ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ዙፊሊያ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

30:21 *ለእናንተም ከራሳችሁ ጥንዶችን ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፤ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፤ በዚህ ውስጥ ለሚያስውሉ ሕዝቦች ታምራቶች አሉ*። وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

“ዙፊሊያ” ζῷονφιλία ማለት የግሪክ ሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “ዙኡ” ζῷον ማለት “እንስሳ” ማለት ሲሆን “ፊሊያ” φιλία ማለት “ጾታዊ-ፍቅር” ማለት ነው፤ ሰው ከእንስሳ ጋር የሚያደርገው ጾታዊ ተራክቦ “ዙፊሊያ” ወሊ-አዑዝቢሏህ ይባላል፤ አምላካችን አላህ ለሰው ልጆች በጥንድ መጣመር፣ በስሜት መርካት፣ በመካከላቸው ፍቅርና እዝነት ያደረገው ከራሳችን ብቻ እና ብቻ ነው፦
30:21 *ለእናንተም ከራሳችሁ ጥንዶችን ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፤ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፤ በዚህ ውስጥ ለሚያስውሉ ሕዝቦች ታምራቶች አሉ*። وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ
16፥72 አላህም *ከራሳችሁ ለእናንተ ጥንዶችን አደረገ፡፡ ለእናንተም ከጥንዶቻችሁ ልጆችን፣ የልጅ ልጆችንም አደረገላችሁ፡፡ ከመልካሞችም ጸጋዎች ሰጣችሁ*፡፡ ታድያ በውሸት ያምናሉን? በአላህም ጸጋ እነርሱ ይክዳሉን? وَاللَّهُ جَعَلَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا وَجَعَلَ لَكُم مِّنْ أَزْوَاجِكُم بَنِينَ وَحَفَدَةً وَرَزَقَكُم مِّنَ الطَّيِّبَاتِ ۚ أَفَبِالْبَاطِلِ يُؤْمِنُونَ وَبِنِعْمَتِ اللَّهِ هُمْ يَكْفُرُونَ

በተለይ “አንፉሥኩም” أَنفُسِكُمْ የሚለው ቃል ድርብ-ተውላጠ ስም”reflexive pronoun” ሲሆን “እራሳችሁ”yourself” ማለት ነው፤ ከራሳችን ብቻ ልጆችን የልጅ ልጆችን ጥንድ በመሆን አድርጎልናል፤ ከዚያ ውጪ ያሉት ከእንስሳ ጋር ያለው ጾታዊ ተራክቦ ሀራም ነው፤ ይህ ደግሞ በነብያችን”ﷺ” ሐዲስ እንዲህ ተብራርቷል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 20, ሐዲስ 2661
ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ማንም ከቤተሰቡ ጋር ተራክቦ ቢያደርግ ይገደል፤ *ማንም ከእንስሳ ጋር ተራክቦ ቢያደርግ እርሱም እንስሳውም ይገደል*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ وَقَعَ عَلَى ذَاتِ مَحْرَمٍ فَاقْتُلُوهُ وَمَنْ وَقَعَ عَلَى بَهِيمَةٍ فَاقْتُلُوهُ وَاقْتُلُوا الْبَهِيمَةَ ‏”‏
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 114-115
ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ማንም ከእንስሳ ጋር ተራክቦ ቢያደርግ እርሱም ከእርሱ ጋር ያለው(እንስሳው) ይገደል*። እኔም፦ በእንስሳቱ ላይ ምን ዓይነት ጥፋት ሊደርስ ይችላል? ብዬ ጠየኩት፤ እርሱም(ኢብኑ ዐባሥ)፦ ነብዩ *በዚህ ድርጊት ያለችውን እንስሳይቱን ስጋ መብላት አልፈቀዱም”* ብሎ መለሰልኝ። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ أَتَى بَهِيمَةً فَاقْتُلُوهُ وَاقْتُلُوهَا مَعَهُ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ قُلْتُ لَهُ مَا شَأْنُ الْبَهِيمَةِ قَالَ مَا أُرَاهُ إِلاَّ قَالَ ذَلِكَ أَنَّهُ كَرِهَ أَنْ يُؤْكَلَ لَحْمُهَا وَقَدْ عُمِلَ بِهَا ذَلِكَ الْعَمَلُ ‏.
በመቀጠል ኢብኑ ዐባሥም፦ *”ከእንስሳ ጋር ተራክቦ ያደረገን የአቀጣጥ ሁኔታ አልተገለጸም”* አለ። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ لَيْسَ عَلَى الَّذِي يَأْتِي الْبَهِيمَةَ حَدٌّ ‏.‏

“ከእንስሳ ጋር ተራክቦ ያደረገን የአቀጣጥ ሁኔታ አልተገለጸም” ማለት የአገዳደሉ ሁኔታ ለምሳሌ በስቅላት፣ በውግራት፣ በመሰየፍ ይሁን አልተገለጸም፤ ግራም ነፈሰ ቀኝ ማንም ከእንስሳ ጋር ተራክቦ ቢያደርግ እርሱም ከእርሱ ጋር ያለው እንስሳው ይገደላል፤ ይህንን አይደለም እስልምና ጋር ብቻ ከራሳችሁም ባይብል ማመሳከር ትችላላችሁ፦
ዘጸአት 22፥19 *ከእንስሳ ጋር የሚረክስ ፈጽሞ ይገደል*።
ዘሌዋውያን 20፥15 *ማናቸውም ሰው ከእንስሳ ጋር ቢገናኝ ፈጽሞ ይገደል፤ እንስሳይቱንም ግደሉአት*።

አምላካችን አላህ ዕውቅና የሰጠው በሁለት ተቃራኒ ጥንዶች የሚደረግ ተራክቦ”Heterosexuality” ብቻ ነው፤ በኢስላም አይደለም ከእንስሳ ጋር ይቅርና ከሰው ጋር ተመሳሳይ ጾታዊ ተራክቦ”Homosexuality” ሀራም ነው፤ እሩቅ ሳንሄድ ከራሳችን ጥንዶች ጋርም በወር አበባ ጊዜ የሚደረግ ተራክቦ ሆነ በመቀመጫ የሚደረግ ተራክቦ”anal sexuality” ኩፍር ነው፦
ጃሚዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 135
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንዳለው፦ “ነብዩ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ ማንም በሓይድ ላይ ካለች ሴት ወይም በመቀመጫዋ በኩል ተራክቦ ቢያደርግ በሙሐመድ”ﷺ” ላይ በተወረደው ክዷል። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ مَنْ أَتَى حَائِضًا أَوِ امْرَأَةً فِي دُبُرِهَا أَوْ كَاهِنًا فَقَدْ كَفَرَ بِمَا أُنْزِلَ عَلَى مُحَمَّدٍ صلى الله عليه وسلم ‏”‏

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ማኪሪን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥54 *"እነርሱም አደሙ አላህም አድማቸውን መለሰባቸው። አላህም ከአድመኞች ሁሉ በላጭ ነው"*፡፡ وَمَكَرُوا وَمَكَرَ اللَّهُ ۖ وَاللَّهُ خَيْرُ الْمَاكِرِينَ

ዒሣ ወደ የእስራኤልንም ልጆች በተአምራት በመጣባቸው እና ከእነርሱ እነዚያ የካዱት፦ "ይህ ግልጽ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም" ብለው ሊገሉት ሲያስቡ አሏህ ወደ ራሱ ወሰደው፦
5፥110 *"የእስራኤልንም ልጆች በተአምራት በመጣህባቸው እና ከእነርሱ እነዚያ የካዱት ይህ ግልጽ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም ባሉ ጊዜ፣ ሊገድሉህ ሲያስቡህ ከአንተ ላይ በከለከልኩልህም ጊዜ ያደረኩልህን ውለታ አስታውስ"*። وَإِذْ كَفَفْتُ بَنِي إِسْرَائِيلَ عَنكَ إِذْ جِئْتَهُم بِالْبَيِّنَاتِ فَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْهُمْ إِنْ هَـٰذَا إِلَّا سِحْرٌ مُّبِينٌ
3፥55 *አላህም ባለ ጊዜ አስታውስ! ዒሣ ሆይ! እኔ ወሳጂህ ወደ እኔም አንሺህ ነኝ"*፡፡ إِذْ قَالَ اللَّهُ يَا عِيسَىٰ إِنِّي مُتَوَفِّيكَ وَرَافِعُكَ إِلَيَّ
4፥158 *"ይልቁንስ አላህ ዒሣን ወደ እርሱ አነሳው፥ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው"*፡፡ بَل رَّفَعَهُ اللَّهُ إِلَيْهِ ۚ وَكَانَ اللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًا

አሏህ አሸናፊ እና ጥበበኛ ነው፥ ከእስራኤል ልጆች እነዚያ የካዱት ሊገሉት ሲማከሩ፣ ሲያቅዱ፣ ሲያሴሩና ሲያድሙ በአሸናፊነቱ እና በጥበቡ አከሸፈባቸው፥ አሏህ ምክራቸውን፣ ዕቅዳቸውን፣ ሴራቸውን፣ ተንኮላቸውን እና አድማቸው ዒሣን ወደ ራሱ በመውሰድ መለሰባቸው፦
3፥54 *"እነርሱም አደሙ አላህም አድማቸውን መለሰባቸው፡፡ አላህም ከአድመኞች ሁሉ በላጭ ነው"*፡፡ وَمَكَرُوا۟ وَمَكَرَ ٱللَّهُ ۖ وَٱللَّهُ خَيْرُ ٱلْمَٰكِرِينَ

"መከሩ" مَكَرُوا۟ ማለት "አሳሳቱ" ማለት ሳይሆን "መከሩ" "ዐቀዱ" "አሴሩ" "አደሙ" ማለት ነው፥ ዐውዱ ላይ "አሳሳቱ" ብለን ብናስቀምጥ "ማንን አሳሳቱ" ለሚለው ጥያቄ ትርጉም አይሰጥም። ባይሆን "መከሩ" "ዐቀዱ" "አሴሩ" "አደሙ" ከተባለ በማን ላይ "መከሩ" "ዐቀዱ" "አሴሩ" "አደሙ" ? ለሚለው ዒሣን ለመግደል "መከሩ" "ዐቀዱ" "አሴሩ" "አደሙ" የሚል ምላሽ ይኖረዋል። አሏህም ዒሣን ለመግደል የተማከሩትን ምክር፣ ያቀዱትን ዕቅድ፣ ያሴሩትን ሴራ፣ ያደሙትን አድማ ወደ ራሱ በመውሰድ አከሸፈባቸው፥ አሏህም ከአድመኞች ሁሉ በላጭ ነው። "አድመኞች" ለሚለው የገባው ቃል "ማኪሪን" مَٰكِرِين ሲሆን "መካሪዎች" "አቃጂዎች” "ተንኮለኞ" "ሴረኞች" እና "አድመኞች” ማለት ነው፥ እዚህ አንቀጽ ላይ "ማኪሪን" مَٰكِرِين የተባሉት ከእስራኤል ልጆች እነዚያ የካዱት ዒሣን ሊገሉት ሲያሴሩ የነበሩት ናቸው። አሏህ ከእነዚህ ሴረኞች ሁሉ በላጭ ነው፥ ለምሳሌ እነዚያን የመካ ከሃድያን ነቢያችንን"ﷺ" ሊያስሩ ወይም ሊገሉ ወይም ከመካ ሊያወጡ በእሳቸው ላይ በመከሩ ጊዜ አሏህ ምክራቸውን መልሶባቸዋል፦
8፥30 *እነዚያም የካዱት ሊያስሩህ ወይም ሊገድሉህ ወይም ከመካ ሊያወጡህ በአንተ ላይ ”በመከሩብህ” ጊዜ አስታውስ፡፡ ”ይመክራሉም” አላህም ”ተንኮላቸውን ይመልስባቸዋል”፡፡ አላህም ”ከመካሪዎቹ ሁሉ በላይ ነው”*፡፡ وَإِذْ يَمْكُرُ بِكَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لِيُثْبِتُوكَ أَوْ يَقْتُلُوكَ أَوْ يُخْرِجُوكَ ۚ وَيَمْكُرُونَ وَيَمْكُرُ ٱللَّهُ ۖ وَٱللَّهُ خَيْرُ ٱلْمَٰكِرِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "መከሩ" ለሚለው የገባው ቃል "የምኩሩ" يَمْكُرُ መሆኑን እና "ይመክራሉ" ለሚለው የገባው ቃል "የምኩሩነ" يَمْكُرُونَ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። "መክር" مَكْر ማለት "ምክር" "ዕቅድ" "ሴራ" "ደባ" "ተንኮል" ማለት ነው፥ መላእክት ሰዎች በሚስጥር የሚመሳጠሩትን ምክር ሰምተም ይጽፋሉ፦
10፥21 *"አላህ ቅጣተ ፈጣን ነው፥ «መልክተኞቻችን የምትመክሩትን "ምክር" በእርግጥ ይጽፋሉ» በላቸው"*፡፡ قُلِ اللَّهُ أَسْرَعُ مَكْرًا ۚ إِنَّ رُسُلَنَا يَكْتُبُونَ مَا تَمْكُرُونَ
፨ ሲጀመር፦ አሏህ በግስ መደብ ደረጃ "መከረ" مَكَرَ ማለትም "ዐቀደ" ተብሏል እንጂ በስም መደብ "አሏህ "አል-ማኪር" ٱلْمَٰكِر ነው" የሚል ቁርኣን ላይ የለም፥ "ማኪሪን" مَٰكِرِين የሚለው ቃል "ማኪር" مَٰكِر ለሚለው የብዙ ቁጥር ነው። በቁርኣን "ማኪሪን" مَٰكِرِين የተባሉት ዒሣን ሊገሉት ሲያሴሩ የነበሩት ከእስራኤል ልጆች እነዚያ የካዱት እና የመካ ከሃዲያን ናቸው።

፨ ሲቀጥል በዓለማችን ላይ 58 የተለያዩ በእንግሊዝኛ የተዘጋጁ የቁርኣን ትርጉሞች አሉ፥ ሁሉም "ማኪሪን" مَٰكِرِين ለሚለው የተጠቀሙት ቃል "አቃጆች"planners" "ሴረኞች"plotters" "ተንኮለኞች"schemers" እንጂ "አሳሳቾች"deceivers" በፍጹም አይደለም። እሩቅ ስንሄድ ነቢያችን"ﷺ" ወደ አሏህ ዱዓእ ሲያረጉ፦ "ምክሩን ለእኔ ስጠኝ እንጂ በሌላ አታስመክረኝ" ብለዋል፥ የተጠቀሙበት ቃላት የረባው "መከረ" مَكَرَ ከሚል ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 48, ሐዲስ 182
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" በዱዓእ ላይ እንዲህ ይሉ ነበር፦ *"ጌታ ሆይ! እርዳኝ እንጂ አታስረዳኝ! ድልን ስጠኝ እንጂ ለድል አታሰጠኝ! ምክሩን ለእኔ ስጠኝ እንጂ በሌላ አታስመክረኝ"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم يَدْعُو يَقُولُ ‏ "‏ رَبِّ أَعِنِّي وَلاَ تُعِنْ عَلَىَّ وَانْصُرْنِي وَلاَ تَنْصُرْ عَلَىَّ وَامْكُرْ لِي وَلاَ تَمْكُرْ عَلَىَّ


፨ ሢሰልስ ሙዳየ-ቃላት ላይ "ማኪር" مَٰكِر ማለት የተለያየ አማራጭ ትርጉም ስላለው "አሳሳች"deceiver" የሚል ትርጉም ቢኖረው እንኳን የቁርኣኑ ዐውደ-ንባብ ላይ ዒሣን ሊገሉት ሲያሴሩ የነበሩት ከእስራኤል ልጆች እነዚያ የካዱት እና የመካ ከሃዲያን "አሳሳቾች ናቸው" ቢባል እነማንን አሳሳቱ ለሚለው ጥያቄ በየትኛውም ቀመር እና ስሌት መልስ አይሆናችሁም። ዐረቢኛ ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብና ትርጉም እንደሌለው ዕሙር ነው። የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ እሙን ነው፥ መታየት ያለበት ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብ፣ የአንቀጹን ምህዋር፣ አውታርና ምህዳር እንደሆነ ቅቡል ነው፦
27፥50 *"ተንኮልንም መከሩ፥ እነርሱም የማያወቁ ሲኾኑ በተንኮላቸው አጠፋናቸው"*፡፡ وَمَكَرُوا مَكْرًا وَمَكَرْنَا مَكْرًا وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ

፨ ሲያረብብ ስሑታን እና ታካቾች ሳይፈሩና ሳያፍሩ ሳይማሩና ሳይመራመሩ ቁርኣን ላይ ሰጊጎት”eisegesis” አፈሣሰር የሚፈሥሩት ባይብል ላይ ፈቲሆት”exegesis” አረዳድ ስለሌላቸው ነው። ለምሳሌ፦ እግዚአብሔር ሰዎች ሐሰትን ያምኑ ዘንድ የስሕተትን አሠራር የሆነውን ክፉን መንፈስ ይልካል፥ ይህም ክፉም መንፈስ ከእግዚአብሔር ጋር እተመካከረ ለእግዚአብሔር ያሳስትለታል። የሚሳሳተው ሰው እና የሚያሳስተው ክፉ መንፈስ ለእግዚአብሔር ናቸው፦
2ኛ ተሰሎንቄ 2፥12 ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ *ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል*።
መሣፍንት 9፥23 *እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም ሰዎች መካከል ክፉን መንፈስ ሰደደ*፤
1ኛ ነገሥት 22፥20-23 እግዚአብሔርም፦ ወጥቶ በሬማት ዘገለዓድ ይወድቅ ዘንድ *አክዓብን የሚያሳስት ማን ነው?* አለ። አንዱም እንዲህ ያለ ነገር፥ ሌላውም እንዲያ የለ ነገር ተናገረ። *መንፈስም ወጣ በእግዚአብሔርም ፊት ቆሞ፦ እኔ አሳስተዋለሁ አለ*። እግዚአብሔርም፦ በምን? አለው እርሱም፦ *ወጥቼ በነቢያቶቹ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ አለ*። እግዚአብሔርም፦ *ማሳሳትስ ታሳስተዋለህ፥ ይሆንልሃልም ውጣ፥ እንዲሁም አድርግ አለ*። አሁንም፦ እነሆ፥ እግዚአብሔር በእነዚህ *በነቢያትህ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ አድርጎአል፥ እግዚአብሔርም በላይህ ክፉ ተናግሮብሃል*።
ኢዮብ 12፥16 ኃይልና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው፤ *የሚስተውና የሚያስተው ለእርሱ ናቸው*።

እግዚአብሔር፦ “ነቢዩም ቢታለል ያንን ነቢይ ያታለልኩት እኔ እግዚአብሔር ነኝ” ይለናል፥ ሕዝቅኤልን፣ ኤርሚያስን እና ኢሳይያስን ያታለላቸው እርሱ እንደሆነ እራሳቸው ይናገራሉ፦
ሕዝቅኤል 14፥9 *ነቢዩም ቢታለል ቃልንም ቢናገር፥ ያንን ነቢይ ያታለልሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ*፥
ኤርሚያስ 20፥7 አቤቱ፥ *አታለልኸኝ እኔም ተታለልሁ*፥
ኢሳይያስ 63፥17 *አቤቱ፥ ከመንገድህ ለምን “አሳትኸን”?* እንዳንፈራህም ልባችንን ለምን አጸናህብን? ስለ ባሪያዎችህ ስለ ርስትህ ነገዶች ተመለስ።

ስለዚህ ቁርኣንን ለማብጠልጠል ሞራል የሚኖራችሁ ባይብል ላይ ያሉትን እነዚህን አናቅጽ በትክክል ስትረዱ እና ስታስረዱ ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሌሊት እና መዓልት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

10፥67 *"እርሱ ያ ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት ጨለማ፥ ቀንንም ልትሠሩበት ብርሃን ያደረገላችሁ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ሕዝቦች በእርግጥ ታምራቶች አሉ"*፡፡ هُوَ الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ اللَّيْلَ لِتَسْكُنُوا فِيهِ وَالنَّهَارَ مُبْصِرًا ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَسْمَعُونَ

ምድር በደቡብና በሰሜን በሚገኙት ዋልታዎች ከምዕራብ ወደ ምስራቅ በራሷ ዛቢያ በ 360 ድግሪ ስትሽከረከር መዓልት እና ሌሊት ይፈራረቃል፥ ይህ ሂደት በአማካኝ 24 ሰዓት ይፈጃል። ምድር በራሷ ዛቢያ ስለምትሽከረከር መዓልት እና ሌሊት በአንድ ጊዜ እየተደራረቡ ይፈራረቃሉ፦
39፥5 ሰማያትንና ምድርን በእወነት ፈጠረ፡፡ *”ሌሊትን በቀን ላይ ይጠቀልላል፥ ቀንንም በሌሊት ላይ ይጠቀልላል”*። خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِالْحَقِّ ۖ يُكَوِّرُ اللَّيْلَ عَلَى النَّهَارِ وَيُكَوِّرُ النَّهَارَ عَلَى اللَّيْلِ

“ይጠቀልላል” ለሚለው የገባው ቃል “ዩከወሩ” يُكَوِّرُ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። “ከወረ” كَوَّرَ ማለት “ጠቀለለ” “ደረበ” ማለት ነው፥ አንድን ነገር በሌላ ነገር መደረብ”overlap” እራሱ “ከወረ” كَوَّرَ ነው። "መዓልት" በአማካኝ 12 ሰዓት ያቀፈ የብርሃኑ ክፍል ሲሆን "ሌሊት" በአማካኝ 12 ሰዓት ያቀፈ የጨለማው ክፍል ነው፦
10፥67 *"እርሱ ያ ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት ጨለማ፥ ቀንንም ልትሠሩበት ብርሃን ያደረገላችሁ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ሕዝቦች በእርግጥ ታምራቶች አሉ"*፡፡ هُوَ الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ اللَّيْلَ لِتَسْكُنُوا فِيهِ وَالنَّهَارَ مُبْصِرًا ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَسْمَعُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ የሌሊት ተቃራኒ ለሆነው "ቀን" ለሚለው ቃል የገባው "ነሃር" نَّهَار ሲሆን በትክክሉ ዐማርኛ "መዓልት" ይባላል፥ "ሌሊት" ለሚለው ደግሞ "ለይል" لَّيْل ነው። ነገር ግን "የውም" يَوْم የሚለው ቃል መዓልትን፣ ሌሊትን፣ 24 ሰዓት የያዘውን ሌሊት እና መዓልት፣ አንድ ሺህ ዓመትን ወዘተ.. ሊያመላክት ይችላል፦
22፥47 አላህም ቀጠሮውን በፍጹም የማይጥስ ሲሆን በቅጣት ያቻኩሉሃል፡፡ *”እጌታህም ዘንድ አንዱ ቀን ከምትቆጥሩት ቀን እንደ ሺሕ ዓመት ነው”*፡፡ وَيَسْتَعْجِلُونَكَ بِالْعَذَابِ وَلَن يُخْلِفَ اللَّهُ وَعْدَهُ ۚ وَإِنَّ يَوْمًا عِندَ رَبِّكَ كَأَلْفِ سَنَةٍ مِّمَّا تَعُدُّونَ
32፥5 *”ነገሩን ሁሉ ከሰማይ ወደ ምድር ያዘጋጃል፡፡ ከዚያም ከምትቆጥሩት ዘመን ልኩ ሺህ ዓመት በሆነ ቀን ውስጥ ወደ እርሱ ይወጣል”*፡፡ يُدَبِّرُ الْأَمْرَ مِنَ السَّمَاءِ إِلَى الْأَرْضِ ثُمَّ يَعْرُجُ إِلَيْهِ فِي يَوْمٍ كَانَ مِقْدَارُهُ أَلْفَ سَنَةٍ مِّمَّا تَعُدُّونَ

“የውመል ቂያማህ” يَوْمَ الْقِيَامَة “የውሚል ሒሣብ” يَوْمِ الْحِسَاب “የውሚድ-ዲን” يَوْمِ الدِّين “የውመል ፈትሕ” يَوْمَ الْفَتْح “የውመል ጀምዕ” يَوْمِ الْجَمْع ሲባል የብርሃኑን ክፍል መዓልት ወይም 24 ሰዓት የያዘውን ሌሊት እና መዓልት እንዳልሆነ ዕሙር ነው። እዚህ ድረስ ከተግባባ አምላካችን አሏህ በጂብሪል ለዘከሪያ ሲናገር፦ "ምልክትህ ሦስት ቀን በጥቅሻ ቢኾን እንጅ ሰዎችን አለማናገርህ ነው" ብሎት ነበር፦
3፥41 *«ጌታዬ ሆይ! ለእኔ ምልክትን አድርግልኝ» አለ፡፡ «ምልክትህ ሦስት ቀን በጥቅሻ ቢኾን እንጅ ሰዎችን አለማናገርህ ነው፡፡ ጌታህንም በብዙ አውሳ፡፡ በማታና በጧትም አወድሰው» አለው*፡፡ قَالَ رَبِّ اجْعَل لِّي آيَةً ۖ قَالَ آيَتُكَ أَلَّا تُكَلِّمَ النَّاسَ ثَلَاثَةَ أَيَّامٍ إِلَّا رَمْزًا ۗ وَاذْكُر رَّبَّكَ كَثِيرًا وَسَبِّحْ بِالْعَشِيِّ وَالْإِبْكَارِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ቀን" የሚለው "አያም" أَيَّام ሲሆን "የውም" يَوْم ለሚለው ቃል ብዜት ነው፥ "አያም" أَيَّام በጥቅሉ የመጣ “ሙጅመል” مُجّمَل ሲሆን በሌላ አንቀጽ "ለያል"لَيَال በሚል መጥቷል፦
19፥10 *«ጌታዬ ሆይ! ለእኔ ምልክትን አድርግልኝ አለ፡፡ ምልክትህ ጤናማ ሆነህ ሳለህ ሦስት ሌሊት ሰዎችን ለማነጋገር አለመቻልህ ነው» አለው*፡፡ قَالَ رَبِّ اجْعَل لِّي آيَةً ۚ قَالَ آيَتُكَ أَلَّا تُكَلِّمَ النَّاسَ ثَلَاثَ لَيَالٍ سَوِيًّا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሌሊት" የሚለው "ለያል"لَيَال ሲሆን "ለይል" لَّيْل ለሚለው ቃል ብዜት ነው፥ "ለያል"لَيَال በተናጥል “ሙፈሰል” مُفَصَّل ሆኖ የመጣ ነው። ስለዚህ አሏህ ለእኛ ከዘከሪያህ ጋር ምን እንዳለው አንድ አንቀጽ ላይ "አያም" أَيَّام ብሎ በጥቅሉ ሲነግረን ሌላ አንቀጽ ላይ ደግሞ "ለያል"لَيَال ብሎ በተናጥል ነግሮናል። "ቀን" ጊዜ ስለሆነ ጊዜ ደግሞ ሌሊት እና መዓልት ያቀፈ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 78, ሐዲስ 205
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ" እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አሏህም አለ፦ "የአደም ልጆች ጊዜን ይራገማሉ፥ እኔ የጊዜ ባለቤት ነኝ። ሌሊት እና መዓልት በእጆቼ ናቸው"*። قَالَ قَالَ أَبُو هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ قَالَ اللَّهُ يَسُبُّ بَنُو آدَمَ الدَّهْرَ، وَأَنَا الدَّهْرُ، بِيَدِي اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ ‏"‌‏.‏

በሌሊት እና በመዓት ውስጥ ያለውን የአሏህን ተአምራት ከሚያስተነትኑ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የማታውቁትን አትናገሩ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥169 *"እርሱ ሰይጣን የሚያዛችሁ በኃጢኣትና በጸያፍ ነገር በአላህም ላይ የማታውቁትን እንድትናገሩ ብቻ ነው"*፡፡ إِنَّمَا يَأْمُرُكُم بِالسُّوءِ وَالْفَحْشَاءِ وَأَن تَقُولُوا عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ

"ሀምዛህ" هَمْزَة የሚለው ቃል "ሀምዘ" هَمَزَ‎ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ይህ ء ሐርፍ ነው፥ ሀምዛህ እራሱ "ሀምዘቱል ቀጥዕ" هَمْزَة الْقَطْع እና "ሀምዘቱል ወስል" هَمْزَة الوَصْل ተብሎ ለሁለት ይከፈላል፦
"ሀምዘቱል ቀጥዕ"
"ቀጥዕ" قَطْع የሚለው ቃል "ቀጦዐ" قَطَعَ ማለትም "ቆረጠ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የተቆረጠ" ማለት ነው፥ ምልክቱ "አ" أَ "ኢ" إِ "ኡ" أُ ነው።
"ሀምዘቱል ወስል"
"ወስል" وَصْل የሚለው ቃል "ወሶለ" وَصَلَ ማለትም "ቀጠለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የተቀጠለ" ማለት ነው፥ ምልክቱ ይህ "አ" ٱ ነው። ለምሳሌ፦ "አሏህ" ٱللَّه የሚለው ስም መነሻ ቃል ላይ አለ፥ አሏህ "ኢሥሙል ጀላላህ" اِسْم الْجَلَالَة ስለሆነ ከፊለፊቱ "ሊ" لِ ማለትም "ለ" የምትል መስተዋድድ ስትመጣ ሀምዘቱል ወስል ትጨፈለቅ እና "ሊ-ሏህ" لِلَّهِ ይሆናል፥ ለምሳሌ አንድ ናሙና እንይ፦
1፥2 *"ምስጋና "ለአሏህ" ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው"*። الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ

"ሊ" لِ በሥነ-ሰዋስው "ሐርፉል ጀር" حَرْفُ الْجَرِّ ማለትም "መስተዋድድ"preposition" ናት። ይህ ሆኖ ሳለ ኢሥላም ዱር ሙሥሊሙ ሐሩር እንዲሆን ቀን ከሌሊት ደፋ ቀና፥ ጠብ እርግፍ የሚሉት አግድም አደግ ዕውቀት ያላቸው ሚሽነሪዎች በመስተዋድድ የተነሳ ሀምዘቱል ወስል የተዋጠውን "ሏህ" للَّه ወስደው ከግብጻውያን "ላህ" ⲟⲟϩ ጋር ወስደው ሊያምታቱ ይሞክራሉ። በግብጻውያን ኮፕቲክ ቋንቋ ትክክለኛ አነባነቡ "አህ" ⲟⲟϩ ሲሆን "ጨረቃ" ማለት ነው፥ "ላህ" ወይም "ያህ" ተብሎም ሊነበብ ይችላል። ስለዚህ፦ "ምስጋና ለአሏህ ይገባው" ማለት "ምስጋና "ለ-ጨረቃ" ይገባው" ማለት ነው" ይላሉ፥ ይህ ብዙ ካለማወቅ የሚመጣ የተሳከረ አመለካከት ነው።

፨ ሲጀመር አሏህ ጨረቃን የፈጠረ እንጂ ጨረቃ አይደለም፥ አምላካችን አሏህ እራሱ፦ "ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ" ብሎ ተናግሯል፦
41፥37 *”ሌሊት እና ቀንም፣ ጸሐይ እና ጨረቃም ከታምራቶቹ ናቸው፥ ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፤ ለዚያም ለፈጠራቸው ለአላህ ሰገዱ፤ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደሆናችሁ ለሌላ አትስገዱ”*። وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ

ኩሻዊ ቃል "ላህ" እና ሴማዊ ቃል "አሏህ" የሚለውን ይዞ ማምታታት እጥረተ-ዕውቀት ነው፥ አንድ ቃል ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብና ትርጉም እንደሌለው ዕሙር ነው። "አሏህ" ٱللَّه በሚለው ስም ውስጥ ላም ሸዳህ لَّ አለው፥ "ሸዳህ" شَدّة‎ የሚለው ቃል "ሸደ" شَدَّ ማለትም "አጠበቀ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ማጥበቂያ"emphasis" ማለት ነው። የኮፕቲኩ "ላህ" ላይ ግን ላም ሸዳህ አይደለችም።

፨ ሲቀጥል ዐረብ ክርስቲያኖች ባይብልን በዐረቢኛ ሲያዘጋጁ "ለ-አሏህ" ለማለት በተመሳሳይ ልክ እንደ ቁርኣኑ "ሊ-ሏህ" لِلَّهِ እያሉ አስቀምጠዋል፦
ዘፍጥረት 8፥20 *"ኑሕ "ለ-አሏህ" መሠውያውን ሠራ"*። ثُمَّ بَنَى نُوحٌ مَذْبَحًا للهِ.
12፥7 *"ኢብራም ለተገለጠለት "ለ-አሏህ" በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ"*። فَبَنَى أبْرَامُ هُنَاكَ مَذْبَحًا للهِ الَّذِي ظَهَرَ لَهُ

እንደ እናንተ ሙግት፦ "ኑሕ ለአሏህ መሠውያውን ሠራ" ሲል "ኑሕ ለ-ጨረቃ መሠውያውን ሠራ" እያለ ነውን? "ኢብራም ለተገለጠለት ለአሏህ በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ" ሲል "ኢብራም ለተገለጠለት ለ-ጨረቃ በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ" እያለ ነውን? ይህ ውኃ የማያነሳ ሙግት ነው! እንቀጥል፦
ዘፍጥረት 35፥1 *"ለተገለጠልህ "ለ-አሏህ" መሠውያውን አድርግ"*። وَابْنِ مَذْبَحًا هُنَاكَ للهِ الَّذِي ظَهَرَ لَكَ
ዘጸአት 35፥5 *"ከእናንተ ዘንድ "ለ-አሏህ" ቍርባንን አቅርቡ!"* قَدِّمُوا مِمَّا تَمْلُكُونَ تَقْدِمَةً للهِ

ፈጣሪ ያዕቆብን፦ "ለተገለጠልህ ለ-አሏህ መሠውያውን አድርግ" ሲለው "ለተገለጠልህ ለ-ጨረቃ መሠውያውን አድርግ" እያለው ነውን? ፈጣሪ ሙሴን፦ "ለ-አሏህ ቍርባንን አቅርቡ" ሲለው "ለ-ጨረቃ ቍርባንን አቅርቡ" እያለው ነውን? ይህ ውኃ የማይቋጥር ሙግት ነው! እንቀጥል፦
አብድዩ 1፥21 *"ንግሥናምም "ለ-አሏህ" ይሆናል" وَسَيَكُونُ المُلْكُ للهِ

አብድዩ፦ "ንግሥናምም ለ-አሏህ ይሆናል" ሲል "ንግሥናምም ለ-ጨረቃ ይሆናል" እያለው ነውን? አንባቢያንን ላለማሰልቸት እንጂ ብዙ የሙግት ናሙናዎችን ማቅረብ ይቻል ነበር።

፨ ሢሰልስ "አህ" ⲟⲟϩ ሲነበብ "ያህ" ተብሎም መነበብ ከቻለ በዕብራይስጥ "ያህ" בְּיָ֥הּ የእስራኤል አምላክ ነው፦
መዝሙር 68፥4 *”ወደ ሰማያት ለወጣም መንገድ አድርጉ፤ ስሙ “ያህ” ነው”*። שִׁ֤ירוּ לֵֽאלֹהִים֮ זַמְּר֪וּ שְׁ֫מֹ֥ו סֹ֡לּוּ לָרֹכֵ֣ב בָּ֭עֲרָבֹות בְּיָ֥הּ שְׁמֹ֗ו וְעִלְז֥וּ לְפָנָֽיו׃

እንግዲያውስ በዚህ አንቀጽ ላይ "ያህ" בְּיָ֥הּ የተባለው የግብጻውያኑ "ጨረቃ" ነውን? በሰፈሩበት ቁና መሰፈር ይሉካል እንደዚህ ነው። አየህ ሐሰት በእውነት ፊት እሳት የነካው ሰም፣ ጸሐይ ያየው ቅቤ፣ ነፋስ የጎበኘው አቧራ ይሆናል፥ ሚሽነሪዎች ሆይ! ሸይጧን የሚያዛችሁ በኃጢኣትና በጸያፍ ነገር በአላህም ላይ የማታውቁትን እንድትናገሩ ብቻ ነውና በንስሓ ወደ አሏህ ኑ፦
2፥169 *"እርሱ ሰይጣን የሚያዛችሁ በኃጢኣትና በጸያፍ ነገር በአላህም ላይ የማታውቁትን እንድትናገሩ ብቻ ነው"*፡፡ إِنَّمَا يَأْمُرُكُم بِالسُّوءِ وَالْفَحْشَاءِ وَأَن تَقُولُوا عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ታላቁ ጦርነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

53፥4 *እርሱ ንግግሩ የሚወረድ ወሕይ እንጅ ሌላ አይደለም*፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْيٌ يُوحَىٰ

አምላካችን አሏህ ነቢያችንን"ﷺ" ነቢይ አድርጎ ልኳል፥ ነቢያችን"ﷺ" የሩቅ ነገርን ሁሉ ከልብ ወለድ አይናገሩም። ስለ ሩቅ ነገር የሚናገሩት ንግግር የሚወርድ ወሕይ እንጂ ሌላ አይደለም፦
53፥3 *ከልብ ወለድም አይናገርም*፡፡ وَمَا يَنطِقُ عَنِ الْهَوَىٰ
53፥4 *እርሱ ንግግሩ የሚወረድ ወሕይ እንጅ ሌላ አይደለም*፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْيٌ يُوحَىٰ

በግሪክ ኮይኔ "አፓካሊፕስ" ἀποκάλυψις ማለት "የተደበቀን ነገር መግለጥ" ማለት ሲሆን አምላካችን አሏህ ለነቢያችንን"ﷺ" ካወረደው ጉዳይ አንዱ “አል-ገይቡል ሙሥተቅበል” ٱلْغَيْب ٱلْمُسْتَقْبَل ነው፥ ከነገሩን አል-ገይቡል ሙሥተቅበል መካከል ስለ መጨረሻው ቀን ምልክቶች ነው። ከንዑሳን የመጨረሻ ቀን ምልክቶች አንዱ "አል-መልሐመቱል ኩብራ" ነው፥ "አል-መልሐመቱል ኩብራ" الْمَلْحَمَة الكُبْرَى ማለት "ታላቁ ጦርነት" ወይም "አርማጌዶን" ማለት ነው። ሰዓቲቱ ሲቃረብ ዒልም በዓሊም ሞት ምክንያት ይወሰዳል፥ በጃሂል ጀህል ይስፋፋል። ብዙ አል-ሀርጅ ይሆናል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 41, ሐዲስ 8
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምሪው ኢብኑል ዓሲ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በእርግጥ አሏህ ከሰዎች ዒልምን አይነጥቅም ግን ዓሊም ሳይኖር ሰዎች ጁሃልን እስኪጠይቁ እና ጁሃልም ያለ ዒልም እስኪስቱና እስኪያያሳስቱ ድረስ ዑለማእን በመውሰድ ዒልምን ቢነጥቅ እንጂ"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرِو بْنِ الْعَاصِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ اللَّهَ لاَ يَقْبِضُ الْعِلْمَ انْتِزَاعًا يَنْتَزِعُهُ مِنَ النَّاسِ وَلَكِنْ يَقْبِضُ الْعِلْمَ بِقَبْضِ الْعُلَمَاءِ حَتَّى إِذَا لَمْ يَتْرُكْ عَالِمًا اتَّخَذَ النَّاسُ رُءُوسًا جُهَّالاً فَسُئِلُوا فَأَفْتَوْا بِغَيْرِ عِلْمٍ فَضَلُّوا وَأَضَلُّوا ‏"‏ ‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 92, ሐዲስ 14
አቢ ሙሣ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ሰዓቲቱ ሲቃረብ ጀህል ይስፋፋል፥ ዒልም ይወሰዳል። ብዙ አል-ሀርጅ ይሆናል፥ አል-ሀርጅ ማለት ግድያ ነው"*። عَنْ أَبِي مُوسَى قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ بَيْنَ يَدَىِ السَّاعَةِ لأَيَّامًا يَنْزِلُ فِيهَا الْجَهْلُ، وَيُرْفَعُ فِيهَا الْعِلْمُ، وَيَكْثُرُ فِيهَا الْهَرْجُ، وَالْهَرْجُ الْقَتْلُ ‏"‌‏.‏

"ዒልም" عِلْم ማለት "ዕውቀት" ማለት ሲሆን "ዓሊም" عَالِم ማለት ደግሞ "ዐዋቂ" ማለት ነው፥ የዐሊም ብዙ ቁጥር "ዑለማእ" عُلَمَاء ወይም "ዓሊሙን" عَالِمُون ነው። "ጀህል" جَهْل ማለት "መሃይምነት" ማለት ሲሆን "ጃሂል" جَاهِل ማለት ደግሞ "መሃይም" ማለት ነው፥ የጃሂል ብዙ ቁጥር "ጁሃል" جُهَّال ወይም "ጃሂሉን" جَاهِلُون ነው። ዛሬ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ መጠነ ሰፊ የዑለማዎች ሞት የምናየው ይህንን ትንቢት አመላካች ይሆን? መሃይማኖች ሲስቱ እና ሲያስቱ የእርስ በእርስ እልቂት ይመጣል፥ "አል-ሀርጅ" الْهَرْج ማለት "የእርስ በእርስ እልቂት ወይም መገዳደል" ማለት ነው። ከዚያ ዓለም ዐቀፍ ይዘት ያለው ታላቁ ጦርነት ይመጣል፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 39, ሐዲስ 4
ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በይቱል መቅዲሥ ሲለመልም የስሪብ ፍርስራሽ ትሆናለች፣ የስሪብ ፍርስራሽ በሆነች ጊዜ ታላቁ ጦርነት ይመጣል፣ ታላቁ ጦርነት ሲመጣ ቁሥጦንጢኒያህ ድል ታረጋለች፣ ቁሥጦንጢኒያህ ድል ባደረገች ጊዜ አል-ደጃል ይመጣል"*። عَنْ مُعَاذِ بْنِ جَبَلٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ عُمْرَانُ بَيْتِ الْمَقْدِسِ خَرَابُ يَثْرِبَ وَخَرَابُ يَثْرِبَ خُرُوجُ الْمَلْحَمَةِ وَخُرُوجُ الْمَلْحَمَةِ فَتْحُ قُسْطَنْطِينِيَّةَ وَفَتْحُ الْقُسْطَنْطِينِيَّةِ خُرُوجُ الدَّجَّالِ ‏"‏

"የስሪብ" يَثْرِب የመዲና ጥንታዊ ስም ነው፥ የስሪብ ፍርስራሽ በሆነች ጊዜ ታላቁ ጦርነት ይመጣል። "ቁሥጦንጢኒያህ" قُسْطَنْطِينِيَّة ማለት "ቆስጠንጢኒያ"Constantinople" ማለት ነው፥ ቆስጠንጢኒያ ከ 306 – 337 ድኅረ-ልደት ሲገዛ በነበረው በሮሙ ቄሳር በቆስጠንጢኖስ ስም የተሰየመችው የአሁኗ ቱርክ ናት። በታላቁ ጦርነት የሙሥሊሙ መሰብሰቢያ ቦታ ከሻም ከተሞች አንዷ በሆነችው ዲመሽቅ ተብላ በምትጠራ ከተማ አቅራቢያ በጉጧህ ነው፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 39, ሐዲስ 4298
አቢ አድ-ደርዳእ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በታላቁ ጦርነት የሙሥሊሙ መሰብሰቢያ ቦታ ከሻም ከተሞች አንዷ በሆነችው ዲመሽቅ ተብላ በምትጠራ ከተማ አቅራቢያ በጉጧህ ነው"*። عَنْ أَبِي الدَّرْدَاءِ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ إِنَّ فُسْطَاطَ الْمُسْلِمِينَ يَوْمَ الْمَلْحَمَةِ بِالْغُوطَةِ إِلَى جَانِبِ مَدِينَةٍ يُقَالُ لَهَا دِمَشْقُ مِنْ خَيْرِ مَدَائِنِ الشَّامِ ‏"‏

"ዲመሽቅ" دِمَشْق ማለት "ደማስቆ" ማለት ነው፥ "ጉጧህ" غُوطَة የሻም ደቡብ ምዕራብ ክፍል ነው። አሏህ ነቢያችን"ﷺ" የተናገሩትን የሩቅ ነገር የምናስተውል እና የምናስተነትን ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የቁርኣን ሸፋዓህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

6፥149 *«የተሟላው አስረጅ የአላህ ነው፥ በሻም ኖሮ ሁላችሁንም ባቀናችሁ ነበር» በላቸው"*፡፡ قُلْ فَلِلَّهِ الْحُجَّةُ الْبَالِغَةُ ۖ فَلَوْ شَاءَ لَهَدَاكُمْ أَجْمَعِينَ

በሥነ-ኑባሬ ጥናት"ontology" ባሕርይ የኑባሬ መገለጫ እንጂ እራሱ ኑባሬ አይደለም፥ ለምሳሌ የወሒድ ንግግር "ወሒድ" ሳይሆን ከወሒድ የሚወጣ የወሒድ ባሕርይ ነው፥ ወሒድ ተናጋሪ እንጂ ንግግር አይደለም። የወሒድ ንግግር ከወሒድ ውጪ ሌላ ማንነት ወይም ምንነት አይደለም፥ ምክንያቱም ሲፋህ የዛት መገለጫ ባሕርይ ነውና። “ዛት” ذَات ማለት "ኑባሬ"being" ወይም “ህላዌ”essence” ማለት ሲሆን “ምንድን” ተብሎ የሚጠየቅ “ምንነት” ነው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 33
አቢ ሁረይራህ"ረ. ዐ.” እንደተናገረው፦ *"ኢብራሂም አላበለም በሦስት ጉዳይ ላይ ቢሆን እንጂ፥ ከእነርሱ ሁለቱ ለአሏህ ዐዘ ወጀል “ዛት” ብሎ ነው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ لَمْ يَكْذِبْ إِبْرَاهِيمُ ـ عَلَيْهِ السَّلاَمُ ـ إِلاَّ ثَلاَثَ كَذَبَاتٍ ثِنْتَيْنِ مِنْهُنَّ فِي ذَاتِ اللَّهِ عَزَّ وَجَلَّ

እዚህ ሐዲስ ላይ "ዛት" ذَات ተብሎ መቀመጡ በራሱ አሏህ ዛት እንዳለው የሚያሳይ ነው። “ሲፋህ” صِفَة የሚለው ቃል “ወሰፈ” وَصَفَ‎ ማለትም “ገጠለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መገለጫ”description" ወይም “ባሕርይ”attribute" ማለት ነው፥ የሲፋህ ብዙ ቁጥር ደግሞ “ሲፋት” صِفَات‎ ነው፦
21፥22 *የዐርሹ ጌታ አላህም “ከሚሉት” ሁሉ ጠራ*። فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ

“ከሚሉት” ለሚለው ቃል የገባው “የሲፉነ” يَصِفُونَ ሲሆን “ባሕርይ ካደረጉለት”they attribute” ማለት ነው፥ ፍጡራን ከወሰፉት ሲፋህ ሁሉ የጠራ ነው። እዚህ ድረስ ስለ ዛት እና ስለ ሲፋህ ይህን ያህል ከተግባባን ዘንዳ ስለ ቁርኣን ደግሞ እናያለን፥ ቁርኣን የአሏህ ንግግር ነው፦
9፥6 *”ከሙሽሪኮችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅህ የአሏህን ንግግር እስኪሰማ ድረስ አስጠጋው”*፡፡ أَحَدٌ مِّنَ الْمُشْرِكِينَ اسْتَجَارَكَ فَأَجِرْهُ حَتَّىٰ يَسْمَعَ كَلَامَ اللَّهِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ከላመል ሏህ" كَلَامَ اللَّهِ የሚል ቃል መኖሩ በራሱ ቁርኣን የአሏህ ንግግር መሆኑን ያስጨብጣል፥ “ከላም” كَلَٰم ማለትም “ንግግር”speech” ማለት ሲሆን አሏህ ደግሞ “ሙተከለም” مُتَكَلِّم ማለትም “ተናጋሪ”speaker” ነው፥ አሏህ ዐዋቂ እንጂ ዕውቀት እንዳልሆነ ሁሉ አሏህ ተናጋሪ እንጂ ንግግር አይደለም። ዕውቀት ከዐዋቂው የማንለየው ባሕርይው እንደሆነ ሁሉ ንግግርም ከተናጋሪው የማንለየው ባሕርይ ነው፥ ዕውቀው የዐዋቂው ባሕርይ እንጂ ዐዋቂው እንዳልሆነ ሁሉ ንግግርም የተናጋሪው ባሕርይ እንጂ ታናጋሪው አይደለም። የአሏህ ዕውቀት እና ንግግር "ፍጡር ነው ወይስ ፈጣሪ? በሚል ሁለት ስሑት ቀጠና"false dichotomy” ለመጠየቅ መሞከር የሥነ-ኑባሬ ጥናት ያለመረዳት ችግር ነው፥ የአሏህ ዕውቀት እና ንግግር ፍጡርም ፈጣሪም ሳይሆን የራሱ የአሏህ ባሕርይ የሚባል ሦስተኛ ቀጠና"trichotomy” መኖሩን ከዐለማወቅ የሚመጣ ጠባብነት ነው፥ የአሏህ ባሕርይ ከአሏህ ሌላ የሆነ ማንነትም ምንነትም በፍጹም አይደለም።

ሚሽነሪዎች፦ "ቁርኣን ከአሏህ ሌላ እራሱን የቻለ ማንነት ነው፥ ምክንያቱም ወደ አሏህ የሚያማልድ አማላጅ ስለተባለ" ብለው የሥላሴን እሳቤ ለማስደገፍ ስሑት ሙግት ያቀርባሉ። እኛ ደግሞ፦ "ቁርኣን የአሏህ ባሕርይ እንጂ እራሱን የቻለ ማንነት አይደለም" ብለን ስሙር ሙግት እናቀርባለን፥ እስቲ "ቁርኣን ከአሏህ ሌላ እራሱን የቻለ ማንነት ነው" ለማለት ያስደፈራቸውን ሐዲስ እንመልከት፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 6, ሐዲስ 302
አቡ ኡማህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ *"ቁርኣንን ቅሩ! የትንሳኤ ቀን ለሚቀሩት ወዳጆቹ ሸፊዕ ሆኖ ይመጣል"*። يَقُولُ حَدَّثَنِي أَبُو أُمَامَةَ، الْبَاهِلِيُّ قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ "‏ اقْرَءُوا الْقُرْآنَ فَإِنَّهُ يَأْتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ شَفِيعًا لأَصْحَابِهِ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 33, ሐዲስ 130
አቢ ሁረይራህ"ረ. ዐ.” እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"እስከሚያስምር ድረስ ለሚቀራው ወዳጁ የሚያማልድ ሠላሳ አናቅጽ የያዘ ሡራህ በቁርኣን ውስጥ አለ፥ እርሱም፦ "ያ ንግሥና በእጁ የኾነው አምላክ የተባረከ(ተመሰገነ) ይሁን" የሚለው ሡራህ ነው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏"‏ إِنَّ سُورَةً فِي الْقُرْآنِ ثَلاَثُونَ آيَةً شَفَعَتْ لِصَاحِبِهَا حَتَّى غُفِرَ لَهُ ‏{تَبَارَكَ الَّذِي بِيَدِهِ الْمُلْكُ}‏ ‏"‏
ሠላሳ አናቅጽ የያዘ ሡራህ ሡረቱል ሙልክ ነው። "ሸፋዓህ" شَفَاعَة የሚለው ቃል "ሸፈዐ" شَفَعَ ማለትም "አማለደ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ምልጃ" ማለት ሲሆን "ሸፊዕ" شَفِيع ማለት ደግሞ “አማላጅ” ማለት ነው። ቁርኣን ለሚቀሩት ወዳጆቹ ያማልዳል ማለት የሚቀሩት ወዳጆቹ በመቅራታቸው የትንሳኤ ቀን ወሮታና አጼፌታ ትሩፋትና ስርጉት ያገኙበታል፤ ቁርኣን ስለተቀራ ወሮታና አጼፌታ ትሩፋትና ስርጉት ያስገኛል ማለት እንጂ ልክ ማንነት እንዳለው ቅዋሜ ማንነት ያማልዳል ማለት አይደለም። ይህ "ኢስጢላሕ" اِصْطِلَاح ማለትም "ፈሊጣዊ አገላለጽ"idiomatic expression" ነው፥ ለምሳሌ ፆም በትንሳኤ ቀን ለሚፆሙ እንደሚያማልድ ይናገራል፦
ሚሽካቱል መሷቢሕ መጽሐፍ 7, ሐዲስ 7
ሙሥነድ አሕመድ 6589
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ፆም እና ቁርኣን በትንሳኤ ቀን ለአሏህ ባሪያ ያማልዳሉ። ፆምም፦ "ጌታ ሆይ! በመዓልት ምግብ እና ፍላጎትን ለከለከልኩት ላማልደው" ይላል፥ ቁርኣንም፦ "ጌታ ሆይ! በሌሊት እንቅልፍ ለከለከልኩት ላማልደው" ይላል፥ እናም ያማልዳሉ"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ الصِّيَامُ وَالْقُرْآنُ يَشْفَعَانِ لِلْعَبْدِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ يَقُولُ الصِّيَامُ أَيْ رَبِّ مَنَعْتُهُ الطَّعَامَ وَالشَّهَوَاتِ بِالنَّهَارِ فَشَفِّعْنِي فِيهِ وَيَقُولُ الْقُرْآنُ مَنَعْتُهُ النَّوْمَ بِاللَّيْلِ فَشَفِّعْنِي فِيهِ قَالَ فَيُشَفَّعَانِ

"ፆም" ልክ እንደ ሰው እና መላእክት እራሱን የቻለ ማንነት ሆኖ ሳይሆን ለሚፆሙት ጿሚዎች በትንሳኤ ቀን አጅር ያስገኛል ማለት እንደሆነ ሁሉ ቁርኣንም ለሚቀሩት ቃሪዎች በትንሳኤ ቀን አጅር ያስገኛል ማለት ነው፥ ቁርኣን ያማልዳል የተባለው ፆም ያማልዳል በተባለበት ስሌትና ቀመር ነው። ፆም ሆነ ቁርኣን እራሳቸውን የቻሉ ማንነት ሳይሆኑ ማውራታቸው "ኢስጢላሕ" اِصْطِلَاح ነው፥ በባይብልም ቢሆን እራሳቸውን የቻሉ ማንነት ሳይኖራቸው የተናገሩ ቀላይ እና ባሕር ናቸው፦
ኢዮብ 28፥14 *"ቀላይ፦ "በእኔ ውስጥ የለችም" ይላል፤ ባሕርም፦ "በእኔ ዘንድ የለችም" ይላል"*። תְּהֹ֣ום אָ֭מַר לֹ֣א בִי־הִ֑יא וְיָ֥ם אָ֝מַ֗ר אֵ֣ין עִמָּדִֽי׃

ቀላይ እና ባሕር እራሳቸው የቻሉ ቅዋሜ-ማንነት ወይም እኔነት ሳይኖራቸው እንዴት "እኔ" ይላሉ? መናገር ሳይችሉ እንዴ "ይላል" ተባሉ? ብለን ስንጠይቅ እነርሱም፦ "ምነካህ ወሒድ? ይህ እኮ "ፈሊጣዊ አገላለጽ"idiomatic expression" ነው" የሚል ምላሽ ይሰጣሉ፥ እንግዲያውስ ፆም እና ቁርኣን የተናገሩትም "ኢስጢላሕ" اِصْطِلَاح ስለሆነ ከላይ በባይብሉ ናሙና መልክ እና ልክ ተረዱት! በሰፈሩት ቁና መሰፈር እንደዚህ ነው። ቁርኣን ላይ እርርና ምርር ብላችሁ ከመንጨርጨራችሁና ከመንተክተካችሁ በፊት "ፍጡርነትን ከፈጣሪነቱ ጋር አንድ አድርጎ እና ፍጡርነቱን አምላክ አድርጎ እንዲመለክ አድርጓል፣ ፈጣሪ ፍጡር ሆነ፣ ሰው አምላክ ሆነ" ከሚል ሺርክ ቅድሚያ እራሳችሁን አድኑ! "ሑጃህ" حُجَّة ማለት "አስረጅ" ማለት ነው፥ ቁርኣን አስረጅ ነው። ቁርኣን አምነክበት ስትቀራው አስረጅ ይሆልካል ወይ ክደከው ስታስተባብለው አስረጅ ይሆንብካል፦
6፥149 *«የተሟላው አስረጅ የአላህ ነው፥ በሻም ኖሮ ሁላችሁንም ባቀናችሁ ነበር» በላቸው"*፡፡ قُلْ فَلِلَّهِ الْحُجَّةُ الْبَالِغَةُ ۖ فَلَوْ شَاءَ لَهَدَاكُمْ أَجْمَعِينَ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 2, ሐዲስ 1
አቡ ማሊክ አል-አሽዐሪይ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ቁርኣን አስረጅ ይሆልካል ወይ አስረጅ ይሆንብካል"*። عَنْ أَبِي مَالِكٍ الأَشْعَرِيِّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم " الْقُرْآنُ حُجَّةٌ لَكَ أَوْ عَلَيْكَ "

አሏህ ቁርኣንን ቀርተው አስረጅ ከሚሆንላቸው እና አጅሩን ከሚያገኙ ባሮቹ ያርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ረሒም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

12፥64 *"እርሱም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነው"* وَهُوَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ

አምላካችን አሏህ እጅግ በጣም አዛኝ ነው፥ እርሱም፦ "እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ" ብሎናል፦
2፥160 *"እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ"*፡፡ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ
2፥163 *"አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፥ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ እርሱ እጅግ በጣም ሩኅሩህ አዛኝ ነው"*፡፡ وَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الرَّحْمَـٰنُ الرَّحِيمُ

ሁለቱም አናቅጽ ላይ "አዛኝ" ለሚለው የገባው ቃል "አር-ረሒም" الرَّحِيم ነው። ዐቃቤ ክርስትና አንቶንይ ሮጀርስ፦ "አንደኛው አሏህ ሌላውን አሏህ ስለሚያናግረው በአንድ መለኮት ውስጥ ብዙ ማንነት እንዳሉ ማሳያ ነው" በማለት አንሸዋሮና አንከዋሮ፣ ቀንሶና ደምሮ፣ አብዝቶና አባዝቶ ይዋሻል፥ ወትሮም አባይ መቅጠፍ ልምዱ ነው። ለዚህ ቅጥፈቱ ማጣቀሻ አለኝ ያለበትን ሐዲስ እስቲ እንመልከት፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 78, ሐዲስ 18
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አሏህ ፍጥረትን ሲፈጥርና ፍጥረቱን ፈጥሮ በጨረሰ ጊዜ፦ "ረሒምም፦ "ይህ ቦታ እኔ ከቆራጮች በአንተ እጠበቃለው" አለች፥ አሏህም፦ "አዎ! ከአንቺ ጋር የቀጠለን እንድቀጥል የቆረጠን እንድቆርጥ አትፈልጊምን? አለ። እርሷም፦ "እፈልጋለው! ጌታ ሆይ! አለች፥ አሏህም፦ "ይህ ላንቺ ይሁን" አለ"። የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ"፦ "ከፈቀዳችሁ፦ "ብትሽሾሙም በምድር ላይ ማበላሸትን ዝምድናችሁንም መቁረጥን ከጀላችሁን?" የሚለውን አንቀጽ አንብቡ!" አሉ"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ إِنَّ اللَّهَ خَلَقَ الْخَلْقَ حَتَّى إِذَا فَرَغَ مِنْ خَلْقِهِ، قَالَتِ الرَّحِمُ هَذَا مَقَامُ الْعَائِذِ بِكَ مِنَ الْقَطِيعَةِ‏.‏ قَالَ نَعَمْ أَمَا تَرْضَيْنَ أَنْ أَصِلَ مَنْ وَصَلَكِ‏.‏ وَأَقْطَعَ مَنْ قَطَعَكِ‏.‏ قَالَتْ بَلَى يَا رَبِّ‏.‏ قَالَ فَهْوَ لَكِ ‏"‌‏.‏ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ فَاقْرَءُوا إِنْ شِئْتُمْ ‏{‏فَهَلْ عَسَيْتُمْ إِنْ تَوَلَّيْتُمْ أَنْ تُفْسِدُوا فِي الأَرْضِ وَتُقَطِّعُوا أَرْحَامَكُمْ‏}‌‏"‌‏.‏

"አንድ ቃልን ለሁለት የተለያዩ ነገሮችን የሚለውን"two different things by the same word" አንድ ነገር አርጎ መውሰድ "Fallacy of equivocation" ነው። እዚህ ሐዲስ ማብቂያ ላይ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" "ረሒም" رَّحِم የተባለችው ማን እንደሆነች ለማመልከት ይህንን የቁርኣን አንቀጽ ጠቅሰዋል፦
47፥22 *ብትሽሾሙም በምድር ላይ ማበላሸትን "ዝምድናችሁንም" መቁረጥን ከጀላችሁን?* فَهَلْ عَسَيْتُمْ إِن تَوَلَّيْتُمْ أَن تُفْسِدُوا فِي الْأَرْضِ وَتُقَطِّعُوا أَرْحَامَكُمْ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ዘመዶች" ለሚለው የገባው ቃል "አርሓም" أَرْحَام ሲሆን "ረሒም" رَّحِم ማለትም "ዘመድ" ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፦
60፥3 *"ዘመዶቻችሁም" እና ልጆቻችሁም በትንሣኤ ቀን አይጠቅሟችሁም"*። لَن تَنفَعَكُمْ أَرْحَامُكُمْ وَلَا أَوْلَادُكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ
4፥1 *"ያንንም በእርሱ የምትጠያየቁበትን አላህን እና "ዝምድናዎችንም" ከመቁረጥ ተጠንቀቁ"*፡፡ አላህ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ ነውና፡፡ وَاتَّقُوا اللَّهَ الَّذِي تَسَاءَلُونَ بِهِ وَالْأَرْحَامَ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلَيْكُمْ رَقِيبًا

ሲቀጥል በአንስታይ መደብ "ቃለት" قَالَتْ ማለትም "አለች" የሚለው ቃል እና "ለኪ" لَكِ ማለትም "ለአንቺ" የሚለው ቃል በራሱ አሏህን እንደማያመላክቱ አመላካች ናቸው። የሴት ማኅፀን እራሱ በነጠላ "ረሒም" رَّحِم በብዜት "አርሓም" أَرْحَام ይባላል፦
3፥6 *"እርሱ ያ በማሕጸኖች ውስጥ እንደሚሻ አድርጎ የሚቀርጻችሁ ነው"*፡፡ هُوَ الَّذِي يُصَوِّرُكُمْ فِي الْأَرْحَامِ كَيْفَ يَشَاءُ
13፥8 አላህ ሴት ሁሉ የምታረግዘውን እና ማኅፀኖችም የሚያጎድሉትን የሚጨምሩትንም ያውቃል"*፡፡ اللَّهُ يَعْلَمُ مَا تَحْمِلُ كُلُّ أُنثَىٰ وَمَا تَغِيضُ الْأَرْحَامُ وَمَا تَزْدَادُ
"ረሒም" رَّحِم የሚለውን የማኅፀን ስሟን አምላካችን አሏህ እራሱ "አር-ረማን" الرَّحْمَـٰن ከሚለው ስሙ የጠራበት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 78, ሐዲስ 19
አቢ ሁራይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ረሒም የሚለው ቃል ከአር-ረሕማን የመጣ ነው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ إِنَّ الرَّحِمَ سُجْنَةٌ مِنَ الرَّحْمَنِ،
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 27, ሐዲስ 13 ዐብዱ አር-ረሕማን እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”አሏህም፦ "እኔ አሏህ ነኝ! እኔ አረ-ረሕማን ነኝ! እኔ ረሒም(ማኅፀን) ፈጠርኩኝ፥ ለእርሷ ከስሜ ስሟን አረባሁኝ። ማንም ከእርሷ ጋር የቀጠለ እኔም ከእርሱ ጋር እቀጥላለው፥ ማንም ከእርሷ ጋር ያቋረጠ እኔም ከእርሱ ጋር አቋርጣለው"*። فَقَالَ عَبْدُ الرَّحْمَنِ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ قَالَ اللَّهُ أَنَا اللَّهُ وَأَنَا الرَّحْمَنُ خَلَقْتُ الرَّحِمَ وَشَقَقْتُ لَهَا مِنَ اسْمِي فَمَنْ وَصَلَهَا وَصَلْتُهُ وَمَنْ قَطَعَهَا بَتَتُّهُ ‏"‏

እዚህ ሐዲስ ላይ "አረባሁኝ" ለሚለው የገባ ቃል "ሸቀቅቱ" شَقَقْتُ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። "ኢሽቲቃቅ" اِشْتِقَاق የሚለው ቃል "ኢሽተቀ" اِشْتَقَّ ማለትም "አረባ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "እርባታ"derivation" ወይም "ሥርወ-ቃል"etymology" ማለት ነው። ኢሽቲቃቅ በሁለት ዐበይት ጎራ ይመደባል፥ እርሱም "ኢሽቲቃቁል ከቢር" اِشْتِقَاق ٱلْكَبِير እና "ኢሽቲቃቁ አስ-ሶጊር" اِشْتِقَاق ٱلْصَغِر ነው።
1ኛ. "ኢሽቲቃቁል ከቢር"
"ከቢር" كَبِير‎ ማለት "ትልቅ" ማለት ሲሆን አንድ ቃል ከግስ መደብ ሲረባ ነው፥ ይህ ትልቁ እርባታ ነው። ለምሳሌ፦ "ቀውል" قَوْل የሚል ቃል "ቃለ" قَالَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ነው።
2ኛ. "ኢሽቲቃቁ አስ-ሶጊር"
"ሶጊር" صَغِر ማለት "ትንሽ" ማለት ሲሆን አንድ ቃል ከስም መደብ ሲረባ ነው፥ ይህ ትንሹ እርባታ ነው። ለምሳሌ፦ "ዘመድ" እና "ማኅፀን" የሚሉ ቃላት የያዘው "ረሒም" رَّحِم እራሱ "አር-ረማን" الرَّحْمَـٰن ከሚለው መርባቱ ይህንን ያሳያል።

ስለዚህ "ረሒም" رَّحِم የተባሉት የእናት ማኅፀን እና ዘመድ አዛኞች ናቸው፥ ከእነዚህ አዛኞች መቁረጥ የአሏህ እዝነት ያስቆርጣል መቀጠል የአሏህ እዝነት ያስቀጥላል። ነቢያችንም"ﷺ" ለዓለማት እዝነት ስለተላኩ "ረሒም" رَّحِيم ተብለዋል፥ ቅሉ ግን እነዚህ ሁሉ አዛኞች የተባሉት አሏህ አዛኝ በተባለበት ስሌትና ቀመር አይደለም። የአሏህ የእዝነቱ ጥልቀትና ስፋት፥ ምጥቀትና ልቀት ከሌሎች እዝነት ይለያል፥ አምላካችን አሏህ ከአዛኞች ሁሉ የበለጠ አዛኝ ነው፦
9፥128 *”ከራሳችሁ የሆነ ችግራችሁ በእርሱ ላይ ጽኑ የሆነ፣ በእናንተ ላይ የሚጓጓ፣ በምእምናን ላይ ርኅሩኅ "አዛኝ" የኾነ መልክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ”*፡፡ لَقَدْ جَاءَكُمْ رَسُولٌ مِّنْ أَنفُسِكُمْ عَزِيزٌ عَلَيْهِ مَا عَنِتُّمْ حَرِيصٌ عَلَيْكُم بِالْمُؤْمِنِينَ رَءُوفٌ رَّحِيمٌ
12፥64 *"እርሱም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነው"* وَهُوَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ
21፥83 አዩብንም ጌታውን «እኔ መከራ አገኘኝ *አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» ሲል በተጣራ ጊዜ አስታውስ"*፡፡ وَأَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ أَنِّي مَسَّنِيَ الضُّرُّ وَأَنتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መሢሑ አድ-ደጃል

መሢሑ አድ-ደጃል ባለ አንድ ዓይን ነው፥ ዓይኑ የታበሰ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 54, ሐዲስ 129
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ደጃል ዓይኑ የታበሰ ነው፤ በዓይኖቹ መካከል “ካፊር” የሚል ጽሑፍ አለ፤ ከዚያም “ከፈረ” የሚል አነባነብ ሁሉም ሙሥሊም ያነበዋል”*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ الدَّجَّالُ مَمْسُوحُ الْعَيْنِ مَكْتُوبٌ بَيْنَ عَيْنَيْهِ كَافِرٌ ‏”‏ ‏.‏ ثُمَّ تَهَجَّاهَا ك ف ر ‏”‏ يَقْرَؤُهُ كُلُّ مُسْلِمٍ ‏”‏

“የታበሰ” ለሚለው ቃል የገባው “መምሡሑ” مَمْسُوحُ ሲሆን ቁርኣን ላይ “ማበስ” ለሚለው የስም መደብ “መሥሕ” مَسْح በሚል መጥቷል፦
38፥33 «በእኔ ላይ መልሷት» አለ አጋዶችዋንና አንገቶችዋንም *ማበስ* ያዘ፡፡ رُدُّوهَا عَلَىَّ ۖ فَطَفِقَ مَسْحًۢا بِٱلسُّوقِ وَٱلْأَعْنَاقِ

በዓይኖቹ መካከል “ካፊር” የሚል ጽሑፍ አለ፤ “ካፊር” كَافِر ማለት “ከሃዲ” ማለት ሲሆን “ከፈረ” የሚል አነባነብ ሁሉም ሙሥሊም ያነበዋል፤ “ከፈረ” كَفَرَ ማለት “ካደ” ማለት ነው፤ “ፋ” ف በሸዳ ተሽዲድ ስናረጋት ደግሞ “ከፍፈረ” كَفَّرَ ሲሆን “ሸፈነ” ማለት ነው፤ “ካፉር” كَافُور ማለት “የተሸፈነ” ማለት ነው፤ ለምሳሌ በጀነት ለበጎ አድራጊዎች መበረዣዋ “ካፉር” ተብላለች፦
76፥5 በጎ አድራጊዎች መበረዣዋ *ካፉር* ከኾነች ጠጅ ይጠጣሉ፡፡ إِنَّ ٱلْأَبْرَارَ يَشْرَبُونَ مِن كَأْسٍۢ كَانَ مِزَاجُهَا كَافُورًا

“አድ-ደጃል” الدَّجَّال የሚለው ቃል “ደጀለ” دَجَلَ ማለትም “አጭበረበረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “አጭበርባሪ” ወይም “ሐሳዌ” ማለት ነው። ዋናው ደጃል “መሢሑ አድ-ደጃል” ማለት “ሐሳዌ መሢሕ” ማለት ነው። አሜሪካ ባለ አንድ ዶላሯ ላይ ያለው ባለ አንድ ዓይን ፒራሚድ የደጃል ምልክት ነው፥ በግብጽ አባት ኦስሪስ መለኮት ሲሆን ከእናት አይሲስ ሰው ከሆነች ጋር ተጋብተው አምላክ እና ሰው የሆነ ልጅ ሆረስ ተወለደ ይላሉ። ሆረስ የሚጠበቀው የዓለማችን ሐሳዌ መሢሕ ነው። ባለ አንድ ዓይን ከግብጽ ፒራሚዱ ጋር ያለው ግንኙነት ትልቅ ነው። በቀይ ያሰመርኩበትን ምልክቶች እዩት!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ኢብሊሥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

15፥32 *"አላህም «ኢብሊሥ ሆይ! ከሰጋጆቹ ጋር የማትኾን ለአንተ ምን ምክንያት አለህ» አለው"*፡፡ قَالَ يَا إِبْلِيسُ مَا لَكَ أَلَّا تَكُونَ مَعَ السَّاجِدِينَ

“ኢብሊሥ” إِبْلِيس የሚለው ቃል "በለሠ" بَلَسَ ማለትም "ተስፋ ቆረጠ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ተስፋ የቆረጠ" ማለት ነው፦
30፥12 *"ሰዓቲቱም በምትቆምበት ቀን አመጸኞች "ጭጭ ይላሉ"*፡፡ وَيَوْمَ تَقُومُ السَّاعَةُ يُبْلِسُ الْمُجْرِمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ፦ "ጭጭ ይላሉ" ለሚለው የግስ መደብ የገባው ቃል "ዩብሊሡ" يُبْلِسُ ሲሆን የወደፊት ግስ ነው፥ "ተስፋ ይቆርጣሉ" ማለት ነው። "ሙብሊሥ" مُبْلِس ማለት "ተስፋ ቆራጭ" ማለት ሲሆን የሙብሊሥ ብዙ ቁጥር "ሙብሊሡን" مُبْلِسُون ነው፦
23፥77 *በእነርሱም ላይ የብርቱ ቅጣት ባለቤት የኾነ ደጃፍን በከፈትንባቸው ጊዜ እነርሱ ያን ጊዜ በእርሱ "ተስፋ ቆራጮች" ናቸው*፡፡ حَتَّىٰ إِذَا فَتَحْنَا عَلَيْهِم بَابًا ذَا عَذَابٍ شَدِيدٍ إِذَا هُمْ فِيهِ مُبْلِسُونَ

"ተስፋ ቆራጮች" ለሚለው የገባው ቃል "ሙብሊሡን" مُبْلِسُون መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። "ኢብሊሥ” إِبْلِيس የሚለው ቃል 11 ጊዜ በ 11 ቦታ ከጂን ለሆነ ፍጡር የተሰጠ የግብር ስም ነው፦
18፥50 ለመላእክትም ለአደም ስገዱ! ባልናቸው ጊዜ የሆነውን አስታውስ ። ወዲያውም ሰገዱ፥ *ኢብሊሥ ብቻ ሲቀር ከጂን ነበር ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ"*፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ كَانَ مِنَ الْجِنِّ فَفَسَقَ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِ

"ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። “ጂኒ” جِنِّيّ የሚለው ቃል “ጀንነ” جَنَّ ማለትም “ሰወረ” ወይም “ደበቀ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ስውር” ወይም “ድብቅ” ማለት ነው፥ “ጂን” جِنّ ደግሞ የጂኒ ብዙ ቁጥር ነው፥ ኢብሊሥ ተፈጥሮው ከጂን ነው። ይህ ማንነት ጌታውን አሏህን አልታዘዝም በማለት ከአሏህ ትእዛዝ ወጣ፥ ከአሏህ ትእዛዝ ሲወጣ የአሏህ እዝነት ሲለየው ከአሏህ እዝነት ተስፋ ቆረጠ አሏህም "ኢብሊሥ" إِبْلِيس አለው፦
15፥32 *"አላህም «ኢብሊሥ ሆይ! ከሰጋጆቹ ጋር የማትኾን ለአንተ ምን ምክንያት አለህ» አለው"*፡፡ قَالَ يَا إِبْلِيسُ مَا لَكَ أَلَّا تَكُونَ مَعَ السَّاجِدِينَ

ከዚያ ከአሏህ ራሕመት ተባረረ፥ “ሸይጧን” شَّيْطَان የሚለው ቃል “ሸጠነ” شَّطَنَ ማለትም “ራቀ” ወይም “ተገለለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ከአላህ ራሕመት “የተገለለ” ወይም “የራቀ” ማለት ነው፦
7፥13 *"ከእርሷ ውረድ! በእርሷ ውስጥ ልትኮራ አይገባህምና፡፡ ውጣም አንተ ከወራዶቹ ነህና አለው"*፡፡ قَالَ فَاهْبِطْ مِنْهَا فَمَا يَكُونُ لَكَ أَن تَتَكَبَّرَ فِيهَا فَاخْرُجْ إِنَّكَ مِنَ الصَّاغِرِينَ

“ሸያጢን” شَيَاطِين ደግሞ የሽይጧን ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሰይጣናት” ማለት ነው። “ሸይጧን” ልክ እንደ “ሌባ” “ውሸታም” “ባለጌ” የግብር ስም እንጂ የተጽውዖ ስም አይደለም፥ ሸይጧን የሰውም የጂኒም አለ፦
6፥112 እንደዚሁም ለነቢያት ሁሉ *ከሰው እና ከጂን የኾኑን ሰይጣናት ጠላት* አደረግን፡፡ وَكَذَٰلِكَ جَعَلْنَا لِكُلِّ نَبِيٍّ عَدُوًّا شَيَاطِينَ الْإِنسِ وَالْجِن
114፥6 *«ከጂኒዎችም ከሰዎችም ሰይጣናት እጠበቃለሁ»* በል። مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ
23፥97 በልም *«ጌታዬ ሆ! ከሰይጣናት ጉትተጎታዎች በአንተ እጠበቃለሁ»* ፡፡ وَقُل رَّبِّ أَعُوذُ بِكَ مِنْ هَمَزَاتِ الشَّيَاطِينِ

አደም እና ሐዋን ያሳሳተ እና በጌታው ላይ ያመጸው ኢብሊሥ ዋና ሸይጧን ሲሆን የተጸውዖ ስሙ በቁርኣን እና በሶሒሕ ሐዲስ አልተገለጸም። ይህ ዋናው ሸይጧን የትንሳኤ ቀን፦ “ለእኔም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልበረኝም፥ ግን ጠራኋችሁ፡፡ ለእኔም ታዘዛችሁ፥ ስለዚህ አትውቀሱኝ! እራሳችሁን ውቀሱ!” ይላል፦
14፥22 *ነገሩም በተፈጸመ ጊዜ ሰይጣን፦ «አላህ እውነተኛውን ቃል ኪዳን ገባላችሁ፥ ቃል ኪዳንም ገባሁላችሁ። አፈረስኩባችሁም፥ ለእኔም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልበረኝም፡፡ ግን ጠራኋችሁ፥ ለእኔም ታዘዛችሁ፡፡ ስለዚህ አትውቀሱኝ! እራሳችሁን ውቀሱ! እኔ የምረዳችሁ አይደለሁም፥ እናንተም የምትረዱኝ አይደላችሁም፡፡ እኔ ከአሁን በፊት ለአላህ ተጋሪ በአደረጋችሁት ነገር ካድኩ፥ በዳዮቹ ለእነርሱ በእርግጥ አሳማሚ ቅጣት አላቸው» ይላቸዋል*። وَقَالَ الشَّيْطَانُ لَمَّا قُضِيَ الْأَمْرُ إِنَّ اللَّهَ وَعَدَكُمْ وَعْدَ الْحَقِّ وَوَعَدتُّكُمْ فَأَخْلَفْتُكُمْ ۖ وَمَا كَانَ لِيَ عَلَيْكُم مِّن سُلْطَانٍ إِلَّا أَن دَعَوْتُكُمْ فَاسْتَجَبْتُمْ لِي ۖ فَلَا تَلُومُونِي وَلُومُوا أَنفُسَكُم ۖ مَّا أَنَا بِمُصْرِخِكُمْ وَمَا أَنتُم بِمُصْرِخِيَّ ۖ إِنِّي كَفَرْتُ بِمَا أَشْرَكْتُمُونِ مِن قَبْلُ ۗ إِنَّ الظَّالِمِينَ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

ስለዚህ ለምንሠራው መጥፎ ሥራ ኢብሊሥን ተጠያቂ ማድረግ አንችልም፥ ሸይጧን ለእኛ ግልጽ ጠላት ነው። እርሱ የሚያጠቃን በእርምጃዎቹ ነው። አላህ ከኢብሊሥ፣ ከእርምጃዎቹ እና ከሰራዊቱ ይጠብቀን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ማሊክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥26 *በል፡- «የንግሥና "ባለቤት" የኾንክ አላህ ሆይ! ለምትሻው ሰው ንግሥናን ትሰጣለህ፡፡ ከምትሻውም ሰው ንግሥናን ትገፋለህ"*፡፡ قُلِ اللَّهُمَّ مَالِكَ الْمُلْكِ تُؤْتِي الْمُلْكَ مَن تَشَاءُ وَتَنزِعُ الْمُلْكَ مِمَّن تَشَاءُ

አምላካችን አሏህ "ማሊክ" مَالِك ተብሏል፥ "ማሊክ" مَالِك ማለት "ባለቤት"owner" ማለት ሲሆን በእርግጥም እርሱ የፍርዱ ቀን "ባለቤት" ነው፦
1፥4 *"የፍርዱ ቀን "ባለቤት" ለኾነው"*፡፡ مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ማሊክ" مَالِك የሚለውን ቃል የሐፍሥ ቂራኣት “ሚም” م ፈትሓህ ያ ስኩን “ማ” مَا በሚል ሪዋያህ ሁለት ሐረካህ መድ ስቦ “ማሊክ” مَالِك ብሎ ሲቀራው፥ የወርሽ ቂራኣት ደግሞ “ሚም” م ፈትሓህ “መ” مَ በሚል ሪዋያህ አንድ ሐረካህ ስቦ “መሊክ” مَلِك ተብሎ ይቀራዋል። አምላካችን አሏህ የንግሥና ባለቤት ነው፦
3፥26 *በል፡- «የንግሥና "ባለቤት" የኾንክ አላህ ሆይ! ለምትሻው ሰው ንግሥናን ትሰጣለህ፡፡ ከምትሻውም ሰው ንግሥናን ትገፋለህ"*፡፡ قُلِ اللَّهُمَّ مَالِكَ الْمُلْكِ تُؤْتِي الْمُلْكَ مَن تَشَاءُ وَتَنزِعُ الْمُلْكَ مِمَّن تَشَاءُ

አሏህ ለሚሻው ሰው የሚሰጠው ንግሥና እና የራሱ ንግሥና ይለያያል፥ አሏህ በንግሥናው ተጋሪ የለውም። እርሱ ንጉሥ የተባለው ፍጡራን በተባሉበት ስሌትና ቀመር አይደለም፥ በሰማያት፣ በምድር፣ በመካከላቸው ያለ ንግሥና የእርሱ ብቻ ነው። እንዲሁ እርሱ "ባለቤት" የተባለበት ሰው "ባለቤት" በተባለበት ሒሳብ አይደለም፥ አሏህ ሰውን በእንስሳ ላይ "ባለቤት" እንዲሆን ፈጥሮታል፦
36፥71 *”እኛ እጆቻችን ከሠሩት ለእነርሱ እንስሳዎችን መፍጠራችንን አያውቁምን? እነርሱም ለእርሷ ባለ መብቶች ናቸው”*፡፡ أَوَلَمْ يَرَوْا أَنَّا خَلَقْنَا لَهُم مِّمَّا عَمِلَتْ أَيْدِينَا أَنْعَامًا فَهُمْ لَهَا مَالِكُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ባለ መብቶች” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ማሊኩን” مَالِكُون ሲሆን “ማሊክ” مَالِك ለሚለው ቃል ብዜት ነው። አንድ ስም ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብና ትርጉም እንደሌለው ዕሙር ነው፥ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ እሙን ነው። መታየት ያለበት ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብ፣ የአንቀጹን ምህዋር፣ አውታርና ምህዳር እንደሆነ ቅቡል ነው። ለምሳሌ ከአሥራ ዘጠኝ የጀሀነም ዘበኞች አንዱ እና የእነርሱ አለቃ የተጸውዖ ስሙ "ማሊክ" مَالِك ነው፦
43፥77 *«ማሊክ ሆይ! ጌታህ በእኛ ላይ በሞት ይፍረድ፡፡» እያሉ ይጣራሉም፡፡ «እናንተ በቅጣቱ ውስጥ ዘላለም ነዋሪዎች ናችሁ» ይላቸዋል*፡፡ وَنَادَوْا يَا مَالِكُ لِيَقْضِ عَلَيْنَا رَبُّكَ ۖ قَالَ إِنَّكُم مَّاكِثُونَ

ሚሽነሪዎች፦ "ማሊክ አሏህ ነው፥ የእሳት ሰዎች አሏህን "ጌታህ" ማለታቸው አሏህ ጌታ አለው" በማለት "ኢየሱስ አምላክ አለው" ለሚለው ሙግታችን የእከክልኝ ልከክልህ ተዋናይ በመሆን ተውኔት ይተውናሉ።

፨ ሲጀመር የእሳት ሰዎች፦ "ጌታህ" እያሉ የሚጠይቁት ከአሥራ ዘጠኝ የጀሀም ዘበኞች አንዱ እና የእነርሱ አለቃ የሆነውን ማሊክን ብቻ ሳይሆን ሌሎችን የጀሀነም ዘበኞችን የሆኑትን መላእክትን ጭምር ነው፦
40፥49 *"እነዚያም በእሳት ውሰጥ ያሉት ለገሀነም ዘበኞች «"ጌታችሁን" ለምኑልን፥ ከእኛ ላይ ከቅጣቱ አንድን ቀን ያቃልልን» ይላሉ"*፡፡ وَقَالَ الَّذِينَ فِي النَّارِ لِخَزَنَةِ جَهَنَّمَ ادْعُوا رَبَّكُمْ يُخَفِّفْ عَنَّا يَوْمًا مِّنَ الْعَذَابِ

ልብ አድርግ የእሳት ሰዎች ማሊክን "ጌታህ" ባሉበት ሒሳብ የጀሀነም ዘበኞችን "ጌታችሁ" ብለዋል፣ የእሳት ሰዎች ማሊክን በጠየቁበት ስሌት የጀሀነም ዘበኞችን ጠይቀዋል፣ ማሊክ ለእሳት ሰዎች በመለሰበት ቀመር የእሳት ዘበኞች ለእሳት ሰዎች መልሰዋል፦
43፥77 *«እናንተ በቅጣቱ ውስጥ ዘላለም ነዋሪዎች ናችሁ» ይላቸዋል*፡፡ قَالَ إِنَّكُم مَّاكِثُونَ
40፥50 *«እንግዲያውስ ጸልዩ! የከሓዲዎችም ጸሎት በከንቱ እንጂ አይደለም» ይሏቸዋል*፡፡ قَالُوا فَادْعُوا ۗ وَمَا دُعَاءُ الْكَافِرِينَ إِلَّا فِي ضَلَالٍ
፨ ሲቀጥል ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" የእሳት ሰዎች "ማሊክ" ያሉት የእሳት ዘበኛ የሆነውን መልአክ እንደሆነ በጂብሪል አማካኝነት ነግረውናል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 59 , ሐዲስ 47
ሠሙራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“በሌሊት ላይ ሁለት ሰዎች ወደ እኔ ሲመጡ አየሁኝ፥ ከእነርሱ አንዱ(ጂብሪል) እንዲህ አለ፦ "ያ እሳት የሚያይዝ “ማሊክ” ሲሆን “የእሳት ዘበኛ” ነው፥ እኔ ጂብሪል ነኝ። ይህ ሚካኢል ነው"*። عَنْ سَمُرَةَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ رَأَيْتُ اللَّيْلَةَ رَجُلَيْنِ أَتَيَانِي قَالاَ الَّذِي يُوقِدُ النَّارَ مَالِكٌ خَازِنُ النَّارِ، وَأَنَا جِبْرِيلُ، وَهَذَا مِيكَائِيلُ ‏"‌‏.‏

ምን ትፈልጋላችሁ? ማሊክ የእሳት ዘበኛ መሆኑ ከታወቀ ዘንዳ ማሊክ ከአሥራ ዘጠኝ የእሳትንም ዘበኞች አንዱ ነው፥ የእሳትንም ዘበኞች መላእክት ሲሆኑ በቁጥር አሥራ ዘጠኝ ናቸው። ከእነርሱ መካከል የልኡካኑ ቡድን አለቃ ማሊክ ነው፥ እነዚህ መላእክት ጨካኞች እና ኃይለኞች የኾኑ መላእክት ሲሆኑ አሏህ ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፥ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ፦
74፥30 *"በእርሷም ላይ አሥራ ዘጠኝ ዘበኞች አሉባት"*፡፡ عَلَيْهَا تِسْعَةَ عَشَرَ
74፥31 *"የእሳትንም ዘበኞች መላእክት እንጅ ሌላ አላደረግንም"*፡፡ وَمَا جَعَلْنَا أَصْحَابَ النَّارِ إِلَّا مَلَائِكَةً
66፥6 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! መቀጣጠያዋ ሰዎች እና ደንጋዮች ከኾነች እሳት እራሳችሁን እና ቤተሰቦቻችሁን ጠብቁ! በእርሷ ላይ ጨካኞች እና ኃይለኞች የኾኑ መላእክት አሉ፡፡ አላህን ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፥ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَائِكَةٌ غِلَاظٌ شِدَادٌ لَّا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ

፨ ሢሰልስ በሴማዊ ፎኔሺያን “ሞለክ” מֹלֶךְ የሚለው ስም በዕብራይስጥ “መለክ” מֶלֶךְ የሚባል ሲሆን “ንጉሥ” ማለት ነው፥ ከነዓናውያን እና አሞናውያን ጣዖት አድርገው ላመለኩት ስም ሆኖ አገልግሏል። ይህ ጣዖት ከነዓናውያን እና አሞናውያን በእሳት እንዳይቀጣቸው የበኩር ልጃቸው በሄኖም ሸለቆ ላይ “ቶፌት” תָּפְתֶּה ማለትም "የእሳት ምድጃ” ሠርተው መስዋዕት ያቀርቡለት፣ ይሰግዱለት እና ያመልኩት ነበር፦
ዘሌዋውያን 18፥21 *"ከዘርህም “ለሞሎክ” לַמֹּ֑לֶךְ በእሳት አሳልፈህ አትስጥ"*።
ዘሌዋውያን 20፥2 *"ማናቸውም ሰው ዘሩን “ለሞሎክ” לַמֹּ֖לֶךְ ቢሰጥ ፈጽሞ ይገደል"*።
አሞጽ 5፥26 *ለራሳችሁም የሠራችኋቸውን ምስሎች፥ “የእናንተ ሞሎክን” מַלְכְּכֶ֔ם ድንኳን እና የአምላካችሁን የሬፋን ኮከብ አነሣችሁ*።

አሞጽ 5፥26 ላይ “ሞለክ” מֹלֶךְ ተብሎ የተቀመጠውን ግሪክ ሰፕቱአጀንት”LXX” ላይ “ባሲለዩስ” βασιλεύς ነው፥ ትርጉሙም “ንጉሥ” ማለት ነው። ሞሎክ ወይም ሞለክ በዕብራይስጥም “መለክ” מֶ֖לֶךְ ተብሏል፦
ኢሳይያስ 30፥33 ከቀድሞም ጀምሮ ቶፌት(የማቃጣያ ስፍራ) ተዘጋጅታለች፥ "ለንጉሥም" ተበጅታለች"*። כִּֽי־עָר֤וּךְ מֵֽאֶתְמוּל֙ תָּפְתֶּ֔ה גַּם־ [הוּא כ] (הִ֛יא ק) לַמֶּ֥לֶךְ הוּכָ֖ן הֶעְמִ֣יק

እዚህ አንቀጽ ላይ "ንጉሥ" ለሚለው የገባው ቃል “መለክ” מֶלֶךְ ሲሆን ለሞሎክ የገባ ቃል ነው። ልብ አድርግ “መለክ” מֶלֶךְ የሚለው ቃል እና ትርጉሙ አንድ ነው ማለት ቃሉ እና ትርጉሙ የወከለው አሳብ አንድ ነው ማለት አይደለም፥ ምክንያቱም “መለክ” מֶלֶךְ የሚለው ስም ለጣዖት ስም ሆኖ ቢያገለግልም ለፈጣሪ ግን የባሕርይ ስም ሆኖ ተገልፃል። ታዲያ ፈጣሪ የከነዓናውያን እና የአሞናውያን ጣዖት ነውን? "ነው" እንደማትሉኝ ግልፅ ነው፥ ፈጣሪ ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር “መለክ” מֶלֶךְ ማለትም “ንጉሥ” ነው። እርሱ ታላቅ ንጉሥ ነው፦
መዝሙር 74፥12 *ያህዌህ ግን ከዓለም አስቀድሞ “ንጉሥ” מֶ֖לֶךְ ነው"*።
መዝሙር 95፥3 *ያህዌህ ታላቅ አምላክ ነውና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ ታላቅ “ንጉሥ” מֶ֖לֶךְ ነውና*።

ያህዌህ “መለክ” מֶ֖לֶךְ ስለተባለ እና ጣዖቱ “መለክ” מֶ֖לֶךְ ስለተባለ ያህዌህ ጣዖቱ ነውን? "አይ ያህዌህ “መለክ” የተባለበት እና ጣዖቱ “መለክ” በተባለበት ስሌት አይደለም" ካላችሁ እንግዲያውስ ከላይ ያለውንም የሙግት ነጥብ በዚህ መልክ እና ልክ ተረዱት!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፍልስጥኤም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥251 *"በአላህም ፈቃድ ድል መቷቸው፥ ዳውድም ጃሉትን ገደለ"*፡፡ فَهَزَمُوهُم بِإِذْنِ اللَّهِ وَقَتَلَ دَاوُودُ جَالُوتَ

"ፊልሥጢን" فِلَسْطِين ማለት "ፍልስጥኤም" ማለት ሲሆን በአንድ ወቅት የፍሊሥጢን ንጉሥ "ጃሉት" جَالُوت ማለትም "ጎልያድ" እና ሠራዊቱ ከጧሉት ማለትም ከሳኦል ሠራዊት ተዋግተዋል፦
2፥249 *ጧሉትም በሠራዊቱ ታጅቦ በወጣ ጊዜ፡- «አላህ በወንዝ ፈታኛችሁ ነው፥ ከርሱም የጠጣ ሰው ከእኔ አይደለም፡፡ ያልቀመሰውም ሰው በእጁ መዝገንን የዘገነ ሰው ብቻ ሲቀር እርሱ ከእኔ ነው» አለ፡፡ ከእነርሱም ጥቂቶች ሲቀሩ ከርሱ ጠጡ፡፡ እርሱ እና እነዚያም ከእርሱ ጋር ያመኑት ወንዙን ባለፉት ጊዜ፡- «ጃሎትን እና ሠራዊቱን በመዋጋት ለኛ ዛሬ ችሎታ የለንም» አሉት፡፡ እነዚያ እነርሱ አላህን ተገናኝዎች መኾናቸው የሚያረጋግጡት፡- «ከጥቂት ጭፍራ በአላህ ፈቃድ ብዙን ጭፍራ ያሸነፈች ብዙ ናት፤ አላህም ከታጋሾች ጋር ነው» አሉ*፡፡ فَلَمَّا فَصَلَ طَالُوتُ بِالْجُنُودِ قَالَ إِنَّ اللَّهَ مُبْتَلِيكُم بِنَهَرٍ فَمَن شَرِبَ مِنْهُ فَلَيْسَ مِنِّي وَمَن لَّمْ يَطْعَمْهُ فَإِنَّهُ مِنِّي إِلَّا مَنِ اغْتَرَفَ غُرْفَةً بِيَدِهِ ۚ فَشَرِبُوا مِنْهُ إِلَّا قَلِيلًا مِّنْهُمْ ۚ فَلَمَّا جَاوَزَهُ هُوَ وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ قَالُوا لَا طَاقَةَ لَنَا الْيَوْمَ بِجَالُوتَ وَجُنُودِهِ ۚ قَالَ الَّذِينَ يَظُنُّونَ أَنَّهُم مُّلَاقُو اللَّهِ كَم مِّن فِئَةٍ قَلِيلَةٍ غَلَبَتْ فِئَةً كَثِيرَةً بِإِذْنِ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ مَعَ الصَّابِرِينَ

ከዚያም በጦርነቱ ተፋልመው ተስፋ በቆረጡ ጊዜ ዳውድ ጃሉትን ገሎታል፦
2፥250 *ለጃሉት እና ለሠራዊቱ በተሰለፉም ጊዜ፡- «ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አንቧቧ፤ ጫማዎቻችንንም አደላድል፤ በከሓዲያን ሕዝቦችም ላይ እርዳን» አሉ፡፡ وَلَمَّا بَرَزُوا لِجَالُوتَ وَجُنُودِهِ قَالُوا رَبَّنَا أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًا وَثَبِّتْ أَقْدَامَنَا وَانصُرْنَا عَلَى الْقَوْمِ الْكَافِرِينَ
2፥251 *"በአላህም ፈቃድ ድል መቷቸው፥ ዳውድም ጃሉትን ገደለ"*፡፡ فَهَزَمُوهُم بِإِذْنِ اللَّهِ وَقَتَلَ دَاوُودُ جَالُوتَ

ቁርኣን ላይ ስለ ፍልስጥኤማውያን የሚናገረው እነዚህ አናቅጽ ላይ ነው። ሚሽነሪዎች፦ "ፍልስጥኤማውያን ፍልስጥኤም የምትባል አገር የላቸውም" እያሉ ባላነበቡት ነገር ይዘባርቃሉ። ፈጣሪ እስራኤልን ከግብጽ ምድር እንዳወጣ ሁሉ በጥንት ጊዜ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር አውጥቶ የራሳቸው ግዛት ሰቷቸዋል፦
አሞጽ 9፥7 እስራኤልን ከግብጽ ምድር፥ *ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?*
ኢዮኤል 3፥4 ጢሮስና ሲዶና *የፍልስጥኤምም ግዛት ሁሉ ሆይ*፥ ከእናንተ ጋር ለእኔ ምን አለኝ? በውኑ ብድራትን ትመልሱልኛላችሁን?

"የፍልስጥኤምም ግዛት" የሚለው ይሰመርበት። ፍልስጥኤም ግዛት ከነበረች ለምን መብቷ አይከበረም? እስራኤላውያን ቦታቸው መጥተው ሰፈሩባቸው እንጂ ጥንትም ቢሆን የእስራኤል ቅም አያት አብርሃም ከከላዳውያን ኡር በፍልስጥኤም ምድር ብዙ ቀን እንግዳ ሆኖ ተቀምጧል፦
ዘፍጥረት 21፥34 *"አብርሃምም በፍልስጥኤም ምድር ብዙ ቀን እንግዳ ሆኖ ተቀመጠ"*።

ፍልስጥኤም መጤ ሳትሆን የራሷ ምድር ስለሆነ "በፍልስጥኤም ምድር" የሚል ኃይለ-ቃል ተጽፏል። ባይብል ላይ ብዙ ቦታ "የፍልስጥኤም ምድር" እያለ ይናገራል፦
ኤርምያስ 25፥20 የተደባለቀውንም ሕዝብ ሁሉ፥ የዖፅ ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፥ *የፍልስጥኤም ምድር ነገሥታትንም ሁሉ አስቀሎናንም ጋዛንም አቃሮንንም የአዞጦንንም ቅሬታ"*።
ዘጸአት 13፥17 እንዲህም ሆነ ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ ምንም ቅርብ ቢሆን እግዚአብሔር *በፍልስጥኤማውያን ምድር* መንገድ አልመራቸውም።

ፍልስጥኤማውያን የራሳቸው አገር አላቸው፥ እስራኤላውያን የሰፈሩበት ከነዓን ሁሉ ሳይቀር የፍልስጥኤማውያን ምድር ነው፦
2ኛ ነገሥት 8፥2 ሴቲቱም ተነሥታ እንደ እግዚአብሔር ሰው ቃል አደረገች፤ ከቤተ ሰብዋም ጋር ሄዳ *"በፍልስጥኤም አገር ሰባት ዓመት ተቀመጠች"*።
ሶፎንያስ 2፥5 *"የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ"*፥ የእግዚአብሔር ቃል በአንተ ላይ ነው።

ዛሬ አገር እና ግዛት እንደሌላቸው እና መጤ እንደሆኑ ታይቶ እየተፈናቀሉ ነው፥ አሏህ ነስሩን ያቅርብላቸው! አሚን። ይህንን የምንለው ስለ ሐቅ እና ስለ ፍትሕ ነው፥ "ኢሥላም ሰም እና ወርቅ የያዘ ቅኔ ነው፥ ሰሙ ሐቅ ሲሆን ወርቁ ፍትሕ ነው" ስንል ዕውር ድንብ ጸለምተኛ ሙግት ይዘን ሳይሆን ጠቅሰንና አጣቅሰን በመሞገትና በመሟገት ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቅዳሴ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥30 *ጌታህ ለመላእክት፦ «እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ» ባለ ጊዜ የኾነውን አስታውስ! እነርሱም፦ «እኛ ከማመስገን ጋር የምናጠራህ "ለአንተም የምንቀድስ" ስንኾን በእርሷ ውስጥ የሚያጠፋን እና ደሞችንም የሚያፈስን ታደርጋለህን?» አሉ፡፡ አላህም፦ «እኔ የማታውቁትን ነገር አውቃለሁ» አላቸው*፡፡ وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي جَاعِلٌ فِي الْأَرْضِ خَلِيفَةً ۖ قَالُوا أَتَجْعَلُ فِيهَا مَن يُفْسِدُ فِيهَا وَيَسْفِكُ الدِّمَاءَ وَنَحْنُ نُسَبِّحُ بِحَمْدِكَ وَنُقَدِّسُ لَكَ ۖ قَالَ إِنِّي أَعْلَمُ مَا لَا تَعْلَمُونَ

ለአንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ተከታይ "ቅዳሴ" ማለት በግዕዝ፣ በእዝል እና በአራራይ ከ-"አሐዱ" እስከ "እትዉ በሠላም" የሚዜም ዜማ ማለት ነው፥ ይህ የተሳሳተ መቅድመ-መረዳት"presupposed understand" ነው። ያሬድ በ 527 ድኅረ-ልደት ግዕዝ፣ እዝል እና አራራይ የሚባሉትን ዜማ ከመድረሱ ከ 1200 ዓመት በፊት ቅዳሴ ነበረ፦
ኢሳይያስ 8፥13 *ነገር ግን የሠራዊት ጌታ ያህዌን "ቀድሱት!"* אֶת־יְהוָ֥ה צְבָאֹ֖ות אֹתֹ֣ו תַקְדִּ֑ישׁוּ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ቀድሱ" ለሚለው የገባው የዕብራይስጡ ቃል "ተቅዲሡ" תַקְדִּ֑ישׁוּ ሲሆን "አመስግኑ" "አወድሱ" "አሞግሱ" "አሞካሹ" ማለት ነው። "ቅዳሴ" የሚለው የግዕዙ ቃል እራሱ "ቀደሰ" ማለትም "አመሰገነ" "አወደሰ" "አሞገሰ" "አሞካሸ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ምስጋና" "ውዳሴ" "ሙገሳ" "ሙካሻ" ማለት ነው፥ ይህንን የቋንቋ ሙግት በቀላሉ ከተረዳን ዘንዳ መላእክት ለአሏህ፦ "ለአንተም የምንቀድስ" ሲሉ "ለአንተም የምናመሰግን" "የምናወድስ" "የምናሞግስ" "የምናሞካሽ" ማለታቸው እንጂ በግዕዝ፣ በእዝል እና በአራራይ የሚዜም ያሬዳዊ ዜማ "ለአንተም የምናዜም" ማለታቸው በፍጹም አይደለም፦
2፥30 *ጌታህ ለመላእክት፦ «እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ» ባለ ጊዜ የኾነውን አስታውስ! እነርሱም፦ «እኛ ከማመስገን ጋር የምናጠራህ "ለአንተም የምንቀድስ" ስንኾን በእርሷ ውስጥ የሚያጠፋን እና ደሞችንም የሚያፈስን ታደርጋለህን?» አሉ፡፡ አላህም፦ «እኔ የማታውቁትን ነገር አውቃለሁ» አላቸው*፡፡ وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي جَاعِلٌ فِي الْأَرْضِ خَلِيفَةً ۖ قَالُوا أَتَجْعَلُ فِيهَا مَن يُفْسِدُ فِيهَا وَيَسْفِكُ الدِّمَاءَ وَنَحْنُ نُسَبِّحُ بِحَمْدِكَ وَنُقَدِّسُ لَكَ ۖ قَالَ إِنِّي أَعْلَمُ مَا لَا تَعْلَمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የምቀድስ" ለሚለው የገባው ቃል "ኑቀዲሡ" نُقَدِّسُ ሲሆን "የምናመሰግን" "የምናወድስ" "የማሞግስ" "የምናሞካሽ" ማለት ነው። እሩቅ ሳንሄድ "ቀዳሲ" ማለት "አመስጋኝ" "አወዳሽ" "አሞጋሽ" "አሞካሽ" ማለት ሲሆን "ቅዱስ" ማለት ደግሞ "ምስጉን" "ተመስጋኝ" "ተወዳሽ" "ተሞጋሽ" "ተሞካሽ" ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ "ምስጉን" "ተመስጋኝ" "ተወዳሽ" "ተሞጋሽ" "ተሞካሽ" ስለሆነ "አል-ቁዱሥ" الْقُدُّوس ተብሏል፦
62፥1 *"በሰማያት ያለው በምድርም ያለው ሁሉ ለአላህ ንጉሥ፣ "ቅዱስ"፣ አሸናፊ፣ ጥበበኛ ለኾነው ያሞግሳል"*፡፡ يُسَبِّحُ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ الْمَلِكِ الْقُدُّوسِ الْعَزِيزِ الْحَكِيمِ

የምስጋና ቦታ "መቅደስ" ሲባል "ማመስገኛ" "ማወደሻ" "ማሞገሻ" "ማሞካሻ" ማለት ነው፥ ለምሳሌ ሡለይማን የገነባው የማመስገኛ፣ የማወደሻ፣ የማሞገሻ እና የማሞካሻ ቤት “በይቱል መቅዲሥ” بَيْت الْمَقْدِس ተብሏል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 1473
ዐብደላህ ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ሡለይማን ኢብኑ ዳዉድ በይቱል መቅዲሥን ገንብቶ በጨረሰ ጊዜ አላህን ሦስት ነገሮች ጠይቋል። አንደኛ በፍርዱ የሚያስማማበትን ፍርድ ጠየቀ ያም ተሰጠው፣ ሁለተኛ ከእርሱ በኃላ ማንም የማይኖረውን ንግሥና፣ ሦስተኛ ሶላት ለማድረግ እንጂ ወደዚህ መሥጂድ የሚመጣውን ልክ እናቱ ስትወልደው ከኀጢአት ነጻ እንደሆነ እንዲሆን”*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، عَنِ النَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏”‏ لَمَّا فَرَغَ سُلَيْمَانُ بْنُ دَاوُدَ مِنْ بِنَاءِ بَيْتِ الْمَقْدِسِ سَأَلَ اللَّهَ ثَلاَثًا حُكْمًا يُصَادِفُ حُكْمَهُ وَمُلْكًا لاَ يَنْبَغِي لأَحَدٍ مِنْ بَعْدِهِ وَأَلاَّ يَأْتِيَ هَذَا الْمَسْجِدَ أَحَدٌ لاَ يُرِيدُ إِلاَّ الصَّلاَةَ فِيهِ إِلاَّ خَرَجَ مِنْ ذُنُوبِهِ كَيَوْمَ وَلَدَتْهُ أُمُّهُ

ለነቢያችን"ﷺ" ወሕይ መውረድ የጀመረው እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 610 ድኅረ-ልደት ሲሆን ያሬድ ደግሞ ግዕዝ፣ እዝል እና አራራይ የሚባሉትን ዜማ የደረሰው በ 527 ድኅረ-ልደት ነው፥ በሁለቱ መካከል የ 83 ዓመት ልዩነት ስላለ ነቢያችን"ﷺ" የቅዳሴን እሳቤ ከያሬድ የወሰዱት ለማስመሰል የተቃጣው ሙከራ በቋንቋ ሙግት ድባቅ ገብቷል። "ቅዳሴ የተጀመረው በያሬድ ነው" የሚለው ትርክት ፉርሽ ነው፥ አሁን ፊሽካው ተነፍቷል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የመርየም ልጅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥75 *የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ እናቱም በጣም እውነተኛ ናት*፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ وَأُمُّهُ صِدِّيقَةٌ

የኢትዮጵያ የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን በተለምዶ “ኢየሱስ ብቻ”only Jesus” የሚባሉት፦ “ኢየሱስ የማርያም ልጅ አይደለም” ይላሉ። ይህንን ስሑት ሙግት በስሙር ሙግት ለመመለስ ቅድሚያ ከቁርኣን እንነሳ፥ አምላካችን አላህ መሢሑን ኢየሱስን በ 23 ቦታ “ኢብኑ መርየም” ابْن مَرْيَم ማለትም “የመርየም ልጅ” ይለዋል። ለናሙና ያክል አንድ አንቀጽ እንመልከት፦
5፥75 *የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ እናቱም በጣም እውነተኛ ናት*፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ وَأُمُّهُ صِدِّيقَةٌ

“እናቱ” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ልጅ የሚጠራው በአባቱ ስም የእከሊት ልጅ ሳይሆን የእከሌ ልጅ ነው፥ ነገር ግን ዒሣ አባት ስለሌለው በእናቱ ስም “የመርየም ልጅ” ይባላል። ባይብል ኢየሱስ የማርያም ልጅ መሆኑን ያስተባብላልን? እረ በፍጹም። ከዚያ ይልቅ ኢየሱስ የማርያም የማኅፀኗ ፍሬ ነው፥ ፅንሱም ከራሷ በታምር የተጸነሰ ነው፦
ሉቃስ 1፥42 አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ ፤የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው*።
ማቴዎስ 1፥20 *”ከእርስዋ” የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ*።

“ከእርስዋ የተፀነሰው” የሚለው ይሰመርበት። “ከ” የሚለው መስተዋድድ በራሱ ጽንሱ የራሷ ፍሬ መሆኑን ቁልጭ እና ፍንትው አርጎ ያሳያል። የእርሷ ፍሬ፣ የእርሷ ፅንስ ስለሆነ እና ከእርሷ ስለተወለደ ልጇ ነው፦
ሉቃስ 2፥7 የበኵር *ልጅዋንም ወለደች”*።
ማቴዎስ 1፥25 የበኩር *ልጅዋንም” እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም*

የወንጌላት ጸሐፊያን ሆነ መልአኩ ማርያም የኢየሱስ እናት መሆኗን “እናቱ” በማለት በአገናዛቢ ዘርፍ ይናገራሉ፦
ሉቃስ 2፥33 ዮሴፍ እና *እናቱም* ስለ እርሱ በተባለው ነገር ይደነቁ ነበር።
ማቴዎስ 2፥11 ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን *ከእናቱ* ከማርያም ጋር አዩት።
ማቴዎስ 2፥13 ሕፃኑን እና *እናቱንም* ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ።
ማቴዎስ 2፥14 እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑን እና *እናቱን* በሌሊት ያዝ።

ኢየሱስም 81 ጊዜ እራሱን “የሰው ልጅ” እያለ ይጠራ እንደነበር በአራቱ ወንጌላት ዘገባ ተዘግቧል፥ እራሱን “የሰው ልጅ” ያለበት 30 ጊዜ ማቴዎስ ላይ፣ 14 ጊዜ ማርቆስ ላይ፣ 25 ጊዜ ሉቃስ ላይ እና 12 ጊዜ ዮሐንስ ላይ ሰፍሯል። በ 250 ድኅረ-ልደት በተገኘው የማቴዎስ ደንገል”papyrus” 1 ላይ 30 ጊዜ እራሱን “የሰው ልጅ” እያለ ይጠራ እንደነበር ጥናቶች ያመላክታሉ። “የ” መነሻ ቅጥያ ያለበት “ሰው” የሚለው ቃል ማርያምን የሚያመላክት ነው፥ “የሰው ልጅ” ሲል “”የማርያም ልጅ” ለማለት ነው። ኢየሱስ ስለራሱ በሦስተኛ መደብ “የሰው ልጅ” መሆኑን አበክሮና አዘክሮ ተናግሯል፦
ዮሐንስ 5፥27 *”የሰው ልጅም” ስለ ሆነ ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን ሰጠው*።
ማቴዎስ 11፥19 *”የሰው ልጅ” እየበላ እና እየጠጣ መጣ”*።

ኢየሱስ የሚያደርጋቸው በሙሉ ሥልጣን ከአምላኩ ተሰጥቶ ነው። ከማርያም ስለተፀነሰ የመራብ እና የመጠማት፥ የመብላት እና የመጠጣት ባሕርይ አለው። ወደ አፉ የበላውን እና የጠጣውን ደግሞ በሌላ መልኩ ከሰውነት ያስወግዳል፦
ማቴዎስ 15፥17 *ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ አልፎ ወደ እዳሪ እንዲጣል አትመለከቱምን?*

ወደ ሰማይ ካረገስ በኃላ? ጋረገ በኃላም እስጢፋኖስ በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ ያየው “የሰው ልጅ” የተባለውን ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 7፥56 እነሆ፥ ሰማያት ተከፍተው *”የሰው ልጅም” በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ” አለ*።

ኢየሱስ “የሰው ልጅ” ነው ብሎ ማመን አንቀጸ-እምነት ነው፥ የክርስትና ሊሒቃን ሆኑ ሥነ-መለኮታውያን በዚህ ይስማማሉ፦
ዮሐንስ 9፥35 ኢየሱስም ወደ ውጭ እንዳወጡት ሰማ፥ ሲያገኘውም፦ *አንተ በሰው ልጅ ታምናለህን? አለው*። አዲስ ትርጉም
Jesus heard that they had thrown him out, and when he found him, he said, *”Do you believe in the Son of Man?”* (New International Version)
ግሪኩ፦ Ἤκουσεν Ἰησοῦς ὅτι ἐξέβαλον αὐτὸν ἔξω, καὶ εὑρὼν αὐτὸν εἶπεν Σὺ πιστεύεις εἰς τὸν υἱὸν τοῦ ἀνθρώπου

“ቶን ሁኦን ቶዩ አንትሮፓዩ” τὸν υἱὸν τοῦ ἀνθρώπου ማለት “የሰው ልጅ” ማለት ነው። “በሰው ልጅ” ታምናለህን? የሚለው በመቀየር “በእግዚአብሔር ልጅ” ታምናለህን? ብሎ መበረዝ ለምን አስፈለገ? ይህ ለሁሉም የክርስትና ክፍል የቤት ሥራ ነው። ዋና ነጥቡ ኢየሱስ ራሱ “በሰው ልጅ” ታምናለህን? ብሎ መጠየቁ በራሱ ኢየሱስን “የሰው ልጅ” ነው” ብሎ ማመን ዐቂዳህ ነው። የኢትዮጵያ የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ኢየሱስ “የሰው ልጅ” መባሉ ሽሙጥና ለበጣ ነው ብለው ቢሉም እኛም ሙሥሊሞች ግን ኢየሱስ “የመርየም ልጅ” ነው” ብለን እናምናለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቅርቢቱ ሰማይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

37፥6 *"እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት"*፡፡ إِنَّا زَيَّنَّا السَّمَاءَ الدُّنْيَا بِزِينَةٍ الْكَوَاكِبِ

በቅዱስ ቁርኣን ላይ "ዓለም" عَالَم ማለት አንድ ነጠላ "ዓለም"uni-verse" ሲሆን "ዐለሚን" عَٰلَمِين ደግሞ ብዙ ዐለማት"multi-verse" ማለት ነው። የምንኖርበት ዓለም "ዱንያ" دُّنْيَا ሲባል የቅርቢቱ ሕይወት እና ዓለም የሚያመለክት ነው፥ "ዱንያ" دُّنْيَا የሚለው ቃል "አድና" أَدْنَى‎ ማለትም "ቅርብ" ለሚለው ተባዕታይ መደብ አንስታይ መደብ ሲሆን "ቅርቢቱ" ማለት ነው። የምኖርበትን ዓለም ውስጥ ያሉትን ከዋክብትን አቅፎ የያዘው ሰማይ ደግሞ "አሥ-ሠማኡ አድ-ዲንያ" السَّمَاء الدُّنْيَا ማለትም "ቅርቢቱን ሰማይ" ይባላል፦
37፥6 *"እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት"*፡፡ إِنَّا زَيَّنَّا السَّمَاءَ الدُّنْيَا بِزِينَةٍ الْكَوَاكِبِ

"ሠማእ" سَّمَاء የሚለው ቃል "ሠማ" سَمَا ማለትም "ከፍ አለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ከፍታ" ወይም "አርያም" አሊያም "ሰማይ" ማለት ነው፦
88፥18 *"ወደ ሰማይም እንዴት ከፍ እንደ ተደረገች"*። وَإِلَى السَّمَاءِ كَيْفَ رُفِعَتْ

ይህቺ የቅርቢቱ ሰማይ የያዘችውን ኦዞን፣ አየር፣ በረዶ እና ዝናብ ነጥብ በነጥብ ኢንሻሏህ እናያለን፦

ነጥብ አንድ
"ኦዞን"
የቅርቢቱ ሰማይ የጋዝ ክምችት የያዘች ከባቢ አየር ስትሆን በውስጧ 78% ናይትሮጅን፣ 21% ኦክስጅን፣ 0.93% አርገን፣ 0.038% ካርቦን ዳይኦክሳይድ የተባሉ ንጥረ ነገሮችን ይዛለች። የከባቢ አየር የላይኛው ክፍል ማለትም ስትራቶስፌር ወደ ምድር ከሚመጣው አልትራቫዮሌት ጨረር ውስጥ 99% የሚሆነውን ውጦ የሚያስቀረውን “ኦዞን”ozone" የተባለ የኦክስጅን ቅንብር ይዟል፥ ይህንን ኦዞን አምላካችን አሏህ፦ "ቢናእ" بِنَاء ማለትም "ጣሪያ" ይለዋል፦
40፥64 *"አሏህ ያ ምድርን መርጊያ ሰማይንም "ጣሪያ" ያደረገላችሁ ነው*፡፡ اللَّهُ الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ الْأَرْضَ قَرَارًا وَالسَّمَاءَ بِنَاءً
2፥22 *"እርሱ ያ ለእናንተ ምድርን ምንጣፍ ሰማይንም "ጣሪያ" ያደረገ ነው"*። الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ الْأَرْضَ فِرَاشًا وَالسَّمَاءَ بِنَاءً

"ቢናእ" بِنَاء የሚለው ቃል "በና" بَنَى ማለትም "ገነባ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ግንብ" ማለት ነው፥ ይህ የተገነባው የኦዞን ሽፋን ሕይወት ያላቸውን ነገሮች በሙሉ ሰዎችን፣ እንስሳትን እና ፕላንክተን የሚባሉትን በባሕር ውስጥ የሚገኙ ጥቃቅን እጽዋትን ከጠፈር ከሚመጣ አደገኛ ጨረር ይከላከላል። አምላካችን አሏህ በግስ መደብ፦ "በነይና-ሃ" بَنَيْنَاهَا ማለትም "ገነባናት" ይለናል፦
51፥47 *"ሰማይንም በኀይል ገነባናት፥ እኛም በእርግጥ ቻዮች ነን"*፡፡ وَالسَّمَاءَ بَنَيْنَاهَا بِأَيْدٍ وَإِنَّا لَمُوسِعُونَ

ከዚህም በተጨማሪ ይህ ኦዞን በየዕለቱ በሚሊዮን በሚቆጠሩ ሚቲሮይድስ በተባሉ ከህዋ ከሚመጡ ተወርዋሪ አካላት እንዳንደበደብ ይከላከልልናል፥ እነዚህ ሚቲሮይድስ ከትንሽ ቅንጣት እስከ ትልቅ ድንጋይ የሚደርስ መጠን አላቸው። ደግነቱ ከእነዚህ ሚትሮይድስ መካከል አብዛኞቹ በከባቢ አየር ውስጥ ተቃጥለው ይጠፋሉ፥ በዚህ ጊዜ ኃይለኛ ብርሃን ስለሚፈጥሩ ሚቲዮር ወይም ተወርዋሪ ኮከቦች ተብለው ይጠራሉ። ይህን ኦዞን ለፕላኔታችን ይህንን ሁሉ የሚከላከል ከፍ የተደረገ እና የተገነባ ጣራያ ነው፦
52፥5 *"ከፍ በተደረገው ጣሪያም"*፡፡ وَالسَّقْفِ الْمَرْفُوعِ
21፥32 *"ሰማይንም የተጠበቀ ጣሪያም አደረግን"*፡፡ وَجَعَلْنَا السَّمَاءَ سَقْفًا مَّحْفُوظًا

"መሕፉዝ" مَّحْفُوظ ማለት "የተጠበቀ" ማለት ሲሆን ይህ ኦዞን ከላይ ያሉት አደጋዎች እንዳይደርሱብን የተጠበቀ ነው፦
ተፍሢሩል ጀላለይን 21፥32 *"ሰማይንም ጣሪያም አደረግን" ማለት ሰማይን ለምድር ልክ እንደ ቤት ጣሪያ ማለት ነው፥ "የተጠበቀ" ማለት ከሚወድ ነገር የተጠበቀ ነው"*። { وَجَعَلْنَا ٱلسَّمَآءَ سَقْفاً } للأرض كالسقف للبيت { مَّحْفُوظاً } عن الوقوع
ነጥብ ሁለት
"አየር"
አምላካችን አሏህ በሰማይ አየር ውስጥ ወፎች እንዳይወድቁ የሚይዛቸው “ኤሮዳይናሚክ”Aerodynamics” በሚባል ሕግ ነው፦
16፥79 *"ወደ በራሪዎች በሰማይ አየር ውስጥ ለመብረር የተገሩ ሲኾኑ ከመውደቅ አላህ እንጂ ሌላ የማይዛቸው ኾነው አይመለከቱምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተአምራቶች አሉ"*፡፡ أَلَمْ يَرَوْا إِلَى الطَّيْرِ مُسَخَّرَاتٍ فِي جَوِّ السَّمَاءِ مَا يُمْسِكُهُنَّ إِلَّا اللَّهُ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ

በእይታ ደረጃ በራሪ አእዋፋት በሰማይ አየር ሲበሩ የሚይዛቸው ምንም ነገር አለመታየቱ በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተአምር አለበት፥ ሰዎች ይህ እንዳይወድቁ የሚያደርጋቸውን ሕግ አይተው በ 1799 ድኅረ-ልደት ላይ የንስር ወፍ ንድፍ አይሮፕላን ሠርተዋል። በራሪዎችም ክንፎቻቸውን በአየር ላይ ያንሳፈፉ ኾነው ለአሏህ ተሥቢሕ ያረጋሉ፦
24፥41 *"አላህ በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ በራሪዎችም ክንፎቻቸውን በአየር ላይ ያንሳፈፉ ኾነው ለእርሱ የሚያጠሩ መኾናቸውን አላወቅህምን? ሁሉም ስግደቱን እና ማጥራቱን በእርግጥ ዐወቀ፥ አላህም የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው*፡፡ أَلَمْ تَرَ أَنَّ اللَّهَ يُسَبِّحُ لَهُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَالطَّيْرُ صَافَّاتٍ ۖ كُلٌّ قَدْ عَلِمَ صَلَاتَهُ وَتَسْبِيحَهُ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ بِمَا يَفْعَلُونَ

ነጥብ ሦስት
"በረዶ"
የሚያጅበው ነገር አንድ ሰው ከደመና በላይ በአይሮፕላን ላይ ሆኖ ሲጓዝ ደመናው ልክ እንደ ጋራዎች የተደራረበ ሆኖ ይታየዋል፦
24፥43 *"አላህ ደመናን የሚነዳ መኾኑን አላየህምን? ከዚያም ከፊሉን ከከፊሉ ያገናኛል፥ ከዚያም የተደራረበ ያደርገዋል፡፡ ዝናቡንም ከመካከሉ የሚወጣ ኾኖ ታየዋለህ፥ ከሰማይም በውስጧ ካሉት ጋራዎች በረዶን ያወርዳል"*፡፡ أَلَمْ تَرَ أَنَّ اللَّهَ يُزْجِي سَحَابًا ثُمَّ يُؤَلِّفُ بَيْنَهُ ثُمَّ يَجْعَلُهُ رُكَامًا فَتَرَى الْوَدْقَ يَخْرُجُ مِنْ خِلَالِهِ وَيُنَزِّلُ مِنَ السَّمَاءِ مِن جِبَالٍ فِيهَا مِن بَرَدٍ

የቅርቢቱ ሰማይ ውስጥ ካሉት የበረዶ ጋራዎች ቁርጥራጭ ቅሪት አለ፥ ይህም ቅሪት "ኪሰፍ" ይባላል፥ “ኪሰፍ” كِسَف ማለት “ቅሪት"fragment" ማለት ሲሆን ይህም ቁርጥራጭ ቅሪት ከደመናው በረዶዎች ሆኖ ሲወርድ የሰማይ ቁርጥራጮች ይባላል፦
30፥48 *አላህ ያ ነፋሶችን የሚልክ ነው፥ ደመናንም ይቀሰቅሳሉ፡፡ በሰማይ ላይም እንደሚሻ ይዘረጋዋል፥ ቁርጥራጮችም ያደርገዋል፡፡ ዝናቡንም ከደመናው መካከል ሲወጣ ታያለህ፥ በእርሱም ከባሮቹ የሚሻውን በለየ ጊዜ ወዲያውኑ እነርሱ ይደሰታሉ*፡፡ اللَّهُ الَّذِي يُرْسِلُ الرِّيَاحَ فَتُثِيرُ سَحَابًا فَيَبْسُطُهُ فِي السَّمَاءِ كَيْفَ يَشَاءُ وَيَجْعَلُهُ كِسَفًا فَتَرَى الْوَدْقَ يَخْرُجُ مِنْ خِلَالِهِ ۖ فَإِذَا أَصَابَ بِهِ مَن يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ إِذَا هُمْ يَسْتَبْشِرُونَ

ነጥብ አራት
"ዝናብ"
ባሕር ውስጥ፣ ውቂያኖስ ውስጥ፣ ኩሬ ውስጥ ያለው ውኃ ትነተ-ስርገት”evaporation” ሆኖ ወደ ሰማይ እንደሚመለስ በ 1905 ድኅረ-ልደት የታወቀ ሲሆን ቁርኣን ግን ውኃ ከታች ወደ ላይ ሰራጊ(ወጪ) እንደ ሆነ እና ሰማይም የወረደው ውኃ ሚመለስበት ቦታ እንደሆነ አበክሮ እና አዘክሮ ይናገራል፦
67፥30 *«አያችሁን? ውኃችሁ ሠራጊ ቢኾን ፈሳሺን ውኃ የሚያመጣላቸሁ ማን ነው?» በላቸው*፡፡ قُلْ أَرَأَيْتُمْ إِنْ أَصْبَحَ مَاؤُكُمْ غَوْرًا فَمَن يَأْتِيكُم بِمَاءٍ مَّعِينٍ
86፥11 *"የመመለስ ባለቤት በኾነችው ሰማይም እምላለሁ"*፡፡ وَالسَّمَاءِ ذَاتِ الرَّجْعِ

በቅርቢቱ ሰማይ ውስጥ የሚመለሰው ውኃ ደመና ይሠራና ተመልሶ ዝናብ ሆኖ ይዘንባል፦
6፥99 *"እርሱም ያ ከሰማይ ውኃን ያወረደ ነው"*፡፡ وَهُوَ الَّذِي أَنزَلَ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً
56፥68 *"ያንንም የምትጠጡትን ውኃ አየችሁን?* أَفَرَأَيْتُمُ الْمَاءَ الَّذِي تَشْرَبُونَ
56፥69 *"እናንተ ከደመናው አወረዳችሁትን? ወይስ እኛ አውራጆቹ ነን?* أَأَنتُمْ أَنزَلْتُمُوهُ مِنَ الْمُزْنِ أَمْ نَحْنُ الْمُنزِلُونَ

በቅርቢቱ ሰማይ ባሉት በአጽናፎች ውስጥ ያሉትን እነዚህ ተአምራት አምላካችን አሏህ ወደፊት እንደሚያሳየን እና እንደሚያሳውቀትን ቃል ገብቶልን ነበር፥ ዛሬ በዘመናችን ይህንን ማየታችን እና ማወቃችን መታደል ነው፦
27፥93 ምስጋናም ለአላህ ነው፡፡ *”ተዓምራቶቹን ወደፊት ያሳያችኋል፡፡ «ታውቁታላችሁ»* በላቸው፡፡ ጌታህም ከምትሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡ وَقُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ سَيُرِيكُمْ آيَاتِهِ فَتَعْرِفُونَهَا ۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَافِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ
41፥53 እርሱም ቁርኣን እውነት መኾኑ ለእነርሱ እስከሚገለፅላቸው ድረስ *”በአጽናፎቹ ውስጥ እና በራሳቸውም ውስጥ ያሉትን ተዓምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን*”፡፡ ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ መኾኑ አይበቃቸውምን? سَنُرِيهِمْ آيَاتِنَا فِي الْآفَاقِ وَفِي أَنفُسِهِمْ حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَهُمْ أَنَّهُ الْحَقُّ ۗ أَوَلَمْ يَكْفِ بِرَبِّكَ أَنَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም