ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.4K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
አልገደሉትም

@ገቢር አንድ

http://bit.ly/2HWzE0a

@ገቢር ሁለት

http://bit.ly/2HUcLuz

@ገቢር ሦስት

http://bit.ly/2HSQxJa

@ገቢር አራት

http://bit.ly/2HYIDOy

@ገቢር አምስት

http://bit.ly/2HWJ3Fd
የመጨረሻው ቀን

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

33፥21 ለእናንተ *አላህን እና "የመጨረሻውን ቀን" የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አላችሁ*፡፡ لَّقَدْ كَانَ لَكُمْ فِي رَسُولِ اللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِّمَن كَانَ يَرْجُو اللَّهَ وَالْيَوْمَ الْآخِرَ وَذَكَرَ اللَّهَ كَثِيرًا

“ዱንያ” دُّنْيَا ማለት “ቅርቢቱ” ማለት ሲሆን የምንኖርበት ይህንን ዓለም ያመለክታል፥ “አኺራህ” آخِرة ማለት “መጨረሻይቱ” ማለት ሲሆን የሚቀጥለውን ዓለም ያመለክታል። የዚህ ዓለም የሚያበቃበት ቀን "የመጨረሻው ቀን ነው። "የመጨረሻው ዘመን ጥናት”Eschatology” በኢሥላም “አል-አኺሩ አዝ-ዘማን” الْآخِر الْزَمَان ይባላል፥ በቁርኣን "የውመል አኺር" يَوْم الْآخِر ማለትም "መጨረሻው ቀን" ተብሎ ብዙ ቦታ ተጠቅሷል፥ ከስድስቱ አርካኑል ኢማን መካከልም አንዱ "በመጨረሻው ቀን" ማመን ነው፦
33፥21 ለእናንተ *አላህን እና "የመጨረሻውን ቀን" የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አላችሁ*፡፡ لَّقَدْ كَانَ لَكُمْ فِي رَسُولِ اللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِّمَن كَانَ يَرْجُو اللَّهَ وَالْيَوْمَ الْآخِرَ وَذَكَرَ اللَّهَ كَثِيرًا
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 5
ዑመር ኢብኑ ኽጣብ እንዳስተላለፈው፦ “አንድ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰና በጣም ጥቁር ጸጉር ያለው ሰው በመጣ ጊዜ ከአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ጋር ነበርን፤ ወደ እርሳቸው ሲጓዝ አይታይም ነበር፤ ወደ ነብዩ”ﷺ” እስከሚደርስ ድረስ ከእኛ መካከል ማንም ዐላወቀውም፤ ጉልበቱን በእራሳቸው ጉልበት ተቃራኒ አድርጎ ከዚያም እንዲህ አለ፦ *”ሙሐመድ ሆይ! ኢማን ምንድን ነው? እርሳቸውም፦ “በአላህ ማመን፣ በመላእክቱ ማመን፣ በመጽሐፍቱ ማመን፣ በነቢያቱ ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን እና በሰናይ እና እኩይ ቀደር ማመን ነው” አሉ*። ‏ قَالَ عُمَرُ بْنُ الْخَطَّابِ كُنَّا عِنْدَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَجَاءَ رَجُلٌ شَدِيدُ بَيَاضِ الثِّيَابِ شَدِيدُ سَوَادِ الشَّعَرِ لاَ يُرَى عَلَيْهِ أَثَرُ السَّفَرِ وَلاَ يَعْرِفُهُ مِنَّا أَحَدٌ حَتَّى أَتَى النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم فَأَلْزَقَ رُكْبَتَهُ بِرُكْبَتِهِ ثُمَّ قَالَ يَا مُحَمَّدُ مَا الإِيمَانُ قَالَ ‏”‏ أَنْ تُؤْمِنَ بِاللَّهِ وَمَلاَئِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ وَالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ

"የውም" يَوْم ማለት "ቀን" ማለት ሲሆን መአልት እና ሌሊት ያቀፈ የሀያ አራት ሰዓት እርዝማኔ ብቻ ሳይሆን ፍርድ የሚከናወንበት አንድ ሺህ ዓመት ያመለክታል፦
22፥47 አላህም ቀጠሮውን በፍጹም የማይጥስ ሲሆን በቅጣት ያቻኩሉሃል፡፡ *"እጌታህም ዘንድ አንዱ ቀን ከምትቆጥሩት ቀን እንደ ሺሕ ዓመት ነው"*፡፡ وَيَسْتَعْجِلُونَكَ بِالْعَذَابِ وَلَن يُخْلِفَ اللَّهُ وَعْدَهُ ۚ وَإِنَّ يَوْمًا عِندَ رَبِّكَ كَأَلْفِ سَنَةٍ مِّمَّا تَعُدُّونَ
32፥5 *"ነገሩን ሁሉ ከሰማይ ወደ ምድር ያዘጋጃል፡፡ ከዚያም ከምትቆጥሩት ዘመን ልኩ ሺህ ዓመት በሆነ ቀን ውስጥ ወደ እርሱ ይወጣል"*፡፡ يُدَبِّرُ الْأَمْرَ مِنَ السَّمَاءِ إِلَى الْأَرْضِ ثُمَّ يَعْرُجُ إِلَيْهِ فِي يَوْمٍ كَانَ مِقْدَارُهُ أَلْفَ سَنَةٍ مِّمَّا تَعُدُّونَ

ይህ የመጨረሻ ቀን፦
"የውመል መውዑድ" يَوْم الْمَوْعُودِ
"የውሙል ሐቅ" يَوْمُ الْحَقّ
"የውሙል ኹሩጅ" يَوْمُ الْخُرُوج
"የውመል ቂያማህ" يَوْمَ الْقِيَامَة
"የውሚ አድ-ዲን" يَوْمِ الدِّين
"የውመል ፈትሕ" يَوْمَ الْفَتْح
"የውመል ጀምዕ" يَوْمِ الْجَمْع
"የውሙል ፈስል" يَوْمُ الْفَصْل
"የውመ አት-ተላቅ" يَوْمَ التَّلَاق
"የውሚል ሒሣብ" يَوْمِ الْحِسَاب
"የውመ አት-ተናድ" يَوْمَ التَّنَاد
"የውሙል ወዒድ" يَوْمُ الْوَعِيد
"የውመል ሐሥራህ" يَوْمَ الْحَسْرَة
"የውሙም መሽሁድ" يَوْمٌ مَّشْهُود
"የውሙል ኹሉድ" يَوْمُ الْخُلُود ተብሏል።
ይህንን ጥርስ እና ምላሱን እየነቀስን ኢንሻላህ ነጥብ በነጥብ እናያለን፦
ነጥብ አንድ
"የውመል መውዑድ"
"የውመል መውዑድ" يَوْم الْمَوْعُودِ ማለት "የተቀጠረው ቀን" ማለት ነው፦
85፥2 *"በተቀጠረው ቀንም እምላለው"*። وَالْيَوْمِ الْمَوْعُودِ

አላህ ፍጥረትን ወሮታና አጸፌታ፥ ምንዳና ትሩፋት የሚከፍበትን ቀን ቀጥሯል። ይህ ቀጠሮ መጪ ነው፥ በዚያ ቀን ሰማዩ ተሰንጣቂ ነው፥ ቀጠሮው ተፈጻሚ ነው። ከሃድያን ቢዚያ ቀን፦ "ይህ ያ አዛኙ ጌታ በእርሱ የቀጠረን መልክተኞቹም እውነትን የነገሩን ነው" ይላሉ፦
29፥5 *የአላህን መገናኘት ተስፋ የሚያደርግ ሰው ይዘጋጅ፡፡ የአላህ ቀጠሮ በእርግጥ መጪ ነውና*፡፡ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡ مَن كَانَ يَرْجُو لِقَاءَ اللَّهِ فَإِنَّ أَجَلَ اللَّهِ لَآتٍ ۚ وَهُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ
34፥30 *«ለእናንተ ከእርሱ አንዲትንም ሰዓት የማትዘገዩበት የማትቀድሙበትም የቀጠሮ ቀን አላችሁ» በላቸው*፡፡ قُل لَّكُم مِّيعَادُ يَوْمٍ لَّا تَسْتَأْخِرُونَ عَنْهُ سَاعَةً وَلَا تَسْتَقْدِمُونَ
73፥18 *"ሰማዩ በእርሱ በዚያ ቀን ተሰንጣቂ ነው፡፡ ቀጠሮው ተፈጻሚ ነው*፡፡ السَّمَاءُ مُنفَطِرٌ بِهِ ۚ كَانَ وَعْدُهُ مَفْعُولًا
36፤52 *«ወይ ጥፋታችን! ከመኝታችን ማን ቀሰቀሰን? ይህ ያ አዛኙ ጌታ በእርሱ የቀጠረን መልክተኞቹም እውነትን የነገሩን ነው» ይላሉ*፡፡ قَالُوا يَا وَيْلَنَا مَن بَعَثَنَا مِن مَّرْقَدِنَا ۜ ۗ هَـٰذَا مَا وَعَدَ الرَّحْمَـٰنُ وَصَدَقَ الْمُرْسَلُونَ

ነጥብ ሁለት
"የውሙል ሐቅ"
"የውሙል ሐቅ" يَوْمُ الْحَقّ ማለት "የተረጋገጠ ወይም የእውነት ቀን" ማለት ነው፦
78፥39 *ይህ የተረጋገጠው ቀን ነው፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መመለስን ይይዛል*፡፡ ذَٰلِكَ الْيَوْمُ الْحَقُّ ۖ فَمَن شَاءَ اتَّخَذَ إِلَىٰ رَبِّهِ مَآبًا

“አል-የቂን” الْيَقِين ማለት “እርግጠኝነት” ማለት ሲሆን በሦስት ይከፈላል፥ እርሱም፦
“ዒልመል የቂን” عِلْمَ الْيَقِين ማለትም "እርግጠኛ ዕውቀት"
“ዐይነል የቂን” عَيْنَ الْيَقِين ማለትም "እርግጠኛ ማየት"
“ሐቁል የቂን” حَقُّ الْيَقِين ማለትም "እርግጠኛ እውነት" ነው።
አማንያን ጀነት ውስጥ ያለው ጸጋ መቅመስ፥ ከሃድያን ጀሃነም ውስጥ ያለው ቅጣት መቅመስ ሐቁል የቂን ነው፦
77፥43 *«ትሠሩት በነበራችሁት ዋጋ የምትደሰቱ ኾናችሁ ብሉ፣ ጠጡም፤» ይባላሉ*፡፡ كُلُوا وَاشْرَبُوا هَنِيئًا بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
46፥34 *እነዚያም የካዱት ሰዎች በእሳት ላይ በሚቀረቡ ቀን «ይህ እውነት አይደለምን?» ይባላሉ፡፡ «እውነት ነው፤ በጌታችን ይኹንብን» ይላሉ፡፡ አላህም «ትክዱ በነበራችሁት ምክንያት ቅጣቱን ቅመሱ» ይላቸዋል”*፡፡ وَيَوْمَ يُعْرَضُ الَّذِينَ كَفَرُوا عَلَى النَّارِ أَلَيْسَ هَـٰذَا بِالْحَقِّ ۖ قَالُوا بَلَىٰ وَرَبِّنَا ۚ قَالَ فَذُوقُوا الْعَذَابَ بِمَا كُنتُمْ تَكْفُرُونَ

ኢንሻሏህ ይቀጥላል.....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የመጨረሻው ቀን

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

50፥42 *ጩኸቲቱን በእውነት የሚሰሙበት ቀን ያ ከመቃብር "የመውጫው ቀን" ነው*፡፡ يَوْمَ يَسْمَعُونَ الصَّيْحَةَ بِالْحَقِّ ۚ ذَٰلِكَ يَوْمُ الْخُرُوجِ

ነጥብ ሦስት
"የውሙል ኹሩጅ"
"የውሙል ኹሩጅ" يَوْمُ الْخُرُوج ማለት "የመውጫው ቀን ነው" ማለት ነው፥ ጠሪው መልአክ በሚጠራበት ቀን ሰዎች ከመቃብራቸው ይወጣሉ፦
53፥6 ከእነርሱም ዙር፡፡ *ጠሪው መልአክ ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን አስታውስ*፡፡ فَتَوَلَّ عَنْهُمْ ۘ يَوْمَ يَدْعُ الدَّاعِ إِلَىٰ شَيْءٍ نُّكُرٍ
50፥41 *"የሚነገርህን አዳምጥም፡፡ ጠሪው ከቅርብ ስፍራ በሚጠራበት ቀን ከመቃብራቸው ይወጣሉ*፡፡ وَاسْتَمِعْ يَوْمَ يُنَادِ الْمُنَادِ مِن مَّكَانٍ قَرِيبٍ
50፥42 *ጩኸቲቱን በእውነት የሚሰሙበት ቀን ያ ከመቃብር "የመውጫው ቀን" ነው*፡፡ يَوْمَ يَسْمَعُونَ الصَّيْحَةَ بِالْحَقِّ ۚ ذَٰلِكَ يَوْمُ الْخُرُوجِ
30፥25 *ሰማይና ምድርም በትዕዛዙ መቆማቸው እና ከዚያም *ከምድር ጥሪን በጠራችሁ ጊዜ እናንተ ወዲያውኑ የምትወጡ መሆናችሁ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ أَن تَقُومَ السَّمَاءُ وَالْأَرْضُ بِأَمْرِهِ ۚ ثُمَّ إِذَا دَعَاكُمْ دَعْوَةً مِّنَ الْأَرْضِ إِذَا أَنتُمْ تَخْرُجُونَ

"የምትወጡ" ለሚለው የገባው ቃል "ተኽሩጁነ" تَخْرُجُونَ መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። ጠሪው መልአክ የሚጣራበት የመጀመሪያው መነፋት ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ሲሆን ሁለተኛው መነፋት ሰዎች ከመቃብራቸው የሚወጡበት ነው፦
39፥68 *በቀንዱም ይነፋል፥ በሰማያት ውስጥ ያለው ፍጡር እና በምድርም ውስጥ ያለው ፍጡር ሁሉ አላህ የሻው ሲቀር በድንጋጤ ይሞታል፡፡ ከዚያም በእርሱ ሌላ መንነፋት ይነፋል፥ ወዲያውም እነርሱ የሚሠራባቸውን የሚጠባበቁ ኾነው ቋሚዎች ይኾናሉ*፡፡ وَنُفِخَ فِي الصُّورِ فَصَعِقَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَمَن فِي الْأَرْضِ إِلَّا مَن شَاءَ اللَّهُ ۖ ثُمَّ نُفِخَ فِيهِ أُخْرَىٰ فَإِذَا هُمْ قِيَامٌ يَنظُرُونَ
36፥51 *"በቀንዱም ይነፋል፥ ወዲያውኑም እነርሱ ከመቃብሮቻቸው ወደ ጌታቸው በፍጥነት ይገሰግሳሉ*፡፡ وَنُفِخَ فِي الصُّورِ فَإِذَا هُم مِّنَ الْأَجْدَاثِ إِلَىٰ رَبِّهِمْ يَنسِلُونَ

ይህ በመለከት ሁለቱን መነፋት የሚነፋው መልአክ "ሷሒቡ አስ-ሱር" صَاحِب الصُّور ማለት "የመለከት ባለቤት" የመላእክት አለቃ ኢሥራፊል ነው።

ነጥብ አራት
"የውመል ቂያማህ"
“ቂያማህ” قِيَٰمَة የሚለው ቃል “ቃመ” قَامَ ማለትም “ተነሣ” ወይም “ቆመ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ትንሣኤ” ማለት ነው። "የውመል ቂያማህ" يَوْمَ الْقِيَامَة ማለት "የትንሣኤ ቀን" ማለት ነው፥ አምላካችን አላህ ስለ ትንሳኤ አጽንዖትና አንክሮት ለመስጠት በትንሣኤ ቀን ምሏል፦
75፥1 *"ነገሩ ከሓዲዎች እንደሚሉት አይደለም፡፡ *"በትንሣኤ ቀን እምላለሁ"*፡፡ لَا أُقْسِمُ بِيَوْمِ الْقِيَامَةِ
23፥16 *"ከዚያም እናንተ "በትንሣኤ ቀን" ትቀሰቀሳላችሁ"*፡፡ ثُمَّ إِنَّكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ تُبْعَثُونَ
39፥68 *"ከዚያም በእርሱ ሌላ መንነፋት ይነፋል፥ ወዲያውም እነርሱ የሚሠራባቸውን የሚጠባበቁ ኾነው "ቋሚዎች" ይኾናሉ*፡፡ ثُمَّ نُفِخَ فِيهِ أُخْرَىٰ فَإِذَا هُمْ قِيَامٌ يَنظُرُونَ

"ቃኢም" قَآئِم ማለት "ቃሚ" ማለት ነው፥ የቃኢም ብዙ ቁጥር ደግሞ "ቂያም" قِيَام ማለት ሲሆን "ቋሚዎች" ማለት ነው። ትንሳኤ እንዳለ በዕውቀት ያወቁ እና በእምነት ያመኑ የዕውቀት እና የእምነት ባለቤቶች እነዚያ የካዱትን በትንሳኤ ቀን፦ "ይህም የካዳችሁት የትንሣኤ ቀን ነው፡፡ ግን እናንተ የማታውቁ ነበራችሁ" ይሏቸዋል፥ እነዚያ የካዱት በትንሣኤ ቀን ሙስሊሞች በኾኑ ኖሩ በብዛት ይመኛሉ። እነርሱ "ከአላህ ሌላ አምላክ የለም" በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ፦
30፥56 *እነዚያንም ዕውቀትንና እምነትን የተሰጡት «በአላህ መጽሐፍ (ፍርድ) እስከ ትንሣኤ ቀን በእርግጥ ቆያችሁ፡፡ ይህም የካዳችሁት የትንሣኤ ቀን ነው፡፡ ግን እናንተ የማታውቁ ነበራችሁ» ይሏቸዋል*፡፡ وَقَالَ الَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ وَالْإِيمَانَ لَقَدْ لَبِثْتُمْ فِي كِتَابِ اللَّهِ إِلَىٰ يَوْمِ الْبَعْثِ ۖ فَهَـٰذَا يَوْمُ الْبَعْثِ وَلَـٰكِنَّكُمْ كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ
15፥2 *"እነዚያ የካዱት በትንሣኤ ቀን ሙስሊሞች በኾኑ ኖሩ በብዛት ይመኛሉ"*፡፡ رُّبَمَا يَوَدُّ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْ كَانُوا مُسْلِمِينَ
37፥35 *እነርሱ "ከአላህ ሌላ አምላክ የለም" በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ*፡፡ إِنَّهُمْ كَانُوا إِذَا قِيلَ لَهُمْ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّهُ يَسْتَكْبِرُونَ
ነጥብ አምስት
"የውሚድ ዲን"
“ዲን” دِين የሚለው ቃል “ዳነ” دَانَ ማለትም “ፈረደ” “በየነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ሃይማኖት” “ፍትሕ” “ፍርድ” “ሕግ” “መርሕ” ማለት ነው። "የውሚድ ዲን" يَوْمِ الدِّين ማለት "የፍርዱ ቀን" ማለት ነው፦
1፥4 *"የፍርዱ ቀን" ባለቤት ለኾነው"*፡፡ مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ
37፥20 *«ዋ ጥፋታችን! ይህ "የፍርዱ ቀን" ነው» ይላሉም*፡፡ وَقَالُوا يَا وَيْلَنَا هَـٰذَا يَوْمُ الدِّينِ
56፥6 *"ፍርድን ማግኘትም የማይቀር ነው"*፡፡ وَإِنَّ الدِّينَ لَوَاقِعٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ፍርድ" ለሚለው ቃል የገባው በአመልካች መስተአምር "አድ-ዲን" الدِّين መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። “ዲን” دِين ሦስት ደረጃ አለው፥ እርሱም፦
“ኢሥላም” إِسْلَٰم
“ኢማን” إِيمَٰن
“ኢሕሣን” إِحْسَٰن ናቸው።
ዲን ለአላህ ብቻ በማጥራት አላህን ማምለክ ነው፦
39፥11 በል «እኔ *አላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ያጠራሁ ኾኜ እንዳመልከው ታዘዝኩ"*፡፡ قُلْ إِنِّي أُمِرْتُ أَنْ أَعْبُدَ اللَّهَ مُخْلِصًا لَّهُ الدِّينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ያጠራ" ለሚለው ቃል የገባው "ሙኽሊስ" مُخْلِص ነው። "ኢኽላስ" إِخْلَاص የሚለው ቃል "ኸለሰ" خَلَصَ ማለትም "ጠራ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ከእዩልኝ እና ከስሙልኝ፥ ከወቀሳ እና ከሙገሳ ነጻ ሆኖ ዲንን ለአላህ ብቻ "ማጥራት" ማለት ነው። ዒባዳን በኢኽላስ የሚሠራ ሙሥሊም "ሙኽሊስ" مُخْلِص ይባላል። አላህ ዘንድ ዲን ኢሥላም ብቻ ነው፥ ከኢሥላም ዲን ሌላ ዲንን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይ የለውም፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፦
3፥19 *አላህ ዘንድ ሃይማኖት ኢሥላም ብቻ ነው*፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ
3፥85 *ከኢሥላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይ የለውም፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው*፡፡ وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ الْإِسْلَامِ دِينًا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِي الْآخِرَةِ مِنَ الْخَاسِرِينَ

ነጥብ ስድስት
"የውመል ፈትሕ"
"የውመል ፈትሕ" يَوْمَ الْفَتْح ማለት "የፍርድ ቀን" ማለት ነው፥ በቁርኣን ከተገለጹ የአላህ ስሞች መካከል "አል-ፈታሕ" الْفَتَّاح ማለትም "ፈራጁ" ነው፦
32፥29 *«"በፍርድ ቀን" እነዚያን የካዱትን ሰዎች እምነታቸው አይጠቅማቸውም፡፡ እነርሱም ጊዜን አይሰጡም»* በላቸው፡፡ قُلْ يَوْمَ الْفَتْحِ لَا يَنفَعُ الَّذِينَ كَفَرُوا إِيمَانُهُمْ وَلَا هُمْ يُنظَرُونَ
34፥26 *«ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል፡፡ ከዚያም በመካከላችን በእውነት ይፈርዳል፡፡ እርሱም በትክክል ፈራጁ ዐዋቂው ነው»* በላቸው፡፡ قُلْ يَجْمَعُ بَيْنَنَا رَبُّنَا ثُمَّ يَفْتَحُ بَيْنَنَا بِالْحَقِّ وَهُوَ الْفَتَّاحُ الْعَلِيمُ

"ፈትሕ" فَتْح የሚለው ቃል "ፈተሐ" فَتَحَ ማለትም "ከፈተ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መክፈት" ማለት ነው፥ "መፋቲሕ" مَفَاتِح ማለት እራሱ "መክፈቻ" ማለት ነው። ቁርኣን ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብና ትርጉም አለው ማለት አይደለም፥ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው። መታየት ያለበት ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብ ነው፥ እዚህ ዐውድ ላይ "ፈትሕ" فَتْح ማለት "ፍርድ" ማለት ነው፦
26፥118 *«በእኔ እና በእነርሱም መካከል ፍርድን "ፍረድ"! አድነኝም!፡፡ ከእኔ ጋር ያሉትን ምእምናንም፡፡»* فَافْتَحْ بَيْنِي وَبَيْنَهُمْ فَتْحًا وَنَجِّنِي وَمَن مَّعِيَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ፍረድ" ለሚለው ግስ የገባው ቃል "ኢፍተሕ" افْتَحْ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። በፍርድ ቀን ለካፊር ይፈረድበታል፥ ለሙእሚን ይፈረድለታል።
ኢንሿላህ ይቀጥላል......

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የመጨረሻው ቀን

ገቢር ሦስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

42፥7 እንደዚሁም የከተሞች እናት የኾነችውን እና በአካባቢዋ ያሉትንም ልታስጠነቅቅ *የመሰብሰቢያውንም ቀን በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲኾን ልታስጠነቅቅ ዐረብኛ የኾነን ቁርኣን ወደ አንተ አወረድን*፡፡ وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لِّتُنذِرَ أُمَّ الْقُرَىٰ وَمَنْ حَوْلَهَا وَتُنذِرَ يَوْمَ الْجَمْعِ لَا رَيْبَ فِيهِ

ነጥብ ሰባት
"የውሙል ጀምዕ"
"የውመል ጀምዕ" يَوْم الْجَمْع ማለት "የመሰብሰቢያውንም ቀን" ማለት ነው፦
42፥7 እንደዚሁም የከተሞች እናት የኾነችውን እና በአካባቢዋ ያሉትንም ልታስጠነቅቅ *የመሰብሰቢያውንም ቀን በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲኾን ልታስጠነቅቅ ዐረብኛ የኾነን ቁርኣን ወደ አንተ አወረድን*፡፡ وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لِّتُنذِرَ أُمَّ الْقُرَىٰ وَمَنْ حَوْلَهَا وَتُنذِرَ يَوْمَ الْجَمْعِ لَا رَيْبَ فِيهِ

“አሐድ” أحَد ማለት “አንድ” ማለት ነው፣
“ኢስነይን” اِثْنَيْن‎ ማለት “ሁለት” ማለት ነው፣
“ሱላሳእ” ثُّلَاثَاء ማለት “ሦስት” ማለት ነው፣
“አርቢዓእ” أَرْبِعَاء ማለት “አራት” ማለት ነው፣
“ኸሚሥ” خَمِيس ማለት “አምስት” ማለት ነው፣
“ጁሙዓህ” جُمُعَة ማለት ደግሞ “ስብስብ” ማለት ነው፥ "የውሙል ጁሙዓህ" يَوْمُ الْجُمُعَة ማለት እራሱ "የስብስብ ቀን" ማለት ነው። አደም የተፈጠረው በጁሙዓህ ቀን ነው፥ ቂያማህ የሚቆመውም በጁሙዓህ ቀን ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 4, ሐዲስ 1
አቡ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"መልካም ቀን ፀሐይ ከወጣችበት የጁሙዓህ ቀን ነው፥ በዚያ ቀን አደም ተፈጠረ፣ በዚያ ቀን ወደ ጀነት ገብቷል፥ ከጀነት በዚያ ቀን ወጥቷል፣ ሰዓቲቱ በጁሙዓህ ቀን እንጂ አትቆምም"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ خَيْرُ يَوْمٍ طَلَعَتْ فِيهِ الشَّمْسُ يَوْمُ الْجُمُعَةِ فِيهِ خُلِقَ آدَمُ وَفِيهِ أُدْخِلَ الْجَنَّةَ وَفِيهِ أُخْرِجَ مِنْهَا وَلاَ تَقُومُ السَّاعَةُ إِلاَّ فِي يَوْمِ الْجُمُعَةِ ‏"‏

አምላካችን አላህ በመሰብሰቢያውንም ቀን ሰውን ሁሉ ሰብሳቢ ነው፥ ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል፡፡ ከዚያም በመካከላችን በእውነት ይፈርዳል፦
3፥9 «ጌታችን ሆይ! *አንተ በእርሱ ለመምጣቱ ጥርጥር የሌለበት በኾነ ቀን ሰውን ሁሉ ሰብሳቢ ነህ*፡፡ ምንጊዜም አላህ ቀጠሮውን አያፈርስምና፡፡» رَبَّنَا إِنَّكَ جَامِعُ النَّاسِ لِيَوْمٍ لَّا رَيْبَ فِيهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُخْلِفُ الْمِيعَادَ
34፥26 *«ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል፡፡ ከዚያም በመካከላችን በእውነት ይፈርዳል፡፡ እርሱም በትክክል ፈራጁ ዐዋቂው ነው»* በላቸው፡፡ قُلْ يَجْمَعُ بَيْنَنَا رَبُّنَا ثُمَّ يَفْتَحُ بَيْنَنَا بِالْحَقِّ وَهُوَ الْفَتَّاحُ الْعَلِيمُ

ትክክለኛ ፈራጅ እርሱ ብቻ ስለሆነ በዚያ ቀን ለፍርድ ይሰበስባል፥ ያ ቀን መምጣቱ ጥርጥር የለበትም፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች ዐያውቁም፦
4፥26 *«አላህ ሕያው ያደርጋችኋል፥ ከዚያም ያሞታል። ከዚያም ወደ ትንሣኤ ቀን ይሰበስባችኋል፥ በእርሱ ጥርጥር የለበትም፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች ዐያውቁም»* በላቸው፡፡ قُلِ اللَّهُ يُحْيِيكُمْ ثُمَّ يُمِيتُكُمْ ثُمَّ يَجْمَعُكُمْ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ لَا رَيْبَ فِيهِ وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ
4፥87 አላህ ከእርሱ በስተቀር አምላክ የለም፡፡ *"ወደ ትንሣኤ ቀን በእርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲኾን በእርግጥ ይሰበስባችኋል"*፡፡ በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማነው? اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ لَيَجْمَعَنَّكُمْ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ لَا رَيْبَ فِيهِ ۗ وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ اللَّهِ حَدِيثًا

ነጥብ ስምንት
"የውሙል ፈስል"
"የውሙል ፈስል" يَوْمُ الْفَصْل ማለት የመለያው ቀን" ማለት ነው፥ የመለያው ቀን ለሁሉም ቀጠሯቸው ነው፦
44፥40 *"የመለያው ቀን" ለሁሉም ቀጠሯቸው ነው"*፡፡ إِنَّ يَوْمَ الْفَصْلِ مِيقَاتُهُمْ أَجْمَعِينَ

አምላካችን አላህ በመለያው ቀን አማንያንን ወደ ጀነት በማስገባት፥ ከሃድያንን ወደ እሳት በማስገባት በፍርድ ይለያል፦
32፥25 *ጌታህ እርሱ በዚያ በእርሱ ይለያዩበት በነበሩት ነገር በትንሣኤ ቀን በመካከላቸው በፍርድ ይለያል*፡፡ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ يَفْصِلُ بَيْنَهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فِيمَا كَانُوا فِيهِ يَخْتَلِفُونَ
22፥17 *እነዚያ ያመኑት፣ እነዚያም ይሁዳውያን የሆኑ፣ ሳቢያኖችም፣ ክርስቲያኖችም፣ መጁሶችም፣ እነዚያም ያጋሩ አላህ በትንሣኤ ቀን በመካከላቸው በፍርድ ይለያል*፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ በእርግጥ ዐዋቂ ነውና፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَالَّذِينَ هَادُوا وَالصَّابِئِينَ وَالنَّصَارَىٰ وَالْمَجُوسَ وَالَّذِينَ أَشْرَكُوا إِنَّ اللَّهَ يَفْصِلُ بَيْنَهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ

ከሃድያን አስተባባዮች ስለሆኑ "ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉ የነበራችሁት "የመለያው ቀን" ነው" ይባላሉ፦
77፥14 *የመለያውም ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ?* وَمَا أَدْرَاكَ مَا يَوْمُ الْفَصْلِ
77፥15 ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ
37፥21 *«ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉ የነበራችሁት "የመለያው ቀን" ነው»* ይባላሉ፡፡ هَـٰذَا يَوْمُ الْفَصْلِ الَّذِي كُنتُم بِهِ تُكَذِّبُونَ
ነጥብ ዘጠኝ
"የውመት ተላቅ"
"የውመት ተላቅ" يَوْمَ التَّلَاق ማለት "የመገናኛውን ቀን" ማለት ነው፦
40፥15 *"እርሱ ደረጃዎችን ከፍ አድራጊ የዐርሹ ባለቤት ነው፡፡ "የመገናኛውን ቀን" ያስጠነቅቅ ዘንድ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ከትዕዛዙ መንፈስን ያወርዳል*፡፡ رَفِيعُ الدَّرَجَاتِ ذُو الْعَرْشِ يُلْقِي الرُّوحَ مِنْ أَمْرِهِ عَلَىٰ مَن يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ لِيُنذِرَ يَوْمَ التَّلَاقِ

ሰው አላህን ተገናኝቶ በሠራው ሰናይ ሥራ ወይም በሠራው እኩይ ሥራ ከጌታው ይተሳሰባል፦
84፥6 *"አንተ ሰው ሆይ! አንተ "ጌታህን እስከምትገናኝ" ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ፥ "ተገናኚውም" ነህ"*፡፡ يَا أَيُّهَا الْإِنسَانُ إِنَّكَ كَادِحٌ إِلَىٰ رَبِّكَ كَدْحًا فَمُلَاقِيهِ

ሶላት መስገድ ጌታቸውን የሚገናኙ መኾናቸውን በዕውቀት የሚያረጋግጡ በኾኑት ላይ ቀላል ናት፥ ግን አላህን አግኝቼ ይተሳሰበኛል ብሎ እርግጠኛ ባልሆነ ላይ ግን ከባድ ናት፦
2፥46 *(ሶላት) እነዚያ "ጌታቸውን የሚገናኙ እነርሱም ወደ እርሱ ተመላሾች መኾናቸውን የሚያረጋግጡ በኾኑት ላይ እንጅ ከባድ ናት*፡፡ الَّذِينَ يَظُنُّونَ أَنَّهُم مُّلَاقُو رَبِّهِمْ وَأَنَّهُمْ إِلَيْهِ رَاجِعُونَ

እኩያን ለእነርሱ፦ "ስገዱም" በተባሉ ጊዜ አይሰግዱም ነበር፥ ቅጣቱን ሲቀምሱ፦ ”ከሰጋጆቹ አልነበርንም" ይላሉ፦
77፥48 *"«ለእነርሱ ስገዱም» በተባሉ ጊዜ አይሰግዱም"*፡፡ وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ارْكَعُوا لَا يَرْكَعُونَ
74፥43 እነርሱም ይላሉ፦ *”ከሰጋጆቹ አልነበርንም”*፡፡ قَالُوا لَمْ نَكُ مِنَ الْمُصَلِّين

ነጥብ አስር
"የውሚል ሒሣብ"
"የውሚል ሒሣብ" يَوْمِ الْحِسَاب ማለት "የመተሳሰቢያ ወይም የምርመራ ቀን" ማለት ነው፦
38፥52 *"ይህ ለምርመራው ቀን የምትቀጠሩት ተስፋ ነው"*፡፡ هَـٰذَا مَا تُوعَدُونَ لِيَوْمِ الْحِسَابِ

"ሒሣብ" حِسَاب የሚለው ቃል "ሐሢበ" حَسِبَ ማለትም "መረመረ" "ተቆጣጠረ" ተሳሰበ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ምርመራ" "ቁጥጥር" "መተሳሰብ" "ማወራረድ" ማለት ነው። በቁርኣን ከተገለጹ የአላህ ውብ ስሞች መካከል "አል-ሐሢብ" الْحَسِيب ሲሆን "ተቆጣጣሪ" "መርማሪ" "ተሳሳቢ" ማለት ነው፦
4፥86 በሰላምታ በተከበራችሁም ጊዜ ከእርሷ ይበልጥ ባማረ ሰላምታ አክብሩ፡፡ ወይም እርሷኑ መልሷት፡፡ *"አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነውና"*፡፡ وَإِذَا حُيِّيتُم بِتَحِيَّةٍ فَحَيُّوا بِأَحْسَنَ مِنْهَا أَوْ رُدُّوهَا ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ حَسِيبًا
2፥284 *በሰማያት ውስጥና በምድርም ውስጥ ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ በራሳችሁ ውስጥ ያለውን ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት አላህ በእርሱ ይቆጣጠራችኋል*፡፡ لِّلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۗ وَإِن تُبْدُوا مَا فِي أَنفُسِكُمْ أَوْ تُخْفُوهُ يُحَاسِبْكُم بِهِ اللَّهُ

"ይቆጣጠራችኋል" ለሚለው የገባው ቃል "ዩሓሢብኩም" يُحَاسِبْكُم መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። በራሳችን ውስጥ ያለውን ብንገልጽ ወይም ብንደብቅ አምላካችን አላህ በእርሱ ማለትም በችሎታው ይቆጣጠረናል። እንዲሁ የፍርዱ ቀን ሰዎች የሠሩት ኸይር ሥራ፥ ወይም ሸር ሥራ ይተሳሰባል።
ኢንሿላህ ይቀጥላል......

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የመጨረሻው ቀን

ገቢር አራት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

50፥20 *"በቀንዱም ውስጥ ይነፋል፥ ያ ቀን የዛቻው ቀን ነው"*፡፡ وَنُفِخَ فِي الصُّورِ ۚ ذَٰلِكَ يَوْمُ الْوَعِيدِ

ነጥብ አሥራ አንድ
"የውመት ተናድ"
"የውመት ተናድ" يَوْمَ التَّنَاد ማለት "የመጠራሪያን ቀን" ማለት ነው፦
40፥32 *«ሕዝቦቼ ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ የመጠራሪያን ቀን እፈራለሁ»* አላቸው። وَيَا قَوْمِ إِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ يَوْمَ التَّنَادِ

"እፈራለው" ያለው በመጠራሪያን ቀን የሚኖረውን የመጨረሻውን ቀን ቅጣት ነው፥ "የመጨረሻውንም ቀን ፍሩ" ተብሏል፦
11፥103 *"በዚህ ውስጥ የመጨረሻውን ቀን ቅጣት ለሚፈሩ ሁሉ መገሰጫ አለ"*፡፡ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّمَنْ خَافَ عَذَابَ الْآخِرَةِ
29፥36 ወደ መድየንም ወንድማቸውን ሹዐይብን ላክን፦ *«ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን አምልኩ! "የመጨረሻውንም ቀን" ፍሩ! በምድርም ውስጥ የምታጠፉ ሆናችሁ አታበላሹ»* አላቸውም፡፡ وَإِلَىٰ مَدْيَنَ أَخَاهُمْ شُعَيْبًا فَقَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَارْجُوا الْيَوْمَ الْآخِرَ وَلَا تَعْثَوْا فِي الْأَرْضِ مُفْسِدِينَ

"በእናንተ ላይ የመጠራሪያን ቀን" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ሕዝቦቼ በክህደት ከቀጠሉ እና የእሳት ሰዎች ከሆኑ የጀነት ሰዎች የእሳትን ሰዎችን፦ "ጌታችን ቃል የገባልንን እውነት ኾኖ አገኘን፥ ጌታችሁ የዛተባችሁንስ እውነት ኾኖ አገኛችሁትን? ሲሉ ይጣራሉ፦
7፥44 *"የገነትም ሰዎች የእሳትን ሰዎችን «ጌታችን ቃል የገባልንን እውነት ኾኖ አገኘን፥ ጌታችሁ የዛተባችሁንስ እውነት ኾኖ አገኛችሁትን?» ሲሉ "ይጣራሉ"*፡፡ «አዎን አገኘን» ይላሉ፡፡ በመካከላቸውም «የአላህ ርግማን በበደለኞች ላይ ይኹን» ሲል ለፋፊ ይለፍፋል፡፡ وَنَادَىٰ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ أَصْحَابَ النَّارِ أَن قَدْ وَجَدْنَا مَا وَعَدَنَا رَبُّنَا حَقًّا فَهَلْ وَجَدتُّم مَّا وَعَدَ رَبُّكُمْ حَقًّا ۖ قَالُوا نَعَمْ ۚ فَأَذَّنَ مُؤَذِّنٌ بَيْنَهُمْ أَن لَّعْنَةُ اللَّهِ عَلَى الظَّالِمِينَ

"ይጣራሉ" የሚለው ይሰመርበት። በጀነት ሰዎች እና በእሳትን ሰዎች መካከል ግርዶች አለ፥ ይህ ቦታ "አዕራፍ" أَعْرَاف ይባላል። በዚህ ቦታ ሰናይና እኩይ ሥራቸው በሚዛን እኩል የሆኑት ሰዎች "አስሓቡል አዕራፍ" أَصْحَابُ الْأَعْرَاف ይባላሉ፥ የጀነት ሰዎች የአዕራፍ ሰዎችን፦ "ሰላም ለእናንተ ይኹን" በማለት ይጣራሉ፦
7፥46 በመካከላቸውም ግርዶሽ አልለ፡፡ በአዕራፍም ላይ ሁሉንም በምልክታቸው የሚያውቁ ሰዎች አሉ፡፡ የገነትንም ሰዎች ሰላም ለእናንተ ይኹን በማለት ይጣራሉ፡፡ እነርሱም የአዕራፍ ሰዎች የሚከጅሉ ሲኾኑ ገና አልገቧትም፡፡ وَبَيْنَهُمَا حِجَابٌ ۚ وَعَلَى الْأَعْرَافِ رِجَالٌ يَعْرِفُونَ كُلًّا بِسِيمَاهُمْ ۚ وَنَادَوْا أَصْحَابَ الْجَنَّةِ أَن سَلَامٌ عَلَيْكُمْ ۚ لَمْ يَدْخُلُوهَا وَهُمْ يَطْمَعُونَ

ነጥብ አሥራ ሁለት
"የውሙል ወዒድ"
"የውሙል ወዒድ" يَوْمُ الْوَعِيد ማለት "የዛቻው ቀን" ማለት ነው፦
50፥20 *"በቀንዱም ውስጥ ይነፋል፥ ያ ቀን የዛቻው ቀን ነው"*፡፡ وَنُفِخَ فِي الصُّورِ ۚ ذَٰلِكَ يَوْمُ الْوَعِيدِ

በሃይማኖት ማስገደድ የለም፥ ቅኑ መንገድ ከጠማማው ተገልጧል። የሻም ሰው ይመን፥ የሻም ሰው ይካድ፦
2፥256 *በሃይማኖት ማስገደድ የለም፥ ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ*፡፡ لَا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ ۖ قَد تَّبَيَّنَ الرُّشْدُ مِنَ الْغَيِّ
18፥29 *«እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፥ የሻም ሰው ይካድ»* በላቸው፡፡ وَقُلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُرْ

"የሻም ሰው ይመን፥ የሻም ሰው ይካድ" ማለት ዛቻ ነው። በግድ እምኑ በማለት በእነርሱ ላይ አስገዳጅ አይደለንም፥ የአላህ ዛቻ የሚፈራን ሰው በቁርኣን ማስታወስ ብቻ ነው፥ ከዚያም በዛቻው ቀን የገነትም ሰዎች የእሳትን ሰዎችን፦ ጌታችሁ "የዛተባችሁንስ" እውነት ኾኖ አገኛችሁትን? ሲሉ ይጣራሉ፦
50፥45 እኛ የሚሉትን ሁሉ ዐዋቂ ነን፡፡ *"አንተም በእነርሱ ላይ አስገዳጅ አይደለህም፡፡ ስለዚህ ዛቻዬን የሚፈራን ሰው በቁርኣን አስታውስ*፡፡ نَّحْنُ أَعْلَمُ بِمَا يَقُولُونَ ۖ وَمَا أَنتَ عَلَيْهِم بِجَبَّارٍ ۖ فَذَكِّرْ بِالْقُرْآنِ مَن يَخَافُ وَعِيدِ
7፥44 *"የገነትም ሰዎች የእሳትን ሰዎችን «ጌታችን ቃል የገባልንን እውነት ኾኖ አገኘን፥ ጌታችሁ "የዛተባችሁንስ" እውነት ኾኖ አገኛችሁትን?» ሲሉ "ይጣራሉ"*፡፡ «አዎን አገኘን» ይላሉ፡፡ በመካከላቸውም «የአላህ ርግማን በበደለኞች ላይ ይኹን» ሲል ለፋፊ ይለፍፋል፡፡ وَنَادَىٰ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ أَصْحَابَ النَّارِ أَن قَدْ وَجَدْنَا مَا وَعَدَنَا رَبُّنَا حَقًّا فَهَلْ وَجَدتُّم مَّا وَعَدَ رَبُّكُمْ حَقًّا ۖ قَالُوا نَعَمْ ۚ فَأَذَّنَ مُؤَذِّنٌ بَيْنَهُمْ أَن لَّعْنَةُ اللَّهِ عَلَى الظَّالِمِينَ

አላህ በቁርኣን ዝቶበት የነበረው ቀን ሲመጣ ያ ቀን የዛቻው ቀን ነው። ካፊሮች አንዱ ሌላውን በመውቀስ ሲጨቃጨቁ አላህ፦ "ወደ እናንተ ዛቻን በእርግጥ ያስቀደምኩ ስኾን እኔ ዘንድ አትጨቃጨቁ" ይላቸዋል፥ ቀድሞውኑ አላህ፦ "እኛ ለበደለኞች አጥሯ በእነርሱ የከበበ የኾነችውን እሳት አዘጋጅተናል፥ ከጥም እርዳታንም ቢፈልጉ እንደ ዘይት ዝቃጭ ባለ ፊቶችን በሚጠብስ ውሃ ይረዳሉ፡፡ መጠጡ ከፋ፥ መደገፊያይቱም ምንኛ አስከፋች" ብሎ ተናግሯል፦
50፥28 *"አላህ «ወደ እናንተ ዛቻን በእርግጥ ያስቀደምኩ ስኾን እኔ ዘንድ አትጨቃጨቁ» ይላቸዋል*፡፡ قَالَ لَا تَخْتَصِمُوا لَدَيَّ وَقَدْ قَدَّمْتُ إِلَيْكُم بِالْوَعِيدِ
18፥29 *«እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ» በላቸው፡፡ እኛ ለበደለኞች አጥሯ በእነርሱ የከበበ የኾነችውን እሳት አዘጋጅተናል፥ ከጥም እርዳታንም ቢፈልጉ እንደ ዘይት ዝቃጭ ባለ ፊቶችን በሚጠብስ ውሃ ይረዳሉ፡፡ መጠጡ ከፋ፥ መደገፊያይቱም ምንኛ አስከፋች*። وَقُلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُرْ ۚ إِنَّا أَعْتَدْنَا لِلظَّالِمِينَ نَارًا أَحَاطَ بِهِمْ سُرَادِقُهَا ۚ وَإِن يَسْتَغِيثُوا يُغَاثُوا بِمَاءٍ كَالْمُهْلِ يَشْوِي الْوُجُوهَ ۚ بِئْسَ الشَّرَابُ وَسَاءَتْ مُرْتَفَقًا
ነጥብ አሥራ ሦስት
የውመል ሐሥራህ"
"የውመል ሐሥራህ" يَوْمَ الْحَسْرَة ማለት "የቁልጭቱን ቀን" ማለት ነው፦
19፥39 *እነርሱም አሁን በዝንጋቴ ላይ ኾነው ሳሉ እነርሱም የማያምኑ ሲኾኑ ነገሩ በሚፈረድበት ጊዜ "የቁልጭቱን ቀን አስጠንቅቃቸው*፡፡ وَأَنذِرْهُمْ يَوْمَ الْحَسْرَةِ إِذْ قُضِيَ الْأَمْرُ وَهُمْ فِي غَفْلَةٍ وَهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ

በዚህ ቀን ኩፋሮች በቁጭት ከሚሉት መካከል፦ “ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በኾነ ዋ ምኞቴ” “አላህን በተገዛን መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ” በማለት ይቆጫሉ፦
25፥27 *በዳይም «ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በኾነ ዋ ምኞቴ!» እያለ በጸጸት ሁለት እጆቹን የሚነክስበትን ቀን አስታውስ*፡፡ وَيَوْمَ يَعَضُّ الظَّالِمُ عَلَىٰ يَدَيْهِ يَقُولُ يَا لَيْتَنِي اتَّخَذْتُ مَعَ الرَّسُولِ سَبِيلًا
33፥66 ፊቶቻቸው በእሳት ውሰጥ በሚገለባበጡ ቀን *«ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ» እያሉ ይጸጸታሉ*፡፡ يَوْمَ تُقَلَّبُ وُجُوهُهُمْ فِي النَّارِ يَقُولُونَ يَا لَيْتَنَا أَطَعْنَا اللَّهَ وَأَطَعْنَا الرَّسُولَا

ኩፋሮች ከቁጭትዋ የተነሳ ሲቆጩ የእሳት ዘበኞች፦ “አስጠንቃቂ አልመጣችሁምን?” በማለት ይጠይቋቸዋል፦
67፥8 *ከቁጭትዋ የተነሳ ልትቆራረጥ ትቀርባለች፡፡ በውስጧ ጭፍሮች በተጣሉ ቁጥር ዘበኞችዋ *«አስጠንቃቂ አልመጣችሁምን?*» በማለት ይጠይቋቸዋል፡፡ تَكَادُ تَمَيَّزُ مِنَ الْغَيْظِ ۖ كُلَّمَا أُلْقِيَ فِيهَا فَوْجٌ سَأَلَهُمْ خَزَنَتُهَا أَلَمْ يَأْتِكُمْ نَذِيرٌ

ኩፋሮች ይህንን መልእክት ተቀብለው ከሙሥሊሞች ጋር በመሆን አንዱን አምላክ ማምለክ ሲገባቸው የተውበት በሩ ከተዘጋ በኃላ በቁጭቱ ቀን፦ “ታላቅ ዕድልን አገኝ ዘንድ ከእነርሱ ጋር በኾንኩ ወይ ምኞቴ” “ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ መልካምን ሥራ ባስቀደምኩ ኖሮ” “ዋ ምኞቴ! ምንነው ዐፈር በኾንኩ” “ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ” ይላሉ፦
4፥73 ከአላህም የኾነ ችሮታ ቢያገኛችሁ በእናንተና በእርሱ መካከል ፍቅር እንዳልነበረች ሁሉ *«ታላቅ ዕድልን አገኝ ዘንድ ከእነርሱ ጋር በኾንኩ ወይ ምኞቴ!»* ይላል፡፡ وَلَئِنْ أَصَابَكُمْ فَضْلٌ مِّنَ اللَّهِ لَيَقُولَنَّ كَأَن لَّمْ تَكُن بَيْنَكُمْ وَبَيْنَهُ مَوَدَّةٌ يَا لَيْتَنِي كُنتُ مَعَهُمْ فَأَفُوزَ فَوْزًا عَظِيمًا
89፥24 *«ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ መልካምን ሥራ ባስቀደምኩ ኖሮ»* ይላል፡፡ يَقُولُ يَا لَيْتَنِي قَدَّمْتُ لِحَيَاتِي
78፥40 እኛ ሰው ሁሉ እጆቹ ያስቀደሙትን በሚያይበትና ከሓዲውም፦ *ዋ ምኞቴ! ምንነው ዐፈር በኾንኩ* በሚልበት ቀን ቅርብ የኾነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ፡፡ إِنَّا أَنذَرْنَاكُمْ عَذَابًا قَرِيبًا يَوْمَ يَنظُرُ الْمَرْءُ مَا قَدَّمَتْ يَدَاهُ وَيَقُولُ الْكَافِرُ يَا لَيْتَنِي كُنتُ تُرَابًا
25፥28 *«ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ*፡፡ يَا وَيْلَتَىٰ لَيْتَنِي لَمْ أَتَّخِذْ فُلَانًا خَلِيلًا

ነጥብ አሥራ አራት
"የውሙም መሽሁድ"
"የውሙም መሽሁድ" يَوْمٌ مَّشْهُود ማለት "የሚመሰከሩበት ቀን" ማለት ነው፦
11፥103 *በዚህ ውስጥ የመጨረሻውን ቀን ቅጣት ለሚፈሩ ሁሉ መገሰጫ አለ፡፡ ይህ የትንሣኤ ቀን ሰዎች በእርሱ የሚሰበሰቡበት ቀን ነው፡፡ ይህም የሚመሰከሩበት ቀን ነው"*፡፡ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّمَنْ خَافَ عَذَابَ الْآخِرَةِ ۚ ذَٰلِكَ يَوْمٌ مَّجْمُوعٌ لَّهُ النَّاسُ وَذَٰلِكَ يَوْمٌ مَّشْهُودٌ

በቁርኣን አናቅጽ ላይ “ሻሂድ” شَاهِد ማለት የሚመሰክር “መስካሪ” ማለት ሲሆን “መሽሁድ” مَشْهُود ማለት ደግሞ የሚመሰከርበት “ተመስካሪ” ማለት ነው። በተቀጠረው ቀን መስካሪ በተመስካሪ ላይ ይመሰክራሉ፦
85፥2 *”በተቀጠረው ቀንም እምላለው”*። وَالْيَوْمِ الْمَوْعُودِ
85፥3 *”በመስካሪ እና በተመስካሪ እምላለሁ”*፡፡ وَشَاهِدٍ وَمَشْهُودٍ

“መስካሪ” የተባሉት “ነቢያት” ሲሆኑ “የሚመሰከርባቸው” ደግሞ “ኡማቸው” ናቸው፦
16፥84 *”ከየሕዝቡም ሁሉ መስካሪን የምንቀሰቅስበትን ቀን አስታውስ”*፡፡ وَيَوْمَ نَبْعَثُ مِن كُلِّ أُمَّةٍ شَهِيدًا
4፥41 *”ከሕዝቦችም ሁሉ መስካሪን ባመጣን ጊዜ አንተንም በእነዚህ ሕዝብ ላይ መስካሪ አድርገን በምናመጣህ ጊዜ የከሓዲዎች ኹኔታ እንዴት ይኾን?”* فَكَيْفَ إِذَا جِئْنَا مِن كُلِّ أُمَّةٍ بِشَهِيدٍ وَجِئْنَا بِكَ عَلَىٰ هَـٰؤُلَاءِ شَهِيدًا
16፥89 *”በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ ከራሳቸው በእነርሱ ላይ መስካሪን የምንቀሰቅስበትን አንተንም በእነዚህ ሕዝብ ላይ መስካሪ አድርገን የምናመጣህን ቀን አስታውስ”*፡፡ وَيَوْمَ نَبْعَثُ فِي كُلِّ أُمَّةٍ شَهِيدًا عَلَيْهِم مِّنْ أَنفُسِهِمْ ۖ وَجِئْنَا بِكَ شَهِيدًا عَلَىٰ هَـٰؤُلَاء
28፥75 *”ከሕዝቦችም ሁሉ መስካሪን እናወጣለን፡፡ ያን ጊዜ እውነተኛውም አምላክነት ለአላህ ብቻ መኾኑን ያውቃሉ፡፡ ይቀጣጥፉት የነበሩትም ከእነርሱ ይጠፋቸዋል”*፡፡ وَنَزَعْنَا مِن كُلِّ أُمَّةٍ شَهِيدًا فَقُلْنَا هَاتُوا بُرْهَانَكُمْ فَعَلِمُوا أَنَّ الْحَقَّ لِلَّهِ وَضَلَّ عَنْهُم مَّا كَانُوا يَفْتَرُونَ

“ኡማህ” أُمَّة ማለት “ሕዝብ” ማለት ሲሆን በአንድ ነቢይ ዘመነ-መግቦት”dispensation” የሚቆዩትን “ሰዎች” ያመለክታል። እያንዳንዱ ነቢይ በራሱ ኡማህ ላይ በትንሳኤ ቀን ይመሰክራሉ።
አሥራ አምስት
"የውሙል ኹሉድ"
ኹሉድ" خُلُود‎ የሚለው ቃል "ኸለደ" خَلَدَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ዘላለማዊነት" ማለት ነው፥ "የውሙል ኹሉድ" يَوْمُ الْخُلُود ማለት "የዘላለማዊነት ወይም የመዘውተሪያ ቀን" ማለት ነው፦
50፥34 *"«በሰላም ግቧት ይህ "የመዘውተሪያ ቀን" ነው»* ይባላሉ፡፡ ادْخُلُوهَا بِسَلَامٍ ۖ ذَٰلِكَ يَوْمُ الْخُلُودِ

የትንሳኤ ቀን የጀነት ባለቤቶች በጀነት ውስጥ ለዘላለም ይኖራሉ፥ የእሳት ባለቤቶች በእሳት ውስጥ ለዘላለም ይኖራሉ። ሞት ይጠፋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 81, ሐዲስ 134
አቡ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ለጀነት ባለቤቶች፦ "ለእናንተ ዘላለማዊነት እንጂ ሞት የለም" ይባላሉ፥ ለእሳት ባለቤቶች፦ "ለእናንተ ዘላለማዊነት እንጂ ሞት የለም" ይባላሉ"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ يُقَالُ لأَهْلِ الْجَنَّةِ خُلُودٌ لاَ مَوْتَ‏.‏ وَلأَهْلِ النَّارِ يَا أَهْلَ النَّارِ خُلُودٌ لاَ مَوْتَ ‏"‌‏

"ኻሊድ" خَالِد ማለት "ዘላለማዊ" "ዘውታሪ" ማለት ነው፥ የኻሊድ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ኻሊዲን" خَالِدِين ወይም "ኻሊዱን" خَالِدُون ሲሆን "ዘላለማውያን" ወይም "ዘውታሪያን" ማለት ነው። በጀነት የሚኖሩ አማንያን "አስሓቡል ጀናህ" أَصْحَابُ الْجَنَّة ማለትም "የገነት ጓዶች" ሆነው ለዘላለም ይኖራሉ፦
2፥82 *እነዚያም ያመኑት በጎ ሥራዎችንም የሠሩት እነዚያ የገነት ጓዶች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው*፡፡ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ أُولَـٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ

በተቃራኒው ጀሀነም የሚኖሩ ከሃድያን "አስሓቡን ናር" أَصْحَابُ النَّار ማለትም "የእሳት ጓዶች" ሆነው ለዘላለም ይኖራሉ፦
2፥39 *እነዚያም በመልክተኞቻችን የካዱ በአንቀጾቻችንም ያስተባበሉ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው*፡፡ وَالَّذِينَ كَفَرُوا وَكَذَّبُوا بِآيَاتِنَا أُولَـٰئِكَ أَصْحَابُ النَّارِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ

የአላህ ዘላለማዊነት መነሻ የሌለው ቀዳማይ፥ መዳረሻ የሌለው ደኃራይ ነው። በጀነት እና በጀሀነም ያሉትን መነሻ ያላቸው ስለሆኑ ዘላለማዊነታቸው ቂደም አይደለም፥ "ቂደም" قِدَم የሚለው ቃል "ቀዱመ" قَدُمَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጅማሬ ወይም መነሻ የሌለው ቀዳማዊ ዘላለም"pre eternity" ማለት ነው፥ ይህ ዘላለማዊነት የአላህ ብቻ ነው።
ነገር ግን በጀነት እና በጀሀነም ያሉትን ዘላለማዊነታቸው በቃእ ነው፥ "በቃእ" بَقَاء የሚለው ቃል "በቂየ" بَقِيَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ፍጻሜ ወይም መዳረሻ የሌለው ደኃራዊ ዘላለም"post eternity" ማለት ነው። ስለ የመጨረሻው ቀን እሳቤ ከብዙ በጥቂቱ ይንን ይመስላል። አምላካችን አላህ ዒባዳችንን በኢኽላስ ተቀብሎ አስሓቡል ጀናህ ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የሥላሴአውያን ቅዠት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

15፥74 ላይዋንም ከታችዋ አደረግን፡፡ በእነሱም ላይ የሸክላ ደንጊያዎችን አዘነብንባቸው፡፡ فَجَعَلْنَا عَالِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِمْ حِجَارَةً مِّن سِجِّيلٍ

አምላካችን አላህ ወንድ እና ወንድ በተዳሩት ሰዶማውያን ላይ የሸክላ ደንጊያዎች የሆነ ዝናብ ከላይ አዝንቦባቸዋል፦
15፥74 ላይዋንም ከታችዋ አደረግን፡፡ በእነርሱም ላይ የሸክላ ደንጊያዎችን አዘነብንባቸው፡፡ فَجَعَلْنَا عَالِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِمْ حِجَارَةً مِّن سِجِّيلٍ
7፥84 *በእነርሱም ላይ ዝናብን አዘነብንባቸው*፡፡ የኃጢአተኞችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት፡፡ وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِم مَّطَرًا ۖ فَانظُرْ كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُجْرِمِينَ
27፥58 በእነርሱም ላይ ዝናብን አዘነብንባቸው፡፡ የተስፈራሪዎቹም ዝናብ ከፋ፡፡ وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِم مَّطَرًا ۖ فَسَاءَ مَطَرُ الْمُنذَرِينَ

ይህ ዘገባ በተመሳሳይ ባይብል ላይ አለ፦
ዘፍጥረት 19፥24 *እግዚአብሔርም በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበ*።
ነገር ግን የሥላሴ አማንያን እዚህ አንቀጽ ላይ “ወልድ” እና “አብ” የሚል ሃይለ-ቃል ሳይኖር፦”እግዚአብሔር ወልድ በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ እሳትና ዲን አዘነበ” ብለው ይተረጉማሉ፤ አንቀጹ ላይ፦ “አንደኛው ማንንነት ከሌላው ማንነት ዘንድ እሳትና ዲን አዘነበ” አይልም። ነገር ግን የሚለው፦ “እግዚአብሔርም በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ እሳትና ዲን አዘነበ” ነው፤

ለመሆኑ ስንት እግዚአብሔር አለ? እስቲ እናስተንትን፦
ዘዳግም 6፥4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር *አንድ እግዚአብሔር ነው*።
እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ከሆነ በሰዶምና በገሞራ ላይ እሳትና ዲን ያዘነበው እራሱ እግዚአብሔር ከራሱ ዘንድ ነው፤ ይህንን ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
“ሥስተኛ መደብ”
እግዚአብሔር እራሱን በሦስተኛ መደብ አድርጎ፦ “ሰዶምንና ገሞራን እግዚአብሔር ገለበጣቸው” ይለናል፦
አሞጽ 4፥11 *ሰዶምንና ገሞራን እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ እንዲሁ ገለበጥኋችሁ… ይላል እግዚአብሔር።
ኤርምያስ 50፥40 *ሰዶምንና ገሞራን በአጠገባቸውም የነበሩትን ከተምች እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ ይላል
እግዚአብሔር*፥ እንዲሁ ሰው በዚያ አይቀመጥም የሰውም ልጅ አይኖርባትም።

እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦ ሰይጣን ሆይ፥ እግዚአብሔር ይገሥጽህ ብሎታል፦
ዘካርያስ 3፥2 *እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦ ሰይጣን ሆይ፥ እግዚአብሔር ይገሥጽህ*፤ ኢየሩሳሌምን የመረጠ እግዚአብሔር ይገሥጽህ፤ በውኑ ይህ ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ አይደለምን? *አለው*።

ያ ማለት አንደኛው እግዚአብሔር በሌላው እግዚአብሔር እየገሰጸ ነው ማለት አይደለም፤ እራሱ በራሱ እየገሰጸው ነው፦
ኢዮብ 2÷3 *እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦ በውኑ ባሪያዬን ኢዮብን ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ*፥ ከክፋትም የራቀ ሰው የለም፤
እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦ “እኔንም የሚፈራ” በማለት ፋንታ በሦስተኛ መደብ “እግዚአብሔርንም የሚፈራ” ብሏል፦
ዘጸአት 20፥7 *የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና*።

እግዚአብሔርም፦ “የእኔን ስም በከንቱ አትጥራ፤ ስሜን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አላነጻውምና” በማለት ፋንታ በሦስተኛ መደብ “የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና” ብሏል፦
ዘካርያስ 10፥12 *በአምላካቸው በእግዚአብሔር አበረታቸዋለሁ፥ በስሙም ይመካሉ፥ ይላል እግዚአብሔር*።

እራሱ እግዚአብሔር በአምላካቸው በእግዚአብሔር አበረታቸዋለሁ ማለቱ አንባቢ ልብ ይለዋል። ይህንን ናሙና በሌሎች ጥቅሶች አንብቡት፦
1ኛ ሳሙኤል 20፥12-13 *ዮናታንም ዳዊትን አለው፦….እግዚአብሔር በዮናታን ይህን ያድርግ ይህንም ይጨምር*፤
1ኛ ነገሥት 1፥33 ንጉሡም አላቸው፦ የጌታችሁን ባሪያዎች ይዛችሁ ሂዱ፥ ልጄንም ሰሎሞንን በበቅሎዬ ላይ አስቀምጡት፥ ወደ ግዮንም አውርዱት፤
አስቴር 8፥7-8 *ንጉሡም አርጤክስስ ንግሥቲቱን አስቴርንና አይሁዳዊውን መርዶክዮስን፦ እነሆ የሐማን ቤት ለአስቴር ሰጥቻለሁ፥ እርሱም እጆቹን በአይሁድ ላይ ስለ ዘረጋ በግንድ ላይ ተሰቀለ።

በንጉሡ ስም የተጻፈና በንጉሡ ቀለበት የታተመ አይገለበጥምና እናንተ ደግሞ ደስ የሚያሰኛችሁን በንጉሡ ስም ስለ አይሁድ ጻፉ፥ በንጉሡም ቀለበት አትሙ፡ አላቸው*።
ሉቃስ 9፥26 *በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅ በክብሩ በአባቱና በቅዱሳን መላእክቱ ክብርም ሲመጣ* በእርሱ ያፍርበታል።

አንድ ማንነት በሦስተኛ መደብ መገለጹ ያንን ማንነት ብዙ እንደማያደርገው ካየን ዘንዳ አሁን ደግሞ “ዘንድ” የሚለው መስተዋድድ በአንድ ማንነት እንዴት እንዳገለገለ በሚቀጥለው ነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ ሁለት
“ዘንድ”
ዳዊት የምስጋና ስእለት ከእርሱ ዘንድ ሰጥቷል፦
መዝሙር 56፥12 አቤቱ፥ *የምስጋና ስእለት የምሰጥህ ከእኔ ዘንድ ነው*።
ዳዊት አንድ ሰውና ማንነት ሆኖ ሳለ ሰጪ እርሱ የሚሰጠው ከእርሱ ዘንድ እንደሆነ ተናግሯል፤ ያ ማለት ዳዊት ሁለት ሰው ወይም ሁለት ማንነት መሆኑን ያሳያልን? አንድ ሆኖ ሳለ “አለይ” עָלַ֣י ማለትም “ዘንድ” የሚል መስተዋድድ ይጠቀማል፤ ይህ የተለመደ ሰዋስው ነው፦
ዘዳግም 15፥12 “አንተም” ወንድምህን ዕብራዊውን ወይም ዕብራዊቱን ብትገዛ ስድስት ዓመት ያገልግሉህ በሰባተኛውም ዓመት *ከአንተ ዘንድ አርነት አውጣው*።

“ከአንተ ዘንድ” የሚለው ቃል “መሚከ” מֵעִמָּֽךְ ተብሎ የተቀመጠ ሲሆን “አንተ” በሚል ተውላጠ-ስም ላይ “ዘንድ” የሚል መስተዋድድ መነሻ ቅጥያ ሆኖ መጥቷል፤ “አንተ ከአንተ ዘንድ አርነት አውጣው” ማለት ያ ሰው ሁለት ሰው ወይም ሁለት ማንነት ሆነ ማለት ነው? የእግዚአብሔርም ክብር የእግዚአብሔርን ቤት ሞልቶት ነበር፦
2ኛ ዜና 7፥2 *የእግዚአብሔርም ክብር የእግዚአብሔርን ቤት ሞልቶት ነበርና* ካህናቱ ወደ እግዚአብሔር ቤት መግባት አልቻሉም።
ዘኍልቍ 14፥20 እግዚአብሔርም አለ፦ *”እንደ ቃልህ ይቅር አልሁ፤ ነገር ግን እኔ ሕያው ነኛ በእውነት የእግዚአብሔር ክብር ምድርን ሁሉ ይሞላል”*።

“የ” የሚል አገናዛቢ ቃል “እግዚአብሔር” በሚለው ቃል ላይ መነሻ ቅጥያ ሆኖ መግባቱ እና “እግዚአብሔር” የሚለው ቃል ሁለቴ መግባቱ ሁለት እግዚአብሔር ወይም ሁለት ማንነቶች አያሳም።

በተጨማሪም “የእኔ ክብር ምድርን ሁሉ ይሞላል” በማለት ፈንታ “በእውነት የእግዚአብሔር ክብር ምድርን ሁሉ ይሞላል” ማለቱ እግዚአብሔር ወይም ሁለት ማንነቶች እንደማያሳይ ሁሉ ከላይ ያለውን የዘፍጥረትን 19፥24 ያለውን ጥቅስ በዚህ ስሌትና ቀመር መረዳት ይቻላል። የሥላሴ አማንያን ሁለት ቃላት ከተገኘ አብ እና ወልድ ሦስት ቃላት ከተገኘ ሥላሴ የሚል ቅዠት አላቸው፤ የሥላሴ አማንያን ቅዠት አያልቅም።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሦስት አምላክ

እዚህ ቻናል ስንት ሰው አለ? ብል ሺህ ትሉኛላችሁ፥ ከሰማያት በላይ ስንት አምላክ አለ? ብል 1 አምላክ ትሉኛላችሁ። እዚህ ቻናል ያለው ሰው 17100 ሺህ የሆነው በአካል የተለያየን ስለሆንን ነው፥ አምላክ በአካል ሦስት ከሆነ አንድ ሳይሆን ሦስት አምላክ ነው። የሥላሴ አማንያን "ኤሎሂም” אלהים ማለት "አማልክት" ማለት ሲሆን ሥላሴን ያሳያል ይላሉ፥ በጣም ጥሩ ሦስቱ አካላት አማልክት ናቸው ማለት ነው። ለዛውም ሦስት አምላክ ሳይሆን ሦስት አምላክት ነው፥ እነዚህ ሥስት አካሎች “ጌቶች” ይባላሉ። “አጋዕዝተ-ዓለም ሥላሴ” ማለት “የዓለም ጌቶች ሥላሴ” ማለት ነው፥ “እግዚእ” በነጠላ “ጌታ” ማለት ሲሆን “አጋዕዝት” ማለት ደግሞ በብዜት “ጌቶች” ማለት ነው፥ ስለዚህ ሥላሴ ሦስት ጌቶች ናቸው። ተመልሰው አንድ አምላክ አንድ ጌታ ትላላችሁ። ዘመወዛገብ ይሉሃል እንዲህ ነው፥ እራሳችሁ ሳይገባችሁ እንዴት ማስረዳት ትችላላችሁ?

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
መንገድ ጠራጊ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥17 *እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ*፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

የሥላሴ አማንያን ከባይብል ኢየሱስን አምላክ ለማድረግ የማይቆፍሩት ጉድጓድ፣ የማይፈነቅሉት ድንጋይ፣ የማይደረምሱት መሬት የለም። ኢሳይያስ ላይ ያህዌህ መንገድ እንደሚጠረግለት ተነግሮ አዲስ ኪዳን ላይ ግን መጥምቁ ዮሐንስ መንገድ የጠረገው ለኢየሱስ ስለሆነ "ኢየሱስ ያህዌህ ነው" ብለው ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፦
ኢሳይያስ 40፥3 የአዋጅ ነጋሪ ቃል፦ *"የያህዌን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካከሉ"*።
ማርቆስ 1፥2 *"እነሆ መንገድህን የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ፥ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ ተብሎ በነቢዩ በኢሳይያስ እንደ ተጻፈ"*።

እዚህ ጥቅስ ላይ ብዙ ችግር አለ። አንደኛ "በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ" የሚለው ኢሳይያስ ላይ የለም። ሁለተኛ "እነሆ መንገድህን የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ" የሚለው "በነቢዩ በኢሳይያስ እንደ ተጻፈ" ይላል እንጂ ኢሳይያስ አልተጻፈም። የተጻፈው ሚልክያስ ላይ ነው፦
ሚልክያስ 3፥1 *"እነሆ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል"*።

ሦስተኛ በትንቢቱ ላይ "በፊቴ" እንጂ "በፊትህ" የሚል የለም። አራተኛ ሙግቱን ጠበብ አርገነው አብ ለወልድ በሁለተኛ መደብ "በፊትህ" ካለ መልእክተኛውን መንገድ የሚጠርገው በሚልክያስ ላይ "በፊቴ" ላለው አብ እና በማርቆስ ላይ "በፊትህ" ለተባለው ለወልድ ነው። ምክንያቱም አብ ለወልድ "መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ" ብሎ መንገድ ጠራጊውን ዮሐንስን ልኳል፦
ዮሐንስ 1፥6 *"ከእግዚአብሔር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ"*።
ሉቃስ 1፥76 *"ደግሞም አንተ ሕፃን ሆይ፥ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፥ መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሄዳለህና"*።

ዮሐንስ የልዑል ነቢይ ከሆነ ልዑል የተባለው አብ እንጂ ኢየሱስ አይደለም፥ ኢየሱስ የልዑል ልጅ እንጂ ልዑል አልተባለም። ሲቀጥል ሉቃስ 1፥76 ላይ "ጌታ" የተባለው "አብ" ነው፥ ዐውደ-ንባቡ ላይ "በጌታ ፊት ሊያቆሙት ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት" ይላል፦
ሉቃስ 1፥32 *እርሱ ታላቅ ይሆናል "የልዑል ልጅም" ይባላል*።
ሉቃስ 2፥22 በጌታ ፊት ሊያቆሙት...ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት"*።

ስለዚህ "መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሄዳለህና" ሲል "ጌታ" የተባለው አብ ነው፥ ምክንያቱም ወልድን "በጌታ ፊት ሊያቆሙት ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት" ስለሚል። ዮሐንስ የአብ ማለትም ያያህዌን መንገድ እና የወልድ ማለትም የመሢሑን መንገድ ጠራጊ ነው። አራት ቆጠራችሁ? አምስተኛ ደግሞ ብሉይ ላይ የተጠቀሰ ጥቅስ አዲስ ላይ ፍጻሜ ካገኘ ብሉይ ላይ ያለ ጥቅስ የአዲስ ኪዳኑ ማንነት ነው ተብሎ በአራት ነጥብ አይደመደምም። አንዳንድ ናሙና እስቲ እንይ፦
2 ሳሙኤል 7፥14 *"እኔም አባት እሆነዋለሁ፥ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ ክፉ ነገርም ቢያደርግ፥ ሰው በሚቀጣበት በትርና በሰው ልጆች መቀጫ እገሥጸዋለሁ"*።
ዕብራውያን 1፥5 *"ደግሞም፦ እኔ አባት እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል" ያለው ከቶ ለማን ነው?*።

"እኔ አባት እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል" የሳሙኤል ዐውደ-ንባብ የሚናገረው ለንጉሥ ሰለሞን ነው፥ የዕብራውያን ጸሐፊ ለኢየሱስ ነው ይለናል። እና ኢየሱስ ብሉይ ላይ የነበረው ሰለሞን ነውን? እንደ እናንተ እምነት ኢየሱስ ያህዌህ ከሆነ ያህዌህ አምላክ እንዴት ፍጡሩን ሰለሞን ይሆናል? መልሱ፦ "ድርብ አጠቃቀም ነው" የሚል ነው፥ እንግዲያውስ ብሉይ ላይ የያህዌህ መንገድ ተብሎ አዲስ ላይ የጌታ መንገድ መባሉ "ድርብ አጠቃቀም ነው" በሚል ስሌትና ቀመር መረዳት ይቻላል። ናሙናውን እንቀጥል፦
ሆሴዕ 11፥1-2 *"እስራኤል ሕፃን በነበረ ጊዜ ወደድሁት፥ ልጄንም ከግብፅ ጠራሁት። አብዝቼ ብጠራቸው አጥብቀው ከፊቴ ራቁ፤ ለበኣሊምም ይሠዉ ነበር፥ ለተቀረጹ ምስሎችም ያጥኑ ነበር"*።
ማቴዎስ 2፥14-15 *"እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ፦ "ልጄን ከግብፅ ጠራሁት" የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብፅ ሄደ፥ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ"*።

"ልጄንም ከግብፅ ጠራሁት" የሆሴዕ ዐውደ-ንባብ የሚናገረው ለእስራኤል ሕዝብ ነው፥ የማቴዎስ ጸሐፊ ለኢየሱስ ነው ይለናል። ታዲያ ኢየሱስ ሲጠራ አጥብቆ ከአምላክ ፊት የራቀ ነውን? ለበኣሊምም ይሠዋ ነበርን? ለተቀረጹ ምስሎችም ያጥን ነበርን? ቅሉ ግን "ድርብ አጠቃቀም ነው" የሚል ነው፥ እንግዲያውስ ብሉይ ላይ የያህዌህ መንገድ ተብሎ አዲስ ላይ የጌታ መንገድ መባሉ "ድርብ አጠቃቀም ነው" በሚል ልክና መልክ መረዳት ይቻላል። ስድስተኛ "የያህዌህን መንገድ ማለት የያህዌህ ሕግ፣ ሥርዓት፣ ትእዛዝ፣ መርሕ እና ቃል ነው፦
መዝሙር 18፥21 *"የያህዌህን መንገድ ጠብቄአለሁ፥ በአምላኬም አላመፅሁም"*።
መዝሙር 18፥30 *"የአምላኬ መንገድ ፍጹም ነው፥ የያህዌህን ቃል የነጠረ ነው፥ በእርሱ ለሚታመኑት ሁሉ ጋሻ ነው"*።
ምሳሌ 10፥29 *የያህዌህ መንገድ ያለ ነውር ለሚሄድ አምባ ነው፥ ጥፋት ግን ክፋትን ለሚያደርጉ*።
ኤርምያስ 5፥4 እኔም፦ የያህዌህን መንገድና የአምላካቸውን ሕግ አላወቁምና እነዚህ በእውነት ድሆችና ሰነፎች ናቸው"*።

የኢየሱስ ትምህርት እና ሕግ የያህዌህ ሕግ ነው፥ የራሱ ሳይሆን የላከኝ አብ የሰጠው ትእዛዝ ነው፦
ዮሐንስ 12፥49 *እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፥ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ"*።
ዮሐንስ 14፥24 የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም፤ *"የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም"*።
ዮሐንስ 17፥8 *"የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና እነርሱም ተቀበሉት"*።

የአብን ቃል ወደ እራሱ በማስጠጋት "ቃሌ" ማለቱ በራሱ የአብ እና የወልድ መንገድ አንድ መሆኑን ያሳያል። ዮሐንስ አዋጅ ነጋሪ የሆነ እና የጠረገው የያህዌህን እና የመሢሑን መንገድ ነው። ስለዚህ ኢሳይያስ 40፥3 ኢየሱስ ያህዌህ መሆኑን በፍጹም አያሳይም። እነዚያ ፈጣሪን ከሴት የተወለደው መሢሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፦
5፥17 *እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ*፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ግመልህን እሰርና በአላህ ላይ ተመካ!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።

6፥159 *”ቁርጥ ሐሳብም ባደረግህ ጊዜ በአላህ ላይ ተመካ፡፡ አላህ በእርሱ ላይ ተመኪዎችን ይወዳልና”*፡፡ فَإِذَا عَزَمْتَ فَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُتَوَكِّلِينَ

አምላካችን አላህ ለእስራኤልም ልጆች፦ “ከእኔ ሌላ መመኪያን አትያዙ” በማለት ተናግሯል፦
17፥2 ሙሳንም መጽሐፉን ሰጠነው፡፡ ለእስራኤልም ልጆች መሪ አደረግነው፡፡ *”ከእኔ ሌላ መመኪያን አትያዙ! አልናቸውም”*፡፡ وَآتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ وَجَعَلْنَاهُ هُدًى لِّبَنِي إِسْرَائِيلَ أَلَّا تَتَّخِذُوا مِن دُونِي وَكِيلًا

“አል-ወኪል” الْوَكِيل ማለት “መመኪያ” “መጠጊያ” “መሸሸጊያ” ማለት ሲሆን በቁርኣን ከተገለጹ 99 ስሞች አንዱ ነው፦
39፥9 እርሱም የምሥራቅና የምዕራብ ጌታ ነው፡፡ *”ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ መጠጊያ አድርገህም ያዘው”*፡፡ رَّبُّ الْمَشْرِقِ وَالْمَغْرِبِ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ فَاتَّخِذْهُ وَكِيلًا

አላህን መጠጊያ መመኪያ፣ መጠጊያ፣ መሸሸጊያ አድርጎ መያዝ “ተወኩል” تَوَكُّل ይባላል። ሰይጧን በእነዚያ ባመኑት እና በአላህ ላይ በሚመኩት ላይ ስልጣን የለውም፦
16፥99 *”እርሱ በእነዚያ ባመኑት እና በጌታቸው ላይ በሚጠጉት ላይ ለእርሱ ስልጣን የለውምና”*፡፡ إِنَّهُ لَيْسَ لَهُ سُلْطَانٌ عَلَى الَّذِينَ آمَنُوا وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ

“በሚጠጉት” ለሚለው ቃል የገባው “የተወከሉን” يَتَوَكَّلُون ሲሆን ቁርጥ ሐሳብም ባደረጉ ጊዜ አላህ በቂዬ ነው ብለው በአላህ ላይ ሙሉ ለሙሉ የተወከሉ ባሮቹ ደግሞ “ሙተወከሉን” مُتَوَكِّلُون ይባላል፦
39፥38 *«አላህ በቂዬ ነው፡፡ በእርሱ ላይ ተመኪዎች ይመካሉ»* በል፡፡ قُلْ حَسْبِيَ اللَّهُ ۖ عَلَيْهِ يَتَوَكَّلُ الْمُتَوَكِّلُونَ
6፥159 *”ቁርጥ ሐሳብም ባደረግህ ጊዜ በአላህ ላይ ተመካ፡፡ አላህ በእርሱ ላይ ተመኪዎችን ይወዳልና”*፡፡ فَإِذَا عَزَمْتَ فَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُتَوَكِّلِينَ

"ቁርጥ ሐሳብም ባደረግህ" ማለት አንድ ሙሥሊም ሙሲባህ ሲመጣበት ጥንቃቄ በማድረግ ሰበቡ ያደርሳል፥ ከዚያ በላይ ከአቅሙ በላይ ያለውን ለአላህ ሰጥቶ በአላህ ላይ ይመካል። ለዛ ነው ነቢያችን"ﷺ" "ግመልህን እሰርና በአላህ ላይ ተመካ" ያሉት፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 2707
አነሥ ኢብኑ ማሊ እንዳስተላለፈው፦ “አንድ ሰው፦ *"የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ሆይ! ግመሌን ልሰራትና በአላህ ላይ ልመካ ወይስ ልተዋትና በአላህ ላይ ልመካ? ብሎ ጠየቀ። እርሳቸውም፦ "እሰራትና በአላህ ላይ ተመካ" አሉት"*። قَالَ سَمِعْتُ أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ، يَقُولُ قَالَ رَجُلٌ يَا رَسُولَ اللَّهِ أَعْقِلُهَا وَأَتَوَكَّلُ أَوْ أُطْلِقُهَا وَأَتَوَكَّلُ قَالَ ‏ "‏ اعْقِلْهَا وَتَوَكَّلْ ‏"‏

አምላካችን አላህ ሰበቡን አንድርሰን በእርሱ ላይ የምመካ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተስሊብ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

12፥41 *"የወህኒ ቤት ጓደኞቼ ሆይ! አንደኛችሁማ ጌታውን (ንጉሡን) ጠጅ ያጠጣል፡፡ ሌላውማ "ይሰቀላል"፡፡ ከራሱም በራሪ (አሞራ) ትበላለች፡፡ ያ ፍቹን የምትጠይቁት ነገር ተፈጸመ"* አላቸው፡፡  يَا صَاحِبَيِ السِّجْنِ أَمَّا أَحَدُكُمَا فَيَسْقِي رَبَّهُ خَمْرًا ۖ وَأَمَّا الْآخَرُ فَيُصْلَبُ فَتَأْكُلُ الطَّيْرُ مِن رَّأْسِهِ ۚ قُضِيَ الْأَمْرُ الَّذِي فِيهِ تَسْتَفْتِيَانِ

አምላካችን አላህ በዩሱፍ ዘመን የነበረው ክስተት "ነቅሱ ዐለይከ" نَقُصُّ عَلَيْكَ ማለትም "እንተርክልሃለን" በማለት ክስተቱን ይተርካል፦
12፥3 እኛ ይህንን ቁርኣን ወደ አንተ በማውረዳችን በጣም መልካም ዜናዎችን በአንተ ላይ እንተርክልሃለን፡፡ እነሆ ከእርሱ በፊት በእርግጥ ከዘንጊዎቹ ነበርክ"*፡፡ نَحْنُ نَقُصُّ عَلَيْكَ أَحْسَنَ الْقَصَصِ بِمَا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ هَـٰذَا الْقُرْآنَ وَإِن كُنتَ مِن قَبْلِهِ لَمِنَ الْغَافِلِينَ

አላህ በሡረቱ ዩሱፍ ከተረካቸው አንዱ ስለ ተስሊብ ነው፥ "ተስሊብ" تَصْلِيب የሚለው ቃል "ሶልለበ" صَلَّبَ‎ ማለትም "ሰቀለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ስቅላት" ማለት ነው። "ሶልብ" صَلْب የሚለው ቃል "ሶለበ" صَلَبَ‎  ማለትም "ተሰቀለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ስቅለት" ማለት ነው። የግብጽ ነገሥታት ወንጀለኛ በስቅላት ይቀጡ እንደነበር እንዲህ ይተርክልናል፦
12፥41 *"የወህኒ ቤት ጓደኞቼ ሆይ! አንደኛችሁማ ጌታውን (ንጉሡን) ጠጅ ያጠጣል፡፡ ሌላውማ "ይሰቀላል"፡፡ ከራሱም በራሪ (አሞራ) ትበላለች፡፡ ያ ፍቹን የምትጠይቁት ነገር ተፈጸመ"* አላቸው፡፡  يَا صَاحِبَيِ السِّجْنِ أَمَّا أَحَدُكُمَا فَيَسْقِي رَبَّهُ خَمْرًا ۖ وَأَمَّا الْآخَرُ فَيُصْلَبُ فَتَأْكُلُ الطَّيْرُ مِن رَّأْسِهِ ۚ قُضِيَ الْأَمْرُ الَّذِي فِيهِ تَسْتَفْتِيَانِ

እዚህ አንቀጽ "ይሰቀላል" ለሚለው የግስ መደብ የገባው ቃል "ዩስለቡ"  يُصْلَبُ ነው። "ጌታው" የተባለው በዩሱፍ ዘመን የነበረው ፈርዖን ነው፥ የግብጽ ነገሥታት ወንጀለኛ በስቅላት እንደሚቀጡ የሚያሳይ ታሪካዊ ሆነ ሥነ-ቁፋሮአዊ መረጃ አልተገኘም። ታሪክ ሆነ ሥነ-ቁፋሮ ወንጀለኛ በስቅላት ያለው መረጃ በ 559 ቅድመ-ልደት በፋርሳዊያን ጊዜ ነው፥ ያ ማለት ከዚያ በፊት ወንጀለኛ በስቅላት አይቀጡም ነበር ማለት አይደለም። ምክንያቱም ታሪክ ያለፈውን ክስተት የሚተርክ የምርምር ጥናት እና አሰሳ ሲሆን በታሪክ ጥናት ውስጥ ለታሪክ ምንጭ የሚሆኑ ሁለት መረጃዎች አሉ፥  አንደኛው ትውፊት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የሥነ-ቁፋሮ ጥናት ነው። “ትውፊት” ከትውልድ ወደ ትውልድ በቃል የሚተላለፍ ቅብብል ሲሆን "ሥነ-ቁፋሮ ጥናት" ደግሞ በተለያየ ቁስ ላይ የተጻፉትን ጽሑፎች አስሶና ቆፍሮ የሚያቀርብ የታሪክ ምንጭ ነው። ትውፊት ሆነ ሥነ-ቁፋሮ ጥናት ባህል ላይ እና ስልጣኔ ላይ መሠረት ያደረጉ ግምት”speculation” ናቸው።

ይህን ግምት የታሪክ ምሁራን በስድስት ከፍለው ያስቀምጡታል፥ እነዚህም፦ መቼ ተገኘ ጊዜን፣ የት ተገኘ ቦታን፣ ማን ደረስው ምንጭን፣ ቅድመ-ሁኔታ፣ ስምምነት እና ዋጋነት ናቸው። አራቱ ግምቶች መቼ ተገኘ፣ የት ተገኘ፣ ማን ደረስው እና ቅድመ-ትንታኔ ላዕላይ ኂስ ሲባሉ  አምስተኛው ግምት ስምምነት ደግሞ ታኅታይ እና ውጫዊ ኂስ ነው፥ በመቀጠል ስድስተኛው ግምት ዋጋነት ውስጣዊ ኂስ ነው። የታሪክ ምሁራን እንደሚያስተነትኑት ታሪክ መረጃ እንጂ ማስረጃ አይደለም። አምላካችን አላህ በዩሱፍ ዘመን የነበረው ክስተት የተረከው ትረካ ግን ማስረጃ መሆን ይችላል፥ ምክንያቱም እርሱ “አል-ገይቡል ማዲ” ٱلْغَيْب الْمَاضِي ማለትም “ኀላፊያት የሩቅ ነገር” በትክክል የሚያውቅ ሁሉን ዐዋቂ ነውና።

እዚህ ድረስ ከተግባባ የግብጽ ነገሥታት ወንጀለኛ በስቅላት እንደሚቀጡ የሚያሳይ ታሪካዊ ሆነ ሥነ-ቁፋሮአዊ መረጃ አለመገኘቱ ክስተቱን ውሸት ካደረገው እንግዲያውስ ከፋርሳዊያን በፊት አንድ ሺህ ዓመት ቀደም ብሎ የግብጽ ነገሥታት ወንጀለኛ በስቅላት እንደሚቀጡ የሚያሳይ ተመሳሳይ ታሪክ እና ትርክት በባይብል ቁልጭና ፍንትው ብሎ ተቀምጧል፦
ዘፍጥረት 40፥19  *"እስከ ሦስት ቀን ድረስ ፈርዖን ራስህን ከፍ ያደርጋል፥ "በእንጨትም ላይ ይሰቅልሃል"፣ ወፎችም ሥጋህን ይበሉታል"*። שלשת ימים ישא פרעה את־ראשך מעליך ותלה אותך על־עץ ואכל העוף את־בשרך מעליך׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "ይሰቅላል" ለሚለው "ታላህ" תָלָ֥ה ሲሆን የሚገርመው በፋርሱ ንጉሥ በአርጤክስስ እጃቸውን ያነሱት ሁለቱ የአርጤክስስ ጃንደረቦች በስቅላት "ተሰቀሉ" ለሚለው የግስ መደብ የገባው ተመሳሳይ ርቢ ያለው "ዪታሉ" יִּתָּל֥וּ ነው፦
አስቴር 2፥23 *"ነገሩም ተመረመረ፥ እንዲህም ሆኖ ተገኘ፥ "ሁለቱም በዛፍ ላይ ተሰቀሉ" ያም በንጉሡ ፊት በታሪክ መጽሐፍ ተጻፈ"*። ויבקש הדבר וימצא ויתלו שניהם על עץ ויכתב בספר דברי הימים לפני המלך׃

በእንጨት ላይ በማንጠልጠል የሚቀጣው ቅጣት ስቅላት ይባላል። ቅሉና ጥቅሉ የስቅለት ቅጣት ከፋርሳውያን 1000 ዓመት በፊት  በፈርዖኑ ጊዜ ነበረ፦
ዘፍጥረት 40፥22 *"የእንጀራ አበዛዎቹንም አለቃ "ሰቀለው"፥ ዮሴፍ እንደተረጎመላቸው"*።
ዘፍጥረት 41፥13 እንዲህም ሆነ እንደ ተረጐመልን እንደዚያው ሆነ፤ እኔ ወደ ሹመቴ ተመለስሁ፥ *"እርሱም ተሰቀለ"*።

ከፋርሳውያን 800 ዓመት በፊት በሙሴ ጊዜ ነበረ፦
ዘዳግም 21፥22-23 *"ማንም ሰው ለሞት የሚያበቃውን ኃጢአት ቢሠራ፥ እንዲሞትም ቢፈረድበት፥ *"በእንጨትም ላይ ብትሰቅለው፥ በእንጨት ላይ የተሰቀለ"* በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና ሬሳው በእንጨት ላይ አይደር።

ከፋርሳውያን 400 ዓመት በፊት በዳዊት ጊዜ ነበረ፦
2 ሳሙኤል 21፥12 ዳዊትም ሄደ፥ ሳኦልንም በጊልቦዓ በገደሉ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን *"ከሰቀሉአቸው"* ስፍራ ከቤትሳን አደባባይ ከሰረቁት ከኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን አጥንት ወሰደ፤

የብሪታኒካ የዓለም ሃይማኖቶች መድብለ ዕውቀት ገጽ 270 ላይ፦ "ወንጀለኛ በስቅላት መስቀል የተጀመረው በ 559 ቅድመ-ልደት በፋርሳዊያን ጊዜ ነው" ካለ ከላይ ያሉት የባይብል ትርክቶች ገደል ገቡ ማለት ነው። አይ "ታሪክ እና ሥነ-ቁፋሮ ያልደረሱበት ጉዳይ ነው" ካላችሁ እንግዲያውስ ከላይ ያለውንም የአምላካችን የአላህ ትርክት ታሪክ እና ሥነ-ቁፋሮ ያልደረሱበት ጉዳይ ነው በሚል ቀመርና ስሌት ተረዱት።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ይሄድልናል ወይስ ይሄድላቸዋል?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

6፥19 *«እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው፥ እኔም ከምታጋሩት ነገር ንጹሕ ነኝ»* በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ وَإِنَّنِى بَرِىٓءٌۭ مِّمَّا تُشْرِكُونَ

"ሰፕቱጀንት" ወይም "ሰፕቱአጀንት"Ἑβδομήκοντα" ማለት "ሰባ" ማለት ሲሆን በ 280 ቅድመ-ልደት በአሌክሳንድያ ይኖሩ የነበሩ የግሪክ አይሁዳውያን 70 ምሁራን ስም ነው፥ በሮማውያን ቁጥር ምልክት"LXX" ይባላል። እነዚህ ምሁራን 72 ነበሩ፥ ሁለቱ ሲሞቱ ሰባው ሊቃናት የዕብራይስጡን ቅዱሳን ጽሑፎች ወደ ሄለናዊ ግሪክ ኮይኔ ተርጉመውታል። እዚህ ትርጉም ላይ ለዚህ ሕዝብ ማንስ ይሄድላቸዋል? የሚል ኃይለ-ቃል አለ፦
ኢሳይያስ 6፥8 *የጌታንም ድምፅ፦ ማንን እልካለሁ? ለዚህ ሕዝብ ማንስ ይሄድላቸዋል? ሲል ሰማሁ። እኔም፦ እነሆኝ፥ እኔን ላከኝ" አልሁ"*። καὶ ἤκουσα τῆς φωνῆς Κυρίου λέγοντος· τίνα ἀποστείλω, καὶ τίς πορεύσεται πρὸς τὸν λαὸν τοῦτον; καὶ εἶπα· ἰδοὺ ἐγώ εἰμι· ἀπόστειλόν με.

ልብ አድርግ የሚለው "ይሄድላቸዋል" ነው። ለማን ሲባል "ለዚህ ሕዝብ" ኢሳይያስም በብዜት "እኔን ላኩኝ" ሳይሆን በነጠላ "እኔን ላከኝ" ብሏል፥ ጌታም፦ "ሂድ፥ ይህን ሕዝብ፦ መስማትን ትሰማላችሁ አታስተውሉምም፤ ማየትንም ታያላችሁ አትመለከቱምም" በላቸው" አለ፦
ኢሳይያስ 6፥9 *"እርሱም፦ ሂድ፥ ይህን ሕዝብ፦ መስማትን ትሰማላችሁ አታስተውሉምም፤ ማየትንም ታያላችሁ አትመለከቱምም" በላቸው"*።

ነገር ግን ከግሪክ ሰፕቱጀት 100 ዓመት በኃላ 875 ድኅረ-ልደት የተዘጋጀው ማሶሬቲክ እደ-ክታብ ላይ በተቃራኒው ማንስ ይሄድልናል? የሚል ኃይለ-ቃል አለ፦
ኢሳይያስ 6፥8 *የጌታንም ድምፅ፦ ማንን እልካለሁ? ይሄድልናል? ሲል ሰማሁ። እኔም፦ እነሆኝ፥ እኔን ላከኝ" አልሁ"*። וָאֶשְׁמַ֞ע אֶת־קֹ֤ול אֲדֹנָי֙ אֹמֵ֔ר אֶת־מִ֥י אֶשְׁלַ֖ח וּמִ֣י יֵֽלֶךְ־לָ֑נוּ וָאֹמַ֖ר הִנְנִ֥י שְׁלָחֵֽנִ

ትክክሉ የቱ ነው? ይሄድላቸዋል የሚለው የግሪክ ሰፕቱጀንት ወይስ ይሄድልናል የማሶሬቲክ እደ-ክታብ? ሁለቱን ለመዳኘት ከግሪክ ሰፕቱጀንት በፊት የነበረውን የነቢያት ፓሌዎ ዕብራይስጥ ጽሑሮች ጠፍተዋል፥ ግን ከደኃራይ ማሶሬቲክ ይልቅ ቀዳማይ ሰፕቱጀንት ሚዛን ይደፋል። ሙግቱን እናጥብብ እና "ይሄድልናል" ቢባልስ ሥላሴን ያሳያልን? በፍጹም። ምክንያቱን አንድ ማንነት ብዜት ተሳቢ ተውላጠ-ስም ተጠቀመ ማለት ያ ማንነት ሥላሴ ነበር ማለት አይደለም፥ "ኒ" נִי የነበረው ነጠላ ተሳቢ ተውላጠ-ስም በብዜት "ኑ" נוּ በሚል መጥቷል፦
ዕዝራ 4፥7 *"በአርጤክስስ ዘመን ቢሽላም፥ ሚትሪዳጡ፥ ጣብኤል ተባባሪዎቹም ለፋርስ ንጉሥ ለአርጤክስስ ጻፉ"*።
ዕዝራ 4፥18 ሰላም! *"አሁንም "ወደ እኛ" עֲלֶ֑ינָא የላካችሁት ደብዳቤ በፊቴ ተተርጕሞ ተነበበ"*።

ልብ አድርግ "አርጤክስስ" የሚለው ቃላ ላይ መነሻ ቅጥያ ያለው "ለ" የሚለው መስተዋድድ ለንጉሡ ብቻ የተላከ ደብዳቤ ነው። ንጉሡ ግን በዐረማይክ "ና" נָא ብሎ በብዜት ተጠቅሟል፥ ግን ንጉሡ አንድም ሦስትም ሆኖ አይደለም፦
ዳንኤል 2፥25 *የዚያን ጊዜም አርዮክ ዳንኤልን ፈጥኖ ወደ ንጉሡ አስገባውና፦ "ከይሁዳ ምርኮኞች ያለውን ለንጉሡ ፍቺውን የሚያስታውቀውን ሰው አግኝቼአለሁ" አለው*።
ዳንኤል 2፥36 ሕልሙ ይህ ነው፥ *"አሁንም ፍቺውን በንጉሡ ፊት እንናገራለን" נֵאמַ֥ר *።

"አማር" אֲמַר በሚል ግስ ላይ "ኔ" נֵ የሚል "ባለቤት ተውላጠ-ስም አለ። አርዮክ ወደ ንጉሡ ያስገባው ዳንኤልን ብቻ ሆኖ ሳለ ዳንኤን በብዜት "እንናገራለን" ብሏል፥ ግን ዳንኤል አንድም ሦስትም ሆኖ አይደለም። ሙግቱን አሁንም እናጥብበውና "ይሄድልናል" የሚለው ከአንድ በላይ ላሉ ማንነቶች ነው ነው ብንል እንኳን አሁንም ሥላሴን በፍጹም አያሳይም። ዐውዱ ላይ መላእክት አሉ፥ ኢሳይያስ ሲናገር ከሱራፌልም አንዱ እየበረረ ወደ እርሱ መጥቶ፦ "እነሆ፥ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህም ከአንተ ተወገደ፥ ኃጢአትህም ተሰረየልህ" አለው፦
ኢሳይያስ 6፥2 *"ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር"*።
ኢሳይያስ 6፥5-7 *"እኔም፦ ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸውም በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ! አልሁ*። ከሱራፌልም አንዱ እየበረረ ወደ እኔ መጣ፥ በእጁም ከመሠዊያው በጕጠት የወሰደው ፍም ነበረ። አፌንም ዳሰሰበትና፦ እነሆ፥ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህም ከአንተ ተወገደ፥ ኃጢአትህም ተሰረየልህ፡ አለኝ*።

እንደ ባይብሉ እግዚአብሔር የሰማይም ሠራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው አሉ፥ ያዕቆብ ከእግዚአብሔር እና ከመልአኩ ጋር ስለተነጋገረ " ከእኛ ጋር ተነጋገረ" ብሏል፦
1ኛ ነገሥት 22፥19 *"እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀምጦ፥ የሰማይም ሠራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ*።
ሆሴዕ 12፥4 ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ፤ አልቅሶም ለመነው። በቤቴልም አገኘው፥ *"በዚያም "ከ-እኛ" ጋር עִמָּֽנוּ ተነጋገረ"*።

አየክ "ኑ" נוּ የሚለው ተሳቢ ተውላጠ-ስም ከመላእክት ጋር እንዳገለገለ? በምንም ሒሳብ ሥላሴን አያመለከትም። በተረፈ አንዱ አምላክ አንድ ማንነት ኖሮት ለግነት እኛነት ሲጠቀም በውስጡ ሦስት አባላት አሉት ብሎ ሌሎችን ማንነቶችን በማንነቱ ላይ ማጋራት ሺርክ ነው። እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው፥ እኔም ከምታጋሩት ነገር ንጹሕ ነኝ፦
6፥19 *«እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው፥ እኔም ከምታጋሩት ነገር ንጹሕ ነኝ»* በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ وَإِنَّنِى بَرِىٓءٌۭ مِّمَّا تُشْرِكُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ከእኛ እንደ አንዱ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

14፥52 *ይህ ቁርኣን ለሰዎች ገላጭ ነው፡፡ ሊመከሩበት፣ በእርሱም ሊያስጠነቅቁበት፣ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት እና የአእምሮ ባለቤቶችም ሊገሰፁበት የተወረደ ነው*፡፡ هَـٰذَا بَلَاغٌ لِّلنَّاسِ وَلِيُنذَرُوا بِهِ وَلِيَعْلَمُوا أَنَّمَا هُوَ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ وَلِيَذَّكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ

ቁርኣን ከወረደበት አንዱ ፈጣሪ አላህ አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት ነው፦
14፥52 *ይህ ቁርኣን ለሰዎች ገላጭ ነው፡፡ ሊመከሩበት፣ በእርሱም ሊያስጠነቅቁበት፣ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት እና የአእምሮ ባለቤቶችም ሊገሰፁበት የተወረደ ነው*፡፡ هَـٰذَا بَلَاغٌ لِّلنَّاسِ وَلِيُنذَرُوا بِهِ وَلِيَعْلَمُوا أَنَّمَا هُوَ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ وَلِيَذَّكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ

ይህ የአንድ አምላክ እሳቤ በመለኮታዊ ቅሪት እንዲህ ተቀምጧል፦
ዘዳግም 6፥4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ *አምላካችን ያህዌህ አንድ ያህዌህ ነው*። שְׁמַע, יִשְׂרָאֵל: יְהוָה אֱלֹהֵינוּ, יְהוָה אֶחָד.

ያህዌህ አንድ ያህዌህ ሲሆን እርሱ ሌሎችን ማንነቶችን ጨምሮ፦ “ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ” ብሏል፦
ዘፍጥረት 3፥22 *ያህዌህ አምላክም አለ፦ *እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ*፤ וַיֹּאמֶר יְהוָה אֱלֹהִים, הֵן הָאָדָם הָיָה כְּאַחַד מִמֶּנּוּ, לָדַעַת, טוֹב וָרָע; וְעַתָּה פֶּן-

“እንደ አንዱ” እና “እኛ” ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን ነጥብ በነጥብ ጥርስና ምላሱን እየነቀስን እናየዋለን፦

ነጥብ አንድ
“እንደ አንዱ”
“ከ-አሐድ” כְּאַחַ֣ד ማለት “እንደ አንዱ”as one of” ማለት ነው፤ ያ ማለት በከፊል መመሳሰልን ያሳያል፦
1ኛ ሳሙኤል 17፥36 *እኔ ባሪያህ “አንበሳ እና ድብ” መታሁ፤ ይህም ያልተገረዘው ፍልስጥኤማዊ የሕያውን አምላክ ጭፍሮች ተገዳድሮአልና “ከእነርሱ እንደ አንዱ” ይሆናል*። גַּם אֶת-הָאֲרִי גַּם-הַדֹּב, הִכָּה עַבְדֶּךָ; וְהָיָה הַפְּלִשְׁתִּי הֶעָרֵל הַזֶּה, כְּאַחַד מֵהֶם, כִּי חֵרֵף, מַעַרְכֹת אֱלֹהִים חַיִּים.

“ከ-አሐድ ሜሄም” כְּאַחַד מֵהֶם ማለት “ከእነርሱ እንደ አንዱ”as one of them” ማለት ሲሆን ፍልስጥኤማዊ ጎልያድ በዳዊት በመገደል ደረጃ “እንደ አንበሳ እና ድብ” ይሆናል ማለት ነው እንጂ ጎልያድ አውሬ ይሆናል ማለት አይደለም፣ “እንደ” የሚለው ተውሳከ-ግስ የተወሰነን መመሳሰል ለማመልከት የሚገባ ነው፣ ልክ እንደዚሁ አደም መልካምና ክፉ በማወቅ እንደ እንደ እነርሱ ሆኗል፤ ለዛ ነው “ከ-አሐድ ሜንሁ” כְּאַחַ֣ד מִמֶּ֔נּוּ ማለትም “ከእኛ እንደ አንዱ”as one of us” የሚለው፤ ያህዌህ ታዲያ ማንን ጨምሮ ነው “እኛ” የሚለው?

ነጥብ ሁለት
“እኛ”
ያህዌህ “እኛ” የሚለው ማንን ጨምሮ ነው የሚለው ለመረዳት እዚሁ ዐውድ ላይ አዳም ከእኛዎቹ እንደ አንዱ የሚሆነው “መልካምንና ክፉን ለማወቅ” እንደሆነ ይሰመርበት፤ እዛው ዐውድ ላይ አዳም ቢበላ “እንደ አማልክትም መልካምንና ክፉን የሚያውቁ” እንደሆነ ተነግሯል፦
ዘፍጥረት 3፥5 ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ *“እንደ አማልክትም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ”* ያህዌህ ስለሚያውቅ ነው እንጂ። כִּי, יֹדֵעַ אֱלֹהִים, כִּי בְּיוֹם אֲכָלְכֶם מִמֶּנּוּ, וְנִפְקְחוּ עֵינֵיכֶם; וִהְיִיתֶם, כֵּאלֹהִים, יֹדְעֵי, טוֹב וָרָע.

የግዕዙ ዕትም፦
ዘፍጥረት 3፥5 *“ዘይቤ ከመ ኢትኩኑ አማልክተ ወኢታምሩ ሠናየ ወእኩየ”*

የኢንግሊሹ ዕትም፦
For God doth know that in the day ye eat thereof, then your eyes shall be opened, and *ye shall be as gods, knowing good and evil*.(KJV)

የግሪክ ሰፕቱአጀንት”LXX”፦
ዘፍጥረት 3፥5 ᾔδει γὰρ ὁ Θεός, ὅτι ᾗ ἂν ἡμέρᾳ φάγητε ἀπ᾿ αὐτοῦ, διανοιχθήσονται ὑμῶν οἱ ὀφθαλμοὶ καὶ ἔσεσθε ὡς *θεοί*, γινώσκοντες καλὸν καὶ πονηρόν.

የግዕዙ ዕትም ላይ “አማልክት” ብሎ እንዳስቀመጠው አስተውል፤ “ኤሎሂም” כֵּֽאלֹהִ֔ים ማለት “አማልክት” ማለት ነው፤ ይህ ቃል ለነጠላ ማንነት ወይንም ለብዙ ማንነት ይውላል፤ እዚህ አንቀጽ ላይ ግን ለብዙ መባሉን በግሪክ ሰፕቱጀንት ላይ “ቶኢ” θεοί ማለትም “አማልክት” ብሎ በብዙ ቁጥር አስቀምጦታል፤ ልብ አድርግ የቴኦ ነጠላ “ቴኦስ” Θεὸς ነው፤ “ቴኦስ” ብሎ በነጠላ አለማስቀመጡ ለብዙ ማንነቶች መሆኑን ያሳያል፤ በኢንግሊሹም ደግሞ በብዙ ቁጥር “gods” መባሉን አስተውል። በብሉይ ደግሞ ብዙ ቦታ አማልክት የተባሉት መላእክት ናቸው፦
መዝሙር 97፥7 *”አማልክትም” כֵּֽאלֹהִ֔ים ሁሉ ስገዱለት*።
መዝሙር 104፥4 *“አማልክትን” כֵּֽאלֹהִ֔ים መንፈስ የሚያደርግ፥*
መዝሙር 8፥5 *“ከአማልክትን” כֵּֽאלֹהִ֔ים እጅግ ጥቂት አሳነስኸው*፤
መዝሙር 103፥20 የቃሉንም ድምፅ የምትሰሙ *“አማልክቱ” כֵּֽאלֹהִ֔ים ሁሉ ያህዌህን ባርኩ*።
መዝሙር 138፥1 *”በአማልክት כֵּֽאלֹהִ֔ים ፊት እዘምርልሃለሁ*።

ስለዚህ አዳም ዛፉን ሲበላ መልካም እና ክፉውን በማወቅ እንደ መላእክት ከሆነ ያህዌህ ደግሞ መልካምና ክፉ ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ የሚለው እነዚህን አማልክት ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው፦
ሆሴዕ 12፥4 *በጕልማስነቱም ጊዜ “ከአምላክ” ጋር ታገለ፤ “ከመልአኩም” ጋር ታግሎ አሸነፈ፤ አልቅሶም ለመነው። በቤቴልም አገኘው፥ በዚያም “ከእኛ” ጋር ተነጋገረ*።

ያዕቆብ የተነጋገረው ከመልአኩ ጋር እና ከያህዌህ ጋር ነው፤ ያህዌህ መልአኩን ጨምሮ “ከእኛ” እንዳለ አንባቢ ልብ ይለዋል። አይ ያህዌህ እኛ የሚለው ሥላሴን ያሳየል ከተባለ ዕውዱ ላይ ስለ ሥላሴ የሚያሳይ ሃይለ-ቃል ፈልቅቆ ማሳየት ይጠበቅባችኃል፤ ወይም ይህ አንቀጽ ስለ ሥላሴ ያወራል ብሎ የተናገረ ነብይ ወይም ሐዋርያ ጠቅሳችሁና አጣቅሳችሁ መሞገትና መሟገት ይጠበቅባችኃል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ይህ ያውቁ ኖሯል?
በዓለም ላይ 23 ሺ የክርስትና ዓይነት አለ። ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ፦
1.ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
2. ኦርቶዶክስ ቅባት
3. ኦርቶዶክስ ጸጋ
4. ኦርቶዶክስ ተሃድሶ
5. ካቶሊክ
6. ፕሮቴስታንት
7. የይሆዋ ምስክር
8. ኦንልይ ጂሰስ
9. አድቬንቲስት
10. ዴቪድያን
11. የእግዚአብሔር መንግሥት(የካሳ ኬርጋ)
12. ሞርሞን
13. ኒው ኤጅ ሙቭመንት
14. ቢብሊካል ዩኒታሪያን
15. ናዝራዊያን አሉ።

ለዛሬ ይህ በቂ ነው። ለበለጠ ትምህርት በዚህ ተከታተሉ፦ https://tttttt.me/Wahidcom
እንፍጠር ወይስ ልፍጠር?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

38፥71 ጌታህ ለመላእክት *«እኔ ሰውን ከጭቃ እፈጥራለሁ»* ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن طِينٍ

አምላካችን አላህ ለመላእክት የተናገረው፦ “እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ፤ ሰውን ከጭቃ እፈጥራለሁ” የሚል ነው እንጂ “እንፍጠር” አላላቸውም፦
2፥30 ጌታህ ለመላእክት፡- *«እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ»* ባለ ጊዜ አስታውስ፤ وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي جَاعِلٌ فِي الْأَرْضِ خَلِيفَةً
38፥71 ጌታህ ለመላእክት *«እኔ ሰውን ከጭቃ እፈጥራለሁ»* ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن طِينٍ

“እንፍጠር” የሚባለው መፍጠር ለሚችል ማንነትና ምንነት ብቻ ነው፤ በባይብልም ከሄድን ያህዌህ ለመላእክት ያለው፦ “ሰው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለምና የሚስማማውን ረዳት አበጅለታለው” የሚል ነው፦

1ኛ. ዕብራይስጡ፦
ዘፍጥረት 2፥18 וַיֹּאמֶר יְהוָה אֱלֹהִים, לֹא-טוֹב הֱיוֹת הָאָדָם לְבַדּוֹ; אֶעֱשֶׂה-לּוֹ עֵזֶר, כְּנֶגְדּוֹ.

2ኛ. ኢንግሊሹ፦
Genesis 2፥18 The LORD God said, “It is not good for the man to be alone. I will make a helper suitable for him.” NIV

3ኛ. አዲሱ መደበኛ ትርጉም፦
ዘፍጥረት 2፥18 ያህዌህ ኤሎሂም፦ “ሰው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለምና የሚስማማውን ረዳት *አበጅለታለው”* አለ።

4ኛ. 1879 አማርኛ እትም፦
ዘፍጥረት 2፥18 እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ “ሰው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለም፤ የምትረዳውን፣ በአገቡ የምትሆን፣ የምትስማማውን *ልፍጠርለት*።

የዕብራይስጡ ላይ “ኤሴህ” אֶֽעֱשֶׂהּ ማለትም “ልፍጠር” አለ እንጂ “እንፍጠር” አላለም፤ እንግሊዘኞቹም፦ “I will make” ብለው አስቀምጠውታል። ታዲያ “እንፍጠር” ከየት መጣ? አዎ ግሪክ ሰፕቱአጀን”LXX” እና ግዕዙ ላይ “እንፍጠር” የሚል አለ፦

1ኛ. ግሪክ ሰፕቱአጀን፦
Καὶ εἶπε Κύριος ὁ Θεός· οὐ καλὸν εἶναι τὸν ἄνθρωπον μόνον· ποιήσωμεν αὐτῷ βοηθὸν κατ᾿ αὐτόν.

2ኛ. ግዕዙ፦
ወይቤ እግዚአብሔር ኢኮነ ሠናይ ለእጓለ እመሕያው ይንበር ባሕቲቱ *ንግበር* ሎቱ ቢጸ ዘይረድኦ።

3ኛ. አማርኛ 1954 እትም፦
ዘፍጥረት 2፥18 እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት *እንፍጠርለት*።

የግሪክ ሰፕቱአጀን ላይ “ፓኢሴሜን” ποιήσωμεν ማለት “እንፍጠር” ብሎ አስቀምጦታል፤ ግዕዙም፦ “ንግበር” ማለትም “እንፍጠር” ብሎ አስቀምጠውታል። ታዲያ “እንፍጠር” ያለውም ለማን ነው? ስንል ኩፋሌ ላይ ደግሞ ለፍጡራን እንዳለ ይናገራል፦

1ኛ. ግዕዙ፦
ኩፋሌ 4፥4 *ወይቤለነ እግዚአብሔር ለነ*፤ አኮ ሰናይ የሀሉ ብእሲ ባሕቲቱ፤ አላ *ንግበር* ሎቱ መርድአ ዘከማሁ፤ መወየደ *እግዚአብሔር አምላክነ* ሕድመተ ላዕሌሁ ወኖመ”

2ኛ. አማርኛው፦
ኩፋሌ 4፥4 *ፈጣሪያችን* እግዚአብሔር ለእኛ *እንዲህ አለን*፦ “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት *”እንፍጠርለት”*።

“ፈጣሪያችን” የሚል ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ እግዚአብሔር እንፍጠር ያለው ለፈጠራቸው መሆኑን ለማሳየት እዛው አንቀጽ ላይ፦ “እንዲህ አለን” ይላሉ፤ ያላቸውም፦ “እንፍጠርለት” ነው፤ እነዚህ ማንነቶች እነማን ናቸው? ብለን ስንሞግት “መላእክት ናቸው” ይሉናል፤ አንቀጹ ላይ መላእክት ስለመሆናቸው ምንም ሽታው እንኳን የለም። ነገር ግን ኩፋሌ 1፥25 ኩፋሌ 2፥1 ኩፋሌ 2፥4 ኩፋሌ 4፥1 ለሙሴ የፊቱ መልአክ እየተናገረ ነው በሚል መላእክት ናቸው እንበልና ሙግቱን እናጥበው፤ መላእክት ይፈጥራሉ እንዴ? እኔ “እንብላ” ብዬ ብል የሚበላ ማንነትን እያናገርኩኝ ነው፤ የማይበላ ከሆነ “ልብላ” ብዬ ነው የምለው እንጂ “እንብላ” አልለውም፤ የማይፈጥር ማንነት እንፍጠር ወይስ ልፍጠር? የቱ ነው ስሜት የሚሰጠው?