ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
አላህ እና ጣዖታት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

መግቢያ
አንድን እምነት ለማመን ቅድሚያ ስለዚያ እምነት በቂ እውቀት ይጠይቃል፤ በመሃይምነት እውር ድንብር የሆነ ፀለምተኛ እምነት መከልተል በኢስላም አይሰራም፦
17፥36 ለአንተም በእርሱ #እውቀት #የሌለህን ነገር #አትከተል

የእውቀት መጀመሪያ ደግሞ የፈጠረንን ፈጣሪያችንን ማወቅ ነው፤ በኢስላም የመጀመሪያው እርምጃ “ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩ” ማመን ሳይሆን “ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩን” ማወቅ ነው፦
47:19 እነሆ “ከአላህ ሌላ አምላክ” لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ አለመኖሩን #እወቅ

“ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ” لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ “ከአሏህ በቀር ሌላ አምላክ የለም” ማለት ነው፣ ጣኦታትን የምንክድበት፣ ከአላህ ሌላ በሃቅ ሊመለክ የሚችል አምላክ አለምኖሩን የምናምንበት ቃለ-ምስክርነት ነው፦
2:256 ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ፡፡ #በጣዖትም “የሚክድ” እና #በአላህ “የሚያምን” ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፡፡
39:17 እነዚያም #ጣዖትን “የሚያመልኳት” يَعْبُدُوهَا ከመሆን የራቁ ወደ #አላህም የዞሩ ለእነርሱ #ብስራት አላቸው፤ ስለዚህ ባሮቼን አብስር ።
43፥26-27 ኢብራሂምም ለአባቱ እና ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ “እኔ ከምታመልኩት ሁሉ #ንጹሕ ነኝ፤ ከዚያ #ከፈጠረኝ #በቀር #አላመልክም እርሱ በእርግጥ ይመራኛልና”።
16:36 በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ “#አላህን #አምልኩ #ጣዖትንም #ራቁ” በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፤

ይህ ቃለ-ምስክርነት በቁርአን “ጠንካራን ዘለበት” ይባላል፦
31:22 እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ ፊቱን وَجْهَهُ ወደ አላህ የሚሰጥም يُسْلِمْ ሰው፣ #ጠንካራ #ገመድ بِالْعُرْوَةِ በእርግጥ ጨበጠ፤ የነገሩም ሁሉ ፍጻሜ ወደ አላህ ነው።
2:256 በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን #ጠንካራ #ዘለበት بِالْعُرْوَةِ በእርግጥ ጨበጠ፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡

ይህ ቃለ-ምስክርነት ሁለት ማዕዘናት አለው፤ አንደኛው ነፍይ ሲሆን ሁለተኛ ኢሥባት ነው፤ ይህንን እሳቤ ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
“ነፍይ”
“ነፍይ” نفي ማለት “አፍራሽ” ሲሆን አሉታዊ ቃል ነው፤ ይህም አሉታዊ ቃል፦ “ላ ኢላሃ” لَا إِلَٰهَ “ሌላ አምላክ የለም” ብለን ስንል ማንኛውንም ጣኦታት ውድቅ የምናደርግበት ነው፤ በቁርአን ከአላህ ውጪ የሚደረግ ባዕድ አምልኮ “ጣኡት” لطَّاغُوتِ ፣ “አውሳን” أَوْثَٰن እና “አስናም” أَصْنَام ይባላሉ፣ “አውሳን” ማለት ከድንጋይ ተቀርፀው አምልኮ ለሚቀርብላቸው ሲሆን፤ “አስናም” ደግሞ ከእንጨት፣ ብር፣ ነሐስ ተሰርተው አምልኮ ለሚቀርብላቸው ነው። እነዚህ ጣኦታት ከዓለማቱ ጌታ ሌላ የሚመለኩ ምንነትና ማንነት ናቸው፤ እጅጉን ከዓለማቱ ጌታ ከአላህ ተለይተው ተቀምጧል፦
1. “ጣኡት”
2:256 #በጣዖትም لطَّاغُوتِ የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፡፡
4:76 እነዚያ ያመኑት ሰዎች፣ በአላህ መንገድ ይጋደላሉ፤ እነዛ የካዱትም #በጣዖት لطَّاغُوتِ መንገድ ይጋደላሉ፤
16:36 በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን አምልኩ #ጣዖትንም لطَّاغُوتِ ራቁ፤ በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፤

2.”አውሳን”
29:17 ከአላህ ሌላ የምታመልኩት #ጣዖታትን أَوْثَانًا ብቻ ነው፤ ውሸትንም ትቀጣጥፋላችሁ፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምታመልኩአቸው ለእናንተ ሲሳይን ሊሰጧችሁ አይችሉም፤
29:25 ኢብራሂም አለም፦ ከአላህ ሌላ #ጣዖታትን أَوْثَانًا አማልክት የያዛችሁት በቅርቢቱ ሕይወት በመካከላችሁ ለመዋደድ ብቻ ነው፤ ከዚያም በትንሣኤ ቀን ከፊላችሁ በከፊሉ ይክዳል፤ ከፊላችሁም ከፊሉን ይረግማል፤ መኖሪያችሁም እሳት ናት፤ ለእናንተም ከረዳቶች ምንም የላችሁም።

3. “አስናም”
6:74 ኢብራሒምም ለአባቱ ለአዘር «#ጣዖታትን أَصْنَامًا አማልክት አድርገህ ትይዛለህን እኔ አንተንም ሕዝቦችህንም በግልጽ መሳሳት ውስጥ ኾናችሁ አያችኋለሁ» ባለ ጊዜ አስታውስ.
21:57 በአላህም ስም እምላለሁ ዟሪዎች ሆናችሁ ከኼዳችሁ በኋላ #ጣዖቶቻችሁን أَصْنَامًا ተንኮል እሰራባቸዋለሁ፣ አለ።
14:35 ኢብራሂምም ባለ ጊዜ አስታውስ ፦ ጌታዬ ሆይ! ይህንን አገር ጸጥተኛ አድርገው፤ እኔንም ልጆቼንም #ጣዖታትን أَصْنَامًا ከማምለክ አርቀን፤