ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.9K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
“ማ የሻኡነ ኢላ አን የሻኣሏህ” وَمَا تَشَاءُونَ إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّه ማለትም “አላህ ካልፈቀደ አትፈቅዱም” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ሰው ይህ ነጻ ፈቃድ ስላለው በፈቃዱ ማመን ወይም መካድ ይችላል፦
18፥29 *«እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ»* በላቸው፡፡ وَقُلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُر

“የሻም ሰው ይመን፥ የሻም ሰው ይካድ” ዛቻ ነው። በኃላ ይጠየቃል፥ ትሩፋትና ቅጣት ይቀበላል። አምላካችን አላህ እርሱ የሚወደው እምነት እና የሚጠላው ክህደት ይህ ነው ብሎ ሁለቱንም የእምነት መንገድ እና የክህደት መንገድ በተከበረ ቃሉ ነግሮናል፦
39፥7 *ብትክዱ አላህ ከእናንተ የተብቃቃ ነው፡፡ ለባሪያዎቹም ከህደትን አይወድም፡፡ ብታመሰግኑም፤ እርሱን ይወድላችኋል*፡፡ إِن تَكْفُرُوا فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنكُمْ ۖ وَلَا يَرْضَىٰ لِعِبَادِهِ الْكُفْرَ ۖ وَإِن تَشْكُرُوا يَرْضَهُ لَكُمْ
2፥256 በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ *ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ*፡፡ لَا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ ۖ قَد تَّبَيَّنَ الرُّشْدُ مِنَ الْغَيِّ ۚ
90፥10 *ሁለትን መንገዶችም አልመራነውምን?* وَهَدَيْنَاهُ النَّجْدَيْنِ
76፥3 *እኛ ወይ አመስጋኝ ወይም ከሓዲ ሲኾን መንገዱን ገለጽንለት*፡፡ إِنَّا هَدَيْنَاهُ السَّبِيلَ إِمَّا شَاكِرًا وَإِمَّا كَفُورًا

ቅኑ የእምነት መንገድ ከጠማማው የክህደት መንገድ ተገልጧል፥ አመስጋኝ ወይም ከሓዲ የመሆን ያለመሆን ምርጫው ተገልጿል። ለዚያ ነው ዛሬ በዓለማችን ላይ ሁለት ተቃራኒ የሆኑ አማኝ እና ከሓዲ ያሉት፦
64፥2 እርሱ ያ የፈጠራችሁ ነው፡፡ *ከእናንተም ከሓዲ አለ፡፡ ከእናንተም አማኝ አለ*፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ተመልካች ነው፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَكُمْ فَمِنكُمْ كَافِرٌ وَمِنكُم مُّؤْمِنٌ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
14፥7 ጌታችሁም *«ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ ብትክዱም እቀጣችኋለሁ፤ ቅጣቴ በእርግጥ ብርቱ ነውና» በማለት ባስታወቀ ጊዜ አስታውሱ*፡፡ وَإِذْ تَأَذَّنَ رَبُّكُمْ لَئِن شَكَرْتُمْ لَأَزِيدَنَّكُمْ ۖ وَلَئِن كَفَرْتُمْ إِنَّ عَذَابِي لَشَدِيدٌ

“ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ” ማለት ለአማንያን የተዘጋጀ ትሩፋት ጀነት እንዳለ የሚጠቁም ነው፥ “ብትክዱም እቀጣችኋለሁ” ማለት ለከሓድያን የተዘጋጀ ቅጣት ጀሃነም እንዳለ የሚጠቁም ነው። ስለዚህ ቅጣትና ሽልማት፣ የተፈቀና የተከለለ ነገር መኖሩ፥ እኩይና ሰናይ ነገር መኖሩ በራሱ ሰው ነጻ ፈቃድ እንዳለው የሚያሳይ ማስረጃ ነው። አንድ ሰው ነጻ ፈቃድ የለኝም ብሎ ሰው ቢገድል፣ ቢሳደብ፣ ቢማታ ወዘተ አይደለም አላህ በአኺራ ሰዎች በዱንያህ ይጠይቁታል። ኢቭን መብቱን ለማስከበር ግዴታውን መወጣቱ በራሱ ሰው ነጻ ፈቃድ እንዳለው ማስረጃ ነው። 
በኢሥላም ዐቂዳህ ውስጥ ሁለት ጠርዘኛ እሳቦት ነበሩ፥ አንደኛው እሳቤ “አል-ጀብሪያህ” الجبرية ማለትም ሰው በአላህ ዕውቀትና ፈቃድ ብቻ የሚኖር ነጻ ፈቃድ የሌለው ፍጡር”Necessitarian” ነው የሚሉ እና ሁለተኛው እሳቤ “አል-ቀደሪያህ” القدريه‎ ማለትም ሰው ያለ አላህ ዕውቀትና ፈቃድ ብቻውን በራሱ ነጻ ፈቃድ ያለው ፍጡር”Libriterian” ነው የሚል ነው። ሁለቱም ጽንፍ ያላቸው እሳቦት በኢሥላም ዐቂዳህ አንዳች ቦታ የላቸውም። ሰው በአላህ ዕውቀትና ፈቃድ ነጻ ፈቃድ ያለው ፍጡር ነው። አምላካችን አላህ ለሰው የሰጠው መልካም እና ክፋ የማሰብ፣ የመናገር፣ የማድረግ ነጻ ምርጫ በችሎታችን ልክ ነው፤ ያለ ችሎታችን ልክ አያስገድደንም፦
23፥62 *ማንኛይቱንም ነፍስ ችሎታዋን እንጂ አናስገድዳትም*፡፡ وَلَا نُكَلِّفُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا
2፥286 *አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም*፡፡ لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا

ኢቭን አላህ ስንፈራው እንኳን የቻልነውን ያክል ነው፥ አላህ የምንፈራው በተረዳነው፣ በገባን፣ በደረስንበትና ባወቅነክ ልክ ነው። ይህ ተገቢ ፍርሃት ነው፦
65፥16 *አላህንም የቻላችሁትን ያክል ፍሩት*፤ ትዕዛዙን ስሙም፤ ታዘዙም፤ ለግሱም፤ ለነፍሶቻችሁ መልካምን ይሰጣችኋልና። فَاتَّقُوا اللَّهَ مَا اسْتَطَعْتُمْ وَاسْمَعُوا وَأَطِيعُوا وَأَنفِقُوا خَيْرًا لِّأَنفُسِكُمْ
3፥102 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *አላህን ተገቢውን መፍራት ፍሩት*፡፡ እናንተም ሙስሊሞች ኾናችሁ እንጅ አትሙቱ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ حَقَّ تُقَاتِهِ وَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ውሸት ጥሩ አይደለም!

"ማተብህን በአንገትህ እሰረው" አይልም፦
ምሳሌ 6፥20-22 ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ትእዛዝ ጠብቅ፥ የእናትህንም ሕግ አትተው፤ ሁልጊዜም በልብህ አኑረው፥ በአንገትህም እሰረው። ስትሄድም ይመራሃል፤ ስትተኛ ይጠብቅሃል፤ ስትነሣ ያነጋግርሃል።

"በአንገትህም እሰረው" የሚለው ማተብን ሳይሆን "የአባትህ ትእዛዝ እና የእናትህን ሕግ" ነው። በአንገት መታሰር እማሬአዊ ሳይሆን ፍካሬአዊ መሆኑን ለማወቅ "ሁልጊዜም በልብህ አኑረው" ይላል። ማተብ ልብ ውስጥ እንዴት ይኖራል? ማተም ይመራልን? ይጠብቃልን? ያነጋግራልን? "ስትሄድም ይመራሃል፤ ስትተኛ ይጠብቅሃል፤ ስትነሣ ያነጋግርሃል" የሚለው የአባትህ ትእዛዝ እና የእናትህን ሕግ ነው። ትእዛዝ መብራት፥ ሕግም ብርሃን ነውና፦
ምሳሌ 6፥23 ትእዛዝ መብራት፥ ሕግም ብርሃን ነውና፥ የተግሣጽም ዘለፋ የሕይወት መንገድ ነውና፥

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
አሥራ ሁለቱ ነገዶች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥20 ሙሳም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ *«ሕዝቦቼ ሆይ የአላህን ጸጋ *በውስጣችሁ ነቢያትን ባደረገ* እና መንግሥትም ባደረጋችሁ ከዓለማትም ለአንድም ያልሰጠውን ችሮታ በሰጣችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ ያደረገውን ጸጋ አስታውሱ፡፡»* وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ يَا قَوْمِ اذْكُرُوا نِعْمَةَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ جَعَلَ فِيكُمْ أَنبِيَاءَ وَجَعَلَكُم مُّلُوكًا وَآتَاكُم مَّا لَمْ يُؤْتِ أَحَدًا مِّنَ الْعَالَمِينَ

“ነቢይ” نبي የሚለው ቃል “ነበአ” نَبَّأَ ማለትም “አወራ” ወይም “ተናገረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን “አውሪ” ወይም “ነጋሪ” ማለት ነው፤ ይህንን እስቲ ከቁርአን እንመልከት፦
66፡3 ነቢዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሠጠረ ጊዜ አስታውስ እርሱንም በነገረችና አላህ እርሱን ማውራትዋን ባሳወቀው ጊዜ ከፊሉን አስታወቀ ከፊሉንም ተወ፤ በእርሱም ባወራት ጊዜ *ይህን ማን “ነገረህ”? አለች፤ ዐዋቂው ውስጠ አዋቂው “ነገረኝ” አላት*። وَإِذْ أَسَرَّ النَّبِيُّ إِلَى بَعْضِ أَزْوَاجِهِ حَدِيثًا فَلَمَّا نَبَّأَتْ بِهِ وَأَظْهَرَهُ اللَّهُ عَلَيْهِ عَرَّفَ بَعْضَهُ وَأَعْرَضَ عَنْ بَعْضٍ فَلَمَّا نَبَّأَهَا بِهِ قَالَتْ مَنْ أَنْبَأَكَ هَذَا قَالَ نَبَّأَنِيَ الْعَلِيمُ الْخَبِيرُ ፤

በዚህ አንቀጽ ውስጥ “ማን ነገረህ” ለሚለው ቃል የገባው “መን አንበአከ” مَنْ أَنْبَأَكَْ ሲሆን “ነገረኝ” ለሚለው ደግሞ “ነበአኒየ” نَبَّأَنِيَ ነው፤ የሁለቱም ግስ ርቢ “ነበአ” نَبَّأَ የሚለው ቃል ነው፤ ስለዚህ ነቢይ ማለት ሁሉን ዐዋቂውና ውስጠ ዐዋቂው አላህ የሚያናግረው እና የሚነግረው ማለት ነው፤ በዚህ ስሌት አሥራ ሁለቱ ነገዶች በሙሳ ዘመን በኢስራኢል ልጆች የተነሱ ነቢያት ናቸው፦
5፥20 ሙሳም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ *«ሕዝቦቼ ሆይ የአላህን ጸጋ *በውስጣችሁ ነቢያትን ባደረገ* እና መንግሥትም ባደረጋችሁ ከዓለማትም ለአንድም ያልሰጠውን ችሮታ በሰጣችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ ያደረገውን ጸጋ አስታውሱ፡፡»* وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ يَا قَوْمِ اذْكُرُوا نِعْمَةَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ جَعَلَ فِيكُمْ أَنبِيَاءَ وَجَعَلَكُم مُّلُوكًا وَآتَاكُم مَّا لَمْ يُؤْتِ أَحَدًا مِّنَ الْعَالَمِينَ

"በውስጣችሁ ነቢያትን ባደረገ ጊዜ" የሚለው ይሰመርበት፤ እነዚህ ነብያት ነገዶቹ ናቸው፤ አላህ ወደ ነገዶቹ ወሕይ አውርዷል፦
4፥163 እኛ ወደ ኑሕና ከርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን ወደ አንተም አወረድን፡፡ ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሓቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ *ወደ ነገዶቹም፣ ወደ ዒሳም፣ ወደ አዩብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሃሩንና፣ ወደ ሱለይማንም አወረድን*፡፡ ለዳውድም ዘቡርን ሰጠነው፡፡ إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَىٰ نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِن بَعْدِهِ ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَعِيسَىٰ وَأَيُّوبَ وَيُونُسَ وَهَارُونَ وَسُلَيْمَانَ ۚ وَآتَيْنَا دَاوُودَ زَبُورًا
3፥84 «በአላህ አመንን፡፡ በእኛ ላይ በተወረደውም፣ በኢብራሂምና በኢስማዒልም፣ በኢስሓቅም፣ በያዕቆብም፣ *በነገዶችም ላይ በተወረደው*፤ ለሙሳና ለዒሳም ለነቢያትም ሁሉ ከጌታቸው በተሰጠው አመንን፡፡ ከእነርሱ መካከል አንድንም አንለይም፡፡ እኛ ለእርሱ ታዛዦች ነን» በል፡፡ قُلْ آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ عَلَيْنَا وَمَا أُنزِلَ عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَالنَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ
2፥136 «በአላህና ወደኛ በተወረደው፣ ወደ ኢብራሂምም ወደ ኢስማዒልና ወደ ኢስሐቅም ወደ ያዕቁብ እና *ወደ ነገዶቹም በተወረደው* በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት በዚያም ነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት ከነርሱ በአንድም መካከል የማንለይ ስንኾን አመንን፤ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን» በሉ፡፡ قُولُوا آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْنَا وَمَا أُنزِلَ إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَمَا أُوتِيَ النَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ

አላህ ወሕይ የሚወርድላቸውን እነዚህን ነገዶች አሥራ ሁለት አለቆች አድርጎ አስነሳቸው፤ ለአሥራ ሁለትም ሕዝቦች ከፋፈላቸው፦
5፥12 *አላህም የእስራኤልን ልጆች የጠበቀ ቃል ኪዳን በእርግጥ ያዘባቸው፡፡ ከእነርሱም አሥራ ሁለትን አለቆች አስነሳን*፡፡ وَلَقَدْ أَخَذَ اللَّهُ مِيثَاقَ بَنِي إِسْرَائِيلَ وَبَعَثْنَا مِنْهُمُ اثْنَيْ عَشَرَ نَقِيبًا
7፥160 *አሥራ ሁለት ነገዶች ሕዝቦች አድርገንም ከፋፈልናቸው*፡፡ ወደ ሙሳም ወገኖቹ መጠጣትን በፈለጉበት ጊዜ «ድንጋዩን በበትርህ ምታው» ስንል ላክን፡፡ መታውም *ከእርሱ አሥራ ሁለት ምንጮችም ፈለቁ*፡፡ وَقَطَّعْنَاهُمُ اثْنَتَيْ عَشْرَةَ أَسْبَاطًا أُمَمًا ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ إِذِ اسْتَسْقَاهُ قَوْمُهُ أَنِ اضْرِب بِّعَصَاكَ الْحَجَرَ ۖ فَانبَجَسَتْ مِنْهُ اثْنَتَا عَشْرَةَ عَيْنًا
ጥንት የአሥራ ሁለቱ አበው የቃልኪዳን መጽሐፍ የነበረ ሲሆን አይሁዳውን በ 90 ድህረ-ልደት”AD” በጀሚኒያ ጉባኤ ውሳኔ የአፓክራፋ መጽሐፍ ብለው ቀንሰውታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አምላካችን አላህ የመጽሐፉ ባለቤቶች ከመጽሐፉ ይሸሽጉት ከነበሩት ብዙውን የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛውን በእርግጥ ልኳል፦
5፥15 *የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን በእርግጥ መጣላችሁ*፡፡ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ قَدْ جَاءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ

“አፓክራፋ” የሚለው ቃል “አፓክራፈስ” ἀπόκρυφος ከሚለው ግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን “ድብቅ” ማለት ነው፤ ከደበቁት መጽሐፍት ውስጥ ካሉት መለኮታዊ ቅሪት አስፈላጊውን አላህ የገለጸ ሲሆን ከደበቁት መጽሐፍት ውስጥ ካሉት መለኮታዊ ቅሪት ብዙውን ትቶታል፤ ወደ ነብያት ምን ተወርዶ እንደነበረ መልእክተኛው እንዲገልጹ ቁርኣንን አውርዷል፦
16፥44 በግልጽ ማስረጃዎችና በመጻሕፍት ላክናቸው፡፡ *ወደ አንተም ለሰዎች ወደ እነርሱ የተወረደውን ልትገልጽላቸው እና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን*፡፡ بِالْبَيِّنَاتِ وَالزُّبُرِ ۗ وَأَنزَلْنَا إِلَيْكَ الذِّكْرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيْهِمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ

ይህ ቁርኣን ከበፊቱ ከአላህ የተወረዱትን የአላህ ንግግሮች የሚያረጋግጥ እና በእነዚያ ንግግሮች ውስጥ ያለውን ጭብጥ የሚዘረዝር ነው፦
10፥37 ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ ከሆነ ፍጡር የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፤ *ግን ያንን ከእርሱ በፊት ያለውን የሚያረጋግጥ እና በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው*፡፡ وَمَا كَانَ هَـٰذَا الْقُرْآنُ أَن يُفْتَرَىٰ مِن دُونِ اللَّهِ وَلَـٰكِن تَصْدِيقَ الَّذِي بَيْنَ يَدَيْهِ وَتَفْصِيلَ الْكِتَابِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِن رَّبِّ الْعَالَمِينَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሠለፊያህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

9፥100 *ከስደተኞቹ እና ከረዳቶቹም ሲኾኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነርሱ ወዷል እነርሱም ወደዋል፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው*፡፡ وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَانٍ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي تَحْتَهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ

“ሠለፍ” سَلَف የሚለው ቃል “ሠለፈ” سَلَفَ ማለትም “ቀደመ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ቀደምት” ማለት ነው፥ አምላካችን አላህ ስለ ቀዳማውያን እንዲህ ይናገራል፦
9፥100 *ከስደተኞቹ እና ከረዳቶቹም ሲኾኑ “የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች” እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነርሱ ወዷል እነርሱም ወደዋል፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው*፡፡ وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَانٍ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي تَحْتَهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ

“የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። እነዚህም “ሶሓቢይ” صَحَابِيّ ሲባሉ የነቢያችን”ﷺ” ውድ “ባልደረባ”companion” ናቸው። እነዚህ ባልደረቦች በሁለት ይከፈላሉ፥ እነርሱም፦ “ሙሃጂር” እና “ነሲር” ናቸው። “ሙሃጂር” مُهَاجِر ማለት “ስደተኛ” ማለት ሲሆን የሙሃጂር ብዙ ቁጥር “ሙሃጂሩን” مُهَاجِرُون ነው፥ ሙሃጂሩን ከመካ ወደ መዲና የተሰደዱትን መካውያን ሶሓባዎችን ያመለክታል። መዲና ላይ ከመካ የተሰደዱትን እረድተው የተቀበሉ ሶሓባዎች “ነሲር” نَصِير ማለትም “ረዳት” በብዜት “አንሷር” أَنْصَار ይባላሉ፦
8፥74 *እነዚያም ያመኑና የተሰደዱ በአላህም መንገድ ላይ የታገሉ፣ እነዚያም ያስጠጉ እና የረዱ እነዚያ እነርሱ በእውነት አማኞች ናቸው፡፡ ለእነሱም ምሕረትና የከበረ ሲሳይ አላቸው*፡፡ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَهَاجَرُوا وَجَاهَدُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَالَّذِينَ آوَوا وَّنَصَرُوا أُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُؤْمِنُونَ حَقًّا ۚ لَّهُم مَّغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ

“የተሰደዱ” የተባሉት ሙሃጂሩን ሶሓቢይ ሲሆኑ “የረዱ” የተባሉት ደግሞ አንሷር ሶሓቢይ ናቸው፥ እነዚህ የመጀመሪያው ትውልድ ናቸው። “የተከተሏቸው” የተባሉት ሁለተኛው ትውልድ “ታቢዒይ” تَابِعِيّ እና ሦስተኛው ትውልድ “ታቢዑ አት-ታቢዒን” تَابِع التَابِعِين ናቸው። እነዚህ ሦስት ትውልድ ሠለፍ ናቸው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 83, ሐዲስ 72
ዒምራን ኢብኑ ሑሰይን እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ከእናንተ ምርጡ የእኔ ትውልድ ነው፥ ቀጥሎ ያሉት እነርሱን የሚከተሉት ነው፥ ለጥቆ ያሉት የሚከተሉትን የሚከተሉ ናቸው”*። قَالَ سَمِعْتُ عِمْرَانَ بْنَ حُصَيْنٍ، يُحَدِّثُ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ خَيْرُكُمْ قَرْنِي، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُمْ، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُم

የመጀመሪያው ትውልድ ሶሓቢይ ነው፣ ቀጥሎ ያሉት እነርሱን የሚከተሉት ታቢዒይ ነው፣ ለጥቆ ያሉት የሚከተሉትን የሚከተሉ ታቢዑ አት-ታቢዒን ናቸው። እነዚህ ሦስት ትውልድ “አሥ-ሠለፉ አስ-ሷሊሑን” ٱلسَلَف ٱلصَالِحُون ማለትም “መልካሞቹ ቀደምት” ሲሆኑ የእነርሱ መንሀጅ ጂሃድ ነው። “መንሀጅ” مَنْهَج ማለት “ፍኖት” “ፋና” “መንገድ” ማለት ነው። “በአላህም መንገድ ላይ የታገሉ” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። “ጂሃድ” جِهَاد የሚለው ቃል “ጃሀደ” جَٰهَدَ ማለትም “ታገለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ትግል” ማለት ነው። “ጁሁድ” جُهْد ማለት “መታገል” ነው፥ ጂሃድ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ በሐቅ እና በባጢል መካከል የሚደረግ ትግል ነው። እውነትን ለማንገሥ ሐሰትን ለማርከስ፥ ከሙገሳ እና ከወቀሳ ነጻ ሆኖ በአላህ መንገድ የሚታገል፣ የሚጥርና የሚጋደል በነጠላ “ሙጃሂድ” مُجَٰهِد ይባላል፥ በብዜት ደግሞ “ሙጃሂዱን” مُجَاهِدُون ይባላሉ፦
49፥15 *ምእምናን እነዚያ በአላህ እና በመልእከተኛው ያመኑት ከዚያም ያልተጠራጠሩት “በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው”፡፡ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው*፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ثُمَّ لَمْ يَرْتَابُوا وَجَاهَدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۚ أُولَـٰئِكَ هُمُ الصَّادِقُونَ

ምእምናን ማለት በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው፥ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 15, ሐዲስ 28
አነሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”በንብረታችሁ፣ በነፍሶቻችሁ እና በአንደበታችሁ ሙሽሪኮችን ታገሉ”*። عَنْ أَنَسٍ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏:‏ ‏ “‏ جَاهِدُوا الْمُشْرِكِينَ بِأَمْوَالِكُمْ وَأَنْفُسِكُمْ وَأَلْسِنَتِكُمْ ‏
እኩይ ድርጊት ለመታገል ሦስት ምርጫ አለን፥ እርሱም፦
1. በእጅ መታገል፣
2. በአንደበት መታገል፣
3. በልብ መታገል ነው፦
ሪያዱ አስ-ሳሊሒን መጽሐፍ 1, ሐዲስ 184
አቢ ሠዒድ አል-ኹድሪይ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ *“ከእናንተ ውስጥ እኩይ ነገር ያየ በእጁ ይቀይረው፣ ካልቻለ በምላሱ ያውግዝ፣ ይህንንም ካልቻለ በልቡ ይጥላው። በልብ መጥላት ደካማው ኢማን ነው”*። عن أبي سعيد الخدري رضي الله عنه قال‏:‏ سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول‏:‏ ‏ “‏من رأى الخد منكرًا فليغيره بيده ، فإن لم يستطع فبلسانه، فإن لم يستطع فبقلبه وذلك أضعف الإيمان
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 86
ዐብደላህ ኢብኑ መሥዑድ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፦ *”አላህ ከእኔ ሕዝብ በፊት ከነቢይ አንድንም አላከም፥ ሡናውን የሚይዙ እና በትእዛዙ የሚመሩ ሐዋርያት እና ባልደረቦች ከሕዝቡ ቢያደርግለት እንጂ። ከዚያም ከእነርሱ በኃላ የማያደርጉትን የሚናገሩ እና ያልታዘዙትን የሚያደርጉ ተተኪዎች ይመጣሉ። እነርሱን በእጁ የታገላቸው እርሱ አማኝ ነው፣ በምላሱ የታገላቸው እርሱ አማኝ ነው፣ በልቡ የታገላቸው እርሱ አማኝ ነው። ከዚህ ውጪ የጎመንዘር ያህል ኢማን የለም”*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ مَسْعُودٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ‏ “‏ مَا مِنْ نَبِيٍّ بَعَثَهُ اللَّهُ فِي أُمَّةٍ قَبْلِي إِلاَّ كَانَ لَهُ مِنْ أُمَّتِهِ حَوَارِيُّونَ وَأَصْحَابٌ يَأْخُذُونَ بِسُنَّتِهِ وَيَقْتَدُونَ بِأَمْرِهِ ثُمَّ إِنَّهَا تَخْلُفُ مِنْ بَعْدِهِمْ خُلُوفٌ يَقُولُونَ مَا لاَ يَفْعَلُونَ وَيَفْعَلُونَ مَا لاَ يُؤْمَرُونَ فَمَنْ جَاهَدَهُمْ بِيَدِهِ فَهُوَ مُؤْمِنٌ وَمَنْ جَاهَدَهُمْ بِلِسَانِهِ فَهُوَ مُؤْمِنٌ وَمَنْ جَاهَدَهُمْ بِقَلْبِهِ فَهُوَ مُؤْمِنٌ وَلَيْسَ وَرَاءَ ذَلِكَ مِنَ الإِيمَانِ حَبَّةُ خَرْدَلٍ ‏

ስለዚህ ሠለፍ ማለት ከላይ የተጠቀሱት ሦስቱ ትውልድ ሲሆኑ የሦስቱ ትውልድ መንሀጅ ደግሞ ጂሃድ ነው። እኛ ደግሞ የእነርሱን ፈለግ መከተል ያለብን ሙዕሚን ነን። ከምእምኖቹ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው በዚህ ዓለም በተሾመበት ጥመት ተሹሞ መጨረሻው እሳት ነው፦
4፥115 ቅኑም መንገድ ለእርሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምእምኖቹ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው በዚህ ዓለም በተሾመበት ጥመት ላይ እንሾመዋለን፤ ገሀነምንም እናገባዋለን፡፡ መመለሻይቱም ከፋች! وَمَن يُشَاقِقِ الرَّسُولَ مِن بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ الْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ الْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِ جَهَنَّمَ ۖ وَسَاءَتْ مَصِيرًا

ይህንን የቀደምት ሠለፎች መንሃጅ የሚተገብር “ሠለፊይ” سَلَفِيّ ይባላል፥ የሠለፊይ ብዙ ቁጥር “ሠለፊዩን” سَلَفِيُّون‎ ነው። "ሠለፊያህ" سَلَفِيَّة ተግባር እንጂ የፊቃ ስም በፍጹም አይደለም። አሥ-ሠለፉ አስ-ሷሊሑን የተረዱበትን እና የተገበሩበትን መንሀጅ ለመረዳትና ለመተግበር ያብቃን፥ አላህ በአሥ-ሠለፉ አስ-ሷሊሑን መንሀጅ የምንመራ ያርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አልገደሉትም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥157 *«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም ረገምናቸው፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነርሱ ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ መገደል በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም*፡፡ وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا الْمَسِيحَ عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ اللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَـٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ لَفِي شَكٍّ مِّنْهُ ۚ مَا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا اتِّبَاعَ الظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًا

አምላካችን አላህ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር ሁሉ የሚያውቀው ነው፤ የፈጠረ አምላክ እርሱ ዕውቀተ ረቂቁ፣ ውስጥ ዐዋቂው ሲኾን አያውቅምን? በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማነው? ማንም የለም፦
25፥6 *«ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው፡፡ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና»* በላቸው፡፡ قُلْ أَنزَلَهُ ٱلَّذِى يَعْلَمُ ٱلسِّرَّ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۚ إِنَّهُۥ كَانَ غَفُورًۭا رَّحِيمًۭا
67፥14 *የፈጠረ አምላክ እርሱ ዕውቀተ ረቂቁ፣ ውስጥ ዐዋቂው ሲኾን አያውቅምን?* أَلَا يَعْلَمُ مَنْ خَلَقَ وَهُوَ اللَّطِيفُ الْخَبِيرُ
4፥87 አላህ ከእርሱ በስተቀር አምላክ የለም፡፡ ወደ ትንሣኤ ቀን በእርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲኾን በእርግጥ ይሰበስባችኋል፡፡ *በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማነው?* اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ لَيَجْمَعَنَّكُمْ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ لَا رَيْبَ فِيهِ ۗ وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ اللَّهِ حَدِيثًا

የመጸሐፉ ሰዎች አይሁድና ክርስቲያኖች የአላህን ንግግር ከሰው ንግግር ጋር በመቀላቀል በርዘውታል፦
3:71 የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! *“እዉነቱን በዉሸት” ለምን ትቀላቅላላችሁ*? “እዉነቱንም” እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን ትደብቃላችሁ? يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ

“እውነት” የተባለው ከአላህ የወረደው ሲሆን “ውሸት” የተባለው ደግሞ የሰው ንግግር በእጆቻቸው ፅፈው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ብለው የቀጠፉት ጭማሬ ነው፦
2:79 *ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው*፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው፡፡ فَوَيْلٌۭ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ ٱلْكِتَٰبَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ ٱللَّهِ لِيَشْتَرُوا۟ بِهِۦ ثَمَنًۭا قَلِيلًۭا ۖ فَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ

የነብያችን”ﷺ” ቅርብ ባልደረባ ኢብኑ ዓባስ”ረ.ዐ.” የሱረቱል በቀራ 2:79 አንቀጽ ሲፈስረው እንዲህ ይላል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 52, ሐዲስ 46:
ኢብኑ አባስ ሲናገር፦ ሙስሊሞች ሆይ ለምን የመጽሐፉ ሰዎችን ትጠይቃላችሁ? በተመሳሳይ መጽሐፋችሁ ከአላህ ዘንድ ለነቢዩ የተወረደው ወቅታቂ ንግግርና የምትቀሩት እያለ? *መጽሐፋ አልተበረዘምን? አላህ ለእናንተ የመጽሐፉ ሰዎች በእጆቻቸው በርዘው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» እንደሚሉ አውርዷል*። حَدَّثَنَا يَحْيَى بْنُ بُكَيْرٍ، حَدَّثَنَا اللَّيْثُ، عَنْ يُونُسَ، عَنِ ابْنِ شِهَابٍ، عَنْ عُبَيْدِ اللَّهِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُتْبَةَ، عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ يَا مَعْشَرَ الْمُسْلِمِينَ، كَيْفَ تَسْأَلُونَ أَهْلَ الْكِتَابِ، وَكِتَابُكُمُ الَّذِي أُنْزِلَ عَلَى نَبِيِّهِ صلى الله عليه وسلم أَحْدَثُ الأَخْبَارِ بِاللَّهِ، تَقْرَءُونَهُ لَمْ يُشَبْ، وَقَدْ حَدَّثَكُمُ اللَّهُ أَنَّ أَهْلَ الْكِتَابِ بَدَّلُوا مَا كَتَبَ اللَّهُ وَغَيَّرُوا بِأَيْدِيهِمُ الْكِتَابَ، فَقَالُوا هُوَ مِنْ عِنْدِ اللَّهِ، لِيَشْتَرُوا بِهِ ثَمَنًا قَلِيلاً أَفَلاَ يَنْهَاكُمْ مَا جَاءَكُمْ مِنَ الْعِلْمِ عَنْ مُسَاءَلَتِهِمْ، وَلاَ وَاللَّهِ مَا رَأَيْنَا مِنْهُمْ رَجُلاً قَطُّ يَسْأَلُكُمْ عَنِ الَّذِي أُنْزِلَ عَلَيْكُمْ.
እውነት የሆነው የአላህ ንግግር ከሰው ንግግር ጋር ስለተቀላቀለ እውነትን ከሐሰት ለመለየት አምላካችን አላህ ቁርአንን አውርዷል፤ “ፉርቃን” فُرْقَان ማለት “እውነትን ከሐሰት የሚለይ” ማለት ነው፦
25፥1 ያ *ፉርቃንን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስጠንቃቂ ይኾን ዘንድ ያወረደው አምላክ ክብርና ጥራት ተገባው*፡፡ تَبَارَكَ ٱلَّذِى نَزَّلَ ٱلْفُرْقَانَ عَلَىٰ عَبْدِهِۦ لِيَكُونَ لِلْعَٰلَمِينَ نَذِيرًا
3፥4 ከእርሱ በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ አወረዳቸው፡፡ *”ፉርቃንንም አወረደ”*፡፡ مِن قَبْلُ هُدًۭى لِّلنَّاسِ وَأَنزَلَ ٱلْفُرْقَانَ

ቁርኣን ፉርቃን ነው፤ እውነትን ከሐሰት ለመለየት ወርዷል፤ ይህንን ካየን ዘንዳ ወደ ዒሳ ጉዳይ ላይ እንግባ፤ የእስራኤልንም ልጆች ነፍሶቻቸው በማትወደው ነገር መልእክተኛ በመጣላቸው ቁጥር ከፊሉን አስተባበሉ፤ ከፊሉንም ይገድላሉ፤ ነቢያትንም ያለ አግባብ በመግደላቸው ምክንያት ረገማቸው፦
2፥87 *ነፍሶቻችሁ በማትወደው ነገር መልክተኛ በመጣላችሁ ቁጥር ከመከተል ትኮራላችሁን? ከፊሉን አስተባበላችሁ፤ ከፊሉንም ትገድላላችሁ*፡፡ أَفَكُلَّمَا جَآءَكُمْ رَسُولٌۢ بِمَا لَا تَهْوَىٰٓ أَنفُسُكُمُ ٱسْتَكْبَرْتُمْ فَفَرِيقًۭا كَذَّبْتُمْ وَفَرِيقًۭا تَقْتُلُون
5፥70 የእስራኤልን ልጆች የጠበቀ ቃል ኪዳን በእርግጥ ያዝንባቸው፡፡ ወደ እነርሱም መልክተኞችን ላክን፡፡ *ነፍሶቻቸው በማትወደው ነገር መልእክተኛ በመጣላቸው ቁጥር ከፊሉን አስተባበሉ፤ ከፊሉንም ይገድላሉ*፡፡ لَقَدْ أَخَذْنَا مِيثَٰقَ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ وَأَرْسَلْنَآ إِلَيْهِمْ رُسُلًۭا ۖ كُلَّمَا جَآءَهُمْ رَسُولٌۢ بِمَا لَا تَهْوَىٰٓ أَنفُسُهُمْ فَرِيقًۭا كَذَّبُوا۟ وَفَرِيقًۭا يَقْتُلُونَ
4፥155 ቃል ኪዳናቸውንም በማፍረሳቸው፣ በአላህም አንቀጾች በመካዳቸው፣ *ነቢያትንም ያለ አግባብ በመግደላቸው* እና «ልቦቻችا ሽፍኖች ናቸው» በማለታቸው ምክንያት ረገምናቸው፡፡ فَبِمَا نَقْضِهِم مِّيثَٰقَهُمْ وَكُفْرِهِم بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَقَتْلِهِمُ ٱلْأَنۢبِيَآءَ بِغَيْرِ حَقٍّۢ وَقَوْلِهِمْ قُلُوبُنَا غُلْفٌۢ ۚ بَلْ طَبَعَ ٱللَّهُ عَلَيْهَا بِكُفْرِهِمْ فَلَا يُؤْمِنُونَ إِلَّا قَلِيلًۭا

በመቀጠል ሁሉም አይሁዳውን ዒሳ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከዝሙት የተወለደ ነው የሚል አቋም አላቸው፤ ፅንሱ ያለ አባት መወለዱን በምን ያውቃሉ? ማንስ ነግሮአቸዋል? ያ ነገር ታምር ቢሆንም መርየም አመንዝራ እንደሆነች በማሰብ በመርየም ላይ ከባድ ቅጥፈትን ቀጥፈዋል፤ ይህንን በማለታቸው አላህ ኮንኗቸዋል፦
4፥156 በመካዳቸውም *በመርየም ላይ ከባድ ቅጥፈትን በመናገራቸውም* ምክንያት ረገምናቸው፡፡ وَبِكُفْرِهِمْ وَقَوْلِهِمْ عَلَىٰ مَرْيَمَ بُهْتَٰنًا عَظِيمًۭا

አላህ ሆን ብሎ ከዝሙት እንደተወለደ ቢያስመስልባቸው ኖሮ ስለቀጠፉ መርገሙ ትርጉም አይኖረውም፤ ግን አይሁዳውያን አሁንም ሁሉም የዝሙት ልጅ ነው የሚል አቋም አላቸው። አንቀጹ እንዲህ ይቀጥላል፦
4፥157 *እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም ረገምናቸው*፡፡ وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا ٱلْمَسِيحَ عِيسَى ٱبْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ ٱللَّهِ

ይህንን ቅጥፈት የእራሳቸው ባይሆን ኖሮ ሰቀልንና ገደልን በማለታቸው ይረግማቸው ነበርን? ሁለቱንም ማለትም ዲቃላ ልጅ ማለታቸውና ሰቀልን ማለታቸው ስለመሰላቸው ነው፤ ግን ሁለቱንም አላህ በግልፅ ነግሯቸዋል፤ እየነገራቸው በመቅጠፋቸው ረገማቸው። እርግማን የበረከት ተቃራኒ ነው፦
4፥157 *አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነርሱ ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም*፡፡ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ ٱلَّذِينَ ٱخْتَلَفُوا۟ فِيهِ لَفِى شَكٍّۢ مِّنْهُ ۚ مَا لَهُم بِهِۦ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا ٱتِّبَاعَ ٱلظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًۢا

ሰቀልን፣ ገደልን እና ተሰቀለ፣ ተገደለ የሚል ትምህርት ስላለ “አልገደሉትም አልሰቀሉትም” የሚለው ይህንን ያሳያል፤ “ሹብ” شُبِّ ማለት “መምሰል” ማለት ነው፤ የሰቀሉትና የገደሉት መስሏቸዋል፤ በእርግጥም አልገደሉትም፤ “ሊገድሉህ ሲያስቡህ ከአንተ ላይ በከለከልኩልህም ጊዜ ያደረግሁልህን ውለታ አስታውስ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ በዚህ ባህርያቸው ዒሳ በተአምራት በመጣባቸውና ከእነርሱ እነዚያ የካዱት ይህ ግልጽ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም ብለው ሊገድሉት ሲያስቡህ አላህ ወሰደው፤ አይሁዶችም ሊገሉት አደሙ አላህም ወደራሱ በመውሰድ አድማቸውን መለሰባቸው፤ አላህም ከአድመኞች ሁሉ በላጭ ነው፦
5፥110 አላህ በሚል ጊዜ አስታውስ፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! በአንተና በእናትህ ላይ የዋልኩላችሁን ጸጋዬን አስታውስ፡፡ … *የእስራኤልንም ልጆች በተአምራት በመጣህባቸውና ከእነርሱ እነዚያ የካዱት ይህ ግልጽ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም ባሉ ጊዜ፣ ሊገድሉህ ሲያስቡህ ከአንተ ላይ በከለከልኩልህም ጊዜ ያደረግሁልህን ውለታ አስታውስ*፡፡ وَإِذْ كَفَفْتُ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ عَنكَ إِذْ جِئْتَهُم بِٱلْبَيِّنَٰتِ فَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِنْهُمْ إِنْ هَٰذَآ إِلَّا سِحْرٌۭ مُّبِينٌۭ
3፥54 *አይሁዶችም አደሙ አላህም አድማቸውን መለሰባቸው፡፡ አላህም ከአድመኞች ሁሉ በላጭ ነው*፡፡ وَمَكَرُوا۟ وَمَكَرَ ٱللَّهُ ۖ وَٱللَّهُ خَيْرُ ٱلْمَٰكِرِينَ
“መከረ” مَكَرَ ማለት “አቀደ” “አሴረ” ማለት ነው፤ “ማኪሪን” مَٰكِرِين ማለት “ሴረኞች” አቃጂዎች” እና “አድመኞች” ማለት ነው፤ አላህ ከማኪሪን ሁሉ በላጭ ነው አለ እንጂ “ማኪር” مَٰكِرِ አልተባለም። “መክር” مَكْر ማለት “ምክር” “እቅድ” “ሴራ” ማለት ነው፤ ለምሳሌ አላህ፦ እነዚያም የካዱት ሊያስሩህ ወይም ሊገድሉህ ወይም ከመካ ሊያወጡህ በአንተ ላይ *”በመከሩብህ”* ጊዜ” ምክራቸውን በመመለስ መለኮታዊ ጥበቃ ለነብያችን አርጎላቸዋል፦
8፤30 እነዚያም የካዱት ሊያስሩህ ወይም ሊገድሉህ ወይም ከመካ ሊያወጡህ በአንተ ላይ *”በመከሩብህ”* ጊዜ አስታውስ፡፡ *”ይመክራሉም”* አላህም *”ተንኮላቸውን ይመልስባቸዋል”*፡፡ አላህም *”ከመካሪዎቹ ሁሉ በላይ ነው”*፡፡ وَإِذْ يَمْكُرُ بِكَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لِيُثْبِتُوكَ أَوْ يَقْتُلُوكَ أَوْ يُخْرِجُوكَ ۚ وَيَمْكُرُونَ وَيَمْكُرُ ٱللَّهُ ۖ وَٱللَّهُ خَيْرُ ٱلْمَٰكِرِينَ

ነብያችንም”ﷺ” በግልጽ፦ “ዒሣ አልሞተም፤ ከትንሳኤ ቀን በፊት ይመጣል” ብለውናል፦
ተፍሲሩል አጥ-ጠበሪ 3፥55
ሐሰን እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም፦ አሉ፦ “ዒሣ አልሞተም፤ ከትንሳኤ ቀን በፊት ይመጣል” قال الحسن: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم لليهود: ” إن عيسَى لم يمتْ، وإنه راجعٌ إليكم قبل يوم القيامة.

ሙፈሲሪን ማለትም የቁርአን አብራሪዎች ይህንን አንቀፅ በማስመልከት የተለያየ ትንተና ስጥተዋል፤ ይህንን ትንተና መነሻ ያደረጉት ቁርኣንን እና ሐዲስን መሰረት አድርገው ሳይሆን ኢስራኢልያት ሪዋያ መሰረት አድርገው ነው፤ በነጥብ አንድ ላይ ያሉትን የወንጌሎች ታሪካዊ ዳራ መሰረት ያደረገ አፈሳሰር ነው፤ ከኢስራኢልያት የሚገኙ ሪዋያ ሙሉ ለሙሉ ትክክል ነው ማለት አይቻልም። ምክንያቱም አንድ ተፍሲር ስሙር አፈሳሰር ነው የሚባለው አንደኛ ከሐዲስ በሚገኘው ሰሒህ ሪዋያ፣ ሁለተኛ ቁርአን በቁርአን ሲፈሰር፤ ሥስተኛ ዐውዱ ላይ የሚገኘው ነጥብ፣ አራተኛ የቁርኣኑ ቋንቋና ሰዋሰዉ በተቀመጠው ነጥብ ነው። ሌላው አይሁዳውያን ዒሳን፦ “የአላህን መልክተኛ እና አልመሲሕ” ነው ሲሉ አምነውበት ሳይሆን የለበጣ ንግግር ነው፤ ለምሳሌ ቁሬሾች ነብያችንን”ﷺ”፦ “ቁርኣን የተወረደለት ሆይ” ብለዋል፤ ያ ማለት ቁርኣን በነብያችን”ﷺ” ላይ መወረዱ አምነውበት ሳይሆን የለበጣ ንግርግ እንደሆነ ሁሉ የአይሁዳውያንም በዚሁ ስሌት የለበጣ ንግግር ነው፦
15፥6 *«አንተ ያ በእርሱ ላይ ቁርኣን የተወረደለት ሆይ! አንተ በእርግጥ ዕብድ ነህ»* አሉም፡፡ وَقَالُوا يَا أَيُّهَا الَّذِي نُزِّلَ عَلَيْهِ الذِّكْرُ إِنَّكَ لَمَجْنُونٌ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወዐላሙ ዐለይኩም
የአሏህ ሁሉን ቻይነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

24፥45 *አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና*፡፡ يَخْلُقُ اللَّهُ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

የምናመልከው አምላክ በአንድ ምንነቱ ላይ ሁሉት ወይም ሦስት ማንነት የሌለበት፤ በአምላክነቱ ላይ ሰውነት የሌለበት፣ በጌትነቱ ላይ ባርነት የሌለበት፣ በሕያውነቱ ላይ ሞት የሌለበት፣ በጥበቃው ላይ እንቅልፍ የሌለበት፣ በኀያልነቱ ላይ ድካም የሌለበት፣ በፈጣሪነቱ ፍጡርነት የሌለበት ነው። መከፋፈል፣ ሰው መሆን፣ ባሪያ መሆን፣ መሞት፣ ማንቀላፋት፣ መድከም፣ መፈጠር የፍጡር ባህርይ ናቸው፤ ፈጣሪ እነዚህን የፍጡራን ባህርይ አይሆንም፤ በእርሱ ባህርይ ውስጥ ማስሆን እንጂ መሆን የሚባል ባህርይ የለውም። ይህንን እሳቤ ለመረዳት ስለ ተቅዲር እሳቤ እስቲ እንይ፦
“ተቅዲር” تَقْدِير ማለት “ሁሉን ቻይነት” ማለት ነው፤ “አል-ቀዲር” القَدِير ማለት “ሁሉን ቻይ” “ከሃሊ ኩሉ” ማለት ሲሆን ከአላህ ስሞች ውስጥ አንዱ ነው፤ “ቀዲር” قَدِير የሚለው ቃል “ቀደረ” قَدَرَ ማለትም “ቻለ” ወይም “ወሰነ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ቃዲር” قَادِر ማለትም “ኃያል” ማለትም ነው፤ “ቀደር” قَدَر ማለት “ችሎታ” ማለት ሲሆን “ቀድር” قَدْر ደግሞ “ውሳኔ” ማለት ነው፤ ይህ የአላህ ባህርይ ነው፤ አላህ “ሁሉን ቻይ” ነው ማለት “ሁሉንም ነገር ማድረግ ይችላል” ማለት ነው፦
24፥45 *አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና*፡፡ يَخْلُقُ اللَّهُ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
5፥17 *የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው*፡፡ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِير
35፥1 *በፍጥረቱ ውስጥ የሚሻውን ይጨምራል፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና*፡፡ يَزِيدُ فِي الْخَلْقِ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
29፥20 *በምድር ላይ ኺዱ፤ መፍጠርንም እንዴት እንደ ጀመረ ተመልከቱ፡፡ ከዚያም፤ አላህ የመጨረሻይቱን መነሳት ያስነሳል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና*» በላቸው፡፡ قُلْ سِيرُوا فِي الْأَرْضِ فَانظُرُوا كَيْفَ بَدَأَ الْخَلْقَ ۚ ثُمَّ اللَّهُ يُنشِئُ النَّشْأَةَ الْآخِرَةَ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

አላህ ቻይነቱ በነገር ሁሉ ነው፤ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል፤ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፤ መፍጠር የፈጣሪ ባህርይ ሲሆን መፈጠር የፍጡር ባህርይ ነው፤ “ነገር ሁሉ” በሚለው ዓረፍተ-ነገር ውስጥ “ነገር” የሚለው ቃል ፍጥረትን እንጂ ፈጣሪን አያካትትም ምክንያቱም ነገር ፍጡር ነው፤ የተፈጠረ ነገር እራሱን አይፈጥርም፤ “ሸይዕ” شَىْء ማለት “ነገር’thing” ማለት ሲሆን አምላካችን አላህ ደግሞ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው፦
39፥62 *አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ
6፥102 ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ *ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው*፤ ስለዚህ ተገዙት፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ ۖ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ فَاعْبُدُوهُ ۚ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ
13፥16 *አላህ ሁሉንም ነገር ፈጣሪ ነው*፤ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው፤ በል፡፡ قُلِ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ
40፥62 ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው፤ *የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው*፤ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ታዲያ ከእምነት ወዴት ትመለሳላችሁ፡፡ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ فَأَنَّىٰ تُؤْفَكُون

ሁሉንም ነገር ሁሉ ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው» ወዲያውም ይኾናል፦
2፥117 ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ *ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው» ወዲያውም ይኾናል*፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
16፥40 *ለማንኛውም ነገር መኾኑን በሻነው ጊዜ ቃላችን ለእርሱ «ኹን» ማለት ብቻ ነው፤ ወዲውም ይኾናል*፡፡ إِنَّمَا قَوْلُنَا لِشَيْءٍ إِذَا أَرَدْنَاهُ أَن نَّقُولَ لَهُ كُن فَيَكُونُ
በባይብል አብርሃምንና ሳራን፣ ዘካሪያስንና ኤልሳቤጥን በስተ-እርጅናቸው ልጅ ለመስጠት የሚሳነው ምንም ነገር እንደሌለ ሁሉ ኢየሱስን ያለ አባት ለማስገኘት የሚሳነው ነገር የለም፦
ዘፍጥረት 18፥14 በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው *ነገር* አለን?
ሉቃስ 1፥37 ለእግዚአብሔር የሚሳነው *ነገር* የለምና።

“ነገር” በሚለው ውስጥ ኢየሱስም እንደሚካተት አንባቢ ልብ ይለዋል፤ ፈጣሪ ነገር ለማስገኘት የሚያቅተው ነገር የለም፤ ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፦
ኤርምያስ 32፥27 እነሆ፥ እኔ የሥጋ ሁሉ አምላክ ያህዌህ ነኝ፤ በውኑ እኔን የሚያቅተኝ *ነገር* አለን?
መክብብ 3፥11 *ነገርን ሁሉ* በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤

“ቴትራ-ግራማተን” Τετραγράμματον ማለት ከቀኝ ወደ ግራ የሚነበቡ አራት ፊደላት “ያህዌህ” יהוה‎ ይባላል፤ “ያህዌህ” ማለት “ሃያ” היה ማለትም “ማድረግ” ወይም “ማስሆን” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “እንዲሆን የሚያደርግ“He Causes to Become” ማለት ነው። “ኤልሻዳይ” אֵל שַׁדַּי ማለት ደግሞ “ሁሉን ቻይ አምላክ” ማለት ነው፤ ፈጣሪ ሁሉን ቻይ ያሰኘው ሁሉን ነገር በማድረግ፣ ልጅ በመስጠት እና ዘር በማብዛት እንጂ ነገር በመሆን ወይም እራሱን በመፍጠሩ አሊያም ሁሉን ነገር በመደረግ አይደለም፦
ኢዮብ 42፥2 *ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ*፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ።
ዘፍጥረት 17፥1 አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና፦ *እኔ ኤልሻዳይ ነኝ* በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጹምም ሁን፤
ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል *አደርጋለሁ፥ እጅግም አበዛሃለሁ* አለው።
ዘፍጥረት 28፥3 *ሁሉን የሚችል አምላክም ለብዙ ሕዝብ ጉባኤ እንድትሆን ይባርክህ፥ ያፍራህ፥ ያብዛህ*፤

ፈጣሪ “ነው” እንጂ “ሆነ” አይባልም፤ ከሆነ ማን አደረገው? እራሱን እራሱ አስገኘ? ፈጣሪ ሁሉን ቻይነቱ በማስሆን እንጂ በመሆን አይደለም፤ በማድረግ እንጂ በመደረግ አይደለም፤ “ሆነ” ከተባለ የሚያስሆን አለ፤ “ተደረገ” ከተባለ አድራጊ አለ፤ የሚያስሆንና የሚያደርግ አድራጊ ፈጣሪ ነው፤ የሚሆንና የሚደረግ ተደራጊ ደግሞ ፍጡር ነው፤ “ሆነ” “ተደረገ” ማለት መለወጥና መለዋወጥን ያሳያል፤ ፈጣሪ አይለወልጥም አይለዋወጥም፦
ሚልክያስ 3፥6 *እኔ ያህዌህ አልለወጥም*፤

በተረፈ ፈጣሪ ነገር መሆን ይችላል ወይም አይችልም ተብሎ በባይብል ላይ ሆነ በቁርኣን ላይ ስላልተቀመጠ ይህ ጥያቄ በራሱ አውራ የሆነ ፍልስፍናዊ ተፋልሶ”philosophical fallacy” ነው። ለምሳሌ ፈጣሪ ሊሸከመው የማይችለውን ድንጋይ መፍጠር ይችላል ወይስ አይችልም? ብዬ ብጠይቅ፤ ሊሸከመው የማይችለውን ድንጋይ መፍጠር ይችላል ቢባል ሁሉን ቻይ አይደለም፤ ምክንያቱም ሊሸከመው የማይችል ድንጋይ ስላለ። ሊሸከመው የማይችለውን ድንጋይ መፍጠር አይችልም ቢባል ሁሉን ቻይ አይደለም፤ ምክንያቱም ሊሸከመው የማይችል ድንጋይ መፍጠር ስላልቻለ። በሁለቱም መልስ ሁሉን ቻይነትነቱን ያበላሸዋል፤ ይህ ጥያቄ ፋላስይ ነው፤ ፈጣሪ ሁሉን ቻይ አለመሆን ይችላል ወይስ አይችልም? ሁሉን ቻይ አለመሆን ካልቻለ ሁሉን ቻይ አይደለም። ሁሉን ቻይ አለመሆን ከቻለ ሁሉን ቻይ አይሆንም። ፈጣሪ መከራን ማስወገድ አይችልም ወይስ መከራን ማስወገድ አይፈልግም? ፈጣሪ መከራን ማስወገድ ካልቻለ ፈጣሪ ደካማ ነው፤ ወይም ፈጣሪ መከራን ማስወገድ ካልፈለገ ፈጣሪ መልካም አይደለም።
ስለዚህ ፈጣሪ ደካማ ነው ወይም መልካም አይደለም፡፡ ይህ አለሌ ጥያቄ መጽሐፍትን ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ስላልሆነ ስሁት ሙግት ነው። ፍልስፍና የተቆላ ገብስ ነው፤ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ግን ሲዘሩት አይበቅልም።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወዐላሙ ዐለይኩም
ሙርተድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

17፥33 *"ያቺንም አላህ ያወገዛትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ"*፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ

ሚሽነሪዎች ጭረውና ተፍጨርጭረው፥ በድንፋና በጋጋታ ኢሥላምን ጭራቅ ለማድረግ እንደ ጓያ ነቃይ የፍለፊቱን መውሰድ ልማዳቸው ነው። ከትልቅ እስከ ደቂቅ ያለ አንዳች ከልካይ የባልቴት እና የወይዛዝርት የቡና ወሬ ሲዶልቱ አጂብ ያሰኛል፥ የአህያ ስጋ አልጋ ሲሉት አመድ ነው። እስቲ ስለ ሙርተድ ከሥረ-መሠረቱ እንይ! "ሙእሚን" مُؤْمِن የሚለው ቃል "አመነ" آمَنَ ማለትም "አመነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አማኝ" ወይም በግዕዙ "ምእመን" ማለት ነው፥ የሙእሚን ብዙ ቁጥር "ሙእሚኑን" مُؤْمِنُون ወይም "ሙእሚኒን" مُؤْمِنِين ሲሆን "አማኞች" ወይም በግእዙ "ምእመናን" ማለት ነው። ምእመናን አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት ናቸው፦
25፥68 *እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፣ "ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት፣ የማያመነዝሩትም ናቸው፡፡ ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል*፡፡ وَالَّذِينَ لَا يَدْعُونَ مَعَ اللَّهِ إِلَـٰهًا آخَرَ وَلَا يَقْتُلُونَ النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ وَلَا يَزْنُونَ ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ يَلْقَ أَثَامًا

"እነዚያ" የሚለው አንጻራዊ ተውላጠ ስም ቁጥር 62 ላይ "ምእመናን" የሚለው ተክቶ የመጣ ነው። "ይህን" የሚለው ተውላጠ ስም ከአሏህ ሌላ መገዛት፣ አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ፣ ማመንዘን ሲያመለክት፥ ይህንን የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል። አሏህ ነፍስን ያለ ሐቅ መግደል ሐራም አድርጓል፦
17፥33 *"ያቺንም አላህ ያወገዛትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ"*፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሐርረመ" حَرَّمَ የሚለው ቃል "ከለከለ" ማለት ነው። "ሐራም" حَرَام የሚለው ቃል እራሱ "ክልክል" ማለት ነው። አምላካችን አሏህ አንዲት ነፍስ መግደል ሐራም ስላደረገ "አትግደሉ" የሚል ሕግ አውጥቷል። ግን አንዲት ነፍስ ጥፋት ካጠፋች "በሕግ" ልትገደል ስለምትችል "ያለ ሕግ አትግደሉ" የሚል መርሕ አለ። በኢሥላም ሸሪዓህ ሥር ሰዎች ወንጀል ሲሠሩ ዝም ተብለው አይታዩም፥ ባይሆን በሕግ ይጠየቃሉ ይገደላሉም። ሙሥሊም የሆኑ ሰዎች ደግሞ በሦስት ወንጀሎች ምክንያት ይገደላሉ፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 28 ሐዲስ 34
ዐብደሏህ ኢብኑ መሥዑድ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ *"ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፥ እኔንም የአላህ መልእክተኛ መሆኔን የመሰከረ የሙሥሊም ደም ማፍሰስ አይቻልም፥ ከሦስት ጉዳይ በስተቀር። እርሱም፦ በጋብቻ ላይ ዝሙት ከሰራ፣ ሰው ከገደለ እና ”ሃይማኖቱን ትቶ ጀመዓውን የሚከፋፍል ከሆነ በስተቀር”*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لاَ يَحِلُّ دَمُ امْرِئٍ مُسْلِمٍ يَشْهَدُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَنِّي رَسُولُ اللَّهِ إِلاَّ بِإِحْدَى ثَلاَثٍ الثَّيِّبُ الزَّانِ وَالنَّفْسُ بِالنَّفْسِ وَالتَّارِكُ لِدِينِهِ الْمُفَارِقُ لِلْجَمَاعَةِ ‏"‏ ‏.‏

ሙሉ ሐዲሱ እንደዚህ ነው፥ ኢማም ቡኻርይ በከፊል፣ ሡነን አቢዳውን፣ ሡነን ነሳኢ፣ ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ፣ ኢብኑ ማጃህ በተመሳሳይ ዘግበውታል። እዚህ ሐዲስ ላይ "አል-ሙፋሪቅ" الْمُفَارِق የሚለው የስም መደብ "ፋረቀ" فَارَقَ ማለትም "ከፈለ" ከሚል የግስ መደብ የመጣ ሲሆን "ከፋፋይ" ማለት ነው። "ጀማዓህ" جَمَاعَة ማለት "ማኅበረሰብ" ማለት ሲሆን ይህንን የሙሥሊም ማኅበረሰብ አሏህ እና መልእክተኛውን በመዋጋት ሊከፋፍል የሚፈልግ በዚህ ሐዲስ መሠረት ቅጣቱ ግድያ ወይም ስቅላ አሊያም ከአገር መባረር ነው፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 3
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ "የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ *"ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፥ ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ መሆኑን የመሰከረ የሙሥሊም ደም መፍሰስ አይቻልም ከሦስት ጉዳይ በስተቀር፦ በጋብቻ ላይ ዝሙት ከሰራ ይወገራል፣ አሏህ እና መልክተኛውን የሚዋጋ ይገደላል ወይም ይሰቀላል አሊያም ከአገር ይባረራል፣ ሰውን ከገደለ ይገደላል"*። عَنْ عَائِشَةَ، رضى الله عنها قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لاَ يَحِلُّ دَمُ امْرِئٍ مُسْلِمٍ يَشْهَدُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ إِلاَّ بِإِحْدَى ثَلاَثٍ رَجُلٌ زَنَى بَعْدَ إِحْصَانٍ فَإِنَّهُ يُرْجَمُ وَرَجُلٌ خَرَجَ مُحَارِبًا لِلَّهِ وَرَسُولِهِ فَإِنَّهُ يُقْتَلُ أَوْ يُصْلَبُ أَوْ يُنْفَى مِنَ الأَرْضِ أَوْ يَقْتُلُ نَفْسًا فَيُقْتَلُ بِهَا ‏"‏ ‏.‏

"ሃይማኖቱን ትቶ ጀመዓውን የሚከፋፍል" የሚለው ምን ማለት እንደሆነ "አሏህ እና መልክተኛውን የሚዋጋ" በሚል ተፈሥሯል። እዚህ ሐዲስ ላይ "ሙሓሪብ" مُحَارِب ማለት "ተዋጊ" ማለት ሲሆን "ሐርብ" حَرْب ማለት እራሱ "ውጊያ" ማለት ነው። አላህንና መልክተኛውን የሚዋጉ እና በምድርም ላይ ለማጥፋት የሚተጉ ሰዎች ቅጣት መገደል ወይም መሰቀል ወይም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በማፈራረቅ መቆረጥ ወይም ከአገር መባረር ነው፦
5፥33 *"የእነዚያ አላህንና መልክተኛውን የሚዋጉ እና በምድርም ላይ ለማጥፋት የሚተጉ ሰዎች ቅጣት መገደል ወይም መሰቀል ወይም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በማፈራረቅ መቆረጥ ወይም ከአገር መባረር ነው፡፡ ይህ በእነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት ነው፡፡ በመጨረሻይቱም ለእነርሱ ከባድ ቅጣት አላቸው"*፡፡ إِنَّمَا جَزَاءُ الَّذِينَ يُحَارِبُونَ اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَيَسْعَوْنَ فِي الْأَرْضِ فَسَادًا أَن يُقَتَّلُوا أَوْ يُصَلَّبُوا أَوْ تُقَطَّعَ أَيْدِيهِمْ وَأَرْجُلُهُم مِّنْ خِلَافٍ أَوْ يُنفَوْا مِنَ الْأَرْضِ ۚ ذَٰلِكَ لَهُمْ خِزْيٌ فِي الدُّنْيَا ۖ وَلَهُمْ فِي الْآخِرَةِ عَذَابٌ عَظِيمٌ
ከኢሥላም ወጥቶ አሏህ እና መልእክተኛውን መዋጋት እና በምድርም ላይ ለማጥፋት መትጋት ማለት በጥቅሉ ዲኑል ኢሥላምን መዋጋት "ኢርቲዳድ" ይባላል። "ኢርቲዳድ" اِرْتِدَاد‎ የሚለው ቃል "ኢርተደ" اِرْتَدَّ‎ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ምልሰት" ማለት ነው፥ ከኢማን በኃላ ወደ ኩፍር የተመለሰ ሰው ደግሞ "ሙርተድ" مُرْتَدّ‎ ይባላል፦
3፥90 *እነዚያ ከእምነታቸው በኋላ የካዱ ከዚያም ክህደትን የጨመሩ ጸጸታቸው ፈጽሞ ተቀባይ የላትም፡፡ እነዚያም የተሳሳቱ እነርሱ ናቸው"*፡፡ إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا بَعْدَ إِيمَانِهِمْ ثُمَّ ازْدَادُوا كُفْرًا لَّن تُقْبَلَ تَوْبَتُهُمْ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الضَّالُّونَ
47፥25 *"እነዚያ ለእነርሱ ቅኑ መንገድ ከተብራራላቸው በኋላ ወደ ኋላቸው የተመለሱት ሰይጣን ለእነርሱ መመለሳቸውን ሸለመላቸው፡፡ ለእነርሱም አዝዘናጋቸው"*፡፡ إِنَّ الَّذِينَ ارْتَدُّوا عَلَىٰ أَدْبَارِهِم مِّن بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُمُ الْهُدَى ۙ الشَّيْطَانُ سَوَّلَ لَهُمْ وَأَمْلَىٰ لَهُمْ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የተመለሱት" ለሚለው የገባው ቃል "ኢርተዱ" ارْتَدُّوا መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። ለምሳሌ እኔ እና ባለቤቴ ልጃችንን፦ "1+1=2 ነው" ብለን ሐቁን አስተምረን ነገር ግን በተቃራኒው በጎን በኩል ሠራተኛችን፦ "1+1=3 ነው" ብትል ቅድሚያ በጠረጴዛ ዙርያ "1+1=3 ነው" ያለችበት ሥነ-አመክንዮ ይጠየቃል፥ አይ፦ "እኔ ተመችቶኛል፥ ስለዚህ ባጢል የሆነውን ትምህርት ማስተማሬን እቀጥላለው" ካለች ያለን ምርጫ የልጁ አእምሮ እንዳይበላሽ እርሷን ማባረር ነው። በተመሳሳይ መልኩ በጀመዓው ላይ ፈሳድ የሚያሰራጭ አንድ ሙርተድ በሙሥሊም ጀመዓውን ውስጥ በባጢል ትምህርት እከፋፍላለው ቢል ቅድሚያ በዓሊሞች ውይይት ይመከራል፥ አልሰማ ካለ ግን ለኡማው ንጽህና ይገደላል። ኡስታዛችን ሷዲቅ”ሐፊዞሁሏህ” ይህንን የተናገረበትን ሙሉውን ዐውደ-ትምህርት ከማቅረብ ይልቅ ከፊትና ከኃላ ቆርጠው ፕሮፓጋንዳቸውን መንዛት ቅጥፈት ነው።

ሚሽነሪዎ የምዕራባውያንን እሳቦትና ርዕዮት ተንተርሰው ይህንን የሙርተድ ቅጣት መናኛ ምክንያት እንደሆነ ለማሳየት መንፈቅፈቃቸውና መነፋረቃቸው የራሳቸውን ባይብል አገላብጠው ካለማየት የሚመጣ የተንሸዋረረና የተውረገረገ፥ የተሳከረና የደፈረሰ መረዳት ነው። በባይብል አንድ ሰው፦ "ከአንዱ አምላክ በስተቀር ሌላ አምላክ እናምልክ" ቢል ለምን አልክ? ተብሎ ውይይት እናድርግ የሚባል ሳይሆን በቀጥታ ይገደላል፦
ዘዳግም 13፥6 *"የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም በብብትህ ያለች ሚስትህ ወይም እንደ ነፍስህ ያለ ወዳጅህ በስውር፦ "*።
ዘዳግም 13፥7 *"ና፥ ሄደን ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ወደ አንተ የቀረቡት ከአንተም የራቁት አንተን ከብበውህ ያሉ አሕዛብ ከሚያመልኩአቸው አማልክት፥ አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ፡ ብሎ ቢያስትህ፥ እሺ አትበለው"*።
ዘዳግም 13፥8 *"አትስማውም፤ ዓይንህም አይራራለት፥ እትማረውም፥ አትሸሽገውም"*።
ዘዳግም 13፥9 *"ነገር ግን ፈጽመህ ግደለው! እርሱን ለመግደል በፊት የአንተ እጅ፥ ከዚያም በኋላ የሕዝቡ ሁሉ እጅ በላዩ ትሁን"*።
ዘዳግም 13፥10 *"ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ካወጣህ ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ሊያርቅህ ወድዶአልና እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው"*።
ዘዳግም 13፥11 *"እስራኤልም ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ፥ እንዲህም ያለ ክፉ ሥራ እንደ ገና በአንተ መካከል አያደርጉም"*።

አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ መጥራት "ክፉ ሥራ " ስለሆነ ጠሪውን "እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው" ይላል። አይደለም ወደ ሺርክ የሚጠራ ይቅርና በግሉ ሌላ አምላክን ሲያምልክ ከተገኘ ይገደል የሚል ወፍራም ትእዛዝ አለ፦
ዘጸአት 22፥20 *"ከእግዚአብሔር በቀር ለአንዳች አምላክ የሚሠዋ ፈጽሞ “ይገደል” וְהִרְג֧וּ "*።
ዘዳግም 17፥3 *"ሄዶም ሌሎች አማልክትን ያመለከ፥ እኔ ላላዘዝኋቸው ለፀሐይና ለጨረቃ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ የሰገደ ቢገኝ"*።
ዘዳግም 17፥4 *"ቢያወሩልህም ብትሰማም፥ ያንን ፈጽመህ መርምር፤ እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ በእስራኤልም መካከል እንዲህ ያለ ርኵሰት እንደ ተሠራ እርግጥ ሆኖ ቢገኝ"*።
ዘዳግም 17፥5 *"ይህን ክፉ ነገር የሠሩትን ያን ወንድ ወይም ያችን ሴት ወደ በርህ ታመጣቸዋለህ፥ እስኪሞቱም ድረስ በድንጋይ ትወግራቸዋለህ"*።

በተግባርም እስራኤላውያን ሆነ ክርስትናው በአውሮፓ ላይ እስከ 19ኛ ክፍለ-ዘመን ይህንን መርሕ ይተገብሩት እንደነበር ታሪክ በወርቃማ ብዕሩ ያሰፈረው ነገር ነው። መጽሐፋችሁን አትመሩበትም ማለት መጽሐፋችሁ ስለ ሙርተድ አይናገርም ማለት አይደለም። “የእስራኤልንም አምላክ የማይፈልግ እንዲገደል መሐላ አለ፦
2ኛ ዜና 15፥12-13 *"በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ይሹ ዘንድ ቃል ኪዳን አደረጉ፤ “የእስራኤልንም አምላክ እግዚአብሔርን የማይፈልግ”፥ ታናሽ ወይም ታላቅ፥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን፥ “ይገደል” ዘንድ ማሉ"*።

"ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከምቢያው ቂጥጥ" ይሉሃል እንደዚህ ነው። ባይብሉን ሳይፈትሹ ሐዲስን መንቀፍ ስሑት ኂስ ነው። አሁንስ ሐዲሱን ለመተቸት ሞራሉ አላችሁን?

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰሠሙ ዐለይኩም
ቁጥር በቁርኣን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

72፥28 እነርሱ ዘንድ ባለው ነገር እውቀቱ የከበበ እና * ነገሩንም ሁሉ “በቁጥር” ያጠቃለለ ሲሆን”* የጌታቸውን መልክቶች ያደረሱ መሆናቸውን ያውቅ ዘንድ ጠባቂ ያደርጋል። لِّيَعْلَمَ أَن قَدْ أَبْلَغُوا رِسَالَاتِ رَبِّهِمْ وَأَحَاطَ بِمَا لَدَيْهِمْ وَأَحْصَىٰ كُلَّ شَيْءٍ عَدَدًا

“ወር” የሚለው ቃል “ሸህር” شَهْر ሲሆን ይህ ቃል በነጠላ በቁርኣን 12 ጊዜ ሰፍሮ ይገኛል፦ (1ኛ. 2:185 2ኛ. 2፥194 3ኛ. 2፥196 4ኛ. 2፥217 5ኛ. 5፥2 6ኛ. 5፥97 7ኛ. 9፥36 8ኛ. 9:37 9ኛ. 34:12 10ኛ.46፥15 11ኛ.58፥4 12ኛ.97፥3)፤ የሚያጅበው የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ዐሥራ ሁለት ወር ነው፤ እነዚህም፦
1ኛ ወር ሙሐረም
2ኛ ወር ሰፈር
3ኛ ወር ረቢዑል-አወል
4ኛ ወር ረቢዑ-ሣኒ
5ኛ ወር ጀማዱል-አወል
6ኛ ወር ጀማዱ-ሣኒ
7ኛ ወር ረጀብ
8ኛ ወር ሻዕባን
9ኛ ወር ረመዷን
10ኛ ወር ሸዋል
11ኛ ወር ዙል-ቀዒዳህ
12ኛ ወር ዙል-ሒጃህ ናቸው፦
9፥36 *የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነርሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው*፡፡ إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ

የዘመናችን የሥነ-ፈለክ ጥናት እንደሚያትተው የጨረቃ ፈለክ ምድራችንን በ 384,408 km በሆነ ዑደት”Revolution” ለመዞር የሚወስድባት ጊዜ 27 ቀናት ነው። አምላካችን አላህም በቁርኣን “ቀመር” قَمَر ማለትም “ጨረቃ” የሚለውን ቃል የተጠቀመው “27” ጊዜ ብቻ ነው። ጨረቃ ፕላኔታችንን በምእራባዊ አቅጣጭ 360 ድግሪ ለመዞር 19 ዓመት ይፈጅባታል።
የሚያስደምመው ነገር “ዓመት” የሚለው ቃል የተጠቀሰው “ሢኒን” سِنِين በብዜት 12 ጊዜ ወይም “ሠናህ” سَنَة በነጠላ 7 ጊዜ በጥቅሉ “19” ጊዜ ብቻ ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት የዓለማቱ ጌታ ነገርን ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ስለሆነ ነው፦
72፥28 እነርሱ ዘንድ ባለው ነገር እውቀቱ የከበበ እና * ነገሩንም ሁሉ “በቁጥር” ያጠቃለለ ሲሆን”* የጌታቸውን መልክቶች ያደረሱ መሆናቸውን ያውቅ ዘንድ ጠባቂ ያደርጋል። لِّيَعْلَمَ أَن قَدْ أَبْلَغُوا رِسَالَاتِ رَبِّهِمْ وَأَحَاطَ بِمَا لَدَيْهِمْ وَأَحْصَىٰ كُلَّ شَيْءٍ عَدَدًا

"ቀናት" የሚለው ቃል በቁርኣን "አያም" أَيَّامٍ ሲሆን 30 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን ለናሙና ያክል ይኸው፦
2:184 2:185 2:196 2:203 3:41 3:140 5:89 7:54 10:3 10:102 11:7 11:65 14:5 22:28 32:4 57:4 69:7 69:24 2:184 3:24 2:203

"ቀን" የሚለው ቃል በቁርኣን "የውም" يَوْم ሲሆን 365 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን ለመዘርዘር ጊዜና ቦታ ጥበት ስላለ ለመርማሪ ትቼዋለው።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ነጃሺይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥83 *”ወደ መልክተኛውም የተወረደውን ቁርኣን በሰሙ ጊዜ እውነቱን ከማወቃቸው የተነሳ ዓይኖቻቸው እንባን ሲያፈሱ ታያለህ፡፡ «ጌታችን ሆይ! አመንን ከመስካሪዎቹም ጋር ጻፈን » ይላሉ”*፡፡ وَإِذَا سَمِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَى الرَّسُولِ تَرَىٰ أَعْيُنَهُمْ تَفِيضُ مِنَ الدَّمْعِ مِمَّا عَرَفُوا مِنَ الْحَقِّ ۖ يَقُولُونَ رَبَّنَا آمَنَّا فَاكْتُبْنَا مَعَ الشَّاهِدِينَ

“አል-ሐበሻህ” الْحَبَشَة ማለት “አሰባሳቢው” ማለት ሲሆን የመን ከሚኖሩ በመህራህ ሕዝቦች መካከል ሲኖሩ “የዕጣን አሰባሳቢዎች” ይባሉ የነበሩ ናቸው። “አል-ሐበሻህ” የመን ከሚኖሩ ከመህራህ ሕዝቦች ወደ ሰሜኑ ክፍል የተሰበሰቡ ሴማዊ ሕዝቦች መጠሪያ ነው። ስለ አል-ሐበሻህ በግርድፉና በሌጣው ካየን ዘንዳ ቁርኣን ሲወርድ በአል-ሐበሻህ ውስጥ ስለ ነገሠው ንጉሥ ደርዝና ፈርጅ ባለው መልኩ እንዳስሳለን።
“ነጃሺይ” نَّجَاشِيَّ ማለት “ንጉሥ” ማለት ሲሆን ወደ ጠቃሽ አመልካች መስተአምር “አል” ال ተደርጎ ሲነበብ “አን-ነጃሺይ” النَّجَاشِيَّ ሲሆን “ንጉሡ”the king” ማለት ነው፥ ይህ ስም የማዕረግ ስም ነው። ይህ ንጉሥ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠት ከ 614–631 ድኅረ-ልደት በአክሱም መንግሥት የነገሠ ንጉሥ ነው፥ የተጸውዖ ስሙም በዐረቢኛ አነባነብ “አስሐማህ” أَصْحَمَة ሲባል፥ በአገራችን “አርማህ” ይባላል። “ንጉሥ አርማህ” በነቢያችን”ﷺ” ሐዲስ በጥቅሉ “አስሐማህ አን-ነጃሺይ” أَصْحَمَةَ النَّجَاشِيِّ ይባላል። ይህ ንጉሥ የነቢያችን”ﷺ” ባልደረቦች ከ 615–616 ድኅረ-ልደት ተቀብሎ አስተናግዷል፥ እንዲሁ እርሱ እና ሹማምንቱ ወደ መልክተኛውም የተወረደውን ሱረቱል መርየምን በሰሙ ጊዜ እውነቱን ከማወቃቸው የተነሳ ዓይኖቻቸው እንባን አንብተዋል፦
5፥83 *”ወደ መልክተኛውም የተወረደውን ቁርኣን በሰሙ ጊዜ እውነቱን ከማወቃቸው የተነሳ ዓይኖቻቸው እንባን ሲያፈሱ ታያለህ፡፡ «ጌታችን ሆይ! አመንን ከመስካሪዎቹም ጋር ጻፈን » ይላሉ”*፡፡ وَإِذَا سَمِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَى الرَّسُولِ تَرَىٰ أَعْيُنَهُمْ تَفِيضُ مِنَ الدَّمْعِ مِمَّا عَرَفُوا مِنَ الْحَقِّ ۖ يَقُولُونَ رَبَّنَا آمَنَّا فَاكْتُبْنَا مَعَ الشَّاهِدِينَ

የንጉሡ መሥለም የኢሥላም ጠል”Islamophobia” አቀንቃኝ የሆነው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እንደዋሸው የአክራሪዎች ፈጠራ ሳይሆን “ጌታችን ሆይ! አመንን ከመስካሪዎቹም ጋር ጻፈን” ብለው በቁርኣኑ ማመናቸውን አምላካችን አላህ በቅዱስ ቃሉ እንደነገረን ነው። ከመጽሐፉም ባለቤቶች ለአላህ ፈሪዎች በአላህ አንቀጾችም ጥቂትን ዋጋ የማይለወጡ እነ ነጃሺይ እና ሹማምንቱ በአላህ እና በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ቁርኣን አምነዋል፦
3፥199 *”ከመጽሐፉም ባለቤቶች ለአላህ ፈሪዎች በአላህ አንቀጾችም ጥቂትን ዋጋ የማይለወጡ ሲኾኑ በአላህ እና በዚያ ወደ እናንተ በተወረደው፥ በዚያም ወደ እነርሱ በተወረደው የሚያምኑ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚያ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው*፡፡ አላህ ምርመራው ፈጣን ነው፡፡ وَإِنَّ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ لَمَن يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْهِمْ خَاشِعِينَ لِلَّهِ لَا يَشْتَرُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۗ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ سَرِيعُ الْحِسَابِ

በአላህ እና በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ቁርኣን ካመኑ ሠልመዋል ማለት ነው። በነቢያችንም”ﷺ” ሐዲስ ላይ ነቢያችን”ﷺ” ነጃሺይ ከመስለምም አልፎ ጻዲቅ ሰው እንደሆነ ነግረውናል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 63, ሐዲስ 103
ጃቢር እንደተረከው፦ “አን-ነጃሺይ በሞተ ጊዜ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ዛሬ ጻዲቅ ሰው ሞቷል፥ ተነሱ! ለወንድማችሁ ለአስሐማህ የግንዘት ጸሎት አድርጉ!”*። عَنْ جَابِرٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم حِينَ مَاتَ النَّجَاشِيُّ ‏ “‏ مَاتَ الْيَوْمَ رَجُلٌ صَالِحٌ، فَقُومُوا فَصَلُّوا عَلَى أَخِيكُمْ أَصْحَمَةَ
“ሷሊሕ” صَالِح ማለት “መልካም” ወይም ጻዲቅ” ማለት ሲሆን የሷሊሕ ብዙ ቁጥር “ሷሊሒን” صَّالِحِين ማለትም “መልካሞች” ወይም “ጻድቃን” ማለት ነው፦
3፥114 *በአላህና በመጨረሻው ቀን ያምናሉ፡፡ በጽድቅ ነገርም ያዛሉ፡፡ ከመጥፎ ነገርም ይከለክላሉ፡፡ በበጎ ሥራዎችም ይጣደፋሉ፡፡ እነዚያም ከመልካሞቹ ናቸው*፡፡ يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَيَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ وَيُسَارِعُونَ فِي الْخَيْرَاتِ وَأُولَـٰئِكَ مِنَ الصَّالِحِينَ
2፥130 ከኢብራሂምም ሕግጋት እራሱን የበደለ ሰው ካልኾነ በስተቀር የሚያፈገፍግ ማነው? ማንም የለም። በቅርቢቱም ዓለም በእርግጥ መረጥነው፥ *በመጨረሻይቱም ዓለም እርሱ ከመልካሞቹ ነው*፡፡ وَمَن يَرْغَبُ عَن مِّلَّةِ إِبْرَاهِيمَ إِلَّا مَن سَفِهَ نَفْسَهُ ۚ وَلَقَدِ اصْطَفَيْنَاهُ فِي الدُّنْيَا ۖ وَإِنَّهُ فِي الْآخِرَةِ لَمِنَ الصَّالِحِينَ

አስሐማህ አን-ነጃሺይ “ሷሊሕ” መባሉን አስተውል። ከዚያ በመቀጠል እርሱ የነቢያችን”ﷺ” ባልደረቦች የሃይማኖት ወንድም ስለሆነ “አኺኩም” أَخِيكُمْ ማለትም “ወንድማችሁ” ተብሏል። ምእመናን ደግሞ ወንድማማቾች ናቸው፦
49፥10 *”ምእመናን ወንድማማቾች ናቸው”*፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 63, ሐዲስ 106
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” ለባልደረቦቻቸው ስለ ስለዚያ ቀን ስለሞተበት ስለ ሐበሻው አን-ነጃሺይ ሞት እንደነገሯቸው፦ *”ለወንድማችሁ ኢሥቲግፋር አርጉ!”*። أَنَّ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَخْبَرَهُمَا أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم نَعَى لَهُمُ النَّجَاشِيَّ صَاحِبَ الْحَبَشَةِ فِي الْيَوْمِ الَّذِي مَاتَ فِيهِ، وَقَالَ ‏ “‏ اسْتَغْفِرُوا لأَخِيكُمْ ‏”‌‏

በኢሥላም “ሶላቱል ጀናዛህ” صَلَاة الجَنَازَة ማለትም “የግንዘት ጸሎት” የሚደረገው ለሙሥሊም ብቻ ነው። ለንጉሥ አርማህ ደግሞ የሶላቱል ጀናዛህ ክፍል የሆነው “ሶላቱል ጋኢብ” صَلَاة الغَائِبٌ ማለትም “የሩቅ ጀናዛህ” ተደርጓል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 63, ሐዲስ 105
ጃቢር አብኑ ዐብደሏህ እንደተረከው፦ *”ነቢዩም”ﷺ” አስሐማህ አን-ነጃሺይ ላይ የግንዘት ጸሎት አድርገዋል፥ አራት ተክቢራህ በእርሱ ላይ አድርገዋል”*። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ ـ رضى الله عنهما أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم صَلَّى عَلَى أَصْحَمَةَ النَّجَاشِيِّ، فَكَبَّرَ عَلَيْهِ أَرْبَعًا‏

ከላይ የተዘረዘሩት ሐዲሳት ንጉሥ አርማህ የአላህ ጥሪ ተውሒድን እንደተቀበለ ፍንትውና ቁልጭ አድርጎ ያሳያሉ። ስለዚህ የኢሥላም ጠል አቀንቃኝ የሆነው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በማኅበራዊ መገናኛ-ብዙኃን ላይ የነዛው ጨባጣና ለማጣ ወሬ እንዲህ ድባቅ ይገባል። አስሐማህ አን-ነጃሺይ መሥለሙ በዓለም የሚገኝ መላው ሙሥሊም ሁሉ የሚቀበለው እውነታ ነው። ይህን እውነታ አለመቀበል ትችላለክ፥ ግን ይህ ትርክት የአክራሪዎች እንጂ የሁሉም ሙሥሊም እንዳይደለ ለመቅጠፍ የሞከርከው ቅጥፈት ለዛሬ አልተሳካልህም። በአፈ-ጮሌነት ቤተ-መንግሥት እንደገባከው በአፈ-ጮሌነት ጀነት አትገባም። ግልባጩን ለመምህር አባይነህ ካሴ አድርሱልኝ! አላህ ሂዳያህ ይስጣችሁ፥ ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 69, ሐዲስ 1
አቢ መሥዑድ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አንድ ሙሥሊም አንድ ነገር ለቤተሰቡ ወጪ አርጎ ሲያወጣ አላህ ገንዘቡን ሶደቃ እንዳዎጣ ይቆጥርለታል"*። عَنْ أَبِي مَسْعُودٍ الأَنْصَارِيِّ، فَقُلْتُ عَنِ النَّبِيِّ فَقَالَ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ إِذَا أَنْفَقَ الْمُسْلِمُ نَفَقَةً عَلَى أَهْلِهِ وَهْوَ يَحْتَسِبُهَا، كَانَتْ لَهُ صَدَقَة

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
አያሙል ቢድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

"የውም" يَوْم ማለት በነጠላ "ቀን" ማለት ነው፥ የየውም ብዙ ቁጥር ደግሞ "አያም" أَيَّامٍ ሲሆን "ቀናት" ማለት ነው። "አል-ቢድ" الْبِيضِ ማለት "አስኳል" ማለት ነው። በጥቅሉ "አያሙል ቢድ" أَيَّامُ الْبِيضِ ማለት "የቀናት አስኳል" ማለት ነው፥ በጨረቃ አቆጣጠር ወር በገባ አሥራ ሦስተኛ፣ አሥራ አራተኛው እና አሥራ አምስተኛው ቀናት "አያሙል ቢድ" ይባላሉ፦
ሡነን ነሳኢ መጽሐፍ 22 , ሐዲስ 331
ጀሪር ኢብኑ ዐብደሏህ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ከወር ሁሉ ለሦስት ቀናት መፆም የሁልጊዜ መጾም ነው፥ የአያሙል ቢድ ጮራዎች አሥራ ሦስተኛ፣ አሥራ አራተኛው እና አሥራ አምስተኛው ቀናት ናቸው"*። عَنْ جَرِيرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ صِيَامُ ثَلاَثَةِ أَيَّامٍ مِنْ كُلِّ شَهْرٍ صِيَامُ الدَّهْرِ وَأَيَّامُ الْبِيضِ صَبِيحَةَ ثَلاَثَ عَشْرَةَ وَأَرْبَعَ عَشْرَةَ وَخَمْسَ عَشْرَةَ ‏"‏

ወር በገባ ለሦስት ቀናት የፆመ ወሩን ሙሉ እንደፆመ ነው። ምክንያቱም አምላካችን አላህ አንድ መልካም ሥራ ምንዳው አሥር እጥፍ እንደሆነ በቅዱስ ቃሉ ነግሮናል፦
6፥160 *”በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ዐሥር ብጤዎችዋ አሉት”*፡፡ በክፉ ሥራም የመጣ ሰው ብጤዋን እንጅ አይመነዳም፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡ مَن جَاءَ بِالْحَسَنَةِ فَلَهُ عَشْرُ أَمْثَالِهَا ۖ وَمَن جَاءَ بِالسَّيِّئَةِ فَلَا يُجْزَىٰ إِلَّا مِثْلَهَا وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

ስለዚህ አንድ መልካም ሥራ አሥር ብጤዎች ካሉት ሦስት ቀናት መፆም የአንድ ወር ምንዳ አለው። 3×10= 30 ቀናት ወይም 1 ወር ይሆናል። ይህ ከነቢያችን"ﷺ" የተገኘ ሡናህ ነው፥ አምላካችን አሏህ፦ "መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት" ስላለ ይህንን ሡናህ ከእሳቸው ተቀብለናል፦
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

ያ ሙበሽሪን! እንዲህ በጨዋ ደንብ እና በሥነ-ምግባር አግባብ ስትጠይቁ ያምርባችኃል፥ አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መሓላ እና ማካካሻው

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥225 *"በመሐላዎቻችሁ በውድቁ ሳታስቡ በምትምሉት አላህ አይዛችሁም፡፡ ግን ልቦቻችሁ ባሰቡት ይይዛችኋል*፡፡ አላህም በጣም መሐሪ ታጋሽ ነው፡፡ لَّا يُؤَاخِذُكُمُ اللَّهُ بِاللَّغْوِ فِي أَيْمَانِكُمْ وَلَـٰكِن يُؤَاخِذُكُم بِمَا كَسَبَتْ قُلُوبُكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ حَلِيمٌ

"የሚን" يَمِين ማለት በነጠላ "መሓላ" ማለት ሲሆን "የየሚን" ብዙ ቁጥር በብዜት ደግሞ "አይማን" أَيْمَان ነው። ሰዎች ሆን ብለው ለውሸት ብለው ወይም ክብራቸውን እንዳይነካ በሚምሉት መሓላ አላህ ይጠይቃቸዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 52, ሐዲስ 35
ኢብኑ መሥዑድ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ማንም ንብረት ለመያዝ መሓላን በውሸት የሚይዝ አሏህን በተገናኘ ጊዜ በውሸት መሓላው አሏህ ይቆጣዋል"*። عَنِ ابْنِ مَسْعُودٍ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَنْ حَلَفَ عَلَى يَمِينٍ لِيَقْتَطِعَ بِهَا مَالاً لَقِيَ اللَّهَ وَهْوَ عَلَيْهِ غَضْبَانُ ‏"‌‏

ሆን ተብሎ በልብ ተወጥኖ የሚማል መሓላ የሚያስጠይቅ እና የሚያስቀጣ ሲሆን በውድቁ ሳናስበውና ሳንወጥን በምንምለው ግን አያስጠይቅም አያስቀጣም፦
2፥225 *"በመሐላዎቻችሁ በውድቁ ሳታስቡ በምትምሉት አላህ አይዛችሁም፡፡ ግን ልቦቻችሁ ባሰቡት ይይዛችኋል*፡፡ አላህም በጣም መሐሪ ታጋሽ ነው፡፡ لَّا يُؤَاخِذُكُمُ اللَّهُ بِاللَّغْوِ فِي أَيْمَانِكُمْ وَلَـٰكِن يُؤَاخِذُكُم بِمَا كَسَبَتْ قُلُوبُكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ حَلِيمٌ

"ልቦቻችሁ ባሰቡት ይይዛችኋል" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። "ለግው" لَغْو የሚለው ቃል "አልገ" ٱلْغَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ሆን ሳይባል"unintentional" ማለት ነው። ነገር ግን ዐውቀን በድፍረት ሆነ ሳናውውቅ በስህተት ለማልነው መሓላ ማካካሻ አሥርን ምስኪኖች ማብላት ወይም እነርሱን ማልበስ አሊያም ጫንቃን ነጻ ማውጣት ነው፥ ከተባሉት አንዱን ያላገኘም ሰው ሦስት ቀኖችን መፆም ነው፦
5፥89 *"አላህ በመሐላዎቻችሁ በውድቁ አይዛችሁም፥ ግን መሐላዎችን ባሰባችሁት ይይዛችኋል፡፡ ማስተሰሪያውም ቤተሰቦቻችሁን ከምትመግቡት ከመካከለኛው ምግብ አሥርን ምስኪኖች ማብላት ወይም እነርሱን ማልበስ ወይም ጫንቃን ነጻ ማውጣት ነው፥ ከተባሉት አንዱን ያላገኘም ሰው ሦስት ቀኖችን መፆም ነው። ይህ በማላችሁ ጊዜ የመሐላዎቻችሁ ማካካሻ ነው፡፡ መሐላዎቻችሁንም ጠብቁ! እንደዚሁ አላህ ለእናንተ አንቀጾችን ያብራራል፡፡ እናንተ ልታመሰግኑ ይከጀላልና"*፡፡ لَا يُؤَاخِذُكُمُ اللَّهُ بِاللَّغْوِ فِي أَيْمَانِكُمْ وَلَـٰكِن يُؤَاخِذُكُم بِمَا عَقَّدتُّمُ الْأَيْمَانَ ۖ فَكَفَّارَتُهُ إِطْعَامُ عَشَرَةِ مَسَاكِينَ مِنْ أَوْسَطِ مَا تُطْعِمُونَ أَهْلِيكُمْ أَوْ كِسْوَتُهُمْ أَوْ تَحْرِيرُ رَقَبَةٍ ۖ فَمَن لَّمْ يَجِدْ فَصِيَامُ ثَلَاثَةِ أَيَّامٍ ۚ ذَٰلِكَ كَفَّارَةُ أَيْمَانِكُمْ إِذَا حَلَفْتُمْ ۚ وَاحْفَظُوا أَيْمَانَكُمْ ۚ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمْ آيَاتِهِ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ

"ማስተሰሪያ" ለሚለው ቃል የገባው “ከፍፋራህ” كَفّارَة መሆኑን ልብ በል። “ከፍፋራህ” كَفّارَة የሚለው ቃል "ከፍፈረ" كَفَّرَ‎ ማለትም "ሸፈነ" "አስተሰረየ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ማስተሰረያ" "ማካካሺያ" ማለት ነው። መልካም ነገርን ላለመሥራት፣ አላህንም ላለመፍራት፣ በሰዎችም መካከል ላለማስታረቅ መሓላን መጠቀም ሐራም ነው፥ አንድ ሰው ሌላው በሚጎዳ ነገር ከማለም ከፍፋራህ ያወጣል። መኃላ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ካመዘነ ለመሐላህ መፍረስ ማስተሰሪያ የተሻለ ነገር አሥርን ምስኪኖች ማብላት ወይም እነርሱን ማልበስ አሊያም ጫንቃን ነጻ ማውጣት ነው፥ ከተባሉት አንዱን ያላገኘም ሰው ሦስት ቀኖችን መጾም ነው፦
2፥224 *"መልካም እንዳትሠሩ፣ አላህንም እንዳትፈሩ፣ በሰዎችም መካከል እንዳታስታርቁ ለመሐላዎቻችሁ ግርዶ አታድርጉ"*፡፡ አላህም ሰሚ አዋቂ ነው፡፡ وَلَا تَجْعَلُوا اللَّهَ عُرْضَةً لِّأَيْمَانِكُمْ أَن تَبَرُّوا وَتَتَّقُوا وَتُصْلِحُوا بَيْنَ النَّاسِ ۗ وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 83, ሐዲስ 5
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"በአሏህ ይሁንብኝ! ከእናንተ ማናቸውም ቢሆኑ ቤተሰቡን ሊጎዳ የሚችል መሐላ ከፈጸመ መሓላውን ካፈረሰው ይልቅ ታላቅ ኃጢአት ነው፥ ስለዚህ ከፋራውን ያውጣ!*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَنِ اسْتَلَجَّ فِي أَهْلِهِ بِيَمِينٍ فَهْوَ أَعْظَمُ إِثْمًا، لِيَبَرَّ ‏"‌‏.‏ يَعْنِي الْكَفَّارَةَ‏.‏
ሡነን ነሣኢ መጽሐፍ 35, ሐዲስ 24
ዐብዱ አር-ረሕማን ኢብኑ ሠሙራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"መሓላን በማልህ ጊዜ ከእርሷ የሚሻውን ነገር ካየህ ከዚያ ለመሐላህ መፍረስ ማስተሰሪያ የተሻለ ነገር አድርግ! "*። عَنْ عَبْدِ الرَّحْمَنِ بْنِ سَمُرَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ إِذَا حَلَفْتَ عَلَى يَمِينٍ فَرَأَيْتَ غَيْرَهَا خَيْرًا مِنْهَا فَكَفِّرْ عَنْ يَمِينِكَ وَائْتِ الَّذِي هُوَ خَيْرٌ ‏"‏
ስለዚህ ቁርኣኑ ሆነ ሐዲሱ "በውሸት ማሉ እና መሓላችሁን አፍርሱ" በፍጹም አይልም። አሏህ ላይ ማመጽ ወይም ሰው የሚጎዳ ነገር ካልሆነ በስተቀር መሓላ ማፍረስ በራሱ ሐራም ነው፥ የውሸት መሓላ ደግሞ ከዐበይት ኃጢአቶች አንዱ ነው፦
16፥91 ቃል ኪዳንም በገባችሁ ጊዜ በአላህ ቃል ኪዳን ሙሉ፡፡ *"መሓሎቻችሁንም ከአጠነከራችኋት በኋላ አላህን በእናንተ ላይ በእርግጥ መስካሪ ያደረጋችሁ ስትኾኑ አታፍርሱ"*፡፡ አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃልና፡፡ وَأَوْفُوا بِعَهْدِ اللَّهِ إِذَا عَاهَدتُّمْ وَلَا تَنقُضُوا الْأَيْمَانَ بَعْدَ تَوْكِيدِهَا وَقَدْ جَعَلْتُمُ اللَّهَ عَلَيْكُمْ كَفِيلًا ۚ إِنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ مَا تَفْعَلُونَ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 83, ሐዲስ 53
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምሪው እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" አሉ፦ *"ዐበይት ኃጢአቶች በአሏህ ላይ ማሻረክ፣ ወላጆችን አለማክበር፣ ነፍስን መግደል እና የውሸት መሓላ ናቸው"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ الْكَبَائِرُ الإِشْرَاكُ بِاللَّهِ، وَعُقُوقُ الْوَالِدَيْنِ، وَقَتْلُ النَّفْسِ، وَالْيَمِينُ الْغَمُوسُ ‏"‌‏.‏

እንዲህ ጥያቄ ለመጠየቅ ቅንነቱ ካለ መተናነሱ ይታከልበታል፥ መተናነስ ደግሞ ከትህትና ወደ ልዕልና፣ ከእርደት ወደ እርገት፣ ከቀንበር ወደ መንበር የሚያሸጋግር መጓጓዣ ነው። ዛሬ ብዙ ወደ ኢሥላም የመጡ ሺ በክንፉ ሺ በአክናፉ የተባለላቸው ትሁታን ሚስጥራቸው በመተናነስ መጠየቃቸው ነውና በቅንነት ጠይቁ!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም