፤ እግር አላቸው አይሄዱምም፤ በጕሮሮአቸውም አይናገሩም።
መዝሙር 97፥7 #ለተቀረጸ #ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ #በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ፤

የጣኦት አምልኮ በምስል እና በሃውልት ሲሆን ይህንን ድርጊት ሲደረግ ያየ ሰው አቀጣጡ ማንኮታኮትና ማቃጠል ነው፦
ዘዳግም 12፥3 መሠዊያቸውንም አፍርሱ፥ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውንም በእሳት አቃጥሉ፥ የአማልክቶቻቸውንም #የተቀረጹ #ምስሎች #አንከታክቱ
ዘዳግም 7፣25 #የተቀረጸውንም የአምላኮቻቸውን #ምስል #በእሳት #ታቃጥላለህ፤ የተሠራባቸውን ብርና ወርቅ አትመኝ፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመድበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ።

በትንሳኤ ቀንም ቅጣቱ ጀሃነም ነው፦
ራዕይ 21፥8 ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም #ጣዖትንም #የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።

ራዕይ ላይ “ጣዖትን ማምለክ” ተብሎ የተቀመጠው የግሪኩ ቃል “ኤዶልላትሬአ” εἰδωλολατρεία ሲሆን የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ እርሱም፦ “ኤዶሎን” εἴδωλον “ምስል” እና
“ላትሬኦ” λατρεύω “አምልኮ” ነው፤ ይህም ቃል አዲስ ኪዳን ላይ 7 ጊዜ ተጠቅሟል። ይህንን በሚቀጥለው ነጥብ ስለ አምልኮ እንቀጥል፦