ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.3K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
የጴጥሮስ መንበር

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥14 ከእነዚያም "እኛ "ነሷራ" ነን" ካሉት የጠበቀ ቃል ኪዳናቸውን ያዝን፡፡ በእርሱም ከታዘዙበት ነገር ፈንታን ተውት፡፡ وَمِنَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّا نَصَارَىٰ أَخَذْنَا مِيثَاقَهُمْ فَنَسُوا حَظًّا مِّمَّا ذُكِّرُوا بِهِ

ኢየሱስ ለጴጥሮስ፦ "የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል" ብሎታል፦
ማቴዎስ 16፥19 የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።

ጴጥሮስ የኢየሱስ ተተኪ፣ ወኪል፣ እንደራሴ ነው፥ ጴጥሮስ ከኢየሱስ እንዲህ ያለ ሥልጣን ስለተቀበለ በሐዋርያት መካከል ሊቀ መንበር ነው፥ "ካቴድራ" καθέδρα ማለት "ወንበር" ማለት ነው፦
ማቴዎስ 23፥2 ጻፎች እና ፈሪሳውያን በሙሴ “ወንበር” ተቀምጠዋል። λέγων Ἐπὶ τῆς Μωϋσέως καθέδρας ἐκάθισαν οἱ γραμματεῖς καὶ οἱ Φαρισαῖοι.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ወንበር" ለሚለው የገባው ቃል "ካቴድራስ" καθέδρας ሲሆን "ካቴድራል"cathedral" የሚለው ቃል እራሱ "ካቴድራስ" ከሚል የመጣ ነው፥ በግዕዝ "መንበር" ይባላል። "ፔትሮስ" Πέτρος ማለት "ዓለት" ማለት ነው፥ ኢየሱስ ጴጥሮስን፦ "ዓለት ነህ" "በዚህ ዓለት ላይ ኤክሌሲያ እሠራለው" ብሏል፦
ማቴዎስ 16፥18 እኔም እልሃለሁ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚህም ዓለት ላይ ቤተ ኤክሌሲያዬን እሠራለሁ፥ የሲዖል ደጆችም አይችሉአትም። κἀγὼ δέ σοι λέγω ὅτι σὺ εἶ Πέτρος, καὶ ἐπὶ ταύτῃ τῇ πέτρᾳ οἰκοδομήσω μου τὴν ἐκκλησίαν, καὶ πύλαι Ἅιδου οὐ κατισχύσουσιν αὐτῆς.

የጴጥሮስ የተጸውዖ ስሙ "ስምዖን" ሲሆን "ጴጥሮስ" ግን የማዕረግ ስሙ ነው፥ በዐረማይስጥ "ኬፋ" ܟ݁ܺܐܦ݂ܳܐ ማለት እራሱ "ዐለት" ማለት ነው። በጴጥሮስ ዐለትነት ላይ የተመሠረተችው ጉባኤ "የሲዖል ደጆችም አይችሉአትም" ተብሏል። "ኤክሌሲያ" ἐκκλησία የሚለው የግሪኩ ቃል ከሁለት ቃላት የተዋቀረ ቃል ነው፥ እርሱም "ኤክ" ἐκ ማለትም "ከ" ከሚል መስተዋድድ እና "ካሌኦ" καλέω ማለትም "የተጠራ" ከሚል ግስ ነው። በጥቅሉ "ተጠርተው የወጡ" ማለት ነው፥ ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን ሙያዊ ፍቺው ደግሞ "ጉባኤ" "ማኅበር" "ስብሰባ" ማለት ነው። ኢየሱስ በጴጥሮስ "እሠራለው" ያለው ስብስብ "ኤክሌሲያ" ተብሏል፥ ጴጥሮስም እንዲህ ብሏል፦
ቀለሜንጦስ 10፥4 "እኔ ጴጥሮስ መንፈሳዊ አባታችሁ ነኝ፥ በዚህ የሾመኝ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። "ዓለት" ተብዬ በእርሱ ዘንድ ተሹሜአለው፥ እናንተ በእኔ መሠረታት ላይ ትታነጹ ዘንድ እኔም በተሰጠኝ ችሎታ ይህንን ሠራሁኝ"።

ይህችን ኤክሌሲያ "ካቶሊክ" ያላት የአንጾኪያው ኤጲስ ቆጶስ አግናጥዮስ በ 110 ድኅረ-ልደት ነው፥ "ክርስትና" የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ያመጣው ይህ ሰው ነው። በሮም የሞተው የአንጾኪያው ኤጲስ ቆጶስ አግናጥዮስ ለሰርምኔስ በጳፈው ደብዳቤ በግሪኩ "ካቶሊኮስ" καθολικός የሚል ቃል የተጠቀመ ሲሆን ትርጉሙ "ዓለም ዐቀፍ" በግዕዝ "ኲላዊት" በሮማይስጥ "ካቶሊክ" ነው።
የፈረንሳዩ ኤጲስ ቆጶስ ሔራንዮስ በ 180 ድኅረ-ልደት ላይ "እውነታው ያለው በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንጂ ሌላ በየትም አይደለም" ብሏል፦
የምንፍቅናዎች ተቃውሞ 3፥4 "እውነታው ያለው በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንጂ ሌላ በየትም አይደለም"።
Against heresies 3፥4 "The truth is to be found nowhere else but in the Catholic Church".

ሮም ውስጥ የጴጥሮስ መንበር ሲኖር የኒቂያ ጉባኤም በ 325 ድኅረ ልደት "የሮሙ የጴጥሮስ በዓለ መንበር ሐዋርያት እንዳዘዙ አለቃም ፈራጅም ይሁን" በማለት አዘዙ፦
ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 4 ቁጥር 40
"ሊቃነ ጳጳሳት በዓለም ሁሉ አራት ብቻ እንዲሆኑ በኒቂያ የተሰበሰቡት የቅዱሳን ማኅበር አዘዙ። ከእነርሱም የሮሙ የጴጥሮስ በዓለ መንበር ሐዋርያት እንዳዘዙ አለቃም ፈራጅም ይሁን"።

በመቀጠል የኒቂያ ጉባኤ ሊቀ ጳጳስን "ካቶሊኮስ በሚባል ታላቅ ስም ያክብሩት" በማለት ተናግረዋል፦
ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 4 ቁጥር 43
"ካቶሊኮስ በሚባል ታላቅ ስም ያክብሩት"

በጴጥሮስ መንበር ላይ የሚቀመጥ ሐዋርያዊ መተካካት"apostolic succession" ያለው ጳጳስ በክርስቲያኖች አለቆች እና በሰዎች ማኅበር ላይ ሥልጣን እንዳለው እንደ ጴጥሮስ አለቃ ነውና። እርሱ በሕዝቡ እና በአብያተ ክርስቲያናቱ ላይ የክርስቶስ ምትክ ነው ተብሏል፦
ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 4 ቁጥር 54
"እርሱ በክርስቲያኖች አለቆች እና በሰዎች ማኅበር ላይ ሥልጣን እንዳለው እንደ ጴጥሮስ አለቃ ነውና። እርሱ በሕዝቡ እና በአብያተ ክርስቲያናቱ ላይ የጌታችን የክርስቶስ ምትክ ነው"።

ይህንን የሥልጣን ቦታ በመያዝ በቀጣይነት ጴጥሮስን የሚተኩ ሰዎች በትውፊት "ክርስቶስ ደንግጓል" ብለው ተተኪዎቹ የሮማ ጳጳሳት ናቸው፦
“ይህንን የሥልጣን ቦታ በመያዝ በቀጣይነት ጴጥሮስን የሚተኩ ሰዎች መኖር እንዳለባቸው ክርስቶስ ደንግጓል፤ ተተኪዎቹ ደግሞ የሮማ ጳጳሳት ናቸው።”​—ኒው ካቶሊክ ኢንሳይክሎፒዲያ (2003) ጥራዝ 11፣ ገጽ 495-496

ኢንሻሏህ ይቀጥላል....

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የጴጥሮስ መንበር

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥14 ስለዚህ እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ በመካከላቸው ጠብንና ጥላቻን ጣልንባቸው፡፡ አላህም ይሠሩት የነበሩትን ሁሉ በእርግጥ ይነግራቸዋል። فَأَغْرَيْنَا بَيْنَهُمُ الْعَدَاوَةَ وَالْبَغْضَاءَ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ ۚ وَسَوْفَ يُنَبِّئُهُمُ اللَّهُ بِمَا كَانُوا يَصْنَعُونَ

በካቶሊክ ትውፊት ከጴጥሮስ ጀምሮ እስከ ዛሬ 366 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እየተተካኩ መጥተዋል ብለው ያምናሉ፥ ሠለስቱ ምዕት ማለትም ኒቂያ ላይ የተሰበሰቡት 318 ጳጳጳት የጴጥሮስን መንበር የማይቀበል በሲኖዶክስ እንዲወገድ አዘዋል፦
ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 4 ቁጥር 42
"ይህቺ የሠራናትን ሕግ ያፈረሰውን ሲኖዶስ ያወግዘዋል"።

"ሲኖዶስ" σύνοδος ማለት "ጉባኤ" "ስብሰባ"council" ማለት ነው። ይህ የጴጥሮስ መንበር በ451 ድኅረ ልደት በኬልቄዶን ሲኖዶስ የጽብሓውያን አብያተ ክርስቲያናትን"oriental churches" አውግዟል፥ በመቀጠል ይህ የጴጥሮስ መንበር በ 1053 ድኅረ ልደት በሲኖዶስ የመለካውያን አብያተ ክርስቲያናትን"eastern churches" አውግዟል። የጽብሓውያን እና የመለካውያን ስለተወገዙ "ጵጵስናቸው የኑፋቄ ነው" ብለው ያምናሉ፥ ምክንያታቸው "የጴጥሮስን ሰንሰለት የጠበቀ ሐዋርያዊ መተካካት እና ትውፊት በትክክል እኛ ጋር ነው" ያለው የሚል ክፉኛ ሙግት አላቸው።

ዛሬ በዓለም ላይ ከ1.3 ቢሊዮን ምእመናን ያቀፈው ጉባኤ ሮም መቀመጫ ያረገ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ነው፥ በ 381 የቆስጠንጥኒያ ጉባኤ አንቀጸ እምነቱ እንዲህ ነበረ፦
፨በግሪክ፦ "Εἰς μίαν, ἁγίαν, καθολικὴν καὶ ἀποστολικὴν Ἐκκλησίαν"·
፨በኢንግሊሽ፦ "we believe in one, holy, Catholic and Apostolic Church".
፨በዐማርኛ፦ "በአንዲት፣ ቅድስት፣ ካቶሊካዊት እና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን"

"ካቶሊኮን" καθολικὴν የጴጥሮስ መንበር የያዘ የሮማ መቀመጫ የሆነው "ሐዋርያዊ መተካካት ነው" ብለው ያምናሉ። ይህቺ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ናት እንግዲህ በታሪክ ላይ በጦርነት፣ በባርያ ንግድ፣ በቅኝ ግዛት ስትበድል እና ስትገድል የኖረችው፥ ግዝት እና ግዞት የእጇ በመሆን የአንበሳውን ድርሻ በመውሰድ ዋንጫውን ወስዳለች።

ይህንን የክርስትና ታሪካዊ ሥነ መለኮት ወደ ቁርኣን ገብተን ስንመዝን ዒሣ ከአይሁዳውያን ክህደት በተሰማውም ጊዜ፡- «ወደ አላህ "ረዳቶቼ" እነማን ናቸው?» አለ፥ ሐዋርያትም፡- «እኛ የአላህ "ረዳቶች" ነን" አሉ፦
3፥52 ዒሣ ከእነርሱ ክህደት በተሰማውም ጊዜ፡- «ወደ አላህ "ረዳቶቼ" እነማን ናቸው?» አለ፥ ሐዋርያትም፡- «እኛ የአላህ "ረዳቶች" ነን፤ በአላህ አምነናል፤ እኛም ትክክለኛ ታዛዦች መኾናችንን መስክር» አሉ፡፡ فَلَمَّآ أَحَسَّ عِيسَىٰ مِنْهُمُ ٱلْكُفْرَ قَالَ مَنْ أَنصَارِىٓ إِلَى ٱللَّهِ ۖ قَالَ ٱلْحَوَارِيُّونَ نَحْنُ أَنصَارُ ٱللَّهِ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَٱشْهَدْ بِأَنَّا مُسْلِمُونَ

"አንሷር" أَنصَار ማለት "ረዳት" ማለት ሲሆን ሐዋርያት፦ "እኛ አንሷር ነን" ብለዋል፥ እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዛዦች" ለሚለው የገባው ቃል "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون መሆኑን ልብ አድርግ! አምላካችን አሏህ " "እኛ "ነሷራ" ነን" ካሉት ከሐዋርያት ጋር የጠበቀ ቃል ኪዳንን ይዟል፦
5፥14 ከእነዚያም "እኛ "ነሷራ" ነን" ካሉት የጠበቀ ቃል ኪዳናቸውን ያዝን፡፡ በእርሱም ከታዘዙበት ነገር ፈንታን ተውት፡፡ وَمِنَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّا نَصَارَىٰ أَخَذْنَا مِيثَاقَهُمْ فَنَسُوا حَظًّا مِّمَّا ذُكِّرُوا بِهِ

"ነስራኒይ" نَصْرَانِيّ የሚለው ቃል "ነሰረ" نَصَرَ ማለትም "ረዳ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ረዳት" ማለት ነው፥ "ነሷራ" نَصَارَىٰ ደግሞ የነስራኒይ ብዙ ቁጥር ሲሆን "ረዳቶች" ማለት ነው። ከሐዋርያት ሕልፈት በኃላ ግን በእነርሱ እግር ሥር ተተካን የሚሉት ነሷራ ከታዘዙበት ነገር ፈንታን ተውት፥ በተውሒድ ላይ ተሥሊሥ በመጨመር እንዲሁ ተሠግዎት፣ ምንኩስና ወዘተ... የሚባል የፓጋን ትምህርት በመጨመር ወሰን አለፉ፦
4፥171 እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ፡፡ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَا تَغْلُوا فِي دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا عَلَى اللَّهِ إِلَّا الْحَقَّ
4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ
57፥27 "የፈጠሩዋትንም ምንኩስና በእነርሱ ላይ አልጻፍናትም" وَرَهْبَانِيَّةً ابْتَدَعُوهَا مَا كَتَبْنَاهَا عَلَيْهِمْ

እነዚህ አበው የዒሣን ትምህርት ከግሪክ ወሮም ፍልስፍና፣ ወግ፣ ዐረማዊነት ጋር ቀይጠዋል፥ ወራት እና ሳምንት በጣዖታት ስም መሆናቸው በራሱ ይህ የቅሰጣ ውጤት ነው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ በመካከላቸው ጠብ እና ጥላቻ መኖሩ የአሏህ ቅጣት ነው፦
5፥14 ስለዚህ እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ በመካከላቸው ጠብንና ጥላቻን ጣልንባቸው፡፡ አላህም ይሠሩት የነበሩትን ሁሉ በእርግጥ ይነግራቸዋል። فَأَغْرَيْنَا بَيْنَهُمُ الْعَدَاوَةَ وَالْبَغْضَاءَ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ ۚ وَسَوْفَ يُنَبِّئُهُمُ اللَّهُ بِمَا كَانُوا يَصْنَعُونَ

"ስለዚህ" ማለት በእርሱም ከታዘዙበት ነገር ፈንታን በመተዋቸው የምሥራቅ ክርስቲያን እና የምዕራብ ክርስቲያን ጋር፣ የምሥራቁ ከምሥራቅ ጋር፣ የምዕራቡ ከምዕራቡ ጋር እርስ በእርስ በመካከላቸው ጠብ እና ጥላቻ መኖሩ የአሏህ ቁጣ ነው። "መሢሒይ" مَسِيحِيّ ወይም "መሢሒያህ" مَسِيحِيَّة ጠላቶቻቸው ያወጡላቸው የለበጣ እና የሽሙጥ ስም ሲሆን "ቅቡዓዊ" "ቅቡዓን" "መሢሕያዊ" "መሢሐውያን" "ክርስቶሳዊ" "ክርስቶሳውያን" ማለት ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 11፥26 ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ። التَّلَامِيذُ مَسِيحِيِّينَ لِأوَّلِ مَرَّةٍ فِي أنطَاكِيَّةَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ክርስቲያን" ለሚለው የገባው ቃል "መሢሒዪን" مَسِيحِيِّينَ ሲሆን "መሢሒይ" مَسِيحِيّ ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ሳምኬት በሚባለው ክፍል ገጽ 550 ላይ "ክርስቲያን" ማለት "ቅቡዕ(የተቀባ) ቅቡዓዊ መሢሓዊ" ማለት እንደሆነ ገልጸዋል። ክርስቲያኖች ሆይ! እውን ክርስቶሶች ናችሁን? አሏህም የዒሣን ተከታዮች "መሢሒዪን" مَسِيحِيِّينَ አላላቸው።
አሏህ ለቅኖች ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሕፃኑ ኢየሱስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

21፥22 የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ። فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ

ማርያም የወለደችው ፀንሳ የነበረውን ፆታው ወንድ የሆነ ሰው ነው፦
ሉቃስ 1፥31 “እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ”።

“ወንድ” የፆታ መለያ የሆነ የሥጋ መደብ ነው፥ ፆታው ወንድ ስለሆነ የወንድ ሩካቤ ሥጋ አለው። ይህ ሩካቤ ሥጋ”sex organ” ሽንት ለመሽናት እና ከሴት ጋር ተራክቦ”intercourse” ለማድረግ ያገለግላል፥ አምላክ ግን ወንድ አይደለም። እርሱ መንፈስ ነው፦
ዮሐንስ 4፥24 አምላክ መንፈስ ነው። Πνεῦμα ὁ Θεός,

"መንፈስ" ማለት "ረቂቅ" "ምጡቅ" ማለት ነው፥ ይህ ረቂቅ እና ምጡቅ ኑባሬ ፆታ የለውም። ወንድ ወይም ሴት አይደለም፥ ፆታ ስለሌለው የተራክቦ መፈጸሚያ ሩካቤ ሥጋ የለውም።
መለኮት አይፈጠርም፣ አይፀነስም፣ አያድግም፣ አይወለድም፥ ያ የተወለደው ሕፃን ግን ማኅፀን ውስጥ ተፈጥሮ፣ ተፀንሶ፣ አድጎ፣ ተወልዶ፣ በመጠቅለያ ተጠቅልሎ ተኝቷል፦
ሉቃስ 2፥6 “በዚያም ሳሉ የመውለጃዋ ወራት ደረሰ፥ የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው”።

አምላክ ሁሉን ያካበበ እንጂ በመጠቅለያ የሚጠቀለል በፍጹም አይደለም፥ እርሱ በጥበቃው ላይ እንቅልፍ እና መኝታ የሌለበት እንጂ በግርግም የሚተኛ አይደለም። አምላክ ጅማሮ እና መነሻ የለውም፥ ይህ ሕፃን ልጅ ግን ስምንት ቀን ሆኖት ጅማሮ እና መነሻ አለው። ወንድ ሩካቤ ሥጋው ላይ ያለውን ሸለፈት በስምንተኛ ቀን ይገረዛል፦
ዘፍጥረት 17፥12 የስምንት ቀን ልጅ ይገረዝ፤

ኢየሱስም ስምንት ቀን ሲሞላው ተገርዟል፥ በማኅፀን "ከመረገዙ" ማለትም "ከመፀነሱ" በፊት ስም እንደወጣለት ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ፦
ሉቃስ 2፥21 ”ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይጸነስ በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ”።
ሮሜ 15፥9 ”ክርስቶስ ስለ አምላክ እውነት የመገረዝ አገልጋይ ሆነ” እላለሁ።

አምላክ "የስምንት ቀን ልጅ ይገረዝ" ላለው ሕግ ክርስቶስ መገዛቱ በራሱ አምላክ እና የተገረዘው ክርስቶስ ሁለት ለየቅ ሃልዎቶች ናቸው። ይህ የተገረዘውን ሕጻን በጌታ ፊት ያቆሙት ዘንድ ዮሴፍ እና ማርያም ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት፦
ሉቃስ 2፥24 ”እንደ ሙሴም ሕግ የመንጻታቸው ወራት በተፈጸመ ጊዜ፥ በጌታ ሕግ፦ የእናቱን ማኅፀን የሚከፍት ወንድ ሁሉ ለጌታ የተቀደሰ ይባላል ተብሎ እንደ ተጻፈ ”በጌታ ፊት ሊያቆሙት፥ በጌታም ሕግ፦ ሁለት ዋሊያ ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች እንደ ተባለ፥ መሥዋዕት ሊያቀርቡ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት”።

አስቡት ፈጣሪ ፆታ ኖሮት፣ ወንድ ሆኖ፣ ተገርዞ፣ በጌታ ፊት ሊያቆሙት ሲወስዱት? አያችሁ የሁሉ ጌታ እና ሕጻኑ ሁለት የተለያዩ ኑባሬ እንደሆኑ? በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጥር 6 ቀን በዓመት አንዴ “ግዝረተ ኢየሱስ” ተብሎ የተገዘረበትን ዓመታዊ ክብረ በዓል ትዘክራለች፥ “ግዝረት” ማለት የግዕዝ ቃል ሲሆን “ግርዘት”circumcision” ማለት ነው። እንደተገረዘም በሃይማኖተ-አበው ላይ ፍትውና ቁልጭ ብሎ ተቀምጧል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 70፥24
“ወከመ ሰብእ ተገዝረ በሥርዓተ ሥጋ።

ትርጉም፦ ”ሰውም እንደ መሆኑ ለስጋ እንደሚገባ ተገዘረ”

አንዱን አምላክ ተፀነሰ፣ ተወልዶ፣ ተኝቶ፤ ወንድ ሆኖ፣ ተገረዘ ማለት ትልቁ ክህደት ነው፥ የዐርሹ ጌታ አሏህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፦
21፥22 የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ። فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ

አሏህ ለቅኖች ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
Video
አይሁዳውያን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

በሉም «በዚያ ወደኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው አመንን፡፡ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን፡፡» وَقُولُوا آمَنَّا بِالَّذِي أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَـٰهُنَا وَإِلَـٰهُكُمْ وَاحِدٌ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ

"አህለል ኪታብ" أَهْلَ الْكِتَاب ማለት "የመጽሐፉ ባለቤቶች" ማለት ሲሆን እነዚህም አይሁዳውያን እና ክርስቲያኖች ናቸው፥ እኛ ሙሥሊሞችን እና እነርሱን የፈጠረ አምላካችን አንድ አምላክ ነው፦
29፥46 የመጽሐፉን ባለቤቶችም በዚያች እርሷ መልካም በኾነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ፡፡ ከእነርሱ እነዚያን የበደሉትን ሲቀር፡፡ በሉም «በዚያ ወደኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው አመንን፡፡ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን፡፡» وَلَا تُجَادِلُوا أَهْلَ الْكِتَابِ إِلَّا بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ إِلَّا الَّذِينَ ظَلَمُوا مِنْهُمْ ۖ وَقُولُوا آمَنَّا بِالَّذِي أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَـٰهُنَا وَإِلَـٰهُكُمْ وَاحِدٌ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ

በእኛ እና በእርሱ መካከል ትክክል ወደ የሆነች ቃል 'ተውሒድ" ናት፥ ነገር ግን ክርስቲያኖች አንድ በሚለው ቃል ላይ ሦስት በማለት ተሥሊሥን ጨምረዋል። አይሁዳውያን ግን እስካሁን የሚያመልኩት አንድ አምላክን ነው፥ አይሁዳውያን አሏህ አንድ አምላክ እንደሆነ ብቻ ያምናሉ። መሢሑ ደግሞ ከዳዊት ዘር የሚመጣ የአሏህ ነቢይ እንጂ አሏህ ጋር አብሮ የሚኖር ወይም አሏህ ነው ብለው አያምኑም፥ እኛም ይህ መሢሕ ኢየሱስ ሲሆን ከዳዊት ዘር የሚመጣ የአሏህ ነቢይ እንጂ አሏህ ጋር አብሮ የሚኖር ወይም አሏህ ነው ብለን አናምንም።

እኛ እና አይሁዳውያን ልዩነታችን ምንድን ነው ታዲያ? ከተባለ፦
1ኛ. አይሁዳውያን በነቢያችን"ﷺ" ነቢይነት እና ቁርኣን የአሏህ ቃል መሆኑን አያምኑም።
2ኛ. "ኢየሱስ መሢሕ ነው" ብለው ከማመን ይልቅ "ሐሠተኛ ነቢይ፣ የዝሙተኛ ልጅ፣ ዕብድ ነው" ብለው ያምናሉ።
3ኛ. ሊቃውንቶቻቸው ባወጡላቸው ሰውኛ ሸሪዓህ ሐራሙን ሐላል፣ መክሩሕ የሆነውን ሙሥተሐብ፣ ሙባሕ የሆነው ፈርድ እያረጉ በአሏህ ጌትነት ላይ ሊቃውንቶቻቸውን አርባብ በማድረግ አሻርከዋል።

አይሁዳውያን እኛን የሚጠሉን በተውሒድ አር-ሩቡቢያህ ነው እንጂ የአብርሃምን አምላክ በብቸኝነት እንደምናመልክ ጠንቅቀው ያውቃሉ። አንድ ጊዜ አንድ ራባይ(የአይሁድ መምህር) ሲነግረኝ፦ "ሙሥሊሞች በምኩራባችን ገብተው ሶላት መቆም ይችላሉ፥ ነገር ግን ክርስቲያኖች ሦስት አካላትን ስለሚያመልኩ ለክርስቲያኖች አይፈቀድም። አንድ አይሁድ የጸሎት ሰዓት ደርሶበት መሥጂድ ገብቶ መጸለይ ይፈቀድለታል፥ ቤተክርስቲያን ውስጥ ግን አይፈቀድለትም" አለኝ፥ ለምን ስለው "ሙሥሊሞች የምታመልኩት በአንድነቱ ሦስትነት የሌለበትን ነው" አለኝ።

በእርግጥ ቪድዮ ላይ የምትመለከቱት ራባይ፦ "አሏህ በሁሉም ጊዜ የነበረ ቃል ነው። እኛ ከዐረብ ጋር ተመሳሳይ አምላክ አለን፥ ተመሳሳይ በሆነ በአንድ አምላክ እናምናለን። ይህ እንቆቅልሽ ነው፥ ክርስቲያኖች በሥላሴ ያምናሉ። ነገር ግን የክርስቲያኖች አምላካቸው አይሁዳውያን የሚጠሩት የዛ ክፍል ነውን? ያ የእኛ እምነት አይደለም። እንደዛ(እንደ ሥላሴ) እንድናምን አልተፈቀደልንም፥ በአጠቃላይ እኛ በክርስቲያን አስተሳሰብ ከዐረቦች እንሻላለን፥ በጥቅሉ ሲናገሩ። ነገር ግን የጋራ ነጥብ ያለን ከዐረቦች ጋር ነው፥ ተመሳሳይ አምላክ አለን ብለን የምናምነው ከዐረቦች ጋር ነው" ብሏል። አንዱ ጠያቂም፦ "ሙሥሊም የአምላክን ስም ለይተዋልን? ለውጠዋልን? ብሎ ጠየቀ፥ ራባዩ፦ "የአምላክን ስም አለወጡም፥ አሏህ እኮ በተመሳሳይ "አለካህ" ነው። ለምን ይቀይራሉ? ከአብርሃም እና ከእስማኤል ልጆች የመጡ ናቸው፥ እኛ ከይስሐቅ መጣን እነርሱ ከእስማኤል መጡ" በማለት ተናግረዋል።

እርግጥ ነው! ከአይሁዳውያን ዳራ የመጡት ኢየሱስ እና ሐዋርያቱ ሥላሴን አላስተማሩም፥ ተውሒድን ብቻ አስተምረዋል። ክርስቲያኖች ሥላሴን የቀየጡት ከግሪክ እና ከሮም ጋር ለመመሳሰል ነው፥ ሥላሴ ለአይሁዳውያን እንግዳ እና ባዕድ ትምህርት ነው። እስራኤላውያን የሚያመልኩት አንድ ማንነት እና ምንነት የሆነ አምላክ ነው፥ ከዚህ ውጪ እነርሱ የማያውቁት የሥላሴ ትምህርት ማሳሳቻ ነው፦
ዘዳግም 13፥6 አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት "እናምልክ" ብሎ ቢያስትህ እሺ አትበለው።

"አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን" የሚለው ይሰመርበት! ሥላሴን አይሁዳውያን አያውቁትም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የመላእክት አለቃ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

81፥21 በዚያ ስፍራ ትእዛዙ ተሰሚ፤ ታማኝ የኾነ መልእክተኛ ቃል ነው፡፡ مُّطَاعٍ ثَمَّ أَمِينٍ

ሚሽነሪዎች ጋንጩር እንዳለበት ክልው ክልው የሚያረጋቸው ነገር አለ፥ ካለማወቅ ይሁን በማወቅ መላ ቅጡ እና ቅጥ አንባሩ ጠፍቶባቸዋል። "አሏህ እያለ እንዴት መላእክት ለጂብሪል ይታዘዛሉ" የሚል መናኛ ሙግት ይሟገታሉ፥ መጠየቁ አግባብ ሆኖ ሳለ ልክ እንደ ዐዋቂ ሙግት አደራጅቶ መሰንዘር ግን አግባብ አይደለም።
እንደሚታወቀው ወደ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" በታማኝነት መልእክት ከአሏህ ዘንድ የሚያስተላልፍ መልአኩ ጂብሪል "ሙጧዕ" مُّطَاع ማለትም "አዛዥ" ወይም "ትእዛዙ ተሰሚ" ተብሏል፦
81፥21 በዚያ ስፍራ "ትእዛዙ ተሰሚ" እንዲሁ ታማኝ የኾነ መልእክተኛ ቃል ነው፡፡ مُّطَاعٍ ثَمَّ أَمِينٍ
ተፍሢሩል ጀላለይን 81፥21 "ትእዛዙ ተሰሚ" ማለት "በሰማይ እና በምድር መላእክት ይታዘዙለታል፥ "ታማኝ" ማለት "ታማኝነቱ በወሕይ ላይ ነው።
{ مُّطَاعٍ ثَمَّ } أي تطيعه الملائكة في السموات والأَرض { أَمِينٍ } على الوحي.

እዚህ አንቀጽ ላይ ጂብሪል "አዛዥ" ወይም "ትእዛዙ ተሰሚ" መባሉ እኮ ጂብሪል "የመላእክት አለቃ" መሆኑን የሚያሳይ ነው።
ይህንን ለማስረዳት በሰፈራችሁት ቁና ሰፍረን እናሳያችሁ! "ሊቅ" ማለት "ምሁር" ማለት ብቻ ሳይሆን "አለቃ" ማለትም ጭምር ነው፥ ለምሳሌ፦ "ሊቀ ጳጳሳት" ማለት "የጳጳሳት አለቃ" ማለት ሲሆን "ሊቃነ ጳጳሳት" ማለት "የጳጳሳት አለቆች" ማለት ነው። ስለዚህ "ሊቃውንት" ማለት "ምሁራን" ማለት ብቻ ሳይሆን "አለቆች" ማለትም ጭምር ነው፦
ጦቢት 12፥15 "ከከበሩ ሰባት አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ" አላቸው።
ዳንኤል 10፥13 ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ። וְהִנֵּ֣ה מִֽיכָאֵ֗ל אַחַ֛ד הַשָּׂרִ֥ים הָרִאשֹׁנִ֖ים בָּ֣א לְעָזְרֵ֑נִי

እዚህ አንቀጽ ላይ "አለቃ" ለሚለው የገባው ቃል የዕብራይስጡ ማሶሬት ላይ "ሳር" שַׂר ሲሆን የግሪክ ሰፑአጀንቱ ላይ ደግሞ "አርኾስ" ἀρχός ነው፥ ይህም "መሪ" "ገዢ" "አዛዥ" ማለት ነው። "አዛዥ" መባል በራሱ አንደኛው መልአክ ሌላውን መልአክ እንደሚመራው፣ እንደሚገዛው፣ እንደሚያዘው ጉልኅ ማሳያል ነው፥ ጦቢት ላይ ሊቃነ መላእክት"archangels" ሰባት መሆናቸው ሲገለጽ ዳንኤል ላይ ደግሞ ሚካኤል ከሊቃነ መላእክት አንዱ ሊቀ መላእክት መሆኑን ያሳያል። ሚካኤል "የመላእክት አለቃ" መባሉ በራሱ አንድ ሊቀ መላእክት መልአክ ሆኖ ሌሎችን መላእክት ማዘዙን እና ለራሱ የሥራ ድርሻ የሚላላኩለት መላእክት እንዳሉት ቁልጭ አርጎ ያሳያል፦
ይሁዳ 1፥9 "የመላእክት አለቃ ሚካኤል" ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር፦ ጌታ ይገሥጽህ፥ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።
ራእይ 22፥7 በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤል እና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። Καὶ ἐγένετο πόλεμος ἐν τῷ οὐρανῷ, ὁ Μιχαὴλ καὶ οἱ ἄγγελοι αὐτοῦ τοῦ πολεμῆσαι μετὰ τοῦ δράκοντος.

"መላእክቱ" የሚለው ቃል "አንጌሎኢ አውቶዩ" ἄγγελοι αὐτοῦ ሲሆን "የእርሱ መላእክት"his angels" ማለት ሲሆን "የ" አጋናዛቢ ዘርፍ የተገናዘበለት "እርሱ" የሚለው ተውላጠ ስም "ሚካኤል" የሚለው ስም ተክቶ እና ለውጦ የመጣ ነው።
ሰባቱ የመላእክት ሊቃውንት(አለቆች) ደግሞ በትውፊት ሚካኤል፣ ገብርኤል፣ ሩፋኤል፣ ራጉኤል፣ ዑራኤል፣ ፋኑኤል፣ ሳቁኤል ናቸው፥ እነዚህ ሰባቱ መላእክት በዙፋኑ ፊት የሚቆሙ ሰባቱ መላእክት፣ ሰባት የእሳት መብራቶች፣ ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት(መንፈሶች)፣ የእግዚአብሔር ዓይኖች ተብለዋል፦
ራእይ 8፥2 በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን "ሰባቱን መላእክት" አየሁ፥
ራእይ 4፥5 በዙፋኑም ፊት "ሰባት የእሳት መብራቶች" ይበሩ ነበር፥ እነርሱም "ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት" ናቸው።
ዘካርያስ 4፥2 "ሰባትም መብራቶች" ነበሩበት፤
ዘካርያስ 4፥10 "እነዚህ ሰባቱ" ደስ ብሎአቸው በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ያያሉ፤ "እነዚህም" በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ "የእግዚአብሔር ዓይኖች" ናቸው።

የሚገርመው አንዱ መልአክ ሌላውን መልአክ በትእዛዛዊ ግሥ "ስደድ" "ቍረጥ" "ሩጥ" "በለው" በማለት ያዘዋል፦
ራእይ 14፥17 ሌላ መልአክም በሰማይ ካለው መቅደስ ወጣ፥ እርሱም ደግሞ ስለታም ማጭድ ነበረው። በእሳትም ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ ስለታም ማጭድ ያለውን፦ ዘለላዎቹ ፈጽመው በስለዋልና ስለታሙን ማጭድህን "ስደድ" እና በምድር ያለውን የወይን ዛፍ ዘለላዎች "ቍረጥ" ብሎ በታላቅ ድምፅ ጠራ።
ዘካርያስ 2፥3-4 እነሆም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ወጣ፥ ሌላም መልአክ ሊገናኘው ወጣ፥ እንዲህም አለው፦ "ሩጥ" ይህንም ጕልማሳ እንዲህ "በለው"፦ ኢየሩሳሌም በውስጥዋ ካሉት ሰዎችና እንስሶች ብዛት የተነሣ ቅጥር እንደሌላቸው መንደሮች ሆና ትኖራለች።

በመላእክት መካከል ያለው መተታዘዝ የግብር መተታዘዝ"functional obedience" እንጂ የባሕርይ መተዛዘዝ"ontological obedience" ስላልሆነ ከላይ ያለውን መላእክት ለጂብሪል መታዘዛቸውን በዚህ ስሌት እና ሒሣብ መረዳት ትችላላችሁ።
እንግዲህ ዐቃቢያነ እሥልምና የኢሥላም ዘቦች፣ አበጋዞች እና አርበኞች ብቻ ሳይሆኑ ስንዱ ከበርቴዎች እና ለመጪው ትውልድ ማኅቶት እና ማዕዶት መሆናቸውን ተረድታችሁ እርማት እንደምትወስዱ ኢንሻሏህ ተስፋ አለን።
አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
Photo
ፍቅር ሲዝም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

33፥40 ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድንም ሰው አባት አይደለም። ነገር ግን የአላህ መልክተኛ እና "የነቢያት መደምደሚያ" ነው፥ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው። مَا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِنْ رِجَالِكُمْ وَلَٰكِنْ رَسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا

በ 2000 ድኅረ ልደት እንደ ጽብሓውያን ኦርቶዶክስ አቆጣጠር ኢትዮጵያ ውስጥ ደምሻሽ የሚባል የብልጽግና ፓርቲ እና የዶክተር ዐቢይ ደጋፊ "ነቢይ ነኝ፥ መጽሐፍ ከአምላክ በገብርኤል በኩል ተቀብያለው" በማለት ተነስቷል፥ ይህ ምስሉ ላይ የምትመለከቱት ራስታዊ ሰው በፍቅር ጭንብል ሰዎች እየቀጠፈ ይገኛል። እኛም ለጥንቃቄ መልስ መስጠት ይገባናል፥ ሥር ከሰደደ “ነቢይ ነኝ” ወይም “መልእክተኛ ነኝ” ብለው እንደተነሱት ሚርዛ ጉላም አሕመድ የአሕመዲያ መሥራች፣ ሚርዛ ሑሤን ዒሊይ የበሃኢይ መሥራች፣ ዶክተር ራሺድ ኸሊፋህ የቁርኣንያ መሥራች መርዙ መረጨቱ አይቀርም።

"ነቢይ" نَبِيّ የሚለው ቃል "ነበአ” نَبَّأَ ማለትም "አወራ" ወይም "ተናገረ" ከሚል ሥርወ-ቃል ሲሆን "አውሪ" "ተናጋሪ" "ነባቢ" "ነባይ" ማለት ነው፥ አንድ ሰው ከአሏህ ዘንድ "ነበእ" نَبَأ ማለትም "የሩቅ ወሬ" "የሩቅ ንግግር" "ነቢብ" ሲወርድለት ነቢይ ይሰኛል። ነቢይነት በአዳም ተጀምሮ በነቢያችን”ﷺ” ተጠናቋል፥ ነቢያችን”ﷺ” የነቢያት መደምደሚያ ናቸው። ከነቢያችን”ﷺ” በኃላ ነቢይ ብቻ ሳይሆን ረሡልም አይመጣም፥ ነቢይነት እና መልእክተኝነት በእርሳቸው ተደምድሟል፦
33፥40 ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድንም ሰው አባት አይደለም። ነገር ግን የአላህ መልክተኛ እና "የነቢያት መደምደሚያ” ነው"፥ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው። مَا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِنْ رِجَالِكُمْ وَلَٰكِنْ رَسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 2272
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”በእርግጥም መልእክተኛነት እና ነቢይነት ተዘግቷል። ከእኔ በኃላ መልእክተኛም ነቢይም የለም። حَدَّثَنَا أَنَسُ بْنُ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ” إِنَّ الرِّسَالَةَ وَالنُّبُوَّةَ قَدِ انْقَطَعَتْ فَلاَ رَسُولَ بَعْدِي وَلاَ نَبِيَّ

ታዲያ "ነብይ እና ረሱም ከነቢያችን”ﷺ” በኃላ የለም" ከተባለ “ነብይ ነኝ” ወይም “መልእክተኛ ነኝ” ብለው የሚነሱ ሰዎች ምንድን ናቸው? ሲባል ኃሣዌ ነብይ እና መልእክተኛ ናቸው። “ደጃል” دَّجَّال የሚለው ቃል “ደጀለ” دَجَلَ ማለትም “አጭበረበረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “አጭበርባሪ” ወይም “ሐሳዌ” ማለት ነው፥ ወደ ሠላሳ የሚቃረቡ ደጃሎች “እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ” ወይም “እኔ የአላህ ነብይ ነኝ” ብለው እንደሚነሱ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ነግረውናል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 54, ሐዲስ 108
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “የመጨረሻይቱ ሰአት አትቆምም ሠላሳ የሚቃረቡ ደጃሎች ቀጣፊዎች ተነስተውስ፦ “እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ” ብለው ቢናገሩ ቢሆን እንጂ”*። عَنْ أَبِي، هُرَيْرَةَ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ” لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يُبْعَثَ دَجَّالُونَ كَذَّابُونَ قَرِيبٌ مِنْ ثَلاَثِينَ كُلُّهُمْ يَزْعُمُ أَنَّهُ رَسُولُ اللَّهِ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 13
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ከእኔ ዑማ ውስጥ ሠላሳ የሚያህሉ ቀጣፊዎች፦ “ነቢይ ነኝ” ብለው ይነሳሉ፥ ነገር ግን እኔ የነቢያት መደምደሚያ ነኝ። ከእኔ በኃላ ነቢይ የለም”። وَحَتَّى تَعْبُدَ قَبَائِلُ مِنْ أُمَّتِي الأَوْثَانَ وَإِنَّهُ سَيَكُونُ فِي أُمَّتِي كَذَّابُونَ ثَلاَثُونَ كُلُّهُمْ يَزْعُمُ أَنَّهُ نَبِيٌّ وَأَنَا خَاتَمُ النَّبِيِّينَ لاَ نَبِيَّ بَعْدِي

አምላካችን አሏህ ከሐሣዌ ነቢያት ቅጥፈት ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መንፈስ ቅዱስ ጌታ ነውን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥78 ከእነርሱም እርሱ ከመጽሐፉ ያይደለ ሲኾን ከመጽሐፉ መኾኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙ ክፍሎች አሉ፡፡ እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልኾነ ሲኾን «እርሱ ከአላህ ዘንድ ነውም» ይላሉ፡፡ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑም በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ፡፡ وَإِنَّ مِنْهُمْ لَفَرِيقًا يَلْوُونَ أَلْسِنَتَهُم بِالْكِتَابِ لِتَحْسَبُوهُ مِنَ الْكِتَابِ وَمَا هُوَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَقُولُونَ هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَمَا هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَيَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

መጽሐፉን እንዳሻቸው ሲለቀልቁ የሚውሉ ዐላዋቂ ሳሚ የሆኑ ሚሽነሪዎች፦ "መንፈስ ቅዱስ ጌታ ተብሏል" በማለት ጳውሎስ ለማለት ያልፈለገው እጁን ጠብዝዘው "ይህንን ነው ለማለት የፈለገው" በማለት ቁልመማዊ ሕፀፅ"strawman fallacy" ይጠቀማሉ፥ "መንፈስ ቅዱስ ጌታ ተብሏል" ብለው የቆለመሙትን ጥቅስ በሰከነ እና በሰላ ልብ እስቲ እንመልከት፦
2 ቆሮንቶስ 3፥17 ጌታ ግን መንፈስ ነው። ὁ δὲ Κύριος τὸ Πνεῦμά ἐστιν·

፨ሲጀመር እዚህ አንቀጽ ላይ "ጌታ" ለሚለው የገባው ቃል "ኩሪዮስ" κύριος ሲሆን በባለቤት ሙያ የመጣ ነው፥ "ኩሪዮስ" ከሚል ቃል በፊት "ሆ" ὁ የሚል የባለቤት ውስን አመልካች መስተአምር ገብቷል። "ውስን መስተአምር ስለሌለው ንዑስ ባለቤት"predicate nominative" ነው" የሚለው ቅጥፈት ወይ አለማወቅ ነው አሊያም ሆን ተብሎ ማጭበርበር ነው፥ "ኩሪዮስ" በባለቤት ስለመጣ ማንነትን የሚያሳይ ነው።
፨ሲቀጥል እዚሁ አንቀጽ ላይ "መንፈስ" ለሚለው የገባው ቃል "ፕኒውማ" πνεῦμα ሲሆን በርቱዕ ተሳቢ ሙያ የመጣ ነው፥ "ፕኒውማ" ከሚል ቃል በፊት "ቶ" τὸ የሚል የተሳቢ ውስን አመልካች መስተአምር ገብቷል። "ፕኒውማ" ዐቢይ ባለቤት"subjective nominative" ነው" የሚለው ቅጥፈት ወይ አለማወቅ ነው አሊያም ሆን ተብሎ ማጭበርበር ነው፥ "ፕኒውማ" በተሳቢ ስለመጣ ምንነትን የሚያሳይ ነው፦
ዮሐንስ 4፥24 አምላክ መንፈስ ነው። Πνεῦμα ὁ Θεός,

"መንፈስ" ማለት "ረቂቅ" "ምጡቅ" ማለት ነው፥ ጌታ አምላክ ከሰው አእምሮ እና ከፍጥረት የረቀቀ ምጡቅ ሃልዎት ነው። "ጌታ ግን መንፈስ ነው" በሚል እንጂ "መንፈስ ጌታ ነው" በሚል የትኞቹም መተርጉማን አልተረጎሙት፥ ይህ እራሱ የሚያሳየው "ከዓለም ዓቀፍ የትርጉም ምሁራን እኔ እሻላለው፥ እነርሱ ተሳስተዋል" ማለት ባዶ ትእቢትነት መሆኑን በሙግት እያጋለጥን ነው።
፨ሢሰልስ መንፈስ ጌታ ከሆነ "የጌታ መንፈስ" የሚለው ቃል ስሜት አይሰጥም፦
2 ቆሮንቶስ 3፥17 የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ። οὗ δὲ τὸ Πνεῦμα Κυρίου, ἐλευθερία.

"መንፈስ ጌታ ነው፥ የመንፈስ መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ" ትርጉም አይሰጥም፥ "መንፈስ" በአገናዛቢ ለጌታ ገንዘብ ሆኖ የገባ እንጂ "ጌታ" አይደለም።
፨ሲያረብብ በተጨማሪ አንድ ተመሳሳይ ሰዋስው እንይ፦
ሉቃስ 16፥15 ነገር ግን አምላክ ልባችሁን ያውቃል። ὁ δὲ Θεὸς γινώσκει τὰς καρδίας ὑμῶν·

"ዴ" δέ ማለት "ግን" ወይም "እና" ማለት ሲሆን "ሆ" ὁ የሚለው ውስን መስተአምር "ዴ" ከሚለው መስተጻምር በፊት ይምጣ እንጂ "ቴዎስ" Θεὸς የሚለውን ለማጻመር የመጣ ነው፥ በተመሳሳይ ለባለቤት የመጣው "ሆ" ὁ የሚለው ውስን መስተአምር "ዴ" δέ ከሚለው መስተጻምር በፊት ይምጣ እንጂ "ኩሪዮስ" κύριος የሚለውን ለማጻመር የመጣ ነው። "መንፈስ ግን ጌታ ነው" ብለው ካሉ "ልባችሁ አምላክን ያውቃል" ይሆን ነበር፥ ቅሉ እና ጥቅሉ "መንፈስ ግን ጌታ ነው" ወይም "ልባችሁ አምላክን ያውቃል" ብሎ የተረጎመ ተርጓሚ የለም። ስለዚህ "ጌታ መንፈስ ነው" የሚለውን "መንፈስ ጌታ ነው" በማለት በመጽሐፉ ያለውን ንግግር ለማለት ያልፈለገውን "እንዲህ ለማለት ፈልጎ ነው" በማለት እየተረጎሙ ቋንቋውን ያጣምማሉ፦
3፥78 ከእነርሱም እርሱ ከመጽሐፉ ያይደለ ሲኾን ከመጽሐፉ መኾኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙ ክፍሎች አሉ፡፡ እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልኾነ ሲኾን «እርሱ ከአላህ ዘንድ ነውም» ይላሉ፡፡ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑም በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ፡፡ وَإِنَّ مِنْهُمْ لَفَرِيقًا يَلْوُونَ أَلْسِنَتَهُم بِالْكِتَابِ لِتَحْسَبُوهُ مِنَ الْكِتَابِ وَمَا هُوَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَقُولُونَ هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَمَا هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَيَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ምላስ" ለሚለው የገባው ቃል "ሊሣን" لِسَان ሲሆን "ቋንቋ" ማለት ነው፥ ቃሉ የወረደበትን ቋንቋ ወደ ሌላ ቋንቋ በመተርጎም እና ሙዳየ ቃላት"dictionary" በማበጀት መልእክቱን በትርጉም"interpretation" ያጣምማሉ። ሁለተኛ "ሊሣን" لِسَان ማለት "ምላስ" ማለት ሲሆን ዐውደ-ንባቡ ለማለት ያልፈለገውን እጁን ጠምዝዞ "እንዲህ ለማለት ነው" ብሎ በምላስ ማጣመም “ስሑት ትርጓሜ” ወይም “ሰጊጎት”Eisegesis” ይባላል። በምላስ ሆነ በቋንቋ የሚተረጎመውን አተረጓጎም ከአሏህ ዘንድ ያልኾነ ሲኾን «እርሱ ከአሏህ ዘንድ ነው» ይላሉ፡፡ ይህ የብርዘት ሂደት "አት-ተሕሪፉል መዕና" ٱلْتَحْرِيف ٱلْمَعْنًى ይባላል፥ "መዕና" مَعْنًى ማለት "መልእክት" "እሳቤ" "አሳብ"notion" ማለት ነው። የመጽሐፉ ሰዎች ክርስቲያን እና አይሁድ አሳላጭ በመሆን በመጻሕፍት ውስጥ ስርዋጽ በማሳለጥ አስገብተዋል፥ ስርዋጽ ማለት በመቀነስ እና በመጨመር እንዲሁ የሌለን እንዳለ በማስመሰል መበረዝ ነው። አሏህ ከመጽሐፉ ሰዎች ፈሣድ ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኢየሱስ ሁለት ልደት የለውም። ይነበብ፦
1. https://tttttt.me/Wahidcom/3006

2. https://tttttt.me/Wahidcom/3265

ልደት ዘኢየኃልቅ"eternal generation" 381 ድኅረ ልደት በቆስጥንጥኒያ ጉባኤ የጸደቀ እሳቤ ነው።
በግ በግን ከወለደ ሁለት በጎች ናቸው እንጂ ሁለቱ አንድ በግ አይባሉም፥ ሰው ሰውን ከወለደ ሁለት ሰዎች ናቸው እንጂ ሁለቱ አንድ ሰው አይባሉም። አምላክ አምላክን ወለደ ከተባለ ሁለት አምላክ ናቸው ማለት ነው እንጂ ሁለቱም አንድ አምላክ አይባሉም።
ግን በኢሥላም አሏህ አንድ ነው። አልወለደም፤ አልተወለደምም፦
112፥3 *አልወለደም፤ አልተወለደምም*፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom
ሲጀመር አገራችን ያሉ ታቦታት የሚባሉት የሙሴ አይነት ታቦት አይደሉም።
፨ የሙሴ ታቦት በወርቅ የተለበጠ ሲሆን የአገራችን ግን የፋርኒሽ ቅብ ነው፣
፨ የሙሴ ታቦት ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ሲሆን የአገራችን ግን 60 ሳንቲ ሜትር አካባቢ ነው፣
፨ የሙሴ ታቦት ውስጡ ጽላት ያለበትና በጽላቱም ላይ አስርቱ ትእዛዛት የተጻፉበት ሲሆን የአገራችን ግን ውስጡ ውጪው የሚባል የሌለው ወጥ ጣውላ ሲሆን ጽላት የሌለበት፣ አስርቱ ትእዛዝ ለመጻፍ ቦታ የማይበቃው እና አስርቱ ትእዛዝ ያልተጻፈበት ግን የማርያም፣ የገብርኤል፣ የሥላሴ ወዘተ.. ስም የተጻፈበት ነው።
የዚህ ዓለም አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

1፥2 "ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው"። الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ

“ዓለም” عَالَم የሚለው ቃል "ዐሊመ" عَلِمَ ማለትም "ዐወቀ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የታወቀ" ወይም "ዓለም" ማለት ነው፥ የዓለም ብዙ ቁጥር ደግሞ “ዐለሚን” عَٰلَمِين ወይም "ዓለሙን" عَالَمُون ሲሆን "ዐለማት" ማለት ነው። አምላካችን አሏህ የእነዚህ ሁሉ ዓለማት ጌታ ነው፦
1፥2 "ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው"። الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ
6፥164 በላቸው «እርሱ አላህ የሁሉ ነገር ጌታ ሲኾን ከአላህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን? قُلْ أَغَيْرَ اللَّهِ أَبْغِي رَبًّا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَيْءٍ

"የሁሉ ነገር ጌታ" የሚለው ይሰመርበት! "ሸይእ" شَيْء ማለት "ነገር" ማለት ሲሆን "ፍጥረት" የተባለውን ሁሉ ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ነው።
"እግዚአብሔር" ደግሞ የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ "እግዚእ" ማለት "ገዥ" "ጌታ" ማለት ሲሆን "ብሔር" ማለት "አገር" "ዓለም" ማለት ነው። በጥቅሉ "እግዚአብሔር" ማለት "የብሔር ጌታ" "የዓለም ገዥ" ማለት ነው፥ ዓለም እና በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ የፈጣሪ ነው። ይህንን ዓለም የፈጠረ አንድ አምላክ ነው፦
መዝሙር 50፥12 "ብራብም ለአንተ አልነግርህም፥ ዓለም እና ሞላው የእኔ ነውና።
መዝሙር 24፥1 ምድርና ሞላዋ ለያህዌህ ናት፥ ዓለም እና በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ።
ኤርምያስ 10፥12 ምድርን በኃይሉ የፈጠረ፥ ዓለሙን በጥበቡ የመሠረተ ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው።
ማቴዎስ 13፥35 "ዓለም" ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ። ἐρεύξομαι κεκρυμμένα ἀπὸ καταβολῆς κόσμου.

እዚህ አንቀጽ ላይ በኮዴክስ ቤዛይ "ዓለም" ለሚለው የገባው ቃል "ኮስሞስ" κόσμος ነው፥ ይህንን ዓለም የፈጠረው አንዱ አምላክ ሆኖ ሳለ ግን ይህንን ዓለም የሚገዛው የዚህ ዓለም ገዥ ዲያብሎስ ነው፦
ዮሐንስ 12፥31 አሁን "የዚህ ዓለም ገዥ" ወደ ውጭ ይጣላል። νῦν ὁ ἄρχων τοῦ κόσμου τούτου ἐκβληθήσεται ἔξω·

እዚህ አንቀጽ ላይ "ዓለም" ለሚለው የገባው ቃል "ኮስሞስ" κόσμος እንደሆነ ልብ አድርግ! ፈጣሪ የፈጠረውን ዓለም እርሱ በማስተናበር መግዛት ሲገባው ገዥው ግን ወደ ውጪ የሚጣለው ዲያብሎስ ነው፥ "ኮስሞስ" κόσμος ለሚለው ተለዋዋጭ ቃል "አይኦኖስ" αἰῶνος ሲሆን "ዓለም" በሚል ፍቺ መጥቷል፦
ሉቃስ 20፥34 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ "የዚህ ዓለም ልጆች ያገባሉ ይጋባሉም"። καὶ εἶπεν αὐτοῖς ὁ Ἰησοῦς Οἱ υἱοὶ τοῦ αἰῶνος τούτου γαμοῦσιν καὶ γαμίσκονται,

"የዚህ ዓለም" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! ዲያብሎስ "የዚህ ዓለም ገዥ" በተባለበት አፍ "የዚህ ዓለም አምላክ" ተብሏል፦
2 ቆሮንቶስ 4፥4 "የዚህ ዓለም አምላክ" የማያምኑትን አሳብ አሳወረ። ἐν οἷς ὁ θεὸς τοῦ αἰῶνος τούτου ἐτύφλωσεν.

ስለዚህ "አምላክ" የሚለው ስያሜ ለፍጡር ከተነገረ ግብር እንጂ ባሕርይን አመላካች አይደለም፥ "አምላክ" ማለት "ፈጣሪ" ማለት ብቻ ሳይሆን "ገዥ" ማለትም ነው። የይሆዋ ምስክሮች፦ "ሆ ቴዎስ" ὁ θεὸς ለአንድ አምላክ ብቻ የሚጠቀምበት ነው" ሲሉ ዲያብሎስ "ሆ ቴዎስ" ὁ θεὸς መባሉን ሲሰሙ ምን ይውጣቸው ይሆን? "ሆ" ὁ በባለቤት የሚመጣ ውስን መስተአምር ሲሆን በዕብራይስጥ "ሃ" הָ֣ ነው፥ የእስራኤል መሳፍንት በውስን መስተአምር "ሃ-ኤሎሂም" הָ֣אֱלֹהִ֔ים ተብለዋል፦
ዘጸአት 21፥6 "ጌታው ወደ "አማልክትን" ይውሰደው"። וְהִגִּישֹׁ֤ו אֲדֹנָיו֙ אֶל־הָ֣אֱלֹהִ֔ים
ዘጸአት 22፥8 ሌባውም ባይገኝ ባለቤቱ ወደ "አማልክትን" אלהים ይቅረብ"። אִם־לֹ֤א יִמָּצֵא֙ הַגַּנָּ֔ב וְנִקְרַ֥ב בַּֽעַל־הַבַּ֖יִת אֶל־הָֽאֱלֹהִ֑ים

"መስፍን" ማለት "ገዥ" "ፈራጅ" "መኰንን" ማለት ነው፥ የመስፍን ብዙ ቁጥር "መሳፍንት" ሲሆን "ገዥዎች" "ፈራጆች" "መኳንንት" ማለት ነው። "ኤሎሃ" אֱלוֹהַּ ማለት "አምላክ" ማለት ነው፥ የኤሎሃ ብዙ ቁጥር "ኤሎሂም" אֱלֹהִ֔ים ሲሆን "አማልክት" ማለት ነው። የእስራኤል መኳንንት "አማልክት" መባላቸው "ገዥዎች" ለመባል እንጂ "ፈጣሪዎች" ለመባል ካልሆነ እንግዲያውስ ዲያብሎስ "አምላክ" ሲባል "ገዥ" መባሉ እንጂ "ፈጣሪ" መባልን አያሳይም፥ ስለዚህ "አምላክ" የተባለ ሁሉ "ፈጣሪ" ነው ብሎ ማሰብ አሻሚ ሕፀፅ"Fallacy of equivocation" ነው፦
ፊልጵስዩስ 3፥19 ሆዳቸው "አምላካቸው" ነው። ὧν ὁ θεὸς ἡ κοιλία

እዚህ አንቀጽ ላይ "አምላክ" ለሚለው የገባው ቃል "ሆ ቴዎስ" ὁ θεὸς እንደሆነ ልብ አድርግ! ሆዳም ሰው ሆዱ ፈጣሪው አይደለም፥ ሆዳም ሰው ሆዱን "አምላኬ" እያለ በመስገድ እና በመጸለይ አያመልክም። ነገር ግን ለሆዱ ቅድሚያ በመስጠት ለሆዱ ይገዛል ማለት ነው፥ ዲያብሎስ "አምላክ" የተባለው ሆድ "አምላክ" በተባለበት "ገዥ" ለማለት ተፈልጎ ነው።
የሚገርመው ዲያብሎስ የዚህ ዓለም አምላክ በመሆን የማያምኑትን የልብ ዓይናቸው የሆነውን አሳብ እንዳሳወረ ሁሉ ያህዌም የማያምኑትን የልብ ዓይናቸውን አሳወረ፦
ዮሐንስ 12፥40 "ዓይኖቻቸውን አሳወረ" Τετύφλωκεν αὐτῶν τοὺς ὀφθαλμοὺς

የዚህ ዓለም ገዥ ማን ነው? እግዚአብሔር ወይስ ዲያብሎስ? የማያምኑትን የልብ ዓይናቸውን የሚያሳውረው ማን ነው? እግዚአብሔር ወይስ ዲያብሎስ? አሏህ "የዓለማቱ ጌታ" መባሉን ዲያብሎስ "የዚህ ዓለም ገዥ" ከመባባሉ ጋር የምትያያይዙ ሚሽነሪዎች ጓዳ ጎድጓዳችሁን ስለምናውቅ እንዲህ በአፍጢማችሁ መደፋት አለና ተጠንቀቁ። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የምዕራባውያን እና የአሜሪካ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያ ወንድ ለወንድ ሴት ለሴት ታጋባለች፥ መጪው ደግሞ የአፍሪካ ፕሮቴስታንት እንደሆነ ጥናቶች ያመላክታሉ። ፕሮቴስታንት አጥፍቶ ጠፊ ፈሣድ መሆኑን በምዕራቡ ክርስትና ማየት በቂ ነው። ስለ ግብረ ሰዶም ያንብቡ፦ https://tttttt.me/Wahidcom/2779
የአምላክ ጥበብ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

43፥59 እርሱ በርሱ ላይ የለገስንለት ለእስራኤለም ልጆች ተአምር ያደረግነው የኾነ ባሪያ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا عَبْدٌ أَنْعَمْنَا عَلَيْهِ وَجَعَلْنَاهُ مَثَلًا لِّبَنِي إِسْرَائِيلَ

ፈጣሪ በጥበብ ምድርን እንደ መሠረተ፣ በማስተዋልም ሰማያትን እንደ አጸና እና በእውቀቱ ቀላያት እንደ ተቀደዱ የምሳሌ ተናጋሪ ይናገራል፦
ምሳሌ 3፥19 ያህዌህ በጥበብ ምድርን መሠረተ፥ በማስተዋልም ሰማያትን አጸና። በእውቀቱ ቀላያት ተቀደዱ፥ ደመናትም ጠልን ያንጠባጥባሉ።

በቁርኣን ውስጥ አሏህ አፍ እንዳለው ያልተገለጸ ሲሆን በባይብል ውስጥ ግን አምላክ አፍ ኖሮት ከአፉ ጥበብ፣ ማስተዋል፣ ዕውቀት እንደወጡ ይናገራል፦
ሲራክ 24፥3 እኔ(ጥበብ) ከልዑል "አፍ ወጣሁ" ምድርንም እንደ ጉም ሽፈንኋት።
ምሳሌ 2፥6 "ከ-"አፉም" እውቀት እና ማስተዋል "ይወጣሉ"።

ፈጣሪ እና ጥበቡ ሁለት የተለያዩ ማንነት ሳይሆኑ ጥበብ የራሱ ባሕርይ ሲሆን ፈጣሪ የራሱ ማንነት ያለው ምንነት ነው፦
ኢሳይያስ 44፥24 ከማኅፀን የሠራህ፥ የሚቤዥህ ያህዌህ እንዲህ ይላል፦ "ሁሉን የፈጠርሁ፥ ሰማያትን ለብቻዬ የዘረጋሁ ምድርንም ያጸናሁ ያህዌህ እኔ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ማን ነበረ?
ምሳሌ 8፥27 ሰማዮችን በዘረጋ ጊዜ አብሬ ነበርሁ፥ በቀላያት ፊት ክበብን በደነገገ ጊዜ፥

ፈጣሪ ሰማያትን ሲዘረጋ እና ምድርን ሲያጸና ከእርሱ ጋር ማንም የለም፥ ጥበብ ግን ማንነት ሳትሆን የራሱ ባሕርይ ስለሆነች በምሳሌአዊ ንግግር "ሰማዮችን በዘረጋ ጊዜ አብሬ ነበርሁ" አለች። ይህ የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ የሰሎሞን ምሳሌ ነው፦
ምሳሌ 1፥1 የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ የሰሎሞን ምሳሌዎች።
ምሳሌ 8፥1 በውኑ ጥበብ አትጮኽምን?
ማስተዋልስ ድምፅዋን አትሰጥምን?

ጥበብ እና ማስተዋል ከአምላክ አፍ የሚወጡ ባሕርያት ሆነው ሳለ ጥበብ አትጮኽምን? ማስተዋልስ ድምፅዋን አትሰጥምን? መባሉ “ፈሊጣዊ አገላለጽ”idiomatic expression” ነው፥ ለምሳሌ፦ እራሳቸውን የቻሉ ማንነት ሳይኖራቸው የተናገሩ ቀላይ እና ባሕር ተጠቃሽ ናቸው፦
ኢዮብ 28፥14 “ቀላይ፦ “በእኔ ውስጥ የለችም” ይላል፤ ባሕርም፦ “በእኔ ዘንድ የለችም” ይላል”። תְּהֹ֣ום אָ֭מַר לֹ֣א בִי־הִ֑יא וְיָ֥ם אָ֝מַ֗ר אֵ֣ין עִמָּדִֽי׃

ቀላይ እና ባሕር እራሳቸው የቻሉ ቅዋሜ-ማንነት ወይም እኔነት ሳይኖራቸው መናገራቸው ከተገለጸ እንግዲያውስ ጥበብ መጮኽዋ እና ማስተዋል ድምፅ መስጠቷ አያስደንቅም። በምሳሌ ስምንት ውስጥ ያለውን ምሳሌ ብቻ ሳይሆን ትርጓሜም ነው፦
ምሳሌ 1፥6 ምሳሌን እና ትርጓሜን የጠቢባንና ቃልና የተሸሸገውን ነገር ለማስተዋል።

"ትርጓሜ" የተባለው በውስጠ ታዋቂነት ኢየሱስ ጥበብ ተብሏል፥ እራሱም በሦስተኛም መደብ ስለራሱ፦ "ጥበብ በሥራዋ ጸደቀች" ብሏል፦
ማቴዎስ 11፥19 የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፥ እነርሱም፦ እነሆ፥ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ ይሉታል። "ጥበብም በልጆችዋ ጸደቀች"።

ለኢየሱስ በላተኛ፣ የወይን ጠጅ ጠጭ፣ ቀራጮች፣ ኃጢአተኞች ወደ እርሱ በመምጣት ወዳጆች ሲሆኑ "ጥበብ በሥራዋ ጸደቀች" ተባለ፥ ኮዴክስ ኤፍሬማይ "በልጆችዋ" τεκνων αυτης ሲል ኮዴክስ ሲናቲከስ ደግሞ "በሥራዋ" εργων αυτης ይላል። ኢየሱስ የአምላክ ጥበብ የተባለበት ምክንያት እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት በክርስቶስ ርስትን ለመቀበል ስለፈጠረው ነው፦
1 ቆሮንቶስ 2፥7 ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን እና ተሰውሮም የነበረውን የእግዚአብሔርን ጥበብ በምሥጢር እንናገራለን።
ምሳሌ 8፥21 ለሚወድዱኝ ርስት አወርሳቸው ዘንድ እና ቤተ መዛግብታቸውንም እሞላ ዘንድ እግዚአብሔር የመንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ፥ በቀድሞ ሥራው መጀመሪያ።
ኤፌሶን 1፥11 እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን።

እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ለመቀበል እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሁሉን አስቀድሞ ፈጠረው፥ ኢየሱስ ምሳሌ ውስጥ ተሰውሮ የነበረውን የአምላክ ጥበብ ነው፦
1 ቆሮንቶስ 1፥24 የእግዚአብሔር ኃይል እና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው።

እዚህ አንቀጽ ላይ "ጥበብ" ለሚለው የገባው የግሪኩ ቃል "ሶፊአን" σοφίαν በሴት አንቀጽ አንስታይ መደብ ነው፥ "የእግዚአብሔር ኃይል" መባሉ ተምሳሌታዊ እንደሆነ ሁሉ "የእግዚአብሔር ጥበብ" መባሉ ተምሳሌታዊ ነው። ምክንያቱም እራሱ ኢየሱስ አሁን እየኖረ ያለው በእግዚአብሔር ኃይል ነው፥ የጌታ ኃይል ከእርሱ ጋር ነበረ፦
2 ቆሮንቶስ 134 ነገር ግን በእግዚአብሔር ኃይል በሕይወት ይኖራል።
ሉቃስ 5፥17 እርሱም እንዲፈውስ የጌታ ኃይል ሆነለት።
ኃይል እና ጥበብ በአምላክ ዘንድ ያሉ የእርሱ ባሕርዮት ሲሆኑ እርሱ ምድርን በኃይሉ የፈጠረ፥ ዓለሙን በጥበቡ የመሠረተ ነው፦
ኢዮብ 12፥16 ኃይል እና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው።
ኢዮብ 12፥13 በያህዌህ ዘንድ ጥበብና ኃይል አለ።
ኤርምያስ 10፥12 ምድርን በኃይሉ የፈጠረ፥ ዓለሙን በጥበቡ የመሠረተ ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው።

ኃይል፣ ጥበብ፣ ማስተዋል ባሕርያት ናቸው። ኢየሱስ ቃል በቃል የአምላክ ጥበብ የማይሆንበት ምክንያት የጥበብ መንፈስ አርፎበታል፥ ጥበብ ሞልቶበት በጥበብ ያድግ ነበር፦
ኢሳይያስ 11፥2 የያህዌህ መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የእውቀትና ያህዌህን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።
ሉቃስ 2፥40 ሕፃኑም አደገ፥ ጥበብም ሞልቶበት በመንፈስ ጠነከረ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበረ።
ሉቃስ 2፥52 ኢየሱስም ደግሞ በጥበብ እና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።

ታዲያ ምሳሌ ላይ በጥበብ ንግግር ውስጥ ፦ "ጌታ ከሁሉ አስቀድሞ ፈጠረኝ" ለምን አለ? ሲባል አንድ ጥቅስ ለሁለት ነገር መዋሉ በባይብል አዲስ አይደለም። ለምሳሌ፦
ሆሴዕ 11፥1 እስራኤል ሕፃን በነበረ ጊዜ ወደድሁት፥ ልጄንም ከግብፅ ጠራሁት። አብዝቼ ብጠራቸው አጥብቀው ከፊቴ ራቁ፤ ለበኣሊምም ይሠዉ ነበር፥ ለተቀረጹ ምስሎችም ያጥኑ ነበር።
ዘጸአት 4፥22 ፈርዖንንም፦ ያህዌህ እንዲህ ይላል፦ "እስራኤል" የበኵር ልጄ ነው፤ ይገዛልኝ ዘንድ ልጄን ልቀቅ፡ አልሁህ፤ አንተም ትለቅቀው ዘንድ እንቢ አልህ፤ እነሆ እኔ የበኵር ልጅህን እገድላለሁ፡ ትለዋለህ።

ከግብፅ ተጠርቶ ለበኣሊም ይሠዋ የነበረ እና ለተቀረጹ ምስሎች ያጥን የነበረ የእስራኤል ሕዝብ ነው፥ "ልጄን ከግብፅ ጠራሁት" የሚለው ለእስራኤል የተነገረ ሲሆን ግን በውስጥ ታዋቂነት ለኢየሱስ ተጠቅመውበታል፦
ማቴዎስ 2፥14 እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ፦ "ልጄን ከግብፅ ጠራሁት" የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብፅ ሄደ፥ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ።

"ልጄንም ከግብፅ ጠራሁት" ከሚለው በፊት እና በኃላ ያለውን ለኢየሱስ እንደማንጠቀምበት ሁሉ ከምሳሌ 8፥21-25 ካለው በፊት እና በኃላ ያለውን ለኢየሱስ አንጠቀምበትም። ኢየሱስ አሏህ ለእስራኤለም ልጆች ተአምር ያደረገው የኾነ ባሪያ እንጅ ሌላ አይደለም፦
43፥59 እርሱ በርሱ ላይ የለገስንለት ለእስራኤለም ልጆች ተአምር ያደረግነው የኾነ ባሪያ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا عَبْدٌ أَنْعَمْنَا عَلَيْهِ وَجَعَلْنَاهُ مَثَلًا لِّبَنِي إِسْرَائِيلَ

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መንፈስ "ፈጣሪ" ነውን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

40፥62 ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው፤ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፤ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ታዲያ ከእምነት ወዴት ትመለሳላችሁ?፡፡ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ فَأَنَّىٰ تُؤْفَكُونَ

በባይብል ሁሉንም ሰው የፈጠረ አንድ አምላክ አለ፥ ይህ አንድ አምላክ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው፦
ሚልክያስ 2፥10 ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን?
ኤርምያስ 51፥19 የያዕቆብ እድል ፈንታ እንደ እነዚህ አይደለም፥ እርሱ የሁሉ ፈጣሪ ነውና፤ እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነው፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ "ያህዌህ" ነው።

ያህዌህ አምላክ ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፥ ይህ አንድ አምላክ ሰው ያበጀውም በእጆቹ ነው፦
ዘፍጥረት 2፥7 ያህዌህ አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው።
መዝሙር 119፥73 እጆችህ ሠሩኝ አበጃጁኝም።

የያህዌህ እጆች ልክ እንደ ያህዌህ እራሳቸውን የቻሉ ማንነት ሳይሆኑ የምንነቱ መገለጫ ባሕርያት ናቸው፥ እነርሱ "ሠሩ" ስለተባሉ በስም መደብ "ሠሪዎች" እንደማይባሉ ሁሉ በተመሳሳይ ያህዌህ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ ስላለበት እና በአፉ እስትንፋስ ስለፈጠረ የአፉ እስትንፋስ "ፈጣሪ" አይደለችም፦
ዘፍጥረት 2፥7 በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት።
ኢዮብ 33፥4 የያህዌህ መንፈስ ፈጠረችኝ፥ የሁሉን ቻዩ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠችኝ። רֽוּחַ־אֵ֥ל עָשָׂ֑תְנִי וְנִשְׁמַ֖ת שַׁדַּ֣י תְּחַיֵּֽנִי׃

በሴት አንቀጽ "ዓሳቴኒይ" עָשָׂתְנִי ተብሎ የተቀመጠው የግሥ መደብ "ፈጠረችኝ" ማለት ነው፥ "የያህዌህ መንፈስ" ማለት "የሁሉን ቻዩ እስትንፋስ" ማለት ነው፥ እስትንፋሱ "ፈጠረች" ስለተባለ "ፈጣሪ" ከተባለች እጆቹ "ሠሩ" ስለተባሉ በስም መደብ "ፈጣሪዎች" ይባሉ ነበር። ቅሉ ግን እስትንፋስ ሆነ እጆቹ መፍጠሪያ እንጂ ፈጣሪዎች አይደሉም። ሌላ ናሙና እንመልከት፦
መዝሙር 8፥3 የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ።
መዝሙር 102፥25 ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው። וּֽמַעֲשֵׂ֖ה יָדֶ֣יךָ שָׁמָֽיִם׃

የያህዌህ ጣቶች እና እጆች ሰማያትን ስለሠሩ በስም መደብ "ፈጣሪዎች" እንደማይባሉ ሁሉ በተመሳሳይ የያህዌህ መንፈስ ስለፈጠረች "ፈጣሪ" አትባልም። ተጨማሪ ናሙና እንመልከት፦
ኢሳይያስ 48:13 እጄም ምድርን መሥርታለች ቀኜም ሰማያትን ዘርግታለች።

የያህዌህ እጅ ምድርን ስለመሠረት እና ቀኙ ሰማያትን ስለዘረጋች በስም መደብ "መሥራቾች" "ዘርጊዎች" ወይም "ፈጣሪዎች" እንደማይባሉ ሁሉ በተመሳሳይ የያህዌህ መንፈስ ስለፈጠረች "ፈጣሪ" አትባልም።
እንግዲህ የያህዌህ መንፈስ ልክ እንደ ያህዌህ ማንነት ካለው የያህዌህ እጆች፣ ጣቶች፣ ቀኙ ብዙ ማንነቶች ሊሆኑ ነው፥ ያ ደግሞ ሥላሴን ከሦስት በላይ ሊያደርግ ነው። ነገር ግን በግሥ መደብ የሚመጣ ድርጊት ባለቤቱ ያህዌህ ስለሆነ "ሠሪ" "ፈጣሪ" "መሥራች" "ዘርጊ" እርሱ ብቻ ነው እንጂ የእርሱን ባሕርይን እየሸነሸንን ማንነት አበጅተን ፈጣሪ አናረጋቸው። ለምሳሌ፦
ኢሳይያስ 1፥20 እምቢ ብትሉ ግን ብታምፁም፥ ሰይፍ ይበላችኋል፤ የያህዌህ አፍ ይህን ተናግሮአልና።
"የያህዌህ አፍ ይህን ተናግሮአል" የሚለው ይሰመርበት! የያህዌህ አፍ ስለተናገረ "ተናጋሪ" የሚለው የስም መደብ የምንጠቀመው ለያህዌህ እንጂ ለአፉ አይደለም፥ የያህዌህ ቅንዓት ያደርጋል፦
ኢሳይያስ 9፥7 የያህዌህ ቅንዓት ይህን ያደርጋል።

"የያህዌህ ቅንዓት ይህን ያደርጋል" የሚለው ይሰመርበት! የያህዌህ ቅንዓት ስላደረገ "አድራጊ" የሚለው የስም መደብ የምንጠቀመው ለያህዌህ እንጂ ለቅንዓት አይደለም፥ ሩቅ ሳንሄድ አንድ ሰው በአንደበቱ ስለሚያስተምር አስተማሪ ይባላል እንጂ አፉ "አስተማሪ" አይደለም፦
መዝሙር 37፥30 የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል፥ አንደበቱም ፍርድን ይናገራል።

አፍ ስላስተማረ "አስተማሪ" እንደማይባል እና አንደበት ስለተናገረ "ተናጋሪ" እንደማይባል ሁሉ እስትንፋስም ስለፈጠረች "ፈጣሪ" በፍጹም አትባልም፥ የሰው አፍ እና አንደበት እንደ ሰው ራሳቸውን የቻሉ ማንነቶች እንዳልሆኑ ሁሉ እስትንፋስም እንደ አምላክ ራሷን የቻለች ማንነት አይደለችም። የመጨረሻ ናሙና እንመልከት፦
ሉቃስ 11፥49 ስለዚህ ደግሞ የአምላክ ጥበብ እንዲህ አለች፦ ወደ እነርሱ ነቢያትንና ሐዋርያትን እልካለሁ፥ ከእነርሱም ይገድላሉ ያሳድዱማል።
ሲራክ 24፥3 እኔ(ጥበብ) ከልዑል "አፍ ወጣሁ" ምድርንም እንደ ጉም ሽፈንኋት።

ከአምላክ አፍ የምትወጣ የአምላክ ጥበብ ስለምትልክ "ላኪ" እንደማትባል ሁሉ እስትንፋስም ስለፈጠረች "ፈጣሪ" በፍጹም አትባልም። ዕውቀት እና ማስተዋል ከአምላክ አፍ የሚወጡ ባሕርያት ናቸው፥ በማስተዋሉ ሰማያትን አጸና እንዲሁ በእውቀቱ ቀላያት ተቀደዱ፦
ምሳሌ 2፥6 "ከ-"አፉም" ዕውቀት እና ማስተዋል "ይወጣሉ"።
ምሳሌ 3፥19 ያህዌህ በጥበብ ምድርን መሠረተ፥ በማስተዋልም ሰማያትን አጸና። በእውቀቱ ቀላያት ተቀደዱ፥ ደመናትም ጠልን ያንጠባጥባሉ።
ኤርምያስ 10፥12 ምድርን በኃይሉ የፈጠረ፥ ዓለሙን በጥበቡ የመሠረተ ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው።

እንግዲህ እስትንፋስ ማንነት ከሆነች እጆች፣ ጣቶች፣ ቀኝ፣ አፍ፣ ጥበብ፣ ማስተዋል፣ እውቀት፣ ኃይል ስንት ማንነቶች አሉ? መፍጠሪያውን ፈጣሪ ካረግን ስንት ፈጣሪዎች አሉ? ስለዚህ እንደባይብሉ የአምላክ እስትንፋስ ልክ እንደ ዕውቀት፣ ማስተዋል፣ ጥበብ ከአፉ የምትወጣ ባሕርይ ናት፦
መዝሙር 33፥6 ሠራዊታቸውም ሁሉ "በ-"አፉ እስትንፋስ" ጸኑ። וּבְר֥וּחַ פִּ֝֗יו כָּל־צְבָאָֽם׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "እስትንፋስ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ሩሓህ" רוּחַ ሲሆን "መንፈስ" ማለት ነው፥ መንፈስ በተለያየ ጊዜ ለተለያየ ሥራ ከአፉ ወይም ከአፍንጫው የሚወጣ እስትንፋስ ከሆነ እራሱን የቻለ ማንነት እና ፈጣሪ በፍጹም አይደለም፦
ዘጸአት 15፥8 በአፍንጫህ እስትንፋስ ውኆች ተከመሩ። וּבְר֤וּחַ אַפֶּ֙יךָ֙ נֶ֣עֶרְמוּ מַ֔יִם

እዚህ አንቀጽ ላይ "እስትንፋስ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል በተመሳሳይ "ሩሓህ" רוּחַ ነው፥ አፍ እና አፍንጫ ሁለት የተለያዩ ከሆኑ ከሁለቱ የሚወጡትን እስትንፋሶች እየሸነሸንን አካላት የምንሰጥ እና "ፈጣሪዎች" የምንል ከሆነ ሥንት አካሎች እና ፈጣሪዎች ሊኖሩ ነው?
ወደ ቁርኣን ስንመጣ አምላካችን አሏህ አንድ ማንነት እና ምንነት ሲሆን የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፥ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፦
40፥62 ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው፤ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፥ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም። ታዲያ ከእምነት ወዴት ትመለሳላችሁ?፡፡ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ فَأَنَّىٰ تُؤْفَكُونَ

ክርስቲያኖች ሆይ! እንዲህ ተወሳስቦ ከሚያወዛግብ ትምህርት ወጥታችሁ አንዱን አምላክ አሏህን እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሁለት ልደት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥75 የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ እናቱም በጣም እውነተኛ ናት፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ وَأُمُّهُ صِدِّيقَةٌ

"ልደት" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ጌነሲስ" γένεσις ሲሆን ሰማይ እና ምድር ምንም እንኳን የተፈጠሩ ቢሆኑም "ልደት" እንዳላቸው ተገልጿል፦
ዘፍጥረት 2፥4 የሰማይ እና የምድር “ልደት” ይህ ነው። Αὕτη ἡ βίβλος γενέσεως οὐρανοῦ καὶ γῆς,

እዚህ አንቀጽ ላይ "ልደት" ለሚለው በሰፕቱአጀንት”LXX” ላይ የገባው ቃል "ጌኔሲስ” γένεσις ሲሆን "ኦሪት ዘፍጥረት" በግዕዙ "ኦሪት ዘልደት" ይባላል፥ “ፍጥረት” እና “ልደት” በሚል ቃል ላይ ያለው መነሻ ቅጥያ “ዘ” የሚለው አገናዛቢ ዘርፍ “የ” ማለት ሲሆን “የ-ፍጥረት” ወይም “የ-ልደት” ማለት ነው። ሰማይ እና ምድር ልደት አላቸው ማለት ጅማሬ እና መነሻ አላቸው ማለት ከሆነ ኢየሱስ ልደት ስላለው ጅማሮ እና መነሾ አለው፦
ማቴዎስ 1፥18 የኢየሱስ ክርስቶስም “ልደት” እንዲህ ነበረ። Τοῦ δὲ Ἰησοῦ Χριστοῦ ἡ γένεσις οὕτως ἦν.
ሉቃስ 3፥23 ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር።

ዕድሜው ሠላሳ ዓመት የሆነው ጅማሬ እና መነሻ ስላለው ነው፥ ከዚህ ልደት ውጪ ኢየሱስ ሌላ ልደት የለውም። ነገር ግን 381 ድኅረ ልደት የተሰበሰበው የቁስጥንጥንያ ጉባኤ "ልደት ዘኢየኃልቅ" የሚባል እሳቤ አጽድቀዋል፥ "ልደት ዘኢየኃልቅ" ማለት "ዘላለማዊ ውልደት"eternal generation" ማለት ነው። ለዚህ እሳቤ ድምዳሜ ያደረሷቸውን ጥቅሳት እስቲ እንመልከት፦
ምሳሌ 8፥25 "ወዘንበለ አድባር ይተከሉ፥ ወእምቅድመ አውግር "ወለደኒ"።
ትርጉም፦ “ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ፥ ከኮረብቶች በፊት "ወለደኝ"።

በግዕዝ "ወለደኒ" ማለት "ወለደኝ" ማለት ነው፥ አንዱ አምላክ ፆታ ስለሌለው፣ ወንድም ሴትም ስላልሆነ እና የባሕርይ መውለድ እና መወለድ ስለሌለው "ወለደኝ" ማለት "ፈጠረኝ" ማለት እንደሆነ አንድምታው እና ሃይማኖተ-አበው እንቅጩን ፍርጥ አርገው ነግረውናል፦
ምሳሌ 8፥25 አንድምታ፦ “ወለደኒ” ስለ ሥጋ “ፈጠረኝ” አልሁ።
ሃይማኖተ-አበው ዘባስልዮስ ምዕራፍ 32 ቁጥር 18
ግዕዙ፦ “ወለደኒ” ይተረጎም በወልደ እግዚአብሔር ወብሂለ “ፈጠረኒ” በእንተ ትስብእቱ።
ትርጉም፦ “ወለደኝ” ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ስለመሆኑ “ፈጠረኝ” ማለት ሰው ስለ መሆኑ ይተረጎማል።

“ወለደኝ” ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ከሆነ ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠ አብን አህሎ እና መስሎ ከአብ ያለ እናት መወለድን ሳይሆን ከድንግል ማርያም ተፈጥሮ መወለዱን ቁልጭ አርጎ የሚያሳይ ነው፥ የካርቴጁ ጡርጡሊያኖስ “ወለደኝ” ማለት “ፈጠረኝ” ማለት እንደሆነ ተናግሯል፦
"በመጀመሪያ ምድርን ከመፍጠሩ፣ ተራሮች ሳይሠሩ በፊት እኔን የመንገዱ መጀመሪያ አድርጎ ፈጠረኝ፤ ደግሞም እርሱ ከኮረብታዎች ሁሉ በፊት እኔን "ወለደኝ" ማለትም እርሱ "ፈጠረኝ" ማለት ነው"። Tertullian of Carthage (220 AD) on proverb 8:22: The Writings of Tertullian Volume II page 421]

ቀጣዩ ጥቅስ ደግሞ የዕብራይስጡ ማሶሬት፣ አብዛኛው እና አብላጫው እንግሊዝኛ ቅጂዎች እና በዐማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላይ ግን “ከንጋት ማኅፀን በቅዱስ ግርማህ ደምቀህ የጎልማሳነትህን ልምላሜ እንደ ጠል ትቀበላለህ”Arrayed in holy splendor, your youth will come to you like dew from the morning’s womb” ብለው ያስቀመጡት ሲሆን ግሪክ ሰፕቱጀንት፣ ግዕዙ እና ጥቂት የእንግሊዝኛ ትርጉም፦ "ከማኅፀን ወለድኩህ”I have begotten thee from the womb" ብለው አስቀምጠውታል፦
መዝሙር 119(110)፥3 ἐκ γαστρὸς πρὸ ἑωσφόρου ἐγέννησά σε.
ግዕዙ፦ “ወለድኩከ እም ከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽባሕ”
ትርጉም፦ “ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከማኅፀን ወለድኩህ”

“ከርሥ” ማለት “ማኅፀን”the womb” ማለት ሲሆን ይህ ማኅፀን የድንግል ማርያም ማኅፀን ነው፥ ስለዚህ እምድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት የተወለደበት የመጀመሪያ "ልደት" የሚባል ትምህርት የለም። በአገራችን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ ኦርቶዶክስ ቅብዓት፣ ኦርቶዶክስ ጸጋ፣ ኦርቶዶክስ ካራ የሚባሉ ሲኖሩ ኦርቶዶክስ ካራ "የክርስቶስ ሰዋዊ ምንነት የአብ ልጅነት ያገኘው በራሱ ቀቢነት በመቀባት ልጅነቱ ሦስተኛ ልደት ነው" ይላሉ።
የሚገርመው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ "ማርያም አምላክን ወለደች" ከማለት አልፈው "አምላክ ለማርያም የባሕርይ ልጇ ነው፥ ማርያም ለአምላክ የባሕርይ እናቱ ናት" ይላሉ፥ የአምላክነት ባሕርይ ከሌላት ከባሕርይዋ የአምላክነት ባሕርይን ካልወሰደ የባሕርይ እናቱ እንዴት ትሆናለች?
አንድ ሰው ከወላጆቹ ዘርን ስለሚካፈል ለወላጆቹ የባሕርይ ልጅ ነው፥ ማርያም ሰው ናትና ከእርሷ የተካፈለው የሰው ባሕርይ ብቻ ስለሆነ ማርያም የሰው እናት ብቻና ብቻ ናት።

ወደ ቁርኣን ስንመጣ አምላካችን አሏህ መሢሑን ኢየሱስን በ 23 ቦታ “ኢብኑ መርየም” ابْن مَرْيَم ማለትም “የመርየም ልጅ” ይለዋል፥ ለናሙና ያክል አንድ አንቀጽ እንመልከት፦
5፥75 የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ "እናቱም" በጣም እውነተኛ ናት፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ وَأُمُّهُ صِدِّيقَةٌ

“እናቱ” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! ልጅ የሚጠራው በአባቱ ስም "የእከሊት ልጅ" ሳይሆን "የእከሌ ልጅ" ነው፥ ነገር ግን ዒሣ አባት ስለሌለው በእናቱ ስም “የመርየም ልጅ” ይባላል። "አምላክ አምላክን ወለደ" ብላችሁ ለምታባዙ አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የጌታችን ክብር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

72፥3 ‹እነሆም የጌታችን ክብር ላቀ፡፡ ሚስትንም ልጅንም አልያዘም፡፡› وَأَنَّهُ تَعَالَىٰ جَدُّ رَبِّنَا مَا اتَّخَذَ صَاحِبَةً وَلَا وَلَدًا

ከጂን የኾኑ ጭፈሮች ቁርኣንን አዳምጠው "እኛ አስደናቂ የኾነን ቁርኣን ሰማንም" ማለታቸው ወደ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ተወርዷል፦
72፥1 በል «እነሆ ከጂን የኾኑ ጭፈሮች ቁርኣንን አዳመጡ፡፡‹እኛ አስደናቂ የኾነን ቁርኣን ሰማንም› አሉ ማለት ወደ እኔ ተወረደ፡፡ قُلْ أُوحِيَ إِلَيَّ أَنَّهُ اسْتَمَعَ نَفَرٌ مِّنَ الْجِنِّ فَقَالُوا إِنَّا سَمِعْنَا قُرْآنًا عَجَبًا

ከጂን የኾኑ ጭፈሮች ወደ ቀጥታ መንገድ የሚመራውን ቁርኣንን መስማት ብቻ ሳይሆን በቁርኣኑ አምነው በአሏህ ላይ ማንንም እንደማያጋሩ ተናግረዋል፦
72፥2 ‹ወደ ቀጥታ መንገድ የሚመራን ቁርአን ሰማን፥ በእርሱም አመንን፡፡ በጌታችንም አንድንም አናጋራም፡፡› يَهْدِي إِلَى الرُّشْدِ فَآمَنَّا بِهِ ۖ وَلَن نُّشْرِكَ بِرَبِّنَا أَحَدًا

በጌታችን አሏህ አንድነት አምነው ማንንም ሳያጋሩ ተጋሪዎች እና ልጅ ያልያዘውን ጌታቸውን አልቀዋል፦
72፥3 ‹እነሆም የጌታችን ክብር ላቀ፡፡ ሚስትንም ልጅንም አልያዘም፡፡› وَأَنَّهُ تَعَالَىٰ جَدُّ رَبِّنَا مَا اتَّخَذَ صَاحِبَةً وَلَا وَلَدًا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ክብር" ለሚለው የገባው ቃል "ጀድ" جَدّ ሲሆን ክርስቲያን ፕሪንስ لَعْنَتَ اللَّهِ عَلَيْه ግን፦ "ጀድ" جَدّ ማለት "አያት"Grand Father" ማለት ነውና ከጂን የኾኑ ጭፈሮች "የጌታችን አያት" ብለዋል፥ ስለዚህ አሏህ አያት አለው" በማለት ያለ ዐውዱ በመቆልመም ሲቀጥፍ ይሰማል፥ ከዐውደ ንባቡ አንጻር "የጌታችን አያት ላቀ" ትርጉም አይሰጥም። በሥነ አፈታት ጥናት"hermeneutics" አንድ ዐውደ ንባብ የሚፈታው በሰጊጎት"eisegesis" ሳይሆን በፈቲሆት"exegesis" ነው፥ "ላቀ" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ "ተዓላ" تَعَالَىٰ ሲሆን የአሏህ ዑሉው ለማሳየት ብዙ ቦታ መጥቷል፦
7፥190 አላህም ከሚያጋሩት ሁሉ "ላቀ"፡፡ فَتَعَالَى اللَّهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ
27፥63 አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ "ላቀ"፡፡ تَعَالَى اللَّهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ

"ላቀ" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ "ተዓላ" تَعَالَىٰ እንደሆነ ልብ አድርግ! "ዑሉው" عُلُوّ ማለት "ልዕልና"transcendence" ማለት ሲሆን ከሁሉ ነገር በላይ የላቀው አሏህ ብቻ ስለሆነ የላቀው የአሏህ ክብር እንጂ ከመነሾ አንድ ብቻ የሆነ አሏህ አባት፣ አያት"Grand Father" የለውም፦
112፥1 በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ
112፥2 «አላህ የሁሉ መጠጊያ ነው፡፡ اللَّهُ الصَّمَدُ
112፥3 «አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ
112፥4 «ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም፡፡» وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ

"አልተወለደም" ከተባለ አባት፣ አያት፣ ቅድመ አያት የለውም፥ ይህ የሁሉ መጠጊያ አምላክ የሚመስለው ቢጤ ማንም ከሌለው አባት፣ አያት፣ ቅድመ አያት የለውም።
፨ሲቀጥል አንድ ቃል ቋንቋዊ ፍቺው "መዕና ሉገዊይ" مَعْنًى لُغَوِيّ ሲባል ሸሪዓዊ ፍቺው ደግሞ "መዕና ሸርዒይ" مَعْنًى شَرْعِيّ ይባላል፥ አንድ ቃል ቋንቋዊ ፍቺው ሆነ ሸሪዓዊ ፍቺው ብዙ ትርጉም ይይዛል። ለምሳሌ፦ "ተእዊል" تَأْوِيل ማለት "መጨረሻ" ማለት ነው፦
4፥59 ይህ የተሻለ "መጨረሻውም" ያማረ ነው*፡፡ ذَٰلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا
7፥53 የዛቻውን "መጨረሻ" እንጂ ሌላ አይጠባበቁም፡፡ هَلْ يَنظُرُونَ إِلَّا تَأْوِيلَهُ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "መጨረሻ" ለሚለው ቃል የገባው ቃል "ተእዊል" تَأْوِيل መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። "ተእዊል" تَأْوِيل በሌላ ፍቺው "ትርጉም"interpretation" ማለት ነው፦
12፥6 ከንግግሮችም "ትርጉምን" ያስተምርሃል፡፡ وَيُعَلِّمُكَ مِن تَأْوِيلِ الْأَحَادِيثِ
12፥101 ጌታዬ ሆይ! ከንግሥና በእርግጥ ሰጠኸኝ፡፡ ከሕልሞችም "ትርጉም" አስተማርከኝ፡፡ رَبِّ قَدْ آتَيْتَنِي مِنَ الْمُلْكِ وَعَلَّمْتَنِي مِن تَأْوِيلِ الْأَحَادِيثِ