ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
70 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
መካህ እና መዲናህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

9፥28 *"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አጋሪዎች እርኩሶች ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህም ዓመታቸው በኋላ የተከበረውን መስጊድ አይቅረቡ"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّمَا الْمُشْرِكُونَ نَجَسٌ فَلَا يَقْرَبُوا الْمَسْجِدَ الْحَرَامَ بَعْدَ عَامِهِمْ هَـٰذَا

“መካህ” مَـكَّـة‎ ወይም “በካህ” بَكَّة አምላካችን አሏህ የማለበት እና ጸጥተኛ አገር ነው፦
90፥1 *”በዚህ አገር እምላለሁ”*፡፡ لَا أُقْسِمُ بِهَـٰذَا الْبَلَدِ
95፥3 *”በዚህ በጸጥተኛው አገርም እምላለሁ”*፡፡ وَهَـٰذَا الْبَلَدِ الْأَمِينِ

ለሰዎች መጸለያ መጀመሪያ የተኖረው ቤት በዚህ አገር ውስጥ ይገኛል፥ ይህም የአሏህ ቤት "በይቱል ሐረም" بَيْت الْحَرَام ማለትም "የተቀደሰው ቤት" ወይም "የተከበረው ቤት" ይባላል፦
3፥96 *"ለሰዎች መጸለያ መጀመሪያ የተኖረው ቤት ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲኾን ያ በበካህ ያለው ነው"*፡፡ إِنَّ أَوَّلَ بَيْتٍ وُضِعَ لِلنَّاسِ لَلَّذِي بِبَكَّةَ مُبَارَكًا وَهُدًى لِّلْعَالَمِينَ
5፥97 *"ከዕባን የተከበረውን ቤት፣ ክልክል የኾነውንም ወር፣ መስዋዕቱን እና ባለ ምልክቶቹንም መንጋዎች አላህ ለሰዎች መቋቋሚያ አደረገ"*፡፡ جَعَلَ اللَّهُ الْكَعْبَةَ الْبَيْتَ الْحَرَامَ قِيَامًا لِّلنَّاسِ وَالشَّهْرَ الْحَرَامَ وَالْهَدْيَ وَالْقَلَائِدَ

የዚህን ቤት መሠረት የጣለው ኢብራሂም ነው፥ ይህ ቤት ያለበትን አገር የቀደሰውም እርሱ ነው። ልክ ነቢያችን"ﷺ" መዲናን ለመሥጂድ እንደቀደሱት ኢብራሂም መካህን ለመሥጂዱል ሐረም ቀድሶታል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 15, ሐዲስ 521
ጃቢር እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ኢብራሂም መካን ቀድሷል፥ እኔም መዲናን ቀድሻለው"*። عَنْ جَابِرٍ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ إِبْرَاهِيمَ حَرَّمَ مَكَّةَ وَإِنِّي حَرَّمْتُ الْمَدِينَةَ

"ሐረምቱ" حَرَّمْتُ የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! "ሐረመ" حَرَّمَ ማለት "ቀደሰ" ወይም "አከበረ" ማለት ነው፥ ይህ መካህ የሚገኘው መሥጂድ እራሱ "መሥጂዱል ሐረም” مَسْجِد الْحَرَام ማለትም “የተቀደሰው መሥጂድ” ወይም "የተከበረው መሥጂድ" ይባላል፦
9፥28 *"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አጋሪዎች እርኩሶች ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህም ዓመታቸው በኋላ የተከበረውን መስጊድ አይቅረቡ"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّمَا الْمُشْرِكُونَ نَجَسٌ فَلَا يَقْرَبُوا الْمَسْجِدَ الْحَرَامَ بَعْدَ عَامِهِمْ هَـٰذَا

"ነጀሥ" نَجَس የሚለው ቃል "ነጂሠ" نَجِسَ ማለትም "ረከሰ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ርኩስ" ማለት ነው፥ መካህ እና መዲና የተቀደሱ ሥፍራዎች ስለሆኑ በሺርክ የተነጃጀሡ ሙሽሪኮች ወደ እዛ እንዳይቀርቡ አምላካችን አሏህ፦ "የተከበረውን መስጊድ አይቅረቡ" በማለት ነግሮናል። ተወዳጁ ነቢያችንም"ﷺ" በሐዲስ ላይ ከእነዚህ ስፍራዎች ክርስቲያን እና አይሁድ እንዲወጡ አዘዋል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 21, ሐዲስ 69
ዑመር ኢብኑ ኸጧብ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ብኖር ኢንሻሏህ አይሁድ እና ክርስቲያንን ከዐረቢያ ባሕረ-ገብ አስወጣለው"*። عَنْ عُمَرَ بْنِ الْخَطَّابِ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لَئِنْ عِشْتُ إِنْ شَاءَ اللَّهُ لأُخْرِجَنَّ الْيَهُودَ وَالنَّصَارَى مِنْ جَزِيرَةِ الْعَرَبِ ‏"‏

"ጀዚራህ" جَزِيرَة ማለት "ባሕረ-ገብ" ማለት ሲሆን ይህም የዐረቢያ ባሕረ-ገብ በነቢያችን"ﷺ" ጊዜ እና በቀደምት ሠለፎች ጊዜ 180,000 km2 የሆነውን መካህን እና መዲህናን የሚያመለክት ብቻ ነው። ሚሽነሪዎች ግን በዘመናችን ያሉትን 3,237,500 km2 የያዘውን የዐረቢያ "ባሕረ-ገብ"Peninsula" ባህሬንን፣ ጆርዳንን፣ ኩዌትን፣ ኦማንን፣ ኳታርን፣ የመንን፣ ሠዑዲይን፣ ኢማራትን በማመልከት ከዐረቢያ ምድር አህሉል ኪታብ እንዲወጡ እንደታዘዘ ይናገራሉ፥ ቅሉ ግን "ጀዚራቱል ዐረብ" جَزِيرَة الْعَرَب የተባለው "አል-ሒጃዝ" ٱلْحِجَاز‎ ነው። "ሒጃዝ" حِجَاز‎ የሚለው ቃል "ሐጀዘ" حَجَزَ ማለትም "ለየ" "ከለለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የተለየ" "የተከለለ" ማለት ነው፥ መካህ እና መዲናህ የተቀደሱ ሥፍራዎች በመሆን ተለይተዋል፤ ተከልለዋል። ከላይ ያለውን ሐዲስ የተረከልን ዑመር ኢብኑ ኸጧብ እራሱ አይሁድ እና ክርስቲያን ከአል-ሒጃዝ ምድር አስወጥቷል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 57, ሐዲስ 60
ዑመር ኢብኑ ኸጧብ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"ዑመር ኢብኑ ኸጧብ አይሁድ እና ክርስቲያን ከአል-ሒጃዝ ምድር አስወጣ"*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما أَنَّ عُمَرَ بْنَ الْخَطَّابِ، أَجْلَى الْيَهُودَ وَالنَّصَارَى مِنْ أَرْضِ الْحِجَازِ
ቁርኣን እና ሐዲስ ውስጥ እየተፈናጀሉ መፈናጀል ብቻ ሳይሆን ባይብል ውስጥ እኮ እግዚአብሔር እራሱ ለምጻሙን ሁሉ፥ ፈሳሽ ነገርም ያለበትን ሁሉ፥ በሬሳም የረከሰውን ሁሉ ከሰፈሩ እንዲያወጡ አዟቸዋል፦
ዘኍልቍ 5፥1-4 *"እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ የእስራኤል ልጆች ለምጻሙን ሁሉ፥ ፈሳሽ ነገርም ያለበትን ሁሉ፥ በሬሳም የረከሰውን ሁሉ ከሰፈሩ እንዲያወጡ እዘዛቸው፤ ወንዱንና ሴቱን አውጡ፤ እኔ በመካከሉ የማድርበትን ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ ከሰፈሩ አውጡአቸው። የእስራኤልም ልጆች እንዲሁ አደረጉ፥ ከሰፈሩ አወጡአቸው፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተናገረው፥ የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ"*።

"ሰፈር"camp" ሁሉም ሰው የማይገባበት ሥፍራ ነው። ከላይ የተዘረዘሩት ሰዎች የሚወጡበት ምክንያት ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ ነው፥ "ከሰፈሩ አወጡአቸው" የሚለው ይሰመርበት። በአዲስ ኪዳንም ቢሆን ሴሰኛ ወይም ገንዘብን የሚመኝ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካር ወይም ነጣቂ ከሆነ ከእርሱ ጋር ምግብ መብላት የተከለከ ነው፥ ከዚያም ባሻገር፦ "አውጡት" የሚል ወፍራም ትእዛዝ አለ፦
1ኛ ቆሮንቶስ 5፥11-13 *"አሁን ግን ወንድሞች ከሚባሉት አንዱ ሴሰኛ ወይም ገንዘብን የሚመኝ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካር ወይም ነጣቂ ቢሆን ከእርሱ ጋር እንዳትተባበሩ እጽፍላችኋለሁ፤ እንደነዚህ ካለው ጋር መብል እንኳን አትብሉ። ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት"*።

የማትገቡበት ቦታ የማትረግጡት ዋልታ እንደሌለ ሁሉ እኛም ባይብል ላይ ገብተን አሳብን ረብጣ በሆነ አሳብ ማረቃችንና ማርቀቃችን አይቀርም። የወታደር ሰፈር"cantonment" ለተለየ ዓላማ ከወታደር ውጪ ማንም አይገባም፥ የገባም እንዲወጣ ይደረጋል፥ ያ ማለት ሰውን ማግለል እንዳልሆነ እና እዛ ሰፈር ለመግባት መስፈርቱ ወታደር መሆን እንደሆነ ሁሉ መካህ እና መዲናህ ውስጥ ለመኖር መስፈርቱ ሙሥሊም መሆን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ግብረ-ሰዶም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

15፥74 *ላይዋንም ከታችዋ አደረግን፡፡ በእነሱም ላይ የሸክላ ደንጊያዎችን አዘነብንባቸው*፡፡ فَجَعَلْنَا عَالِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِمْ حِجَارَةً مِّن سِجِّيلٍ

ሥነ-ጋብቻ ጥናት””matrimony” ስለ ጋብቻ ሲናገር በዋነኝነት ለሁለት ይከፍሉታል፦ አንደኛ “ተቃራኒ ጾታ ጋብቻ”Hetero-sexual” ሲሆን ሁለተኛው “ተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ”homo-sexual” ” ነው።
ተቃራኒ ጾታ ጋብቻ በመለኮት መጽሐፍት ውስጥ የተቀመጠ ሲሆን ተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ግን በመለኮት መጽሐፍት ውስጥ አንዳች ድጋፍ የሌለው ነው።
ግብረ-ሰዶም”homosexual” ማለት የሰዶማውያን ሥራ ማለት ነው፤ ግብረ-ሰዶም በራሱ ለሁለት ይከፈላል፤ እርሱም፦ በወንድ እና በወንድ መካከል ያለው የግብረ ሰዶማዊ ግንኙነት”Gays” አንዱ ሲሆን ሌላው ደግሞ በሴት እና በሴት መካከል ያለው የግብረ ሰዶማዊ ግንኙነት”Lesbians” ነው። አምላካችን አላህ ነብዩ ሉጥን በዚህ ድርጊት በተሰማሩ ሕዝቦች መካከል ፍርድንና ዕውቀትን ሰጥቶ ላከው፤ ሉጥም በእርግጥ ከመልክተኞቹ አንዱ ነው፦
37፥133 *ሉጥም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው*። وَإِنَّ لُوطًا لَّمِنَ الْمُرْسَلِينَ
21፥74 *ሉጥንም ፍርድንና ዕውቀትን ሰጠነው፡፡ ከዚያችም መጥፎ ሥራዎችን ትሠራ ከነበረችው ከተማ አዳንነው፡፡ እነርሱ ክፉ ሰዎች አመጸኞች ነበሩና*፡፡ وَلُوطًا آتَيْنَاهُ حُكْمًا وَعِلْمًا وَنَجَّيْنَاهُ مِنَ الْقَرْيَةِ الَّتِي كَانَت تَّعْمَلُ الْخَبَائِثَ ۗ إِنَّهُمْ كَانُوا قَوْمَ سَوْءٍ فَاسِقِينَ

የሰዶም ከተማ ይሰሩት የነበረው መጥፎ ሥራ ይህ ነው፤ በዚህ ሥራቸው ክፉ ሰዎችና አመጸኞች ናቸው። ሉጥንም ለሕዝቦቹ፦ “እናንተ የምታዩ ስትኾኑ ፀያፍን ነገር ትሠራላችሁን? በእርሷ ከዓለማት አንድም አልቀደማችሁም” አላቸው፦
27፥54 ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ *”እናንተ የምታዩ ስትኾኑ ፀያፍን ነገር ትሠራላችሁን?”* وَلُوطًا إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ أَتَأْتُونَ الْفَاحِشَةَ وَأَنتُمْ تُبْصِرُونَ
29፥28 ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ *”እናንተ ጠያፍን ስራ ትሠራላችሁን? በእርሷ ከዓለማት አንድም አልቀደማችሁም”*፡፡ وَلُوطًا إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ إِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ الْفَاحِشَةَ مَا سَبَقَكُم بِهَا مِنْ أَحَدٍ مِّنَ الْعَالَمِينَ
7፥80 ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ *”አስቀያሚን ሥራ ትሠራላችሁን? በእርሷ ከዓለማት አንድም አልቀደማችሁም”*፡፡ وَلُوطًا إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ أَتَأْتُونَ الْفَاحِشَةَ مَا سَبَقَكُم بِهَا مِنْ أَحَدٍ مِّنَ الْعَالَمِينَ

“ከዓለማት አንድም አልቀደማችሁም” ማለት ይህንን ድርጊት ጀማሪዎቹ እነርሱ መሆናቸውን ያሳያል። ወንዶቹ ሴቶች እያሉ ከወንድ ጋር መዳራታቸው ወሰን ማለፍ ነው፦
7፥81 *”እናንተ ከሴቶች ሌላ ወንዶችን በመከጀል በእርግጥ ትመጡባቸዋላችሁን? በእውነቱ እናንተ ወሰንን አላፊዎች ሕዝቦች ናችሁ”*፡፡ إِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ الرِّجَالَ شَهْوَةً مِّن دُونِ النِّسَاءِ ۚ بَلْ أَنتُمْ قَوْمٌ مُّسْرِفُونَ
26፥166 *”ከሚስቶቻችሁም ጌታችሁ ለእናንተ የፈጠረላችሁን ትተዋላችሁን? በእውነቱ እናንተ ወሰን አላፊዎች ሕዝቦ ናችሁ”*፡፡ وَتَذَرُونَ مَا خَلَقَ لَكُمْ رَبُّكُم مِّنْ أَزْوَاجِكُم ۚ بَلْ أَنتُمْ قَوْمٌ عَادُونَ

ይህንን ድርጊት በጀመሩት በሰዶማውያን ላይ አላህ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን በመላክ የሸክላ ደንጊያዎችን አዘነበባቸው፦
54፥34 *እኛ በእነርሱ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን ላክን፡፡ የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ እነርሱን በሌሊት መጨረሻ ላይ አዳንናቸው*፡፡ إِنَّا أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ حَاصِبًا إِلَّا آلَ لُوطٍ ۖ نَّجَّيْنَاهُم بِسَحَرٍ
15፥74 *ላይዋንም ከታችዋ አደረግን፡፡ በእነሱም ላይ የሸክላ ደንጊያዎችን አዘነብንባቸው*፡፡ فَجَعَلْنَا عَالِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِمْ حِجَارَةً مِّن سِجِّيلٍ
7፥84 *በእነርሱም ላይ ዝናብን አዘነብንባቸው፡፡ የኃጢአተኞችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት*፡፡ وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِم مَّطَرًا ۖ فَانظُرْ كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُجْرِمِينَ
26፥173 *በእነርሱም ላይ የድንጋይን ዝናምን አዘነምንባቸው፤ የተስፈራሪዎቹም ዝናም ምንኛ ከፋ*፡፡ وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِم مَّطَرًا ۖ فَسَاءَ مَطَرُ الْمُنذَرِينَ
ይህ ድርጊት አላህ ዘንድ እጅግ ክፉ ስለነበር ከተማዎቹ ላይዋንም ከታችዋ ተገለበጡ፦
15፥74 *ላይዋንም ከታችዋ አደረግን፡፡ በእነሱም ላይ የሸክላ ደንጊያዎችን አዘነብንባቸው*፡፡ فَجَعَلْنَا عَالِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِمْ حِجَارَةً مِّن سِجِّيلٍ
9፥70 የእነዚያ ከእናንተ በፊት የነበሩት የኑሕ ሕዝቦች፣ የዓድና የሰሙድም፣ የኢብራሂምም ሕዝቦች የመድየን ባለቤቶች እና *የተገልባጮቹም ከተሞች ወሬ አልመጣላቸውምን?* أَلَمْ يَأْتِهِمْ نَبَأُ الَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ قَوْمِ نُوحٍ وَعَادٍ وَثَمُودَ وَقَوْمِ إِبْرَاهِيمَ وَأَصْحَابِ مَدْيَنَ وَالْمُؤْتَفِكَاتِ
53፥53 *የተገለበጠችውንም ከተማ ደፋ*፡፡ وَالْمُؤْتَفِكَةَ أَهْوَىٰ

ከላይ ያየነው የሰዶማውያን ሥራ ወሰን ማለፍ እንደሆነ ሉጥ እንዳስጠነቀቃቸው ሀሉ አላህም በቁርኣን የነገረን ከተቃራኒ ጾታ ውጪ የያደርጉ እነርሱ ወሰን አላፊዎች ናቸው፤ ወሰንንም አትለፉ ተብለናል፦
23፥6 *በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዟቸው ላይ ሲቀር፤ እነርሱ በእዚህ የማይወቀሱ ናቸውና፡፡ ከዚህም ወዲያ የፈለጉ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ወሰን አላፊዎች ናቸው*፡፡ إِلَّا عَلَىٰ أَزْوَاجِهِمْ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُمْ فَإِنَّهُمْ غَيْرُ مَلُومِينَ فَمَنِ ابْتَغَىٰ وَرَاءَ ذَٰلِكَ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْعَادُونَ
11፥112 *እንደ ታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡ ከአንተ ጋር ያመኑትም ቀጥ ይበሉ፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና*፡፡ فَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ وَمَن تَابَ مَعَكَ وَلَا تَطْغَوْا ۚ إِنَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

ይህ ድርጊት በማድረግ ወሰን ያለፈ የሚጠብቀው ቅጣት በአኺራ እሳት ነው፦
4፥30 *ወሰን በማለፍና በመበደልም ይህንን የሠራ ሰው እሳትን እናገባዋለን*፡፡ ይኸም በአላህ ላይ ገር ነው፡፡ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ عُدْوَانًا وَظُلْمًا فَسَوْفَ نُصْلِيهِ نَارًا ۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرًا

በዱኒያህ ደግሞ ያለው ቅጣት በኢስላም የሙስሊም ሸሪዓ ባለበት ህገ-መንግሥት ግድያ ነው፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 20, ሐዲስ 2658
ከኢብኑ ዐባሥ እንደተላለፈው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ *”ማንም የሉጥ ሕዝብ የሚያደርጉት ድርጊት ሲያደርጉ ብታገኙ ሁለቱንም ግደሏቸው”*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ مَنْ وَجَدْتُمُوهُ يَعْمَلُ عَمَلَ قَوْمِ لُوطٍ فَاقْتُلُوا الْفَاعِلَ وَالْمَفْعُولَ بِهِ ‏”‏ ‏

ሚሽነሪዎች፦ “በኢስላም ግብረ-ሰዶም ሃራም የሆነበት ጥቅስና ቅጣት የለም” ብለው ሲቀጥፉ ተመልሰው ደግሞ፦ “እንዴት ይገደላል? መብቱ ነው” ይላሉ፤ ይህንን የሚሉት የምዕራባውያንን እሳቦትና ዕርዮት ይዘው ነው። መብቱ ከሆነ ለምን ፈጣሪ ሰዶማውያንን በዚህ ድርጊታቸው አጠፋቸው? ለምንስ ይህንን ድርጊት የሚፈጽሙ ይገደሉ አለ?፦
ዘፍጥረት 19፥24 *እግዚአብሔርም በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበ፤ እነዚያንም ከተሞች፥ በዙሪያቸው ያለውንም ሁሉ፥ በከተሞቹም የሚኖሩትን ሁሉ፥ የምድሩንም ቡቃያ ሁሉ ገለበጠ*።
ዘሌዋውያን 20፥13 *ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በላያቸው ነው*።

ይህ ብሉይ ኪዳን ላይ ነው እንዳትሉ በአዲስ ኪዳን የተፈቀደበትን ጥቅስ ማምጣት ይጠበቅባችኃል። በአዲስ ኪዳን መፍቀድም መከልከልም የሚችል ነብይ ኢየሱስ ነው፤ ኢየሱስ ሕግን ለመሻር አልመጣሁም ብሏል፤ እንደውም ሰማይና ምድር እስከሚያልፍ ድረስ የሙሴ ሕግ እንደሚሰራ ይናገራል፦
ማቴዎስ 5፥17 *እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ*።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የአይሁዳውያን ፈሣድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥64 *"ለጦር እሳትን ባጫሩ ቁጥር አላህ ያጠፋታል፡፡ በምድርም ውስጥ ለማበላሸት ይሮጣሉ፡፡ አላህም አበላሺዎችን አይወድም"*፡፡ كُلَّمَا أَوْقَدُوا نَارًا لِّلْحَرْبِ أَطْفَأَهَا اللَّهُ ۚ وَيَسْعَوْنَ فِي الْأَرْضِ فَسَادًا ۚ وَاللَّهُ لَا يُحِبُّ الْمُفْسِدِينَ

"ፈሣድ" فَسَاد የሚለው ቃል "ፈሠደ" فَسَدَ ማለትም "አበላሸ" "አጠፋ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ብልሽት" ወይም "ጥፋት" ማለት ነው፥ በፈሣድ የተሰማሩ ሰዎች በነጠላ "ሙፍሢድ" مُفْسِد በብዜት "ሙፍሢዲን" مُفْسِدِين ይባላሉ። አይሁዳውያን ለጦር እሳትን ማጫር እና በምድርም ውስጥ ለማበላሸት መሮጣቸውን አምላካችን አሏህ ይነግረናል፦
5፥64 *"ለጦር እሳትን ባጫሩ ቁጥር አላህ ያጠፋታል፡፡ በምድርም ውስጥ ለማበላሸት ይሮጣሉ፡፡ አላህም አበላሺዎችን አይወድም"*፡፡ كُلَّمَا أَوْقَدُوا نَارًا لِّلْحَرْبِ أَطْفَأَهَا اللَّهُ ۚ وَيَسْعَوْنَ فِي الْأَرْضِ فَسَادًا ۚ وَاللَّهُ لَا يُحِبُّ الْمُفْسِدِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "አበላሺዎች" ለሚለው የገባው ቃል "ሙፍሢዲን" مُفْسِدِين እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። አይሁዳውያን በምድር ላይ በእርግጥ ሁለት ጊዜ ያበላሻሉ፦
17፥4 *"ወደ እስራኤል ልጆች በመጽሐፉ ውስጥ እንዲህ በማለት አወረድን፦ "በምድር ላይ በእርግጥ ሁለት ጊዜ ታጠፋላችሁ፥ ትልቅንም ኩራት ትኮራላችሁ"* وَقَضَيْنَآ إِلَىٰ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ فِى ٱلْكِتَٰبِ لَتُفْسِدُنَّ فِى ٱلْأَرْضِ مَرَّتَيْنِ وَلَتَعْلُنَّ عُلُوًّۭا كَبِيرًۭا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ታጠፋላችሁ" ለሚለው የገባው ቃል "ለቱፍሢዱነ" لَتُفْسِدُنَّ ሲሆን "ታበላሻላችሁ" ማለት ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ባመጡት ፈሣድ ቅጣቱ ለአሏህ የኾኑን ባሮች የብርቱ ኃይል ባለቤቶች የኾኑትን ናቡነደፆርን እና ሰራዊቱን በ 606 ቅድመ-ልደት”BC” ተነስተው ሡለይማን የገነባውን በይቱል መቅዲሥ አጥፍተውታል፥ በመቀጠል እንደ ግሪጎርያን አቆጣጠር በ 70 ድህረ-ልደት”AD” የሮም ጦር መሪ የሆነው ጀነራል ቲቶ እና ሰራዊቱ ከበው አጥፍተዋል። ይህ ተፈጻሚ ቀጠሮም ነበር፦
17፥5 *“ከሁለቱ የመጀመሪያይቱ ቀጠሮ በመጣም ጊዜ ለእኛ የኾኑን ባሮች የብርቱ ኃይል ባለቤቶች የኾኑትን በእናንተ ላይ እንልካለን፡፡ በቤቶችም መካከል ይበረብሩታል፡፡ ይህ ተፈጻሚ ቀጠሮም ነበር"*፡፡ فَإِذَا جَاءَ وَعْدُ أُولَاهُمَا بَعَثْنَا عَلَيْكُمْ عِبَادًا لَّنَا أُولِي بَأْسٍ شَدِيدٍ فَجَاسُوا خِلَالَ الدِّيَارِ ۚ وَكَانَ وَعْدًا مَّفْعُولًا

ከዚያ አምላካችን አሏህ ነቢያችንን”ﷺ” ከመሥጂዱል ሐረም ወደ መሥጂዱል አቅሷ በሌሊት አስኪዷቸዋል፦
17፥1 ”ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጊድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ ሩቁ መስጊድ በሌሊት ውስጥ ያስኼደው ጌታ ጥራት ይገባው፡፡ ከተዓምራቶቻችን ልናሳየው አስኼድነው”፡፡ እነሆ እርሱ አላህ ሰሚው ተመልካቺው ነው፡፡ سُبْحَانَ الَّذِي أَسْرَىٰ بِعَبْدِهِ لَيْلًا مِّنَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ إِلَى الْمَسْجِدِ الْأَقْصَى الَّذِي بَارَكْنَا حَوْلَهُ لِنُرِيَهُ مِنْ آيَاتِنَا ۚ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ያስኼደው” ለሚለው የገባው የግስ መደብ “አሥሯ” أَسْرَىٰ ሲሆን “ኢሥሯ” إِسْرَا የሚለው የስም መደብ እራሱ “ሣረ” سَارَ ማለትም “ተጓዘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ጉዞ” ማለት ነው። “ለይለቱል ኢሥሯ” لَيْلَة الإِسْرَا ማለት “የሌሊት ጉዞ” ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ ነቢያችንን”ﷺ” ከበይቱል ሐረም ወደ በይቱል መቅዲሥ በሌሊት ያስኬዳቸው “አል-ቡራቅ” በሚባል እንስሳ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 318
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ከአህያ ከፍ ብሎ ከበቅሎ ያነሰ፥ ነጭና ረዘም ያለ እንስሳ አል-ቡራቅ መጣልኝ። የእይታው መጨረሻ ላይ ኮቴውን ያሳርፋል፥ በእርሱ እስከ በይቱል መቅዲሥ ተጓዝኩኝ”*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ أُتِيتُ بِالْبُرَاقِ – وَهُوَ دَابَّةٌ أَبْيَضُ طَوِيلٌ فَوْقَ الْحِمَارِ وَدُونَ الْبَغْلِ يَضَعُ حَافِرَهُ عِنْدَ مُنْتَهَى طَرْفِهِ – قَالَ فَرَكِبْتُهُ حَتَّى أَتَيْتُ بَيْتَ الْمَقْدِسِ
“አል-ቡራቅ” الْبُرَاق የሚለው ቃል “በረቀ” بَرَقَ ማለትም “በረቀ” “በለጨ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ብርቅታ” “ብልጭታ” ማለት ነው፥ “መብረቅ” እራሱ “በርቅ” بَرْق ይባላል። ይህ እንስሳ ከአህያ ከፍ ብሎ ከበቅሎ ያነሰ፥ ነጭና ረዘም ያለ እንስሳ ነው። ይህ የተቀደሠ ሥፍራ በዚያ ጊዜ በሮሙ ባዛንታይን ሥር ነበር፥ ከዚያ እንደ ጎርጎሮሳውያን በ 640 ድኅረ-ልደት በዑመር ኢብኑል ኸጧብ"ረ.ዐ." ጀምሮ እስከ እስከ 1917 ድኅረ-ልደት በሙሥሊም የተለያዩ መንግሥት፣ ግዛት እና ሥርወ-መንግሥት ሥር ነበር። ከዚያ በእንግሊዝ አማካኝነት አይሁዳውያን ከተበተነቡት ወዚህ ቅዱስ ሥፍራ ተሰበሰቡ፥ አምላካችን አሏህ፦ "የኋለኛይቱም ቀጠሮ በመጣ ጊዜ እናንተን የተከማቻችሁ ስትኾኑ እናመጣችኋለን" ባለው መሠረት መጡ፦
17፥104 *"ከእርሱም በኋላ ለእሰራኤል ልጆች «ምድሪቱን ተቀመጡባት የኋለኛይቱም ቀጠሮ በመጣ ጊዜ እናንተን የተከማቻችሁ ስትኾኑ እናመጣችኋለን» አልናቸው"*፡፡ وَقُلْنَا مِن بَعْدِهِ لِبَنِي إِسْرَائِيلَ اسْكُنُوا الْأَرْضَ فَإِذَا جَاءَ وَعْدُ الْآخِرَةِ جِئْنَا بِكُمْ لَفِيفًا

ከዚያም በኋላ አሏህ ለእነርሱ ድልን መለስንላቸው፣ በገንዘቦችና በወንዶች ልጆችም ጨመረላቸው፣ በወገንም እንዲበዙ አረጋቸው፦
17፥6 *"ከዚያም በኋላ ለእናንተ በእነርሱ ላይ ድልን መለስንላችሁ፡፡ በገንዘቦችና በወንዶች ልጆችም ጨመርንላችሁ፡፡ በወገንም የበዛችሁ አደረግናችሁ"*፡፡ ثُمَّ رَدَدْنَا لَكُمُ الْكَرَّةَ عَلَيْهِمْ وَأَمْدَدْنَاكُم بِأَمْوَالٍ وَبَنِينَ وَجَعَلْنَاكُمْ أَكْثَرَ نَفِيرًا

አሁን ያለነው በኃለኛ ቀጠሮ ውስጥ ነው፥ አምላካችን አሏህ አይሁዳውያን ያጠፉትን ጥፋት እንዲያጠፉ ሙሥሊሞችን ይልካል፦
17፥7 ”የኋለኛይቱም ጊዜ ቀጠሮ በመጣ ጊዜ ፊቶቻችሁን ሊያስከፉ፣ መስጁዱንም በመጀመሪያ ጊዜ እንደገቡት ሊገቡ እና ያሸነፉትንም ሁሉ ፈጽመው ማጥፋትን እንዲያጠፉ እንልካቸዋልን”*፡፡ فَإِذَا جَآءَ وَعْدُ ٱلْـَٔاخِرَةِ لِيَسُۥٓـُٔوا۟ وُجُوهَكُمْ وَلِيَدْخُلُوا۟ ٱلْمَسْجِدَ كَمَا دَخَلُوهُ أَوَّلَ مَرَّةٍۢ وَلِيُتَبِّرُوا۟ مَا عَلَوْا۟ تَتْبِيرًا

"መስጁዱንም በመጀመሪያ ጊዜ እንደገቡት" የሚለው ይሰመርበት! መሥጂዱል አቅሷን ለመጀመሪያ ጊዜ የገቡት በዑመር ኢብኑል ኸጧብ"ረ.ዐ." ጊዜ ሙሥሊሞች ናቸው፥ ልክ እንደ እነርሱ ወደዚያ ቅዱስ ሥፍራ እንዲገቡ አሏህ ሙሥሊሞችን ይልካል። "ያሸነፉት" የተባሉት አይሁዳውያን ሲሆኑ የእነርሱ ሁለተኛው ፈሣድን ዛሬ ዓለምን አጥለቅቋል። "በምድር ላይ በእርግጥ ሁለት ጊዜ ታጠፋላችሁ" የሚለው ይሰመርበት! ዛሬ ጽዮናውያን አይሁድ በባንክ ወለድ፣ በአስካሪ መጠጥ ምርት፣ በዝሙት ፊልም ኢንዱስትሪ ዓለምን እያበላሹ ይገኛሉ። ይህንን የአይሁድ ፈሣድ እንዲያጠፉ ቅጣተ ፈጣን የሆነው አሏህ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ በእነርሱ ላይ ክፉ ቅጣትን የሚያቀምሳቸው ሙሥሊሞች ይልካል፦
17፥167 *"ጌታህም እስከ ትንሣኤ ቀን ክፉ ቅጣትን የሚያቀምሳቸውን በእነርሱ ላይ በእርግጥ የሚልክ መኾኑን ባስታወቀ ጊዜ አስታውሳቸው፡፡ ጌታህ በእርግጥ ቅጣተ ፈጣን ነው፡፡ እርሱም በእርግጥ እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው"*፡፡ وَإِذْ تَأَذَّنَ رَبُّكَ لَيَبْعَثَنَّ عَلَيْهِمْ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ مَن يَسُومُهُمْ سُوءَ الْعَذَابِ ۗ إِنَّ رَبَّكَ لَسَرِيعُ الْعِقَابِ ۖ وَإِنَّهُ لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 54, ሐዲስ 103
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ሙሥሊሞች ከአይሁድ ጋር ሳይዋጉ በፊት ሰዓቲቱ አትቆምም፥ አይሁዳዊ ከድንጋይ ወይም ከዛፍ ሥር ይደበቃሉ። ድንጋዩ እና ዛፉ፦ "ሙሥሊም ሆይ! የአሏህ ባሪያ ሆይ! ከእኔ ሥር አይሁድ ተደብቋልና ግደሉት" እስኪሏቸው ድረስ ሙሥሊሞች አይሁድን ይገሏቸዋል"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يُقَاتِلَ الْمُسْلِمُونَ الْيَهُودَ فَيَقْتُلُهُمُ الْمُسْلِمُونَ حَتَّى يَخْتَبِئَ الْيَهُودِيُّ مِنْ وَرَاءِ الْحَجَرِ وَالشَّجَرِ فَيَقُولُ الْحَجَرُ أَوِ الشَّجَرُ يَا مُسْلِمُ يَا عَبْدَ اللَّهِ هَذَا يَهُودِيٌّ خَلْفِي فَتَعَالَ فَاقْتُلْهُ ‏.‏ إِلاَّ الْغَرْقَدَ فَإِنَّهُ مِنْ شَجَرِ الْيَهُودِ ‏"‏ ‏.‏

"አይሁዳውያን ተሰብስበው መሢሕ መጥቶ የአይሁድ ንጉሥ ይሆናል" ብለው የሚያምኑ የዘመናችን ጽዮናውያን ክርስቲያን ከጽዮናውያን አይሁድ ጋር ማበራቸው አጂብ የሚያሰኝ ነው፥ ጽዮናውያን አይሁድ መሢሕ አርገው የሚቀበሉት እና የሚከተሉት ሐሣዌ መሢሑን ነው። አሏህ በጽዮናውያን አይሁድ ላይ የሚልካቸው ሙሥሊሞች ከነቢያችን"ﷺ" ኡማህ የመጨረሻዎቹ ከመሢሑ አድ-ደጃል ጋር እስኪጋደሉ ድረስ በሐቅ ላይ ሆነው በጠላቶቻቸው ላይ ድልን ይቀናጃሉ፥ እውነተኛው መሢሕ የመርየም ልጅ ዒሣ ሲመጣ በሻም ሉድ በር ላይ ሐሣዌ መሢሑን ያገኘው እና ይገለዋል፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 15, ሐዲስ 8
ዒምራን ኢብኑ ሑሶይን እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ከእኔ ኡማህ የመጨረሻዎቹ ከመሢሑ አድ-ደጃል ጋር እስኪጋደሉ ድረስ በሐቅ ላይ ሆነው በጠላቶቻቸው ላይ ድልን ይቀናጃሉ"*። عَنْ عِمْرَانَ بْنِ حُصَيْنٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لاَ تَزَالُ طَائِفَةٌ مِنْ أُمَّتِي يُقَاتِلُونَ عَلَى الْحَقِّ ظَاهِرِينَ عَلَى مَنْ نَاوَأَهُمْ حَتَّى يُقَاتِلَ آخِرُهُمُ الْمَسِيحَ الدَّجَّالَ ‏"‏ ‏.‏
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 33, ሐዲስ 87 ኢብኑ ጃሪያህ አል-አንሷሪይ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለለው፦ *"ዒሣ ኢብኑ መርየም በሉድ በር ላይ ደጃልን ይገለዋል"*። عَنْ بْنَ جَارِيَةَ الأَنْصَارِيَّ يَقُولُ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ يَقْتُلُ ابْنُ مَرْيَمَ الدَّجَّالَ بِبَابِ لُدٍّ ‏

አምላካችን አሏህ ከጽዮናውያን አይሁድ ፈሣድ ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ

ውድና የተከበራችሁ ወንድምና እሕቶቼ!

አምላካችን አላህ ፈቃዱ ከሆነ: በረመዷን ወር ተቋርጦ የነበረውን የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ማታ 3:30 እንቀጥላለን ኢንሻአላህ።
ዐቂቃህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

"ዐቂቃህ" عَقِيقه ማለት አዲስ ለተወለደ ሕፃን ልጅ የሚታረድ መስዋዕት የሚደረግ እርድ ነው። የተወደደ እና የተፀና የተከበደ ነቢያዊ"ﷺ" ፈለግ የሆነ እርድ ነው። ዐቂቃህ ማረድ "ማሱና ሙአከዳ" ማለትም በጣም የጠበቀ እና የተወደደ ሱናህ ነው። የዐቂቃህ ዓላማው የተደነገገበት ምክንያት ለአላህ ምስጋና ለማድረስ ነው። ይህም አንድ ሰው ልጅ ስለተወለደለት በመደሰት በ 7ኛው ቀን ደስታውን ለመግለፅ፣ ይህንንም ደስታውን ሰዎች እንዲያውቁት ለማድረግ እና የተወለደውም ልጅ የማን እንደሆነ ለማሣወቅ ነውና። አላህ ደግሞ ልጁን እንደሚጠብቀው፥ እንዲሁ ሷሊህ ልጅ እንዲሆንለት ምክንያትም እንዲሆነው የሚደረግ አርዶ ሰውን የማብላት ሥርዓት ዐቂቃህ ይባላል፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 27, ሐዲስ 3285
ሠሙራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ማንኛውም ሕጻን በዐቂቃው መውጣት አለበት። በሰባተኛው ቀን እርድ ይታረድለት፣ የራሱ ጸጉር ይላጭ እንዲሁ ስም ይውጣለት"*። عَنْ سَمُرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ "‏ كُلُّ غُلاَمٍ مُرْتَهَنٌ بِعَقِيقَتِهِ تُذْبَحُ عَنْهُ يَوْمَ السَّابِعِ وَيُحْلَقُ رَأْسُهُ وَيُسَمَّى

በአብዛኞቹ ሙሥሊም ምሁራን እንዳሉት ዐቂቃህ መደረግ ያለበት ትልቅ ሱናህ ነው፥ እንደ አንዳንድ ምሁራን ደግሞ ዐቂቃ ማድረግ ዋጅብ ማለትም የውዴታ ግዴታ ነው የሚሉ ዑለማዎችም አሉ። በላጩና የተመረጠው የዐቂቃህ ማውጫ ጊዜም ልጅ በተወለደ በሰባተኛው ቀን ነው የሚሆነው።

ወላጆች አሊያም አያቶች ማለትም የወላጅ አባት እና እናት ለልጃቸው አሊያም ለልጅ ልጃቸው ዐቂቃህ ማውጣት አለባቸውም ይችላሉም።
የተወለደው ልጅ ወንድ ከሆነ ሁለት በግ ወይም ሁለት ፍየል ሴት ከሆነች ደግሞ አንድ በግ ወይም አንድ ፍየል ሊታረድ ይወደዳል።

እንዲሁም ስሙን ደህና ኢሥላማዊ ስም በመምረጥ ሊጠራው ይገባል።
ለምሳሌ ወንድ ከሆነ ዐብዱራሕማን፣ ዐብዱላህ፣ ሙሐመድ ወዘተ ....ሲሆን ሴት ከሆነችም ደግሞ አሲያ፣ መሪየም፣ ኸዲጃ፣ ፈጢማ ወዘተ...ብሎ ስም ቢያወጣላቸው ይወደዳል።

የመስኩ ምሁራን፦ "ሰባተኛው ቀን ያልታረደ እንደሆነ በ14ኛው ቀን ሊታረድ ይችላል ያም ካልሆነ በ 21ኛው ቀን ቢያወጣ ችግር የለውም" ይላሉ። በአጠቃላይ አንድ ልጅ እስኪጎረምስ ድረስ ዐቂቃህ ማውጣት ይችላል የሚሉ ዐሊሞች አሉ፣ እናም ቀኑ አልፎዋል ብለን ይህን የጠበቀና የተወደደ የነቢያችን"ﷺ" ሱናህ ከመተግበር አንዘናጋ። ዑለማዎች፦ "ምን አልባት ሕፃኑ ሰባት ቀን ሳይሞላው የሞተ እንደሆነ ዐቂቃህ ማረዱ አስፈላጊ አይሆንም" ብለዋል።

አንድ ሰው በህፃንነቱ ወላጆቹ ዐቂቃህ ካላወጡለትና ትልቅ ሰው ከሆነ በሁዋላና አቅሙ ካለው ጓደኞቹን ሰብስቦ አላማውን ነግሯቸው ማለትም ዐቂቃህ እንደሆነ ነግሯቸው ዐቂቃህ ማውጣት ይችላል። ስለዚህ ዕድሜያችን የፈለገ ያህል ቢሆንም ዐቂቃን ነይተን ማውጣት እንችላለንና አንዘናጋ።

የታረደው እንሠሣ ሥጋው በዒድ አል-አድሃ በዓል እንደሚደረገው ሁሉ ሦስት ቦታ መከፈል አለበት። አንድ ሦስተኛው- ለድሃ፣ አንድ ሦስተኛው- ለጓደኞች እና አንድ ሦስተኛው ደግሞ ለቤተሰብ ይሠጣል።
አንድ ሰው የታረደውን ሥጋ ሁሉንም ለድሆችና ችግረኛ ሰዎች መስጠት ይችላል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፈረሰኛ ሆኖ ጦር እና ጋሻ ሳይዝ፣ ምንሽር እና ዝናር ሳታጠቅ፣ በሽለላ እና በቀረርቶ ሳይፎክር የብዙ ቢልዮን ልቦችን የማረከ ብቸኛው አሸናፊ መጽሐፍ የአሏህ ንግግር ቁርኣን ነው፦
41፥41 *"እነዚያ በቁርኣን እርሱ አሸናፊ መጽሐፍ ሲኾን በመጣላቸው ጊዜ የካዱት ጠፊዎች ናቸው"*፡፡ إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا بِالذِّكْرِ لَمَّا جَاءَهُمْ ۖ وَإِنَّهُ لَكِتَابٌ عَزِيزٌ

ይህንን አሸናፊ መጽሐፍ ተምሮ ማስተማር የመሰለ ፀጋ የለም፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 66, ሐዲስ 49
ዑስማን"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ከእናንተ በላጩ ቁርኣንን ተምሮ ያስተማረ ነው"*። نْ عُثْمَانَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ خَيْرُكُمْ مَنْ تَعَلَّمَ الْقُرْآنَ وَعَلَّمَهُ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ስርቆት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥38 *"ሰራቂውን እና ሰራቂይቱን በሠሩት ነገር ለቅጣት ከአላህ የኾነን መቀጣጫ እጆቻቸውን ቁረጡ! አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው"*፡፡ وَالسَّارِقُ وَالسَّارِقَةُ فَاقْطَعُوا أَيْدِيَهُمَا جَزَاءً بِمَا كَسَبَا نَكَالًا مِّنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٌ

"ሠሪቃህ" سَرِقَة የሚለው ቃል "ሠረቀ" سَرَقَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ስርቆት" ማለት ነው፥ ስርቆት የሰው ሐቅ የሚነካ ሐገ-ወጥ ወንጀል እና አሏህ በፍጹም የማይተወው በደል ነው። ስርቆት የሰው ሐቅ ስለሆነ በደሉ የሚተወው በዳዩ ተበዳዩን ይቅርታ ከጠየቀው ወይም በካሳ ከካሰው ብቻ ነው፥ አለበለዚያ ግን ይቅርታ ከተበዳዩ ካላገኘ ወይም ለተበዳዩ ካሳን ካልተከፈለ አሏህ በፍጹም የማይተወው በደል ስለሆነ በዚህ ዓለም ያለውን ቅጣት ባይቀበል እንኳን የፍርዱ ቀን በአሏህ ዘንድ ይቀጣል። አንድ ሰው ስርቆት በሚሰርቅበት ጊዜ እርሱ በልቡ ኢማን የመቀነሱ ውጤት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 86, ሐዲስ 40
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ዝሙት በሚዞምት ጊዜ እርሱ አማኝ አይደለም፣ ስርቆት በሚሰርቅበት ጊዜ እርሱ አማኝ አይደለም፣ ስካር በሚሰክርበት ጊዜ እርሱ አማኝ አይደለም። ግን ከዚያ በኋላ የንስሐ በር ክፍት ነው"*፡፡ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لاَ يَزْنِي الزَّانِي حِينَ يَزْنِي وَهْوَ مُؤْمِنٌ، وَلاَ يَسْرِقُ حِينَ يَسْرِقُ وَهْوَ مُؤْمِنٌ، وَلاَ يَشْرَبُ حِينَ يَشْرَبُهَا وَهْوَ مُؤْمِنٌ، وَالتَّوْبَةُ مَعْرُوضَةٌ بَعْدُ ‏"‌‏.‏

በመደበኛ ስርቆት ተግባር ላይ የተሰማራ ተባእት "ሣሪቅ" سَارِق ሲባል በመደበኛ ስርቆት ተግባር ላይ የተሰማራች እንስት ደግሞ "ሣሪቃህ" سَارِقَة ትባላለች፥ ሰራቂውን እና ሰራቂይቱን ለስርቆጣቸው ያለው ሸሪዓዊ ቅጣት እጆቻቸው መቆረጥ ነው፦
5፥38 *"ሰራቂውን እና ሰራቂይቱን በሠሩት ነገር ለቅጣት ከአላህ የኾነን መቀጣጫ እጆቻቸውን ቁረጡ! አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው"*፡፡ وَالسَّارِقُ وَالسَّارِقَةُ فَاقْطَعُوا أَيْدِيَهُمَا جَزَاءً بِمَا كَسَبَا نَكَالًا مِّنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٌ

አሏህ ይህንን ሑክም አድርጎ በመቅጣት አሸናፊ እና ይህንን ትእዛዝ በማዘዝ ጥበበኛ ነው። በሸሪዓህ የቅጣት ዓይነቶች ሦስት ናቸው፥ እነርሱም፦ "ሑዱድ" حُدُود "ቂሷስ" قِصَاص እና "ተዕዚር" تَعْزِیر ናቸው። "ሐድ" حَدّ‎ ማለት "ውሳኔ" ማለት ነው፥ የሐድ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሑዱድ" حُدُود ሲሆን "ውሳኔዎች" ማለት ነው። ከአሏህ ውሳኔዎች አንዱ ለስርቆት ቅጣት መቀጣጫ ነው፥ 1 ዲናር 12 ዲርሃም ሲሆን ሩብ ¼ ዲናር ደግሞ 3 ዲርሃም ነው። አንድ ሌባ ሩብ ዲናር ወይም 3 ዲርሃም እና ከዚያ በላይ ዋጋ ያለው ነገር ሲሰርቅ ብይኑ እጁ መቆረጥ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 29, ሐዲስ 3
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ሩብ ዲናር እና ከዚያ በላይ እንጂ የሌባ እጅ መቆረጥ የለበትም "*። عَنْ عَائِشَةَ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لاَ تُقْطَعُ يَدُ السَّارِقِ إِلاَّ فِي رُبْعِ دِينَارٍ فَصَاعِدًا ‏"‏ ‏.‏

ነገር ግን ሰራቂ ተሰራቂን “ዐፉው” عَفُوّ ማለትም “ይቅርታ” ከጠየቀ ወይም ተሰራቂ “ከፋራህ” كَفّارَة ማለትም “ካሳ” የሚገባው ከሆነ ሰራቂ ካሳ ከከፈለ ከአራቱ መዛሂብ አንዱ የኢማም ሻፊዒይ መዝሃብ"school of thought" እንዳስቀመጡት የመቆረጡ ቅጣት በምሕረት ይተውለታል። ለምሳሌ ሰራቂ ከተሰራቂ 10,000 ብር ሰርቆ ከሆነ ያንኑ 10,000 ብር መክፈል አለበት፥ ግን ሰራቂ መስረቁ ቢታወቅበት የባሰ የተወሳሰበ አደጋ ካለው ሰራቂ ገንዘቡን “ሃዲያህ” هادِيَة ማለትም “ሶጦታ” አርጎ ለተሰራቂ ይሰጠዋል፥ ተሰራቂ በሕይወት ከሌለ ደግሞ ሰራቂ ገንዘቡን “ሶደቀቱል ጃሪያህ” صَدَقَة الجارِيَة አርጎ ለመሣኪን ይሰጣል። በዚህ መልኩ የስርቆትን በደል የተጸጸተ እና ከላይ የተዘረዘሩትን የይቅርታ፣ የካሳ፣ የሃዲያህ፣ የሶደቀቱል ጃሪያህ ሥራውን ካሳመረ አሏህ ጸጸቱን ከእርሱ ይቀበለዋል፥ አሏህ መሓሪ አዛኝ ነውና፦
5፥39 *"ከበደሉም በኋላ የተጸጸተ እና ሥራውን ያሳመረ አላህ ጸጸቱን ከእርሱ ይቀበለዋል፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና"*፡፡ فَمَن تَابَ مِن بَعْدِ ظُلْمِهِ وَأَصْلَحَ فَإِنَّ اللَّهَ يَتُوبُ عَلَيْهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
የስርቆት ቅጣቱ እና ምሕረቱ ይህ ሆኖ ሳለ ሚሽነሪዎች የኢሥላምን ሕግ በምዕራባውያን እሳቦት፣ ርዕዮት እና አብዮት በመመዘን የስርቆትን ቅጣት ይቃወማሉ፥ ቅሉ ግን የራሳቸውን ባይብል በቅጡ አለማንበባቸው እጅጉን ያሳብቃል። እስቲ ስለ ስርቆት ቅጣት ከባይብል መሳ ለመሳ እንመልከት! ያህዌህ ፍርድን የሚወድ፣ ስርቆትን እና በደልን የሚጠላ ነው፥ ለሰረቀ ሰው የሰጠ ብይኑ ደግሞ እንዲገደል ነው፦
ኢሳይያስ 61፥8 እኔ ያህዌህ ፍርድን የምወድድ ስርቆትን እና በደልን የምጠላ ነኝ"*።
ዘጸአት 21፥16 *"ሰውን ሰርቆ ቢሸጥ ወይም በእጁ ቢገኝ እርሱ ፈጽሞ ይገደል"*።

"የራሷ እያረረባት የሰውን ታማስላለች" ማለት እንደዚህ ነው፥ በአዲስ ኪዳን ይህ የስርቆት ቅጣት በፍጹም አልተሻረም። "የስርቆቱ ቅጣት ተሽሯል" የሚል ካለ የተሻረበትን ማስረጃ ዱቅ ማድረግ ይጠበቅባችኃል፥ እንደውም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ አሊያም ነጣቂዎች የአምላክን መንግሥት አይወርሱም፦
1 ቆሮንቶስ 6፥10 *"ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም"*።

ምዕራባውያን የኢሉሚናቲ አጀንዳ ከጀርባ ስለተሸከሙ በመጨረሻይቱ ዓለም ቅጣት እና ሽልማት አያምኑም፥ የሌብነት ወንጀል የሚያስቀጣ ከሆነ ለምዕራባውያን ልቅነት ጥብቅና ምን አስቆማችሁ? ፕሮቴስታንቱስ በመሠልጠን መሠይጠንን ዓላማ እና ዒላማ አንድርጎ ነው፥ ኦርቶዶክሱ ግን ፍትሐ-ነገሥት ላይ ያለውን የሌቦች ቅጣት እንዴት ሳታዩት ቀራችሁ? እንግዲያውስ በፍትሐ ነገሥት የሌባ ቅጣት እንደየ ደረጃው በጋለ ብረት መተኮስ፣ እጅ መቁረጥ እና ግድያ ነው፦
ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 49 ቁጥር 1762 የሌቦች ቅጣት *"እመቦ ብእሲ ዘይበውእ ውስተ ምሥዋእ መዓልተ እው ሌሊተ ወይነሥእ እምዘውስቲታ ምንተኒ ይኲሐልዎ በሐጺን ርሱን"*

ትርጉም፦ *"በቀን ወይም በሌሊት ከቤተ-መቅደስ ገብቶ በውስጧ ካለው ማናቸውምን የወሰደ ቢኖር በጋለ ብረት ይተኩሱት"*።

ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 49 ቁጥር 1764 የሌቦች ቅጣት *"እለኒ ይነድኡ መርዔቱ ዘኢኮነ ሎሙ በቀዳሚ ጊዜ ይዝብትዎሙ፣ ወበዳግም ይሰድድዎሙ፣ ወበሣልስ ይምትሩ እደዊሆሙ"*

ትርጉም፦ *"የእነርሱ ያልሆኑትን መንጋ የሚነዱትን ሰዎች በመጀመሪያ ጊዜ ይግረፏቸው፣ በሁለተኛ ጊዜ ያባሯቸው፣ በሦስተኛ ጊዜ ግን እጃቸውን ይቁረጧቸው"*።

ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 49 ቁጥር 1766 የሌቦች ቅጣት *"ወሰረቅተ ሌሊትኒ እለ ይመጽኡ ኀበ ቤት ምስለ ሐቅል"*

ትርጉም፦ *"የጦር መሣሪያ ይዘው ወደ ቤት የሚመጡ የሌሊት ሌቦች ሞት ይገባቸዋል"*።

"በሰፈሩት ቁና መሰፈር" ይሉካል እንደዚህ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን በጥል ሰዓት ሴት የወንድ ብልትን በእጇ ብትይዝ እጇ እንዲቆረጥ ወፍራም ትእዛዝ አለ፦
ዘዳግም 25፥11-12 *"ሁለት ሰዎች እርስ በርሳቸው ቢጣሉ፥ የአንደኛውም ሚስት ባልዋን ከሚመታው ሰው እጅ ታድነው ዘንድ ብትቀርብ፥ እጅዋንም ዘርግታ ብልቱን ብትይዝ እጅዋን ቍረጥ! ዓይንህም አትራራላት"*።

አሏህ ለሁላችንም ሂዳያህ ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኢማን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

8፥4 *"እነዚያ በእውነት አማኞች እነርሱ ብቻ ናቸው፡፡ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ደረጃዎች ምህረት እና የከበረ ሲሳይም አላቸው"*፡፡ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُؤْمِنُونَ حَقًّا ۚ لَّهُمْ دَرَجَاتٌ عِندَ رَبِّهِمْ وَمَغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ

አሏህ ዘንድ ዒባዳህ ተቀባይነት መስፈቱ ሦስት ሲሆን እርሱም፦ ኢማን፣ ኢኽላስ እና ኢትባዕ ነው፥ “ኢማን” إِيمَٰن የሚለው ቃል “አሚነ” أَمِنَ ማለትም “አመነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “እምነት” ማለት ነው። "አርካኑል ኢማን" ማለት "የእምነት መሠረቶች" ማለት ሲሆን እነዚህም፦ በአሏህ ማመን፣ በመላእክቱ ማመን፣ በመጽሐፍቱ ማመን፣ በነቢያቱ ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን እና በቀደር ማመን ናቸው፥ ይህ በሐዲሱል ጂብሪል ተገልጿል፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 5
ዑመር ኢብኑ ኽጣብ እንዳስተላለፈው፦ “አንድ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰና በጣም ጥቁር ጸጉር ያለው ሰው በመጣ ጊዜ ከአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ጋር ነበርን፤ ወደ እርሳቸው ሲጓዝ አይታይም ነበር፤ ወደ ነብዩ”ﷺ” እስከሚደርስ ድረስ ከእኛ መካከል ማንም ዐላወቀውም፤ ጉልበቱን በእራሳቸው ጉልበት ተቃራኒ አድርጎ ከዚያም እንዲህ አለ፦ *”ሙሐመድ ሆይ! ኢማን ምንድን ነው? እርሳቸውም፦ “በአላህ ማመን፣ በመላእክቱ ማመን፣ በመጽሐፍቱ ማመን፣ በነቢያቱ ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን እና በሠናይ እና እኩይ ቀደር ማመን ነው” አሉ*። قَالَ عُمَرُ بْنُ الْخَطَّابِ كُنَّا عِنْدَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَجَاءَ رَجُلٌ شَدِيدُ بَيَاضِ الثِّيَابِ شَدِيدُ سَوَادِ الشَّعَرِ لاَ يُرَى عَلَيْهِ أَثَرُ السَّفَرِ وَلاَ يَعْرِفُهُ مِنَّا أَحَدٌ حَتَّى أَتَى النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم فَأَلْزَقَ رُكْبَتَهُ بِرُكْبَتِهِ ثُمَّ قَالَ يَا مُحَمَّدُ مَا الإِيمَانُ قَالَ ‏”‏ أَنْ تُؤْمِنَ بِاللَّهِ وَمَلاَئِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ وَالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ ‏”‏

በኢማም አቡ መንሱር አል-መቱሪዲይ የተቀመረው መቱሪዲይያህ የሚባለው ስሑት ዐቂዳህ፦ "ኢማን የማይጨምር እና የማይቀንስ ቋሚ ነው" የሚል እሳቤ አለው፥ ከዚህ በተቃራኒው አምላካችም አሏህ ኢማን በምእመናን ላይ አንቀጹ ሲነበብ እንደሚጨምር ይናገራል፦
8፥2 *"ፍጹም ምእምናን እነዚያ አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚፈሩት፣ "በእነርሱም ላይ አንቀጾቻችን በተነበቡ ጊዜ እምነትን የሚጨምሩላቸው"፣ በጌታቸውም ላይ ብቻ የሚመኩት ናቸው"*፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ اللَّهُ وَجِلَتْ قُلُوبُهُمْ وَإِذَا تُلِيَتْ عَلَيْهِمْ آيَاتُهُ زَادَتْهُمْ إِيمَانًا وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ

"በእነርሱም ላይ አንቀጾቻችን በተነበቡ ጊዜ እምነትን የሚጨምሩላቸው" የሚለው ይሰመርበት! ኢማናቸው እየጨመረ የሚሄድ እነዚያ በእውነት አማኞች እነርሱ ብቻ ናቸው፦
8፥4 *"እነዚያ በእውነት አማኞች እነርሱ ብቻ ናቸው፡፡ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ደረጃዎች ምህረት እና የከበረ ሲሳይም አላቸው"*፡፡ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُؤْمِنُونَ حَقًّا ۚ لَّهُمْ دَرَجَاتٌ عِندَ رَبِّهِمْ وَمَغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ

ኢማን የሚቀንሰው በትልቁ ኩፍር አሊያም በትንሹ ኩፍርም ሊሆን ይችላል፥ ከኢማን በኃላ ወደ ትልቁ ኩፍር በመሄድ አሊያም ሐራም ነገር በመሥራት ወደ ትንሹ ኩፍር በመሄድ ነው፦
3፥90 እነዚያ ከእምነታቸው በኋላ የካዱ ከዚያም ክህደትን የጨመሩ ጸጸታቸው ፈጽሞ ተቀባይ የላትም፡፡ እነዚያም የተሳሳቱ እነርሱ ናቸው፡፡ إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا بَعْدَ إِيمَانِهِمْ ثُمَّ ازْدَادُوا كُفْرًا لَّن تُقْبَلَ تَوْبَتُهُمْ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الضَّالُّونَ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 86, ሐዲስ 40
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ዝሙት በሚዞምት ጊዜ እርሱ አማኝ አይደለም፣ ስርቆት በሚሰርቅበት ጊዜ እርሱ አማኝ አይደለም፣ ስካር በሚሰክርበት ጊዜ እርሱ አማኝ አይደለም። ግን ከዚያ በኋላ የንስሐ በር ክፍት ነው"*፡፡ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لاَ يَزْنِي الزَّانِي حِينَ يَزْنِي وَهْوَ مُؤْمِنٌ، وَلاَ يَسْرِقُ حِينَ يَسْرِقُ وَهْوَ مُؤْمِنٌ، وَلاَ يَشْرَبُ حِينَ يَشْرَبُهَا وَهْوَ مُؤْمِنٌ، وَالتَّوْبَةُ مَعْرُوضَةٌ بَعْدُ ‏
ሡነን ነሣኢይ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 148
ዐብደሏህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ሙእሚንን መግደል ደግሞ ኩፍር ነው፥ መሳደብ ደግሞ ዓመፅ ነው"*። فَقَالَ حَدَّثَنِي عَبْدُ اللَّهِ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ قِتَالُ الْمُؤْمِنِ كُفْرٌ وَسِبَابُهُ فُسُوقٌ ‏.‏
መግደል፣ ዝሙት፣ ስርቆት፣ ስካር ወዘተ የኢማን መኳተት እና መኳተን ነው፥ ሙእሚን ሊፈራ እና ሊሳሳት ይችላል፥ ግን አይዋሽም፦
ማሊክ ሙተዋቲር መጽሐፍ 56, ሐዲስ 19
ማሊክ እንደነገረኝ ሶፍዋን ኢብኑ ሡለይማን እንደተረከው፦ *"ሙእሚን ሊፈራ ይችላልን? ተብለው የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ተጠየቁ፥ እርሳቸውም፦ "አዎ" አሉ። ቀጥሎ "ሙእሚን ሊሳሳት ይችላልን? ተብለው ተጠየቁ፥ እርሳቸውም፦ "አዎ" አሉ። ቀጥሎ "ሙእሚን ሊዋሽ ይችላልን? ተብለው ተጠየቁ፥ እርሳቸውም፦ "በፍጹም" አሉ። وَحَدَّثَنِي مَالِكٌ، عَنْ صَفْوَانَ بْنِ سُلَيْمٍ، أَنَّهُ قَالَ قِيلَ لِرَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أَيَكُونُ الْمُؤْمِنُ جَبَانًا فَقَالَ ‏"‏ نَعَمْ ‏"‏ ‏.‏ فَقِيلَ لَهُ أَيَكُونُ الْمُؤْمِنُ بَخِيلاً فَقَالَ ‏"‏ نَعَمْ ‏"‏ ‏.‏ فَقِيلَ لَهُ أَيَكُونُ الْمُؤْمِنُ كَذَّابًا فَقَالَ ‏"‏ لاَ ‏"‏ ‏.‏

የዲን ደረጃዎች ሦስት ሲሆኑ እነርሱም፦ ኢሥላም፣ ኢማን እና ኢሕሣን ናቸው፥ አንድ የአሏህ ባሪያ በኢስላም “ሙሥሊም” مُسْلِم የሚል የመጀመሪያ ደረጃ ሲኖረው፣ በኢማን “ሙእሚን” مُؤْمِن የሚል ሁለተኛ ደረጃ ሲኖረው፣ በኢሕሣን ደግሞ “ሙሕሢን” مُحْسِن የሚል ሦስተኛ ደረጃ አለው። ሙእሚን ካበለ ኢማኑ ዘነበለ፥ ሙእሚን ከዋሸ ኢማኑ ተበላሸ ማለት ነው። ስለዚህ አንድ ሙሥሊም ሲኳትን እና ሲኳትት ኢማን የሚቀንስ የሚጨምር ነገር ነው፥ አንድ ሙሥሊም ለሌላው ሙሥሊም ወንድሙን ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ ካልወደደ እራሱ የኢማን መቀነስ ምልክት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 6
አነሥ እንደተረከው፦ ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ከእናንተ መካከል ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም"*። عَنْ أَنَسٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لا يُؤْمِنُ أَحَدُكُمْ حَتَّى يُحِبَّ لأَخِيهِ مَا يُحِبُّ لِنَفْسِهِ ‏"‌‏.‏

ኢማን ካመንክ በኃላ ጥርጣሬ ሲገባ እራሱ ይቀንሳል፥ እውነተኛ አማኞች ጥርጣሬአቸው በዕውቀት አጥፍተው ከዚያም በነፍሶቻቸው እና በገንዘቦቻቸው በአሏህ መንገድ ጂሃድ ላይ ያሉ ብቻ ናቸው፦
49፥15 *ምእምናን እነዚያ በአላህ እና በመልእከተኛው ያመኑት ከዚያም ያልተጠራጠሩት “በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው”፡፡ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው*፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ثُمَّ لَمْ يَرْتَابُوا وَجَاهَدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۚ أُولَـٰئِكَ هُمُ الصَّادِقُونَ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 56, ሐዲስ 5
አቢ ሠዒድ አል-ኹድሪይ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "አንዱ፦ *"የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ሆይ! ከሰዎች በላጩ ማን ነው? ብሎ ጠየቀ፥ እርሳቸውም፦ "በነፍሱ እና በገንዘቡ በአሏህ መንገድ የታገለ ሙእሚን ነው" አሉ"*። أَنَّ أَبَا سَعِيدٍ الْخُدْرِيَّ ـ رضى الله عنه ـ حَدَّثَهُ قَالَ قِيلَ يَا رَسُولَ اللَّهِ، أَىُّ النَّاسِ أَفْضَلُ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ مُؤْمِنٌ يُجَاهِدُ فِي سَبِيلِ اللَّهِ بِنَفْسِهِ وَمَالِهِ

አምላካችን አሏህ በጂሃዱል ቀልቢያህ፣ ቀውሊያህ እና ዐመሊያ የምንታገል ሙእሚን ያርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
‏اسلام عليكم ورحمته الله وبركاته
አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ።
የዶ/ር Dan Alan Brubaker መፅሀፍን መዳሰስ በድጋሚ ጀምረናል።

ዛሬ ደግሞ ክፍል -4 ይዘን ቀርበናል። በዚህ ክፍል ዶክተሩ ያቀረበውን ምሳሌ 3 -ላይ ምላሽ ተሰጥቶበታል። አላህ የሚለው ስም 9 ቦታ ተጨምሯል ለሚለው ክስ ምላሽ።

Like and Share
Jzk
t.me/Abuyusra3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
‏اسلام عليكم ورحمته الله وبركاته
አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ።
የዶ/ር Dan Alan Brubaker መፅሀፍን ዳሰሳ።

ዛሬ ደግሞ ክፍል -5 ይዘን ቀርበናል።
በዚህ ክፍል ዶክተሩ ያቀረበውን ምሳሌ 4 -ላይ ምላሽ ተሰጥቶበታል።

Like and Share
ጠልሰም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥102 *"ሰይጣናትም በሡለይማን ዘመነ መንግሥት የሚያነቡትን ተከተሉ፡፡ ሡለይማንም አልካደም፥ ግን ሰይጣናት ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲኾኑ ካዱ"*፡፡ وَاتَّبَعُوا مَا تَتْلُو الشَّيَاطِينُ عَلَىٰ مُلْكِ سُلَيْمَانَ ۖ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَانُ وَلَـٰكِنَّ الشَّيَاطِينَ كَفَرُوا يُعَلِّمُونَ النَّاسَ السِّحْرَ

"ጠልሰም" ማለት ቋንቋዊ ትርጉሙ "ማስዋብ" ማለት ሲሆን ሃይማኖታዊ ትርጉሙ "አስማታዊ ጥበብ" ማለት ነው፥ ይህ ጠልሰም የሚባለው የአስማት ትምህርት በየገዳማቱ በብራናዎች ተጽፎ ይገኛል። በተለይ ሰሜን ሸዋ በሚገኘው የደብረ ሊባኖስ ገዳም፣ ቢሾፍቱም በቤተ ሩፋኤል ገዳም፣ ትግራይ በደብረ ዳሞ ገዳም፣ ላሊበላ በይምርሃነ ክርስቶስ ገዳም፣ ጐጃም ጣና ቂርቆስ ገዳም፣ ወሎ በአቡነ ይምርሃነ ክርስቶስ ገዳም ውስጥ በስፋት ትምህርቱ ይሰጣል። ነገር ግን ፈጣሪ፦ "አስማተኛ በአንተ ዘንድ አይገኝ" ብሎ አዟል፦
ዘዳግም 18፥11 *"አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ"*።

በጠልሰም ትምህርት ውስጥ የሞቱ ቅዱሳን ማናገር "ምስሓበ ቅዱሳን" የሚባል ትምህርት እና ከአጋንንት ጋር መነጋገር "ምስሓበ መናፍስት" ትምህርት ዐቢይ ትምህርት ነው፥ ነገር ግን ፈጣሪ መናፍስትንም መጥራት እና የሞቱ ሙታንን መሳብ ሐራም አርጎታል። ይህ ልማድ ከፈጣሪ የተወረደ ግልጠተ-መለኮት ሳይሆን እነዚያ አሕዛብ የሚያደርጉትን ርኵሰት ነው፥ ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በፈጣሪ ፊት የተጠላ ነው፦
ዘዳግም 18፥9 *"አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ ጊዜ እነዚያ አሕዛብ የሚያደርጉትን ርኵሰት ታደርግ ዘንድ አትማር"*።
ዘዳግም 18፥12 *"ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው"*።

የሞቱ ሰዎች ከሞቱ በኃላ ከዚህ ዓለም ጋር ግንኙነት የሚያደርጉበት ዓይን፣ ጆሮ፣ ጭንቅላት ወዘተ ይፈራርሳል፥ የምንናገረውን አይሰሙም፣ የምንሠራውን ዓያዩም፣ የምናስበውን ዐያውቁም። ሕዝቡ በጸሎት መጠየቅ ያለበት ሁሉን ማየት፣ መስማት እና ማወቅ የሚችለውን አንዱን አምላክ ብቻ ነው፦
ኢሳይያስ 8፥19 *"እነርሱም፦ "የሚጮኹትን እና ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው የሚናገሩትን መናፍስት ጠሪዎችን እና ጠንቋዮችን ጠይቁ" ባሉአችሁ ጊዜ፥ ሕዝቡ ከአምላኩ መጠየቅ አይገባውምን? ወይስ ለሕያዋን ሲሉ ሙታንን ይጠይቃሉን?"*

አጋንንት ከእኛ እይታ ረቂቅ እና ምጡቅ የሆኑትን መናፍስት ሲሆኑ እነርሱን መጥራት ሆነ የሞቱ ሰዎችን ስቦ ማናገር ሐራም ነው፥ በሞቱ ሰዎች ስም እና ድምጽ የሚነግዱትም አጋንንት ናቸው። ይህ ሆኖ ሳለ ግን በኢትዮጵያውያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን እና ገዳማት ውስጥ፦ ዐውደ-ነገሥት፣ ፍካሬ-ከዋክብት፣ ጥበበ-ሰሎሞን፣ መጽሐፈ-ቱላዳሚ፣ መጽሐፈ-ቆጵሪያኖስ የሚባሉ መጽሐፍት አሉ። እነዚህ መጽሐፍት ሰውን፦ የሚያሳብድ መስተአብድ፣ የሚያጣላ መስተጻርር፣ የሚያፋቅር መስተፋቅር፣ የሚያዋድድ መስተዋድድ፣ የሚያጣምር መስተጻምር፣ የሚያሳውቅ መስተአምር ናቸው። እነዚህም በጠልሰም የሚሠሩ ናቸው። በዚህ አድራጎት የተበተባችሁ ሰዎች የፈጠራችሁን የዓለማቱን ጌታ አሏህን ብቻ በብቸኝነት እንድታመልኩት ጥሪያችን ነው። ሙሽሪክ ጥሪው በአሏህ ለማስካድ እና በእርሱም ዕውቀት የሌለንን ነገር በእርሱ እንዳጋራ እንድናጋራ ነው፥ ሙሥሊም ግን የሚጣራው ወደ አሸናፊው መሓሪው አሏህ ነው፦
40፥42 *«በአላህ ልክድ እና በእርሱም ለእኔ ዕውቀት የሌለኝን ነገር በእርሱ እንዳጋራ ትጠሩኛላችሁ፡፡ እኔም ወደ አሸናፊው፤ መሓሪው አላህ እጠራችኋለሁ*፡፡ تَدْعُونَنِي لِأَكْفُرَ بِاللَّهِ وَأُشْرِكَ بِهِ مَا لَيْسَ لِي بِهِ عِلْمٌ وَأَنَا أَدْعُوكُمْ إِلَى الْعَزِيزِ الْغَفَّارِ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ክርስትና ከሶርያ ወደ አገራችን በ4ኛው ክፍለ-ዘመን በፍሬምናጥስ ሲገባ በእንግድነት የተቀበለች አገራችን ኢትዮጵያ ናት፥ አገራችን ውስጥ ከዋቄፈና ውጪ ሁሉም ከተለያዩ ቦታ የመጡ እምነቶች ናቸው። ኢትዮጵያ ከክርስትናም በፊት የራሷ ባህል፣ ቋንቋ፣ ፊደል፣ ትውፊት ነበራት፥ ፍሬምናጥስ ለኢትዮጵያ ከሶርያ ይዞ የመጣችው የእምነት ዶግማ እንጂ ባህላችንን፣ ቋንቋችንን፣ ፊደላችንን፣ ትውፊታችንን አይደለም። የኦርቶዶክስ ዶግማው ደግሞ ለራሳቸው ለኦርቶዶክሳውያን እንጂ ለእኛም ሆነ ለአገራችን ያደረገው አውንታዊ ተጽዕኖ እና በጎ አስተዋፅዎ የለም።
ኡሉል ዐዝም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

46፥35 *"ከመልእክተኞችም የቆራጥነት ባለቤቶች የኾኑት እንደ ታገሱ ሁሉ ታገስ"*፡፡ فَاصْبِرْ كَمَا صَبَرَ أُولُو الْعَزْمِ مِنَ الرُّسُلِ

አምላካችን አሏህ ወደ መጀመሪያው ነቢይ ወደ አደም ወሕይን አውርዷል፥ ግን አደም አሏህ አትብላ ያለውን በመርሳት ቆራጥነትን አልተገኘበትም፦
20፥115 *"ወደ አደምም ከዚህ በፊት ኪዳንን በእርግጥ አወረድን፡፡ ረሳም፡፡ ለእርሱም ቆራጥነትን አላገኘንለትም"*፡፡ وَلَقَدْ عَهِدْنَا إِلَىٰ آدَمَ مِن قَبْلُ فَنَسِيَ وَلَمْ نَجِدْ لَهُ عَزْمًا

"ዐዝም" عَزْم ማለት "ቆራጥነት" ማለት ነው። ዩኑሥ ከአሏህ መልእክተኞች መካከል አንዱ ነው፥ በትእግስት ቆራጥነት ስላልታየበት፦ "እንደ ዓሣው ባለቤትም አትኹን" የሚል መመሪያ አለ፦
37፥139 *"ዩኑሥም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው"*፡፡ وَإِنَّ يُونُسَ لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ
68፥48 *"ለጌታህም ፍርድ ታገሥ! እንደ ዓሣው ባለቤትም አትኹን፡፡ እርሱ በጭንቀት የተመላ ኾኖ ጌታውን በተጣራ ጊዜ"*፡፡ فَاصْبِرْ لِحُكْمِ رَبِّكَ وَلَا تَكُن كَصَاحِبِ الْحُوتِ إِذْ نَادَىٰ وَهُوَ مَكْظُومٌ

"ኡሉል ዐዝም" أُولُو الْعَزْمِ ማለት "የቆራጥነት ባለቤት" ማለት ሲሆን ከአሏህ መልእክተኞች መካከል "የቆራጥነት ባለቤት" የተባሉት መልእክተኞች የትእግስት ምሳሌ ስለሚሆኑ፦ "ከመልእክተኞችም የቆራጥነት ባለቤቶች የኾኑት እንደ ታገሱ ሁሉ ታገስ" የሚል መመሪያ አለ፦
46፥35 *"ከመልእክተኞችም የቆራጥነት ባለቤቶች የኾኑት እንደ ታገሱ ሁሉ ታገስ"*፡፡ فَاصْبِرْ كَمَا صَبَرَ أُولُو الْعَزْمِ مِنَ الرُّسُلِ

"ረሡል" رَسُول ማለት "መልእክተኛ" ማለት ሲሆን "ሩሡል" رُّسُل ማለት ደግሞ "መልእክተኞች" ማለት ነው፥ "ሩሡል" ከሚለው ቃል በፊት "ሚን" مِن ማለትም "ከ" የሚል መስተዋድድ መምጣቱ በራሱ "ኡሉል ዐዝም" የተባሉት ሁሉም መልእክተኞች ሳይሆኑ በከፊል መሆናቸውን ጉልኅ ማሳያ ነው። እነዚህም "ኡሉል ዐዝም" የሚባሉት መልእክተኞች ኑሕ፣ ኢብራሂም፣ ሙሣ፣ ዒሣ እና ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ናቸው፥ አሏህ ከእነዚህ የቆራጥነት ባለቤት መልእክተኞች ጋር የከበደን ቃል ኪዳን አድርጓል፦
33፥7 *"ከነቢዮችም የጠበቀ ኪዳናቸውን ከአንተም፣ ከኑሕም፣ ከኢብራሒምም፣ ከሙሣም ከመርየም ልጅ ዒሳም በያዝን ጊዜ አስታወስ፡፡ ከእነርሱም የከበደን ቃል ኪዳን ያዝን"*፡፡ وَإِذْ أَخَذْنَا مِنَ النَّبِيِّينَ مِيثَاقَهُمْ وَمِنكَ وَمِن نُّوحٍ وَإِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ ۖ وَأَخَذْنَا مِنْهُم مِّيثَاقًا غَلِيظًا
42፥13 *"ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፣ ያንንም ወደ አንተ ያወረድነውን፣ ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን፣ ሙሳን እና ዒሳንም ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም አትለያዩ ማለትን ደነገግን"*፡፡ شَرَعَ لَكُم مِّنَ الدِّينِ مَا وَصَّىٰ بِهِ نُوحًا وَالَّذِي أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ وَمَا وَصَّيْنَا بِهِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَىٰ ۖ أَنْ أَقِيمُوا الدِّينَ وَلَا تَتَفَرَّقُوا فِيهِ

“ፈድል” فَضْل የሚለው ቃል “ፈዶለ” فَضَّلَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ስጦታ” “ችሮታ” “ጸጋ”Bounty” ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ መልእክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በደረጃ በማብለጥ የተለያየ ፈድል ሰቷቸዋል፦
2፥253 *"እነዚህን መልእክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አበለጥን፥ ከእነርሱ ውስጥ አላህ ያነጋገረው አለ፡፡ ከፊሎቻቸውንም በደረጃዎች ከፍ አደረገ"*፡፡ تِلْكَ الرُّسُلُ فَضَّلْنَا بَعْضَهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ ۘ مِّنْهُم مَّن كَلَّمَ اللَّهُ ۖ وَرَفَعَ بَعْضَهُمْ دَرَجَاتٍ

እዚህ አንቀጽ ላይ "አበለጥን" ለሚለው የግስ መደብ የገባው ቃል "ፈደልና" فَضَّلْنَا ሲሆን ፈድል በመስጠት ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በደረጃ ማብለጡን ቁልጭ አርጎ ያሳያል። ነገር ግን የተሰጣቸው ፀጋ የራሳቸው ስላልሆነ እኛ አንዱን መልእክተኛ ከሌላው መልእክተኛ ሳንለይ በሁሉም መልእክተኞች መልእክት እናምናለን፦
4፥152 *"እነዚያም በአላህ እና በመልክተኞቹ ያመኑ፣ ከእነርሱም በአንድም መካከል ያለዩ እነዚያ ምንዳዎቻቸውን በእርግጥ ይሰጣቸዋል፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው"*፡፡ وَالَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرُسُلِهِ وَلَمْ يُفَرِّقُوا بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ أُولَـٰئِكَ سَوْفَ يُؤْتِيهِمْ أُجُورَهُمْ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 87, ሐዲስ 54
አቡ ሠዒድ እንደተረከው፦ ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በነቢያት መካከል አታማርጡ"*። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لاَ تُخَيِّرُوا بَيْنَ الأَنْبِيَاءِ ‏"‌‏.‏

አምላካችን አሏህ ከመልእክተኞች የቆራጥነት ባለቤቶች ከሆኑት ጋር መልካም ጎረቤት ያርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
በይቱል መቅዲሥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

21፥71 *”እርሱን(ኢብራሂምን) እና ሉጥንም ወደዚያች፤ በውስጧ ለዓለማት ወደ ባረክናት ምድር በመውሰድ አዳን”*፡፡ وَنَجَّيْنَاهُ وَلُوطًا إِلَى الْأَرْضِ الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا لِلْعَالَمِينَ

ለሰዎች መጸለያ መጀመሪያ የተኖረው ቤት በመካህ አገር ውስጥ ይገኛል፥ ይህም የአሏህ ቤት “በይቱል ሐረም” بَيْت الْحَرَام ማለትም “የተቀደሰው ቤት” ወይም “የተከበረው ቤት” ይባላል፦
3፥96 “ለሰዎች መጸለያ መጀመሪያ የተኖረው ቤት ብሩክ እና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲኾን ያ በበካህ ያለው ነው”፡፡ إِنَّ أَوَّلَ بَيْتٍ وُضِعَ لِلنَّاسِ لَلَّذِي بِبَكَّةَ مُبَارَكًا وَهُدًى لِّلْعَالَمِينَ
14፥37 «ጌታችን ሆይ! እኔ *"አዝመራ በሌለው ሸለቆ ውስጥ በተከበረው ቤትክ አጠገብ ከዘሮቼ አስቀመጥኩ"*፡፡ رَّبَّنَا إِنِّي أَسْكَنتُ مِن ذُرِّيَّتِي بِوَادٍ غَيْرِ ذِي زَرْعٍ عِندَ بَيْتِكَ الْمُحَرَّمِ

ይህንን ቤት መሠረት ጥሎ የመሠረተው ኢብራሂም ነው፥ ይህ ቤት ያለበትን አገር መካን የቀደሰውም እርሱ ነው፦
2፥127 *ኢብራሂምና ኢስማኢልም* «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል፡፡ አንተ ሰሚውና ዐዋቂው አንተ ነህና» የሚሉ ሲኾኑ *"ከቤቱ መሠረቱን ከፍ ባደረጉ ጊዜ አስታውስ"*፡፡ وَإِذْ يَرْفَعُ إِبْرَاهِيمُ الْقَوَاعِدَ مِنَ الْبَيْتِ وَإِسْمَاعِيلُ رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّا ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 25, ሐዲስ 69
የነቢዩ"ﷺ" ባልተቤት ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ለእርሷ፦ *"የአንቺ ሕዝብ(ቁረይሽ) ከዕባህን ሲገነቡ በኢብራሂም በተመሠረተው እንዳልገነቧት ታውቂያለሽ? አሏት። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنهم ـ زَوْجِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ لَهَا ‏"‏ أَلَمْ تَرَىْ أَنَّ قَوْمَكِ لَمَّا بَنَوُا الْكَعْبَةَ اقْتَصَرُوا عَنْ قَوَاعِدِ إِبْرَاهِيمَ ‏"‌‏.‏
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 15, ሐዲስ 521
ጃቢር እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ኢብራሂም መካን ቀድሷል፥ እኔም መዲናን ቀድሻለው”። عَنْ جَابِرٍ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّ إِبْرَاهِيمَ حَرَّمَ مَكَّةَ وَإِنِّي حَرَّمْتُ الْمَدِينَةَ

"ቀዋዒድ" قَوَاعِد ማለት "መሠረት" ማለት ሲሆን ኢብራሂም የዚህ ቤት መሥራች መሆኑን ፍትው እና ቁልጭ አርጎ ያሳያል፥ በተጨማሪም “ሐረመ” حَرَّمَ የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! “ሐረመ” حَرَّمَ ማለት “ቀደሰ” ወይም “አከበረ” ማለት ሲሆን ይህም ቤት “በይቱል ሐረም” بَيْت الْحَرَام ይባላል። ከዚያም አምላካችን አሏህ ኢብራሂምን በውስጧ ለዓለማት ወደ ባረክናት ምድር ወደ ሻም ወሰደው፦
21፥71 *”እርሱን(ኢብራሂምን) እና ሉጥንም ወደዚያች፤ በውስጧ ለዓለማት ወደ ባረክናት ምድር በመውሰድ አዳን”*፡፡ وَنَجَّيْنَاهُ وَلُوطًا إِلَى الْأَرْضِ الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا لِلْعَالَمِينَ

“መሥጂድ” مَسْجِد የሚለው ቃል “ሠጀደ” سَجَدَ ማለትም “ሰገደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መስገጃ” "ማምለኪያ" ማለት ሲሆን “ሡጁድ” سُّجُود ደግሞ “ስግደት” ማለት ነው፥ የጥንት ሰዎች መሥጂድ አርገው የሚሠሩት ድንኳን ነበር። በኢብራሂም መካህ የተመሠረተው የመጀሪያው መሥጂድ “አል-መሥጂዱል ሐረም” الْمَسْجِدِ الْحَرَام ማለትም “የተከበረ ወይም የተቀደሰ መሥጂድ” ሲሆን ሁለተኛው መሥጂድ ደግሞ በሻም ምድር በኢብራሂም የተመሠረተው “አል-መሥጂዱል አቅሷ” الْمَسْجِدِ الْأَقْصَى ማለትም “የሩቅ መሥጂድ” ነው። በሁለቱ መሣጂድ ምሥረታ መካከል ያለው የጊዜ ልዩነት 40 ዓመት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 45
አቢ ዘር ሰምቶ እንደተረከው፦ “እኔም፦ ”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በምድር ላይ መጀመሪያ የተመሠረተው የትኛው መሥጂድ ነው? አልኩኝ። እርሳቸውም፦ “አል-መሥጂዱል ሐረም” አሉ። እኔም፦ “ከዚያስ ቀጥሎ? ብዬ አልኩኝ። እርሳቸውም፦ “አል-መሥጂዱል አቅሷ” አሉ። እኔም፦ “በሁለቱ መካከል ምን ያህል የጊዜ ልዩነት አለ? ብዬ አልኩኝ። እርሳቸውም፦ “አርባ ዓመት” አሉ”። قَالَ سَمِعْتُ أَبَا ذَرٍّ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ، أَىُّ مَسْجِدٍ وُضِعَ فِي الأَرْضِ أَوَّلُ قَالَ ‏”‏ الْمَسْجِدُ الْحَرَامُ ‏”‌‏.‏ قَالَ قُلْتُ ثُمَّ أَىٌّ قَالَ ‏”‏ الْمَسْجِدُ الأَقْصَى ‏”‌‏.‏ قُلْتُ كَمْ كَانَ بَيْنَهُمَا قَالَ ‏”‏ أَرْبَعُونَ سَنَةً،

“ዉዲዐ” وُضِعَ ማለት “ተመሠረተ” ማለት ነው፥ ከዚያም አምላካችን አሏህ ዙሪያውን በባረከው በሁለተኛው የሩቁ መሥጂድ ላይ ሱለይማን ሕንጻ አል-በይቱል መቅዲሥ ገነባ፦
34፥13 ”ከምኩራቦች፣ ከምስሎችም እንደ ገንዳ ከኾኑ ገበታዎችም፣ ከተደላደሉ ታላላቅ ድስቶችም የሚሻውን ሁሉ ይሠሩለታል”፡፡ አልናቸውም፡፡ يَعْمَلُونَ لَهُ مَا يَشَاءُ مِن مَّحَارِيبَ وَتَمَاثِيلَ وَجِفَانٍ كَالْجَوَابِ وَقُدُورٍ رَّاسِيَاتٍ