ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
አልገደሉትም

@ገቢር አንድ
https://tttttt.me/Wahidcom/656

@ገቢር ሁለት
https://tttttt.me/Wahidcom/658

@ገቢር ሦስት
https://tttttt.me/Wahidcom/667

@ገቢር አራት
https://tttttt.me/Wahidcom/679

@ገቢር አምስት
https://tttttt.me/Wahidcom/681

ስለ ስቅለት እና በስቅለት ዙሪያ ማብራሪያ ነው። ያንብቡ!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በዘካቱል ማል ዙሪያ የሸይኽ ኢልያስን ማብራሪያ እንዲመለከቱ በትህትና እጠይቃለው።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የወር ደመወዝተኛን የሚመለከት የዘካህ አወጣጥ!
በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ
የሩሃማ ኢፍጧር

"ሩሐማእ" رُحَمَاء የቁርኣኑ ቃል ከሆነ ፊደሉ "ሩሐማእ" እንጂ "ሩሃማ" አይደለም፦
48፥29 የአላህ መልክተኛ ሙሐመድ እነዚያም ከእርሱ ጋር ያሉት ወዳጆቹ በከሓዲዎቹ ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው አዛኞች ናቸው፡፡ مُّحَمَّدٌ رَّسُولُ اللَّهِ ۚ وَالَّذِينَ مَعَهُ أَشِدَّاءُ عَلَى الْكُفَّارِ رُحَمَاءُ بَيْنَهُمْ

እዚህ አንቀጽ ላይ "አዛኞች" ለሚለው የገባው ቃል "ሩሐማእ" رُحَمَاء ነው። የኢፍጧሩ ስም ግን "ሩሃማ" ከሆነ "ሩሃማ" የሚለው ባይብል ውስጥ ያለ ስም ነው፥ ትርጉሙ "ምሕረት የተገባት" ማለት ነው፦
ሆሴዕ 2፥1-2 ወንድሞቻችሁን፦ ዓሚ፥ እኅቶቻችሁንም፦ #ሩሃማ" በሉአቸው። #እናታችሁ #ሚስቴ አይደለችምና እኔም ባልዋ አይደለሁምና ተምዋገቱ፤ ከእናታችሁ ጋር ተምዋገቱ። ግልሙትናዋን ከፊትዋ፥ ምንዝርናዋንም ከጡቶችዋ መካከል ታስወግድ፤

የሩሃማ እናት የፈጣሪ ሚስት አይደለችም ይላል። ግልሙትናዋ እና ጡቶችዋ እያለ የሚናገረው የሩሃማን እናት ነው። "ሎሩሃማን" ማለት "ምሕረት የማይገባት" ማለት ነው። ሎሩሃማን ብሉይ ኪዳን ላይ የነበረውን ዓመተ ፍዳ፣ ኩነኔ፣ ዓለም የሚያሳይ ሲሆን ሩሃማ በስቅለት ሞት ዓመተ ምሕረትን ያሳያል ብለው ያምናሉ። ሩሃማ ከሆነ በምን ሒሣብ ነው ይህ እሳቤ እና ስያሜ የሙሥሊም ኢፍጧር ላይ ስም የሆነው?

ዲን መቀለጃ አይደለም። አትቀላቅሉ! የሰዎችን ከንቱ ዝንባሌ አንከተል፦
42፥15 ለዚህም ድንጋጌ ሰዎችን ጥራ፣ እንደታዘዝከውም ቀጥ በል፣ ዝንባሌዎቻቸውንም አትከተል!፡፡ فَلِذَٰلِكَ فَادْعُ ۖ وَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَاءَهُمْ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ጥሪያችን የተሰኘው የብዙ ንፅፅር ኡሥታዞች የያዘ ድረ-ገጽ(ዌብ ሳይት) የሚሽነሪዎችን ሴራ እና ደባ ዶግ አመድ ለማድረግ እና ድባቅ ለማስገባት የተለያየ አርዕስት ይዞ ብቅ ብሏል። ጊዜ ካለዎት ሊንኩን በማስፈንጠር ይጎብኙት! ሼር በማድረግ ያስጎብኙ፦https://tiriyachen.org/
ፍልስጥኤም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥251 *"በአላህም ፈቃድ ድል መቷቸው፥ ዳውድም ጃሉትን ገደለ"*፡፡ فَهَزَمُوهُم بِإِذْنِ اللَّهِ وَقَتَلَ دَاوُودُ جَالُوتَ

"ፊልሥጢን" فِلَسْطِين ማለት "ፍልስጥኤም" ማለት ሲሆን በአንድ ወቅት የፍሊሥጢን ንጉሥ "ጃሉት" جَالُوت ማለትም "ጎልያድ" እና ሠራዊቱ ከጧሉት ማለትም ከሳኦል ሠራዊት ተዋግተዋል፦
2፥249 *ጧሉትም በሠራዊቱ ታጅቦ በወጣ ጊዜ፡- «አላህ በወንዝ ፈታኛችሁ ነው፥ ከርሱም የጠጣ ሰው ከእኔ አይደለም፡፡ ያልቀመሰውም ሰው በእጁ መዝገንን የዘገነ ሰው ብቻ ሲቀር እርሱ ከእኔ ነው» አለ፡፡ ከእነርሱም ጥቂቶች ሲቀሩ ከርሱ ጠጡ፡፡ እርሱ እና እነዚያም ከእርሱ ጋር ያመኑት ወንዙን ባለፉት ጊዜ፡- «ጃሎትን እና ሠራዊቱን በመዋጋት ለኛ ዛሬ ችሎታ የለንም» አሉት፡፡ እነዚያ እነርሱ አላህን ተገናኝዎች መኾናቸው የሚያረጋግጡት፡- «ከጥቂት ጭፍራ በአላህ ፈቃድ ብዙን ጭፍራ ያሸነፈች ብዙ ናት፤ አላህም ከታጋሾች ጋር ነው» አሉ*፡፡ فَلَمَّا فَصَلَ طَالُوتُ بِالْجُنُودِ قَالَ إِنَّ اللَّهَ مُبْتَلِيكُم بِنَهَرٍ فَمَن شَرِبَ مِنْهُ فَلَيْسَ مِنِّي وَمَن لَّمْ يَطْعَمْهُ فَإِنَّهُ مِنِّي إِلَّا مَنِ اغْتَرَفَ غُرْفَةً بِيَدِهِ ۚ فَشَرِبُوا مِنْهُ إِلَّا قَلِيلًا مِّنْهُمْ ۚ فَلَمَّا جَاوَزَهُ هُوَ وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ قَالُوا لَا طَاقَةَ لَنَا الْيَوْمَ بِجَالُوتَ وَجُنُودِهِ ۚ قَالَ الَّذِينَ يَظُنُّونَ أَنَّهُم مُّلَاقُو اللَّهِ كَم مِّن فِئَةٍ قَلِيلَةٍ غَلَبَتْ فِئَةً كَثِيرَةً بِإِذْنِ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ مَعَ الصَّابِرِينَ

ከዚያም በጦርነቱ ተፋልመው ተስፋ በቆረጡ ጊዜ ዳውድ ጃሉትን ገሎታል፦
2፥250 *ለጃሉት እና ለሠራዊቱ በተሰለፉም ጊዜ፡- «ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አንቧቧ፤ ጫማዎቻችንንም አደላድል፤ በከሓዲያን ሕዝቦችም ላይ እርዳን» አሉ፡፡ وَلَمَّا بَرَزُوا لِجَالُوتَ وَجُنُودِهِ قَالُوا رَبَّنَا أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًا وَثَبِّتْ أَقْدَامَنَا وَانصُرْنَا عَلَى الْقَوْمِ الْكَافِرِينَ
2፥251 *"በአላህም ፈቃድ ድል መቷቸው፥ ዳውድም ጃሉትን ገደለ"*፡፡ فَهَزَمُوهُم بِإِذْنِ اللَّهِ وَقَتَلَ دَاوُودُ جَالُوتَ

ቁርኣን ላይ ስለ ፍልስጥኤማውያን የሚናገረው እነዚህ አናቅጽ ላይ ነው። ሚሽነሪዎች፦ "ፍልስጥኤማውያን ፍልስጥኤም የምትባል አገር የላቸውም" እያሉ ባላነበቡት ነገር ይዘባርቃሉ። ፈጣሪ እስራኤልን ከግብጽ ምድር እንዳወጣ ሁሉ በጥንት ጊዜ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር አውጥቶ የራሳቸው ግዛት ሰቷቸዋል፦
አሞጽ 9፥7 እስራኤልን ከግብጽ ምድር፥ *ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?*
ኢዮኤል 3፥4 ጢሮስና ሲዶና *የፍልስጥኤምም ግዛት ሁሉ ሆይ*፥ ከእናንተ ጋር ለእኔ ምን አለኝ? በውኑ ብድራትን ትመልሱልኛላችሁን?

"የፍልስጥኤምም ግዛት" የሚለው ይሰመርበት። ፍልስጥኤም ግዛት ከነበረች ለምን መብቷ አይከበረም? እስራኤላውያን ቦታቸው መጥተው ሰፈሩባቸው እንጂ ጥንትም ቢሆን የእስራኤል ቅም አያት አብርሃም ከከላዳውያን ኡር በፍልስጥኤም ምድር ብዙ ቀን እንግዳ ሆኖ ተቀምጧል፦
ዘፍጥረት 21፥34 *"አብርሃምም በፍልስጥኤም ምድር ብዙ ቀን እንግዳ ሆኖ ተቀመጠ"*።

ፍልስጥኤም መጤ ሳትሆን የራሷ ምድር ስለሆነ "በፍልስጥኤም ምድር" የሚል ኃይለ-ቃል ተጽፏል። ባይብል ላይ ብዙ ቦታ "የፍልስጥኤም ምድር" እያለ ይናገራል፦
ኤርምያስ 25፥20 የተደባለቀውንም ሕዝብ ሁሉ፥ የዖፅ ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፥ *የፍልስጥኤም ምድር ነገሥታትንም ሁሉ አስቀሎናንም ጋዛንም አቃሮንንም የአዞጦንንም ቅሬታ"*።
ዘጸአት 13፥17 እንዲህም ሆነ ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ ምንም ቅርብ ቢሆን እግዚአብሔር *በፍልስጥኤማውያን ምድር* መንገድ አልመራቸውም።

ፍልስጥኤማውያን የራሳቸው አገር አላቸው፥ እስራኤላውያን የሰፈሩበት ከነዓን ሁሉ ሳይቀር የፍልስጥኤማውያን ምድር ነው፦
2ኛ ነገሥት 8፥2 ሴቲቱም ተነሥታ እንደ እግዚአብሔር ሰው ቃል አደረገች፤ ከቤተ ሰብዋም ጋር ሄዳ *"በፍልስጥኤም አገር ሰባት ዓመት ተቀመጠች"*።
ሶፎንያስ 2፥5 *"የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ"*፥ የእግዚአብሔር ቃል በአንተ ላይ ነው።

ዛሬ አገር እና ግዛት እንደሌላቸው እና መጤ እንደሆኑ ታይቶ እየተፈናቀሉ ነው፥ አሏህ ነስሩን ያቅርብላቸው! አሚን። ይህንን የምንለው ስለ ሐቅ እና ስለ ፍትሕ ነው፥ "ኢሥላም ሰም እና ወርቅ የያዘ ቅኔ ነው፥ ሰሙ ሐቅ ሲሆን ወርቁ ፍትሕ ነው" ስንል ዕውር ድንብ ጸለምተኛ ሙግት ይዘን ሳይሆን ጠቅሰንና አጣቅሰን በመሞገትና በመሟገት ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ያ ሙሥሊሙን ወሙሥሊማት ፈሠላሙሏሂ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ!
እንኳን የዒዱል ፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
"ተቀበለሏህ ሚና ወሚንኩም ሷሊሐል አዕማል፥ ዒድ ሙባረክ! تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال! عيد مبارك
ሸዋል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

ሚሽነሪዎች የማያውቁትን ከመጠየቅ ይልቅ፦ “ዘካህ ከመቶ 2.5% ስጡ የሚል መረጃ የለም፣ ሪባ ማለት አራጣ ማለት እንጂ ወለድ ማለት አይደለም፥ የቁርኣን አወራረድ ሁለት አይነት ነው የሚል መረጃ ከቁርኣንም ከሐዲስም መረጃ የለም” እያሉ ዲስኩራቸውን ሲደሶክሩ ነበር። ለእናንዳንዱ አርስት ከቁርኣና ከሐዲስ ከዚህ ቀደም ምላሽ ሰተናል። ዛሬ ደግሞ፦ “ሸዋልን ጹሙ! የሚል ቁርኣን ላይ የለም” እያሉ ይደሶክራሉ። ሚሽነሪዎች ሆይ! ጮቤ ረግጣችሁ አንባጒሮ አትፍጠሩ። ተረጋጉ! የጅብ ችኩል አትሁኑ! በሰላና በሰከነ መንፈስ ጠይቁ መልስ ይሰጣችኃል። ከሆያ ሆዬ ወደ አንቺ ሆዬ ትንሽ እንኳን እደጉ።
የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ዐሥራ ሁለት ወር ነው፥ እነዚህም፦
1ኛ ወር ሙሐረም
2ኛ ወር ሰፈር
3ኛ ወር ረቢዑል-አወል
4ኛ ወር ረቢዑ-ሣኒ
5ኛ ወር ጀማዱል-አወል
6ኛ ወር ጀማዱ-ሣኒ
7ኛ ወር ረጀብ
8ኛ ወር ሻዕባን
9ኛ ወር ረመዷን
10ኛ ወር ሸዋል
11ኛ ወር ዙል-ቀዒዳህ
12ኛ ወር ዙል-ሒጃህ ናቸው፦
9፥36 *የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነርሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው*፡፡ إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ

ከእነዚህ አስራ ሁለት ወራት አንዱ 10ኛ ወር “ሸዋል” ነው፥ “ሸዋል” شَوَّال ማለት “ማንሳት” ወይም “መሸከም” ማለት ሲሆን የወር ስም ነው። ነቢያችን”ﷺ” እንድናደርገው ሙስተሐብ አድርገው ከሰጡት ሱና መካከል ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን መጾም ነው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 78
አቢ አዩብ እንደተረከው፦ “ነቢዩ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *ማንም ረመዷንን የጾመ ከዚያም ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን ያስከተለ ዋጋው ዓመቱን ሙሉ እንደጾመ ነው”*። عَنْ أَبِي أَيُّوبَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ مَنْ صَامَ رَمَضَانَ ثُمَّ أَتْبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ فَذَلِكَ صِيَامُ الدَّهْرِ ‏

የረመዷን ሰላሳ ቀን እና የሸዋል ስድስት ቀን ጾም ጾመን ዓመት እንደጾምን የሚያስቆጥርበትን ስሌት ማወቅ ይቻላል። አምላካችን አላህ አንድ መልካም ሥራ ምንዳው አሥር እጥፍ እንደሆነ በቅዱስ ቃሉ ነግሮናል፦
6፥160 *”በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ዐሥር ብጤዎችዋ አሉት”*፡፡ በክፉ ሥራም የመጣ ሰው ብጤዋን እንጅ አይመነዳም፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡ مَن جَاءَ بِالْحَسَنَةِ فَلَهُ عَشْرُ أَمْثَالِهَا ۖ وَمَن جَاءَ بِالسَّيِّئَةِ فَلَا يُجْزَىٰ إِلَّا مِثْلَهَا وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

ስለዚህ አንድ መልካም ሥራ አሥር ብጤዎች ካሉት የረመዷን አንድ ወር መጾም የአሥር ወር ምንዳ አለው። 1×10=10 ወር ይሆናል። እንዲሁ የሸዋል ስድስት ቀን መጾም የስድሳ ቀን ምንዳ አለው፥ ስድስት ቀናት በአሥር እጥፍ ስድሳ ቀን ነውና፥ 6×10=60 ቀን ወይም 2 ወር ይሆናል። ሲጠቀለል የረመዷን የአሥር ወር ምንዳ እና የሸዋል ሁለት ወር ምንዳ 12 ወር ይሆናል፥ 10+2=12 ወር ይሆናል። አንድ ዓመት ደግሞ 12 ወር መሆኑ እሙን ነው። አሊያም ሠላሳ የረመዳን ቀን እና ስድስት የሸዋል ቀን በአስር ምንዳ ሲባዛ 360 ቀናት ይሆናሉ፥ 36×10= 360 ይሆናል። አንድ ዓመት ደግሞ ጨረቃ ወፀሐይ"lunisolar" የሆነው የአይሁዳውያን አቆጣጠር 360 ቀናት መሆኑ ቅቡል ነው።
አምላካችን አሏህ በተከበረ ቃሉ፦ “መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት” ይለናል፦
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

ስለዚህ ኢሥላም ሰው ሠራሽ ሕግና ሥርዓት ሳይሆን ዐቂደቱ አር-ረባንያህ ነው። ይህንን ስንል አርቲ ቡርቲና ቶራ ቦራ የሆነ ስሑትና መሪር የቡና ወሬ ይዘን ሳይሆን ቁርኣንና ሐዲስን ያማከለ ስሙርና ጥዑም ማስረጃ ይዘን ነው።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ክርስቲያን ወንድሞቻችን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

49፥10 *"ምእመናኖች ወንድማማቾች ናቸው"*፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ

"አኽ" أَخ ማለት "ወንድም" ማለት ሲሆን "ኡኽት" أُخْت ማለት "እኅት" ማለት ነው፥ "ኢኽዋህ" إِخْوَة ወይም "ኢኽዋን" إِخْوَان የአኽ ብዙ ቁጥር ሲሆን "ወንድማማቾች" ማለት ነው። "ኡኹዋህ" أُخُوَّة‎ ማለት "ወንድማማችነት" ማለት ሲሆን ወንድማማችነት እንደየ ዐውዱ የተለያየ አገባብ አለው። "ክርስቲያን" የሚለው ቃል "ሃይማኖትን" ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ቃል ነው፥ ለአንድ ሙሥሊም የሃይማኖት ወንድሙ ሙሥሊም እንጂ ክርስቲያን በፍጹም አይደለም። ሰዎች የሃይማኖት ወንድሞቻችን እንዲሆኑ ከተፈለገ ተውበት ወደ አሏህ ሊያደርጉ፣ ሶላትንም ሊሰግዱ፣ ዘካንም ሊሰጡ በጥቅሉ ምን አለፋን ሙሥሊም መሆን አለባቸው፦
9፥11 *"ቢጸጸቱም፣ ሶላትንም ቢሰግዱ፣ ዘካንም ቢሰጡ የሃይማኖት ወንድሞቻችሁ ናቸው"*፡፡ فَإِن تَابُوا وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَآتَوُا الزَّكَاةَ فَإِخْوَانُكُمْ فِي الدِّينِ
49፥10 *"ምእመናኖች ወንድማማቾች ናቸው"*፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ

ቁርኣን ላይ "ምእመናኖች ወንድማማቾች ናቸው" የሚል እንጂ "ክርስቲያን ወንድሞቻችሁ ናቸው" የሚል ኃይለ-ቃል የለም። በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ኖርዌይ በኖቤል ሽልማቱ ጊዜ፦ "ምእመናኖች ወንድማማቾች ናቸው" የሚለውን ቆርጦ በመቀጠል "ሰብአዊነት አንድ ወንድማማችነት ነው"Humanity is but a single Brotherhood" ብለው ለፓለቲካ ንግድና ትርፍ ተጠቅመውበታል፥ ይህ ትልቅ ስህተት ነው።
ወደ ነጥቤ ስገባ "ክርስትና" በቁርኣን ውስጥ መለኮታዊ ዕውቅና ያለው "ሃይማኖት" አይደለም፦
3፥19 *"አላህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው"*፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ
3፥85 *"ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይ የለውም፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው"*፡፡ وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ الْإِسْلَامِ دِينًا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِي الْآخِرَةِ مِنَ الْخَاسِرِينَ

ቁርኣን ከኢሥላም ሌላ ሃይማኖትን ዕውቅና ካልሰጠ እና ዕውቅና መስጠቱ እራሱ በአኺራ ላይ ኪሳራ ከሆነ "ክርስቲያን ወንድሞቻችን" እያላችሁ የምትሉ ይህንን ኪሳራ እያያችሁ ግቡበት። አገራዊ ወንድማማችነት ከሃይማኖት ወንድማማችነት ይለያል፥ የሕዝብ ወንድማማችነት በቁርኣን ውስጥ ብዙ ቦታ ተጠቅሷል፦
7፥56 ወደ ዓድም *ወንድማቸውን ሁድን ላክን*፡፡ «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ የአላህን ቅጣት አትፈሩምን» አላቸው፡፡ وَإِلَىٰ عَادٍ أَخَاهُمْ هُودًا ۗ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَـٰهٍ غَيْرُهُ ۚ أَفَلَا تَتَّقُونَ
11፥61 *ወደ ሰሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን*፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ አምላክ የላችሁም፡፡ وَإِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمْ صَالِحًا ۚ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَـٰهٍ غَيْرُهُ ۖ هُوَ أَنشَأَكُم مِّنَ الْأَرْضِ وَاسْتَعْمَرَكُمْ فِيهَا فَاسْتَغْفِرُوهُ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ ۚ إِنَّ رَبِّي قَرِيبٌ مُّجِيبٌ
11፥84 *ወደ መድየንም ወንድማቸውን ሹዐይብን ላክን*፡፡ አላቸው «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለናንተ አምላክ የላችሁም፡፡ وَإِلَىٰ مَدْيَنَ أَخَاهُمْ شُعَيْبًا ۚ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَـٰهٍ غَيْرُهُ ۖ وَلَا تَنقُصُوا الْمِكْيَالَ وَالْمِيزَانَ ۚ إِنِّي أَرَاكُم بِخَيْرٍ وَإِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ مُّحِيطٍ

ዐድ፣ ሰሙድ፣ መድየም ወዘተ የሕዝብ ስም እንጂ የሃይማኖት ስም ስላልሆነ በተመሳሳይ "ኢትዮጵያዊ ወንድሞቻችን" ማለት ይቻላል። ከእናቴ እና ከአባቴ አብራክ የተገኘውን ወንድሜን እራሱ "ወንድሜ" ማለት ይቻላል፦
12፥5 አባቱም አለ «ልጄ ሆይ! ሕልምህን *ለወንድሞችህ* አታውራ፡፡ ላንተ ተንኮልን ይሰሩብሃልና፡፡ ሰይጣን ለሰው ግልጽ ጠላት ነውና፡፡» قَالَ يَا بُنَيَّ لَا تَقْصُصْ رُؤْيَاكَ عَلَىٰ إِخْوَتِكَ فَيَكِيدُوا لَكَ كَيْدًا ۖ إِنَّ الشَّيْطَانَ لِلْإِنسَانِ عَدُوٌّ مُّبِينٌ
7፥151 ሙሳም፡- «ጌታዬ ሆይ! *ለእኔም ለወንድሜም ማር*፡፡ በእዝነትህም ውስጥ አግባን፡፡ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» አለ፡፡ قَالَ رَبِّ اغْفِرْ لِي وَلِأَخِي وَأَدْخِلْنَا فِي رَحْمَتِكَ ۖ وَأَنتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ

ስለዚህ ለመወደድ ብለን "ክርስቲያን ወንድሞቻችን" በማለት ዲናችን የማይለውን አንበል! ኢትዮጵያውያን እርስ በእርስ ሊያስተሳስረን የሚችል ብዙ የጋራ እሴት እያለን በማናምንበት ነገር ውስጥ ባንነካካ እና የሌላ እምነት አምልኮ ባንፈጽም ሰናይ ነው። አሏህ ሂዳያህ ለሁላችንም ይስጠን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አል-አርዱል ሙቀደሣህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥21 *«ሕዝቦቼ ሆይ! ያችን አላህ ለእናንተ ያደረጋትን የተቀደሰችውን መሬት ግቡ፡፡ ወደ ኋላችሁም አትመለሱ፡፡ ከሳሪዎች ኾናችሁ ትመለሳላችሁና፡፡»* يَا قَوْمِ ادْخُلُوا الْأَرْضَ الْمُقَدَّسَةَ الَّتِي كَتَبَ اللَّهُ لَكُمْ وَلَا تَرْتَدُّوا عَلَىٰ أَدْبَارِكُمْ فَتَنقَلِبُوا خَاسِرِينَ

ስለ አል-አርዱል ሙቀደሣህ ከነቢዩሏህ ኢብራሂም እስከ ነቢያችን"ﷺ" ያለውን ክስተት ከቁርኣን እና ከሐዲስ በግርድፉና በሌጣው ኢንሻሏህ እናያለን። "አሽ-ሻም” اَلـشَّـام‎ ማለት በቋንቋ ደረጃ ከሄድን “አሽ-ሸማል” الشِّمَال ማለትም “ግራ” ማለት ነው፥ ለምሳሌ የአሽ-ሻም ተቃራኒ “አል-የመን” اَلْـيَـمَـن ማለት “አል-የሚን” الْيَمِين ማለትም “ቀኝ” ማለት ነው። ነቢያችን”ﷺ” ከሚኖሩበት በስተ ግራ ያለችው አሽ-ሻም ስትሆን በስተ ቀኝ ያለችው አል-የመን ናት። አምላካችን አሏህ በየመን አገር እና በሻም አገር መካከልም ቅጥልጥል ከተሞችን አድርጓል፦
34፥18 *”በእነርሱ እና በዚያች በውስጧ በባረክናት ምድር መካከልም ቅጥልጥል ከተሞችን አደረግን”*፡፡ وَجَعَلْنَا بَيْنَهُمْ وَبَيْنَ الْقُرَى الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا قُرًى ظَاهِرَةً

እዚህ አንቀጽ ላይ "ባረክና" بَارَكْنَا ማለት "የባረክን" ማለት ሲሆን የተባረከችውም ምድር የሻም ምድር ናት፥ አምላካችን አሏህ ኢብራሂምን እና ሉጥንም ወደዚያች፤ በውስጧ ለዓለማት ወደ ባረካት ምድር በመውሰድ አዳናቸው፦
21፥71 *”እርሱን(ኢብራሂምን) እና ሉጥንም ወደዚያች፤ በውስጧ ለዓለማት ወደ ባረክናት ምድር በመውሰድ አዳን”*፡፡ وَنَجَّيْنَاهُ وَلُوطًا إِلَى الْأَرْضِ الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا لِلْعَالَمِينَ

አምላካችን አሏህ በአል-መሥጂዱል አቅሳ ዙሪያውን ያለውን ሶሪያን፣ ፍልስጥኤም፣ ዮርዳኖስን፣ ሊባኖስን ወዘተ ባርኮታል፦
17፥1 *ያ ባሪያውን “ከተከበረው መስጊድ” ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ “ሩቁ መስጊድ” በሌሊት ውስጥ ያስኼደው ጥራት ይገባው፤ ከታምራቶቻችን ልናሳየው አስኼድነው"*። እነሆ እርሱ አላህ ሰሚው ተመልካቺው ነው። سُبْحَٰنَ ٱلَّذِىٓ أَسْرَىٰ بِعَبْدِهِۦ لَيْلًۭا مِّنَ ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ إِلَى ٱلْمَسْجِدِ ٱلْأَقْصَا ٱلَّذِى بَٰرَكْنَا حَوْلَهُۥ لِنُرِيَهُۥ مِنْ ءَايَٰتِنَآ ۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ

"ዙሪያውን ወደ ባረክነው" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። “መሥጂድ” مَسْجِد የሚለው ቃል “ሠጀደ” سَجَدَ ማለትም “ሰገደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መስገጃ” ማለት ሲሆን “ሡጁድ” سُّجُود ደግሞ “ስግደት” ማለት ነው፥ የጥንት ሰዎች መሥጂድ አርገው የሚሠሩት ድንኳን ነበር። በመካህ የተመሠረተው የመጀሪያው መሥጂድ “አል-መሥጂዱል ሐረም” الْمَسْجِدِ الْحَرَام ማለትም “የተከበረ መሥጂድ” ሲሆን ሁለተኛው መሥጂድ ደግሞ በሻም ምድር የተመሠረተው "አል-መሥጂዱል አቅሷ” الْمَسْجِدِ الْأَقْصَى ማለትም “የሩቅ መሥጂድ” ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 45
አቢ ዘር ሰምቶ እንደተረከው፦ “እኔም፦ *”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በምድር ላይ መጀመሪያ የተመሠረተው የትኛው መሥጂድ ነው? አልኩኝ። እርሳቸውም፦ “አል-መሥጂዱል ሐረም” አሉ። እኔም፦ “ከዚያስ ቀጥሎ? ብዬ አልኩኝ። እርሳቸውም፦ “አል-መሥጂዱል አቅሷ” አሉ። እኔም፦ “በሁለቱ መካከል ምን ያህል የጊዜ ልዩነት አለ? ብዬ አልኩኝ። እርሳቸውም፦ “አርባ ዓመት” አሉ”*። قَالَ سَمِعْتُ أَبَا ذَرٍّ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ، أَىُّ مَسْجِدٍ وُضِعَ فِي الأَرْضِ أَوَّلُ قَالَ ‏”‏ الْمَسْجِدُ الْحَرَامُ ‏”‌‏.‏ قَالَ قُلْتُ ثُمَّ أَىٌّ قَالَ ‏”‏ الْمَسْجِدُ الأَقْصَى ‏”‌‏.‏ قُلْتُ كَمْ كَانَ بَيْنَهُمَا قَالَ ‏”‏ أَرْبَعُونَ سَنَةً،

“ዉዲዐ” وُضِعَ ማለት “ተመሠረተ” ማለት ነው፥ በሁለቱ መሣጂጅ መካከል ያለው የጊዜ ልዩነት 40 ዓመት ነው፥ እነዚህ መሣጂድ የተመሠረቱት በኢብራሂም ጊዜ ነው፦
2፥127 *"ኢብራሂምና ኢስማኢልም «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል፡፡ አንተ ሰሚውና ዐዋቂው አንተ ነህና» የሚሉ ሲኾኑ "ከቤቱ መሠረቶቹን ከፍ ባደረጉ ጊዜ አስታውስ"*፡፡ وَإِذْ يَرْفَعُ إِبْرَاهِيمُ الْقَوَاعِدَ مِنَ الْبَيْتِ وَإِسْمَاعِيلُ رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّا ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ
"አል-አርዱል ሙቀደሣህ" الْأَرْضَ الْمُقَدَّسَة ማለት "ቅድስት መሬት"The Holy Earth" ማለት ነው፥ ሙሣም ለሕዝቦቹ ይህቺን ምድር፦ "የተቀደሰችውን መሬት" ብሏታል፦
5፥21 *«ሕዝቦቼ ሆይ! ያችን አላህ ለእናንተ ያደረጋትን የተቀደሰችውን መሬት ግቡ፡፡ ወደ ኋላችሁም አትመለሱ፡፡ ከሳሪዎች ኾናችሁ ትመለሳላችሁና፡፡»* يَا قَوْمِ ادْخُلُوا الْأَرْضَ الْمُقَدَّسَةَ الَّتِي كَتَبَ اللَّهُ لَكُمْ وَلَا تَرْتَدُّوا عَلَىٰ أَدْبَارِكُمْ فَتَنقَلِبُوا خَاسِرِينَ

አሏህ ለሙሣ ሕዝቦች ቅድስት ምድር ያደረጋት ሲሆን የሙሣ ሕዝቦች በምድረ በዳ በአላህ ላይ በማመጻቸው የተቀደሰችው መሬት በእነርሱ ላይ አርባ ዓመት እርም ሆነች፥ በምድረ በዳ ተንከራተቱ፦
5፥26 *”እርስዋም የተቀደሰችው መሬት በእነርሱ ላይ አርባ ዓመት እርም ናት፡፡ በምድረ በዳ ይንከራተታሉ”*፡፡ «በአመጸኞችም ሕዝቦች ላይ አትዘን» አለው፡፡ قَالَ فَإِنَّهَا مُحَرَّمَةٌ عَلَيْهِمْ ۛ أَرْبَعِينَ سَنَةً ۛ يَتِيهُونَ فِي الْأَرْضِ ۚ فَلَا تَأْسَ عَلَى الْقَوْمِ الْفَاسِقِينَ

ከዚያም ደካሞች የነበሩትን ሕዝቦች በውስጧ የባረካትን የሻም ምድር ምሥራቆችዋንም ምዕራቦቿንም አወረሳቸው፦
7፥137 *”እነዚያንም ደካሞች የነበሩትን ሕዝቦች ያችን በውስጧ የባረክናት ምድር ምሥራቆችዋንም ምዕራቦቿንም አወረስናቸው፡፡ የጌታህም መልካሚቱ ቃል በእስራኤል ልጆች ላይ በመታገሳቸው ተፈጸመች”*፡፡ وَأَوْرَثْنَا الْقَوْمَ الَّذِينَ كَانُوا يُسْتَضْعَفُونَ مَشَارِقَ الْأَرْضِ وَمَغَارِبَهَا الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا ۖ وَتَمَّتْ كَلِمَتُ رَبِّكَ الْحُسْنَىٰ عَلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ بِمَا صَبَرُوا ۖ

ከዚያም አምላካችን አላህ ዙሪያውን በባረከው በሁለተኛው የሩቁ መሥጂድ ለሱለይማንም በትእዛዙ በኃይል የምትነፍስ ነፋስ ስትኾን ገራለት፥ ሱለይማን እዛው አቅሳ መስገጃው ላይ ሕንጻ አል-በይቱል መቅዲሥ ገነባ፦
21፥81 *”ለሱለይማንም በትእዛዙ በኃይል የምትነፍስ ነፋስ ስትኾን በእርሷ ውስጥ ወደባረክናት ምድር የምትፈስ ስትኾን ገራንለት”*፡፡ በነገሩ ሁሉም ዐዋቂዎች ነበርን፡፡ وَلِسُلَيْمَانَ الرِّيحَ عَاصِفَةً تَجْرِي بِأَمْرِهِ إِلَى الْأَرْضِ الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا ۚ وَكُنَّا بِكُلِّ شَيْءٍ عَالِمِينَ
34፥13 *”ከምኩራቦች፣ ከምስሎችም እንደ ገንዳ ከኾኑ ገበታዎችም፣ ከተደላደሉ ታላላቅ ድስቶችም የሚሻውን ሁሉ ይሠሩለታል”*፡፡ አልናቸውም፡፡ يَعْمَلُونَ لَهُ مَا يَشَاءُ مِن مَّحَارِيبَ وَتَمَاثِيلَ وَجِفَانٍ كَالْجَوَابِ وَقُدُورٍ رَّاسِيَاتٍ

አሏህ ለሱለይማን ከጥንት በተመሠረተው መሥጂድ ላይ “መሐሪብ” እንዲሠራ ከጂኒዎች የሚሻውን ሁሉ እንዲሠሩለት ገራለት። እዚህ አንቀጽ ላይ “ምኩራብ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “መሐሪብ” مَّحَٰرِيب ሲሆን “አል-በይቱል መቅዲሥ” ٱلْبَيْت الْمَقْدِس ነው። “አል-በይቱል መቅዲሥ” ማለት “የተቀደሰ ቤት” ማለት ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 1473
ዐብደላህ ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ሡለይማን ኢብኑ አቢ ዳዉድ በይቱተል መቅዲሥን ገንብቶ በጨረሰ ጊዜ አላህን ሦስት ነገሮች ጠይቋል። አንደኛ በፍርዱ የሚያስማማበትን ፍርድ ጠየቀ፥ ያም ተሰጠው፣ ሁለተኛ ከእርሱ በኃላ ማንም የማይኖረውን ንግሥና፣ ሦስተኛ ሶላት ለማድረግ እንጂ ወደዚህ መሥጂድ የሚመጣውን ልክ እናቱ ስትወልደው ከኀጢአት ነጻ እንደሆነ እንዲሆን”*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، عَنِ النَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏”‏ لَمَّا فَرَغَ سُلَيْمَانُ بْنُ دَاوُدَ مِنْ بِنَاءِ بَيْتِ الْمَقْدِسِ سَأَلَ اللَّهَ ثَلاَثًا حُكْمًا يُصَادِفُ حُكْمَهُ وَمُلْكًا لاَ يَنْبَغِي لأَحَدٍ مِنْ بَعْدِهِ وَأَلاَّ يَأْتِيَ هَذَا الْمَسْجِدَ أَحَدٌ لاَ يُرِيدُ إِلاَّ الصَّلاَةَ فِيهِ إِلاَّ خَرَجَ مِنْ ذُنُوبِهِ كَيَوْمَ وَلَدَتْهُ أُمُّهُ

“ቢናእ” بِنَاء የሚለው ቃል “በና” بَنَىٰ ማለትም “ገነባ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ግንባታ” ወይም “ሕንጻ” ማለት ነው። ሡለይማን የገነባው ጥንት በተመሠረተው መሥጂድ ላይ ነው፥ እርሱ ገንቢ እንጂ መሥራች አለመሆኑ እሙልና ቅቡል ነው። ከዚያ የእስራኤል ልጆች ሁለት ጊዜ አጠፉ፥ ከሁለቱ የመጀመሪያይቱ ቀጠሮ በመጣም ጊዜ ለአላህ የኾኑን ባሮች የብርቱ ኃይል ባለቤቶች የኾኑትን ናቡነደፆርን እና ሰራዊቱን በ 606 ቅድመ-ልደት”BC” ተነስተው ይህንን መሐሪብ ማለኪያ አጥፍተውታል። ይህ ተፈጻሚ ቀጠሮም ነበር፦
17፥4 *ወደ እስራኤልም ልጆች በመጽሐፉ ውስጥ እንዲህ በማለት አወረድን፡፡ በምድር ላይ በእርግጥ ሁለት ጊዜ ታጠፋላችሁ፡፡ ትልቅንም ኩራት ትኮራላችሁ*፡፡ وَقَضَيْنَا إِلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ فِي الْكِتَابِ لَتُفْسِدُنَّ فِي الْأَرْضِ مَرَّتَيْنِ وَلَتَعْلُنَّ عُلُوًّا كَبِيرًا
17፥5 *"ከሁለቱ የመጀመሪያይቱ ቀጠሮ በመጣም ጊዜ ለእኛ የኾኑን ባሮች የብርቱ ኃይል ባለቤቶች የኾኑትን በእናንተ ላይ እንልካለን፡፡ በቤቶችም መካከል ይበረብሩታል፡፡ ይህ ተፈጻሚ ቀጠሮም ነበር*፡፡ فَإِذَا جَاءَ وَعْدُ أُولَاهُمَا بَعَثْنَا عَلَيْكُمْ عِبَادًا لَّنَا أُولِي بَأْسٍ شَدِيدٍ فَجَاسُوا خِلَالَ الدِّيَارِ ۚ وَكَانَ وَعْدًا مَّفْعُولًا
የኋለኛይቱም ጊዜ ቀጠሮ በመጣ ጊዜ መሥጂዱን በመጀመሪያ ጊዜ እንደገቡት ሊገቡ እና ያሸነፉትንም ሁሉ ፈጽመው ማጥፋትን እንዲያጠፉ በ 70 ድህረ-ልደት”AD” የሮም ጦር መሪ የሆነው ጀነራል ቲቶ እና ሰራዊቱ ከበው አጥፍተዋል፦
17፥7 *”የኋለኛይቱም ጊዜ ቀጠሮ በመጣ ጊዜ ፊቶቻችሁን ሊያስከፉ፣ መስጁዱንም በመጀመሪያ ጊዜ እንደገቡት ሊገቡ እና ያሸነፉትንም ሁሉ ፈጽመው ማጥፋትን እንዲያጠፉ እንልካቸዋልን”*፡፡ فَإِذَا جَآءَ وَعْدُ ٱلْـَٔاخِرَةِ لِيَسُۥٓـُٔوا۟ وُجُوهَكُمْ وَلِيَدْخُلُوا۟ ٱلْمَسْجِدَ كَمَا دَخَلُوهُ أَوَّلَ مَرَّةٍۢ وَلِيُتَبِّرُوا۟ مَا عَلَوْا۟ تَتْبِيرًا

ወደዚህ በይቱል መቅዲሥ ነቢያችን"ﷺ" እና ሶሓባዎች ለአስራ ስድስት ወይም ለአስራ ሰባት ወራት ያክል ቂብላህ አርገው ወደዚያ ይጸልዩ ነበር፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 656
አነሥ እንደተረከው፦ *"ነቢዩም"ﷺ" እና ሶሓባዎች ወደ በይቱል መቅዲሥ ይጸልዩ ነበር፥ ይህቺ አንቀጽ በወረደች ጊዜ፦ "ስለዚህ ፊትህን ወደ ተከበረው መሥጂድ አግጣጫ አዙር! የትም ስፍራ ብትኾኑም ፊቶቻችሁን ወደርሱ አግጣጫ አዙሩ" የሚል መጣ"*። عَنْ أَنَسٍ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم وَأَصْحَابَهُ كَانُوا يُصَلُّونَ نَحْوَ بَيْتِ الْمَقْدِسِ فَلَمَّا نَزَلَتْ هَذِهِ الآيَةُ ‏{‏ فَوَلِّ وَجْهَكَ شَطْرَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ وَحَيْثُ مَا كُنْتُمْ فَوَلُّوا وُجُوهَكُمْ شَطْرَهُ ‏}‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 19
በሯእ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *" ለአስራ ስድስት ወይም ለአስራ ሰባት ወራት ያክል ከነቢዩም"ﷺ" ጋር ወደ ወደ በይቱል መቅዲሥ እንጸልይ ነበር፥ ከዚያም አሏህ እርሳቸው ወደ ተከበረው መሥጂድ እንዲቀጣጩ አዘዛቸው"*። قَالَ سَمِعْتُ الْبَرَاءَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ صَلَّيْنَا مَعَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم نَحْوَ بَيْتِ الْمَقْدِسِ سِتَّةَ عَشَرَ ـ أَوْ سَبْعَةَ عَشَرَ ـ شَهْرًا، ثُمَّ صَرَفَهُ نَحْوَ الْقِبْلَةِ‏.‏

“ቂብላህ” قِبْلَة የሚለው ቃል “አቅበለ” أَقْبَلَ “ተቀጣጨ” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን “አቅጣጫ”direction” ማለት ነው፥ ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን ሃይማኖታዊ ፍቺው ደግሞ አቅጣጫ በመቀጣጨት የሚደረግ “የውዳሴ ነጥብ”point of adoration” ነው። ቂብላህ ወደ አል-መሥጂዱል ሐረም ከመታዘዙ በፊት ወደ በይቱል መቅዲሥ እየጸለዩ እያሉ ስለሞቱት አሏህ፦ "አላህ እምነታችሁን ስግደታችሁን የሚያጠፋ አይደለም" ብሎ ተናግሯል፦
2፥143 *"አላህም እምነታችሁን ስግደታችሁን የሚያጠፋ አይደለም፥ አላህ ለሰዎች በጣም ርኅሩኅ አዛኝ ነውና"*፡፡ وَمَا كَانَ اللَّهُ لِيُضِيعَ إِيمَانَكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ بِالنَّاسِ لَرَءُوفٌ رَّحِيمٌ
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3227
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *"ነቢዩም"ﷺ" ፊታቸውን ወደ ከዕባህ በተቀጣጩ ጊዜ ሶሓባዎች፦ "የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! እነዚያ ወደ በይቱል መቅዲሥ እየጸለዩ እያሉ ስለሞቱት ወንድሞቻችን እንዴት ይሆናሉ? አሏህም፦ "አላህ እምነታችሁን ስግደታችሁን የሚያጠፋ አይደለም" የሚል አንቀጽ አወረደ"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ لَمَّا وُجِّهَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم إِلَى الْكَعْبَةِ قَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ كَيْفَ بِإِخْوَانِنَا الَّذِينَ مَاتُوا وَهُمْ يُصَلُّونَ إِلَى بَيْتِ الْمَقْدِسِ فَأَنْزَلَ اللَّهُ‏:‏ ‏(‏وَمَا كَانَ اللَّهُ لِيُضِيعَ إِيمَانَكُمْ ‏)‏

አምላካችን አሏህ ነቢያችንን”ﷺ” ከመሥጂዱል ሐረም ወደ መሥጂዱል አቅሷ በሌሊት አስኪዷቸዋል፦
17፥1 *”ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጊድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ ሩቁ መስጊድ በሌሊት ውስጥ ያስኼደው ጌታ ጥራት ይገባው፡፡ ከተዓምራቶቻችን ልናሳየው አስኼድነው”*፡፡ እነሆ እርሱ አላህ ሰሚው ተመልካቺው ነው፡፡ سُبْحَانَ الَّذِي أَسْرَىٰ بِعَبْدِهِ لَيْلًا مِّنَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ إِلَى الْمَسْجِدِ الْأَقْصَى الَّذِي بَارَكْنَا حَوْلَهُ لِنُرِيَهُ مِنْ آيَاتِنَا ۚ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ያስኼደው” ለሚለው የገባው የግስ መደብ “አሥሯ” أَسْرَىٰ ሲሆን “ኢሥሯ” إِسْرَا የሚለው የስም መደብ እራሱ “ሣረ” سَارَ ማለትም “ተጓዘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ጉዞ” ማለት ነው። “ለይለቱል ኢሥሯ” لَيْلَة الإِسْرَا ማለት “የሌሊት ጉዞ” ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ ነቢያችንን”ﷺ” ከበይቱል ሐረም ወደ በይቱል መቅዲሥ በሌሊት ያስኬዳቸው “አል-ቡራቅ” በሚባል እንስሳ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 318
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ከአህያ ከፍ ብሎ ከበቅሎ ያነሰ፥ ነጭና ረዘም ያለ እንስሳ አል-ቡራቅ መጣልኝ። የእይታው መጨረሻ ላይ ኮቴውን ያሳርፋል፥ በእርሱ እስከ በይቱል መቅዲሥ ተጓዝኩኝ”*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ أُتِيتُ بِالْبُرَاقِ – وَهُوَ دَابَّةٌ أَبْيَضُ طَوِيلٌ فَوْقَ الْحِمَارِ وَدُونَ الْبَغْلِ يَضَعُ حَافِرَهُ عِنْدَ مُنْتَهَى طَرْفِهِ – قَالَ فَرَكِبْتُهُ حَتَّى أَتَيْتُ بَيْتَ الْمَقْدِسِ

“አል-ቡራቅ” الْبُرَاق የሚለው ቃል “በረቀ” بَرَقَ ማለትም “በረቀ” “በለጨ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ብርቅታ” “ብልጭታ” ማለት ነው፥ “መብረቅ” እራሱ “በርቅ” بَرْق ይባላል። ይህ እንስሳ ከአህያ ከፍ ብሎ ከበቅሎ ያነሰ፥ ነጭና ረዘም ያለ እንስሳ ነው። ስለ አል-አርዱል ሙቀደሣህ ከነቢዩሏህ ኢብራሂም እስከ ነቢያችን"ﷺ" ያለውን ክስተት ከቁርኣን እና ከሐዲስ በግርድፉና በሌጣው ይህንን ይመስላል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሰገደለት ወይስ ሰገደበት?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

25፥60 *"ለእነርሱም፦ "ለአልረሕማን ስገዱ" በተባሉ ጊዜ "አልረሕማን ማነው? ለምታዘን እንሰግዳለን? ይላሉ፡፡ ይህ መራቅንም ጨመራቸው"*፡፡ وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ اسْجُدُوا لِلرَّحْمَـٰنِ قَالُوا وَمَا الرَّحْمَـٰنُ أَنَسْجُدُ لِمَا تَأْمُرُنَا وَزَادَهُمْ نُفُورًا ۩

"ሡጁድ" سُّجُود የሚለው ቃል "ሠጀደ" سَجَدَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ስግደት" ማለት ነው፥ ሥጁድ ሶላት ውስጥ ከሚከወኑ ዒባዳህ መካከል አንዱ ነው፦
22፥77 *"እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ በስግደታችሁ አጎንብሱ፣ በግንባራችሁም ተደፉ፣ ጌታችሁንም አምልኩ፣ በጎንም ነገር ሥሩ፣ ልትድኑ ይከጀልላችኋልና"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا ارْكَعُوا وَاسْجُدُوا وَاعْبُدُوا رَبَّكُمْ وَافْعَلُوا الْخَيْرَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ ۩

"በግንባራችሁም ተደፉ" ለሚለው ትእዛዛዊ ግስ የገባው ቃል "ኢሥጁዱ" اسْجُدُوا ሲሆን በሶላት ውስጥ ያለው ሥጁድ ለአሏህ ብቻ የሆነ መተናነስ፣ መጎባደድ፣ ማሸርገድ ነው፦
25፥60 *"ለእነርሱም፦ "ለአልረሕማን ስገዱ" በተባሉ ጊዜ "አልረሕማን ማነው? ለምታዘን እንሰግዳለን? ይላሉ፡፡ ይህ መራቅንም ጨመራቸው"*፡፡ وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ اسْجُدُوا لِلرَّحْمَـٰنِ قَالُوا وَمَا الرَّحْمَـٰنُ أَنَسْجُدُ لِمَا تَأْمُرُنَا وَزَادَهُمْ نُفُورًا ۩

"ለ-አር-ረሕማን ስገዱ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! "አር-ረሕማን" لرَّحْمَـٰن በሚለው ስም መነሻ ላይ "ሊ" لِ ማለት "ለ" የሚል መስተዋድድ መምጣቱ በሶላት ውስጥ ያለው ሥጁድ "ለ"አሏህ መሆኑ እሙንና ቅቡል መሆኑን ያስረግጣል። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ ሚሽነሪዎች የሚሰገድበት ነገር የሚሰገድለት ነገር አድርገው ያጣመሙትን ሐዲስ እንመልከት፦
ቡሉጉል መራም መጽሐፍ 6, ሐዲስ 40
ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"ሐጀሩል አሥወድን ሳመው እና ሰገደበት"*። وَعَنْ اِبْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اَللَّهُ عَنْهُمَا: { أَنَّهُ كَانَ يُقَبِّلُ اَلْحَجَرَ اَلْأَسْوَدَ وَيَسْجُدُ عَلَيْهِ }

እዚህ ሐዲስ ላይ በሐጅሩል አሥወድ ላይ መሰገዱ በራሱ ሐጅሩል አሥወድ የሚሰገድበት እንጂ የሚሰገድለት አለመሆኑ ፍንትውና ቁልጭ አርጎ ያሳያል። እንደሚሽነሪዎች ቅጥፈት "ሰገደለት" ለማለት መግባት የነበረበት ቃል "የሥጁዱ ለ-ሁ" يَسْجُدُ لَهُ እንጂ "የሥጁዱ ዐለይ-ሂ" يَسْجُدُ عَلَيْهِ አይደለም፥ ቅሉና ጥቅሉ ግን ሐዲሱ ላይ የሚለው "የሥጁዱ ዐለይ-ሂ" يَسْجُدُ عَلَيْهِ ነው። "የሥጁዱ ዐለይ-ሂ" يَسْجُدُ عَلَيْهِ ማለት "ሰገደበት" ማለት እንጂ "ሰገደለት" ማለት እንዳልሆነ የምንረዳው ለመስገጃ ምንጣፍ የምንጠቀምበት ሰዋስው መሆኑ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 4, ሐዲስ 321
አቢ ሠዒድ አል-ኹድሪይ እንደዘገበው፦ "ነቢዩን"ﷺ" ጎብኝቷቸው እንዲህ አለ፦ *"በምንጣፉ ላይ እየጸለዩ ሲሰግዱበት ዐየኃቸው"*። حَدَّثَنِي أَبُو سَعِيدٍ الْخُدْرِيُّ، أَنَّهُ دَخَلَ عَلَى النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ فَرَأَيْتُهُ يُصَلِّي عَلَى حَصِيرٍ يَسْجُدُ عَلَيْهِ

"ሲሰግዱበት" ለሚለው የገባው ቃል በተመሳሳይ "የሥጁዱ ዐለይ-ሂ" يَسْجُدُ عَلَيْهِ መሆኑን ልብ በል! ምንጣፍ "የሚሰገድበት" ሆኖ ሳለ "የሚሰገድለት" ብሎ አንሸዋሮ እና አሳክሮ ሲነግሩት ቂል ሰው ካልሆነ በስተቀር እንደማይቀበል ሁሉ ሐጀሩል አሥወድ ሰገደበት የሚለውን ሰገደለት ብሎ ሲነገረው የሚቀበል ቂል ሰው ብቻ ነው። ስለዚህ ሐጀሩል አሥወድ የተሰገድበት ምንጣፉ ተሰገደበት በተባለበት ቃላት ከነበረ አንሸዋሮ "ተሰግዶለታል" የሚለው ቅጥፈት ድባቅ ይገባል ማለት ነው፥ ውሸት በእውነት ፊት እሳት የነካው ሰም፣ ፀሐይ ያየው ቅቤ፣ ነፋስ የጎበኘው አቧራ ይሆናል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

47፥19 *እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ*፡፡ فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه

ከንፈር እና ከንፈር ሳይነካካ በምላስ የሚዘከር ዚክር ቢኖር “ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ” ብቻ ነው፥ ነቢያችን”ﷺ”፦ "በላጩ ዚክር ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ ነው" ብለውናል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 48, ሐዲስ 14
ጃቢር ኢብኑ ዐብደሏህ”ረ.ዐ” ሰምቶ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *”በላጩ ዚክር "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" ነው"*። قَالَ سَمِعْتُ جَابِرَ بْنَ عَبْدِ اللَّهِ، رضى الله عنهما يَقُولُ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ “‏ أَفْضَلُ الذِّكْرِ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ

ይህ በላጭ የዚክር ዓይነት ተህሊል ይባላል፥ “ተህሊል” تَهْلِيل‎ የሚለው ቃል “ሐለለ” هَلَّلَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ” لَا إِلٰهَ إِلَّا اللّٰه ማለት ነው፥ “ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ” لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه ማለት “አምላክ የለም፥ ከአሏህ በስተቀር” ማለት ነው። ይህ ተህሊል ሁለት ማዕዘናት አሉት፥ እነርሱም፦ “ነፍይ” እና “ኢስባት” ናቸው። “ነፍይ” نَفْي የሚለው ቃል “ነፋ” نَفَى‎ ማለትም “አፈረሰ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማፍረስ” ማለት ነው። ነፍይ “ላ ኢላሀ” لَا إِلَـٰهَ ማለትም “አምላክ የለም” በማለት ጣዖታትን የምናፈራርስበት አዋጅ ነው፦
2፥256 “በጣዖትም የሚክድ እና በአላህ የሚያምን ሰው ለእርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ”፡፡ فَمَن يَكْفُرْ بِالطَّاغُوتِ وَيُؤْمِن بِاللَّهِ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ لَا انفِصَامَ لَهَا

“ኢስባት” إِثْبَات የሚለው ቃል “አስበተ” أَثْبَتَ‎ ማለትም “አጸደቀ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማፅደቅ” ማለት ነው፥ ኢስባት "ኢለል ሏህ” إِلَّا اللّٰه ማለትም “ከአሏህ በቀር” በማለት የምናጸድቅበት አዋጅ ነው። “ላ ኢላሀ” ስንል በጣዖት መካዳችን ሲሆን "ኢለል ሏህ” ስንል ደግሞ በሐቅ የሚመለክ አሏህ ብቻ መሆኑን ማመናችን ነው፥ በጣዖትም የሚክድ እና በአላህ የሚያምን ሰው ለእርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፡፡ ይህ የላ ኢላሀ ኢለል ሏህ ዘለበት የጨበጠ ሰው ሙሥሊም ይባላል፦
31፥22 *"እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ ፊቱን ወደ አላህ የሚሰጥም ሰው ጠንካራን ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ"*፡፡ وَمَن يُسْلِمْ وَجْهَهُ إِلَى اللَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ

2፥256 እና 31፥22 ላይ "ዘለበት" ለሚለው የገባው ቃል "ዑርዋህ" عُرْوَة ሲሆን በጣዖትም የሚክድ እና በአሏህ የሚያምን ሰው ፊቱን ወደ አላህ የሚሰጥ ሰው ነው፥ "የሚሰጥ" ለሚለው የገባው ቃል እራሱ "ዩሥሊም" يُسْلِمْ መሆኑ በራሱ "ሙሥሊም" مُسْلِم ማለት የላ ኢላሀ ኢለል ሏህ ዘለበት በትክክል ዐውቆ እራሱ ለአሏህ የሰጠ ማለት ነው፦
47፥19 *እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ*፡፡ فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه

እዚህ አንቀጽ ላይ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه የሚል አዋጅ አለ፥ "ዕወቅ" የሚለው ደግሞ ከአሏህ ሌላ አምላክ አለመኖሩን ነው። "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" የሚለውን በትክክል ዐውቆ እና አሏህን በብቸኝነት አምልኮ እንዲሁ በአሏህ ላይ ምንም ነገር ያላሻረከ ጀነት ይገባል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 43
ዑስማን እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ማንም "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" የሚለውን በትክክል ዐውቆ የሞተ ጀነት ገባ"*። عَنْ عُثْمَانَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَنْ مَاتَ وَهُوَ يَعْلَمُ أَنَّهُ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ دَخَلَ الْجَنَّةَ ‏"‏ ‏.‏
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 176
ጃቢር ኢብኑ ዐብዱል ሏህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ማንም በአሏህ ላይ ምንም ነገር ሳያጋራ አሏህን የሚገናኝ ጀነት ገባ"*። حَدَّثَنَا جَابِرُ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ مَنْ لَقِيَ اللَّهَ لاَ يُشْرِكُ بِهِ شَيْئًا دَخَلَ الْجَنَّةَ
"ዐቂዳህ" عَقِيدَة የሚለው ቃል "ዐቀደ" عَقَدَ‎ ማለትም "ቋጠረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መቋጠር" ማለት ነው፥ አንድ ሙእሚን ዐቂዳህ ምንድን ነው? ማለታችን በልብህ የቋረጠከው አንቀጸ-እምነት"Creed" ምንድን ነው? ማለታችን ነው። ይህ በልብ ውስጥ የተቋጠረው ዐቂዳህ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه ሲሆን ትልቁ የኢማን ቅርንጫፍ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 60
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ኢማን ከሰባ ወይም ከስልሳ በላይ ቅርንጫፎች አሉት፤ ትልቁ ቅርንጫፍ “ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ” የሚለው ቃል ነው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الإِيمَانُ بِضْعٌ وَسَبْعُونَ أَوْ بِضْعٌ وَسِتُّونَ شُعْبَةً فَأَفْضَلُهَا قَوْلُ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ

አምላካችን አሏህ በመጀመርያ መደብ፦ "ላ ኢላሀ ኢላ አና" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَ ማለትም "ከእኔ ሌላ አምላክ የለም" በማለት ይናገራል፦
21፥25 *"ከአንተ በፊትም እነሆ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለም" እና አምልኩኝ! በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም"*፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ

"አምልኩኝ" የሚለው ይህ አንድ እኔነት አምልኮ የእርሱ ሐቅ እና ገንዘቡ የሆነው አንዱ አምላክ አሏህ ነው። ይህ አንዱ አምላክ በየሕዝቡ ሁሉ ከእነርሱ የሆነ መልእክተኛ በመላክ፦ "አላህን አምልኩ! ከእርሱ ሌላ አምላክ የላችሁም" ወይም "አላህን አምልኩ! ጣዖትንም ራቁ" በማለት ይናገራል፦
23፥32 *"በውስጣቸውም ከእነርሱ የኾነን መልክተኛ፦ "አላህን አምልኩ! ከእርሱ ሌላ አምላክ የላችሁም፥ አትጠነቀቁምን? በማለት ላክን"*፡፡ فَأَرْسَلْنَا فِيهِمْ رَسُولًا مِّنْهُمْ أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَـٰهٍ غَيْرُهُ ۖ أَفَلَا تَتَّقُونَ
16፥36 *"በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን አምልኩ! ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል"*፡፡ وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَ

ስለዚህ "ከሊመቱል ዐቂዳህ" كَلِمَة الْعَقِيدَة የሆነው "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" የነቢያት ዐቂዳህ ነው፥ የኢሥላምን መሠረትና ውቅር፣ ዋልታና ማገር፣ አስኳልና አንኳር ይህ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" ነው። ይህንን ከሊመቱል ዐቂዳህ ሰምተውና ዐውቀው በማስተባበል ሳይቀበሉ የሞቱ ሰዎች በሚቀሰቀሱበት በትንሣኤ ቀን የእሳት ቅጣት የመቅመሳቸው ምክንያት፦ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ስለነበር ነው፥ በፍርዱ ቀን እነዚያ በኩራት የካዱት ሙሥሊሞች ቢሆኑ ኖሮ በብዛት ይመኛሉ፦
37፥35 *"እነርሱ፦ "ከአላህ ሌላ አምላክ የለም" በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ"*፡፡ إِنَّهُمْ كَانُوا إِذَا قِيلَ لَهُمْ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّهُ يَسْتَكْبِرُونَ
15፥2 *"እነዚያ የካዱት በፍርዱ ቀን ሙስሊሞች በኾኑ ኖሮ በብዛት ይመኛሉ"*፡፡ رُّبَمَا يَوَدُّ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْ كَانُوا مُسْلِمِينَ

አምላካችን አሏህ የላ ኢላሀ ኢለል ሏህን ዘለበት ጨብጠው እስከ መጨረሻው ከሚጸኑት ሙሥሊሞች ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ምእመናን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

9፥71 *"ምእመናን እና ምእመናት ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ በደግ ነገር ያዛሉ፥ ከክፉም ይከለክላሉ"*፡፡ وَالْمُؤْمِنُونَ وَالْمُؤْمِنَاتُ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ يَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ

ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ የሚለውን የአሏህን ዘለበት የያዙ ምእመናን በልቦቻችሁም መካከል ስምምነት ስላለ አይለያዩም፥ በጸጋውም ወንድማማቾች ናቸው፦
3፥103 *"የአላህንም ዘለበት ሁላችሁም ያዙ፤ አትለያዩም፣ ጠበኞችም በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋ አስታውሱ! በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፥ በጸጋውም ወንድማማቾች ኾናችሁ"*፡፡ وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا ۚ وَاذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ كُنتُمْ أَعْدَاءً فَأَلَّفَ بَيْنَ قُلُوبِكُمْ فَأَصْبَحْتُم بِنِعْمَتِهِ إِخْوَانًا
49፥10 *"ምእመናን ወንድማማቾች ናቸው፡፡ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል አስታርቁ! ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ"*፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ فَأَصْلِحُوا بَيْنَ أَخَوَيْكُمْ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ

"ሙእሚን" مُؤْمِن ማለት ኢማን ያለው "አማኝ" ወይም "ምእመን" ማለት ነው፥ የሙእሚን ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሙእሚኑን" مُؤْمِنُون ወይም "ሙእሚኒን" مُؤْمِنِين ማለት ሲሆን "አማኞች" ወይም "ምእመናን" ማለት ነው። አማንያን ሳይግባቡ ሲቀር ማስታረቅ ግዴታ ነው፥ ምእምን እና ምእምናትም ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፦
9፥71 *"ምእመናን እና ምእመናት ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው"*፡፡ وَالْمُؤْمِنُونَ وَالْمُؤْمِنَاتُ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 45, ሐዲስ 83
አቡ ሙሣ እንደተረከው፥ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ሙእሚን ለሙእሚን ልክ አንዱ ለሌላው እንደሚደግፈው ሸክላ ነው"*። عَنْ أَبِي مُوسَى، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ الْمُؤْمِنُ لِلْمُؤْمِنِ كَالْبُنْيَانِ يَشُدُّ بَعْضُهُ بَعْضًا ‏"‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 46, ሐዲስ 7
አቡ ሙሣ" እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" አሉ፦ *"ሙእሚን ለሙእሚን ልክ እንደተሳሰረ ግንብ ነው፥ አንዱ ሌላውን ያጠነክራል። ጣታቸውን በማያያዝ አመለከቱ"*። عَنْ أَبِي مُوسَى، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ إِنَّ الْمُؤْمِنَ لِلْمُؤْمِنِ كَالْبُنْيَانِ، يَشُدُّ بَعْضُهُ بَعْضًا ‏"‌‏.‏ وَشَبَّكَ أَصَابِعَهُ‏.‏

ምእመናን እርስ በእርስ አንዱ ሌላውን በደግ ነገር ያዛሉ፥ ከክፉም ይከለክላሉ። ጥፋት ካለ እንኳን ሙእሚን ለሙእሚን እራሱን የሚያይበት መስታወቱ ስለሆነ በደግ ነገር ያዘዋል፥ ከክፉም ነገርም ይከለክለዋል፦
9፥71 *" በደግ ነገር ያዛሉ፥ ከክፉ ነገርም ይከለክላሉ"*፡፡ يَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ
ሡነን አቡ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 146
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፥ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ሙእሚን የሙእሚን መስታወት ነው፥ ሙእሚን በሙእሚን ወንድሙ ላይ ክስረቱን የሚያስቆም እና ከጀርባው የሚጠብቀው ነው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ الْمُؤْمِنُ مِرْآةُ الْمُؤْمِنِ وَالْمُؤْمِنُ أَخُو الْمُؤْمِنِ يَكُفُّ عَلَيْهِ ضَيْعَتَهُ وَيَحُوطُهُ مِنْ وَرَائِهِ ‏"‏ ‏.‏

የዲን ወንድምነት ከአብራክ ወንድምነት ይበልጣል፥ ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ የሚለውን የአሏህን ዘለበት የያዙ ምእመናን እርስ በእርስ ያለው ግኑኝነት፣ ስሜት፣ ጉዳት እና ህመም ልክ እንደ አንድ ሰው አንድ አካል የተለያዩ ክፍሎች ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 45, ሐዲስ 84
አን-ኑዕማን ኢብኑ በሺር እንደተረከው፦ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በመዋደዳቸው፣ በመተዛዘናቸው እና በመራራታቸው የምእመናን ምሳሌ ልክ እንደ አንድ አካል ነው፥ አንዱ የአካል ክፍል በታመመ ጊዜ ሌሎቹ የአካሉ ክፍሎች እንቅልፍ በማጣት እና በትኩሳት ይጠራራሉ"*። عَنِ النُّعْمَانِ بْنِ بَشِيرٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَثَلُ الْمُؤْمِنِينَ فِي تَوَادِّهِمْ وَتَرَاحُمِهِمْ وَتَعَاطُفِهِمْ مَثَلُ الْجَسَدِ إِذَا اشْتَكَى مِنْهُ عُضْوٌ تَدَاعَى لَهُ سَائِرُ الْجَسَدِ بِالسَّهَرِ وَالْحُمَّى ‏"‏ ‏.‏
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 45, ሐዲስ 86
አን-ኑዕማን ኢብኑ በሺር እንደተረከው፦ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ሙእሚኖች ልክ እንደ አንድ ሰው ነው፥ ራሱ ሲታመም ሌሎቹ የአካሉ ክፍሎች በትኩሳት እና እንቅልፍ በማጣት ይጠራራሉ"*። عَنِ النُّعْمَانِ بْنِ بَشِيرٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ الْمُؤْمِنُونَ كَرَجُلٍ وَاحِدٍ إِنِ اشْتَكَى رَأْسُهُ تَدَاعَى لَهُ سَائِرُ الْجَسَدِ بِالْحُمَّى وَالسَّهَرِ ‏"‏ ‏.‏

ይህ ትስስር ድንቅ ትስስር ነው፥ በዘር፣ በብሔር፣ በዘውግ፣ በቋንቋ፣ በትውፊት፣ በባህል የማይተዋወቁ በዓለም ላይ ያሉት ምእመናን አንዱ የሌላው ህመም ያመዋል፣ ይጎዳዋል፣ እንቅልፍ ያሳጣዋል። እሩቅ ሳንሄድ በፍልስጥኤማውያን ላይ እየደረሰባቸው ያለው በደል የዲን ጉዳይ ስለሆነ እና ሙሥሊም በመሆናቸው ስለሆነ ህመሙ የጋራ ሆኖ ያመናል፥ ስለዚህ የፍልስጥኤማውያን ጉዳይ ልክ እንደ አዛርባጃን የድንበር ጉዳይ፣ እንደ ግብፅ የፓለቲካ ጉዳይ፣ እንደ ዒራቅ የኢኮኖሚ ጉዳይ ሳይሆን የላ ኢላሀ ኢለል ሏህ ጉዳይ ነው። በመላው ዓለም ላይ ያሉ ምእመናን በዱንያህ ላይ የሚደርስባቸው እንግልት፣ መከራ፣ ስደት፣ ሞት ይህቺ ዱንያህ ለሙእሚን እስር ቤት ስለሆነች ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 55, ሐዲስ 1
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ዱንያህ ለሙእሚን እስር ቤት ናት፥ ለካፊር ደግሞ ጀናህ ናት"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ الدُّنْيَا سِجْنُ الْمُؤْمِنِ وَجَنَّةُ الْكَافِرِ ‏"‏ ‏.‏

አምላካችን አሏህ በዓለም ላይ ላሉት ምእመናን ነስሩን ያቅርብልን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኡማህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

16፥36 *”በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን አምልኩ፥ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልእክተኛን በእርግጥ ልከናል*፡፡ وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِى كُلِّ أُمَّةٍۢ رَّسُولًا أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ وَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلطَّٰغُوت

“ኡማህ” أُمَّة የሚለው ቃል “አመ” أَمَّمَ ማለትም “በዛ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ሕዝብ” ወይም “ብዙኃን” ማለት ነው። “ኡመም” أُمَم የኡማህ ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሕዝቦች” ማለት ነው። ለምሳሌ አምላካችን አሏህ በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ “አላህን አምልኩ፥ ጣዖትንም ራቁ” በማለት መልእክተኛን በእርግጥ ልኳል፦
16፥36 *”በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን አምልኩ፥ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልእክተኛን በእርግጥ ልከናል*፡፡ وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِى كُلِّ أُمَّةٍۢ رَّسُولًا أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ وَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلطَّٰغُوت

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሕዝብ" ለሚለው የገባው ቃል "ኡማህ" أُمَّة መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። በባይብልም ቢሆን "ሕዝብ" ለሚለው የገባው የዐረማይኩ እና የዕብራይስጡ ቃል "ኡማህ" אֻמָּה ነው፦
ዳንኤል 3፥29 *"እኔም እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም አምላክ ላይ የስድብን ነገር የሚናገር ወገን እና "ሕዝብ" በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚናገሩ ይቈረጣሉ"*። ומני שים טעם די כל־עם אמה ולשן די־יאמר [שלה כ] (שלו ק) על אלההון די־שדרך מישך ועבד נגוא הדמין יתעבד וביתה נולי ישתוה כל־קבל די לא איתי אלה אחרן די־יכל להצלה כדנה׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሕዝብ" ለሚለው የገባው ቃል "ኡማህ" אֻמָּה መሆኑም ልብ አድርግ! የሕዝብ ብዙ ቁጥር ደግሞ "አሕዛብ" ሲሆን "ሕዝቦች" ማለት ነው። ሌላም ጥቅስ ላይ ሳይቀር "አሕዛብ" ወይም "ሕዝቦች" ለሚለው የገባው ቃል "ኡማህ" אֻמַּה ሲሆን ብዙ ቁጥሩ ደግሞ "ኡሚም" אֻמִּֽים ነው፦
መዝሙር 117፥1 *"አሕዛብ ሁላችሁ ያህዌህን አመስግኑት! "ወገኖችም" ሁሉ ያመስግኑት"*። הַֽלְל֣וּ אֶת־יְ֭הוָה כָּל־גֹּויִ֑ם בְּח֗וּהוּ כָּל־הָאֻמִּֽים

ስለዚህ "ኡማህ" ማለት "ኢሥላማዊ ሕዝብ" ማለት ነው፥ "ኦሮሙማ" ማለት "የኦሮሞ ኢሥላማዊ ሕዝብ" ማለት ነው" ላላችሁን የኦርቶ-ዐማራህ የፓለቲከኛ ነጋዴዎች ከላይ ያለውን ቃል በዛ ቀመር እና ስሌት ተርጉሙት እና መቀመቅ ውስጥ እንደምትገቡ አልጠራጠርም።

"ኦሮሞ" Oromo በሚለው መድረሻ ቅጥያ ቃል ላይ "ኦሮሞነት" ብለን ባሕርይን ለማመልከል ስንፈልግ "ኦሮሙማ" Oromummaa ብለን እንጠቀማል፥ ለምሳሌ፦
፨"ቢሊሰ" Bilisa ማለት "ነጻ" ማለት ሲሆን "ነጻነት" ብለን ባሕርይ ለማመልከት ደግሞ "ቢሊሱማ" Bilisummaa እንላለን፣
፨"ቶኮ" Tokko ማለት "አንድ" ማለት ሲሆን "አንድነት" ብለን ባሕርይ ለማመልከት ደግሞ "ቶኩማ" Tokkummaa እንላለን፣
፨"ኢትዮጵያ" Itiyoopiyaa ብለን "ኢትዮጵያዊነት" ብለን ባሕርይ ለማመልከት ደግሞ "ኢትዮጵያዉማ" Itiyoopiyaawummaa እንላለን።

እዚህ ድረስ ከተግባባን እስቲ ይህንን ጠባብ ሙግት በቋንቋ ሙግት አፈታት እንመልከት፦
"ዐማሐራህ" ማለት የሁለት የዕብራይስጥ ቃላት ውቅር ነው፥ "አማ" "ኡማ" ማለት "ሕዝብ" ማለት ሲሆን "ሐራማ" "ሐርማ" ማለት "ተራራ" ማለት ነው። በጥቅሉ "በተራራ ላይ የሚኖር ሕዝብ" ማለት ነው፥ በኦርቶ-ዐማራህ ትርጉም "ዐማ" ማለት ሃይማኖት ሲሆን "ሐራማ" ማለት ዘር ማለት ነው" በማለት ዐማራ ማለት የዘር እና የሃይማኖት ውሕደት እንበል? እንደውም "መስከረም" ማለት የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ "መስክ" ማለት "ሜዳ" ማለት ሲሆን "አረም" ማለት "ያልታረመ" ማለት ነው። በጥቅሉ "መስከረም" ማለት "የመስክ አረም" ማለት ነው፥ "ያልታረምሽ የሜዳ አረም ወይም በዬኔታ ሚዲያ ላይ ያልታረመ ቃላት የምትዘራ" እንበላት? ያስኬዳል? እንዲህ መቦተረፍ ይቻላል፥ ቅሉና ጥቅሉ ግን ቅጥፈት መጋለጡ አይቀርም። እረ በመጠበብ ዘመን አንጥበብ!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የምናመልከው አንዱ አምላክ

እኛ ሙሥሊሞች የምናመልከው አንዱ አምላክ አሏህ፦
1. በአንድ ምንነቱ ላይ ሁለት ወይም ሦስት ማንነት የሌለበት፣
2. በአምላክነቱ ላይ ሰውነት የሌለበት፣
3. በጌትነቱ ላይ ባርነት የሌለበት፣
4. በሕያውነቱ ላይ ሞት የሌለበት ፣
5. በጥበቃው ላይ እንቅልፍ የሌለበት፣
6. በኃያልነቱ ላይ ድካም የሌለበት፣
7. በፈጣሪነቱ ፍጡርነት የሌለበት ነው።

መከፋፈል፣ ሰው መሆን፣ ባሪያ መሆን፣ መሞት፣ ማንቀላፋት፣ መድከም፣ መፈጠር የፍጡር ባሕርይ ናቸው፥ ፈጣሪ እነዚህን የፍጡራን ባሕርይ አይሆንም። በእርሱ ባሕርይ ውስጥ ማስሆን እንጂ መሆን የሚባል ባሕርይ የለውም፥ እርሱ አድራጊ እንጂ ተደራጊ አይደለም።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሙት ማስነሳት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

46፥33 ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ፥ እነርሱንም በመፍጠሩ ያልደከመው አላህ ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ መኾኑን አላስተዋሉምን? በማስነሳት ቻይ ነው፡፡ እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡ أَوَلَمْ يَرَوْا أَنَّ اللَّهَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَلَمْ يَعْيَ بِخَلْقِهِنَّ بِقَادِرٍ عَلَىٰ أَن يُحْيِيَ الْمَوْتَىٰ ۚ بَلَىٰ إِنَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

ሚሽነሪዎች ሁልጊዜ ቋ ያለ ጉፋያ ሃሳብ እንደ በቀቀን መደጋገም ይወዳሉ፤ የማይመክን ሃሳብ ይዞ ከመሞገት ይልቅ መንፈቅፈቁንና መነፋረቁን፥ መንሰክሰኩንና መንከንከኑን ተያይዘውታል፤ ጭራሽ ኢየሱስ ሙት ማስነሳቱ ለአምላክነቱ ማስረጃ አድርገው አርፈውታል።
አምላካችን እና ጌታችን አላህ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ፤ እነርሱንም በመፍጠሩ ያልደከመው፤ ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ ነው፤ እርሱም በመጀመሪያ መደብ፦ “እኛ ሙታንን በእርግጥ ሕያው እናደርጋለን” ይለናል፦
46፥33 ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ፤ እነርሱንም በመፍጠሩ ያልደከመው አላህ ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ መኾኑን አላስተዋሉምን? በማስነሳት ቻይ ነው፡፡ እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡ أَوَلَمْ يَرَوْا أَنَّ اللَّهَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَلَمْ يَعْيَ بِخَلْقِهِنَّ بِقَادِرٍ عَلَىٰ أَن يُحْيِيَ الْمَوْتَىٰ ۚ بَلَىٰ إِنَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
36፥12 *”እኛ ሙታንን በእርግጥ ሕያው እናደርጋለን”*፡፡ ያስቀደሙትንም ሥራ ፈለጎቻቸውንም እንጽፋለን፡፡ ነገሩንም ሁሉ ገላጭ መሪ በኾነ መጽሐፍ ውስጥ አጠቃለልነው፡፡ إِنَّا نَحْنُ نُحْيِي الْمَوْتَىٰ وَنَكْتُبُ مَا قَدَّمُوا وَآثَارَهُمْ ۚ وَكُلَّ شَيْءٍ أَحْصَيْنَاهُ فِي إِمَامٍ مُّبِينٍ

አላህ “ማኅየዊ” ማለትም “አስነሺ” “ሕይወት ሰጪ” ነው። “ትንሳኤ” ለሚለው የግስ መደብ የገባው ቃል “አቃመ” أَقَامَ “አሕያ” أَحْيَا “በዐሰ” بَعَثَ ነው። ይህንን ቃል ይዘን ወደ ባይብል ከገባን በባይብል ሙት አስነሺ የተባለው ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያት እና ነቢያትም ጭምር ናቸው፦
ማቴዎስ 10፥8 ድውዮችን ፈውሱ፤ *”ሙታንን አስነሡ”*፤ ለምጻሞችን አንጹ፤ አጋንንትን አውጡ፤ በከንቱ ተቀበላችሁ፥ በከንቱ ስጡ። اشفُوا المَرضَى، أقِيمُوا المَوتَى، اشفُوا البُرصَ، أخرِجُوا الأرواحَ الشِّرِّيرَةَ. أخَذْتُمُ السُّلطانَ لِعَمَلِ ذَلِكَ مَجّاناً، فَأعطُوا الآخَرِينَ مَجّاناً أيضاً.

“አስነሱ” ለሚለው ቃል “አቂሙ” أقِيمُوا በሚል መጥቷል፤ ታዲያ ሐዋርያቱ አምላክ ነበሩን? ኢየሱስ የሠራውን ሥራ በእርሱ መልእክተኝነት ያመኑ ሰዎችም እርሱ ከሠራው ሥራ ይበልጥ ሊሠሩ እንደሚችሉ እራሱ ተናግሯል፦
ዮሐንስ 14፥13 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን *”እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል”*፥

በዚህ መሰረት በኢየሱስ ነብይነት ያመኑት ሃዋርያትም ኢየሱስ የሠራውን ሥራ ማለትም ሰው ከሞት ማስነሳት ሠርተውቷል፦
የሐዋርያት ሥራ 9:40 ጴጥሮስም ሁሉን ወደ ውጭ አስወጥቶ ተንበርክኮም ጸለየ፥ *”ወደ ”ሬሳውም ዘወር ብሎ። ጣቢታ ሆይ፥ ”ተነሺ” አላት። እርስዋም ዓይኖችዋን ከፈተች ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች”*።

ብሉይ ኪዳን ላይ የነበሩት ሁለት ነቢያት ኤልያስ እና ኤልሳዕ የሁለት ሴቶችን ልጆች አስነስተዋል፦
1. ኤልያስ፦
1ኛ ነገሥት 17፥21-23 *በብላቴናውም ላይ ሦስት ጊዜ ተዘረጋበት፥ ወደ እግዚአብሔርም። አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ የዚህ ብላቴና ነፍስ ወደ እርሱ ትመለስ ዘንድ እለምንሃለሁ ብሎ ጮኸ፤ እግዚአብሔርም “የኤልያስን ቃል ሰማ፤ የብላቴናው ነፍስ ወደ እርሱ ተመለሰች”፥ እርሱም ዳነ፤ ኤልያስም ብላቴናውን ይዞ ከሰገነቱ ወደ ቤት አወረደው፥ ኤልያስም። እነሆ፥ “ልጅሽ በሕይወት ይኖራል” ብሎ ለእናቱ ሰጣት*።

2. ኤልሳዕ፦
1ኛ ነገሥት 4፥32-34 *ኤልሳዕም ወደ ቤት በገባ ጊዜ እነሆ፥ “ሕፃኑ ሞቶ” በአልጋው ላይ ተጋድሞ ነበር። ገብቶም በሩን ከሁለቱ በኋላ ዘጋ፥ ወደ እግዚአብሔርም ጸለየ፤ መጥቶም በሕፃኑ ላይ ተኛ፤ “አፉንም በአፉ፥ ዓይኑንም በዓይኑ፥ እጁንም በእጁ ላይ አድርጎ ተጋደመበት፤ የሕፃኑም ገላ ሞቀ”፤ ተመልሶም በቤቱ ውስጥ አንድ ጊዜ ወዲህና ወዲያ ተመላለሰ፤ ደግሞም ወጥቶ ሰባት ጊዜ በሕፃኑ ላይ ተጋደመ፤ ሕፃኑም ዓይኖቹን ከፈተ*።

የዕብራውያን ጸሐፊ ይህንን ጉዳይ በማስታወስ በኤልያስ እና በኤልሳዕ ዘመን የነበሩት ሁለት ሴቶሽ ሙታን ልጆቻቸውን በትንሳኤ ተቀበሉ ይለናል፦
11፥35 *ሴቶች ሙታናቸውን “በትንሣኤ” ተቀበሉ*፤

ልብ በል “ትንሳኤ” የተባለው በብሉይ ኪዳን ሁለት ነብያት የሞቱ ሰዎችን ያስነሱትን የሴቶችን ህፃናት እንደሆነ እሙንና ቅቡል ነው፤ ታዲያ ሁለት ነቢያት ኤልያስ እና ኤልሳዕ የሁለት ሴቶችን ልጆች ስላስነሱ አምላክ ናቸውን? አይ፦ “ሐዋርያቱ እና ነቢያቱ ሙት ያስነሱት በጸሎት ነው” ይሉናል፤ ኢየሱስስ ጸልዮ እኮ ነው ሙት ያስነሳው፤ ኢየሱስ እግዚአብሔርን ለምኖ ሰዎች እግዚአብሔር እንዳላከው እንዲያምኑበት የተሰጠው ስራ እንደሆነ ተናግሯል፦
ዮሐንስ 11፥41-44 ድንጋዩንም አነሡት። *ኢየሱስም ዓይኖቹን ወደ ላይ አንሥቶ። “አባት ሆይ፥ ስለ ሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ፤ ሁልጊዜም እንድትሰማኝ” አወቅሁ፤ ነገር ግን “አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ ዘንድ” በዚህ ዙሪያ ስለ ቆሙት ሕዝብ ተናገርሁ አለ። ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ። አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና ብሎ ጮኸ። የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ፤ ፈቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበር። ኢየሱስም። ፍቱትና ይሂድ ተዉት አላቸው*።
ኢየሱስ የሚያደርጋቸው ታምራት ሁሉ በፈጣሪ ስም እንጂ ከራሱ ምንም ማድረግ አይችልም፦
ዮሐንስ 10፥25 ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል። ነገርኋችሁ አታምኑምም *”እኔ በአባቴ ስም የማደርገው ሥራ ስለ እኔ ይመሰክራል”*።
ዮሐንስ 5:30 *”እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም”*፤

እንዴት አምላክ የሆነ ህላዌ “ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም” ይላል? እንዴትስ አምላክ የሆነ ህላዌ በሌላ ማንነትና ምንነት ስም ታምር ያደርጋል? ጭራሽኑ የሚያደርጋቸው ሥራዎች ከፈጣሪ በጸጋ ያገኛቸው እንደሆኑ እና ለእርሱ መእክተኛነት ማስረጃ እንደሆኑ አበክሮ እና አዘክሮ ይናገራል፦
ዮሐንስ 17፥4 እኔ ላደርገው *የሰጠኸኝን* ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤
ዮሐንስ 5፥36 አብ ልፈጽመው *የሰጠኝ* ሥራ” ይህ የማደርገው ሥራ፥ አብ እንደ ”ላከኝ” ስለ እኔ ይመሰክራልና።
ዮሐንስ 11፥42 ሁልጊዜም እንድትሰማኝ አወቅሁ፤ ነገር ግን *”አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ ዘንድ”* በዚህ ዙሪያ ስለ ቆሙት ሕዝብ ተናገርሁ አለ።

የየናዝሬቱ ኢየሱስ ያደረጋቸው ተአምራት፣ ድንቆች እና ምልክቶችም እግዚአብሔር በኢየሱስ በኩል ያደረገው ነው፤ በተጨማሪም ከእግዚአብሔር ለእስራኤል ሰዎች የተላከ ሰው መሆኑን በአጽንዖትና በአንክሮት የሚያሳይ ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 2፥22 የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ *የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ “በእርሱ”” በኩል ባደረገው “”ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም” ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእስራኤል ሰዎች የተላከ ሰው ነበረ፤ ይህ ሰው በራሱ ፈቃድ ሳይሆን በላከውን ፈቃድ ሙት ሲያስነሳ የነበረ ሰው ነው፦
ዮሐንስ 5፥30 *እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም”*፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ *”የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና”*።

አምላካችን እና ጌታችን አላህም ዒሣ ምን አስተምሮ እንደነበር በተናገረበት አንቀጽ ላይ ዒሣ ሙት ማስነሳቱ ለመልእክተኛነቱ ማስረጃ እንደሆነ ነግሮናል፦
3፥49 ወደ እስራኤልም ልጆች መልክተኛ ያደርገዋል፡፡ ይላልም፡- «እኔ ከጌታዬ ዘንድ በተዓምር ወደ እናንተ መጣሁ፡፡ እኔ ለናንተ ከጭቃ እንደ ወፍ ቅርፅ እፈጥራለሁ፡፡ በርሱም እተነፍስበታለሁ፡፡ በአላህም ፈቃድ ወፍ ይኾናል፡፡ በአላህም ፈቃድ ዕውር ኾኖ የተወለደን፣ ለምጸኛንም አድናለሁ፡፡ ሙታንንም *”አስነሳለሁ”*፡፡ የምትበሉትንና በቤታችሁ የምታደልቡትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፡፡ የምታምኑ እንደኾናችሁ ለእናንተ በዚህ ውስጥ በእርግጥ ተዓምር አለበት፡፡» وَرَسُولًا إِلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنِّي قَدْ جِئْتُكُم بِآيَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ ۖ أَنِّي أَخْلُقُ لَكُم مِّنَ الطِّينِ كَهَيْئَةِ الطَّيْرِ فَأَنفُخُ فِيهِ فَيَكُونُ طَيْرًا بِإِذْنِ اللَّهِ ۖ وَأُبْرِئُ الْأَكْمَهَ وَالْأَبْرَصَ وَأُحْيِي الْمَوْتَىٰ بِإِذْنِ اللَّهِ ۖ وَأُنَبِّئُكُم بِمَا تَأْكُلُونَ وَمَا تَدَّخِرُونَ فِي بُيُوتِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

ይህም ታምር ከአላህ ለእርሱ ነቢይነት የተሰጠው ስጦታ ነው፦
2፥87 ሙሳንም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ ከበኋላውም መልክተኞችን አስከታተልን፡፡ *የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ታምራቶችን ሰጠነው*፡፡ በቅዱሱ መንፈስም አበረታነው፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ وَقَفَّيْنَا مِن بَعْدِهِ بِالرُّسُلِ ۖ وَآتَيْنَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ الْبَيِّنَاتِ وَأَيَّدْنَاهُ بِرُوحِ الْقُدُسِ
2፥253 እነዚህን መልክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አበለጥን፡፡ ከእነርሱ ውስጥ አላህ ያነጋገረው አልለ፡፡ ከፊሎቻቸውንም በደረጃዎች ከፍ አደረገ፡፡ *የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ታምራቶችን ሰጠነው*፡፡ በቅዱሱ መንፈስም አበረታነው፡፡ تِلْكَ الرُّسُلُ فَضَّلْنَا بَعْضَهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ ۘ مِّنْهُم مَّن كَلَّمَ اللَّهُ ۖ وَرَفَعَ بَعْضَهُمْ دَرَجَاتٍ ۚ وَآتَيْنَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ الْبَيِّنَاتِ وَأَيَّدْنَاهُ بِرُوحِ الْقُدُسِ

"ግልጽ ተአምራት ሰጠነው" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! ስለዚህ ኢየሱስ በአላህ ፈቃድ ሙት ማስነሳቱ ፈጣሪ ሙት አስነሺ በተባለበት መልክ እና ልክ በፍጹም አይደለም። ከዛ ይልቅ ለእርሱ መልእክተኛነት ማስረጃ መሆኑን እንረዳለን እንጂ ጭራሽ ለአምላክነት ሸርጥ ነው ብሎ እንደ ደሊል መረጃ ማቅረብ እጅግ በጣም ሲበዛ ቂልነት ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም