ቅማል
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
41፥6 በላቸው «እኔ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ። ወደ እኔ የሚወረድልኝ፦ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው" ማለትን ነው»። قُلْ إِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ
"ሰው" የሚለው ስም የባሕርይ ስም ነው፥ ሰው ምንነታዊ መሠረት ነው። ሰው ምንነትን"Ontology" የሚያሳይ ሲሆን ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" በምንነት ሰው ብቻ እና ብቻ ናቸው፦

18፥110 በላቸው «እኔ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፡፡ ወደ እኔ የሚወረድልኝ፦ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው" ማለትን ነው»፡፡ قُلْ إِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ
ነቢያችን"ﷺ" ከሰው የዘለለ ምንነት የላቸውም፥ "ኢነማ" أَنَّمَا ማለት "ብቻ" ማለት ሲሆን "ብቻ" የሚለው ገላጭ ቅጽል ነቢያችን"ﷺ" በምንነት መልአክ ወይም አምላክ አለመሆናቸውን የሚያሳይ ነው። "ነቢይ" "መልእክተኛ" "ባሪያ" መገለጫ ሲሆኑ ቀዋሜን ያሳያል፥ "ነቢይ" "መልእክተኛ" "ባሪያ" ማንነታዊ መገለጫ ነው። "ነቢይ" "መልእክተኛ" "ባሪያ" የሚለው ማንነትን"Metaphysics" የሚያሳይ ሲሆን ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" በማንነት "ነቢይ" "መልእክተኛ" "ባሪያ" ናቸው። በምንነት ሰው እንደመሆናቸው መጠን የሰው ባሕርዮት"Attributes" ሁሉ አላቸው፥ ሰው እንደመሆናቸው መጠን የሚበጠር ጠጕር አላቸው። ሰው መሆናቸውን ታሳቢ እና ዋቢ አድርገን ዘይነብ የአሏህን መልእክተኛ"ﷺ" ራስ "ታበጥር" ነበር፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 20 ሐዲስ 153
ዘይነብ እንደተረከችው፦ "የአሏህን መልእክተኛ"ﷺ" ራስ "ታበጥር" ነበር"። عَنْ زَيْنَبَ، أَنَّهَا كَانَتْ تَفْلِي رَأْسَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم
"ታበጥር ነበር" ለሚለው የገባው ቃል "ተፍሊ" تَفْلِي ሲሆን ሥርወ መሠረቱ "ተፈለ" تَفَلَ ነው፥ "ተፈለ" تَفَلَ ማለት "አወዛ" "ዳበሰ" "አበጠረ" ማለት እንጂ "ቀመለ" ማለት አይደለም። "sunnah.com" የሚባል ድረ ገጽ ላይ "ቅማል ትቀምል ነበር"She was picking lice" የሚለው እልም ያለ ስህተት ነው፥ በስም መደብ "ቅማል" ሆነ በግሥ መደብ "መቅመል" የሚል ዐረቢኛው ላይ የለም። "ቀምል" قَمْل የሚለው ቃል "ቀመለ" قَمَلَ ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ቅማል"Lice" ማለት ነው፥ በስም መደብ "ቀምል" قَمْل የሚል ቃል ሆነ በግሥ መደብ "ቀመለ" قَمَلَ የሚል ቃል ሐዲሱ ላይ የለም። ቅማል ቢኖር ኖሮ "ቀምል" قَمْل የሚል ቃል በግልጽ ይቀመጥ ነበር፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 64 ሐዲስ 230
ከዕብ ኢብኑ ዑጅራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "በሑደይቢያህ ስምምነት ጊዜ ወደ እኔ "ነቢዩ"ﷺ" ሲመጡ ቅማል ፊቴ ላይ ይወርድ ነበር፥ እርሳቸውም፦ "የራስክ ቅማል ይረብሹካል? አሉ። እኔም፦ "አዎ" አልኩኝ፥ እርሳቸውም፦ "ተላጭ" አሉኝ"። عَنْ كَعْبِ بْنِ عُجْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ أَتَى عَلَىَّ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم زَمَنَ الْحُدَيْبِيَةِ، وَالْقَمْلُ يَتَنَاثَرُ عَلَى وَجْهِي فَقَالَ {أَيُؤْذِيكَ هَوَامُّ رَأْسِكَ}. قُلْتُ نَعَمْ. قَالَ " فَاحْلِقْ ".
እዚህ ሐዲስ ላይ "ቅማል" ለሚለው የገባው ቃል "ቀምል" قَمْل እንደሆነ ልብ አድርግ! በሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 20 ሐዲስ 153 ላይ "ታበጥር ነበር"She was combing" ብለው የተረጎሙ የእንግሊዝኛ መተርጉማን መኖራቸው እንዳለ ሆኖ የእንግሊዝኛ መተርጉማን ብዙ ጊዜ ይሳሳታሉ። ለምሳሌ፦ "ላ ኢላሃ ኢለል ሏህ" لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ ማለት "ከአሏህ በቀር አምላክ የለም"There is no god but Allah" የሚል ሆኖ ሳለ በእንግሊዘኛው ላይ "ከነቢዩ በቀር አምላክ የለም"There is no god but Prophet" ብለው ተርጉመውታል፦
Al-Adab Al-Mufrad Book 31, Hadith 97
'There is no god but Allah, the Immense, the Forbearing. ""There is no god but Prophet"", the Lord of the heavens and the earth and the Lord of the Immense Throne.'" عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ قَالَ: كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم يَدْعُو عِنْدَ الْكَرْبِ: لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ الْعَظِيمُ الْحَلِيمُ، لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ رَبُّ السَّمَاوَاتِ وَالأَرْضِ وَرَبِّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ.

"Sunnah.com" የሚባለው ድረ ገጽ መሳሳታቸው የምታውቁት ሌላ ሐዲስ ላይ እራሷ ዘይነብ በመጀመርያ መደብ "የአሏህ መልእክተኛን"ﷺ" ጠጕር አበጥር ነበር"I used to comb the hair of the Messenger of Allah" ማለቷት በትክክል ማስቀመጣቸው ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1 ሐዲስ 206
ዘይነብ ቢንት ጀሕሽ እንደተረከችው፦ "የነሐስ ገንዳ ነበራት፥ እንዲህም አለች፦ "በገንዳ ውስጥ የአሏህን መልእክተኛ"ﷺ" ጠጕር "አበጥር" ነበር"። عَنْ زَيْنَبَ بِنْتِ جَحْشٍ، أَنَّهُ كَانَ لَهَا مِخْضَبٌ مِنْ صُفْرٍ قَالَتْ فَكُنْتُ أُرَجِّلُ رَأْسَ رَسُولِ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ فِيهِ .
"ተፍሊ" تَفْلِي ማለት "ታበጥር" ሆኖ ሳለ "ትቀምል" በሚል የሚፈታ ቢሆን ኖሮ ኡሙ ሒራም የእርሳቸውን እራስ "ታበጥር ነበር" ለሚለው ቃል "She was picking lice" ብለው ያስቀምጡ ነበር፦
አል አደቡል ሙፍረድ መጽሐፍ 41 ሐዲስ 1
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" የዑባዳህ ኢብኑ አስ ሷሚት ያገባትን የሚልሐምን ልጅ ኡሙ ሒራምን ይጎበኙ ነበር፥ እርሷ እርሳቸው ትመግበው እና እራሳቸውን "ታበጥር" ነበር"። أَنَّهُ سَمِعَ أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ يَقُولُ: كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم يَدْخُلُ عَلَى أُمِّ حَرَامِ ابْنَةِ مِلْحَانَ، فَتُطْعِمُهُ، وَكَانَتْ تَحْتَ عُبَادَةَ بْنِ الصَّامِتِ، فَأَطْعَمَتْهُ وَجَعَلَتْ تَفْلِي رَأْسَهُ.
"ታበጥር ነበር" ለሚለው የገባው ቃል በተመሳሳይ "ተፍሊ" تَفْلِي ሆኖ ሳለ "ትቀመል ነበር"She was picking lice" በሚል ለምን አልተረጎሙት? እናታችን ዓኢሻህ በተመሳሳይ የነቢያችንን"ﷺ" ጠጕር ታበጥር ነበር፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 6 ሐዲስ 2
ከዕብ ኢብኑ ዑጅራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "በወር አበባ ላይ ሆኜ የአሏህን መልእክተኛ"ﷺ" ጠጕር "አበጥር" ነበር"። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أُرَجِّلُ رَأْسَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَأَنَا حَائِضٌ.
ቅማል በሰው አካል ላይ በንጽሕና ጉድለት አሊያም በልብስ መሸጋገር የሚፈጠር የተባይ ዓይነት ነው፥ ቅማል፣ ቅጫም፣ ፎሮፎር፣ ቆሮቆር ከምንነት ጋር የተያያዘ እንጂ በአንድ ነቢይ ላይ ግልጠተ መለኮቱን አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር አይደለም።
አንድ ነቢይ ግን የአምላክን መሠረታዊ ሕግ የሚጻረር ከሆነ የማንነት ጉዳይ ነውና ነቢይነቱ ጥያቄ ሊገባ ይችላል፥ ለምሳሌ፦ ዳዊት ነቢይ ሆኖ ሳለ ከሰይጣን መልእክት ተቀብሎ አስተናግዷል። ፈጣሪ ሳያዘው "የሚናገር ነቢይ እርሱ ይገደል" የሚል ትእዛዝ እያለ አልተገደለም፦
1ኛ ዜና 21፥1 ሰይጣንም በእስራኤል ላይ ተነሣ፥ እስራኤልንም ይቈጥር ዘንድ ዳዊትን አንቀሳቀሰው።
ዘዳግም 18፥20 ነገር ግን ይናገር ዘንድ ያላዘዝሁትን በስሜ በድፍረት የሚናገር ወይም በሌላ አማልክት ስም የሚናገር ነቢይ እርሱ ይገደል።
ዳዊት ነቢይ ሆኖ ሳለ የሰው ሚስት የኦርዮን ሚስት ደፍሯል፥ የደፈረ ሰው "ይገደል" የሚል ትእዛዝ እያለ አልተገደለም፦
2ኛ ሳሙኤል 12፥10 ስለዚህም አቃልለኸኛልና፥ የኬጢያዊውንም የኦርዮን ሚስት ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃልና ለዘላለም ከቤትህ ሰይፍ አይርቅም።
ዘዳግም 22፥25 ነገር ግን ሰው የታጨችውን ልጃገረድ በሜዳ ቢያገኛት፥ በግድ አሸንፎም ቢደርስባት፥ ያ የደረሰባት ሰው ብቻውን ይገደል።
ዳዊት ነቢይ ሆኖ ሳለ ሰውን ያለ ወንጀሉ ኦርዮንን ገሏል፥ "ሰውንም እስኪሞት ድረስ የሚመታ ፈጽሞ ይገደል" የሚል ትእዛዝ እያለ አልተገደለም፦
ዘሌዋውያን 24፥17 ሰውንም እስኪሞት ድረስ የሚመታ ፈጽሞ ይገደል።
2ኛ ሳሙኤል 12፥9 ኬጢያዊውን ኦርዮን በሰይፍ መትተሃል፥ ሚስቱንም ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃል፤ እርሱንም በአሞን ልጆች ሰይፍ ገድለሃል።
መልሳቸው "ዳዊት ሰው ነው፥ ሊሳሳት ይችላል። ምንም ወንጀል ቢሠራ ፈጣሪ እስከመረጠው ድረስ ነቢይነቱ አይፋቅም" የሚል ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 2፥30 ነቢይ ስለ ሆነ ከወገቡም ፍሬ በዙፋኑ ያስቀምጥ ዘንድ እግዚአብሔር መሐላ እንደ ማለለት ስለ አወቀ።
"ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ" ነገር ነው፥ የእኛን ነቢይ ግን በተገኘው አጋጣሚ ጥንቡርኩሳቸው ለማውጣት ደፋ ቀና ስትሉ አታፍሩም? ጦሳቸውን እና ጥንቡሳሳቸውን ውሰዱልን። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም

ወደ ቻናሉ የምትገቡ አዳዲስ አንባቢያን በቅድሚያ እንኳን ደህና መጣችሁ! ለሃይማኖታዊ ንጽጽር ከላይ ጀምሩ፦ https://tttttt.me/Wahidcom/18
ሕይወትን መስጠት
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
3፥49 "በአሏህም ፈቃድ ዕውር ኾኖ የተወለደን፤ ለምጸኛንም አድናለሁ፡፡ ሙታንንም አስነሳለሁ"፡፡ وَأُبْرِئُ الْأَكْمَهَ وَالْأَبْرَصَ وَأُحْيِي الْمَوْتَىٰ بِإِذْنِ اللَّهِ ۖ
የናዝሬቱ ኢየሱስ በአምላክ እና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራ እና በቃል ብርቱ ነቢይ ነበር፥ ኢየሱስ አምላክ ሲያደርግ እያየ የሚያደርግ እንጂ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፦
ሉቃስ 24፥19 እርሱም፦ ይህ ምንድር ነው? አላቸው። እነርሱም እንዲህ አሉት፦ “በአምላክ እና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ”።
ዮሐንስ 5፥19 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ፥ እንዲህም አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፥ ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና።
"ያ" የሚለውን የሩቅ አመልካችን ተውላጠ ስም አብ ለኢየሱስ ለማሳየት የሚያደርገውን ሥራ ያመላክታል፥ “ይህን” የሚለው የቅርብ አመልካችን ተውላጠ ስም “ያ” የሚለውን ተክቶ የመጣ ሲሆን አብ ለወልድ እንዲያደርግ የሚያሳየውን ሥራ ያመላክታል፦
ዮሐንስ 14፥31 አብም እንዳዘዘኝ እንዲሁ አደርጋለሁ።
አንድ አምላክነት ያለው ማንነት ምን መሥራት እንዳለበት ሌላ ማንነት እንዴት ያሳየዋል? አብ ወልድ ምን ማድረግ እንዳለበት ያሳየዋል፦
ዮሐንስ 5፥20 አብ ወልድን ይወዳልና፥ የሚያደርገውንም ሁሉ ያሳየዋል፤ እናንተም ትደነቁ ዘንድ ከዚህ የሚበልጥ ሥራ ያሳየዋል።
ኢየሱስ የሚያደርገውን ሁሉ አብ እያሳየው ብቻ ነው፥ “ከዚህ የሚበልጥ ሥራ ያሳየዋል” ሲል የሚሠራውን ሥራ ፈጣሪ እያሳየው ያደርጋል ማለት ነው። ከፈጣሪ እያየ የሚሠራ ማንነት እራሱ ፈጣሪ ከሆነ አንዱ የሚያሳይ ሁለተኛው እያየ የሚኮርጅ ሁለት ፈጣሪ ይሆን ነበር። ወልድ ምን ምን ማድረግ እንዳለበት አብ ያሳየዋል ማለት ወልድ ሙታንን እንዲያስነሳ፣ ለምጻም እንዲያነጻ፣ ሽባ እንዲተረትር መመሪያ፣ ሥልጣን እና ኃይል ይሰጠዋል ማለት ነው፥ ለምሳሌ ፈሪሳውያን በሰይጧን ዘንድ ያዩት ያደርጋሉ ማለት ሰይጧን መመሪያ እየሰጣቸው ያደርጋሉ ማለት እንደሆነ ሁሉ ኢየሱስም በአብ ዘንድ ያየውን ያደርጋል ማለት አብ መመሪያ እየሰጠው ያደርጋል ማለት ነው፦
ዮሐንስ 8፥38 እኔ በአባቴ ዘንድ ያየሁትን እናገራለሁ፤ እናንተም ደግሞ በአባታችሁ ዘንድ ያያችሁትን ታደርጋላችሁ።
ኢየሱስ ተአምር እንዲሠራ የጌታ ኃይል ሆኖሎት እንጂ ከራሱ አንዳች ሊያደርግ አይቻለውም። ኢየሱስ ከራሱ ምንም ማድረግ ካልቻለ ሁሉን ቻይ አምላክ አይደለም፦
ሉቃስ 5፥17 እርሱም እንዲፈውስ የጌታ ኃይል ሆነለት።
ዮሐንስ 5፥30 እኔ “ከ”-“ራሴ” አንዳች ላደርግ አይቻለኝም።
“እኔ” የሚለው ባለቤት ተውላጠ ስም እና "እራሴ" የሚለው ድርብ ተውላጠ ስም የኢየሱስን ሙሉ "እኔነትን" እንጂ ሥጋን አያሳይም፥ ሥጋ ብቻውን ማንነት ስላልሆነ “እኔ” እና "እራሴ" ሰለማይል ኢየሱስ ከማንነቱ ምንም ማድረግ አይችልም። ኢየሱስ በአምላክ የተደገፈ ጥገኛ ባሪያ ነው፦
ኢሳይያስ 42፥1 እነሆ "ደግፌ የያዝሁት" ባሪያዬ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት "ምርጤ፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፥ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል።
መንፈሱን ያሳረፈበት ተአምር እንዲሠራ ነው። ጭራሽ ኢየሱስ የሚያደርገው ሥራ በፈጣሪ ስም ሲሆን እርሱ ነቢይ ስለመሆኑ የሚመሰክር ነው፦
ዮሐንስ 10፥25 እኔ በአባቴ ስም የማደርገው ሥራ ስለ እኔ ይመሰክራል።
ዮሐንስ 5፥36 አብ ልፈጽመው የሰጠኝ ሥራ ይህ የማደርገው ሥራ አብ እንደ ላከኝ ስለ እኔ ይመሰክራልና።
ኢየሱስ የሚያደርገው ሥራ ሁሉ እርሱ መልእክተኛ ስለመሆኑ ምስክር እንዲሆን በስጦታ ያገኘው ስለሆነ “አብ ልፈጽመው የሰጠኝ ሥራ” በማለት እንቅጩን ፍርጥ አድርጎ ይናገራል፦
ዮሐንስ 17፥4 እኔ ላደርገው "የሰጠኸኝን ሥራ" ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤
“የሰጠኸኝን ሥራ” የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! ሁሉን ማድረግ የሚችል ማንነት ከሌላ ማንነት የሚሠራበትን ዐቅም በስጦታ በፍጹም አይቀበልም፥ ቅሉ እና ጥቅሉ ግን አብ እንዳዘዘው ኢየሱስ ያደርጋል። ኢየሱስ ሲያደርግ የነበረውን ሥራ ሙት ማስነሳት፣ ሽባ መተርተር፣ ዕውር ማብራት ወዘተ በእርሱ የሚያምን ሰው ሊያደርገው ይችላል፥ እረ ኢየሱስ ካደረገው በላይ የሚበልጥ ያደርጋል፦
ዮሐንስ 14፥13 እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፥ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል።
እውነት ኢየሱስ ሁሉን ቻይ አምላክ ቢሆን ኖሮ ሁሉን የሚችል አምላክ ሊያደርግ የሚችለውን ሰው ሊያደርግ ይችላልን? ከሁሉን የሚችል አምላክ በላይ የሚበልጥ ሥራ ሊሠራ ይችላልን? ነገሩ ኢየሱስ፦ "የሚሳናችሁም ነገር የለም" ብሏል፦
ማቴዎስ 17፥20 የሚሳናችሁም ነገር የለም።

ስለዚህ ኢየሱስ የሚያደርገው ሥራ የአምላክነት ሥራ ሳይሆን በጸጋ እና በስጦታ እንዲሥራ የታዘዘው ሥራ ነው፥ ምክንያቱም ኢየሱስ ከሚያደርገው የሚበልጥ ተከታዮቹ ለማድረግ የሚሳናቸው ምንም ነገር እንደሌለ ተናግሯልና። ኢየሱስ ሙታንን ብዙ ጊዜ ማስነሳቱ በራሱ ለትንሣኤ ዘጉባኤ ናሙና ነው፥ እርሱ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያትም ሙታንን አስነስተዋል፦
ማቴዎስ 10፥8 ድውዮችን ፈውሱ፣ "ሙታንን አስነሡ"፣ ለምጻሞችን አንጹ፣ አጋንንትን አውጡ፣ በከንቱ ተቀበላችሁ፥ በከንቱ ስጡ።
"ሙታንን አስነሡ" የሚለው ይሰመርበት! በኢየሱስ ነቢይነት የሚያምኑት ሐዋርያት ኢየሱስ የሚያደርገውን አድርገዋል፦
ዮሐንስ 14፥13 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፥ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል።
ኢየሱስ ሲያደርግ የነበረው ሥራ ለምጻም ማንጻት፣ ድውይ መፈወስ፣ ሙት ማስነሳት ወዘተ ነው፥ “ማኅየዊ” ማለትም “አስነሺ” “ሕይወት ሰጪ” ማለት ነው፦
ዮሐንስ 5፥21 አብ ሙታንን እንደሚያነሣ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው፥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል።
ወልድ "ሕይወት ይሰጣል" ማለት በዚህ ዐውድ "ሙታን ያስነሳል" ማለት ነው። ኢየሱስ፦ "ከደቀ መዛሙርቴ አንዱን እልክላችኃለው፥ ይፈውሳችኃል ሕይወት ይሰጣችኃል" ብሏል፦
"ኢየሱስም፦ "ከደቀ መዛሙርቴ አንዱን እልክላችኃለው፥ ይፈውሳችኃል ሕይወት ይሰጣችኃል" አለ"።
Church History (Eusebius) Book I(1) Chapter 13 Number 14
ኢየሱስ "ከደቀ መዛሙርቴ አንዱን እልክላችኃለው፥ ይፈውሳችኃል ሕይወት ይሰጣችኃል" የሚለው ቃል አራቱ ወንጌላት ላይ ያልሰፈረ ተብሎ የተዘገበ እውነት ነው፥ ሙግቱን እናጥብበውና ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ "ሕይወትን ይሰጣል" ሲባል "ሙት ያስነሳል" ከሆነ ልክ እንደ ኢየሱስ የሐዋርያው አለቃ የሆነው ጴጥሮስ ሙት አስነስቷል፦
ሐዋርያት 9፥40 ጴጥሮስም ሁሉን ወደ ውጭ አስወጥቶ ተንበርክኮም ጸለየ፥ ወደ ሬሳውም ዘወር ብሎ፦ ጣቢታ ሆይ፥ ተነሺ አላት። እርስዋም ዓይኖችዋን ከፈተች ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች።
ኢየሱስ "ሕይወት ይሰጣል" ብላችሁ ጮቤ ስትረግጡ የነበራችሁ ሰዎች የጴጥሮስን ሕይወት መስጠት ስትሰሙ ምን ይውጣችሁ ይሆን? በእርግጥ ኢየሱስ በአሏህ ፈቃድ ሙታንን አስነስቷል፦
3፥49 "በአሏህም ፈቃድ ዕውር ኾኖ የተወለደን፤ ለምጸኛንም አድናለሁ፡፡ ሙታንንም አስነሳለሁ"፡፡ وَأُبْرِئُ الْأَكْمَهَ وَالْأَبْرَصَ وَأُحْيِي الْمَوْتَىٰ بِإِذْنِ اللَّهِ ۖ
ክርስቲያኖች ሆይ! ኢየሱስ ያመለከው አምላክ አምልካችሁ ለመዳን ወደ ዲኑል ኢሥላም እንድትመጡ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
Photo
ወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር
ማኅበራችን ወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር በርካታ ሥራዎችን እየከወነ የሚገኝ ማኅበር ነው። ለአብነት፦
● የኢሥላምን ጥንፍፍ መልእክት ለሙሥሊሙ እና ሙሥሊም ላልሆነው ማኅበረሰብ በተለያዩ መዳረሻ መንገዶች ተደራሽ ማድረግ፣
● የዳዕዋ ክህሎት ስልጠና መስጠት፣
● ሙሥሊም ያልሆኑ ወገኖች ስለ ኢሥላም ያላቸውን ጥያቄዎች የሚያቀርቡበትን መድረክ ማመቻቸት እና አጥጋቢ ምላሾችን መስጠት፣
● የሃይማኖት ንጽጽር ኮርሶችን መስጠት፣
● አዳዲስ ሠለምቴዎችን ተቀብሎ መሠረታዊ የኢሥላም ትምህርቶችን መስጠት፣
● ከቤታቸው ለሚባረሩ ሠለምቴ ወንድሞች እና እኅቶች ማረፊያ ቦታ አዘጋጅቶ መቀበል፣
● ከቤት የሚባረሩ ሠለምቴዎችን ከተቀበለ በኋላ ለእነርሱ መሠረታዊ ፍላጎቶችን (ቤት፣ ቀለብ እና ትራንስፖርት) ማሟላት እና ክትትል ማድረግ፣
● ለሠለምቴዎች ማረፊያ፣ ዲናቸውን መማርያ እና ማስተዳደሪያ የሚሆን ሕንጻ መገንባት፣
● የኢሥላምን መልእክት የሚያንጸባርቁ መጻሕፍትን መጻፍ እና ማሳተም፣
እዚህ ማኅበር አባል ለመሆን እና በአሳብ፣ በጉልበት፣ በገንዘብ ለማገዝ እንመዘግባለን። የአባልነት መስፈርቶች፦
1ኛ. ሙሥሊም መሆን፣
2ኛ. ኢኽላስ፣
3ኛ. ቆራጥነት፣
4ኛ. ታማኝነት፣
5ኛ. የዲን ወኔ እና የኩፍር ኃይላት ጥቃት ቁጭት ያለው ሙሥሊም መሆን ብቻ እና ብቻ ነው።
ሠለምቴዎችን በወራዊ መዋጮ በቋሚነት መደገፍ የምትፈልጉ እና የበለጠ መረጃ ለማግኘት ሙሥሊም ወንድሞች እና እኅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አድሚናት በቴሌ ግራም ያግኙ፦
1. ወንድም አቡ ኑዓይም፦ https://tttttt.me/arhmanu
2. እኅት ዘሃራ፦ https://tttttt.me/Zhara_mustefa
3. ወንድም ሑሤይን፦ https://tttttt.me/Hussu707
4. እኅት ሐዊ፦ https://tttttt.me/hawin922
5. ወንድም ዐብዱ፦ https://tttttt.me/Abi_Abik
6. እኅት ጀሙቲ፦ https://tttttt.me/Jemuti12
7. ወንድም ኢብኑ ረሻድ፦ https://tttttt.me/IbunReshed
8.እኅት እናት፦ https://tttttt.me/enattenat
9. ወንድም እስሚዞ፦ https://tttttt.me/Esmitiz_hubi
10. እኅት መርየም፦ https://tttttt.me/J_y_A_M
11. ኡሥታዝ አቡ ሩመይሳ፦ https://tttttt.me/aburumaisa037
12. እኅት ሹሹ፦ https://tttttt.me/umusara45
13. ወንድም ፈይሰል፦ https://tttttt.me/feyselsan
14. እኅት ፈቲ፦ https://tttttt.me/Feti_12
15. ወንድም ሙከሚል፦ https://tttttt.me/Mukamil_Hussan
16. እኅት አሲያ፦ https://tttttt.me/Ccccftb3

የኢየሱስ ጌታ
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል "ጌታዬን እና ጌታችሁን አሏህን አምልኩ" ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَا أَمَرْتَنِي بِهِ أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ
በኢሥላም አስተምህሮት የኢየሱስ ጌታ አሏህ ነው፥ ኢየሱስ ከአሏህ የተሰጠው ተልእኮ "ጌታዬን እና ጌታችሁን አሏህን አምልኩ" የሚል ነበር፦

በባይብል ደግሞ "ኩሪዮስ" κύριος ማለት "ጌታ" ማለት ሲሆን ለአንዱ ፈጣሪ የሚውል ቢሆንም ለፍጡራን ክብር እና ማዕረግ፣ እልቅና እና ልዕልና፣ ሥልጣን እና ሹመት ለማመልከት ይገባል፥ ለምሳሌ፦ ሣራ ለአብርሃም፦ "ጌታ" ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት፦
1 ጴጥሮስ 3፥6 እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም፦ "ጌታ" ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት። ὡς Σάρρα ὑπήκουσεν τῷ Ἀβραάμ, κύριον αὐτὸν καλοῦσα·
እዚህ አንቀጽ ላይ "ጌታ" ለሚለው የገባው ቃል በግሪክ ኮይኔ "ኩሪዮስ" κύριος ሲሆን ሳራ አብርሃምን "ጌታዬ" ስትለው የገባው ቃል "አዶኒ" אדֹנִ֗י ነው፦
ዘፍጥረት18፥12 ሣራም በልብዋ እንዲህ ስትል ሳቀች። ካረጀሁ በኋላ በውኑ ፍትወት ይሆንልኛልን? "ጌታዬም" ፈጽሞ ሸምግሎአል። וַתִּצְחַ֥ק שָׂרָ֖ה בְּקִרְבָּ֣הּ לֵאמֹ֑ר אַחֲרֵ֤י בְלֹתִי֙ הָֽיְתָה־לִּ֣י עֶדְנָ֔ה וַֽאדֹנִ֖י זָקֵֽן׃
እዚህ አንቀጽ ላይ ሳራ አብርሃም በዕብራይስጥ "አዶኒ" אדֹנִ֗י ስትለው "አዶኒ" אדֹנִ֗י የሚለው ለፍጡራን የሚውል ማዕረግ ነው። የኢየሱስ ጌትነት በመደረግ ላይ የተመሠረተ መነሾ እና ጅማሮ ያለው ስለሆነ የባሕርይ ጌትነት በፍጹም አይደለም፦
የሐዋርያት ሥራ 2፥36 ኢየሱስን አምላክ ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ። ἀσφαλῶς οὖν γινωσκέτω πᾶς οἶκος Ἰσραὴλ ὅτι καὶ Κύριον αὐτὸν καὶ Χριστὸν ἐποίησεν ὁ Θεός, τοῦτον τὸν Ἰησοῦν.
እዚህ አንቀጽ ላይ "አምላክ" ባለቤት ሲሆን "ኢየሱስ" ተሳቢ ነው፥ በባለቤት እና በተሳቢ መካከል "እንዳደረገው" የሚል ተሻጋሪ ግሥ አለ። ጌታ አድራጊው አንዱ አምላክ ሲሆን ጌታ ተደራጊው ኢየሱስ ነው፥ አምላክ ኢየሱስን ጌታ ካረደገው የኢየሱስ ጌትነት መነሾ እና ጅማሮ ያለው ስለሆነ እና ጌታ ከመደረጉ በፊት በባዶነት ስለሚቀደም ጌትነቱ ክብር እና ማዕረግ፣ እልቅና እና ልዕልና፣ ሥልጣን እና ሹመት ያሳያል። ምክንያቱም "እንዳደረገው" ለሚለው የገባው ቃል "ኤፓዬሴን" ἐποίησεν ሲሆን ከዚህ በፊት ያልሆነ ወደ መሆን በመደረግ ለመጣ ነገር በግሪክ ኮይኔ ይጠቀምበታል፦
ዘፍጥረት 45፥9 "አምላክ" በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ "ጌታ" አደረገኝ። ἐποίησέ με ὁ Θεὸς κύριον πάσης γῆς Αἰγύπτου·
የግሪክ ሰፕቱአጀንት ዮሴፍ "አደረገኝ" ላለበት የተጠቀመበት ቃል "ኤፓዬሴ" ἐποίησέ እንደሆነ ልብ አድርግ! አምላክ ዮሴፍን ጌታ ማድረጉ ክብር እና ማዕረግ፣ እልቅና እና ልዕልና፣ ሥልጣን እና ሹመት ያሳያል ከተባለ እንግዲያውስ አምላክ ኢየሱስን ጌታ ማድረጉ ክብር እና ማዕረግ፣ እልቅና እና ልዕልና፣ ሥልጣን እና ሹመት ያሳያል። "አዶናይ" אֲדֹנָ֥י ማለት "ጌታዬ" ማለት ነው፥ መሢሑ በትንቢት መነጽር ያህዌህን "ጌታዬ" ብሎታል፦
ኢሳይያስ 61፥1 "የ-"ጌታዬ" የያህዌህ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ያህዌህ ቀብቶኛልና። ר֛וּחַ אֲדֹנָ֥י יְהוִ֖ה עָלָ֑י יַ֡עַן מָשַׁח֩ יְהוָ֨ה אֹתִ֜י לְבַשֵּׂ֣ר עֲנָוִ֗ים
እዚህ አንቀጽ ላይ "አዶናይ" אֲדֹנָ֥י ማለት "ጌታዬ" ማለት ከሆነ ኢየሱስ አምላኩን "ጌታዬ" ማለቱ በራሱ የሚገዛለት ጌታ እንዳለው አመላካች ነው፥ ኢየሱስ አንድም ጊዜ "አዶናይ" אֲדֹנָ֥י አልተባለም። ኢየሱስ በትንቢት መነጽር የፈጠረው ጌታ እንዳለው ተናግሯል፦
ምሳሌ 8፥22 "ጌታ" በቀድሞ ተግባሩ "ፈጠረኝ"። κύριος ἔκτισέν με ἀρχὴν ὁδῶν αὐτοῦ εἰς ἔργα αὐτοῦ
በግሪክ ሰፕቱአጀንት እዚህ አንቀጽ ላይ "ፈጠረኝ" ለሚለው የገባው ቃል "ኤክቲሴን ሜ" ἔκτισέν με ሲሆን፣ በዕብራይስጥ ማሶሬት "ካናኒ" קָ֭נָנִי ሲሆን፣ በግዕዝ ደግሞ "ፈጠረኒ" ነው፥ ቀደምት የቤተክርስቲያን አበው ምሳሌ 8፥22 ላይ "ፈጠረኝ" የሚለው ኢየሱስ እንደሆነ ያለምንም ልዩነት በወጥ ፍሰት አብራርተዋል። ኢየሱስን የፈጠረ ጌታ ጌትነቱ የባሕርይ ሲሆን የዓለማቱ ጌታ ነው፥ በጌትነቱ ላይ ባርነት የሌለበት ይህ ጌታ ኢየሱስን "ባሪያዬ" ይለዋል፦
ኢሳይያስ 42፥1 እነሆ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፥ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል። הֵ֤ן עַבְדִּי֙ אֶתְמָךְ־בֹּ֔ו בְּחִירִ֖י רָצְתָ֣ה נַפְשִׁ֑י נָתַ֤תִּי רוּחִי֙ עָלָ֔יו מִשְׁפָּ֖ט לַגֹּויִ֥ם יֹוצִֽיא׃

በጌትነቱ ላይ ባርነት ያለበት ኢየሱስ የባሕርይ ጌታ አለመሆኑን ይህ ጥቅስ በቂ አስረጅ ነበር። ማርያም እና ዮሴፍ ኢየሱስ በጌታው ፊት ሊያቆሙት ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት፦
ሉቃስ 2፥24 "በጌታ ፊት ሊያቆሙት"፥ በጌታም ሕግ፦ “ሁለት ዋሊያ ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች፡” እንደ ተባለ፥ መሥዋዕት ሊያቀርቡ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት።
"በጌታ ፊት ሊያቆሙት" የሚለው ይሰመርበት! የተወሰደው ኢየሱስ እና ጌታው በማንነት ሆነ በምንነት ሁለት ለየቅል የሆኑ ሃልዎት ናቸው፥ "የባሕርይ ጌታ" ማለት ጌትነቱ በራሱ የተብቃቃ እና ጌትነቱ የራሱ ገንዘቡ የሆነ ማለት ነው። ይህ የኢየሱስ ጌታ እና አምላክ አንዱ ጌታ አምላክ ነው፦
ዘዳግም 6፥4 እስራኤል ሆይ ስማ! አምላካችን ያህዌህ አንድ ያህዌህ ነው። שְׁמַע, יִשְׂרָאֵל: יְהוָה אֱלֹהֵינוּ, יְהוָה אֶחָד.
ማርቆስ 12፥29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ “ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፦ "እስራኤል ሆይ ስማ! ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው"። ἀπεκρίθη ὁ Ἰησοῦς ὅτι Πρώτη ἐστίν Ἄκουε, Ἰσραήλ, Κύριος ὁ Θεὸς ἡμῶν Κύριος εἷς ἐστιν,
እዚህ አንቀጽ ሆነ ዘዳግም 6፥4 ግሪክ ሰፕቱአጀት ላይ "አንድ" ለሚል የገባው ቃል "ሄይስ" εἷς ሲሆን ለአንድ ማንነት የሚል አንስታይ መደብ ነው። ከ 130 እስከ 202 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው ኢራንዮስ ዘልዮን"Irenaeus of Lyon" የፖሊካርፐስ ዘሰርምኔስ ተማሪ ሲሆን "እስራኤል ሆይ ስማ! ጌታ አምላካችን አንድ አምላክ ነው" የተባለው የኢየሱስ አባት እንደሆነ በግልጽ አስቀምጧል፦
"ኦሪት ያወጀው፣ ነቢያት ያስተማሩት፣ እንዲሁ ክርስቶስ አባቱ እንደሆነ የመሰከረለት፦ "እስራኤል ሆይ ስማ! ጌታ አምላካችን አንድ አምላክ ነው" የሚል አይደለምን?" ዘዳግም 6፥4 ።
Against Heresies (St. Irenaeus) Book V(5) Chapter 11 Number 1
የአይሁድ ሕግ ዐዋቂ ኢየሱስን "አንድ ነው ከእርሱም በቀር ሌላ የለም" ብለህ መልካም ተናገር በማለት የኢየሱስ ተልእኮ ከጥንት ነቢያት የተለየ እንዳልሆነ አረጋግጦአል፦
ማርቆስ 12፥32 ጻፊውም፦ “መልካም ነው፥ መምህር ሆይ! "አንድ ነው ከእርሱም በቀር ሌላ የለም" ብለህ በእውነት ተናገርህ።
አሁንም እዚህ አንቀጽ "አንድ" ለሚል የገባው ቃል "ሄይስ" εἷς ሲሆን ይህ አንዱ ጌታ አምላክ ለኢየሱስ የአባቱን የዳዊትን ዙፋን የሚሰጥ ነው፦
ሉቃስ 1፥32 ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል።
ሰጪ አንዱ ጌታ አምላክ ባለቤት ሲሆን ተሰጪ ማርያም የፀነሰችው ወንድ ልጅ ተሳቢ ነው፥ "ይሰጠዋል" የሚል ተሻጋሪ ግሥ"Transitive Verb" በባለቤት እና በተሳቢ መካከል መኖሩ ጌታ አምላክን ከወንድ ልጅ በምንነት ሆነ በማንነት ይለየዋል፦
ራእይ 21፥22 ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እና በጉ መቅደስዋ ናቸው።
ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ አብ እና በጉ መሢሑ "እና" በሚል መስተጻምር መለየታቸው እና "ናቸው" በሚል የብዜት አያያዥ ግሥ መቀመጣቸው የኢየሱስ ጌታ እና አምላክ ከኢየሱስ በሰዋስው ተለይቶ ተቀምጧል፦
ማቴዎስ 4፥10 ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ።
ኢየሱስ ጠቅሶ እና አጣቅሶ "እርሱንም ብቻ አምልክ" ብሎ ካስተማረ "እርሱ" ተብሎ በነጠላ ተውላጠ ስም የተቀመጠውን ጌታ አምላክ ማምለክ ከጀሀነም ዘውታሪነት ነጻ ያወጣል። እንግዲህ ኢየሱስ ጌታ ካለው፣ ለጌታው ባሪያ ከሆነ፣ ጌትነቱ በመደረግ ላይ የተመሠረተ መነሻ እና ጅማሮ ካለው እንግዲያውስ በጌትነቱ ባርነት የሌለበትን የባሕርይ ጌታ የሆነውን አሏህን በብቸኝነት አምልኩ! እንደ ኢየሱስ ለጌታችን ባሪያ መሆን ምንኛ መታደል ነው? ስለዚህ የኢየሱስን ጌታ እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። ጌታችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ማኢዳህ
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
5፥115 አሏህ፡- «እኔ ማዕድዋን በእናንተ ላይ አውራጅዋ ነኝ፡፡ በኋላም ከእናንተ የሚክድ ሰው እኔ ከዓለማት አንድንም የማልቀጣውን ቅጣት እቀጣዋለሁ» አለ፡፡ قَالَ اللَّهُ إِنِّي مُنَزِّلُهَا عَلَيْكُمْ ۖ فَمَن يَكْفُرْ بَعْدُ مِنكُمْ فَإِنِّي أُعَذِّبُهُ عَذَابًا لَّا أُعَذِّبُهُ أَحَدًا مِّنَ الْعَالَمِينَ
የቁርባን ነገረ መለኮት"Eucharistic Theology" በክርስትና ዐበይት ከሚባሉ አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት መካከል አንዱ ነው፥ አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት"Five Fundamental Sacraments" የሚባሉት፦ ምሥጢረ ሥላሴ፣ ምሥጢረ ሥጋዌ፣ ምሥጢረ ጥምቀት፣ ምሥጢረ ቁርባን እና ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ናቸው። በምሥጢረ ቁርባን እሳቤ ውስጥ ዐበይት ክርስቲያኖች "ክርስቶስ ከሰማይ የወረደ እንጀራ ነው" ብለው ያምናሉ፦
ዮሐንስ 6፥51 ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው።
"ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ ሥጋዬ ነው" ስለሚል ክርስቶስ እራሱ የሚበላ ማዕድ እንደሆነ ይናገራሉ፥ ይህም ማዕድ ሥጋ መብላት እና ደም መጠጣት እንደሆነ ተነግሯል፦
ዮሐንስ 6፥53 ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።
"ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነው" ብሏል ተብሏል፦
ዮሐንስ 6፥54 ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና።
"የክርስቶስ ሥጋ እና ደም ምሳሌአዊ ሳይሆን እውነተኛ መብል እና መጠጥ ነው፥ የጌታ እራት የሚባለው እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም ይለወጣል" የሚል እምነት በካቶሊክ እና በኦርቶዶክስ ትምህርት ውስጥ አለ፦
ማቴዎስ 26፥26 ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና፦ “እንካችሁ፥ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው፡” አለ።
ነገር ግን ጠርጡሊያኖስ ዘካርቴጅ እንጀራው የሥጋው ምሳሌ እንደሆነ ተርጉሞታል፦
"እንጀራውን አንሥቶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፥ "ሥጋዬም ይህ ነው፥ እርሱም የሥጋዬ ምሳሌ ነው" ብሎ የራሱን ሥጋ አደረገው"።
Against Marcion (Tertullian) Book IV(4) Chapter 40
በጽዋ ውስጥ ያለውን ወይን ደግሞ "ደሜ ይህ ነው" እንዳለ ተዘግቧል፦
ማቴዎስ 26፥27-28 ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ፦ “ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።
አውግስጢኖስ ዘሂፓ ወይኑ የደሙ ምሳሌ እንደሆነ ተርጉሞታል፦
"የሥጋው እና የደሙን ምሳሌ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ"።
Expositions on the Psalms (Augustine) Psalm Chapter 3 Number 1
ካቶሊክ "እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም በኑባሬ ደረጃ ይለወጣል" የሚል ትምህርታቸው "የኑባሬ ለውጥ"Tran Substantiation" ሲባል በኦርቶዶክስ ደግሞ "እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም በተማልሎአዊ ይለወጣል" ሲባል ተማልሎአዊ ለውጥ"Mystical Change" ነው፥ በሁለቱም እምነት "የበቃ ሰው በከለር፣ በጣዕም፣ በይዘት ተቀይሮ ያየዋል" የሚል እምነት አላቸው። ሰዎች ጠፍጥፈው የሠሩት እንጀራ እና የጠመቁት ወይንን "የአምላክ ሥራ የሆነው ኢየሱስ ነው" ማለት የጤና ነው? መለኮት የተዋሐደው ነፍስ የተለየው ሥጋ ከሰው ሰውነት ጋር ሲዋሐድ የሰው ሰውነት አምላክ ይሆናልን? ቁርባን በልተው ሲጸዳዱት ያ መለኮት ይጸዳዱታልን?
በፕሮቴስታንት ደግሞ ሁሉም ባይሆንም "ኅብስቱ ከሥጋው ጋር እንዲሁ ወይኑ ከደሙ ጋር ኅብረት ብቻ አለው እንጂ አይለወጥም" የሚል ትምህርታቸው አላቸው፥ ይህም "የኑባሬ ኅብረት"Con Substantiation" ይባላል።
"ፋሲካ" በሚባል "በዓል" ላይ በመሸም ጊዜ ኢየሱስ ከአሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ እንደተቀመጠ ይናገራል፦
ማቴዎስ 26፥20 በመሸም ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጠ። Ὀψίας δὲ γενομένης ἀνέκειτο μετὰ τῶν δώδεκα μαθητῶν
"ጠረጴዛ" የሚለው የግዕዙ ቃል እራሱ "ማዕድ" ወይም "ገበታ" ማለት እንጂ ባለ አራት እግር ያለው "ጻሕል(ሳሕን) ወይም "ወጭት" አይደለም፥ "ጠረጴዛ" የሚለው የግዕዙ ቃል እራሱ "ትራፔዛ" τράπεζα ከሚል ግሪክ ኮይኔ የመጣ ሲሆን "ማዕድ" ማለት ነው። ለምሳሌ፦
የሐዋርያት ሥራ 16፥34 ወደ ቤቱም አውጥቶ ማዕድ አቀረበላቸው። ἀναγαγών τε αὐτοὺς εἰς τὸν οἶκον παρέθηκεν τράπεζαν,
እዚህ አንቀጽ ላይ "ማዕድ" ለሚለው የገባው ቃል "ትራፔዛን" τράπεζα እንደሆነ ልብ አድርግ!

እዚህ ድረስ ከተግባባን ወደ ቁርኣን ስንመጣ "ማኢዳህ" مَائِدَة ማለት "ማዕድ" ማለት ሲሆን ሐዋርያት ኢየሱስን፦ «የመርየም ልጅ ዒሣ ሆይ! ጌታህ በእኛ ላይ ከሰማይ ማዕድን ሊያወርድልን ይችላልን?» ብለው ጠየቁት፦
5፥112 ሐዋርያት፡- «የመርየም ልጅ ዒሣ ሆይ! ጌታህ በእኛ ላይ ከሰማይ ማዕድን ሊያወርድልን ይችላልን?» ባሉ ጊዜ አስታውስ፡፡ «ምእመናን እንደ ኾናችሁ አሏህን ፍሩ» አላቸው፡፡ إِذْ قَالَ الْحَوَارِيُّونَ يَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ هَلْ يَسْتَطِيعُ رَبُّكَ أَن يُنَزِّلَ عَلَيْنَا مَائِدَةً مِّنَ السَّمَاءِ ۖ قَالَ اتَّقُوا اللَّهَ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
5፥113 «ከእርሷ ልንበላ ልቦቻችንም ሊረኩ እውነት ያልከንም መኾንህን ልናውቅና በእርሷም ላይ ከመስካሪዎች ልንኾን እንፈልጋለን» አሉ፡፡ قَالُوا نُرِيدُ أَن نَّأْكُلَ مِنْهَا وَتَطْمَئِنَّ قُلُوبُنَا وَنَعْلَمَ أَن قَدْ صَدَقْتَنَا وَنَكُونَ عَلَيْهَا مِنَ الشَّاهِدِينَ
ኢየሱስም ወደ አሏህ «ጌታችን አሏህ ሆይ! ለእኛ ለመጀመሪያዎቻችንና ለመጨረሻዎቻችን በዓል የምትኾንን ከአንተም ተአምር የኾነችን ማዕድ ከሰማይ በእኛ ላይ አውርድ፡፡ ስጠንም፡፡ አንተ ከሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነህና» አለ፦
5፥114 የመርየም ልጅ ዒሣ አለ፡- «ጌታችን አሏህ ሆይ! ለእኛ ለመጀመሪያዎቻችንና ለመጨረሻዎቻችን በዓል የምትኾንን ከአንተም ተአምር የኾነችን ማዕድ ከሰማይ በእኛ ላይ አውርድ፡፡ ስጠንም፡፡ አንተ ከሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነህና» አለ። قَالَ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ اللَّهُمَّ رَبَّنَا أَنزِلْ عَلَيْنَا مَائِدَةً مِّنَ السَّمَاءِ تَكُونُ لَنَا عِيدًا لِّأَوَّلِنَا وَآخِرِنَا وَآيَةً مِّنكَ ۖ وَارْزُقْنَا وَأَنتَ خَيْرُ الرَّازِقِينَ
"ዒድ" عِيد ማለት "በዓል" ማለት ሲሆን ይህም በዓል ፋሲካ ነው፥ በዚህ በዓል ከሰማይ የወረደው ማዕድ ኢየሱስ ሳይሆን በተአምር ከሰማይ የመጣ ማዕድ ነው፦
5፥115 አሏህ፡- «እኔ ማዕድዋን በእናንተ ላይ አውራጅዋ ነኝ፡፡ በኋላም ከእናንተ የሚክድ ሰው እኔ ከዓለማት አንድንም የማልቀጣውን ቅጣት እቀጣዋለሁ» አለ፡፡ قَالَ اللَّهُ إِنِّي مُنَزِّلُهَا عَلَيْكُمْ ۖ فَمَن يَكْفُرْ بَعْدُ مِنكُمْ فَإِنِّي أُعَذِّبُهُ عَذَابًا لَّا أُعَذِّبُهُ أَحَدًا مِّنَ الْعَالَمِينَ
ስለዚህ ከሰማይ የወረደው ማዕድ ኢየሱስ ሳይሆን ለኢየሱስ እና ለሐዋርያት ለበዓሉ እንዲበሉት የተሰጠ ማዕድ ነው፥ ቁርኣን ባይብል ላይ የገባውን የተሳሳተ "የጌታ ማዕድ" በዚህ መልኩ አስተካክሎታል። ከሰማይ ማዕድ ማውረድ ለአሏህ ቀላል ነው፥ ምነው እስራኤላውያን በምድረ በዳ እያሉ አሏህ መናን እና ድርጭትን ከሰማይ አውርዷል እኮ፦
20፥80 በእናንተም ላይ መና እና ድርጭትን አወረድንላችሁ፡፡ وَنَزَّلْنَا عَلَيْكُمُ الْمَنَّ وَالسَّلْوَىٰ
2፥57 በእናንተም ላይ ደመናን አጠለልን፥ በእናንተ ላይ መናን እና ድርጭትን አወረድን፡፡ وَظَلَّلْنَا عَلَيْكُمُ الْغَمَامَ وَأَنزَلْنَا عَلَيْكُمُ الْمَنَّ وَالسَّلْوَىٰ
በባይብልም ቢሆን እስራኤላውያን በምድረ በዳ እያሉ የሰማይ ኅብስት የሆነ መና እና ድርጭት እንደወረደላቸው ይናገራል፦
መዝሙር 78፥24 ይበሉም ዘንድ "መናን" አዘነበላቸው፥ የሰማይንም እንጀራ ሰጣቸው።
መዝሙር 105፥40 ለመኑ፥ "ድርጭትን" አመጣላቸው፥ የሰማይንም እንጀራ አጠገባቸው።
መዝሙር 77(78)፥19 አምላክን እንዲህ ብለው አሙት፦ "አምላክ በምድረ በዳ ማዕድን ያሰናዳ ዘንድ ይችላልን? καὶ κατελάλησαν τοῦ Θεοῦ καὶ εἶπαν· μὴ δυνήσεται ὁ Θεὸς ἑτοιμάσαι τράπεζαν ἐν ἐρήμῳ;
እዚህ አንቀጽ ላይ "ማዕድ" ለሚለው የገባው ቃል "ትራፔዛን" τράπεζαν ሲሆን በዐረቢኛ ባይብል ላይ "ማኢዳህ" مَائِدَة ነው፥ በክርስትና ላይ ያለው የጌታ እራት ትምህርት በአራት አናቅጽ ታርሟል። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ዲኑል ኢሥላም ከፍ እንዲል የላ ኢላሃ ኢለል ሏህ ባንዲራ እንዲውለበለብ መማር እና ማስተማር የአንድ ሙሥሊም መርሕ መሆን አለበት።
አሏህ ዒባደቱል ቀውሊያህ የሆነውን ደዕዋችሁን በኢኽላስ ይቀበላችሁ! አሚን።

ከሰማይ ነው!
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
3፥49 ወደ እስራኤልም ልጆች መልእክተኛ ያደርገዋል፡፡ ይላልም፡- "እኔ ከጌታችሁ በተአምር ወደ እናንተ መጣሁ"፡፡ وَرَسُولًا إِلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنِّي قَدْ جِئْتُكُم بِآيَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ
"ከ-ሰማይ" ማለት በቀላሉ "ከ-አምላክ" ማለት ነው። ለምሳሌ፦ ዮሐንስ በውኃ ያጠምቅ ነበር፥ ይህ የዮሐንስ በውኃ ማጥመቅ ወይም የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ ነበረች፦
ዮሐንስ 1፥26 ዮሐንስ መልሶ፦ "እኔ በውኃ አጠምቃለሁ፤ ዳሩ ግን እናንተ የማታውቁት በመካከላችሁ ቆሞአል።
ማርቆስ 11፥30 የዮሐንስ ጥምቀት "ከ-ሰማይ" ነበረችን ወይስ "ከ-ሰው"? መልሱልኝ።
መልሱ "ከ-ሰማይ" ነበረች፥ "ከ-ሰማይ" ሲባል "ከ-አምላክ" ማለት ነው። ምክንያቱም "ከ-ሰማይ" ለሚለው ተቃራኒ "ከ-ሰው" የሚል ቃል አለ፥ ስለዚህ "የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ ነበረች" ማለት ቃል በቃል ዮሐንስ የሚያጠምበት ውኃ አምላክ ዘንድ በቅድመ ህልውና"Pre Existence" ትኖር ነበር ማለት አይደለም። የዮሐንስ ጥምቀት ብቻ ሳይሆን ዮሐንስ እራሱ "ከ-አምላክ" ነው፦
ዮሐንስ 1፥6 "ከ-አምላክ" የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ "ሰው" ነበረ። Ἐγένετο ἄνθρωπος, ἀπεσταλμένος παρὰ Θεοῦ, ὄνομα αὐτῷ Ἰωάνης·
ዮሐንስ አምላክ ጋር ኖሮ ኖሮ የተላከ ሳይሆን አምላክ የሚለውን እና የሚናገረው መልእክት ሰቶት የተላከ ነቢይ ነው፥ በተጨማሪ "ሰው" ለሚለው የገባው ቃል "አንትሮፓስ" ἄνθρωπος ሲሆን "ሰው" መባሉ በራሱ ከተወለደ በኃላ "ከ-አምላክ" የተላከ መሆኑን ቁልጭ አርጎ ያሳያል። የአምላክን ቃል የሚሰማ "ከ-አምላክ ነው፣ የማይሰማ ደግሞ "ከ-አምላክ አይደለም፣ በጎ የሚያደርግ "ከ-አምላክ ነው። ያ ማለት የአምላክን ቃል የሚሰማ ሰው እና በጎ የሚያደርግ ሰማይ ላይ ከአምላክ ጋር አብሮ ኖሮ የመጣ ነው ማለት አይደለም፦
ዮሐንስ 8፥47 "ከ-አምላክ የሆነ" የአምላክን ቃል ይሰማል፤ እናንተ "ከ-አምላክ አይደላችሁምና" ስለዚህ አትሰሙም።
3 ዮሐንስ 1፥11 በጎ የሚያደርግ "ከ-አምላክ ነው"።
1 ዮሐንስ 4፥4: ልጆች ሆይ! እናንተ "ከ-አምላክ ናችሁ።
1 ዮሐንስ 4፥6 እኛ "ከ-አምላክ ነን"።
አይሁዳውያን፦ "ሰው ከመፈጠሩ በፊት ቅድመ ህልውና አለው" ብለው አያምኑም፥ ቅሉ ግን ኢየሱስ፦ "ይህ ሰው ከ-አምላክ አይደለም" "ይህ ሰው ከ-አምላክ ነው" ብለው ሲከራከሩ "ይህ ሰው ሰማይ ላይ ከአምላክ ጋር አብሮ ኖሮ የመጣ ነው ወይም አይደለም" ማለታቸው አልነበረም፦
ዮሐንስ 9፥16"ከፈሪሳውያንም አንዳንዶቹ፦ ይህ ሰው ሰንበትን አያከብርምና "ከ-አምላክ አይደለም" አሉ።
ዮሐንስ 9፥33 ይህ ሰው "ከ-አምላክ ባይሆን ምንም ሊያደርግ ባልቻለም ነበር።
እዚህ ድረስ በቅጡ እና በአግባብ ከተግባባን ዘንድ ኢየሱስም "ከ-ሰማይ" የሆነ "ሰው" ነው፦
1 ቆሮንቶስ 15፥47 ሁለተኛው "ሰው" "ከ-ሰማይ" ነው። ὁ δεύτερος ἄνθρωπος ἐξ οὐρανοῦ.
"ሰው" የሚለው ይሰመርበት! "ሰው" ለሚለው የገባው ቃል በተመሳሳይ "አንትሮፓስ" ἄνθρωπος ሲሆን ኢየሱስ ሰው የሆነው ከማርያም ሆኖ ሳለ ከተወለደ በኃላ ከአምላክ ስለተላከ "ከ-ሰማይ ነው" ተባለ እንጂ የተላከው ከተወለደ በኃላ ነው፦
ገላትያ 4፥4 አምላክ “ከ-ሴት የተወለደውን” ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ። ἐξαπέστειλεν ὁ Θεὸς τὸν Υἱὸν αὐτοῦ, γενόμενον ἐκ γυναικός, γενόμενον ὑπὸ νόμον,
“የተወለደው” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ጌኖሜኖን” γενόμενον ሲሆን “ጊኖማይ” γίνομαι ማለትም “ሆነ” ወይም “ተወለደ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “የሆነውን” ማለት ነው፥ ኢየሱስ ከማርያም ሰው መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ታዲያ ያ ሰው ለምን "ከ-ሰማይ" ተባለ? "ከ-ሰማይ" ማለትም "ከ-አምላክ" የተላከ ስለሆነ ነው፦
ዮሐንስ 7፥29 እኔ ግን "ከ-እርሱ ዘንድ ነኝ፥ እርሱም "ልኮኛልና" አውቀዋለሁ።
ዮሐንስ 6፥51 "ከ-ሰማይ" የወረደ ሕያው "እንጀራ" እኔ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው "እንጀራ ሥጋዬ ነው"።
"እንጀራ ሥጋዬ ነው" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! "እንጀራ" በፍካሬአዊ "ሥጋውን" ካመላከተ "ከ-ሰማይ" የወረደ "እንጀራ" እኔ ነኝ" ሲል "ከ-ሰማይ" የወረደ "ሥጋ" እኔ ነኝ" ማለቱ ነው፥ ሥጋ የሆነ ከማርያም ከሆነ ከድንግል ማርያም ሰው ሆኖ የተወለደው ሕፃን ነው። ምክንያቱም አንድ ሰው ወንድ ወይም ሴት የሚሰኘው በማሕፀን ሲፀነስ ነውና፥ እውነተኛ እንጀራ የተባለውን የሥጋ መደብ እና የፆታ አንቀጽ ያለው ወንድ ልጅ ሲሆን ይህም ወንድ ልጅ "ከ-ሰማይ" የሰጠው አብ ነው። ለምሳሌ፦ ልጆች የአምላክ በጎ ስጦታ ናቸው፥ አስተዋይ ሚስት ደግሞ ፍጹም በረከት ናት፦
መዝሙር 127፥3 እነሆ ልጆች የአምላክ ስጦታ ናቸው።
ምሳሌ 18፥22 ሚስት ያገኘ በረከትን አገኘ።
ምሳሌ 19፥14 አስተዋይ "ሚስት ግን "ከ-አምላክ ዘንድ ናት"።
ስለዚህ በጎ ስጦታ ልጆች እና ፍጹም በረከት አስተዋይ ሚስት ከሰማይ ይወርዳሉ፦
ያዕቆብ 1፥17 በጎ ስጦታ ሁሉ እና ፍጹም በረከት ሁሉ "ከ-ላይ ናቸው"፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ "ከ-ብርሃናት አባት ይወርዳሉ"።
"ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ" የሚለው ይሰመርበት! በጎ ስጦታ ልጆች እና ፍጹም በረከት አስተዋይ ሚስት ከአብ ስለሚወርዱ ከመፈጠራቸው በፊት ቅድመ ህልውና አላቸውን? ወይስ ቃል በቃል ልጆች እና ሚስት ከሰማይ ወርደዋል? ኒቆዲሞስ ኢየሱስን "መምህር ሆነህ ከአምላክ ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን" ሲለው ተልኮ መምጣቱን እንጂ ቅድመ ህልውናን በፍጹም አያመለክትም፦
ዮሐንስ 3፥2 መምህር ሆነህ ከአምላክ ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን” አለው።
በእርግጥ መሢሑ ዒሣ ከጌታው በተአምር ወደ እስራኤል ልጆች የመጣ መልእክተኛ ነው፦
3፥49 ወደ እስራኤልም ልጆች መልእክተኛ ያደርገዋል፡፡ ይላልም፡- "እኔ ከጌታችሁ "በተአምር ወደ እናንተ መጣሁ"፡፡ وَرَسُولًا إِلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنِّي قَدْ جِئْتُكُم بِآيَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ
"ከጌታችሁ በተአምር ወደ እናንተ መጣሁ" የሚል ይሰመርበት! ነቢዩ ሙሣም በተመሳሳይ "ከጌታችሁ በተአምር ወደ እናንተ መጣሁ" በማለት ይናገራል፦
7፥105 "ከጌታችሁ ወደ እናንተ በተአምር መጣሁ"፡፡ የእስራኤልንም ልጆች ከእኔ ጋር ልቀቅ፡፡ قَدْ جِئْتُكُم بِبَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ فَأَرْسِلْ مَعِيَ بَنِي إِسْرَائِيلَ
ሙሣ "ከጌታችሁ ወደ እናንተ በተአምር መጣሁ" ስላለ ቅድመ ህልውና እንደማያሳይ ሁሉ ዒሣም "ከጌታችሁ ወደ እናንተ በተአምር መጣሁ" ሲል ቅድመ ህልውናን አያሳይም። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

የጌታ መልአክ
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
19፥19 «ንጹሕን ልጅ ለአንቺ ልሰጥሽ፥ እኔ የጌታሽ መልእክተኛ ብቻ ነኝ» አላት፡፡ قَالَ إِنَّمَا أَنَا رَسُولُ رَبِّكِ لِأَهَبَ لَكِ غُلَامًا زَكِيًّا
"ጌታ" በግሪክ ሰፕቱጀንት"LXX" ውስጥ "ኩሪዮስ" κύριος ሲሆን "ዮድ ሄ ቫቭ ሔ" יְהוָֹה የሚለውን ቴትራ ግራማቶን ተክቶ መጥቷል፥ ብሉይ ኪዳን ላይ "የጌታ መልአክ" በኢ-አመልካች ውስን መስተአምር "አንጌሎስ ኩርዩ" ἄγγελος Κυρίου በሚል አሊያም "በአመልካች ውስን መስተአምር "ሆ አንጌሎስ ኩርዩ" ὁ ἄγγελος Κυρίου በሚል መጥቷል። ለምሳሌ፦ "የያህዌህ መልአክ" የሚለው "የጌታ መልአክ" በሚል መጥቷል፦
ዘፍጥረት 16፥7 የጌታ መልአክ በውኃ ምንጭ አጠገብ በበረሀ አገኛት፤ ምንጩም ወደ ሱር በምትወስደው መንገድ አጠገብ ነው። Εὗρε δὲ αὐτὴν ἄγγελος Κυρίου ἐπὶ τῆς πηγῆς τοῦ ὕδατος ἐν τῇ ἐρήμῳ, ἐπὶ τῆς πηγῆς ἐν τῇ ὁδῷ Σούρ.
እዚህ አንቀጽ ላይ "ጌታ" ለሚለው የገባው ቃል "ኩሪዮስ" κύριος ሲሆን "ያህዌህ" יְהוָֹה የሚለውን ቴትራ ግራማቶን ተክቶ የመጣ ነው፥ "መልአክ" ለሚለው የገባው ቃል "አንጌሎስ" ἄγγελος ሲሆን "መልእክተኛ" ማለት ነው። መልአኩ ከጌታ ይዞት የመጣው መልእክት "ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ፥ ከብዛቱም የተነሣ አይቆጠርም" የሚል ነው፦
ዘፍጥረት 16፥10 የጌታ መልአክ፦ “ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ፥ ከብዛቱም የተነሣ አይቆጠርም” አላት። καὶ εἶπεν αὐτῇ ὁ ἄγγελος Κυρίου· πληθύνων πληθυνῶ τὸ σπέρμα σου, καὶ οὐκ ἀριθμηθήσεται ὑπὸ τοῦ πλήθους.
"የጌታ መልአክ" ማንኛውንም ከአንዱ ጌታ አምላክ የሚላክ ሰማያዊ እና መንፈሳዊ ፍጡር ሊያመለክት የሚችል ቃል ነው። አብርሃም ልጁን ሊሠዋ የነበረው ለጌታ አምላክ ሆኖ ሳለ መልአኩ መልእክተኛ ነውና የጌታን መልእክት፦ "አንድ ልጅህን ለእኔ አልከለከልህምና" በማለት ተናግሯል፦
ዘፍጥረት 22፥11 የጌታ መልአክ ከሰማይ ጠራና፦ “አብርሃም አብርሃም፡” አለው፤ እርሱም፦ “እነሆኝ፡” አለ። እርሱም፦ “በብላቴናው ላይ እጅህን አትዘርጋ፥ አንዳችም አታድርግበት፤ "አንድ ልጅህን ለእኔ አልከለከልህምና" አምላክን የምትፈራ እንደ ሆንህ አሁን አውቄአለሁ፡” አለ። καὶ ἐκάλεσεν αὐτὸν ἄγγελος Κυρίου ἐκ τοῦ οὐρανοῦ καὶ εἶπεν· ῾Αβραάμ, ῾Αβραάμ. ὁ δὲ εἶπεν· ἰδοὺ ἐγώ. καὶ εἶπε· μὴ ἐπιβάλῃς τὴν χεῖρά σου ἐπὶ τὸ παιδάριον μηδὲ ποιήσῃς αὐτῷ μηδέν· νῦν γὰρ ἔγνων, ὅτι φοβῇ σὺ τὸν Θεὸν καὶ οὐκ ἐφείσω τοῦ υἱοῦ σου τοῦ ἀγαπητοῦ δι᾿ ἐμέ.
"አንድ ልጅህን ለእኔ አልከለከልህምና" የሚለው መልእክት ከጌታ በመልአኩ የተላለፈ መልእክት መሆኑን የምንረዳው ይህ የጌታ መልአክ ለአብርሃም ከሰማይ ሁለተኛ ጊዜ ጠርቶ “ጌታም፦ ‘በራሴ ማልሁ፤ ይህን ነገር አድርገሃልና፥ አንድ ልጅህንም አልከለከልህምና" ይላል" ማለቱ ነው፦
ዘፍጥረት 22፥15 የጌታ መልአክም አብርሃምን ከሰማይ ሁለተኛ ጊዜ ጠራው፥ እንዲህም አለው፦ “ጌታም፦ ‘በራሴ ማልሁ፤ ይህን ነገር አድርገሃልና፥ አንድ ልጅህንም አልከለከልህምና" "ይላል"። καὶ ἐκάλεσεν ἄγγελος Κυρίου τὸν ῾Αβραὰμ δεύτερον ἐκ τοῦ οὐρανοῦ, λέγων· κατ᾿ ἐμαυτοῦ ὤμοσα, λέγει Κύριος, οὗ εἵνεκεν ἐποίησας τὸ ρῆμα τοῦτο, καὶ οὐκ ἐφείσω τοῦ υἱοῦ σου τοῦ ἀγαπητοῦ δι᾿ ἐμέ,
"ይላል" የሚለው ይሰመርበት! መልአኩ "ይላል" ካለ "አንድ ልጅህንም አልከለከልህምና" ያለው ጌታ አምላክ ነው፥ አስተላላፊው ደግሞ የጌታ መልአክ ነው። "አንድ ልጅህንም አልከለከልህምና" መልእክቱ የላኪው እንጂ የተላኪው አይደለም። አብርሃምን ከሰማይ "አብርሃም" ፍጡር መልአክ መሆኑን ኩፋሌ ቁልጭ አርጎ ያሳያል፦
ኩፋሌ 14፥13 በሰማይም ሆኜ “አብርሃም፥ አብርሃም” ብዬ ጠራሁት። እርሱም ደንግጦ፥ “እነሆ፥ እኔ አለሁ” አለኝ።