ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.3K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
"ልጁ" የሚል ግሪኩ ላይ የለም። ዐውዱ ስለ አብ ስለሚናገር አንደኛችሁን እንደ ቄስ ተክለ-ማርያም ገዛኸኝ ደሙ የአብ ነው ብላችሁ እረፉት። "ውድ" የሚለውን "በውድ ልጁ" በሚል እንደተረዳችሁት፥ "ገዛ" የሚለውን "በገዛ ልጁ" በሚል ተረዱት።
ሲያረብብ የሐዋርያት ሥራ "ሄን" ἣν ማለትም "እርሱ" የሚለው አንጻራዊ ተውላጠ-ስም "ክርስቶስ" የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው፦
1 ጴጥሮስ 1፥19 *በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ*።

አየህ "በገዛ ደሙ የዋጃትን" የሚለውን "በክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ" በሚለው ይፈታል፥ በቀላሉ ክርስቶስ የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን በገዛ ደሙ መዋጀቱን ያሳያል። ክርስቶስ ደግሞ እግዚአብሔር ሳይሆን የእግዚአብሔር ነው፥ እግዚአብሔር ለክርስቶስ ራስ ነው፦
1ኛ ቆሮንቶስ 3፥23 *ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው*።
1ኛ ቆሮንቶስ 11፥3 *የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ*።

ጳውሎስ፦ "አንድ እግዚአብሔር አለ፥ በእግዚአብሔር እና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው" ብሎናል፥ ደሙ የእግዚአብሔር ሳይሆን በመካከለኛ ያለው የሰው ደም ነው፦
1 ጢሞቴዎስ 2፥5 *አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔር እና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው*።
ዕብራውያን 12፥23 *የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት "ደም" ደርሳችኋል*።

የሚገርመው እኮ "ቴኦዩ" Θεοῦ ማለትም "የእግዚአብሔርን" ቤተክርስቲያን የሚል የግሪክ እደ-ክታባት እንዳለ ሁሉ "ኩርዮዩ" Κυρίοῦ ማለትም "የጌታን" ቤተክርስቲያን የሚል አለ። American Standard Version በበኩሉ በገዛ ደሙ የዋጃትን የጌታን ቤተ ክርስቲያን" ብለው ተርጉመውታል፦
Acts 20:28 (ASV) The church of the *Lord* which he purchased with his own blood.

የ 1980 አዲስ ትርጉም፦ "ጌታ በገዛ ደሙ የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ" ብለው ተርጉመውታል፦
የሐዋርያት ሥራ 20፥28 *ጌታ በገዛ ደሙ የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ*።

አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ ላይም ፦ "ብዙ የጥንት ቅጆች የጌታን" እንዳሉት እና "በገዛ ልጁ ደም ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፥ የገዛ የሚለው ቃል ተወዳጅነትን ለመግለጽ የገባ ቃል ነው። ይህም ልጁን ያመለክታል" ብሎ ተናግሯል። ይህ የትርጉም ሥራ ሢሠራ ከተሳተፉት መካከል ምራቅ የዋጠ ተወያይ የሚባለው ዶክተር ተስፋዬ ሮበሌ ሲሆን፥ ግን እርሱ፦ "በገዛ ደሙ የዋጃትን የጌታን ቤተ ክርስቲያን" እና "በገዛ ልጁ ደም የዋጃትን የእግዚአብሔ ቤተ ክርስቲያን" የሚል የለም" ሲል ቀጥፏል። ብዙ ጊዜ ይዋሻል፥ ወትሮም አባይ መዋሸት ልምዱ ነው።
በጥቅሉ የጳውሎስ ንግግር ላይ "የልጅ ደም" ወይም "መዋጀት" አሊያም "ልጅ" የእኛ የሙሥሊሞች እሳቤ አይደለም። ዋናው ነጥብ የሐዋርያት ሥራ 20፥28 ላይ ጳውሎስ "እግዚአብሔር ደም አለው" አላለም የሚል ነው። ፈጣሪ የፍጡር ደም ጥገኝነት አይጠይቅም፥ ፍጡሩን ኢየሱስ ፈጣሪ ነው ማለት ክህደት ነው፦
5፥17 *እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ*፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሊቃውንት እና መነኮሳት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

9፥31 *ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊያመልኩ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ሊቃውንቶቻቸውን እና መነኮሳታቸውን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፥ እንዲሁ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ያዙ። ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው*፡፡ اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا إِلَـٰهًا وَاحِدًا ۖ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ سُبْحَانَهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ

ሚሽነሪዎች፦ "እኛ ሊቃውንቶቻችንን እና መነኮሳቶቻችንን አማልክት አድርገን አልያዝን፥ እነርሱን አምልከንም አናውቅም። ስለዚህ ቁርኣን ያቀረበብን ክስ አግባብ አይደለም" ይላሉ። በኢሥላም ያሉ የመስኩ ሊሒቃን፦ “ውኃን ከጡሩ፥ ነገርን ከሥሩ” ይላሉና እኛም ከሥሩ ይህንን ተጻራሪ ምልከታ እንመልከት።
"ሐብር" حَبْر ወይም "ሒብር" حِبْر ማለት "ምሁር" "ሊቅ" "ዐዋቂ" ማለት ነው፥ የሐብር ወይም የሒብር ብዙ ቁጥር ደግሞ "አሕባር" أَحْبَار ሲሆን "ምሁራን" "ሊቃውንት" "ሊሒቃን" ማለት ነው። እነዚህም ምሁራን የአይሁዳውያን ምሁራን ናቸው፦
26፥197 *የእስራኤል ልጆች ሊቃውንት የሚያውቁት መኾኑ ለእነርሱ(ለመካ ከሓዲዎች) ምልክት አይኾናቸውምን?* أَوَلَمْ يَكُن لَّهُمْ آيَةً أَن يَعْلَمَهُ عُلَمَاءُ بَنِي إِسْرَائِيلَ

"ዐሊም" عَلِيم ማለት "ዐዋቂ" ማለት ነው፥ እዚህ አንቀጽ ላይ የተቀመጠው የዐሊም ብዙ ቁጥር "ዑለማእ" عُلَمَاء ሲሆን "ሊቃውንት" ማለት ነው።
"ራሂብ" رَاهِب ማለት "መነኩሴ" ማለት ነው፥ የራሂብ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሩህባን" رُهْبَان ሲሆን "መነኮሳት" ማለት ነው። እነዚህም መነኮሳት የክርስቲያን መነኮሳት ናቸው፦
57፥27 ከዚያም በዱካዎቻቸው ላይ መልክተኞቻችንን አስከታተልን፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሳንም አስከተልን፡፡ ኢንጂልንም ሰጠነው፡፡ በእነዚያም በተከተሉት ሰዎች ልቦች ውሰጥ መለዘብንና እዝነትን አደረግን፡፡ *”አዲስ የፈጠሩዋትንም ምንኩስና በእነርሱ ላይ አልጻፍናትም፡፡ ግን የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ ፈጠሩዋት፡፡ ተገቢ አጠባበቋንም አልጠበቋትም*”፡፡ ከእነርሱም ለእነዚያ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጠናቸው፡፡ ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፡፡ ثُمَّ قَفَّيْنَا عَلَىٰ آثَارِهِم بِرُسُلِنَا وَقَفَّيْنَا بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ وَآتَيْنَاهُ الْإِنجِيلَ وَجَعَلْنَا فِي قُلُوبِ الَّذِينَ اتَّبَعُوهُ رَأْفَةً وَرَحْمَةً وَرَهْبَانِيَّةً ابْتَدَعُوهَا مَا كَتَبْنَاهَا عَلَيْهِمْ إِلَّا ابْتِغَاءَ رِضْوَانِ اللَّهِ فَمَا رَعَوْهَا حَقَّ رِعَايَتِهَا ۖ فَآتَيْنَا الَّذِينَ آمَنُوا مِنْهُمْ أَجْرَهُمْ ۖ وَكَثِيرٌ مِّنْهُمْ فَاسِقُونَ

ክርስቲያኖች አዲስ የፈጠሩዋትንም ምንኩስና አላህ በእነርሱ ላይ አልደነገገም፥ ግን የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ ፈጠሩዋት።
እዚህ ድረስ ከተግባባን ድንጋጌ ውስጥ አምስት ሕግጋት አሉ፥ እነርሱም፦
1ኛ. “ፈርድ” فَرْد‎ ማለትም “የታዘዘ” ግዴታ ነው።
2ኛ. “ሙስተሐብ” مُسْتَحَبّ‎ ማለትም “የተወደደ” ሡናህ ነው።
3ኛ. “ሙባሕ” مُبَاح‌‌‎ ማለትም “የተፈቀደ” ሐላል ነው።
4ኛ. “መክሩህ” مَكْرُوه‎ ማለትም “የተጠላ” ድርጊት ነው።
5ኛ. “ሐራም” حَرَام ማለትም “የተከለከለ” ድርጊት ነው።
አንድን ነገር ፈድር፣ ሙስተሐብ፣ ሙባሕ፣ መክሩህ፣ እና ሐራም ማለት የሚችለው አላህ ብቻ ሆኖ ሳለ የአይሁዳውያን ሊቃውንት እና የክርስትና መነኮሳት ሐላሉን ሐራም፥ ሐራሙን ሐላል በማድረግ ሕግጋትን ከገዛ ዝንባሌአቸው ደነገጉ፦
9፥31 *ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊያመልኩ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ሊቃውንቶቻቸውን እና መነኮሳታቸውን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፥ እንዲሁ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ያዙ። ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው*፡፡ اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا إِلَـٰهًا وَاحِدًا ۖ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ سُبْحَانَهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ

ታላቁ ሙፈሢር ኢብኑ ከሲር "አማልክት አድርገው ያዙ" ማለት ምን ማለት እንደሆነ በዚህ ሐዲስ ፈሥሮታል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3378
ዐዲይ ኢብኑ ሓቲም እንደተረከው፦ *"ወደ ነቢዩም”ﷺ” ስመጣ በአንገቴ ዙሪያ የወርቅ መስቀል ነበረኝ፥ እርሳቸውም፦ "ይህንን ጣዖት ከአንተ አስወግድ" አሉ። ሱረቱል በራኣህ "ሊቃውንቶቻቸውን እና መነኮሳታቸውን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ" የሚለው ሲነበብ ሰማዋቸው። እርሳቸውም፦ ለእነርሱ አያመልኳቸውም፥ ነገር ግን ሐላል ባደረጉላቸው ጊዜ ሐላል አርገው ይቀበሉታል። ሐራም ባደረጉላቸው ጊዜ ሐራም አርገው ይቀበሉታል" አሉ*። عَنْ عَدِيِّ بْنِ حَاتِمٍ، قَالَ أَتَيْتُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم وَفِي عُنُقِي صَلِيبٌ مِنْ ذَهَبٍ ‏.‏ فَقَالَ ‏"‏ يَا عَدِيُّ اطْرَحْ عَنْكَ هَذَا الْوَثَنَ ‏"‏ ‏.‏ وَسَمِعْتُهُ يَقْرَأُ فِي سُورَةِ بَرَاءَةََ ‏:‏ ‏(‏ اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِنْ دُونِ اللَّهِ ‏)‏ قَالَ ‏"‏ أَمَا إِنَّهُمْ لَمْ يَكُونُوا يَعْبُدُونَهُمْ وَلَكِنَّهُمْ كَانُوا إِذَا أَحَلُّوا لَهُمْ شَيْئًا اسْتَحَلُّوهُ وَإِذَا حَرَّمُوا عَلَيْهِمْ شَيْئًا حَرَّمُوهُ
መስቀል በአንገት ላይ ማድረግ ከመነኮሳት የመጣ ትእዛዝ እንጂ ከአላህ ዘንድ አይደለም። ሲጀመር "ረብ" رَبّ የሚለው ቃል "ረበ" رَبَّ ማለትም "አዘዘ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጌታ" ወይም "አዛዥ" ማለት ነው፥ የረብ ብዙ ቁጥር ደግሞ "አርባብ" أَرْبَاب ሲሆን "ጌቶች" ማለት ነው። "አላህ ብቻውን ትእዛዝ አውጪ ነው" ብሎ አላህ ከፍጡራን መነጠል "ተውሒደ አር-ሩቡቢያህ" تَوْحِيد الرُبُوبِيّة ነው፥ "ሩቡቢያህ" رُبُوبِيّة ማለት በራሱ "ጌትነት" ማለት ነው። "ያልታዘዙ ሲኾኑ" የሚለው ይህንኑ ነው፥ ነቢያችን"ﷺ" ሆኑ አሚሮቻችን አላህ ባዘዘው ያዛሉ፥ በከለከለው ይከለክላሉ እንጂ የእራሳቸው ድንጋጌ አያወጡም። ነገር ግን አይሁዳውያን ሊቃውንቶቻቸውን ክርስቲያኖች መነኮሳታቸውን ከአላህ ሌላ ድንጋጌ በመቀበል ጌቶች አድርገው ያዙ። "አያመልኳቸውም" የሚለው ይሰመርበት፥ አላህ በአምልኮ ከፍጡራን መነጠል "ተውሒደል ኡሉሂያህ" تَوْحِيد الأُلُوهِيَّة ነው፥ "ኡሉሂያህ" أُلُوهِيَّة ማለት በራሱ "አምላክነት" ማለት ነው። ተውሒድ ትክክለኛ የሆነች ቃል ናት፥ ተውሒደል ኡሉሂያህ "አላህን እንጅ ሌላን ላናመልክ" ነው፣ ተውሒደ አር-ሩቡቢያህ "ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አርባብ አድርጎ ላይዝ" ነው፦
3፥64 *የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ እርሷም አላህን እንጅ ሌላን ላናመልክ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አርባብ አድርጎ ላይዝ ነው"* በላቸው፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ تَعَالَوْا إِلَىٰ كَلِمَةٍ سَوَاءٍ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا اللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِ شَيْئًا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ ۚ

ነገር ግን መደንገግ የሚችለው አላህ ብቻ ሆኖ ሳለ ሌላ ማንነት የደነገገውን ድንጋጌ ማድረግ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ ሕግን የሚደነግግልን አርባብ አድርጎ መያዝ ነው፥ ይህ በአላህ ጌትነት ላይ ማሻረክ ነው፦
42፥21 ከሃይማኖት *አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነርሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አሏቸውን?* أَمْ لَهُمْ شُرَكَاءُ شَرَعُوا لَهُم مِّنَ الدِّينِ مَا لَمْ يَأْذَن بِهِ اللَّهُ

"ሸሪክ" شَرِيك ማለት "ተጋሪ" ማለት ነው፥ የሸሪክ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሹረካእ" شُرَكَاء ሲሆን "ተጋሪዎች" ማለት ነው፥ አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ነገር ሐላል ማድረግ ለእነርሱ የደነገጉ በአላህ ሐቅ ላይ ተጋሪዎች አሏቸው። ለዚህ ነው "ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው" ነው ያለው፥ ስለዚህ "ሊቃውንቶቻቸውን እና መነኮሳታቸውን በአላህ ላይ በማጋራት ጌቶች አድርገው ያዙ ማለት በዚህ ስሌት እንረዳዋለን።
ሲቀጥል "ጌቶች" የሚለው "አማልክት" ተብሎ ቢቀመጥም "አምላክ አድርጎ መያዝ" ማለት ያንን ማንነት ሆነ ምንነት በቀጥታ ማምለክ ብቻ አይደለም። ምክንያቱም ለአላህ የሚገባውን ሐቅ ለዝንባሌ መስጠት በራሱ አምላክ አድርጎ መያዝ ከሆነ ለአላህ የሚገባውን ሐቅ ለሊቃውንቶቻቸውን እና ለመነኮሳታቸውን መስጠት አምላክ አድርጎ መያዝ ነው፦
25፥43 *ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን? አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትኾናለህን?* أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا
12፥53 «ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ *ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና*፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡ وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ

መቼም ዝንባሌውን በቀጥታ "አምላኬ" እያለ የሚያመልክ ፍጡር የለም። ዝንባሌ ከነፍሢያችን ነው፥ ነፍሢያህ አላህ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በሐራም ነገር በእርግጥ አዛዥ ናት። ነፍሢያህ ሐራሙን በማዘዟ ዝንባሌን አምላክ አድርጎ እንደሚያዝ ሁሉ እነርሱም ሊቃውንቶቻቸውን እና መነኮሳታቸውን በሐራም በመታዘዝ፥ በሐላል በመከልከል አምላክ አድርገው ይዘዋል። ከላይ የቀረበው ተጻራሪ ምልከታ በዚህ የሙግት አግባብ ሐቁን አውጥተናል፥ ባጢል በሐቅ ፊት እሳት የነካው ሰም፣ ፀሐይ ያየው ቅቤ፣ ነፋስ የጎበኘው አቧራ ይሆናል፦
17፥81 በልም *«እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»* وَقُلْ جَآءَ ٱلْحَقُّ وَزَهَقَ ٱلْبَٰطِلُ ۚ إِنَّ ٱلْبَٰطِلَ كَانَ زَهُوقًۭا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኢና ሊሏሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን

የዐሊማችን የሼኽ ኢብራሂም ሲራጅ ከዱንያ መለየት የተሰማን ጥንቅ ሀዘን በቃላት የሚገለጽ አይደለም። ይህ ጥልቅ ሀዘን ሲነካን፦ "ኢና ሊሏሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን" إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُون ብለናል፦
2፥156 እነዚያን መከራ በነካቻቸው ጊዜ «እኛ ለአላህ ነን፥ እኛም ወደ እርሱ ተመላሾች ነን» የሚሉትን አብስር፡፡ الَّذِينَ إِذَا أَصَابَتْهُم مُّصِيبَةٌ قَالُوا إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ

አምላካችን አላህ ለቤተሰባቸው፣ ለተማሪዎቻቸው እና ለሚወዷቸው ሁሉ ጽናቱን፣ መጽናናቱን እና ትእግስቱ ይስጠን። ሃዘናችንን አጅር የምናገኝበት ያርግልን። እርሳቸውንም ጀነቱል ፊርደውሥ ይወፍቃቸው! አሚን።
ተስዊር

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

59፥24 *እርሱ አላህ ፈጣሪው፣ አስገኚው፣ "ቅርፅን አሳማሪው" ነው፡፡ ለእርሱ መልካሞች ስሞች አሉት*፡፡ هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ

አምላካችን አላህ በማኅፀን ውስጥ እንደሚሻ አርጎ የሚቀርፀን እርሱ ነው፥ እርሱ በሚሻው መንገድ ስለሚቀርፀን "አል-ሙሶዊር" الْمُصَوِّرُ የሚል ስም አለው፦
59፥24 *እርሱ አላህ ፈጣሪው፣ አስገኚው፣ "ቅርፅን አሳማሪው" ነው፡፡ ለእርሱ መልካሞች ስሞች አሉት*፡፡ هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ
3፥6 *እርሱ ያ በማሕጸኖች ውስጥ እንደሚሻ አድርጎ የሚቀርፃችሁ ነው*፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ هُوَ الَّذِي يُصَوِّرُكُمْ فِي الْأَرْحَامِ كَيْفَ يَشَاءُ ۚ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
64፥3 ሰማያትንና ምድርን በእውነት ፈጠረ፡፡ *ቀረፃችሁም ቅርፃችሁንም አሳመረ*፡፡ መመለሻችሁም ወደ እርሱ ነው፡፡ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِالْحَقِّ وَصَوَّرَكُمْ فَأَحْسَنَ صُوَرَكُمْ ۖ وَإِلَيْهِ الْمَصِيرُ
82፥8 *በማንኛውም በሻው ቅርፅ በገጣጠመህ*፡፡ فِي أَيِّ صُورَةٍ مَّا شَاءَ رَكَّبَكَ

"ሙሶዊር" مُصَوِّر የሚለው ቃል "ሶወረ" صَوَّرَ ማለትም "ቀረፀ" "ሳለ" "ሠራ" "ፈጠረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ቀራፅ" "ሰዓሊ" "ሠሪ" "ፈጣሪ" ማለት ነው። አላህ አደምን በሚሻው ቅርፅ ፈጥሮታል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 79, ሐዲስ 1
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"አላህ አደምን በቅርጹ ፈጠረ፥ ስፋቱ ስድሳ ይዘት ነበር። በፈጠረው ጊዜ፦ ሒድና እዚያ የተቀመጡትን የመላእክት ቡድን ሰላም በል! ሰላምታህን ምን ብለው እንደሚመልሱ ስማቸው! ሰላምታህም የአንተና የዝርያህ ሰላምታ ትሆናለች" አለው። አደምም፦ "አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም" አለ፥ እነርሱም፦ "አሥ-ሠላሙ ዐለይከ ወራሕመቱሏህ" አሉ፥ እነርሱ፦ "ወራሕመቱሏህ" ጨበሩለት። ነቢዩም"ﷺ"፦ *"ማንም ጀነት የሚገባው በአደም ቅርፅ ነው" አሉ"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ خَلَقَ اللَّهُ آدَمَ عَلَى صُورَتِهِ، طُولُهُ سِتُّونَ ذِرَاعًا، فَلَمَّا خَلَقَهُ قَالَ اذْهَبْ فَسَلِّمْ عَلَى أُولَئِكَ النَّفَرِ مِنَ الْمَلاَئِكَةِ جُلُوسٌ، فَاسْتَمِعْ مَا يُحَيُّونَكَ، فَإِنَّهَا تَحِيَّتُكَ وَتَحِيَّةُ ذُرِّيَّتِكَ‏.‏ فَقَالَ السَّلاَمُ عَلَيْكُمْ‏.‏ فَقَالُوا السَّلاَمُ عَلَيْكَ وَرَحْمَةُ اللَّهِ‏.‏ فَزَادُوهُ وَرَحْمَةُ اللَّهِ، فَكُلُّ مَنْ يَدْخُلُ الْجَنَّةَ عَلَى صُورَةِ آدَمَ

"ሱራህ" صُورَة‎ በሚለው ቃል መድረሻ ላይ ያለው "ሂ" هِ የሚለው አገናዛቢ ተውላጠ ስም "አደም" آدَم የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው፥ ምክንያቱም "ሱራቲ-አደም" صُورَةِ آدَمَ የሚለው "ሱራቲ-ሂ" صُورَتِهِ ለሚለው ተለዋዋጭ ነው። "ሱራቲ-ሂ" صُورَتِهِ የሚለው ወደ አላህ የሚጠጋ ነው" የሚሉ ምሁራን አሉ። ይህንን ለመረዳት ስለ ኢዷፋህ እሳቤው ሊኖረን ይገባል። "ኢዷፋህ" إِضَافَة የሚለው ቃል "አዷፈ" أَضَافَ‎ ማለትም "አገናዘበ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አገናዛቢ"possessive" ማለት ነው፥ የኢዷፋህ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ኢዷፋት" إِضَافَات‎ ነው። ኢዷፋህ በሁለት ዐብይ ክፍል ይከፈላሉ፥ እነርሱም "ኢዷፈቱ አሽ-ሸሪፋህ" إِضَافَة الشَرِيفَة እና "ኢዷፈቱ አስ-ሲፋህ" إِضَافَة الصِفَة ናቸው።

ነጥብ አንድ
"ኢዷፈቱ አሽ-ሸሪፋህ"
"ሸሪፋህ" شَرِيفَة የሚለው ቃል "ሸሩፈ" شَرُفَ ማለትም "ላቀ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "እልቅና" ማለት ነው፥ የሸሪፋህ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሸሪፋት" شَرِيفَات‎ ነው። ነቢያችን"ﷺ" የአደምን ቅርፅ ወደ አላህ በማስጠጋት በአገናዛቢ "ቅርፁ" ማለታቸው እልቅናን ያመለክታል፥ ልክ የአላህ ቤት፣ የአላህ ግመል፣ የአላህ ምድር ተብሎ በቁርኣን እደተቀመጠው ማለት ነው፦
2፥125 ቤቱንም ለሰዎች መመለሻና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ፡፡ ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም *ቤቴን* ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ وَإِذْ جَعَلْنَا الْبَيْتَ مَثَابَةً لِّلنَّاسِ وَأَمْنًا وَاتَّخِذُوا مِن مَّقَامِ إِبْرَاهِيمَ مُصَلًّى ۖ وَعَهِدْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ أَن طَهِّرَا بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْعَاكِفِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ
11፥64 ሕዝቦቼም ሆይ! ይህቺ ለእናንተ ተዓምር ስትሆን *የአላህ ግመል ናት*፡፡ ተውዋትም፡፡ *በአላህ ምድር* ውስጥ ትብላ፡፡ በክፉም አትንኳት፡፡ ቅርብ የሆነ ቅጣት ይይዛችኋልና» አላቸው፡፡ وَيَا قَوْمِ هَـٰذِهِ نَاقَةُ اللَّهِ لَكُمْ آيَةً فَذَرُوهَا تَأْكُلْ فِي أَرْضِ اللَّهِ وَلَا تَمَسُّوهَا بِسُوءٍ فَيَأْخُذَكُمْ عَذَابٌ قَرِيبٌ

ቤት፣ ግመል፣ ምድር የአላህ ባሕርይ ሳይሆኑ እልቅና ለመስጠት እንደሆኑ ሁሉ "የአደም ቅርፅ" ወደ አላህ በማስጠጋት እልቅና ሰቶቷል። ይህ አንዱ የምሁራን እይታ ነው።

ነጥብ ሁለት
"ኢዷፈቱ አስ-ሲፋህ"
"ሲፋህ" صِفَة የሚለው ቃል "ወሰፈ" وَصَفَ‎ ማለትም "ገጠለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መገለጫ" ወይም "ባሕርይ" ማለት ነው፥ የሲፋህ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሲፋት" صِفَات‎ ነው። "ሱራህ" صُورَة‎ የሚለው ቃል "መልክ" በሚል ከመጣ ባሕርይን ታሳቢ ያደረገ ነው፥ የአላህ ዕውቀት፣ የአላህ ቻይነት፣ የአላህ እይታ፣ የአላህ መስማት፣ የአላህ እጅ ወዘተ የአላህ ባሕርያት ናቸው። አላህ በባሕርይው አደምን ፈጥሮታል፥ ለምሳሌ በእጆቹ ፈጥሮታል፦
38፥75 አላህም «ኢብሊስ ሆይ! *በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት* ከመስገድ ምን ከለከለህ? አሁን ኮራህን? ወይስ ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?» አለው፡፡ قَالَ يَٰٓإِبْلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسْجُدَ لِمَا خَلَقْتُ بِيَدَىَّ ۖ أَسْتَكْبَرْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ ٱلْعَالِينَ

ይህ የምሁራን ሁለተኛ እይታ ነው። ኢንሻላህ ስለ ተስዊር በክፍል ሁለት እንዳስሳለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተኩላ እና አህያ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

22፥8 *ከሰዎችም ውስጥ ያለ ዕውቀት፣ ያለ ማስረጃም፣ ያለ አብራሪ መጽሐፍም በአላህ ነገር የሚከራከር ሰው አለ*፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يُجَادِلُ فِي اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَلَا هُدًى وَلَا كِتَابٍ مُّنِيرٍ

ከዕለታት አንድ ቀን ተኩላ እና አህያ፦ "የሳር ቀለም እንዲህ ነው እንዲያ ነው" በሚል ክርክር ውስጥ ገቡ። አህያ፦ “የሳር ቀለም ቢጫማ ነው” አለ። ተኩላ፦ "በፍፁም ! አረንጓዴ ነው” አለ።
ክርክራቸው እየጦፈ መጣ፤ ሊያስማማ የሚችል ነጥብ ላይ መድረስ አልቻሉም። በመጫረሻም የጫካ ንጉሥ ከሆነው አንበሳ ዘንድ ቀርበው መሸማገል እንዳለባቸው ወሰኑ። ሽምግልናው ተጀመረ፥ ሁለቱም የመከራከሪያ አሳባቸውን አቀረቡ። አንበሳም የሁለቱን የመከራከያ ነጥብ በጥሞና አዳመጠ፥ የፍርድ ሒደቱን ለመከታተል የታደሙት እንስሳት በሙሉ ውሳኔውን ለመስማት ጆሯቸውን ጣል አደረጉ። አንበሳው ታዳሚውንም ሆነ ተኩላውን ቅር የሚያሰኝ የፍርድ ውሳኔ አስተላለፈ፥ ተኩላው በአንድ ወር እስራት እንዲቀጣ ሲወሰንበት፤ አህያው ደግሞ በነፃ ተሰናበተ።

በፍርዱ ውሳኔ ቅር የተሰኘው ተኩላ እንዲህ በሚል ስሞታ አቀረበ፦ "ክቡር አንበሳ ሆይ! የሳር ቀለም አረንጓዴ አይደለምን? አንበሳም፦ "አዎ! በርግጥ አረንጓዴ ነው” በማለት መለሰ። ተኩላውም፦ "ታዲያ በየትኛው ጥፋቴ ነው ለአንድ ወር ያክል ዘብጥያ እንድወርድ የወሰንክብኝ? አንበሳውም፦ “ትክክል ነህ! በአመለካከትህ ቅንጣት ስህተት አላስተዋልኩም። ጥፋትህ በዚህ ጉዳይ ከአህያ ጋር ክርክር ውስጥ መግባትህ ነው። ነገሮችን በጥልቀት መረዳት እና መገንዘብ ከማይችል አካል ጋር መከራከር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ሊያመዘን አንደሚችል የአንድ ወር እስራት የወሰንኩብህ ትምህርት ትቀስም ዘንድ ብየ ነው” አለው።
ከተኩላ እና ከአህያው የምንማረው ቁምነገር ቢኖር ያለ ዕውቀት፣ ያለ ማስረጃም፣ ያለ አብራሪ መጽሐፍም ከሚከራከር ሰው ጋር ጊዜን፣ ጉልበትን፣ ዕውቀትን አለማባከንን ነው፦
22፥8 *ከሰዎችም ውስጥ ያለ ዕውቀት፣ ያለ ማስረጃም፣ ያለ አብራሪ መጽሐፍም በአላህ ነገር የሚከራከር ሰው አለ*፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يُجَادِلُ فِي اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَلَا هُدًى وَلَا كِتَابٍ مُّنِيرٍ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተስዊር

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

23፥14 *ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ*፡፡ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ

"ሙሶዊር" مُصَوِّر ማለት "ቀራፅ" "ሰዓሊ" "ሠሪ" "ፈጣሪ" ማለት እንደሆነ አይተን ነበር፥ የሙሶዊር ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሙሶዊሩን" مُصَوِّرُون ወይም "ሙሶዊሪን" مُصَوِّرِين ሲሆን "ቀራፆች" "ሰዓሊዎች" ማለት ነው፦
23፥14 *ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ*፡፡ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ

"ሰዓሊዎች" ለሚለው ቃል የገባው "ኻሊቂን" خَالِقِين ሲሆን "ሙሶዊሪን" مُصَوِّرِين ማለት ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 37, ሐዲስ 150
ዐብደላህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”በትንሳኤ ቀን ከሰዎች በጣም ተቀጪ ሰዓሊዎች ናቸው"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ أَشَدَّ النَّاسِ عَذَابًا يَوْمَ الْقِيَامَةِ الْمُصَوِّرُونَ ‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 182
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"የስዕላት ባለቤት በትንሳኤ ቀን ይቀጣሉ፥ ለእነርሱም፦ "የፈጠራችሁትን ሕያው አድርጉ" ይባላሉ"*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ إِنَّ أَصْحَابَ هَذِهِ الصُّوَرِ يُعَذَّبُونَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ، وَيُقَالُ لَهُمْ أَحْيُوا مَا خَلَقْتُمْ

ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብና ትርጉም አለው ማለት አይደለም፥ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው። መታየት ያለበት ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብ ነው። ነቢያችን”ﷺ” በቁርኣን ከተሰጣቸው አንዱ አንድ ቃላት ሰፊ ትርጉም ነው፥ ይህም “ጀዋሚዓል ከሊም” ነው። “ጀዋሚዓል ከሊም” جَوَامِعَ الْكَلِم ማለት “አንድ ቃል ሆኖ ብዛት ትርጉም ያለው” ማለት ነው። "ሱራህ" صُورَة‎ ማለት ብዙ አውራ ትርጉም ያለው ሲሆን "ስዕል" "ቅርፅ" "መልክ" "ፎቶ" ማለት ነው፥ "ሱወር" صُوَر ደግሞ የሱራህ ብዙ ቁጥር ሲሆን "ስዕላት" "ቅርፃት" ማለት ነው። "የፈጠራችሁትን" ለሚለው የገባው ቃል "ኸለቅቱም" خَلَقْتُمْ ሲሆን ስዕሉን ስለሳሉት እና ቅርፁን ስለቀረፁት እንጂ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተውት አይደለም፥ ይህ "ኢሕቲራዕ" اِخْتِرَاع ማለትም "ፈጠራ" ነው። በእጃቸው የፈጠሩትን ላይ እንደ አላህ ሩሕ ማድረግ አይችሉም፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 77, ሐዲስ 179
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ *"በዚህ ዓለም ቅርፅ የቀረፀ በትንሳኤ ቀን በውስጡ ሩሕ እንዲነፋበት ይጠየቃል፥ ግን መንፋት አይችልም"*። فَقَالَ سَمِعْتُ مُحَمَّدًا صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ مَنْ صَوَّرَ صُورَةً فِي الدُّنْيَا كُلِّفَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَنْ يَنْفُخَ فِيهَا الرُّوحَ، وَلَيْسَ بِنَافِخٍ

እዚህ ሐዲስ "ሶወረ" صَوَّرَ ማለት "ቀረፀ" "ሳለ" "ሠራ" ማለት ነው። "ኸልቅ" خَلْق የሚለው ቃል "ተስዊር" تَصْوِير ለሚለው ተለዋዋጭ ቃል ሆኖ እንደገባ አንባቢ ልብ ይለዋል፥ ይህ የቋንቋ ሙግት ታሳቢ ያደረገ ነው። ነቢያችን"ﷺ" ባልደረቦቻቸውን ወደ ሐበሻህ ሲልኳቸው ከሔዱት መካከል በአክሱም ቤተክርስቲያን ውስጥ ስዕላትን አይተዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 77
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"ኡሙ ሐቢባህ እና ኡሙ ሠለማህ በሐበሻህ ስላዩአት በውስጧ ስዕሎች ስለነበሩባት ቤተክርስቲያን ዘክረዋል፥ ስለዚህ ለነቢዩም"ﷺ"ዘክረዋል። እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦ "በእነዚያ ሰዎች መካከል የትኛውም ሷሊሕ ሰው ቢሞት በመቃብሩ ላይ የአምልኮ ስፍራ ቢገነቡ እና እነዚህን ስዕላት ቢያደርጉ፥ በትንሳኤ ቀን በአላህ ዘንድ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ ክፉ ናቸው"*፡፡ عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّ أُمَّ حَبِيبَةَ، وَأُمَّ سَلَمَةَ ذَكَرَتَا كَنِيسَةً رَأَيْنَهَا بِالْحَبَشَةِ فِيهَا تَصَاوِيرُ، فَذَكَرَتَا لِلنَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ ‏ "‏ إِنَّ أُولَئِكَ إِذَا كَانَ فِيهِمُ الرَّجُلُ الصَّالِحُ فَمَاتَ بَنَوْا عَلَى قَبْرِهِ مَسْجِدًا، وَصَوَّرُوا فِيهِ تِلْكَ الصُّوَرَ، فَأُولَئِكَ شِرَارُ الْخَلْقِ عِنْدَ اللَّهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ

"ተስዊራህ" تَصْوِيرَة ማለት "ስዕል" ማለት ነው፥ የተስዊራህ ብዙ ቁጥር "ተሷዊር" تَصَاوِير ማለት ሲሆን "ስዕላት" ማለት ነው። ስዕል በአምልኮ ውስጥ ምንም ሚና መኖር የለበትም፥ የሥላሴ፣ የኢየሱስ፣ የማርያም፣ የመላእክት እና የቅዱሳን ሰዎች ስዕል ስሎ በፊታቸው መለማመን ባዕድ አምልኮ ነው። በተመሳሳይ ቁረይሾች የአላህ ቤት ውስጥ ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል በእጆቻቸው አዝላም የያዙ አስመስለው ስዕላት ስለው ነበር፥ "አዝላም" أَزْلاَم ማለት "የጥንቆላ ቀስት" ማለት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 32
ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"ነቢዩ"ﷺ" በአላህ ቤት ስዕላት በተመለከቱ ጊዜ ባልደረቦቻቸው እንዲያጠፉ እንኪያዙ ድረስ ወደ እዚያ አልገቡም። ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል"ሠላም በእነርሱ ላይ ይሁን! በእጆቻቸው አዝላም የያዙ ስዕላት ነበሩ። እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦ "አላህ ይርገማቸው(ቁረይሾችን)! ወሏሂ ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል በአዝላም አይለማመዱም"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم لَمَّا رَأَى الصُّوَرَ فِي الْبَيْتِ لَمْ يَدْخُلْ، حَتَّى أَمَرَ بِهَا فَمُحِيَتْ، وَرَأَى إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ ـ عَلَيْهِمَا السَّلاَمُ ـ بِأَيْدِيهِمَا الأَزْلاَمُ فَقَالَ ‏ "‏ قَاتَلَهُمُ اللَّهُ، وَاللَّهِ إِنِ اسْتَقْسَمَا بِالأَزْلاَمِ قَطُّ
የኢብራሂም አባት እና የኢብራሂም ሕዝቦች ቅርጻ ቅርጽ የሆነ አስናምን ያመልኩ ነበር፥ “አስናም” أَصْنَام ማለት ከእንጨት፣ ከብር፣ ከነሐስ፣ ከወርቅ ተሠርተው አምልኮ የሚቀርብላቸው ናቸው፦
26፥70 *ለአባቱና ለሕዝቦቹ «ምንን ታመልካላችሁ?*» ባለ ጊዜ፡፡ إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِۦ مَا تَعْبُدُونَ
26፥71 *አስናምን እናመልካለን፥ እርሷንም በመገዛት ላይ እንቆያለን*» አሉ፡፡ قَالُوا۟ نَعْبُدُ أَصْنَامًۭا فَنَظَلُّ لَهَا عَٰكِفِينَ
21፥52 ለአባቱ እና ለሕዝቦቹ «ይህቺ *"ቅርጻ ቅርጽ"* ያቺ እናንተ ለእርሷ ተገዢዎች የኾናችሁት ምንድን ናት?» ባለ ጊዜ መራነው፡፡ إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِ مَا هَـٰذِهِ التَّمَاثِيلُ الَّتِي أَنتُمْ لَهَا عَاكِفُونَ

"ቲምሳል" تِمْثَال ማለት "ምስል" "ቅርጽ" ማለት ነው፥ የቲምሳል ብዙ ቁጥር ደግሞ "ተማሲል" تَمَاثِيل ሲሆን "ምስሎች" "ቅርጻ ቅርጽ" ማለት ነው። የአምልኮ ይዘት ያላቸው ማንኛውም ምስል ሆነ ስዕል ያለበት ቤት መላእክት አይገቡም፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 37, ሐዲስ 156
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”መላእክት ምስሎች ወይም ስዕሎች ያለበት ቤት አይገቡም"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لاَ تَدْخُلُ الْمَلاَئِكَةُ بَيْتًا فِيهِ تَمَاثِيلُ أَوْ تَصَاوِيرُ

ስለ ሱራህ በመስኩ ምሁራን ዘንድ ያለው እይታ በአራት ይከፈላሉ፥ እነርሱም፦
1ኛ. ለምንም ነገር ሱራህ መጠቀም ሐራም ነው፣
2ኛ. በእጅ የተሠራ እንጂ ልክ እንደ መስታዎት እራሳችንን የሚያሳዩ በካሜራ እና በፊልም የሚታዩ ነገሮች ችግር የላቸውም፣
3ኛ. ለፓስፓርት፣ ለመታወቂያ እና ለሰርተፍኬት ብቻ መጠቀም ይቻላል፣
4ኛ. ለአምልኮ አንጠቀም እንጂ ስዕል እና ቅርጻ ቅርጽ በራሱ ሥነ-ጥበብ"art" ነው" የሚሉ ናቸው።
አራተኛውን እይታ ለማስደገፍ፦ "ሡለይማን በቤተ-መንግሥቱ ምስሎች አድርጓል፥ እነዚህ ምስሎች ስዕሎች ነበሩ" ይላሉ፦
34፥13 *ከምኩራቦች፣ "ከምስሎችም"፣ እንደ ገንዳ ከኾኑ ገበታዎችም፣ ከተደላደሉ ታላላቅ ድስቶችም የሚሻውን ሁሉ ይሠሩለታል*፡፡ يَعْمَلُونَ لَهُ مَا يَشَاءُ مِن مَّحَارِيبَ وَتَمَاثِيلَ وَجِفَانٍ كَالْجَوَابِ وَقُدُورٍ رَّاسِيَاتٍ ۚ اعْمَلُوا آلَ دَاوُودَ شُكْرًا ۚ وَقَلِيلٌ مِّنْ عِبَادِيَ الشَّكُورُ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 34፥13
ወሱዲይ ከወድሐክን፣ ዐጢይል ዐውፊይ አለ ብሎ እንደተናገረው፦ *"ምስሎች ማለት ስዕሎች ናቸው"*። فقال عطية العوفي ، والضحاك والسدي : التماثيل : الصور

በሱራህ እሳቤ ዙሪያ "አንጡራ መረጃ አላገኘንም" ካላችሁ በአካባቢያችሁ ወደሚገኙት ምሁራን እና ሊሒቃን ጎራ ብላችሁ ጠይቁ! አሏሁ አዕለም።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መካህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

90፥1 *"በዚህ አገር እምላለሁ"*፡፡ لَا أُقْسِمُ بِهَـٰذَا الْبَلَدِ

"መካህ" مَـكَّـة‎ ማለት "የተመጠመጠ" ማለት ሲሆን "በካህ" بَكَّة ማለት ደግሞ የመካህ ተለዋዋጭ ቃል ነው። ልክ አንድ ሕጻን ልጅ የእናቱን ጡት ምጥጥ እንደሚያደርግ ሁሉ ስፍራው ውኃ ምጥጥ የሚያረግ ስለሆነ ይህንን ስም ተሰየመ። ይህ አገር አላህ የማለበት እና ነቢያችን"ﷺ" የሰፈሩበት አገር ነው፥ አላህም የዚህ አገር ጌታ ተብሏል፦
90፥1 *"በዚህ አገር እምላለሁ"*፡፡ لَا أُقْسِمُ بِهَـٰذَا الْبَلَدِ
90፥2 *"አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትኾን"*፡፡ وَأَنتَ حِلٌّ بِهَـٰذَا الْبَلَدِ
27፥91 *"የታዘዝኩት የዚህችን አገር ጌታ ያንን ክልል ያደረጋትን እንዳመልክ ብቻ ነው"*፡፡ ነገሩንም ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ከሙስሊሞችም እንድኾን ታዝዣለሁ" በላቸው፡፡ إِنَّمَا أُمِرْتُ أَنْ أَعْبُدَ رَبَّ هَـٰذِهِ الْبَلْدَةِ الَّذِي حَرَّمَهَا وَلَهُ كُلُّ شَيْءٍ ۖ وَأُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ مِنَ الْمُسْلِمِين

ይህ አገር ጸጥተኛ አገር ነው፥ ኢብራሂም በዱዓው ይህ አገር ጸጥተኛ እንዲሆን እና እርሱና ልጆቹንም ጣዖታትን ከማምለክ እንዲያርቅ አላህን የለመነበት አገር ነው፦
95፥3 *"በዚህ በጸጥተኛው አገርም እምላለሁ"*፡፡ وَهَـٰذَا الْبَلَدِ الْأَمِينِ
2፥126 ኢብራሂም ባለ ጊዜ አስታውስ፦ "ጌታዬ ሆይ! *"ይህንን ጸጥተኛ አገር አድርግ"*፡፡ وَإِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ رَبِّ اجْعَلْ هَـٰذَا بَلَدًا آمِنًا
14፥35 ኢብራሂምም ባለ ጊዜ አስታውስ፦ «ጌታዬ ሆይ! *"ይህንን አገር ጸጥተኛ አድርገው፡፡ እኔንም ልጆቼንም ጣዖታትን ከማምለክ አርቀን"*፡፡ وَإِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ رَبِّ اجْعَلْ هَـٰذَا الْبَلَدَ آمِنًا وَاجْنُبْنِي وَبَنِيَّ أَن نَّعْبُدَ الْأَصْنَامَ

አምላካችን አላህ በዚህ አገር በሚገኘው ጥንታዊ ቤት አጽንዖት ለመስጠት ምሏል፥ እልቅና እና ክብር በመስጠት ወደ ራሱ በማስጠጋት “በይቲይ” بَيْتِىَ ማለትም “ቤቴ” በማለት ይናገራል፦
52፥4 *"በደመቀው ቤትም እምላለው"*፡፡ وَالْبَيْتِ الْمَعْمُورِ
22፥26 ለኢብራሂምም፦ *”የቤቱን” ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ፣ በእኔ ምንንም አታጋራ! ”ቤቴንም” ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው፣ ”ባልነው ጊዜ አስታውስ”*። وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَٰهِيمَ مَكَانَ ٱلْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِى شَيْـًۭٔا وَطَهِّرْ بَيْتِىَ لِلطَّآئِفِينَ وَٱلْقَآئِمِينَ وَٱلرُّكَّعِ ٱلسُّجُودِ

"ሚዞሩት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ጧዒፊን” طَّائِفِين መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። “ጦዋፍ” طَواف የሚለው ቃል “ጧፈ” طَافَ ማለትም “ዞረ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ዙረት” ማለት ነው። ቤቱን በመጎብኘት ሰባት ጊዜ መዞር አምላካችን አላህ ለኢብራሂም የሰጠው ትእዛዝ ነው፦
22፥29 ከዚያም እንደ ጠጉርና ጥፍር ያሉትን ትርፍ አካላቸውንና ዕድፋቸውን ያስወግዱ፡፡ ስለቶቻቸውንም ይሙሉ፤ *በጥንታዊውም ቤት ይዙሩ*፡፡ ثُمَّ لْيَقْضُوا تَفَثَهُمْ وَلْيُوفُوا نُذُورَهُمْ وَلْيَطَّوَّفُوا بِالْبَيْتِ الْعَتِيقِ

“ይዙሩ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የጠወፉ” يَطَّوَّفُوا መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ቤቱን የሚዞሩት ዘዋሪዎች ደግሞ “ጧዒፍ” طَآئِف ይባላሉ፥ ለሰዎች መጸለያ መጀመሪያ የተኖረው ቤት በዚህ አገር ውስጥ ይገኛል፦
3፥96 *"ለሰዎች መጸለያ መጀመሪያ የተኖረው ቤት ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲኾን ያ በበካህ ያለው ነው"*፡፡ إِنَّ أَوَّلَ بَيْتٍ وُضِعَ لِلنَّاسِ لَلَّذِي بِبَكَّةَ مُبَارَكًا وَهُدًى لِّلْعَالَمِينَ

የዚህን ቤት መሠረት የጣለው ኢብራሂም ነው፥ መካህን የቀደሰውም እርሱ ነው። ነቢያችን"ﷺ" መዲናን ለመሥጂድ እንደቀደሱት ኢብራሂም መካህን ለመስጂደል ሐረም ቀድሶታል፦
2፥127 *ኢብራሂምና ኢስማኢልም* «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል፡፡ አንተ ሰሚውና ዐዋቂው አንተ ነህና» የሚሉ ሲኾኑ *"ከቤቱ መሠረቶቹን ከፍ ባደረጉ ጊዜ አስታውስ"*፡፡ وَإِذْ يَرْفَعُ إِبْرَاهِيمُ الْقَوَاعِدَ مِنَ الْبَيْتِ وَإِسْمَاعِيلُ رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّا ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 15, ሐዲስ 521
ጃቢር እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ኢብራሂም መካን ቀድሷል፥ እኔም መዲናን ቀድሻለው"*። عَنْ جَابِرٍ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ إِبْرَاهِيمَ حَرَّمَ مَكَّةَ وَإِنِّي حَرَّمْتُ الْمَدِينَةَ

"ሐረምቱ" حَرَّمْتُ የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። "ሐረመ" حَرَّمَ ማለት "ቀደሰ" ወይም "አከበረ" ማለት ነው፥ ይህ መካህ የሚገኘው ቤት እራሱ "በይተል ሐረም” ْبَيْتَ ٱلْحَرَامَ ማለትም “የተቀደሰው ቤት” ወይም "የተከበረው ቤት" ይባላል፦
14፥37 «ጌታችን ሆይ! እኔ *"አዝመራ በሌለው ሸለቆ ውስጥ በተከበረው ቤት አጠገብ ከዘሮቼ አስቀመጥኩ፡፡ ጌታችን ሆይ! ሶላትን ያቋቁሙ ዘንድ አስቀመጥኳቸው"*፡፡ ከሰዎችም ልቦችን ወደ እነርሱ የሚናፍቁ አድርግ፡፡ ያመሰግኑህም ዘንድ ከፍሬዎች ስጣቸው፡፡ رَّبَّنَا إِنِّي أَسْكَنتُ مِن ذُرِّيَّتِي بِوَادٍ غَيْرِ ذِي زَرْعٍ عِندَ بَيْتِكَ الْمُحَرَّمِ رَبَّنَا لِيُقِيمُوا الصَّلَاةَ فَاجْعَلْ أَفْئِدَةً مِّنَ النَّاسِ تَهْوِي إِلَيْهِمْ وَارْزُقْهُم مِّنَ الثَّمَرَاتِ لَعَلَّهُمْ يَشْكُرُون

ኢብራሂም በተከበረው ቤት አጠገብ ከዘሮቼምቹ ሶላትን ያቋቁሙ ዘንድ አስቀምጧል፥ ከዘሮቹም አዘውትረው ለአላህ የሚሰግዱ እና የሚታዘዙ እንዲሆኑ ዱዓ አርጓል፦
10፥40 «ጌታዬ ሆይ! *ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፡፡ ከዘሮቼም አድርግ*፡፡ ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ። رَبِّ اجْعَلْنِي مُقِيمَ الصَّلَاةِ وَمِن ذُرِّيَّتِي ۚ رَبَّنَا وَتَقَبَّلْ دُعَاءِ
2፥128 «ጌታችን ሆይ! *"ለአንተ ታዛዦችም አድርገን፡፡ ከዘሮቻችንም ለአንተ ታዛዦች ሕዝቦችን አድርግ"*፡፡ ሕግጋታችንንም አሳውቀን፡፡ በእኛም ላይ ተመለስን፤ አንተ ጸጸትን ተቀባዩ ሩኅሩኅ አንተ ብቻ ነህና፡፡» رَبَّنَا وَاجْعَلْنَا مُسْلِمَيْنِ لَكَ وَمِن ذُرِّيَّتِنَا أُمَّةً مُّسْلِمَةً لَّكَ وَأَرِنَا مَنَاسِكَنَا وَتُبْ عَلَيْنَا ۖ إِنَّكَ أَنتَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ
"ሙሥሊመይኒ" مُسْلِمَيْنِ ሙሰና ሲሆን ለሁለቱ ማለትም ለኢብራሂም እና ለኢሥማዒል የገባ ቃል ነው፥ "ለአንተ ታዛዦችም አድርገን" ማለቱ ይህንን ያሳያል። "ሙሥሊማህ" مُّسْلِمَة ደግሞ "ሙሥሊም" مُسْلِم ለሚለው አንስታይ መደብ ሲሆን አምላካችን አላህ የኢሥላምን አስኳል የተውሒድን ቃል በዝርዮቹም ውስጥ ቀሪ ቃል አርጓታል፦
43፥28 *”በዝርዮቹም ውስጥ ይመለሱ ዘንድ ቀሪ ቃል አደረጋት”*፡፡ وَجَعَلَهَا كَلِمَةً بَاقِيَةً فِي عَقِبِهِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

ኢብራሂም፦ "ከዘሮቼ" አለ እንጂ "ዘሮቼ" አላለም። "ዘሮቼ" በሚለው ቃል መነሻ ላይ "ከ" የሚል መስተዋድድ መኖሩ ሁሉም ዘሮቹ ሁሉ አማንያን እንዳልሆኑ እንደውም ከእነዚህ በተቃራኒው በክደት ጣዖታውያን የሆኑ አሉ፥ ከእነርሱ በእነርሱ ላይ አንቀጾችህን የሚያነብላቸውን፣ መጽሐፍን እና ጥበብንም የሚያስተምራቸውን እና ከክህደት የሚያጠራቸውን መልእክተኛ አላህ ልኳል፦
2፥129 «ጌታችን ሆይ! በውስጣቸውም ከእነርሱ የኾነን መልክተኛ በእነርሱ ላይ አንቀጾችህን የሚያነብላቸውን መጽሐፍን እና ጥበብንም የሚያስተምራቸውን *"ከክህደት የሚያጠራቸውንም ላክ"*፤ አንተ አሸናፊው ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና» የሚሉም ሲኾኑ፡፡ رَبَّنَا وَابْعَثْ فِيهِمْ رَسُولًا مِّنْهُمْ يَتْلُو عَلَيْهِمْ آيَاتِكَ وَيُعَلِّمُهُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُزَكِّيهِمْ ۚ إِنَّكَ أَنتَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
2፥151 በውስጣችሁ ከእናንተው የኾነን በእናንተ ላይ አንቀጾቻችንን የሚያነብላችሁ እና *"ከክህደትም የሚያጠራችሁ*፣ መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራችሁ፣ ታውቁት ያልነበራችሁትንም ነገር የሚያሳውቃችሁ የኾነን መልክተኛ እንደላክን ጸጋን ሞላንላችሁ፡፡ كَمَا أَرْسَلْنَا فِيكُمْ رَسُولًا مِّنكُمْ يَتْلُو عَلَيْكُمْ آيَاتِنَا وَيُزَكِّيكُمْ وَيُعَلِّمُكُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُعَلِّمُكُم مَّا لَمْ تَكُونُوا تَعْلَمُون

ይህ መልእክተኛ"ﷺ" ሲመጣ ከክህደትም የሚያጠራችሁ ነው። ይህም ክህደት በአላህ ላይ ጣዖታትን ማጋራት ነው። በኢብራሂም ተገንብቶ የነበረው ቤት ቁረይሾች በማዛባት ገንብተው ነበር፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 25, ሐዲስ 69
የነቢዩ"ﷺ" ባልተቤት ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ለእርሷ፦ *"የአንቺ ሕዝብ(ቁረይሽ) ከዕባህን ሲገነቡ በኢብራሂም በተመሠረተው እንዳልገነቧት ታውቂያለሽም? አሏት። እርሷም፦ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ለምን በኢብራሂም በተመሠረተውን ተመልሰው አይገነቧትም? አለች። እርሳቸውም፦ "የአንቺ ሕዝብ በኩፍር ባይከስቱት ኖሮ አደርገው ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنهم ـ زَوْجِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ لَهَا ‏"‏ أَلَمْ تَرَىْ أَنَّ قَوْمَكِ لَمَّا بَنَوُا الْكَعْبَةَ اقْتَصَرُوا عَنْ قَوَاعِدِ إِبْرَاهِيمَ ‏"‌‏.‏ فَقُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ أَلاَ تَرُدُّهَا عَلَى قَوَاعِدِ إِبْرَاهِيمَ‏.‏ قَالَ ‏"‏ لَوْلاَ حِدْثَانُ قَوْمِكِ بِالْكُفْرِ لَفَعَلْتُ ‏

ቁረይሾች በአላህ ቤት ዙሪያ ሦስት መቶ ስድሳ ኑሱብ እና በአላህ ቤት ውስጥ ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል በእጆቻቸው አዝላም የያዙ ስዕላት ሠርተው ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 64, ሐዲስ 320
ዐብደላህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"ነቢዩ"ﷺ" በመክፈት ቀን ወደ መካህ በገቡ ጊዜ ሦስት መቶ ስድሳ ኑሱብ በአላህ ቤት ዙሪያ ነበሩ። እርሳቸውም እነርሱን በእጃቸው መምቻ በመምታት ሲጀምሩ፦ "እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና" አሉ"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ دَخَلَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم مَكَّةَ يَوْمَ الْفَتْحِ وَحَوْلَ الْبَيْتِ سِتُّونَ وَثَلاَثُمِائَةِ نُصُبٍ، فَجَعَلَ يَطْعُنُهَا بِعُودٍ فِي يَدِهِ وَيَقُولُ ‏ "‏ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ، جَاءَ الْحَقُّ، وَمَا يُبْدِئُ الْبَاطِلُ وَمَا يُعِيدُ ‏"‌‏.‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 32
ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ *”ነቢዩ”ﷺ” በአላህ ቤት ስዕላት በተመለከቱ ጊዜ ባልደረቦቻቸው እንዲያጠፉ እንኪያዙ ድረስ ወደ እዚያ አልገቡም። ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል”ሠላም በእነርሱ ላይ ይሁን! በእጆቻቸው አዝላም የያዙ ስዕላት ነበሩ። እርሳቸውም፦ “አላህ ይርገማቸው(ቁረይሾችን)! ወሏሂ ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል በአዝላም አይለማመዱም” አሉ"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم لَمَّا رَأَى الصُّوَرَ فِي الْبَيْتِ لَمْ يَدْخُلْ، حَتَّى أَمَرَ بِهَا فَمُحِيَتْ، وَرَأَى إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ ـ عَلَيْهِمَا السَّلاَمُ ـ بِأَيْدِيهِمَا الأَزْلاَمُ فَقَالَ ‏ “‏ قَاتَلَهُمُ اللَّهُ، وَاللَّهِ إِنِ اسْتَقْسَمَا بِالأَزْلاَمِ قَطُّ

"ኑስብ" نُصْب ማለት "ሐውልት" ማለት ሲሆን የኑስብ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ኑሱብ" نُصُب ወይም "አንሷብ" أَنْصَاب ነው፥ “አዝላም” أَزْلاَم ማለት ደግሞ “የጥንቆላ ቀስት” ማለት ነው። አንሷብም አዝላምም ከሰይጣን ሥራ የኾኑ እርኩስ ብቻ ናቸው፦
5፥90 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሚያሰክር መጠጥ ቁማርም *"አንሷብም አዝላምም ከሰይጣን ሥራ የኾኑ እርኩስ ብቻ ናቸው"*፡፡ እርኩስን ራቁትም ልትድኑ ይከጀላልና፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّمَا الْخَمْرُ وَالْمَيْسِرُ وَالْأَنصَابُ وَالْأَزْلَامُ رِجْسٌ مِّنْ عَمَلِ الشَّيْطَانِ فَاجْتَنِبُوهُ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
ነቢያችን"ﷺ" ከባልደረቦቻቸው ጋር ሆነው አንሷብን እና አዝላምን ካስወገዱ በኃላ ከዕባን አድሰዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 25, ሐዲስ 68
ጃቢር ኢብኑ ዐብደሏህ"ረ.ዐ" ሰምቶ እንዳስተላለፈው፦ *"ከዕባህ በሚገነባ ጊዜ ነቢዩ"ﷺ" እና ዐባሥ ለግንባታ ድንጋዮች ለማምጣት ሔዱ። ዐባሥ ለነቢዩ"ﷺ"፦ "የወገቦትን መታጠቂያ አንገቶት ላይ ያድርጉ" አለ"*። قَالَ سَمِعْتُ جَابِرَ بْنَ عَبْدِ اللَّهِ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ لَمَّا بُنِيَتِ الْكَعْبَةُ ذَهَبَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم وَعَبَّاسٌ يَنْقُلاَنِ الْحِجَارَةَ فَقَالَ الْعَبَّاسُ لِلنَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم اجْعَلْ إِزَارَكَ عَلَى رَقَبَتِك

ይህ ቤት ንድፉ ርዝመት፣ ስፋት፣ ቁመት ያለው ባለ ሦስት ቅጥ ስለሆነ “ከዕባህ” ተብሏል፥ “ከዕባህ” كَعْبَة ማለት “አንኳር“The Cube” ማለት ነው። ሁላችንም ቂብላችን ወደዚህ ቤት ነው፥ “ቂብላህ” قِبْلَة የሚለው ቃል “አቅበለ” أَقْبَلَ ማለትም “ተቀጣጨ” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን “አቅጣጫ”direction” ማለት ነው። የትም ቦታ ሆነን ለአንድነት ለአላህ የምንሰግደው ወደ ከዕባህ ነው፦
2፥149 *ከየትም ለጉዞ ከወጣህበት ስፍራ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ አግጣጫ አዙር*፡፡ وَمِنْ حَيْثُ خَرَجْتَ فَوَلِّ وَجْهَكَ شَطْرَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ ۖ

“መሥጂድ” مَسْجِد የሚለው ቃል “ሠጀደ” سَجَدَ ማለትም “ሰገደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መስገጃ” ማለት ሲሆን “ሡጁድ” سُّجُود ደግሞ “ስግደት” ማለት ነው። ይህ የመጀመሪያው መሥጂድ ነው። እንግዲህ በመላው ዓለም የሚገኙ ሙሥሊሞች በሕይወት ዘመናቸው አንዴ በመካህ የሚገኘው የአላህን ቤት መጎብኘት ፈርድ ነው። “ሐጅ” حَجّ የሚለው ቃል “ሐጀ” حَجَّ ማለትም “ጎበኘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን “ጉብኝት” ማለት ነው። “ሐጅ” حَجّ መደበኛ ዐብይ ጉብኝት ሲሆን “ዑምራ” عُمْرَة ደግሞ መደበኛ ያልሆነ ንዑስ ጉብኝት ነው፦
2፥196 *ሐጅን እና ዑምራንም ለአላህ ሙሉ*፡፡ وَأَتِمُّوا الْحَجَّ وَالْعُمْرَةَ لِلَّه
3፥97 በውስጡ ግልጽ የኾኑ ተዓምራቶች የኢብራሒምም መቆሚያ አለ፡፡ ወደ ውስጡ የገባ ሰው ጸጥተኛ ይኾናል፡፡ ለአላህም በሰዎች ላይ ወደ እርሱ መኼድን በቻለ ሁሉ ላይ *ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው*፡፡ የካደም ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው፡፡ فِيهِ آيَاتٌ بَيِّنَاتٌ مَّقَامُ إِبْرَاهِيمَ ۖ وَمَن دَخَلَهُ كَانَ آمِنًا ۗ وَلِلَّهِ عَلَى النَّاسِ حِجُّ الْبَيْتِ مَنِ اسْتَطَاعَ إِلَيْهِ سَبِيلًا ۚ وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ
2፥158 *ሶፋና መርዋ ከአላህ ምልክቶች ናቸው፤ “ቤቱን በሐጅ ወይም በዑምራህ ሥራ የጎበኘ” ሰው በሁለቱ መካከል በመመላለሱ በእርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም*፡፡ إِنَّ الصَّفَا وَالْمَرْوَةَ مِن شَعَائِرِ اللَّهِ ۖ فَمَنْ حَجَّ الْبَيْتَ أَوِ اعْتَمَرَ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِ أَن يَطَّوَّفَ بِهِمَا

“የጎበኘ” ለሚለው ቃል የገባው “ሐጀ” حَجَّ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። የአላህ ቤት የሚጎበኝ ተባዕት "ሓጅ" حَاجّ ሲባል፥ የአላህ ቤት የሚምትጎበኝ እንስት ደግሞ "ሓጃህ" حَاجَّة‎ ትባላለች። የሓጅ ወይም የሓጃህ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሑጇጅ" حُجَّاج‎ ይባላሉ። አምላካችን አላህ በቅድስት አገር የሚገኘውን ቤቱን ከሚጎበኙት ሑጇጅ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የሰው ሩሕ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

17፥85 *ስለ ሩሕ ይጠይቁሃል፥ «ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው፥ ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው*፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الرُّوحِ ۖ قُلِ الرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّي وَمَا أُوتِيتُم مِّنَ الْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًا

“ሩሕ” رُّوح ማለት “መንፈስ” ማለት ሲሆን አንድን አካል ሕያው የሚሆንበት ንጥረ-ነገር ነው። “ዐን” عَنِ ማለት “ስለ”about” ማለት ነው፦
17፥85 *ስለ ሩሕ ይጠይቁሃል፥ «ሩሕ ከጌታዬ “ነገር” ነው፥ ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው*፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الرُّوحِ ۖ قُلِ الرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّي وَمَا أُوتِيتُم مِّنَ الْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًا
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3433 
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”ቁራይሾች ለአይሁዳውያን፦ “ይህንን ሰው ስለ ሆነ ነገር የምንጠይቀው ጥያቄ ስጡን” አሉ። የሁዲም፦ “ስለ ሩሕ ጠይቁት” አለ፥ እነርሱም ስለ ሩሕ ጠየቁት። አላህም፦ “ስለ ሩሕ ይጠይቁሃል፥ «ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው፥ ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው” የሚለውን አንቀጽ አወረደ”*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ قَالَتْ قُرَيْشٌ لِيَهُودَ اعْطُونَا شَيْئًا نَسْأَلُ عَنْهُ هَذَا الرَّجُلَ فَقَالَ سَلُوهُ عَنِ الرُّوحِ قَالَ فَسَأَلُوهُ عَنِ الرُّوحِ فَأَنْزَلَ اللَّهُ ‏:‏ ‏(‏ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الرُّوحِ قُلِ الرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّي وَمَا أُوتِيتُمْ مِنَ الْعِلْمِ إِلاَّ قَلِيلاً ‏)‏

ሩሕ “ነገር” ከሆነ ደግሞ ነገር አላህ የፈጠረው ነው፥ አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፦
39፥62 *አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ

ሙሶዊር” مُصَوِّر ማለት “ቀራፅ” “ሰዓሊ” “ሠሪ” ማለት ነው፥ የሙሶዊር ብዙ ቁጥር ደግሞ “ሙሶዊሩን” مُصَوِّرُون ወይም “ሙሶዊሪን” مُصَوِّرِين ሲሆን “ቀራፆች” “ሰዓሊዎች” ማለት ነው። የስዕላት ባለቤትን በትንሳኤ ቀን የፈጠሩትን ሩሕ በመንፋት ሕያው እንዲያደርጉ ይጠየቃሉ፥ ግን አይችሉም፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 182
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የስዕላት ባለቤት በትንሳኤ ቀን ይቀጣሉ፥ ለእነርሱም፦ “የፈጠራችሁትን ሕያው አድርጉ” ይባላሉ”*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ إِنَّ أَصْحَابَ هَذِهِ الصُّوَرِ يُعَذَّبُونَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ، وَيُقَالُ لَهُمْ أَحْيُوا مَا خَلَقْتُمْ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 77, ሐዲስ 179
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ *”በዚህ ዓለም ቅርፅ የቀረፀ በትንሳኤ ቀን በውስጡ ሩሕ እንዲነፋበት ይጠየቃል፥ ግን መንፋት አይችልም”*። فَقَالَ سَمِعْتُ مُحَمَّدًا صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ “‏ مَنْ صَوَّرَ صُورَةً فِي الدُّنْيَا كُلِّفَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَنْ يَنْفُخَ فِيهَا الرُّوحَ، وَلَيْسَ بِنَافِخٍ

“የፈጠራችሁትን” ለሚለው የገባው ቃል “ኸለቅቱም” خَلَقْتُمْ ሲሆን ስዕሉን ስለሳሉት እና ቅርፁን ስለቀረፁት እንጂ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተውት አይደለም፥ ሩሕ ከአላህ ነገር ስለሆነ በእጃቸው የፈጠሩትን ላይ ሩሕ ማድረግ አይችሉም። አምላካችን አላህ አደምን ከአፈር ፈጥሮ ያንን የፈጠረውን አካል ሩሕ በማድረግ ሕያው አድርጎታል፦
38፥72 *ፍጥረቱንም ባስተካከልኩ እና በእርሱ ውስጥ “ከ-መንፈሴ” በነፋሁበት ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ኾናችሁ ውደቁ» አልኩ*፡፡ فَإِذَا سَوَّيْتُهُ وَنَفَخْتُ فِيهِ مِن رُّوحِي فَقَعُوا لَهُ سَاجِدِينَ

“ሩሕ” رُوح በሚለው ቃል ላይ “ሚን” مِنْ ማለትም “ከ” የሚል መስተዋድድ መነሻ ቅጥያ አለ፥ ይህ የሚያሳየው “ሩሕ” አካል ህያው የሚሆንበት ንጥረ-ነገር መሆኑን ነው። ለምሳሌ አላህ ምድርን ወደ እራሱ በማስጠጋት እልቅና ክብር ለመስጠት “አርዲ” أَرْضِي ማለትም “ምድሬ” በማለት ይናገራል፦
20፥55 *ከእርሷ ከምድር ፈጠርናችሁ*፡፡ በእርሷም ውስጥ እንመልሳችኋለን፡፡ ከእርሷም በሌላ ጊዜ እናወጣችኋለን፡፡ مِنْهَا خَلَقْنَاكُمْ وَفِيهَا نُعِيدُكُمْ وَمِنْهَا نُخْرِجُكُمْ تَارَةً أُخْرَىٰ
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! *ምድሬ* በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ እኔንም ብቻ አምልኩኝ፡፡ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّ وَاسِعَةٌ فَإِيَّايَ فَاعْبُدُونِ

“አርድ” أَرْض በሚለው ቃል ላይ “ሚን” مِنْ ማለትም “ከ” የሚል መስተዋድድ መነሻ ቅጥያ አለ፥ ይህ የሚያሳየው “አርድ” አካል የተሠራበት ነገር መሆኑን ነው። አምላካችን አላህ የሰውን አካል ከምድር ፈጥሮ የፈጠረበትን ምድር ወደ እራሱ በማስጠጋት እልቅና ክብር ለመስጠት “ምድሬ” እንዳለ ሁሉ የሰውን መንፈስ ወደ እራሱ በማስጠጋት እልቅና ክብር ለመስጠት “መንፈሴ” ብሏል። ልክ እንደዚሁ የዒሣ አፈጣጠርም ከአደም አፈጣጠር ጋር ይመሳሰላል፦
3፥59 አላህ ዘንድ *የዒሳ ምሳሌ እንደ አዳም ብጤ ነው፡፡ ከአፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለእርሱ «ኹን» አለው፤ ኾነም*፡፡ إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ اللَّهِ كَمَثَلِ آدَمَ ۖ خَلَقَهُ مِن تُرَابٍ ثُمَّ قَالَ لَهُ كُن فَيَكُونُ
አምላካችን አላህ አደምን ከአፈር ፈጥሮ ከሩሕ በመንፋት ሕያው እንዳደረገው ሁሉ መርየም ማሕፀን ውስጥ ዒሣን ፈጥሮ ከሩሕ በመንፋት ሕያው አድርጎታል፦
21፥91 ያችንም ብልቷን የጠበቀቺውን *”በእርሷም ውስጥ ከመንፈሳችን የነፋንባትን”* እርሷንም ልጅዋንም ለዓለማት ተዓምር ያደረግናትን መርየምን አስታውስ፡፡ وَالَّتِي أَحْصَنَتْ فَرْجَهَا فَنَفَخْنَا فِيهَا مِن رُّوحِنَا وَجَعَلْنَاهَا وَابْنَهَا آيَةً لِّلْعَالَمِينَ

ለአደም ሲሆን “ፊ-ሂ” فِيهِ ማለትም “በ-እርሱ ውስጥ” ብሏል፥ “እርሱ” የተባለው የአደም አካል ነው። በአደም አካል ውስጥ ሩሕ እንደነፋበት ያሳያል። በተመሳሳይ ለመርየም ሲሆን “ፊ-ሃ” فِيهَا ማለትም “በ-እርሷ ውስጥ” ብሏል፥ “እርሷ” የተባለችው የዒሣ እናት መርየም ናት። በመርየም ማሕፀን ውስጥ ሩሕ እንደነፋባት ያሳያል። ስለዚህ የዒሣ አካል ሕያው የሆነበት ሩሕ ከአላህ የሆነ ነው፦
4፥171 እላንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፤ በአላህም ላይ እውነትን እንጂ አትናገሩ! የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ የአላህ መልክተኛ ብቻ ነው። ወደ መርየም የጣላት የይኹን ቃሉም ነው። *”ከ-እርሱ” የሆነ መንፈስ ነው*። يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ

“ከ” የሚለው መስተዋድድ መነሻ ቅጥያ ያለው “እርሱ” የሚለው ተውላጠ-ስም “አላህ” የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው። “ሚን-ሁ” مِنْهُ የሚለው አካሉ ከመርየም ሩሑ ከአላህ መሆን የሚያሳይ ነው፥ አንድ ተመሳሳይ የሰዋስው ሙግት እንይ፦
45፥13 ለእናንተም *በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ በመላ “ከ-እርሱ” ሲኾን የገራላችሁ ነው*፡፡ በዚህ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ተዓምራት አልለበት፡፡ وَسَخَّرَ لَكُم مَّا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا مِّنْهُ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

“በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ በመላ ከእርሱ ነው” የሚለው ይሰመርበት። “ሚን-ሁ” مِنْهُ ማለትም “ከ-እርሱ” የሚለው ፍጥረት ከአላህ መሆኑን እንደሚያሳይ ሁሉ የዒሣም ሩሕ ከአላህ መሆኑን ያሳያል። ስለዚህ የሰው መንፈስ ሁሉ ከአላህ የሆነ ነገር ነው፦
17፥85 *ስለ ሩሕ ይጠይቁሃል፥ «ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው፥ ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው*፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الرُّوحِ ۖ قُلِ الرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّي وَمَا أُوتِيتُم مِّنَ الْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًا

“ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ስለዚህ የሁላችንም ሩሕ ከአፈር ሳይሆን ከጌታዬ ነገር ነው። አምላካችን አላህ ሩሕ በፅንስ ላይ ሲነፋበት ሕያው ይሆናል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 46, ሐዲስ 1
ዐብደሏህ እንደተረከው፦ “እውነተኛ ታማኝ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”የእያንዳንዳቹህ ፍጥረት በእናቱ ሆድ ውስጥ ሂደቱ በአርባ ቀናት ይሰበሰባል። ከዚያም በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ያ ዐለቃህ ይሆናል፣ ከዚያም በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ያ ሙድጋህ ይሆናል። *ከዚያም መልአክ ወደ እርሱ ይላካል እና በእርሱ ሩሕ ይነፋል*። እርሱም አራት ነገሮችን ሲሳዩን፣ ፍጻሜውን፣ ሥራውን እና ሐዘኑን ወይም ደስታው እንዲጽፍ ይታዘዛል። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ حَدَّثَنَا رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَهُوَ الصَّادِقُ الْمَصْدُوقُ “‏ إِنَّ أَحَدَكُمْ يُجْمَعُ خَلْقُهُ فِي بَطْنِ أُمِّهِ أَرْبَعِينَ يَوْمًا ثُمَّ يَكُونُ فِي ذَلِكَ عَلَقَةً مِثْلَ ذَلِكَ ثُمَّ يَكُونُ فِي ذَلِكَ مُضْغَةً مِثْلَ ذَلِكَ ثُمَّ يُرْسَلُ الْمَلَكُ فَيَنْفُخُ فِيهِ الرُّوحَ وَيُؤْمَرُ بِأَرْبَعِ كَلِمَاتٍ بِكَتْبِ رِزْقِهِ وَأَجَلِهِ وَعَمَلِهِ وَشَقِيٌّ أَوْ سَعِيدٌ

ስለ ሰው ሩሕ የተሰጠን ዕውቀት ጥቂት ስለሆነ “ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም” ብሎናል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የቁርኣን ሡራህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

17፥106 *ቁርኣንንም በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ኾነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፥ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው*፡፡ وَقُرْءَانًۭا فَرَقْنَٰهُ لِتَقْرَأَهُۥ عَلَى ٱلنَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍۢ وَنَزَّلْنَٰهُ تَنزِيلًۭا

አምላካችን አላህ ቁርኣንን ወደ ነቢያችን"ﷺ" በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ኾነው ያነቡት ዘንድ ከፋፍሎ ቀስ በቀስ አወረደው፦
17፥106 *ቁርኣንንም በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ኾነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፥ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው*፡፡ وَقُرْءَانًۭا فَرَقْنَٰهُ لِتَقْرَأَهُۥ عَلَى ٱلنَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍۢ وَنَزَّلْنَٰهُ تَنزِيلًۭا

"ከፋፈልነው" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ቁርኣን በሱራህ የተከፋፈለ ነው፥ ሡራዎች የሚለያዩት በመካከላቸው “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው" በሚል በሥመላህ ነው፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 398
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”ነቢዩ”ﷺ” ሁለት ሡራዎች አይለያዩ በመካከላቸው “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” የሚለው ቃል ወደ እርሳቸው ቢወርድላቸው እንጂ”*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم لاَ يَعْرِفُ فَصْلَ السُّورَةِ حَتَّى تُنَزَّلَ عَلَيْهِ ‏{‏ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ ‏}

“ሡራህ” سُورَة ማለት “ምዕራፍ” ወይም “ክፍል” አሊያም “ደረጃ” ማለት ነው። የሡራህ ብዙ ቁጥር "ሡወር" سُوَر‎ ነው። አምላካችን አላህ ቁርኣንን በሡራህ መከፋፈሉን ለማመልከት ብዙ አናቅጽ ላይ "ሡራህ" እያለ ይናገራል፦
24፥1 *"ይህች ያወረድናት እና የደነገግናት "ሡራህ" ናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ትገሰፁ ዘንድ ግልጾችን አንቀጾች አውርደናል"*፡፡ سُورَةٌ أَنزَلْنَاهَا وَفَرَضْنَاهَا وَأَنزَلْنَا فِيهَا آيَاتٍ بَيِّنَاتٍ لَّعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
9፥64 መናፍቃን በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ነገር የምትነግራቸው *"ሡራህ" በእነርሱ ላይ መውረዷን ይፈራሉ*፡፡ «አላግጡ አላህ የምትፈሩትን ሁሉ ገላጭ ነው» በላቸው፡፡ يَحْذَرُ الْمُنَافِقُونَ أَن تُنَزَّلَ عَلَيْهِمْ سُورَةٌ تُنَبِّئُهُم بِمَا فِي قُلُوبِهِمْ ۚ قُلِ اسْتَهْزِئُوا إِنَّ اللَّهَ مُخْرِجٌ مَّا تَحْذَرُونَ

ስለዚህ የቁርኣን ሡራህ ሡራህ የተባለው ከዓለማቱ ጌታ ከአላህ ዘንድ ነው። 114 ሡራዎች ወደ ነቢያችን”ﷺ” ልብ በጨረቃ አቆጣጠር ከ 610 ድኅረ-ልደት እስከ 632 ድኅረ-ልደት ለ 23 ዓመት ቀስ በቀስ ወረደ። ለ 13 ዓመት 86 ሡራዎች በመካ ሲወርዱ፥ ለ 10 ዓመት ደግሞ 28 ሡራዎች የወረዱት በመዲና ነው። ነቢያችን”ﷺ” በ 40 ዓመታቸው ጀምሮ እስከ 63 ዓመታቸው ወሕይ ቀስ በቀስ በሒደት ወረደ፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 63, ሐዲስ 128
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” በ 40 ዓመታቸው ወሕይ መቀበል ጀመሩ፥ በመካ 13 ዓመት ወሕይ እየተቀበሉ ቆይተው ከዚያ ተሰደው እንደ ስደተኛ 10 ዓመት ቆይተው በ 63 ዓመታቸው በሆነ ጊዜ ሞተዋል*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ بُعِثَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم لأَرْبَعِينَ سَنَةً، فَمَكُثَ بِمَكَّةَ ثَلاَثَ عَشْرَةَ سَنَةً يُوحَى إِلَيْهِ، ثُمَّ أُمِرَ بِالْهِجْرَةِ فَهَاجَرَ عَشْرَ سِنِينَ، وَمَاتَ وَهُوَ ابْنُ ثَلاَثٍ وَسِتِّينَ‏.‏

በዚህም በመካ የወረዱት 86 ሡራዎች "መኪያህ" مَكِّيَّة ሲባሉ፥ በመዲና የወረዱት 28 ሡራዎች ደግሞ "መደኒያህ" مَدَنِيَّة ይባላሉ። የሡራዎችን ቅድመ-ተከተል እና ስም ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" በተናገሩት መሠረት የተቀመጠ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3366
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *"ለዑስማን ኢብኑ ዐፋን፦ "ሡረቱል አንፋልን ከመቶ በታች የሆነችበት፣ ሡረቱል በራኣህ(ተውባህ) ከመቶ በላይ የሆነችበት፣ በመካከላቸውም “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” የሚለው ያልተጻፈበት(ሱረቱል በራኣህ) እና ባለ ሰባት አናቅጽ(ሡረቱል ፋቲሓህ) የሆችበት ምክንያታችሁ ምንድን ነው? አልኩኝ። ዑስማን እንዲህ ብሎ መለሰ፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" አንዳች የቁርኣን ክፍል በሚወርድላቸው ጊዜ ከጸሐፊዎቹ አንዱን በመጥራት፦ "ይህንን አንቀጽ እንዲህ ተብሎ በሚጠራው ሡራህ ውስጥ አስቀምጡት" ይሉ ነበር። አሁንም በድጋሚ የተወሰኑ የቁርኣን አንቀጾች ሲወርድላቸው፦ "እነዚህን አንቀጾች እንዲህ ተብሎ በሚጠራው ሡራህ ውስጥ አስቀምጡት" ይሉ ነበር"*። حَدَّثَنَا ابْنُ عَبَّاسٍ، قَالَ قُلْتُ لِعُثْمَانَ بْنِ عَفَّانَ مَا حَمَلَكُمْ أَنْ عَمَدْتُمْ، إِلَى الأَنْفَالِ وَهِيَ مِنَ الْمَثَانِي وَإِلَى بَرَاءَةَ وَهِيَ مِنَ الْمِئِينَ فَقَرَنْتُمْ بَيْنَهُمَا وَلَمْ تَكْتُبُوا بَيْنَهُمَا سَطْرَ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ وَوَضَعْتُمُوهُمَا فِي السَّبْعِ الطُّوَلِ مَا حَمَلَكُمْ عَلَى ذَلِكَ فَقَالَ عُثْمَانُ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم مِمَّا يَأْتِي عَلَيْهِ الزَّمَانُ وَهُوَ تَنْزِلُ عَلَيْهِ السُّوَرُ ذَوَاتُ الْعَدَدِ فَكَانَ إِذَا نَزَلَ عَلَيْهِ الشَّىْءُ دَعَا بَعْضَ مَنْ كَانَ يَكْتُبُ فَيَقُولُ ضَعُوا هَؤُلاَءِ الآيَاتِ فِي السُّورَةِ الَّتِي يُذْكَرُ فِيهَا كَذَا وَكَذَا وَإِذَا نَزَلَتْ عَلَيْهِ الآيَةُ فَيَقُولُ ضَعُوا هَذِهِ الآيَةَ فِي السُّورَةِ الَّتِي يُذْكَرُ فِيهَا كَذَا
ይህ ሐዲስ የሚያሳየው የሡራው ቅድመ-ተከተል እና እከሌ የሚለው ስም በአላህ ነቢይ የታዘዘ መሆኑን ነው። እርሳቸውም በንግግራቸው ሡረቱል በቀራህ፣ ሡረቱል አለ ዒምራን፣ ሡረቱል ከህፍ፣ ሡረቱል ያሢን ወዘተ እያሉ መናገራቸው በራሱ በእርሳቸው መሰየሙን ቁልጭ እና ፍንትው አድርጎ የሚያስረዳ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 66, ሐዲስ 64
አቢ መሥዑድ አል-አንሷሪይ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በሌሊት ከሡረቱል በቀራህ ከመጨረሻው ሁለት አናቅጽ ከቀራ በቂው ነው"*። عَنْ أَبِي مَسْعُودٍ الأَنْصَارِيِّ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ الآيَتَانِ مِنْ آخِرِ سُورَةِ الْبَقَرَةِ مَنْ قَرَأَ بِهِمَا فِي لَيْلَةٍ كَفَتَاهُ ‏
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 45, ሐዲስ 3125
ነዋሥ ኢብኑ ሠምዓን እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ቁርኣን በዱኒያ ውስጥ በሚሠሩበት ባለቤቶቹ ላይ የትንሳኤ ቀን ይመጣል። ሡረቱል በቀራህ እና ሡረቱል አለ ዒምራን በፊቱ ይሆናሉ"*። عَنْ نَوَّاسِ بْنِ سَمْعَانَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ يَأْتِي الْقُرْآنُ وَأَهْلُهُ الَّذِينَ يَعْمَلُونَ بِهِ فِي الدُّنْيَا تَقْدُمُهُ سُورَةُ الْبَقَرَةِ وَآلُ عِمْرَانَ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 6, ሐዲስ 311
አቢ አድ-ደርዳእ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ማንም ከሡረቱል ከህፍ መጀመሪያ አሥር አናቅጽ ያፈዘ ከደጃል ይጠበቃል"*። عَنْ أَبِي الدَّرْدَاءِ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَنْ حَفِظَ عَشْرَ آيَاتٍ مِنْ أَوَّلِ سُورَةِ الْكَهْفِ عُصِمَ مِنَ الدَّجَّالِ ‏
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 21, ሐዲስ 33
መዕቂል ኢብኑ የሣር እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ሡረቱል ያሢን በሙታናችሁ ላይ ቅሩ!"*። عَنْ مَعْقِلِ بْنِ يَسَارٍ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ اقْرَءُوا ‏{‏ يس ‏}‏ عَلَى مَوْتَاكُمْ

ከሦስት ሡራህ በስተቀር እያንዳንዱ ሡራህ ስማቸው በውስጣቸው አለ። እነዚህም ስማቸው በውስጣቸው ያልተጠቀሱ ሦስት ሡራዎች ሡረቱል ፋቲሓህ፣ ሡረቱል አንቢያህ እና ሡረቱል ኢኽላስ ናቸው። በተረፈ ሁሉም ስማቸው በውስጣቸው አለ፥ ለምሳሌ "በቀራህ" بَقَرَة ማለት "ጊደር" ማለት ሲሆን ስለ ጊደሯ የሚናገር ሡራህ ነው፦
2፥68 «ለኛ ጌታህን ጠይቅልን፤ እርሷ ምን እንደኾነች ዕድሜዋን ያብራራልን» አሉ፡፡ «እርሱ እርሷ ያላረጀች ጥጃም ያልኾነች በዚህ መካከል ልከኛ የኾነች *"ጊደር"* ናት ይላችኋል፥ የታዘዛችሁትንም ሥሩ» አላቸው፡፡ قَالُوا ادْعُ لَنَا رَبَّكَ يُبَيِّن لَّنَا مَا هِيَ ۚ قَالَ إِنَّهُ يَقُولُ إِنَّهَا بَقَرَةٌ لَّا فَارِضٌ وَلَا بِكْرٌ عَوَانٌ بَيْنَ ذَٰلِكَ ۖ فَافْعَلُوا مَا تُؤْمَرُونَ

ኢሥላም ሰው ሠራሽ ሕግና ሥርዓት ሳይሆን ዐቂደቱ አር-ረባንያህ ነው። ይህንን ስንል አርቲ ቡርቲና ቶራ ቦራ የሆነ ስሑትና መሪር የቡና ወሬ ይዘን ሳይሆን ቁርኣንና ሐዲስን ያማከለ ስሙርና ጥዑም ማስረጃ ይዘን ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የጌቶች ጌታ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

37፥5 *የሰማያትና የምድር በመካከላቸው ያለውም ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው*፡፡ የምሥራቆችም ጌታ ነው፡፡ رَّبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا وَرَبُّ الْمَشَارِقِ

በባይብል እሳቤ እግዚአብሔር ኢየሱስን ጌታ አደረገው፦
የሐዋርያት ሥራ 2፥36 አለ። እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን *ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው* የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።

መቼም አንድ ጤነኛ የሆነ ሰው፦ "ፈጣሪን ፈጣሪ ጌታ አደረገው" ብሎ እንደማይቀበል እሙንና ቅቡል ነው፥ ይስሐቅ ያዕቆብን ጌታ አደረግሁት ይላል፦
ዘፍጥረት 27፥37 ይስሐቅም መለሰ ዔሳውንም አለው። እነሆ፥ *ጌታህ አደረግሁት*፥ ወንድሞቹንም ሁሉ ለእርሱ ተገዦች ይሆኑ ዘንድ ሰጠሁት፥

ይህም ሥልጣንና ሹመትን አሊያም ማዕረግና እልቅናን ያመለክታል። ዮሴፍ፦ “እግዚአብሔር ጌታ አደረገኝ” ይላል፦
ዘፍጥረት 45፥9 *እግዚአብሔር በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ጌታ አደረገኝ*፤ ወደ እኔ ና! አትዘግይ።

"ኢየሱስ ጌታ ተደረገ" ሲባል "ያዕቆብ ጌታ ተደረገ" ወይም "ዮሴፍ ጌታ ተደረገ" በተባለበት ሒሳብ እንጂ "የዓለማቱ ጌታ" የሚለውን አያመለክትም፤።ይህም በራሡ የተብቃቃ አሊያም የባሕርይ ገንዘቡ ሣይሆን በስጦታ ያገኘው ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ሿሚና ሠያሚ ሲሆን ኢየሱስ ሹምና ሥዩም ነው፥ እግዚአብሔር ኢየሱስን "ራስ" አድርጎታልና፦
ሐዋ. ሥራ 5፥31 ይህን እግዚአብሔር፥ ለእስራኤል ንስሐን የኃጢአትንም ስርየት ይሰጥ ዘንድ፥ *ራስም መድኃኒትም አድርጎ* በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው።

"ጌታ" እና "ራስ" ተለዋዋጭ ቃላት ናቸው። ባሎች ራሶች ናቸው፥ የወንዶች ራስ ደግሞ ክርስቶስ ስለሆነ የጌቶች ጌታ ተብሏል፦
ራእይ 17፥14 እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም *"የጌቶች ጌታ እና የነገሥታት ንጉሥ”* ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል።
ራእይ 19፥16 በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት፦ *“የነገሥታት ንጉሥ እና የጌቶች ጌታ"* የሚል ስም አለው።

ልብ አድርግ ኢየሱስ "የጌቶች ጌታ" የተባለው "የነገሥታት ንጉሥ" በተባለበት ስሌትና ቀመር ነው። "የነገሥታት ንጉሥ" ማዕረግ ደግሞ ለፍጡራንም አገልግሎት ላይ ይውላል፦
ዕዝራ 7፥12 *“ከነገሥታት ንጉሥ”* ከአርጤክስስ ለሰማይ አምላክ ሕግ ጸሐፊ ለካህኑ ለዕዝራ፥ ሙሉ ሰላም ይሁን፤
ሕዝቅኤል 26፥7 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ከሰሜን *“የነገሥታት ንጉሥ”* የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን ከፈረሶችና ከሰረገሎች ከፈረሰኞችም ከጉባኤና ከብዙ ሕዝብ ጋር በጢሮስ ላይ አመጣለሁ።
ዳንኤል 2፥37 አንተ፥ ንጉሥ ሆይ፥ የሰማይ አምላክ መንግሥትንና ኃይልን፥ ብርታትንና ክብርን የሰጠህ *“የነገሥታት ንጉሥ”* አንተ ነህ።

አይ አርጤክስስ ሆነ ናቡከደነፆር የነገሥታት ንጉሥነትን ያገኙት ከአንዱ አምላክ ነው ከተባለ ኢየሱስም ንግሥናውን ሆነ ጌትነቱን ያገኘው ከአንዱ አምላክ በስጦታ ነው። ሲቀጥል "ጌታ" ማለት "ገዢ" ማለት ነው፥ "የጌቶች ጌታ" ማለት "የምድር ነገሥታት ገዢ" ማለት ነው፦
ራእይ 1፥5 *"የምድርም ነገሥታት ገዥ"* ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

ነጥቡ ያለው እዚህ ጋር ነው። እግዚአብሔር ለኢየሱስ ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቶአል ሲባል ሁሉን ካስገዛለት ከእግዚአብሔር በቀር መሆኑ ግልጥ ነው፥ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ለእግዚአብሔር ይገዛል፦
1 ቆሮንቶስ 15፥27-28 *ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቶአልና። ነገር ግን፦ ሁሉ ተገዝቶአል፡ ሲል፥ ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጥ ነው። ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል*።

ይህ አንቀጽ የሚያሳየው "የጌቶች ጌታ" ወይም "የምድር ነገሥታት ገዢ" የተባለውን ኢየሱስን የሚገዛው ሌላ ምንነትና ማንነት እንዳለ ነው። እርሱ የኢየሱስ እና የአጠቃላይ ፍጥረት ገዢ ነው፦
1 ቆሮንቶስ 11፥3 *የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ*።
1 ዜና 29፥11 *አንተም በሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያልህ ራስ ነህ*።

"ራስ" ማለት "ገዢ" ማለት ነው። "ያህዌህ በሁሉ ላይ ራስ ነው" ሲባል ፍጥረት ለያህዌህ የሚገዛው ሚስት ለባሏ የደረጃ መገዛት"functional subordination" እንደምትገዛው ሳይሆን የሥነ-ኑባሬ መገዛት"ontological subordination" ነው። "ሁሉ" በሚለው ቃል ውስጥ ደግሞ ኢየሱስም ስለሚካተት ኢየሱስ ለእግዚአብሔር የሚገዛው የሥነ-ኑባሬ መገዛት ነው። ለምሳሌ ወንድ የሴት ራስ ነው ማለት የሴት ገዢ ነው ማለት ነው፦
ዘፍጥረት 3፥16 ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም *ገዥሽ* ይሆናል።
1ኛ ቆሮንቶስ 14፥34 ሴቶች በማኅበር ዝም ይበሉ፤ *ሕግ ደግሞ እንደሚል እንዲገዙ* እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውምና።
1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥11 ሴት በነገር ሁሉ *እየተገዛች* በዝግታ ትማር።
1ኛ ጴጥሮስ 3፥5-6 ቅዱሳት ሴቶች ደግሞ *ለባሎቻቸው ሲገዙ* ተሸልመው ነበርና፤ እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም፦ *"ጌታ"* ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት።
ዘፍጥረት 18፥12 ሣራም በልብዋ እንዲህ ስትል ሳቀች፦ ካረጀሁ በኋላ በውኑ ፍትወት ይሆንልኛልን? *ጌታዬም* ፈጽሞ ሸምግሎአል።

ሕግ የሚለው "ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል" የሚል ነው። እግዚአብሔር ለኢየሱስ ገዢ ከሆነ ተገዢ ማንነት በፍጹም መመለክ የለበትም። ሴት ለቧላ የምትገዛው "ጌታ" እያለች እንደሆነ ኢየሱስ ሆነ ሁሉም ፍጥረት ለአብ የሚገዙት "የሰማይና የምድር ጌታ" እያሉ ነው፦
ማቴዎስ 11፥25 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፦ *አባት ሆይ፥ የሰማይና የምድር ጌታ*፥
ሐዋ. ሥራ 17፥24 ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ *እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና* እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም።

ዋናው ነጥብ ኢየሱስ "የጌቶች ጌታ" የተባለበት ሥልጣንና ሹመት፥ ማዕረግንና እልቅናን ያመለክታል እንጂ የሚመመለክ መሆኑን በፍጹም አያሳይም። ምክንያቱም አንደኛ ጌትነቱን ከራሱ ያገኘው አይደለም፣ ሁለተኛ እርሱ እራሱ የሚገዛው ገዢ አለው፣ ሦስተኛ ፈጣሪ ኢየሱስን “ባሪያዬ” ስለሚለው፦
ኢሳይያስ 42፥1 *እነሆ ደግፌ የያዝሁት “ባሪያዬ”*።

“ባሪያዬ” መባሉ በራሱ ፈጣሪ ተመላኪ ኢየሱስ አምላኪ መሆኑን ቁልጭና ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ባሪያ ከሆነ እግዚአብሔር የኢየሱስ ጌታ ነው።
በቁርኣን እሳቤ ደግሞ የሰማያትና የምድር በመካከላቸው ያለውም ፍጡር ሁሉ ጌታ አምላካችን አላህ ነው፥ አላህ የሁሉ ነገር ጌታ ስለሆነ ለእኛ ለሙሥሊሞች ከአላህ ሌላ የምንገዛው ጌታ የለንም፦
37፥5 *የሰማያትና የምድር በመካከላቸው ያለውም ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው*፡፡ የምሥራቆችም ጌታ ነው፡፡ رَّبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا وَرَبُّ الْمَشَارِقِ
6፥164 በላቸው «እርሱ *አላህ “የሁሉ ጌታ” ሲሆን ከአላህ በቀር “ሌላን ጌታ” እፈልጋለሁን? ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም*፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሷቢኢኢን ወይስ ሷቢኡኡን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

የአንድ ሰው ንግግር ምንም አይነት ግጭት ሊኖርበይ ወይም ላይኖርበት ይችላል፥ በተቃራኒው "መለኮታዊ መገለጥ ነው" ተብሎ ግን ያልሆነ ከሆነ እና ከተበዘረ በእርሱ ውስጥ ግጭት ይገኛል። የፈጣሪ ንግግር ፈጽሞ አይጋጭም፥ ቁርኣን ከዓለማቱ ጌታ ስለወረደ በውስጡ የእርስ በእርስ ግጭት የለበትም፦
4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

የክርስትናው ዐቃቤ እምነት ሳሙኤል ግሪን ግን፦ "ቁርኣን እርስ በእርሱ ይጋጫል" ብሎ ቅሪላ ትችት ያቀርባል፥ ይጋጫል ያላቸውን አናቅጽ ጥርስና ምላሱን ብትን አድርገን እስቲ እንያቸው፦
2፥62 እነዚያ ያመኑ እነዚያም ይሁዳውያን የኾኑ፣ ክርስቲያኖችም፣ *ሳቢያኖችም* ከእነርሱ በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምንም ሥራ የሠራ ለነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَالَّذِينَ هَادُوا وَالنَّصَارَىٰ وَالصَّابِئِينَ مَنْ آمَنَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَعَمِلَ صَالِحًا فَلَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሳቢያኖች" ለሚለው የገባ ቃል "ሷቢኢኢን" صَّابِئِين ነው። ነገር ግን በሌላ አንቀጽ ተመሳሳይ መልእክት ላይ የገባው "ሷቢኡኡን" صَّابِئُون ነው፦
5፥69 እነዚያ ያመኑና እነዚያም አይሁዳውያን የኾኑ፣ *ሳቢያኖችም*፣ ክርስቲያኖችም ከእነርሱ በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነና መልካምን ሥራ የሠራ ሰው በእነርሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፡፡ እነርሱም አያዝኑም፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَالَّذِينَ هَادُوا وَالصَّابِئُونَ وَالنَّصَارَىٰ مَنْ آمَنَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَعَمِلَ صَالِحًا فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ

"ሷቢእ" صَّابِئ በነጠላ ሲሆን በብዜት "ሀምዛህ" ء ከስራ ያ ስኩን ባለ ሁለት ሐረካት ተስቦ "ኢኢ" ئِي ገብታ በ "ኑን" ن ሲጨርስ "ሷቢኢኢን" صَّابِئِين ወይም "ሀምዛህ" ء ደማህ ዋው ስኩን ባለ ሁለት ሐረካት ተስቦ "ኡኡ" ئُو ገብታ በ "ኑን" ن ሲጨርስ "ሷቢኡኡን" صَّابِئُون ይሆናል።
ሳሙኤል ግሪን፦ "አንዱ ጥቅስ ላይ "ሷቢኢኢን" ማለቱን፥ ሌላውን ጥቅስ ላይ "ሷቢኡኡን" ማለቱ የሰዋስው ግጭት ነው" ይላል። ይህ የዐረቢኛ ሰዋስውን ካለመረዳት የሚመጣ የተሳከረ ምልከታ ነው።
ሲጀመር ቁርኣን ላይ "ሙፍረድ" مُفْرَد ማለትም "ነጠላ" የነበረ ቃል ወደ "ጀምዕ" جَمْع ማለትም "ብዜት" ሲመጣ ከስራ ያ ስኩን ባለ ሁለት ሐረካት ተስቦ በ "ኑን" ن መጨረስ ወይንም ደማህ ዋው ስኩን ባለ ሁለት ሐረካት ተስቦ በ "ኑን" ن መጨረስ ይቻላል። ለምሳሌ "ሙሥሊም" مُسْلِم የነበረው ነጠላ ቃል በብዜት "ሙሥሊሚሚን" مُسْلِمِين ወይም "ሙሥሊሙሙን" مُّسْلِمُون መሆን ይችላል፦
43፥69 እነዚያ በአንቀጾቻችን ያመኑ እና ፍጹም *ታዛዦች* የነበሩ። الَّذِينَ آمَنُوا بِآيَاتِنَا وَكَانُوا مُسْلِمِينَ
21፥108 «ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ነው፥ ታዲያ እናንተ ፍጹም *ታዛዦች* ናችሁን?» በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

ልብ አድርግ የመጀመሪያው አንቀጽ ላይ "ሚም" م ከስራ ያ ስኩን ባለ ሁለት ሐረካት "ሚሚ" مِي ሆኖ በ "ኑን" ن ሲጨርስ፥ በሁለተኛው አንቀጽ م ደማህ ዋው ስኩን ባለ ሁለት ሐረካት "ሙሙ" مُو ሆኖ በ "ኑን" ن ይጨርሳል። ብዙ ናሙና አለ፥ ለምሳሌ በነጠላ "ሙእሚን" مُؤْمِنِينَ የነበረው በብዜት "ሙእሚኒኒን" مُؤْمِنِين ወይም "ሙእሚኑኑን" مُؤْمِنِين ተብሎ ሊቀመጥ ይችላል። ይህ የመድ ሕግ ነው፥ መድ مَدْ ማለት በተጅዊድ ሕግ "መሳቢያ”stretch” ማለት ነው።

ሲቀጥል ሳሙኤል ግሪን "ሀምዛህ" ء ከስራ ያ ስኩን ባለ ሁለት ሐረካት ተስቦ "ኢኢ" ئِي የምትለዋን "ሀምዛህ" ء ከሥራተይን "ኢን" ٍ አድርጎ በመረዳት፥ እንዲሁ "ሀምዛህ" ء ደማህ ዋው ስኩን ባለ ሁለት ሐረካት ተስቦ "ኡኡ" ئُو የምትለዋን "ሀምዛህ" ء ደማተይን "ኡን" ٌ አድርጎ በመረዳት መድን ከተንዊን ጋር ቀላቅሏል። ይህ የሚያሳየው ስለ ኢዕራብ ምንም ግንዛቤ እንደሌለው ያሳብቅበታል። "ኢዕራብ" إِﻋْﺮَاب ማለት "ሙያ"case" ማለት ሲሆን ኢዕራብ በሦስት ይከፈላል፥ እነርሱም፦ "መርፉዕ" مَرْفُوع ማለትም "ባለቤት"nominative"፣ "መንሱብ" مَنْصُوب ማለትም "ተሳቢ"accusative" እና "መጅሩር" مَجْرُور ማለትም "አገናዛቢ"genetive" ናቸው።

ኢዕራብ አገልግሎቱ በሐረካት እና በተንዊን ላይ ነው፥ "ሐረካት" حَرَكَاتْ ማለት "እንቅስቃሴ"motion ማለት ሲሆን አጭር አናባቢ”short vowel” ነው፥ እነዚህ አጭር አናባቢ በመንሱብ "ፈትሓህ" فَتْحَة ሲሆን፣ በመጅሩር "ከሥራህ" كَسْرَة ሲሆን፣ በመርፉዕ ደግሞ "ደማህ" ضَمَّة ነው።
"ተንዊን" تَنْوِين ማለት "ኑናዊነት"nunation" "ኑን" ن ድርብ አናባቢ”double vowel” ስትመጣ ነው፥ ተንዊን በመንሱብ "ፈትሐተይን" فَتْحَتَين ፣ በመጅሩር "ከሥረተይን" كَسْرَتَين እና በመርፉዕ "ደመተይን" ضَمَّتَين ነው። አንድ ቃል ተንዊን ሆኖ ከመጣ ነኪራህ ነው፥ "ነኪራህ" نَكْرَه ማለት "ኢ-አመልካች መስተአምር"indefinite article" ማለት ነው።
ነገር ግን "ሷቢኢኢን" صَّابِئِين ወይም "ሷቢኡኡን" صَّابِئُون በሚለው ቃል መነሻ ላይ "አል" ال የሚል "ማዕሪፋህ" مَعْرِفَة ማለትም "አመልካች መስተአምር"definite article" ስላለ ነኪራህ አይደለም። ነኪራክ ካልሆነ ደግሞ የኢዕራብ ልዩነት ኖሮት ትርጉሙን አያዛባም። ስለዚህ የሳሙኤል ግሪን እንኩቶ ትችት ዜሮ ይገባል።
ከላይ የቀረበውን ጥያቄ ሆነ የተሰጠውን መልስ ለመረዳት የተጅዊድ እሳቤ መያዝ ያሻል፥ የቁርኣንን መሠረትና ውቅር፣ ዋልታና ማገር፣ ጥልቀትና ስፋት፣ ድርና ማግ ለመረዳት ተጅዊድ ወሳኝ ጉዳይ ነው። አላህ ቁርኣንን ተረድተው ከሚጠቀሙ ባሮቹ ያርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የሴት ምስክርነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥135 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *"በትክክል ቀዋሚዎች በነፍሶቻችሁ ወይም በወላጆችና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢኾንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሀብታም ወይም ድኻ ቢኾን አላህ በእነርሱ ከእናንተ ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ፡፡ ብታጠምሙም ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ بِالْقِسْطِ شُهَدَاءَ لِلَّهِ وَلَوْ عَلَىٰ أَنفُسِكُمْ أَوِ الْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ ۚ إِن يَكُنْ غَنِيًّا أَوْ فَقِيرًا فَاللَّهُ أَوْلَىٰ بِهِمَا ۖ فَلَا تَتَّبِعُوا الْهَوَىٰ أَن تَعْدِلُوا ۚ وَإِن تَلْوُوا أَوْ تُعْرِضُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا

በራሳችን ሆነ በወላጆቻን ወይንም በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢኾንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች መሆን አለብን። አላህ በምንሠራው ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው ብሎ ሀብታም ወይም ድኻ ሳንል፣ ሳናዳላ፣ ዝንባሌን ሳንከተል፣ ፍትህን ሳናጣምም፣ ሐቅን ሳንመሰክር ሳንቀር ብንመሰክር በጀነት ውስጥ የምከብርን ነን፦
70፥33 *"እነዚያም እነርሱ በምስክርነታቸው ትክክለኞች የኾኑት"*፡፡ وَٱلَّذِينَ هُم بِشَهَٰدَٰتِهِمْ قَآئِمُونَ
70፥35 *"እነዚህ በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው"*፡፡ أُو۟لَٰٓئِكَ فِى جَنَّٰتٍۢ مُّكْرَمُونَ

አንድ ሙዕሚን ለአላህ ብሎ ቀጥተኛ በፍትሕ መስካሪ መሆን አለበት፥ ጥላቻ ካለማስተካከል ከመጣ ከአላህ ፍራቻ የራቀ ነው፦
5፥8 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሕዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ አስተካክሉ፡፡ እርሱ ማስተካከል ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ لِلَّهِ شُهَدَاءَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

“ቂሥጥ” قِسْط ማለት “ፍትሕ” ማለት ነው፥ ለአላህ ተብሎ ቀጥተኛ ለመሆን ፍትሕ ወሳኝ ነጥብ ነው። ይህ በነሲብ ከመመስከር ይታደገናል፥ “ተዕዲሉ” تَعْدِلُوا ተብሎ የተቀመጠው የግስ መደብ የስም መደቡ “ዐድል” عَدْل ሲሆን አሁን “ፍትሕ” ማለት ነው። ይህም ፍትሐዊ ምስክርነት በቁርኣን በአራት ይከፈላል። እነርሱም፦ የፍቺ ምስክርነት፣ የኑዛዜ ምስክርነት፣ የዝሙት ምስክርነት እና የዕዳ ምስክነት ናቸው።

ነጥብ አንድ
"የፍቺ ምስክርነት"
65፥2 *"ጊዜያቸውንም ለመዳረስ በተቃረቡ ጊዜ በመልካም ያዙዋቸው፡፡ ወይም በመልካም ተለያዩዋቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶችን አስመስክሩ፡፡ ምስክርነትንም ለአላህ አስተካክሉ"*፡፡ ይህ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የኾነ ሰው ሁሉ በእርሱ ይገሰጽበታል፡፡ አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል፡፡ فَإِذَا بَلَغْنَ أَجَلَهُنَّ فَأَمْسِكُوهُنَّ بِمَعْرُوفٍ أَوْ فَارِقُوهُنَّ بِمَعْرُوفٍ وَأَشْهِدُوا ذَوَيْ عَدْلٍ مِّنكُمْ وَأَقِيمُوا الشَّهَادَةَ لِلَّهِ ۚ ذَٰلِكُمْ يُوعَظُ بِهِ مَن كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۚ وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَل لَّهُ مَخْرَجًا

በፍቺ ምስክርነት ላይ ሴት እና ወንድ ያላቸው የምስክርነት ድርሻ ልዩነት የለውም።

ነጥብ ሁለት
"የኑዛዜ ምስክርነት"
5፥106 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *"አንዳችሁን ሞት በመጣበት ጊዜ በኑዛዜ ወቅት የመካከላችሁ ምስክርነት ከእናንተ ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶች የኾኑ ሰዎች ወይም በምድር ብትጓዙና የሞት አደጋ ብትነካችሁ ከሌሎቻችሁ የኾኑ ሁለት ሌሎች ሰዎች መመስከር ነው፡፡ ብትጠራጠሩ ከዐሱር ሶላት በኋላ ታቆሟቸው እና የሚመሰክርለት ሰው የዝምድና ባለቤት ቢኾንም እንኳ «በርሱ ዋጋን አንገዛም የአላህንም ምስክርነት አንደብቅም፤ ያን ጊዜ ደብቀን ብንገኝ እኛ ከኃጢአተኞች ነን» ብለው በአላህ ስም ይምላሉ"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا شَهَادَةُ بَيْنِكُمْ إِذَا حَضَرَ أَحَدَكُمُ الْمَوْتُ حِينَ الْوَصِيَّةِ اثْنَانِ ذَوَا عَدْلٍ مِّنكُمْ أَوْ آخَرَانِ مِنْ غَيْرِكُمْ إِنْ أَنتُمْ ضَرَبْتُمْ فِي الْأَرْضِ فَأَصَابَتْكُم مُّصِيبَةُ الْمَوْتِ ۚ تَحْبِسُونَهُمَا مِن بَعْدِ الصَّلَاةِ فَيُقْسِمَانِ بِاللَّهِ إِنِ ارْتَبْتُمْ لَا نَشْتَرِي بِهِ ثَمَنًا وَلَوْ كَانَ ذَا قُرْبَىٰ ۙ وَلَا نَكْتُمُ شَهَادَةَ اللَّهِ إِنَّا إِذًا لَّمِنَ الْآثِمِينَ

በኑዛዜ ምስክርነት ላይ ሴት እና ወንድ ያላቸው የምስክርነት ድርሻ ልዩነት የለውም።
ነጥብ ሦስት
"የዝሙት ምስክርነት"
24፥4 *"እነዚያም ጥብቆችን ሴቶች በዝሙት የሚሰድቡ ከዚያም አራትን ምስክሮች ያላመጡ ሰማኒያን ግርፋት ግረፏቸው፡፡ ከእነርሱም ምስክርነትን ሁልጊዜ አትቀበሉ እነዚያም እነሱ አመጸኞች ናቸው"*፡፡ وَالَّذِينَ يَرْمُونَ الْمُحْصَنَاتِ ثُمَّ لَمْ يَأْتُوا بِأَرْبَعَةِ شُهَدَاءَ فَاجْلِدُوهُمْ ثَمَانِينَ جَلْدَةً وَلَا تَقْبَلُوا لَهُمْ شَهَادَةً أَبَدًا ۚ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْفَاسِقُونَ

በዝሙት ምስክርነት ላይ ሴት እና ወንድ ያላቸው የምስክርነት ድርሻ ልዩነት የለውም።

ነጥብ አራት
"የዕዳ ምስክርነት"
2፥282 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *"እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ በዕዳ በተዋዋላችሁ ጊዜ ጻፉት፡፡ ጸሐፊም በመካከላችሁ በትክክል ይጻፍ፡፡ ጸሐፊም አላህ እንደ አሳወቀው መጻፍን እንቢ አይበል፡፡ ይጻፍም፡፡ ያም በርሱ ላይ ዕዳው ያለበት ሰው በቃሉ ያስጽፍ፡፡ አላህንም ጌታውን ይፍራ፡፡ ከእርሱም ካለበት ዕዳ ምንንም አያጉድል፡፡ ያም በርሱ ላይ ዕዳው ያለበት ቂል፣ ወይም ደካማ፣ ወይም በቃሉ ማስጻፍን የማይችል ቢኾን ዋቢው በትክክል ያስጽፍለት፡፡ ከወንዶቻችሁም ሁለትን ምስክሮች አስመስክሩ፡፡ ሁለትም ወንዶች ባይኾኑ ከምስክሮች ሲኾኑ ከምትወዱዋቸው የኾኑን አንድ ወንድና አንደኛዋ ስትረሳ አንደኛይቱ ሌላዋን ታስታውሳት ዘንድ ሁለት ሴቶች ይመስክሩ"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا تَدَايَنتُم بِدَيْنٍ إِلَىٰ أَجَلٍ مُّسَمًّى فَاكْتُبُوهُ ۚ وَلْيَكْتُب بَّيْنَكُمْ كَاتِبٌ بِالْعَدْلِ ۚ وَلَا يَأْبَ كَاتِبٌ أَن يَكْتُبَ كَمَا عَلَّمَهُ اللَّهُ ۚ فَلْيَكْتُبْ وَلْيُمْلِلِ الَّذِي عَلَيْهِ الْحَقُّ وَلْيَتَّقِ اللَّهَ رَبَّهُ وَلَا يَبْخَسْ مِنْهُ شَيْئًا ۚ فَإِن كَانَ الَّذِي عَلَيْهِ الْحَقُّ سَفِيهًا أَوْ ضَعِيفًا أَوْ لَا يَسْتَطِيعُ أَن يُمِلَّ هُوَ فَلْيُمْلِلْ وَلِيُّهُ بِالْعَدْلِ ۚ وَاسْتَشْهِدُوا شَهِيدَيْنِ مِن رِّجَالِكُمْ ۖ فَإِن لَّمْ يَكُونَا رَجُلَيْنِ فَرَجُلٌ وَامْرَأَتَانِ مِمَّن تَرْضَوْنَ مِنَ الشُّهَدَاءِ أَن تَضِلَّ إِحْدَاهُمَا فَتُذَكِّرَ إِحْدَاهُمَا الْأُخْرَىٰ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ስትረሳ" ለሚለው ቃል የገባው "ተዲለ" تَضِلَّ ሲሆን "ደለ" ضَلَّ ማለት "ረሳ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ነው። በተጨማሪም "ታስታውሳት" ለሚለው ቃል የገባው "ቱዘከረ" َتُذَكِّر ሲሆን "ዘከረ" ذَكَرَ ማለት "አስታወሰ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ነው። እዚህ አንቀጽ ላይ "ዚክራ" ذِكْرَىٰ ማለትም "ማስታወስ" እና "ደላል" ضَلَال ማለትም "መርሳት" ሁለት ተቃራኒ ነገር ሆነው ነው የመጡት። ይህንን እሳቤ ይህ ሐዲስ ያጠናክርልናል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 52, ሐዲስ 22
አቢ ሠዒድ አል-ኹድሪይ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"የሴት ምስክርነት የወንድ ግማሽ ምስክርነት አይደለምን? ሴቶችም፦ "አዎ" አሉ፥ እርሳቸውም፦ "ይህ የሴት ዐቅል ዝንጉነት ነው"*። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ أَلَيْسَ شَهَادَةُ الْمَرْأَةِ مِثْلَ نِصْفِ شَهَادَةِ الرَّجُلِ ‏"‌‏.‏ قُلْنَا بَلَى‏.‏ قَالَ ‏"‏ فَذَلِكَ مِنْ نُقْصَانِ عَقْلِهَا

"ኑቅሳን" نُقْصَان የሚለው "ነቀሰ" نَقَصَ‎ ማለትም "ዘነጋ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ዝንጉነት" ማለት ነው። የፍቺ ምስክርነት፣ የኑዛዜ ምስክርነት፣ የዝሙት ምስክርነት ላይ በወንድ እና በሴት አንዳች የምስክርነት ልዩነት የለም። ነገር ግን የዕዳ ምስክርነት ላይ አንድ ወንድ እና ሁለት ሴቶች ነው፥ ምክንያቱም አንደኛዋ ስትረሳ አንደኛይቱ ሌላዋን ታስታውሳት ዘንድ ነው። ሴት ልጅ በወሊድ እና በወር አበባ ጊዜ ህመም ስለሚኖርባት በማስታወስ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለባት የሥነ-እንስት"gynecology" ምሁራን ያትታሉ። የፍቺ ምስክርነት፣ የኑዛዜ ምስክርነት፣ የዝሙት ምስክርነት ወቅታዊ ስለሆኑ የሚረሱ አይደሉም፥ የዕዳ ምስክነት ግን የረዥም ጊዜ ሒደት ነው። በዚህ ሒደት ውስጥ ሴት ልጅ በወሊድ እና በወር አበባ ጊዜ ህመም ስለሚኖርባት በማስታወስ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ስለሚኖር ሁለቱን እንስት ይረዳዳሉ።
በተተፈ ሴት እና ወንድ በአላህ ዘንድ ምንም የኑባሬ ልዩነት የላቸውም፥ ወንዱም ሰው እንደሆነ ሴቷም ሰው ናት። ባይብል እና አዋልድ ግን፦ "ሴት “ደካማ ፍጥረት ናት። በተፈጥሮዋ ደካማ ናት፤ የሰማችውን ሁሉ ሳታመዛዝን አሜን ብላ ትቀበላለችና” ይለናል፦
1 ጴጥሮስ 3፥7 እንዲሁም፥ እናንተ ባሎች ሆይ፥ *”ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑ”* ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ።
ቀለሜንጦስ 2÷14 *”ሴት በተፈጥሮዋ ደካማ ናት፤ የሰማችውን ሁሉ ሳታመዛዝን አሜን ብላ ትቀበላለችና”*።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም