ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.4K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
የሴት ውርስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥176 *ወንድም እና እህት ወንዶችና ሴቶች ቢኾኑም ለወንዱ የሁለት ሴቶች ድርሻ ብጤ አለው*፡፡ አላህ እንዳትሳሳቱ ለእናንተ ያብራራል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ فَإِن كَانَتَا اثْنَتَيْنِ فَلَهُمَا الثُّلُثَانِ مِمَّا تَرَكَ ۚ وَإِن كَانُوا إِخْوَةً رِّجَالًا وَنِسَاءً فَلِلذَّكَرِ مِثْلُ حَظِّ الْأُنثَيَيْنِ ۗ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمْ أَن تَضِلُّوا ۗ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

“ሸሪዓህ” شَرِيعَة የሚለው ቃል "ሸረዐ" شَرَعَ ማለትም "ደነገገ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ድንጋጌ" "ሕግ" "መርሕ" ማለት ነው፥ "ተሽሪዕ" تَشْرِيع ማለት በራሱ "ሕጋዊነት" ማለት ነው። የሸሪዓ ተክለ-ንጥር"element" አራት ናቸው፥ እነርሱም፦ “ቁርኣን” قُرْءَان የአምላካችን የአላህ”ﷻ” ንግግር፣ “ሡናህ” سُنَّة‎ የነቢያችን”ﷺ” ሐዲስ፣ “ቂያሥ” قِيَاس ዐሊሞች የሚያመዛዝኑበት “ማመጣጠን”Analogy” እና “ኢጅማዕ” إِجْمَاع‎ የምሁራን ስምምነት “ሲኖዶስ”acadamic agreement” ነው።
“ቂያሥ” قِيَاس የሚለው ቃል "ቃሠ" قَاسَ ማለትም "አመጣጠነ" "አመዛዘነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ማመጣጠን" "ማመዛዘን" ማለት ነው። በሸሪዓህ ቂያሥ ከሚደረጉት እሳቦት አንዱ "ሚራስ" ነው፥ "ሚራስ" مِيرَاثٌ የሚለው ቃል "ወሪሰ" وَرِثَ ማለትም "ወረሰ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ውርስ" ማለት ነው። ይህም ውርስ የሟች መብት፣ ግዴታ እና ሀብት በሕይወት ላሉት ወራሾቹ የሚተላለፍበት መንገድ ነው። አንድ ወንድ ልጅ ከወላጆቹ የሚያገኘው ውርስ የሴትን ልጅ እጥፍ ሲሆን አንዲት ሴት ልጅ ከወላጆቿ የምታገኘው ውርስ የወንድ አንድ ሁለተኛ ½ ነው፦
4፥176 *ወንድም እና እህት ወንዶችና ሴቶች ቢኾኑም ለወንዱ የሁለት ሴቶች ድርሻ ብጤ አለው*፡፡ አላህ እንዳትሳሳቱ ለእናንተ ያብራራል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ فَإِن كَانَتَا اثْنَتَيْنِ فَلَهُمَا الثُّلُثَانِ مِمَّا تَرَكَ ۚ وَإِن كَانُوا إِخْوَةً رِّجَالًا وَنِسَاءً فَلِلذَّكَرِ مِثْلُ حَظِّ الْأُنثَيَيْنِ ۗ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمْ أَن تَضِلُّوا ۗ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ
4፥11 *አላህ በልጆቻችሁ ውርስ በሚከተለው ያዛችኋል፡፡ ለወንዱ የሁለት ሴቶች ድርሻ ብጤ አለው፡፡ ሁለት ወይም ከሁለት በላይም የኾኑ ሴቶች ብቻ ቢኾኑ ለእነርሱ ሟቹ ከተወው ድርሻ ከሦስት ሁለት እጁ አላቸው፡፡ አንዲትም ብትኾን ለእርሷ ግማሹ አላት*፡፡ يُوصِيكُمُ اللَّهُ فِي أَوْلَادِكُمْ ۖ لِلذَّكَرِ مِثْلُ حَظِّ الْأُنثَيَيْنِ ۚ فَإِن كُنَّ نِسَاءً فَوْقَ اثْنَتَيْنِ فَلَهُنَّ ثُلُثَا مَا تَرَكَ ۖ وَإِن كَانَتْ وَاحِدَةً فَلَهَا النِّصْفُ

"ግማሽ" ማለት አንድ ሁለተኛ ½ ማለት ነው። በሸሪዓችን አንዲት ሴት ከምታገኘው ገንዘብ ለቤተሰቧ ማለትም ለባሏ እና ለልጆቿ የመስጠት ግዴታ የላባትም፥ በተቃራኒው አንድ ወንድ ሀብትና ንብረት ለቤተሰቡ ማለትም ለሚስቱ እና ለልጆቹ የሚያስፈልገውን ወጪ በሙሉ የማሟላት ግዴታ አለበት፦
4፥34 *ወንዶች በሴቶች ላይ አሳዳሪዎች ናቸው፡፡ አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡ እና ወንዶች ከገንዘቦቻቸው ለሴቶች በመስጠታቸው ነው*፡፡ الرِّجَالُ قَوَّامُونَ عَلَى النِّسَاءِ بِمَا فَضَّلَ اللَّهُ بَعْضَهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ وَبِمَا أَنفَقُوا مِنْ أَمْوَالِهِمْ
2፥233 *እናቶችም ልጆቻቸውን ሙሉ የኾኑን ሁለት ዓመታት ያጥቡ፡፡ ይህም ማጥባትን መሙላት ለሻ ሰው ነው፡፡ ለእርሱም በተወለደለት አባት ላይ ምግባቸው እና ልብሳቸው በችሎታው ልክ አለበት*፡፡ ነፍስ ችሎታዋን እንጂ አትገደድም፡፡ وَالْوَالِدَاتُ يُرْضِعْنَ أَوْلَادَهُنَّ حَوْلَيْنِ كَامِلَيْنِ ۖ لِمَنْ أَرَادَ أَن يُتِمَّ الرَّضَاعَةَ ۚ وَعَلَى الْمَوْلُودِ لَهُ رِزْقُهُنَّ وَكِسْوَتُهُنَّ بِالْمَعْرُوفِ ۚ لَا تُكَلَّفُ نَفْسٌ إِلَّا وُسْعَهَا
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 12, ሐዲስ 99
ሙዓዊያህ አል-ቁሸይሪይ እንደተረከው፦ "ወደ አላህ መልእክተኛ”ﷺ” መጣሁና ስለሚስቶቻችም ምን ይሉናል? ብዬ ጠየኳቸው። እርሳቸውም፦ *"የምትበሉትን አብሏቸው! የምትለብሱትን አልብሷቸው!" አሉ”* مُعَاوِيَةَ الْقُشَيْرِيِّ قَالَ أَتَيْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ فَقُلْتُ مَا تَقُولُ فِي نِسَائِنَا قَالَ ‏ “‏ أَطْعِمُوهُنَّ مِمَّا تَأْكُلُونَ وَاكْسُوهُنَّ مِمَّا تَكْتَسُونَ
ቡሉጉል መራም መጽሐፍ 8, ሐዲስ 206
ጃቢር ኢብኑ ዐብደሏህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" በረጅሙ በሐዲሱል ሐጅ ስለ ሴት አንስተው እንዲህ አሉ፦ *"እነርሱ(ሴቶች) በእናንተ ላይ መብት አላቸው፥ እናንተም ምግባቸውን እና አልባሳታቸው በደግነት አድርጉላቸው"*። وَعَنْ جَابِر بْنِ عَبْدِ اَللَّهِ ‏- رضى الله عنه ‏- عَنْ اَلنَّبِيِّ ‏- صلى الله عليه وسلم ‏-‏-فِي حَدِيثِ اَلْحَجِّ بِطُولِهِ‏- قَالَ فِي ذِكْرِ اَلنِّسَاءِ: { وَلَهُنَّ عَلَيْكُمْ رِزْقُهُنَّ وَكِسْوَتُهُنَّ بِالْمَعْرُوفِ.‏ }
ለምሳሌ የወላጆች ውርስ 150 ሺህ ቢኖር 50 ሺህ ለሴቷ፥ 100 ሺህ ለወንዱ ነው። ወንዱ ከውርሱ 80 ሺህ ለቤተሰቡ ቢያውል 20 ይቀረዋል፥ ሴቷ ምንም ወጪ ስለማታወጣ 50 ሺህ ተቀማጭ ስላላት በ 30 ሺ ትበልጠዋለች። ነገር ግን የሴት ውርስ የሚሆነው ሁልጊዜ አንድ አይነት አይደለም፥ ለምሳሌ ወላጆች ሟች ልጅ ካላቸው እና ሟቹ ልጃቸው ልጆች ካሉት እናትና አባቱ እኩል እኩል አንድ ስድስተኛ ይወርሳሉ፦
4፥11 *”ለአባት እና ለእናቱም ለእርሱ ልጅ እንዳለው ከሁለቱ ለእያንዳንዱ ከስድስት አንድ አላቸው”*፡፡ وَلِأَبَوَيْهِ لِكُلِّ وَاحِدٍ مِّنْهُمَا السُّدُسُ مِمَّا تَرَكَ إِن كَانَ لَهُ وَلَدٌ ۚ

ሟቹ ልጅ ከሌለው አባት አንድ ስድስተኛ ሲያገኝ፥ እናት ከአባት በላይ ሲሶ ማለትም አንድ ሦስተኛ ትወርሳለች፦
4፥11 *”ለእርሱም ልጅ ባይኖረውና ወላጆቹ ቢወርሱት ለእናቱ ሲሶው አላት”*፡፡ فَإِن لَّمْ يَكُن لَّهُ وَلَدٌ وَوَرِثَهُ أَبَوَاهُ فَلِأُمِّهِ الثُّلُثُ

እዚህ ጋር ሚስት ከባል የበለጠ ውርስ አላት። ባል እና ሚስት ልጆች ከወለዱ ሚስት ባሏ ሲሞት አንድ ስምንተኛ የምትወርስ ሲሆን፥ ባል ደግሞ ሚስቱ ስትሞት አንድ አራተኛ ይወርሳል። ባል እና ሚስት ልጆች ካልወለዱ ሚስት ባሏ ሲሞት አንድ አራተኛ የምትወርስ ሲሆን፥ ባል ደግሞ ሚስቱ ስትሞት ግማሽ አንድ ሁለተኛ ይወርሳል፦
4፥12 *”ለእናንተም ሚስቶቻችሁ ከተዉት ንብረት ለእነርሱ ልጅ ባይኖራቸው ግማሹ አላችሁ፡፡ ለእነርሱም ልጅ ቢኖራቸው ከተዉት ሀብት ከአራት አንድ አላችሁ፡፡ ይህም በእርሷ ከሚናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከዕዳ በኋላ ነው፡፡ ለእናንተም ልጅ ባይኖራችሁ ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ ለሚስቶች ከአራት አንድ አላቸው፡፡ ለእናንተም ልጅ ቢኖራችሁ ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ ከስምንት አንድ አላቸው። ይህም በርሷ ከምትናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከዕዳ በኋላ ነው”*፡፡ وَلَكُمْ نِصْفُ مَا تَرَكَ أَزْوَاجُكُمْ إِن لَّمْ يَكُن لَّهُنَّ وَلَدٌ ۚ فَإِن كَانَ لَهُنَّ وَلَدٌ فَلَكُمُ الرُّبُعُ مِمَّا تَرَكْنَ ۚ مِن بَعْدِ وَصِيَّةٍ يُوصِينَ بِهَا أَوْ دَيْنٍ ۚ وَلَهُنَّ الرُّبُعُ مِمَّا تَرَكْتُمْ إِن لَّمْ يَكُن لَّكُمْ وَلَدٌ ۚ فَإِن كَانَ لَكُمْ وَلَدٌ فَلَهُنَّ الثُّمُنُ مِمَّا تَرَكْتُم ۚ مِّن بَعْدِ وَصِيَّةٍ تُوصُونَ بِهَا أَوْ دَيْنٍ

ሟች ወላጅም ልጅም የሌለው ከሆነ ወንድሙ ወይም እኅቱ ቢኖሩ ከሁለቱ ለያንዳንዳቸው ከስድስት አንድ አላቸው፦
4፥12 ወላጅም ልጅም የሌለው በጎን ወራሾች የሚወርስ ወንድ ወይም ሴት ቢገኝ ለእርሱም ለሟቹ ወንድም ወይም እኅት ቢኖር ከሁለቱ ለያንዳንዳቸው ከስድስት አንድ አላቸው፡፡ وَإِن كَانَ رَجُلٌ يُورَثُ كَلَالَةً أَوِ امْرَأَةٌ وَلَهُ أَخٌ أَوْ أُخْتٌ فَلِكُلِّ وَاحِدٍ مِّنْهُمَا السُّدُسُ

እዚህ ጋርም የሟች ወንድም እና እህት እኩል እኩል ናቸው። እንግዲህ የውርስ ሕግ ቂያሥ ሲደረግ ሴት ከወላጆቿ የወንድን ግማሽ ½ ብታገኝም፥ ልጅ ካለው ልጇ አንድ ስድስተኛ ⅙ ፣ ልጅ ከሌለው ልጇ አንድ ሦስተኛ ⅓ ፣ ባል ቢሞትባት ልጅ ካላቸው አንድ ስምንተኛ ⅛ ፣ ባል ቢሞትባት ልጅ ከሌላቸው አንድ አራተኛ ¼ ፣ ከሟች ወንድሟ ወይም እህቷ የምታገኘው ከወንድሟ ጋር እኩል = በመሆን ውርስ ታገኛለች። ይህንን የምታገኘውን ውርስ ዘንግቶ ተጨቆናለች ማለት ፍትሓዊነት አይደለም። ሚሽነሪዎች፦ “በቁርኣን ሴት በውርስ የተጨቆነች ናት” የሚሉት በየትኛው ቀመርና ሴት ቀምረውትና አስልተዉት ነው? በየትኛው መስፈትና ሚዛን ለክተውትና መዝነውት ነው? ይልቁኑስ በባይብል ሴት ልጅ የምትወርሰው ወላጅ ወንድ ልጅ ከሌለው ነው፦
ዘኍልቍ 27፥8 ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ *ሰው ቢሞት ወንድ ልጅም ባይኖረው፥ ርስቱ ለሴት ልጁ ይለፍ!*

ለምሳሌ ሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፥ ስለዚህ የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች ውርስ አልፎላቸዋል፦
ዘኍልቍ 26፥33 *የኦፌርም ልጅ ሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም*።
ዘኍልቍ 27፥7 *የሰለጰዓድ ልጆች እውነት ተናግረዋል፤ በአባታቸው ወንድሞች መካከል የርስት ድርሻ ስጣቸው፤ የአባታቸውን ርስት ለእነርሱ አሳልፈህ ስጥ*።

አንድ ሰው ወንድም ሴትም ልጅ ከሌለውስ? ለወንድሞቹ ያወርሳል፥ ለእህት ማውረስ የሚባል ሕግ የለም፦
ዘኍልቍ 27፥9 *ሴት ልጅም ባትኖረው ርስቱን ለወንድሞቹ ስጡ!*

ወንድሞች ከሌሉትስ? ለእህቶቹ ያወርሳል? እረ በፍጹም ለአጎቶቹ ያወርሳል፥ ለአክስት ማውረስ የሚባል ሕግ የለም፦
ዘኍልቍ 27፥10 *ወንድሞችም ባይኖሩት ርስቱን ለአባቱ ወንድሞች ስጡ!*

ባይብል ሟች ለእናት፣ ለሚስት፣ ለእህት፣ ለአክስት የሚያወርሰውን ድርሻና መብት ምንም ያስቀመጠው ነገር የለም። የሴት ውርስ ጭቆና ባይብል ላይ እያለ ቁርኣን ላይ መፈለግ የተቆላበት እያለ የተጋፈበትን መፈለግ ነው። “የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ” ወይም “ቅቤ አንጣሪዋ እያለች ጎመን ቀቃይዋን ምች መታት” ይላል ያገሬ ሰው። አላህ ሂዳያ ይስጣችሁ! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቂሰቱል ገራኒቅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

69፥44-46 በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት ያላልነውን "በቀጠፈ" ኖሮ وَلَوْ تَقَوَّلَ عَلَيْنَا بَعْضَ ٱلْأَقَاوِيلِ ፤ በኀይል በያዝነው ነበር لَأَخَذْنَا مِنْهُ بِٱلْيَمِينِ ፡፡ ከዚያም ከእርሱ የልቡን ሥር በቆረጥን ነበር ثُمَّ لَقَطَعْنَا مِنْهُ ٱلْوَتِينَ ፡፡

ዊሊያም ሙኢር በ 1819 AD ተወልዶ በ 1905 AD ያለፈ "ሙስተሽሪቅ" مستشرق ማለትም "የመካከለኛው ምስራቅ ጥንተ-ነገር አጥኚ"Orientalist" ሲሆን እርሱ ለመጀመሪያ ጊዜ በ 1858 AD በመጽሐፉ ሽፋን ላይ "ሰይጣናዊ አንቀፅ"Satanic Verse" ብሎ ጻፈ፤ በመቀጠል የእርሱን ፈለግ የተከተለው ሳልማን ሩሽዲ 1988 AD በመጽሐፉ ሽፋን ላይ "ሰይጣናዊ አንቀፅ" ብሎ ጻፈ፤ ይህ መጽሐፍ በምዕራባዊያና በሚሽነሪዎች እገዛ በዓለማችን ላይ ትልቅ የህትመት ሽፋን ተሰቶት ተሰራጭቶ ነበር። ይህ ስያሜ ከትችት የመነጨ ሲሆን ይህ ስያሜ በኢስላም ጽሑፎች ውስጥ የለም። በኢስላማዊ ጥናት ውስጥ ግን "ቂሰቱል ገራኒቅ" قصة الغرانيق ይባላል፤ "ገራኒቅ" غرانيق ማለት "የውሃ ወፍ"crane" ማለት ነው።
"ቂሰቱል ገራኒቅ" ማለት ይህ ነው፦
"ቲልከል ገራኒቁል ዑልያ፤ ወኢንነ ሸፋዐተሁንነ ለቱርጃ" تِلْكَ الْغَرَانِيقُ الْعُلْيَ وَ إِنَّ شَفاَعَتَهُنَّ لَتُرْجَى.
‹እነዚህ የተከበሩ ናቸው ምልጃቸው ተቀባይነት ያገኘው ናቸው›These are the high-flying ones, verily their intercession is to be hoped for!

ይህንን ከማየታችን በፊት ሙሉ ታሪካዊ ዳራውን እንመልከት፤ የረመዷን ወር ነብያችን”ﷺ” ወደ ተከበረው የሐረም መስጊድ ሄዱ፤ ቁረይሾች ተሰባስበው ባሉበት በድንገት ከመካከላቸው ቆሙና ሱረቱል ነጅም የተሰኘውን የቁርዓን ክፍል አነበቡ፤ ይህንን ሱራ አንብበው ሲጨርሱ "ለአላህም ስገዱ አምልኩትም" አንቀፅ ስለነበር ሁሉም ሙስሊሞች ሰገዱ፤ ከኃላ ሲሰሙ የነበሩት ቁረይሾች አብረው ሰገዱ፦
53፥62 ለአላህም ስገዱ አምልኩትም فَٱسْجُدُوا۟ لِلَّهِ وَٱعْبُدُوا۟ ۩ ፡፡
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 17 , ሐዲስ 5:
ኢብኑ ዐባስ"ረ.ዓ." እንደተረከው፦ ነቢዩ”ﷺ” ሱረቱል ነጅምን በቀሩ ጊዜ ሰገድኩ፣ ከእርሳቸው ጋር ሙስሊሞች፣ ሙሽሪኮች፣ ጂኒዎችና ሰዎችም ሰገዱ عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم سَجَدَ بِالنَّجْمِ وَسَجَدَ مَعَهُ الْمُسْلِمُونَ وَالْمُشْرِكُونَ وَالْجِنُّ وَالإِنْسُ‏.‏ ።

አረብ ሙሽሪኮች የሰገዱበት ምክንያት ""አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን?"" የሚለውን አንቀጽ ነብያችን”ﷺ” ስላነበቡ እንደሆነ ሰሒህ የሆነው ሐዲስ ላይ ከላይ ተቀምጧል።
ይህ የመጀመሪያው እይታ ሲሆን ነገር ግን ሁለተኛው እይታ ከዚህ በኃላ ያለው ታሪክ ኢብኑ ሃጅር አል አስቃላኒ እና ሼኽ አልባኒ ደኢፍ ነው ብለው አስቀምጠውታል፤ ራዚም፦ "በሙናፊቃን የተቀጠፈ መውዱዕ ነው" ብሏል(ተፍሲሩል ራዚ 11/134)። በተጨማሪም ኢብኑ ከሲር ሲናገር ይህ ታሪክ ደኢፍ ነው ብሎ ከደኢፍ ሁለተኛውን ክፍል ሙርሰል እንደሆነና በእርሱ አስተሳሰብ ሳሒህ እንዳልሆነ ተናግሯል። ይህንን ደኢፍ ታሪክ ኢብኑ ሂሻም፣ አል-ፈይሩዝ አባዲ፣ ተፍሲሩል ጀላለይን እና ኢብኑ ጀሪር አጥ-ጣባሪ ዘግበውታል፤ እንደውም ኢብኑ ጀሪር አጥ-ጣባሪ መግቢያው ላይ እንዲህ ይላል፦
"በዚህ መጽሐፍ ትረካ አንባቢ ተቃራኒ ወይም ተገቢ ሆኖ በሚያገኝበት ጊዜ ይህ የእኛ ባህርይ እንዳልሆነ ማወቅ አለበት፤ ነገር ግን ካለፉት ሰዎች ወደ እኛ የተላለፈ ትረካ ነው" (ታሪኩር ረሱል ወል ሙልክ ቅፅ 1, ገፅ 3)

ስለዚህ ከዚህ በታች ያለው የኢብኑ ጀሪር አጥ-ጣባሪ ትረካ ደኢፍ የሆሃንበት አጋጣሚ አለ ማለት ነው፤ አንዳንድ ሙፈሲሪን መሰረት ያደረጉበትን የኢብኑ ጀሪር አጥ-ጣባሪ ትረካ እስቲ እንየው፦
"አላህ፦ "በኮከብ እምላለሁ በገባ ጊዜ፡፡ ባልደረባችሁ አልተሳሳተም፤ አልጠመመምም፡፡ ከልብ ወለድም አይናገርም፡" የሚለውን አንቀጽ አወረደ፤ በመቀጠል፦
"አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን?"
ይህንን በአነበቡ ጊዜ ሸይጣን ""በንባቡ ላይ""፦
"ቲልከል ገራኒቁል ዑልያ፤ ወኢንነ ሸፋዐተሁንነ ለቱርጃ" تِلْكَ الْغَرَانِيقُ الْعُلْيَ وَ إِنَّ شَفاَعَتَهُنَّ لَتُرْجَى.
‹እነዚህ የተከበሩ ናቸው ምልጃቸው ተቀባይነት ያገኘው ናቸው› የሚለውን ቃል ጣለ።
አላህም፦ "ከመልክተኛና ከነቢይም ከአንተ በፊት አንድንም አላክንም ባነበበ ጊዜ ሰይጣን በንባቡ ላይ የሚጥል ቢሆን እንጅ፡፡ ወዲያውም አላህ ሰይጣን የሚጥለውን ያስወግዳል" የሚለውን አንቀፅ አወረደ።
(ታሪኩር ረሱል ወል ሙልክ ቅፅ 1, ገፅ 108)

"በንባቡ ላይ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ፊ ዑምኒይየቲሂ" فِي أُمْنِيَّتِهِ ሲሆን በነብያችን”ﷺ” ንባብ ማለትም "አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን?" ብለው ባሉ ጊዜ ጎን ለጎን ሸይጣን፦ ‹እነዚህ የተከበሩ ናቸው ምልጃቸው ተቀባይነት ያገኘው ናቸው› የሚለውን ቃል ጣለ። እንግዲህ ይህ ነው "ቂሰቱል ገራኒቅ" የሚባለው፤ ሙሽሪክ ከሃድያን ይህ ሱራ ሲነበብ «ይህንን ቁርኣን አታዳምጡ፡፡ ታሸንፉም ዘንድ ሲነበብ በእርሱ ውሰጥ ተንጫጩ» አሉ፦
41፥26 እነዚያም የካዱት «ይህንን ቁርኣን አታዳምጡ፡፡ ታሸንፉም ዘንድ "ሲነበብ" በእርሱ ውሰጥ ተንጫጩ» አሉ وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَا تَسْمَعُوا۟ لِهَٰذَا ٱلْقُرْءَانِ وَٱلْغَوْا۟ فِيهِ لَعَلَّكُمْ تَغْلِبُونَ ፡፡
በዚህ ሰአት ከእውነት "በራቀ ጭቅጭቅ ውስጥ" ሆነው "አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን?" የሚለው አንቀፅ ሲነበብ በሚንጫጩት ልብ ውስጥ ፈተና ሊያደርግ ሸይጣን ልብስብስን ቃልን ጣለ፤ ሁልጊዜ በእያንዳንዱ ነብይ ዘመን ነብዩ ባነበበ ጊዜ ሰይጣን ልቦቻቸውም ደረቆች በሆኑት ውስጥ ልብስብስን ቃልን ይጥላል፤ ይህን የሚያደርገው የቀጠፈውን እንዲቀጣጥፉ ነው፦
22፥53 ሰይጣን የሚጥለውን ነገር ለእነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ላለባቸው ልቦቻቸውም ደረቆች ለሆኑት ፈተና ሊያደርግ ይጥላል፡፡ በዳዮችም ከእውነት "በራቀ ጭቅጭቅ ውስጥ" ናቸው لِّيَجْعَلَ مَا يُلْقِى ٱلشَّيْطَٰنُ فِتْنَةًۭ لِّلَّذِينَ فِى قُلُوبِهِم مَّرَضٌۭ وَٱلْقَاسِيَةِ قُلُوبُهُمْ ۗ وَإِنَّ ٱلظَّٰلِمِينَ لَفِى شِقَاقٍۭ بَعِيدٍۢ ፡፡
6:112-113 እንደዚሁም *ለነቢያት ሁሉ ከሰውና ከጋኔን የኾኑን ሰይጣናት ጠላት አደረግን*፡፡ ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ለማታለል *ልብስብስን ቃል ይጥላሉ*፡፡ ጌታህም በሻ ኖሮ ባልሠሩት ነበር፡፡ *ከቅጥፈታቸውም ጋር ተዋቸው*፡፡ *የሚጥሉትም ሊያታልሉ* እና የእነዚያም በመጨረሻይቱ ሕይወት የማያምኑት ሰዎች ልቦች ወደእርሱ እንዲያዘነብሉ እንዲወዱትም እነርሱ *ይቀጥፉ የነበሩትንም እንዲቀጣጥፉ* ነው፡፡
22፥52 ከመልክተኛና ከነቢይም ከአንተ በፊት አንድንም አላክንም ባነበበ ጊዜ ሰይጣን በንባቡ ላይ የሚጥል ቢሆን እንጅ፡፡ ወዲያውም አላህ ሰይጣን የሚጥለውን ያስወግዳል፡፡ ከዚያም አላህ አንቀጾቹን ያጠነክራል፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍۢ وَلَا نَبِىٍّ إِلَّآ إِذَا تَمَنَّىٰٓ أَلْقَى ٱلشَّيْطَٰنُ فِىٓ أُمْنِيَّتِهِۦ فَيَنسَخُ ٱللَّهُ مَا يُلْقِى ٱلشَّيْطَٰنُ ثُمَّ يُحْكِمُ ٱللَّهُ ءَايَٰتِهِۦ ۗ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌۭ ፡፡

ይህ አንቀፅ ሙጅመል ማለትም ጥቅላዊ ነው፤ ምክንያቱም *"ከአንተ በፊት"* የሚለው ገለጻ ከነብያችን በፊት በነበሩት ነብያትና መልእክተኞችም ላይም ከሰውና ከጋኔን የኾኑን ሰይጣናት ለማታለል *ልብስብስን ቃል* ይጥላሉ፤ ወዲያውም አላህ ሰይጣን የሚጥለውን ያስወግዳል፡፡ ከዚያም አላህ አንቀጾቹን ያጠነክራል፤ ሸኹል ኢስላም ኢብኑ ተምያህ ይህንን እይታ ይጋራሉ። ነገር ግን በወቅቱ ነብያችን”ﷺ” "አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን?" የሚለው አንቀጽ በአሉታዊ መልኩ አንብበው ሲጨርሱ በንባቡ ላይ ሸይጣን፦ "እነዚህ የተከበሩ ናቸው ምልጃቸው ተቀባይነት ያገኘው ናቸው" የሚለውን ለሙሽሪኮች ሲያነብ ሙሽሪኮች ይህን ቃል ሲሰሙ፦ "ነቢዩ”ﷺ” አማልክቶቻችንን አወድሷል" ሲሉ ዋሹ፤ የዚህ ቅጥፈት ዜና ወደ ሐበሻ ከተሰደዱ ሰሐቦች ዘንድ ከእውነታው እጅግ በተለየና በራቀ መልኩ ተሰማ፤ አላህም ነብያችንን”ﷺ” "ከዚያም ወደ አንተ ካወረድነው ሌላን በእኛ ላይ ትዋሽ ዘንድ ሊፈትኑህ በእርግጥ ተቃረቡ፡፡ ያን ጊዜም ወዳጅ አድርገው በያዙህ ነበር" በማለት ይህ ቅጥፈት ለማስዋሸት ፈተና መሆኑን እና ቢዋሹ ወዳጆች አድርገው ይይዧቸው እንደነበር ተናገረ፦
17፥73 እነሆ ከዚያም ወደ አንተ ካወረድነው ሌላን በእኛ ላይ ትዋሽ ዘንድ ሊፈትኑህ በእርግጥ ተቃረቡ፡፡ ያን ጊዜም ወዳጅ አድርገው በያዙህ ነበር وَإِن كَادُوا۟ لَيَفْتِنُونَكَ عَنِ ٱلَّذِىٓ أَوْحَيْنَآ إِلَيْكَ لِتَفْتَرِىَ عَلَيْنَا غَيْرَهُۥ ۖ وَإِذًۭا لَّٱتَّخَذُوكَ خَلِيلًۭا ፡፡

ሙሽሪኮች ጠላት መሆናቸው በራሱ ከአላህ ቃል ሌላ ቃልን እንዳልተናገሩ በቂ ማስረጃ ነው፤ ምክንያቱም ነብያችንን”ﷺ” ወዳጅ አድርገው አለመያዛቸው ነው፤ በተጨማሪም በመቀጠል ከአላህ ውጪ ከሌላ ማንነት ሆነ ምንነት ከፊል ቃልን አምጥቶ ቢቀጥፉ የልብ ስራቸውን እንደሚቆርጥ በመናገር ከሌላ ህልውና ምንም እንዳላሉ መስክሮላቸዋል፤ ፦
69፥44-46 በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት ያላልነውን "በቀጠፈ" ኖሮ وَلَوْ تَقَوَّلَ عَلَيْنَا بَعْضَ ٱلْأَقَاوِيلِ ፤ በኀይል በያዝነው ነበር لَأَخَذْنَا مِنْهُ بِٱلْيَمِينِ ፡፡ ከዚያም ከእርሱ የልቡን ሥር በቆረጥን ነበር ثُمَّ لَقَطَعْنَا مِنْهُ ٱلْوَتِينَ ፡፡

""የልቡን ሥር በቆረጥን ነበር ""ብሎ ማለት የቱን ያህል በግህደተ-መለኮት ቀልድ እንደሌለ የሚያሳይ ሃይለ-ቃል ነው። ከአላህ ወዲህ የትኛው ንግግር ማስረጃ ሊሆን ይችላል? ቁርአንን አላህ ነው ያወረደው፤ አላህ ከሰው ሆነ ከሸይጣን ቃላት ጠብቆታል፣ ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፦
15:9 እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡
41:42 ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፤ ጥበበኛ ምስጉን ከሆነውጌታ የተወረደ ነው።

በቂሰቱል ገራኒቅ ዋቢ ደርስ የዶክተር ሸኽ ያሲር ”ሀፊዘሁላህ” ሌክቸር እዚህ ይመልከቱ፦
https://youtu.be/wFq5ZnD6pFQ
መደምደሚያ
ይህንን የተመታ እና የተመምታታ ውሃ የማያነሳ ሙግት ሳልማን ሩሽዲ በ 1988 AD "ሰይጣናዊ አንቀፅ" የሚል መጽሐፉን ሲያራግቡ ከነበሩት መካከል ሚሽነሪዎች አንዶቹ ናቸው፤ እስቲ በዚህ ሂስ ባይብል ላይ ያለውን ዳዊት እንመልከተው፤ ይህን ሙግት የዳዊትን ነብይነት ለማስተባበል ሳይሆን እሾህክን በእሾክ እንዴት እንደሆነ ለማሳየት ነው፤ ዳዊት እስራኤልን ቁጠር ሳይባል ቆጥሮ ዳዊት በሰራው ስህተት እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ቸነፈርን ልኮ ከእስራኤልም ሰባ ሺህ ሰዎች በመቅሰፍት ገደለ፦
2ኛ ሳሙኤል 24.14 እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ቸነፈርን ሰደደ፤ ከእስራኤልም ሰባ ሺህ ሰዎች ወደቁ።

ይህ ስህተት የራሱ የዳዊት እንደሆነ አምኗል፣ ይቅርታም ጠይቋል፣ ከዚያም ባሻገር ይህ የእኔ ስህተት ነው ህዝቡን አትንካ ብሎ ጸለየ፣ ነገር ግን የዳዊት ልመናም አልሰራም፦
1ኛ ዜና መዋዕል 21፥8 ዳዊትም እግዚአብሔርን፦ ይህን በማድረግ እጅግ በድያለሁ፤ አሁን ግን ታላቅ ስንፍና አድርጌአለሁና የባሪያህን ኃጢአት ታስወግድ ዘንድ እለምንሃለሁ አለው።
1ኛ ዜና መዋዕል 21፥17 ዳዊትም እግዚአብሔርን፦ ሕዝቡ ይቈጠር ዘንድ ያዘዝሁ እኔ አይደለሁምን? የበደልሁና ክፉ የሠራሁ እኔ ነኝ፤ እነዚህ በጎች ግን ምን አድርገዋል? አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሁን፥ ነገር ግን ይቀሠፍ ዘንድ በሕዝብህ ላይ አትሁን አለው።

ታዲያ ዳዊት ማን ቁጠር ብሎት ነው የቆጠረው? ስንል
ዳዊት እስራኤልን የቆጠረው ሰይጣን "ቁጠር" ብሎት ነው ይለናል፦
2ኛ ሳሙኤል 24.1 ደግሞም የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ ዳዊትንም፦ *ሂድ፥ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር* ብሎ በላያቸው አስነሣው።

ሂድ፥ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር ያለው ሰይጣን ነው፥ እርሱ የተባለው ህቡዕ ተውላጠ-ስም ሰይጣን መሆኑን ሌላ ጥቅስ ይነግረናል፦
1ኛ ዜና መዋዕል 21፥1 ሰይጣንም በእስራኤል ላይ ተነሣ፥ እስራኤልንም ይቈጥር ዘንድ ዳዊትን "አንቀሳቀሰው"።

"አንቀሳቀሰው" ብለው ያስቀመጡት የዕብራይስጡ ቃል "የሰት" תְּסִיתֵ֥נִי ሲሆን "ሱት" סוּת ማለትም "አሳሳተ" ከሚል ግስ የመጣ ነው ፣ ለሃሰተኛ ነብይ ማሳሳት "የስቲአከ" יְסִֽיתְךָ֡ ማለትም "ቢያስትህ" በሚል መጥቷል፦
ዘዳግም 13.6 አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ቢያስትህ יְסִֽיתְךָ֡፥

ዳዊትም ከሰይጣን መልዕክት የተቀበለውን ለኢዮአብንና ለሕዝቡ አለቆች ቍጠሩ ብሎ አስተላልፏል፦
ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 21.8 ዳዊትም ኢዮአብንና የሕዝቡን አለቆች፦ ሂዱ፥ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ዳን ድረስ እስራኤልን ቍጠሩ፥ ድምራቸውንም አውቅ ዘንድ አስታውቁኝ አላቸው።

አንዱ ይህንን ሙግት ሳቀርብለት ዳዊት ነብይ አይደለም ብሎ ሽምጥጥ አድርጎ ሊክደኝ ሞክሯል፤ በባይብል የተብራራው ዳዊት የፈጣሪ ነብይ እንደሆነ ይናገራል፦
2፡29-30 ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አባቶች አለቃ ስለ ዳዊት እንደ ሞተም እንደ ተቀበረም ለእናንተ በግልጥ እናገር ዘንድ ፍቀዱልኝ፤ መቃብሩም እስከ ዛሬ በእኛ ዘንድ ነው። *ነቢይ ስለ ሆነ*፥

አዎ ዳዊት ነብይ ነበረ ከተባለ፤ የነብይ መስፈርቱ ከፈጣሪ መልዕክት መቀበል ወይስ ከሰይጣን መልዕክት መቀበል ? ፍርዱን ለህሊና።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አላህን ያታልላሉ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥9 *አላህን እና እነዚያን ያመኑትን ያታልላሉ፥ የማያውቁ ሲኾኑ እራሳቸውን እንጅ ሌላን አያታልሉም"*፡፡ يُخَادِعُونَ اللَّهَ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَمَا يَخْدَعُونَ إِلَّا أَنفُسَهُمْ وَمَا يَشْعُرُونَ

ሚሽነሪዎች፦ "መታለል የዐላዋቂነት ባሕርይ ነው፥ አላህ በሙናፊቃን ይታለላል" ይላሉ። እኛም መለስ ብለን ሙናፊቃን አላህን እና እነዚያን ያመኑትን ያታልላሉ፥ ነገር ግን የማያውቁ ሲኾኑ እራሳቸውን እንጅ ሌላን አያታልሉም፦
2፥9 *አላህን እና እነዚያን ያመኑትን ያታልላሉ፥ የማያውቁ ሲኾኑ እራሳቸውን እንጅ ሌላን አያታልሉም"*፡፡ يُخَادِعُونَ اللَّهَ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَمَا يَخْدَعُونَ إِلَّا أَنفُسَهُمْ وَمَا يَشْعُرُونَ

"እራሳቸውን እንጅ ሌላን አያታልሉም" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። “ኒፋቅ” نِفَاق የሚለው ቃል “ናፈቀ” نَافَقَ ማለትም “ነፈቀ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ኑፋቄ” ወይም “ምንፍቅና” አሊያም “አስመሳይነት” “በአፉ አምኖ በልቡ የሚክድ” ማለት ነው። ኒፋቅ ያለበት ግለሰብ ደግሞ በነጠላ “ሙናፊቅ” مُنَٰفِق ሲባል በብዜት “ሙናፊቁን” مُنَٰفِقُون ወይም “ሙናፊቂን” مُنَٰفِقِين ይባላል። አላህ አያየንም፣ አይሰማንም፣ ዐያውቅብንም ብሎ ማለት አላህን ማታለል ነው፥ ግን ሰውን በሚያታልሉበት ስሌት አላህ ማታለል ስለማይቻል እራሳቸውን እንጅ ሌላን አያታልሉም። ለንጽጽር ከባይብል አንድ ጥቅስ ብንመለከት ጥሩ ነው፦
ኤርምያስ 3፥20 የእስራኤል ቤት ሆይ፥ *ሚስት ባልዋን እንደምታታታልል እንዲሁ አታለላችሁኝ* ይላል እግዚአብሔር።

ልብ አድርግ ባል በሚስት መታለል የዐላዋቂነት ባሕርይ ነው፥ የእስራኤል ቤት እግዚአብሔርን ያታለሉት ሚስት ባልዋን እንደምታታልል ነው። መታለል የዐላዋቂነት ባሕርይ ከሆነ እግዚአብሔር በእስራኤል ቤት እንዴት ይታለላል? ከላይ ያለው ጥያቄ እንዲህ በአጭር ጥያቄ ድባቅ ይገባል፥ ኅጹጻን እሳቦት ላላቸው ይህ ንጽጽር በቂ ነው። አላህ ሂዳያህ ይስጣቸው! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዘፈን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

31፥6 ከሰዎችም ያለ ዕውቀት ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት *"አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ"*፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يَشْتَرِي لَهْوَ الْحَدِيثِ لِيُضِلَّ عَن سَبِيلِ اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَيَتَّخِذَهَا هُزُوًا ۚ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ مُّهِينٌ

"ዐዝፍ" عَزْف የሚለው ቃል "ዐዘፈ" عَزَفَ ማለትም "ሞዘቀ" ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን "ሙዚቃ" ማለት ነው። የሙዚቃ መጫወቻ በነጠላ "ሚዕዘፍ" مِعْزَف ሲባል በብዜት "መዓዚፍ" مَعَازِف ይባላል። ሙዚቃ ሐራም መሆኑን በጥልቅ ያብራራው ከነቢያችን"ﷺ" ተወዳጅ ሰሓቢይ መካከል ኢብኑ መሥዑድ"ረ.ዐ." ነው፥ ከቀደምት ሠለፎች አንዱ እርሱ ቁርኣንን የተረዳበት መንገድ መረዳት የጤናማ ሥነ-አፈታት ጥናት ነው። እርሱ ይህንን የቁርኣን አንቀጽ ይዞ ስለ ዘፈን እንዲህ ይላል፦
31፥6 ከሰዎችም ያለ ዕውቀት ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት *"አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ"*፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يَشْتَرِي لَهْوَ الْحَدِيثِ لِيُضِلَّ عَن سَبِيلِ اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَيَتَّخِذَهَا هُزُوًا ۚ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ مُّهِينٌ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 31፥6
"ኢብኑ መሥዑድ እንደተናገረው፦ *"ከሰዎችም ከአላህ መንገድ ሊያሳስት ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ" የሚለው ወሏሂ እርሱ "ዘፈን" ነው"*። كما قال ابن مسعود في قوله تعالى : ( ومن الناس من يشتري لهو الحديث ) قال : هو - والله - الغناء .

"ለህወል ሐዲስ" لَهْوَ الْحَدِيث ማለትም "አታላይ ወሬ" ማለት ሲሆን "ጊናእ" ነው፥ "ጊናእ" غِنَاء የሚለው ቃል "ገና" غَنَّى‎ ማለትም "ዘፈነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ዘፈን" ማለት ነው። አምላካችን አላህ ኢብሊሥ የሚከተሉትን በድምጹ እንደሚያታልላቸው ተናግሯል። ይህም ድምጹ መደበሪያ፣ ዘፈን፣ ላግጣ እና ስላቅ ነው፦
17፥64 *ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምጽህ አታል*፡፡ وَاسْتَفْزِزْ مَنِ اسْتَطَعْتَ مِنْهُم بِصَوْتِكَ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 17፥64
*"ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምጽህ አታል" የተባለው እርሱ ዘፈን ነው፥ ሙጃሒድም አለ፦ "ድምጽ የተባለው መደበሪያ፣ ዘፈን፣ ላግጣና ስላቅ ነው"*። واستفزز من استطعت منهم بصوتك قيل هو الغناء قال مجاهد باللهو والغناء أي استخفهم بذلك

"ሐላል" حَلَال ማለት "የተፈቀደ" ማለት ሲሆን “ሐራም” حَرَام ማለት "የተከለከለ" ማለት ነው። ዝሙት እና አስካሪ መጠጥ ሐራም እንደሆነ ሁሉ ሙዚቃም ከዝሙት እና ከአስካሪ መጠጥ ጋር ተያይዞ ክልክል መሆኑ በነቢያችን"ﷺ" ሐዲስ ተነግሯል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 74, ሐዲስ 16
አቡ ዐሚር ወይም አቡ ማሊኩል አሽዐሪይ እንደተረከው፦ "ወሏሂ አልዋሸውም! ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቷል፦ *"ከኡመቴ ውስጥ ጥቂት ሰዎች ለራሳቸው ዝሙትን፣ ሐር ልብስን፣ አስካሪ መጠጥን እና ሙዚቃን ሐላል የሚያደርጉ ይሆናሉ”*። قَالَ حَدَّثَنِي أَبُو عَامِرٍ ـ أَوْ أَبُو مَالِكٍ ـ الأَشْعَرِيُّ وَاللَّهِ مَا كَذَبَنِي سَمِعَ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ "‏ لَيَكُونَنَّ مِنْ أُمَّتِي أَقْوَامٌ يَسْتَحِلُّونَ الْحِرَ وَالْحَرِيرَ وَالْخَمْرَ وَالْمَعَازِفَ

"ሙዚቃን ሐላል የሚያደርጉ ይሆናሉ" ማለት ሙዚቃ ሐራም ነው ማለት ነው። እዚህ ሐዲስ ላይ "ሙዚቃ" የሚለው "መዓዚፍ" مَعَازِف ሲሆን "ሚዕዘፍ" مِعْزَف ለሚለው የብዙ ቁጥር ነው። ዘፈን መናገሻው መሸታ ቤት ሲሆን መሸታ ቤት መጠጥ እና ዝሙት በሙዚቃ መሳሪያ የታጀበበት ሥፍራ ነው። "ጀረሥ" جَرَس ማለት "ደውል" ማለት ቢሆንም አጠቃላይ የሙዚቃ መሳሪያን "አጅራሥ" أَجْرَاس ይባላል። ጀረስ የሸይጧን መዝሙር ነው፥ የሙዚቃ መሳሪያ ያለበት ቤት መላእክት አይገቡም፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 37 , ሐዲስ 159
አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ "የአላህ መልክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ጀረሥ የሸይጧን መዝሙር ነው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ الْجَرَسُ مَزَامِيرُ الشَّيْطَانِ
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 36 , ሐዲስ 18
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "የአላህ መልክተኛም”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ *"መላእክት ጀረሥ ያለበት ቤት አይገቡም”*። وَقَالَتْ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ لاَ تَدْخُلُ الْمَلاَئِكَةُ بَيْتًا فِيهِ جَرَسٌ ‏

"ሚዝማር" مِزْمَار ወይም "መዝሙር" مَزْمُور የሚለው ቃል "ዘመረ" زَمَرَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መዝሙር" ወይም "ዝማሬ" ማለት ነው፥ የሚዝማር ወይም የመዝሙር ብዙ ቁጥር "መዛሚር" مَزَامِير ነው። አላህ ለዳውድ የሰጠው "ዘቡር" زَّبُور እራሱ "መዛሚር" مَزَامِير ተብሏል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 6, ሐዲስ 280
አቡ ሙሣ እንደተረከው፦ "የአላህ መልክተኛም”ﷺ” ለአቡ ሙሣ እንዲህ አሉ፦ *"ትላንት የቂርኣን አነቀራርህን ስሰማህ ብታየኝ ኖሮ በእርግጥም ደስ ይልህ ነበር። ዝማሬ ከዳዉድ ቤተሰብ መዝሙር ተሰቶሃል"*። عَنْ أَبِي مُوسَى، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم لأَبِي مُوسَى ‏ "‏ لَوْ رَأَيْتَنِي وَأَنَا أَسْتَمِعُ لِقِرَاءَتِكَ الْبَارِحَةَ لَقَدْ أُوتِيتَ مِزْمَارًا مِنْ مَزَامِيرِ آلِ دَاوُدَ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 66, ሐዲስ 72
አቡ ሙሣ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩ”ﷺ” ለእርሱ እንዲህ አሉ፦ *"አቡ ሙሣ ሆይ! ከዳዉድ ቤተሰብ መዝሙር ዝማሬ ተሰቶሃል"*። عَنْ أَبِي مُوسَى ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ لَهُ ‏ "‏ يَا أَبَا مُوسَى لَقَدْ أُوتِيتَ مِزْمَارًا مِنْ مَزَامِيرِ آلِ دَاوُدَ

"ሚዝማር" مِزْمَار የአቀራር ስልት ሲሆን "ቂራአት" قِرَاءَت ለሚለው ተለዋዋጭ ሆኖ መጥቷል። ቁርኣንን መቅራት ለአላህ የምናቀርበው ዝማሬ ነው። ነገር ግን ከዚያ በተቃራኒው ሙዚቃ እና ዘፈን የሸይጧን መዝሙር ነው፥ ዘፈን ስናዳምጥ ቁርኣን መቅራት እንችልም። ቁርኣን ስንቀራ ዘፈን ያስጠላናል። ዘፈን እና ቁርኣን ሁለት ተቃራኒ ናቸው፥ ቁርኣን ስንቀራ ቀልብ ረጥቦ ለአላህ የምናቀርበት ዝማሬ ነው። ዘፈን ሲዘፈን ቀልብ ደርቆ ለሸይጧን የሚቀርብ ዝማሬ ነው። አላህ ቁርኣንን የምቀራ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሶላቱ አሥ-ሡናህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

12፥108 *«ይህች መንገዴ ናት፡፡ ወደ አላህ እጠራለሁ፡፡ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን፡፡ ጥራትም ለአላህ ይገባው፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም»* በል፡፡ قُلْ هَـٰذِهِ سَبِيلِي أَدْعُو إِلَى اللَّهِ ۚ عَلَىٰ بَصِيرَةٍ أَنَا وَمَنِ اتَّبَعَنِي ۖ وَسُبْحَانَ اللَّهِ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ

"ሶላቱ አሥ-ሡናህ" صَّلَات ማለት "የሡናህ ሶላት" ማለት ነው። ሡናህ” سُنَّة ማለት “ፈለግ” “ፍኖት” “መንገድ” “ፋና” ማለት ነው፥ አምላካችን አላህ የነቢያችንን”ﷺ” ፈለግ እንድንከተል ይናገራል፦
12፥108 *«ይህች መንገዴ ናት፡፡ ወደ አላህ እጠራለሁ፡፡ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን፡፡ ጥራትም ለአላህ ይገባው፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም»* በል፡፡ قُلْ هَـٰذِهِ سَبِيلِي أَدْعُو إِلَى اللَّهِ ۚ عَلَىٰ بَصِيرَةٍ أَنَا وَمَنِ اتَّبَعَنِي ۖ وَسُبْحَانَ اللَّهِ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ
6፥153 *«ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ የጥመት መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከቀጥተኛው መንገድ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በእርሱ አዘዛችሁ፡፡»* በላቸው وَأَنَّ هَـٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُون

"መንገዴ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። የነቢያችንን”ﷺ” ፈለግ ወይም መንገድ መከተል ሡናህ ይባላል። ሡናህ” سُنَّة ሌላው ትርጉሙ “ሙስተሐብ” مُسْتَحَبّ‎ ማለትም “የተወደደ” ማለት ነው፥ የተወደዱ የሡናህ ሶላቶች አስራ ሁለት ናቸው። እነርሱም፦ አራት ረክዓህ ከዙህር በፊት፣ ሁለት ረክዓህ ከዙህር በኃላ፣ ሁለት ረክዓህ ከመግሪብ በኃላ፣ ሁለት ረክዓህ ከዒሻእ በኃላ፣ ሁለት ረክዓህ ከሶላቱል ፈጅር በፊት ናቸው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 268
ኡሙ ሐቢባህ እንደተረከችው፦ "የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ማንም በመአልት እና በሌሊት አስራ ሁለት ረክዓህ የሰገደ ለእርሱ በጀነት ቤት ይገነባለታል። አራት ረክዓህ ከዙህር በፊት፣ ሁለት ረክዓህ ከዙህር በኃላ፣ ሁለት ረክዓህ ከመግሪብ በኃላ፣ ሁለት ረክዓህ ከዒሻእ በኃላ፣ ሁለት ረክዓህ ከሶላቱል ፈጅር በፊት ነው"*። عَنِ الْمُسَيَّبِ بْنِ رَافِعٍ، عَنْ عَنْبَسَةَ بْنِ أَبِي سُفْيَانَ، عَنْ أُمِّ حَبِيبَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَنْ صَلَّى فِي يَوْمٍ وَلَيْلَةٍ ثِنْتَىْ عَشْرَةَ رَكْعَةً بُنِيَ لَهُ بَيْتٌ فِي الْجَنَّةِ أَرْبَعًا قَبْلَ الظُّهْرِ وَرَكْعَتَيْنِ بَعْدَهَا وَرَكْعَتَيْنِ بَعْدَ الْمَغْرِبِ وَرَكْعَتَيْنِ بَعْدَ الْعِشَاءِ وَرَكْعَتَيْنِ قَبْلَ صَلاَةِ الْفَجْرِ

እነዚህ አስራ ሁለቱ የጠበቁ የሡናህ ሶላት ሲሆኑ፥ ከዐስር ሶላት በፊት ሁለት ረክዓህ ወይም አራት ረክዓህ የተወደዱ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 23
ዐሊይ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"ነቢዩ"ﷺ" ከዐስር በፊት ሁለት ረክዓህ ይሰግዱ ነበር"*። عَنْ عَلِيٍّ، عَلَيْهِ السَّلاَمُ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يُصَلِّي قَبْلَ الْعَصْرِ رَكْعَتَيْنِ
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 282
ዐሊይ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"ነቢዩ"ﷺ" ከዐስር በፊት አራት ረክዓህ ይሰግዱ ነበር፥ በመካከላቸው በተሥሊም(ማሰላመት) ይለይ ነበር"*። عَنْ عَلِيٍّ، قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم يُصَلِّي قَبْلَ الْعَصْرِ أَرْبَعَ رَكَعَاتٍ يَفْصِلُ بَيْنَهُنَّ بِالتَّسْلِيمِ

አምላካችን አላህ በጀነት ቤት ከሚገነባላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኮሮና ወረርሽኝ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

26፥80 *”በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል”*፡፡ وَإِذَا مَرِضْتُ فَهُوَ يَشْفِينِ

"ጧዑን" طَّاعُون ማለት "መቅሰፍት" "ወረርሽ" "በሽታ" ማለት ነው። ነቢያችን"ﷺ" በመጨረሻ ዘመን የሚመጣ መቅሰፍት እንዳለ ተናግረዋል። ይህ መቅሰፍት መዲና አይገባም፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 92, ሐዲስ 81
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦*"በመዲና ተራሮች ላይ ጠባቂ መላኢካዎች አሉ። መቅሰፍትም ሆነ አድ-ደጃል ወደ ወደዚያ መግባት አይችሉም"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ عَلَى أَنْقَابِ الْمَدِينَةِ مَلاَئِكَةٌ، لاَ يَدْخُلُهَا الطَّاعُونُ وَلاَ الدَّجَّالُ

እዚህ ሐዲስ ላይ የተጠቀመው "ጧዑን" طَّاعُون በተለየ መልኩ "ሙፈሰል" مُفَصَّل ሲሆን "መውታን" مَوْتَان "ሙታን" مُوتَان ማለትም "መቅሰፍት" ማለት ነው። ይህ በመጨረሻ ዘመን የሚመጣው መቅሰፍት መዲና አይገባም።
ነገር ግን "ጧዑን" طَّاعُون በጥቅል መልኩ “ሙጅመል” مُجّمَل ሆኖ በየጊዜው የሚመጣውን ማንኛውንም ወረርሽ ለማመልከት አገልግሎት ላይ ውሏል። ሙጅመል ከሆኑት ጧዑን ማንኛውም ከአላህ ዘንድ ለበደላችን ቅጣት ሲሆን ለንጹሓን የአላህ ባሮች ደግሞ ምሕረት እና ሰማዕትነት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 56, ሐዲስ 46
አነሥ ኢብኑ ማሊክ"ረ.ዐ" እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *“ወረርሽኝ ለሁሉም ሙሥሊም ሰማዕትነት ነው”"* عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ الطَّاعُونُ شَهَادَةٌ لِكُلِّ مُسْلِمٍ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 76, ሐዲስ 49
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"የአላህን መልእክተኛ"ﷺ" ስለ ወረርሽኝ ጠየኳቸው። እርሳቸውም፦ *"አላህ ለሚሻው ሰው ይልክበታል፥ ለአማኞች ግን ምሕረት ነው። በአንድ አካባቢ ወረርሽኝ መከሰቱን ከሰማችሁ ወደ ከተማዋ አትግቡ! በከተማዋ ውስጥ ከሆናችሁ ደግሞ አላህ ምሕረቱን እስኪያመጣ እና የሰማዕትነት አጅር እኪሰጣችሁ ከከተማዋ አትውጡ!" አሉ"*። عَنْ عَائِشَةَ، زَوْجِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّهَا أَخْبَرَتْنَا أَنَّهَا سَأَلَتْ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنِ الطَّاعُونِ فَأَخْبَرَهَا نَبِيُّ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ أَنَّهُ كَانَ عَذَابًا يَبْعَثُهُ اللَّهُ عَلَى مَنْ يَشَاءُ، فَجَعَلَهُ اللَّهُ رَحْمَةً لِلْمُؤْمِنِينَ، فَلَيْسَ مِنْ عَبْدٍ يَقَعُ الطَّاعُونُ فَيَمْكُثُ فِي بَلَدِهِ صَابِرًا، يَعْلَمُ أَنَّهُ لَنْ يُصِيبَهُ إِلاَّ مَا كَتَبَ اللَّهُ لَهُ، إِلاَّ كَانَ لَهُ مِثْلُ أَجْرِ الشَّهِيدِ ‏

በጥቅል ከተገለጹት ወረርሽኝ አንዱ ኮሮና ወረርሽኝ"Corona virus" ያለ አንዳች ከላይ በፍጥነት እየተዛመተ ያለ ቫይረስ ነው። ይህ ፈተና ነው፥ ይህ ፈተና የበደለውንም ያልበደለውን ሳይለኝ የሚያጠቃ ፈተና ነው። የዚህ በሽታ ምሕረቱ ከአላህ ዘንድ ነው፥ ህመምን የሚያሽር አላህ ነው፦
8፥25 *ከእናንተም ውስጥ እነዚያን የበደሉትን ብቻ ለይታ የማትነካን ፈተና ተጠንቀቁ፡፡ አላህም ቅጣቱ ብርቱ መኾኑን እወቁ*፡፡ وَاتَّقُوا فِتْنَةً لَّا تُصِيبَنَّ الَّذِينَ ظَلَمُوا مِنكُمْ خَاصَّةً ۖ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ
26፥80 *”በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል”*፡፡ وَإِذَا مَرِضْتُ فَهُوَ يَشْفِينِ

አላህ ምሕረቱ ያምጣልን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሸሃዳህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

57፥19 *እነዚያም በአላህ እና በመልክተኞቹ ያመኑት እነዚያ እነርሱ በጣም እውነተኞቹ በጌታቸውም ዘንድ መስካሪዎቹ ናቸው*፡፡ ለእነርሱ ምንዳቸው ብርሃናቸውም አልላቸው፡፡ እነዚያም የካዱት በአንቀጾቻችንም ያስተባበሉት እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ وَالَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرُسُلِهِ أُولَـٰئِكَ هُمُ الصِّدِّيقُونَ ۖ وَالشُّهَدَاءُ عِندَ رَبِّهِمْ لَهُمْ أَجْرُهُمْ وَنُورُهُمْ ۖ وَالَّذِينَ كَفَرُوا وَكَذَّبُوا بِآيَاتِنَا أُولَـٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَحِيمِ

"ሸሃዳህ” شَهَادَة‎ የሚለው ቃል “ሸሂደ” شَهِدَ ማለትም “መሰከረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምስክርነት” ማለት ነው፥ ሻሂድ شَاهِد አሊያም “ሸሂድ” شَهِيد ደግሞ “ምስክር” ማለት ሲሆን የሻሂድ ብዙ ቁጥር “ሹሀዳእ” شُهَدَاء ነው። አንድ ሰው ወደ ዲኑል ኢሥላም የሚገባበት “ቃለ-ምስክርነት” ሸሃዳህ ይባላል። ይህም ቃለ-ምስክርነት “ላ ኢላሀ ኢለሏህ ሙሐመዱን ረሱሉሏህ” لَا إِلَٰهَ إِلَّا ٱللَّٰهُ مُحَمَّدٌ رَسُولُ ٱللَّٰه ማለትም “ከአላህ በስተቀር አምላክ የለም፥ ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ ነው” የሚል ነው። በእያንዳንዱ ዘመን የተለያዩ መልእክተኛ ስላሉ በዛ ዘመን ባለው መልእክተኛ ለምሳሌ በዒሣ ከሆነ “ዒሣ ረሱሉሏህ” ብለው ይቀበሉ ነበር። ለምሳሌ አላህ በዒሣ ዘመን “በእኔ እና በመልክተኛዬ እመኑ” በማለት ወሕይ አውርዷል፦
5፥111 ወደ ሐዋርያትም *«በእኔ እና በመልክተኛዬ እመኑ»* በማለት ባዘዝኩ ጊዜ አስታውስ፡፡ «አመንን፤ እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክር» አሉ፡፡ وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى الْحَوَارِيِّينَ أَنْ آمِنُوا بِي وَبِرَسُولِي قَالُوا آمَنَّا وَاشْهَدْ بِأَنَّنَا مُسْلِمُونَ

በአላህ እና በመልክተኞቹ ማመን ወደ ዱኑል ኢሥላም የሚያስገባ ቁልፍ ነው። እነዚያ ያመኑት መስካሪዎች ናቸው፦
57፥19 *እነዚያም በአላህ እና በመልክተኞቹ ያመኑት እነዚያ እነርሱ በጣም እውነተኞቹ በጌታቸውም ዘንድ መስካሪዎቹ ናቸው*፡፡ ለእነርሱ ምንዳቸው ብርሃናቸውም አልላቸው፡፡ እነዚያም የካዱት በአንቀጾቻችንም ያስተባበሉት እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ وَالَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرُسُلِهِ أُولَـٰئِكَ هُمُ الصِّدِّيقُونَ ۖ وَالشُّهَدَاءُ عِندَ رَبِّهِمْ لَهُمْ أَجْرُهُمْ وَنُورُهُمْ ۖ وَالَّذِينَ كَفَرُوا وَكَذَّبُوا بِآيَاتِنَا أُولَـٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَحِيمِ

አላህ እራሱ፣ መላእክቶች እና የዕውቀት ባለቤቶችም "ላ ኢላሀ ኢለሏህ" ብለው መስክረዋል፦
3፥18 *አላህ በማስተካከል አስተናባሪ ሲኾን ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለ መኾኑን መሰከረ፡፡ መላእክቶችና የዕውቀት ባለቤቶችም እንደዚሁ መሰከሩ፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አሸናፊው ጥበበኛው ነው*፡፡ شَهِدَ اللَّهُ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ وَالْمَلَائِكَةُ وَأُولُو الْعِلْمِ قَائِمًا بِالْقِسْطِ ۚ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

ነቢያችን"ﷺ" ረሱል መሆናቸውን አላህ "መስክሩ" ብሏል፦
3፥81 *«እንግዲያስ መስክሩ፤ እኔም ከእናንተ ጋር ከመስካሪዎቹ ነኝ» አላቸው*፡፡ قَالَ فَاشْهَدُوا وَأَنَا مَعَكُم مِّنَ الشَّاهِدِينَ

“ላ ኢላሀ ኢለሏህ ሙሐመዱን ረሱሉሏህ” لَا إِلَٰهَ إِلَّا ٱللَّٰهُ مُحَمَّدٌ رَسُولُ ٱللَّٰه የሚለው ቁርኣን ውስጥ አለ፥ "ላ ኢላሀ ኢለሏህ" لَا إِلَٰهَ إِلَّا ٱللَّٰه እዚህ አንቀጽ ላይ አለ፦
47፥19 እነሆ *ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም* ዕወቅ!፡፡ فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّهُ

"ሙሐመዱን ረሱሉሏህ" مُحَمَّدٌ رَسُولُ ٱللَّٰه የሚለው ደግሞ እዚህ አንቀጽ ላይ አለ፦
48፥29 የአላህ መልክተኛ ሙሐመድ እነዚያም ከእርሱ ጋር ያሉት ወዳጆቹ በከሓዲዎቹ ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው አዛኞች ናቸው፡፡ አጎንባሾች፣ ሰጋጆች ኾነው ታያቸዋለህ፡፡ ከአላህ ችሮታንና ውዴታን ይፈልጋሉ፡፡ ምልክታቸው ከስግደታቸው ፈለግ ስትኾን በፊቶቻቸው ላይ ናት፡፡ مُّحَمَّدٌ رَّسُولُ اللَّهِ ۚ وَالَّذِينَ مَعَهُ أَشِدَّاءُ عَلَى الْكُفَّارِ رُحَمَاءُ بَيْنَهُمْ ۖ تَرَاهُمْ رُكَّعًا سُجَّدًا يَبْتَغُونَ فَضْلًا مِّنَ اللَّهِ وَرِضْوَانًا ۖ سِيمَاهُمْ فِي وُجُوهِهِم مِّنْ أَثَرِ السُّجُودِ

አንድ ላይ በአንድ አንቀጽ ላይ፦ "ላ ኢላሀ ኢሏ ሁወ፥ አኒ ረሱሉሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ إِنِّي رَسُولُ اللَّهِ በል ተብሎ ተቀምጧል፦
7፥158 በላቸው፡- «እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ወደ እናንተ ወደ ሁላችሁም *የአላህ መልክተኛ ነኝ፡፡ እርሱም ያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ የኾነ ነው፡፡ እርሱ እንጂ ሌላ አምላክ የለም*፡፡ ሕያው ያደርጋል፥ ያሞታል። قُلْ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنِّي رَسُولُ اللَّهِ إِلَيْكُمْ جَمِيعًا الَّذِي لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ يُحْيِي وَيُمِيتُ

ነቢያችን"ﷺ" በሐዲሳቸው፦ “ኣላ ኢላሀ ኢለሏህ ሙሐመዱን ረሱሉሏህ” لَا إِلَٰهَ إِلَّا ٱللَّٰهُ مُحَمَّدٌ رَسُولُ ٱللَّٰه ከኢሥላም መሠረት አንዱ እንደሆነ ነግረውናል፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 4
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ኢሥላም በአምስቱ መሠረቶች ላይ ተገንብቷል፤ እነርሱም፦ “ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፥ ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ ነው” በሚል ምስክርነት፣ ሶላትን በመቆም፣ ዘካህን በመስጠት፣ ረመዷንን በመፆም እና የአላህ በይት በመጎብኘት”*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ بُنِيَ الإِسْلاَمُ عَلَى خَمْسٍ شَهَادَةُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ وَإِقَامُ الصَّلاَةِ وَإِيتَاءُ الزَّكَاةِ وَصَوْمُ رَمَضَانَ وَحَجُّ الْبَيْتِ

መመስከር ማለት ዐውቄአለው፣ ዐምኛለው፣ እናገራለው፣ እተገብራለው ማለት ነው። አምላካችን አላህ ሹሀዳእ ከሚላቸው ባሮቹ ያርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
እሳት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

104፥6 *የተነደደችው የአላህ እሳት ናት*፡፡ نَارُ اللَّهِ الْمُوقَدَةُ

"አን-ናር" النَّار ማለት "እሳት" ማለት ሲሆን "ሙቀት"heat" እና "ነበልባል"flame" ነው፥ እሳት የተፈጠረው ከሰው በፊት በስድስት ቀናት ውስጥ ነው፦
50፥38 *"ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን"*፡፡ ድካምም ምንም አልነካንም፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَمَا مَسَّنَا مِن لُّغُوبٍ

አደም የተፈጠረው በጁሙዓህ ቀን ሲሆን ጂኒዎች የተፈጠሩት ከአደም በፊት ከእሳት ነበልባል ነው፦
15፥27 ጃንንም ከሰው በፊት *ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው*፡፡ وَالْجَانَّ خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ مِن نَّارِ السَّمُومِ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 7, ሐዲስ 26
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"መልካም ቀን ፀሐይ ከወጣችበት የጁሙዓህ ቀን ነው፥ በዚያ ቀን አደም ተፈጠረ። በዚያ ቀን ወደ ጀነት ገብቷል፥ ከጀነት በዚያ ቀን ወጥቷል"*። أَنَّهُ سَمِعَ أَبَا هُرَيْرَةَ، يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ خَيْرُ يَوْمٍ طَلَعَتْ عَلَيْهِ الشَّمْسُ يَوْمُ الْجُمُعَةِ فِيهِ خُلِقَ آدَمُ وَفِيهِ أُدْخِلَ الْجَنَّةَ وَفِيهِ أُخْرِجَ مِنْهَا

ስለዚህ ጂኒዎች የተፈጠሩበት እሳት የተፈጠረው ከሰው በፊት በስድስት ቀናት ውስጥ ነው፥ ግን በመጀመርያ ቀን ይሁን፣ በሁለተኛው ቀን ይሁን፣ በሦስተኛው ቀን ይሁን ወዘተ.. ዐናውቅም። "ነበልባል" ለሚለው የገባው ቃል "ሠሙም" سَمُوم ሲሆን በጀሀነም ላለው ፍጥረት ቅጣት "መርዝ" ነው፦
52፥27 «አላህም በእኛ ላይ ለገሰ፡፡ *የመርዛም እሳት* ቅጣትንም ጠበቀን፡፡ فَمَنَّ اللَّهُ عَلَيْنَا وَوَقَانَا عَذَابَ السَّمُومِ

"ሠሙም" سَمُوم የሚለው ቃል "ሠመ" سَمَّ ማለትም "መረዘ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን የእሳት "ነበልባል" ለሰው ሰውነት ስሚያቃጥል መርዝ ነው፥ "ሡም" سُمّ ማለት እራሱ ቅጽል ሲሆን "መርዛም" ማለት ነው። "ጀሀነም" جَهَنَّم‎ የሚለው ቃል ትርጉም ሁለት እይታ አለ፥ አንዱ እይታ "ጀሀነም" የሚለው ቃል "ሙሽተቅ” مُشتَق ማለትም "ከዐረቢኛ ቃል የሚረባ ቃል" ሲሆን "ጀሒም" ከሚለው የስም መደብ የመጣ ነው። "ጀሒም" جَحِيم የሚለው ቃል "ጀሑመ" جَحُمَ ማለትም "አቃጠለ" ነደደ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ማቀጣጠያ" "ማንደጃ" ማለት ነው፦
81፥12 *"ገሀነምም በተነደደች ጊዜ"*። وَإِذَا الْجَحِيمُ سُعِّرَتْ

"እዚህ አንቀጽ ላይ "ገሀነም" ለሚለው ቃል የገባው "ጀሒም" جَحِيم መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። "ነዒም" نَعِيم ማለት "ጸጋ" ማለት ሲሆን የጀሒም" ተቃራኒ ነው። ሁለተኛው እይታ "ጀሀነም" የሚለው ቃል “ጃሚድ” جامِد ማለትም "ከዐረቢኛ ቃል የማይረባ ቃል" ሲሆን "ጌሄኑም" ከሚል ሴማዊ ዳራ የመጣ ሙዐረብ ነው፥ “ሙዐረብ” مُعَرَّب ማለትም “ዐረቢኛ ውስጥ ገብቶ ዐረቢኛ የሆነ" ማለት ነው። እዚህ ዓለም ላይ ያለው እሳት እራሱ ከሰባው የጀሀነም እሳት አንዱ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 59, ሐዲስ 75
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"የእናንተ እሳት ከሰባው የጀሀነም እሳት ክፍል ነው። አንዱም፦ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ይህ ለቅጣት በቂ ነውን? አለ፥ እርሳቸውም፦ "እሳቱ ከተለመደው እሳት የበለጠ ስድሳ ዘጠኝ ክፍሎች አሉት፥ እያንዳንዱ የእሳት ክፍል ልክ እንደዚህ ጠንካራ ነው" አሉት*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ نَارُكُمْ جُزْءٌ مِنْ سَبْعِينَ جُزْءًا مِنْ نَارِ جَهَنَّمَ ‏"‌‏.‏ قِيلَ يَا رَسُولَ اللَّهِ، إِنْ كَانَتْ لَكَافِيَةً‏.‏ قَالَ ‏"‏ فُضِّلَتْ عَلَيْهِنَّ بِتِسْعَةٍ وَسِتِّينَ جُزْءًا، كُلُّهُنَّ مِثْلُ حَرِّهَا ‏

ከሰባው አንዱ የእሳት ክፍል ምድራችን ውስጥ ይገኛል። የምድርን 20% የያዘው የመሬት አስኳል"core" እራሱ 8653 መጠን(tonne) ድኝ"sulphur" ነው። ውስጣዊ አስኳሉ"inner core" እራሱ ጠጣር እሳት ነው፥ ይዞታው በራዲየስ እስከ 1220 ኪሎ ሜትር ሲሆን የሙቀቱ መጠን ደግሞ 5,400 ድግሪ ሴሊሽየስ °C ወይም 9,800 ዲግሪ ፋረንሃይት °F ነው። ውጫዊ አስኳሉ"outer core" እራሱ ፈሳሽ እሳት ነው፥ ይዞታው በራዲየስ እስከ 2,890 ኪሎ ሜትር ሲሆን የሙቀቱ መጠን ደግሞ 4,400 ድግሪ ሴሊሽየስ °C ወይም 7,952 ዲግሪ ፋረንሃይት °F ነው። ይህ የምድራችን የእሳት ሙቀት በክረምት እና በበጋ ይመጣል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 5, ሐዲስ 237
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"እሳት ወደ ጌታዋ በቅሬታ፦ "ጌታ ሆይ! የእኔ አንዱ ክፍል ሌላውን ክፍል በላ" አለች። ለእርሷም ሁለት መተንፈሻዎች ተደረገላት፥ አንደኛው መተንፈሻ በክረምት ሲሆን ሌላይኛው መተንፈሻ ደግሞ በበጋ ነው። ለዛ ነው ጽንፍ ሙቀት እና ቅዝቃዜ የምታገኙት"*። أَنَّهُ سَمِعَ أَبَا هُرَيْرَةَ، يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ اشْتَكَتِ النَّارُ إِلَى رَبِّهَا فَقَالَتْ يَا رَبِّ أَكَلَ بَعْضِي بَعْضًا ‏.‏ فَأَذِنَ لَهَا بِنَفَسَيْنِ نَفَسٍ فِي الشِّتَاءِ وَنَفَسٍ فِي الصَّيْفِ فَهُوَ أَشَدُّ مَا تَجِدُونَ مِنَ الْحَرِّ وَأَشَدُّ مَا تَجِدُونَ مِنَ الزَّمْهَرِيرِ
ሰሜናዊ ንፍቀ-ክበብ"Northern Hemisphere" ከታህሳስ እስከ መጋቢት ክረምት ሲሆን ከሰኔ እስከ መስከረም በጋ ነው። በተቃራኒው ደቡባዊ ንፍቀ-ክበብ"Southern Hemisphere" ከታህሳስ እስከ መጋቢት በጋ ሲሆን ከሰኔ እስከ መስከረም ክረምት ነው።
የሙቀት መጠን በሰሜናዊ ንፍቀ-ክበብ ከሰኔ እስከ መስከረም ባለው የበጋ ጊዜ ሲመጣ በደቡባዊ ንፍቀ-ክበብ ከሰኔ እስከ መስከረም ያለውን የክረምት ጊዜ ያመጣል፥ በተቃራኒው በደቡባዊ ንፍቀ-ክበብ ከታህሳስ እስከ መጋቢት ባለው የበጋ ጊዜ ሲመጣ በሰሜናዊ ንፍቀ-ክበብ ከታህሳስ እስከ መጋቢት ያለውን የክረምት ጊዜ ያመጣል።
ስለዚህ በሰሜናዊ ንፍቀ-ክበብ በበጋ ጊዜ የሚመጣው ሙቀት በደቡባዊ ንፍቀ-ክበብ ባለው የክረምት ጊዜ ነው፥ በደቡባዊ ንፍቀ-ክበብ በበጋ ጊዜ የሚመጣው ሙቀት በሰሜናዊ ንፍቀ-ክበብ ባለው የክረምት ጊዜ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 39, ሐዲስ 2796
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"እሳት ወደ ጌታዋ በቅሬታ፦ "ጌታ ሆይ! የእኔ አንዱ ክፍል ሌላውን ክፍል በላ" አለች። ለእርሷም ሁለት መተንፈሻዎች ተደረገላት፥ አንደኛው መተንፈሻ በክረምት ሲሆን ሌላይኛው መተንፈሻ ደግሞ በበጋ ነው። በክረምት ማስተንፈሻዋ ዘምሀሪር ሲባል፥ በበጋ ማስተንፈሻዋ ደግሞ ሠሙም ይባላል"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ اشْتَكَتِ النَّارُ إِلَى رَبِّهَا وَقَالَتْ أَكَلَ بَعْضِي بَعْضًا فَجَعَلَ لَهَا نَفَسَيْنِ نَفَسًا فِي الشِّتَاءِ وَنَفَسًا فِي الصَّيْفِ فَأَمَّا نَفَسُهَا فِي الشِّتَاءِ فَزَمْهَرِيرٌ وَأَمَّا نَفَسُهَا فِي الصَّيْفِ فَسَمُومٌ ‏

ሰው እራሱ ከምድር አፈር ስለተሠራ በውስጡ ሙቀት አለው። "ሰው" የሚለው ቃል በግዕዝ “ሰብእ” ማለት ሲሆን "ሰባት" ማለት ነው። ሦስቱ ባሕርያተ-ነፍስ ማለትም የነፍስ ባሕርያት ልብ፣ ነቢብ እና ሕያው ነው፥ አራቱ ባሕርያተ-ስጋ ማለትም የስጋ ጥንታዊ ንጥረ-ነገር"classical element" ውኃ፣ እሳት፣ አፈር እና ነፋስ ነው። ውኃ እርጥበት፣ እሳት ሙቀት፣ አፈር ደረቅነት፤ ነፋስ ቅዝቃዜ አላቸው። ሰው ሙቀት ያለው በውስጡ የእሳት ባሕርይ ስላለው ነው፥ የሰውነት ሙቀት ከ 37.5 ድግሪ ሴሊሽየስ °C ወይም 99.5 ዲግሪ ፋረንሃይት °F በላይ ሲሆን ትኩሳት"fever" ይባላል። "አል-ሑማ" الْحُمَّى ማለት "ትኩሳት" ማለት ነው፥ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ"፦ "ትኩሳት ከእሳት ነው፥ በውኃ አብርዱት" ብለውናል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 28, ሐዲስ 2216
ራፊዕ ኢብኑ ኻሊድ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ትኩሳት ከእሳት ነው፥ በውኃ አብርዱት"*። رَافِعِ بْنِ خَدِيجٍ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ الْحُمَّى فَوْرٌ مِنَ النَّارِ فَأَبْرِدُوهَا بِالْمَاءِ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 59, ሐዲስ 73
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችውም፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ትኩሳት ከእሳት ሙቀት ነው፥ በውኃ አብርዱት"*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ الْحُمَّى مِنْ فَيْحِ جَهَنَّمَ، فَأَبْرِدُوهَا بِالْمَاءِ ‏

እሳት በነበልባል ደረጃ ሳይደርስ በሙቀት ደረጃ ያለው እራሱ የእሳት ክፍል ነው። እንግዲህ እዚህ ዓለም ላይ ያለው እሳት እራሱ ከሰባው የጀሀነም እሳት አንዱ ሲሆን የተቀሩት ስድሳ ዘጠኝ የእሳት ክፍሎት ለከሓዲዎችም መቀጣጫ የእሳት ቅጣት ናቸው፥ ይህቺ የተነደደችው የአላህ እሳት ናት። እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እራሳችሁን እና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ፦
8፥14 *ይህ ቅጣታችሁ ነው ቅመሱትም፡፡ ለከሓዲዎችም "የእሳት ቅጣት" በእርግጥ አለባቸው*፡፡ ذَٰلِكُمْ فَذُوقُوهُ وَأَنَّ لِلْكَافِرِينَ عَذَابَ النَّارِ
104፥6 *የተነደደችው "የአላህ እሳት" ናት*፡፡ نَارُ اللَّهِ الْمُوقَدَةُ
66፥6 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እራሳችሁን እና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا النَّاسُ

አላህ ከእሳት ቅጣት ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዱዓችን ምላሽ የማያገኝበት አምስት ምክንያት አሉ። እነርሱም፦
1ኛ.ዱዓእ ያደረግነው ነገር ሐላል ሳትሆን ሐራም ከሆነ፣
2ኛ. ዱዓእ ያደረግነው ነገር መጥቶ የሚጎዳን ከሆነ፣
3ኛ. ዱዓእ ያደረግነው ነገር በኢማን ካልሆነ፣
4ኛ. አላህ ዱዓእ ካደረግነው ነገር የተሻለ አስቦልን፣
5ኛ. አላህ ትእግስትን እና ጽናትን ሊያስተምረን፣

አላህ ዱዓችንን በኢማን እና በኢኽላስ ይቀበለን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ተማሪው ነቢይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥48 *"መጽሐፍንና ጥበብንም ተውራትንና ኢንጂልንም ያስተምረዋል"*፡፡ وَيُعَلِّمُهُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَالتَّوْرَاةَ وَالْإِنجِيلَ

"ተዕሊም" تَعْلِيم የሚለው ቃል "ዐለመ" عَلَّمَ ማለትም "አስተማረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ትምህርት" ማለት ነው። አምላካችን አላህ "ሙዐሊም" مُعَلِّم ማለትም "አስተማሪ" "ዐዋቂ" ነው፥ ዒሣ ደግሞ አላህ ያስተማረው "ሙዐለም" مُعَلَّم ማለትም "ተማሪ" ነው፦
3፥48 *"መጽሐፍንና ጥበብንም ተውራትንና ኢንጂልንም ያስተምረዋል"*፡፡ وَيُعَلِّمُهُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَالتَّوْرَاةَ وَالْإِنجِيلَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ያስተምረዋል" ለሚለው የገባው ግስ "ዩዐለሙ-ሁ" يُعَلِّمُهُ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። አንድ ማንነትና ምንነት ከሌላ ኑባሬ ከተማረ ፊሽካው ተነፋ፥ ያ ማንነትና ምንነት "ሁሉን ዐዋቂ" አይደለም። በባይብልም ከሔድን ኢየሱስን የላከው ማንነት እንዳስተማረው እራሱ አበክሮና አዘክሮ ተናግሯል፦
ዮሐንስ 8፥28 *"አባቴም "እንዳስተማረኝ" እነዚህን እናገር ዘንድ እንጂ ከራሴ አንዳች እንዳላደርግ በዚያን ጊዜ ታውቃላችሁ*"።
ዮሐንስ 7፥15-17 አይሁድም፦ *"ይህ ሰው ሳይማር መጻሕፍትን እንዴት ያውቃል? ብለው ይደነቁ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ "ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም። ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቢሆን ወይም እኔ ከራሴ የምናገር ብሆን ያውቃል*።

ምን ትፈልጋለህ? የላከው ካስተማረው ውጪ የራሱ ዕውቅት የሌለው አካል እንዴት ይመለካል? "ራስ"own self" የሚለው ድርብ ተውላጠ-ስም ነው፥ "ራሴ" የሚለው ማንነት "እግዚአብሔር" ከተባለው ማንነት በመደብ ተውላጠ-ስም መለየቱ በራሱ ያስተማረው እግዚአብሔር እና ተማሪው ኢየሱስ ሁለት መሆናቸውን ፍንትውና ቁልጭ አርጎ ያሳያል። ከራሱ ምንም ማድረግ የማይችል እና ከተማረው ውጪ ከራሱ ምንም የማይናገር ኢየሱስ የጥበብ፣ የማስተዋል፣ የምክር፣ የኃይል፣ የእውቀት መንፈስ ስላረፈበት በሰዎች ያለውን ነገር ያውቅ ነበር፦
ኢሳይያስ 11፥2 *የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል*።

ፈጣሪ አንድ ነብይ ሲያስነሳ እውቀትን፣ ጥበብን፣ ማስተዋልን ይሰጠዋል፥ በዚህም የሩቅ ሚስጥራትን ያውቃል እንጂ በራሱ ሁሉን ዐዋቂ አይደለም። አንድ ነብይ ከሰው በላይ የሆነ ዕውቀት እንዳለው ከአይሁዳውያን መረዳት ይቻላል፦
ሉቃስ 7፥39 የጠራው ፈሪሳዊም አይቶ፦ *"ይህስ ነቢይ ቢሆን፥ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች እንዴትስ እንደ ነበረች ባወቀ ነበር"* አለ።
ዮሐንስ 4፥17-19 ሴቲቱ መልሳ፦ ባል የለኝም አለችው። ኢየሱስ፦ *ባል የለኝም በማለትሽ መልካም ተናገርሽ፥ አምስት ባሎች ነበሩሽና፥ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ባልሽ አይደለም። በዚህስ እውነት ተናገርሽ" አላት። ሴቲቱም፦ *ጌታ ሆይ! አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያለሁ*"።

አይሁዳውያን አንድ ሰው መጥቶ በልባቸውን ያለውን ቢነግራቸው "ፈጣሪ ነህ" ሳይሆን የሚሉት፥ "ነቢይ ነህ" የሚሉት። ምክንያቱም የልብን የሚያውቅ ፈጣሪ ስለሆነ ያ ሰው ነቢይ ካልሆነ የልብን ማወቅ አይችልም። ኢየሱስ ደግሞ ከራሱ ሳይሆን ከፈጣሪ እየሰማ የሚናገር ሰው ነበረ፥ አክሎም፦ "የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና" ማለቱ በራሱ ዕውቀቱ ሁሉ ከፈጣሪ የሰማው ነው፦
ዮሐንስ 12፥49 *"እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፥ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ*"።
ዮሐንስ 5፥30 *እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ "እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ"*።
ዮሐንስ 8፥26 *"የላከኝ እውነተኛ ነው እኔም "ከእርሱ የሰማሁትን" ይህን ለዓለም እናገራለሁ" አላቸው*።
ዮሐንስ 15፥15 *"ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና"*።
ዮሐንስ 8፥40 ነገር ግን አሁን *ከእግዚእብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው* ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ?

መቼም "እግዚአብሔር ከእግዚአብሔር እየሰማ ሲናገር ነበር" ብላችሁ ዓይናችሁ በጨው አጥባችሁ እንደማታሞኙን ቅቡል ነው። ከእግዚአብሔር እየሰማ የሚናገረው ኢየሱስ ግን እዚሁ አንቀጽ ላይ "ሰው" ነው" ተብሏል። "ነቢይ" የሚለው የግዕዝ ቃል እራሱ "ነበየ" ማለትም "ተናገረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ነባቢ" "ተናጋሪ" ማለት ነው፥ ከፈጣሪ የሚመጣለት ንግግር ደግሞ "ነቢብ" ይባላል። ኢየሱስ ደግሞ ነቢይ ነው፦
ማርቆስ 6፥4 ኢየሱስም፦ *"ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ዘመዶቹ ከገዛ ቤቱም በቀር ሳይከበር አይቀርም* አላቸው።
ማቴዎስ 21፥11 ሕዝቡም፦ *ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ነው* አሉ።
ሉቃስ 24፥19 *በእግዚአብሔር እና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ"*።
ዮሐንስ 9፥17 አንተ ዓይኖችህን ስለ ከፈተ ስለ እርሱ ምን ትላለህ? ደግሞ አሉት። እርሱም፦ *"ነቢይ ነው* አለ።

ይህ አፍጦና አፋጦ፥ አግጦና አንጋጦ የሚታይ እውነት ነው። የናዝሬቱ ኢየሱስ በእግዚአብሔር እና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ነው፥ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ተማሪ ነው። መቼም ይህንን ስትሰሙ ቆሌ ተገፎና ቆሽት አሮ፦ "ሰማይ ተንዶ ሊናጫነኝ ነው፥ ምድር ተከፍቶ ሊውጠኝ ነው" እንደምትሉ እሙን ነው። የክርስትና ደርዛዊ ሥነ-መለኮትን በዘመናዊነት ማዘመን መላላጫና መጋጋጫ በሌለው እፉቅቅ እና እንብርክክ እየተጎተቱ መሔድ ነው። አላህ ሂዳያ ይስጣችሁ፥ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አርባ አራቱ ታቦት

ድሮ ድሮ አርባ አራቱ ታቦት ሲባል አርባ አራት ቅዱሳን ይመስሉኝ ወይም አርባ አራት ታቦታት ያሉ ይመስለኝ ነበር። ቅሉ ግን አርባ አራቱ ታቦት እያሉ የሚጠሯቸው በጎንደር ከተማ ያሉትን አርባ አራት ታቦታት ነው፥ በእነዚህ አርባ አራቱ ታቦታት መሃላ ይፈጽማሉ። አርባ አራቱ ታቦታት ስም ዝርዝር የሚከተለው ናቸው፦
1) ፊት ሚካኤል
2) ፊት አቦ
3) አደባባይ ኢየሱስ
4) ግምጃ ቤት ማርያም
5) እልፍኝ ጊዬርጊስ
6) መድኃኔዓለም
7) ቅዱስ ገብርኤል
8) ጠዳ እግዚአብሔር አብ
9) አባ እንጦንዮስ
10) ደብረብርሃን ሥላሴ
11) አደባባይ ተክለሃይማኖት
12) ሠለስቱ ምእት
13) ልደታ ለማርያም
14) አጣጣሚ ሚካኤል
15) አቡነ ኤውሰጣቴዎስ
16) ቅዱስ ሩፋኤል
17) ደፈጫ ኪዳነምህረት
18) ቁስቋም ደብረ ፀሐይ
19) መጥምቁ ዬሐንስ
20) በኣታ ለማርያም
21) ቅዱስ ቂርቆስ
22) ዬሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
23) አባ ጃሌ ተክለሃይማኖት
24) ፈንጥር ልደታ
25) ደብረ ምጥማቅ ማርያም
26) አባ ዐቢየ እግዚእ
27) ቅዱስ ፋሲለደስ
28) ሐዋርያት
29) ቀሃ ኢየሱስ
30) አርባዕቱ እንሰሳት
31) ጎንደሮች ጊዮርጊስ
32) ጎንደሮች ማርያም
33) አበራ ጊዮርጊስ
34) ብላጅግ ቅዱስ ሚካኤል
35) አባ ሳሙኤል
36) አይራ ሚካኤል
37) ጓራ ዮሐንስ
38) ወረንግቦ ጊዮርጊስ
39) አሮጌ ልደታ
40) አዘዞ ተክለሃይማኖት
41) ምንዝሮ ተክለሃይማኖት
42) ሰራራ ማርያም
43) ዳሞት ጊዮርጊስ
44) ጫጭቁና ማርያም

መሳቅ አይቻልም እዘንላቸው። አላህ ሂዳያህ ይስጣቸው! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ነቢይ እና ረሡል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

22፥52 *”ከመልእክተኛ እና ከነቢይም”* ከአንተ በፊት አንድንም አልላክንም፥ ባነበበ ና ዝም ባለ ጊዜ፣ ሰይጣን በንባቡ ላይ ማጥመሚያን ቃል የሚጥል ቢሆን እንጂ። وَمَا أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلِكَ مِنْ رَسُولٍ وَلَا نَبِيٍّ إِلَّا إِذَا تَمَنَّىٰ أَلْقَى الشَّيْطَانُ فِي أُمْنِيَّتِهِ

"ወሕይ" وَحْى የሚለው ቃል “አውሓ” أَوْحَىٰٓ ማለትም “ገለጠ” ወይም “አወረደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ግልጠተ-መለኮት” ወይም “ግህደተ-መለኮት”Revelation” ማለት ነው። አምላካችን አላህ ወደ ነቢያት ወሕይ ስለሚያወርድ “አውሐይና” أَوْحَيْنَا ማለትም “አወረድን” ብሎ ይናገራል፦
4፥163 *"እኛ ወደ ኑሕ እና ከእርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን፥ ወደ አንተም አወረድን፡፡ ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሓቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ ወደ ነገዶቹም፣ ወደ ዒሳም፣ ወደ አዩብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሃሩን እና ወደ ሱለይማንም አወረድን፡፡ ለዳውድም ዘቡርን ሰጠነው*፡፡ إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَىٰ نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِن بَعْدِهِ ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَعِيسَىٰ وَأَيُّوبَ وَيُونُسَ وَهَارُونَ وَسُلَيْمَانَ ۚ وَآتَيْنَا دَاوُودَ زَبُورًا

አምላካችን አላህ ወደ ነቢያት ወሕይ የሚያወርደው በሦስት አይነት መንገድ ነው፥ አንደኛው መንገድ በራእይ፣ ሁለተኛ መንገድ ከግርዶ ወዲያ፣ ሦስተኛው መንገድ መልአክን በመላክ ነው፦
42፥51 *ለሰው አላህ “በራእይ”፣ ወይም “ከግርዶ ወዲያ”፣ ወይም “መልክተኛን መልአክን” የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን “የሚያወርድለት” ቢሆን እንጅ በገሃድ “ሊያናግረው” ተገቢው አይደለም”*፥ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና። وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ ٱللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَآئِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًۭا فَيُوحِىَ بِإِذْنِهِۦ مَا يَشَآءُ ۚ إِنَّهُۥ عَلِىٌّ حَكِيمٌۭ

እነዚህ ወሕይ የሚወርድላቸው ሰዎች በሁለት ይከፈላሉ፥ እነርሱም "ነቢይ" እና "ረሡል" ይባላሉ። ይህን እሳቤ ነጥብ በነጥብ፥ ጥንልልና ጥንፍፍ አርገን እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"ነቢይ"
"ነቢይ" نَبِيّ የሚለው ቃል "ነበአ” نَبَّأَ ማለትም "አወራ" ወይም "ተናገረ" ከሚል ሥርወ-ቃል ሲሆን "አውሪ" ወይም "ተናጋሪ" ማለት ነው፥ የነቢይ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ነቢዩን" نَبِيُّون ወይም "አንቢያእ" أَنْبِيَاء ነው። አንድ ሰው ከአላህ ዘንድ "ነበእ" نَبَأ ማለትም "የሩቅ ወሬ" ወይም "የሩቅ ንግግር" ሲወርድለት ነቢይ ይሰኛል፦
66፥3 *”ነቢዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሰጠረ ጊዜ አስታውስ፡፡ እርሱንም በነገረች እና አላህ እርሱን ማውራትዋን ባሳወቀው ጊዜ ከፊሉን አስታወቀ፤ ከፊሉንም ተወ፡፡ በእርሱም ባወራት ጊዜ «ይህን ማን ነገረህ?» አለች፡፡ «ዐዋቂው ፥ውስጠ ዐዋቂው ነገረኝ» አላት”*። وَإِذْ أَسَرَّ ٱلنَّبِىُّ إِلَىٰ بَعْضِ أَزْوَٰجِهِۦ حَدِيثًۭا فَلَمَّا نَبَّأَتْ بِهِۦ وَأَظْهَرَهُ ٱللَّهُ عَلَيْهِ عَرَّفَ بَعْضَهُۥ وَأَعْرَضَ عَنۢ بَعْضٍۢ ۖ فَلَمَّا نَبَّأَهَا بِهِۦ قَالَتْ مَنْ أَنۢبَأَكَ هَٰذَا ۖ قَالَ نَبَّأَنِىَ ٱلْعَلِيمُ ٱلْخَبِيرُ

በዚህ አንቀጽ ውስጥ “ማን ነገረህ” ለሚለው ቃል የገባው “መን አንበአከ” مَنْ أَنْبَأَكَْ ሲሆን መልሱ “ነበአኒየ” نَبَّأَنِيَ ማለትም “ነገረኝ” ማለት ነው። “አንበአከ” أَنْبَأَكَْ ሆነ “ነበአኒየ” نَبَّأَنِيَ የሁለቱም ግስ ርቢ “ነበአ” نَبَّأَ ነው። ስለዚህ “ነቢይ” ማለት ሁሉን ዐዋቂው፥ ውስጠ ዐዋቂው አላህ የሚያናግረው እና የሚነግረው ማለት ነው። ከዚያም ባሻገር መመሪያው እራሱ በራሱ የነቢይነት መደብ ውስጥ ነው፦
15፥49 *”ባሮቼን እኔ ይቅርባዩ መሓሪው እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው”*፡፡ نَبِّئْ عِبَادِي أَنِّي أَنَا الْغَفُورُ الرَّحِيمُ

“ንገራቸው” نَبِّئْ ለሚለው ትእዛዛዊ ግስ አሁንም “ነበእ” نَبِّئْ ሲሆን “ነበአ” نَبَّأَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ነው። አንድ ነቢይ ለአማንያን በመልካም ለማዘዝ እና በመጥፎ ለመከልከል ያስጠነቅቃል፥ ለራሱም ዒባዳህ ምን ምን ማድረግ እንዳለበት አላህ ይነግረዋል።

ነጥብ ሁለት
"ረሡል"
"ረሡል" رَسُول የሚለው ቃል "አርሠለ" أَرْسَلَ ማለትም "ላከ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መልእክተኛ" ማለት ነው፥ የረሡል ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሩሡል" رُسُل ነው። አንድ ነቢይ ሕግ ያለበት "ሪሣላህ" رِسَالَة ማለትም "መልእክት" ሲወርድለት ረሡል" ይሆናል፦
5፥48 ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡ በመካከላቸውም *”አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ”*፡፡ እውነቱም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል፡፡ *”ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን”*፡፡ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ ۖ فَٱحْكُم بَيْنَهُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ عَمَّا جَآءَكَ مِنَ ٱلْحَقِّ ۚ لِكُلٍّۢ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةًۭ وَمِنْهَاجًۭا

"ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። "እናንተ" የተባሉት መልእክተኞቹ ናቸው፥ እዚህ አንቀጽ ላይ “ሕግ” ለሚለው ቃል የገባው “ሺርዓህ” شِرْعَة መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። “መንገድ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሚንሃጅ” مِنْهَاج ሲሆን “መንሃጅ” مَنْهَج ማለት ነው። አምላካችን አላህ”ﷻ” ለሁሉም መልእክተኞች በዘመናቸው ሸሪዓህ እና መንሃጅ ማድረጉን ያሳያል። ረሡል ለአማንያን እና ለከሃድያን ለማስጠንቀቅ በሸሪዓህ ይላካል፦
22፥52 *”ከመልእክተኛ እና ከነቢይም”* ከአንተ በፊት አንድንም አልላክንም፥ ባነበበ ና ዝም ባለ ጊዜ፣ ሰይጣን በንባቡ ላይ ማጥመሚያን ቃል የሚጥል ቢሆን እንጂ። وَمَا أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلِكَ مِنْ رَسُولٍ وَلَا نَبِيٍّ إِلَّا إِذَا تَمَنَّىٰ أَلْقَى الشَّيْطَانُ فِي أُمْنِيَّتِهِ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ነቢይ" نَبِيّ እና "ረሡል" رَسُول በሚሉት የማዕረግ ስሞች መካከል “ወ” وَ ማለትም “እና” የሚል መስተጻምር አለ፥ ይህም ነቢይ እና ረሡል ሁለት የተለያየ ደረጃ መሆኑን ቁልጭና ፍንትው አድርጎ ያሳያል። በተጨማሪም “አልላክንም” የሚለው አጽንዖታዊ ቃል “ቢሆን እንጂ” በሚል አፍራሽ ቃል በመምጣቱ ነብይ በመልካም እንዲያዝ በመጥፎ እንዲከለክል ለአማንያን እንደተላከ ሁሉ መልእክተኛ ደግሞ ለአማንያንና ለከሃድያን ለማስጠንቀቅና ለማብሰር ይላካል። መልእክተኛ መልክተኛ ለመሆን ነቢይነትን አሳልፎ ስለሆነ መልእክተኛ ሁሉ ነቢይ ነው፥ ነቢይ ሁሉ ግን መልእክተኛ አይደለም። ምክንያቱም ሪሣላ ሳይወርድለት ነቢይ ብቻ ሆኖ የሚቀር አለ፥ ለምሳሌ አደም የመጀመሪያው ነቢይ ሲሆን ኑሕ ደግሞ የመጀመሪያው ረሡል ነው፦
ኢማም አሕመድ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 1781
አቡ ዘር እንደተረከው፦ *”የአላህ ነቢይ”ﷺ” ሆይ የመጀመሪያው ነቢይ ማን ነው? ብሎ አለ። እርሳቸውም፦ “አደም ነው” አሉ። እርሱም፦ “እርሱ ነቢይ ነበርን? ብሎ አለ። እርሳቸውም፦ “አዎ” አሉ”*። عَن أَبُو ذَرٍّ قُلْتُ : يَا نَبِيَّ اللَّهِ، فَأَيُّ الْأَنْبِيَاءِ كَانَ أَوَّلَ. قَالَ : ” آدَمُ “. قَالَ : قُلْتُ : يَا نَبِيَّ اللَّهِ، أَوَنَبِيٌّ كَانَ آدَمُ ؟ قَالَ : ” نَعَمْ،
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4476
አነሥ እንደተረከው፦ "ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *"......(አደምም)፦ “ኑህ ጋር ሂዱ! እርሱ በምድር ላይ የተላከ የመጀመሪያው መልእክተኛ ነው፥ ወደ ምድር ባለቤቶች አላህ ልኮታል” ይላቸዋል"*። ائْتُوا نُوحًا فَإِنَّهُ أَوَّلُ رَسُولٍ بَعَثَهُ اللَّهُ إِلَى أَهْلِ الأَرْضِ‏.‏

ነጥብ ሦስት
"መደምደሚያ"
ነቢያችን”ﷺ” የነቢያት መደምደሚያ ናቸው። ከነቢያችን”ﷺ” በኃላ ነቢይ ብቻ ሳይሆን ረሡልም አይመጣም። ነቢይነት እና መልእክተኝነት በእርሳቸው ተደምድሟል፦
33:40 ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድንም ሰው አባት አይደለም። ነገር ግን የአላህ መልክተኛ እና *”የነቢያት መደምደሚያ” ነው"*፥ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው። مَا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِنْ رِجَالِكُمْ وَلَٰكِنْ رَسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 2272
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”በእርግጥም መልእክተኛነት እና ነቢይነት ተዘግቷል። ከእኔ በኃላ መልእክተኛም ነቢይም የለም*። حَدَّثَنَا أَنَسُ بْنُ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ” إِنَّ الرِّسَالَةَ وَالنُّبُوَّةَ قَدِ انْقَطَعَتْ فَلاَ رَسُولَ بَعْدِي وَلاَ نَبِيَّ

ታዲያ "ነብይ እና ረሱም ከነቢያችን”ﷺ” በኃላ የለም" ከተባለ “ነብይ ነኝ” ወይም “መልእክተኛ ነኝ” ብለው የተነሱት ሚርዛ ጉላም አሕመድ የቃዲያኒይ መስራች፣ ሚርዛ ሑሤን ዐሊይ የባሃኢያህን መስራች፣ ዶክተር ራሺድ ኸሊፋክ የቁርኣንያህ መስራች ምንድን ናቸው? ሲባል ኃሣዌ ነብይ እና መልእክተኛ ናቸው። “አድ-ደጃል” الدَّجَّال የሚለው ቃል “ደጀለ” دَجَلَ ማለትም “አጭበረበረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “አጭበርባሪ” ወይም “ሐሳዌ” ማለት ነው። እነዚህ ወደ ሠላሳ የሚቃረቡ ደጃሎች “እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ” ወይም “እኔ የአላህ ነብይ ነኝ” ብለው ይነሳሉ፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 54, ሐዲስ 108
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “የመጨረሻይቱ ሰአት አትቆምም *ሠላሳ የሚቃረቡ ደጃሎች ቀጣፊዎች ተነስተውስ፦ “እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ” ብለው ቢናገሩ ቢሆን እንጂ”*። عَنْ أَبِي، هُرَيْرَةَ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ” لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يُبْعَثَ دَجَّالُونَ كَذَّابُونَ قَرِيبٌ مِنْ ثَلاَثِينَ كُلُّهُمْ يَزْعُمُ أَنَّهُ رَسُولُ اللَّهِ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 13
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *ከእኔ ዑማ ውስጥ ሠላሳ የሚያህሉ ቀጣፊዎች፦ “ነቢይ ነኝ” ብለው ይነሳሉ፥ ነገር ግን እኔ የነቢያት መደምደሚያ ነኝ። ከእኔ በኃላ ነቢይ የለም”*። وَحَتَّى تَعْبُدَ قَبَائِلُ مِنْ أُمَّتِي الأَوْثَانَ وَإِنَّهُ سَيَكُونُ فِي أُمَّتِي كَذَّابُونَ ثَلاَثُونَ كُلُّهُمْ يَزْعُمُ أَنَّهُ نَبِيٌّ وَأَنَا خَاتَمُ النَّبِيِّينَ لاَ نَبِيَّ بَعْدِي

"አሏሁ አዕለም" اَللّٰهُ أَعْلَم‎

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መለከት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

39፥68 *በቀንዱም ይነፋል፥ በሰማያት ውስጥ ያለው ፍጡር እና በምድርም ውስጥ ያለው ፍጡር ሁሉ አላህ የሻው ሲቀር በድንጋጤ ይሞታል፡፡ ከዚያም በእርሱ ሌላ መንነፋት ይነፋል፥ ወዲያውም እነርሱ የሚሠራባቸውን የሚጠባበቁ ኾነው ቋሚዎች ይኾናሉ*፡፡ وَنُفِخَ فِي الصُّورِ فَصَعِقَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَمَن فِي الْأَرْضِ إِلَّا مَن شَاءَ اللَّهُ ۖ ثُمَّ نُفِخَ فِيهِ أُخْرَىٰ فَإِذَا هُمْ قِيَامٌ يَنظُرُونَ

“ሱር” صُّور የሚለው ቃል “ሶወረ” صَوَّرَ ማለትም “ቀረፀ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ቅርፅ" ማለት ነው፥ ይህ ቅርፅ ነጋሪት የሚጎሰምበት የመለከት ቀንድ ነው። "ቀርን" قَرْن ማለት "ቀንድ" ማለት ሲሆን ለመለከት የሚቀረጽ ቀንድ ነው፦
ሡነን አቢዳውድ መጽሐፍ 42, ሐዲስ 147
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፦ "ነቢዩም አሉ፦ *"ሱር የሚነፋበት ቀንድ ነው"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ "‏ الصُّورُ قَرْنٌ يُنْفَخُ فِيهِ ‏"‏

በፍርድ ቀን ጠሪው መልአክ ወደ አስደንጋጭ ነገር በቀንዱ በሚጠራበትን ቀን በሰማያት ውስጥ ያለው ፍጡር እና በምድርም ውስጥ ያለው ፍጡር ሁሉ አላህ የሻው ሲቀር በድንጋጤ ይሞታል፦
53፥6 ከእነርሱም ዙር፡፡ *ጠሪው መልአክ ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን አስታውስ*፡፡ فَتَوَلَّ عَنْهُمْ ۘ يَوْمَ يَدْعُ الدَّاعِ إِلَىٰ شَيْءٍ نُّكُرٍ
39፥68 *በቀንዱም ይነፋል፥ በሰማያት ውስጥ ያለው ፍጡር እና በምድርም ውስጥ ያለው ፍጡር ሁሉ አላህ የሻው ሲቀር በድንጋጤ ይሞታል፡፡ ከዚያም በእርሱ ሌላ መንነፋት ይነፋል፥ ወዲያውም እነርሱ የሚሠራባቸውን የሚጠባበቁ ኾነው ቋሚዎች ይኾናሉ*፡፡ وَنُفِخَ فِي الصُّورِ فَصَعِقَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَمَن فِي الْأَرْضِ إِلَّا مَن شَاءَ اللَّهُ ۖ ثُمَّ نُفِخَ فِيهِ أُخْرَىٰ فَإِذَا هُمْ قِيَامٌ يَنظُرُونَ

"አስ-ሶዕቃህ" الصَّعْقَةُ የሚለው ቃል "ሶዒቀ" صَعِقَ ማለት "እራሱ ሳተ" ወይም "ምንም ሆነ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "እራስን መሳት" ወይንም "ምንም መሆን" ማለት ነው። ፍጥረት በትንሳኤ ቀን ፊተኛው መነፋት ሲነፋ እራስን ይስታል ወይም ምንም ይሆናል፦
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 658
አውሥ ኢብኑ አውሥ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ከቀናችሁ በላጩ ቀን የጁሙዓህ ቀን ነው፥ በዚያ ቀን አደም ተፈጠረ፥ በዚያ ቀን ሞተ። በዚያ ቀንም መለከት ይነፋል፥ ሁሉ በድንጋጤ ይሞታል”*። عَنْ أَوْسِ بْنِ أَوْسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ إِنَّ مِنْ أَفْضَلِ أَيَّامِكُمْ يَوْمَ الْجُمُعَةِ فِيهِ خُلِقَ آدَمُ وَفِيهِ قُبِضَ وَفِيهِ النَّفْخَةُ وَفِيهِ الصَّعْقَةُ

"አኽራ" أُخْرَىٰ ማለት "ሌላ" ማለት ሲሆን "ሌላ መንነፋት" የሚለው ሁለተኛውን መነፋት ነው፥ በሁለቱ ማለትም በፊተኛው መነፋት እና በኃለኛው መነፋት መካከል ያለው ክፍተት አርባ ነው፦
ኢማም ቡኻሪ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4814
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በሁለቱ መነፋት ያለው ክፍተት አርባ ነው"*። قَالَ سَمِعْتُ أَبَا هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ بَيْنَ النَّفْخَتَيْنِ أَرْبَعُونَ ‏"‌‏

ይህ አርባ ቀን ይሁን ወይም ወር አሊያም ዓመት ምንም አልተገለጸም። በሁለተኛው መነፋት የሚሠራባቸውን የሚጠባበቁ ኾነው ቋሚዎች ይኾናሉ፥ “ቂያማህ” قِيَٰمَة የሚለው ቃል “ቃመ” قَامَ ማለትም “ተነሣ” “ቆመ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ትንሣኤ” ማለት ነው። ጠሪው መልአክ በሚጠራበት ቀን ከመቃብራቸው ይወጣሉ፦
50፥41 *"የሚነገርህን አዳምጥም፡፡ ጠሪው ከቅርብ ስፍራ በሚጠራበት ቀን ከመቃብራቸው ይወጣሉ*፡፡ وَاسْتَمِعْ يَوْمَ يُنَادِ الْمُنَادِ مِن مَّكَانٍ قَرِيبٍ
50፥42 *ጩኸቲቱን በእውነት የሚሰሙበት ቀን ያ ከመቃብር የመውጫው ቀን ነው*፡፡ يَوْمَ يَسْمَعُونَ الصَّيْحَةَ بِالْحَقِّ ۚ ذَٰلِكَ يَوْمُ الْخُرُوجِ
36፥51 *"በቀንዱም ይነፋል፥ ወዲያውኑም እነርሱ ከመቃብሮቻቸው ወደ ጌታቸው በፍጥነት ይገሰግሳሉ*፡፡ وَنُفِخَ فِي الصُّورِ فَإِذَا هُم مِّنَ الْأَجْدَاثِ إِلَىٰ رَبِّهِمْ يَنسِلُونَ
ይህ በመለከት ሁለቱን መነፋት የሚነፋው መልአክ "የመለከት ባለቤት" ነው፥ "ሷሒብ" صَاحِب ማለት "ጓድ" ወይም "ባለቤት" ማለት ነው፥ ዩኑስ "ሷሒቡል ሑት" صَاحِب الْحُوت ሲባል "የዓሣው ባለቤት" እንደሚባል ሁሉ ይህ መልአክ "ሷሒቡ አስ-ሱር" صَاحِب الصُّور ማለት "የመለከት ባለቤት" ተብሏል፦
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 32, ሐዲስ 31
አቢ ሠዒድ አል-ኹድሪይ እንደተረከው፦ *"የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" "ሷሑበል ሱርን" አውስተዋል። በቀኙ ጂብሪል፥ በግራው ሚካኢል መሆናቸውን ተናግረዋል"*። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ قَالَ ذَكَرَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم صَاحِبَ الصُّورِ فَقَالَ ‏ "‏ عَنْ يَمِينِهِ جِبْرَائِلُ وَعَنْ يَسَارِهِ مِيكَائِلُ ‏"‏

ይህ ሷሒቡ አስ-ሱር በሌላ ሐዲስ "ኢሥራፊል" ተብሏል፥ “ኢሥራፊል” إِسْرَافِيل ማለት “ሩፋኤል” ማለት ሲሆን ከአራቱ የመላእክት አለቃ አንዱ ነው፦
ሡነን አን-ነሣኢ መጽሐፍ 50 , ሐዲስ 92
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ ይሉ ነበር፦ *"አላህ ሆይ! የጂብሪል እና የሚካኢል ጌታ፣ የኢሥራፊል ጌታ በአንተ ከእሳት ቅጣት እና ከቀብር ቅጣት እጠበቃለው"*። عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّهَا قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ اللَّهُمَّ رَبَّ جِبْرَائِيلَ وَمِيكَائِيلَ وَرَبَّ إِسْرَافِيلَ أَعُوذُ بِكَ مِنْ حَرِّ النَّارِ وَمِنْ عَذَابِ الْقَبْرِ

ይህ አቧራ የሚያስነሳ ጥያቄ አልነበረም። በባይብልም ቢሆን ወይም በትውፊት በፍርድ ቀን ሰባት የመላእክት አለቆች ሚካኤል፣ ገብርኤል፣ ሩፋኤል፣ ኡራኤል፣ ራጉኤል፣ ፋኑኤል(ጀርምኤል)፣ ሳቁኤል(ሰራኤል) ሰባት መለከት ተሰቷቸው ነጋሪት እንደሚነፉ ይናገራል፦
ማቴዎስ 24፥31 *"መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ"*።
ራእይ 8፥2 *"በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፥ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው*።
ራእይ 8፥6 *"ሰባቱንም መለከት የያዙ ሰባቱ መላእክት ሊነፉ ተዘጋጁ"*።
ዳንኤል 10፥13 *"ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ"*።
ኤፌሶን 3፥10 *"በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት "አለቆች" እና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ"*።

ሚካኤል ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ነው፥ ሌሎች የመላእክት ስላሉ "ዋነኞቹ አለቆች" ብሎ አስቀምጦታል። "አለቆች" የሚለው የግሪኩ ቃል "አርኬስ" ἀρχαῖς ሲሆን "አርኬ" ἄρχω ማለትም "አለቃ" ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ በመላእክት አለቃ ድምፅ የፈጣሪ መለከት ሲነፋ ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ፦
1ኛ ቆሮንቶስ 15፥52 *"መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ"*፥ እኛም እንለወጣለን።
1 ተሰሎንቄ 4፥16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ *"በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ*።

መልአክ በበድን አካል ላይ መንፋቱ ስትገረሙበት ነፋስ በበድን ላይ እፍ ብሎ እንደሚነፋ መነገሩ ተደመሙበት፦
ሕዝቅኤል 37፥9 እርሱም፦ *የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ ለነፋስ ትንቢት ተናገር! ለነፋስም፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፋስ ሆይ! ከአራቱ ነፋሳት ዘንድ ና፥ እነዚህም የተገደሉት በሕይወት ይኖሩ ዘንድ እፍ በልባቸው፡ በል! አለኝ*።

ነፋስ በተገደሉት በድን ላይ "እፍ" የሚለው እንዴት ነው? ይህንን መመለስ ከቻላችሁ ኢሥራፊል እንዴት እንደሚነፋ መረዳት ቀላል ነው። አላህ ሂዳያ ይስጣችሁ፥ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም