ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ጂብራኢል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥97 “ለጂብሪል ጠላት የኾነ ሰው በቁጭት ይሙት” በላቸው፡፡ قُلْ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّجِبْرِيلَ

ጂብሪል ከመላእክት አለቆች አንዱ ነው፦
2፥97 “ለጂብሪል ጠላት የኾነ ሰው በቁጭት ይሙት” በላቸው፡፡ قُلْ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّجِبْرِيلَ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 59 , ሐዲስ 47
ሠሙራህ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “በሌሊት ላይ ሁለት ሰዎች ወደ እኔ ሲመጡ አየሁኝ፥ ከእነርሱ አንዱ እንዲህ አለ፦ “ያ እሳት የሚያይዝ “ማሊክ” ሲሆን የእሳት ዘበኛ ነው፥ “እኔ ጂብሪል ነኝ”። ይህ ሚካኢል ነው”። عَنْ سَمُرَةَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ رَأَيْتُ اللَّيْلَةَ رَجُلَيْنِ أَتَيَانِي قَالاَ الَّذِي يُوقِدُ النَّارَ مَالِكٌ خَازِنُ النَّارِ، وَأَنَا جِبْرِيلُ، وَهَذَا مِيكَائِيلُ ‏”‌‏.‏

“ኢል” ئِيل የሚለው ቃል “ኢላህ” إِلَـٰه ለሚለው ምጻረ ቃል ሲሆን “አምላክ” ማለት ነው፥ “ኢል” ئِيل የሚለው ቃል በመላእክት ስም መዳረሻ ቅጥያ ሆኖ ይመጣል። ለምሳሌ “ሚካ-ኢል” مِيكَائِيل እና “ጂብራ-ኢል” جِبْرَائِيل ተጠቃሽ ናቸው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 196
ዘይድ ኢብኑ ሓሪሳህ እንደተረከው፦ የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ጂብራኢል ስለ ውዱእ አስተማረኝ”። زَيْدِ بْنِ حَارِثَةَ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ عَلَّمَنِي جِبْرَائِيلُ الْوُضُوءَ

“ጂብሪል” جِبْرِيل “ሀምዘቱል ወስል” هَمْزَة الوَصْل ተውጦ ሲነበብ ሲሆን “ሀምዘቱል ወስል” هَمْزَة الوَصْل በግልጽ ሲመጣ ደግሞ “ጂብራ-ኢል” جِبْرَائِيل ይሆናል፥ ይህንን በዐረቢኛው ባይብልም ማየት ይቻላል፦
ሉቃስ 1፥19 መልአኩም መልሶ፦ እኔ በአሏህ ፊት የምቆመው ጂብራኢል ነኝ። فَأجَابَهُ المَلَاكُ: «أنَا جِبْرَائِيلُ الَّذِي أقِفُ فِي حَضْرَةِ اللهِ
ዳንኤል 9፥21 ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው “ሰው” ጂብሪል እነሆ እየበረረ መጣ። أيْ بَيْنَمَا كُنْتُ أُصَلِّي هَذِهِ الصَّلَاةَ – طَارَ الرَّجُلُ جِبرِيلُ الَّذِي رَأيْتُهُ قَبْلًا فِي الرُّؤيَا مُسرِعًا فَوَصَلَ إلَيَّ فِي وَقْتِ ذَبِيحَةِ المَسَاءِ.

“ጂብራ-ኢል” جِبْرَائِيل ወይም “ጂብሪል” جِبْرِيل የሚለው ቃል “ጂብር” جِبْرَ እና “ኢል” ئِيل ከሚሉ ሁለት ቃላት የተዋቀረ ነው፥ “ጂብር” جِبْرየሚለው ቃል “ጀበረ” جَبَرَ ማለትም “ጀገነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ጀግና” ማለት ነው። “ጂብራ-ኢል” جِبْرَائِيل ማለት በጥቅሉ “የአምላክ ጀግና” ማለት ነው፥ በተመሳሳይ በዕብራይስጥ “ገብር-ኤል” גַּבְרִיאֵל ነው። “ጌቤር” גָּבַר ማለት “ጀግና” “ኃያል” “ብርቱ” ማለት ነው፦
2 ሳሙኤል 1፥23 ከአንበሳም ይልቅ “ብርቱዎች” ነበሩ። קלו מאריות גברו׃

“ገበር” גֶּבֶר ሲሆን ደግሞ “ሰው” ማለት ነው፦
ኢዮብ 34፥7 እንደ ኢዮብ ያለ “ሰው” ማን ነው? מי־גבר כאיוב

“ገብር-ኤል” גַּבְרִיאֵל በዚህ ትርጉሙ “የአምላክ ሰው” ማለት ነው፥ “ኤል” אֵל የሚለው ቃል “ኤሎሃ” אֱלוֹהַּ ለሚለው ምጻረ ቃል ሲሆን “አምላክ” ማለት ነው። ጂብሪል በሰው አምሳል ወደ ሰዎች ስለሚመጣ የአምላክ ሰው ነው፥ ወደ መርየም የመጣው ትክክለኛ ሰው ተመስሎ ነው፦
19፥17 ከእነሱም መጋረጃን አደረገች፡፡ መንፈሳችንምም (ጂብሪልን) ወደርሷ ላክን፡፡ ለእርሷም ትክክለኛ ሰው ሆኖ ተመሰለላት፡፡ فَاتَّخَذَتْ مِن دُونِهِمْ حِجَابًا فَأَرْسَلْنَا إِلَيْهَا رُوحَنَا فَتَمَثَّلَ لَهَا بَشَرًا سَوِيًّا

ጂብሪል ወደ ነቢያችን”ﷺ” የሚመጣው በሚወዱት ባልደረባ በዲሕያህ ኢብኑ ኸሊፋህ በሚባል ሰው ተመስሎ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 66, ሐዲስ 2
አቡ ዑስማን እንደተረከው፦ “ጂብሪል ወደ ነቢዩ”ﷺ” ሲመጣ ኡሙ ሠላማህ ከእርሳቸው ጋር ነበረች፥ ጂብሪል መናገር ጀመረ። ነቢዩም”ﷺ”፦ “ኡሙ ሠላማህ ይህ ማን ነው? አሉ፥ እርሷም፦ “ይህ ዲሕያህ ነው” አለች። ጂብሪል በሄደ ጊዜ እርሷም፦ “ወሏሂ! በነቢዩ”ﷺ” ሑጥባህ ላይ ስለ ጂብሪል ዜና እስኪነግሩን ድረስ ከዲሕያህ በስተቀር ሌላ ማንንም አላሰብኩም ነበር”። عَنْ أَبِي عُثْمَانَ، قَالَ أُنْبِئْتُ أَنَّ جِبْرِيلَ، أَتَى النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم وَعِنْدَهُ أُمُّ سَلَمَةَ فَجَعَلَ يَتَحَدَّثُ فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم لأُمِّ سَلَمَةَ ‏ “‏ مَنْ هَذَا ‏”‌‏.‏ أَوْ كَمَا قَالَ قَالَتْ هَذَا دِحْيَةُ‏.‏ فَلَمَّا قَامَ قَالَتْ وَاللَّهِ مَا حَسِبْتُهُ إِلاَّ إِيَّاهُ حَتَّى سَمِعْتُ خُطْبَةَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم يُخْبِرُ خَبَرَ جِبْرِيلَ أَوْ كَمَا قَالَ،

በባይብልም ቢሆን ገብርኤል በሰው አምሳያ ወደ ዳንኤል ስለመጣ “ሰው” ተብሏል፦
ዳንኤል 9፥21 ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው “ሰው” ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ።

ምነው አብርሃም ቤት የገቡት ሦስቱ መላእክት “ሰዎች” ተብለው የለ እንዴ?፦
ዘፍጥረት 18፥2 ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ “ሦስት ሰዎች” በፊቱ ቆመው አየ።
ዘፍጥረት 18፥16 “ሰዎቹም” ከዚያ ተነሥተው ወደ ሰዶም አቀኑ አብርሃምም ሊሸኛቸው አብሮአቸው ሄደ።
ዘፍጥረት 18፥22 “ሰዎቹም” ከዚያ ፊታቸውን አቀኑ፥ ወደ ሰዶምም ሄዱ።

እንዲሁ ከአብርሃም ቤት ወደ ሰዶም ያቀኑት ሁለቱ መላእክት ሁለቱ ሰዎች ተብለዋል እኮ፦
ዘፍጥረት 19፥1 “ሁለቱም መላእክት” በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ።
ዘፍጥረት 19፥10 “ሁለቱም ሰዎች” እጃቸውን ዘርግተው ሎጥን ወደ እነርሱ ዘንድ ወደ ቤት አገቡት መዝጊያውንም ዘጉት።
ዘፍጥረት 19፥12 “ሁለቱም ሰዎች” ሎጥን አሉት። እኛ ይህን ስፍራ እናጠፋለንና፥ ጩኸታቸው በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ሆኖአልና እናጠፋውም ዘንድ እግዚአብሔር ሰድዶናል።

እንግዲህ ተረጋግተን ልጡ የተራሰ ጉድጓዱ የተማሰ ምርምር ስናረግ “ገብርኤል” ማለት “የአምላክ ሰው” ማለት መሆኑን እና ገብርኤል በሰው አምሳል ስለሚመጣ “ሰው” መባሉን አስረግጠን እና ረግጠን ካስረዳን ዘንዳ “ጂብራኢል እንዴት በሰው አምሳል ይመጣል” ብላችሁ የተቻችሁት ትችት የጨባራ ለቅሶ እና ተስካር ነው፥ ዙሪያ ገቡን ሳትመረምሩ መተቸት እንዲህ ድባቅ ያስገባል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቁልቢ ገብርኤል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

11:120 ከመልክተኞቹም ወሬዎች ተፈላጊውን ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናረካበትን “እንተርክልሃለን፥ በዚህችም እውነቱ ነገር “ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ” መጥቶልሃል”፡፡ وَكُلًّۭا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَ ۚ وَجَآءَكَ فِى هَٰذِهِ ٱلْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌۭ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ

"ቁልቢ" የሚለው ቃል የመጣው አንድ ሸይኽ አንድ ሰውን ሩቂያህ ቀርተውለት ይድንና እርሳቸውን፦ "አድነውኛል" ሲላቸው እርሳቸውም፦ ያዳንኩህ እኔ ሳልሆን አሏህ ነውና "ቁል ረቢ" አሉት፥ "ቁል" قُلْ ማለት "በል" ማለት ሲሆን "ረቢ" رَبِّي ማለት ደግሞ "ጌታዬ" ማለት ነው። በጥቅሉ "ቁል ረቢ" قُلْ رَبِّي ማለት "በል ጌታዬ" ማለት ሲሆን "ረ" የምትለዋን ሐርፍ አውጥተው "ቁል-ቢ" አሉት፥ ክርስቲያኖች "ቁልቢ ገብርኤል" የሚሉት አናንያን፣ አዛሪያን እና ሚሳኤልን ከእሳት ያዳናቸውን መልአክ ነው።
አናንያንም ሲድራቅ፥ ሚሳኤልንም ሚሳቅ፥ አዛርያንም አብደናጎ ብሎ ስም ያወጣላቸው የጃንደረቦቹም አለቃ ነው፦
ዳንኤል 1፥7 የጃንደረቦቹም አለቃ ስም አወጣላቸው፤ ዳንኤልን ብልጣሶር፥ አናንያንም ሲድራቅ፥ ሚሳኤልንም ሚሳቅ፥ አዛርያንም አብደናጎ ብሎ ጠራቸው።

እነዚህ ሦስት ልጆች ናቡከደነጾር ላቆማቸው ጣዖታት "አንስገድም" በማለታቸው ምክንያት በሚነድ እቶን እሳት ውስጥ ጣላቸው፥ ቅሉ ግን እንኳን ሊቃጠሉ ከሦስቱ ጋር አራተኛ ሰው ተገኝቶ ከእሳት አዳናቸው፦
ዳንኤል 3፥23 እነዚህም ሦስቱ ሰዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ታስረው በሚነድደው በእቶኑ እሳት ውስጥ ወደቁ።
ዳንኤል 3፥25 እርሱም፦ "እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም፤ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል" ብሎ መለሰ።

ናቡከደነጾር ጣዖታዊ እንደመሆኑ መጠን "አማልክት" የሚለው ፈጣሪን ሳይሆን በእርሱ እሳቤ "የቅዱሳን አማልክት" የሚሏቸውን ጣዖታት ነው፥ ለምሳሌ "ብልጣሶር" የሚለውን ስም ናቡከደነጾር "የአምላኬ ስም" ማለቱ ይህንን አመላካች ነው፦
ዳንኤል 4፥8 በመጨረሻም "የቅዱሳን አማልክት" መንፈስ ያለበት እንደ አምላኬ ስም ብልጣሶር የሚባለው ዳንኤል በፊቴ ገባ።
ዳንኤል 5፥11 "የቅዱሳን አማልክት" መንፈስ ያለበት ሰው በመንግሥትህ ውስጥ አለ።
ዳንኤል 2፥11 "ከአማልክት" በቀር በንጉሡ ፊት የሚያሳየው ማንም የለም" አሉ።
ዳንኤል 3፥12 በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ የሾምሃቸው ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም የሚባሉ አይሁድ አሉ፤ ንጉሥ ሆይ፥ እነዚህ ሰዎች ትእዛዝህን እንቢ ብለዋል፤ "አማልክትህን" አያመልኩም።
ዳንኤል 3፥18 ነገር ግን፥ ንጉሥ ሆይ፥ እርሱ ባያድነን፥ "አማልክትህን" እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ" አሉት።

ስለዚህ ናቡከደነጾር አራተኛውን ሰው "የአማልክት ልጅ" ይመስላል" ሲል የራሱ ግምት እንጂ አራተኛው ሰው በእርግጥ መልአክ ሲሆን ይህም መልአክ የናቡከደነጾር አማልክት መልአክ ሳይሆን የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ የላከው መልአክ ነው፦
ዳንኤል 3፥28 ናቡከደነፆርም መልሶ፦ "መልአኩን" የላከ፥ ከአምላካቸውም በቀር ማንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፥ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም "አምላክ" ይባረክ።

ሲጀመር ፕሮቴስታንት "የአማልክትን ልጅ ይመስላል" የሚለውን የናቡከደነጾር የተሳሳተ እይታ ይዘው አራተኛ ሰው ሆኖ የታየው መልአክ "ኢየሱስ ነው" ብለው አርፈውታል፥ ኢየሱስ የሦስቱ ልጆች አምላክ የላከው መልአክ ከሆነ አምላክ ሳይሆን መልአክ ስለሚሆን እና በተጨማሪም አምላክን አምላክ ስለማይልክ የግድ ኢየሱስ ከአምላክ ውጪ ይሆናል።
ሲቀጥል "አራተኛው ሰው የአምላክ ልጅ" ቢባል እንኳን አራተኛው ሰው "መልአክ" ስለተባለ "የአምላክ ልጅ" የተባለው መልአኩ ይሆናል እንጂ "የአምላክ ልጅ" የተባለ ሁሉ ኢየሱስ ነው ብሎ ድምዳሜ ላይ መድረስ ቂልነት ነው፥ ምክንያቱም መላእክት "የአምላክ ልጆች" ተብለዋልና፦
ኢዮብ 1፥6 ከዕለታት አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፤ "የአምላክ ልጆች" በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም መጡ።
ኢዮብ 2፥1 ከዕለታት አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፤ "የአምላክ ልጆች" በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም መጡ።
ኢዮብ 38፥7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ "የእግዚአብሔርም ልጆች" ሁሉ እልል ሲሉ።
ከፕሮቴስታንት የተዛባ አመለካከት በተቃራኒ ኦርቶዶክሳውያን አራተኛ ሰው ሆኖ የታየው መልአክ "ገብርኤል ነው" ብለው ታኅሣሥ አሥራ ዘጠኝ ቀን በዓመት አንዴ ዓመታዊ በዓል ያረጉለታል፦
፨ስንካር ዘውርኀ ታኅሣሥ 19
"ታኅሣሥ አሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን የመላእክት አለቃ የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው፥ እርሱም አናንያን፣ አዛሪያን እና ሚሳኤልን በባቢሎን አገር በነደደ እሳት ውስጥ በጨመሩአቸው ጊዜ ያዳናቸው ነው"
፨ድርሳነ ገብርኤል ምዕራፍ 2 ቁጥር 1-2
"የእግዚአብሔር መልአክ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል አናንያ፣ አዛሪያ እና ሚሳኤል ወዳሉበት ወረደ፥ የእሳቱን ነበልባል መታው። እርሱም እንደ ነፋስ ቀዘቀዘ፥ የእሳቱም ነበልባል ምንም አልነካቸውም ለመውጣትም አላስጨነቃቸውም"

አናንያን፣ አዛሪያን እና ሚሳኤልን ከእሳት ያዳናቸው አራተኛው ሰው ሆኖ የታየው መልአክ ማን ነው? በሚለው ውዝግቡ በዚህ አያበቃም። በድርሳነ ሚካኤል ላይ ደግሞ አናንያን፣ አዛሪያን እና ሚሳኤልን ከእሳት ያዳናቸው አራተኛው ሰው ሆኖ የታየው መልአክ "ሚካኤል ነው" ይለናል፦
ድርሳነ ሚካኤል ዘውርኀ ታኅሣሥ ቁጥር 82-84
"በታኅሣሥ አሥራ ሁለት የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል መታሰቢያ በዓል ነው፥ በዚች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን ባቢሎን ወደምትባል አገር ልኮታልና። አናንያ፣ አዛሪያ እና ሚሳኤል ከሚባሉ ከሦስቱ ጎልማሶች ጋር የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ከሚነድ እሳት ውስጥ በጨመራቸው ጊዜ አራተኛ ሆኖ ታየ፥ ሚካኤልም የእሳቱን ነበልባል በበትሩ መትቶ ከሦስቱ ጎልማሶች ላይ አዳናቸው"

ይህ ውዝግብ መቼም አይፈታም። አንደኛ አራተኛ ሰው ሆኖ የታየው መልአክ ማን ነው? ሚካኤል ወይስ ገብርኤል? ሚካኤል እና ገብርኤል አንድ መልአክ ነውን? አይ ሁለቱም እንዳትሉ ናቡከደነጾር ያየው አራተኛ እንጂ አራተኛ እና አምስተኛ በፍጹም አይደለም። ሁለተኛ ፈጣሪ አናንያን፣ አዛሪያን እና ሚሳኤልን ከእሳት ያዳናቸው ቀን መቼ ነው? ታኅሣሥ አሥራ ዘጠኝ ወይስ ታኅሣሥ አሥራ ሁለት?
አምላካችን አሏህ ለነቢያችን”ﷺ” ከእርሳቸው በፊት ያለፉትን የሩቅ ወሬ መተረኩ ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ ነው፦
11:120 ከመልክተኞቹም ወሬዎች ተፈላጊውን ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናረካበትን “እንተርክልሃለን፥ በዚህችም እውነቱ ነገር “ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ” መጥቶልሃል”፡፡ وَكُلًّۭا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَ ۚ وَجَآءَكَ فِى هَٰذِهِ ٱلْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌۭ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ

አሏህ ስለ አናንያ፣ አዛሪያ እና ሚሳኤል አሊያም ስለ ዳንኤል ምንም የነገረን ነገር የለም፥ አስፈላጊ ግሳጼ እና ማስታወሻ ቢሆን ኖሮ ይተርክልን ነበር። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የማርያም ዘር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥36 «እኔም እርስዋን እና ዝርያዋን ከተረገመው ሰይጣን በአንተ እጠብቃቸዋለሁ» وَإِنِّي أُعِيذُهَا بِكَ وَذُرِّيَّتَهَا مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ

አምላካችን አሏህ አንዲት ነፍስ የሆነውን አደምን ፈጥሮ ከእርሱ አጥንት መቀናጃ ትሆነው ዘንድ ሐዋን ፈጥሯታል፦
4፥1 እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁን ከእርስዋም መቀናጆዋን የፈጠረውን ከእነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶች የበተነውን ጌታችሁን ፍሩ፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ اتَّقُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ وَخَلَقَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَبَثَّ مِنْهُمَا رِجَالًا كَثِيرًا وَنِسَاءً
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 567
ዐሊይ”ረ.ዐ.” እንደተረከው ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦
"እጅግ የላቀው አሏህ አደምን ፈጠረው፥ ሐዋንም ከእርሱ አጭር አጥንት ፈጠራት"። عَنْ عَلِيٍّ، أَنَّ النَّبِيَّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ إِنَّ اللَّهَ تَعَالَى لَمَّا خَلَقَ آدَمَ خُلِقَتْ حَوَّاءُ مِنْ ضِلَعِهِ الْقَصِيرِ

አሏህ ሐዋን ያለ ያለ ሴት ዘር ከአደም አጥንት መፍጠር ከቻለ ዒሣን ያለ ወንድ ዘር ከመርየም እንቁላል መፍጠር ይችላል፥ የመርየም እናት፦ "እርስዋን እና ዝርያዋን" በማለቷ ዒሣ የመርየም ዘር እንደሆነ አስረግጦ እና ረግጦ ያሳያል፦
3፥36 «እኔም እርስዋን እና ዝርያዋን ከተረገመው ሰይጣን በአንተ እጠብቃቸዋለሁ» وَإِنِّي أُعِيذُهَا بِكَ وَذُرِّيَّتَهَا مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ

"ዙሪያህ" ذُرِّيَّة ማለት "ዘር"offspring" ማለት ሲሆን "ዙሪያህ" ذُرِّيَّة በሚለው መድረሻ ቅጥያ ላይ "ሃ" هَا የሚለው አንስታይ አገናዛቢ ተውላጠ ስም መርየምን አመላካች ስለሆነ ዒሣ የመርየም ዘር መሆኑን ቁልጭ እና ፍንትው አርጎ ያሳያል። አሏህ ያንን ከመርየም የፈጠረውን አካል ሩሕ በማስገባት ሕያው አድርጎታል፦
66፥12 የዒምራንን ልጅ መርየምንም ያችን ብልቷን የጠበቀችውን ምሳሌ አደረገ፡፡ በእርሱም ውስጥ ከመንፈሳችን ነፋን፡፡ وَمَرْيَمَ ابْنَتَ عِمْرَانَ الَّتِي أَحْصَنَتْ فَرْجَهَا فَنَفَخْنَا فِيهِ مِن رُّوحِنَا

"ፊ-ሂ" فِيهِ ማለት "በ-እርሱ ውስጥ” ማለት ነው፥ "ሂ" هِ የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም "እርሱ" ማለት ሲሆን ያንን የተፈጠረውን ፅንስ የሚያሳይ ነው።
በባይብልም ቢሆን ኢየሱስ የማርያም ዘር ነው። ለምሳሌ ፈጣሪ ከዳዊት ወገብ ሰሎሞንን ዘር አድርጎ አውጥቶታል፦
2 ሳሙኤል 7፥12 ዕድሜህም በተፈጸመ ጊዜ ከአባቶችህም ጋር ባንቀላፋህ ጊዜ "ከወገብህ የሚወጣውን ዘርህን" ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ።

"ዘር" የሚወጣ ነገር ስለሆነ "የሚወጣ" ተብሏል። ሌዋውያን አብርሃም በሕይወት እያለ አልነበሩም፥ ግን ዘር ከአብርሃም ወደ ይስሐቅ፣ ከይስሐቅ ወደ ያዕቆብ፣ ከያዕቆብ ወደ ሌዊ እየተመዘዘ ስለወጣ "ከአብርሃም ወገብ ቢወጡ" በማለት የሌዊ ልጆች ሌዋውያን ከአብርሃም ወገብ እንደወጡ ይናገራል፦
ዕብራውያን 7፥5 እነርሱ ምንም "ከአብርሃም ወገብ ቢወጡ"፥ ከእነርሱ አሥራትን በሕግ እንዲያስወጡ ትእዛዝ አላቸው።

"ዘር" ከወላጅ አብራክ እንደሚወጣ በቁና ማስረጃ ማምጣት ይቻላል፥ ለናሙና ያክል ዘፍጥረት 46፥26 ዘጸአት 1፥5 እና መሣፍንት 8፥30 ተመልከት!
"ፉሌ" φυλή ማለት "ነገድ" "ወገን" ማለት ነው፥ የአሴር ወገን እና የቢንያም ወገን የሚለውን ማጣቀሻ ሉቃስ 2፥36 እና የሐዋርያት ሥራ 13፥21 ተመልከት! በተመሳሳይም ኢየሱስ ከይሁዳ ነገድ ወጥቷል፦
ዕብራውያን 7፥14 ጌታችን ከይሁዳ "ነገድ" φυλή "እንደወጣ" የተገለጠ ነውና።
ሙሴ ስለ ይሁዳን ነገድ በክህነት ጉዳይ ምንም አልተናገረም፥ ከይሁዳ ነገድ መሠዊያውን ያገለገለ ማንም የለም፦
ዕብራውያን 7፥14 ስለዚህም ነገድ ሙሴ ምንም እንኳ ስለ ክህነት አልተናገረም።
ዕብራውያን 7፥13 ይህ ነገር የተነገረለት "እርሱ በሌላ "ነገድ" ተካፍሎአልና"፥ ከዚያም መሠዊያውን ያገለገለ ማንም የለም። ἐφ’ ὃν γὰρ λέγεται ταῦτα, φυλῆς ἑτέρας μετέσχηκεν, ἀφ’ ἧς οὐδεὶς προσέσχηκεν τῷ θυσιαστηρίῳ·

"ከዚያም" የሚለው አመልካች ተውላጠ ስም "ሌላ ነገድ" የሚለውን የይሁዳን ነገድ አመላካች ነው፥ ኢየሱስ ከይሁዳ ነገድ "ተካፍሎአል" ይለናል። የተካፈለው ደግሞ ሥጋ እና ደም ነው፦
ዕብራውያን 2፥14 እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ እርሱ ደግሞ "በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ"። ἐπεὶ οὖν τὰ παιδία κεκοινώνηκεν αἵματος καὶ σαρκός, καὶ αὐτὸς παραπλησίως μετέσχεν τῶν αὐτῶν,

"በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! መንፈሳዊ ወንድሞቹ ከወላጆቻቸው ሥጋ እና ደም እንደተካፈሉ ሁሉ እርሱ ደግሞ ከይሁዳ ነገድ ከሆነችው ከማርያም ሥጋ እና ደም ተካፍሏል፥ የያዘው ዘር ከሰማይ የሆነ የመላእክትን ሳይሆን የአብርሃምን ዘር ነው፦
ዕብራውያን 2፥16 "የአብርሃምን ዘር ይዞአል" እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም።
ራእይ 5፥5 እነሆ ከይሁዳ "ነገድ" የሆነው አንበሳ።
ሉቃስ 1፥42 "የ-ማኅፀንሽም ፍሬ" የተባረከ ነው።

"ከይሁዳ "ነገድ" የሆነው" የሚለው ይሰመርበት! በእርግጥም ኢየሱስ የማርያም የማኅፀኗ ፍሬ ነው፥ "የ" የሚለው አገናዛቢ ዘርፍ ማርያምን ባለቤትነት የሚያደርግ ድንቅ ጥቅስ ነው። የአባት ሀብለ በራሂ"paternal chromosome" ግማሽ 23% የእናት ሀብለ በራሂ"maternal chromosome" 23% ተገናኛተው 46% ሀብለ በራሂ ሕዋስ"diploid" ሆነው አንድ ሰው ይወለዳል፥ ማርያም ግን ያለ ወንድ ዘር በማፀኗ ያለውን እንቁላል እንድትጸንስ ለአምላክ የሚሳነው ነገር ስለሌለ ያለ ወንድ ሀብለ በራሂ በሴት ሀብለ በራሂ ብቻ ኢየሱስ ተፈጥሯል። ሴት እንዴት "ዘር" ይኖራታል? ካላችሁ እንግዲያውስ "ዘር" የተባለው "ሀብለ በራሂ"chromosome" ነው፥ ሴት እንቁላሏ ሀብለ በራሂ ስለሆነ "ዘር" ይባላል፦
ዘፍጥረት 16፥10 "ዘርሽን" እጅግ አበዛለሁ።

በ 100 ድኅረ ልደት ግብፅ ተወልዶ በ 160 ድኅረ ልደት ቆጵሮስ የሞተው ቫለንቲኑስ የኖስቲስ መሪ የነበረው የቴዎዳስ ተማሪ ነው፥ ቫለንቲኑስ "ኢየሱስ የማርያም ዘር አይደለም" የሚል አቋም ያለው ሲሆን የእርሱ ተማሪዎች ቫለንቱሳውያን ይህንን አቋም በጥንት ጊዜ ያራምዱ ነበር። በመቀጠል በ 1496 ድኅረ ልደት ተወልዶ በ 1561 ድኅረ ልደት የሞተው ሜኖ ስምዖን "ኢየሱስ የማርያም ዘር አይደለም" የሚል አቋም ያለው ሲሆን የእርሱ ተማሪዎች ሜኖናይተስ ይህንን አቋም በጥንት ጊዜ ያራምዱ ነበር፥ የእነርሱ እርዝራዥ 1527 ድኅረ ልደት ዳግም መጥምቃውያን"Anabaptism" አራት ቡድናት ያቀፈ ሲሆን "ኢየሱስ የማርያም ዘር አይደለም" የሚል አቋም ነበራቸው። በመሠለስ በ 2001 ድኅረ ልደት እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር ቢሾፕ ተክለ ማርያም ገዛሃኝ ከአሓዳዊ ጴንጤቆስጣል አንጃ ወጥተው "ኢየሱስ የማርያም ዘር አይደለም" በሚል አቋም የራሳቸው የሐዋርያት ቤተክርስቲያን መሥርተዋል። አሏህ ለሁሉም ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አርጋኖን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

17፥64 ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምጽህ አታል፡፡ وَاسْتَفْزِزْ مَنِ اسْتَطَعْتَ مِنْهُم بِصَوْتِكَ

"አርጋኖን" የሚለው ቃል "ኦርጋኖን" ὄργᾰνον ከሚል ግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን "የሙዚቃ መሣሪያ"organ" ማለት ነው። "እንዚራ"የሚለው ቃል "አንዘረ" ማለትም "ነዘረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የሚነዝር" ማለት ነው፥ "እንዚራ" በግሪክ ኮይኔ "ኪታራ" κῐθᾰ‌ρᾱ ሲሆን በኢንግሊዝኛ "ጊታር"guitar" ይባላል። እነዚህ የሙዚቃ መሣሪያ የተጀመሩት በቃየን ቤተሰብ በሆነው በላሜሕ ሁለት ልጆች ነው፦
ቀሌምንጦስ 3፥39 "የቃየን ቤተሰብ የሆነው ዕውሩ ላሜሕ ዮፍሊን እና በልቄን የሚባሉት ሁለት ልጆች ነበሩት፥ እነዚህ ልጆች በመሰንቆ በአርጋኖን፣ በእንዚራ እና በከበሮ ዘፈኑ"።

በኢሥላም የሙዚቃ መሣሪያ ለአምልኮ መጠቀም ሐራም ነው፥ "ሐላል" حَلَال ማለት “የተፈቀደ” ማለት ሲሆን “ሐራም” حَرَام ማለት “የተከለከለ” ማለት ነው። ዝሙት እና አስካሪ መጠጥ ሐራም እንደሆነ ሁሉ የሙዚቃ መሣሪያም ከዝሙት እና ከአስካሪ መጠጥ ጋር ተያይዞ ክልክል መሆኑ በነቢያችን”ﷺ” ሐዲስ ተነግሯል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 74, ሐዲስ 16
አቡ ዐሚር ወይም አቡ ማሊኩል አሽዐሪይ እንደተረከው፦ “ወሏሂ አልዋሸውም! ነቢዩ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቷል፦ ”ከኡመቴ ውስጥ ጥቂት ሰዎች ለራሳቸው ዝሙትን፣ ሐር ልብስን፣ አስካሪ መጠጥን እና የሙዚቃ መሣሪያ ሐላል የሚያደርጉ ይሆናሉ”። قَالَ حَدَّثَنِي أَبُو عَامِرٍ ـ أَوْ أَبُو مَالِكٍ ـ الأَشْعَرِيُّ وَاللَّهِ مَا كَذَبَنِي سَمِعَ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ “‏ لَيَكُونَنَّ مِنْ أُمَّتِي أَقْوَامٌ يَسْتَحِلُّونَ الْحِرَ وَالْحَرِيرَ وَالْخَمْرَ وَالْمَعَازِفَ

"የሥተሒሉነ" يَسْتَحِلُّونَ የሚለው ቃል "ሐላል" حَلَال ለሚለው የግስ መደብ ሲሆን “ሐላል የሚያደርጉ” ማለት ነው፥ እዚህ ሐዲስ ላይ “የሙዚቃ መሣሪያ” የሚለው “መዓዚፍ” مَعَازِف ሲሆን “ሚዕዘፍ” مِعْزَف ለሚለው የብዙ ቁጥር ነው። አምላካችን አሏህ ኢብሊሥ የሚከተሉትን በድምጹ እንደሚያታልላቸው ተናግሯል። ይህም ድምጹ መደበሪያ፣ ዘፈን፣ ላግጣ እና ስላቅ ነው፦
17፥64 ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምጽህ አታል፡፡ وَاسْتَفْزِزْ مَنِ اسْتَطَعْتَ مِنْهُم بِصَوْتِكَ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 17፥64
”ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምጽህ አታል” የተባለው እርሱ ዘፈን ነው፥ ሙጃሒድም አለ፦ “ድምጽ የተባለው መደበሪያ፣ ዘፈን፣ ላግጣና ስላቅ ነው”። واستفزز من استطعت منهم بصوتك قيل هو الغناء قال مجاهد باللهو والغناء أي استخفهم بذلك

አሏህ በሙዚቃ መሣሪያ ከሚመጣ ፈሣድ ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቤ አሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሰብአ ሰገል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

16፥51 አላህም አለ፦ ”ሁለት አማልክትን አትያዙ! እርሱ ”አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እኔንም ብቻ ፍሩ!”፡፡ وَقَالَ ٱللَّهُ لَا تَتَّخِذُوٓا۟ إِلَٰهَيْنِ ٱثْنَيْنِ ۖ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَإِيَّٰىَ فَٱرْهَبُونِ

“መጁሢያህ” مَجُوسِيَّة ማለት “ጥንቆላ” “አስማት” “ኮከብ ቆጠራ” ማለት ሲሆን በጥንቆላ፣ በአስማት እና በኮከብ ቆጠራ የተሰማሩት እነርሱ ደግሞ “መጁሥ” مَجُوس ይባላሉ፥ “መጁሥ” مَجُوس የሚለው ቃል ሙዐረብ የሆነ ቃል ሲሆን “ጠንቋይ” “አስማተኛ” “ኮከብ ቆጣሪ” ማለት ነው። በተለምዶ “ዞራስተራውያን” ይባላል፥ እነዚህ ሰዎች እሳት እየተለማመኑ እና በኮከብ እየተመሩ የሚኖሩ ናቸው። አምላካችን አሏህ በትንሣኤ ቀን በመካከላቸው በፍርድ ከሚለያቸው መካከል መጁሦች ናቸው፦
22፥17 “እነዚያ ያመኑት፣ እነዚያም ይሁዳውያን የሆኑ፣ ሳቢያኖችም፣ ክርስቲያኖችም፣ መጁሦች እና እነዚያም ያጋሩ አላህ በትንሣኤ ቀን በመካከላቸው በፍርድ ይለያል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ በእርግጥ ዐዋቂ ነውና”፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَالَّذِينَ هَادُوا وَالصَّابِئِينَ وَالنَّصَارَىٰ وَالْمَجُوسَ وَالَّذِينَ أَشْرَكُوا إِنَّ اللَّهَ يَفْصِلُ بَيْنَهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ

መጁሦች፦ “ሰማይን፣ ብርሃንን፣ ህይወትን፣ ወንድን የፈጠረው “አሁራ” የተባለው አምላክ ሲሆን በተቃራኒው ምድርን፣ ጨለማን፣ ሞት፣ ሴትን የፈጠረው “አንግራ” የተባለው አምላክ ነው” ብለው ሁለት አምላክ ያመልካሉ፥ ይህ የሁለት አምላክ ጣምራ ትምህርት አምላካችን አሏህ፦ “ሁለት አማልክትን አትያዙ! እርሱ ”አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እኔንም ብቻ ፍሩ!” በማለት ይናገራል፦
16፥51 አላህም አለ፦ ”ሁለት አማልክትን አትያዙ! እርሱ ”አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እኔንም ብቻ ፍሩ!”፡፡ وَقَالَ ٱللَّهُ لَا تَتَّخِذُوٓا۟ إِلَٰهَيْنِ ٱثْنَيْنِ ۖ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَإِيَّٰىَ فَٱرْهَبُونِ

ስለ መጁሥ እዚህ ድረስ ካየን ዛንዳ ስለ መጁሥ ከባይብል እስቲ እንይ! በአዲስ ኪዳን ግሪክ ኮይኔ “መጉሥ” μάγος ማለት “አስማተኛ” “ኮከብ ቆጣሪ” “ጠንቋይ” ማለት ነው፥ “በርያሱስ” በግሪክ “ባር-ኤሱስ” Βαρϊησοῦς ማለትም “የኢየሱስ ልጅ” ማለት ሲሆን “መጉን” μάγον ተብሏል። የሐዋርያት ሥራ 13፥6 ተመልከት! የሐዋርያት ሥራ 13፥6 “ጠንቋይ” ለሚለው የገባው ቃል “መጉን” μάγον ነው፥ የመጉሥ ብዙ ቁጥር ደግሞ “መጎኢ” μάγοι ሲሆን መጎኢ የተወለደውን ኢየሱስን ለመጎብኘት ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ካለችው ከፋርሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጥተዋል፦
ማቴዎስ 2፥1 “ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ”። Τοῦ δὲ Ἰησοῦ γεννηθέντος ἐν Βηθλέεμ τῆς Ἰουδαίας ἐν ἡμέραις Ἡρῴδου τοῦ βασιλέως, ἰδοὺ μάγοι ἀπὸ ἀνατολῶν παρεγένοντο εἰς Ἱεροσόλυμα
አለቃ ኪዳነ-ወልድ ክፍሌ ሳምኬት ገፅ 661 እና ሳን ገፅ 848 ላይ “ሠገል” ማለት “ጠንቋይ” ማለት እንደሆነ እና “ሠገል” የሚለው ቃል “ሠገለ” አስጠነቆለ” ከሚል የመጣ ሲሆን “ጥንቆላ” ማለት እንደሆነም አስቀምጠዋል።
ጥንቆላ፣ አስማት እና ኮከብ ቆጠራ መላእክት ከሰማይ ይዘውት የመጡት እንደሆነ መጽሐፈ ሆኖክ 2፥11-23 ይናገራል፥ ዘይገርም!
“ሰብእ” ማለት ደግሞ “ሰው” ማለት ሲሆን በጥቅሉ “ሰብአ ሰገል” ማለት “የጥንቆላ ሰው” ወይም “ጠንቋይ ሰው” ማለት ነው።
ስንክሳር ዘወርኅ ታኅሣሥ 29 ቁጥር 4-5
“ኢየሱስ በተወለደ ጊዜ እነሆ የፍልስፍና ሰዎች ከምሥራቅ መጥተው ወደ ኢየሩሳሌም ደረሱ፥ “ኮከቡን በምሥራቅ አይተን እንሰግድለት ዘንድ መጥተናልና፥ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? እያሉ። እነዚህ ፈላስፎች ከበለዓም ወገን ናቸው፥ እነርሱም በከዋክብት የሚፈላሰፉ ናቸው”።

ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ጻድቃን ሳይሆኑ በከዋክብት የሚፈላሰፉ ጠንቋዮች ናቸው። የማቴዎስ ወንጌል 2፥2 አንድምታው እንዲህ ይላል፦
“ስለምን በኮከብ መራቸው ቢሉ በለመዱት ለመሳብ ኮከብ ያመልኩ ነበርና”።

በግሪኩ “መጎኢ” μάγοι ማለትም “ጠንቋዮች” “አስማተኞች” “ኮከብ ቆጣሪዎች” ማለት ነው፥ በኮከብ እየተመሩ መምጣታቸው ይህ ማሳያ ነው። እጅ መንሻ ይዘው ከሰገዱ በኃላ ወደ አገራቸው ወደ ምስራቅ ሄዱ፦
ማቴዎስ 2፥12 “ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ተረድተው በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ”።

የእነዚህ ሰዎች የቁጥራቸው መጠን “ሦስት ነው” የሚል እና “ሦስት ነገሥታት ጋስፓር፣ ሜልክዮር እና ባልታዛር ናቸው” የሚል ሽታው ባይብል ላይ የለም፥ በተለምዶ ኢየሱስ ሲወለድ እጅ መንሻ ሰተዋል የሚባለው ውሸት ነው፦
ማቴዎስ 2፥11 “ወደ ቤት ሲገቡም ልጁን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት”።

የገቡት “ቤት” ውስጥ እንጂ “ግርግም” ጋር አይደለም፥ ግርግም በረት ውስጥ ወይም ሜዳ ላይ ያለ የእንስሳት መመገቢያ አሸንዳ ነው። ሳባ(የመን) ሆነ ኩሽ(ኢትዮጵያ) የሚገኙት ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ሳይሆን በስተ ደቡብ ነው፦
ማቴዎስ 12፥42 “ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች”።

“ዓዜብ” ማለት “ደቡብ” ማለት እንደሆነ ባይብልን በሥነ-አፈታት ጥናት ላጠና ሰው እንግዳ አይደለም። ለሰሎሞን የተነገረውን እጅ መንሻ ለኢየሱስ በማድረግ መጁሦችን ኢትዮጵያውያን ናቸው ማለት ስሑት ሥነ-አመክንዮ ነው፦
መዝሙር 72፥9-11 “በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፥ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ። የተርሴስ እና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ፤ የዓረብ እና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ። ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል። አሕዛብም ሁሉ ይገዙለታል”።

እዚህ አንቀጽ ላይ “ኢትዮጵያ” ብለው ሆን ብለው ለማደናበር ያስቀመጡት ቃል “ሲዪም” צִיִּ֑ים ሲሆን “የምድረበዳ ሕዝቦች” ማለት ነው፥ ኢትዮጵያ ቢባል እንኳን “ይሰግዳሉ” አለ እንጂ “እጅ መንሻን ያቀርባሉ” አይልም። “ኢትዮጵያ እጅ መንሻን ያቀርባሉ” ቢል እንኳን ዐውዱ እየተናገረ ያለው ለንጉሥ ሰሎሞን እንጂ ለኢየሱስ በፍጹም አይደለም፥ የሳባ ንግሥትን እጅ መንሻ ለንጉሥ ሰሎሞን አምጥታለች፦ 1ኛ ነገሥት 10፥1-1-2 ይመልከቱ!

ሲቀጥል ከባቢሎን ምርኮ በኃላ ለመቅደሱ መልሶ ግንባታ ግብፅ፣ ኩሽ እና ሳባ ወርቅንና ዕጣን አምጥተው ለእስራኤል እንደሚሰግዱ የሚያሳይ እንጂ ስለ ኢየሱስ ሽታው የለውም፦
ኢሳይያስ 60፥6 “የግመሎች ብዛት፥ የምድያምና የጌፌር ግመሎች፥ ይሸፍኑሻል፤ ሁሉ ከሳባ ይመጣሉ፥ ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ የእግዚአብሔርንም ምስጋና ያወራሉ”።
ኢሳይያስ 45፥14 እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ የግብፅ ድካም እና የኢትዮጵያ ንግድ ቁመተ ረጅሞችም የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ፤ ለአንተም ይሆናሉ እጆቻቸውም ታስረው ይከተሉሃል፤ በፊትህም ያልፋሉ፥ ለአንተም እየሰገዱ፦ በእውነት እግዚአብሔር በአንተ አለ፥ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም፡ ብለው ይለምኑሃል”*።

እዚህ አንቀጽ ላይ “ኢትዮጵያ” የሚለው ዕብራይስጡን ብትመለከት የሚለው “ኩሽ” כּ֥וּשׁ ነው። “ኢትዮጵያ” ብለው በዐማርኛ የተረጎሙት በዕብራይስጡ “ኩሽ” כּ֥וּשׁ መሆኑን አስምርበት! ስለዚህ ሰብአ ሰገል ፋርሣውያን እንጂ ኩሻውያን ወይም ሳባውያን በፍጹም አይደሉም፥ ጠንቋይን ቅዱስ የማድረግ አባዜ እና ሁሉም ታሪክ ኢትዮጵያዊ የማድረግ አባዜ ምንኛው እንደተጸናወታቸው ዓይኑን ለገለጠ ሰው ግልጽ ነው። አሏህ ለሁሉም ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ባል እና ሚስት?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥55 ከዚያም መመለሻችሁ ወደ እኔ ነው፥ በእርሱ ትለያዩበትም በነበራችሁት ነገር በመካከላችሁ እፈርዳለሁ፡፡ ثُمَّ إِلَيَّ مَرْجِعُكُمْ فَأَحْكُمُ بَيْنَكُمْ فِيمَا كُنتُمْ فِيهِ تَخْتَلِفُونَ

ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ “ማርያም እና ዮሴፍ ባል እና ሚስት ናቸው ወይም አይደሉም” አይልም፥ ስለ ዮሴፍም ምንም የተጠቀሰ ነገር የለም። በዝምታ የታለፈውን ነገር ሆኖ ሳለ “ማርያም ኢየሱስን ከወለደች በኃላ ድንግል ሆኖ ቀጥላለች አሊያም አግብታ ወልዳለች” አንልም፥ የእርሷ ማግባት አለማግባት የሥነ-መለኮት ትምህርታችን ላይ የሚኖረው አሉታዊ ሆነ አውንታዊ ትርጉም የለውም። ማርያም ከዮሴፍ ጋር ጋብቻ ብትመሠርት ነውር አይደለም፥ ጋብቻ ክቡር ነገር ነውና። በድንግልና እስከ መጨረሻው ብትኖር እሰየው ነው፥ ድንግል በመሆኗ ክብሯ አይቀንስምና። ቅሉ ግን ባይብል ላይ ማርያም እና ዮሴፍ ባል እና ሚስት እንደሆኑ የሚጠቁሙ አናቅጽ አሉ፦
ማቴዎስ 1፥19 እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ። Ἰωσὴφ δὲ ὁ ἀνὴρ αὐτῆς, δίκαιος ὢν καὶ μὴ θέλων αὐτὴν δειγματίσαι, ἐβουλήθη λάθρᾳ ἀπολῦσαι αὐτήν.

እዚህ አንቀጽ ላይ ዐማርኛው ላይ “እጮኛ” ብለው ቢያስቀምጡትም ግሪኩ ግን “አነር” ἀνὴρ ማለትም “ባል” ብሎ ያስቀምጠዋል፥ የተለያየ ስመ ጥር የእንግሊዝኛ ትርጉሞች ግሪኩን በመከተል “ባሏ”her husband” ብለው አስቀምጠዋል። “አነር” ἀνὴρ የሚለው ቃል “ባል” በሚል ብዙ ቦታ ተጠቅሷል፦
ማርቆስ 10፥12 እርስዋም “ባልዋን” ፈትታ ሌላ ብታገባ ታመነዝራለች፡ አላቸው። καὶ ἐὰν αὐτὴ ἀπολύσασα τὸν ἄνδρα αὐτῆς γαμήσῃ ἄλλον, μοιχᾶται.

አንድ ወንድ አንዲትን ሴት ለሚስትነት አጭቶ ከሌላ ብታመነዝር ያ የታጨችለት ወንድ ለፍርድ ሸንጎ ይገልጣትና በድንጋይ ትወገራለች፦
ዘሌዋውያን 20፥10 ማናቸውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ወይም ከባልንጀራው ሚስት ጋር ቢያመነዝር አመንዝራውና አመንዝራይቱ ፈጽመው ይገደሉ።

ዮሴፍ ግን ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ። “ዮሴፍ ለማርያም “ባል” መባሉ ማርያምን ለመጠበቅ ስለሆነ “ጠባቂ” በሚል ይፈታል” የሚል ሙግት ያላቸው ማርያም ለዮሴፍ “ሚስት” መባሏ ዮሴፍን ለመጠበቅ ስለሆነ “ጠባቂት” በሚል ይፈታልን? ውኃ የማያነሳ እና የማይቋጥር ሙግት ነው፦
ማቴዎስ 1፥20 የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና “እጮኛህን” ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ። Ἰωσὴφ υἱὸς Δαυείδ, μὴ φοβηθῇς παραλαβεῖν Μαρίαν τὴν γυναῖκά σου, τὸ γὰρ ἐν αὐτῇ γεννηθὲν ἐκ Πνεύματός ἐστιν Ἁγίου·

እዚህ አንቀጽ ላይ ዐማርኛው ላይ “እጮኛ” ብለው ቢያስቀምጡትም ግሪኩ ግን “ጉኔ” γυνή ማለትም “ሚስት” ብሎ ያስቀምጠዋል፥ የተለያየ ስመ ጥር የእንግሊዝኛ ትርጉሞች ግሪኩን በመከተል “ሚስትህ”your wife” ብለው አስቀምጠዋል። “ጉኔ” γυνή የሚለው ቃል “ሚስት” በሚል ብዙ ቦታ ተጠቅሷል፦
ማቴዎስ 5፥31 “ሚስቱን” የሚፈታት ሁሉ የፍችዋን ጽሕፈት ይስጣት ተባለ። Ἐρρέθη δέ Ὃς ἂν ἀπολύσῃ τὴν γυναῖκα αὐτοῦ, δότω αὐτῇ ἀποστάσιον.

ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቅቶ የጌታ መልአክ እንዳዘዘው ሚስቱን ወሰደ፥ “በኵር” ማለት “መጀመሪያ” ማለት ሲሆን ማርያም የመጀመሪያ ልጅዋን እስክትወልድ ድረስ ዮሴፍ አላወቃትም፦
ማቴዎስ 1፥24 ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቅቶ የጌታ መልአክ እንዳዘዘው አደረገ፤ “እጮኛውንም” ወሰደ። καὶ παρέλαβεν τὴν γυναῖκα αὐτοῦ·
ማቴዎስ 1፥25 የበኵር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ “አላወቃትም”።

በጥንት ዕብራውያን አነጋገር “ማወቅ” በጋብቻ ውስጥ ተራክቦን”sex” ማድረግ ለማሳየት የሚገባ ቃል ነው፦
ዘፍጥረት 4፥1 አዳምም ሚስቱን ሔዋንን “አወቀ”፤ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች።
ዘፍጥረት 4፥17 ቃየንም ሚስቱን “አወቀ”፤ ፀነሰችም፥ ሄኖሕንም ወለደች።
1 ሳሙኤል 1፥19-20 ሕልቃናም ሚስቱን ሐናን “አወቃት”፤ እግዚአብሔርም አሰባት፤ “የመፅነስዋም” ወራት ካለፈ በኋላ ሐና ወንድ ልጅ ወለደች።

እነዚህ አናቅጽ ላይ “ማወቅ” ማለት “ተራክቦ” መሆኑን የሚያስረግጠው ከማወቅ በኃላ “ፅንስ” እና “ውልደት” መከተሉ ነው፥ በተመሳሳይ “አላወቃት” የሚለው ቃል “እስክትወልድ” ከሚለው ከውልደት ጋር ተዛምዶ ስለመጣ ከወለደች በኃላ ያውቃታል ማለትን ያስይዛል። ንጉሥ ዳዊት ሲሸመግል ይበርደው ስለነበር ተኝታ የምታሞቀው ድንግል ሴት ሱነማይቱ አቢሳን አመጡለት፥ ነገር ግን ስላረጀ ተራክቦ ስለማያደርግ “አያውቃትም ነበር” ተብሏል፦
1 ነገሥት 1፥4 ንጉሡ ግን “አያውቃትም ነበር”።

እንግዲህ ሔልቪዲዮስ”Helvidius” እና የቡልጋሪያው ኤጲስ ቆጶስ ቦኖሱስ”Bonosus” 383 ድኅረ ልደት “ማርያም እና ዮሴፍ ባል እና ሚስት ናቸው” በማለት ዲሞራይተስ”Dimoerites” የሚባለው ቡድን መሥርተው ይህንን ሙግት ያቀርባሉ፥ የእነርሱ ሙግትም በ 391 ድኅረ ልደት በካፑአ ጉባኤ”Council of Capua” ተወግዟል። አፓክሪፋ ከሚባሉት አንዱ በሁለተኛ ክፍለ ዘመን የተዘጋጀው የያዕቆብ ወንጌል ማርያም ኢየሱስን ከወለደች በኃላ ከዮሴፍ ጋር በጋብቻ እንደተሳሰረች ያትታል። ይህ ክርስቲያኖችን የሚያወዛግብ ርዕስ ሲሆን እየተከራከሩ በሚወዛገቡት ነገር አሏህ በትንሳኤ ቀን ይፈርዳል፦
3፥55 ከዚያም መመለሻችሁ ወደ እኔ ነው፥ በእርሱ ትለያዩበትም በነበራችሁት ነገር በመካከላችሁ እፈርዳለሁ፡፡ ثُمَّ إِلَيَّ مَرْجِعُكُمْ فَأَحْكُمُ بَيْنَكُمْ فِيمَا كُنتُمْ فِيهِ تَخْتَلِفُونَ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የአብ መምጣት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

13፥41 እኛ ምድርን ከጫፎችዋ የምናጎድላት ኾነን የምንመጣባት መኾናችንን አላዩምን? አላህም ይፈርዳል፡፡ ለፍርዱም ገልባጭ የለውም፡፡ أَوَلَمْ يَرَوْا أَنَّا نَأْتِي الْأَرْضَ نَنقُصُهَا مِنْ أَطْرَافِهَا ۚ وَاللَّهُ يَحْكُمُ لَا مُعَقِّبَ لِحُكْمِهِ

አሏህ ከከተሞችም እነዚያን በአካባቢያችሁ የነበሩትን በእርግጥ በማጥፋት መጥቶባቸዋል፥ አሏህ፦ “የምንመጣባት” ማለቱ እርምጃ መውሰዱ ቁልጭ አርጎ ያሳያል፥ ምድርን ከጫፎችዋ ማጉደል ማለት ከከተሞችም እነዚያን በአካባቢያችሁ የነበሩትን ማጥፋት ማለት እንደሆኑ ታላቁ ሙፈሢር ኢብኑ ከሲር ተናግሯል፦
13፥41 እኛ ምድርን ከጫፎችዋ የምናጎድላት ኾነን የምንመጣባት መኾናችንን አላዩምን? አላህም ይፈርዳል፡፡ ለፍርዱም ገልባጭ የለውም፡፡ እርሱም ምርመራው ፈጣን ነው፡፡ أَوَلَمْ يَرَوْا أَنَّا نَأْتِي الْأَرْضَ نَنقُصُهَا مِنْ أَطْرَافِهَا ۚ وَاللَّهُ يَحْكُمُ لَا مُعَقِّبَ لِحُكْمِهِ ۚ وَهُوَ سَرِيعُ الْحِسَابِ
46፥27 ከከተሞችም እነዚያን በአካባቢያችሁ የነበሩትን በእርግጥ አጠፋን ከክሕደታቸው ይመለሱም ዘንድ አስረጂዎችን መላለስን፡፡ وَلَقَدْ أَهْلَكْنَا مَا حَوْلَكُم مِّنَ الْقُرَىٰ وَصَرَّفْنَا الْآيَاتِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

በባይብል ደግሞ ፈጣሪ እንደሚመጣ መዝሙር 96፥13 ኢሳይያስ 35፥4 ኢሳይያስ 66፥15 ራእይ 1፥4 ራእይ 1፥8 ራእይ 22፥7 ራእይ 22፥12 ላይ ይናገራል፥ ይህ የሚመጣው አንድ አምላክ የፍጥረት ሁሉ አስገኝ ስለሆነ “አብ” ተብሏል። አብ እንደሚመጣ ዳንኤል፦ “በዘመናት የሸመገለው እስኪመጣ ድረስ” በማለት ተናግሯል፦
ዳንኤል 7፥22 በዘመናት የሸመገለው እስኪመጣ ድረስ፥ ፍርድም ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪሰጥ ድረስ።

የዳንኤልን ንግግር ይዘው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ላይ ስለ አብ መምጣት እንደሆነ ተናግረዋል፦
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 10 ቁጥር 13
“ወበእንተ ምጽአተ አብ ይቤ ነቢይ ዳንኤል ወአምጹ መናብርተ ለብሉየ መዋዕል”።

ትርጉም፦ “ነቢዩ ዳንኤል ስለ አብ ማምጣት፦ “በዘመናት ለሸመገለው መናብርት አመጡለት” አለ”።

ዮሐንስ አቡ ቀለምሲስ ስለ ወልድ መምጣል፦ “እነሆ ከደመና ጋር ይመጣል” ብሎ ከተናገረ በኃላ ስለ አብ መምጣት፦ “ያለውና የነበረው “የሚመጣውም” በማለት ተናግሯል፦
ራእይ 1፥7፤ እነሆ ከደመና ጋር ይመጣል።
ራእይ 1፥8 ያለውና የነበረው “የሚመጣውም” ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ፡ ይላል።

የዮሐንስ አቡ ቀለምሲስ ንግግር ይዘው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ላይ ስለ ወልድ እና አብ መምጣት እንደሆነ ተናግረዋል፦
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 10 ቁጥር 18
“ወካዕበመ ነገረ ዮሐንስ አቡ ቀለምሲስ በእንተ ምጽአተ አብ ወወልድ”።

ትርጉም፦ “ሁለተኛም ዮሐንስ አቡ ቀለምሲስ ስለ አብ እና ወልድ መምጣት ተናገረ”።

በተመሳሳይ ዳዊት፦ “እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል” በማለት ስለ አብ መምጣት ተናግሯል፦
መዝሙር 50፥2 ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ “ይመጣል”።

የዳዊትን ንግግር ይዘው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ላይ፦ “ዳዊት፦ “እግዚአብሔር በግልጽ ይመጣል” ብሎ ስለ አብ ተናገረ” በማለት ተናግረዋል፦
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 10 ቁጥር 6
“ዳዊት እግዚአብሔር ገሀደ ይመጽእ አብ ዘበእንቲአሁ ይቤ በእንተ አብ”።

ትርጉም፦ “ዳዊት፦ “እግዚአብሔር በግልጽ ይመጣል” ብሎ ስለ አብ ተናገረ”።

በዘመናት የሸመገለው የተባለው አብ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ሲፈርድ ኢየሱስ በእርሱ ፊት ለሚያምኑት ይመሰክርላቸውን ለካዱት ደግሞ ይመሰክርባቸዋል፦
ዳንኤል 7፥9 ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ፥ በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ።
ማቴዎስ 10፥32-33 ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።

የኢየሱስን ንግግር ይዘው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ላይ፦ “የአብ መምጣት ባይኖር ኖሮ፦ “በሰው ፊት ያመነብኝ እኔም በአባቴ ፊት አምነዋለው፥ በሰው ፊት የካደኝ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ” በአላለም ነበር” በማለት ተናግረዋል፦
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 10 ቁጥር 17
“እመሰ ኢሀሎ ምጽአተ አብ እምኢይቤ ለዘአምነኒ በገጸ ሰብእ አእምኖ በገጸ አቡዬ፥ ወለዘክህደኒ በገጸ ሰብእ እክህዶ በገጸ አቡዬ ዘበሰማያት”

ትርጉም፦ “የአብ መምጣት ባይኖር ኖሮ፦ “በሰው ፊት ያመነብኝ እኔም በአባቴ ፊት አምነዋለው፥ በሰው ፊት የካደኝ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ” በአላለም ነበር”

አንዱ አምላክ አብ በሙሴ ዘመን ከቅዱሳኑ መላእክት ጋር እንደመጣ ተነግሯል፦
ዘዳግም 33፥2 እንዲህም አለ፦ ያህዌህ ከሲና “መጣ”፣ በሴይርም ተገለጠ፣ ከፋራን ተራራ አበራላቸው፣ “ከአእላፋትም ቅዱሳኑ መጣ”፤ በስተ ቀኙም የእሳት ሕግ ነበረላቸው።

“በስተ ቀኙም የእሳት ሕግ ነበረላቸው” የሚለውን ስንረዳ የእሳት ሕግ የተባለው ቶራህ ሲሆን ቅዱሳኑ የተባሉት መላእክት ናቸው፦
ሐዋ. ሥራ 7፥53 በመላእክት ሥርዓት ሕግን ተቀበላችሁ። Who have received the law by the disposition of angels.
ዕብራውያን 2፥2 በመላእክት የተነገረው ቃል ጽኑ ከሆነ።

ከእነዚህ አናቅጽ የምንረዳው የሙሴ ሕግ የወረደው በመላእክት ሥርዓት ሲሆን በመላእክት የተነገረው ቃል ነው፥ ስለዚህ አብ ከቅዱሳኑ መላእክት ጋር ለፍርድ ይመጣል፦
ዘካርያስ 14፥5 አምላኬ ያህዌህም ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ይመጣል።

ስለ አብ ለፍርድ መምጣት በቁና ጥቅስ ማቅረብ ይቻል ነበር፥ ቅሉ ግን አንባቢያንን ማሰልቸት ነው። አብ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ላይ ይህንን ሐቅ ተናግረዋል፦
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 10 ቁጥር 22
“ወአነሂ እብሎሙ እመሰኬ ቦቱ እምቃለ መጻሕፍት ዘይነግር በእንተ ኢመጺአ አብ”

ትርጉም፦ “እኔም ከመጻሕፍት ቃል ስለ አብ አለመምጣት የሚናገር ካለ በሽንገላ ቃል ስለምን አሰናከለኝ?”

አምላካችን አሏህ የፍርዱ ቀን እንደሚመጣ በተከበረ ቃሉ ተናግሯል፥ የአምላካች የአሏህ መምጣት በትእዛዙ ፍርድ ማስተላለፍ እና ውሳኔ መስጠት ያመላክታል። ሙፈሢሮች ያስቀመጡት በዚህ መልኩ ነው፦
89፥22 መላእክትም ሰልፍ ሰልፍ ኾነው ጌታህ በመጣ ጊዜ። وَجَاءَ رَبُّكَ وَالْمَلَكُ صَفًّا صَفًّا
ተፍሢሩ ኢብኑ ከሲር 89፥22 “ጌታህ በመጣ ጊዜ” ማለት በፍጡራኑ በፍርድ መለየት ነው”።
( وجاء ربك ) يعني : لفصل القضاء بين خلقه ،

ስለዚህ አሏህ ለፍርድ መምጣቱ እርርር እና ምርር ብላችሁ ለመንጨርጨር እና ለመንተክተክ ከመቸኮላችሁ በፊት መጻሕፍታችሁን አገላብጣችሁ ማጥናት ይኖርባችኃል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዘላለማዊ ውልደት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥35 ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

በ 325 ድኅረ ልደት የተሰተበሰቡት የኒቂያ ጉባኤ ኢየሱስን፦ “አብን አህሎ እና መስሎ ከአብ ባሕርይ ባሕርይን ወስዶ፤ ከአካሉ አካልን ወስዶ ተገኘ ወይም ከአምላክ የተገኘ አምላክ” ሲሉት በ 381 የተሰበሰቡት የቁስጥንጥንያ ጉባኤ ደግሞ፦ "ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠ አብን አህሎ እና መስሎ ከአብ ያለ እናት ተወለደ" አሉት፥ ይህ አወላደል "ዘላለማዊ ውልደት"eternal generation" ይሉታል። ኢንሻሏህ ለዚህ አስተምህሮት ድምዳሜ ላይ አደረሱን የሚሏቸውን የባይብል አናቅጽ ጥርስ እና ምላሱን እየነቀስንና እያደማን እናየዋለን፦
ምሳሌ 8፥25 ግዕዙ፦ "ወዘንበለ አድባር ይተከሉ፥ ወእምቅድመ አውግር “ወለደኒ”።

ትርጉም፦ "ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ፥ ከኮረብቶች በፊት “ወለደኝ”።

ይህንን ጥቅስ ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ፣ አንግሊካን እና የይሆዋ ምስክሮች ለኢየሱስ ሲያውሉት በተቃራኒው ፕሮቴስታንት፣ የፕሮቴስንታንት ግልባጭ ተሐድሶያውያን እና የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ደግሞ የፈጣሪ ባሕርይ ለሆነው ለጥበብ ያውሉታል።
በግዕዝ “ወለደኒ” ማለት “ወለደኝ” ማለት ሲሆን “ወለደኝ” ማለት “ፈጠረኝ” ማለት እንደሆነ አንድምታው እና ሃይማኖተ-አበው እንቅጩን ፍርጥ አርገው ነግረውናል፦
ምሳሌ 8፥25 አንድምታ፦ “ወለደኒ” ስለ ስጋ “ፈጠረኝ” አልሁ።

ሃይማኖተ-አበው ዘባስልዮስ ምዕራፍ 32 ቁጥር 18
ግዕዙ፦ “ወለደኒ” ይተረጎም በወልደ እግዚአብሔር ወብሂለ “ፈጠረኒ” በእንተ ትስብእቱ።

ትርጉም፦ “ወለደኝ” ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ስለመሆኑ “ፈጠረኝ” ማለት ሰው ስለ መሆኑ ይተረጎማል።

“ወለደኝ” ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ከሆነ ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠ አብን አህሎ እና መስሎ ከአብ ያለ እናት መወለድን ሳይሆን ከድንግል ማርያም መፈጠርን ቁልጭ አርጎ የሚያሳይ ነው፥፦
ዕብራውያን 1፥5 "አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፥ ደግሞም፦ እኔ አባት እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል"።

"ዛሬ" በሚባል ጊዜ ውስጥ ለተፈጠረው ሰው ፈጣሪ "አባት" ሲባል ለፈጠረው ፈጣሪ ደግሞ ያ ፍጡር "ልጅ" ተብሏል፥ ኢየሱስ "ልጅ" የተባለው ከአብ ምንነትና ማንነት ስለወጣ እና ስለተገኘ ቢሆን ኖሮ "መንፈስ ቅዱስም ከአብ የወጣ እና የተገኘ ነው" ስለምትሉ መንፈስ ቅዱስም "ልጅ" ይባል ነበር። ነገር ግን "ልጅ" የተባለበት ትርጉም "ፍጡር" ማለት ነው፥ በአምላክ ልብ ቀድሞውኑ መወሰኑ ለማመልከት ከፍጥረት በፊት እንደተፈተጠረ መናገሩ ጉልኅ ማሳያ የሚሆነው ለዚያ ነው፦
ምሳሌ 8፥22 ግዕዙ፦ "እግዚአብሔር ፈጠረኒ ቀዳሜ ኩሉ ተግባሩ"።

ትርጉም፦ "እግዚአብሔር በቀድሞ ሥራው ሁሉ ፈጠረኝ"

አንድምታው፦ "በአዲስ ተፈጥሮ ከሚፈጥራቸው ምእመናን አስቀድሞ እግዚአብሔር አስቀድሞ ፈጠረኝ"

በአዲስ ኪዳን እግዚአብሔር አዲስ ፍጥረት ከመፍጠሩ በፊት ኢየሱስን በድንግል ማርያም ማሕፀን ውስጥ መፍጠሩን የሚያሳይ ነው፦
አንድምታው፦ "የምእመናን የሥራቸው በኲር እሆን ዘንድ እግዚአብሔር ፈጠረኝ"

የአንጾኪያው ኤዎስጣቴዎስ በ 337 ድኅረ ልደት ይህንኑ ጉዳይ በአጽንዖት እና በአንክሮት ያጠናክርልናል፦
"የመንገዱ መጀመሪያ አድርጎ ጌታ ፈጠረኝ" የሚለው ንግግር የተነገረው በድንግል ማሕፀን ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ የተተከለውን ከሴት የተወለደውን ሰው ነው"።
Ancient Christian Commentary On scriptures page 63.

እሩቅ ሳንሄድ እግዚአብሔር ኢየሱስ የሾመው እኮ በአዲስ ኪዳን ከድንግል ማርያም ከተወለደ በኃላ ነው፥ ነገር ግን መሾሙ እንቅድመ ዓለም በልበ አምላክ ቀድሞውኑ አስቀድሞ ስለተወሰነ፦ "ከጥንቱ ከዘላለም ጀምሮ ተሾምሁ፥ ምድር ከመፈጠርዋ አስቀድሞ" ብሏል፦
ምሳሌ 8፥23 "ከጥንቱ ከዘላለም ጀምሮ ተሾምሁ፥ ምድር ከመፈጠርዋ አስቀድሞ"።

መቼም እምቅድመ ዓለም ሿሚ እና ተሿሚ ካለ አንዱ ጋር ያለው ሌላው ጋር የሌለ ሹመት እና ስዩም አለ ማለት ነው፥ የእስክንድርያው አርጌንስ፦ "አብ በላጭ ገዢ ወልድ ተበላጭ ተገዢ በመሆን "ዘላለማዊ የአገልግሎት መገዛዛት"eternal functional subordination"(EFS) በአብ እና በወልድ መካከል አለ" ለማለት ያስደፈረው "ከጥንቱ ከዘላለም ጀምሮ ተሾምሁ" የሚለው ጥቅስ ነው።
ስንቀጥል ፈጣሪ ኢየሱስን ከድንግል ማርያም በማኅፀኗ ውስጥ ያለ አባት ዘር"sperm cell" ፈጥሮታል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘመጠሊጎን 44፥3
ግዕዙ፦ "ወለሊሁ ሐነፀ ሥጋሁ ውስጠ ከርሠ ድንግል"

ትርጉም፦ “እርሱ ሥጋውን በድንግል ማኅፀን ፈጠረ"

ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 124፥19
ግዕዙ፦ "ንብሎ ፍጡረ እስመ ውእቱ ተወልደ በሥጋ እምብእሲት"

ትርጉም፦ "ከሴት በሥጋ ስለተወለደ "ፍጡር ነው" እንላለን"

ሃይማኖተ-አበው ዘጎርጎርዮስ 35፥6
ግዕዙ፦ "ወዓዲመ ይትበሀል "ፍጡረ" በእንተ ዘኮነ ሥጋ"

ትርጉም፦ "ሥጋ ስለሆነ "ፍጡር" ይባላል"

ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 76፥19
ግዕዙ፦ "ተፈጥረ እምከርሠ ድንግል"

ትርጉም፦ "ከድንግል ማኅፀን ተፈጠርኩኝ"

ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 76፥21
ቄርሎስም አለ፦ "እግዚአብሔር ዘፈጠረኒ እምከርሥ"

ትርጉም፦ "በማኅፀን የፈጠረኝ እግዚአብሔር"

እንግዲህ ፈጣሪ ኢየሱስን ከድንግል ማርያም እንደፈጠረው ካየን ዘንዳ ይህንን ጉዳይ እምቅድመ ዓለም በልበ አምላክ ከእርሷ ማኅፀን እንደፈጠረው ይናገራል፦
መዝሙር 110፥3 ግዕዙ፦ "ወለድኩከ እም ከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽባሕ"

ትርጉም፦ "ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከማኅፀን ወለድኩህ"

"ከማኅፀን ወለድኩህ"I have begotten thee from the womb" የሚለው ቃል ግሪክ ሰፕቱጀንት ላይ የሚገኝ ሲሆን የዕብራይስጡ ማሶሬት፣ አብዛኛው እና አብላጫው እንግሊዝኛ ቅጂዎች እና በዐማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላይ ግን "ከንጋት ማኅፀን በቅዱስ ግርማህ ደምቀህ የጎልማሳነትህን ልምላሜ እንደ ጠል ትቀበላለህ"Arrayed in holy splendor, your youth will come to you like dew from the morning’s womb" ብለው አቀምጠውታል።
"ከርሥ" ማለት "ማኅፀን"the womb" ማለት መሆኑን "እምከርሠ ድንግል" "ውስጠ ከርሠ ድንግል" የሚል ብዙ ቦታ ስላለ ይህ ማኅፀን የድንግል ማርያም ማኅፀን ነው፥ ድንግል ማርያም በልበ አምላክ እምቅድመ ዓለም ነበረች፦
ነገረ-ማርያም ቅዱስ ያሬድ በዚቅ
"ዘእንበለ ይትፈጠር ሰማይ ወምድር፣ ወዘእበለ ይሳረር ምድረ ገነት ሀለወት ስብሕት፣ ቅድስት፣ ወቡርክት ይእቲ ማርያም"

ትርጉም፦ "የተመሰገነች፣ የተቀደሰች እና የተባረከች እርሷ ማርያም ሰማይ እና ምድር ሳይፈጠር እና የገነት ምድር ሳይመሠረት ነበረች"

ስለዚህ ማርያም ሆነ ልጇ በልበ አምላክ አስቀድመው ነበሩ እንጂ በህልውና ደረጃ ሁለቱም የተፈጠሩት ከጊዜ በኃላ ነው፥ ያለ ማርያም ማኅፀን አስቀድሞ ስላልፈጠረው ያሬድ በዚቁ፦ "አዝማንየ አዝማንኪ አምጣንየ አምጣንኪ፥ ማርያም አቀፍኪዮ ወአነ ዮም ወለድኩዮ"

ትርጉም፦ "ዘመኖቼ ዘመኖችሽ መጠኖቼ መጠንሽ ናቸው፥ ማርያም ሆይ! እኔ ዛሬ ወለድኩት አንቺ ደግሞ ታቀፍሺው"

"ዛሬ" የሚለው የጊዜ ተውሳከ ግስ ውልደቱ በጊዜ ውስጥ ጅማሮ እና መነሻ እንዳለው አመላካች ነው፥ ፈጣሪ ከድንግል ሆድ በማውጣት የላከው መልእክተኛ ከእርሷ የተወለደ ነው፦
መዝሙር 22፥9 "አንተ ግን "ከሆድ" አውጥተኸኛልና"።
መዝሙር 22፥10 "ከእናቴ "ሆድ" ጀምረህ አንተ አምላኬ ነህ"።
ገላትያ 4፥4 "የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ"።

"ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ" የማርያም ሆድ ቃል በቃል እንዳልነበረ ሁሉ ኢየሱስም ቃል በቃል ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ አልተወለደም፥ ስለዚህ "ዘላለማዊ ውልደት" የሚለው የክርስትና ተስተምህሮት እንደዚህ ድባቅ ይገባል። መርየም፦ "ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል" ስትል አምላካችን አሏህ በመልአሉ፦ "አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ “ኹን” ይለዋል፥ ወዲውኑም ይኾናል" አላት፦
3፥47 ፦”ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፥ “ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ “ኹን” ይለዋል፥ ወዲውኑም ይኾናል” አላት፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

አምላካችን አሏህ ነገርን መፍጠር በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ብሎ ወዲያውን የሚሆን ከሆነ ለእርሱ እምቅድመ ዓለም ሆነ ድኅረ ዓለም ከእከሌ የወለደው እርሱን የሚመስል እና የሚያህል የባሕርይ ልጅ የለውም፦
19፥35 ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አሏህ ሰሚ ነው!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

64፥4 በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ የምትደብቁትንም የምትገልጡትንም ያውቃል፡፡ አላህም በልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ يَعْلَمُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَيَعْلَمُ مَا تُسِرُّونَ وَمَا تُعْلِنُونَ ۚ وَاللَّهُ عَلِيما بِذَاتِ الصُّدُورِ

አምላካችን አሏህ ማንኛውም ሰው የሚናገረው ይቅርና ሳይናገር የሚናገረውን ነገር ከመናገሩ በፊት በልቡ የሚያስበውን ሁሉ ያውቃል፦
64፥4 በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ የምትደብቁትንም የምትገልጡትንም ያውቃል፡፡ አላህም በልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ يَعْلَمُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَيَعْلَمُ مَا تُسِرُّونَ وَمَا تُعْلِنُونَ ۚ وَاللَّهُ عَلِيمٌ بِذَاتِ الصُّدُورِ

እዚህ ድረስ የአሏህን ዐዋቂነት ከተረዳን ዘንዳ በሐዲስ ላይ የተገለጸውን አጽንዖታዊ እና አንክሮታዊ ንግግር እስቲ በሰከነ እና በሰላ አእምሮ እንመልከት፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 169
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቷል፦ "አሏህ ውብ ድምጽ ያለው ነቢይ ቁርኣንን ሲቀራ እንደሚሰማው ምንንም ነገር አይሰማም"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّهُ سَمِعَ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ مَا أَذِنَ اللَّهُ لِشَىْءٍ مَا أَذِنَ لِنَبِيٍّ حَسَنِ الصَّوْتِ بِالْقُرْآنِ يَجْهَرُ بِهِ ‏"‌‏.‏

እዚህ ጋር "መስማት" የሚለው ቃል የበለጠ "መቅቡል" መሆኑን ለማመልከት የገባ አጽንዖታዊ እና አንክሮታዊ አነጋገር ነው፥ ለምሳሌ አምላካችን አሏህ ሁሉን ነገር ተመልካች ሆኖ ሳለ ልባችንን እና ሥራችንን እንጂ ቅርጻችንን እና ገንዘባችንን እንደማይመለከት በሐዲስ ላይ ተነግሯል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 45, ሐዲስ 42
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ ”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”አሏህ ወደ ልባችሁ እና ወደ ሥራችሁ እንጂ ወደ ቅርጻችሁ እና ወደ ገንዘባችሁ አይመለከትም”፡፡ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّ اللَّهَ لاَ يَنْظُرُ إِلَى صُوَرِكُمْ وَأَمْوَالِكُمْ وَلَكِنْ يَنْظُرُ إِلَى قُلُوبِكُمْ وَأَعْمَالِكُمْ ‏”‏

ያ ማለት ቃል በቃል ቅርጻችንን እና ገንዘባችንን አይመለከትም ማለት እንዳልሆነ ሁሉ መልካም ድምጽ ያለው ነቢይ ቁርኣንን ሲቀራ እንደሚሰማው ምንንም ነገር አይሰማም ማለት ቃል በቃል የሚወሰድ ሳይሆን ጉዳዩን አጽንዖት እና አንክሮት ለመስጠት የመጣ ግነታዊ ንግግር ነው። እሩቅ ስንሄድ በባይብል ጌታ አምላክ ጻድቃንን ይሰማል ያያል፥ በተቃራኒው ከንቱ ነገርን አይሰማም አይመለከተውም፦
1 ጴጥሮስ 3፥12 የጌታ ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸውና፥ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል።
ኢዮብ 35፥13 በእውነት አምላክ ከንቱ ነገርን አይሰማም፥ ሁሉን የሚችል አምላክም አይመለከተውም።

ስለዚህ ጌታ አምላክ የማይሰማው እና የማይመለከተው ነገር ካለ ሁሉን ነገር አይሰማም አይመለከትም ማለት ነው? ሐዲሱን የጦስ ዶሮ ለማድረግ ስትዳዱ የራሳችሁን አረረባችሁ፥ አጭር እና ቀጭን ዓረፍተ ነገር በአንድ ቋት ውስጥ የመፈረጅ አባዜ እንደተጸናወታችሁ ያስታውቅባችኃል። ከርሞ ጥጃ፣ አድሮ ቃሪያ እና ታጥቦ ጭቃ መሆንስ ምንድን ነው? ሆድ ወዶ፣ አፍ ክዶ፣ ክፉ ለምዶ አይሆንምና ከላይ ያለውን መልስ በቅጡ እና በጥሞና አንብቡት!

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
6ኛ ዙር የነሕው ደርሥ!

"አን-ነሕው" اَلنَّحْو ማለት "ሰዋስው"grammar" ማለት ሲሆን የቁርኣንን እና የጥንቱን የአነጋገር ዘይቤ በዐማርኛ እና በእንግሊዝኛ በተደገፈ መልኩ መማር የምትፈልጉ ሁሉ ቦታው ክፍት ነው። ደርሡ (ትምህርቱ) የሚፈጀው 7 ወር ኢንሻሏህ ሲሆን ሦስት ተርም አለው።

፨ የመጀመሪያው ተርም ዐጽመ-አሳብ በኢሥም ላይ የሚያውጠነጥኑ ሲሆኑ 11 ናቸው፥ እነርሱም፦
1. ኢሥሙል ማዕሪፍ፣
2. ኢሥሙል ዐለም፣
3. ኢሥሙል ጂንሥ፣
4. ኢሥሙል ዐደድ፣
5. ኢሥሙ አድ-ደሚር፣
6. ኢሥሙል ኢሻራህ፣
7. ኢሥሙል መውሱል፣
8. ኢሥሙል ኢሥቲፍሃም፣
9. ኢሥሙል ሚልክ፣
10. ኢሥሙል ወስፍ፣
11. ኢሥሙ አዝ-ዘርፍ ናቸው።

፨ የሁለተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በፊዕል ላይ የሚያውጠነጥኑ ሲሆኑ 7 ናቸው፥ እነርሱም፦
1. ሸኽስ፣
2. ዐደድ፣
3. ጂንሥ፣
4. ተወቱር፣
5. ሲጋህ፣
6. ሓላህ፣
7. ጁምላህ ናቸው።

፨ የሦስተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በሐርፍ ላይ የሚያውጠነጥኑ ሲሆኑ 7 ናቸው፥ እነርሱም፦
1. ሐርፉል ጀር፣
2. ሐርፉል አጥፍ፣
3. ሐርፉ አት-ተፍሲል፣
4. ሐርፉል መስደሪይ፣
5. ሐርፉ አን-ነፍይ፣
6. ሐርፉል ሐስድ
7. ሐርፉ አሽ-ሸርጥ ናቸው።

ደርሡ በሳምንት አንዴ የሚለቀቅ ሲሆን በሁለት ሳምንት አንዴ የሁለቱ ሳምንት ጥያቄ ፈተና ይኖራል። ፈተናው ከ 10 የሚወሰድ ሲሆን ከ 6-10 ማምጣት ይጠበቅባችኃል። ከ 6 በታች ሦስት ጊዜ ካመጣችሁ በሰርተፍኬት አናስመርቅም።

የነሕው ደርሥ ቦርድ አባላት አሥር ሲሆኑ ዋና ዋናዎቹ አራት ናቸው፥ እነርሱ፦
1. ወንድም ወሒድ የደርሡ ጦማሪ፣
2. እኅት ሐደል የደርሡ አቅራቢ፣
3. እኅት ሐናን የደርሡ ፈተና አርቃቂ
4. ወንድም መህዲ የደርሡ ፈታኝ እና ውጤት ክፍል ናቸው።

ቦታ ሳይያዝ ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልዎ!

ለመመዝገብ፦
እኅት ሐድልን፦ https://tttttt.me/Ohanw9
እኅት ሐናንን፦https://tttttt.me/han2013
እኅት ረምላን፦https://tttttt.me/REMLANEG
እኅት ሐቢባን፦ https://tttttt.me/Mahbubo
እኅት አበባን፦ https://tttttt.me/temariwa_lji
ወንድም መህዲን፦ወንድምን፦https://tttttt.me/ibnu_See
እኅት ሰላምን፦https://tttttt.me/SelamS9
አኅት ዘሃራን፦https://tttttt.me/Zhara_mustefa
እኅት አበባ፦http://tttttt.me/temariwa_lji

በውስጥ ያናግሩ!
የባሕርይ ልጅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

112፥3 አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

ፈጣሪ ፆታ የሌለው ረቂቅ እና ምጡቅ ማንነት ስለሆነ የመውለድ እና የመወለድ ባሕርይ የለውም፥ በባይብል “መወለድ” በፍካሬአዊ አነጋገር “መፈጠር” የሚለውን ለማመልከት የመጣ ነው። ይሽሩ የእስራኤላውያን የቁልምጫ ስም ሲሆን ይሽሩን ለማመልከት በሁለተኛ መደብ "የወለደህን" የሚለውን በሦስተኛ መደብ "የፈጠረውን" በሚል ተለዋዋጭ ቃል መምጣቱ በራሱ “መወለድ” ማለት “መፈጠር” ማለት ነው፦
ዘዳግም 32፥18 "የወለደህን" አምላክ ተውህ። NIV
ዘዳግም 32፥15 "የፈጠረውን" አምላክ ተወ። NIV

ይህ ሆኖ ሳለ እነ ጳውሎስ ፍቃዱ፦ "ኢየሱስ "የባሕርይ ልጅ" ስለሆነ ለኢየሱስ የሚገባው ቃል በግሪክ ኮይኔ "ሁዮስ" υιος ሲሆን ከኢየሱስ ውጪ ያሉት ደግሞ "የጸጋ ልጅ" ስለሆኑ "ቴክኖን" τέκνον ነው" ይላሉ፥ ይህ እልም ያለ ቅጥፈት ነው። "ሁዮስ" υιος የሚለው ቃል ከኢየሱስ ውጪ ላሉትም ያገለግላል፦
ማቴዎስ 5፥9 የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር "ልጆች" υἱοὶ ይባላሉና።
ማቴዎስ 5፥45 በሰማያት ላለ አባታችሁ "ልጆች" υἱοὶ ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ።
ሉቃስ 6፥35 የልዑልም "ልጆች" υἱοὶ ትሆናላችሁ።
ሉቃስ 20፥36 የትንሣኤም ልጆች ስለ ሆኑ የእግዚአብሔር "ልጆች" υἱοὶ ናቸው።
ሮሜ 8፥14 በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር "ልጆች" υἱοὶ ናቸውና።
ሮሜ 9፥26 የሕያው እግዚአብሔር "ልጆች υἱοὶ ተብለው ይጠራሉ።
ገላትያ 3፥26 የእግዚአብሔር "ልጆች" υἱοὶ ናችሁና።

"ሁዮኢ" υἱοὶ የሚለው ቃል "ሁዮስ" υιος ለሚለው ብዙ ቁጥር ሲሆን "ልጆች" ማለት ነው፥ እነ ጳውሎስ ፍቃዱ ለምን መቅጠፍ አስፈለጋቸው? ክርስቲያኖች ባይብልን "አያነቡም" ብለው ንቀታቸውን እያሳዩአቸው ነው። "ቴክኖን" τέκνον የባሕርይ ልጅነትን ለማመልከት ብዙ ቦታ መጥቷል፦
ማቴዎስ 21፥28 ነገር ግን ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት፤ ወደ አንደኛው ቀርቦ፦ "ልጄ" Τέκνον ሆይ፥ ዛሬ ሂድና በወይኔ አትክልት ሥራ" አለው።
ቆላስይስ 3፥21 አባቶች ሆይ! ልባቸው እንዳይዝል "ልጆቻችሁን" τέκνα አታበሳጩአቸው።

"ቴክና" τέκνα የሚለው ቃል "ቴክኖን" τέκνον ለሚለው ብዙ ቁጥር ሲሆን "ልጆች" ማለት ነው፥ ስለዚህ "ቴክኖን" τέκνον የሚመጣው የጸጋ ልጅነት ለማመልከት ብቻ ነው" የሚለው ንግግር እልም ያለ ቅጥፈት ነው።
በመቀጠል፦ "ባይብል ኢየሱስ የባሕርይ ልጅ እንደሆነ ለማመልከት "ሁዮስ" υιος በሚል ቃል ፊት "ሆ" ὁ ወይም "ቶን" τῶν የሚል አመልካች መስተአምር ሲጠቀም ነገር ግን ከኢየሱስ ውጪ ላሉት በአመልካች መስተአምር አይጠቀምም" የሚል ሁለተኛ ቅጥፈት አላቸው፥ ነገር ግን ከኢየሱስ ውጪ ላሉት አመልካች መስተአምር ይጠቀማል፦
ሮሜ 8፥19 የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን "ልጆች" τῶν υἱῶν መገለጥ ይጠባበቃልና።

"ቶን" τῶν የሚል አመልካች መስተአምር እንደገባ ተመልከት! ሲቀጥል ያለ አመልካች መስተአምር ለኢየሱስም ገብቷል፦
ዮሐንስ 10፥36 "የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ" ስላልሁ ὅτι εἶπον Υἱὸς τοῦ Θεοῦ εἰμι;

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሁዮስ" υιος ከሚለው ፊት ለፊት "ቶን" τῶν ወይም "ሆ" ὁ የሚል አመልካች መስተአምር የለውም፥ እና እንደ እናንተ አባባል ኢየሱስ የጸጋ ልጅ ነው ማለት ነው። እንደ ኦርቶዶክሳውያን ገብርኤል "የእግዚአብሔር ልጅ" ተብሏል፦
ዳንኤል 3፥25 "ወገጹ ለራብዓይ ከመ ወልደ እግዚአብሔር ይመስል"

ትርጉሙ፦ "የአራተኛውም መልክ "የእግዚአብሔርን ልጅ ይመስላል"።

"ላ ባር ኤላሂም"  דָּמֵ֖ה לְבַר־אֱלָהִֽין የሚለውን የዐረማይኩን ማሶሬት በግዕዙ "የአምላክ ልጅ"the Son of God" ብለውታል፥ "ላ" דָּ ማለት አመልካች መስተአምር ነው። እና እንደ እናንተ አባባል ገብርኤል የባሕርይ ልጅ ነው ማለት ነው፦
ግብረ ሕማማት የቅዳሜ ሌሊት ምዕራፍ 57 የነቢዩ ዳንኤል ትንቢት ቁጥር 92 ላይ፦ "የአራተኛው መልክ የእግዚአብሔርን ልጅ ይመስላል"

ኦርቶዶክሳውያን አራተኛ ሰው ሆኖ የታየው መልአክ “ገብርኤል ነው” ብለው ታኅሣሥ አሥራ ዘጠኝ ቀን በዓመት አንዴ ዓመታዊ በዓል ያረጉለታል፥ ስንካር ዘውርኀ ታኅሣሥ 19 እና ድርሳነ ገብርኤል ምዕራፍ 2 ቁጥር 1-2 ተመልከት!
በነገራችን ላይ "የባሕርይ ልጅ" የሚለው እሳቤ ከአንድ ምንነት ዘርን ወስዶ ያንን ምንነት አህሎ እና መስሎ መወለድ ማለት ሲሆን ለሰው የሚውል ቃል ነው፦
ኢሳይያስ 51፥2 ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም...ተመልከቱ! አንድ ብቻውን በሆነ ጊዜ ጠራሁት፥ ባረክሁትም አበዛሁትም።

አብርሃም በማንነት "አንድ" ሆኖ ሳለ እስማኤል እና ይስሐቅ ከእርሱ ማንነት ማንነትን ወስደው ከእርሱ ምንነት ምንነት ወስደው ልጆች ሲሆን አብርሃም ከአንድ ወደ ብዙኃነት ሲመጣ "አበዛሁት" አለው። በግሪካውያን "አምላክ አንድ ነው" ብለው ስለማያምኑ "እኛ የአምላክ ዘር ነን" ብለው ያምናሉ፥ ለምሳሌ፦ ከ 315-310 ቅድመ ልደት ይኖር የነበረው ባለ ቅኔው አራተስ"Aratus" እራሱ ይህንን ይናገር ነበር፦
የሐዋርያት ሥራ 17፥28 "ከእናንተ ከባለ ቅኔዎች አንዳንዶች ደግሞ፦ "እኛ ደግሞ ዘሩ ነንና" ብለው እንደ ተናገሩ። τινες τῶν καθ’ ὑμᾶς ποιητῶν εἰρήκασιν Τοῦ γὰρ καὶ γένος ἐσμέν.

"ጌኑስ" γένος ማለት "ዘር" "ውሉድ"offspring" ማለት ሲሆን ጳውሎስ ከአራተስ ጠቅሶ "የአምላክ ዘር ከሆንን" በማለት አጽድቆላቸዋል፦
የሐዋርያት ሥራ 17፥29 እንግዲህ የአምላክ ዘር ከሆንን..። γένος οὖν ὑπάρχοντες τοῦ Θεοῦ 

ወደ ኢሥላም ከመጣችሁ እንዲህ አይነት ውስብስብ ትምህርት የለም። አሏህ አንድ ነው፥ እርሱ እንደ ፍጡራን የመወለድ እና የመወለድ የለውም፦
112፥1 በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ
112፥3 አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡ لَمْ يَلِدْ ባሕርይوَلَمْ يُولَدْ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ታቦታችን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

11፥112 *እንደ ታዘዝከውም ቀጥ በል! ከአንተ ጋር ያመኑትም ቀጥ ይበሉ፣ ወሰንንም አትለፉ! እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና*፡፡ فَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ وَمَن تَابَ مَعَكَ وَلَا تَطْغَوْا ۚ إِنَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

“ጽሌ” የሚለው የግዕዝ ቃል “ሰሌዳ” ወይም “ፊደል” ማለት ሲሆን የጽሌ ብዙ ቁጥር ደግሞ “ጽላት” ሲሆን “ሰሌዳዎች” ወይም “ፊደሎች” ማለት ነው፥ በዐረቢኛ “ለውሕ” لَوْح ማለት "ፊደል" "ሰሌዳ" ማለት ነው። አምላካችን አሏህ ለሙሳ ቃላትን በፊደል ላይ ጽፎ እንደሰጠው በተከበረ ቃሉ ይናገራል፦
7፥145 *ለእርሱም በሰሌዳዎቹ ላይ ከነገሩ ሁሉ ግሳጼንና ለነገሩም ሁሉ ማብራራትን ጻፍንለት*፡፡ وَكَتَبْنَا لَهُ فِي الْأَلْوَاحِ مِن كُلِّ شَيْءٍ

እዚህ አንቀጽ ላይ "አልዋሕ" أَلْوَاح ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ለውሕ” لَوْح ለሚለው የብዙ ቁጥር ሲሆን "ፊደሎች" "ሰለዳዎች" ማለት ነው። ይህን እሳቦት በፔንታተች በተመሳሳይ መልኩ ተዘግቧል፦
ዘጸአት 24፥12 *ያህዌህም ሙሴን፦ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፥ በዚያም ሁን፤ እነርሱን ታስተምር ዘንድ እኔ የጻፍሁትን ሕግና ትእዛዝ የድንጋይም ጽላት እሰጥሃለሁ አለው*።

“ታቦት” ማለት ደግሞ “ማህደር” “ሰገባ” “ሳጥን” “ማደሪያ” ማለት ሲሆን በዐረቢኛ “ታቡት” تَّابُوت ይባላል፥ አምላካችን አሏህ ስለ "ታቡት" እንዲህ ይለናል፦
2፥248 ነቢያቸውም ለእነርሱ፡- *«የንግሥናው ምልክት ከጌታችሁ የኾነ እርጋታ የሙሳ ቤተሰብና የሃሩን ቤተሰብ ከተውትም ቅርስ በውስጡ ያለበት መላእክት የሚሸከሙት ኾኖ “ሳጥኑ” ሊመጣላችሁ ነው*፡፡ አማኞች ብትኾኑ በዚህ ለእናንተ እርግጠኛ ምልክት አልለ» አላቸው፡፡ وَقَالَ لَهُمْ نَبِيُّهُمْ إِنَّ آيَةَ مُلْكِهِ أَن يَأْتِيَكُمُ التَّابُوتُ فِيهِ سَكِينَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَبَقِيَّةٌ مِّمَّا تَرَكَ آلُ مُوسَىٰ وَآلُ هَارُونَ تَحْمِلُهُ الْمَلَائِكَةُ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ሳጥኑ” ለሚለው ቃል የገባው በአመልካች መስተአምር “አት-ታቡት” التَّابُوت መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። ታቦት የጽላቱ ማህደር ወይም ሰገባ ሲሆን ይህን እሳቦት በፔንታተች በተመሳሳይ መልኩ ተዘግቧል፦
ዘጸአት 25፥10 *ከግራር እንጨትም “ታቦትን” ይሥሩ፤ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን*።
ዘዳግም 10፥5 *ተመልሼም ከተራራው ወረድሁ፥ “ጽላቶችንም በሠራሁት ታቦት ውስጥ አደረግኋቸው” ያህዌህም እንዳዘዘኝ በዚያ ኖሩ*።

ስለ ታቦት እና ጽላት ዝርዝር ማብራሪያ ይህንን ሊንክ ይጫኑ፦ https://tttttt.me/Wahidcom/2645

እኛ ሙሥሊሞች፦ "ታቦት ጣዖት ነው" በፍጹም አላልንም። ምክንያቱም ታቦት የጽላት ማስቀመጫ ሳጥን ነው። ባይሆን የአገራችን የተዋሕዶ ክርስቲያኖች ግን፦ "ጣዖቱን ታቦት ነው" እያሉን ነው፥ ምክንያቱም አንድ ድንጋይ፣ ወርቅ፣ ብረት፣ እንጨት የጸጋ ይሁን የአምልኮ ስግደት ከተሰገደለት ያ ነገር ጣዖት ነው። ያንን ቅርጻ ቅርጽ ለምን የጸጋ ስግደት ትሰግዱለታላችሁ? ስንላቸው "ታቦት ነው" ይሉናል፥ ለታቦት የሰገደ ሰው በባይብል የለም፣ ለታቦት ስገዱ የሚል የለም፣ ሙሴ ከግራር እንጨት የሠራው ታቦት አንድ ሲሆን ጠፍቷል።

ሲጀመር አገራችን ያሉ ታቦታት የሚባሉት የሙሴ አይነት ታቦት አይደሉም፥ የሙሴ ታቦት በወርቅ የተለበጠ እንጂ እንደ አገራችን የፋርኒሽ ቅብ አይደለም። ይዘታቸው አንድ አይነት አይደሉም።
የሥላሴ ታቦት የአምልኮ ስግደት እንዲሁ የማርያም፣ የመላእክት እና የቅዱሳን ታቦታት የጸጋ ስግደት ይሰገድላቸዋል፥ ታዲያ የሚመለክ እና የሚሰገድለት እንጨት በምን አግባብ ነው ለአንድ ሙሥሊም "ታቦታችን" የሚያሰኘው? የጋራ እሴት ያልሆነን የሺርክ ተግባራትን ሆነ ቁሳቁስ ወደ ራስ በማስጠጋት በአገናዛቢ ዘርፍ "የእኛ" ማለት ወሰን ማለፍ ነው፦
11፥112 *እንደ ታዘዝከውም ቀጥ በል! ከአንተ ጋር ያመኑትም ቀጥ ይበሉ፣ ወሰንንም አትለፉ! እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና*፡፡ فَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ وَمَن تَابَ مَعَكَ وَلَا تَطْغَوْا ۚ إِنَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

"ታቦታችን" የሚሉትን ሰዎች ባለማወቅ ከሆነ ከስህተታቸው እንዲታረሙ በትህትና ማስተማር ነው! እየተሳደቡ አርማለው ማለት ስህተትን በስህተት መድገም ነውና ከጥቅሙ ጉዳቱ ይብሳል። ነገር ግን እያወቁ ለስም፣ ለዝና፣ ለክብር እና ለመወደድ የሚያደርጉም ካሉ በእሳት እየተጫወቱ ከመሆንም ባሻገር ሌላውን እያጠመሙ ስለሆነ አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሕይወት ሰጠው

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥33 «ሰላምም በእኔ ላይ ነው፡፡ በተወለድሁ ቀን፣ በምሞትበትም ቀን፣ ሕያው ኾኜ በምቀሰቀስበትም ቀን፡፡» وَالسَّلَامُ عَلَيَّ يَوْمَ وُلِدتُّ وَيَوْمَ أَمُوتُ وَيَوْمَ أُبْعَثُ حَيًّا

"ሄአውቶ" ἑαυτῷ ድርብ ተውላጠ ስም ሲሆን "ራስ"own self" ማለት ነው፥ አንድ ምንነት የራሱ ፈቃድ፣ ማንነት፣ እኔነት፣ አንተነት፣ እርሱነት እንዳለው አመላካች ነው፦
ያዕቆብ 1፥14 ነገር ግን እያንዳንዱ "በራሱ" ምኞት ሲሳብ እና ሲታለል ይፈተናል።
ፊልጵስዩስ 2፥3 እያንዳንዱ ባልንጀራው "ከራሱ" ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር።

ዲያብሎስ "ከራሱ" ይናገራል ማለት እና ሊቀ ካህናት ቀያፋ የተናገረ "ከራሱ" አይደለም ማለት ዲያቢሎስ ሆነ ቀያፋ እራሳቸው የቻለ ማንነት እንዳላቸው አመላካች ነው፦
ዮሐንስ 8፥44 ሐሰትን ሲናገር "ከራሱ" ይናገራል።
ዮሐንስ 11፥51 ይህንም የተናገረ "ከራሱ" አይደለም።

በተጨማሪም የጠራው ፈሪሳዊም አይቶ "በራሱ" ይህንን አሰበ፦
ሉቃስ 7፥39 "ይህስ ነቢይ ቢሆን ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች እንዴትስ እንደ ነበረች ባወቀ ነበር፥ ኃጢአተኛ ናትና" ብሎ "በራሱ" ἑαυτῷ አሰበ።

ፈሪሳዊ በራሱ ያሰበው የራሱ ፈቃድ፣ ማንነት፣ እኔነት፣ አንተነት፣ እርሱነት ስላለው ነው፥ ስለዚህ እያንዳንዱ "በራሱ" ምኞት የሚመኘው፣ እያንዳንዱ ባልንጀራው "ከራሱ" ይልቅ እንዲሻል በትሕትና የመቁጠር ዐቅም ያለው፣ ፈሪሳዊ በራሱ ማሰብ የቻለው ፈጣሪ ሕይወትን ለሁሉም ስለሰጣቸው ነው። ፈጣሪ እያንዳንዱ ሕያው ነገር በራሱ እዲኖር ሕይወትን ይሰጣል፦
የሐዋያት ሥራ 17፥25 እርሱም ሕይወትን እና እስትንፋስን ሁሉንም ለሁሉ ይሰጣልና።

በተመሳሳይ ወልድ "በራሱ" የራሱ ፈቃድ፣ ማንነት፣ እኔነት፣ አንተነት፣ እርሱነት ያለው ነው፥ ይህ ማንነት ከ-"ራሱ" ምንም ማድረግ ስለማይችል የፍጡር ማንነት ነው፦
ዮሐንስ 5፥30 እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም።

አዳም ከአፈር ከተፈጠረ በኃላ ሕያው እንዲሆን መንፈስ ቅዱስ እንደተነፋበት ሁሉ ኢየሱስም ከማርያም ተፈጥሮ ሕያው እንዲሆን መንፈስ ቅዱስ ወደ ማርያም ማኅፀን መጥቷል። ከእርሷ የተፀነሰው ፅንስ ሕያው የሆነው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና፦
ሉቃስ 1፥35 መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል።
ማቴዎስ 1፥20 ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና።

አብ የራሱ ማንነት፣ እኔነት፣ አንተነት፣ እርሱነት እራሱን የቻለ ሕይወት አለው፦
ዮሐንስ 6፥57 ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን።

ወልድ ወደ ህልውና የመጣው ከአብ የተነሳ ነው፥ ወልድ የራሱ እኔነት እንዲኖረው አብ ሕይወትን ሰጠው፦
ዮሐንስ 5፥26 አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና።

ወልድ ሕይወትን በስጦታ ያገኘ ሃልዎት ከሆነ ሕይወት ከመሰጠቱ በፊት ሕይወት አልባ ስለሆነ በባዶነት የተቀደመ ነው፥ ሕይወት የተሰጠው ማንነት እና ምንነት መነሻ እና ጅማሮ ስላለው ፍጡር ነው። አንድምታ፦ "ሕይወት የባሕርይው ይሆን ዘንድ ሕይወትን ሰጠው" ሲል የሂፓፑ አውጉስጢዮስ ደግሞ ሕይወት ሰጠው ማለት "እርሱ(አብ) ወልድን ወልዶታል" ማለት ነው በማለት ይናገራል፦
፨ እንዲህ አለ፦ ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልን? በአጭሩም እላለሁኝ፦ "እርሱ(አብ) ወልድን ወልዶታል"
Augustine on the Gospel of John. Tractates (Lectures) 19 number 13

አብ ረቂቅ እና ምጡቅ ስለሆነ ለወልድ ሕይወት በመስጠት ፈጥሮታል ማለት ነው፥ ወልድ የአብ ግኝት ስለሆነ የአብ ጥገኛ ነው። ይህንን የሂፓፑ አውጉስጢዮስ ያጠናክርልናል፦
፨አብ በራሱ ሕይወት ያለው እንጂ ከወልድ አይደለም፥ ወልድ ግን በራሱ ሕይወት ያለው ከአብ ነው። ወልድ በራሱ እንዲኖር ከአብ የተወለደ ነው፥ ነገር ግን አብ በራሱ እንዲኖር አልተወለደም።
Augustine on the Gospel of John. Tractates (Lectures) 19 number 13

አብ የማንም ጥገኛ ስላልሆነ በራሱ ሕይወት ያለው እንጂ ከወልድ ሕይወት አልተሰጠውም፥ ወልድ ግን ከአብ የተሰጠ ሕይወት ስላገኘ አብ ፈጥሮታል፦
፨ ልክ እርሱ እንደሚለው፦ "አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው ወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ወልዶታል" ማለቱ ነው።
Augustine on the Gospel of John. Tractates (Lectures) 19 number 13

አብ ወልድን የፈጠረው ከማርያም ማኅፀን ነው፦
መዝሙር 110፥3 ግዕዙ፦ "ወለድኩከ እም ከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽባሕ"

ትርጉም፦ "ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከማኅፀን ወለድኩህ"

"ከማኅፀን ወለድኩህ"I have begotten thee from the womb" የሚለው ቃል ግሪክ ሰፕቱጀንት ላይ የሚገኝ ነው፥ "ከርሥ" ማለት "ማኅፀን"the womb" ሲሆን ከድንግል ማኅፀን መፈጠሩን ተናግሯል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 76፥19
ግዕዙ፦ "ተፈጥረ እምከርሠ ድንግል"

ትርጉም፦ "ከድንግል ማኅፀን ተፈጠርኩኝ"

ኢየሱስ ማሕፀን ውስጥ ሕይወት የተሰጠው ፍጡር ስለሆነ በሕይወት የሚኖረው በእግዚአብሔር ኃይል ነው፦
2 ቆሮንቶስ 13፥4 ነገር ግን በእግዚአብሔር ኃይል በሕይወት ይኖራል።

ኢየሱስ አብ ሕይወት ከሰጠው በኃላ ይሞት እና ድጋሚ ሕይወት እንደሚቀበል እራሱ ተናግሯል፦
ዮሐንስ 10፥17 ሕይወቴን "ዳግም" እወስድ ዘንድ አኖራታለውና ስለዚህ አብ ይወደኛል። διὰ τοῦτό με ὁ Πατὴρ ἀγαπᾷ ὅτι ἐγὼ τίθημι τὴν ψυχήν μου, ἵνα πάλιν λάβω αὐτήν.

"ፓሊን" πάλιν ማለት "ድጋሚ" "ሁለተኛ" "ዳግም"again" ማለት ነው፥ ድጋሚ ሕይወቱን እንደሚቀበል መናገሩ በራሱ መጀመሪያ ሕይወት እንደተሰጠው አመላካች ነው። "አኖራታለውና" ማለቱ ወልድ ሕይወቱን በጽድቅ ለሚፈርደው ለአብ እንደሚሰጥ ነው፥ ነፍሱን ከሰጠ በኃላ ይሞታል። ከሞተ በኃላ "ድጋሚ" ሕይወትን ከአብ ይቀበላል፦
ዮሐንስ 10፥18 እኔ "በራሴ"(of Myself) አኖራለው እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ "ዳግምም" ልቀበላት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ። οὐδεὶς ἦρεν αὐτὴν ἀπ’ ἐμοῦ, ἀλλ’ ἐγὼ τίθημι αὐτὴν ἀπ’ ἐμαυτοῦ. ἐξουσίαν ἔχω θεῖναι αὐτήν, καὶ ἐξουσίαν ἔχω πάλιν λαβεῖν αὐτήν· ταύτην τὴν ἐντολὴν ἔλαβον παρὰ τοῦ Πατρός μου.

ለወልድ ሕይወትን የሰጠው አብ እስከሆነ ድረስ ከአብ ውጪ ማንም ሕይወቱን አይወስዳትም፥ ወልድ ከአብ የተሰጠውን ሕይወት ለአብ፦ "ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለው" ብሎ ማኖር(መስጠት) ሆነ በትንሳኤ ዳግም(ድጋሚ) ሕይወትን መቀበል ስልጣን የተቀበለው ከአብ በትእዛዝ ነው። ወልድ ከራሱ ምንም ማድረግ የማይችል እና ሕይወት አልባ የነበረ ሆኖ ሳለ ሕይወት የተሰጠው ፍጡር ነው፥ አብ አስገኚ ወልድ ደግሞ ግኝት ከሆነ ከፈጣሪ ሕይወት የተሰጠው ማንነትና ምንነት እንዴት ይመለካል? አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አርጋለችን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥105 ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ናቸው፥ እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ናቸው፡፡ إِنَّمَا يَفْتَرِي الْكَذِبَ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ۖ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَاذِبُونَ

ድንግል ማርያም ነሐሴ 15 ወይም 16 ቀን "ወደ ሰማይ አርጋለች" ተብሎ በካቶሊክ፣ በመለካውያን ኦርቶዶክስ እና በጽብሓውያን ኦርቶዶክስ ይታመናል፥ ከሐዋርያት ኅልፈት በኃላ ያሉት የቤተክርስቲያን አበው ስለ ማርያም ድንግልና፣ ንጽህና፣ ምስጋና ይናገሩ እንጂ ስለ አማሟቷ ምንም የተናገሩት ነገር የለም። የማርያም ዕርገት ለመጀመሪያ ጊዜ የተወሳው በአራተኛው ክፍለ ዘመን በኤጵፋኒዮስ ዘሳልሚስ ነው፦
"እርሷ ልክ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ድንግል እንደነበረው፣ ሁልጊዜም እንዳለው፣ እንደ ተወሰደ እና ሞትን ግን እንዳላየው ልክ ኤልያስን ነች"።
The Panarion of Epiphanius of Salamis book II De Fide Page 641

ይህንን ይበል እንጂ "ዐርጋ ይሁን ተሰውታ ማንም በትክክል አያውቅም" ብሏል፦
"ዐርጋ ይሁን ተሰውታ ማንም በትክክል አያውቅም"።
The Panarion of Epiphanius of Salamis book II De Fide Page 635

ቅሉ ግን ከ 505 እስከ 571 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው ኢትዮጵያዊ ያሬድ እና ከ 675 እስከ 749 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው የደማስቆ ዮሐንስ ስለ ማርያም እርገት"assumption" ተናግረዋል፥ ነገር ግን ባይብል ላይ ስለ ማርያም እርገት ይቅርና ስለ አሟሟቷ ምንም ሽታው የለም። ይህ አላዋጣ ሲላቸው፦ "ቁርኣን ማርያም እና ልጇ እንዳረጉ ይናገራል" ብለው አረፉት፥ እንደ ጓያ ነቃይ የፊት ለፊቱን ብቻ በመመልከት "ይደግፈናል" ብለው የሚናገሩለት ጥቅስ ይህ ነው፦
23፥50 የመርየምን ልጅ እና እናቱንም ተአምር አደረግናቸው፥ የመደላደል እና የምንጭ ባለቤት ወደ ኾነች ከፍተኛ ስፍራም አስጠጋናቸው፡፡ وَجَعَلْنَا ابْنَ مَرْيَمَ وَأُمَّهُ آيَةً وَآوَيْنَاهُمَا إِلَىٰ رَبْوَةٍ ذَاتِ قَرَارٍ وَمَعِينٍ

እዚህ አንቀጽ "አስጠጋን" ለሚለው የገባው ቃል "አወይና" آوَيْنَا ነው እንጂ "ረፈዕና" رَفَعْنَا አይደለም፥ ሲቀጥል "ረብዋህ" رَبْوَة ማለት "ከፍተኛ ስፍራ" ማለት ሲሆን ዝናብ እና ፍሬ ያለበትን የአትክልት ቦታ ያመለክታል፦
2፥265 የእነዚያም የአላህን ውዴታ ለመፈለግ እና ለራሳቸው እምነትን ለማረጋገጥ ገንዘቦቻቸውን የሚለግሱ ሰዎች ምሳሌ በተስተካከለች "ከፍተኛ ስፍራ" ላይ እንዳለች አትክልት፣ ብዙ ዝናብ እንደነካት ፍሬዋንም እጥፍ ኾኖ እንደሰጠች፣ ዝናብም ባይነካት ካፊያ እንደሚበቃት ብጤ ነው፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡ وَمَثَلُ الَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُمُ ابْتِغَاءَ مَرْضَاتِ اللَّهِ وَتَثْبِيتًا مِّنْ أَنفُسِهِمْ كَمَثَلِ جَنَّةٍ بِرَبْوَةٍ أَصَابَهَا وَابِلٌ فَآتَتْ أُكُلَهَا ضِعْفَيْنِ فَإِن لَّمْ يُصِبْهَا وَابِلٌ فَطَلٌّ ۗ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ከፍተኛ ስፍራ" ለሚለው የገባው ቃል "ረብዋህ" رَبْوَة መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። ይህ ከፍተኛ ስፍራ በሌላ አንቀጽ "ሩቅ ስፍራ" ተብሏል፦
19፥22 ወዲያውኑም አረገዘችው፡፡ በእርሱም (በሆዷ ይዛው) ወደ "ሩቅ ስፍራ" ገለል አለች፡፡ فَحَمَلَتْهُ فَانتَبَذَتْ بِهِ مَكَانًا قَصِيًّا

እዚህ ሩቅ ስፍራ መደላደል የሆነ ፍራፍሬ እና ምንጭ የሆነ ወንዝ ያለበት ነው፦
19፥24 ከበታቿም እንዲህ ሲል ጠራት፦ "አትዘኝ! ጌታሽ ከበታችሽ ትንሽን ወንዝ በእርግጥ አድርጓል"፡፡ فَنَادَاهَا مِن تَحْتِهَا أَلَّا تَحْزَنِي قَدْ جَعَلَ رَبُّكِ تَحْتَكِ سَرِيًّا
19፥25 የዘምባባይቱንም ግንድ ወደ አንቺ ወዝውዣት! በአንቺ ላይ የበሰለን የተምር እሸት ታረግፍልሻለችና፡፡ وَهُزِّي إِلَيْكِ بِجِذْعِ النَّخْلَةِ تُسَاقِطْ عَلَيْكِ رُطَبًا جَنِيًّا

ሢሠልስ ቀደምት ሠለፎች ሆኑ የእነርሱ መንሃጅ ያላቸው ሙፈሢሮች ያስቀመጡት በዚህ መልክ እና ልክ ነው፦
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 23፥50
"አል አውፊ እንደተረከው ኢብኑ ዐባሥ እንዲህ አለ፦ "የመደላደል እና የምንጭ ባለቤት ወደ ኾነች ከፍተኛ ስፍራም አስጠጋናቸው" በሚለው "ምንጭ" የተባለው "የሚንቦሎቦል ውኃ" ሲሆን ይህም ወንዝ የላቀው አሏህ፦ "ጌታሽ ከበታችሽ ትንሽን ወንዝ በእርግጥ አድርጓል" በማለት ያወሳው ነው። رواه العوفي ، عن ابن عباس في قوله : ( وآويناهما إلى ربوة ذات قرار ومعين ) ، قال : المعين الماء الجاري ، وهو النهر الذي قال الله تعالى : ( قد جعل ربك تحتك سريا )

ስለዚህ "ቁርኣን ማርያም እና ልጇ እንዳረጉ ይናገራል" የሚለው ጥራዝ ነጠቅ ወሬ ያልሰከነ እና የደፈረሰ ስሑት ሙግት ነው። ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአሏህ አንቀጾች የማያምኑት ናቸው፥ እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ናቸው፦
16፥105 ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ናቸው፥ እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ናቸው፡፡ إِنَّمَا يَفْتَرِي الْكَذِبَ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ۖ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَاذِبُونَ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ደውል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

17፥64 ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምፅህ አታል፡፡ وَاسْتَفْزِزْ مَنِ اسْتَطَعْتَ مِنْهُم بِصَوْتِكَ

“ዐዝፍ” عَزْف የሚለው ቃል “ዐዘፈ” عَزَفَ ማለትም “ሞዘቀ” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን “ሙዚቃ” ማለት ነው፥ የሙዚቃ መጫወቻ በነጠላ “ሚዕዘፍ” مِعْزَف ሲባል በብዜት “መዓዚፍ” مَعَازِف ይባላል። ሸይጧን በድምፁ ሰዎችን የሚወሰውሰው እና የሚነሽጠው በዘፈን እና በሙዚቃ መሣሪያ ነው፦
17፥64 ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምፅህ አታል፡፡ وَاسْتَفْزِزْ مَنِ اسْتَطَعْتَ مِنْهُم بِصَوْتِكَ
ተፍሢሩል ኢብኑ ዐባሥ 17፥64
"ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምፅህ አታል" በድምፅህ ሲል በሙዚቃ መሣሪያ ድምፅ፣ በዘፈን ድምፅ እና በሌላ አጸያፊ ነገር ማለቱ ነው"።
{ مَنِ ٱسْتَطَعْتَ مِنْهُمْ بِصَوْتِكَ } بدعوتك ويقال بصوت المزامير والغناء وسائر المناكير.

"ጀረሥ" جَرَس የሚለው ቃል "ጀረሠ" جَرَسَ ማለትም "ደወለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ደውል" ማለት ነው፥ "አጅራሥ" أَجْرَاس ደግሞ የጀረሥ ብዙ ቁጥር ሲሆን አጠቃላይ የሙዚቃ መሣሪያን የሚወክል ነው። ጀረስ የሸይጧን መዝሙር ነው፥ የሙዚቃ መሣሪያ ያለበት ቤት መላእክት አይገቡም፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 37 , ሐዲስ 159
አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ “የአላህ መልክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”ጀረሥ የሸይጧን መዝሙር ነው”። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْجَرَسُ مَزَامِيرُ الشَّيْطَانِ
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 36 , ሐዲስ 18
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ “የአላህ መልክተኛም”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ ”መላእክት ጀረሥ ያለበት ቤት አይገቡም”። وَقَالَتْ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ “‏ لاَ تَدْخُلُ الْمَلاَئِكَةُ بَيْتًا فِيهِ جَرَسٌ ‏

እዚህ ድረስ ከተግባባን ጎትቶ ጎትጉቶ በአንድ ቋት ውስጥ የመፈረጅ አባዜ የተጠናወታቸው ሚሽነሪዎች ያቀረቡትን ሐዲስ ማየት ይቻላል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 1 , ሐዲስ 2
የምእመናን እናት ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ ሓሪሥ ኢብኑ ሂሻም"ረ.ዐ." የአሏህ መልእክተኛን"ﷺ" እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፥ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" ሆይ! ወሕይ እንዴት ነው የሚመጣልዎት? ብሎ ጠየቃቸው፥ የአሏህ መልክተኛም”ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አንዳንድ ጊዜ “እንደ” ደወል ድምፅ ይመጣልኛል"። عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ الْمُؤْمِنِينَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ الْحَارِثَ بْنَ هِشَامٍ ـ رضى الله عنه ـ سَأَلَ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ يَا رَسُولَ اللَّهِ كَيْفَ يَأْتِيكَ الْوَحْىُ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ أَحْيَانًا يَأْتِينِي مِثْلَ صَلْصَلَةِ الْجَرَسِ

እዚህ ሐዲስ ላይ የተጠቀሰው ቃል "እንደ ደውል ድምፅ" የሚል ሆኖ ሳለ ሐሳውያን "ደውል" የምትለዋን ቃል ብቻ ይመዙና በመለጠቅ "ደውል የሰይጣን መዝሙር ነው፥ መላእክት ደውል ያለበት ቤት አይገቡም" ከሚሉት ዘገባዎች ጋር ሊያምታቱ ይሞክራሉ፥ “አንድ ቃልን ለሁለት የተለያዩ ነገሮችን የሚውለውን እንደ አንድ ነገር አርጎ መውሰድ "የማወላወል ሕፀፅ"fallacy of equivocation" ነው። "ጀረስ" جَرَسٌ እኮ እራሱ መሣሪያው ሲሆን "ሚሥለ ሶልሶለቲል ጀረሥ" مِثْلَ صَلْصَلَةِ الْجَرَس ደግሞ "እንደ ደውል ድምፅ" ማለት ነው፥ ከደውል ምሳሌ የተወሰደው ድምፁ ብቻ ሆኖ ሳለ "ደውል" በሚለው ቃል ላይ መነሻ የሆነውን "እንደ" የሚለውን መስተዋድድ ለምን መዝለል አስፈለገ? ኢማም አሥ ሡዩጢይ በዚህ መልክ እና ልክ አስቀምጠውታል፦
አል ኢትቃን ፊ ዑሉሙል ቁርኣን
"እንደ ደውል ድምፅ" የተባለው የመልአኩ ጂብሪል የክንፉ እንቅስቃሴ ድምፅ ነው"።

ተጨማሪ ናሙና ከሐዲስ ማየት ይቻላል፥ "ትርንጎ" እና "ተምር" ተክል እንጂ ሰዎች አይደሉም። ቅሉ ግን "እንደ" በሚል መስተዋድድ የተወሰነ ነገርን ለመግለጽ መጥተዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 66, ሐዲስ 84
አቢ ሙሣ እንደተረከው፦ ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ቁርኣንን የሚቀራ እና የሚተገብር አማኝ "እንደ" ትርንጎ ነው፥ ሽታው መልካም እና ጣዕሙ ጣፋጭ ጥሩ ነው። ቁርኣንን የማይቀራ እና ግን የሚተገብር አማኝ ደግሞ "እንደ" ተምር ነው፥ ሽታ የሌለው እና ጣዕም ያለው ነው"። عَنْ أَبِي مُوسَى، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ الْمُؤْمِنُ الَّذِي يَقْرَأُ الْقُرْآنَ وَيَعْمَلُ بِهِ كَالأُتْرُجَّةِ، طَعْمُهَا طَيِّبٌ وَرِيحُهَا طَيِّبٌ، وَالْمُؤْمِنُ الَّذِي لاَ يَقْرَأُ الْقُرْآنَ وَيَعْمَلُ بِهِ كَالتَّمْرَةِ، طَعْمُهَا طَيِّبٌ وَلاَ رِيحَ لَهَا

"እንደ ትርንጎ" ማለት እና "እንደ ተምር" ማለት "ትርንጎ" እና "ተምር" ማለት ነውን? "አይ" ካላችሁ እግዲያውስ ከላይ ያለውንም ሐዲስ በዚህ ቀመር እና ስሌት ተረዱት! ሌላ ናሙና ተመልከቱ! ኢየሱስ አንበሳ ተብሏል፥ ዲያብሎስም አንበሳ ተብሏል፦
ራእይ 5፥5 እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ።
1 ጴጥሮስ 5፥8 ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ "እንደ" ሚያገሣ "አንበሳ" ይዞራልና።

ስለዚህ እንደ እናንተ ስሑት ኂስ ኢየሱስ ዲያብሎስ ነው? ቅሉ ግን "እንደ" የሚለውን መስተዋድድ መዝለል የለብንም፥ ያልሞተ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላል፦
መክብብ 9፥4 ያልሞተ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላል።

እዚህ ጋር አንበሳ የተባለው ኢየሱስ ከሆነ ከኢየሱስ ያልሞተ ውሻ ይሻላል ብለን እንሞግታችሁ? "አንበሳ" የተባለ ሁሉ ኢየሱስ ነው" ተብሎ አይደመደምም፦
2 ጢሞቴዎስ 4፥17 ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ፥ ከአንበሳ አፍም ዳንሁ።

እዚህ አንቀጽ ላይ "አንበሳ" የተባለው አንዳንዶች "ሰይጣን ነው" ሲሉ፣ አንዳንዶች "የዱር አንበሳ ነው" ሲሉ፣ ሌሎች "ኔሮ ቄሳር ነው" ሲሉ፣ ሌሎች "ሄሉዩስ ቄሳር ነው" ሲሉ፣ ሎሎች ደግሞ "እለእክንድሮስ ነው" ይላሉ፥ አዘለም አቀፈ ኢየሱስ አንበሳ የተባለበት የዱር እንስሳት፣ ሰይጣን፣ ኔሮ፣ ሄሉዩስ፣ እለእክንድሮስ በተባሉበት ሒሣብ እንዳልሆነ ሁሉ ደውል እና እንደ የደውል ድምፅ የተባለውን አታምታቱ!
አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሥሉስ አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ

"ሥሉስ" ማለት ሦስት ማለት ሲሆን "ሥሉስ አምላክ" ማለት "ሦስት አምላክ" ማለት ነው፥ ሥላሴ ሦስት አምላክ ስለመሆኑ በቁና ማስረጃ እስቲ እናቅርብ፦

፨ሰይፈ ሥላሴ ዘረቡዕ ምዕራፍ 4 ቁጥር 31
“መለኮት በአካል ሦስት ሲሆን በባሕርይ አንድ ነው”።

፨ ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 22
“ሦስት ልዑላን ገዢዎች ናቸው”።

፨ ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 23
“ሦስት ጌቶች ናቸው”።

፨ ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 26
“ሦስት ነገሥታት አንድ አገዛዝ ናቸው”።

፨ ሰይፈ ሥላሴ ዘረቡዕ ምዕራፍ 4 ቁጥር 52
“እነዚህ ገዢዎች በገጽ ሦስት በፈቃድ አንድ ናቸው”።

፨ ሰይፈ ሥላሴ ዘረቡዕ ምዕራፍ 4 ቁጥር 21
"እግዚአብሔር ሦስት ሲሆን አንድ፥ አንድ ሲሆን ሦስት የሚሆን እርሱ አንድ ቅዱስ ነው።

አንቀጸ እምነታቸው ላይ "አምላክ ሦስት ነው" የሚል እያለ ዓይናቸውን በጨው አጥበው "አምላክ ሦስት ነው" አንልም የሚሉት ነገርስ?
አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም