ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.8K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ተፍሢር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

38፥29 ይህ ወደ አንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ *የአእምሮ ባለቤቶችም አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑ እና እንዲገሰጹ አወረድነው*፡፡ كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِّيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ أُولُو الْأَلْبَاب

የቁርኣንን መሠረትና ውቅር፣ ዋልታና ማገር፣ ምጥቀትና ርዝመት፣ ጥልቀትና ስፋት፣ ድርና ማግ በቅጡ ለማወቅና ለመረዳት ተደቡር ወሳኝ ነጥብ ነው፤ “ተደቡር” تَدَبُر ማለት “ማስተንተን” ማለት ነው፤ “ዱቡር” دُبُر ማለት “ጀርባ” ማለት ሲሆን ከቁርኣን ሑሩፍ በስተ-ጀርባ ያለውን ዕውቀት መረዳት ተደቡር ይባላል፤ አምላካችን አላህ ብሩክ የሆነው መጽሐፍ ቁርኣንን ወደ ነቢያችን”ﷺ” ያወረደው የአእምሮ ባለቤቶችም አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑ ነው፦
38፥29 ይህ ወደ አንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ *የአእምሮ ባለቤቶችም አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑ እና እንዲገሰጹ አወረድነው*፡፡ كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِّيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ أُولُو الْأَلْبَاب

“እንዲያስተነትኑ” ለሚለው ቃል የገባው “ሊየደበሩ” لِيَدَّبَّرُوا መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። የአእምሮ ባለቤቶችም አንቀጾቹን ለማስተንተን በተደቡር ይፈሥሩታል፤ “ተፍሢር” تَفْسِير የሚለው ቃል “ፈሠረ” فَسَرَ ማለትም “አብራራ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማብራሪያ”commentary” ማለት ነው፦
25፥33 በጥያቄም አይመጡብህም እውነተኛውን መልስ መልካምን *”ፍችም”* የምናመጣልህ ብንኾን እንጅ፡፡ وَلَا يَأْتُونَكَ بِمَثَلٍ إِلَّا جِئْنَاكَ بِالْحَقِّ وَأَحْسَنَ تَفْسِيرًا

“ፍች” ለሚለው ቃል የገባው “ተፍሢራ” تَفْسِيرًا ሲሆን የተፍሢር አንስታይ መደብ ነው፤ ቁርኣን በማስተንተን የሚፈሥሩ የአእምሮ ባለቤቶች በነጠላ “ሙፈሢር” مُفسّر‎ ይባላሉ፥ በብዜት ደግሞ “ሙፈሥሩን” مفسّرون‎ ይባላሉ። ይህ የሥነ-አፈታት ጥናት”hermeneutics” በአምስት አይነት አፈታት ይፈታል፤ እነርሱም፦ የዐውድ ሙግት፣ የቋንቋ ሙግት፣ የሰዋስው ሙግት፣ የተዛማች ሙግት እና የታሪክ ሙግት ይባላሉ። እስቲ እናስተንትን፦

ነጥብ አንድ
“የዐውድ ሙግት”
“የዐውድ ሙግት”contextual approach” ማለት አንቀጹ ላይ ያለውን እና ከአንቀጹ በፊትና በኃላ ያሉትን አናቅጽ በማስተንተን የአንቀጹን ምህዋር፣ አውታርና ምህዳር መረዳት ነው፤ ይህ “ሢያቅ” سیاق ማለትም “ዐውድ”context” በምሁራን ዘንድ “ስሙር ትርጓሜ” ወይም ፈቲሆት”exegesis” ይባላል፤ ለናሙና ያክል አንድ አንቀጽ እንመልከት፦
2፥79 *ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው*፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው፡፡ فَوَيْلٌۭ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ ٱلْكِتَٰبَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ ٱللَّهِ لِيَشْتَرُوا۟ بِهِۦ ثَمَنًۭا قَلِيلًۭا ۖ فَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ የአላህን ንግግር የሚሰሙ እና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ የሰው ንግግር በእጆቻቸው ፅፈው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ብለው የበረዙት እነማን እንደሆኑ ቁጥር 75 ላይ ዐውደ-ንባቡን ተከትለን ማግኘት እንችላለን፦
2፥75 *ከእነርሱ የኾኑ ጭፍሮች የአላህን ንግግር የሚሰሙ እና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ “የሚለውጡት” ሲኾኑ ለእናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?”* أَفَتَطْمَعُونَ أَن يُؤْمِنُوا لَكُمْ وَقَدْ كَانَ فَرِيقٌ مِّنْهُمْ يَسْمَعُونَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ يُحَرِّفُونَهُ مِن بَعْدِ مَا عَقَلُوهُ وَهُمْ يَعْلَمُون

ዐውደ-ንባቡ ለማለት ያልፈለገውን እጁን ጠምዝዞ እንዲህ ለማለት ነው ብሎ መፈሠር “ስሁት ትርጓሜ” ወይም “ሰጊጎት”Eisegesis” ይባላል፤ ይህ ቃሉ ላይ ያላለውን መሰግሰግ ነው። አብዛኛውን ሳይፈሩና ሳያፍሩ ሳይማሩና ሳይመራመሩ ስሁታን የሆኑ ታካቾች ይጠቀሙበታል። ስለ ዐውድ ሙግት በግርድፉ ይህ በቂ ነው፤ እስቲ የቋንቋ ሙግት እንመልከት፦
ነጥብ ሁለት
“የቋንቋ ሙግት”
“የቋንቋ ሙግት”linguistical approach” ማለት ቁርኣን በወረደበት ቋንቋ መረዳት ነው፤ አምላካችን አላህ ቁርኣንን ያወረደው በዐረቢኛ ነው፦
43፥3 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን አደረግነው*፡፡ إِنَّا جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
12፥2 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው*፡፡ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
13፥37 *እንደዚሁ በዐረብኛ የተነገረ ፍትሕ ሲኾን አወረድነው*፡፡ وَكَذَٰلِكَ أَنزَلْنَاهُ حُكْمًا عَرَبِيًّا

ዐረቢኛ ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ ሀሳብና ትርጉም አለው ማለት አይደለም፤ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጒም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው፤ ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው ሐሳብ መታየት ያለበት። ለናሙና ያክል አንዳንድ የቋንቋ ሙግት እንመልከት፦
“ፊ” فِي ማለት “ውስጥ” ማለት ቢሆንም “ቢ” بـِ ማለትም “በ” በሚል ይመጣል፦
2፥195 *”በ”አላህም መንገድ ለግሱ*፡፡ በእጆቻችሁም ነፍሶቻችሁን ወደ ጥፋት አትጣሉ፡፡ በጎ ሥራንም ሥሩ፤ አላህ በጎ ሠሪዎችን ይወዳልና፡፡ وَأَنفِقُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَلَا تُلْقُوا بِأَيْدِيكُمْ إِلَى التَّهْلُكَةِ ۛ وَأَحْسِنُوا ۛ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ

“ላ” َلَا ማለትም “አይደለም” ማለት ቢሆንም “ለቀድ” َلَقَدْ ማለትም “እርግጥ” በሚል ይመጣል፦
70፥40 *በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ “በእርግጥ” ቻዮች ነን*፡፡ فَلَا أُقْسِمُ بِرَبِّ الْمَشَارِقِ وَالْمَغَارِبِ إِنَّا لَقَادِرُونَ

“ማ” مَا ማለት “አይደለም” ማለት ቢሆንም “አለዚ” الَّذِي ማለትም “ያ” በሚል ይመጣል፦
2፥285 *መልክተኛው ከጌታው ወደ እርሱ በተወረደው አመነ፡፡ ምእምኖቹም እንደዚሁ አመኑ*፡፡ آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِ وَالْمُؤْمِنُون

“ወ” وَ ማለት “እና” ማለት ቢሆንም “ቢ” بـِ ማለትም “በ” በሚል ይመጣል፦
53፥1 *”በ”ኮከብ እምላለሁ በገባ ጊዜ*፡፡ وَالنَّجْمِ إِذَا هَوَىٰ

በሌጣው ይህ በቂ ነው፤ እስቲ የሰዋስው ሙግት እንመልከት፦

ነጥብ ሦስት
“የሰዋስው ሙግት”
“የሰዋስው ሙግት”grammatical approach” ማለት በቁርኣን ላይ ስም፣ ተውላጠ-ስም ለምሳሌ ባለቤት፣ ተሳቢ፣ አገናዛቢ፣ አመልካች፣ አንጻራዊ፣ ድርብ ተውላጠ-አስማት(ስሞች) መረዳት፣ ግሥ፣ ተውሳከ-ግሥ፣ መስተጻምር፣ መስተዋድድ መረዳትን ያጠቃልላል። ይህ እሳቤ “አል በላጋህ” ይባላል፤ “አል በላጋህ” البلاغة ማለት “የንግግር ስልት”rhetoric” ማለት ነው፤ ይህም በስም፣ በተውላጠ-ስም፣ በግስ፣ በገላጭ፣ በመስተዋድድ፣ በመስተጻምር ላይ የሚታየው የነጠላና የብዜት፣ የተባእታይና የአንስታይ፣ የተለዋዋጭ ቃላት የአነጋገር ስልት ነው፤ በግሪክ “ሬቶሪኮስ” ῥητορικός ይሉታል። ለናሙና ያክል የተወሰኑ ጥቅሶችን ማየት ይቻላል፦
36፥78 ለእኛም ምሳሌን አደረገልን፡፡ መፈጠሩንም ረሳ፡፡ *«አጥንቶችን እነርሱ የበሰበሱ ሲኾኑ ሕያው የሚያደርጋቸው ማነው?»* አለ፡፡ وَضَرَبَ لَنَا مَثَلًا وَنَسِيَ خَلْقَهُ ۖ قَالَ مَن يُحْيِي الْعِظَامَ وَهِيَ رَمِيمٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ዐዝም” عَظْم በነጠላ “አጥንት”bone” ማለት ነው፤ “ዒዛም” عِظَام ደግሞ የዐዝም ብዜት ሲሆን “አጥንቶች” ማለት ነው፤ እዚህ አንቀጽ ላይ አጥንቶች ለሚለው ስም ተክቶ የገባው ነጠላ አንስታይ ተውላጠ ስም በነጠላ “ሂየ” هِيَ እንጂ በብዜት “ሁነ” هُنَ አይደለም። በተጨማሪ፦
27፥88 *”ጋራዎችንም እርሷ” እንደ ደመና አስተላለፍ የምታልፍ ስትኾን የቆመች ናት ብለህ የምታስባት ሆና ታያታለህ*፡፡ የዚያን ነገሩን ሁሉ ያጠነከረውን የአላህን ጥበብ ተመልከት፡፡ እርሱ በምትሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡ وَتَرَى الْجِبَالَ تَحْسَبُهَا جَامِدَةً وَهِيَ تَمُرُّ مَرَّ السَّحَابِ ۚ صُنْعَ اللَّهِ الَّذِي أَتْقَنَ كُلَّ شَيْءٍ ۚ إِنَّهُ خَبِيرٌ بِمَا تَفْعَلُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ጀበል” جَبَلْ በነጠላ “ጋራ” ማለት ነው፤ “ጂባል” جِبَالْ ደግሞ የጀበል ብዜት ሲሆን “ጋራዎች” ማለት ነው፤ እዚህ አንቀጽ ላይ ጋራዎች ለሚለው ስም ተክቶ የገባው ነጠላ አንስታይ ተውላጠ ስም በነጠላ “ሂየ” هِيَ እንጂ በብዜት “ሁነ” هُنَ አይደለም። በወፍ በረር ለቅምሻ ያክል ይህ በቂ ነው፤ እስቲ የተዛማች ሙግት እንመልከት፦
ነጥብ አራት
“የተዛማች ሙግት”
“የተዛማች ሙግት””textual approach” ማለት ቁርኣንን በቁርኣን መፈሠር ነው፤ ቁርኣን አንድ እሳቤ በአንድ ሱራህ ላይ ያንጠለጥል እና በሌላ ሱራህ የተቀሩትን እሳቤ ይጨርሰዋል፤ ይህ የቁርኣን አንዱ ውበት ነው፦
39፥23 *አላህ ከዜና ሁሉ መልካምን፣ ተመሳሳይ፣ ተደጋጋሚ የኾነን መጽሐፍ አወረደ*፡፡ اللَّهُ نَزَّلَ أَحْسَنَ الْحَدِيثِ كِتَابًا مُّتَشَابِهًا مَّثَانِيَ تَقْشَعِرُّ

“ሙተሻቢህ” مُتَشَٰبِه ማለትም “ተመሳሳይ” ማለት ሲሆን አንቀጾችን አንዱ ሱራህ ላይ ተናግሮ ሌላ ሱራህ ላይ ተመሳሳዩን የተቀረውን ይናገራል፤ ይህ አላህ ከነቢያችን”ﷺ” በፊት የነበረውን ክስተትና መስተጋብር አንዱ ሱራህ ላይ ተናግሮ ያንጠለጥለው እና እንደገና በሌላ ሱራህ የተቀሩትን መሳ ለመሳ ይደግመዋል፤ ይህም እሳቤ “መሳኒይ” مَّثَانِى ማለትም “ተደጋጋሚ” ይባላል። ይህንን በተለያዩ ሱራዎች የተለያዩ ናሙናዎችን ማየት እንችላለን፤ ኢብራሂም ለመላእክቶቹ ያላቸው ሙሉ ንግግሩ፦ “ሰላም ያልታወቃችሁ ሕዝቦች ናችሁ፤ እኛ ከእናንተ ፈሪዎች ነን” ሲሆን አላህ ግን ይህንን የኢብራሂም ንግግር በአንድ ሱራህ ላይ አንጠልጥሎ የተቀረውን በሌላ ሱራህ ላይ ደግሞ ይጨርሰዋል፦
51፥24 *የተከበሩት የኢብራሂም እንግዶች ወሬ መጥቶሃልን?* هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ ضَيْفِ إِبْرَاهِيمَ الْمُكْرَمِينَ
51፥25 በእርሱ ላይ በገቡ እና ሰላም ባሉት ጊዜ አስታውስ፤ እርሱም፦ *«ሰላም ያልታወቃችሁ ሕዝቦች ናችሁ»* አላቸው፡፡ إِذْ دَخَلُوا عَلَيْهِ فَقَالُوا سَلَامًا ۖ قَالَ سَلَامٌ قَوْمٌ مُّنكَرُونَ
15፥51 *ከኢብራሂም እንግዶችም ወሬ ንገራቸው*፡፡ وَنَبِّئْهُمْ عَن ضَيْفِ إِبْرَاهِيمَ
15፥52 በእርሱ ላይ በገቡ እና ሰላም ባሉት ጊዜ የኾነውን አስታውስ፤ እርሱም፦ *«እኛ ከእናንተ ፈሪዎች ነን»* አላቸው፡፡ إِذْ دَخَلُوا عَلَيْهِ فَقَالُوا سَلَامًا قَالَ إِنَّا مِنكُمْ وَجِلُونَ

ሌላ ናሙና ሙሳ ለጌታው ያለው ሙሉ ንግግሩ፦ “ጌታዬ ሆይ! እኔ ከእነርሱ ነፍስን ገድያለሁ፣ ለእነርሱም በእኔ ላይ የደም ወንጀል አለ” ሲሆን አላህ ግን ይህንን የሙሳን ንግግር በአንድ ሱራህ ላይ አንጠልጥሎ የተቀረውን በሌላ ሱራህ ላይ ደግሞ ይጨርሰዋል፦
28፥33 ሙሳም አለ፦ *«ጌታዬ ሆይ! እኔ ከእነርሱ ነፍስን ገድያለሁ*፤ ስለዚህ እንዳይገድሉኝ እፈራለሁ፡፡ قَالَ رَبِّ إِنِّي قَتَلْتُ مِنْهُمْ نَفْسًا فَأَخَافُ أَن يَقْتُلُون
26፥14 ሙሳም አለ፦ *«ለእነርሱም በእኔ ላይ የደም ወንጀል አለ*፤ ስለዚህ እንዳይገድሉኝ እፈራለሁ። وَلَهُمْ عَلَيَّ ذَنبٌ فَأَخَافُ أَن يَقْتُلُونِ

ይህንን ሙግት ደርዝና ፈርጅ ባለው መልኩ ማስቀመጥ ይቻል ነበር፤ ነገር ግን ከላይ ያለው በቂ ነው፤ እስቲ የታሪክ ሙግት እንመልከት፦

ነጥብ አምስት
“የታሪክ ሙግት”
“የታሪክ ሙግት”historical approach” ማለት ቁርኣን የወረደበትን ዳራ መረዳት ነው፤ ይህ “ሠበቡ አን-ኑዙል” سَبَب النزول ወይም “አሥባቡ አን-ኑዙል” أسباب النزول ይባላል፤ “ሠበብ” سَبَب ማለት “ምክንያት” ማለት ሲሆን የሠበብ ብዙ ቁጥር ደግሞ “አሥባብ” أسباب ነው፤ “ኑዙል” نُزُل ማለት “አወራረድ” ማለት ነው።
ይህ የአወራረድ ምህዋር”circumstance of revelation” ነቢያችን”ﷺ” በተላኩበት ጊዜ ሰዎች በጥያቄ ሲመጡ አላህ “ይጠይቁሃል” “በላቸው” በማለት መልስ ይሰጣል፦
25፥33 *በጥያቄም አይመጡብህም እውነተኛውን መልስ፣ መልካምን ፍች የምናመጣልህ ብንኾን እንጅ*። وَلَا يَأْتُونَكَ بِمَثَلٍ إِلَّا جِئْنَاكَ بِالْحَقِّ وَأَحْسَنَ تَفْسِيرًا

ለምሳሌ አንድ አንቀጽ መመልከት ይቻላል፤ መዲና ላይ የነበሩ አይሁዳውያን፦ “ማንም የሚስቱን ሃፍረት በጀርባ በኩል ተራክቦ ያደረገ ልጁ ጠንጋራ ይሆናል” የሚል የተንጋደደ መረዳት ሲይዙ አምላካችን አላህ፦ “ሴቶቻችሁ ለእናንተ እርሻ ናቸው፡፡ እርሻችሁንም በፈለጋችሁት ኹኔታ ድረሱ” የሚለውን አንቀጽ አወረደ፦
2፥223 *”ሴቶቻችሁ ለእናንተ እርሻ ናቸው፡፡ እርሻችሁንም በፈለጋችሁት ኹኔታ ድረሱ”*፡፡ ለራሳችሁም መልካም ሥራን አስቀድሙ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ *”እናንተም ተገናኝዎቹ መኾናችሁን ዕወቁ”*፡፡ ምእመናንንም በገነት አብስር፡፡ نِسَاؤُكُمْ حَرْثٌ لَّكُمْ فَأْتُوا حَرْثَكُمْ أَنَّىٰ شِئْتُمْ ۖ وَقَدِّمُوا لِأَنفُسِكُمْ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ وَاعْلَمُوا أَنَّكُم مُّلَاقُوهُ ۗ وَبَشِّرِ الْمُؤْمِنِينَ
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3245
ከጃቢር ኢብኑ ሙንከዲር ሰምቶ እንደተረከው፦ *”አይሁዳውያን፦ “ማንም የሚስቱን ሃፍረት በጀርባ በኩል ተራክቦ ያደረገ ልጁ ጠንጋራ ይሆናል” አሉ፤ ከዚያም አላህ፦ “ሴቶቻችሁ ለእናንተ እርሻ ናቸው፡፡ እርሻችሁንም በፈለጋችሁት ኹኔታ ድረሱ” የሚለውን አንቀጽ አወረደ”*። عَنِ ابْنِ الْمُنْكَدِرِ، سَمِعَ جَابِرًا، يَقُولُ كَانَتِ الْيَهُودُ تَقُولُ مَنْ أَتَى امْرَأَتَهُ فِي قُبُلِهَا مِنْ دُبُرِهَا كَانَ الْوَلَدُ أَحْوَلَ فَنَزَلَتْ ‏:‏ ‏(‏نِسَاؤُكُمْ حَرْثٌ لَكُمْ فَأْتُوا حَرْثَكُمْ أَنَّى شِئْتُمْ ‏)‏

ይህ ሙግት የቁርኣን መቸት”Setting” ማለትም “መቼ? እና የት?” እንደወረደ የምናጠናበትም ጭምር ነው፤ ይህ የሰበቡ አን-ኑዙል አፈሣሠር ነቢያችን”ﷺ” እና ሶሓባዎች በአስተላለፉት መረዳት “አት-ተፍሢር ቢል መእሱር” التفسير بالمأثور‎ ወይም “አት-ተፍሢር ቢ አር-ሪዋያህ” التفسير بالرواية‎ ይባላል። በኢብኑ ጀሪር አጥ-ጠበሪ የተዘጋጀው ተፍሢሩል ጃሚል በያን እና በኢብኑ ከሲር የተዘጋጀው ተፍሢሩል ቁርኣን አል-ዚዙም በዚህ አፈሳሰር ተመራጭ ነው።
ሌላው ከላይ የዐውድ፣ የቋንቋ፣ የሰዋስው እና የተዛማች ሙግት አፈሣሠር “ተፍሢር ቢ አር-ረእይ” التفسير بالرأي‎ ወይም “አት-ተፍሢር ቢ አድ-ዲራያህ” التفسير بالدراية‎ ይባላል፤ ይህ በፊቅህ “ኢጅቲሀድ” اجتهاد‌‎ ይወጅብበታል፤ የኢጅቲሀድ ምሁር ደግሞ “ሙጅተሂድ” مجتهد‎ ይባላል። በአል-በይዷዊይ የተዘጋጀው አንዋረል ተንዚል እና በኢማም ፈኽሩል ዲኑል ራዚ የተዘጋጀው መፋቲሑል ገይብ በዚህ አፈሣሠር ተመራጭ ነው።
በተረፈ ከአህለል ኪታብ የሚገኝ ኢሥራዒልያት አፈሣሠር መረጃ መሆን ይችላል እንጂ ማስረጃ አይሆንም። የአላህ ንግግር በዐሊም ትንተና ተደግፎ አይቆምም ተገፍቶ አይወድቅም። ምሰሶ በሰንበሌጥ አይደገፍም አይወድቅም። የአላህ ንግግር ምሰሶ ነው፥ የዐሊም ትንተና ሰንበሌጥ ነው። አምላካችን አላህ ቁርኣንን ከሚያስተነትኑ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የሡናህ አፅዋማት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

53፥4 *እርሱ ንግግሩ የሚወረድ ወሕይ እንጅ ሌላ አይደለም*፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْيٌ يُوحَىٰ

“ሶውም” صَوْم የሚለው ቃል "ሷመ" صَامَ‎ ማለትም "ፆመ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ፆም" ማለት ነው፥ "ሲያም" صِيَام ለሶውም ተለዋዋጭ ቃል ነው። አንድ ሰው ምንም ነገር ሳይቀምስ ሲቀር “ፆሙን ዋለ” ይባላል፥ ያ ማለት ከምግብና ከመጠጥ “ተከለከለ” አሊያም “ተቆጠበ” ማለት ነው። ጾም ማለት “መከልከል” ወይም “መቆጠብ” መሆኑን የምናውቀው የአለመናገር ተቃራኒ የሆነውን “ዝምታን” ለማመልከት “ሶውም” صَوْم የሚለው ቃል አገልግሎት ላይ ውሏል፦
19፥26 «ብይም፣ ጠጭም፣ ተደሰችም፡፡ እኔ ለአልረሕማን *”ዝምታን ተስያለሁ”*፤ ዛሬም ሰውን በፍጹም አላነጋግርም» በይ፡፡ فَكُلِي وَاشْرَبِي وَقَرِّي عَيْنًا ۖ فَإِمَّا تَرَيِنَّ مِنَ الْبَشَرِ أَحَدًا فَقُولِي إِنِّي نَذَرْتُ لِلرَّحْمَـٰنِ صَوْمًا فَلَنْ أُكَلِّمَ الْيَوْمَ إِنسِيًّا

ዋናው ጾም ረመዷን ላይ የሚጾም ሲሆን ይህንን ጾም መጾም ፈርድ ነው፥ "ፈርድ" فَرْض የሚለው ቃል “ፈረደ” فَرَضَ ማለትም “ተገደደ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ግዴታ” ወይም "የታዘዘ" ማለት ነው። ነገር ግን በነቢያችን"ﷺ" የተወደዱ የሡና አፅዋማት “ሙሥተሐብ” ናቸው፥ "ሙሥተሐብ" مُسْتَحَبّ‎ ማለትም “የተወደደ” ማለት ነው። እነዚህን አፅዋማት በግርድፉ እና በሌጣው እንይ፦

"ሙሐረም"
"ሙሐረም" مُحَرَّمُ የመጀመሪያው ወር ሲሆን አንድ ሙሥሊም በዚህ ወር በፈለገው ቀን ጀምሮ የፈለገውን ቀን ያህል መጾም ይችላል፥ ይህ ጾም ምርጥ ጾም ተብሏል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 13, ሐዲስ 261
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአሏህ መልዕክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ከረመዷን በኋላ ምርጥ ፆም የአላህን ወር ሙሐረምን መፆም ነው፡፡ ከግዴታ ሶላቶች ቀጥሎ ምርጥ ሰላት የሌሊት ሶላት ነው"*፡፡ الْحِمْيَرِيِّ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، - رضى الله عنه - قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ أَفْضَلُ الصِّيَامِ بَعْدَ رَمَضَانَ شَهْرُ اللَّهِ الْمُحَرَّمُ وَأَفْضَلُ الصَّلاَةِ بَعْدَ الْفَرِيضَةِ صَلاَةُ اللَّيْلِ ‏"‏ ‏.‏

"ሻዕባን"
"ሸዕባን" شَعْبَان ስምንተኛው ወር ሲሆን አንድ ሙሥሊም በዚህ ወር በፈለገው ቀን ጀምሮ የፈለገውን ቀን ያህል መጾም ይችላል፥ ይህም ጾም የነቢያችን"ﷺ" ሡናህ ነው፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 14, ሐዲስ 119
እሜቴ ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"የተወደደ ወር በአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" የተባለለት በሻዕባን መጾም ነው፥ ከዚያም ረመዷንን ይፆሙ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، تَقُولُ كَانَ أَحَبَّ الشُّهُورِ إِلَى رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أَنْ يَصُومَهُ شَعْبَانُ ثُمَّ يَصِلُهُ بِرَمَضَانَ ‏.‏

"ሲያሙ ዳውድ"
"ሲያሙ ዳውድ" صِيَامُ دَاوُد ማለት "የዳውድ ጾም" ማለት ሲሆን ነቢዩሏህ ዳውድ አንድ ቀን ይፆም ነበር፥ አንድ ቀን ደግሞ ይፈታ ነበር። ይህም ፆም በነቢያችን"ﷺ" "ምርጥ ፆም" የተባለለት ሡናህ ነው፦
ሡነን ነሣኢ መጽሐፍ 22 , ሐዲስ 299
ዐደሏህ ኢብኑ ዐምሪው እንደተረከው፦ "የአሏህ መልዕክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ከፆሞች ምርጥ ፆም የዳውድ"ዐለይሂ አሥ-ሠላም" ፆም ነው፡፡ አንድ ቀን ይፆም ነበር፥ አንድ ቀን ደግሞ ይፈታ ነበር"*፡፡ عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ أَفْضَلُ الصِّيَامِ صِيَامُ دَاوُدَ عَلَيْهِ السَّلاَمُ كَانَ يَصُومُ يَوْمًا وَيُفْطِرُ يَوْمًا ‏"‏ ‏
"አል ኢስነይን ወል ኸሚሥ"
"አል ኢስነይን ወል ኸሚሥ" الاِثْنَيْنِ وَالْخَمِيس ማለት "ሰኞ እና ሐሙስ" ማለት ነው። ሥራዎች ሰኞ እና ሐሙስ ወደ አላህ ይቀርባሉ፥ በተጨማሪም ይቅር የተባባሉ ሙሥሊሞችን አሏህ ይቅር የሚልበት ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 66
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ሥራዎች ሰኞ እና ሐሙስ ወደ አላህ ይቀርባሉ፥ ሥራዬ ፆመኛ ሆኜ እንዲቀርብልኝ እወዳለሁኝ”*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ تُعْرَضُ الأَعْمَالُ يَوْمَ الاِثْنَيْنِ وَالْخَمِيسِ فَأُحِبُّ أَنْ يُعْرَضَ عَمَلِي وَأَنَا صَائِم
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 7, ሐዲስ 1812
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “ነቢዩ”ﷺ” ሰኞ እና ሐሙስ ይፆሙ ነበር። እንዲህም ተባለ፦ *”የአላህ መልክተኛ”ﷺ” ሆይ! ለምን ሰኞ እና ሐሙስ ይፆማሉ? እርሳቸውም፦ “ሰኞ እና ሐሙስ አላህ ሁሉንም ሙሥሊም ይቅር ይላል ከተቷቷዉት ሁለት በስተቀር። እርሳቸውም፦ “እነዚህ ሁለቱን እስኪስማሙ ድረስ ተዋቸው”*። عَنْ سُهَيْلِ بْنِ أَبِي صَالِحٍ، عَنْ أَبِيهِ، عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ كَانَ يَصُومُ الاِثْنَيْنِ وَالْخَمِيسَ ‏.‏ فَقِيلَ يَا رَسُولَ اللَّهِ إِنَّكَ تَصُومُ يَوْمَ الاِثْنَيْنِ وَالْخَمِيسِ فَقَالَ ‏ “‏ إِنَّ يَوْمَ الاِثْنَيْنِ وَالْخَمِيسِ يَغْفِرُ اللَّهُ فِيهِمَا لِكُلِّ مُسْلِمٍ إِلاَّ مُهْتَجِرَيْنِ يَقُولُ دَعْهُمَا حَتَّى يَصْطَلِحَا ‏”‏ ‏

"አያሙል ቢድ"
"የውም" يَوْم ማለት በነጠላ "ቀን" ማለት ነው፥ የየውም ብዙ ቁጥር ደግሞ "አያም" أَيَّامٍ ሲሆን "ቀናት" ማለት ነው። "አል-ቢድ" الْبِيضِ ማለት "አስኳል" ማለት ነው። በጥቅሉ "አያሙል ቢድ" أَيَّامُ الْبِيضِ ማለት "የቀናት አስኳል" ማለት ነው፥ በጨረቃ አቆጣጠር ወር በገባ አሥራ ሦስተኛ፣ አሥራ አራተኛው እና አሥራ አምስተኛው ቀናት "አያሙል ቢድ" ይባላሉ፥ በእነዚህ ቀናት ወይም በወር ሦስት ቀናትን የፆመ አጅሩ ወሩን ሙሉ እንደፆመ ነው፦
ሡነን ነሣኢ መጽሐፍ 22 , ሐዲስ 331
ጀሪር ኢብኑ ዐብደሏህ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ከወር ሁሉ ለሦስት ቀናት መፆም የሁልጊዜ መጾም ነው፥ የአያሙል ቢድ ጮራዎች አሥራ ሦስተኛ፣ አሥራ አራተኛው እና አሥራ አምስተኛው ቀናት ናቸው"*። عَنْ جَرِيرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ صِيَامُ ثَلاَثَةِ أَيَّامٍ مِنْ كُلِّ شَهْرٍ صِيَامُ الدَّهْرِ وَأَيَّامُ الْبِيضِ صَبِيحَةَ ثَلاَثَ عَشْرَةَ وَأَرْبَعَ عَشْرَةَ وَخَمْسَ عَشْرَةَ ‏"‏

"ዓሹራእ"
ከሙሐረም ወር ውስጥ አሥረኛው ቀን በላጭ ቀን ነው፤ ይህ ዐሥረኛው ቀን “ዓሹራእ” ይባላል፥ “ዓሹራእ” عَاشُورَاء‎ የሚለው ቃል “ዐሽር” عَشْرٍ ማለትም “ዐሥር” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን “ዐሥረኛ” ማለት ነው። የዓሹራእ ቀን መጾም ያለፈውን አንድ ዓመት ወንጀል ከአላህ ያስተሰርያል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 7, ሐዲስ 1810
አቢ ቀታዳህ እንዳስተላለፉት፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ *”የዓሹራእ ቀን መጾም ያለፈውን አንድ ዓመት ወንጀል ከአላህ ያስተሰርያል”*። عَنْ أَبِي قَتَادَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ صِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ إِنِّي أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ

"ሸዋል"
"ሸዋል" شَوَّال አሥረኛው ወር ሲሆን በሸዋል ወር ስድስቱን ተከታታይ ቀናት መፆም የቻለ ወይም በወሩ ውስጥ ስድስት ቀናት የፆመ አጅሩ ከረመዷን ጋር ዓመቱን ሙሉ እንደጾመ ይቆጠራል፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 78
አቢ አዩብ እንደተረከው፦ “ነቢዩ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *ማንም ረመዷንን የጾመ ከዚያም ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን ያስከተለ ዋጋው ዓመቱን ሙሉ እንደጾመ ነው”*። عَنْ أَبِي أَيُّوبَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ مَنْ صَامَ رَمَضَانَ ثُمَّ أَتْبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ فَذَلِكَ صِيَامُ الدَّهْرِ

"ዐረፋህ"
"ዐረፋህ" عَرَفَةَ ከ12ኛ ወር ከዙል-ሒጃህ የአሥረኛው ቀን ዋዜማ ዘጠነኛው ቀን መጾም ያለፈውን ዓመት እና የቀጣዩን ዓመት ኃጢአት ያስተሰርያል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 7 , ሐዲስ 1802
አቢ ቀታዳህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልዕክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"የዐረፋ ቀን ፆም ያለፈውን ዓመት እና የቀጣዩን ዓመት ኃጢአት እንደሚያብስ ከአሏህ እከጅላለሁ"*። عَنْ أَبِي قَتَادَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ إِنِّي أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ وَالَّتِي بَعْدَهُ ‏"‏ ‏.‏

ነቢያችን”ﷺ” በዐቂዳህ እና በፊቅህ ነጥብ ላይ የሚናገሩት ንግግር ሁሉ ወሕይ ነው፥ “ወሕይ” وَحْي የሚለው ቃል “አውሓ” أَوْحَىٰٓ ማለትም “ገለጠ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ግልጠተ-መለኮት" ማለት ነው። በዐቂዳህ እና በፊቅህ ነጥብ ላይ የሚናገሩት ንግግር ሁሉ ከአሏህ ዘንድ የተገለጠ መገለጥ ነው፦
53፥3 *ከልብ ወለድም አይናገርም*፡፡ وَمَا يَنطِقُ عَنِ الْهَوَىٰ
53፥4 *እርሱ ንግግሩ የሚወረድ ወሕይ እንጅ ሌላ አይደለም*፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْيٌ يُوحَىٰ

ከላይ የተዘረዘሩት የሡናህ አፅዋማት ከነቢያችን"ﷺ" ንግግር የተገኘ እንጂ ልክ እንደ ፍትሐ-ነገሥት ከጊዜ በኃላ በስምምነት ከልብ ወለድ የተደነገገ አይደለም። አምላካችን አሏህ የመልእክተኛው ሡናህ የምንከተል ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሦስት አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥171 *”እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ”*፡፡ .. *”«ሦስት ናቸው» አትበሉም”*፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ *”አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው”*፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ ۖ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ ۖ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ ۚ ٱنتَهُوا۟ خَيْرًۭا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا ٱللَّهُ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ سُبْحَٰنَهُۥٓ أَن يَكُونَ لَهُۥ وَلَدٌۭ ۘ لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًۭا

“ትራይ-ቴእይዝም” τριθεισμός ማለት የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “ትራይ” τρι “ሦስት” እና “ቴኦስ” θεισμός “አምላክ” የሚል ውቅር ነው፤ ትርጉሙም “ሦስት አምላክ”triple deity” ማለት ነው፤ ይህ “አምላክ ሥስት ነው””tritheism” የሚባለው ትምህርት ከአንድ አምላክ ትምህርት ጋር ይጋጫል፤ “ሞኖ-ቴእይዝም” μονοθεϊσμός ማለት የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “ሞኖ” μονο “ብቸኛ” እና “ቴኦስ” θεισμός “አምላክ” የሚል ውቅር ነው፤ ትርጉሙም “ብቸኛ አንድ አምላክ”only one deity” ማለት ነው፤ “ሥላሴ” ማለት “ሥሉስ” ማለትም “ሦስት” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን “ሦስትነት” ማለት ነው፤ አምላክ በስም፣ በግብር፣ በአካል ሦስት ሲሆን በህላዌ፣ በኑባሬ፣ በመለኮት አንድ ነው የሚለው ተስተምህሮት “ሥላሴ” ይባላል፤ “እንዘ አሐዱ ሠለስቱ ወእንዘ ሠለስቱ አሐዱ፤ ይሤለሱ በአካላት ወይትዋሐዱ በመለኮት” ትርጉሙ፦ “አንድ ሲሆን ሦስት ደግሞ ሦስት ሲሆኑ አንድ፤ በአካል ሦስት ሲሆን በመለኮት አንድ ናቸው” ምንጭ የዘወትር ፀሎት። አምላክ አንድም ሦስትም ትምህርት “Triune God” ይባላል፤ “እግዚአብሔር ሦስት አካል አንድ ባህርይ ነው” ምንጭ ሰይፈ ሥላሴ ቁጥር 5 ።
ሦስት ፊት እና ሦስት መልክ ያላቸው እነዚህ ሥስት አካላት፦
1ኛ. “ሆ ቴኦስ ሆ ፓቴራስ” Ο Θεός ο πατέρας ማለትም “እግዚአብሔር አብ”God the father”
2ኛ. “ሆ ቴኦስ ሆ ሁዎስ” Ο Θεός ο γιος ማለትም “እግዚአብሔር ወልድ”God the son”
3ኛ. “ሆ ቴኦስ ሆ ኑማቶ ሃጂኦን” Ο Θεός ο Πνεῦμα τὸ Ἅγιον ማለትም “እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ”God the holy spirit” ናቸው።
አምላካችን አላህ “ሦስት ናቸው” አትበሉም፤ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናል፤ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው በማለት ሥስትነትን ይቃወማል፦
4፥171 *”እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ”*፡፡ .. *”«ሦስት ናቸው» አትበሉም”*፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ *”አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው”*፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ ۖ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ ۖ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ ۚ ٱنتَهُوا۟ خَيْرًۭا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا ٱللَّهُ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ سُبْحَٰنَهُۥٓ أَن يَكُونَ لَهُۥ وَلَدٌۭ ۘ لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًۭا

ነጥብ አንድ
“አማልክት”
ዶክተር ሻቢር፣ ዶክተር ቢላል፣ ዶክተር ዛኪር ካልክ በኃላ አይ አንድ ዶክተር ነው ብትል ቂልነት ነው፤ እግዚአብሔር አብ፣ እግዚአብሔር ወልድ፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ካልክ በኃላ አንድ እግዚአብሔር ማለት ቂልነት ነው፤ እነዚህ ሥስት አካሎች “ጌቶች” ይባላሉ፤ “አጋዕዝተ-ዓለም ሥላሴ” ማለት “የዓለም ጌቶች ሥላሴ” ማለት ነው፤ “እግዚእ” በነጠላ “ጌታ” ማለት ሲሆን “አጋዕዝት” ማለት ደግሞ በብዜት “ጌቶች” ማለት ነው፤ ስለዚህ ሥላሴ ሦስት ጌቶች ናቸው፤ እነዚህ ሥስት አካሎች “አምላኮች” ወይም “አማልክት” ናቸው፤ “ኤሎሂም” אלהים ማለት ብዜት ሲሆን “አምላኮች” ወይም “አማልክት” ማለት ሲሆን “ኤሎሃ” אלוהּ ደግሞ “አምላክ” ማለት ነው፤ “ኤሎሂም” ሥላሴን ካመለከተ ሥላሴ ሥስት አምላክ ናቸው፤ ሥላሴን “ፈጣሪዎች” ማለታችሁ በራሱ ይህንን ያሳያል፦
“ሥሉስ ቅዱስ ሆይ! የአደምና የሔዋን *”ፈጣሪዎቻቸው እንደመሆናችሁ”* መልክአ ሥላሴ ቁጥር 39

አንድ ሰው ሦስት ማንነቶች ካሉት ያ ሰው ሦስት ሰዎች እንጂ አንድ ሰው አይባልም፤ ምክንያቱም አንድ ሰው ያሰኘው ማንነቱ ነውና፤ በተመሳሳይ አንድ አምላክ ሦስት ማንነቶች ካሉት ያ አምላክ ሦስት አምላክ እንጂ አንድ አምላክ አይባልም፤ ምክንያቱም አንድ አምላክ ያሰኘው ማንነቱ ነውና፤ “አካል” ማለት “ማንነት” ሲሆን “ህላዌ” ደግሞ “ምንነት” ማለት ነው፤ ሥላሴ በማንነት ሦስት ሲሆኑ በምንነት አንድ ናቸው፤ ሰዎች በማንነት ሰባት ቢሊዮን ሲሆን በምንነት ግን አንድ ናቸው፤ ምክንያቱም ሁሉ ምነታቸው ሰው ሰለሆነ። በሁለቱ ማለትም በሰማያትና በምድር ውስጥ ከአንዱ ማንነት ከአላህ ሌላ አማልክት የሆኑ ማንነቶች በነበሩ ኖሮ በተበላሹ ነበር፤ በፈጠረው ነገር በተለየ ነበር፤ ከፊላቸውም በከፊሉ ለይ በላቀ ነበር፤ የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ፦
21፥22 በሁለቱ ውስጥ *”ከአላህ ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ በተበላሹ ነበር”*፡፡ የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡ لَوْ كَانَ فِيهِمَآ ءَالِهَةٌ إِلَّا ٱللَّهُ لَفَسَدَتَا ۚ فَسُبْحَٰنَ ٱللَّهِ رَبِّ ٱلْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ
23፥91 አላህ ምንም ልጅን አልያዘም፤ *ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ ያን ጊዜ አምላክ ሁሉ በፈጠረው ነገር በተለየ ነበር፡፡ ከፊላቸውም በከፊሉ ለይ በላቀ ነበር*፡፡ አላህ “ከሚመጥኑት” ሁሉ ጠራ፡፡ مَا ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ مِن وَلَدٍۢ وَمَا كَانَ مَعَهُۥ مِنْ إِلَٰهٍ ۚ إِذًۭا لَّذَهَبَ كُلُّ إِلَٰهٍۭ بِمَا خَلَقَ وَلَعَلَا بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍۢ ۚ سُبْحَٰنَ ٱللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ

“ከሚሉት” ወይም ‘ከሚመጥኑት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የሲፉነ” يَصِفُونَ ማለት “ባህርይ ካደረጉለት”they attribute” ነገር ሁሉ የጠራ ነው።
ነጥብ ሁለት
“አካላት”
“አካል” ሲባል “ማንነት” ተብሎ መቀመጥ ሲኖርበት ነገር ግን መልክአ-ሥላሴ የተባለው መጽሐፍ “አካል” ማለት “ተክለ-ሰውነት”body” አድርጎ ሥላሴ “ደም” “ወርች” “ጎን” “ከርስ” “ኩላሊት” “ወገብ” “አብራክ” “ተረከዝ” “ጫማ” “ጥፍር” “ጣት” እንዳላቸው ይናገራል፤ ይህንን ጉድ እስቲ እንይ፦
“ደም”
“ሥሉስ ቅዱስ ሆይ! *ስርየተ ደማችሁ* ስርየተ ኃጢኣት ነውና የነፍሴን ቤት መቃን በስርየት *”ደማችሁ”* እርጩት።”
“ወርች”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! የአዳምን ወርች ላጸና መለኮታዊ *ወርቾቻችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“ጎን”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! የወርቅ አስፈላጊያቸው ላይደለ መለኮታዊ *ጎኖቻችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“ከርስ”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! የፍጡራንን ሆድ ለፈጠረ ለማይመረመር *ከርሳችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“ኩላሊት”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! በህላዌ አካል ትክክል ለሚሆኑ *ኩላሊታችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“ወገብ”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! መታጠቂያው የቸርነት ሰቅ ለሆነው *ወገባችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“አብራክ”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! የፍጥረት ሁሉ አብራክ ለሚያሰግድ *አብራካችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“ተረከዝ”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! ብርሃናት ለተጎናፀፈው *ተረከዛችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“ጫማ”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! ለሚራመድ *ጫማችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“ጥፍር”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! *ከጥፍሮቻችሁ* ጋር ያለመነጣጠል ተባብረው ተመሳስለው ላሉ *ጣቶቻችሁ* ሰላምታ ይገባል።”

ሌላው ይሁን እሺ “ከርስ” እና “አብራክ” ምን ያረግላቸዋል? ከርስ እኮ የምግብ ማከማቻ ሆድ ነው፤ ይበላሉን? አብራክ እኮ የዘር ከረጢት ነው፤ ይወልዳሉን? እስቲ በባይብል አምላክ ሦስት አካል ነው ወይም ሦስት አካል አለው የሚል ጥቅስ ይፈለግ፤ እስቲ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ናቸው የሚል ጥቅስ ይፈለግ፤ የለም፤ አምላክ አንድ “ነው” እንጂ “ናቸው” የሚል የለም፦
ማርቆስ 12፥29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፦ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ *”ነው”*፥

“እርሱ” “አንተ” “አለ” እና “ነው” ተብሎ የሚመለክ አምላክ እንጂ “እነርሱ” “እናንተ” “አሉ” እና “ናቸው” ተብሎ የሚመለክ አምላክ ባይብል ላይ ሽታው እንኳን የለም፤ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል የሆነ ቃል በመጽሐፋችሁ “አምላክ አንድ ብቻ ነው” የሚል ነው፦
ዘዳግም 6፥4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ *”አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው”*፤
ዘዳግም 6፥6 እኔም ዛሬ አንተን *”የማዝዘውን ይህን ቃል”* በልብህ ያዝ።
ዘዳግም 4:2 *”እኔ ያዘዝኋችሁን”* የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን *”ትእዛዝ ትጠብቃላችሁ እንጂ ባዘዝኋችሁ ቃል ላይ አትጨምሩም፥ ከእርሱም አታጎድሉም”*።

“እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው” ብሎ ያዘዘውን ቃል በልብህ ያዝ፤ ይህ ታላቁና ፊተኛይቱ ትእዛዝ አንድ በሚለው ላይ ሁለት ወይም ሶስት አሊያ ከዚያ በላይ አትጨምር፤ አንድ ከሚለው ላይ ካጎደልክ የለም ማለት ነውና አትቀንስ ግን አንድ የሚለውን ብቻ ያዝ፤ ትክክል ወደ ኾነች “አንድ ብቻ ነው” ወደሚለው ቃል ኑ፦
3፥64 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! *”በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ እርሷም አላህን እንጅ ሌላን ላናመልክ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው”*፤ በላቸው፡፡ እምቢ ቢሉም፡- እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡ قُلْ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ تَعَالَوْا۟ إِلَىٰ كَلِمَةٍۢ سَوَآءٍۭ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا ٱللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِۦ شَيْـًۭٔا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًۭا مِّن دُونِ ٱللَّهِ ۚ فَإِن تَوَلَّوْا۟ فَقُولُوا۟ ٱشْهَدُوا۟ بِأَنَّا مُسْلِمُونَ

አል-ሓምዱሊሏሂ ረቢል ዓለሚን ዐላ ኒዕመተል ኢሥላም!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሁለት አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥51 አላህም አለ፦ *"ሁለት አማልክትን አትያዙ"*፡፡ እርሱ *"አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እኔንም ብቻ ፍሩ"*፡፡ وَقَالَ ٱللَّهُ لَا تَتَّخِذُوٓا۟ إِلَٰهَيْنِ ٱثْنَيْنِ ۖ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَإِيَّٰىَ فَٱرْهَبُونِ

"ሸይእ" شَىْء ማለት "ነገር"thing" ማለት ሲሆን ማንኛውንም ነገር ሁሉ የፈጠረ አንድ አምላክ አላህ ብቻ ነው፦
39:62 አላህ *"የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው"*። እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው። ٱللَّهُ خَٰلِقُ كُلِّ شَىْءٍۢ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍۢ وَكِيلٌۭ
40:62 ይሃችሁ፣ ጌታችሁ አላህ ነው፤ *"የነገር ሁሉ ፈጣሪ ነው"*፤ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ታዲያ ከእምነት ወዴት ትመለሳላችሁ?። ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمْ خَٰلِقُ كُلِّ شَىْءٍۢ لَّآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ فَأَنَّىٰ تُؤْفَكُونَ
6:102 ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ *"ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው"*፡፡ ስለዚህ አምልኩት፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ بَدِيعُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۖ أَنَّىٰ يَكُونُ لَهُۥ وَلَدٌۭ وَلَمْ تَكُن لَّهُۥ صَٰحِبَةٌۭ ۖ وَخَلَقَ كُلَّ شَىْءٍۢ ۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌۭ
13፥16 *«አላህ ሁሉን ነገር ፈጣሪ ነው"*፡፡ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው» በል፡፡ قُلِ ٱللَّهُ خَٰلِقُ كُلِّ شَىْءٍۢ وَهُوَ ٱلْوَٰحِدُ ٱلْقَهَّٰرُ

ያ ማለት ከነገር ሁሉ ተቃራኒ ነገርን የፈጠረው አላህ ብቻ ነው፤ ለምሳሌ ሰማይንና ምድርን፣ ብርሃንንና ጨለማን፣ ሞትና ህይወትን፣ ወንድና ሴትን ሁሉ ማለት ነው፦
51፥49 ትገነዘቡም ዘንድ *"ከነገሩ ሁሉ ሁለት ተቃራኒ ዓይነትን ፈጠርን"*፡፡ وَمِن كُلِّ شَىْءٍ خَلَقْنَا زَوْجَيْنِ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
6፥1 ምስጋና ለዚያ *"ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረው፤ ጨለማዎችንና ብርሃንንም"* ላደረገው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ وَجَعَلَ ٱلظُّلُمَٰتِ وَٱلنُّورَ
67፥1 ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መኾኑን ሊሞክራችሁ *"ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ ነው"*፡፡ እርሱም አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلْمَوْتَ وَٱلْحَيَوٰةَ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًۭا ۚ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْغَفُورُ
75፥39 ከእርሱም *"ሁለት ዓይነቶችን ወንድና ሴትን አደረገ"*፡፡ فَجَعَلَ مِنْهُ ٱلزَّوْجَيْنِ ٱلذَّكَرَ وَٱلْأُنثَىٰٓ

ይህ ሆኖ ሳለ ግን ዞራስተርያን ወይም ኖስቲዝም፦ "ሰማይን፣ ብርሃንን፣ ህይወትን፣ ወንድን የፈጠረው "አሁራ" የተባለው አምላክ ነው ሲሉ፤ በተቃራኒው ምድርን፣ ጨለማን፣ ሞት፣ ሴትን የፈጠረው "አንግራ" የተባለው አምላክ ነው ብለው ሁለት አምላክ ያመልካሉ፤ ይህ የሁለት አምላክ ጥምረት ትምህርት "ዱአ-ቴእይዝም"duotheism" ይባላል፤ "ዱአ-ቴእይዝም" δυοθεισμός ማለት የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ "ዱአ" δυο "ሁለት" እና "ቴኦስ" θεισμός "አምላክ" የሚል ትርጉም ነው፤ ትርጉሙም "ሁለት አምላክ"dual deity" ማለት ነው፤ ይህንን ትምህርት ቁርአን ክፉኛ ይቃወማል፦
16፥51 አላህም አለ፦ *"ሁለት አማልክትን አትያዙ"*፡፡ እርሱ *"አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እኔንም ብቻ ፍሩ"*፡፡ وَقَالَ ٱللَّهُ لَا تَتَّخِذُوٓا۟ إِلَٰهَيْنِ ٱثْنَيْنِ ۖ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَإِيَّٰىَ فَٱرْهَبُونِ
ይህ ትምህርት ከሥላሴ የሚለየው አምላክ በምንነት ሆነ በማንነት ሁለት ነው ሲሉ፤ ሥላሴያውያን ደግሞ በማንነት ሦስት በምንነት አንድ ናቸው ብለው ያምናሉ፤ ነገር ግን አንዱ አምላክ በማንነት ሆነ በምንነት አንድ ነው፤ በምንነቱ ሆነ በማንነቱ ተጋሪ የለውም፦
18፥110 ወደ እኔ የሚወረድልኝ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ እኔም ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ" ማለት ነው፤ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም አምልኮ *"አንድንም"* አያጋራ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَآ أَنَا۠ بَشَرٌۭ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُوا۟ لِقَآءَ رَبِّهِۦ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًۭا صَٰلِحًۭا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِۦٓ أَحَدًۢا

"አንድ አምላክ" በሚለው ቃል ላይ "አንድ" የሚለውን የተጠቀመበት "ዋሒድ" وَٰحِد ሲሆን አላህ በምንነቱ ላይ ምንም ምንነት ተጋሪ እንደሌለው ያሳያል፤ "አንድንም አያጋራ" በሚለው ቃል የተጠቀመበት ቃል "አሐድ" أَحَد ሲሆን በአላህ ምንነት ላይ ማንም ማንነት ተጋሪ እንደሌለ ያሳያል፦
72፥20 «እኔ የምግገዛው ጌታየን ብቻ ነው፡፡ በእርሱም *"አንድንም"* አላጋራም» በል፡፡ قُلْ إِنَّمَآ أَدْعُوا۟ رَبِّى وَلَآ أُشْرِكُ بِهِۦٓ أَحَدًۭا
112፥1 በል «እርሱ አላህ *"አንድ"* ነው፡፡ قُلْ هُوَ ٱللَّهُ أَحَدٌ

"አላህ አንድ ነው" በሚለው ቃል ላይ "አንድ" የሚለው "አሐድ" أَحَد መሆኑ በራሱ አላህ አንድ ማንነት ብቻ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፤ ከእርሱ ማንነት ጋር መለኮትን የሚጋራ አንድም ማንነት የለም፦
112፥4 ለእርሱም *"አንድም"* ብጤ የለውም፡፡ وَلَمْ يَكُن لَّهُۥ كُفُوًا أَحَدٌۢ

"ለም" لَمْ ማለት "አፍራሽ ቃል"negative particle" ሲሆን ለማንነት የሚመጣ አፍራሽ ቃል ነው፤ ለእርሱ ማንም ብጤ የሌለው መሆኑን ያሳያል፤ "ለይሠ" لَيْسَ ማለት "አፍራሽ ቃል"negative particle" ሲሆን ለምንነት የሚመጣ አፍራሽ ቃል ነው፤ አላህ የሚመስለው ምንም ምንነት የለም፦
42፥11 *የሚመስለው ምንም ነገር የለም*፡፡ እርሱም *ሰሚው ተመልካቹ* ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِۦ شَىْءٌۭ ۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ

ይህንን ጥልልና ጥንፍፍ ያለ የተውሒድ ትምህርት ከተረዳን በክርስትናው አንጃ ውስጥ የይሆዋ ምስክሮች ደግሞ፦ "ዓለማት ከመፈጠራቸው በፊት ያህዌህ ኢየሱስ ፈጠረውና በኢየሱስ ሁሉን ነገር ፈጠረ" ብለው ያምናሉ፤ ይህ እንጥል ከመቧጠጥ ምንም አይተናነስም፤ ኢየሱስን አናመልክም ሲሉ ተውሒደል ኡሉሂያን ሲያሟሉ፤ ግን ዓለማትን ሲፈጥር ግን አጋዥ ነበረው ብሎ ማለት ተውሒደ አር-ሩቡቢያን ላይ ማሻረክ ነው፤ ከአላህ ጋር በምንነት ተለይቶ ግን ፍጥረትን ሲፈጥር ሆነ ዓለማትን ሲያስተናብር የሚያግዘው አጋዥ የለውም፤ ወደ አላህ በንስሃ ተመለሱ እንላለን፦
34፥22 እነዚያን ከአላህ ሌላ የምታስቧቸውን ጥሩ፡፡ በሰማያትም በምድርም ውስጥ *"የብናኝ ክብደት ያክል ምንንም አይችሉም"*፡፡ ለእነርሱም በሁለቱም ውስጥ *"ምንም ሽርክና የላቸውም"*፡፡ ከእነርሱም ለእርሱ *"ምንም አጋዥ የለውም"*» በላቸው፡፡ قُلِ ٱدْعُوا۟ ٱلَّذِينَ زَعَمْتُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ ۖ لَا يَمْلِكُونَ مِثْقَالَ ذَرَّةٍۢ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَلَا فِى ٱلْأَرْضِ وَمَا لَهُمْ فِيهِمَا مِن شِرْكٍۢ وَمَا لَهُۥ مِنْهُم مِّن ظَهِيرٍۢ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አንድ አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

18፥110 እኔም ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚወረድልኝ፦ *”አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው” ማለት ነው”*፤ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም አምልኮ አንድንም አያጋራ» *”በላቸው”*፡፡ قُلْ إِنَّمَآ أَنَا۠ بَشَرٌۭ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُوا۟ لِقَآءَ رَبِّهِۦ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًۭا صَٰلِحًۭا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِۦٓ أَحَدًۢا

“ኢስላም” ማለት “አንዱን አምላክ በብቸኝነት ማምለክ፣ መገዛት፣ መታዘዝ ማለት ነው”፤ የኢስላም አስኳሉ ደግሞ ተውሒድ ነው፤ ወደ ነብያችን”ﷺ” የሚወርደው ግህደተ-መለኮት፦ “አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው” ማለት ነው፦
18፥110 እኔም ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚወረድልኝ፦ *”አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው” ማለት ነው”*፤ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም አምልኮ አንድንም አያጋራ» *”በላቸው”*፡፡ قُلْ إِنَّمَآ أَنَا۠ بَشَرٌۭ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُوا۟ لِقَآءَ رَبِّهِۦ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًۭا صَٰلِحًۭا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِۦٓ أَحَدًۢا
6፥19 *«እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው”*፡፡ እኔም ከምታጋሩት ነገር ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ وَإِنَّنِى بَرِىٓءٌۭ مِّمَّا تُشْرِكُونَ
21፤108 «ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ *”አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው”* ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም “ታዛዦች” ናችሁን» *በላቸው*፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

“ታዛዦች” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሙስሊሚን” مُّسْلِمُونَ ሲሆን ይህንን አንድ አምላክ በፍፁም መታዘዝን፣ መገዛትን፣ ማምለክን ያሳያል፤ “ኢንነማ” إِنَّمَآ ማለት “ብቻ” ማለት ሲሆን ይህም አንድ አምላክ ብቻ መመለክ የሚገባው ለማሳየት ብዙ ቦታ “አንድ አምላክ ብቻ ነው” በማለት ያስቀምጣል፦
20፥98 *”ጌታችሁ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ የኾነው አላህ ብቻ ነው”*፡፡ እውቀቱ ነገርን ሁሉ አዳረሰ፡፡ إِنَّمَآ إِلَٰهُكُمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِى لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ وَسِعَ كُلَّ شَىْءٍ عِلْمًۭا
2፥163 *”አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም”*፡፡ እርሱ እጅግ በጣም ርኅሩህ አዛኝ ነው፡፡ وَإِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ لَّآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلرَّحْمَٰنُ ٱلرَّحِيمُ

ኢስላም ጥልልና ጥንፍፍ ያለ “ሞኖ-ቴእይዝም” መሆኑ ከላይ ያሉት አናቅጽ ቁልጭና ፍንትው አድርገው ያሳያሉ፤ “ሞኖ-ቴእይዝም” μονοθεϊσμός ማለት የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “ሞኖ” μονο “ብቸኛ” እና “ቴኦስ” θεισμός “አምላክ” የሚል ውቅር ነው፤ ትርጉሙም “ብቸኛ አንድ አምላክ”only one deity” ማለት ነው፤ እንደ ባይብሉ ይህ ብቸኛ አምላክ ኢየሱስን የላከው ብቻ ነው፦
ዮሐንስ 17:3 *”እውነተኛ አምላክ ብቻህን የሆንህ አንተን”* እና የላክኸውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት። “ 1980 አዲስ ትርጉም”
τὸν μόνον ἀληθινὸν Θεὸν καὶ ὃν ἀπέστειλας Ἰησοῦν Χριστόν

ኢየሱስ የላከውን “አንተ” በሚል ሁለተኛ መደብ ነጠላ ባለቤት ተውላጠ-ስም በመጥራት ወደ እርሱ ይፀልይ ነበር፤ ይህንን የላከውን ማንነት “እውነተኛ አምላክ ብቻህን የሆንህ” በማለት የላከው ብቻውን እውነተኛ አምላክ መሆኑን ለማመልከት “ብቻህን” የሚል ገላጭ”adjective” ይጠቀማል፤ ከዚያም ባሻገር እራሱን ከዚያ ከእውነተኛ አምላክ ለመለየት “እና” የሚል መስተጻምር”conjuction” ይጠቀማል፣ ይህ አነጋገሩ የሚያሳየው ኢየሱስ የእውነተኛ አምላክ መልእክተኛ መሆኑን ነው፣ “የላከውን” የሚል ሃይለ-ቃል መጠቀሙ ይሰመርበት፣ መመለክ የሚገባው እርሱ ብቻ መሆኑን ለማሳየትም “እርሱን ብቻ አምልክ” በማለት እና የትንሳኤን ቀን መቼ መከሰት “ከአባት ብቻ በቀር ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም” በማለት “ብቻ” የሚል ወሳኝ ቃላት ይጠቀማል፦
ማቴዎስ 4፥10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ *እርሱንም ብቻ አምልክ* ተብሎ ተጽፎአልና አለው።
ማቴዎስ 24፥36 ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን *”ከአባት ብቻ በቀር”* የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ *”ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም”*።

ይህ ብቸኛ አምላክ ብቻውን አምላክ የሆነ፣ የማይሞት፣ የማይታይ፣ ብቻውን የሆነ ገዥ፣ አንድ ሰው እንኳ ያላየውም ሊያይም የማይቻለው ነው፦
1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥17 *”ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይሞተው፣ ለማይታየውም”*፣ ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን። NIV
6፥15-16 ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና *”ብቻውን የሆነ ገዥ”*፥ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ ያሳያል። *”እርሱ ብቻ የማይሞት ነው”*፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ *”አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም”*፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን።

ይህ ብቸኛ አምላክ “እና” በሚል መስተጻምር እና “በ” በሚል መስተዋድድ ከኢየሱስ ተለይቷል፦
ሮሜ 16፥27 ብቻውን ጥበብ ላለው ለአምላክ *”በ”*ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን። NIV
ይሁዳ 1፥4 *”ብቻውን ያለውን ጌታ አምላክ”* እና ጌታችንንም ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።
denying the only Lord God, and our Lord Jesus Christ.” KJV
ይሁዳ 1፥25 *”ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን”* ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ *”በ”*ጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።
ይህ ብቸኛ የኢየሱስ አምላክ ጥንት የነበሩት የነብያት እምላክ ነው፤ እርሱ በልዕልናው ብቻውን ያለ እና ብቻውን ሁሉንም ነገር የፈጠረ ነው፦
ዘዳግም 32፥39 አሁንም *እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ*፥ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ”* እዩ፤
ኢዮብ 23፥13 *”እርሱ ግን ብቻውን ነው”*፤ እርሱንስ የሚመስለው ማን ነው?
ኢዮብ 9፥8 *”ሰማያትን ብቻውን ይዘረጋል”*።
መዝሙር 136፥7 *”ብቻውን ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ”*፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
ኢሳይያስ 44፥24 ከማኅፀን የሠራህ፥ የሚቤዥህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሁሉን የፈጠርሁ፥ *”ሰማያትን ለብቻዬ የዘረጋሁ ምድርንም ያጸናሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ ከእኔ ጋር ማን ነበረ?”*

“ብቻ” የሚል ገላጭ ቃል ተጠቅሞ ከአንድ በላይ ብዙ ማንነቶች በአንድ መለኮት ውስጥ አሉ ማለት እጅግ ሲበዛ ሞኝነት ነው፤ ሙስሊም በአላህ አንድ እኔነት ላይ ሌላ እኔነት ያላቸው ማንነት ሆነ ምንነት ሳያጋሩ የሚያመልኩ ናቸው፦
24፥55 *”በእኔ ምንም የማያጋሩ ኾነው ያመልኩኛል”*፡፡ ከዚያም በኋላ የካደ ሰው እነዚያ እነርሱ አመጸኞች ናቸው፡፡ يَعْبُدُونَنِى لَا يُشْرِكُونَ بِى شَيْـًۭٔا ۚ وَمَن كَفَرَ بَعْدَ ذَٰلِكَ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْفَٰسِقُونَ
31፥15 *”ለአንተ በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህም አትታዘዛቸው”*፡፡ وَإِن جَٰهَدَاكَ عَلَىٰٓ أَن تُشْرِكَ بِى مَا لَيْسَ لَكَ بِهِۦ عِلْمٌۭ فَلَا تُطِعْهُمَا
22፥26 ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ *«በእኔ ምንንም አታጋራ”*፣ ቤቴንም ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው» *”ባልነው ጊዜ አስታውስ*”፡፡ وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَٰهِيمَ مَكَانَ ٱلْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِى شَيْـًۭٔا وَطَهِّرْ بَيْتِىَ لِلطَّآئِفِينَ وَٱلْقَآئِمِينَ وَٱلرُّكَّعِ ٱلسُّجُودِ
29፥8 ሰውንም በወላጆቹ መልካም አድራጎትን አዘዝነው፡፡ *”ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህ አትታዘዛቸው”*፡፡ መመለሻችሁ ወደ እኔ ነው፡፡ ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፡፡ وَوَصَّيْنَا ٱلْإِنسَٰنَ بِوَٰلِدَيْهِ حُسْنًۭا ۖ وَإِن جَٰهَدَاكَ لِتُشْرِكَ بِى مَا لَيْسَ لَكَ بِهِۦ عِلْمٌۭ فَلَا تُطِعْهُمَآ ۚ إِلَىَّ مَرْجِعُكُمْ فَأُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

እኛስ አላህ ሆይ! አንተን ብቻ እናመልካለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፤ በአንተ አምልኮ ላይ ማንንም ምንንም አካል ሆነ ህላዌ አናጋራም፦
1፥5 *”አንተን ብቻ እናመልካለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን”*፡፡ إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የጀሀነም ሸለቆ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥59 *ከእነርሱም በኋላ “ሶላትን ያጓደሉ” ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ*፡፡ فَخَلَفَ مِن بَعْدِهِمْ خَلْفٌ أَضَاعُوا الصَّلَاةَ وَاتَّبَعُوا الشَّهَوَاتِ ۖ فَسَوْفَ يَلْقَوْنَ غَيًّا

ሶላት በኢማን፣ በኢኽላስ እና በኢቲባዕ ከተፈጸመ ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ በመከልከል ይረዳል፤ ሶላት አላህን በሚፈሩ ላይ እንጅ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት፦
2፥45 በመታገስ እና *”በሶላትም ተረዱ፡፡ እርሷም ሶላት በፈሪዎች ላይ እንጅ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት”*፡፡ وَاسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ وَإِنَّهَا لَكَبِيرَةٌ إِلَّا عَلَى الْخَاشِعِينَ
2፥153 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመታገስ እና *”በሶላት ተረዱ”*፡፡ አላህ ከታጋሾች ጋር ነውና፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ

ሶላት ላይ የሚቆሙ ሙሥሊሞች “ሙሰሊን” ይባላሉ፤ ሶላት የማይቆሙ “ሰቀር” በሚባለው የጀሃነም ሸለቆ ውስጥ ይቀጣሉ፤ እነርሱም ቅጣቱን ሲቀምሱ፦ “ከሙሰሊኖቹ አልነበርንም” ይላሉ፦
74፥43 እነርሱም ይላሉ፦ *”ከሰጋጆቹ አልነበርንም”*፡፡ قَالُوا لَمْ نَكُ مِنَ الْمُصَلِّين

ሶላት በወቅቱ የማይቆሙ እና ያለ ኢኽላስ ሶላት ላይ የሚቆሙ “ወይል” በሚባል የጀሃነም ሸለቆ ውስጥ ይቀጣሉ፦
107፥4 *”ወዮላቸው ለሰጋጆች”*፡፡ فَوَيْلٌ لِّلْمُصَلِّينَ
107፥5 *”ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለኾኑት ሰጋጆች”*፡፡ الَّذِينَ هُمْ عَن صَلَاتِهِمْ سَاهُونَ
107፥6 *”ለእነዚያ እነርሱ ይዩልኝ ባዮች ለኾኑት”*፡፡ الَّذِينَ هُمْ يُرَاءُونَ

ወዮላቸው የተባሉት ሙሰሊን እነማን እንደሆኑ ለማመልከት “እነዚያ” የሚል አመልካች ተውላጠ-ስም ተጠቅሰዋል። እነዚያ እነርሱ በሶላታቸው ላይ ዘውታሪዎች ሆነው የሚቆሙ ሙሰሊን ሲቀሩ በተቃራኒው ሶላትን ያጓደሉ አሊያም የተዉ “ገይ” በሚባል የጀሃነም ሸለቆ ውስጥ ይቀጣሉ፦
70፥22 *”ሰጋጆቹ ብቻ ሲቀሩ”*፡፡ إِلَّا الْمُصَلِّينَ
70፥23 *እነዚያ እነርሱ በሶላታቸው ላይ ዘውታሪዎች የኾኑት”*፡፡ الَّذِينَ هُمْ عَلَىٰ صَلَاتِهِمْ دَائِمُونَ
19፥59 *ከእነርሱም በኋላ “ሶላትን ያጓደሉ” ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ*፡፡ فَخَلَفَ مِن بَعْدِهِمْ خَلْفٌ أَضَاعُوا الصَّلَاةَ وَاتَّبَعُوا الشَّهَوَاتِ ۖ فَسَوْفَ يَلْقَوْنَ غَيًّا

አላህ በሶላታቸው ላይ ዘውታሪዎች ሆነው ከሚቆሙትና ኢኽላስ ካላቸው ሙሰሊን ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ጫት መቃም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥219 *”አእምሮን ከሚቃወም መጠጥ እና ከቁማር ይጠይቁሃል፡፡ «በሁለቱም ውስጥ ታላቅ ኃጢኣትና ለሰዎች ጥቅሞች አሉባቸው፡፡ ግን ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ነው» በላቸው”*፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ ۖ قُلْ فِيهِمَا إِثْمٌ كَبِيرٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ وَإِثْمُهُمَا أَكْبَرُ مِن نَّفْعِهِمَا ۗ

“ጫት”Catha edulis” አእምሮን የሚያመረቅን እና በጤና፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ ሕይወት ላይ እክል ከሚያጋጥሙ እና አሉታዊ የጎንዮሽ ተፅእኖ”negative side effect” ከሚያሳድሩ ነገሮች መካከል እንደሆነ የመስኩ ምሁራን ያትታሉ፥ በኢሥላም ጫት ከኸምር ይመደባል። “ኸምር” خَمْرየሚለው ቃል “ኸመረ” خَمَرَ ማለትም “ሸፈነ” “ደበቀ” “ሰወረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን አእምሮን “የሚሸፍን” “የሚደብቅ” “የሚሰውር” ማለት ነው፥ የሒጃብ አይነት ከሆኑት መካከል “ጉፍታ” እራሱ በቁርኣን “ኺማር” خِمَار ይባላል፦
24፥31 *ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡ ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ*፡፡ وَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا ۖ وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ

“ጉፍታዎች” ለሚለው በብዜት የገባው ቃል “ኹሙር” خُمُر ሲሆን በነጠላ ደግሞ “ኺማር” خِمَار ነው፥ “ኺማር” خِمَار የሚለው ቃል ልክ እንደ “ኸምር” خَمْر ሥርወ-ቃሉ “ኸመረ” خَمَرَ ነው። ጉፍታ ራስን ስለሚሸፍን “ኺማር” خِمَار እንሚባል ሁሉ አእምሮን የሚቃወም ማንኛውም ነገር “ኸምር” خَمْر ይባላል፥ አስካሪ መጠጥ”alcohol” ሆነ “አደንዛዥ ዕፅ”drug” አእምሮን የሚሸፍን ሰለሆነ ኸምር ነው፦
2፥219 *”አእምሮን ከሚቃወም መጠጥ እና ከቁማር ይጠይቁሃል፡፡ «በሁለቱም ውስጥ ታላቅ ኃጢኣትና ለሰዎች ጥቅሞች አሉባቸው፡፡ ግን ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ነው» በላቸው”*፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ ۖ قُلْ فِيهِمَا إِثْمٌ كَبِيرٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ وَإِثْمُهُمَا أَكْبَرُ مِن نَّفْعِهِمَا ۗ

ቁማር መሠረቱ ገንዘብ ነው፥ ገንዘብ ለሰዎች ጥቅም አለው። አልክሆል ሆነ ድራግ በህክምና አገልግሎት ለሰዎች ጥቅም አለው። ነገር ግን ኸምር ሆነ ቁማር ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ስለሆነ ታላቅ ኃጢኣት አለባቸው። አልክሆል ውስጥ የሚካተቱት ጠላ፣ ጠጅ፣ አረቄ፣ ውስኪ፣ ቮድካ ወዘተ.. ሲሆኑ ድራግ ውስጥ የሚካተቱት ደግሞ ሲጋራ፣ ቶባኮ፣ ሲሻ፣ ጫት፣ ኮኬይን፣ ማሪዋና፣ ናርኮት፣ ሄሮይን ወዘተ ናቸው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 74, ሐዲስ 14
ኢብኑ ዑመር”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “ዑመር በአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” አትሮንስ ላይ ኹጥባህ ሲያደርግ እንዲህ አለ፦ *”ኸምር ሐራም መሆኑ የሚናገረው የወረደው ከአምስት ነገር ማለትም ከወይን፣ ከተምር፣ ከስንዴ፣ ከገብስ እና ከማር ስለሚዘጋጁት ኸምር ናቸው። ዐቅልን የሚሰውር ሁሉ ኸምር ነው”*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ خَطَبَ عُمَرُ عَلَى مِنْبَرِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ إِنَّهُ قَدْ نَزَلَ تَحْرِيمُ الْخَمْرِ، وَهْىَ مِنْ خَمْسَةِ أَشْيَاءَ الْعِنَبِ وَالتَّمْرِ وَالْحِنْطَةِ وَالشَّعِيرِ وَالْعَسَلِ، وَالْخَمْرُ مَا خَامَرَ الْعَقْلَ

እዚህ ሐዲስ ላይ “የሚሰውር” ለሚለው የገባው ቃል “ኻመረ” خَامَرَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ ጠላ፣ ጠጅ፣ አረቄ፣ ውስኪ፣ ቮድካ የሚል ስለሌለ መጠጣቱ ይፈቀዳል እንደማንል እና ቂያሥ በማድረግ ሐራም ነው እንደምንል ሁሉ ሲጋራ፣ ቶባኮ፣ ሲሻ፣ ጫት፣ ኮኬይን፣ ማሪዋና፣ ናርኮት፣ ሄሮይን የሚል ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ ስለሌለ ሐላል ነው አንልም፥ እንዲሁ ቂያሥ በማድረግ ሐራም ነው እንላለን። “ቂያሥ” قِيَاس የሚለው ቃል “ቃሠ” قَاسَ ማለትም “አመጣጠነ” “አመዛዘነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማመጣጠን” “ማመዛዘን” ማለት ነው። በሸሪዓህ ቂያሥ ከሚደረጉት እሳቦት አንዱ ኸምር ነው፥ አስካሪ መጠጥ ሆነ አደንዛዥ ዕፅ አእምሮን የሚያነቃቃ እና የሚያደነዝዝ እስከሆነ ድረስ ሙሥኪር ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 36, ሐዲስ 95
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ “ነቢዩ”ﷺ”፦ *”ሙሥኪር ሁሉ ኸምር ነው፥ ኸምር ሁሉ ሐራም ነው”* ሲሉ እንጂ ሌላ ዐላውቅም”። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ وَلاَ أَعْلَمُهُ إِلاَّ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ كُلُّ مُسْكِرٍ خَمْرٌ وَكُلُّ خَمْرٍ حَرَامٌ ‏”‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 30, ሐዲስ 3514
ሙዓዊያህ የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቼ ነበር፦ *”ሙሥኪር ሁሉ ለሁሉም ምእመናን ሐራም ነው”*። سَمِعْتُ مُعَاوِيَةَ، يَقُولُ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ يَقُولُ ‏ “‏ كُلُّ مُسْكِرٍ حَرَامٌ عَلَى كُلِّ مُؤْمِنٍ ‏”‏
“ሙሥኪር” مُسْكِر የሚለው ቃል “ሠኪረ” سَكِرَ
ማለትም “ደነዘዘ” “ሰከረ” “ነፈዘ” “መረቀነ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “የሚያደነዝዝ” “የሚያሰክር” “የሚያነፍዝ” “የሚያመረቅን” ማለት ነው። “ሠከር” سَكَر እራሱ “አደንዛዥ” “አነፋዥ” “አመርቃኝ” “አስካሪ”intoxicant” ማለት ሲሆን “ሡክር” سُكْر ደግሞ “አደንዛዥነት” “አነፋዥነት” “አመርቃኝነት” “አስካሪነት”intoxication” ማለት ነው፦
22፥2 በምታዩዋት ቀን አጥቢ ሁሉ ከአጠባችው ልጅ ትፈዝዛለች፡፡ የእርግዝና ባለቤት የኾነችም ሁሉ እርጉዟን ትጨነግፋለች፡፡ *”ሰዎች የሰከሩ ኾነው ታያለህ፡፡ እነርሱም ከመጠጥ የሰከሩ አይደሉም፡፡ ግን የአላህ ቅጣት ብርቱ ነው”*፡፡ يَوْمَ تَرَوْنَهَا تَذْهَلُ كُلُّ مُرْضِعَةٍ عَمَّا أَرْضَعَتْ وَتَضَعُ كُلُّ ذَاتِ حَمْلٍ حَمْلَهَا وَتَرَى النَّاسَ سُكَارَىٰ وَمَا هُم بِسُكَارَىٰ وَلَـٰكِنَّ عَذَابَ اللَّهِ شَدِيدٌ

ይህ አንቀጽ መስከር ማለት የመጠጥ ስካር ብቻ እንዳልሆነ ፍንትውና ቁልጭ አርጎ ያሳያል። የዘመናችን ስመ-ጥርና አንጋፋ ምሁራን ጫት”Catha edulis” ሐራም እንደሆነ ፈትዋ ሰተዋል። ለምሳሌ ታላቁ ዐሊም ሸይኽ ኢብኑ ባዛ ስለ ጫት እና ሲጋራ ተጠይቀው፦ *”ጫት እና ሲጋራ ሐራም መሆናቸው ምንም ጥርጥር የለውም፥ የጫትን ሐራምነት አስመልክቶ ዑለሞች በርካታ ኪታቦችን ከትበዋል፡፡ ከእነሱም መካከል የቀድሞው የአሥ-ሠዑዲ ዐረቢያህ ሙፍቲ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ኢብራሂም አል-ሸይኽ”ረሒመሁሏህ” አንዱ ናቸው። በጥቅሉ ሙሥሊሞች ጫትና ሲጋራን ሊተዋቸው እና ሊጠነቀቋቸው ይገባል፥ ጫትና ሲጋራን ማንኛውም ሙሥሊም የመተው ግዴታ አለበት። ጫትና ሲጋራን መግዛትም ሆነ መሸጥ እናም በእነርሱ መነገድ አይቻልም፥ ሐራም ነው፡፡ የጫትና ሲጋራ ገንዘብ ሐራም ናቸው፥ ሙሥሊሞችን ከእነዚህ ነገሮች አላህ ያርቃቸው ዘንድ እንማፀነዋለን” ብለዋል።
ሸይኽ ሷሊሕ አል-ፈውዛን”ሃፊዘሁሏህ” ስለ ጫት ተጠይቀው፦ *”ጫት ሐራም ነው፥ ጫት ከሲጋራ የበለጠ ጉዳት አለው፡፡ እርሱ(ጫት) ሐራም ነው” ብለዋል።
ምንጭ አል-ፈትዋ 257/2 ይመልከቱ!

ስለዚህ ጫት መቃም ትክክል ወይም ስህተት መሆን የሚችለው አንድ ግለሰብ ጫትን ስለሚቅም እና ስለማይቅም ሳይሆን ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው መስፈት ነው። ጫት ለሚቅሙ፣ ለሚያስቅሙ እና ለሚያቃቅሙ ይህ ስንኝ ተሰኝቶላቸዋል፦
በቅጠል በሆነ የሚወጣው ሀጃ
ፍየል ትሆን ነበር ከቢላዋ ነጃ!
ጫት መቃም የእርድና ምልክት፥ አለመቃም የፋርነት መለኪያ አይደለም፥ ይህ አስተሳሰብ መሰልጠን ሳይሆን መሰይጠን ነው። እንግዲያውስ ጫት የምትቅሙ፣ የምታስቅሙ፣ የምታቃቅሙ ቆም ብላችሁ ይህንን ፈሣድ ተመልከቱት! አሏህ ከጫት እና በጫት ከሚመጡ ፈሣዶች ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ውግራት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

“ረጅም” رجم የሚለው ቃል “ውግራት”stoning” ማለት ሲሆን የሙሴ አምላክ ለሙሴ የሰጠው ሕግ ነው። “ውግራት” የሚለው ቃል ብሉይ ላይ 22 ጊዜ የተጠቀሰው ለተለያየ ቅጣት ነው፦

ነጥብ አንድ
“ለክህደት ቅጣት”
አንድ ሰው ከአንዱ አምላክ ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ቢሰብክ በድንጋይ ተወግሮ ይገደላል፦
ዘዳግም 13፥7-10 የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም በብብትህ ያለች ሚስትህ ወይም እንደ ነፍስህ ያለ ወዳጅህ በስውር፦ ና፥ ሄደን ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ወደ አንተ የቀረቡት ከአንተም የራቁት አንተን ከብበውህ ያሉ አሕዛብ ከሚያመልኩአቸው አማልክት፥ አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን “””ሌሎች አማልክት እናምልክ”” ብሎ ቢያስትህ እሺ አትበለው፥ አትስማውም፤ ዓይንህም አይራራለት፥ እትማረውም፥ አትሸሽገውም፤ ነገር ግን ፈጽመህ ግደለው፤ እርሱን ለመግደል በፊት የአንተ እጅ፥ ከዚያም በኋላ የሕዝቡ ሁሉ እጅ በላዩ ትሁን። ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ካወጣህ ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ሊያርቅህ ወድዶአልና “”እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው”””።

ሌላው ከአንዱ አምላክ ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ያስተማረ ብቻ ሳይሆን ከአንዱ አምላክ ሌሎች ሌሎች አማልክትን ያመለከ በድንጋይ ተወግሮ ይገደላል፦
ዘዳግም 17፥3-5 “”ሄዶም ሌሎች አማልክትን ያመለከ””፥ እኔ ላላዘዝኋቸው ለፀሐይና ለጨረቃ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ የሰገደ ቢገኝ፥ ቢያወሩልህም ብትሰማም፥ ያንን ፈጽመህ መርምር፤ እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ በእስራኤልም መካከል እንዲህ ያለ ርኵሰት እንደ ተሠራ እርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥ ይህን ክፉ ነገር የሠሩትን ያን ወንድ ወይም ያችን ሴት ወደ በርህ ታመጣቸዋለህ፥ “””እስኪሞቱም ድረስ በድንጋይ ትወግራቸዋለህ”””።
ዘሌዋውያን 20፥1-2 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ደግሞ የእስራኤልን ልጆች እንዲህ በላቸው፦ ከእስራኤል ልጆች ወይም በእስራኤል ዘንድ ከሚቀመጡ እንግዶች ማናቸውም ሰው “”ዘሩን ለሞሎክ ቢሰጥ”” ፈጽሞ ይገደል፤ “”የአገሩ ሕዝብ በድንጋይ ይውገረው””።

በተጨማሪም አንድ ሰው ቢጠነቁልና ቢያስጠነቁል እና አንዱን አምላክ ቢሳደብ በድንጋይ ተወግሮ ይገደላል፦
ዘሌዋውያን 20፥27 ሰው ወይም ሴት መናፍስትን ቢጠሩ ወይም ጠንቋዮች ቢሆኑ ፈጽመው ይገደሉ፤ በ””ድንጋይ ይውገሩአቸው””፤ ደማቸው በላያቸው ነው።
ዘሌዋውያን 24፥13-26 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ ተሳዳቢውን ከስፈሩ ወደ ውጭ አውጣው፤ የሰሙትም ሁሉ እጃቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት፤ ማኅበሩም ሁሉ ይውገረው። ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ትነግራለህ፦ ማናቸውም ሰው አምላኩን ቢሰድብ ኃጢአቱን ይሸከማል። የእግዚአብሔርንም ስም የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደል፤ ማኅበሩም ሁሉ ይውገሩት፤ መጻተኛ ወይም የአገር ልጅ ቢሆን፥ የእግዚአብሔርን ስም በሰደበ ጊዜ ይገደል።

ነጥብ ሁሉት
“ለአመፅ ቅጣት”
አንድ ሰው ለአባቱና ለእናቱ ቃል የማይታዘዝ ዓመፀኛ በድንጋይ ተወግሮ ይገደላል፦
ዘዳግም 21፥18-21 ማንም ሰው ለአባቱ ቃልና ለእናቱ ቃል የማይታዘዝ ቢቀጡትም የማይሰማቸው እልከኛና ዓመፀኛ ልጅ ቢኖረው፥ አባቱና እናቱ ይዘው ወደ ከተማው ሽማግሌዎች ወደሚኖሩበትም ስፍራ በር ያምጡት፤ የከተማውንም ሽማግሌዎች፦ ይህ ልጃችን እልከኛና ዓመፀኛ ነው፥ ለቃላችንም አይታዘዝም ስስታምና ሰካራም ነው ይበሉአቸው። የከተማውም ሰዎች ሁሉ “”እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት””፤ እንዲህም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታርቃለህ፥ እስራኤልም ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ።

ነጥብ ሶስት
“ለዝሙት ቅጣት”
ሴት ልጅ በጋብቻ ጊዜ ድንግልናዋ ካልተገኘ በድንጋይ ተወግራ ትገደላለች፦
ዘዳግም 22፥21 ብላቴናይቱን ወደ አባትዋ ቤት ደጅ ያውጡአት፥ በእስራኤልም ዘንድ የማይገባውን ነገር አድርጋለችና፥ በአባትዋም ቤት አመንዝራለችና የከተማዋ ሰዎች “”እስክትሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩአት””፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።

ከጋብቻ በፊት ለጋብቻ የታጨች ከሆነችና ግን ከሌላው ወንድ ጋር አንሶላ ብትጋፈፍ እርሷም ያቀበጣት ወንድ በድንጋይ ይወገራሉ፦
ዘዳግም 22፥23-24 ማናቸውም ሰው ድንግልና ያላትን ልጃገረድ ቢያጭ፥ ሌላ ሰውም በከተማ ውስጥ አግኝቶ ከእርስዋ ጋር ቢተኛ፥ ሁለቱን ወደዚያች ከተማ በር አውጡአቸው፤ ብላቴናይቱ በከተማ ውስጥ ሳለች አልጮኸችምና፥ ሰውዮውም የባልንጀራውን ሚስት አስነውሮአልና “”እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሩአቸው””፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።

ነጥብ አራት
“ለወሰን ማለፍ ቅጣት”
በሬ ወንድን ወይም ሴትን እስኪሞቱ ድረስ ቢወጋ የበሬው ባለቤት ተዋጊ መሆኑን ካላወቀ በሬው ብቻ ይወገራል፤ ግን እያወቀ ከሆነ በሬውም የበሬውም ባለቤት ተወግረው ይገደላሉ፦
ዘፀአት 21፥28-29 በሬም ወንድን ወይም ሴትን እስኪሞቱ ድረስ ቢወጋ፥ “በሬው ይወገር”፤ ሥጋውም፥ አይበላ፤ የበሬው ባለቤት ግን ንጹሕ ነው። በሬው ግን አስቀድሞ ተዋጊ ቢሆን፥ ሰዎችም ለባለቤቱ ቢመሰክሩለት ባይጠብቀውም፥ ወንድንም ወይም ሴትን ቢገድል፥ “”በሬው ይወገር፥ ባለቤቱ ደግሞ ይገደል””።

የሚገርመው ግን በሬ ወንድ ባሪያ ወይም ሴት ባሪያ ከወጋ
የበሬው ባለቤት ለጌቶቻቸው ሠላሳ የብር ሰቅል ይከፍላል በሬው ብቻ ተወግሮ ይገደላል፦
ዘፀአት 21፥32 በሬው ወንድ ባሪያ ወይም ሴት ባሪያ ቢወጋ፥ የበሬው ባለቤት ሠላሳ የብር ሰቅል ለጌታቸው ይስጥ፥ በሬውም ይወገር።
መደምደሚያ
ከላይ የዘረዘርናቸውን ስለ ውግራት የሚያወሩ አራቱ ነጥቦች ሲቀርቡ ከእነዚህ ሕግጋት ማምለጫ ክርስቲያኖች፦ “ይህ ሕግ ክርስቶስ ሲመጣ ቀርቷል” ብለው የዮሐንስ 8፥1-11 ያለውን ጥቅስ ይጠቅሳሉ፦
ዮሐንስ 8፥2-8 ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጡ በመካከልም እርሱዋን አቁመው። መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት። የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤ መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ። ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው። ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ።

የሚገርመው ነገር ከመነሻው የዮሐንስ 8፥1-11 ላይ ኢየሱስ ሊናገረው ይቅርና የዮሐንስ 8፥1-11 ያለው ክፍል የዮሐንስ ወንጌል ክፍል አይደለም። የትኛውም ቀዳማይ የግሪክ እደ-ክታባት”MSS” ላይ ይህ ንግግር አይገኝም። ይህ ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተከተተው በ 382 በላቲን ቩልጌት ላይ ሲሆን ጨማሪውም የሮሙ ቢሾፕ ጄሮም ነው። በተጨማሪ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከማጥኛ ፅሁፍ ጋር የሚለውን እትም የግርጌ ማስታወሻ እና ሎሎች ስመጥና ገናና ማብራሪያዎች ይመልከቱ፦
1.The Anchor Bible Dictionary, Vol. 1, 1992, page 585:
2. The International Standard Bible Encyclopedia, Vol. 4, page 2637,
3. The Tyndale New Testament Commentaries, I, page 275:
4። Word Biblical Commentary, Vol 33B, , 1975, page887-888:

ሌላዉ ደግሞ የሙሴ አምላክ ዝሙት የሠራ፣ ከአንድ አምላክ ዉጪ ያመለከ ወዘተ.. በድንጋይ ይወገር ሲል እንዴት ነበር ይህ ሕግ ይፈፀም የነበረዉ? ወይንስ ዝም ብሎ የማይፈፀም ሕግ ነበርን? ብሉይ ኪዳይ ላይ ያለው አምላክ ስለ ውግራት ሲናገር በወቅቱ ተሳስቶ ነበርን? ወይስ ያን ጊዜ ጨካኝ የነበረዉ አምላክ ነዉ በኋላ አዲስ ኪዳን ላይ ሩህሩህ ሆነ? እረ ለመሆኑ የአዲስ ኪዳኑ አምላክ ኢየሱስን ሲልክ አሳቡን ቀየረ? ወይስ ብሉይ ላይ የነበሩት ሕጎች ተደመሰሱ? መረጃ ይቅረብልን! ነገር ግን ኢየሱስ "ሕጉ ተሽሯል" ከሚሉት ሰዎች በተቃራኒው ሰማይና ምድር በቂያማ ቀን እስኪያልፍ ድረስ ከሙሴ ሕግ አንዲቷ ትንሿ ሕግ እንኳን እንደማትሻር በአፅንኦትና በአንክሮት ተናግሯል፦
ማቴ 5:17-18 “”እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ””፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። እውነት እላችኋለሁ፥ “”ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም””፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ።

በኢሥላም ሸሪዓው ባለበት አገር ከጋብቻ በፊት ዚና ላደረጉ ሰዎች ብይኑ መቶ ግርፋት ሲሆን በጋብቻ ላይ ደግሞ ዚና ያደረገው አካል የሚደርስበት ብይን ሞት ነው። ይህንን ሕግ ለመተቸት ቅድሚያ ባይብል ላይ ያለውን ሕግ ማየት ያሻል። እግር እራስን አያክምና።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ግድያ በመጽሐፍ ቅዱስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

17፥33 *”ያቺንም አላህ ያወገዛትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ”*፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ

መጽሐፍ ቅዱስ የፍቅር እና የሰላም መጽሐፍ ነው ለምትሉ ሁሉ ከፍትሕ ጋር በተያያዘ አራት ጥያቄዎችን እንጠይቃለን፦

ቁጥር አንድ
መጽሐፍ ቅዱስ የሰላምና የፍቅር መጽሐፍ ከሆነ እንዴት ሰውን ግደሉ ይላል?
ሕዝ 9፥6፤ “”ሽማግሌውንና ጐበዙን ቈንጆይቱንም ሕፃናቶቹንና ሴቶቹን”” ፈጽማችሁ “”ግደሉ””፤ ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፤ በመቅደሴም ጀምሩ አላቸው። በቤቱም አንጻር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ።
መሳ 21:10 ማኅበሩም ወደዚያ አሥራ ሁለት ሺህ ኃያላን ሰዎች ሰድደው። ሂዱ በኢያቢስ ገለዓድም ያሉትን ሰዎች “”ከሴቶችና ከሕፃናት”” ጋር በሰይፍ ስለት “ግደሉ””።
1ሳሙ 15:3፤ አሁንም ሄደህ አማሌቅን ምታ፥ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፥ አትማራቸውም፤ “”ወንዱንና ሴቱን ብላቴናውንና ሕፃኑን በሬውንና በጉን ግመሉንና አህያውን ግደል””።
ዘዳ 20:14 ነገር ግን “”ሴቶቹንና ሕፃናትን እንስሶቹንም”” በከተማይቱም ያለውን ምርኮ ሁሉ በዝብዘህ ለአንተ ትወስዳለህ፤ አምላክህም እግዚአብሔር የሚሰጥህን የጠላቶችህን ምርኮ ትበላለህ።
ዘዳ.3:6፤ በሐሴቦንም ንጉሥ በሴዎን እንዳደረግን ፈጽሞ አጠፋናቸው፤ ከተሞቹን ሁሉ “”ከወንዶችና ከሴቶች ከሕፃናቶችም ጋር አጠፋናቸው””።
ኢያ 6:21፤ በከተማይቱም የነበሩትን ሁሉ፥ “”ወንዱንና ሴቱን፥ ሕፃኑንና ሽማግሌውን፥ በሬውንም በጉንም አህያውንም፥ በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ””።

እንደ ምዕራባውያን ሚዛን ሰው የፈለገውን ማምለክ መብቱና ነፃነቱ አይደለምን? ከዚያ አልፎ አረጋውያንን፣ ሴቶችን፣ ሕፃናትንና እንስሳቱን መግደል ለምን አስፈለገ? እስቲ ይነበብ ይህን የፍቅርና የሰላም መጽሐፍ።

ቁጥር ሁለት
መጽሐፍ ቅዱስ የሰላምና የፍቅር መጽሐፍ ከሆነ እንዴት ሰውን እረዱ ይላል?
ዘጸ 32:27 የእናንተም ሰው ሁሉ ወንድሙን ወዳጁንም ጎረቤቱንም “ይረድ” וְהִרְג֧וּ አላቸው።
1ነገ 18:40 ኤልያስም ከበኣል ነቢያት አንድ ሰው እንዳያመልጥ ያዙ አላቸው። ያዙአቸውም፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ በዚያ “”አሳረዳቸው”” וַיִּשְׁחָטֵ֖ם።
2ነገ 10:11 ኢዩም ከአክዓብ ቤት የቀረውን ሁሉ፥ ታላላቆቹንም ሁሉ፥ ወዳጆቹንና ካህናቱን ማንም ሳይቀር በኢይዝራኤል “አረዳቸው” וַיִּשְׁחָטֵ֖ם ።
2ነገ 10:14፤ እርሱም። በሕይወታቸው ያዙአቸው አለ። ያዙአቸውም፥ በበግ ጠባቂዎችም ቤት አጠገብ ባለው ጕድጓድ አርባ ሁለቱን ሰዎች “አረዷቸው” וַיִּשְׁחָטֵ֖ם ፤ ማንንም አላስቀረም።
1ሳሙ 17:51፤ ዳዊትም ሮጦ በፍልስጥኤማዊው ላይ ቆመ፤ ሰይፉንም ይዞ ከሰገባው መዘዘው፥ ገደለውም፥ ራሱንም “አረደው” וַיְמֹ֣תְתֵ֔הוּ ።

ይህ ምንድን ነው? ቄራ ወይስ የፍቅርና የሰላም መጽሐፍ?

ቁጥር ሶስት
መጽሐፍ ቅዱስ የሰላምና የፍቅር መጽሐፍ ከሆነ እንዴት ሰውን በእሳት አቃጥሉ ይላል?
ዘሌ 20:14 ማናቸውም ሰው እናቲቱንና ልጂቱን ቢያገባ ርኵሰት ነው፤ በመካከላችሁ ኃጢአት እንዳይሆን እርሱና እነርሱ “”በእሳት ይቃጠሉ””።
ዘሌ 21:9 የካህንም ልጅ ራስዋን በግልሙትና ብታረክስ አባትዋን ታረክሰዋለች፤ “”በእሳት ትቃጠል””።
ኢያ 7:15 እርም የሆነውም ነገር የተገኘበት ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አፍርሶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ በደል አድርጎአልና እርሱና ያለው ሁሉ “”በእሳት ይቃጠላሉ””።
ዘዳ 7:5 ነገር ግን እንዲህ አድርጉባቸው፤ መሠዊያቸውን አፍርሱ፥ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውንም ቍረጡ፥ የተቀረጸውን ምስላቸውንም “”በእሳት አቃጥሉ””።
ዘዳ 7:25 የተቀረጸውንም የአምላኮቻቸውን ምስል “”በእሳት ታቃጥላለህ””፤ የተሠራባቸውን ብርና ወርቅ አትመኝ፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመድበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ።
ዘዳ 12:3 መሠዊያቸውንም አፍርሱ፥ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውንም “”በእሳት አቃጥሉ””፥ የአማልክቶቻቸውንም የተቀረጹ ምስሎች አንከታክቱ፤ ከዚያም ስፍራ ስማቸውን አጥፉ።
ኢያ 8:8 በያዛችኋትም ጊዜ ከተማይቱን “”በእሳት አቃጥሉአት””፤ እንደ እግዚአብሔር ቃል አድርጉ፤ እነሆ፥ አዝዣችኋለሁ።

ሰው የሚያመልክበትን የማምለኪያ አፀድ እና የሚኖርበትን ከተማ ማቃጠል ፍቅር ነውን?

ቁጥር አራት
መጽሐፍ ቅዱስ የሰላምና የፍቅር መጽሐፍ ከሆነ እንዴት ሰው ባልሠራው በደል አባቶቻቸው በሠሩት በደል ይገደሉ ይላል?
ይህም ትልቅ በደል ነው፦
በደል አንድ
አካን ሰርቆ ባጠፋው ወንዶችና ሴቶች ልጆቹንም፥ በሬዎቹንም፥ አህያዎቹንም፥ በጎቹንም ለምን መቃጠልና መወገር አስፈለገ?
ኢያሱ 7፥24-25 ኢያሱና እስራኤል ሁሉ የዛራን ልጅ አካንን፥ ብሩንም፥ ካባውንም፥ ወርቁንም፥ #ወንዶችና ሴቶች ልጆቹንም፥ በሬዎቹንም፥ አህያዎቹንም፥ በጎቹንም#፥ ድንኳኑንም፥ ያለውንም ሁሉ ወስደው ወደ አኮር ሸለቆ አመጡአቸው። ኢያሱም። ለምን አስጨነቅኸን? እግዚአብሔር ዛሬ ያስጨንቅሃል አለው እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት# በእሳትም አቃጠሉአቸው#፥ #በድንጋይም ወገሩአቸው#።

በደል ሁለት
በሙሴ ዘመን አማሌቃውያን ከእስራኤል በመዋጋት ተዋጉ፦
ዘጸአት 17፥8 አማሌቅም መጥቶ ከእስራኤል ጋር በራፊድም ተዋጋ።

በሙሴ ዘመን አማሌቃውያን ከእስራኤል በመዋጋት በበደሉት ከ 400 ዓመት በኃላ የልጅ ልጆቻቸውን በሬውንና በጉን ግመሉንና አህያውን በማስገደል ተበቀለ፤ ይህ ምን የሚሉት በደል ነው?
1ኛ ሳሙኤል 15፥2-3 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “”እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ”” አማሌቅ በመንገድ እየተቃወመ ያደረገበትን #እበቀላለሁ#። አሁንም ሄደህ አማሌቅን ምታ፥ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፥ አትማራቸውም #ወንዱንና ሴቱን ብላቴናውንና ሕፃኑን በሬውንና በጉን ግመሉንና አህያውን ግደል#።

አባቶች ስለ ልጆች አይገደሉ፥ ልጆችም ስለ አባቶች አይገደሉ ነገር ግን ሁሉ እያንዳንዱ በኃጢአቱ ይገደል የሚለው ትዕዛዛት የት ገባና ነው ምንም የማያቁትን ህፃናት ከ 400 ዓመት በኃላ የተፈጁት?
ዘዳግም 24፥16 አባቶች ስለ ልጆች አይገደሉ፥ ልጆችም ስለ አባቶች አይገደሉ ነገር ግን ሁሉ እያንዳንዱ በኃጢአቱ ይገደል።
2ኛ ነገሥት 14፥6 በሙሴ ሕግ መጽሐፍም እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔርም፦ ሁሉ በኃጢአቱ ይሙት እንጂ አባቶች በልጆች አይሙቱ፥ ልጆችም በአባቶች አይሙቱ ብሎ እንዳዘዘ የነፍሰ ገዳዮቹን ልጆች “አልገደለም””።

ይህንን የሰው ደም ያለበት መጽሐፍ ነው እንግዲህ የፍቅር እና የሰላም መጽሐፍ እየተባለ የሚሰበክለት? ፍርዱ ለኅሊና።
መደምደሚያ
ምእመናን አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት ናቸው፦
25፥68 *እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፣ “ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት፣ የማያመነዝሩትም ናቸው፡፡ ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል*፡፡ وَالَّذِينَ لَا يَدْعُونَ مَعَ اللَّهِ إِلَـٰهًا آخَرَ وَلَا يَقْتُلُونَ النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ وَلَا يَزْنُونَ ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ يَلْقَ أَثَامًا

“እነዚያ” የሚለው አንጻራዊ ተውላጠ ስም ቁጥር 62 ላይ “ምእመናን” የሚለው ተክቶ የመጣ ነው። “ይህን” የሚለው ተውላጠ ስም ከአሏህ ሌላ መገዛት፣ አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ፣ ማመንዘን ሲያመለክት፥ ይህንን የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል። አሏህ ነፍስን ያለ ሐቅ መግደል ሐራም አድርጓል፦
17፥33 *”ያቺንም አላህ ያወገዛትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ”*፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ሐርረመ” حَرَّمَ የሚለው ቃል “ከለከለ” ማለት ነው። “ሐራም” حَرَام የሚለው ቃል እራሱ “ክልክል” ማለት ነው። አምላካችን አሏህ አንዲት ነፍስ መግደል ሐራም ስላደረገ “አትግደሉ” የሚል ሕግ አውጥቷል። ግን አንዲት ነፍስ ጥፋት ካጠፋች “በሕግ” ልትገደል ስለምትችል “ያለ ሕግ አትግደሉ” የሚል መርሕ አለ። ሰላማዊ ሰዎችን የገደለ የጀነትን ሽታ እንኳን አያሸትም፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 58 ሐዲስ 08
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምር “ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"የሰላም ቃል ኪዳን የተገባለትን የገደለ የጀነትን ሽታ እንኳን አያሸትም፥ የእርሷ ሽታ የአርባ ዓመታት የጉዞ ርቀት ላይ ይገኛል"*። «عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَنْ قَتَلَ نَفْسًا مُعَاهَدًا لَمْ يَرَحْ رَائِحَةَ الْجَنَّةِ، وَإِنَّ رِيحَهَا يُوجَدُ مِنْ مَسِيرَةِ أَرْبَعِينَ عَامًا ‏

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም