ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.3K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
እንኳን አደረሳችሁ!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ ፡፡

“ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፥ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል። ነቢያችን”ﷺ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻና ብቻ ናቸው፥ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ *"የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን" አሏቸው*። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፥ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፦ *"የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” በሁለቱ በአል በኢደል አደሐ እና ኢደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል"*። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ ‏.

ማንኛውም መመሪያ ቁርአን እና የነቢያችን”ﷺ” ሐዲስ ላይ ይገኛል። አላህም፦ “መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት! ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ” ብሎናል፦
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ ፡፡
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 53, ሐዲስ 7
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"“ማንኛውም ሰው ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም"*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ فِيهِ فَهُوَ رَدٌّ ‏”‌‏.‏

በፀሐይ አቆጣጠር መስከረም እንዲሁ በጨረቃ አቆጣጠር ሙሐረም አዲስ ዓመት እና የወር መጀመሪያ ነው። ቅሉ ግን እነዚህን ዘመን መለወጫ በዓል አርጎ በመያዝ፣ ገና እና ፋሲካ "እንኳን አደረሳችሁ" መባባል ሸሪዓዊ መሠረት የሌለው፣ ቀደምት ሠለፎች ያላደረጉት እና ቢድዓህ ነው።
“ሑክም” حُكْم የሚለው ቃል”ሐከመ” حَكَمَ ማለትም “ፈረደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ፍርድ” “ሕግ” "መርሕ" ማለት ነው፥ “አሕካም” أَحْكَام‎ ደግሞ የሑክም ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሕግጋት” ማለት ነው። በኢሥላም አሕካም በአምስት ዋና ዋና ክፍል ሲከፈሉ፥ ከአምስቱ አንዱ "ሐላል" ነው። "ሐላል" حَلاَل ማለት "የተፈቀደ" ማለት ነው፦
16፥116 *"በአላህም ላይ ውሸትን ልትቀጣጥፉ ምላሶቻችሁ በሚመጥኑት ውሸት «ይህ የተፈቀደ ነው፥ ይህም እርም ነው» አትበሉ"*፡፡ وَلَا تَقُولُوا لِمَا تَصِفُ أَلْسِنَتُكُمُ الْكَذِبَ هَـٰذَا حَلَالٌ وَهَـٰذَا حَرَامٌ لِّتَفْتَرُوا عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ
እዚህ አንቀጽ ላይ “የተፈቀደ” ለሚለው የገባው ቃል “ሐላል” حَلاَل መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። አንድ ጉዳይ ሐላል ወይም ሐራም ማለት የሚችለው የዓለማቱ ጌታ አሏህ በነቢዩ”ﷺ” ብቻ እና ብቻ ነው፥ ሐላል የሆነ ጉዳይ ሆነ ሐራም የሆነ ጉዳይ በሸሪዓችን በግልጽ የተቀመጡት ብቻ ናቸው፦
7፥157 *"መልካም ነገሮችንም ለነርሱ ይፈቅድላቸዋል፥ መጥፎ ነገሮችንም በእነርሱ ላይ እርም ያደርግባቸዋል"*፡፡ وَيُحِلُّ لَهُمُ الطَّيِّبَاتِ وَيُحَرِّمُ عَلَيْهِمُ الْخَبَائِثَ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 23, ሐዲስ 4
አን-ኑዕማን ኢብኑ በሺር እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ሐላል ግልጽ ነው፥ ሐራምም ግልጽ ነው። በሁለቱ መካከል ያለው ግን አጠራጣሪ ነገር ነው”። قَالَ سَمِعْتُ النُّعْمَانَ بْنَ بَشِيرٍ، – وَلاَ أَسْمَعُ أَحَدًا بَعْدَهُ يَقُولُ – سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏”‏ إِنَّ الْحَلاَلَ بَيِّنٌ وَإِنَّ الْحَرَامَ بَيِّنٌ وَبَيْنَهُمَا أُمُورٌ مُشْتَبِهَاتٌ ‏”‏

አንድ ጉዳይ በግልጽ መፈቀዱ እና መከልከሉ ካልተገለጸ "ተፈቅዷል" "ተከልክሏል" ማለት የለብንም፥ ያልተፈቀደ እና ያልተከለከለ ነገር ጉዳይ አጠራጣሪ ነው፥ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ደግሞ፦ "የሚያጠራጥርህን ትተህ ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት ያረጋጋል፥ ውሸት ግን ያጠራጥራል" ብለውናል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 2708
አቢል ሐውራእ አሥ-ሠዕዲይ እንደተረከው፦ "እኔ ለሐሠን ኢብኑ ዐሊይ፦ "ከአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ምን ሐፈዝክ? ብዬ አልኩኝ፥ እርሱም፦ "ከአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሐፈዝኩኝ፦ *"የሚያጠራጥርህን ትተህ ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት ያረጋጋል፥ ውሸት ግን ያጠራጥራል"*። عَنْ أَبِي الْحَوْرَاءِ السَّعْدِيِّ، قَالَ قُلْتُ لِلْحَسَنِ بْنِ عَلِيٍّ مَا حَفِظْتَ مِنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ حَفِظْتُ مِنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ دَعْ مَا يَرِيبُكَ إِلَى مَا لاَ يَرِيبُكَ فَإِنَّ الصِّدْقَ طُمَأْنِينَةٌ وَإِنَّ الْكَذِبَ رِيبَةٌ ‏"‏

ቅሉ ግን ከዚያ በተቃራኒ ሸሪዓህ በመቃረን ከሃይማኖት አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነርሱ የደነገጉ በአሏህ ላይ አሻርከዋል፦
42፥21 *"ከሃይማኖት አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነርሱ “የደነገጉ” ተጋሪዎች ለእነርሱ አሏቸውን?"* أَمْ لَهُمْ شُرَكَاءُ شَرَعُوا لَهُم مِّنَ الدِّينِ مَا لَمْ يَأْذَن بِهِ اللَّهُ

እዚህ አንቀጽ ላይ “የደነገጉ” ለሚለው የገባው ቃል “ሸረዑ” شَرَعُوا ሲሆን መለኮታዊ ያልሆነ ከዝንባሌአቸው ሸሪዓህ መደንገጋቸው የሚያሳይ ቃል ነው። “ሸሪክ” شَرِيك ማለት “ተጋሪ” ማለት ነው፥ የሸሪክ ብዙ ቁጥር ደግሞ “ሹረካእ” شُرَكَاء ሲሆን “ተጋሪዎች” ማለት ነው፥ አሏህ በእርሱ ያልፈቀደውን ነገር ሐላል ማድረግ ለእነርሱ የደነገጉ በአላህ ሐቅ ላይ ተጋሪዎች አሏቸው። እነዚህ የአሏህን ሐቅ የሚጋሩ ሰዎች እራሳቸው ተሕሊል እና ተሕሪም በማድረጋቸው ጣዖታት ናቸው፦
4፥60 ወደ እነዚያ እነርሱ በአንተ ላይ በተወረደው እና ከአንተ በፊትም በተወረደው አምነናል ወደሚሉት አላየህምን? “በእርሱ እንዲክዱ በእርግጥ የታዘዙ ሲኾኑ ወደ ጣዖት መፋረድን ይፈልጋሉ”፡፡ أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِينَ يَزْعُمُونَ أَنَّهُمْ آمَنُوا بِمَا أُنزِلَ إِلَيْكَ وَمَا أُنزِلَ مِن قَبْلِكَ يُرِيدُونَ أَن يَتَحَاكَمُوا إِلَى الطَّاغُوتِ وَقَدْ أُمِرُوا أَن يَكْفُرُوا بِهِ

አንድ ሰው አሏህ ካወረደው ውጪ፦ "ይህ ነገር ሐራም ነው፥ ይህ ነገር ሐላል ነው" ካለ እርሱ ጣዖት ነው። “ጧጉት” طَّٰغُوت የሚለው ቃል “ጦጋ” طَغَىٰ ማለትም “ወሰን አለፈ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “በአላህ ሐቅ ላይ ወሰን ማለፍ” ማለት ነው። አምላካችን አሏህ ሸሪዓችን፦ "ሐላል ያለውን ሐላል፥ ሐራም ያለውን ሐራም" የምንለን ያድርገን! ዝንባሌአችንን ከመከተል ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

112፥3 አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

"በሃእ" بهاء ማለት "ክብር" ማለት ሲሆን "አብሃ" أبهى ደግሞ "በሃእ" بهاء ለሚለው ገላጭ ቅጽል ጡዘታዊ ደረጃ"superlative degree" ነው። በሃኢይ بهائی‎ ማለት "ባሃያዊ" ማለት ሲሆን በተሳሳተ አጠራር "ባሃኢ" ይባላሉ።
"በሃኡልላህ" بهاء الله ማለት "የአሏህ ክብር" ማለት ነው ሲሆን፦
፨"በሃኡልላህ" የሚለው ስም ልጁ "አብዱል በሃእ" ለአባቱ ለሚርዛ ሑሤን ዐሊይ ያወጣለት ስም ነው፣
፨በሃኡልላህ ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ እራሱ በሕይወት ዘመኑ "በሃኡልላህ" የሚለውን ስም ዐያውቀውም፣
፨በተጨማሪም "በሃኡልላህ" የሚለው ስም በሚርዛ ሑሤን ዐሊይ ጽሑፎች ውስጥ የለም።
ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ1863 ድኅረ ልደት፦ "እኔ አሏህ ነኝ" ብሎ ማስተማር ጀመረ፦
"ከእኔ ከተከበርኩት እና ከጥበበኛው በቀር አምላክ የለም" አቅዳሥ ገፅ 43
"በዘላለማዊ ጌታ በበሃእ የታዘዘውን ምንም ይሁን ተቀበል" አቅዳሥ ገፅ 144
"ሁሉንም መልእክተኞች ልከናል፥ ሁሉንም መጽሐፍት አውርደናል" አቅዳሥ ገፅ 8
"ዘላለማዊ ጌታ በእስር ቤት ውስጥ ተዋሽቶበታል" ኢሥተደራት ገፅ 34
"ባሃእ ሆይ! የህልውና ፈጣሪ ሆይ! ምስጋና ሁሉ ለአንተ ነው" አል-ሙቢን ገፅ 34
"የአንተን ከፍ ያለ እና የተፈራ አምላክ ባሃእን ታዘዝ!" አል-ሙቢን ገፅ 190
"ባሃእ አንተ በጣም በጎ አድራጊ ጌታ ነህ" አል-ሙቢን ገፅ 297
"እኔ አሏህ ነኝ፥ ከእኔ በቀር አምላክ የለም፥ እኔ የሁሉ ነገር ጌታ ነኝ። ፍጡሮቼ ሆይ እኔን ብቻ አምልኩኝ" ታጀሊያት ገፅ 5

"በሃእ" بهاء የአሏህ ታላቅ ስም ሲሆን የሚርዛ ሑሤን ዐሊይ የቅባት ስሙ እንደሆነ እራሱ ይናገራል። ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ "አሏሁ አብሃ" الله أبهى‎ እያለ እራሱን ያሞጋግስ ነበር፥ "አሏሁ አብሃ" الله أبهى‎ ማለት "አሏህ በሃእ ነው" ማለት ነው።
የሚርዛ ሑሤን ዐሊይ ልጅ ዐባሥ ኢፌንዲ እራሱን "ዐብዱል በሃእ" عبد البهاء ሲል ትርጉሙ "የበሃእ ባሪያ ወይም አምላኪ" ማለቱ ነበር፥ ልክ "ዐብደልላህ" عبد الله‎ ማለት "የአሏህ ባሪያ ወይም አምላኪ" እንደ ማለት ነው።
ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ ሙሣን በሢና ተራራ ላይ ያናገረ እንዲሁ ተወዳጁ ነቢያችንን"ﷺ" በሲድረቱል ሙንተሃ ላይ ያናገረ አሏህ እራሱ እንደሆነ እና ከሟች ዓይኖች ተደብቆ የነበረው አሏህ እራሱ ሆኖ እንደመጣ ይናገራል፦
"እርሱ በእውነቱ የግልጸት ጎኅ የሆነውን፣ በሢና ላይ የተነጋገረውን፣ በእርሱ አማካኝነት የላቀ አድማስ እንዲያበራ የተደረገውን፣ በእርሱ ሢድረቱል ሙንተሃ ላይ የተናገረውን፣ በእርሱ አማካኝነት በሰማያት እና በምድር ላሉት ሁሉ፦ "እነሆ የሁሉ ባለቤት መጥቷል" መካከለኛ የግዴታ ጸሎት
"እርሱ ከሟች ዓይኖች ተደብቆ የነበረው መጥቷል" ቅስማት 13

ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ መቃብሩ ላይ ለጉብኝነት እንዲህ ብለው እንዲጸልዩ ተናግሯል፦
"አምላኬ እና ወዳጄ ሆይ!... የሕይወት ቀናትህ ሁሉ በስቃይ ውቂያኖስ ውስጥ እንድትሰጥም ተደርገሃል፥ በአንድ ወቅት በእግር ብረት እና በሰንሰለት ታስረካል" የባሃኡሏህ ጉብኝነት ከሚል ጸሎት የተወሰደ

እውን የዓለማቱ ጌታ አሏህ በፍጡራኑ ስቃይ እና እስራት ደረሰበት እያላችሁን ነውን? ክርስቲያኖች፦ "ፈጣሪ ተወልዶ በፍጡሮቹ ተገደለ" ከሚሉት ትምህታቸው ልዩነቱን ትነግሩኝ?
አሏህ አንድ ነው፥ እርሱ ከማንነቱ እና ከምንነቱ ማንንም አልወለደም። ከእርሱ ማንነት እና ምንነት የተወለደ ማንም የለም፥ ከእርሱ የተወለደ ማንም አምላክ የለም፦
112፥1 በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ
112፥3 አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ
23፥91 አላህ ምንም ልጅን አልወለደም፡፡ ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ مَا اتَّخَذَ اللَّهُ مِن وَلَدٍ وَمَا كَانَ مَعَهُ مِنْ إِلَـٰهٍ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 496
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “ነቢዩ”ﷺ” አሏህ እንዲህ አሉ፦ “አሏህም አለ፦ “የአደም ልጅ እኔን አስዋሸ፥ እንዲህ ለማድረግ መብት አልነበረውም፡፡ ደግሞም ሰደበኝ፥ እንዲህ ለማድረግም መብት አልነበረውም፡፡ እኔን ማስዋሸቱ የሚያመለክተው፦ “መጀመሪያ ላይ አድርጎ ዳግም አይሠራኝም” የሚለው ንግግሩ ነው፥ ለመሆኑ መጀመሪያ እርሱን መፍጠር ነው ወይስ ዳግም መሥራት ለእኔ ይበልጥ የሚቀል የነበረው? እኔን መሳደቡን የሚያመለክተው እንደፈጠረኝደግሞ፦ “አሏህ ልጅ ወልዷል” ማለቱ ነው፥ እኔ አንድ ነኝ፣ የሁሉ መጠጊያ ነኝ፣ አልወለድኩም፣ አልተወለድኩም፣ ለእኔ አንድም ብጤ የለኝም”፡፡ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ قَالَ اللَّهُ كَذَّبَنِي ابْنُ آدَمَ وَلَمْ يَكُنْ لَهُ ذَلِكَ، وَشَتَمَنِي وَلَمْ يَكُنْ لَهُ ذَلِكَ، فَأَمَّا تَكْذِيبُهُ إِيَّاىَ فَقَوْلُهُ لَنْ يُعِيدَنِي كَمَا بَدَأَنِي، وَلَيْسَ أَوَّلُ الْخَلْقِ بِأَهْوَنَ عَلَىَّ مِنْ إِعَادَتِهِ، وَأَمَّا شَتْمُهُ إِيَّاىَ فَقَوْلُهُ اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا، وَأَنَا الأَحَدُ الصَّمَدُ لَمْ أَلِدْ وَلَمْ أُولَدْ وَلَمْ يَكُنْ لِي كُفْأً أَحَدٌ ‏”‌‏.‏

አሏህ ከሚሉት ነገር ጥራት ይገባውና ከወለደ በአንድነቱ ላይ ብዝኃነት ሊመጣ ነው፥ ከተወለደ ደግሞ መነሾ እና ጅማሮ ሊኖረውን ነው። ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ ከአባቱ ከሚርዛ ዐባሥ ኑሪ እና ከእናቱ ከኸዲጃ ኸኑን የተወለደ ሲሆን አሏህ ግን አይወለድም፥ ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ ከሦስት ሚስቶቹ 14 ልጆች የወለደ ሲሆን አሏህ ግን አይወልድም። ስለዚህ ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ፦ "አሏህ ነኝ" ብሎ የተነሳው ትምህርቱ የሐሠት ትምህርት ነው።

ኢንሻሏህ ይቀጥላል....
ይህንን የበሃኢይን ፈሣድ ለሙሥሊሙ ኡማህ በመግለጥ እና በማጋለጥ ተደራሽነት እንዲኖረው ሼር አርጉ!

ከወንድም አሚን ሪድዋን
https://tttttt.me/Amin_redwan

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

33፥40 ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድም ሰው አባት አይደለም፡፡ ግን የአላህ መልክተኛ እና የነቢያት መደምደሚያ ነው፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ مَّا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِّن رِّجَالِكُمْ وَلَـٰكِن رَّسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا

ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ1863 ድኅረ ልደት ባግዳድ ላይ፦ "እኔ አሏህ ነኝ" ብሎ ሲያውጅ የባግዳድ ምሁራን በዕውቀት ሲያጣድፉት እና ሲያንቆራጥቱት፦ "ነቢይ ነኝ" ብሎ አረፈው።
“ነቢይ” نَبِيّ የሚለው ቃል “ነበአ” نَبَّأَ ማለትም “አወራ” ወይም “ተናገረ” ከሚል ሥርወ-ቃል ሲሆን “አውሪ” ወይም “ተናጋሪ” ማለት ነው፥ የነቢይ ብዙ ቁጥር ደግሞ “ነቢዩን” نَبِيُّون ወይም “አንቢያእ” أَنْبِيَاء ነው። አንድ ሰው ከአላህ ዘንድ “ነበእ” نَبَأ ማለትም “የሩቅ ወሬ” ወይም “የሩቅ ንግግር” ሲወርድለት ነቢይ ይሰኛል፦
66፥3 *”ነቢዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሰጠረ ጊዜ አስታውስ፡፡ እርሱንም በነገረች እና አላህ እርሱን ማውራትዋን ባሳወቀው ጊዜ ከፊሉን አስታወቀ፤ ከፊሉንም ተወ፡፡ በእርሱም ባወራት ጊዜ «ይህን ማን ነገረህ?» አለች፡፡ «ዐዋቂው ፥ውስጠ ዐዋቂው ነገረኝ» አላት”*። وَإِذْ أَسَرَّ ٱلنَّبِىُّ إِلَىٰ بَعْضِ أَزْوَٰجِهِۦ حَدِيثًۭا فَلَمَّا نَبَّأَتْ بِهِۦ وَأَظْهَرَهُ ٱللَّهُ عَلَيْهِ عَرَّفَ بَعْضَهُۥ وَأَعْرَضَ عَنۢ بَعْضٍۢ ۖ فَلَمَّا نَبَّأَهَا بِهِۦ قَالَتْ مَنْ أَنۢبَأَكَ هَٰذَا ۖ قَالَ نَبَّأَنِىَ ٱلْعَلِيمُ ٱلْخَبِيرُ

በዚህ አንቀጽ ውስጥ “ማን ነገረህ” ለሚለው ቃል የገባው “መን አንበአከ” مَنْ أَنْبَأَكَْ ሲሆን መልሱ “ነበአኒየ” نَبَّأَنِيَ ማለትም “ነገረኝ” ማለት ነው። “አንበአከ” أَنْبَأَكَْ ሆነ “ነበአኒየ” نَبَّأَنِيَ የሁለቱም ግስ ርቢ “ነበአ” نَبَّأَ ነው። ስለዚህ “ነቢይ” ማለት ሁሉን ዐዋቂው፥ ውስጠ ዐዋቂው አላህ የሚያናግረው እና የሚነግረው ማለት ነው። ከዚያም ባሻገር መመሪያው እራሱ በራሱ የነቢይነት መደብ ውስጥ ነው፦
15፥49 *”ባሮቼን እኔ ይቅርባዩ መሓሪው እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው”*፡፡ نَبِّئْ عِبَادِي أَنِّي أَنَا الْغَفُورُ الرَّحِيمُ

“ንገራቸው” نَبِّئْ ለሚለው ትእዛዛዊ ግስ አሁንም “ነበእ” نَبِّئْ ሲሆን “ነበአ” نَبَّأَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ነው። አንድ ነቢይ ለአማንያን በመልካም ለማዘዝ እና በመጥፎ ለመከልከል ያስጠነቅቃል፥ ለራሱም ዒባዳህ ምን ምን ማድረግ እንዳለበት አላህ ይነግረዋል።
“ረሡል” رَسُول የሚለው ቃል “አርሠለ” أَرْسَلَ ማለትም “ላከ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መልእክተኛ” ማለት ነው፥ የረሡል ብዙ ቁጥር ደግሞ “ሩሡል” رُسُل ነው። አንድ ነቢይ ሕግ ያለበት “ሪሣላህ” رِسَالَة ማለትም “መልእክት” ሲወርድለት ረሡል” ይሆናል። ረሡል ለአማንያን እና ለከሃድያን ለማስጠንቀቅ በሸሪዓህ ይላካል፦
22፥52 *”ከመልእክተኛ እና ከነቢይም”* ከአንተ በፊት አንድንም አልላክንም፥ ባነበበ ና ዝም ባለ ጊዜ፣ ሰይጣን በንባቡ ላይ ማጥመሚያን ቃል የሚጥል ቢሆን እንጂ። وَمَا أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلِكَ مِنْ رَسُولٍ وَلَا نَبِيٍّ إِلَّا إِذَا تَمَنَّىٰ أَلْقَى الشَّيْطَانُ فِي أُمْنِيَّتِهِ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ነቢይ” نَبِيّ እና “ረሡል” رَسُول በሚሉት የማዕረግ ስሞች መካከል “ወ” وَ ማለትም “እና” የሚል መስተጻምር አለ፥ ይህም ነቢይ እና ረሡል ሁለት የተለያየ ደረጃ መሆኑን ቁልጭና ፍንትው አድርጎ ያሳያል። በተጨማሪም “አልላክንም” የሚለው አጽንዖታዊ ቃል “ቢሆን እንጂ” በሚል አፍራሽ ቃል በመምጣቱ ነብይ በመልካም እንዲያዝ በመጥፎ እንዲከለክል ለአማንያን እንደተላከ ሁሉ መልእክተኛ ደግሞ ለአማንያንና ለከሃድያን ለማስጠንቀቅና ለማብሰር ይላካል። መልእክተኛ መልክተኛ ለመሆን ነቢይነትን አሳልፎ ስለሆነ መልእክተኛ ሁሉ ነቢይ ነው፥ ነቢይ ሁሉ ግን መልእክተኛ አይደለም። ምክንያቱም ሪሣላ ሳይወርድለት ነቢይ ብቻ ሆኖ የሚቀር አለ፥ ለምሳሌ አደም የመጀመሪያው ነቢይ ሲሆን ኑሕ ደግሞ የመጀመሪያው ረሡል ነው፦
ኢማም አሕመድ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 1781
አቡ ዘር እንደተረከው፦ *”የአላህ ነቢይ”ﷺ” ሆይ የመጀመሪያው ነቢይ ማን ነው? ብሎ አለ። እርሳቸውም፦ “አደም ነው” አሉ። እርሱም፦ “እርሱ ነቢይ ነበርን? ብሎ አለ። እርሳቸውም፦ “አዎ” አሉ”*። عَن أَبُو ذَرٍّ قُلْتُ : يَا نَبِيَّ اللَّهِ، فَأَيُّ الْأَنْبِيَاءِ كَانَ أَوَّلَ. قَالَ : ” آدَمُ “. قَالَ : قُلْتُ : يَا نَبِيَّ اللَّهِ، أَوَنَبِيٌّ كَانَ آدَمُ ؟ قَالَ : ” نَعَمْ،
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4476
አነሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”……(አደምም)፦ “ኑህ ጋር ሂዱ! እርሱ በምድር ላይ የተላከ የመጀመሪያው መልእክተኛ ነው፥ ወደ ምድር ባለቤቶች አላህ ልኮታል” ይላቸዋል”*። ائْتُوا نُوحًا فَإِنَّهُ أَوَّلُ رَسُولٍ بَعَثَهُ اللَّهُ إِلَى أَهْلِ الأَرْضِ‏.‏
ነቢያችን”ﷺ” የነቢያት መደምደሚያ ናቸው፥ ከነቢያችን”ﷺ” በኃላ ነቢይ ብቻ ሳይሆን ረሡልም አይመጣም። ነቢይነት እና መልእክተኝነት በእርሳቸው ተደምድሟል፦
33:40 ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድንም ሰው አባት አይደለም። ነገር ግን የአላህ መልክተኛ እና *”የነቢያት መደምደሚያ” ነው”*፥ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው። مَا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِنْ رِجَالِكُمْ وَلَٰكِنْ رَسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 2272
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”በእርግጥም መልእክተኛነት እና ነቢይነት ተዘግቷል። ከእኔ በኃላ መልእክተኛም ነቢይም የለም*። حَدَّثَنَا أَنَسُ بْنُ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ” إِنَّ الرِّسَالَةَ وَالنُّبُوَّةَ قَدِ انْقَطَعَتْ فَلاَ رَسُولَ بَعْدِي وَلاَ نَبِيَّ

ታዲያ “ነብይ እና ረሡም ከነቢያችን”ﷺ” በኃላ የለም” ከተባለ “ነብይ ነኝ” ወይም “መልእክተኛ ነኝ” ብለው የተነሱት ሚርዛ ጉላም አሕመድ የቃዲያኒይ መስራች፣ ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ የባሃኢይ መሥራች፣ ዶክተር ራሺድ ኸሊፋክ የቁርኣኒያህ መስራች ምንድን ናቸው? ሲባል ኃሣዌ ነብይ እና መልእክተኛ ናቸው።
“ደጃል” دَّجَّال የሚለው ቃል “ደጀለ” دَجَلَ ማለትም “አጭበረበረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “አጭበርባሪ” ወይም “ሐሣዌ” ማለት ነው። እነዚህ ወደ ሠላሳ የሚቃረቡ ደጃሎች “እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ” ወይም “እኔ የአላህ ነብይ ነኝ” ብለው እንደሚነሱ በነቢያችን"ﷺ" ተነግሯል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 54, ሐዲስ 108
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “የመጨረሻይቱ ሰአት አትቆምም ሠላሳ የሚቃረቡ ደጃሎች ቀጣፊዎች ተነስተውስ፦ “እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ” ብለው ቢናገሩ ቢሆን እንጂ”። عَنْ أَبِي، هُرَيْرَةَ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ” لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يُبْعَثَ دَجَّالُونَ كَذَّابُونَ قَرِيبٌ مِنْ ثَلاَثِينَ كُلُّهُمْ يَزْعُمُ أَنَّهُ رَسُولُ اللَّهِ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 13
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ከእኔ ዑማ ውስጥ ሠላሳ የሚያህሉ ቀጣፊዎች፦ “ነቢይ ነኝ” ብለው ይነሳሉ፥ ነገር ግን እኔ የነቢያት መደምደሚያ ነኝ። ከእኔ በኃላ ነቢይ የለም”። وَحَتَّى تَعْبُدَ قَبَائِلُ مِنْ أُمَّتِي الأَوْثَانَ وَإِنَّهُ سَيَكُونُ فِي أُمَّتِي كَذَّابُونَ ثَلاَثُونَ كُلُّهُمْ يَزْعُمُ أَنَّهُ نَبِيٌّ وَأَنَا خَاتَمُ النَّبِيِّينَ لاَ نَبِيَّ بَعْدِي

ሰው መነጻጸሪያ ነጥብ ሳይኖረው ፈጽሞና ጨልጦ ወደ ክህደት ሲገባ ማየት እጅጉን ያማል፥ ኢሥላም እውነትን በመግለጥ እና ሐሰትን በማጋለጥ እረገድ ፈር ቀዳጅ እና ፋና ወጊ ነው። ከእውነት በተቃራኒ ደግሞ የሐሰት ትምህርት የሚያራምዱ በዘመናችን የሚንቀሳቀሱ ቃዲያኒይ፣ በሃኢይ፣ ቁርአንያህ ወዘተ የደጃሎች ተከታዮች ናቸው፥ የእነዚህ አንጃዎች መሥራች፦ “ነቢይ ነኝ” ወይም “መልእክተኛ ነኝ” ብለው የተነሱት ሚርዛ ጉላም አሕመድ የአሕመዲያ መሥራች፣ ሚርዛ ሑሤን ዒሊይ የበሃኢይ መስራች፣ ዶክተር ራሺድ ኸሊፋህ የቁርኣንያ መሥራች ሲሆኑ እነዚህ ነቢያችን”ﷺ” ይመጣሉ ብለው ከተነበዩት ደጃሎች መካከል ናቸው። ስለዚህ በእሳት አትጫወት! አልያም እያየህ እሳት ውስጥ ግባበት!

ኢንሻሏህ ይቀጥላል....
ይህንን የበሃኢይን ፈሣድ ለሙሥሊሙ ኡማህ በመግለጥ እና በማጋለጥ ተደራሽነት እንዲኖረው ሼር አርጉ!

ከወንድም አሚን ሪድዋን
https://tttttt.me/Amin_redwan

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ

ገቢር ሦስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥75 የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ

ከአደም ጀምሮ በተለያየ ጊዜ የሚመጡት የአሏህ ነቢያት ተከታታይ ግህደተ-መለኮት”progressive revelation” እና የወሰነላቸው የራሳቸው ዘመነ-መግቦት”dispensation” ነበራቸው፥ ነገር ግን አንድ እድገት ጅማሬ እና ድምድሜ እዳለው ሁሉ ነቢይነትም በአደም ተጀምሮ በነቢያችን”ﷺ” ተጠናቋል። ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ ከባግዳድ ወደ ቁስጥንጥኒያ ሲሄድ ነቢይነት እና መልክተኛነት በነቢያችን”ﷺ” እንደተዘጋ ሳያቅማማ ተናግሯል፦
"ሶለሏህ ዐለይሂ ሠላም የኢሥላም ነቢይ የዓለም መሪ፣ የሕዝቦች ባለአደራ ነው፥ በእርሱ ብቻ መልክተኛነት እና ነቢይነት ተዘግቷል" ኢሽራቃት ገፅ 293

ከነቢያችን”ﷺ” በኃላ ነቢይ እና መልእክተኛ የማይመጣ ከሆነ አንተ ምንድን ነህ ታዲያ? ሲባል ያ በተስፋ ሲጠበቅ የነበረው"the promised one" መሢሕ ነኝ ብሎ አረፈው፦
"የምድር ልዩ ልዩ ሕዝቦች እና ዘሮች "በተስፋ ሲጠበቅ የነበረውን"the promised one" መምጣት እንዴት ሲጠባበቁ እንደቆዩ አስተውል! ነገር ግን እርሱ የእውነት ፀሐይ የሆነድ እንደመጣ ወዲያው ከእነዚያ አምላክ ሊመራቸው ከፈቀደው በስተቀር እነሆ ሌሎች ሁሉ ከእርሱ ሸሹ።" ቅስማት ገፅ 8

በበሃኢይ እምነት በግለሰብ ደረጃ የማይሳሳቱ አካል ከሚባሉት አንዱ ሾጊ ኢቬንዲ ሲሆን የዐባሥ ኢቬንዲ የልጅ ልጅ ነው፥ ሾጊ ኢቬንዲ ከሚርዛ ሑሤን ዐሊይ ጽሑፎች የቀሳሰማቸው ጽሑፎቹ ቅስማት"Gleanings" ይባላሉ። ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ፦ "የዒሣ ዳግም መምጣት ነኝ" በማለት ተናግሯል፥ ይህንን የይገባኛል ጥያቄ በቁርኣን እና በሐዲስ ማጥለል እና ማጠንፈፍ አለብን።
በቁርኣን እና በሐዲስ ዒሣ ካለፉት መልእክተኞች አንዱ እንጂ ሌላ አይደለም፥ ሲመጣም ነብይ ሆኖ ነበእ ሊመጣለት ወይም ረሡል ሆኖ ሪሣላህ ሊወርድለት ሳይሆን የአደም ልጆችን በአንድ አምልኮ በኢሥላም ለመጠቅለል ወይም የነቢያችን"ﷺ" ሸሪዓህ በሆነው ቁርኣን እና ሐዲስ ሊጠቀልል ነው፦
5፥75 የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 55 , ሐዲስ 658:
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የመርየም ልጅ ዒሳ በመካከላችሁ በሚወርድ ጊዜ እንዴት ትሆናላችሁ? እርሱ ሰዎችን በቁርአን ይበይናል እንጂ በኢንጂል አይበይንም*። حَدَّثَنَا ابْنُ بُكَيْرٍ، حَدَّثَنَا اللَّيْثُ، عَنْ يُونُسَ، عَنِ ابْنِ شِهَابٍ، عَنْ نَافِعٍ، مَوْلَى أَبِي قَتَادَةَ الأَنْصَارِيِّ أَنَّ أَبَا هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ كَيْفَ أَنْتُمْ إِذَا نَزَلَ ابْنُ مَرْيَمَ فِيكُمْ وَإِمَامُكُمْ مِنْكُمْ ‏”‌‏.‏ تَابَعَهُ عُقَيْلٌ وَالأَوْزَاعِيُّ‏.‏
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 301
አቢ ሁረይራ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “በመካከላችሁ የመርየም ልጅ በወረደ ጊዜ እና ሲመራችሁ ምን ታደርጋላችሁ? ኢብኑ አቢ ዚዕብም አቢ ሁረይራ የዘገበው መሰረት አድርጎ፦ “ሲመራችሁ ምን ታደርጋላችሁ?” ምን ማለት ነው? አለ፤ እኔም ለእኔ አብራራልኝ አልኩኝ፤ እርሱም አለ፦ “በጌታችሁ ተባረከ ወተዓላ መጽሐፍ እና በመልእክተኛው በነብያችሁ”ﷺ” ፈለግ ይመራችኃል” አለ*። أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ كَيْفَ أَنْتُمْ إِذَا نَزَلَ فِيكُمُ ابْنُ مَرْيَمَ فَأَمَّكُمْ مِنْكُمْ ‏”‏ ‏.‏ فَقُلْتُ لاِبْنِ أَبِي ذِئْبٍ إِنَّ الأَوْزَاعِيَّ حَدَّثَنَا عَنِ الزُّهْرِيِّ عَنْ نَافِعٍ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ‏”‏ وَإِمَامُكُمْ مِنْكُمْ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ ابْنُ أَبِي ذِئْبٍ تَدْرِي مَا أَمَّكُمْ مِنْكُمْ قُلْتُ تُخْبِرُنِي ‏.‏ قَالَ فَأَمَّكُمْ بِكِتَابِ رَبِّكُمْ تَبَارَكَ وَتَعَالَى وَسُنَّةِ نَبِيِّكُمْ صلى الله عليه وسلم ‏.‏الأَرْضِ‏.‏
ዒሣ ተመልሶ ሲመጣ ተልእኮው የሚፈጽመው በወረደለትም ወሕይ በኢንጅል አሊያም አዲስ በሚወርድለት ወሕይ ሳይሆን በቁርኣን እንደሆነ እንቅጩን ፍርጥ ተደርጎ ተቀምጧል።
ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ ከተወለደበት ከ1817 ድኅረ ልደት እስከ ሞተበት 1892 ድኅረ ልደት ምድራዊ ቆይታው 75 ዓመት ነው፥ "አሏህ ነኝ" ብሎ ካወጀበት ከ1863 ድኅረ ልደት እስከ ሞተበት 1892 ድኅረ ልደት ምድራዊ ቆይታው 29 ዓመት ነው። ስለዚህ ዒሣ ሲመጣ የሚቆየው ቆይታ "40 ዓመት ነው" ከሚለው ከነቢያችን"ﷺ" ንግግር ጋር ክፉኛ ይላተማል፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 39, ቁጥር 34
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው፤ ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ “በእኔ እና በዒሣ መካከል ነቢይ የለም። እርሱ ዒሳ ወደፊት ይወርዳል፤ ባያችሁት ጊዜ ታውቁታላችሁ፤ መካከለኛ ቁመት፣ ቀያማ ጸጉር፣ ሁለት ቀለል ያሉ ቢጫ ልብሶችን ይለብሳል፤ እይታል ልክ ነጠብጣብ ከግንባሩ እንደሚወርድ ግን እንደማይረጥብ ነው፤ በኢሥላም መንገድ ህዝቦችን ይታገላል፤ መስቀልንም ይሰባብራል፣ አሳማዎችንም ይገድላል፣ ግብርንም ይተዋል፤ አላህም ከኢስላም በስተቀር ሁለንም ሃይማኖቶች ያጠፋል፤ ዒሣ መሲሑል ደጃልን ያስወግዳል፤ *በምድር ላይ 40 ዓመት ይቆያል፤ ከዚያም ይሞታል*፤ ሙሥሊሞች ይሰግዱበታል። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ لَيْسَ بَيْنِي وَبَيْنَهُ نَبِيٌّ – يَعْنِي عِيسَى – وَإِنَّهُ نَازِلٌ فَإِذَا رَأَيْتُمُوهُ فَاعْرِفُوهُ رَجُلٌ مَرْبُوعٌ إِلَى الْحُمْرَةِ وَالْبَيَاضِ بَيْنَ مُمَصَّرَتَيْنِ كَأَنَّ رَأْسَهُ يَقْطُرُ وَإِنْ لَمْ يُصِبْهُ بَلَلٌ فَيُقَاتِلُ النَّاسَ عَلَى الإِسْلاَمِ فَيَدُقُّ الصَّلِيبَ وَيَقْتُلُ الْخِنْزِيرَ وَيَضَعُ الْجِزْيَةَ وَيُهْلِكُ اللَّهُ فِي زَمَانِهِ الْمِلَلَ كُلَّهَا إِلاَّ الإِسْلاَمَ وَيُهْلِكُ الْمَسِيحَ الدَّجَّالَ فَيَمْكُثُ فِي الأَرْضِ أَرْبَعِينَ سَنَةً ثُمَّ يُتَوَفَّى فَيُصَلِّي عَلَيْهِ الْمُسْلِمُونَ ‏”‏

፨መስቀል እንጨት፣ ብር፣ ወርቅ፣ ብረት ወዘተ ሲሆን ስለሚሰገድለት ዒሣ ሲመጣ ይሰባብረዋል፥ ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ ግን እንኳን መስቀል ሊሰባብር ቀርቶ ለስቅለት ዕውቅና ሰቷል።
፨ዒሣ ሲመጣ ለጤና ጠንቅ የሆኑትን አሳማዎች በማጥፋት እልባት ይሰጣል፥ ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ ግን እንኳን አሳማዎችን ሊያጠፋ ቀርቶ ለለምግብነት ሐላል አርጎት አርፏል።
፨ዒሣ ሲመጣ ሁሉም አህሉል ኪታብ ሙሥሊም ስለሚሆኑ ጂዚያህ ያስቀራል፥ ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ ግን እንኳን ጂዚያህ ሊያስቀር ጭራሽ የአህሉል ኪታብ ዐቂዳህ ዕውቅና ሰቷል።
፨ከመጽሐፉ ሰዎች አይሁዳውያን ሆኑ ክርስቲያኖች ወለም ዘለም እና ውልፍጥ ዝልፍጥ ሳይሉ ዒሣ ከመሞቱ በፊት በእርሱ ነብይነት ብቻ የሚያምን እንጅ አንድም አይገኝም፥ ቅሉ ግን ሁሉም አህሉል ኪታብ በሚርዛ ሑሤን ዐሊይ ነቢይነት እንኳን ከመሞቱ በፊት ከሞተም በኃላ አላመኑም፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 118
ከአቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተላለፈው፤ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ነፍሴ በእጁ በኾነችው ይሁንብኝ! በእናንተ ላይ የመርየም ልጅ እንደ ፍትሐዊ ዳኛ ኾኖ ሊወርድ ይቃረባል፤ መስቀልንም ይሰባብራል፣ አሳማዎችንም ይገድላል፣ ግብርንም ይተዋል፤ ገንዘብንም የሚቀበለው ሰው እስኪጠፋ ድረስ ይበራከታል፤ ለአላህ የሚደረግ አንድ ሱጁድ ዱንያ እና በውስጧ ከያዘችው ኹሉ የበለጠና የተሻለ ይኾናል”
ከዚያም አቡ ሁረይራህ፦ “ከፈለጋችሁ ይህን አንቀጽ አንብቡ” አለ፦
4፥159 *”ከመጽሐፉም ሰዎች ከመሞቱ በፊት በእርሱ በዒሣ በእርግጥ የሚያምን እንጅ አንድም የለም፤ በትንሣኤም ቀን በእነርሱ ላይ መስካሪ ይኾናል”* سَمِعَ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، لَيُوشِكَنَّ أَنْ يَنْزِلَ فِيكُمُ ابْنُ مَرْيَمَ حَكَمًا عَدْلاً، فَيَكْسِرَ الصَّلِيبَ، وَيَقْتُلَ الْخِنْزِيرَ، وَيَضَعَ الْجِزْيَةَ، وَيَفِيضَ الْمَالُ حَتَّى لاَ يَقْبَلَهُ أَحَدٌ، حَتَّى تَكُونَ السَّجْدَةُ الْوَاحِدَةُ خَيْرًا مِنَ الدُّنْيَا وَمَا فِيهَا ‏”‌‏.‏ ثُمَّ يَقُولُ أَبُو هُرَيْرَةَ وَاقْرَءُوا إِنْ شِئْتُمْ ‏{‏وَإِنْ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ إِلاَّ لَيُؤْمِنَنَّ بِهِ قَبْلَ مَوْتِهِ وَيَوْمَ الْقِيَامَةِ يَكُونُ عَلَيْهِمْ شَهِيدًا‏}‌‏.‏

ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ በየትኛው ቀመር እና ስሌት ነው የዒሣ ዳግም መምጣት የሚሆነው? ትልቅ ድፍረት ነው።
ለዛሬ ስለ ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ እዚህ ጋር ይብቃን ኢንሻሏህ ፈሣዱን በማጋለጥ እንቀጥላለን.....
ይህንን የባኢይን ፈሣድ ለሙሥሊሙ ኡማህ በመግለጥ እና በማጋለጥ ተደራሽነት እንዲኖረው ሼር አርጉ!

ከወንድም አሚን ሪድዋን
https://tttttt.me/Amin_redwan

ወሠላሙ ዐለይኩም
የአሏህ መምጣት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

89፥22 መላእክትም ሰልፍ ሰልፍ ኾነው ጌታህ ትዕዛዙ በመጣ ጊዜ። وَجَاءَ رَبُّكَ وَالْمَلَكُ صَفًّا صَفًّا

አምላካችን አሏህ የፍርዱ ቀን እንደሚመጣ በተከበረ ቃሉ ተናግሯል፥ የአምላካች የአሏህ መምጣት በትእዛዙ ፍርድ ማስተላለፍ እና ውሳኔ መስጠት ያመላክታል። ሙፈሢሮች ያስቀመጡት በዚህ መልኩ ነው፦
89፥22 መላእክትም ሰልፍ ሰልፍ ኾነው ጌታህ ትዕዛዙ በመጣ ጊዜ። وَجَاءَ رَبُّكَ وَالْمَلَكُ صَفًّا صَفًّا
ተፍሢሩ ኢብኑ ከሲር 89፥22 "ጌታህ በመጣ ጊዜ" ማለት በፍጡራኑ በፍርድ መለየት ነው"።
( وجاء ربك ) يعني : لفصل القضاء بين خلقه ،
ተፍሢሩል ጀላለይን 89፥22 "ጌታህ በመጣ ጊዜ" ማለት ትእዛዙ ነው"።
{ وَجَآءَ رَبُّكَ } أي أمره

የአሏህ መምጣት ማለት ትእዛዙ፣ ብይኑ፣ ፍርዱ እና ውሳኔው መከናወንን ያሳያል፦
16፥33 ከሓዲዎች መላእክት ወደ እነርሱ መምጣትን ወይም የጌታህ ትእዛዝ መምጣቱን" እንጂ አይጠባበቁም፡፡ هَلْ يَنظُرُونَ إِلَّا أَن تَأْتِيَهُمُ الْمَلَائِكَةُ أَوْ يَأْتِيَ أَمْرُ رَبِّكَ

"የጌታህ ትእዛዝ መምጣቱ" የሚለው ኃይለ-ቃል አስምርበት! አምላካችን አሏህ ትእዛዙ ሲያመጣ ፍርዱን እንደሚያመለክት ከቀድሞ ጊዜ ቅጣቱ መረዳት ይቻላል፦
11፥40 "ትእዛዛችንም በመጣ" እና እቶኑም በገነፈለ ጊዜ «በእርሷ ውስጥ ከየዓይነቱ ሁሉ ሁለት ሁለት ወንድና ሴት እና ቤተሰቦችህንም ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር ያመነንም ሰው ሁሉ ጫን!» አልነው፡፡ ከእርሱም ጋር ጥቂቶች እንጂ አላመኑም፡፡ حَتَّىٰ إِذَا جَاءَ أَمْرُنَا وَفَارَ التَّنُّورُ قُلْنَا احْمِلْ فِيهَا مِن كُلٍّ زَوْجَيْنِ اثْنَيْنِ وَأَهْلَكَ إِلَّا مَن سَبَقَ عَلَيْهِ الْقَوْلُ وَمَنْ آمَنَ ۚ وَمَا آمَنَ مَعَهُ إِلَّا قَلِيلٌ
11፥94 "ትእዛዛችንም በመጣ ጊዜ" ሹዐይብንና እነዚያን ከርሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው ችሮታ አዳን፡፡ እነዚያን የበደሉትንም ጩኸት ያዘቻቸው፡፡ በቤቶቻቸውም ውስጥ ተንከፍርረው አደሩ፡፡ وَلَمَّا جَاءَ أَمْرُنَا نَجَّيْنَا شُعَيْبًا وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ بِرَحْمَةٍ مِّنَّا وَأَخَذَتِ الَّذِينَ ظَلَمُوا الصَّيْحَةُ فَأَصْبَحُوا فِي دِيَارِهِمْ جَاثِمِينَ

አሏህ ከከተሞችም እነዚያን በአካባቢያችሁ የነበሩትን በእርግጥ በማጥፋት መጥቶባቸዋል፦
13፥41 እኛ ምድርን ከጫፎችዋ የምናጎድላት ኾነን የምንመጣባት መኾናችንን አላዩምን? አላህም ይፈርዳል፡፡ ለፍርዱም ገልባጭ የለውም፡፡ እርሱም ምርመራው ፈጣን ነው፡፡ أَوَلَمْ يَرَوْا أَنَّا نَأْتِي الْأَرْضَ نَنقُصُهَا مِنْ أَطْرَافِهَا ۚ وَاللَّهُ يَحْكُمُ لَا مُعَقِّبَ لِحُكْمِهِ ۚ وَهُوَ سَرِيعُ الْحِسَابِ
46፥27 ከከተሞችም እነዚያን በአካባቢያችሁ የነበሩትን በእርግጥ አጠፋን ከክሕደታቸው ይመለሱም ዘንድ አስረጂዎችን መላለስን፡፡ وَلَقَدْ أَهْلَكْنَا مَا حَوْلَكُم مِّنَ الْقُرَىٰ وَصَرَّفْنَا الْآيَاتِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

አሏህ፦ "የምንመጣባት" ማለቱ እርምጃ መውሰዱ ቁልጭ አርጎ ያሳያል፥ ምድርን ከጫፎችዋ ማጉደል ማለት ከከተሞችም እነዚያን በአካባቢያችሁ የነበሩትን ማጥፋት ማለት እንደሆኑ ታላቁ ሙፈሢር ኢብኑ ከሲር ተናግሯል። ሞት ወደ ሰዎች "ይመጣል" ተብሏል፦
2፥180 አንዳችሁን "ሞት በመጣበት ጊዜ" ሀብትን ቢተው ለወላጆችና ለቅርብ ዘመዶች በበጎ መናዘዝ በናንተ ላይ ተጻፈ፡፡ كُتِبَ عَلَيْكُمْ إِذَا حَضَرَ أَحَدَكُمُ الْمَوْتُ إِن تَرَكَ خَيْرًا الْوَصِيَّةُ لِلْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ بِالْمَعْرُوفِ
6፥61 አንዳችሁንም "ሞት በመጣበት ጊዜ" የሞት መልእክተኞቻችን እነርሱ ትእዛዛትን የማያጓድሉ ሲኾኑ ይገድሉታል። إِذَا جَاءَ أَحَدَكُمُ الْمَوْتُ تَوَفَّتْهُ رُسُلُنَا وَهُمْ لَا يُفَرِّطُونَ
የሞት መምጣት ሞትን መገናኘት እንጂ ሞት ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ ስፍራ መንቀሳቀስን እንደማያማለክት ሁሉ የአሏህ መምጣት ፍርድን ያመለክታል። እሩቅ ሳንሄድ በባይብል ያህዌህ እንደሚመጣ ይናገራል፦
ዳንኤል 7፥22 በዘመናት የሸመገለው እስኪመጣ ድረስ፥ ፍርድም ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪሰጥ ድረስ።

"በዘመናት የሸመገለው" አብ እንደሆነ እሙን እና ቅቡል ነው። ለምሳሌ፦ እስራኤላውያን የሚፈልጉት ጌታ ያህዌህ ነው፥ ያህዌህ መቅደሱ የራሱ ነው። ያህዌህ አብ በ 70 ድኅረ ልደት ኢየሩሳሌም በሚገኘው ቤተ መቅደስ ለመፍረድ መጥቷል፦
አሞጽ5፥4 ያህዌንም ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላልና፦ እኔን ፈልጉ፥ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤
ዘሌዋውያን 19፥30 ሰንበታቴን ጠብቁ፥ "መቅደሴንም" አክብሩ! እኔ ያህዌህ ነኝ።
ሚልክያስ 3፥1 እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ "መቅደሱ ይመጣል"።

ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን የተባለው በ 70 ድኅረ ልደት አብ መጥቶ ምድርን በእርግማን የመታበት ነው፥ እነሆ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩ ኤልያስ ተልኳል፦
ሚልክያስ 4፥5-6 እነሆ ታላቁ እና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ። "መጥቼም" ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።

"መጥቼም" የሚለው አብ መሆኑ ዕሙር እና ስሙር ነው። ነቢዩን ኤልያስ በጥላነት ዮሐንስ ሲሆን ዮሐንስም፦ "እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ? አላቸው፦
ማቴዎስ 11፥14 ልትቀበሉትስ ብትወዱ "ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይህ ነው"።
ማቴዎስ 3፥7 እንዲህ አላቸው፦ እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ?

የሚመጣው ቁጣ የተባለው በ 70 ድኅረ ልደት የሮም ወታደር መሪ ጀነራል ቲቶ ኢየሩሳሌምን እና ቤተ መቅደሷን ያጋየበት ነው። ልጁን የላከው የወይኑ አታክልት ጌታ በ 70 ድኅረ ልደት ሲመጣ ክፉዎችን አይሁዳውያን በክፉዎች ሮማንያን አጥፏል፦
ማቴዎስ 21፥40-41 እንግዲህ የወይኑ አትክልት ጌታ "በሚመጣ ጊዜ" በእነዚህ ገበሬዎች ምን ያደርግባቸዋል? እነርሱም፦ "ክፉዎችን በክፉ ያጠፋቸዋል"።

የአብ መምጣት ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ ስፍራ መዘዋወር ካላመለከተ እና ፍርድን ወይም ውሳኔን አሊያም እርምጃን ካመለከተ የአሏህ መምጣት በፍርዱ ቀን እንደሚፈርድ ቁልጭ እና ፍትንው አድርጎ የሚያሳይ ነው። የአሏህን መምጣት ከዒሣ መምጣት ጋር ለማያያዝ የሞከራችሁት ሙከራ ለዛሬ አልተሳካም፥ እዛው መንደራችሁ አቧራ አስነሱ እንጂ "ቅቤ ጥበሱልኝ፥ ዕጣን አጭሱልኝ፣ ቄጤማ ጎዝጉዝልኝ፣ አሪቲ ነስንሱልኝ፣ ከበሮ ደልቁልኝ፣ ነጋሪት ጎስሙልን፣ እንቢልታ ንፉልኝ" የምትሉት ነገር እዚህ እኛ ጋር አይሠራም። ከላይ የቀረበውን ተመሳሳይ ሙግት ስትረዱ "አምልጦኝና አዳልጦኝ ነው" ብትሉ ውልፍጥና ዝልፍጥ አንልም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሦስቱ መልእክተኞች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

40፥78 *ከአንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል፡፡ ከእነርሱ በአንተ ላይ የተረክንልህ አለ፥ ከእነርሱም በአንተ ላይ ያልተረክነው አለ*፡፡ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلًا مِّن قَبْلِكَ مِنْهُم مَّن قَصَصْنَا عَلَيْكَ وَمِنْهُم مَّن لَّمْ نَقْصُصْ عَلَيْكَ

አምላካችን አላህ ከነቢያችን”ﷺ” በፊት መልእክተኞች ልኳል። ከእነርሱ ውስጥ በነቢያችን”ﷺ” ላይ ስማቸው የተተረኩ አሉ፥ ከእነርሱም ውስጥ ስማቸው ያልተተረኩ አሉ፦
40፥78 *ከአንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል፡፡ ከእነርሱ በአንተ ላይ የተረክንልህ አለ፥ ከእነርሱም በአንተ ላይ ያልተረክነው አለ*፡፡ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلًا مِّن قَبْلِكَ مِنْهُم مَّن قَصَصْنَا عَلَيْكَ وَمِنْهُم مَّن لَّمْ نَقْصُصْ عَلَيْكَ

ስማቸው ካልተተረኩት መልእክተኞች መካከል ሦስት መልእክተኞች ወደ አንዲት ከተማ ልኳል፦
36፥13 *ለእነርሱም የከተማይቱን ሰዎች ምሳሌ መልክተኞቹ በመጧት ጊዜ የኾነውን ግለጽላቸው*፡፡ وَٱضْرِبْ لَهُم مَّثَلًا أَصْحَٰبَ ٱلْقَرْيَةِ إِذْ جَآءَهَا ٱلْمُرْسَلُونَ
36፥14 *ወደ እነርሱ ሁለትን ሰዎች በላክን እና ባስተባበሉዋቸው ጊዜ በሶስተኛም በአበረታን እና “እኛ ወደ እናንተ መልክተኞች ነን” ባሏቸው ጊዜ የኾነውን ምሳሌ ግለጽላቸው*፡፡ إِذْ أَرْسَلْنَآ إِلَيْهِمُ ٱثْنَيْنِ فَكَذَّبُوهُمَا فَعَزَّزْنَا بِثَالِثٍۢ فَقَالُوٓا۟ إِنَّآ إِلَيْكُم مُّرْسَلُونَ

ታላቁ ሙፈሢር ኢሥማኢል ኢብኑ ከሲር በተፍሢራቸው ላይ ስለ እነዚህ ሦስት መልእክተኞች ማንነት በነቢብ እና በነሲብ የተተረከውን አስቀምጠዋል፦
አት-ተፍሢል ኢብኑ ከሲር ሱረቱ ያሲን 36፥13-14
*”ለእነርሱም የከተማይቱን ሰዎች ምሳሌ መልክተኞቹ በመጧት ጊዜ የኾነውን ግለጽላቸው” ኢብኑ ኢሥሓቅ ከከዕብ አል-አሕባር፣ ከወህብ ኢብኑ ሙነቢህ በተላለፈው ኢብኑ ዐባሥን መሠረት አድርጎ በዘገበው፦ “ያቺ ከተማይቱ አንጧኪያህ ናት፥ በእርሷም አንጢሕሥ የሚባል ንጉሥ ጣዖት የሚያመልክ የአንጢሕሥ ልጅ፣ የአንጢሕሥ ልጅ ነበረ። አላህ ወደ እርሱ ሦስት መልእክተኞችን ላከ፥ እነርሱም፦ ሷዲቅ፣ ሷዱቅ እና ሻሉም ናቸው። እርሱም በእነርሱ አስተባበለ።
ቡረይዳህ ኢብኑል ሑሰይብ ከዒክረማህ፣ ከቀደታህ እና ከአዝ-ዙህሪይ እንዳገኘው ያቺ ከተማይቱ አንጧኪያህ ናት ብሏል”*።

*”ከተማይቱ አንጧኪያህ ስለመሆኗ እና ከዚህ በታች የምንመለከተውን ትረካ ዐበይት ኢማሞች በታሪኩ ማብራሪያ እርግጠኛ አይደሉም። ኢንሻላህ ተዓላ “ወደ እነርሱ ሁለትን ሰዎች በላክን እና ባስተባበሉዋቸው ጊዜ በሶስተኛም በአበረታን እና እኛ ወደ እናንተ መልክተኞች ነን ባሏቸው ጊዜ የኾነውን ምሳሌ ግለጽላቸው” ሸዕይብ አል-ጀባኢይ ከወሕብ ኢብኑ ሡለይማን፣ ኢብኑ ጁረይጅ አለ ብሎ እንደተናገረው፦ “የመጀመሪያዎቹ ሁለት መልእክተኞች ስም ሸሙን እና ዩሐና ናቸው፥ ሦስተኛው ቡሉስ ነው። ከተማይቱ አንጧኪያህ ናት”*።
( مثلا أصحاب القرية إذ جاءها المرسلون ) .
قال ابن إسحاق – فيما بلغه عن ابن عباس ، وكعب الأحبار ، ووهب بن منبه – : إنها مدينة أنطاكية ، وكان بها ملك يقال له : أنطيخس بن أنطيخس بن أنطيخس ، وكان يعبد الأصنام ، فبعث الله إليه ثلاثة من الرسل ، وهم : صادق وصدوق وشلوم ، فكذبهم .
وهكذا روي عن بريدة بن الحصيب ، وعكرمة ، وقتادة ، والزهري : أنها أنطاكية .

وقد استشكل بعض الأئمة كونها أنطاكية ، بما سنذكره بعد تمام القصة ، إن شاء الله تعالى .
وقوله : ( إذ أرسلنا إليهم اثنين فكذبوهما ) أي : بادروهما بالتكذيب ، ( فعززنا بثالث ) أي : قويناهما وشددنا أزرهما برسول ثالث .
قال ابن جريج ، عن وهب بن سليمان ، عن شعيب الجبائي قال : كان اسم الرسولين الأولين شمعون ويوحنا ، واسم الثالث بولص ، والقرية أنطاكية .

ከላይ እንደተገለጸው የእነዚህ ሦስት መልእክተኞች ስም እና የከተማይቱ ስም በቁርኣን ላይ አልተገለጸም። ግን በተፍሢሩ ላይ ሁለት ዘገባዎች ተቀምጠዋል።
የመጀመሪያው ዘገባ ሦስት መልእክተኞች ሷዲቅ፣ ሷዱቅ እና ሻሉም የተባሉት ትረካ የተፋሰስ ወይም የላይዮሽ ትረካ”vertical narration” ሲሆን ከታች ትውልድ ወደ ላይ ትውልድ ሲወርድና ሲወራረድ ኢብኑ ኢሥሓቅ ከከዕብ አል-አሕባር፣ ከዕብ አል-አሕባር ደግሞ ከወህብ ኢብኑ ሙነቢህ፣ ወህብ ኢብኑ ሙነቢህ ደግሞ ከኢብኑ ዐባሥ የተገኘ ትረካ ነው፦
ኢብኑ ዐባሥ
|
ወህብ ኢብኑ ሙነቢህ
|
ከዕብ አል-አሕባር
|
ኢብኑ ኢሥሓቅ
ይህ የላይዮሽ ዘገባ ሙተሲል ነው። “ሙተሲል” مُتَّصِل ማለት ሰንሰለት የተቀበለበት “አያያዥ ማንነት” ነው። “ኢሥናድ” اِسْنَاد ማለት “ትርክት” ማለት ነው፥ ትረካው የሚተላለፍበት ሰንሰለት ደግሞ “ሠነድ” سَنَد ሲባል የሚያስተላልፈው “ተራኪ” ደግሞ “ሙሥነድ” مُسْنَد ይባላል። ኢሥናዱ፦ “አላህ ወደ እርሱ ሦስት መልእክተኞችን ላከ፥ እነርሱም፦ ሷዲቅ፣ ሷዱቅ እና ሻሉም ናቸው” የሚል ነው፥ ሠነዱ ከዕብ አል-አሕባር እና ወህብ ኢብኑ ሙነቢህ ሲሆን ሙሥነድ ደግሞ ኢብኑ ዐባሥ ነው። ኢብኑ ዐባሥ ደግሞ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” ሶሓቢይ ነው። ስለዚህ የኢብኑ ኢሥሓቅ ዘገባ አስተማማኝ ነው።
አንጢሕሥ በታሪክ ሦስተኛ አንጥያኮስ የተባለው ንጉሥ አንጥያኮስ ኤጴፋኔዎስ ሲሆን አያቱ ሁለተኝ አንጥያኮስ ቴኦስ፥ ቅድመ-አያቱ አንደኛው አንጥያኮስ ሶተር ይባላሉ። ይህ ንጉሥ በ 175 ቅድመ-ልደት ንግሥናን ጨብጧል፥ ዚየስ ኦሊምፒየስ የተባለውን ጣዖት በማምለክና የአሳማ ስጋ መስዋዕት በመሰዋቱ ይታወቃል። አንጧኪያህ በታሪክ አንጾኪያ የሚለው “አናጽ” ከምትባለው የጦርነት አምላክ ወይም “አንጥያኮስ” ከተባለው የነገሥታቱ ስም እንደመጣ ይነገራል። እንደ ኢብኑ ዐባሥ ትርክት አላህ ወደ እነርሱ ሦስት መልእክተኞችን ልኳል።
ሁለተኛው ዘገባ ሦስት መልእክተኞች ሸሙን፣ ዩሐና እና ቡሉስ የተባሉት ትረካ የአግድም ወይም የጎንዮሽ ትረካ”horizontal narration” ሲሆን በአንድ ትውልድ ሸዕይብ አል-ጀባኢይ ከወሕብ ኢብኑ ሡለይማን፥ ወሕብ ኢብኑ ሡለይማን ደግሞ ከኢብኑ ጁረይጅ የተገኘ ትረካ ነው፦
ሸዕይብ አል-ጀባኢይ – ወሕብ ኢብኑ ሡለይማን – ኢብኑ ጁረይጅ
ኢብኑ ጁረይጅ ከሦስተኛው ትውልድ ታቢዑ አት-ታቢዒን ከሚባሉት ነው፥ ብዙ ጊዜ “ኢሥራኢሊያት” إِسْرَائِيلِيَّات ማለትም “የአይሁድ እና የክርስትና ትረካ” ያስተላልፋል። አባቱ ጁረይጅ ሲሆን የሮማ ክርስቲያን የነበረ፥ ስሙም ግሪጎሪ ነበር። የእርሱ ዘገባ ከሁለተኛ ትውልድ ከታቢዒይ እና ከመጀመሪያ ትውልድ ከሶሓቢይ የመጣ ኢሥናድ የለም። ሠነድ እና ሙሥነድ የሌለው ኢሥናድ ሙዐለቅ ነው፥ “ሙአለቅ” مُعَلَّق ማለት በሙሐዲስ እና በሙሥነድ መካከል ምንም አይነት ተራኪና ትረካ ሳይኖር ሲቀር “ሙዐለቅ” ይባላል። “ሙሐዲስ” مُحَدِيث ማለት “ዘጋቢ” ማለት ነው። ስለዚህ ከሸዕይብ አል-ጀባኢይ የተገኘው ዘገባ ደካማ ስለሆነ ውድቅ ነው።
ሲቀጥል ሸሙን ስምዖን ጴጥሮስ፣ ዩሐና ዮሐንስ እና ቡሉስ ጳውሎስ ከሆኑ እነዚህ ሦስት ሰዎች በዒሣ እና በነቢያችን”ﷺ” መካከል ያሉ ናቸው፥ በዒሣ እና በነቢያችን”ﷺ” መካከል ደግሞ ምንም ነቢይ የለም፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 43, ሐዲስ 190
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ለዒሣ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለም በመጨረሻይቱ ዓለም ቅርብ ነኝ። እነርሱም፦ “ይህ እንዴት ይሆናል? የአላህ መልእክተኛም፦ ሆይ!” አሉ። እርሳቸው፦ “ነቢያት ወንድማማቾች ናቸው፣ እናቶቻቸው ይለያያሉ፣ ነገር ግን ሃይማኖታቸው አንድ ነው። በእኔ እና በእርሱ መካከል አንድም ነቢይ የለም” አሉ”*። قَالَ هَذَا مَا حَدَّثَنَا أَبُو هُرَيْرَةَ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَذَكَرَ أَحَادِيثَ مِنْهَا وَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ أَنَا أَوْلَى النَّاسِ بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ فِي الأُولَى وَالآخِرَةِ ‏”‏.‏ قَالُوا كَيْفَ يَا رَسُولَ اللَّهِ قَالَ ‏”‏ الأَنْبِيَاءُ إِخْوَةٌ مِنْ عَلاَّتٍ وَأُمَّهَاتُهُمْ شَتَّى وَدِينُهُمْ وَاحِدٌ فَلَيْسَ بَيْنَنَا نَبِيٌّ ‏

ስለዚህ በኢየሱስ እና በነቢያችን”ﷺ” መካከል ያሉት ስምዖን ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ እና ጳውሎስ ነቢይ ካልነበሩ ከሸዕይብ አል-ጀባኢይ የተገኘው ዘገባ ሙድጠሪብ ነው፥ “ሙድጠሪብ” مُضْطَرِب ማለት አንድ ዘገባ የተቃረኑ የዘገባ ሰነድ ሲኖረው ወይንም ዘገባው የተቃረነ መትን ሲኖረው “ሙድጠሪብ” ይባላል። ሢሰልስ ኢብኑ ከሲር፦ “ከዚህ በታች የምንመለከተውን ትረካ ዐበይት ኢማሞች በታሪኩ ማብራሪያ እርግጠኛ አይደሉም” ብሎ አስተማማኝ ትርክት እንዳልሆነ አበክሮና አዘክሮ አስቀምጧል። ሚሽነሪዎች ጳውሎስን በኢሥላም ውስጥ ለማስገባት እና “የአላህ መልእክተኛ ነው! ተቀበሉት” ለማለት ያቀረቡት ስሑት ሙግት ለዛሬ አልተሳካም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተስዊር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

23፥14 *ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ*፡፡ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ

“ሙሶዊር” مُصَوِّر ማለት “ቀራፅ” “ሰዓሊ” “ሠሪ” “ፈጣሪ” ማለት ነው፥ የሙሶዊር ብዙ ቁጥር ደግሞ “ሙሶዊሩን” مُصَوِّرُون ወይም “ሙሶዊሪን” مُصَوِّرِين ሲሆን “ቀራፆች” “ሰዓሊዎች” ማለት ነው፦
23፥14 *ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ*፡፡ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ

“ሰዓሊዎች” ለሚለው ቃል የገባው “ኻሊቂን” خَالِقِين ሲሆን “ሙሶዊሪን” مُصَوِّرِين ማለት ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 37, ሐዲስ 150
ዐብደላህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”በትንሳኤ ቀን ከሰዎች በጣም ተቀጪ ሰዓሊዎች ናቸው”*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّ أَشَدَّ النَّاسِ عَذَابًا يَوْمَ الْقِيَامَةِ الْمُصَوِّرُونَ ‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 182
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የስዕላት ባለቤት በትንሳኤ ቀን ይቀጣሉ፥ ለእነርሱም፦ “የፈጠራችሁትን ሕያው አድርጉ” ይባላሉ”*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ إِنَّ أَصْحَابَ هَذِهِ الصُّوَرِ يُعَذَّبُونَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ، وَيُقَالُ لَهُمْ أَحْيُوا مَا خَلَقْتُمْ

ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብና ትርጉም አለው ማለት አይደለም፥ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው። መታየት ያለበት ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብ ነው። ነቢያችን”ﷺ” በቁርኣን ከተሰጣቸው አንዱ አንድ ቃላት ሰፊ ትርጉም ነው፥ ይህም “ጀዋሚዓል ከሊም” ነው። “ጀዋሚዓል ከሊም” جَوَامِعَ الْكَلِم ማለት “አንድ ቃል ሆኖ ብዛት ትርጉም ያለው” ማለት ነው። “ሱራህ” صُورَة‎ ማለት ብዙ አውራ ትርጉም ያለው ሲሆን “ስዕል” “ቅርፅ” “መልክ” “ፎቶ” ማለት ነው፥ “ሱወር” صُوَر ደግሞ የሱራህ ብዙ ቁጥር ሲሆን “ስዕላት” “ቅርፃት” ማለት ነው። “የፈጠራችሁትን” ለሚለው የገባው ቃል “ኸለቅቱም” خَلَقْتُمْ ሲሆን ስዕሉን ስለሳሉት እና ቅርፁን ስለቀረፁት እንጂ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተውት አይደለም፥ ይህ “ኢሕቲራዕ” اِخْتِرَاع ማለትም “ፈጠራ” ነው። በእጃቸው የፈጠሩትን ላይ እንደ አላህ ሩሕ ማድረግ አይችሉም፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 77, ሐዲስ 179
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ *”በዚህ ዓለም ቅርፅ የቀረፀ በትንሳኤ ቀን በውስጡ ሩሕ እንዲነፋበት ይጠየቃል፥ ግን መንፋት አይችልም”*። فَقَالَ سَمِعْتُ مُحَمَّدًا صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ “‏ مَنْ صَوَّرَ صُورَةً فِي الدُّنْيَا كُلِّفَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَنْ يَنْفُخَ فِيهَا الرُّوحَ، وَلَيْسَ بِنَافِخٍ

እዚህ ሐዲስ “ሶወረ” صَوَّرَ ማለት “ቀረፀ” “ሳለ” “ሠራ” ማለት ነው። “ኸልቅ” خَلْق የሚለው ቃል “ተስዊር” تَصْوِير ለሚለው ተለዋዋጭ ቃል ሆኖ እንደገባ አንባቢ ልብ ይለዋል፥ ይህ የቋንቋ ሙግት ታሳቢ ያደረገ ነው። ነቢያችን”ﷺ” ባልደረቦቻቸውን ወደ ሐበሻህ ሲልኳቸው ከሔዱት መካከል በአክሱም ቤተክርስቲያን ውስጥ ስዕላትን አይተዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 77
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ *”ኡሙ ሐቢባህ እና ኡሙ ሠለማህ በሐበሻህ ስላዩአት በውስጧ ስዕሎች ስለነበሩባት ቤተክርስቲያን ዘክረዋል፥ ስለዚህ ለነቢዩም”ﷺ”ዘክረዋል። እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦ “በእነዚያ ሰዎች መካከል የትኛውም ሷሊሕ ሰው ቢሞት በመቃብሩ ላይ የአምልኮ ስፍራ ቢገነቡ እና እነዚህን ስዕላት ቢያደርጉ፥ በትንሳኤ ቀን በአላህ ዘንድ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ ክፉ ናቸው”*፡፡ عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّ أُمَّ حَبِيبَةَ، وَأُمَّ سَلَمَةَ ذَكَرَتَا كَنِيسَةً رَأَيْنَهَا بِالْحَبَشَةِ فِيهَا تَصَاوِيرُ، فَذَكَرَتَا لِلنَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ ‏ “‏ إِنَّ أُولَئِكَ إِذَا كَانَ فِيهِمُ الرَّجُلُ الصَّالِحُ فَمَاتَ بَنَوْا عَلَى قَبْرِهِ مَسْجِدًا، وَصَوَّرُوا فِيهِ تِلْكَ الصُّوَرَ، فَأُولَئِكَ شِرَارُ الْخَلْقِ عِنْدَ اللَّهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ

“ተስዊራህ” تَصْوِيرَة ማለት “ስዕል” ማለት ነው፥ የተስዊራህ ብዙ ቁጥር “ተሷዊር” تَصَاوِير ማለት ሲሆን “ስዕላት” ማለት ነው። ስዕል በአምልኮ ውስጥ ምንም ሚና መኖር የለበትም፥ የሥላሴ፣ የኢየሱስ፣ የማርያም፣ የመላእክት እና የቅዱሳን ሰዎች ስዕል ስሎ በፊታቸው መለማመን ባዕድ አምልኮ ነው። በተመሳሳይ ቁረይሾች የአላህ ቤት ውስጥ ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል በእጆቻቸው አዝላም የያዙ አስመስለው ስዕላት ስለው ነበር፥ “አዝላም” أَزْلاَم ማለት “የጥንቆላ ቀስት” ማለት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 32
ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ *”ነቢዩ”ﷺ” በአላህ ቤት ስዕላት በተመለከቱ ጊዜ ባልደረቦቻቸው እንዲያጠፉ እንኪያዙ ድረስ ወደ እዚያ አልገቡም። ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል”ሠላም በእነርሱ ላይ ይሁን! በእጆቻቸው አዝላም የያዙ ስዕላት ነበሩ። እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦ “አላህ ይርገማቸው(ቁረይሾችን)! ወሏሂ ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል በአዝላም አይለማመዱም”*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم لَمَّا رَأَى الصُّوَرَ فِي الْبَيْتِ لَمْ يَدْخُلْ، حَتَّى أَمَرَ بِهَا فَمُحِيَتْ، وَرَأَى إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ ـ عَلَيْهِمَا السَّلاَمُ ـ بِأَيْدِيهِمَا الأَزْلاَمُ فَقَالَ ‏ “‏ قَاتَلَهُمُ اللَّهُ، وَاللَّهِ إِنِ اسْتَقْسَمَا بِالأَزْلاَمِ قَطُّ

የኢብራሂም አባት እና የኢብራሂም ሕዝቦች ቅርጻ ቅርጽ የሆነ አስናምን ያመልኩ ነበር፥ “አስናም” أَصْنَام ማለት ከእንጨት፣ ከብር፣ ከነሐስ፣ ከወርቅ ተሠርተው አምልኮ የሚቀርብላቸው ናቸው፦
26፥70 *ለአባቱና ለሕዝቦቹ «ምንን ታመልካላችሁ?*» ባለ ጊዜ፡፡ إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِۦ مَا تَعْبُدُونَ
26፥71 *አስናምን እናመልካለን፥ እርሷንም በመገዛት ላይ እንቆያለን*» አሉ፡፡ قَالُوا۟ نَعْبُدُ أَصْنَامًۭا فَنَظَلُّ لَهَا عَٰكِفِينَ
21፥52 ለአባቱ እና ለሕዝቦቹ «ይህቺ *”ቅርጻ ቅርጽ”* ያቺ እናንተ ለእርሷ ተገዢዎች የኾናችሁት ምንድን ናት?» ባለ ጊዜ መራነው፡፡ إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِ مَا هَـٰذِهِ التَّمَاثِيلُ الَّتِي أَنتُمْ لَهَا عَاكِفُونَ

“ቲምሳል” تِمْثَال ማለት “ምስል” “ቅርጽ” ማለት ነው፥ የቲምሳል ብዙ ቁጥር ደግሞ “ተማሲል” تَمَاثِيل ሲሆን “ምስሎች” “ቅርጻ ቅርጽ” ማለት ነው። የአምልኮ ይዘት ያላቸው ማንኛውም ምስል ሆነ ስዕል ያለበት ቤት መላእክት አይገቡም፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 37, ሐዲስ 156
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”መላእክት ምስሎች ወይም ስዕሎች ያለበት ቤት አይገቡም”*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ لاَ تَدْخُلُ الْمَلاَئِكَةُ بَيْتًا فِيهِ تَمَاثِيلُ أَوْ تَصَاوِيرُ

ስለ ሱራህ በመስኩ ምሁራን ዘንድ ያለው እይታ በአራት ይከፈላሉ፥ እነርሱም፦
1ኛ. ለምንም ነገር ሱራህ መጠቀም ሐራም ነው፣
2ኛ. በእጅ የተሠራ እንጂ ልክ እንደ መስታዎት እራሳችንን የሚያሳዩ በካሜራ እና በፊልም የሚታዩ ነገሮች ችግር የላቸውም፣
3ኛ. ለፓስፓርት፣ ለመታወቂያ እና ለሰርተፍኬት ብቻ መጠቀም ይቻላል፣
4ኛ. ለአምልኮ አንጠቀም እንጂ ስዕል እና ቅርጻ ቅርጽ በራሱ ሥነ-ጥበብ”art” ነው” የሚሉ ናቸው። ለምሳሌ “ፊደል” የሚለው ቃል “ፈደለ” ማለትም “ቀረፀ” ወይም “ጻፈ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ቅርፅ” ወይም “ጽሑፍ” ማለት ነው፥ ፊደል የቃላት ቅርፅ ናቸው። “ሐርፍ” حَرْف የሚለው ቃል እራሱ “ሐረፈ” حَرَفَ ማለትም “ጻፈ” ወይም “ቀረፀ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ቅርፅ” ወይም “ጽሑፍ” በሚል ይመጣል፥ ቃል በጽሑፍ ወይም በቅርፅ ማስቀመጥን ያመለክታል። አራተኛውን እይታ ለማስደገፍ፦ “ሡለይማን በቤተ-መንግሥቱ ምስሎች አድርጓል፥ እነዚህ ምስሎች ስዕሎች ነበሩ” ይላሉ፦
34፥13 *ከምኩራቦች፣ “ከምስሎችም”፣ እንደ ገንዳ ከኾኑ ገበታዎችም፣ ከተደላደሉ ታላላቅ ድስቶችም የሚሻውን ሁሉ ይሠሩለታል*፡፡ يَعْمَلُونَ لَهُ مَا يَشَاءُ مِن مَّحَارِيبَ وَتَمَاثِيلَ وَجِفَانٍ كَالْجَوَابِ وَقُدُورٍ رَّاسِيَاتٍ ۚ اعْمَلُوا آلَ دَاوُودَ شُكْرًا ۚ وَقَلِيلٌ مِّنْ عِبَادِيَ الشَّكُورُ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 34፥13
ወሱዲይ ከወድሐክን፣ ዐጢይል ዐውፊይ አለ ብሎ እንደተናገረው፦ *”ምስሎች ማለት ስዕሎች ናቸው”*። فقال عطية العوفي ، والضحاك والسدي : التماثيل : الصور

“ዒሣ የወፍ ቅርፅ እንዲሠራ መፈቀዱ በራሱ “ቅርፅ መቅረፅ በራሱ ችግር የለውም” የሚል አቋም አላቸው። በሱራህ እሳቤ ዙሪያ “አንጡራ መረጃ አላገኘንም” ካላችሁ በአካባቢያችሁ ወደሚገኙት ምሁራን እና ሊሒቃን ጎራ ብላችሁ ጠይቁ! አሏሁ አዕለም።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የአሏህ መታየት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

84፥15 ይከልከሉ! እነርሱ በዚያ ቀን ከጌታቸው ማየት ተጋራጆች ናቸው፡፡ كَلَّا إِنَّهُمْ عَن رَّبِّهِمْ يَوْمَئِذٍ لَّمَحْجُوبُونَ

የትንሣኤ ቀን ምእመናን በጀነት ውስጥ ይሆናሉ፥ ለእነርሱ በውስጧ ሲኾኑ የሚሹት ሁሉ አለላቸው፡፡ በጀነት ውስጥ ያለው ተጨማሪ መንፈሳዊ ጸጋ አሏህን ማየት ነው፦
50፥35 ለእነርሱ በውስጧ ሲኾኑ የሚሹት ሁሉ አለላቸው፡፡ ”እኛም ዘንድ ጭማሪ አለ”፡፡ لَهُم مَّا يَشَآءُونَ فِيهَا وَلَدَيْنَا مَزِيدٌۭ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 354
ሱሀይብ እንደተረከው፦ "ነቢዩም’ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "እነዚያ የጀናህ ባለቤቶች ጀናህ በሚገቡ ጊዜ የተከበረው እና ከፍ ያለው አሏህ፦ "ጭማሪ እንድሰጣችሁ ትፍልጋላችሁን? ብሎ ይጠይቃቸዋል፥ እነርሱም፦ ፊታችንን አላበራህምን? ጀናትንስ አላስገባከንምን? ከእሳትስ አላዳንከንምን? ይላሉ። ከዚያ እርሱ ግርዶሹን ያነሳል፥ ለእነርሱ የወደደው አሸናፊው እና ክብራማ የሆነውን ከጌታቸውን ፊት በስተቀር ለእነርሱ ምንም ነገር በእነርሱ ዘንድ የለም"። عَنْ صُهَيْبٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ إِذَا دَخَلَ أَهْلُ الْجَنَّةِ الْجَنَّةَ - قَالَ - يَقُولُ اللَّهُ تَبَارَكَ وَتَعَالَى تُرِيدُونَ شَيْئًا أَزِيدُكُمْ فَيَقُولُونَ أَلَمْ تُبَيِّضْ وُجُوهَنَا أَلَمْ تُدْخِلْنَا الْجَنَّةَ وَتُنَجِّنَا مِنَ النَّارِ - قَالَ - فَيَكْشِفُ الْحِجَابَ فَمَا أُعْطُوا شَيْئًا أَحَبَّ إِلَيْهِمْ مِنَ النَّظَرِ إِلَى رَبِّهِمْ عَزَّ وَجَلَّ ‏"‏ ‏.‏

የምእመናን ፊቶች በትንሣኤ ቀን አብሪዎች ናቸው፥ ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው፡፡ ፊቶቻቸውንም ጥቁረት እና ውርደት አይሸፍናቸውም፦
75፥22 ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፡፡ وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ نَّاضِرَةٌ
75፥23 ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው፡፡ إِلَىٰ رَبِّهَا نَاظِرَةٌ
10፥26 ለእነዚያ መልካም ለሠሩት መልካም ነገር እና ”ጭማሪም አላቸው"። ፊቶቻቸውንም ጥቁረት እና ውርደት አይሸፍናቸውም፥ እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡ لِّلَّذِينَ أَحْسَنُوا۟ ٱلْحُسْنَىٰ وَزِيَادَةٌۭ ۖ وَلَا يَرْهَقُ وُجُوهَهُمْ قَتَرٌۭ وَلَا ذِلَّةٌ ۚ أُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلْجَنَّةِ ۖ هُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ

በተቃራኒው የከሓዲያን ፊቶች በትንሣኤ ቀን ጨፍጋጊዎች ናቸው፥ ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች። ምክንያቱም እነዚያ እነርሱ ከሓዲዎቹ አመጸኞቹ ናቸው፦
75፥24 ፊቶችም በዚያ ቀን ጨፍጋጊዎች ናቸው፡፡ وَوُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ بَاسِرَةٌ
80፥40 ፊቶችም በዚያ ቀን በላያቸው ላይ ትቢያ አለባቸው። وَوُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ عَلَيْهَا غَبَرَةٌ
80፥41 ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች። تَرْهَقُهَا قَتَرَةٌ
80፥42 እነዚያ እነርሱ ከሓዲዎቹ አመጸኞቹ ናቸው፡፡ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَفَرَةُ الْفَجَرَةُ

እነዚያ ፊቶቻቸው የጠቆሩትማ ከእምነቸው በኋላ የካዱ እና ይክዱ በነበሩት ነገር ቅጣትን የሚቀምሱ ናቸው፥ እነርሱ በትንሣኤ ቀን ከጌታቸው ማየት ተጋራጆች ናቸው፦
3፥106 ፊቶች የሚያበሩበትን ፊቶችም የሚጠቁሩበትን ቀን አስታውስ፡፡ እነዚያ ፊቶቻቸው የጠቆሩትማ «ከእምነታችሁ በኋላ ካዳችሁን ትክዱት በነበራችሁት ነገር ቅጣቱን ቅመሱ» ይባላሉ፡፡ يَوْمَ تَبْيَضُّ وُجُوهٌ وَتَسْوَدُّ وُجُوهٌ ۚ فَأَمَّا الَّذِينَ اسْوَدَّتْ وُجُوهُهُمْ أَكَفَرْتُم بَعْدَ إِيمَانِكُمْ فَذُوقُوا الْعَذَابَ بِمَا كُنتُمْ تَكْفُرُونَ
84፥15 ይከልከሉ! እነርሱ በዚያ ቀን ከጌታቸው ማየት ተጋራጆች ናቸው፡፡ كَلَّا إِنَّهُمْ عَن رَّبِّهِمْ يَوْمَئِذٍ لَّمَحْجُوبُونَ

አምላካችን አሏህ በዛቱ ከፍጥረት ውጪ ቢሆንም ምእመናን በጀነት በዓይናቸው ሳያካብቡት እርሱ በሚፈልገው መልኩ ያዩታል። ፍጡራን እርሱን በማየት አያካብቡትም፥ እርሱ ግን ሁሉን ተመልካች ስለሆነ ሁሉንም ያካብባል፦
6፥103 ዓይኖች አያካብቡትም፡፡ እርሱም ዓይኖችን ያካብባል፡፡ እርሱም ርኅራኄው ረቂቁ ውስጠ ዐዋቂው ነው፡፡ لَّا تُدْرِكُهُ الْأَبْصَارُ وَهُوَ يُدْرِكُ الْأَبْصَارَ ۖ وَهُوَ اللَّطِيفُ الْخَبِيرُ

"አል-ለጢፍ" اللَّطِيف ማለት "ረቂቁ" ማለት ሲሆን አሏህ በፍጡራኑ ዓይን የማይከበብ ረቂቅ ነው፥ እኔ ለማወቅ የሚታወቅ ነገር፣ ለማየት ብርሃን፣ ለመስማት ድምፅ፣ ለመታየት አካል ያስፈልገኛል። አሏህ ግን ከማንም ከምንም ፍጥረት ጋር ስለማይመሳሰል ፍጥረት ሳይኖር ፍጥረቱን የሚያውቅ፣ በጨለማ ውስጥ ያሉትን የሚያይ፣ በልብ የሚንሾካሸኩትን የሚሰማ፣ ለምእመናን በትንሳኤ ቀን ስይካበብ በመገለጥ የሚታይ ነው፦
42፥11 የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ

እሩቅ ሳንሄድ በባይብል አንዱን አምላክ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፥ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፥ እርሱም፦ "ፊቴን ማየት አይቻልህም" ብሏል፦
1 ጢሞቴዎስ 1፥17 ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው "ለማይታየውም" ለዘመናት ንጉሥ ምስጋና እና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን! አሜን።
1 ጢሞቴዎስ 6፥16 ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፥ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም።
ዘጸአት 33፥20 ደግሞም፦ "ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም" አለ።

አንዱን አምላክ አንድ ሰው እንኳ ባያየው እና ሊያይ ባይቻለው ባሮቹ ግን በትንሣኤ ቀን በትንሣኤያዊ ዓይን ፊቱን ያያሉ፦
ኢዮብ 19፥27 ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ፥ በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ። እኔ ራሴ አየዋለሁ፥ ዓይኖቼም ይመለከቱታል።
ራእይ 22፥3 ባሪያዎቹም ያመልኩታል፥ ፊቱንም ያያሉ።

አምላካችን አሏህን በትንሳኤ ቀን እርሱን ከሚያዩት ምእመናን ያርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንድ ባል ሁለተኛ ለማግባት የሚስቱን ፈቃድ ይጠይቃል ወይ? ያድምጡ!
ሃሩን ማን ነው?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

25፥35 *በእርግጥም ለሙሳ መጽሐፍን ሰጠነው፡፡ ከእርሱም ጋር ወንድሙን ሃሩንን ረዳት አደረግንለት*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ وَجَعَلْنَا مَعَهُ أَخَاهُ هَارُونَ وَزِيرًا

ሚሽነሪዎች፦ ቁርኣን ከባይብል ታሪክ ጋር ይጣረሳል" ብለው ሱሪ ባንገት ሊያስገቡ ሲቃጣቸው ይታያል፣ ከሚተቹበት መወዛገብ አንዱ፦ "ቁርአን የሙሴን ወንድ አሮንን የኢየሱስ እናት የማርያም ወንድም ያደርጋል" የሚል ግራጫ ውሸት ይዋሻሉ፥ ይለቃሉ። በኢስላም ላይ ስትቀጥፉ ህሊናን ከሚያሳድድ ጥያቄ አታመልጡም።
ታላቁ ኢትዮጵያዊ ባለቅኔው ሎሬትዬ ጸጋዬ ገብረ መድኅን፦ "የሰው ልጅ ከሁለት ነገር ይማራል፦ አንዱ “ሀ” ብሎ “በሳር” ሲሆን ሁለተኛው “ዋ” ብሎ “በአሳር” ነው" ይለናል። ሚሽነሪ ሃያሲ ሂስ ከመስጠት በፊት “ሀ” ብሎ “በሳር” ከቁርአን መማር አሊያም “ዋ” ብሎ “በአሳር” ተነግሮ ከማያልቅ ታፍሶ ከማይዘለቅ ከዲነል ኢስላም ዕውቀት መማር ነው። መዋተቱና መቃተቱን ትታችሁ ጓዛችሁን ሸክፋችሁ ለመማር ኑ። መቆዘም አያዋጣም። ይህ ነጥብ ምን ያህል እንደተወዛገባችሁ ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እናያለን፣ "ሃሩን" هَارُونَ ማለት በአማርኛችን "አሮን" ተብሎ በቁርአን የተጠቀሱ ሁለት የተለያዩ ግለሰቦች አሉ፣ እነርሱም አንዱ የሙሴ ወንድም ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የኢየሱስ እናት የማርያም ወንድም፣ ይህን ነጥብ በነጥብ እንመልከተው፦

ነጥብ አንድ
"የሙሳ ወንድም ሃሩን"
ሙሳ አንደበተ ኮልታፋ እና ተብታባ ስለነበር ወንድሙ በእርሱ ፋንታ እንዲናገር ወደ አላህ ዱዓ አደረገ፦
20፥29 «ከቤተሰቦቼም ለእኔ ረዳትን አድርግልኝ፡፡ وَاجْعَل لِّي وَزِيرًا مِّنْ أَهْلِي
20፥30 *«ሃሩንን ወንድሜን*፡፡ هَارُونَ أَخِي
20፥32 *«በነገሬም አጋራው*፡፡ وَأَشْرِكْهُ فِي أَمْرِي
28፥34 *«ወንድሜም ሃሩን እርሱ ምላሱ ከእኔ የተባ ነው፡፡ እውነተኛነቴንም የሚያረጋግጥልኝ ረዳት ኾኖ ከእኔ ጋር ላከው፡፡ እኔ ሊያስተባብሉኝ እፈራለሁና*፡፡» وَأَخِي هَارُونُ هُوَ أَفْصَحُ مِنِّي لِسَانًا فَأَرْسِلْهُ مَعِيَ رِدْءًا يُصَدِّقُنِي ۖ إِنِّي أَخَافُ أَن يُكَذِّبُونِ

ሙሳ መልእክተኛ ነው፤ ሃሩን ደግሞ ነቢይ ነው፤ ነገር ግን "በነገሬም አጋራው" ብሎ በጠየቀው መሰረት ተውራት የተባለውን ሪሳላ ስለተጋራ መልእክተኛ ተባለ፤ "ከእኔ ጋር ላከው" የሚለው ይሰመርበት፤ ለዛ ነው አላህ ተውራትን ለሙሳ እና ለሃሩን ሰጠናቸው ያለው፦
21፥48 *ለሙሳ እና ለሃሩንም እውነትንና ውሸትን የሚለይን ብርሃንንም ለጥንቁቆችም መገሰጫን በእርግጥ ሰጠናቸው*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَىٰ وَهَارُونَ الْفُرْقَانَ وَضِيَاءً وَذِكْرًا لِّلْمُتَّقِينَ

ሃሩን በራሱ መልእክተኛ አይደለም፤ ግን ነቢይ ሆኖ ሙሳን በመልእክቱ በማስተላለፍ ይረዳዋል፤ አላህ ወደ ሕዝባቸው በተዓምራታችንና በግልጽ አስረጅ ላካቸው፦
19፥53 *ከችሮታችንም ወንድሙን ሃሩንን ነቢይ አድርገን ሰጠነው*፡፡ وَوَهَبْنَا لَهُ مِن رَّحْمَتِنَا أَخَاهُ هَارُونَ نَبِيًّا
25፥35 *በእርግጥም ለሙሳ መጽሐፍን ሰጠነው፡፡ ከእርሱም ጋር ወንድሙን ሃሩንን ረዳት አደረግንለት*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ وَجَعَلْنَا مَعَهُ أَخَاهُ هَارُونَ وَزِيرًا
23፥45 *ከዚያም ሙሳንና ወንድሙን ሃሩንን በተዓምራታችንና በግልጽ አስረጅ ላክን*፡፡ ثُمَّ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ وَأَخَاهُ هَارُونَ بِآيَاتِنَا وَسُلْطَانٍ مُّبِينٍ

ስለ ነቢዩ ሃሩን በጥቅሉ ይህንን ይመስላል። የሙሳ እና የሃሩን እናት እና አባት አሊያም የቤተሰብ ዝርዝር ስም ሆነ ማንነት ቁርኣን ላይ አልተጠቀሰም።
ነጥብ ሁለት
"የሃሩን እኅት"
አምላካችን አላህ በዒሣ እናት በመርየም ዘመን የነበሩት የመርየም ዘመዶች የዒሣን እናት መርየምን "የሃሩን እኅት" እንዳሏት ተርኮልናል፦
19፥28 *«የሃሩን እኅት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም፡፡ እናትሽም አመንዝራ አልነበረችም» አሏት*፡፡ يَا أُخْتَ هَارُونَ مَا كَانَ أَبُوكِ امْرَأَ سَوْءٍ وَمَا كَانَتْ أُمُّكِ بَغِيًّا

"አሏት" የሚለው ይሰመርበት፤ ባዮቹ የመርየም ዘመዶች ቢሆኑም አላህ ይህንን ተርኮልናል። የኢሳን እናት መርየም የአባቷ ስም አፖክራፋ በሆነው በያዕቆብ ወንጌል ውስጥ "ኢያቂም" יְהוֹיָקִים በቁርኣን ደግሞ "ዒምራን" عمران ነው፤ የእናቷ ስም አፖክራፋ በሆነው በያዕቆብ ወንጌል ውስጥ "አና" חַנָּה በተፍሲር ደግሞ "ሐናህ" حنة ነው፣ ኢያቄም የማርያም አባት ስለመሆኑ ከቁርአን ማየት ይቻላል፦
3፥35 *የዒምራን ባለቤት (ሐና)* «ጌታዬ ሆይ! እኔ በሆዴ ውስጥ ያለውን ፅንስ ከሥራ ነጻ የተደረገ ሲኾን ለአንተ ተሳልኩ፡፡ ከእኔም ተቀበል አንተ ሰሚው ዐዋቂው ነህና» ባለች ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَتِ امْرَأَتُ عِمْرَانَ رَبِّ إِنِّي نَذَرْتُ لَكَ مَا فِي بَطْنِي مُحَرَّرًا فَتَقَبَّلْ مِنِّي ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ
66፥12 *የዒምራንን ልጅ መርየምንም ያችን ብልቷን የጠበቀችውን ምሳሌ አደረገ*፡፡ በእርሱም ውስጥ ከመንፈሳችን ነፍፋን፡፡ በጌታዋ ቃላትና በመጻሕፍቱም አረጋገጠች፡፡ ከታዛዦቹም ነበረች፡፡ وَمَرْيَمَ ابْنَتَ عِمْرَانَ الَّتِي أَحْصَنَتْ فَرْجَهَا فَنَفَخْنَا فِيهِ مِن رُّوحِنَا وَصَدَّقَتْ بِكَلِمَاتِ رَبِّهَا وَكُتُبِهِ وَكَانَتْ مِنَ الْقَانِتِين

ቁርኣን ላይ የመርየም እናት ስሟ ባይጠቀስም ማንነቷ ተገልጻል። ነገር ግን ባይብል ላይ የመርየም እናት እና አባት ስም ሆነ ማንነት አልተገለጸም።
ስለዚህ ከመነሻው በሌለ ነገር ሁለት የተለያዩ ታሪካትን አዛብቶ ግጭት መፍጠር አይቻልም፣ ታዲያ ዒሣ እናት የመርየም ወንድም ሃሩን ማነው? ስንል የስም ሞክሼ እንጂ እራሱ የሙሳ ወንድም አይደለም። ይህንን ከነብያችን"ﷺ" መረዳት ይቻላል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 38, ሐዲስ 13
አል-ሙጊራህ ኢብኑ ሹዕባ እንደተረከው፦ *"ወደ ነጅራን በመጣው ጊዜ የነጅራን ክርስቲያኖች፦"የሃሩን እኅት ሆይ! የሚል ቀርተክልናል፤ ሙሳ ከዒሣ ብዙ ጊዜ በፊት የነበረ ነው" ብለው ጠየቁኝ። እኔም ወደ አላህ መልእክተኛ"ﷺ" ስመለስ ስለዚህ ጉዳይ ጠየኳቸው፣ እሳቸውም አሉ፦ "የድሮ ሰዎች ከራሳቸው በፊት ከነበሩት የነቢያቶች ስሞች ከነቢያቱ ህልፈት በኋላ ይጠቀሙ ነበር*። عَنِ الْمُغِيرَةِ بْنِ شُعْبَةَ، قَالَ لَمَّا قَدِمْتُ نَجْرَانَ سَأَلُونِي فَقَالُوا إِنَّكُمْ تَقْرَءُونَ يَا أُخْتَ هَارُونَ وَمُوسَى قَبْلَ عِيسَى بِكَذَا وَكَذَا ‏.‏ فَلَمَّا قَدِمْتُ عَلَى رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم سَأَلْتُهُ عَنْ ذَلِكَ فَقَالَ ‏ "‏ إِنَّهُمْ كَانُوا يُسَمُّونَ بِأَنْبِيَائِهِمْ وَالصَّالِحِينَ قَبْلَهُمْ

ከነቢያችን"ﷺ" ንግግር የምንረዳው የሙሳ ወንድም ሃሩን እና የዒሳ እናት የመርየም ወንድም ኃሩን የስም መመሳሰል እንጂ እራሱ የሙሳ ወንድም አይደለም። ሁለት የተለያዩ ግለሰቦች ናቸው፣ የእሳቸው ዘመድና ባልደረባም ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." ይህን አንቀጽ ሲፈስረው፦ "አሮን የማርያም ግማሽ ወንድምና የአባቷ ልጅ ነው" በማለት አስቀምጦታል።

ነጥብ ሦስት
"ኢኽዋህ"
“ኢኽዋህ” إِخْوَة ማለት “ወንድማማች እና እህትማማችነት" ማለት ነው፤ አማኞች ደግሞ ወንድም እና እህት ናቸው፦
49፥10 *ምእመናኖች ወንድማመቾች ናቸው*፡፡ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል አስታርቁ፡፡ ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ فَأَصْلِحُوا بَيْنَ أَخَوَيْكُمْ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ

በነብያችን"ﷺ" ሐዲስ የሙሳ ወንድም እና የመርየም ወንድ ሁለት የስም ሞክሼ መሆኑ ተሰምሮበታል፤ ነገር ግን የሙሳ ወንድም እና የመርየም ወንድ አንድ ማንነት ናቸው ቢባል እንኳን አሁንም ችግር የለውም። ምክንያቱም አማኞች ደግሞ ወንድም እና እህት ናቸው በሚል ቀመርና ስሌት መረዳት ይቻላል።
በትውፊት መርየም የሌዊ ዘር ናት፤ ሃሩንም የሌዊ ዘር ነው፤ ስለዚህ ሁለቱም ወንድምና እህት መሆን ይችላሉ፤ "አኽ" أَخ ማለት "ወንድም" ማለት ሲሆን እና "ኡኽት" أُخْت ማለት ደግሞ "እኅት" ማለት ነው፤ ቃሉ የግድ አብራካዊ ወንድምና እህት ብቻ አያመለክትም። ምክንያቱም "ኡኽት" أُخْت የሚለው ቃል "ሚስል" مِثْل ማለትም "ቢጤ" በሚል ይመጣል፦
43፥48 ከተዓምርም አንዲትንም አናሳያቸውም እርሷ *ከብጤዋ* በጣም የበለጠች ብትኾን እንጅ፡፡ ከክህደታቸው ይመለሱም ዘንድ በቅጣት ያዝናቸው፡፡ وَمَا نُرِيهِم مِّنْ آيَةٍ إِلَّا هِيَ أَكْبَرُ مِنْ أُخْتِهَا ۖ وَأَخَذْنَاهُم بِالْعَذَابِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ
7፥38 አንዲቱ ሕዝብ ወደ እሳት በገባች ቁጥር ያሳሳተቻትን *ብጤዋን* ትረግማለች፡፡ كُلَّمَا دَخَلَتْ أُمَّةٌ لَّعَنَتْ أُخْتَهَا

"ብጤዋ" ለሚለው የገባውን ቃል "ኡኽቲሃ" أُخْتِهَا አንዳንድ የኢንግሊሽ ትርጉም "እህትዋን"its sister" በማለት አስቀምጠውታል፦
43፥48 And We showed them not a sign except that it was greater than *its sister*, and We seized them with affliction that perhaps they might return [to faith]. Sahih International

ማጠቃለያ
ይህንን እንዲህ በእንዲህ ካየን ዘንዳ በዐረቢኛ “መርየም” مَرْيَم‎ ፣ በዐረማይክ “ማርአም” ܡܪܝܡ‎ ፣ በግሪክ “ማርያ” mαρία ሲሆን የስሙ መሰረት የዕብራይስጡ “ሚሪየም” מִרְיָם‎ ነው፤ “ሚሪየም” מִרְיָם‎ የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “መር” מר ማለት “ጠብታ” ማለት ሲሆን “የም” ים ደግሞ “ባህር” ማለት ነው፤ በጥቅሉ “ሚሪየም” מִרְיָם‎ ማለት “የባህር ጠብታ” ማለት ነው።
በባይብል ማርያም በሚል ስም የሚጠሩ ሴቶች ስምንት ሲሆኑ እነርሱም፦
1ኛ. የሙሴ እህት፦ ዘጸአት 15፥21
2ኛ. የዕዝራ ልጅ፦ 1ኛ ዜና 4፥17
3ኛ. የኢየሱስ እናት፦ ማቴዎስ 1፥18
4ኛ. መቅደላዊት፦ ሉቃስ 8፥2
5ኛ. የአልዓዛር እህት፦ ዮሐንስ 11፥1
6ኛ. የቀለዮጳም ሚስት፦ ዮሐንስ 19፥25
7ኛ. የማርቆስ እናት፦ 12፥12 እና
8ኛ. የሮሜ ማርያም፦ ሮሜ 16፥6 ናቸው።
የኢየሱስ እናት መርየም ለእናቷ አንድና የስለት ልጅ ብትሆንም በአባቷ ግን ወንድምና እህት እንዳላት ነገረ-ማርያም"Marylogy" ይነግረናል፣ ባይብልም ማርያም እህት እንዳላት ይናገራል፦
ዮሐንስ 19፥25 ጭፍሮችም እንዲህ አደረጉ፦ ነገር ግን በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፥ *የእናቱም እኅት*፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር።

በታሪክ፣ በፔንታተች ሆነ በታልሙድ መጻሕፍት የሙሴና የአሮን አባት "እንበረም" עַמְרָם ሲሆን እናታቸው ደግሞ "ዮከብድ" יוֹכֶ֤בֶד ናት፣ ይህን ከራሳችሁ መጽሐፍ ቅሪት ማየት ይቻላል፦
ዘጸአት 6፥20 *እንበረምም עַמְרָם የአጎቱን ልጅ ዮካብድን יוֹכֶ֤בֶד አገባ፥ “አሮንና ሙሴንም” ወለደችለት*፤

ነገር ግን የሙሴ እህት ማርያም እና የኢየሱስ እናት ማርያም ሁለት የተለያዩ ሴቶች ናቸው። ይህ በቀላለ እንድትረዱት አንድ ናሙና ከባይብል ልስጣችሁ፣ "የጌት ሰው ጎልያድን" የገደለው ማን ነው ዳዊት ወይስ ይሽቢብኖብ?
እዚህ አንቀጽ ላይ የጌት ሰው ጎልያድን ዳዊት እንደገደለው ይናገራል፦
1ኛ ሳሙኤል 17፥4 ከፍልስጥኤማውያንም ሰፈር *የጌት ሰው ጎልያድ*፥ ቁመቱም ስድስት ክንድ ከስንዝር የሆነ፥ ዋነኛ ጀግና መጣ።
1ኛ ሳሙኤል 17፥50 *ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን በወንጭፍና በድንጋይ አሸነፈው፥ ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለ*፤ በዳዊትም እጅ ሰይፍ አልነበረም።

እዚህ አንቀጽ ላይ ደግሞ የጌት ሰው ጎልያድን ይሽቢብኖብ እንደገደለው ይናገራል፦
2ኛ ሳሙኤል 21፥19 ደግሞም በጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰልፍ ነበረ፤ የቤተ ልሔማዊውም የየዓሬኦርጊም ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን *የጌት ሰው ጎልያድን* ገደለ።

አንዱን ክርስቲያን ተወያይ ይህን ጥያቄ ሳቀርብለት "ወሒድ ምን ነካህ ደህና ሰው አልነበርክም እንዴ? ዳዊት የገደለው ጎልያድ እና ይሽቢብኖብ የገደለው ጎልያድ እኮ በተለያየ ዘመን የኖሩ ሁለት ግለሰቦች ናቸው" አለኝ፣ እውነት ነው የአይሁድ ሆነ የክርስቲያን ስመ-ጥርና ዝነኛ ኮሜንታተሮች በተለያዩ ዘመን ይኖሩ የነበሩ ግን በአንድ ቦታ በጌት ይኖሩ የነበሩ ሰዎች መሆናቸውን አስቀምጠዋል፣ ታዲያ ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ነው ነገሩ፣ በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም ይሉሃል እንደዚህ ነው።
ሲቀጥል ወንድምና እህት የግድ የአብራክ ክፋይ የሚለውን አያሲዝም። ሉጥ የኢብራሂም የወንሙ ልጅ ሲሆን ኢብራሂም ለሉጥ ደግሞ አጎት ነው፣ ነገር ግን ሉጥ ለኢብራሂም ወንድም ተብሏል፣ ያ ማለት የአንድ ቤተሰብ መሆንን ካሳየ የሙሳ ወንድም አሮንና መርየም የሌዊ ቤተሰብ ስለሆኑ ወንድም አሊያም እህት ቢባሉ ችግር የለውም፦
ዘፍጥረት14፥12 በሰዶም ይኖር የነበረውን *የአብራምን የወንድም ልጅ ሎጥን* ደግሞ ከብቱንም ወስደው ሄዱ።
ዘፍጥረት14፥14 አብራምም *ወንድሙ* እንደ ተማረከ በሰማ ጊዜ በቤቱ የተወለዱትን ሦስት መቶ አሥራ ስምንት ብላቴኖቹን አሰለፈ፥ ፍለጋቸውንም ተከትሎ እስከ ዳን ድረስ ሄደ።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አህዛብ ማን ነው?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

አንዱ ክርስቲያን በውይይት ላይ ሲናደድ አህዛብ ብሎ ተናገረኝ፤ እኔም አህዛብ ምን ማለትና ምን እንደሆነ ብታውቅ ኖሮ ይቺን ቃል አትደፍራትም ነበር ብዬ ምላሽ ሰጠሁት፤ "አህዛብ" ተብሎ በግሪክ ብሉይ ሰፕቱአጀን እና በአዲስ ኪዳን ግሪክ ኮይኔ ላይ "ኤትኖስ" ἔθνος የሚለው የግሪኩ ቃል "ኤትኒኮስ" ἐθνικός ከሚለው ገላጭ የመጣ ሲሆን በዕብራይስጡ ደሃራይ እደ-ክታባት ላይ ደግሞ "ጎይ" גוי ተብሎ ተቀምጧል፤ ይህ ቃል እንደየ አውዱ ለተለያየ ትርጉም አገልግሎት ላይ የዋለ ሲሆን "ህዝብ" "ብሔር" "አረማዊ" "ይሁዲ ያልሆነ" የሚል ፍቺ እንዳለው የግሪክና የዕብራይስጥ ሙዳየ-ቃላት ያትታሉ፤ ያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እዚህ አርስት ላይ "አህዛብ" ብለን የምንመለከተው "አረማዊ"pagan" የሚለው እሳቤ ነው፤ ሰዎች ይህ ስም የአብርሃምን አምላክ ለሚያመልኩ ለሙስሊሞች እንደ ቅፅል ስም ሲጠቀሙ እጅግ ስላስደመመኝ ይህ ስም ማንን እንደሚመለከትና ማንን አህዛብ እንደሚል ለመፅሐፍ ቅዱስ ቦታውን እንልቀቅ፦

ነጥብ አንድ
"ርኵሰት"
በመፅሐፍ ቅዱስ "የአሕዛብን ርኵሰት" ተብሎ የተቀመጠው ምዋርት፥ ሞራ ገላጭ፥ አስማት፥ መተተት፥ ድግምት፣ ጥንቆላ፥ መናፍስትንም መጥራት፥ ሙታን መሳብ ነው፦
ዘዳግም 18፥9-11 አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ ጊዜ እነዚያ ""አሕዛብ"" የሚያደርጉትን "ርኵሰት" ታደርግ ዘንድ አትማር። ወንድ ልጁን ሴት ልጁን በእሳት የሚያሳልፍ፥ ምዋርተኛም፥ ሞራ ገላጭም፥ አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ።

ታዲያ ይህ በኢስላም ትልቁ ሽርክ ነው፤ ከኢስላም አጥርስ የሚያስወጣ አይደለምን? ይህንን ድርጊትስ ማን ነው በዘመናዊ መልክ የሚያደርገው ሙስሊሙ ወይስ ስም ለጣፊው?

ነጥብ ሁለት
"ግብረ-ሰዶም"
አላህ የፈጠረው ተቃራኒ ፃታ"hetro-sexual" እያለ ዛሬ ወንድ ለወንድ ሴት ለሴት የሆነው ግብረ-ሰዶም"homo-sexual" ማድረግ የአሕዛብን ርኵሰት ነው፦
1ኛ ነገሥት 14፥24 በምድርም ውስጥ "ሰዶማውያን" ነበሩ፤ ከእስራኤልም ልጆች ፊት እግዚአብሔር ያሳደዳቸውን ""የአሕዛብን ርኵሰት" ሁሉ ያደርጉ ነበር።

ታዲያ ይህ በኢስላም አይደለም መጋባት ይቅርና ድርጊቱ ሃራም ነው፤ ማን ነው ታዲያ ወንድ ለወንድ ሴት ለሴት የሚያጋባው ቤተክርስቲያን ወይስ መስኪድ? ህሊና ይፍረደዋ።

ነጥብ ሶስት
"የተቀረፀ ምስል"
ነቢያት "የአሕዛብ ልማድ" ብለው ያስቀመጡት ከእንጨት፣ ከብረት፣ ከብር እና ከወርቅ የተሰሩትን የተቀረፁ ምስሎች ነው፤ እነዚህ ምስሎች አፍ አላቸው አይናገሩም፤ ዓይን አላቸው አያዩም፤ ጆሮ አላቸው አይሰሙም፤ አፍንጫ አላቸው አያሸቱም፤ እጅ አላቸው አይዳስሱም፤ እግር አላቸው አይሄዱም፤ ክፉ መሥራትም አይቻላቸውም ደግምም መልካም ይሠሩ ዘንድ አይችሉም፣ አህዛብ ግን ወደ እነርሱ ይፀልያሉ፣ ይለማመናሉ፣ እጣን ያጨሳሉ፣ ይጎባደዳሉ፣ ያሸረግዳሉ፣ ይሰግዳሉ፣ -ያመልካሉ፦
2ኛ ነገሥት17፥41 እነዚህም "አሕዛብ" እግዚአብሔርን ይፈሩ ነበር፤ ደግሞም "የተቀረጹ ምስሎቻቸውን" ያመልኩ ነበር፤
2ኛ ዜና 16፥26 "የአሕዛብ አማልክት" ሁሉ ጣዖታት ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።
መዝሙር 115፥4-7 የአሕዛብ ጣዖታቶች "የወርቅና የብር፥ የሰው እጅ ሥራ" ናቸው፤ አፍ አላቸው አይናገሩምም፤ ዓይን አላቸው አያዩምም፤ ጆሮ አላቸው አይሰሙምም፤ አፍንጫ አላቸው አያሸትቱምም፤ እጅ አላቸው አይዳሰሱምም፤ እግር አላቸው አይሄዱምም፤ በጕሮሮአቸውም አይናገሩም።
ኢሳይያስ 45፥20 እናንተ "ከአሕዛብ" ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ በአንድነትም ቅረቡ፤ "የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት" የሚሸከሙና ያድን ዘንድ "ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ" እውቀት የላቸውም።
ኤርምያስ 10፥2-5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ "የአሕዛብን መንገድ አትማሩ ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፤ አሕዛብ ይፈሩታልና። "የአሕዛብ ልማድ" ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሠራተኛም እጅ በመጥረቢያ ይሠራል። በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፥ እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል።
እንደ ተቀረጸ ዓምድ ናቸው እነርሱም አይናገሩም፤ መራመድም አይቻላቸውማን ይሸከሙአቸዋል። ክፉ መሥራትም አይቻላቸውምና፥ ደግምም መልካም ይሠሩ ዘንድ አይችሉምና አትፍሩአቸው።

ማን ነው የተቀረፀ ምስል አድርጎ ለቅዱሳን የአክብሮት ስግደት እና ለሶስቱ አካላት የአምልኮ ስግደት የሚሰግደው? በስዕልና በሃውልት ፊት የሚለማመን፣ የሚያመልክ፣ እጣን የሚያጨስ፣ ስለት የሚሳል? ሙስሊሙ ወይስ እውነተኛው አህዛብ? ኅሊና እያለ ምን ይኮናል።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም