ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ምንኩስና

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

57፥27 "የፈጠሩዋትንም ምንኩስና በእነርሱ ላይ አልጻፍናትም" وَرَهْبَانِيَّةً ابْتَدَعُوهَا مَا كَتَبْنَاهَا عَلَيْهِمْ

አምላካችን አሏህ ከሙሣ በኃላ መልእክተኞችን ኢልያስ፣ ዩኑስ እና ስማቸው ያልተጠቀሱ አከታትሎ ልኳል፥ ከእነርሱ በኃላ ለመርየም ልጅ ለዒሣ ኢንጅልን በመስጠት አስከትሎ ልኳል፦
57፥27 ከዚያም በዱካዎቻቸው ላይ መልክተኞቻችንን አስከታተልን፣ የመርየምን ልጅ ዒሳንም አስከተልን፣ ኢንጂልንም ሰጠነው። ثُمَّ قَفَّيْنَا عَلَىٰ آثَارِهِم بِرُسُلِنَا وَقَفَّيْنَا بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ وَآتَيْنَاهُ الْإِنجِيلَ

በመቀጠል በዒሣ ቀዳማይ ተከታዮች በሐዋርያት ልቦች ውስጥ መለዘብን እና እዝነትን አደረገ፦
57፥27 በእነዚያም በተከተሉት ልቦች ውሰጥ መለዘብን እና እዝነትን አደረግን። وَجَعَلْنَا فِي قُلُوبِ الَّذِينَ اتَّبَعُوهُ رَأْفَةً وَرَحْمَةً

"ቢድዓህ" بِدْعَة ደግሞ "በደዐ" بَدَّعَ ማለትም "ፈጠረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ፈጠራ” ማለት ነው፥ ቅሉ ግን ከሐዋርያት ኅልፈት በኃላ የተነሱት የዒሣ ተከታዮች ዒሣ እና ሐዋርያቱ ያላስተማሩትን "ምንኩስና" ፈጠሩ፦
57፥27 "የፈጠሩዋትንም ምንኩስና በእነርሱ ላይ አልጻፍናትም" وَرَهْبَانِيَّةً ابْتَدَعُوهَا مَا كَتَبْنَاهَا عَلَيْهِمْ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ፈጠሩ" ለሚለው የገባው ቃል "ኢብተደዑ" ابْتَدَعُو መሆኑን አብባቢ ልብ ይበል! "ረህባኒያህ" رَهْبَانِيَّة የሚለው ቃል "ረሂበ" رَهِبَ ማለትም "መነኮሰ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ምንኩስና"monasticism" ማለት ነው።
"ራሂብ" رَاهِب ማለት “መነኩሴ"monk" ማለት ነው፥ የራሂብ ብዙ ቁጥር ደግሞ “ሩህባን” رُهْبَان ሲሆን “መነኮሳት” ማለት ነው። ምንኩስና ቢድዓ እንጂ አሏህ የደነገገው ሕግ ስላልሆነ "አልጻፍናትም"(አልደነገግናትም) በማለት ይናገራል፥ ምንኩስናን የፈጠሩት ለእዩልኝ እና ለስሙልኝ ሳይሆን የአሏህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ ነው፦
57፥27 ግን የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ ፈጠሩዋት፥ ተገቢ አጠባበቋንም አልጠበቋትም፡፡ إِلَّا ابْتِغَاءَ رِضْوَانِ اللَّهِ فَمَا رَعَوْهَا حَقَّ رِعَايَتِهَا

በብሕትውና ገዳም ውስጥ መኖር "ምንኩስና" ይባላል። "ባሕቲት" ማለት "ብቻ" ማለት ሲሆን "ብሕትውና" ማለት "ብቸኝነት" ማለት ነው፥ "ባሕታዊ" ማለት ደግሞ "ብቸኛዊ" ማለት ነው፦
መዝሙር 25፥16 "እስመ "ባሕታዊ" ወነዳይ አነ"

ትርጉም፦ "እኔ ብቻዬን እና ችግረኛ ነኝ"

ይህ የብቸኝነት ኑሮ የሚገፉበት ቦታ "ገዳም" ይባላል፥ "ገዳም" የሚለው ቃል "ገደመ" ማለትም "ከለለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የተከለለ ምድረ በዳ" ማለት ነው፦
መዝሙር 65፥11"ወይጸግቡ ጠላተ "ገዳም"

ትርጉም፦ "ምድረ በዳውም" ስብን ይጠግባል"

የገዳም እና የምንኩስና ሕይወት የጀመረው ግብጻዊ ታላቁ እንጦስ"Anthony the Great" በ 270 ድኅረ ልደት ነው፥ እርሱ እና ከእርሱ በኃላ የተነሱት መነኮሳት የምድረ በዳ አበው"Desert Fathers" ይባላሉ። የምንኩስና እሳቤ ከሚያቀነቅኑት የቤተክርስቲያን አበው የእስክንድርያው አርጌንስ፣ የእስክንድርያው አትናቴዎስ፣ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ የቂሳርያው ባስሊዎስ፣ የሂፓፑ አውግስቲኒዮስ፣ የሮሙ ጄሮም፣ የእስክንድርያው መቃርስ ተጠቃሽ ናቸው።

ምንኩስና የፈጣሪ መመሪያ እንዳልሆነ የገባው መነኩሴ ጆቪኒአን"Jovinian" በ 390 ድኅረ ልደት "ምንኩስና አያስፈልግም" በማለቱ በሮሙ ሳውርዮስ እና በሚለኑ አንብሮስ በ 393 ድኅረ ልደት ተወግዟል።
በ 480 ድኅረ ልደት ከሮም፣ ከአንጾኪያ፣ ከቁስጥንጥንያ፣ ከቂሳርያ፣ ከኪልቂያ ተሰደው ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ተሰዓቱ ቅዱሳን መነኮሳት ሲሆኑ ብዙ ቦታ ገዳማትን መሥርተዋል፥ በተለይ ስመ ጥር ገዳማታት አቡነ አረጋዊ የመሠረቱት ደብረ ዳሞ ገዳም እና አቡነ ጰንጤሌዎን የመሠረቱት ጰንጤሌዎን ገዳም ነው።

ከመነኮሳቱ በተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ነቢይነት ያመኑትን አሏህ ምንዳቸውን ወፍቋቸዋል፦
57፥27 ከእነርሱም ለእነዚያ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጠናቸው፥ ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፡፡ فَآتَيْنَا الَّذِينَ آمَنُوا مِنْهُمْ أَجْرَهُمْ ۖ وَكَثِيرٌ مِّنْهُمْ فَاسِقُونَ

ምንኩስና ጅማሬው ተማሉሏዊነት"mysticism" የነበረ ሲሆን የምድረ በዳ አባቶችም ምንኩስናን የፈጠሯት የአሏህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ ነበር፥ ነገር ግንከመነኮሳቱ ብዙዎቹ አመጸኞች በመሆን ተገቢ አጠባበቋንም አልጠበቋትም።
አንድ ሰው ለአኺራ የሚያዳብረውን ፍቅር፣ ትህትና፣ ደግነት፣ ለጋስነት፣ ቸርነት፣ ትእግስት ወዘተ የሚለማመደው በዲንያህ ላይ እያለ ከሰው ጋር በሚኖረው ማኅበራዊ መስተጋብር ነው፥ ገዳም ከተገባ ግን ፍቅር፣ ትህትና፣ ደግነት፣ ለጋስነት፣ ቸርነት፣ ትእግስት መለማመድ እንዴት ይችላል? ከሰው ተገልሎ ገዳም ውስጥ መግባት ከፈተና ሽሽት ነው። አምላካችን አሏህ በትዳር መሰተርን ፈቅዶ ዝሙትን ማድረግ መከልከሉ፣ ንግድን መነገድ ፈቅዶ አራጣን መብላት መከልከሉ፣ መጠጥን መጠጣት ፈቅዶ ኸምርን መጠጣት መከልከሉ፣ ምግብን መብላት ፈቅዶ እሪያን መብላት መከልከሉ፣ እርሱን እንድናመልክ አዞን ጣዖትን ማምለክ መከልከሉ ፈተና አይደለምን? ባዘዘን መልካም ነገር እና በከለከለው ክፉ ነገር ይፈትነናል፦
21፥35 ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ለመፈተንም በክፉ እና በበጎ እንፈትናችኋለን፡፡ ወደ እኛም ትመለሳላችሁ፡፡ كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَنَبْلُوكُم بِالشَّرِّ وَالْخَيْرِ فِتْنَةً ۖ وَإِلَيْنَا تُرْجَعُونَ

ከፈተና ለመሸት መገለል ፋይዳ የለውም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቍጥቋጥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥17 እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

መሢሕ ከዳዊት እና ከእሴይ ሥር የሚያቆጠቁጥ ሰው ነው፥ ይህ ሰው ለፈጣሪ ባሪያ ስለሆነ ፈጣሪ እርሱን "ባርያዬ" ይለዋል፦
ዘካርያስ 3፥8 እነሆ እኔ ባሪያዬን "ቍጥቋጥ" አወጣለሁ።
ዘካርያስ 6፥12 የሠራዊት ጌታ ያህዌህ እንዲህ ይላል፦ እነሆ ስሙ "ቍጥቋጥ" የሚባል ሰው በስፍራው ይበቅላል።

የሚበቅለው "ሰው" መባሉን ልብ አድርግ! ይህ ሰው ስለሚያቆጠቁጥ የማዕረግ ስሙ "ቍጥቋጥ" ተብሏል፦
ኤርምያስ 23፥5 እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ "ቍጥቋጥ" የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ያህዌህ።
ኤርምያስ 33፥15 በዚያም ዘመን በዚያም ጊዜ ለዳዊት የጽድቅን ቍጥቋጥ አበቅልለታለሁ
ኢሳይያስ 11፥1 ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፥ ከሥሩም "ቍጥቋጥ" ያፈራል።

ኢሳይያስ ላይ "ቍጥቋጥ" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "ኔጼር" ‏נֵ֫צֶר‎ ሲሆን ኤርሚያስ እና ዘካርያስ ላይ ደግሞ "ጻማዕ" צֶ֣מַח ብለውታል፥ ይህ መሢሕ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ሲኖር በነቢያት ማለትም በኢሳይያስ፣ በኤርሚያስ እና በዘካርያስ "ቁጥቋጦ" የተባለው ትንቢት ተፈጸመ፦
ማቴዎስ 2፥23 በነቢያት፦ "ናዝራዊ" ይባላል" የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።

"ናዝራዊ" የሚለው ቃል በግሪኩ "ናዞራይኦስ" Ναζωραῖος ሲሆን ይህም ቃል "ኔጼር" ‏נֵ֫צֶר‎ ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል የተገኘ ነው፥ መሢሑ ፈጣሪ የሚያስነሳው ሰው እና ከእሴይ ሥር የሚያቆጠቁጥ "ቍጥቋጥ" ነው። ይህ ሆኖ ሳለ ክርስቲያኖች "ይህ ቍጥቋጥ እራሱ ያህዌህ ነው" በማለት ይዋሻሉ፥ እንደ ማስረጃ አድርገው የሚጠቅሱት ጥቅስ ይህንን ነው፦
ኤርምያስ 23፥6 በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ የሚጠራበትም ስም፦ "ያህዌህ ጽድቁኑ" ተብሎ ነው።

፨ሲጀመር ዐውዱን በአጽንዖት እና በአንክሮት ካየነው ለዳዊት ጻድቅ "ቍጥቋጥ" መሢሑ ሲነሳ ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ "የሚጠራበት" የተባለው ተባታይ አንቀጽ "እስራኤል" እንጂ መሢሑን በፍጹም አይደለም። ይህንን በተመሳሳይ ሰዋስው ሌላ ቦታ ተቀምጧል፦
ኤርምያስ 33፥16 በዚያም ዘመን ይሁዳ ይድናል ኢየሩሳሌምም ተዘልላ ትቀመጣለች፥ የምትጠራበትም ስም፦ "ያህዌህ ጽድቁኑ" ተብሎ ነው።

"ኢየሩሳሌም" የሚለው ቃል "እስራኤል" በሚል ተለዋዋጭ ቃል መምጣቱን ልብ አድርግ! "የምትጠራበት" የተባለችው አንስታይ አንቀጽ እርሷ "ያህዌህ ጽድቁኑ" ተብሎ ነው፥ ስለዚህ "ያህዌህ ጽድቁኑ" ተብሎ የተጠራው መሢሑ ነው" ብሎ መሞገት እጅግ ሲበዛ የዐውድ ክፍል እና የሰዋሰው አወቃቀር በቅጡ ያልተረዳ ሰው ሙግት ነው።

፨ሲቀጥል "ጽድቁኑ" צִדְקֵֽנוּ ማለት "ጽድቃችን" ማለት ሲሆን "ጽድቃችን" በሚል ቃል ላይ "ያህዌህ" የሚለው ስም ለማጫፈር ስለመጣ "እስራኤል" ወይም "ኢየሩሳሌም" ያህዌህ አይሆኑም፥ ምክንያቱም "እስራኤል" ወይም "ኢየሩሳሌም" ቦታ እስከሆኑ ድረስ የቦታ ስም ላይ "ያህዌህ" የሚለው ስም ለማጫፈር ይመጣል፦
ዘፍጥረት 22፥14 አብርሃምም ያንን "ቦታ" "ያህዌህ ይርኤ" ብሎ ጠራው።

"ይርኤ" יִרְאֶ֑ה ማለት "ያያል" ማለት ሲሆን "ያያል" በሚል ቃል ላይ "ያህዌህ" የሚለው ስም ለማጫፈር ስለመጣ ቦታው ያህዌህ ነውን? እንቀጥል፦
ዘጸአት 17፥15፤ ሙሴም "መሠዊያ" ሠራ፥ ስሙንም "ያህዌህ ንሲ" ብሎ ጠራው።

"ንሲ" נִסִּֽי ማለት "ዓላማዬ" ማለት ሲሆን "ዓላማዬ" በሚል ቃል ላይ "ያህዌህ" የሚለው ስም ለማጫፈር ስለመጣ መሠዊያው ያህዌህ ነውን? እንቀጥል፦
መሳፍንት 6፥24 ጌዴዎንም በዚያ ለያህዌህ "መሠዊያ" ሠራ፥ ስሙንም "ያህዌህ ሻሎም" ብሎ ጠራው።

"ሻሎም" שָׁל֑וֹם ማለት "ሰላም" ማለት ሲሆን "ሰላም" በሚል ቃል ላይ "ያህዌህ" የሚለው ስም ለማጫፈር ስለመጣ መሠዊያው ያህዌህ ነውን? እንቀጥል፦
ሕዝቅኤል 48፥35 የከተማይቱ ስም "ያህዌህ ሻማህ" ተብሎ ይጠራል።

"ሻማህ" שָֽׁמָּה ማለት "በዚያ" ማለት ሲሆን "በዚያ" በሚል ቃል ላይ "ያህዌህ" የሚለው ስም ለማጫፈር ስለመጣ ከተማይቱ ያህዌህ ናትን?

፨ሢሰልስ ዋናው የሙግታችን ነጥብ መሢሑ "ያህዌህ ጽድቁኑ" መባሉ ያህዌህ ካስደረገው ኢየሩሳሌም "ያህዌህ ጽድቁኑ" ስለተባለች ያህዌህ ናትን? "ያህዌህ" የሚለው ስም ለማጫፈር የመጣባቸው ቦታ፣ መሠዊያ እና ከተማ ያህዌህ ናቸውን?
ስለዚህ መሢሑ ከሰው የተገኘ ቁጥቋጥ እና ሰው ሆኖ ሳለ "ፈጣሪ ነው" ብሎ ማለት ክህደት ነው፦
5፥17 እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ከሁሉ ይበልጣል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

87፥1 ከሁሉ በላይ የሆነዉን ጌታህን ስም አሞግሥ። سَبِّحِ ٱسْمَ رَبِّكَ ٱلْأَعْلَى

"ሜጋስ" μέγας ማለት "ታላቅ" ማለት ሲሆን ገላጭ ቅጽል"Adjective" ነው፥ የሜጋስ አንጻራዊ ገላጭ ቅጽል "ሜይዞን" μεῖζόν ሲሆን ይህም አንጻራዊ ገላጭ ቅጽል የደረጃን ብልጫ ለማሳየት አገልግሎት ላይ ውሏል፦
ማቴዎስ 11፥11 በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል። ὁ δὲ μικρότερος ἐν τῇ βασιλείᾳ τῶν οὐρανῶν μείζων αὐτοῦ ἐστιν.

እዚህ አንቀጽ ላይ መጥምቁ ዮሐንስን በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚያንሰው "ይበልጠዋል" ለሚለው የገባው ቃል "ሜይዞን" μείζων ሲሆን በላጩም ተበላጩም በባሕርይ "ሰው" ስለሆኑ የደረጃ ብልጫን የሚያመልክት ነው። በተቃራኒው ደግሞ "ሜይዞን" μεῖζόν የሚለው ቃል የባሕርይ መመላለጥን ለማመልከት አገልግሎት ላይ ውሏል፦
ማቴዎስ 12፥6 ነገር ግን እላችኋለሁ ከመቅደስ "የሚበልጥ" ከዚህ አለ። λέγω δὲ ὑμῖν ὅτι τοῦ ἱεροῦ μεῖζόν ἐστιν ὧδε.

እዚህ አንቀጽ ላይ "የሚበልጥ" ለሚለው የገባው ቃል "ሜይዞን" μεῖζόν ሲሆን በላጩ ኢየሱስ ሰው ሲሆን ተበላጩ መቅደስ ደግሞ ድንጋይ በድንጋይ ላይ የተነባበረ ግዑዝ ነገር ነው፥ ይህ የባሕርይ መበላለጥን ያሳያል። ሰው፣ እንስሳ፣ እጽዋት፣ ማዕድናት በባሕርይ የተለያዩ ናቸው፥ የሰው ኑባሬ"being" ሰው ብቻ ነው። እዚህ ድረስ ከተግባባን ከሁሉ በላይ ሁሉን የፈጠረ አንድ አምላክ አብ ከሁሉ ይበልጣል፦
ዮሐንስ 10፥29 የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል። ὁ Πατήρ μου ὃ δέδωκέν μοι πάντων μεῖζόν ἐστιν

እዚህ አንቀጽ ላይ "ይበልጣል" ለሚለው የገባው ቃል "ሜይዞን" μεῖζόν ሲሆን በላጩ አብ ሲሆን ተበላጩ ደግሞ ሁሉም ነው፥ ኢየሱስ አብ ስላልሆነ "ሁሉ" በሚል ቃላት ውስጥ ኢየሱስ ስለሚካተት አብ ኢየሱስን በባሕርይ ይበልጠዋል። ኢየሱስ፦ "ከ"እኔ" አብ ይበልጣል" ብሏል፦
ዮሐንስ 14፥28 "ከ"እኔ" አብ ይበልጣልና። ὁ Πατὴρ μείζων μού ἐστιν.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ይበልጣል" ለሚለው የገባው ቃል "ሜይዞን" μείζων ሲሆን በላጩ አብ ሲሆን ተበላጩ ደግሞ ኢየሱስ ነው፥ "ከ" የሚለው መስተዋድድ መነሻ ቅጥያ የሆነለት "እኔ" የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም የኢየሱስ ሙሉ "እኔነትን" ቁልጭ አርጎ ያሳያል፦
ኤፌሶን 4፥6 ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም "አባት" አለ።

ከሁሉ በላይ የሚሆን አንድ አምላክ የሁሉም ማለትም የኢየሱስም አባት ነው፥ "አብ" ማለት "አባት" ማለት ሲሆን ይህም የሁሉም "አባት" አንድ አምላክ እና ከሁሉ በላይ የሆነ፣ ከሁሉም የሚበልጥ ነው። ከኢየሱስ ሙሉ ለሙሉ እኔነት አብ በባሕርይ ይበልጣል፥ ምክንያቱም አብ የወልድ አስገኚ፣ ፈጣሪ፣ ሕይወት ሰጪ ሲሆን ወልድ ደግሞ ግኝት፣ ፍጡር፣ ሕይወት ተቀባይ ነውና፦
ዮሐንስ 5፥26 አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና።

ስለዚህ ከሁሉ በላይ የሆነዉን አንዱን አምላክ አሏህን እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው፦
87፥1 ከሁሉ በላይ የሆነዉን ጌታህን ስም አሞግሥ። سَبِّحِ ٱسْمَ رَبِّكَ ٱلْأَعْلَى

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ነቢዩ ኢልያሥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

37፥123 ኢልያሥም በእርግጥ ከመልእክተኞቹ ነው፡፡ وَإِنَّ إِلْيَاسَ لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ

ነቢዩ ኢልያሥ አምላካችን አሏህ ከላካቸው መልእክተኞች እና ከመልካሞቹ አንዱ ነው፦
37፥123 ኢልያሥም በእርግጥ ከመልእክተኞቹ ነው፡፡ وَإِنَّ إِلْيَاسَ لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ
6፥85 ዘከሪያንም፣ የሕያንም፣ ዒሳንም፣ ኢልያሥንም መራን፡፡ ሁሉም ከመልካሞቹ ናቸው፡፡ وَزَكَرِيَّا وَيَحْيَىٰ وَعِيسَىٰ وَإِلْيَاسَ ۖ كُلٌّ مِّنَ الصَّالِحِينَ

ነቢዩ ኢልያሥም ለሕዝቦቹ፦ "አላህን አትፈሩምን? በዕልን ትገዛላችሁን? ከሰዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነውንም አምላክ ትተዋላችሁን? አሏህን ጌታችሁን እና የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁን ጌታ ትተዋላችሁን? አላቸው፦
37፥124 ለሕዝቦቹ፦ "አላህን አትፈሩምን?" ባለ ጊዜ አስታውስ። إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ أَلَا تَتَّقُونَ
37፥125 በዕልን ትገዛላችሁን? ከሰዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነውንም አምላክ ትተዋላችሁን? أَتَدْعُونَ بَعْلًا وَتَذَرُونَ أَحْسَنَ الْخَالِقِينَ
37፥126 አላህን ጌታችሁን እና የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁን ጌታ ትተዋላችሁን? اللَّهَ رَبَّكُمْ وَرَبَّ آبَائِكُمُ الْأَوَّلِينَ

"በዕል" بَعْلً ማለት "በኣል" ሲሆን የጣዖት ስም ነው፥ የኢልያሥ ሕዝብ ጌታቸው እና የቀድሞዎቹ አባቶቻቸውን ጌታ አሏህን በብቸኝነት ማምለክ ትተው በዕልን አመለኩ። ነቢዩ ኢልያሥ ይዞት የመጣውን መልእክት ሙኽለሲን የአሏህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ ሌሎቹ አስተባበሉት፥ ስለዚህ እነርሱ ለቅጣት የሚጣዱ ናቸው፦
37፥127 አስተባበሉትም፡፡ ስለዚህ እነርሱ ለቅጣት የሚጣዱ ናቸው፡፡ فَكَذَّبُوهُ فَإِنَّهُمْ لَمُحْضَرُونَ
37፥128 ንጹሕ የተደረጉት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡ إِلَّا عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ

"ኢኽላስ" إِخْلَاص‎ ማለት "ከሙገሳ እና ከወቀሳ ነጻ ሆኖ ለአሏህ የሚቀርብ መተናነስ፣ መጎናደድ፣ ማጥራት" ማለት ሲሆን በቀልቡ ኢኽላስ ያለው የአሏህ ባሪያ በፋዒል "ሙኽሊስ" مُخْلِص በመፍዑል "ሙኽለስ" مَخْلَص ይባላል፥ የሙኽለስ ብዙ ቁጥር "ሙኽለሲን" مُخْلَصِين ነው። አምላካችን አሏህ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ ስለ እርሱ መልካም ዝናን ተለወለት፦
37፥129 በእርሱ ላይም በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንለት፡፡ وَتَرَكْنَا عَلَيْهِ فِي الْآخِرِينَ
37፥130 ሰላም በኢልያሢን ላይ ይሁን፡፡ سَلَامٌ عَلَىٰ إِلْ يَاسِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ኢልያሢን" إِلْ يَاسِين የሚለው ስም "ኢልያሥ" إِلْيَاس ለሚለው ተለዋዋጭ ስም ነው፥ ለምሳሌ፦ "ሢኒን" سِينِين የሚለው ስም "ሠይናእ" سَيْنَآء إِلْيَاسَ ለሚለው ተለዋዋጭ ስም እንደሆነው ማለት ነው፦
23፥20 "ከሲና" ተራራም የምትወጣን ዛፍ በቅባት እና ለበይዎችም መባያ በሚኾን ዘይት ተቀላቅላ የምትበቅልን አስገኘንላችሁ”፡፡ وَشَجَرَةً تَخْرُجُ مِن طُورِ سَيْنَاءَ تَنبُتُ بِالدُّهْنِ وَصِبْغٍ لِّلْآكِلِينَ
95፥2 “በሢኒን ተራራም እምላለሁ”፡፡ وَطُورِ سِينِينَ

ልክ "ሰላም በኢብራሂም ላይ ይሁን" እንዳለው "ሰላም በኢልያሥ ላይ ይሁን" እንደ ማለት ነው፦
37፥109 ሰላም በኢብራሂም ላይ ይሁን፡፡ سَلَامٌ عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 37፥130
ويقال : ميكال ، وميكائيل ، وميكائين ، وإبراهيم وإبراهام ، وإسرائيل وإسرائين ، وطور سيناء ، وطور سينين .

በሌላ መልኩ "ያሢን" يَاسِين በሚለው ቃል ላይ "ኢል" إِلْ የሚለው መነሻ ቅጥያ በሌላ ቂርኣት ለምሳሌ፦ በናፊዑል መደኒይ፣ በኢብኑ አሚሩ አድ-ዲመሽቂይ፣ በየዕቁብ አል የመኒይ "አል" آل ማለትም "ቤተሰብ" "ተከታይ" በሚል ሲቀሩት "አል-ያሢን" آل يَاسِين ማለትም "የኢልያሥ ተከታይ" ይሆናል፥ ልክ በጅምላ "ሰላም በመልክተኞቹም ላይ ይሁን" እንደሚባለው "ሰላም በኢልያሥ ተከታይ ላይ ይሁን" ማለት ነው፦
37፥181 ሰላም በመልክተኞቹም ላይ ይሁን። وَسَلَامٌ عَلَى الْمُرْسَلِينَ
ተፍሢሩል ጀላለይን 37፥130
{ سَلَٰمٌ } منا { عَلَىٰ إِلْ يَاسِينَ } قيل هو (إلياس) المتقدّم ذكره، وقيل: هو ومن أمن معه فجمعوا معه تغليباً، كقولهم للمهلب وقومه: المهلبون، وعلى قراءة (آل ياسين) بالمدّ أي أهله: المراد به إلياس أيضاً.

"ኢሕሣን" إِحْسَٰن ማለት "አሏህን እንደምታየው አርገህ ማምለክ፥ አሊያም አሏህ እንደሚያይህ አርገህ ማምለክ" ማለት ሲሆን የዲን ሦስተኛው ደረጃ ነው፥ "ኢሕሣን" إِحْسَٰن ያለው የአሏህ ባሪያ "ሙሕሢን" مُحْسِن ሲባል የሙሕሢን ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሙሕሢኒን" مُحْسِنِين ነው። አምላካችን አሏህ ሙሕሢኒን የሚባሉ ባሮቹን ይመነዳል፥ በእርግጥም ኢልያሥ ከምእመናን የሆነ የአሏህ ባሪያ ነው፦
37፥131 እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ
37፥132 እርሱ በእርግጥ ከምእመናን ባሮቻችን ነው፡፡ إِنَّهُ مِنْ عِبَادِنَا الْمُؤْمِنِينَ

አምላካችን አሏህ ሙኽለሲን፣ ሙሕሢኒን፣ ሙእሚኒን ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ወንድማማች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

49፥10 ምእመናን ወንድማማች ናቸው፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ

"ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلٰهَ إِلَّا اللّٰه ጠንካራ ዘለበት ነው፥ በጣዖት ክደን በአሏህ ስናምን እራሳችንን ለአሏህ እንሰጣለን፦
2፥256 "በጣዖትም የሚክድ እና በአላህ የሚያምን ሰው ለእርሷ መበጠስ የሌላትን "ጠንካራ ዘለበት" በእርግጥ ጨበጠ"፡፡ فَمَن يَكْفُرْ بِالطَّاغُوتِ وَيُؤْمِن بِاللَّهِ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ لَا انفِصَامَ لَهَا
31፥22 "እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ ፊቱን ወደ አላህ የሚሰጥም ሰው "ጠንካራን ዘለበት" በእርግጥ ጨበጠ"፡፡ وَمَن يُسْلِمْ وَجْهَهُ إِلَى اللَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ

እዚህ አንቀጽ "የሚሰጥ" ለሚለው የገባው ቃል እራሱ "ዩሥሊም" يُسْلِمْ መሆኑ በራሱ "ሙሥሊም" مُسْلِم ማለት የላ ኢላሀ ኢለል ሏህ ዘለበት በትክክል ዐውቆ እራሱ ለአሏህ የሰጠ ማለት ነው፥ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" የሚለውን የአሏህን ገመድ የያዘ ሰው በዘር፣ በብሔር፣ በዘውግ፣ በቋንቋ፣ በባህል አይለያይም፦
3፥103 የአላህን ገመድ ሁላችሁም ያዙ! አትለያዩም። وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا ۚ

"ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" በዘር፣ በብሔር፣ በዘውግ፣ በቋንቋ፣ በባህል ጠበኞች የነበሩትን ሊያስተሳስር የሚችል የአሏህ ፀጋ ነው፦
3፥103 ጠበኞችም በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋ አስታውሱ! በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፥ በጸጋውም ወንድማማቾች ኾናችሁ፡፡ በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ ነበራችሁ፥ ከእርስዋም አዳናችሁ፡፡ እንደዚሁ ትመሩ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾቹን ያብራራል፡፡ وَاذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ كُنتُمْ أَعْدَاءً فَأَلَّفَ بَيْنَ قُلُوبِكُمْ فَأَصْبَحْتُم بِنِعْمَتِهِ إِخْوَانًا وَكُنتُمْ عَلَىٰ شَفَا حُفْرَةٍ مِّنَ النَّارِ فَأَنقَذَكُم مِّنْهَا ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمْ آيَاتِهِ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ

ከእሳት ጉድጓድ ተንጠልጥሎ ለመውጣት የሚያስችል ብቸኛው ገመድ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" የሚለው የአሏህ ገመድ ነው፥ በዘር፣ በብሔር፣ በዘውግ፣ በቋንቋ፣ በባህል ጥላቻ እና ቂም አጥፍቶ የሚያሳማማ፣ የሚያስተሳስር፣ ወንድማማች የሚያረግ ይህ ገመድ ነው። "አኽ" أَخ ማለት "ወንድም" ማለት ሲሆን "ኡኽት" أُخْت ማለት ደግሞ "እኅት" ማለት ነው፥ "ኢኽዋህ" إِخْوَة ወይም "ኢኽዋን" إِخْوَان ማለት "ወንድማማች" ማለት ሲሆን ለሁለቱም ጥቅም ላይ የሚውል ቃል ነው፥ እነዚህ ወንድማማች በልባቸው ውስጥ በዘር፣ በብሔር፣ በዘውግ፣ በቋንቋ፣ በባህል የተፈጠረውን ቂም አሏህ ያስወግድላቸዋል፦
15፥47 በዙፋኖችም ላይ ፊት ለፊት የሚቅጣጩ ወንድማማቾች ኾነው በደረቶቻቸው ውስጥ ከቂም ያለውን ሁሉ እናስወግዳለን፡፡ وَنَزَعْنَا مَا فِي صُدُورِهِم مِّنْ غِلٍّ إِخْوَانًا عَلَىٰ سُرُرٍ مُّتَقَابِلِينَ

"ሠሪር" سَرِير ማለት "ወንበር" "ዙፋን" ማለት ነው፥ "ሠሪር" ለሚለው ቃል ብዜት ደግሞ "ሡሩር" سُرُر ሲሆን "ወንበሮች" "ዙፋኖች" ማለት ነው። በላ ኢላሀ ኢለል ሏህ ጠንካራ ዘለበት ጠንካራ ዘለበት የተሳሰሩ ወንድማማቾች በዙፋኖች ላይ ይሆናሉ፥ ይህም ታላቅ ንግሥና ነው። ምእመናን ወንድማማች ናቸው፦
49፥10 ምእመናን ወንድማማች ናቸው፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ

በዘር፣ በብሔር፣ በዘውግ፣ በቋንቋ፣ በባህል በሁለት ወንድማማች መካከል አለመግባባት ቢፈጠር ለዘርህ፣ ለብሔርህ፣ ለዘውግህ፣ ለቋንቋህ፣ ለባህልህ ወግነህ ትጣላለህ ወይስ ታስታርቃለህ? አሏህን ፈርተን እዝነቱን ከፈለግን ማስታረቅ ግድ ነው፦
49፥10 በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል አስታርቁ፡፡ ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ فَأَصْلِحُوا بَيْنَ أَخَوَيْكُمْ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ

አምላካችን አሏህ በላ ኢላሀ ኢለል ሏህ ጠንካራ ዘለበት ወንድማማችነታችንን የምንጠብቅ ያርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የመደመር ፍልስፍና

ሙሥሊም ከሙሥሊም ውጪ ካሉትን የኅብረተሰብ ክፍሎት ጋር በጋራ እሴት ይኗኗራል፥ በማኅበራዊ እሴት ይረዳዳል። ነገር ግን ሐቅ ከባጢል ጋር ስለማይደመር ኢሥላም ከምዕራባውያን እሳቦት ጋር አይደመርም፥ የመደመር ፍልስፍና የተጃመለ የኢሉሚናቲ ሕዋስ እና የኢሉሚናቲ ራእይ አቅጣጫ መዳረሻ ነው። ጂሃድ በሐቅ እና በባጢል መካከል ያለ ትግል ነውና ይህንን ባጢል እንታገላለን፥ ዓለም እስኪሰማ እና እስኪስማማ ድረስ ይህንን ትግል እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ይቀጥላል።
ሲቀጥል ኢሥላም ዓለም ዓቀፍ ሃይማኖት እንጂ የአንድ አገር ሕዝበኝነት አቀንቃኝ በፍጹም አይደለምና ዲናችንን ከምንም በላይ እናስበልጥ! እሥልምና አይደለም ከዘራችን፣ ከአገራችን፣ ከዘውጋችን ከራሳችንም በላይ ነው።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom
የኢብራሂም ደባ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

21፥57 «በአላህም እምላለሁ ዟሪዎች ኾናችሁ ከሄዳችሁ በኋላ ጣዖቶቻችሁን አሴራባቸዋለሁ» አለ፡፡ وَتَٱللَّهِ لَأَكِيدَنَّ أَصْنَٰمَكُم بَعْدَ أَن تُوَلُّوا۟ مُدْبِرِينَ

“ጧጉት” طَّٰغُوت የሚለው ቃል “ጦጋ” طَغَىٰ ማለትም “ወሰን አለፈ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “በአሏህ ሐቅ ላይ ወሰን ማለፍ” ማለት ነው፥ በአሏህ ሐቅ ላይ ወሰን ማሳለፊያ ምንነት “ጣዖት” ይባላል። በአሏህ ሐቅ ላይ ወሰን ማሳለፊያ ምንነት "አስናም" እና "አውሳን" ናቸው፥ “አስናም” أَصْنَام ከእንጨት፣ ከብር፣ ከነሐስ፣ ከወርቅ ተሠርቶ አምልኮ የሚቀርብለት ጣዖት ሲሆን “አውሳን” أَوْثَٰن ደግሞ ከድንጋይ ተቀርፆ አምልኮ የሚቀርብለት ምንነት ነው። ኢብራሂም ለአባቱ እና ለሕዝቦቹ ስለ አውሳን፦ "ይህቺ ቅርጻ ቅርጽ ያቺ እናንተ ለእርሷ ተገዢዎች የኾናችሁት ምንድን ናት? ብሎ ጠየቃቸው፥ እነርሱም፦ "አባቶቻችንን ለእርሷ ተገዢዎች ኾነው አገኘን" አሉ፦
21፥52 ለአባቱ እና ለሕዝቦቹ፦ «ይህቺ ቅርጻ ቅርጽ ያቺ እናንተ ለእርሷ ተገዢዎች የኾናችሁት ምንድን ናት» ባለ ጊዜ መራነው፡፡ إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِۦ مَا هَٰذِهِ ٱلتَّمَاثِيلُ ٱلَّتِىٓ أَنتُمْ لَهَا عَٰكِفُونَ
21፥53 «አባቶቻችንን ለእርሷ ተገዢዎች ኾነው አገኘን» አሉት፡፡ قَالُوا۟ وَجَدْنَآ ءَابَآءَنَا لَهَا عَٰبِدِينَ

እርሱም፦ "እናንተም አባቶቻችሁም በእርግጥ በግልጽ ስህተት ውስጥ ነበራችሁ" አላቸው፥ እነርሱም፦ "በምሩ መጣህልን ወይንስ አንተ ከሚቀልዱት ነህ? አሉት፦
21፥54 «እናንተም አባቶቻችሁም በእርግጥ በግልጽ ስህተት ውስጥ ነበራችሁ» አላቸው፡፡ قَالَ لَقَدْ كُنتُمْ أَنتُمْ وَآبَاؤُكُمْ فِي ضَلَالٍ مُّبِينٍ
21፥55 «በምሩ መጣህልን ወይንስ አንተ ከሚቀልዱት ነህ» አሉት፡፡ قَالُوا أَجِئْتَنَا بِالْحَقِّ أَمْ أَنتَ مِنَ اللَّاعِبِينَ

እርሱም፦ “አይደለም ጌታችሁ የሰማያትና የምድር ጌታ ያ የፈጠራቸው ነው፡፡ እኔም በዚህ ላይ ከመስካሪዎቹ ነኝ” አላቸው፦
21፥56 «አይደለም ጌታችሁ የሰማያት እና የምድር ጌታ ያ የፈጠራቸው ነው፡፡ እኔም በዚህ ላይ ከመስካሪዎቹ ነኝ» አለ፡፡ قَالَ بَل رَّبُّكُمْ رَبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ٱلَّذِى فَطَرَهُنَّ وَأَنَا۠ عَلَىٰ ذَٰلِكُم مِّنَ ٱلشَّٰهِدِينَ
21፥57 «በአላህም እምላለሁ ዟሪዎች ኾናችሁ ከሄዳችሁ በኋላ ጣዖቶቻችሁን አሴራባቸዋለሁ» አለ፡፡ وَتَٱللَّهِ لَأَكِيدَنَّ أَصْنَٰمَكُم بَعْدَ أَن تُوَلُّوا۟ مُدْبِرِينَ

"አኪደነ" أَكِيدَنَّ ማለት "አደባለው" "አሴራለው" ማለት ነው፥ "ከይድ" كَيْد የሚለው ቃል "ካደ" كَادَ ማለትም "አደበ" "አሴረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ደባ" "ሴራ" ማለት ነው። ይህም ሴራ ዘወር ሲሉ ለእነርሱ የኾነ አንድ ታላቅ ጣዖት ብቻ ሲቀር ስብርብሮችም አደረጋቸው፦
21፥58 ዘወር ሲሉ ለእነርሱ የኾነ አንድ ታላቅ ጣዖት ብቻ ሲቀር ስብርብሮችም አደረጋቸው፥ ወደ እርሱ ይመለሱ ዘንድ እርሱን ተወው፡፡ فَجَعَلَهُمْ جُذَٰذًا إِلَّا كَبِيرًۭا لَّهُمْ لَعَلَّهُمْ إِلَيْهِ يَرْجِعُونَ

አንድ ታላቅ ጣዖት ብቻ ያስቀረው ወደ ታላቁ ጣዖት ተመልሰው የተሰባበሩት ማን እንደሰባበራቸው ሲጠይቁት መልስ ይሰጡ እንደሆነ ዘንድ ነው፥ እነርሱም ጣዖቶቻቸው ተሰባብረው ሲያዩ፦ "በአማልክቶቻችን ይህንን የሠራ ማነው እርሱ በእርግጥ ከበደለኞች ነው? ኢብራሂም ሆይ! በአማልክቶቻችን ይህንን የሠራህ አንተ ነህን? አሉት፦
21፥59 «በአማልክቶቻችን ይህንን የሠራ ማነው እርሱ በእርግጥ ከበደለኞች ነው» አሉ፡፡ قَالُوا مَن فَعَلَ هَـٰذَا بِآلِهَتِنَا إِنَّهُ لَمِنَ الظَّالِمِينَ
21፥62 «ኢብራሂም ሆይ! በአማልክቶቻችን ይህንን የሠራህ አንተ ነህን?» አሉት፡፡ قَالُوا أَأَنتَ فَعَلْتَ هَـٰذَا بِآلِهَتِنَا يَا إِبْرَاهِيمُ

እርሱም፦ "አይደለም ይህ ታላቃቸው ሠራው፡፡ ይናገሩም እንደ ኾነ ጠይቋቸው" አለ፦
21፥63 «አይደለም ይህ ታላቃቸው ሠራው፡፡ ይናገሩም እንደ ኾነ ጠይቋቸው» አለ፡፡ قَالَ بَلْ فَعَلَهُۥ كَبِيرُهُمْ هَٰذَا فَسْـَٔلُوهُمْ إِن كَانُوا۟ يَنطِقُونَ
21፥64 ወደ እራሳቸውም ተመለሱ፥ «እናንተ በመጠየቃችሁ በዳዮቹ እናንተው ናችሁም» ተባባሉ፡፡ فَرَجَعُوٓا۟ إِلَىٰٓ أَنفُسِهِمْ فَقَالُوٓا۟ إِنَّكُمْ أَنتُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ
21፥65 ከዚያም በራሶቻቸው ላይ ተገለበጡ፡፡ «እነዚህ የሚናገሩ አለመኾናቸውን በእርግጥ ዐውቀሃል» አሉ፡፡ ثُمَّ نُكِسُوا۟ عَلَىٰ رُءُوسِهِمْ لَقَدْ عَلِمْتَ مَا هَٰٓؤُلَآءِ يَنطِقُونَ

የእነርሱ ከንቱ አምልኮ የሚያሳፍር ሲሆን የኢብራሂም ሂክማህ ግን ድንቅ ነው፥ በሴራው ሰበረ የተባለው ታላቁ ጣዖት ሆነ ተሰበሩ የተባሉት ጣዖታት የማይናገሩ፣ የማይሰሙ፣ የማያዩ፣ የማይጠቅሙ ነበሩ፦
21፥66 «ታዲያ ለእናንተ ምንም የማይጠቅማችሁን እና የማይጎዳችሁን ነገር ከአላህ ሌላ ታመልካላችሁን?» አላቸው፡፡ قَالَ أَفَتَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَنفَعُكُمْ شَيْـًۭٔا وَلَا يَضُرُّكُمْ

አምልኮ የሚገባው ሁሉን ዐዋቂ፣ ሁሉን ሰሚ፣ ሁሉን ተመልካች፣ በግልጠት የሚናገር፣ በጀነት የሚጠቅም፣ በቅጣት የሚጎዳ የዓለማቱ ጌታ አሏህ ብቻ ነው፥ ይህንን አንዱን አምላክ በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ገዥ እና ተገዥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥65 እርሱ የሰማያት እና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነውና ተገዛው፡፡ እርሱን በመገዛትም ላይ ታገስ፡፡ ለእርሱ ሞክሼን ታውቃለህን? رَّبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا فَاعْبُدْهُ وَاصْطَبِرْ لِعِبَادَتِهِ ۚ هَلْ تَعْلَمُ لَهُ سَمِيًّا

በገዢ እና በተገዢ መካከል ያለው መገዛዛት የአገልግሎት መገዛዛት" functional subordination" እና የባሕርይ መገዛዛት" ontological subordination" ተብሎ ለሁለት ይከፈላል፥ ይህንን ነጥብ በነጥብ እስቲ እንይ፦

ነጥብ አንድ
"የአገልግሎት መገዛዛት"
ለምሳሌ ባል የሚስት ራስ በመሆን ገዥ ሲሆን ሚስት ደግሞ ተገዥ ናት፦
1 ቆሮንቶስ 14፥34 ሴቶች በማኅበር ዝም ይበሉ፤ ሕግ ደግሞ እንደሚል "እንዲገዙ" እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውምና።

የትኛው ሕግ? ስንል "ኦሪት" ማለት "ሕግ" ማለት ሲሆን ኦሪት ዘፍጥረት ላይ ባል የሚስት ገዥ እንደሆነ ይናገራል፦
ዘፍጥረት 3፥16 እርሱም "ገዥሽ" ይሆናል።

ባል እና ሚስት በምንነት ሰው ሲሆኑ አንድ ናቸው፥ በማንነት ግን ሁለት ስለሆኑ ሁለት ሰው ናቸው። በመካከላቸው ያለው መገዛዛት የምንነት ሳይሆን የደረጃ መገዛዛት ነው፦
ኤፌሶን 5፥22 ሚስቶች ሆይ! ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ!

ሚስት ለባሏ የምትገዛው ለክርስቶስ እንደምትገዛው ነው፥ ክርስቶስ ሰው ሲሆን ሚስት ክርስቶስ በመከተል የምትገዛው በደረጃ መገዛዛት ነው። ምክንያቱም ሚስት እና ባል ሰው ሆነው የኤክሌሲያ ክፍል ናቸው፥ ኤክሌሲያ ለክርስቶስ የምትገዛው የደረጃ መገዛት ነው፦
ኤፌሶን 5፥24 ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ እንዲሁ ሚስቶች ደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ።

ባል ሚስቱን ክርስቶስ ኤክሌሲያን የሚገዛው በደረጃ መገዛት ነው፥ ካልሆነ ኤክሌሲያ በሚስት ክርስቶስ በባል መመሰሉ ትርጉም የለውም። “ኤክሌሲያ” ἐκκλησία የሚለው የግሪኩ ቃል ከሁለት ቃላት የተዋቀረ ቃል ነው፥ እርሱም “ኤክ” ἐκ ማለትም “ከ” ከሚል መስተዋድድ እና “ካሌኦ” καλέω ማለትም “የተጠራ” ከሚል ግስ ነው። በጥቅሉ “ተጠርተው የወጡ” ማለት ነው፥ ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን ሙያዊ ፍቺው ደግሞ “ጉባኤ” “ማኅበር” “ስብሰባ” ማለት ነው።
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈ ምሥጢር በሚለው መጽሐፉ ላይ ከሚያበሻቅታቸው መናፍቃን አንዱ የእስክንድርያውን አርጌንስ ሲሆን አንድ ምዕራፍ ሰጥቶ በምዕራፍ 7 ላይ ይወርፈዋል፥ ሲደመድምም፦ "ልቡ ደካማ እና ኅሊናው የእንስሳ" በማለት ያብጠለጥለዋል፦
መጽሐፈ ምሥጢር 7፥17 "ልቡ ደካማ እና ኅሊናው የእንስሳ የሆነ የአርጌንስ ተግሳጽ ተፈጸመ"

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የእስክንድርያው አርጌንስን የሚያነውርበት ምክንያት "አብ የወልድ ገዥ ነው፥ ወልድ የአብ ተገዥ ነው" በማለት ዛሬ የፕሮቴስታንት ሥነ-መለኮት የሚቀበለውም የአገልግሎት መገዛዛት" functional subordination" ስላራመደ ነው።
ነጥብ ሁለት
"የባሕርይ መገዛዛት"
ለምሳሌ ሰው በእንስሳት ላይ ሁሉ ገዥ ነው፦
ዘፍጥረት 1፥28፤ እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ "ግዙአትም" የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ "ግዙአቸው"።

የሰው ኑባሬ እና የእንስሳ ኑባሬ አንድ አይደለም፥ ሰው በምንነት ሰው እንጂ ድመት፣ ውሻ፣ በግ፣ በሬ አይደለም። እንስሳን ሲገዛ የሚገዛው በባሕርይ ነው፦
መዝሙር 8፥6 በእጆችህም ሥራ ሁሉ ላይ ሾምኸው፤ ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፥
መዝሙር 8፥7-8 በጎችንም ላሞችንም ሁሉ ደግሞም የምድረ በዳውን እንስሶች፥ የሰማይንም ወፎች የባሕርንም ዓሦች፥ በባሕር መንገድ የሚሄደውንም ሁሉ።

"ሁሉን" በሚለው ቃል በጎች፣ ላሞች፣ የምድረ በዳውን እንስሶች፣ የሰማይንም ወፎች፣ የባሕርንም ዓሦች፣ በባሕር መንገድ የሚሄደው ያጠቃልላል፥ ይህ ጥቅስ ስለ ሰው የሚናገር ቢሆንም የዕብራውያን ጸሐፊ ከዚህ ጠቅሶ ለኢየሱስ ይጠቀምበታል፦
ዕብራውያን 2፥8 "ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት" ብሎ መሰከረ። ሁሉን ከእርሱ በታች ባስገዛ ጊዜ ያልተገዛለት ምንም አልተወምና። አሁን ግን ሁሉ እንደ ተገዛለት ገና አናይም።

አሁን ግን ሁሉ ማለትም በጎች፣ ላሞች፣ የምድረ በዳውን እንስሶች፣ የሰማይንም ወፎች፣ የባሕርንም ዓሦች፣ በባሕር መንገድ የሚሄደው እንደ ተገዛለት ገና አናይም፥ ግን ዳግም ሲመጣ ሁሉም ከእግሩ በታች ይገዛለታል፦
ኤፌሶን 1፥22 ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት።
1 ቆሮንቶስ 15፥27 ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቶአልና። ነገር ግን፦ "ሁሉ ተገዝቶአል" ሲል፥ ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጥ ነው።

አንዱ አምላክ ለክርስቶስ ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቷል ሲባለው "ሁሉ" በሚለው ቃል ውስጥ ሁሉን ያስገዛለት አንዱን አምላክ አይጨምርም፥ ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ኢየሱስ ሁሉን ላስገዛለት ለአንዱ አምላክ ይገዛል፦
1 ቆሮንቶስ 15፥28 ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል።

በጎች፣ ላሞች፣ የምድረ በዳውን እንስሶች፣ የሰማይንም ወፎች፣ የባሕርንም ዓሦች፣ በባሕር መንገድ የሚሄደው ለኢየሱስ የሚገዛው የባሕርይ መገዛት ሲሆን ኢየሱስ ፍጡር ስለሆነ ለፈጣሪው የሚገዛው የባሕርይ ነው፦
1 ቆሮንቶስ 11፥3 ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ።

"ክርስቶስ" ማለት "የተቀባ" ማለት ነው፥ ይህንን የተቀባ ሰው የቀባው አንዱ አምላክ ሲሆን ይህ አንዱ አምላክ ለዚህ ሰው "ራስ" ከሆነ ይህ መግዛት የባሕርይ ነው። "ራስ" ማለት "ገዥ" ማለት ነው፦
1 ዜና 29፥11 አንተም በሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያልህ ራስ ነህ።

ፈጣሪ በፍጡራኑ ሁሉ ላይ ራስ ከሆነ የእርሱ ገዥነት የባሕርይ እስከሆነ ድረስ በኢየሱስ ላይ የባሕርይ ገዥ ነው፥ እንደ ጳውሎስ እሳቤ መሢሑ በስጦታ እና በጸጋ ያገኘውን የመግዛት ሥልጣን ለሰጠው ማንነት ያስረክባል፦
1 ቆሮንቶስ 15፥24 በኋላም "መንግሥቱን" ለእግዚአብሔር ለአባቱ አሳልፎ "በሰጠ ጊዜ" አለቅነትንም ሁሉና ሥልጣንን ሁሉ ኃይልንም በሻረ ጊዜ፥ ፍጻሜ ይሆናል።

እዚህ ጥቅስ ላይ "በሰጠ ጊዜ" ጊዜ የሚለው ይሰመርበት!! መንግሥትን(መግዛትን) ሲያስረክብ ያኔ እርሱ ራሱ ገዥ ሳይሆን ተገዥ ይሆናል። ኢየሱስ እራሱ የሚገዛው ጌታ ካለው ይህ ጌታ የሰማያት እና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነውና ተገዛው። መሢሑ እራሱ የዓለማቱን ጌታ አሏህን ከመገዛት አይጠየፍም፦
19፥65 እርሱ የሰማያት እና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነውና ተገዛው፡፡ እርሱን በመገዛትም ላይ ታገስ፡፡ ለእርሱ ሞክሼን ታውቃለህን? رَّبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا فَاعْبُدْهُ وَاصْطَبِرْ لِعِبَادَتِهِ ۚ هَلْ تَعْلَمُ لَهُ سَمِيًّا
4፥172 መሢሑ ለአላህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም፡፡ ቀራቢዎች የኾኑት መላእክትም አይጠየፉም፡፡ እርሱን ከመገዛት የሚጠየፍ እና የሚኮራም ሰው አላህ ሁሉንም ወደ እርሱ በእርግጥ ይሰበስባቸዋል፡፡ لَّن يَسْتَنكِفَ الْمَسِيحُ أَن يَكُونَ عَبْدًا لِّلَّهِ وَلَا الْمَلَائِكَةُ الْمُقَرَّبُونَ ۚ وَمَن يَسْتَنكِفْ عَنْ عِبَادَتِهِ وَيَسْتَكْبِرْ فَسَيَحْشُرُهُمْ إِلَيْهِ جَمِيعًا

ኢየሱስ ከመገዛት የማያቅማማለትን አንዱን አምላክ አሏህን ትገዙ ዘንድ ጥሪያችን ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አማላጁ ኢየሱስ

በ 1879 እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር የተዘጋጀው የቁም ጽሑፍ የሚባል የባይብል ዕትም ኢየሱስ አማላጅ እንደሆነ ይናገራል፦
1ኛ ዮሐንስ 2፥1 ከላንትም ማንም ኃጢአት ቢሰራ ከአብ ዘንድ አማላጅ አለን፥ የሱስ ክርስቶስ ጻድቅ። ሮሜ ፰፤፫፬ ዕብ ፯፤፪፭

ኢየሱስ ለምኖ መልስ የሚጠብቅ "አማላጅ" ከተባለ ፍጡር ነው ማለት ነው፥ ምክንያቱም አማላጅ ካለ ተማላጅ አለ። ተማላጁ አንዱ አምላክ ከሆነ አማላጁ ኢየሱስ ይሆናል ማለት ነው፥ የሚገርመው ሮሜ 8፥34 እና ዕብ 7፥25 ማጣቀሻ ያስቀምጣል። በሮሜ 8፥34 ላይ "የሚያስምር" ሲለው እና በዕብ 7፥25 ደግሞ "ጸሎትን የሚያሳርግ" ይለዋል፥ እርሱ የሚያስምር እና ጸሎትን የሚያሳርግ ከሆነ የሚምር እና ጸሎትን የሚቀበል አንድ አምላክ ከኢየሱስ በማንነት ሆነ በምንነት የሚለይ ኑባሬ አለ።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom
ነቢዩ ዙልኪፍል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

21፥85 ኢስማዒልን፣ ኢድሪስን፣ ዙልኪፍልን አስታውስ! ሁሉም ከታጋሾቹ ናቸው፡፡ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِدْرِيسَ وَذَا الْكِفْلِ ۖ كُلٌّ مِّنَ الصَّابِرِينَ

"ዙ አን-ኑን" ذَا النُّونِ ማለት "የዓሣው ባለቤት" ማለት ሲሆን "ዙል-ቀርነይን" ذِي الْقَرْنَيْن ማለት "የሁለቱ ቀንዶች ባለቤት" ወይም "የሁለቱ ክፍለ-ዘመናት ባለቤት" ማለት ነው፦
21፥87 የዓሣውንም ባለቤት ተቆጥቶ በኼደ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَذَا النُّونِ إِذ ذَّهَبَ مُغَاضِبًا
18፥83 “ስለ ዙል-ቀርነይንም ይጠይቁካል፡፡ «በእናንተ ላይ ከእርሱ ወሬን አነባለሁ» በላቸው”፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ عَن ذِي الْقَرْنَيْنِ ۖ قُلْ سَأَتْلُو عَلَيْكُم مِّنْهُ ذِكْرًا

"ዙ" ذَا ማለት በአገዛዛቢ መደብ የመጣ ሲሆን "ባለቤት" ማለት ነው፥ "ኪፍል" كِفْل ማለት "ክፍል" ማለት ሲሆን "ዙልኪፍል" ذَا الْكِفْل ማለት "የክፍል ባለቤት" ማለት ነው። ይህ ነቢይ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ዒራቅ ውስጥ ነበረ፥ እዛ የተወሰነ ክፍል ተሰቶት ይኖር ነበር። ያ የኖረበት ቦታ "ኪፍል" كِفْل ሲባል ነቢዩ ደግሞ "የክፍል ባለቤት" ተብሏል፥ ይህ ነቢይ በቁርኣን ውስጥ ልክ እንደ ኢድሪሥ በማዕረግ ስም ተጠርቷል። የተጸውዖ ስሙ "ሒዝቂያል" حِزْقِيَال ይባላል፥ አይሁዳውያን ኪፍል በሚባል ቦታ የሕዝቅኤልን መቃብር ይጎበኙ ነበር። አምላካችን አሏህ ዙልኪፍልን ከኢስማዒል እና ከኢድሪስ ጋር ያወሳዋል፦
21፥85 ኢስማዒልን፣ ኢድሪስን፣ ዙልኪፍልን አስታውስ! ሁሉም ከታጋሾቹ ናቸው፡፡ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِدْرِيسَ وَذَا الْكِفْلِ ۖ كُلٌّ مِّنَ الصَّابِرِينَ
21፥86 ከችሮታችንም ውስጥ አገባናቸው፡፡ እነርሱ ከመልካሞቹ ናቸውና፡፡ وَأَدْخَلْنَاهُمْ فِي رَحْمَتِنَا ۖ إِنَّهُم مِّنَ الصَّالِحِينَ

አሏህ ኢስማዒልን፣ ኢድሪስን፣ ዙልኪፍልን ከችሮታው ውስጥ አገባቸው፥ ይህም ችሮታ ወሕይ በማውረድ የሚሰጥ ነቢይነት ነው፦
3፥74 በችሮታው (በነቢይነት) የሚሻውን ይመርጣል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡ يَخْتَصُّ بِرَحْمَتِهِ مَن يَشَاءُ ۗ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ
2፥90 አላህ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ከችሮታው (ራእይን) ማውረዱን በመመቅኘት አላህ ባወረደው ነገር መካዳቸው ነው፡፡ أَن يَكْفُرُوا بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ بَغْيًا أَن يُنَزِّلَ اللَّهُ مِن فَضْلِهِ عَلَىٰ مَن يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ

አሏህ "ባሪያችንን አዩብን፣ ባሮቻችንን ኢብራሂምን፣ ኢሥሐቅን፣ የዕቁብን አውሳ" ካለ በኃላ "ኢስማዒልን፣ አልየሰዕን፣ ዙልኪፍልን አውሳ! በማለት ከነቢያት ምድብ ውስጥ ይከታቸዋል፥ ኢስማዒል፣ አልየሰዕ፣ ዙልኪፍል ከበላጮቹ ናቸው። አሏህ መጽሐፍን፣ ጥበብን እና ነቢይነትን ሰቷቸዋል፦
38፥48 ኢስማዒልን፣ አልየሰዕን፣ ዙልኪፍልን አውሳ! ሁሉም ከበላጮቹ ናቸው፡፡ وَاذْكُرْ إِسْمَاعِيلَ وَالْيَسَعَ وَذَا الْكِفْلِ ۖ وَكُلٌّ مِّنَ الْأَخْيَارِ
6፥89 እነዚህ እነዚያ መጽሐፍን፣ ጥበብን እና ነቢይነትን የሰጠናቸው ናቸው፡፡ أُولَـٰئِكَ الَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ وَالْحُكْمَ وَالنُّبُوَّةَ

አምላካችን አሏህ በትንሳኤ ቀን በእነርሱ ላይ ከለገሳቸው ከነቢያት ጋር ያማረ ጓደኛ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኃጢአት ማስተሰረይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥87 የመርየምን ልጅ ዒሣንም ግልጽ ተአምራትን ሰጠነው፡፡ وَآتَيْنَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ الْبَيِّنَاتِ

የናዝሬቱ ኢየሱስ በአምላክ እና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራ እና በቃል ብርቱ ነቢይ ነበር፦
ሉቃስ 24፥19 እርሱም፦ ይህ ምንድር ነው? አላቸው። እነርሱም እንዲህ አሉት፦ "በእግዚአብሔር እና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ"።

ይህ ነቢይ አንዳንዴ ቃል ብቻ ሲናገር ሽባ ይፈውስ ነበር፥ በአልጋ የተኛ ሽባ አምጥተውለት "ኃጢአትህ ተሰረየችልህ" ሲለው ያም ሽባ ተፈውሷል፦
ማቴዎስ 8፥8 የመቶ አለቃውም መልሶ፦ ጌታ ሆይ፥ በቤቴ ጣራ ከታች ልትገባ አይገባኝም፤ ነገር ግን "ቃል ብቻ ተናገር" ብላቴናዬም ይፈወሳል።
ማቴዎስ 9፥2 እነሆም፥ በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን፦ አንተ ልጅ፥ አይዞህ! "ኃጢአትህ ተሰረየችልህ" አለው።

"ጽርፈት" ማለት "ስድብ"blasphemy" ማለት ሲሆን ኢየሱስ፦ "ኃጢአትህ ተሰረየችልህ" ሲል ከጻፎቹ አንዳንዱ "ይህስ ይሳደባል፥ ከአንዱ ከአምላክ በቀር ኃጢአት ሊያስተሰርይ ማን ይችላል? ብለው አሰቡ፦
ማቴዎስ 9፥3 እነሆም ከጻፎቹ አንዳንዱ በልባቸው፦ "ይህስ ይሳደባል" አሉ።
ማርቆስ 2፥7 ይህ ሰው ስለ ምን እንደዚህ ያለ ስድብ ይናገራል? ከአንዱ ከአምላክ በቀር ኃጢአት ሊያስተሰርይ ማን ይችላል? ብለው አሰቡ።

ስድብ ብለው ያሰቡት "ኃጢአት ሊያስተሰርይ የሚችለው አንዱ አምላክ ነው" ብለው ስላሰቡ ኢየሱስ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ስለተሞላ የዕውቀት መንፈስ ስላለው በልባቸው እንዲህ እንዳሰቡ በመንፈስ ቅዱስ አውቆ፦ "ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ? አላቸው፦
ማርቆስ 2፥8 ወዲያውም ኢየሱስ በልባቸው እንዲህ እንዳሰቡ "በመንፈስ አውቆ" እንዲህ አላቸው፦ በልባችሁ ይህን ስለ ምን ታስባላችሁ?
ማቴዎስ 9፥4 ኢየሱስም አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አለ፦ ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ?

እነርሱ በልባቸው፦ "እራሱን አምላክ አርጎ ያስባልን?"That’s blasphemy! Does he think he’s God?” (New Living Translation) ብለው ያሰቡት አሳብ ክፉ አሳብ እንደሆነ ለማመልከት፦ "ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ" አላቸው፥ ስለዚህ "ኢየሱስ አምላክ ነው" ብሎ ማሰብ ክፉ አሳብ ነው። ታዲያ ኢየሱስ ኃጢአት ሊያስተሰርይ እንዴት ቻለ? ካልን አምላክ ስለሆነ ሳይሆን የሰው ልጅ ነውና ኃጢአትን ያስተሰርይ ዘንድ ሥልጣን የሰጠው አምላኩ ነው፦
ማቴዎስ 9፥6 ነገር ግን በምድር ላይ ኃጢአትን ያስተሰርይ ዘንድ ለሰው ልጅ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ።
ማቴዎስ 28፥18 ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይ እና በምድር ተሰጠኝ።

"ሥልጣን ሁሉ" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! በምድር ላይ ኃጢአትን የማስተሰረይ ሥልጣን የሰጠው አንዱ አምላክ ስለሆነ "ተሰጠኝ" በማለት ይናገራል፦
ሉቃስ 10፥22 ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል።
ዮሐንስ 5፥27 የሰው ልጅም ስለ ሆነ ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን ሰጠው።

ምን ትፈልጋለህ? ሁሉም ነገር ከአብ የተሰጠው ነው፥ ለኢየሱስ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ ብሎ እንዲፈርድ ሥልጣን ያገኘው በስጦታ ነው። ኢየሱስ ከራሱ ምንም አልተናገረም፥ "ኃጢአትህ ተሰረየችልህ" ብሎ የሚለውን እና የሚናገረውን ትእዛዝ የሰጠው የላከው ነው፦
ዮሐንስ 12፥49 እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፥ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ።

ኢየሱስ እኮ እንዲፈውስ የጌታ ኃይል የሆነለት ሰው ነው፥ ከራሱ ምንም ማድረግ የማይችለው እና ከላከው እየሰማ "ኃጢአትህ ተሰረየችልህ" በማለት ይፈርድ ነበር፦
ሉቃስ 5፥17 እርሱም እንዲፈውስ የጌታ ኃይል ሆነለት።
ዮሐንስ 5፥30 እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ "እንደ ሰማሁ" እፈርዳለሁ። የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።

የላከውን ፈቃድ ለማድረግ እንጂ የራሱን ፈቃድ የማያደርግ ኢየሱስ ሲፈውስም በላከው ፈቃድ ብቻ ነው። ይህ "ኃጢአትህ ተሰረየችልህ" ብሎ እንዲናገር ለዚህ ሰው ሥልጣን የሰጠው አምላክ እንደሆነ የገባቸው ሕዝቡ ለኢየሱስ ሥልጣን የሰጠውን አምላክን አከበሩ፦
ማቴዎስ 9፥8 ሕዝቡም አይተው ተደነቁ፥ ለሰውም እንዲህ ያለ ሥልጣን የሰጠ እግዚአብሔርን አከበሩ።

የናዝሬቱ ኢየሱስ አምላክ በእርሱ በኩል ተአምራትን ያደረገበት ሰው ነበረ፥ እየፈወሰ ሲዞር አምላክ ከእርሱ ጋር ነበረ እንጂ እራሱ አምላክ አልነበረም፦
የሐዋርያት ሥራ 2፥22 የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ።
የሐዋርያት ሥራ 10፥38 እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና።

"ማስተሰረይ" ማለት "ይቅር ማለት" ማለት ነው፥ ኃጢአትን ይቅር ማለት አምላክ ካስደረገ ሐዋርያትም ኃጢአትን ይቅር ይላሉ፥ እናስ ሐዋርያት አምላክ ናቸውን? በፍጹም፦
ዮሐንስ 20፥23 ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፥ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል" አላቸው።

አምላካችን አሏህ ለመርየምን ልጅ ለዒሣ ግልጽ ተአምራትን ሰቶታል፦
2፥87 የመርየምን ልጅ ዒሣንም ግልጽ ተአምራትን ሰጠነው፡፡ وَآتَيْنَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ الْبَيِّنَاتِ

ሽባ መተርተር፣ ዕውር ማብራት፣ ለምጻም ማንጻት፣ ሙት ማስነሳት ግልጽ ተአምራት ናቸው፥ ለዒሣ ተአምራት የሰጠውን አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
እራስን ማጥፋት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥29 "እራሳችሁንም አትግደሉ! አላህ ለእናንተ አዛኝ ነውና"፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَأْكُلُوا أَمْوَالَكُم بَيْنَكُم بِالْبَاطِلِ إِلَّا أَن تَكُونَ تِجَارَةً عَن تَرَاضٍ مِّنكُمْ ۚ وَلَا تَقْتُلُوا أَنفُسَكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ بِكُمْ رَحِيمًا

"ነፍሥ" نَفْس ማለት "ራስነት"own self-hood" ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ ግን ነፍስን መግደል ሐራም አድርጓል፦
4፥33 ያቺንም አላህ ያወገዛትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ
4፥31 "ልጆቻችሁንም ድኽነትን ለመፍራት አትግደሉ! እኛ እንመግባቸዋለን፡፡ እናንተንም እንመግባለን፡፡ እነርሱን መግደል ታላቅ ኃጢኣት ነውና፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا أَوْلَادَكُمْ خَشْيَةَ إِمْلَاقٍ ۖ نَّحْنُ نَرْزُقُهُمْ وَإِيَّاكُمْ ۚ إِنَّ قَتْلَهُمْ كَانَ خِطْئًا كَبِيرًا

"ልጆቻችሁንም ድኽነትን ለመፍራት አትግደሉ" የሚለው መርሕ በእናት ማኅፀን ውስጥ ያለ ሽልንም ሆን ብሎ እንዲጨነግፍ ማድረግም ጭምር ነው። "እራስን ማጥፋት"Suicide" እራሱ ነፍሥን መግደል ነውና ሐራም ነው፦
4፥29 "እራሳችሁንም አትግደሉ! አላህ ለእናንተ አዛኝ ነውና"፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَأْكُلُوا أَمْوَالَكُم بَيْنَكُم بِالْبَاطِلِ إِلَّا أَن تَكُونَ تِجَارَةً عَن تَرَاضٍ مِّنكُمْ ۚ وَلَا تَقْتُلُوا أَنفُسَكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ بِكُمْ رَحِيمًا

"አንፉሠኩም" أَنفُسَكُمْ ማለት "እራሳችሁን" ማለት ሲሆን ድርብ ተውላጠ ስም"reflexive pronoun" ነው፥ ብዙ ጊዜ እራሳቸው የሚያጠፉ ድባቴ"depression" ያለባቸው ሰዎች፦ "ሕይወት ስህተት ነው፥ የሚታረመው በሞት ነው" የሚል የቂል አስተሳሰብ አላቸው። እራስን ማጥፋት በሐዲስም ሆነ ሐራም ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 76, ሐዲስ 90
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ማንም እራሱን በውጥን ከተራራ ላይ ከፈጠፈጠ እና እራሱን ከገደለ መኖሪያው የጀሀነም እሳት ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَنْ تَرَدَّى مِنْ جَبَلٍ فَقَتَلَ نَفْسَهُ، فَهْوَ فِي نَارِ جَهَنَّمَ

እራስን ማጥፋት በኢሥላም ይህ ያህል ሐራም እንደሆነ ጥልልና ጥንፍፍ ያለ አስተምህሮት እንዳለ ካወቅን ዘንዳ ሚሽነሪዎች፦ "ነቢያችሁ"ﷺ" እራሳቸውን ሊያጠፉ ያስቡ ነበር" ብለው የሚቀጥፉባቸውን ሐዲስ በሰከነ እና በሰላ አእምሮ እንመልከት፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 91, ሐዲስ 1
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ ……..፦ከዚያም ወረቃህ ከሞተ ከጥቂት ቀናት በኃላ ወሕይ ለተወሰነ ጊዜ ያህል በተቋረጠ ጊዜ ነቢዩ”ﷺ” እጅግ አዝነው ነበር፥ "እንደ ደረሰን"፦ “እርሳቸው ብዙ ጊዜ ራሳቸውን ከትልቅ ተራራ ላይ ለመጣል ያስቡ ነበር"። ثُمَّ لَمْ يَنْشَبْ وَرَقَةُ أَنْ تُوُفِّيَ، وَفَتَرَ الْوَحْىُ فَتْرَةً حَتَّى حَزِنَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم فِيمَا بَلَغَنَا حُزْنًا غَدَا مِنْهُ مِرَارًا كَىْ يَتَرَدَّى مِنْ رُءُوسِ شَوَاهِقِ الْجِبَالِ

ሐዲሱ እረጅም ስለሆነ ለመጻፍ ጊዜና ቦታ እንዳይፈጅ እና ለአንባቢያንም እንዳይሰለች በአጭሩ አስቀምጬዋለው፥ ሙሉውን የሚፈልግ መረጃው ስላለ ገብቶ ማየት ይችላል። እዚህ ሐዲስ ላይ "እንደ ደረሰን" ተብሎ የተቀመጠው የዐረቢኛው ቃል “ፊማ በለገና” فِيمَا بَلَغَنَا ነው፥ "በለገ" بَلَغَ ማለት "ደረሰ" ማለት ነው። ቦታው ላይ በጆሮ ያልተሰማ ቅሉ ግን በአሉባልታ የመጣ ነው፥ "እርሳቸው ብዙ ጊዜ ራሳቸውን ከትልቅ ተራራ ላይ ለመጣል ያስቡ ነበር" የሚለው ቃል አሉ አሉ ተብሎ የተነገረ አሉባልታ እንጂ ከተራኪው በሰንሰለት የተላለፈ ትክክለኛ ትረካ ቢሆን ኖሮ "ፊማ ሠሚዕና" فِيمَا سَمِعْنَا ማለትም "እንደሰማነው" ይሆን ነበር።

ሲቀጥል "ፊማ በለገና" فِيمَا بَلَغَنَا ያለው በዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እና በዘጋቢው መካከል ያለ አስተላላፊ “አዝ-ዙህሪይ” الزُّهْرِيّ ነው፥ ይህንን ነጥብ ሀፊዝ ኢብኑ ሐጀረል አስቀላኒ"አሏህ ይዘንላቸው" እንዲህ ይሉናል፦
ፈትሑል ባሪ ፊ ሸርሕ 19/449 ኪታቡል ተዕቢር
”ፊማ በለገና” فِيمَا بَلَغَنَا ብሎ የተናገረው አዝ-ዙሁሪይ ነው። ይህም ማለት ስለ የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ከሚያወራው ጥቅል ትረካ ውስጥ “ፊማ በለገና” የአዝ-ዙሁሪይ ንግግር ብቻ እንጅ ከዘገባው ጋር የተያያዘ አይደለም”። إِنَّ الْقَائِل فِيمَا بَلَغَنَا هُوَ الزُّهْرِيّ ، وَمَعْنَى الْكَلَام أَنَّ فِي جُمْلَة مَا وَصَلَ إِلَيْنَا مِنْ خَبَر رَسُول اللَّه صَلَّى اللَّه عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فِي هَذِهِ الْقِصَّة وَهُوَ مِنْ بَلَاغَات الزُّهْرِيّ وَلَيْسَ مَوْصُولًا

ሢሰልስ "ያስቡ ነበር" ማለት እና "ራሳቸውን አጠፉ" ማለት ሁለት ለየቅል ዐረፍተ ነገር ነው። በባይብል እንደሚታወቀው ሶምሶን እራሱን አጥፍቶ ሌሎችን ያጠፋ ሰው ነው፦
መሣፍንት 16፥30 ሶምሶንም፦ ”ከፍልስጥኤማውያን ጋር ልሙት አለ" ተጎንብሶም ምሰሶቹን በሙሉ ኅይሉ ገፋ፥ ቤቱም በውስጡ በነበሩት በመኳንንቱም በሕዝቡም ሁሉ ላይ ወደቀ፤ በሞቱም የገደላቸው ሙታን በሕይወት ሳለ ከገደላቸው በዙ።

እኛም ዞር ብለን ባይብል ላይ ተመሳሳይ ባይሆንም ስለ እራስን ማጥፋት ጥያቄ እናቀርባለን፤ የዕብራዊያን ጸሐፊ በእምነት ድል ስላደረጉ የብሉይ ኪዳን ሰዎች ሲተርክን እንደ ደመና በዙሪያቸው ካሉት ምስክሮች አንዱ ሶምሶን ነበር፦
ዕብራውያን 11፥32 እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎን፣ ስለ ባርቅ "ስለ ሶምሶንም"፣ ስለ ዮፍታሔም ስለ ዳዊት፣ ስለ ሳሙኤልም፣ ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና። ዕብራውያን 11፥33 እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፥ ጽድቅን አደረጉ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ።
ዕብራውያን 12፥1 እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን።

እራሱን ያጠፋ ሶምሶም "ጽድቅን አደረጉ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ" ከተባሉት አንዱ መሆኑ አጂብ የሚያስብል ነው፥ ማሰብ እና መሞከር አሊያም ማሰብ እና ማድረግ ሁለት ለየቅል የሆኑ ትርጉሞች ናቸው። ይህ የሶምሶን ድርጊት ግን እራስን ለማጥፋት ማሰብ አሊያም መሞከር ሳይሆን እራሱን ማጥፋት ነው፥ መርፌ የራሷን ቀዳዳ ሳትሰፋ የሰውን ልብስ ትሰፋ? ይላል የአገሬ ሰው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
እነዚህ መጣጥፍ በድምፅ ደረጃ ይፈልጋሉን? እንግዲያውስ በይቱብ በድምፅ መኮምኮም ትችላላችሁ። ይህንን ሊንክ ያስፈንጥሩ፦ https://youtu.be/broY6Q4Fuww
ሶደቃህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥263 መልካም ንግግር እና ምሕረት ማድረግ ማስከፋት ከሚከተላት ምጽዋት በላጭ ነው፡፡ አላህም ተብቃቂ ታጋሽ ነው፡፡ قَوْلٌ مَّعْرُوفٌ وَمَغْفِرَةٌ خَيْرٌ مِّن صَدَقَةٍ يَتْبَعُهَا أَذًى ۗ وَاللَّهُ غَنِيٌّ حَلِيمٌ

"ሶደቃህ" صَدَقَة የሚለው ቃል "ሶደቀ" صَدَقَ ማለት "መጸወተ" "ሰጠ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ምጽዋት" "ስጦታ" ማለት ነው፥ የሶደቃህ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሶደቃት" صَدُقَات‎ ሲሆን "ምጽዋቶች" "ስጦታዎች" ማለት ነው፦
2፥271 ምጽዋቶችን ብትገልጹ እርሷ ምንኛ መልካም ናት፡፡ ብትደብቋት እና ለድኾች ብትሰጧትም እርሱ ለእናንተ በላጭ ነው፡፡ ከኃጢአቶቻችሁም ከእናንተ ያብሳል፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡ إِن تُبْدُوا الصَّدَقَاتِ فَنِعِمَّا هِيَ ۖ وَإِن تُخْفُوهَا وَتُؤْتُوهَا الْفُقَرَاءَ فَهُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ ۚ وَيُكَفِّرُ عَنكُم مِّن سَيِّئَاتِكُمْ ۗ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ

"ለሰዎች አርአያ ይሆናል" ተብሎ በመልካም ኒያህ ሶደቃህ በግልጽ መሰጠቷ መልካም ነው፥ ግን ሰዎች ሳያውቋት በድብቅ መሰጠቷ በላጭ ናት። ሶደቃህ በግልጽም ሆነ በድብቅ ለአሏህ ተብሎ እስከተሰጠች ድረስ ኃጢአትን ታሳብሳለች፥ ነገር ግን እዩልኝ እና ስሙልኝ ሆኗ ጉዳት ከምታስከትል ሶደቃህ ይልቅ መልካም ንግግር እና ምሕረት ማድረግ በላጭ ነው፦
2፥263 መልካም ንግግር እና ምሕረት ማድረግ ማስከፋት ከሚከተላት ምጽዋት በላጭ ነው፡፡ አላህም ተብቃቂ ታጋሽ ነው፡፡ قَوْلٌ مَّعْرُوفٌ وَمَغْفِرَةٌ خَيْرٌ مِّن صَدَقَةٍ يَتْبَعُهَا أَذًى ۗ وَاللَّهُ غَنِيٌّ حَلِيمٌ

አምላካችን አሏህ ተብቃቂ ነው፥ በማንም ላይ ጥገኛ ሆኖ የሚፈልግ አይደለም። የእኛ ግልጽ ሆነ ድብቅ ሶዶቃህ ከሰጠን ላይ ስንሰጥ የፍቅሩ መገለጫ ነው፥ ምንዳውም ለራሳችን ነው፦
2፥274 እነዚያ ገንዘቦቻቸውን በሌሊት እና በቀን በድብቅም በግልጽም የሚለግሱ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ الَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُم بِاللَّيْلِ وَالنَّهَارِ سِرًّا وَعَلَانِيَةً فَلَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ

እንደውም መልካም ነገር ሁሉ እኮ ሶደቃህ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 78, ሐዲስ 52
ጃቢር ኢብኑ ዐብደሏህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "መልካም ነገር ሁሉ ሶደቃህ ነው"። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ ـ رضى الله عنهما ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ كُلُّ مَعْرُوفٍ صَدَقَةٌ ‏"‌‏.‏

እዚህ ሐዲስ ላይ "መልካም" ለሚለው የገባው ቃል "መዕሩፍ" مَعْرُوف ሲሆን ይህ መልካም ነገር የሚያዙን ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ናቸው፦
7፥157 በበጎ ሥራ ያዛቸዋል፥ ከክፉም ነገር ይከለክላቸዋል፡፡ يَأْمُرُهُم بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَاهُمْ عَنِ الْمُنكَرِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "በጎ ሥራ" ለሚለው የገባው ቃል "መዕሩፍ" مَعْرُوف ሲሆን ነቢያችን"ﷺ" ካዘዙን መልካም ሥራ አንዱ ፈገግታ ነው፥ ፈገግታ ሶዶቃህ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 27, ሐዲስ 62
አቢ ዘር እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የአንተ ፈገግታ በወንድምህ ፊት ለአንተ ሶደቃህ ነው"። عَنْ أَبِي ذَرٍّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ تَبَسُّمُكَ فِي وَجْهِ أَخِيكَ لَكَ صَدَقَةٌ

በሁለት ወገን ፍትሕ ማድረግ ሶደቃ ነው፣ ሰው እቃን ሊጭን ሲል መርዳት ሶደቃህ ነው፣ መልካም ንግግር ሶደቃህ ነው፣ ወደ ሶላት ማንኛውም እርምጃ ማድረግ ሶደቃህ ነው፣ ከመንገድ ላይ እንቅፋትን ማስወገድ ሶደቃህ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 12, ሐዲስ 72
አቢ ሀረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ "ሶደቃህ በእያንዳንዱ የፀሐይ መውጫ ቀን በእያንዳንዱ የሰው መገጣጠሚያ ግዴታ ነው፥ በሁለት ወገን ፍትሕ ማድረግ ሶደቃህ ነው፣ በእንስሳ ላይ የሚጋልብን ማማከር ወይም ሊጭን ሲል መርዳት ሶደቃህ ነው፣ መልካም ንግግር ሶደቃህ ነው፣ ወደ ሶላት ማንኛውም እርምጃ ማድረግ ሶደቃህ ነው፣ ከመንገድ ላይ እንቅፋት ማስወገድ ሶደቃህ ነው"። وَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏“‏ كُلُّ سُلاَمَى مِنَ النَّاسِ عَلَيْهِ صَدَقَةٌ كُلَّ يَوْمٍ تَطْلُعُ فِيهِ الشَّمْسُ – قَالَ – تَعْدِلُ بَيْنَ الاِثْنَيْنِ صَدَقَةٌ وَتُعِينُ الرَّجُلَ فِي دَابَّتِهِ فَتَحْمِلُهُ عَلَيْهَا أَوْ تَرْفَعُ لَهُ عَلَيْهَا مَتَاعَهُ صَدَقَةٌ – قَالَ – وَالْكَلِمَةُ الطَّيِّبَةُ صَدَقَةٌ وَكُلُّ خَطْوَةٍ تَمْشِيهَا إِلَى الصَّلاَةِ صَدَقَةٌ وَتُمِيطُ الأَذَى عَنِ الطَّرِيقِ صَدَقَةٌ ‏
አንድ ሙእሚን ለቤተሰቡ የሚያወጣው አዝቤዛ ሶደቃህ ነው፥ ሙእሚን አንድ ተክል ተክሎ ሰው ሆነ እንስሳ ቢበላው ሶደቃህ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 78, ሐዲስ 52
አቡ መሥዑድ አል-በድሪይ ሰምቶ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አንድ ሰው ለቤተሰቡ የሚያወጣው ሶደቃህ ነው"። سَمِعَ أَبَا مَسْعُودٍ الْبَدْرِيَّ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ نَفَقَةُ الرَّجُلِ عَلَى أَهْلِهِ صَدَقَةٌ ‏"‌‏.‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 78, ሐዲስ 43
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”ማንም ሙሥሊም የለም አንድ ተክል ተክሎ ሰው ሆነ እንስሳ ቢበላው ሶደቃህ ብትሆንለት እንጂ”። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ مَا مِنْ مُسْلِمٍ غَرَسَ غَرْسًا فَأَكَلَ مِنْهُ إِنْسَانٌ أَوْ دَابَّةٌ إِلاَّ كَانَ لَهُ صَدَقَة

በእርግጥም ሶደቃህ ውስጥን የምታጠራ እና ገንዘብን የምታፋፋ ናት እንጂ ሀብትን አትቀንስም፥ ጭራሽ በትንሳኤ ቀን ለሙእሚን ጥላው ናት፦
9፥103 ከገንዘቦቻቸው ስትኾን በእርሷ የምታጠራቸውና የምታፋፋቸው የኾነችን ምጽዋት ያዝ፡፡ خُذْ مِنْ أَمْوَالِهِمْ صَدَقَةً تُطَهِّرُهُمْ وَتُزَكِّيهِم بِهَا
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 45, ሐዲስ 90
አቢ ሀረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ "ሶደቃህ ሀብትን አትቀንስም"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَا نَقَصَتْ صَدَقَةٌ مِنْ مَالٍ
ሚሽከቱል መሷቢሕ መጽሐፍ 6 ሐዲስ 151
መርሰድ ኢብኑ ዐብደሏህ ከአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ባልደረቦች አንዱ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰማው ብሎ ለእርሱ እንደነገረው እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦ "በትንሳኤ ቀን ለሙእሚን ጥላው ሶደቃው ናት"። وَعَنْ مَرْثَدِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ: حَدَّثَنِي بَعْضِ أَصْحَابِ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنَّهُ سَمِعَ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ: «إِنَّ ظِلَّ الْمُؤْمِنِ يَوْمَ الْقِيَامَة صدقته»

አምላካችን አሏህ ሶዶቃን በኢኽላስ የምንሰጥ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተስፈንጣሪ ውኃ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

86፥5 ሰውም ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት። فَلْيَنظُرِ الْإِنسَانُ مِمَّ خُلِقَ

በቁርኣን "ነሥል" نَسْل ማለት “ዘር” ማለት ሲሆን ይህም ዘር የተንጣለለ ውኃ ነው፥ የወንድ የዘር ፈሳሽ"sperm" ውስጡ ያለው ሕዋስ”cell” በራሱ 80% ሳይቶፕላዝም”Cytoplasm” የሚባል ውኃ ነው። ይህ የዘር ፈሳሽ በተራክቦ ጊዜ ተስፈንጦ ስለሚወጣ "ተስፈንጣሪ ውኃ" ተብሏል፦
32፥8 ከዚያም ዘሩን ከተንጣለለ፣ ከደካማ ውኃ ያደረገ ነው፡፡ ثُمَّ جَعَلَ نَسْلَهُ مِن سُلَالَةٍ مِّن مَّاءٍ مَّهِينٍ
86፥5 ሰውም ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፡፡ فَلْيَنظُرِ الْإِنسَانُ مِمَّ خُلِقَ
86፥6 ከተስፈንጣሪ ውኃ ተፈጠረ፡፡ خُلِقَ مِن مَّاءٍ دَافِقٍ

በዘመናዊ ሳይንስ የወንድ የዘር ፈሳሽ የሚወጣው ከቆለጥ"testicle" እንደሆነ ይነገራል፥ በቁርኣን ደግሞ ከሱልብ እንደሆነ አምላካችን አሏህ ነግሮናል፦
86፥7 ከጀርባ እና ከእርግብግብቶች መካከል የሚወጣ ከኾነ፡፡ يَخْرُجُ مِن بَيْنِ الصُّلْبِ وَالتَّرَائِبِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ጀርባ" የሚለው ቃል "ሱልብ" صُّلْبِ ሲሆን የወንዱን የዘር ሥርወ-አብራክን"loin" የሚያመለክት ነው። ይህንን በቀላሉ ለመረዳት የራሳችሁ ባይብል ላይ "ሱልብ" صُّلْبِ የሚለው ቃል የወንዱን የዘር ሥርወ-አብራክን ለማመልከት ተጠቅሞበታል፦
2ኛ ሳሙኤል 7፥12 "ከወገብህ" የሚወጣውን ዘርህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ። وَتُدفَنُ مَعَ آبَائِكَ، سَأُقِيمُ أحَدَ أبْنَائِكِ خَلَفًا لَكَ مِنْ صُلبِكَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ወገብ" ለሚለው የገባው ቃል በተመሳሳይ "ሱልብ" صُلب መሆኑን ልብ አድርግ! የሚገርመው "ወገብ" ለሚለው የገባው የዕብራይስጥ ቃል "ሚዒን" מֵעֶה ነው፦
2ኛ ሳሙኤል 7፥12 "ከወገብህ" የሚወጣውን ዘርህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ። וַהֲקִימֹתִ֤י אֶֽת־זַרְעֲךָ֙ אַחֲרֶ֔יךָ אֲשֶׁ֥ר יֵצֵ֖א מִמֵּעֶ֑יךָ וַהֲכִינֹתִ֖י אֶת־מַמְלַכְתֹּֽו׃

እውን የወንድ ዘር የሚወጣው ከሚዒን ነው? ምክንያቱም "ሚዒን" מֵעֶה ማለት "ልብ" የሚል ትርጉም አለው፦
መዝሙር 40፥8 ሕግህም "በልቤ" ውስጥ ነው። חָפָ֑צְתִּי וְ֝תֹ֥ורָתְךָ֗ בְּתֹ֣וךְ מֵעָֽי׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "ልብ" ለሚለው የገባው ቃል "ሚዒን" מֵעֶה መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። የወንድ የዘር ሕዋስ ከልብ የሚወጣ ነውን? ወይስ "ሚዒን" מֵעֶה የሚለው ቃል በወቅቱ ባህል ብዙ ነገር ለማመልከት ይመጣል? የወንድ የዘር ፈሳሽ በእንግሊዝኛ "sperm" ሲሆን "ስፐርማ" σπέρμα ከሚል ከኮይኔ ግሪክ የመጣ ነው፦
2ኛ ሳሙኤል 7፥12 "ከወገብህ" የሚወጣውን "ዘርህን" ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ። καὶ ἀναστήσω τὸ σπέρμα σου μετὰ σέ, ὃς ἔσται ἐκ τῆς κοιλίας σου,

እዚህ አንቀጽ ላይ "ዘር" ለሚለው የገባው ቃል "ስፐርማ" σπέρμα ከሆነ እውን የወንድ የዘር ሕዋስ የሚወጣው ከልብ፣ ከወገብ፣ ከሆድ፣ ከጉልበት ነውን? የወንድ ሥርወ-አብራክ "ወገብ" "ጉልበት" "ሆድ" ተብሏል፦
1ኛ ነገሥት 8፥19 "ከወገብህ" የሚወጣው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤት ይሠራል።
ዘፍጥረት 15፥4 "ከጉልበትህ" የሚወጣው ይወርስሃል።
መዝሙር 132፥11 "ከሆድህ" ፍሬ በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።

እንዲሁ የሴቷን እንቁላል ሥርወ-አብራክ "ተራኢብ" تَّرَائِبِ ይለዋል፥ "ተራኢብ" تَّرَائِبِ ማለት "እርግብግቢት"ribcage" ማለት ነው፦
86፥7 ከጀርባ እና ከእርግብግቢት መካከል የሚወጣ ከኾነ፡፡ يَخْرُجُ مِن بَيْنِ الصُّلْبِ وَالتَّرَائِبِ

"ተራኢብ" تَّرَائِبِ የሚለው ቃል "ደረት" "ሆድ" "ማኅፀን" ለማመልከት የሚመጣ ሲሆን የእንቁላል ሕዋስ የሚመረትበት እንቁሊጥን"ovary" ለማመልከት የመጣ ነው። ባይብልም ላይ የሴት የእንቁላል ሕዋስ ከሴት ሆድ እንሚገኝ ይናገራል፦
ዘፍጥረት 30፥2 ያዕቆብም ራሔልን ተቆጥቶ፦ በውኑ እኔ የሆድን ፍሬ በነሣሽ በእግዚአብሔር ቦታ ነኝን? አላት። וַיִּֽחַר־אַ֥ף יַעֲקֹ֖ב בְּרָחֵ֑ל וַיֹּ֗אמֶר הֲתַ֤חַת אֱלֹהִים֙ אָנֹ֔כִי אֲשֶׁר־מָנַ֥ע מִמֵּ֖ךְ פְּרִי־בָֽטֶן׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሆድ" ለሚለው የገባው ቃል "በተን" בֶּטֶן ነው፥ እውን የእንቁላል ሕዋስ ሆድ ውስጥ ይመረታልን? "በተን" בֶּטֶן ማለት እኮ "ደረት" "ልብ" ማለትም ነው፦
ምሳሌ 22፥18 እነርሱን "በልብህ" ብትጠብቅ፥ በከንፈሮችህም ላይ የተዘጋጁ ቢሆኑ፥ የተወደደ ነገር ይሆንልሃልና። כִּֽי־נָ֭עִים כִּֽי־תִשְׁמְרֵ֣ם בְּבִטְנֶ֑ךָ יִכֹּ֥נוּ יַ֝חְדָּ֗ו עַל־שְׂפָתֶֽיךָ׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "ልብ" ለሚለው የገባው ቃል "በተን" בֶּטֶן እንደሆነ ልብ አድርግ! በዘመናዊ ሳይንስ የሴት እንቁላል ሕዋስ እንኳን ደረት፣ ልብ እና ሆድ ውስጥ ማኅፀን ውስጥም አይመረትም። ግን ባይብል ላይ የሴት እንቁላል ሕዋስ የሆድ እና የማኅፀን ፍሬ እንደሆነ ይናገራል፦
ሉቃስ 1፥42 የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። καὶ εὐλογημένος ὁ καρπὸς τῆς κοιλίας σου.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ማኅፀን" ለሚለው የገባው ቃል "ኪሊአስ" κοιλίας ሲሆን የሚገርመው "ልብ" ለሚለው ቃል በግሪኩ ሰፕቱአጀንት ገብቷል፦
ዕንባቆም 3፥16 እኔ ሰምቻለሁ፥ "ልቤም" ደነገጠብኝ። ἐφυλαξάμην, καὶ ἐπτοήθη ἡ κοιλία μου

እዚህ አንቀጽ ላይ "ልብ" ለሚለው የገባው ቃል "ኪሊአ" κοιλίας ከሆነ ታዲያ የሴት እንቁላል ሕዋስ የሚወጣው ከሆድ፣ ከማኅፀን፣ ከልብ ነውን? የወንድስ የዘር ሕዋስ የሚወጣው ከልብ፣ ከሆድ፣ ከወገብ፣ ከጉልበት ነውን? መልሱ "አሁን ዘመናዊ ሳይንስ ልብ፣ ደረት፣ ሆድ፣ ወገብ፣ ጉልበት፣ ማኅፀን የሚለው በድሮ ዘመን ሰፊ አገልግሎት እና ትርጉም አለው" ካላችሁ እግር እራስን አያክምና ሱሪ በአንገቴ ላድርግ አትበሉ! እንግዲያውስ "ሱልብ" صُلب ሆነ "ተራኢብ" تَّرَائِبِ ዘርፈ ብዙ እና መጠነ ሰፊ አገልግሎት እና ትርጉም አለው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ጠንቋይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

26፥221 ሰይጣናት በማን ላይ እንደሚወርዱ ልንገራችሁን? هَلْ أُنَبِّئُكُمْ عَلَىٰ مَن تَنَزَّلُ الشَّيَاطِينُ

"ገይብ" غَيْب የሚለው ቃል "ጋበ" غَابَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የሩቅ ወሬ" "የሩቅ ሚስጥር" ማለት ነው፥ ገይብ ከህዋስ ባሻገር ጥንት የተከሰተ አላፊ፣ አሁን እየተከሰተ ያለ አሁናዊ እና ወደ ፊት የሚከሰት መጻኢ ዕውቀት ነው። አምላካችን አሏህ የሰማያትን እና የምድርን የሩቅ ሚስጥር ያውቃል፥ ይህንን የሩቅ ሚስጥር ለሚፈልገው መልእክተኛ ቢሆን እንጂ ለማንም ዐያሳውቅም፦
49፥18 ”አላህ የሰማያትንና የምድርን “ሩቅ ሚስጥር” ያውቃል”። إِنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ غَيْبَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ
72፥26 «እርሱ ”የሩቅ ሚስጥር” ዐዋቂ ነው፡፡ በምስጢሩም ላይ አንድንም አያሳውቅም፡፡» عَٰلِمُ ٱلْغَيْبِ فَلَا يُظْهِرُ عَلَىٰ غَيْبِهِۦٓ أَحَدًا
72፥27 ከመልክተኛ ለወደደው ቢኾን እንጅ ለሌላ አይገልጽም፡፡ إِلَّا مَنِ ٱرْتَضَىٰ مِن رَّسُولٍۢ

ታዲያ ጠንቋይ እንዴት ያውቃል? "ሢሕር" سِحْر የሚለው ቃል "ሣሐረ" سَحَرَ‎ ማለትም "ጠንቆለ" "ደገመ" "መተተ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጥንቆላ" "ድግምት" "መተት" ማለት ነው፥ በሢሕር ሥራ የተሰማራ ሰው "ሣሒር" سَاحِر ሲባል "ጠንቋይ" "ደጋሚ" "መተተኛ" ማለት ነው። ጠንቋይ አላፊ ክስተትን ከሚሰማው እንዲሁ እየተከሰተ ያለውን ከሚሰማው ያውቅ ይሆናል እንጂ በልብ ውስጥ ያለውን እና ወደፊት የሚከሰተውን አያውቅም፥ ቅሉ ግን ሰዎች የሚያወሩትን እና መላእክት በደመና መካከል የሚነጋገሩትን ሸያጢኑል ጂን ሰምተው ወደ ጠንቋዮች ይጥላሉ፦
26፥223 የሰሙትን ወደ ጠንቋዮች ይጥላሉ፡፡ አብዛኞቻቸውም ውሸታሞች ናቸው፡፡ يُلْقُونَ السَّمْعَ وَأَكْثَرُهُمْ كَاذِبُونَ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 59, ሐዲስ 97
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "በምድር ላይ ስለሚሆነው ነገር መላእክት በደመና መካከል ሲነጋገሩ ሸያጢን የሚናገሩትን ቃል ሰምተው በጠንቋይ ጆሮ ውስጥ ያወርዳሉ"። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ الْمَلاَئِكَةُ تَتَحَدَّثُ فِي الْعَنَانِ ـ وَالْعَنَانُ الْغَمَامُ ـ بِالأَمْرِ يَكُونُ فِي الأَرْضِ، فَتَسْمَعُ الشَّيَاطِينُ الْكَلِمَةَ، فَتَقُرُّهَا فِي أُذُنِ الْكَاهِنِ ‏"‌‏.‏

ወሎ ዲባርቱ፣ የአሪሲዋ እመቤት፣ ሞሚናት፣ ባሌ ኑራ ሑሤን፣ ጠቋር፣ አዳልሞቲ፣ ወሰንጋላ የሚባሉ የሸያጢን መንደሮች ውስጥ የሚወርዱ አውልያ ሆነ ዑቃቤ እነዚህ ሸያጢኑል ጂን ናቸው። ሸያጢኑል ጂን ጠንቋዮችን የሚያንቀጠቅጡ፣ የሚያንዘፈዝፉ፣ የሚያስጓሩ፣ አረፋ የሚያስደፍቁ ናቸው፥ በተለይ የኦሮሞ ኡቃቤ ሻንቆ፣ የትግሬ ኡቃቤ ሽቦዬ፣ የዐማራ ኡቃቤ ዲባርቱ ድቤ ሲመታላቸው የሚወርዱት ሸያጢኑል ጂን ናቸው፦
26፥221 ሰይጣናት በማን ላይ እንደሚወርዱ ልንገራችሁን? هَلْ أُنَبِّئُكُمْ عَلَىٰ مَن تَنَزَّلُ الشَّيَاطِينُ
26፥222 በውሸታም ኀጢአተኛ ሁሉ ላይ ይወርዳሉ፡፡ تَنَزَّلُ عَلَىٰ كُلِّ أَفَّاكٍ أَثِيمٍ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 76, ሐዲስ 76
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ "ሰዎች ስለ ጠንቋይ የአሏህን መልእክተኛ"ﷺ" ጠየቋቸው፦ እርሳቸውም፦ "ምንም ናቸው" አሉ። እነርሱም፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" ሆይ! አንዳንዴ እውነት የሆነ ነገር ይነግሩናል" አሉ፥ የአሏህም መልእክተኛ"ﷺ"፦ "ያቺም ከእውነት የሆነች ቃላት ጂን ይነጥቅና በጓደኛው(ጠንቋዩ) ጆሮ ውስጥ ይጥላል፥ ከዚያም ጠንቋዩ ከመቶ ውሸት ጋር ይደባልቀዋል። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ سَأَلَ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم نَاسٌ عَنِ الْكُهَّانِ‏.‏ فَقَالَ ‏"‏ لَيْسَ بِشَىْءٍ ‏"‌‏.‏ فَقَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ إِنَّهُمْ يُحَدِّثُونَا أَحْيَانًا بِشَىْءٍ فَيَكُونُ حَقًّا‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ تِلْكَ الْكَلِمَةُ مِنَ الْحَقِّ، يَخْطَفُهَا مِنَ الْجِنِّيِّ، فَيَقُرُّهَا فِي أُذُنِ وَلِيِّهِ، فَيَخْلِطُونَ مَعَهَا مِائَةَ كَذْبَةٍ ‏"‌‏

የጥንቆላ ምንጭ ሸያጢኑል ጂን ከሆኑ "ዐዋቂ ቤት" ተብሎ የሚጠራበትን ቤት ሄዶ ማስጠንቆል ትልቁ ሺርክ እና ከኢሥላም አጥር የሚያስወጣ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 682
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንዳለው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ "ማንም በሓይድ ላይ ካለች ሴት ተራክቦ ቢያደርግ ወይም በመቀመጫዋ በኩል ተራክቦ ቢያደርግ አሊያም ወደ ጠንቋ ቢሄድ እና የተጠነቆለውን ቢያምን በሙሐመድ”ﷺ” ላይ በተወረደው ክዷል"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ مَنْ أَتَى حَائِضًا أَوِ امْرَأَةً فِي دُبُرِهَا أَوْ كَاهِنًا فَصَدَّقَهُ بِمَا يَقُولُ فَقَدْ كَفَرَ بِمَا أُنْزِلَ عَلَى مُحَمَّد

አምላካችን አሏህ ከጥንቆላ ሺርክ ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
«ለአደም ስገዱ»

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥34 ለመላእክትም «ለአደም ስገዱ» ባልን ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ

አምላካችን አሏህ ለመላእክት«ለአደም ስገዱ» በማለት አዘዛቸው፦
2፥34 ለመላእክትም «ለአደም ስገዱ» ባልን ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ

የአዳም እና የሔዋን ታሪክ ላይ ሚካኤልም ወጥቶ መላእክቱን ሁሉ ጠራ፡- "ጌታ አምላክ እንዳዘዘው ለአምላክ መልክ ለአዳም ስገዱ" አለ፦
"ሚካኤልም ወጥቶ መላእክቱን ሁሉ ጠራ፡- "ጌታ አምላክ እንዳዘዘው ለአምላክ መልክ ለአዳም ስገዱ" አለ።
Life of Adam and Eve Chapter XIV(14) Number 1

ቀሌምንጦስ ዘሮም"Clement of the Rome" ከጴጥሮስ የተቀበለው ንግግር ተብሎ በሚታመነው መጽሐፍ ላይ እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ ወደ አዳም ራሳቸውን አዘንብለው ለአዳም እንደሰገዱ ይናገራል፦
ቀሌምንጦስ 1፥41 አራዊት፣ እንስሳት፣ ወፎች እና "እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ" ወደ አዳም ተሰበሰቡ ከፊቱም ቁመው ራሳቸውን አዘነበሉ "ለ-"አዳም ሰገዱ"።

"እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ" ማለት መላእክትን ይጨምራል፥ ምክንያቱም መላእክት ፍጡራን ኑባሬዎች ናቸውና፥ ፍጥረት ሁሉም ለአዳም ይታዘዝ እና ቃሉንም ይጠብቅ ነበር፦
ቀሌምንጦስ 1፥42"ፍጥረት ሁሉም ለአዳም "ይታዘዝ" እና ቃሉንም ይጠብቅ ነበር።

አምላካችን አሏህ ለመላእክት«ለአደም ስገዱ» ሲል ለኢብሊሥ "ስገድ" አለማለቱን አያሳይም፥ ምክንያቱም አሏህ «ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ?» ብሎታልና፦
7፥12 አላህ፦ «ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ?» አለው፡፡ قَالَ مَا مَنَعَكَ أَلَّا تَسْجُدَ إِذْ أَمَرْتُكَ

“ባዘዝኳችሁ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ" ሳይሆን “ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ" አለው፥ “ባዘዝኩህ” የሚለው ኃይለ ቃል "ለአደም ስገድ" ብሎ አዞት እንደነበር ቁልጭና ፍንትው አድርጎ ያሳይል። ለምሳሌ፦ ፈጣሪ አዳምን "መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ" ብሎት ነበር፦
ዘፍጥረት 2፥17 ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ።

ጥቅሱ ላይ "አትብላ" እንጂ "አትብሉ" አላላቸውም፥ ነገር ግን ሔዋን፦ "እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ አትንኩትም" ያህዌህ ብሎናል ብላለች፦
ዘፍጥረት 3፥3 ነገር ግን በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ፥ ያህዌህ አለ፦ "እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ አትንኩትም"።

ለሁለቱም ግን "አትብሉ" ያለበት ትእዛዝ አለመገለጹ ግን "አላላቸውም" እንደማንል በተመሳሳይ "ስገድ" ያለበት ጥቅስ አለመኖሩ "ስገድ አላለውም" አያሰኝም። ሲቀጥል "መላእክት" በሚል ቃል መነሻ ቅጥያ ላይ "ለ" የሚለውን መስተዋድድ "ብቻ" በሚል መረዳት የለብንም፦
7፥179 ”ለ”እነርሱ ልቦች አሏቸው፥ ግን አይገነዘቡበትም፣ “ለ”እነርሱም ዓይኖች አሉዋቸው፥ ግን ዐያዩበትም፣ “ለ”እነርሱም ጆሮዎች አሉዋቸው ግን አይሰሙበትም፡፡ لَهُمْ قُلُوبٌ لَّا يَفْقَهُونَ بِهَا وَلَهُمْ أَعْيُنٌ لَّا يُبْصِرُونَ بِهَا وَلَهُمْ آذَانٌ لَّا يَسْمَعُونَ بِهَا

"እነርሱ" የተባሉት ከሰው እና ከጂኒ ያመጹ ከሓድያን ሲሆኑ "እነርሱ" በሚል ቃል መነሻ ቅጥያ ላይ "ለ" የሚለውን መስተዋድድ ስላለ "ልቦች" "ዓይኖች" "ጆሮዎች" ያሉአቸው ኩፋሮች ብቻ ናቸው እንደማንል ሁሉ "ለመላእክት" የሚለውም ለኢብሊሥ እንዳልተባለ ማስረጃ አይሆንም፦
2፥34 ሁሉም ወዲያውኑ ሰገዱ፥ ኢብሊሥ ብቻ ሲቀር። "እምቢ" አለ ኮራም ከከሓዲዎቹም ኾነ፡፡ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ أَبَىٰ وَاسْتَكْبَرَ وَكَانَ مِنَ الْكَافِرِينَ

“ኢብሊሥ ብቻ ሲቀር” በሚለው ኃይለ ቃል ላይ “ሲቀር” የምትለዋን ይዘን "ኢብሊሥ ከመላእክት ነበር" ማለት አሁንም የቁርኣንን ሰዋስው ካለመረዳት የሚመጣ ጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት ነው፦
26፥77 «እነርሱም ለእኔ ጠላቶች ናቸው፡፡ ግን የዓለማት ጌታ ሲቀር እርሱ ወዳጄ ነው»፡፡ فَإِنَّهُمْ عَدُوٌّ لِّي إِلَّا رَبَّ الْعَالَمِينَ

ኢብራሂም፦ “ለእኔ ጠላቶች ናቸው። ግን የዓለማት ጌታ ሲቀር” ማለቱን አስተውል! “ሲቀር” የሚለውን አፍራሽ ቃል ይዘን ከዓለማቱ ጌታ ውጪ ለኢብራሂም ሁሉም ጠላት ነውን? አማንያን፣ ነቢያት፣ መላእክት፣ እንስሳትስ ጠላት ናቸውን? አይ “በቀር” የሚለው በአንጻራዊ ደረጃ  የአሏህን ወዳጅ ለመሆን የገባ እንጂ “ሁሉን ጠላት ናቸው ከአሏህ በቀር” ማለቱን አያሳይም ከተባለ እንግዲያውስ “በቀር” የሚለው በአንጻራዊ ደረጃ ኢብሊሥ ብቻ አለመታዘዙን እንጂ መላእክት ውስጥ መካተቱን አያሳይም።

ዲያብሎስ ክሣደ ልቡናውን በማጽናት እና ራሱን በማኩራት ፈጣሪው ለፈጠረው ለአዳም መስገድን "እምቢ" ብሏል፦
2ኛ መቃብያን 9፥3 ክሣደ ልቡናውን በማጽናት እና ራሱን በማኩራት ፈጣሪው ለፈጠረው ለአዳም መስገድን እምቢ ብሏልና።

ዲያብሎስም ከማዕረጉ የወረደው "ለአዳም አልሰግድም" በማለቱ እንደሆነ በጸጸት ተናግሯል፦
3ኛ መቃብያን 1፥15 "ለአዳም አልሰግድም በማለቴ እግዚአብሔር ስለ አባታቸው ስለ አዳም ከማዕረጌ አዋርዶኛልና።

አሏህ ለመላእክት«ለአደም ስገዱ» ማለቱን አክብሮቱን ያሳያል እንጂ "አደምን አምልኩ" የሚለውን አያሲዝም። እንደዛማ ቢሆንማ ፈጣሪ በኢየሱስ ለፊላድልፍያ ጉባኤ ኤጲስ ቆጶስ ለሆነው ሰው እንደሚያሰግድ ይናገራል፦
ራእይ 3፥9 እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት "ይሰግዱ" ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።  ἰδοὺ ποιήσω αὐτοὺς ἵνα ἥξουσιν καὶ προσκυνήσουσιν ἐνώπιον τῶν ποδῶν σου, καὶ γνῶσιν ὅτι ἐγὼ ἠγάπησά σε.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ስግደት" ለሚለው የገባው ቃል "ፕሩስኩኔኦ" προσκυνέω ነው፥ እና ፈጣሪ ኤጲስ ቆጶሱን እያስመለከ ነው? "ኸረ በፍጹም" ካላችሁ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን እሳቤ በዚህ መልክ እና ልክ መረዳት ቀላል ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መካከለኛ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥75 የመርየም ልጅ አልመሢሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ

ሙሴ ከኢየሱስ መላክ በፊት በብሉይ ኪዳን በአምላክ እና በሕዝቡ መካከል ሆኖ መልእክት ሲያስተላልፍ የነበረ መካከለኛ ነበረ፦
ዘዳግም 5፥5 እኔ የያህዌህን ቃል እነግራችሁ ዘንድ በዚያን ጊዜ በያህዌህ እና በእናንተ መካከል ቆሜ ነበር።

"በያህዌህ እና በእናንተ መካከል" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! ፈጣሪም በሙሴ በኩል፦ "ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ ያህዌህ አምላክህ እኔ ነኝ" አለ፦
ዘዳግም 5፥6 እርሱም አለ፦ "ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ ያህዌህ አምላክህ እኔ ነኝ"።

"ሜሲተስ" μεσίτης ማለት "መካከለኛ"mediator" ማለት ሲሆን ሙሴ ተስፋው የተሰጠው ዘር መሢሑ እስኪመጣ "መካከለኛ" ነበረ፦
ገላትያ 3፥19 ሕጉ የመጣው በመላእክት በኩል በአንድ "መካከለኛ እጅ" ነበር።(አዲሱ መደበኛ ትርጉም) διαταγεὶς δι’ ἀγγέλων ἐν χειρὶ μεσίτου.

ሕግ የመጣው በመላእክት በኩል ነው፥ በተለይ "በስተ ቀኙም የእሳት ሕግ ነበረላቸው" የሚለውን ስንረዳ የእሳት ሕግ የተባለው ቶራህ ሲሆን ቅዱሳኑ የተባሉት መላእክት ናቸው፦
ዘዳግም 33፥2 ከአእላፋትም ቅዱሳኑ መጣ፤ "በስተ ቀኙም የእሳት ሕግ" ነበረላቸው።
ሐዋ. ሥራ 7፥53 በመላእክት ሥርዓት ሕግን ተቀበላችሁ። Who have received the law by the disposition of angels.
ዕብራውያን 2፥2 በመላእክት የተነገረው ቃል ጽኑ ከሆነ።

ገላትያ 3፥19 "መካከለኛ" ለሚለው የገባው ቃል "ሜሲቶዩ" μεσίτου ሲሆን "እጅ" የሚለውን ለማገናዘብ የመጣ አገናዛቢ ነው፥ ይህም "መካከለኛ" የሚለው ቃል "ሙሴ" የሚለውን ስም ተክቶ የመጣ ነው፦
ዘኍልቍ 4፥37 ያህዌህ "በሙሴ እጅ" እንዳዘዘ።
ነህምያ 9፥14 ትእዛዝንና ሥርዓትን ሕግንም በባሪያህ "በሙሴ እጅ" አዘዝሃቸው።
ነህምያ 10፥29 በያህዌህም ባሪያ "በሙሴ እጅ" በተሰጠው በያህዌህ ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥
ነህምያ 8፥15 ያህዌህ "በሙሴ እጅ" እንዳዘዘ በሕጉ ውስጥ ተጽፎ አገኙ።

"በመካከለኛ እጅ" የሚለው "በሙሴ እጅ" የሚለውን ለመተካት የመጣ እንደሆነ ካየን ዘንዳ ሙሴ "መካከለኛ" መባሉ አስረግጠን እና ረግጠን መናገር እንችላለን። መካከለኛው ሙሴ መካከለኛነቱ ለአንድ ማንነት ሳይሆን ለአዛዥ አምላክ እና ለታዛዥ ሕዝቡ ሲሆን አምላክ ግን አንድ ማንነት ነው፦
ገላትያ 3፥20 መካከለኛውም ለአንድ ብቻ አይደለም፥ አምላክ ግን አንድ ነው። ὁ δὲ μεσίτης ἑνὸς οὐκ ἔστιν, ὁ δὲ Θεὸς εἷς ἐστιν.
ኢዮብ 9፥32 እጁን በሁለታችን ላይ የሚያኖር "መካከለኛ" በመካከላችን ምነው በተገኘ። εἴθε ἦν ὁ μεσίτης ἡμῶν καὶ ἐλέγχων καὶ διακούων ἀνὰ μέσον ἀμφοτέρων·

ኢዮብ ከሙሴ በፊት በእርሱ እና በአምላኩ መካከል "መካከለኛ" እንዲኖር ተመኝቶ ከ 400 ዓመት በኃላ ሙሴ መካከለኛ ሆኖ ተነስቷል። ታዲያ ሙሴ ምን ነበር? ሰው እና ነቢይ ወይስ የአምላክ እና የሰው ውሕደት? "መካከለኛ" ማለት "የአምላክ እና የሰው ውሕደት" ነው" ብለው የሚቀጥፉ ሰዎች ሙሴ "መካከለኛ" መባሉን ሲረዱ ምን ይውጣቸው ይሆን? ኢየሱስም በአዲስ ኪዳን "መካከለኛ" የተባለው ሙሴ በተባለበት ቀመር እና ሒሣብ ነው፦
1 ጢሞቴዎስ 1፥5 አንድ አምላክ አለና፥ በአምላክ እና በሰዎች መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። εἷς γὰρ Θεός, εἷς καὶ μεσίτης Θεοῦ καὶ ἀνθρώπων, ἄνθρωπος Χριστὸς Ἰησοῦς,

እዚህ አንቀጽ ላይ በግልጽ እና በማያሻማ መልኩ "መካከለኛ" የተባለው ከአንዱ አምላክ ውጪ "ሰው" እንደሆነ ይናገራል፥ ይህም ሰው በአምላክ እና በሕዝቡ መካከል በሥራ እና በቃል ብርቱ ነቢይ የነበረው የናዝሬቱ ኢየሱስ ነው። የናዝሬቱ ኢየሱስ ከአምላክ እየሰማ ለሕዝቡ የሚናገር መካከለኛ ሰው ነበር፦
ሉቃስ 24፥19 በአምላክ እና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራ እና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ።
ዮሐንስ 8፥40 ነገር ግን አሁን ከአምላክ የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ?።

አምላክ ባለቤት ሲሆን ሰው ተሳቢ ነው፥ በባለቤት እና በተሳቢ መካከል "የሰማሁት" የሚል አጫፋሪ ግሥ አለ። ይህ ቁልጭ እና ፍንትው አድርጎ የሚያሳየው በላከው አምላክ እና በተላከው መካከለኛ ሰው ያለውን የማንነት እና የምንነት ልዩነት ነው። እርግጥ ነው! ኢየሱስ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፦
5፥75 የመርየም ልጅ አልመሢሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም