ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.3K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ፖስተር ቄስ ግርማ ዘውዴ 🙏 እውነታውን አፈረጡት
https://youtu.be/CRKeUTFUdGg
ሂጃብ በደርዘን እያሰፉ 1ሺ ብር እየከፈሉ ነው አሰልጥነው ወደ ጌታ መጣን ሚያስብሏቸው ።

እንዲህ እውነታው በራሳቸው ወገን ሲገለጥ ደስ ይላል ቄስ በላይ እውነታውን ስላጋለጡ እናመሰግናለን
https://youtu.be/CRKeUTFUdGg
ጠባቂዎች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

9፥116 ለእናንተም ከእርሱ በቀር ጠባቂም ረዳትም የላችሁም፡፡ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ

ማመናፈስ እና ማመቻመች የሚወዱ ሚሽነሪዎች ቀን ከሌሊት ወቃሽና ነቃሽ በመሆን ማኮሰስ እና ማራከስ ተያይዘውታል፥ የሃይማኖት ንጽጽር ላይ ያሉት ዐቃቢያነ እሥልምና ደግሞ የሚሽነሪዎችን የቆላ ሀሩር የደጋ ቁር ኢምንት እና ቀቢጽ ያክል ሳይቆጥሩ መልስ ይሰጣሉ። ከሚያንኳስሱትና ከሚያራክሱት ነገር መካከል፦ "ከአሏህ በቀር ጠባቂ የለም" ተብሎ በሌሎች አናቅጽ "መላእክት ጠባቂዎች ናቸው" መባላቸውን ነው። ይህንን የተውረግረገረገ መረዳት በሰከነ እና በሰላ አእምሮ እንየው፦
አምላካችን አሏህ ለአማንያን ጠባቂ ነው፥ ከእርሱ በቀር ጠባቂ የለም። ከእሳት ቅጣት የሚጠብቅ እርሱ ብቻ ነው፦
9፥116 ለእናንተም ከእርሱ በቀር ጠባቂም ረዳትም የላችሁም፡፡ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ
11፥113 ወደ እነዚያም ወደ በደሉት አትጠጉ፡፡ እሳት ትነካችኋለችና፡፡ ከአላህም ሌላ ጠባቂዎች የሏችሁም፡፡ ከዚያም አትረዱም፡፡ وَلَا تَرْكَنُوا إِلَى الَّذِينَ ظَلَمُوا فَتَمَسَّكُمُ النَّارُ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِنْ أَوْلِيَاءَ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ

"ከአላህም ሌላ ጠባቂዎች የሏችሁም" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! እሳት እንዳይነካን ከአሏህ ሌላ ጠባቂዎች የሉም። ቅሉ ግን አምላካችን አሏህ ለሰው ከክፉ የሚጠብቁት ተተካኪዎች መላእክት አድርጓል፦
13፥11 *"ለሰው ከስተፊቱም ከኋላውም በአላህ ትዕዛዝ ከክፉ የሚጠብቁት ተተካኪዎች መላእክት አሉት"*፡፡ لَهُ مُعَقِّبَاتٌ مِّن بَيْنِ يَدَيْهِ وَمِنْ خَلْفِهِ يَحْفَظُونَهُ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ
86፥4 *"ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጅ ሌላ አይደለችም"*፡፡ إِن كُلُّ نَفْسٍ لَّمَّا عَلَيْهَا حَافِظٌ
6፥61 እርሱም ከባሮቹ በላይ ሲኾን ሁሉን አሸናፊ ነው፥ በእናንተም ላይ ጠባቂዎችን ይልካል፡፡ وَهُوَ الْقَاهِرُ فَوْقَ عِبَادِهِ ۖ وَيُرْسِلُ عَلَيْكُمْ حَفَظَةً

መላእክት ጠባቂ የተባሉበት አሏህ ጠባቂ በተባለበት ሒሣብ እና ቀመር በፍጹም እንዳልሆነ እሙን እና ቅቡል ነው። ምክንያቱም “መልአክ” مَلْأَك የሚለው ቃል “ለአከ” لَأَكَ ማለትም “ላከ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ተላላኪ” ማለት ነው፥ የመለክ ብዙ ቁጥር ደግሞ “መላኢክ” مَلَائِك‎ ወይም “መላኢካህ” مَلَائِكَة‎ ነው። እነዚህ የአሏህ መላእክት የተለያየ የሥራ ድርሻ ተሰቷቸው ይጠብቃሉ፦
72፥8 ‹እኛም ሰማይን ለመድረስ ፈለግን፡፡ ብርቱ ጠባቂዎችን እና ችቦዎችንም ተሞልታ አገኘናት፡፡ وَأَنَّا لَمَسْنَا السَّمَاءَ فَوَجَدْنَاهَا مُلِئَتْ حَرَسًا شَدِيدًا وَشُهُبًا
72፥27 ከመልክተኛ ለወደደው ቢኾን እንጅ ለሌላ አይገልጽም፡፡ እርሱም ከስተፊቱም ከስተኋላውም ጠባቂዎችን ያደርግለታል፡፡ إِلَّا مَنِ ارْتَضَىٰ مِن رَّسُولٍ فَإِنَّهُ يَسْلُكُ مِن بَيْنِ يَدَيْهِ وَمِنْ خَلْفِهِ رَصَدًا

ስለዚህ አሏህ "ጠባቂ" የተባለው በራሱ የተብቃቃ እና የባሕርይ ገንዘቡ"ontological term" ሲሆን መላእክት "ጠባቂዎች" የተባሉት የጸጋ እና የሹመት ጉዳይ"functional term" ነው። አንድ ስም ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብ እና ትርጉም እንደሌለው ዕሙር እና ስሙር ነው፥ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ እሙን ነው። መታየት ያለበት ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብ፣ የአንቀጹን ምህዋር፣ አውታርና ምህዳር እንደሆነ ቅቡል ነው። ይህ እንዲገባችሁ ከባይብል አንድ ናሙና እንመልከት! ፈጣሪ ብዙ ቦታ፦ "ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም" ይላል፦
ኢሳይያስ 45፥22 እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ እኔ አምላክ ነኝና፥ "ከእኔም በቀር ሌላ የለም"። פְּנוּ־אֵלַ֥י וְהִוָּשְׁע֖וּ כָּל־אַפְסֵי־אָ֑רֶץ כִּ֥י אֲנִי־אֵ֖ל וְאֵ֥ין עֹֽוד
ዘዳግም 32፥39 አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ "ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ" እዩ!። רְא֣וּ ׀ עַתָּ֗ה כִּ֣י אֲנִ֤י אֲנִי֙ ה֔וּא וְאֵ֥ין אֱלֹהִ֖ים עִמָּדִ֑י אֲנִ֧י אָמִ֣ית וַאֲחַיֶּ֗ה מָחַ֙צְתִּי֙ וַאֲנִ֣י אֶרְפָּ֔א וְאֵ֥ין מִיָּדִ֖י מַצִּֽיל
ኢሳይያስ 45፥5 እኔ ያህዌህ ነኝ፥ ከእኔም ሌላ ማንም የለም። "ከእኔም በቀር አምላክ የለም"። אֲנִ֤י יְהוָה֙ וְאֵ֣ין עֹ֔וד זוּלָתִ֖י אֵ֣ין אֱלֹהִ֑ים אֲאַזֶּרְךָ֖ וְלֹ֥א יְדַעְתָּֽנִי

ኢሳይያስ 45፥22 ላይ "አምላክ" ለሚለው በዕብራይስጡ የገባው ቃል "ኤል" אֵ֖ל ሲሆን "ኤሎሃ" אלוהּ ለሚለው ቃል ምጻረ-ቃል ነው፥ ዘዳግም 32፥39 እና ኢሳይያስ 45፥5 ላይ "አምላክ" ለሚለው በዕብራይስጡ የገባው ቃል "ኤሎሂም" אלהים ሲሆን "ኤሎሃ" אלוהּ ለሚለው ቃል ብዜት ነው። ከእርሱ በቀር ኤሎሂም ከሌለ መላእክት "ኤሎሂም" אלהים ተብለዋል፦
መዝሙር 97፥7 "አማልክትም" ሁሉ ስገዱለት። הִשְׁתַּחֲווּ־לֹ֝ו כָּל־אֱלֹהִֽים
መዝሙር 8፥5 "ከአማልክትን" እጅግ ጥቂት አሳነስኸው። וַתְּחַסְּרֵ֣הוּ מְּ֭עַט מֵאֱלֹהִ֑ים
መዝሙር 138፥1 በአማልክት" ፊት እዘምርልሃለሁ። נגד אלהים אזמרך

እነዚህ ሦስት አናቅጽ ላይ "ኤሎሂም" כֵּֽאלֹהִ֔ים የተባሉት መላክእት ስለሆኑ ግሪክ ሰፕቱጀንት እና የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ፦ "መላእክት" ብለው በግልጽ አስቀምጠዋል። ጥያቄአችን፦ "ያህዌህ ከእኔ ሌላ ኤሎሂም የለም" ካለ ዘንዳ በሌሎች ጥቅሶች መላእክት ለምን ኤሎሂም ተባሉ? አዎ መልሱ፦ "መላእክት "አማልክት" የተባሉት ፈጣሪ "አምላክ" በተባለበት ስሌት እና ቀመር አይደለም" ከሆነ እንግዲያውስ መላእክት ጠባቂ የተባሉበት አሏህ ጠባቂ በተባለበት ሒሣብ እና ቀመር በፍጹም አይደለም። ተግባባን? አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሰው

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

35፥3 እናንተ ሰዎች ሆይ! በእናንተ ላይ ያለውን የአላህን ጸጋ አስታውሱ!፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ اذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ

አምላካችን አሏህ የአደምንም ልጆች በእርግጥ አክብሯል፥ ከፈጠራቸውም ፍጡሮች በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጣቸው፦
17፥70 የአደምንም ልጆች በእርግጥ አከበርናቸው። وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ
17፥70 ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጥናቸው፡፡ وَفَضَّلْنَاهُمْ عَلَىٰ كَثِيرٍ مِّمَّنْ خَلَقْنَا تَفْضِيلًا

ሰው አሏህ ያከበረው ክቡር ፍጡር ነው፥ ሰው ከእንስሳ የበለጠ ፍጡር ነው። በሰው ላይ ያለው የአሏህ ጸጋ ብዙ ነው፦
35፥3 እናንተ ሰዎች ሆይ! በእናንተ ላይ ያለውን የአላህን ጸጋ አስታውሱ!፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ اذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ

ሰው ከእንስሳ በልደት፣ በሞት፣ በመተኛት፣ ከተቃራኒ ፆታ ጋር ተራክቦ በማድረግ የጋራ ተፈጥሮ ቢኖረውም የሚለይበት ሦስት ዐበይት ነገራት ዐቅል፣ ቀውል እና መሥኡሉል ዐደብ አሉት። እነዚህን ሦስት ነገራት ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"ዐቅል"
“ዐቅል” عَقْل የሚለው ቃል “ዐቀለ”عَقَلَ ማለትም "ተገነዘበ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አእምሮ" "አመክንዮ" "መረዳት" "ግንባዜ"metacognition" ማለት ነው። ሰው የማሰብ፣ የማስተንተን፣ የመረዳት ተውህቦ"faculty" ያለው ውሳጣዊ ተፈጥሮ የሆነ አእምሮ ስላለው ነው፥ ሰው ከእንስሳ በዐቅል ይለያል። እንስሳ ሰናይ እና እኩይ የሚያመዛዝኑበት አእምሮ የላቸውም፥ ሰው “መንጢቅ” مَنْطِق ማለትም “ሥነ-አመክንዮ”logic" የሚጠቀመው የዐቅል ባለቤት ስለሆነ ነው። አንድ ሰው ወፈፌ ከሆነ ወደ ዐቅሉ እስኪመለስ ድረስ የሚሠራውን እኩይ ሥራ መላእክት አይመዘግቡበትም፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 48
ዓኢሻህ “ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአላህ መልዕክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ብዕር ከሦስት ሰዎች ተነስቷል፥ እነርሱም፦ የተኛ ሰው እስኪነሳ ድረስ፣ ዕብደ ወደ ዐቅሉ እስኪመለስ ድረስ እና ልጅ እስኪጎሎብት ድረስ”። عَنْ عَائِشَةَ، رضى الله عنها أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ رُفِعَ الْقَلَمُ عَنْ ثَلاَثَةٍ عَنِ النَّائِمِ حَتَّى يَسْتَيْقِظَ وَعَنِ الْمُبْتَلَى حَتَّى يَبْرَأَ وَعَنِ الصَّبِيِّ حَتَّى يَكْبَرَ ‏

ባለማወቅ የሚሠራ መጥፎ ሥራ "ስህተት" ሲባል በመርሳት የማይሠራ መልካም ሥራ "ግድፈት" ይባላል፥ ስህተት ሆነ ግድፈት አያስቀጣም፦
2፥286 “ጌታችን ሆይ! ”ብንረሳ ወይም ብንስት አትቅጣን” በሉ፡፡ رَبَّنَا لَا تُؤَاخِذْنَا إِن نَّسِينَا أَوْ أَخْطَأْنَ
33፥5 በእርሱ በተሳሳታችሁበትም ነገርም በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም፥ ግን ልቦቻችሁ ዐዉቀው በሠሩት ኃጢአት አለባችሁ”። አላህም መሃሪ አዛኝ ነው። وَلَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌۭ فِيمَآ أَخْطَأْتُم بِهِۦ وَلَٰكِن مَّا تَعَمَّدَتْ قُلُوبُكُمْ ۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًۭا رَّحِيمًا

"ብንረሳ" ማለት መሥራቱ ግዴታ የሆነ መልካም ሥራ በመርሳት መግደፍ ሲሆን "ብንስት" ማለት መሥራቱ ክልክል የሆነ መጥፎ ሥራ ባለማወቅ መሳሳት ነው። በተሳሳትንበት ነገር በእኛ ላይ ኃጢአት የለብንም፥ ቅሉ ግን ልባችን እያወቀው በሠራነው መጥፎ ሥራ ኃጢአት አለበት፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 2123
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ ”አላህ በኡማዬ ላይ ስህተት፣ መርሳት እና የገተደዱበትን ነገር አንስቷል”። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، عَنِ النَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ “‏ إِنَّ اللَّهَ وَضَعَ عَنْ أُمَّتِي الْخَطَأَ وَالنِّسْيَانَ وَمَا اسْتُكْرِهُوا عَلَيْهِ
ነጥብ ሁለት
"ቀውል"
“ቀውል” قَوْل የሚለው ቃል “ቀወለ” قَوَّلَ “ማለትም “ተናገረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የንግግር ክህሎት"articulate speech" ማለት ነው፥ ሰው ስሜቱን እና አሳቡ በቃላት የሚገልጽበት እና የሚያስረዳበት ጥበብ "በያን" بَيَان ይባላል፦
55፥4 መናገርን አስተማረው፡፡ عَلَّمَهُ الْبَيَانَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "መናገር" ለሚለው የገባው ቃል "በያን" بَيَان መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ሰው ከእንስሳ በተለየ መልኩ በተለያየ አገር ከሚኖሩ ሌሎች ሰዎች ጋር በስም፣ በተውላጠ-ስም፣ በገላጭ ቅጽል፣ በግስ፣ በተውሳከ ግስ፣ በመስተዋድድ፣ በመስተጻምር የሚግባባው አሏህ ቀውል የሚባል የመናገር ቅኝት እና ተውህቦ"faculty" ስለሰጠው ነው። ቋንቋ መግባቢያ ነው፥ መግባቢያ ሁሉ ቋንቋ አይደለም። እንስሳት እርስ በእርሳቸው ቢግባቡም ቋንቋ የላቸውም፥ እንስሳ በቋንቋ አይናገሩም እንዲሁ በቋንቋ አይረዱም። ሰው ግን አእምሮው ጤነኛ ከሆነ ከእናት ቋንቋው በተጨማሪ የሌላ አገር ቋንቋ ተረድቶ ማስረዳት ይችላል።

ነጥብ ሦስት
"መሥኡሉል ዐደብ"
"መሥዑል" مَسْؤُول ማለት "ተጠያቂነት" ማለት ሲሆን "ዐደብ" اَدَب‎ ማለት ደግሞ "ግብረገብ" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "መሥኡሉል ዐደብ" مَسْؤُول الاَدَب‎ ማለት "ግብረገባዊ ተጠያቂነት"moral accountability" ማለት ነው። አንድ እንስሳት ከእናቱ፣ ከእኅቱ፣ ከሴት ልጁ ጋር ተራክቦ ቢያደርግ አይጠየቅም አይቀጣም፥ ሰው ግን በሚሠራው ሥራ ይጠየቃል፦
16፥93 ትሠሩት ከነበራችሁትም ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ፡፡ وَلَتُسْأَلُنَّ عَمَّا كُنتُمْ تَعْمَلُون
102፥8 ከዚያም ከጸጋችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ። ثُمَّ لَتُسْأَلُنَّ يَوْمَئِذٍ عَنِ النَّعِيمِ

“ነዒም” نَّعِيم ማለት “ጸጋ” ማለት ሲሆን ይህ የተሰጠን ጸጋ አድርግ የተባለውን የመታዘዝዝና ያለመታዘዝ፥ አታድርግ የተባለውን የመከልከልና ያለመከልከል ነጻ ፈቃድ”free will” ነው። ሰው በሚሠራው ሰናይ ሆነ እኩይ ሥራ ግብረገባዊ ተጠያቂነት ስላለው በፍርዱ ቀን ይጠየቃል። አሏህ በሠራው እና በሚሠራው ሥራ አይጠየቅም፥ ሰዎች ግን በሚሠሩት ሥራ ይጠየቃሉ፦
21፥23 ከሚሠራው ሁሉ አይጠየቅም፡፡ እነርሱ ግን ይጠየቃሉ፡፡ لَا يُسْأَلُ عَمَّا يَفْعَلُ وَهُمْ يُسْأَلُونَ

ሰዎች በተሰጣቸው ነጻ ፈቃድ ይሠሩት የነበሩትን መልካም ነገር ይመነዳሉ፥ በተቃራኒው ይሠሩት የነበሩትን መጥፎ ነገር ይቀጣሉ፦
18፥180 “ይሠሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይመነዳሉ”፡፡ سَيُجْزَوْنَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
6፥120 “እነዚያ ኃጢአትን የሚሠሩ ይሠሩት በነበሩት ነገር በእርግጥ ይቀጣሉ”፡፡ نَّ الَّذِينَ يَكْسِبُونَ الْإِثْمَ سَيُجْزَوْنَ بِمَا كَانُوا يَقْتَرِفُونَ

አምላካችን አሏህ የሰውን ልጅ ያከበረበት ጸጋ የሚደንቅ ነው። አሏህ የሰጠንን ጸጋ በአግባብ የምንጠቀም ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሁሉም ከአሏህ ዘንድ ነው!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥78 ደግ ነገር ብታገኛቸው «ይህች ከአላህ ዘንድ ናት» ይላሉ፡፡ ክፉው ብታገኛቸው «ይህቺ ከአንተ ዘንድ ናት» ይላሉ፡፡ «ሁሉም ከአላህ ዘንድ ነው» በላቸው፡፡ وَإِن تُصِبْهُمْ حَسَنَةٌ يَقُولُوا هَـٰذِهِ مِنْ عِندِ اللَّهِ ۖ وَإِن تُصِبْهُمْ سَيِّئَةٌ يَقُولُوا هَـٰذِهِ مِنْ عِندِكَ ۚ قُلْ كُلٌّ مِّنْ عِندِ اللَّهِ

በቁርኣን "ነፍሥ" نَفْس ማለት "ራስነት"own self-hood" ማለት ሲሆን “ማንነት” ነው፥ ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት። አምላካችን አሏህ በክፉ እና በበጎ ይፈትነናል፦
21፥35 ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንፈትናችኋለን፡፡ ወደ እኛም ትመለሳላችሁ፡፡ كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَنَبْلُوكُم بِالشَّرِّ وَالْخَيْرِ فِتْنَةً ۖ وَإِلَيْنَا تُرْجَعُونَ

"እንፈትናችኋለን" ለሚለው ቃል የገባው “ነብሉኩም” نَبْلُوكُم እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። “በላእ” بَلَآء ማለት “በለወ” بَلَوَ ማለትም “ፈተነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ፈተና” ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ ለእኛ ክፉ በሆነው ሞት እና በጎ በሆነው ሕይወት ይፈትነናል፦
67፥2 ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መሆኑን "ሊፈትናችሁ" ሞትን እና ሕይወትን የፈጠረ ነው፤ እርሱም አሸናፊው መሐሪው ነው። الَّذِي خَلَقَ الْمَوْتَ وَالْحَيَاةَ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا ۚ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْغَفُورُ

“ሊፈትናችሁ” ለሚለው ቃል የገባው “ሊየብሉወኩም” لِيَبْلُوَكُمْ እንደሆነ ልብ አድርግ! ሞት እና ሕይወት ፈተና ነው፥ ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ የትም ስፍራ ብንኾን በጠነከሩ ሕንጻዎች ውስጥ ብንኾንም እንኳ ሞት ያገኘናል፦
4፥78 የትም ስፍራ ብትኾኑ በጠነከሩ ሕንጻዎች ውስጥ ብትኾኑም እንኳ ሞት ያገኛችኋል፡፡ أَيْنَمَا تَكُونُوا يُدْرِككُّمُ الْمَوْتُ وَلَوْ كُنتُمْ فِي بُرُوجٍ مُّشَيَّدَةٍ

ሰዎች ደግ ነገር የቡቃያ ዓመት እና የፍራፍሬዎች፣ የምርት፣ የልጆች ሲሳይ ወዘተ... ብታገኛቸው «ይህች ከአላህ ዘንድ ናት» ይላሉ፥ በተቃራኒው ክፉ ነገር ድርቅ፣ ረሃብ፣ የፍራፍሬዎች እና የምርት እጥረት፣ እንዲሁ ሞት ልጆቻቸውን እና እንስሳቸው ሲነካባቸው፦ «ይህቺ ከአንተ ዘንድ ናት» ይላሉ፡፡ ቅሉ ግን ሁሉም ማለትም ክፉውም ነገር እና ደጉም ነገር ከአላህ ዘንድ ነው፦
4፥78 ደግ ነገር ብታገኛቸው «ይህች ከአላህ ዘንድ ናት» ይላሉ፡፡ ክፉው ብታገኛቸው «ይህቺ ከአንተ ዘንድ ናት» ይላሉ፡፡ «ሁሉም ከአላህ ዘንድ ነው» በላቸው፡፡ وَإِن تُصِبْهُمْ حَسَنَةٌ يَقُولُوا هَـٰذِهِ مِنْ عِندِ اللَّهِ ۖ وَإِن تُصِبْهُمْ سَيِّئَةٌ يَقُولُوا هَـٰذِهِ مِنْ عِندِكَ ۚ قُلْ كُلٌّ مِّنْ عِندِ اللَّهِ

"ሁሉም ነገር ከአሏህ ዘንድ ነው" ማለት “ሙጅመል” مُجّمَل ማለትም "ጥቅል" ጉዳይ ነው፥ ሁሉም ከአሏህ ዘንድ የተቀደረ እና የማንጠየቅበት ጉዳይ ነው። እዚህ አንቀጽ ላይ "ክፉ" የተባለው "ተፍጥሮአዊ እኩይ"natural evil" ነው። ቅሉ ግን ከደግ ነገር የሚያገኘን ከአሏህ ነው፥ ከክፉ ነገር የሚያገኘን ከራሳችን ነው፦
4፥79 ከደግ ነገር የሚያገኝህ ከአላህ ነው፥ ከክፉ ነገር የሚያገኝህ ከራስህ ነው፡፡ مَّا أَصَابَكَ مِنْ حَسَنَةٍ فَمِنَ اللَّهِ ۖ وَمَا أَصَابَكَ مِن سَيِّئَةٍ فَمِن نَّفْسِكَ

ደግ ነገር ጸጋ፣ ሞገስ፣ ደግነት እና ምሕረት ሲሆን የሚያገኝህ ከአሏህ ነው። "ሠዪኣህ" سَيِّئَة ማለት "መጥፎ" "ክፉ" "እኩይ" ማለት ሲሆን "ሠዪኣህ" سَيِّئَة በሚለው መነሻ ላይ "ሚን" مِن የሚለው መስተዋድድ "ከ" ማለት ሲሆን ከፊል እና አንጻራዊ ሆኖ የመጣ “ሙፈሰል” مُفَصَّل ማለትም "ተናጥል" ነው። ቁርአኑ ያለው፦ "ክፉ ነገር የሚያገኝህ ከራስህ ነው" ሳይሆን "ከ-ክፉ ነገር የሚያገኝህ ከራስህ ነው" ነው፥ እዚህ አንቀጽ ላይ "ክፉ" የተባለው "ግብረገባዊ እኩይ"moral evil" ነው። እኛን የሚያስጠይቅ ክፉ ነገር ከራሳችን ሲሆን ከክፉ ነገር የሚመደብ ነው፦
42፥30 "ከ"-መከራም ማንኛውም ያገኛችሁ ነገር እጆቻችሁ በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት ነው፡፡ ከብዙውም ይቅር ይላል፡፡ وَمَا أَصَابَكُم مِّن مُّصِيبَةٍ فَبِمَا كَسَبَتْ أَيْدِيكُمْ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ
30፥41 የሰዎች እጆች በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት የዚያን የሠሩትን ከፊሉን ያቀምሳቸው ዘንድ መከራው በየብስ እና በባሕር ተሰራጨ፡፡ እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና፡፡ ظَهَرَ الْفَسَادُ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ بِمَا كَسَبَتْ أَيْدِي النَّاسِ لِيُذِيقَهُم بَعْضَ الَّذِي عَمِلُوا لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

“ኃጢኣት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ፈሣድ” ሲሆን “ፈሣድ” فَسَاد ማለት “ጥፋት” “ብክለት” “ብልሽት” ማለት ነው፥ ይህንን ድርጊት የሚተገብሩ ግለሰቦች ደግሞ “ሙፍሢድ” مُفْسِد ማለትም “አጥፊ” “አበላሺ” “በካይ” ይባላሉ። ሙሲባህ ሳይሆን “ከ”ሙሲባህ ሰዎችን የሚያገኘው የሰዎች እጆች በሠሩት ፈሣድ ነው፥ ለምሳሌ በየብስና በባሕር ተሰራጭቶ የምናየው ጦርነት የሙፍሢዱን ጦስ ነው።
ይህ "የእኩይ ጣጣ"Problem of evil" ጥያቄ የሥነ-አመክንዮን፣ የሥነ-ልቦናን፣ የሥነ-ኑባሬን፣ የሥነ-ምግባርን እና የሥነ-መለኮትን ሙግት ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ጥያቄ ነው። የሥነ-እኩይ ጥናት"ponerology" እራሱን የቻለ ሰፊ እና ጥልቅ ጥናት ነውና ሁላችንም እናጥና!

“አሏሁ አዕለም” اَللّٰهُ أَعْلَم

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አሏህ አይረሳም!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

20፥52 ሙሳም፦ «ዕውቀትዋ እጌታዬ ዘንድ በመጽሐፍ የተመዘገበ ነው፡፡ ጌታዬ አይሳሳትም አይረሳምም» አለው፡፡ قَالَ عِلْمُهَا عِندَ رَبِّى فِى كِتَٰبٍۢ ۖ لَّا يَضِلُّ رَبِّى وَلَا يَنسَى

አምላካችን አሏህ ሁሉን ዐዋቂ ነው፥ ወደ ኃላው የተደረጉት ነገሮች ሁሉ አይረሳም፦
20፥52 ሙሳም፦ «ዕውቀትዋ እጌታዬ ዘንድ በመጽሐፍ የተመዘገበ ነው፡፡ ጌታዬ አይሳሳትም አይረሳምም» አለው፡፡ قَالَ عِلْمُهَا عِندَ رَبِّى فِى كِتَٰبٍۢ ۖ لَّا يَضِلُّ رَبِّى وَلَا يَنسَى

ባለማወቅ የሚሠራ መጥፎ ሥራ “ስህተት” ሲባል በመርሳት የማይሠራ መልካም ሥራ “ግድፈት” ይባላል፥ አሏህ ግን አይሳሳትም አይረሳም። የመጀመሪያይቱ ዘመናት ሕዝቦች ኹኔታ አሏህ ረሺ አይደለም፦
20፥51 ፈርዖንም «የመጀመሪያይቱ ዘመናት ሕዝቦች ኹኔታ ምንድን ነው» አለ፡፡ قَالَ فَمَا بَالُ الْقُرُونِ الْأُولَىٰ
19፥64 ጂብሪል አለ፦ "በጌታህም ትእዛዝ እንጅ አንወርድም፡፡ በፊታችን ያለው፣ በኋላችንም ያለው በዚህም መካከል ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ጌታህም ረሺ አይደለም"፡፡ وَمَا نَتَنَزَّلُ إِلَّا بِأَمْرِ رَبِّكَ ۖ لَهُۥ مَا بَيْنَ أَيْدِينَا وَمَا خَلْفَنَا وَمَا بَيْنَ ذَٰلِكَ ۚ وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِيًّۭا

አምላካችን አሏህ ሰዎችን እንደሚገናኝ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ወሕይን ያወርዳል፥ በዚህ ወሕይ የመገናኛውን ቀን ያጠነቅቅ ዘንድ ነቢይ ይልካል፦
40፥15 እርሱ ደረጃዎችን ከፍ አድራጊ የዐርሹ ባለቤት ነው፡፡ የመገናኛውን ቀን ያጠነቅቅ ዘንድ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ከትዕዛዙ መንፈስን ያወርዳል፡፡ رَفِيعُ ٱلدَّرَجَٰتِ ذُو ٱلْعَرْشِ يُلْقِى ٱلرُّوحَ مِنْ أَمْرِهِۦ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦ لِيُنذِرَ يَوْمَ ٱلتَّلَاقِ

"የመገናኛውን ቀን ያጠነቅቅ ዘንድ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይስመርበት! ይህንን ቀን የፍርዱ ቀን ሲሆን በዚህ ቀን ሰዎች አሏህ ተገናኝተው በሥራቸው ይተሳሰባቸዋል። ይህንን ቀን ሆን ብሎ የረሳ ማለትም የተወ ልክ እርሱ እንደረሳው አሏህ በዚያን ቀን ለጀነት አያስታውሰውም ይረሳዋል፦
45፥34 «ይህንንም ቀናችሁን መገናኘትን እንደ ረሳችሁ ዛሬ እንረሳችኋለን፡፡ መኖሪያችሁም እሳት ናት፡፡ ለእናንተም ከረዳቶች ምንም የላችሁም» ይባላል፡፡ وَقِيلَ الْيَوْمَ نَنْسَاكُمْ كَمَا نَسِيتُمْ لِقَاءَ يَوْمِكُمْ هَٰذَا وَمَأْوَاكُمُ النَّارُ وَمَا لَكُمْ مِنْ نَاصِرِينَ
7፥51 «እነዚያ ሃይማኖታቸውን መሳለቂያና መጫወቻ አድርገው የያዙ የቅርቢቱም ሕይወት ያታለለቻቸው ይህንን ቀናቸውን መገናኘትን እንደ እረሱ በተአምራታችንም ይክዱ እንደነበሩ ዛሬ እንረሳቸዋልን፡፡ الَّذِينَ اتَّخَذُوا دِينَهُمْ لَهْوًا وَلَعِبًا وَغَرَّتْهُمُ الْحَيَاةُ الدُّنْيَا ۚ فَالْيَوْمَ نَنْسَاهُمْ كَمَا نَسُوا لِقَاءَ يَوْمِهِمْ هَٰذَا وَمَا كَانُوا بِآيَاتِنَا يَجْحَدُونَ

ሐቅን አስተባባዮች ይህንን ቀን የረሱት በአእምሮ ዝንጉነት ሳይሆን ሆን ብለው በቸልተኝነትን ነው፥ መቼም አንድ አስተባባይ የመገናኛውን ቀን ተነግሮት ረሳ ማለት ተወ ማለት እንጂ በዐቅሉ ዘነጋ ማለት እንዳልሆነ ቅቡል ነው። ምክንያቱም ዐቅልን ስቶ መዘንጋት አያስጠይቅምና፥ ግን ሆን ብሎ በማስተባበል መተው ያስጠይቃል። አስተባባዮች ሆን ብለው የመገናኛውን ቀን እንደረሱት እንደዚሁ አሏህም የዚያን ቀን ይረሳቸዋል፥ “ከማ” كَمَا ማለትም “እንደ” የሚል መስተዋድድ ሊሰመርበት የሚገባ ነጥብ ነው። በተጨማሪ "ኒሥያን" نِسْيَان የሚለው ቃል "ነሢየ" نَسِيَ‎ ማለትም "ረሳ" "ተወ" "ችላ አለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ተርክ" تَرْك ማለትም "መተው" ማለት ነው፥ ኢማም ቁርጡቢይ የፈሠሩት በዚህ ስሌት ነው፦
ተፍሢሩል ቁርጡቢይ 7፥51
"ዛሬ እንረሳቸዋልን" ማለት “በእሳት እንተዋቸዋለን” ማለት ሲሆን “ይህንን ቀናቸውን መገናኘትን እንደ እንደረሱት” ማለት ደግሞ “ይህንን ሥራቸውን እንደ እንደተዉት እና እንዳስተባበሉት” ማለት ነው። فَالْيَوْمَ نَنْسَاهُمْ أي نتركهم في النار كَمَا نَسُوا لِقَاءَ يَوْمِهِمْ هَذَا أي تركوا العمل به وكذبوا به
ቁርኣን ላይ "መርሳት" የሚለው ቃል "መተው" በሚል ተለዋዋጭ ቃል ብዙ ቦታ መጥቷል፦
32፥14 «ይህንንም ቀናችሁን መገናኘትን "በመርሳታችሁ" ምክንያት ቅጣትን ቅመሱ! እኛ "ተውናችሁ"፡፡ ትሠሩት በነበራችሁትም ጥፋት ዘውታሪን ቅጣት ቅመሱ” ይባላሉ ፡፡ فَذُوقُوا بِمَا نَسِيتُمْ لِقَاءَ يَوْمِكُمْ هَٰذَا إِنَّا نَسِينَاكُمْ ۖ وَذُوقُوا عَذَابَ الْخُلْدِ بِمَا كُنْتُمْ تَعْمَلُونَ
20፥126 ነገሩ እንደዚሁ ነው፡፡ «ታምራታችን መጣችልህ "ተውካትም"፡፡ እንደዚሁም ዛሬ "ትተዋለህ"» ይለዋል፡፡ قَالَ كَذَٰلِكَ أَتَتْكَ ءَايَٰتُنَا فَنَسِيتَهَا ۖ وَكَذَٰلِكَ ٱلْيَوْمَ تُنسَىٰ
9፥67 አላህን ረሱ ስለዚህ እርሱ "ተዋቸው"፡፡ መናፍቃን አመጸኞቹ እነርሱ ናቸው፡፡ نَسُوا اللَّهَ فَنَسِيَهُمْ ۗ إِنَّ الْمُنَافِقِينَ هُمُ الْفَاسِقُونَ
19፥72 ከዚያም እነዚያን የተጠነቀቁትን እናድናለን፡፡ አመጸኞቹንም የተንበረከኩ ኾነው በውስጧ "እንተዋቸዋለን"፡፡ ثُمَّ نُنَجِّي الَّذِينَ اتَّقَوا وَّنَذَرُ الظَّالِمِينَ فِيهَا جِثِيًّا

እዚህ ድረስ ሥሩ የጠለቀ ግንዱ የዘለቀ ኢሥላማዊ ምላሽ ከሰጠን ዘንዳ "በለስ ቀናን" ብላችሁ ቁርኣንን ካነወራችሁ እንግዲያውስ በባብይል እራሱ ፈጣሪ እንደሚረሳ ይናገራል፦
ሆሴዕ 4፥6 የአምላክህንም ሕግ "ረስተሃልና" እኔ ደግሞ ልጆችህን "እረሳለሁ"።
ኤርምያስ 23፥39 የያህዌህ ሸክም ብላችኋልና ስለዚህ፥ እነሆ፥ ፈጽሜ "እረሳችኋለሁ"።

ከላይ ያለው የባይብል ተመሳሳይ ነጥብ አፍጦና አፋጦ፤ አግጦና አንጋጦ ሲመጣ ቆሌ ተገፎ እና ቆሽት አሮ፦ "ሰማይ ተንዶ ሊናጫነኝ ነው፥ ምድር ተከፍቶ ሊውጠኝ ነው" እንደምትሉ እሙን ነው። ነቢያትም ቢሆን ፈጣሪ እንደሚረሳ ይናገራሉ፦
ሰቆቃው ኤርምያስ 5፥20 ስለ ምን ለዘላለም "ትረሳናለህ? ስለ ምንስ ለረጅም ዘመን ትተወናለህ?
መዝሙር 13፥1 አቤቱ፥ እስከ መቼ ፈጽመህ "ትረሳኛለህ? እስከ መቼስ ፊትህን ከእኔ ትሰውራለህ?
መዝሙር 42፥9 ያህዌህን፡— አንተ መጠጊያዬ ነህ፤ ለምን "ረሳኸኝ? ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን አዝኜ እመላለሳለሁ? እለዋለሁ።
መዝሙር 44፥24 ለምንስ ፊትህን ትሰውራለህ? መከራችንንና ችግራችንንስ ለምን "ትረሳለህ"? ማሽቋለጥ እና ማሽቃበጥ፦ "የእናቴ ቀሚስ አደናቀፈኝ" እንደሚያስብል ሳይታለም የተፈታ ነው፥ በሰፈው ቁና መሰፈሩ በራሱ የቀረበውን የሐሠት ክስ"false allegation" የእንቧይ ካብ አድርጎታል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሃይማኖት ያድናል!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥19 አላህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት ኢሥላም ብቻ ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ

ፕሮቴስታንት፦ "እምነት እንጂ ሃይማኖት አያድንም" የሚል መፈክር አላቸው፥ ከፕሮቴስታንት የተሃድሶ አምስቱ የብቸኝነት መፈክር አንዱ "መዳን በእምነት ብቻ"sola fide" የሚል ነው። እኛም እንደ ሙሥሊምነታችን እውነት ሃይማኖት አያድንምን? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ኢንሻሏህ እንሰጣለን።
"ዲን" دِين የሚለው ቃል "ዳነ" دَانَ ማለትም "ሃይመነ" "ደነገገ" "ፈረደ" "በየነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ሃይማኖት" "ፍትሕ" "ፍርድ" "ሕግ" "መርሕ"doctrine" ማለት ነው፦
2፥256 "በሃይማኖት" ማስገደድ የለም፡፡ لَا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ
1፥4 "የፍርዱ" ቀን ባለቤት ለኾነው፡፡ مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ
12፥76 አላህ ባልሻ ኖሮ በንጉሡ "ሕግ" ወንድሙን ሊይዝ አይገባውም ነበር፡፡ كَانَ لِيَأْخُذَ أَخَاهُ فِي دِينِ الْمَلِكِ إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّهُ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ሃይማኖት" "ፍርድ" "ሕግ" ለሚለው የገባው ቃል "ዲን" دِين መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፥ ዲን የእምነት እሴት፣ የእምነት አንቀጽ እና የሥነ-ምግባር መርሕ ነው። ዲን ምእመናንን ወንድማማች የሚያደርግ መርሕ ነው፦
9፥11 ቢጸጸቱም፣ ሶላትንም ቢሰግዱ፣ ዘካንም ቢሰጡ "የሃይማኖት ወንድሞቻችሁ" ናቸው፡፡ فَإِن تَابُوا وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَآتَوُا الزَّكَاةَ فَإِخْوَانُكُمْ فِي الدِّينِ
49፥10 "ምእመናን ወንድማማቾች ናቸው"፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ

"አኽ" أَخ ማለት "ወንድም" ማለት ሲሆን "ኡኽት" أُخْت ማለት ደግሞ "እኅት" ማለት ነው፥ "ኢኽዋህ" إِخْوَة ወይም "ኢኽዋን" إِخْوَان ለሁለቱም ብዜት ሆኖ የሚያገለግል ቃል ነው። ዲን ማለት የእምነት መርሕ መሆኑ ካየን ዘንዳ ይህም ዲን ዲኑል ኢሥላም ነው፦
3፥19 አላህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት ኢሥላም ብቻ ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ
3፥85 ከኢሥላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይ የለውም፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፡፡ وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ الْإِسْلَامِ دِينًا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِي الْآخِرَةِ مِنَ الْخَاسِرِينَ

"ኢሥላም" إِسْلَام የሚለው ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ‎ ማለትም "ታዘዘ" "ተገዛ" "አመለከ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መታዘዝ" "መገዛት" "ማምለክ" ማለት ነው፥ አሏህ ዘንድ ከዲኑል ኢሥላም ሌላ ሃይማኖትን ተቀባትነት የሌለው እና በመጨረሻይቱ ዓለም የሚያከስር ነው። አምላካችን አሏህ ለኢብራሂም፦ "አሥሊም" أَسْلِمْ ሲለው እርሱም፦ "አሥለምቱ" أَسْلَمْتُ አለ፦
2፥131 ጌታው ለእርሱ ”ታዘዝ” ባለው ጊዜ መረጠው፡፡ ለዓለማት ጌታ ”ታዘዝኩ” አለ፡፡ إِذْ قَالَ لَهُۥ رَبُّهُۥٓ أَسْلِمْ ۖ قَالَ أَسْلَمْتُ لِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
22፥34 አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ "ታዘዙ"! ለአላህ ተዋራጆችንም አብስራቸው፡፡ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا ۗ وَبَشِّرِ الْمُخْبِتِينَ

"አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው" የሚለው ኃይለ-ቃል ይስመርበት! በቀጣይ "ታዘዙ" ለሚለው ቃል የተቀመጠው "አሥሊሙ" أَسْلِمُوا ነው፥ ስለዚህ አንዱን አምላክ በብቸኝነት መታዘዝ፣ መገዛት፣ ማምለክ "ኢሥላም" ይባላል።
"ኢማን" إِيمَٰن የሚለው ቃል "አሚነ" أَمِنَ ማለትም "አመነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "እምነት" ማለት ነው፥ የምናምነው ደግሞ ዲናችን ላይ የተቀመጠውን መርሕ ነው እንጂ ጣዖትን እኮ እንክዳለን፦
2፥256 “በጣዖትም የሚክድ እና በአላህ የሚያምን ሰው ለእርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ”፡፡ فَمَن يَكْفُرْ بِالطَّاغُوتِ وَيُؤْمِن بِاللَّهِ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ لَا انفِصَامَ لَهَا

የምናምነው የምናውቀውን ነው፥ የምናውቀው ደግሞ ከአሏህ ዘንድ የመጣውን መርሕ ነው። "ኢማን እንጂ ዲን አያድንም" የሚሉ ፕሮቴስታንቶች ሃይማኖት የእምነት መርሕ መሆኑን በቅጡ ስላልተረዱት እና የሚያምኑበት መርሕ ስለሌላቸው ነው፥ ይህ መረን አልባ ልቅነት ነው። ሃይማኖት ሥርወ-እምነት ነው፥ "ዶግማ" δόγμα ማለት "አንቀጸ-እምነት"creed" ማለት ሲሆን ያለ ዶግማ እምነት የማይታሰብ ነው። ስለዚህ ዲኑል ኢሥላም ድብን አድርጎ ያድናል፦
3፥103 የአላህን ገመድ ሁላችሁም ያዙ! አትለያዩም። ጠበኞችም በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋ አስታውሱ! በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፥ በጸጋውም ወንድማማቾች ኾናችሁ፡፡ በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ ነበራችሁ፥ ከእርስዋም አዳናችሁ፡፡ እንደዚሁ ትመሩ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾቹን ያብራራል፡፡ وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا ۚ وَاذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ كُنتُمْ أَعْدَاءً فَأَلَّفَ بَيْنَ قُلُوبِكُمْ فَأَصْبَحْتُم بِنِعْمَتِهِ إِخْوَانًا وَكُنتُمْ عَلَىٰ شَفَا حُفْرَةٍ مِّنَ النَّارِ فَأَنقَذَكُم مِّنْهَا ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمْ آيَاتِهِ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ

ከእሳት ጉድጓድ ተንጠልጥሎ ለመውጣት የሚያስችል ብቸኛው የአሏህ ገመድ ዲኑል ኢሥላም ብቻ ነው፥ ከእሳት ጉድጓድ አፋፍ ላይ ሳለን አድኖ በሃይማኖት ወንድማማቾች አርጎናል። ሱመ አል-ሓምዱ ሊሏህ!
አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
"ማ" ሐርፍ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

11፥1 አሊፍ ላም ራ! ይህ ቁርኣን አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ የተወረደ ነው፡፡ الر ۚ كِتَابٌ أُحْكِمَتْ آيَاتُهُ ثُمَّ فُصِّلَتْ مِن لَّدُنْ حَكِيمٍ خَبِيرٍ

የቁርኣንን ሑሩፉል ሙፍረዳት በማርባት እና በማባዛት "ሶርፍ" صَّرْف ጉልኅ ሚና ሲኖረው "ሉጋህ" لُّغَة ደግሞ የቁርኣንን ሑሩፉል ሙፍረዳት በማብራራት ጉልኅ ሚና አለው፥ የቁርኣንን ሑሩፉል ሙረከባት በዓረፍተ ነገር በማዋቀር ረገድ "ነሕው" نَحْو ጉልኅ ሚና ሲኖረው "በላጋህ" بَلَاغَة ደግሞ የቁርኣንን ሑሩፉል ሙረከባት የዓረፍተ ነገሩን መልእክት በመግለጽ ጉልኅ ሚና አለው። ቅዱስ ቁርኣን አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው፥ ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው አሏህ ዘንድ የተወረደ ነው፦
11፥1 አሊፍ ላም ራ! ይህ ቁርኣን አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ የተወረደ ነው፡፡ الر ۚ كِتَابٌ أُحْكِمَتْ آيَاتُهُ ثُمَّ فُصِّلَتْ مِن لَّدُنْ حَكِيمٍ خَبِيرٍ

ከቁርኣን አንቀጾቹ በጥንካሬ ከተሰካኩ ሐርፍ አንዷ "ማ" مَا ናት፥ በቁርኣን ውስጥ ማ ሙንፈሲል እና ሙተሲል ሆና ትመጣለች፥ ስለ እርሷ እስቲ እንይ፦

A. "ሙንፈሲል"
"ሙንፈሲል" مُنْفَصِل ማለት "የተነጠለ" ማለት ሲሆን "ማ" مَا የሚለው ሐርፍ በኢሥሙል መውሱል፣ በሐርፉ አን-ነፍይ እና በኢስሙል ኢሥቲፍሃም ውስጥ ሙንፈሰል ሆና ትመጣለች፥ ለምሳሌ፦

ነጥብ አንድ
"ማ ኢሥሙል መውሱል"
"ኢሥሙል መውሱል" اِسْم المَوْصُول ማለት "አንፃራዊ ተውላጠ-ስም"relative pronoun" ማለት ሲሆን ከኢሥሙል መውሱል አንዱ "ማ" مَا ማለት "ምንድን" ማለት ሲሆን "ምንነት" ላለው ኑባሬ የምጠቀምበት አንጻራዊ ተውላጠ-ስም ነው፦
91፥5 "በሰማይቱም በገነባትም ጌታ"። وَالسَّمَاءِ وَمَا بَنَاهَا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ማ" مَا የሚል አንጻራዊ ተውላጠ-ስም ለአሏህ ይጠቀማል። "ዛት" ذَات ማለት "ምንነት"essence" ማለት ሲሆን “ሸኽስ” شَخْص ማለት ደግሞ “ማንነት”person” ማለት ነው።

ነጥብ ሁለት
"ማ ሐርፉ አን-ነፍይ"
"ሐርፉ አን-ነፍይ" حَرْف النَفْي ማለት "አፍራሽ መስተዋድድ" ማለት ሲሆን ከሐርፉ አን-ነፍይ መካከል "ማ" مَا ማለት "አይደለም" ማለት ነው፦
81፥22 ነቢያችሁም በፍጹም ዕብድ አይደለም፡፡ وَمَا صَاحِبُكُم بِمَجْنُونٍ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ማ" مَا የሚል አፍራሽ መስተዋድድ "ላ" لَا የሚለውን ያሁኑ ጊዜ አፍራሽ እና "ለም" لَمْ የሚለውን አላፊ ጊዜ አፍራሽ ተክቶ የሚገባ ተለዋዋጭ መስተዋድ ነው።

ነጥብ ሦስት
"ማ ኢስሙል ኢሥቲፍሃም"
"ኢስሙል ኢሥቲፍሃም" اِسْم الاِسْتِفْهَام ማለት "መጠይቅ ተውላጠ-ስም"interrogative pronoun" ማለት ሲሆን ከሐርፉ አን-ነፍይ መካከል "ማ" مَا ማለት "ምንድን" ማለት ነው፦
51፥31 «እናንተ መልክተኞች ሆይ! ታዲያ ነገራችሁ ምንድን ነው?» አላቸው፡፡ قَالَ فَمَا خَطْبُكُمْ أَيُّهَا الْمُرْسَلُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ማ" مَا የሚል ተውላጠ ስም መጠይቅ ተውላጠ-ስም ነው።

ነጥብ አራት
"ማ ሐርፉል መስደሪይ"
"ሐርፉል መስደሪይ" حَرْف المَصْدَرِي ማለት "ተገዢ መስተጻምር"subordinating conjunction" ማለት ሲሆን ከተገዢ መስተጻምር አንዱ "ማ" مَا ማለት "ምንድን" ማለት ሲሆን ዐማርኛው ላይ ያልሰፈረ ቅሉ ግን ዐረቢኛው ላይ እና እንግሊዝኛው ላይ የተቀመጠ ተገዢ መስተጻምር ነው፦
2፥181 ኑዛዜውን ከሰማውም በኋላ የለወጠው ሰው ኃጢአቱ በነዚያ በሚለውጡት ላይ ብቻ ነው፡፡ አላህ ሰሚ ዐዋቂ ነውና፡፡ فَمَن بَدَّلَهُ بَعْدَ مَا سَمِعَهُ فَإِنَّمَا إِثْمُهُ عَلَى الَّذِينَ يُبَدِّلُونَهُ ۚ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

B. "ሙተሲል"
"ሙተሲል" مُتَّصِل ማለት "የተያያዘ" ማለት ሲሆን "ማ" مَا የሚለው ሐርፍ በተለያዩ መስተዋድዶች ጋር ሙተሲል ሆና ትመጣለች፦ ለምሳሌ፦

ነጥብ አንድ
"ቢማ"
"ቢ" بِ ማለት "በ" ማለት ሲሆን "ማ" مَا በ "ቢ" ተያይዛ ስትመጣ "ቢመ" بِمَ በሚል ቃል መጥቷል፥ ትርጉሙም "በምን" ማለት ነው፦
27፥35 «እኔም ወደእነርሱ ገጸ በረከትን የምልክና መልክተኞቹ በምን እንደሚመለሱ የምጠባበቅ ነኝ፡፡» وَإِنِّي مُرْسِلَةٌ إِلَيْهِم بِهَدِيَّةٍ فَنَاظِرَةٌ بِمَ يَرْجِعُ الْمُرْسَلُونَ

በዚሁ አወቃቀር የልግስናን "ምንነት" ለማመላከት "ቢማ" بِمَا በሚል መጥቷል፦
2817 «ጌታዬ ሆይ! በእኔ ላይ በመለገስህ ይሁንብኝ ከስህተቴ እጸጸታለሁ፤ ለአመጸኞችም ፈጽሞ ረዳት አልሆንም አለ፡፡ قَالَ رَبِّ بِمَا أَنْعَمْتَ عَلَيَّ فَلَنْ أَكُونَ ظَهِيرًا لِّلْمُجْرِمِينَ

ነጥብ ሁለት
"አማ"
"አን" عَن ማለት "ስለ" ማለት ሲሆን "ማ" مَا መነሻ ቅጥያ ላይ "ኑን" ن ትዋጥና "ማ" ሐርፍ ከ "አ" ጋር ተያይዛ ስትመጣ "አመ" عَمَّ በሚል ቃል መጥቷል፥ ትርጉሙም "ስለ ምን" ማለት ነው፦
78፥1 "ስለ ምን" ነገር ይጠያየቃሉ? عَمَّ يَتَسَاءَلُونَ

በዚሁ አወቃቀር ስለ ቅጥፈት "ምንነት" ለማመላከት "ቢማ" بِمَا በሚል መጥቷል፦
29፥13 ሸክሞቻቸውንና ከሸክሞቻቸው ጋር ሌሎች ሸክሞችንም በእርግጥ ይሸከማሉ፡፡ በትንሣኤም ቀን ስለ ሚቀጥፉት በእርግጥ ይጠየቃሉ፡፡ وَلَيَحْمِلُنَّ أَثْقَالَهُمْ وَأَثْقَالًا مَّعَ أَثْقَالِهِمْ ۖ وَلَيُسْأَلُنَّ يَوْمَ الْقِيَامَةِ عَمَّا كَانُوا يَفْتَرُونَ

ነጥብ ሦስት
"ሚማ"
"ሚን" مِن ማለት "ከ" ማለት ሲሆን "ማ" مَا መነሻ ቅጥያ ላይ "ኑን" ن ትዋጥና "ማ" ሐርፍ ከ "ሚ" ጋር ተያይዛ ስትመጣ "ሚመ" مِمَّ በሚል ቃል መጥቷል፥ ትርጉሙም "ከምን" ማለት ነው፦
86፥5 ሰውም ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት!፡፡ فَلْيَنظُرِ الْإِنسَانُ مِمَّ خُلِقَ

በዚሁ አወቃቀር የምርኮን "ምንነት" ለማመላከት "ሚማ" مِمَّا በሚል መጥቷል፦
8፥69 ከጠላት ከማረችሁትም ሀብት የተፈቀደ መልካም ሲኾን ብሉ። አላህንም ፍሩ! አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَكُلُوا مِمَّا غَنِمْتُمْ حَلَالًا طَيِّبًا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

ጊዜ ስለማይበቃ እንጂ ቁርኣንን ለሚያጠና ተማሪ "ፊማ" "ከማ" "ሊማ" "ኢንነማ" "አንነማ" "ከአንማ" "ኩለማ" "አይነማ" "ኒዒማ" "ቢእሠማ" "ፈማ" "አማ" "ኢማ" የሚሉትን ቃላት ማስተንተን እና መተንተን ይችላል። አሏህ የቁርኣንን አንቀጽ ከሚያስተነትኑ እና ከሚተነትኑ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አጋንንት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

15፥27 ጃንንም ከሰው በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው፡፡ وَالْجَانَّ خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ مِن نَّارِ السَّمُومِ

“ጂኒ” جِنِّيّ ወይም “ጂኒይ” جِنِّيّ የሚለው ቃል “ጀንነ” جَنَّ ማለትም “ሰወረ” ወይም “ደበቀ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ስውር” ወይም “ድብቅ” ማለት ነው፥ “ጂን” جِنّ ደግሞ የጂኒ ብዙ ቁጥር ነው። ጂኒዎች የተፈጠሩት ከሰው በፊት ነው፥ ሰው የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ዐፈር እንደሆነ ሁሉ፣ መልአክ የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ብርሃን እንደሆነ ሁሉ፣ ጂን የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ደግሞ እሳት ነው፦
15፥27 ጃንንም ከሰው በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው፡፡ وَالْجَانَّ خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ مِن نَّارِ السَّمُومِ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 55, ሐዲስ 78
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”መላእክት ከብርሃን ተፈጥረዋል፣ አጅ-ጃን ከእሳት ነበልባል ተፈጥሯል፣ ኣደም ለእናንተ እንደተገለጸላችሁ ከሚጭለቀለቅ ሸክላ ተፈጥሯል”፡፡ عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم‏ خُلِقَتِ الْمَلاَئِكَةُ مِنْ نُورٍ وَخُلِقَ الْجَانُّ مِنْ مَارِجٍ مِنْ نَارٍ وَخُلِقَ آدَمُ مِمَّا وُصِفَ لَكُمْ ‏.‏

በነጠላ “ጃን” جَانّ በብዜት “ጂናን” جِنَّان ወይም “ጀዋን” جَوَانّ ከሰው በፊት ከእሳት የተፈጠሩት ፍጥረታት ናቸው። እዚህ ሐዲስ ላይ መላእክት፣ ጃን እና አደምን ለመለየት ሁለት ጊዜ “ወ” وَ ማለትም “እና” የሚል መስተዋድድ መጠቀሙ በራሱ መላእክት እና ጂን ሁለት የተለያዩ ፍጥረታት እንደሆኑ ቁልጭ አርጎ ያሳያል። መላእክት የተፈጠሩበት ንጥረ-ነገር ብቻ ሳይሆን ባሕርያቸውም ይለያል፥ መላእክት ፆታ የላቸውም፦
43፥19 ”መላእክትንም እነርሱ የአልረሕማን ባሮች የኾኑትን ሴቶች አደረጉ”፡፡ ሲፈጠሩ ነበሩን? መመስከራቸው በእርግጥ ትጻፋለች፡፡ ይጠየቃሉም፡፡ وَجَعَلُوا الْمَلَائِكَةَ الَّذِينَ هُمْ عِبَادُ الرَّحْمَـٰنِ إِنَاثًا ۚ أَشَهِدُوا خَلْقَهُمْ ۚ سَتُكْتَبُ شَهَادَتُهُمْ وَيُسْأَلُونَ
37፥150 ወይስ እኛ እነርሱ የተጣዱ ሆነው መላእክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን? أَمْ خَلَقْنَا الْمَلَائِكَةَ إِنَاثًا وَهُمْ شَاهِدُونَ

ከመላእክት መካከል ሴቶች ቢኖሩ ኖሮ ቁሬሾች፦ “መላእክት ሴቶች ናቸው” ማለታቸውን አይቃወምም ነበር። አሏህ መላእክትን ሴቶች አድርጎ አልፈጠረም፦ ጂኒዎች ግን ፆታ አላቸው፥ ዝርያ ስላላቸው ተራብተው ወንድም ሴትም ናቸው፦
18፥50 ”እርሱን እና ዘሮቹን እነርሱ ለእናንተ ጠላቶች ሲኾኑ ከእኔ ላይ ረዳቶች አድርጋችሁ ትይዛላችሁን? ለበዳዮች ልዋጭነቱ ከፋ! أَفَتَتَّخِذُونَهُ وَذُرِّيَّتَهُ أَوْلِيَاءَ مِن دُونِي وَهُمْ لَكُمْ عَدُوٌّ ۚ بِئْسَ لِلظَّالِمِينَ بَدَلًا
72፥6 ‹እነሆም ”ከሰዎች የኾኑ ወንዶች በጋኔን ወንዶች ይጠበቁ ነበሩ”፡፡ ኩራትንም ጨመሩዋቸው፡፡› وَأَنَّهُ كَانَ رِجَالٌ مِّنَ الْإِنسِ يَعُوذُونَ بِرِجَالٍ مِّنَ الْجِنِّ فَزَادُوهُمْ رَهَقًا
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 312
ዘይድ ኢብኑ አርቀም እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “ቆሻሻ ቦታዎች በሰይጣናት ይጎበኛሉ፤ ከእናንተም ወደዚያ ሲገባ፦ *”አላህ ሆይ! ከወንድ እና ከሴት ሰይጣናት በአንተ እጠበቃለው”* ይበል። عَنْ زَيْدِ بْنِ أَرْقَمَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ إِنَّ هَذِهِ الْحُشُوشَ مُحْتَضَرَةٌ فَإِذَا دَخَلَ أَحَدُكُمْ فَلْيَقُلِ اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْخُبُثِ وَالْخَبَائِثِ ‏”‏ ‏.‏

ይህንን ትምህርት ለማሽሟጠጥ ሲሞክሩ በድርሳነ ሚካኤል ላይ አጋንንት የሚጋቡ፣ የሚዋለዱ እና የሚሞቱ ፍጡራን መሆኑ በግልጽ ተቀምጧል፦
ድርሳነ ሚካኤል ምዕራፍ 5 ቁጥር 19 ዘውርኃ ጥር፦ "ወቦ አጋንንት እለ ቦሙ ሥጋ እለ ይነብሩ ውስተ የብስ ወውስተ ማያት፥ ወእሙንቱስ ይትዋሰቡ፣ ወይትዋለዱ ከመ ሰብእ፣ ወአዲ ይመውቱ"።

ትርጉም፦ "በየብስ ውስጥ እና በውኃዎች ውስጥ የሚኖሩ ሥጋ ያላቸው አጋንንት አሉ፥ እነርሱ ግን ይጋባሉ፣ ይዋለዳሉ፣ ዳግመኛም ይሞታሉ"።

"ጋኔን" በነጠላ ሲሆን በብዜት "አጋንንት" ይባላሉ፥ ከአጋንንት በተቃራኒው መላእክት ረቂቃን ፍጡራን፣ የማይሞቱ እና የማይዋሰቡ ፍጥረት እንደሆኑ ተገልጿል፦
ድርሳነ ሚካኤል ምዕራፍ 5 ቁጥር 5 ዘውርኃ ጥር፦ "ወመላእክትሰ መንፈሳውያን እሙንቱ እለ ዘእንበለ ሥጋ፥ ወአልቦ ላዕሌሆም ሞት፣ ወድካም፣ ወትድምርት ከመ ሰብእ ለተዋስቦ"።

ትርጉም፦ "መላእክት ግን ሥጋ የሌላቸው ረቂቃን ናቸው፥ በእነርሱ ላይ ሞት፣ ድካም እና እንደ ሰው በጋብቻ መቀላቀል የለባቸውም"።

እነዚህ ያፈጠጡና ያገጠጡ አናቅጽ ሳታዩ አጽራረ ኢሥላም በመሆን ትችት መሰንዘር ዋልታ ረገጥ ትችት ነው፥ “ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከምቢያው ቂጥጥ” ይሉሃል እንደዚህ ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኤክሌሲያ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥70 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ በአላህ አንቀጾች ለምን ትክዳላችሁ? يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لِمَ تَكْفُرُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ وَأَنتُمْ تَشْهَدُونَ

"ኤክሌሲያ" ἐκκλησία የሚለው የግሪኩ ቃል ከሁለት ቃላት የተዋቀረ ቃል ነው፥ እርሱም "ኤክ" ἐκ ማለትም "ከ" ከሚል መስተዋድድ እና "ካሌኦ" καλέω ማለትም "የተጠራ" ከሚል ግስ ነው። በጥቅሉ "ተጠርተው የወጡ" ማለት ነው፥ ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን ሙያዊ ፍቺው ደግሞ "ጉባኤ" "ማኅበር" "ስብሰባ" ማለት ነው፦
ሐዋ. ሥራ 7፥38 ይህ ሰው በሲና ተራራ ከተናገረው መልአክ እና ከአባቶቻችን ጋር በምድረ በዳ "በማኅበሩ" ውስጥ የነበረው ነው። οὗτός ἐστιν ὁ γενόμενος ἐν τῇ ἐκκλησίᾳ ἐν τῇ ἐρήμῳ μετὰ τοῦ ἀγγέλου τοῦ λαλοῦντος αὐτῷ ἐν τῷ ὄρει Σινᾶ

እዚህ አንቀጽ ላይ በብሉይ ኪዳን በሙሴ ዘመን የነበረው ጉባኤ፣ ማኅበር፣ ስብሰባ "ኤክሌሲያ" ἐκκλησία እንደተባለ አንባቢ ልብ ይለዋል፦
ዘዳግም 9፥10 "ስብሰባ" ተደርጎ በነበረበትም ቀን እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ የነገራችሁ ቃል ሁሉ ተጽፎባቸው ነበር። καὶ ἐπ᾿ αὐταῖς ἐγέγραπτο πάντες οἱ λόγοι, οὓς ἐλάλησε Κύριος πρὸς ὑμᾶς ἐν τῷ ὄρει ἡμέρᾳ ἐκκλησίας·

አሁንም እዚህ የብሉይ አንቀጽ ላይ "ስብሰባ" ለሚለው የገባው የግሪክ ሰፕቱአጀንት ቃል "ኤክሌሲያ" ἐκκλησία ነው። እዚህ ድረስ ከተግባባን ኢየሱስ በጴጥሮስ "እሠራለው" ያለው ስብስብ "ኤክሌሲያ" ተብሏል፦
ማቴዎስ 16፥18 እኔም እልሃለሁ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚህም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የሲዖል ደጆችም አይችሉአትም። κἀγὼ δέ σοι λέγω ὅτι σὺ εἶ Πέτρος, καὶ ἐπὶ ταύτῃ τῇ πέτρᾳ οἰκοδομήσω μου τὴν ἐκκλησίαν, καὶ πύλαι Ἅιδου οὐ κατισχύσουσιν αὐτῆς.

"ቤተ-ክርስቲያን" ማለት ትርጉሙ "የክርስቲያን ቤት" ማለት ነው፥ "ክርስቲያን" የሚለው ቃል ለኢየሱስ ባዕድ ከመሆን ባሻገርም ዐረማዊ ሰዎች ለደቀመዛሙርቱ ያወጡላቸው የለበጣ እና የሽሙጥ ስም ነው። "ክርስቲያን" ማለት "ክርስቶሳውያን" "ቅቡዓን" "መሢሓውያን" ማለት ነው፥ ስለዚህ ግሪኩ ላይ "የክርስቲያን ቤት" የሚል የለም። ከዚያ ይልቅ "ኤክሌሲያ" ἐκκλησία የሚለው ቃል እንደተቀመጠ ልብ አድርግ! "ሐዴስ" ᾍδης ማለት "ሲዖል" "መቃብር" ማለት ነው፥ የሲዖል ደጆች አይችሉአትም የተባለችው ኤክሌሲያ በአንስታይ መደብ ብዜትን ለማመልከት የገባች "ጉባኤ" ወይም "ማኅበር" ናት፦
የሐዋርያው ሥራ 19፥41ይህንም ብሎ "ጉባኤውን" ፈታው። καὶ ταῦτα εἰπὼν ἀπέλυσεν τὴν ἐκκλησίαν.
ዕብራውያን 12፥23 በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት "ማኅበር"። καὶ ἐκκλησίᾳ πρωτοτόκων ἀπογεγραμμένων ἐν οὐρανοῖς,

እነዚህ ሁለቱ አናቅጽ ላይ "ጉባኤ" ወይም "ማኅበር" ለሚለው የገባው ቃል "ኤክሌሲያ" ἐκκλησία መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል።
"ፔትሮስ" Πέτρος ማለት "ዓለት" ማለት ሲሆን የዐረማይክ ይዘቱ "ኬፋስ" Κηφᾶς ነው፥ ኢየሱስ ጴጥሮስን፦ "ዓለት ነህ" "በዚህ ዓለት ላይ ኤክሌሲያ እሠራለው" ብሏል። ጴጥሮስም፦ "እኔ ጴጥሮስ መንፈሳዊ አባታችሁ ነኝ፥ በዚህ የሾመኝ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። "ዓለት" ተብዬ በእርሱ ዘንድ ተሹሜአለው፥ እናንተ በእኔ መሠረታት ላይ ትታነጹ ዘንድ እኔም በተሰጠኝ ችሎታ ይህንን ሠራሁኝ" ብሏል፦
ቀለሜንጦስ 10፥4 "እኔ ጴጥሮስ መንፈሳዊ አባታችሁ ነኝ፥ በዚህ የሾመኝ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። "ዓለት" ተብዬ በእርሱ ዘንድ ተሹሜአለው፥ እናንተ በእኔ መሠረታት ላይ ትታነጹ ዘንድ እኔም በተሰጠኝ ችሎታ ይህንን ሠራሁኝ"።

የጴጥሮስ የተጸውዖ ስሙ "ስምዖን" ሲሆን "ጴጥሮስ" ግን የማዕረግ ስሙ ነው፥ የሮሙ ክሌመንት(ቀለሜንጦስ) ደግሞ የጴጥሮስ ተማሪ እና የጴጥሮስ ወንበር ምትክ ነው፦
ቀለሜንጦስ 10፥4 "ልጄ ቀለሜንጦስ ሆይ! የሠራሁልህን ሥርዓት በጥንቃቄ ጠብቅ"።

ይህንን የክሌመንት ደብዳቤ የጻፈው እራሱ ቀለሜንጦስ ነው፥ "ካቴድራ" καθέδρα ማለት "መንበር" "ወንበር"cathedral" ማለት ሲሆን ሮም ላይ ያለው የጴጥሮስ መንበር ነው። ይህችን ኤክሌሲያ "ዓለም ዓቀፍ" ያላት የአንጾኪያው ኤጲስ ቆጶስ አግናጥዮስ በ 110 ድኅረ-ልደት ነው፥ "ክርስትና" የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ያመጣው ይህ ሰው ነው። በሮም የሞተው የአንጾኪያው ኤጲስ ቆጶስ አግናጥዮስ ለሰርምኔስ በጳፈው ደብዳቤ በግሪኩ "ካቶሊኮስ" καθολικός የሚል ቃል የተጠቀመ ሲሆን ትርጉሙ "ዓለም ዐቀፍ" በግዕዝ "ኲላዊት" በሮማይስጥ "ካቶሊክ" ነው፥ የፈረንሳዩ ኤጲስ ቆጶስ ሔራንዮስ በ 180 ድኅረ-ልደት ላይ፦ "እውነታው ያለው በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንጂ ሌላ በየትም አይደለም" ብሏል፦
የምንፍቅናዎች ተቃውሞ 3፥4 "እውነታው ያለው በኩላዊቷ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንጂ ሌላ በየትም አይደለም"።
Against heresies 3፥4 "The truth is to be found nowhere else but in the Catholic Church".

ይህቺ ሮም መቀመጫ ያደረገው የካቶሊክ ጉባኤ በሮም መንግሥት በቆስጠንጢኒዎስ ዕውቅና ያገኘችው በ 313 ድኅረ-ልደት ነው፥ ሮም ውስጥ የጴጥሮስ መንበር የያዘችው የካቶሊክ ኤክሌሲያ በ 325 ድኅረ-ልደት በሮሙ ንጉሥ በቆስጠንጢኒዎስ ሊቀ መንበርነት የተዘጋጀው የኒቂያ ጉባኤ በ318 ኤጲስ ቆጶሳት ማዕከል ያደረገ ነበር።

በመቀጠል ታላቁ እና ፊተኛው ቴዎዶስዮስ የሮም ንጉሥ በሆነበት ዘመን በ 380 ድኅረ-ልደት ላይ ኤክሌሲያ በሮም መንግሥት ውስጥ የመንግሥት ሃይማኖት ሆነች። 381 ድኅረ-ልደት በሮሙ ንጉሥ በታላቁ እና ፊተኛው ቴዎዶስዮስ ሊቀ መንበርነት የተዘጋጀው የቆስጠንጥኒያ ጉባኤ በ150 ኤጲስ ቆጶሳት ውሳኔ የቆስጠንጥኒያ አንቀጸ እምነት ጸደቀ፥ ይህም የቆስጠንጥኒያ አንቀጸ እምነት፦
፨በግሪክ፦ "Εἰς μίαν, ἁγίαν, καθολικὴν καὶ ἀποστολικὴν Ἐκκλησίαν"·
፨በግዕዝ፦ "ወነአምን በአሐቲ፣ ቅድስት፣ ኲላዊት ወሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን"
፨በኢንግሊሽ፦ "we believe in one, holy, Catholic and Apostolic Church".
፨በዐማርኛ፦ "በአንዲት፣ ቅድስት፣ ኲላዊት እና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን" የሚል ነው።

የኤክሌሲያ አራት ምልክቶች እና ባሕርዮት "አንዲት፣ ቅድስት፣ ኩላዊት እና ሐዋርያዊት" የሚል ነው፥ ከዚያ በኃላ የተደረጉ ጉባኤያትስ? የኤክሌሲያ ታሪክ ኢንሻሏህ በክፍል ሁለት ይቀጥላል....

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኤክሌሲያ

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥71 የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ? እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ? يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لِمَ تَلْبِسُونَ الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُونَ الْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ

"ሲኖዶስ" σύνοδος ማለት "ስብሰባ" ማለት ሲሆን ኤክሌሲያ ካደረገቻው መደበኛ ስብሰባ አንዱ በ 397 ድኅረ-ልደት የካርቴጁ ጉባኤ ነው፥ በካርቴጅ ጉባኤ የቀኖና መጻሕፍት ብለው የፈጣሪ ንግግር ያለበትን ከሰው ንግግር ጋር ቀላቅለዋል፥ ይህ ሒደት “ስይነርጎስ” ይባላል፥ “ስይነርጎስ” συνεργός ማለት “ቅልቅል” ማለት ነው። በተጨማሪም ከወንጌል ላይ የማይፈልጓቸው የወንጌል ክፍሎች በመቀነስ “አፓክሪፋ” አድርገዋል፥ “አፓክሪፋ” የሚለው ቃል “አፓክርፎስ” ἀπόκρυφος ከሚለው ግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን “ድብቅ” ማለት ነው፦
3፥71 የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን "ትቀላቅላላችሁ" እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን "ትደብቃላችሁ"? يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لِمَ تَلْبِسُونَ الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُونَ الْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ

በመጀመር በ431 ድኅረ-ልደት በሮሙ ንጉሥ በትንሹ እና በሁለተኛው ቴዎዶስዮስ ሊቀ መንበርነት የተዘጋጀው የኤፌሶን ጉባኤ 200 ኤጲስ ቆጶሳት በተሰበሰቡበት የቆስጠንጢኒያ ኤጲስ ቆጶስ የነበረው ንስጥሮስን አውግዘዋል፥ በዚህም ምክንያት የሶርያን ቤተክርስቲያን፦ "የቶማስን መንበር በመያዝ የሐዋርያዊ ተተኪ"apostolic succession" ይዤአለው" በማለት የራሷን ቤተክርስቲያን "አንዲት፣ ቅድስት፣ ኩላዊት እና ሐዋርያዊት" በማለት ትሰብካለች፣ ትዘምራለች፣ ታውጃለች። የኒቂያ እና የቆስጠንጥኒያ አጠቃላይ ጉባኤ"ecumenical council" ስትቀበል የተቀሩትን አጠቃላይ ጉባኤያት አትቀበልም።

በመቀጠል በ451 ድኅረ-ልደት የሮሙ ሁለተኛው ቴዎዶስዮስ እኅት በብርክልያ ጠሪነት የተዘጋጀው የኬልቄዶን ጉባኤ 130 ኤጲስ ቆጶሳት በተሰበሰቡበት የአሌክሳንድርያ ኤጲስ ቆጶስ የነበረው ዲዮስቆርዮስን አውግዘዋል፥ በዚህም ምክንያት የኦሬንታል ቤተክርስቲያን ከካቶሊኳ ኤክሌሺአ ተለይታለች። የኦሬንታል ቤተክርስቲያን የሚባሉት የአሌክሳንድሪያ፣ የኢትዮጵያ፣ የሕንድ፣ የአርመንያ አብያተክርስቲያናት ናቸው፥ የኦሬንታል ቤተክርስቲያን፦ "የማርቆስን መንበር በመያዝ የሐዋርያዊ ተተኪ ይዤአለው" በማለት የራሷን ቤተክርስቲያን "አንዲት፣ ቅድስት፣ ኩላዊት እና ሐዋርያዊት" በማለት ትሰብካለች፣ ትዘምራለች፣ ታውጃለች። የኒቂያ፣ የቆስጠንጥኒያ እና የኤፌሶን አጠቃላይ ጉባኤ"ecumenical council" ስትቀበል የተቀሩትን አጠቃላይ ጉባኤያት አትቀበልም፥ የኦሬንታል ቤተክርስቲያን የኬልቄዶን ጉባኤን፦ "የውሾች ጉባኤ"ጉባኤ ከለባት" ትላለች።
የካቶሊክ ቤተክርስትያን ደግሞ የሶርያ ቤተክርስቲያንን እና የኦሬንታል ቤተክርስቲያንን "አውግዤአቸዋለው፣ መናፍቅ ናቸው፣ በአንብሮተ እድ(እጅ በመጫን) የተቀበሉት ምንም ዓይነት ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ የለም" በማለት ትቃወማለች።

፨የባይዛንታይን ቤተክርስቲያን የሮም፣ የአንጾኪያ፣ የኢየሩሳሌም፣ የሰርቢያ፣ የሩሲያ፣ የቡልጋሪያ፣ የግሪክ አብያተክርስቲያናት ሲሆኑ የጴጥሮስ መንበር ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ የሆነ የራሳቸው ትውፊት"tradition" አላቸው።
፨የሶርያም ቤተክርስቲያን የቶማስ መንበር ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ የሆነ የራሳቸው ትውፊት"tradition" አላቸው።
፨የኦሬንታል ቤተክርስቲያን የማርቆስ መንበር ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ የሆነ የራሳቸው ትውፊት"tradition" አላቸው።

በመሠለስ በ 1054 ድኅረ-ልደት "መንፈስ ቅዱስ የሰረጸው ከማን ነው? በሚል የሥነ-መለኮት ውዝግብ እና በኤክሌሲያ አስተዳደር ጉዳይ ለሁለት ተሰነጠቁ፥ ይህ ታልቁ ክፍልል"great Schism" ይባላል። ይህም ክፍፍል ሮም የጴጥሮስ መንበር ያላት በካቶሊክ ኤክሌሲያ እና በተቀሩት የአንጾኪያ፣ የኢየሩሳሌም፣ የሰርቢያ፣ የሩሲያ፣ የቡልጋሪያ፣ የግሪክ አብያተክርስቲያናት መካከል ነው፥ የጴጥሮስ መንበር መቀመጫ አላት የምትባለው የሮም ኤክሌሲያ ምሥራቃዊ አብያተክርስቲያን የሚባሉትን የአንጾኪያ፣ የኢየሩሳሌም፣ የሰርቢያ፣ የሩሲያ፣ የቡልጋሪያ፣ የግሪክ አብያተክርስቲያን አወገዘች።
በካቶሊክ ቤተክርስቲያን የተወገዘችው ምሥራቃዊ ቤተክርስቲያን ከኦሬንታል ቤተክርስቲያን ጋር፦ "መንፈስ ቅዱስ የሰረጸው ከአብ ብቻ ነው" በሚለው በሚያግባባት የጋራ ነጥብ ላይ "ኦርቶዶክስ" የሚል አቋም ያዙ። "ኦርቶዶክስ" ὀρθόδοξος የሚለው የግሪኩ ቃል "ኦርቶ" ὀρθός ማለትም "ትክክለኛ" እና "ዶክሳ" δόξα ማለትም "አመለካከት" ከሚል ከሁለት ቃላት የተዋቀረ ሲሆን "ትክክለኛ አመለካከት" ማለት ነው፥ "ኦርቶዶክስ"የሚለውን ቃል ከጥንት ጀምረው የካቶሊክ ኤክሌሲያ፣ የሶርያ፣ የኦሬንታል እና የምሥራቃዊ ቤተክርስቲያን ለዶግማ የሚጠቀሙበት ስም ነው። ኢንሻሏህ የኤክሌሲያ ታሪክ በክፍል ሦስት እንቋጫለን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኤክሌሲያ

ገቢር ሦስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥171 እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ፡፡ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَا تَغْلُوا فِي دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا عَلَى اللَّهِ إِلَّا الْحَقَّ

በማረበብ ከካቶሊክ ኤክሌሲያ በ 1517 ድኅረ-ልደት የሉተር ተሐድሶ፣ በ 1527 ድኅረ-ልደት የአናፓፕቲዝም ተሐድሶ፣ በ 1530 ድኅረ-ልደት የአንግሊካን ተሐድሶ፣ በ 1790 ድኅረ-ልደት የሬስቶሬሽን ተሐድሶ ወጥተው የየራሳቸው ቤተክርስቲያን በመመሥረት፦ "አንዲት፣ ቅድስት፣ ኩላዊት እና ሐዋርያዊት" በማለት ይስብካሉ፣ ይዘምራሉ፣ ያውጃሉ፥ እነዚህ የተሐድሶ አንጃዎች ሰባቱንም አጠቃላይ ጉባኤ"ecumenical council" ይቀበላሉ።

የሉተር ተሐድሶ አምስት ሶላዎችን ያካተተ ሲሆን በካልቪን እርምደተ ሒደት እየሰፋ የመጣ የፕሮቴስታንት እንቅስቃሴ ዛሬ ላይ እንደ አሸን የሚፈላ የተለያየ ጎጥ ይዟል። ከፕሮቴስታንት ደግሞ አድቬንቲስት፣ ሞርሞር፣ የይሆዋ ምስክሮች፣ የሐዋርያት ቤተ እምነት እና ስፍር ቁጥር የሌላቸው የክርስትና አንጃዎች ወጥተዋል።
ዛሬ በዓለማችን ላይ 2.5 ቢሊዮን ክርስቲያን አለ፥ ከዚያ ውስጥ፦
1ኛ. 1.3 ቢሊዮን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ናት፣
2ኛ. 920 ሚልዮን የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ናት፣
3ኛ. 230 ሚልዮን የምስራቋ ቤተክርስቲያን ናት፣
4ኛ. 62 ሚሊዮን የኦሬንታል ቤተክርስቲያን ናት።

እንግዲህ ትልቋ እና የጥንቷ ኤክሌሲያ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስትሆን ይህቺ ቤተክርስቲያን ከሐዋርያው ህልፈት በኃላ አምላክን ሦስት በማለት ሦስት አካላት ማምለክ፣ ኢየሱስ ሰው ሆኖ ሳለ ሰው ማምለክ፣ የማርያምን ድንግልና፣ የማርያምን የአምላክ እናት መሆን፣ የማርያምን እርገት፣ ወደ ማርያም መጸለይ፣ ፍጡራን የሆኑትን መላእክት እና ሰዎች መለማመን፣ የሕፃናት ጥምቀት፣ ሰንበትን እሑድ ማድረግ፣ መስቀልን ለምልክትነት መጠቀምና መስገድ፣ ስዕልና ሐውልት ለአምልኮ መጠቀም እንዲሁ ምንኩስናን ደንግጋለች፥ ከላይ የተዘረዘሩትን ሐዋርያት አላስተማሩም። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እነዚህን ድንጋጌዎች ከሁለተኛው ክፍለ ዘመን እስከ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን ደንግጋለች፥ ፕሮቴስታንት የቤተክርስቲያን አበው ስለ ሥላሴ እና ስለ ኢየሱስ የተናገሩትን በመቀበል ስለ ማርያም፣ ስለ መላእክት፣ ስለ መስቀል፣ ስለ ስዕል እና ስለ ምንኩስና ያስተማሩትን ዓይናቸውን በጨው አጥበው "አላየንም" ጆሮራቸውን በጥጥ ደፍነው "አልሰማንም" ብለዋል።

የካቶሊክ ኤክሌሲያ እነዚህን ከመስመር የወጡ ትምህርታት የሚያርማትን ሰው የጴጥሮስን መንበር እና የመፍታትና የማሰር ቁልፍ ተቀብያለው በማለት "መናፍቅ" እያለች በግዝት እና በግዞት ስታሰቃይ ነበር፥ ይህቺ ተቋም ሲያሰኛት በጉልበት፣ በበባርነት እና በቅኝ ግዛት ሰዎች ክርስትናን እንዲቀበሉ አርጋለች። ባይብልን ወደ ሌላ ቋንቋ የሚተረጉሙ ሰዎችን ሰቅላለች በእሳት አቃጥላለች። የኢየሱስ ሐዋርያት እንዲህ አላደረጉም፥ ቅሉ ግን እነርሱ አንዱን አምላክ በብቸኝነት የሚያመልኩ ሙሥሊሞች ነበሩ፦
3፥52 ዒሣ ከእነርሱ ክህደት በተሰማውም ጊዜ፦ «ወደ አላህ ረዳቶቼ እነማን ናቸው» አለ፥ ሐዋርያት፡- «እኛ የአላህ ረዳቶች ነን፣ በአላህ አምነናል፣ እኛም ትክክለኛ ታዛዦች መኾናችንን መስክር» አሉ፡፡ فَلَمَّآ أَحَسَّ عِيسَىٰ مِنْهُمُ ٱلْكُفْرَ قَالَ مَنْ أَنصَارِىٓ إِلَى ٱللَّهِ ۖ قَالَ ٱلْحَوَارِيُّونَ نَحْنُ أَنصَارُ ٱللَّهِ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَٱشْهَدْ بِأَنَّا مُسْلِمُونَ

"ታዛዦች" ለሚለው የገባው ቃል "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ሲሆን "ሙሥሊም" مُسْلِم ለሚለው ብዜት ነው። "ረዳቶች" ለሚለው የገባው ቃል "አንሷር" أَنصَار ነው፥ "ነስራኒይ" نَصْرَانِيّ የሚለው ቃል "ነሰረ" نَصَرَ ማለትም "ረዳ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ረጂ" ማለት ነው። የነስራኒይ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ነሷራ" نَصَارَىٰ ነው፥ አምላካችን አሏህ፦ "እኛ ነሷራ ነን" ካሉት ጋር የጠበቀ ቃል ኪዳን ይዞ ነበር፥ ይህም ኪዳን፦ "በእኔ እና በመልክተኛዬ እመኑ" የሚል ትእዛዝ ነው፦
5፥111 ወደ ሐዋርያትም «በእኔ እና በመልክተኛዬ እመኑ» በማለት "ባዘዝኩ" ጊዜ አስታውስ፡፡ «አመንን፤ እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክር» አሉ፡፡ وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى الْحَوَارِيِّينَ أَنْ آمِنُوا بِي وَبِرَسُولِي قَالُوا آمَنَّا وَاشْهَدْ بِأَنَّنَا مُسْلِمُونَ
5፥14 ከእነዚያም፦ "እኛ ነሷራ ነን" ካሉት የጠበቀ ቃል ኪዳናቸውን ያዝን፡፡ በእርሱም "ከታዘዙበት" ነገር ፈንታን ተውት፡፡ وَمِنَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّا نَصَارَىٰ أَخَذْنَا مِيثَاقَهُمْ فَنَسُوا حَظًّا مِّمَّا ذُكِّرُوا بِهِ فَأَغْرَيْنَا بَيْنَهُمُ الْعَدَاوَةَ

አሏህ አንድ አምላክ እንደሆነ እና መሢሑ መልእክተኛ እንደሆነ እንዲያምኑ ያዘዘውን ትእዛዝ ከሐዋርያት ህልፈት በኃላ ያሉት የኤክሌሲያ አበው ፈጣሪ፦ "በአካል ሦስት ነው" በማለት ከታዘዙበት ነገር ፈንታን በመተው ወሰን አለፉ፦
4፥171 እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ፡፡ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَا تَغْلُوا فِي دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا عَلَى اللَّهِ إِلَّا الْحَقَّ
4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉም! ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ

ይህንን ተከታታይ መጣጥፍ የምታነቡ ክርስቲያኖች አንዱን አምላክ በብቸኝነት እንድታመልኩ ወደ ኢሥላም እንጠራችኃለን። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ዋቢ መጽሐፍት ይመልከቱ፦
1.Louis Berkhof(1949)Systematic Theology.
2. Henry Chadwick (2001). The church in ancient society: from Galilee to Gregory the Great.
3. Justo L. González(2010) The Early Church to the Dawn of the Reformation.

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቅጥፈት ይብቃ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥105 ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ብቻ ናቸው፤ እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው፡፡ إِنَّمَا يَفْتَرِي الْكَذِبَ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ۖ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَاذِبُونَ

ግብጻዊ ቄስ ዘካሪያስ لَعْنَتَ اللَّهِ عَلَيْهِ ሁልጊዜ ለሚቀጥፈው ቅጥፈት ምላሽ ሲሰጠው እየተገለባበጠ ኢሥላምን የሚያጠለሽበት ጥላሸት ለመፈለግ ቀን ከሌሊት ይዳክራል፥ ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ብቻ ናቸው። እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው፦
16፥105 ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ብቻ ናቸው፤ እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው፡፡ إِنَّمَا يَفْتَرِي الْكَذِبَ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ۖ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَاذِبُونَ

ከቀጠፈው ቅጥፈት አንዱ ነቢያችንን”ﷺ” ከሬሳ ጋር ተራክቦ እንዳደረጉ አድርጎ መቅጠፉ ነው፥ ወሊ-አዑዝቢሏህ እኔ ለደገሙት ቃል ሰቀጠጠኝ። ኅሊናውን ለሸጠ ሰው እና ሐሰትን ለተከናነበ ሰው ይህን ማድረግ ውስጡን ሰላም አይሰጠውም። እስቲ የሚያነሳቸውን ሐዲሳት እንመልከት፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 23, ሐዲስ 98
አነሥ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ ”የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ሴት ልጅ የቀብር ሥርአት ላይ ነበርን፤ የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” በመቃብር አቅራቢያ ተቀምጠው ዓይኖቻቸው በእንባ ሞልተው አየዋቸው፤ እርሳቸውም፦ “ከመካከላችሁ በዚህ ሌሊት ከሚስቱ ጋር ተራክቦ ያላደረገ አለን? አሉ፤ አቡ ጠልሓህም፦ “እኔ አለሁ” ብሎ መለሰ፤ እርሳቸውም፦ “ወደ መቃብሯ ውረድ” አሉት፤ እርሱም ወደ መቃብሯ ወረዶ ቀበራት"። عَنْ أَنَسٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ شَهِدْنَا بِنْتَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَرَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم جَالِسٌ عَلَى الْقَبْرِ، فَرَأَيْتُ عَيْنَيْهِ تَدْمَعَانِ فَقَالَ ‏”‏ هَلْ فِيكُمْ مِنْ أَحَدٍ لَمْ يُقَارِفِ اللَّيْلَةَ ‏”‌‏.‏ فَقَالَ أَبُو طَلْحَةَ أَنَا‏.‏ قَالَ ‏”‏ فَانْزِلْ فِي قَبْرِهَا ‏”‌‏.‏ فَنَزَلَ فِي قَبْرِهَا فَقَبَرَهَا‏.‏

ከመነሻው እዚህ ሐዲስ ላይ፦ "እከሌ ከሬሳ ጋር ወሲብ ፈጸመ" የሚል ሽታው እንኳን ቢፈለግ የለም፥ ውሸት ሲጋለጥ ከዚህ ይጀመራል።
ሲቀጥል “ኔክሮፊሊያ”Necrophilia” ማለት ከሬሳ ጋር የሚደረግ ተራክቦ ነው፥ በኢሥላም አይደለም ከሞተ ሰው ይቅርና በቁም ካለ ሰው ጋር ተራክቦ ለማድረግ ኒካሕ ይወጅባል። እስቲ ሁለተኛውን ሐዲስ እንመልከት፦
ከንዙል ዑማል 242218
ኢብኑ አባስ እንደተረከው የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ ”የጀነትን ልብስ እስከምትለብስ ልብሴን አለበስኳት፣ በመቃብሯ ውስጥ አብሬ ተጋደምኩኝ፣ ምናልባት የመቃብሩ ጫና ይቀንሳል ብዬ። ለእኔ ከአቡ ጠሊብ በኃላ ከአላህ ፍጥረት በላጭ ናት። ነቢዩም”ﷺ” ይህንን ያሉት የዐሊይ እናት ስለሆነችው ስለፋጢማ ነበር"።

“ከንዙል ዑማል” كنز العمال ማለት “የሠናይ ገባሪ ጥሪኝ” ማለት ነው፥ ዐሊ ኢብኑ ዐብዱል ማሊክ አል-ሂንዲ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 1517 ድህረ-ልደት ያዘጋጀው ሐዲስ ነው።
፨ሲጀመር ይህ ሐዲስ ከመነሻው ዶዒፍ ነው።
፨ሲቀጥል የዐሊይ እናት ለነቢያችን”ﷺ” አክስት ናት፥ ከአቡ ጠሊብ ጋር ሆና ያሳደገቻቸው እርሷ ናት። ከአክስት ጋር አይደለም ሞታ ወሲብ ይቅርና በቁምም ከአክስት ጋር ጋብቻ ክልክል ነው፦
4፥23 እናቶቻችሁ፣ ሴት ልጆቻችሁም፣ እኅቶቻችሁም፣ "አክስቶቻችሁም፣ የሹሜዎቻችሁም፣" የወንድም ሴቶች ልጆችም፣ የእኅት ሴቶች ልጆችም፣ እነዚያም ያጠቡዋችሁ እናቶቻችሁ፣ ከመጥባት የኾኑትም እኅቶቻችሁ፣ የሚስቶቻችሁም እናቶች፣ እነዚያም በጉያዎቻችሁ ያሉት የእነዚያ በእነርሱ የገባችሁባቸው ሚስቶቻችሁ ሴቶች ልጆች፣ "ልታገቧቸው በእናንተ ላይ እርም ተደረጉባችሁ"፡፡ حُرِّمَتْ عَلَيْكُمْ أُمَّهَاتُكُمْ وَبَنَاتُكُمْ وَأَخَوَاتُكُمْ وَعَمَّاتُكُمْ وَخَالَاتُكُمْ وَبَنَاتُ الْأَخِ وَبَنَاتُ الْأُخْتِ وَأُمَّهَاتُكُمُ اللَّاتِي أَرْضَعْنَكُمْ وَأَخَوَاتُكُم مِّنَ الرَّضَاعَةِ وَأُمَّهَاتُ نِسَائِكُمْ وَرَبَائِبُكُمُ اللَّاتِي فِي حُجُورِكُم مِّن نِّسَائِكُمُ اللَّاتِي دَخَلْتُم بِهِنَّ فَإِن لَّمْ تَكُونُوا دَخَلْتُم بِهِنَّ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ وَحَلَائِلُ أَبْنَائِكُمُ الَّذِينَ مِنْ أَصْلَابِكُمْ وَأَن تَجْمَعُوا بَيْنَ الْأُخْتَيْنِ إِلَّا مَا قَدْ سَلَفَ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا
፨ሢሰልስ “በመቃብሯ ውስጥ አብሬ ተጋደምኩኝ” اضْطَجَعَ معها في قبرها ማለት “ወሰብኩኝ” “ተራከብኩኝ” ብሎ የተረጎመላችሁ ማን ነው? “አድጦጀዐ” اضْطَجَعَ ማለት “ተኛ” ማለት እንጂ “ወሰበ” አሊያም “ተራከበ” ማለት አይደለም። ይህ ዐረቢኛው ባይብል ላይ ኤልሳዕ ከሕፃኑ ጋር የተኛውን ለማመልከት አገልግሎት ላይ ውሏል፦
2 ነገሥት 4፥34 መጥቶም በሕፃኑ ላይ "ተኛ"፤ አፉንም በአፉ፥ ዓይኑንም በዓይኑ፥ እጁንም በእጁ ላይ አድርጎ "ተጋደመበት"፤ የሕፃኑም ገላ ሞቀ። ثُمَّ صَعِدَ وَاضْطَجَعَ فَوْقَ الصَّبِيِّ وَوَضَعَ فَمَهُ عَلَى فَمِهِ وَعَيْنَيْهِ عَلَى عَيْنَيْهِ وَيَدَيْهِ عَلَى يَدَيْهِ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ተኛ” ለሚለው ቃል የገባው ቃል “አድጦጀዐ” اضْطَجَعَ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። ታዲያ ኤልያስ ከሕጻኑ ጋር ወሲብ አደረገ ማለት ነውን? አዎ ካላችሁን ነብዩ ኤልሳዕ ግብረ ሰዶማዊ ነው ልትሉ ነው? ምክንያቱም ሕጻኑ ወንድ ሕጻን ነውና። አይ “ተወሰበ” “ተራከበ” ለሚለው ቃል “ነከሐ” نَكَحَ እንጂ “አድጦጀዐ” اضْطَجَعَ አይደለም" ካላችሁ እንግዲያውስ ቅጥፈታችሁን እዚህ ጋር ይብቃ! ምነው በተመሳሳይ ሙሴ ከአባቶቹ ጋር በመቃብር እንደሚተኛ ፈጣሪ ነግሮታል፥ በተጨማሪም ኢዮብ ሰው ከአጥንቱ ጋር በመቃብር እንደሚተኛ ተናግሯል። ኢሳይያስም ነብርም ከፍየል ጠቦት ጋር ይተኛል ብሏል፦
ዘዳግም 31፥16 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ እነሆ፥ *ከአባቶችህ ጋር ትተኛለህ*፤ وَقَال الرَّبُّ لِمُوسَى: «هَا أَنْتَ تَرْقُدُ مَعَ آبَائِك
ኢዮብ 20፥11 አጥንቶቹ ብላቴንነቱን ሞልተዋል፤ ነገር ግን ከእርሱ ጋር በመሬት ውስጥ "ይተኛል"። عِظَامُهُ مَلآنَةٌ قُوَّةً وَمَعَهُ فِي التُّرَابِ تَضْطَجِعُ.
ኢሳይያስ 11፥6 ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋር ይቀመጣል፥ ነብርም ከፍየል ጠቦት ጋር "ይተኛል"፤ فَيَسْكُنُ الذِّئْبُ مَعَ الْخَرُوفِ وَيَرْبُضُ النَّمِرُ مَعَ الْجَدْيِ وَالْعِجْلُ

ሰው በመሬት ውስጥ “ይተኛል” ለሚለው ቃል የወደፊት ግስ የተጠቀመበት “ተድጦጂዑ” تَضْطَجِعُ ሲሆን የእርሱ አላፊ ግስ “አድጦጀዐ” اضْطَجَعَ ነው፥ እና ሰው አፈር ውስጥ ወሲብ ያረጋል ማለቱ ነውን? እረ “መተኛት” ሲባል "ተራክቦ ወይም ወሲብ ማለት አይደለም" ካላችሁ እንግዲያውስ ቅጥፈት ይብቃ! ከላይ ያለውን ዶዒፍ ሐዲስ በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቀልድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

39፥48 ለእነርሱም የሠሩዋቸው መጥፎዎቹ ይገለጹላቸዋል፡፡ በእነርሱም ላይ በእርሱ ያላግጡበት የነበሩት ቅጣት ይሰፍርባቸዋል፡፡ وَبَدَا لَهُمْ سَيِّئَاتُ مَا كَسَبُوا وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُوا بِهِ يَسْتَهْزِئُونَ

ሰው ለማስደሰት ብሎ ሐቅን እየተናገሩ መቀለድ በራሱ ሙባሕ ነው፥ ፈገግታ ሶደቃህ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 27, ሐዲስ 96
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "እነርሱም፦ "የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! ትቀልደናለህን? አሉ፥ እርሳቸውም፦ "ከእውነት በስተቀር ምንም አልተናገርኩም" አሉ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ إِنَّكَ تُدَاعِبُنَا ‏.‏ قَالَ ‏ "‏ إِنِّي لاَ أَقُولُ إِلاَّ حَقًّا ‏"‏ ‏
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 27, ሐዲስ 62
አቢ ዘር እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የአንተ ፈገግታ በወንድምህ ፊት ለአንተ ሶደቃህ ነው"። عَنْ أَبِي ذَرٍّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ تَبَسُّمُكَ فِي وَجْهِ أَخِيكَ لَكَ صَدَقَةٌ

እንዲሁ በትዳር፣ በፍቺ እና በመማለስ ቀልድ የለም፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 13, ሐዲስ 20
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ሦስቱ ነገራት የምር ይሁን የምር፥ የቀልድም ይሁን የምር ናቸው። እነርሱም ትዳር፣ ፍች እና መማለስ ናቸው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ ثَلاَثٌ جِدُّهُنَّ جِدٌّ وَهَزْلُهُنَّ جِدٌّ النِّكَاحُ وَالطَّلاَقُ وَالرَّجْعَةُ ‏”‏

“ረጅዓህ” رَّجْعَة ማለት “መማለስ” ማለት ሲሆን ከተፋቱ በኃላ እንደገና መጋባትን የሚያመላክት እሳቤ ነው። ከዚህ ሁሉ ወዮ የሚያስብ ወንጀል ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ መዋሸት ነው፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 218
በህዝ ኢብኑ ሐኪም ከአባቱ አባቱ ከአያቱ ሰምተው እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ወዮለት ያ በእርሱ ሕዝብን ለማሳቅ ብሎ ለሚዋሸው፥ ወዮለት ወዮለት"። عَنْ بَهْزِ بْنِ حَكِيمٍ، قَالَ حَدَّثَنِي أَبِي، عَنْ أَبِيهِ، قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ وَيْلٌ لِلَّذِي يُحَدِّثُ فَيَكْذِبُ لِيُضْحِكَ بِهِ الْقَوْمَ وَيْلٌ لَهُ وَيْلٌ لَهُ ‏"‏ ‏

በተለይ ዚክር የሆኑትን ቃላት፦ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلٰهَ إِلَّا اللّٰه "አሏሁ አክበር" اللّٰهُ أَكْبَر "አልሓምዱ ሊላህ" ٱلْحَمْدُ لِلَّه "ሡብሓነ አሏህ" سُبْحَانَ اللَّه "አዑዙ ቢሏህ أَعُوذُ بِاللَّهِ እያሉ በአሏህ ስም ላይ የሚቀልዱ የከፋ ኩፍር ነው፥ በአሏህ፣ በአንቀጾቹ እና በመልክተኛው ላይ ማላገጥ ትልቅ ወንጀል ነው። በእነርሱም ላይ በእርሱ ያላግጡበት የነበሩት ቅጣት ይሰፍርባቸዋል፦
9፥65 በእርግጥ ብትጠይቃቸው «እኛ የምንዘባርቅና የምንጫወት ብቻ ነበርን» ይላሉ፡፡ «በአላህ እና በአንቀጾቹ፣ በመልክተኛውም ታላግጡ ነበራችሁን?» በላቸው፡፡ وَلَئِن سَأَلْتَهُمْ لَيَقُولُنَّ إِنَّمَا كُنَّا نَخُوضُ وَنَلْعَبُ ۚ قُلْ أَبِاللَّهِ وَآيَاتِهِ وَرَسُولِهِ كُنتُمْ تَسْتَهْزِئُونَ
39፥48 ለእነርሱም የሠሩዋቸው መጥፎዎቹ ይገለጹላቸዋል፡፡ በእነርሱም ላይ በእርሱ ያላግጡበት የነበሩት ቅጣት ይሰፍርባቸዋል፡፡ وَبَدَا لَهُمْ سَيِّئَاتُ مَا كَسَبُوا وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُوا بِهِ يَسْتَهْزِئُونَ

"ኢሥላማዊ ኮሜዲይ" እያሉ ሕዝብን ለማሳቅ በአሏህ አንቀጾች ከሚያላግጡ ይልቅ አንደኛቸው የዓለማዊ ኮሜዲይ እየሠሩ ቢበሉ ይሻላል እንጂ በዲን መነገድ የቱንም ያህል ገንዘብ ቢገኝበት በዲንያህ ሆነ በአኺራ ኪሳራ ነው። አሏህ የሙሥሊም ማሊያ ለብሰው በዲን ላይ የሚሳለቁትን እና የሚጫወቱትን ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛ ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የአሳማ ሥጋ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥173 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የአሳማ ሥጋን እና በእርሱ ማረድ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ بِهِ لِغَيْرِ اللَّهِ

"ኺንዚር" خِنزِير ማለት "አሳማ" ማለት ሲሆን የአሳማ አስተኔ ምድብ ውስጥ የሚመደቡ ጉንደ እንስሳ "እሪያ" እና "ከርከሮ" ናቸው፥ አሳማ ሴረም ፕሮቲኖችን ስለያዘ ሥጋው በሰውነት ውስጥ የአለርጂን ሂደት የሚያነቃቁ አልቡሚን እና ኢሚውኖ ግሎቡሊን አላቸው። በዚህም ግልጽ ምክንያት አካላችንን በጣም ብዙ ጎጂ ባክቴሪያዎችን እና ጥገኛ ተውሳኮች ይይዛል፥ በአሳማ የጡንቻ ሕብረ ሕዋሳት ውስጥ የሚገኙ ጎጂ ባክቴሪያዎችን እና ጥገኛ ተውሳኮች ሰው የአሳማ ሥጋ ሲበላ ወደ ልቡ ጡንቻ ውስጥ ዘልቀው በመግባት ይራቡና በዚህም ለሕይወቱ አስጊ ሁኔታን ያስከትላል። አምላካችን አሏህም ሰውን የሚጎዳው ይህንን የአሳማ ሥጋ መብላት ክልክሏል፦
2፥173 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የአሳማ ሥጋን እና በእርሱ ማረድ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ بِهِ لِغَيْرِ اللَّهِ
16፥115 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የአሳማን ሥጋን እና ያንን በመታረድ ጊዜ በእርሱ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ لِغَيْرِ اللَّهِ بِهِ
6፥145 በላቸው፡- «ወደ እኔ በተወረደው ውስጥ በክት፣ ወይም ፈሳሽ ደምን፣ ወይም የአሳማ ሥጋን እርሱ ርኩስ ነውና፣ ወይም በአመጽ ከአላህ ስም ሌላ በእርሱ ላይ የተወሳበት ካልኾነ በስተቀር በሚመገበው ተመጋቢ ላይ እርም የኾነን ነገር አላገኝም፡፡ قُل لَّا أَجِدُ فِي مَا أُوحِيَ إِلَيَّ مُحَرَّمًا عَلَىٰ طَاعِمٍ يَطْعَمُهُ إِلَّا أَن يَكُونَ مَيْتَةً أَوْ دَمًا مَّسْفُوحًا أَوْ لَحْمَ خِنزِيرٍ فَإِنَّهُ رِجْسٌ أَوْ فِسْقًا أُهِلَّ لِغَيْرِ اللَّهِ بِهِ

"ሐርረመ" حَرَّمَ ማለት "የተከለከለ" ማለት ነው፥ ይህ ክልከላ እኛን ስለሚጎዳን እንጂ አንድ ሰው በረሃብ ምክንያት ሞት አፋፍ ላይ ቢሆን መብላቱ ሙባሕ ነው። ለመብላት የተገደደ ሰውም በእርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም፥ አምላካችን አሏህ ለነቢያችን"ﷺ ኡማህ ካነሳው ሦስት ነገሮች አንዱ የገተደዱበትን ነገር ነው፦
2፥173 ሽፍታ እና ወሰን አላፊ ሳይኾን ለመብላት የተገደደ ሰውም በእርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም፥ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَلَا إِثْمَ عَلَيْهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
16፥115 አመጸኛም ወይም ወሰን አላፊ ሳይኾን ለመብላት የተገደደ ሰው ይፈቀድለታል፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
6፥145 አመጸኛ እና ወሰን ያለፈ ሳይኾንም የተገደደ ሰው ከተወሱት ቢበላ ኃጢአት የለበትም፡፡ ጌታህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ رَبَّكَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 2123
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ ”አላህ በኡማዬ ላይ ስህተት፣ መርሳት እና የገተደዱበትን ነገር አንስቷል”። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، عَنِ النَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ “‏ إِنَّ اللَّهَ وَضَعَ عَنْ أُمَّتِي الْخَطَأَ وَالنِّسْيَانَ وَمَا اسْتُكْرِهُوا عَلَيْهِ

ነገር ግን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ውጪ ያሉት የክርስትና እምነት ተከታዮች የአሳማ ሥጋ መብላትን ሐላል አርገዋል፥ ቅሉ ግን በባይብልም ቢሆን የአሳማ ሥጋ መብላት ሐራም ነው፦
ዘሌዋውያን 11፥7 እርያም ሰኮናው ተሰንጥቋል፥ ነገር ግን ስለማያመሰኳ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።
ዘዳግም 14፥8 እርያም ሰኮናው ስለ ተሰነጠቀ ነገር ግን ስላላመሰኳ እርሱ ለእናንተ ርኩስ ነው፥ ሥጋውን አትብሉ! በድኑንም አትንኩ።

"ሥጋውን አትብሉ" የሚለው ክልከላ ይሰመርበት! የእሪያን ሥጋ የሚበሉ ግን በጀሃነም በአንድነት ይጠፋሉ፦
ኢሳይያስ 66፥17 "የእሪያን ሥጋ፣ አስጸያፊ ነገርን፣ አይጥንም የሚበሉ በአንድነት ይጠፋሉ" ይላል ያህዌህ።

የክርስትና እምነት ተከታዮች እነዚህን አናቅጽ ስንሰጣቸው፦ "የእሪያን ሥጋ በአዲስ ኪዳን ተፈቅዷል" ይላሉ፥ ነገር ግን መፈቀዱን የሚያሳይ አንድም ጥቅስ አያመጡም፦
ማቴዎስ 15፥11 ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም፥ ከአፍ የሚወጣው ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው" አላቸው።
1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥4 እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም ነውና፥ ከምስጋናም ጋር ቢቀበሉት የሚጣል ምንም የለም"።

እነዚህ ሁለት አናቅጽ ላይ አንጻራዊ ንግግር እንጂ ወደ አፍ የሚገባ የሚያረክሱ ለጣዖት የተሰዋ ምግብ፣ ደም መብላት፣ የታነቀ እንስሳ ሐራም ናቸው፦
1 ቆሮ 10፥28 ማንም ግን፦ "ይህ ለጣዖት የተሠዋ ነው" ቢላችሁ ከዚያ ካስታወቃችሁና ከሕሊና የተነሣ አትብሉ"።
ራእይ 2፥14 ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ እና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።
የሐዋርያት ሥራ 15፥20 ነገር ግን ከጣዖት ርኵሰት፣ ከዝሙት ከታነቀም፣ ከደምም ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቈርጣለሁ።
የሐዋርያት ሥራ 21፥25 አምነው ስለ ነበሩ አሕዛብ ግን ለጣዖት ከተሠዋ ከደምም ከታነቀም ከዝሙትም ነፍሳቸውን እንዲጠብቁ ፈርደን እኛ ጽፈንላቸዋል።

ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ ለጣዖት የተሰዋ ምግብ፣ ደም መብላት፣ የታነቀ እንስሳ አያካትትምን? ከምስጋናም ጋር ቢቀበሉት ለጣዖት የተሰዋ ምግብ፣ ደም መብላት፣ የታነቀ እንስሳ የሚጣል የለምን? አይ፦ "ኢየሱስ አያረክስም ያለው እጅ ሳይታጠቡ መብላትን እንጂ እርኩስ ነው የተባሉትን ምግብ አይደለም፥ ጳውሎስ የሚጣል የለም ያለው መልካም ምግብን ነው" ካላችሁ እንግዲያውስ የአሳማ ሥጋ የተፈቀደበት አንድም ጥቅስ መቼም ልታመጡ አትችሉም። የማታውቁትን ነገር መናገር ዳፋው እና ጦሱ ለራስ ነው፥ ስለዚህ ጨርቄን እና ማቄን ሳትሉ የአሳማ ሥጋ ሐራም መሆኑን ብትቀበሉ ይሻላል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ደም መብላት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥173 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የአሳማ ሥጋን እና በእርሱ ማረድ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ بِهِ لِغَيْرِ اللَّهِ

"ደም" دَّم በአብዛኛው የቀይ ቀለም ያለው የአካል ፈሳሽ ሲሆን በተለያዩ የአካል ክፍሎች በመሰራጨት ለሕዋሳት ምግብ እና ኦክስጅን ያደርሳል፥ እንዲሁም ከእነዚሁ ሕዋሳት ዝቃጩን ያስወግዳል። በደም ውስጥ ሁለት ዓበይት የደም ሕዋሳት ይገኛሉ፥ አንዱ ነጭ የደም ሕዋስ በሽታ አምጪ ተዋስያን ሰውነታችን ገብተው ለበሽታ እንዳያጋልጡ ሲያደርግ ቀይ የደም ሕዋስ ደግሞ ኦክስጅንን እና ምግብን ለሰውነታችን ሕዋሳት ያደርሳል። አምላካችን አሏህ ደምን መብላት ሐራም አድርጓል፦
2፥173 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የአሳማ ሥጋን እና በእርሱ ማረድ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ بِهِ لِغَيْرِ اللَّهِ
16፥115 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የአሳማን ሥጋ እና ያንን በመታረድ ጊዜ በእርሱ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ لِغَيْرِ اللَّهِ بِهِ
6፥145 በላቸው፡- «ወደ እኔ በተወረደው ውስጥ በክት፣ ወይም ፈሳሽ ደም፣ ወይም የአሳማ ሥጋ እርሱ ርኩስ ነውና፣ ወይም በአመጽ ከአላህ ስም ሌላ በእርሱ ላይ የተወሳበት ካልኾነ በስተቀር በሚመገበው ተመጋቢ ላይ እርም የኾነን ነገር አላገኝም፡፡ قُل لَّا أَجِدُ فِي مَا أُوحِيَ إِلَيَّ مُحَرَّمًا عَلَىٰ طَاعِمٍ يَطْعَمُهُ إِلَّا أَن يَكُونَ مَيْتَةً أَوْ دَمًا مَّسْفُوحًا أَوْ لَحْمَ خِنزِيرٍ فَإِنَّهُ رِجْسٌ أَوْ فِسْقًا أُهِلَّ لِغَيْرِ اللَّهِ بِهِ

"ሐርረመ" حَرَّمَ ማለት "የተከለከለ" ማለት ነው፥ ይህ ክልከላ እኛን ስለሚጎዳን እንጂ አንድ ሰው በረሃብ አሊያም በጥማት ምክንያት ሞት አፋፍ ላይ ቢሆን ደም መብላቱ ሙባሕ ነው። ለመብላት የተገደደ ሰውም በእርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም፥ አምላካችን አሏህ ለነቢያችን"ﷺ ኡማህ ካነሳው ሦስት ነገሮች አንዱ የገተደዱበትን ነገር ነው፦
2፥173 ሽፍታ እና ወሰን አላፊ ሳይኾን ለመብላት የተገደደ ሰውም በእርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም፥ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَلَا إِثْمَ عَلَيْهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
16፥115 አመጸኛም ወይም ወሰን አላፊ ሳይኾን ለመብላት የተገደደ ሰው ይፈቀድለታል፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
6፥145 አመጸኛ እና ወሰን ያለፈ ሳይኾንም የተገደደ ሰው ከተወሱት ቢበላ ኃጢአት የለበትም፡፡ ጌታህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ رَبَّكَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 2123
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ ”አላህ በኡማዬ ላይ ስህተት፣ መርሳት እና የገተደዱበትን ነገር አንስቷል”። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، عَنِ النَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ “‏ إِنَّ اللَّهَ وَضَعَ عَنْ أُمَّتِي الْخَطَأَ وَالنِّسْيَانَ وَمَا اسْتُكْرِهُوا عَلَيْهِ

ነገር ግን የአውሮፓ ክርስቲያኖች ደም መብላትን ሐላል አርገዋል፥ በተለይ የአሳማ ደም የደም ቋሊማ"Blood sausage" እንደ ጣፋጭ ምግብ ይታያል። በተጨማሪም የአገራችን ክርስቲያኖች በተለምዶ ደም ጠብሰው ከጨጓራ ጋር ይበላሉ፥ እረ አንዳንዶችም ደም በትኩሱ ይጠጣሉ። ቅሉ ግን በባይብልም ቢሆን ደም መብላት ሐራም ነው፦
ዘሌዋውያን 17፥12 ስለዚህ የእስራኤልን ልጆች፦ "ከእናንተ ማንም ደምን አይበላም፥ በመካከላችሁም ከሚኖሩ እንግዶች ማንም ደምን አይበላም" አልሁ።
ዘሌዋውያን 7፥27 ደም የሚበላ ሰው ሁሉ ያ ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ።
ዘሌዋውያን 17፥14 የሥጋውን ሁሉ ደም አትብሉ! የሚበላውም ሁሉ ተለይቶ ይጥፋ" አልኋቸው።

"የሥጋውን ሁሉ ደም አትብሉ" የሚለው ክልከላ ይሰመርበት! የአውሮፓ ክርስቲያኖች እነዚህን አናቅጽ ስንሰጣው፦ "ደም በአዲስ ኪዳን ተፈቅዷል" ይላሉ፥ ነገር ግን መፈቀዱን የሚያሳይ አንድም ጥቅስ አያመጡም። ከዚያል ይልቅ የኢየሩሳሌም ጉባኤ ደም መብላትን አውግዘዋል፦
የሐዋርያት ሥራ 15፥20 ነገር ግን ከጣዖት ርኵሰት፣ ከዝሙት ከታነቀም፣ ከደምም ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቈርጣለሁ።
የሐዋርያት ሥራ 21፥25 አምነው ስለ ነበሩ አሕዛብ ግን ለጣዖት ከተሠዋ ከደምም ከታነቀም ከዝሙትም ነፍሳቸውን እንዲጠብቁ ፈርደን እኛ ጽፈንላቸዋል።

አሏህ በእርሱ ሸሪዓህ የምንመራ ያርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሌላን አትገዙ!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

11፥2 እንዲህ በላቸው፡- «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስጠንቃቂ እና አብሳሪ ነኝ፡፡» أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ ۚ إِنَّنِي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ

ሚሽነሪዎች ኢየሱስ እንደሚመለክ ለማስመሰል የማይፈነቅሉት ድንጋይ የማይደረምሱት መሬት የለም፥ "በ"ኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ" የሚለውን ሐረግ "ለ"ኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ" በሚል እያንሸዋረሩ ይረዳሉ ያስረዳሉ። ነገር ግን ጳውሎስ ያስቀመጠው በዚህ መልኩ አይደለም፥ እስቲ ከኢሳይያስ ኃይለ-ቃል እንጀምር! ፈጣሪ፦ "ጕልበት ሁሉ "ለ"-እኔ ይንበረከካል" እያለ ይናገራል፦
ኢሳይያስ 45፥23 ጕልበት ሁሉ "ለ"-እኔ ይንበረከካል።

"ለእኔ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! "ለ" እና "በ" ሁለት የተለያዩ መስተዋድዶች ናቸው፦
ፊልጵስዩስ 2፥10 ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ "በ"-ኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ።

"በ" የሚለው መነሻ ቅጥያ ላይ ያለ መስተዋድድ በኢየሱስ ስም ለአብ መንበርከክን ያሳያል እንጂ ለኢየሱስ መንበርከክን አያሳይም። ለምሳሌ፦
ኤፌሶን 5፥20 "በ"-ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንን እና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ።

አምላክና አባት የተባለው እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ሁሉ ይመሰገናል፥ አሁንም ኢየሱስ "በ" በሚል መስተዋድድ አስመላኪ እንጂ "ለ" በሚል መስተዋድድ ተመላኪ አይደለም፦
ቆላስይስ 3፥17 እግዚአብሔር አብን "በ"-እርሱ እያመሰገናችሁ።

የሚመሰገነው አብ በማን ነው? ስንል "በ"-ኢየሱስ ነው። "በ" የሚለው መስተዋድድ አስምሩበት! እግዚአብሔር አብ "በ"-ኢየሱስ ይመሰገናል፦
ሮሜ 1፥8 አምላኬን "በ"-ኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ።

ጳውሎስ አምላኩን እግዚአብሔርን በኢየሱስ ክርስቶስ ያመሰግናል። ሌላ ቦታ ላይ ደግሞ የምስጋናን መሥዋዕት የሚቀርበው "ለ"እግዚአብሔር "በ"ክርስቶስ እንደሆነ ይናገራል፦
ዕብራውያን 13፥15 እንግዲህ ዘወትር "ለ"-እግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ "በ"-እርሱ እናቅርብለት።

"በ" አስመላኪ ሲሆን "ለ" ደግሞ ተመላኪ ነው። ብቻውን ጥበብ ላለው "ለ"-እግዚአብሔር ክብር የሚሰጠው "በ"-ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፦
ሮሜ 7፥25 "በ"-ኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን "ለ"-እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።
ሮሜ 16፥27 ብቻውን ጥበብ ላለው "ለ"-እግዚአብሔር "በ"-ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን! አሜን።

"በ" የሚለውን "ለ" ብሎ ከተረዱት እንግዲያውስ "በ"-ጽዮን" የሚለውን "ለ"-ጽዮን" ብለው መረዳት ይኖርባቸዋል፦
መዝሙር 65፥1 አቤቱ "በ"-ጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል።  לַמְנַצֵּ֥חַ מִזְמֹ֗ור לְדָוִ֥ד שִֽׁיר׃ לְךָ֤ דֻֽמִיָּ֬ה תְהִלָּ֓ה אֱלֹ֘הִ֥ים בְּצִיֹּ֑ון

ዋናው ነጥብ ጉልበት ሁሉ የሚንበረከክ ለኢየሱስ ስም ሳይሆን በኢየሱስ ስም ለፈጣሪ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ አስመላኪ እንጂ ተመላኪ አይደለም፥ ለፈጣሪው ተንበርክኮ የሚያመልክ አካል ተመልሶ ተመላኪ አይሆንም። ኢየሱስ እራሱ በጉልበቱ ተንበርክኮ እና በፊቱ ተደፍቶ ወደ ፈጣሪ ይጸልይ ነበር፦
ማቴዎስ 26፥39 ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀ እና ሲጸልይ።
ሉቃስ 22፥41 ከእነርሱም የድንጋይ ውርወራ የሚያህል ራቀ፥ ተንበርክኮም።

ሸብረክ እና ብርክክ ብሎ ለፈጣሪው ሡጁድ የሚወርድ ኢየሱስ እራሱ አምላኪ መሆኑን ይህ ጥቅስ ጉልኅ ማሳያ ነው። እናንተም እንደ ኢየሱስ አሏህን እንጂ ሌላን አትገዙ፦
11፥2 እንዲህ በላቸው፡- «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስጠንቃቂ እና አብሳሪ ነኝ፡፡» أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ ۚ إِنَّنِي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ባለ ሦስት ፊት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

112፥1 በል «እርሱ አላህ አንድ ነው»፡፡ قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ

አምላካችን አሏህ በምንነት ሆነ በማንነት አንድ አምላክ ነው፥ ከእርሱ ጋር ምንነቱን የሚጋሩ የሆኑ ማንነቶች የሉም። ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፦
112፥1 በል «እርሱ አላህ አንድ ነው»፡፡ قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ
20፥14 እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ፡፡ ሶላትን እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ إِنَّنِي أَنَا اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدْنِي وَأَقِمِ الصَّلَاةَ لِذِكْرِي

"ሸኽስ" شَخْص ማለት "እኔነት"person" ማለት ሲሆን "ማን" ተብሎ የሚጠየቅ "ማንነት" ነው፥ ከነሕው ሕግ አንጻር በሙተከለም "አና" أَنَا እና በጋዒብ "ሁወ" هُوَ ብለን የምንጠቀመው ለሙፍረድ ሸኽስ ነው። "እኔ" ብሎ ሦስት አካል የለምና፥ ባይሆን "እኔ" ማለቱ በራሱ አንድ "እኔነት" እንደሆነ ቁልጭ እና ፍንትው አርጎ ያሳያል።
እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 220 ድህረ-ልደት ጠርጡሊያኖስ፦ "አምላክ በምንነት አንድ በማንነት ሦስት ነው" ብሎ የሥላሴን ቀመር ቀምሯል። "ኡሲያ" οὐσία ማለት "ኑባሬ" "ሃልዎት" "ህላዌ" ማለት ሲሆን ግሪካውያን "ምንነትን" ለማሳየት የሚጠቀሙበት ስያሜ ነው፥ "ፕሮሶፓን" πρόσωπον የሚለው ቃል "ፕሮስ" πρός ማለትም "ዘንድ" እና "ኦፕስ" ὤψ ማለትም "ዓይን" ለሚለው ሁለት ቃላት ውቅር ሲሆን "ፊት" ወይም ለድራማ እና ለቲያትር ብለው ፊት ላይ የሚያጠልቁት "ጭንብል"mask" ማለት ነው፦
ማቴዎስ 6፥17 "ፊትህን" ታጠብ። τὸ πρόσωπόν σου νίψαι,

እዚህ አንቀጽ ላይ "ፊት" ለሚለው የገባው ቃል "ፕሮሶፓን" πρόσωπον እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። አንዱ አምላክ አብ አንድ ፊት እንዳለው በግልጽ ተቀምጧል፦
ራእይ 22፥3 "ፊቱንም" ያያሉ። καὶ ὄψονται τὸ πρόσωπον αὐτοῦ,
ማቴዎስ 18፥10 መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን "ፊት" ያያሉ እላችኋለሁና። λέγω γὰρ ὑμῖν ὅτι οἱ ἄγγελοι αὐτῶν ἐν οὐρανοῖς διὰ παντὸς βλέπουσι τὸ πρόσωπον τοῦ Πατρός μου τοῦ ἐν οὐρανοῖς.

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ፊት" ለሚለው የገባው ቃል "ፕሮሶፓን" πρόσωπον እንደሆነ ልብ አድርግ! በብሉይ ኪዳን ግሪክ ሰፕቱአጀንት ፈጣሪ አንድ ፊት እንዳለው ለማመልከት እና ለማመላከት በነጠላ "ፕሮሶፓን" πρόσωπον ተብሎ ተገልጿል፦
ዘጸአት 33፥20 ደግሞም፦ ሰው አይቶኝ አይድንምና "ፊቴን" ማየት አይቻልህም" አለ። καὶ εἶπεν· οὐ δυνήσῃ ἰδεῖν τὸ πρόσωπόν μου· οὐ γὰρ μὴ ἴδῃ ἄνθρωπος τὸ πρόσωπόν μου καὶ ζήσεται.

ባይብል ላይ ባለ ሦስት ፊት አምላክ ቢኖር ኖሮ "ፕሮሶፓ" πρόσωπᾰ ማለትም "ፊቶች" የሚል ቃል እናገኝ ነበር። ኢየሱስ ከአንዱ አምላክ በተለየ መልኩ የራሱ "ፊት" እንዳለው ተቀምጧል፦
ማቴዎስ 26፥39 ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በ-"ፊቱ" ወደቀ። καὶ προελθὼν μικρὸν ἔπεσεν ἐπὶ πρόσωπον αὐτοῦ,
ማርቆስ 1፥2 መንገድህን የሚጠርግ መልክተኛዬን በ-"ፊትህ" እልካለሁ። ἀποστέλλω τὸν ἄγγελόν μου πρὸ προσώπου σου,

አሁን እነዚህ አናቅጽ ላይ "ፊት" ለሚለው የገባው ቃል "ፕሮሶፓን" πρόσωπον ነው። "አንዱ አምላክ "ሦስት ፊት" አለው" የሚል ከዘፍጥረት እስከ ራእይ በባትሪ ብትፈልጉ አታገኙም፥ አንድ ምንነትን የሚጋሩ ባለ ሦስት ፊት አምላክ በህንድ ብራህማ፣ ቪሽኑ እና ሲቫ ሲሆኑ በግብጽ ደግሞ ኦስሪስ፣ አይሲስ እና ሆረስ ናቸው። ዋቢ መጽሐፍ ይህንን ተመልከቱ፦
[Bible Myths and Their parallels in other Religious By T.w Doane 1882 page 369]

የሥላሴ አማንያን በድፍረት "የእኛ አምላክ "ሥሉስ አምላክ" ነው" ብለዋል፥ "ሥሉስ አምላክ" ማለት "ሦስት አምላክ" ማለት ነው፦
፨ሃይማኖተ አበው ዘዲዮናስዮስ ምዕራፍ 99
“አምላካችን ያለ መለየት ሦስት ነው”።

፨የሐሙስ ሰይፈ ሥላሴ 22-23
“ሦስት ልዑላን ገዢዎች፥ ሦስት ጌቶች ናቸው”

፨መድብለ እንዚራ ስብሐት 11፥69
“ሦስቱ ገዢዎችም በአንቺ ተጠለሉ"

የሥላሴ አማንያን ሆይ! "ፈጣሪን ሦስት ፊት፣ ሦስት ጌቶች፣ ሥሉስ አምላክ(ሦስት አምላክ)፣ ሥሉስ ቅዱስ(ሦስት ቅዱስ)፣ ሦስት ልዑላን ገዢዎች ነው" አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፦
4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም