ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
የአላህ ይቅርታ እና ምሕረት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

15፥49 *"ባሮቼን እኔ ይቅርባዩ መሓሪው እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው"*፡፡ نَبِّئْ عِبَادِي أَنِّي أَنَا الْغَفُورُ الرَّحِيمُ

በቁርኣን ከተጠቀሱ ዘጠና ዘጠኝ ከአላህ የተዋቡ ስሞች መካከል “አል-ገፋር” الغَفَّار ወይም “አል-ገፉር” الغَفُور ሲሆን “ይቅርባዩ” ማለት ነው። “መግፊራህ” مَّغْفِرَة ማለት “ይቅርታ” ማለት ሲሆን የእርሱ ባሕርይ ነው። እንዲሁ በቁርኣን ከተጠቀሱ ዘጠና ዘጠኝ ከአላህ የተዋቡ ስሞች መካከል “አር-ረሒም” ٱلرَّحِيمِ ማለት ደግሞ “እጅግ በጣም መሓሪ” ማለት ነው፥ የአር-ረሕማን ባሕርይ ደግሞ “ረሕማህ” رَّحْمَةً ማለትም "ምሕረት ነው። አምላካችን አላህ በመጀመሪያ መደብ እና በሦስተኛ መደብ፦ "እኔ ይቅርባዩ መሓሪው ነኝ" ይላል፦
15፥49 *"ባሮቼን እኔ ይቅርባዩ መሓሪው እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው"*፡፡ نَبِّئْ عِبَادِي أَنِّي أَنَا الْغَفُورُ الرَّحِيمُ
49፥5 ወደ እነርሱም እስክትወጣ ድረስ እነርሱ በታገሱ ኖሮ ለእነርሱ በላጭ በኾነ ነበር፡፡ *"አላህም እጅግ ይቅርባይ መሓሪ ነው"*፡፡ وَلَوْ أَنَّهُمْ صَبَرُوا۟ حَتَّىٰ تَخْرُجَ إِلَيْهِمْ لَكَانَ خَيْرًۭا لَّهُمْ ۚ وَٱللَّهُ غَفُورٌۭ رَّحِيمٌۭ

የአላህ የይቅርታው ጥልቀትና ስፋት"un-comprehension፥ የምሕረቱ ምጥቀትና ልቀት"un-apprehension" የሚያጅብ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 81, ሐዲስ 56
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ለሰናይ ሥራ ጣሩ፥ ተቃረቡ፥ ተበሰሩ። ማንም በሥራው ጀነት አይገባም። እነርሱም፦ "እርስዎም የአላህ መልእክተኛ ሆይ! እርሳቸውም፦ "እኔም ብሆን አላህ ይቅርታው እና ምሕረቱን እስከሚለግሰኝ ድረስ"*። عَنْ عَائِشَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ سَدِّدُوا وَقَارِبُوا، وَأَبْشِرُوا، فَإِنَّهُ لاَ يُدْخِلُ أَحَدًا الْجَنَّةَ عَمَلُهُ ‏"‌‏.‏ قَالُوا وَلاَ، أَنْتَ يَا رَسُولَ اللَّهِ قَالَ ‏"‏ وَلاَ أَنَا إِلاَّ أَنْ يَتَغَمَّدَنِي اللَّهُ بِمَغْفِرَةٍ وَرَحْمَةٍ

መልካም ሥራ ለጀነት ሰበብ እንጂ ሙሥሊም ጀነት የሚገባው በአላህ ይቅርታና ምሕረት ነው። የአላህን ይቅርታ እና ምሕረት ደግሞ የሚገኘው በተውበት በመቶበት ነው፦
16፥119 ከዚያም ጌታህ ለእነዚያ በስሕተት መጥፎን ለሠሩና ከዚያም ከዚህ በኋላ *"ለተጸጸቱ ሥራቸውንም ላበጁ ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ ይቅርባይ መሓሪ ነው"*፡፡ ثُمَّ إِنَّ رَبَّكَ لِلَّذِينَ عَمِلُوا السُّوءَ بِجَهَالَةٍ ثُمَّ تَابُوا مِن بَعْدِ ذَٰلِكَ وَأَصْلَحُوا إِنَّ رَبَّكَ مِن بَعْدِهَا لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ
3፥89 *"እነዚያ ከዚህ በኋላ ንስሓ የገቡና ሥራቸውን ያሳመሩ ሲቀሩ፡፡ እነዚህንስ ይምራቸዋል፥ አላህ ይቅርባይ መሓሪ ነውና"*፡፡ إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا مِن بَعْدِ ذَٰلِكَ وَأَصْلَحُوا فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

ተውበት ሦስት ሸርጦች አሉት፥ እርሱም፦ ያንን እኩይ ሥራ መተው፣ በሠሩት እኩይ ሥራ መጸጸት እና ወደዚያ እኩይ ሥራ ላለመመለጥ ቆራጥነት ነው። አምላካችን አላህ በተውበት ወደ እርሱ ለሚመለሱ ባሮቹ የቱንም ያክል ወንጀላቸው ቢበዛ እጅግ በጣም ይቅርባይና መሓሪ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 48, ሐዲስ 171
አነሥ ኢብኑ ማሊክ የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ ብሎ እንደተረከው፦ "አላህም አለ፦ *"የአደም ልጅ ሆይ! አንተ በጠራከኝ እና በከጀልከኝ ግዜ ከአንተ ምንም ኀጢአት ቢኖርም እምርሐለሁ፥ ኀጢአትህ ቢበዛም ምንም አይመስለኝም። የአደም ልጅ ሆይ! ኀጢአትህ እስከ ሰማይ ደመና ቢደርስ እንኳን ከዚያም ይቅርታን ከጠየቅከኝ ይቅር እልካለው። የአደም ልጅ ሆይ! አንተ ምድርን የሞላ ኀጢአት ይዘህ በእኔ ግን ሳታጋራ ወደ እኔ ብትመጣ ከዚያም ብትገናኘኝ እኔም በሙሉ ይቅርታ ወደ አንተ እመጣለው"*። يَقُولُ حَدَّثَنَا أَنَسُ بْنُ مَالِكٍ، قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ قَالَ اللَّهُ يَا ابْنَ آدَمَ إِنَّكَ مَا دَعَوْتَنِي وَرَجَوْتَنِي غَفَرْتُ لَكَ عَلَى مَا كَانَ فِيكَ وَلاَ أُبَالِي يَا ابْنَ آدَمَ لَوْ بَلَغَتْ ذُنُوبُكَ عَنَانَ السَّمَاءِ ثُمَّ اسْتَغْفَرْتَنِي غَفَرْتُ لَكَ وَلاَ أُبَالِي يَا ابْنَ آدَمَ إِنَّكَ لَوْ أَتَيْتَنِي بِقُرَابِ الأَرْضِ خَطَايَا ثُمَّ لَقِيتَنِي لاَ تُشْرِكُ بِي شَيْئًا لأَتَيْتُكَ بِقُرَابِهَا مَغْفِرَةً

ማንም ሙሥሊም በመጨረሻይቱ ዓለም በአላህ እስካላሻረከ ድረስ ለሠራው እኩይ ሥራ ተቀጥቶ ቅጣቱን ሲጨርስ በአላህ ይቅርታና ምሕረት ወደ ጀነት ይገባል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 113
አቡ ዘር እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" *"እንዲህ አሉ፦ ጂብሪል ወደ እኔ መጥቶ እንዲህ ሲል አበሰረኝ፦ "ማንም ምንም ነገር በአላህ ላይ ያላሻረከ ወደ ጀነት ይገባል። እኔም፦ "ቢሰርቅም፥ ቢያመነዝርም? ብዬ ጠየኩት። እርሱም፦ "ቢሰርቅም፥ ቢያመነዝርም" አለኝ"*። عَنِ الْمَعْرُورِ، قَالَ سَمِعْتُ أَبَا ذَرٍّ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ أَتَانِي جِبْرِيلُ فَبَشَّرَنِي أَنَّهُ مَنْ مَاتَ لاَ يُشْرِكُ بِاللَّهِ شَيْئًا دَخَلَ الْجَنَّةَ ‏"‌‏.‏ قُلْتُ وَإِنْ سَرَقَ وَإِنْ زَنَى قَالَ ‏"‏ وَإِنْ سَرَقَ وَإِنْ زَنَى
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 201
አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦…. *”ከሰዎች መካከል በሥራቸው ለዘላለም በጀሃነም ሲዘወትሩ ሌሎች ደግሞ ቅጣት ተቀብለው ከጀሃነም ይወጣሉ፣ አላህ የሻው ከጀሃነም ሰዎች መካከል ምሕረት ያደርግለታል። ለመላእክትም፦ “እርሱን ብቻ ያመለከውን አውጡ” ብሎ ያዛቸዋል”*። تَخْطَفُ النَّاسَ بِأَعْمَالِهِمْ، فَمِنْهُمْ مَنْ يُوبَقُ بِعَمَلِهِ، وَمِنْهُمْ مَنْ يُخَرْدَلُ ثُمَّ يَنْجُو، حَتَّى إِذَا أَرَادَ اللَّهُ رَحْمَةَ مَنْ أَرَادَ مِنْ أَهْلِ النَّارِ، أَمَرَ اللَّهُ الْمَلاَئِكَةَ أَنْ يُخْرِجُوا مَنْ كَانَ يَعْبُدُ اللَّهَ
“ከሰዎች መካከል ለዘላለም በጀሃነም የሚዘወተሩ” በአላህ ላይ ያጋሩ ናቸው። አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም። የሚያጋራን ሰው አላህ ጀነትን በእርሱ ላይ በእርግጥ እርም አደረገ፥ የአጋሪው መኖሪያውም እሳት ናት፦
4፥48 *”አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም ኀጢአት ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኀጢአት በእርግጥ ቀጠፈ”*፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدِ افْتَرَىٰ إِثْمًا عَظِيمًا
5:72 *”እነሆ በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፤ መኖሪያውም እሳት ናት”*። ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም። إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ

"ከዚህ ሌላ ያለውንም ኀጢአት ለሚሻው ሰው ይምራል" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት።
አላህ ከሺርክ ሌላ ያለውንም ኀጢአት ለሚሻው ሰው ቀጥቶት አሊያም በነቢያችን”ﷺ” ሸፋዓ ይምራል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 81, ሐዲስ 155
ዒምራን ኢብኑ ሑሴይን”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ጥቂት ሕዝብ ከእሳት ወጥተው ወደ ጀነት በሙሐመድ”ﷺ” ምልጃ ይገባሉ፤ ጀሀነሚዪን ተብለው ይጠራሉ*። حَدَّثَنَا عِمْرَانُ بْنُ حُصَيْن ٍ ـ رضى الله عنهما ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ يَخْرُجُ قَوْمٌ مِنَ النَّارِ بِشَفَاعَةِ مُحَمَّدٍ صلى الله عليه وسلم فَيَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ، يُسَمَّوْنَ الْجَهَنَّمِيِّينَ ‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 3, ሐዲስ 41
አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ *”እኔም፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በትንሳኤ ቀን ማነው እድለኛ ሰው የእርስዎን ምልጃ የሚያገኘው? አልኩኝ፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አቢ ሁረይራ ሆይ! ንግግር ለመማር የአንተን ቆይታ ዐውቃለው፤ እንደማስበው ስለዚህ ጉዳይ ከአንተ በፊት ማንም አልጠየቀኝም። በትንሳኤ ቀን የእኔን ምልጃ የሚያገኝ እድለኛ ሰው ከልቡ ወይም ከነፍሱ፦ “ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” ያለ ነው*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّهُ قَالَ قِيلَ يَا رَسُولَ اللَّهِ، مَنْ أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِكَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ لَقَدْ ظَنَنْتُ يَا أَبَا هُرَيْرَةَ أَنْ لاَ يَسْأَلَنِي عَنْ هَذَا الْحَدِيثِ أَحَدٌ أَوَّلُ مِنْكَ، لِمَا رَأَيْتُ مِنْ حِرْصِكَ عَلَى الْحَدِيثِ، أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ مَنْ قَالَ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ، خَالِصًا مِنْ قَلْبِهِ أَوْ نَفْسِهِ ‏”‌‏.‏

አምላካችን አላህ የእርሱን ይቅርታና ምሕረት አግኝተው ጀነት ከሚገቡ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ጽላት እና ታቦት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

7፥145 *ለእርሱም በሰሌዳዎቹ ላይ ከነገሩ ሁሉ ግሳጼንና ለነገሩም ሁሉ ማብራራትን ጻፍንለት*፡፡ وَكَتَبْنَا لَهُ فِي الْأَلْوَاحِ مِن كُلِّ شَيْءٍ

“ጽሌ” ማለት “ሰሌዳ” “ፊደል” ማለት ነው፤ የጽሌ ብዙ ቁጥር “ጽላት” ሲሆን “ሰሌዳዎች” ወይም “ፊደሎች” ማለት ነው፤ በዕብራይስጥ ደግሞ “ላሁት” לֻחֹ֣ת ሲሆን በዐረቢኛ “ለውሕ” لَوْح ነው፣ አምላካችን አላህ ለሙሳ ቃላትን በፊደል ላይ ጽፎ እንደሰጠው በተከበረ ቃሉ ይናገራል፦
7፥145 *ለእርሱም በሰሌዳዎቹ ላይ ከነገሩ ሁሉ ግሳጼንና ለነገሩም ሁሉ ማብራራትን ጻፍንለት*፡፡ وَكَتَبْنَا لَهُ فِي الْأَلْوَاحِ مِن كُلِّ شَيْءٍ
7፥154 *ከሙሳም ቁጣው በበረደ ጊዜ ሰሌዳዎቹን በግልባጫቸው ውስጥ ለእነዚያ እነርሱ ጌታቸውን የሚፈሩ ለኾኑት መምሪያና እዝነት ያለባቸው ሲኾኑ ያዘ*፡፡ وَلَمَّا سَكَتَ عَن مُّوسَى الْغَضَبُ أَخَذَ الْأَلْوَاحَ ۖ وَفِي نُسْخَتِهَا هُدًى وَرَحْمَةٌ لِّلَّذِينَ هُمْ لِرَبِّهِمْ يَرْهَبُونَ

ይህን ድርጊት በፔንታተች በተመሳሳይ መልኩ ተመዝግቧል፦
ዘጸአት 24፥12 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፥ በዚያም ሁን፤ *እነርሱን ታስተምር ዘንድ እኔ የጻፍሁትን ሕግና ትእዛዝ የድንጋይም ጽላት እሰጥሃለሁ አለው*።

“ታቦት” ማለት “ማህደር” “ሰገባ” “ሳጥን” “ማደሪያ” ማለት ነው፣ በዕብራይስጥ ደግሞ “አሮውን” אֲר֖וֹן ሲሆን በዐረቢኛ “አት-ታቡት” التَّابُوتُ ነው፣ አምላካችን አላህ ስለ ታቡት እንዲህ ይለናል፦
2፥248 ነቢያቸውም ለእነርሱ፡- *«የንግሥናው ምልክት ከጌታችሁ የኾነ እርጋታ የሙሳ ቤተሰብና የሃሩን ቤተሰብ ከተውትም ቅርስ በውስጡ ያለበት መላእክት የሚሸከሙት ኾኖ “ሳጥኑ” ሊመጣላችሁ ነው*፡፡ አማኞች ብትኾኑ በዚህ ለእናንተ እርግጠኛ ምልክት አልለ» አላቸው፡፡ وَقَالَ لَهُمْ نَبِيُّهُمْ إِنَّ آيَةَ مُلْكِهِ أَن يَأْتِيَكُمُ التَّابُوتُ فِيهِ سَكِينَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَبَقِيَّةٌ مِّمَّا تَرَكَ آلُ مُوسَىٰ وَآلُ هَارُونَ تَحْمِلُهُ الْمَلَائِكَةُ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

“ሳጥኑ” ለሚለው ቃል የገባው “አት-ታቡት” التَّابُوتُ ነው፤ ይህ ቃል የሙሳ እናት ለጣለችው ሳጥን አገልግሎት ላይ ውሏል፦
20፥39 *«ሕፃኑን በሳጥኑ ውስጥ ጣይው*፡፡ እርሱንም ሳጥኑን በባሕር ላይ ጣይው፡፡ ባሕሩም በዳርቻው ይጣለው፡፡ ለእኔ ጠላት ለእርሱም ጠላት የኾነ ሰው ይይዘዋልና በማለት ባሳወቅን ጊዜ ለገስንልህ፡፡ أَنِ اقْذِفِيهِ فِي التَّابُوتِ فَاقْذِفِيهِ فِي الْيَمِّ فَلْيُلْقِهِ الْيَمُّ بِالسَّاحِلِ يَأْخُذْهُ عَدُوٌّ لِّي وَعَدُوٌّ لَّهُ ۚ وَأَلْقَيْتُ عَلَيْكَ مَحَبَّةً مِّنِّي وَلِتُصْنَعَ عَلَىٰ عَيْنِي

ይህንን እንዲህ በእንዲህ ካየን ዘንዳ ታቦት የጽላቱ ማህደር ወይም ሰገባ ሲሆን ይህን ድርጊት በፔንታተች በተመሳሳይ መልኩ ተመዝግቧል፦
ዘጸአት 25፥10 *ከግራር እንጨትም “ታቦትን” ይሥሩ፤ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን*።
ዘዳግም 10፥5 *ተመልሼም ከተራራው ወረድሁ፥ “ጽላቶችንም በሠራሁት ታቦት ውስጥ አደረግኋቸው” እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ በዚያ ኖሩ*።
ይህ እንዲህ ከሆነ ይህ ጽላት እና ታቦት የት ገባ? በተለይ የአገራችን ሰዎች እንደሚተርኩልን ይህን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ አቢሲኒያ በዘጠነኛው ክፍለ-ዘመን በሰለሞን ዘመነ-መንግሥት እንደገባ ይነገራል፣ ነገር ግን በዓለማችን ታሪክ ላይ ታቦቱ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ እንደጠፋና ከዚያ በፊት ኢየሩሳሌም ውስጥ እንደነበረ ተዘግቧል፤ በተጨማሪ የእዝራ ሱቱኤል ጸሐፊ ታቦቱ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ እንደተማረከና እንደጠፋ ይዘግባል፦
እዝራ ሱቱኤል 9፥21-23 ቤተ መቅደሳችን እንደፈረሰ አታይም? ግናይቱ እንደጠፍች ምስጋና እንደቀረ ዘውዳችን እንደወደቀ ተድላ ደስታችን እንደጠፍ የህጋች ማደሪያ *ታቦተ ፅዮን እንደተማረከች ንዋየ ቅዱሳት አንዳደፉ ምልኮታችን እንደቀረ። ከዚህ ሁሉ የሚበልጥ ታቦተ ፅዮን እንደጠፍች ቀረች*፤ ከእሷም ንዋየ ቅድሳቱ ተማርኮ ሄደ በጠላቶቻችን በባቢሎን እጅ ወደቅን።

እንደውም በተረፈ ኤርሚያስ ላይ የሚያገለግሉበትን ንዋየ-ቅዱሳት ሁሉ ጌታ እንዳዘዛቸው ለምድር ሰጧት ምድርም ያን ጊዜ ተቀብላ ዋጠችው ይለናል፦
ተረፈ ኤርሚያስ 8፥13 *"ባሮክ እና ኤርምያስም ወደ ቤተ መቅደስ ገቡ የሚያገለግሉበትን ዕቃ ሁሉ ጌታ እንዳዘዛቸው ለምድር ሰጧት ምድርም ያን ጊዜ ተቀብላ ዋጠችው"*።

የአገራችን ታሪክ የተፋለሰ መሆኑን የምናውቀው ይህ ጥቅስ ታቦተ ጽዮን በባቢሎናውያን እንደጠፋች መናገሩ ነው። ከዚያም ባሻገር ከሰለሞን 400 ዓመት በኋላ በኢዮስያስ ዘመነ-መንግሥት ታቦቱ በኢየሩሳሌም መኖሩን በዜና መዋዕል ላይ ተዘግቧል፦
ዜና መዋዕል ካልዕ 35፥3 እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት፥ ለእግዚአብሔርም ለተቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አለ፦ *ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ *አኑሩት*፤ ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም፤

ታቦተ ጽዮን አክሱም ላይ አለች የሚለው ትረካ ከክብረ ነገሥት ውጪ የታሪክ፣ የባይብል እና የሥነ-ቅርፅ መረጃ ሆነ ማስረጃ የለም። ታቦቱ እና ጽላቱ ቢኖሩም እንኳን በአዲስ ኪዳን ጥቅም የላቸውም። የአዲስ ኪዳን ታላቁ ጸሐፊ ጳውሎስ እንደሚነግረን ከሆነ ሙሴ ንዋየ-ቅዱሳቱን የሚሰራው የሚመጣውን ነገር እያየ እንደነበር ተዘግቧል፦
ዕብራውያን 8፥5 እነርሱም *ሙሴ ድንኳኒቱን ሊሠራ ሳለ እንደ ተረዳ፥ ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ የሚሆነውን ያገለግላሉ። በተራራው እንደ ተገለጠልህ ምሳሌ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ተጠንቀቅ ብሎት ነበርና*።
ዘጸአት 25፥40 በተራራ ላይ *እንዳሳየሁህ ምሳሌ እንድትሠራ ተጠንቀቅ*።
የሐዋርያት ሥራ 7፥44 *እንዳየው ምስል አድርጎ ይሠራት ዘንድ ሙሴን ተናግሮ እንዳዘዘው፥ የምስክር ድንኳን ከአባቶቻችን ዘንድ በምድረ በዳ ነበረች*፤
ይህንን ጳውሎስ ታቦትና ጽላት “ጥላ”typology” እንደሆነ ይናገራል፤ ብሉይ ላይ የነበረው ኪዳን በአዲስ ኪዳን ተሽሯል፤ ይህም ኪዳን ጥላነቱ ታቦቱ የሰው አካል ሲሆን የሚጻፍበት ፊደል ደግሞ ለሰው ልብ ምሳሌ ሆኖ አዲሱ ኪዳን በልብ የሚጻፍ መሆኑኑን ይነግረናል፦
ኤርምያስ 31፥31 እነሆ፥ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር *አዲስ ቃል ኪዳን* የምገባበት ወራት ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ከግብጽ አገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር *የምገባው ቃል ኪዳን ይህ* ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ *ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ*፥ *በልባቸውም እጽፈዋለሁ*፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።
ዕብራውያን 8፥10-13 ከዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና ይላል ጌታ፤ *ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ በልባቸውም እጽፈዋለሁ*፥ እኔም አምላክ እሆንላቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑልኛል። .. *አዲስ በማለቱ ፊተኛውን አስረጅቶአል፤ አሮጌና ውራጅ የሆነውስ ሊጠፋ ቀርቦአል*።

ብሉይ ማለት አሮጌ ማለት ነው። አሮጌ ያሰኘው አዲሱ ነው፣ አሮጌው ኪዳን ህጉ በድንጋይ ጽላት ላይ የተጻፈበት ኪዳን ሲሆን አዲሱ ደግሞ በልብ ጽላት ላይ የተጻፈበት ኪዳን ነው፣ በድንጋይ ላይ የተጻፈው ኪዳን አሮጌና ውራጅ እንደተባለ አስተውሉ፣ ከዚያም ባሻገር በአዲሱ ኪዳን አሮጌው ኪዳን ተሽሯል ይላል፦
2ኛ ቆሮ 3፥3 እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፥ *ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት* እንጂ *በድንጋይ ጽላት* ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው።
2ኛ ቆሮ 3፥7 ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለ *ተሻረው* ስለ ፊቱ ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ፥ *ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት* በክብር ከሆነ፥ የመንፈስ አገልግሎት እንዴት ይልቅ በክብር አይሆንም?
2ኛ ቆሮ 3፥13 *የዚያንም ይሻር* የነበረውን መጨረሻ ትኵር ብለው የእስራኤል ልጆች እንዳይመለከቱ፥ በፊቱ መጋረጃ እንዳደረገ እንደ ሙሴ አይደለንም።
2ኛ ቆሮ 3፥14 ነገር ግን አሳባቸው ደነዘዘ፡፡ ብሉይ ኪዳን ሲነበብ ያ መጋረጃ ሳይወሰድ እስከ ዛሬ ድረስ ይኖራልና፤ በክርስቶስ ብቻ *የተሻረ* ነውና።

ምን ትፈልጋለህ? በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸው ጽላት በልብ ጽላት ተሽሯል፣ ቤተመቅደሱም ሰው ሆኗል፦
1ኛ ቆሮ 3፥16-17 *የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ* የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? ማንም *የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ*።
1ኛ ቆሮ 6፥19-20 ወይስ *ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን?*

አዲሱ ኪዳን ህጉ የተጻፈው በልብ ጽላት ላይ ከሆነ ቤተመቅደሱ የሰው አካል ከሆነ እግዚአብሔር ሰው በሰራው ቤተ መቅደስ አይኖርም ይለናል፦
የሐዋርያት ሥራ 17፥24 ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና **እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም**፤
የሐዋርያት ሥራ 7፥50 ነገር ግን ነቢዩ፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት ቤት ትሠራላችሁ? ይላል ጌታ፥ ወይስ የማርፍበት ስፍራ ምንድር ነው? ይህንስ ሁሉ እጄ የሠራችው አይደለምን? እንዳለ፥ ልዑል *የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም*።
ኢሳይያስ 66፥1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ *የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው?*
ኤርምያስ 3፥16 በበዛችሁም ጊዜ በምድርም ላይ በረባችሁ ጊዜ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚያ ዘመን፦ *የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይጠሩም* ልብ አያደርጉትም፥ አያስቡትምም፥ አይሹትምም፥ *ከእንግዲህ ወዲህም አይደረግም*።

የሚገርመው የአገራችን ክርስቲያኖች ከብሉይ ኪዳን ስንጠቅስ “ተሽሯል” ይሉናል፣ የተሻረው ታቦቱትና ጽላቱ እንጂ ሕጉ አይደለም። ሕጉማ በልብ ተጽፏል ተብሏል። የአገራችን ክርስቲያኖች ሕጉ ተሽሯል ይሉና የተጻፈበት ድንጋይ ሆነ የሚቀመጥበት ታቦት አልተሻረም ብለው ድርቅ ይላሉ፣ እራሳቸውን የሚያስጠጉበት ጳውሎስ በግልጽ የድንጋይ ጽላት እንደተሻረና አምላክ ሰው በሰራው ቤተመቅደስ እንደማይኖር ተናግሯል፣ ነገር ግን ዛሬ ያሉት ያገራችን ሰዎች ዛርኒሽ በተቀባ እንጨት ቀርጸው ታቦት ነው ብለው ለታቦቱ ሲሰግዱ፣ ሲለማመኑ፣ ሲማጸኑ፣ ሲሳሉ፣ ዕጣን ሲያጨሱ ይታያል፣ ይህ በትንቢት ስለ እነርሱ የተነገረው እየተፈጸመ ነውና በተውበት ወደ አላህ ተመለሱና አንዱን አምላክ በብቸኝነት አምልኩ፦
ኢሳይያስ 44፥15-19 *ለሰውም ማገዶ ይሆናል፤ ከእርሱም ወስዶ ይሞቃል፥ አንድዶም እንጀራ ይጋግርበታል፤ ከእርሱም አምላክ አበጅቶ ይሰግድለታል፥ የተቀረጸውንም ምስል ሠርቶ በእርሱ ፊት ይንበረከካል። ግማሹን በእሳት ያቃጥላል፥ በዚያ በግማሹ ሥጋ ይበላል፥ ሥጋም ይጠብስበትና ይጠግባል፤ ይሞቃልና፦ እሰይ ሞቅሁ፥ እሳቱን አይቻለሁ ይላል። የቀረውንም እንጨት አምላክ አድርጎ ምስል ይቀርጽበታል፤ በፊቱም ተጐንብሶ ይሰግዳል ወደ እርሱም እየጸለየ፦ አምላኬ ነህና አድነኝ ይላል። አያውቁም፥ አያስቡም፤ እንዳያዩ ዓይኖቻቸውን፥ እንዳያስተውሉ ልቦቻቸውን ጨፍነዋል። በልቡም ማንም አያስብም፦ ግማሽዋን በእሳት አቃጥያለሁ፥ በፍምዋም ላይ እንጀራን ጋግሬአለሁ፥ ሥጋም ጠብሼ በልቻለሁ፤ የቀረውንም አስጸያፊ ነገር አደርጋለሁን? ለዛፍስ ግንድ እሰግዳለሁን? እንዲልም እውቀትና ማስተዋል የለውም*።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ውሸት ሲጋለጥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

17፥81 በልም *«እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»* وَقُلْ جَآءَ ٱلْحَقُّ وَزَهَقَ ٱلْبَٰطِلُ ۚ إِنَّ ٱلْبَٰطِلَ كَانَ زَهُوقًۭا

ሰው የሚዋሸት ከሁለት ነገር አንጻር ነው፥ አንዱ ባለማወቅ ሲሆን ሁለተኛው ሆን ብሎ ህሊናውን በመሸጥ ነው። እውነት ሲገለጥ ውሸት ይጋለጣል፥ እውነት ሲመጣ ውሸት ሁልጊዜ መቋቋው አይችልም። ውሸት በእውነት ፊት እሳት የነካው ሰም፣ ጸሐይ ያየው ቅቤ፣ ነፋስ የጎበኘው አቧራ ይሆናል። እውነትን በውሸት ላይ ስትጥለው ያፈራርሰዋል፥ ምክንያቱም ውሸትም መነሻም መድረሻም የለውምና እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነው፦
21፥18 በእርግጥ *እውነትን በውሸት ላይ እንጥላለን፡፡ አንጎሉን ያፈርሰዋልም፡፡ ወዲያውም እርሱ ጠፊ ነው፡፡ ለእናንተም ከዚያ ከምትመጥኑት ነገር ብርቱ ቅጣት አላችሁ፤ ወዮላችሁ*፡፡ بَلْ نَقْذِفُ بِٱلْحَقِّ عَلَى ٱلْبَٰطِلِ فَيَدْمَغُهُۥ فَإِذَا هُوَ زَاهِقٌۭ ۚ وَلَكُمُ ٱلْوَيْلُ مِمَّا تَصِفُونَ
34፥49 *«እውነቱ መጣ፤ ውሸትም መነሻም መድረሻም የለውም ተወገደ*» በላቸው፡፡ قُلْ جَآءَ ٱلْحَقُّ وَمَا يُبْدِئُ ٱلْبَٰطِلُ وَمَا يُعِيدُ

ይህንን ውሸት ለማጋለጥ እውነቱን እንግለጥ፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 63 ሐዲስ 75
ኑዐይም ኢብኑ ሐማድ እንደተረከው፤ ዐምር ኢብኑ መይሙን አለ፦ “በዘመነ-ድንቁርና ጊዜ ሴት ዝንጀሮ በብዙ ዝንጀሮዎች ተከባ አየው፤ ሕጋዊ ያልሆነ ተራክቦ አድርጋለች በሚል ምክንያት ሁሉም በድንጋይ ወገሯት፤ እኔም ከእነሱ ጋር ወገርኳት። حَدَّثَنَا نُعَيْمُ بْنُ حَمَّادٍ، حَدَّثَنَا هُشَيْمٌ، عَنْ حُصَيْنٍ، عَنْ عَمْرِو بْنِ مَيْمُونٍ، قَالَ رَأَيْتُ فِي الْجَاهِلِيَّةِ قِرْدَةً اجْتَمَعَ عَلَيْهَا قِرَدَةٌ قَدْ زَنَتْ، فَرَجَمُوهَا فَرَجَمْتُهَا مَعَهُمْ‏.‏

ቀጣፊዎች ይህንን ሐዲስ ይዘው፦ “ነብያችሁ”ﷺ” ዝንጅሮ ወግሯል” እያሉ ይቀጥፋሉ፤ ሲጀመር ይህንን ድርጊት አደረኩኝ እያለ ያለው ዐምር ኢብኑ መይሙን እንጂ ነብያችን”ﷺ” አይደሉም፤ ይህን የተናገሩት ነብያችን”ﷺ” ቢሆኑ ኖሮ ሐዲሱ በግልጽ “ቃለ ነብይ” ወይም “ቃለ ረሱል” ብሎ ይጀምር ነበር፤ የነብያችን”ﷺ ንግግር ሽታው እንኳን እዚህ ሐዲስ ላይ የለም።
ሲቀጥል ዐምር ኢብኑ መይሙን የተናገረው በዘመነ-ድንቁርና ጊዜ ማለትም ቁርአን ከመውረዱ በፊት የነበረውን የጨለማ ጊዜ በአውንታዊ ሳይሆን በአሉታዊ ለመግለፅ ነው።
እውነት ተገለጠ ውሸት ተጋለጠ፤ በልም እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነው፦
17፥81 በልም *«እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»* وَقُلْ جَآءَ ٱلْحَقُّ وَزَهَقَ ٱلْبَٰطِلُ ۚ إِنَّ ٱلْبَٰطِلَ كَانَ زَهُوقًۭا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኒፋቅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥145 *መናፍቃን በእርግጥ ከእሳት በታችኛው አዘቅት ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱም ረዳትን አታገኝላቸውም*፡፡ إِنَّ الْمُنَافِقِينَ فِي الدَّرْكِ الْأَسْفَلِ مِنَ النَّارِ وَلَن تَجِدَ لَهُمْ نَصِيرًا

“ኒፋቅ” نِفَاق የሚለው ቃል “ናፈቀ” نَافَقَ ማለትም “ነፈቀ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ኑፋቄ” ወይም “ምንፍቅና” አሊያም “አስመሳይነት” “በአፉ አምኖ በልቡ የሚክድ” ማለት ነው፤ “ኑፋቄ” የሚለው የግዕዝ ቃል “ነፈቀ” ማለትም “ከፈለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ክፍልፍል” ወይም “አራጥቃ” ማለት ነው፤ ዓመት ለሁለት ስንከፍለው ስድስት ወሩ “መንፈቅ” ይባላል። አለቃ ኪዳነ-ወልድ ክፍሌ ገፅ 645።

ስለዚህ “መናፍቅ” ማለት “በከፊሉ አምኖ በከፊሉ የሚክድ” ሙሉ ያልሆነ ጎደሎ እምነት ያለው ማለት ነው፤ ኒፋቅ በውስጥ ኩፍር በውጪ ኢማን የሆነ ሁለት አይነት ገጽታ ያለው ነገር ነው፤ ኒፋቅ ያለበት ግለሰብ ደግሞ በነጠላ “ሙናፊቅ” مُنَٰفِق ሲባል በብዜት “ሙናፊቁን” مُنَٰفِقُون ወይም “ሙናፊቂን” مُنَٰفِقِين ይባላል፤ በአማርኛችን በነጠላ “መናፍቅ” በብዜት “መናፍቃን” ማለት ነው። አላማቸው ኡማውን መከፋፈልና መበታተን ነው፦
63፥7 *እነርሱ እነዚያ ፡- «አላህ መልክተኛ ዘንድ ላሉት ሰዎች እስከሚበታተኑ ድረስ አትቀልቡ» የሚሉ ናቸው፡፡ የሰማያትና የምድር ድልቦችም የአላህ ናቸው፡፡ ግን መናፍቃን አያውቁም*፡፡ هُمُ الَّذِينَ يَقُولُونَ لَا تُنفِقُوا عَلَىٰ مَنْ عِندَ رَسُولِ اللَّهِ حَتَّىٰ يَنفَضُّوا ۗ وَلِلَّهِ خَزَائِنُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَلَـٰكِنَّ الْمُنَافِقِينَ لَا يَفْقَهُونَ

ውጪአቸው አማኝ ነው ውስጣቸው ግን ክህደት አለ፤ ወደ ሶላትም በቆሙ ጊዜ ታካቾች ስዎችን የሚያሳዩ ኾነው ይቆማሉ፤ አላህን እና እነዚያን ያመኑትን ያታልላሉ፤ የማያውቁ ሲኾኑ እራሳቸውን እንጅ ሌላን አያታልሉም፤ ወደ ቁርኣንና ወደ ሐዲስ አይመጡም፦
4፥142 *መናፍቃን አላህን ያታልላሉ፡፡ እርሱም አታላያቸው ነው፡፡ ወደ ሶላትም በቆሙ ጊዜ ታካቾች ስዎችን የሚያሳዩ ኾነው ይቆማሉ፡፡ አላህንም ጥቂትን እንጅ አያወሱም*፡፡ إِنَّ الْمُنَافِقِينَ يُخَادِعُونَ اللَّهَ وَهُوَ خَادِعُهُمْ وَإِذَا قَامُوا إِلَى الصَّلَاةِ قَامُوا كُسَالَىٰ يُرَاءُونَ النَّاسَ وَلَا يَذْكُرُونَ اللَّهَ إِلَّا قَلِيلًا
2፥8 *ከሰዎችም «በአላህና በመጨረሻው ቀን አምነናል» የሚሉ አሉ፤ እነርሱም አማኞች አይደሉም*፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يَقُولُ آمَنَّا بِاللَّهِ وَبِالْيَوْمِ الْآخِرِ وَمَا هُم بِمُؤْمِنِينَ
2፥9 *አላህን እና እነዚያን ያመኑትን ያታልላሉ፤ የማያውቁ ሲኾኑ እራሳቸውን እንጅ ሌላን አያታልሉም*፡፡ يُخَادِعُونَ اللَّهَ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَمَا يَخْدَعُونَ إِلَّا أَنفُسَهُمْ وَمَا يَشْعُرُونَ
3፥167 *እነዚያንም የነፈቁትን* እና ለእነርሱ «ኑ፤ በአላህ መንገድ ተጋደሉ፤ ወይም ተከላከሉ፤» የተባሉትን ሊገልጽ ነው፡፡ «መዋጋት መኖሩን ብናውቅ ኖሮ በተከተልናችሁ ነበር» አሉ፡፡ *እነርሱ ያን ጊዜ ከእምነት ይልቅ ወደ ክህደት የቀረቡ ናቸው፡፡ በልቦቻቸው የሌለውን በአፎቻቸው ይናገራሉ፡፡ አላህም የሚደብቁትን ዐዋቂ ነው*፡፡ وَلِيَعْلَمَ الَّذِينَ نَافَقُوا ۚ وَقِيلَ لَهُمْ تَعَالَوْا قَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ أَوِ ادْفَعُوا ۖ قَالُوا لَوْ نَعْلَمُ قِتَالًا لَّاتَّبَعْنَاكُمْ ۗ هُمْ لِلْكُفْرِ يَوْمَئِذٍ أَقْرَبُ مِنْهُمْ لِلْإِيمَانِ ۚ يَقُولُونَ بِأَفْوَاهِهِم مَّا لَيْسَ فِي قُلُوبِهِمْ ۗ وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا يَكْتُمُونَ
4፥61 ለእነርሱም፡- *«አላህ ወደ አወረደው ቁርኣን እና ወደ መልክተኛው ኑ» በተባሉ ጊዜ መናፍቃን ከአንተ መሸሽን ሲሸሹ ታያቸዋለህ*፡፡ وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ تَعَالَوْا إِلَىٰ مَا أَنزَلَ اللَّهُ وَإِلَى الرَّسُولِ رَأَيْتَ الْمُنَافِقِينَ يَصُدُّونَ عَنكَ صُدُودًا
2፥14 *እነዚያንም ያመኑትን በተገናኙ ጊዜ «አምነናል» ይላሉ፡፡ ወደ ሰይጣኖቻቸውም ባገለሉ ጊዜ «እኛ ከእናንተ ጋር ነን፤ እኛ በእነርሱ ተሳላቂዎች ብቻ ነን»* ይላሉ፡፡ وَإِذَا لَقُوا الَّذِينَ آمَنُوا قَالُوا آمَنَّا وَإِذَا خَلَوْا إِلَىٰ شَيَاطِينِهِمْ قَالُوا إِنَّا مَعَكُمْ إِنَّمَا نَحْنُ مُسْتَهْزِئُونَ

የመናፍቃን ቅጣቱ ከእሳት በታችኛው አዘቅት ውስጥ ናቸው፦
4፥145 *መናፍቃን በእርግጥ ከእሳት በታችኛው አዘቅት ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱም ረዳትን አታገኝላቸውም*፡፡ إِنَّ الْمُنَافِقِينَ فِي الدَّرْكِ الْأَسْفَلِ مِنَ النَّارِ وَلَن تَجِدَ لَهُمْ نَصِيرًا
9፥68 *መናፍቃንንና መናፍቃትን፣ ከሓዲዎችንም አላህ የገሀነምን እሳት በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ ቃል ገብቶላቸዋል፡፡ እርሷ በቂያቸው ናት፡፡ አላህም ረግሟቸዋል፡፡ ለእነርሱም ዘውታሪ ቅጣት አላቸው*፡፡ وَعَدَ اللَّهُ الْمُنَافِقِينَ وَالْمُنَافِقَاتِ وَالْكُفَّارَ نَارَ جَهَنَّمَ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ هِيَ حَسْبُهُمْ ۚ وَلَعَنَهُمُ اللَّهُ ۖ وَلَهُمْ عَذَابٌ مُّقِيمٌ

የሙናፊቅ ምልክቶች ሦስት ናቸው፦ ሲናገር ይዋሻል፣ ሲያምኑት ይከዳል፣ ቃል የገባውን ያፈርሳል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 55, ሐዲስ 12
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው ነብዩ”ﷺ” ሲናገሩ፦ *”የሙናፊቅ ምልክቶች ሦስት ናቸው፦ ሲናገር ይዋሻል፣ ሲያምኑት ይከዳል፣ ቃል የገባውን ያፈርሳል*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ آيَةُ الْمُنَافِقِ ثَلاَثٌ، إِذَا حَدَّثَ كَذَبَ، وَإِذَا اؤْتُمِنَ خَانَ، وَإِذَا وَعَدَ أَخْلَفَ ‏.‏
ነጥብ አንድ
“ሲታመን ይከዳል”
አምላካችን አላህ አማና ሲጣልብን አማናችን መወጣት እንዳለብን እንዲህ ይነግረናል፦
4፥58 *አላህ አደራዎችን ወደ ባለቤቶቻቸው እንድታደርሱ ያዛችኋል*፡፡ በሰዎችም መካከል በፈረዳችሁ ጊዜ በትክክል እንድትፈርዱ ያዛችኋል፡፡ አላህ በርሱ የሚገሥጻችሁ ነገር ምን ያምር! አላህ ሰሚ ተመልካች ነው፡፡ إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُكُمْ أَن تُؤَدُّوا الْأَمَانَاتِ إِلَىٰ أَهْلِهَا وَإِذَا حَكَمْتُم بَيْنَ النَّاسِ أَن تَحْكُمُوا بِالْعَدْلِ ۚ إِنَّ اللَّهَ نِعِمَّا يَعِظُكُم بِهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ سَمِيعًا بَصِيرًا
8፥27 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህንና መልክተኛውን አትክዱ፡፡ *አደራዎቻችሁንም እናንተ እያወቃችሁ አትክዱ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَخُونُوا اللَّهَ وَالرَّسُولَ وَتَخُونُوا أَمَانَاتِكُمْ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
23፥8 *እነዚያም እነርሱ ለአደራዎቻቸው እና ለቃል ኪዳናቸው ጠባቂዎች*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ
70፥32 *እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውን እና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ

ነጥብ ሁለት
“ሲናገር ይዋሻል”
ሙስሊም ከዋሸ ቀኑ ተበላሸ ይላል ያገሬ ሰው፤ አንድ ሙናፊቅ “ተላላ” “አባይ” “ቀላማጅ” “ዋሾ” “በጥራቃ” “ውሸታም” “ሐሰተኛ” “ወሽከታ” ነው፤ አምላካችን አላህ፦ “ሐሰትንም ቃል ራቁ” “ትክክለኛንም ንግግር ተናገሩ” ብሎ ያዘናል፦
22፥30 ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ፡፡ *ሐሰትንም ቃል ራቁ*፡፡ فَاجْتَنِبُوا الرِّجْسَ مِنَ الْأَوْثَانِ وَاجْتَنِبُوا قَوْلَ الزُّورِ
33፥70 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ *ትክክለኛንም ንግግር ተናገሩ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَقُولُوا قَوْلًا سَدِيدًا

ነጥብ ሦስት
“ቃል ገብቶ ያፈርሳል”
ቃል ገብቶ ማፍረስ ከመሃላ አይተናነስም፤ አምላካችን አላህ፦ “በቃል ኪዳኖች ሙሉ” ይለናል፦
5፥1 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በቃል ኪዳኖች ሙሉ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَوْفُوا بِالْعُقُودِ ۚ
23፥8 *እነዚያም እነርሱ ለአደራዎቻቸው እና ለቃል ኪዳናቸው ጠባቂዎች*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ
70፥32 *እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውን እና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ
17፥34 የየቲምንም ገንዘብ የብርታቱን ጊዜ እስኪደርስ ድረስ በዚያች እርሷ መልካም በኾነች ኹኔታ እንጂ አትቅረቡ፡፡ *በኪዳናችሁም ሙሉ፤ ኪዳን የሚጠየቁበት ነውና*፡፡ وَلَا تَقْرَبُوا مَالَ الْيَتِيمِ إِلَّا بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ حَتَّىٰ يَبْلُغَ أَشُدَّهُ ۚ وَأَوْفُوا بِالْعَهْدِ ۖ إِنَّ الْعَهْدَ كَانَ مَسْئُولًا

ነገር ግን ይህ ምልክት የሚታይበት ሁሉ ሙናፊቅ ላይሆን ይችላል፤ ግን መናፍቅ የሚያሰኘው ጉዳይ ነብያችን”ﷺ” እንዲህ ይነግሩናል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 116
ዐብዱላህ ኢብኑ ዐምር”ረ.ዐ.” እንደነገረን የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፡- *“አራት ነገሮች ያሉበት ሰው ግልጽ መናፍቅ ሆኗል፤ ከአራቱ ውስጥ አንዱ ያለበት ሰው ደግሞ እስኪተወው ድረስ ከኑፋቄ ከፊሉ ጠባይ አለበት ማለት ነው፤ አራቱ ነገሮች፡- ሲታመን ይከዳል፣ ሲናገር ይዋሻል፣ ቃል ገብቶ ያፈርሳል፣ ሲሟገት ያስተባብላል*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ أَرْبَعٌ مَنْ كُنَّ فِيهِ كَانَ مُنَافِقًا خَالِصًا وَمَنْ كَانَتْ فِيهِ خَلَّةٌ مِنْهُنَّ كَانَتْ فِيهِ خَلَّةٌ مِنْ نِفَاقٍ حَتَّى يَدَعَهَا إِذَا حَدَّثَ كَذَبَ وَإِذَا عَاهَدَ غَدَرَ وَإِذَا وَعَدَ أَخْلَفَ وَإِذَا خَاصَمَ فَجَرَ ‏”‏ ‏

ነጥብ አራት
“ሲሟገት ያስተባብላል”
መናፍቃን የአላህ አንቀጾች ግልጾች ኾነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ መከራከር ይወዳሉ፦
45፥25 *አንቀጾቻችንም ግልጾች ኾነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ ክርክራቸው* «እውነተኞች እንደ ኾናችሁ አባቶቻችንን አምጡ» *ማለት እንጅ ሌላ አልነበረም*፡፡ وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ آيَاتُنَا بَيِّنَاتٍ مَّا كَانَ حُجَّتَهُمْ إِلَّا أَن قَالُوا ائْتُوا بِآبَائِنَا إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ
10፥95 *ከእነዚያም የአላህን አንቀጾች ከአስተባበሉት አትሁን፡፡ ከከሳሪዎቹ ትሆናለህና*፡፡ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِ اللَّهِ فَتَكُونَ مِنَ الْخَاسِرِينَ
4፥107 *ከነዚያም እራሳቸውን ከሚበድሉት ላይ አትከራከር*፤ አላህ ከዳተኛ ኀጢአተኛ የሆነን ሰው አይወድምና። وَلَا تُجَادِلْ عَنِ الَّذِينَ يَخْتَانُونَ أَنفُسَهُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ خَوَّانًا أَثِيمًا
ነጥብ አምስት
“በጥቂት አለመብቃቃት”
በጥቂት መብቃቃትን የአማኞች ባህርይ ነው፤ በጥቂት አለመብቃቃት የመናፍቃን ባህርይ ነው፦
ኢማም ቡኻሪይ: መጽሐፍ 70, ሐዲስ 22
አቢ ዑመር”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ሙዕሚን በአንድ አንጀት ይመገባል፤ ካፊር ወይም ሙናፊቅ በሰባት አንጀት ይመገባል*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّ الْمُؤْمِنَ يَأْكُلُ فِي مِعًى وَاحِدٍ، وَإِنَّ الْكَافِرَ ـ أَوِ الْمُنَافِقَ فَلاَ أَدْرِي أَيَّهُمَا قَالَ عُبَيْدُ اللَّهِ ـ يَأْكُلُ فِي سَبْعَةِ أَمْعَاءٍ ‏”‌‏.

ሙዕሚን በአንድ አንጀት ይመገባል ማለት ሲበላ በቢሥሚላህ ስለሚጀምር በረካ አለው፣ ያጣቅመዋል እና ይብቃቃል ማለት እንጅ አንድ ነው አንጀቱ ማለት አይደለም። በተጨማሪም ካፊር ወይም ሙናፊቅ በሰባት አንጀት ይመገባል ማለት በቢሥሚላህ ስለማይጀምር በረካ የለውም፣ አያጣቅመውም እና አይብቃቃም ማለት እንጅ ሰባት ነው አንጀቱ ማለት አይደለም። ይህ “መዕነዊይ” ማለትም “ፍካሬአዊ” አነጋገር እንጂ “ሒስሲይ” ማለትም “እማሬአዊ” አይደለም።

ነጥብ ስድስት
“ቁርአንን የሚቀራ ሙናፊቅ”
ቁርአንን የሚቀራ ሙናፊቅ ልክ እንደ አሪቲ ነው፤ ሽታው ያውዳል ጣዕሙ ግን ይመራል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 6 , ሐዲስ 288,
ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *“ቁርአንን የሚቀራ አማኝ ምሳሌው ልክ “እንደ” ትርንጎ ነው፤ ሽታው ጥሩ ነው ጣዕሙም ጥሩ ነው። ቁርአንን የማይቀራ አማኝ ደግሞ ልክ እንደ ተምር ነው፤ ሽታ የለውም ጣዕም ግን አለው። ቁርአንን የሚቀራ ሙናፊቅ አምሳያው ልክ እንደ አሪቲ ነው፤ ሽታው ያውዳል ጣዕሙ ግን ይመራል። ቁርአንን የማይቀራ ሙናፊቅ ደግሞ ልክ እንደ እንቧይ ነው ሽታ የለውም፤ ጣዕሙም መራራ ነው”* عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْمُؤْمِنُ الَّذِي يَقْرَأُ الْقُرْآنَ وَيَعْمَلُ بِهِ كَالأُتْرُجَّةِ، طَعْمُهَا طَيِّبٌ وَرِيحُهَا طَيِّبٌ، وَالْمُؤْمِنُ الَّذِي لاَ يَقْرَأُ الْقُرْآنَ وَيَعْمَلُ بِهِ كَالتَّمْرَةِ، طَعْمُهَا طَيِّبٌ وَلاَ رِيحَ لَهَا، وَمَثَلُ الْمُنَافِقِ الَّذِي يَقْرَأُ الْقُرْآنَ كَالرَّيْحَانَةِ، رِيحُهَا طَيِّبٌ وَطَعْمُهَا مُرٌّ، وَمَثَلُ الْمُنَافِقِ الَّذِي لاَ يَقْرَأُ الْقُرْآنَ كَالْحَنْظَلَةِ، طَعْمُهَا مُرٌّ ـ أَوْ خَبِيثٌ ـ وَرِيحُهَا مُرٌّ ‏”

ኒፋቅ በሁለት ይከፈላል፤ አንደኛው ኒፋቁል አስገር ሲሆን ይህ ባህርይ ያለበት ሙናፊቅ ባይሰኝም ግን ከላይ የተዘረዘሩት የታመኑት ጊዜ መካድ፣ ሲናገሩ መዋሸት፣ ቃል ገብቶ ማፍረስ፣ ቀጠሮን ማዛባት፣ ሲከራከር ማስተባበል ናቸው።
ሁለተኛው ኒፋቁል አክበር ሲሆን ይህ ሰው ሙናፊቅ ይባላል፤ የትልቁ ኒፋቅ ምልክቶች የአላህን መልእክተኛ ማስተባበል፣ የተቀበሉትን መልእክት በከፊሉ ማስተባበል፣ እሳቸውን መጥላት፣ መልእክታቸውን መጥላት፣ በኢስላም ዝቅ ማለት መደሰት፣ የኢስላም የበላይነትን መጥላት ናቸው ወዘተ ናቸው። ሙናፊቅ ማለት የሚችለው አላህ ብቻ ነው። ምክንያቱም ኒፋቅ ልብ ላይ ያለ በሽታ ነው፦
4፥63 *እነዚህ እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው፤ እነርሱንም ተዋቸው፤ ገሥጻቸውም፤ ለእነርሱም በራሳቸው ውስጥ ስሜት ያለውን ቃል ተናገራቸው*። ﺃُﻭﻟَﺌِﻚَ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﻌْﻠَﻢُ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻣَﺎ ﻓِﻲ ﻗُﻠُﻮﺑِﻬِﻢْ ﻓَﺄَﻋْﺮِﺽْ ﻋَﻨْﻬُﻢْ ﻭَﻋِﻈْﻬُﻢْ ﻭَﻗُﻞْ ﻟَﻬُﻢْ ﻓِﻲ ﺃَﻧْﻔُﺴِﻬِﻢْ ﻗَﻮْﻟًﺎ ﺑَﻠِﻴﻐًﺎ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ
3፥118 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *ከእናንተ ሌላ ምስጢረኛን አትያዙ፤ ማበላሸትን አይገቱላችሁም፤ ጉዳታችሁን ይወዳሉ፥ ጥላቻይቱ ከአፎቻቸዉ በእርግጥ ተገለጸች። ልቦቻቸዉም የሚደብቁት ይበልጥ ትልቅ ነዉ*። ልብ የምታደርጉ እንደሆናችሁ ለእናንተ ማብራራያዎችን በእርግጥ ገለጽን። يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا بِطَانَةً مِّن دُونِكُمْ لَا يَأْلُونَكُمْ خَبَالًا وَدُّوا مَا عَنِتُّمْ قَدْ بَدَتِ الْبَغْضَاءُ مِنْ أَفْوَاهِهِمْ وَمَا تُخْفِي صُدُورُهُمْ أَكْبَرُ ۚ قَدْ بَيَّنَّا لَكُمُ الْآيَاتِ ۖ إِن كُنتُمْ تَعْقِلُونَ

አላህ የቀልብ በሽታ ከሆነው ከኒፋቅ ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ግዝረተ-ኢየሱስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

21፥22 *የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ*። فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ

ፈጣሪ ጾታ የለውም። ሴትም ወንድም አይደለም፥ የሴትም የወንድም ሩካቤ ስጋ የለውም። ከዚህ በተቃራኒ ግን ኢየሱስ ጾታ አለው ወንድ ነው፦
ሉቃስ 1፥31 እነሆም፥ ትፀንሻለሽ *"ወንድ"* ልጅም *ትወልጃለሽ*፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።

ጾታው ወንድ ስለሆነ የወንድ ሩካቤ ስጋ አለው፥ ይህ ሩካቤ ስጋ"sex organ" ሽንት ለመሽናት እና ከሴት ጋር ተራክቦ"intercourse" ለማድረግ ያገለግላል። ወንድ ሩካቤ ስጋው ላይ ያለውን ሸለፈት በስምንተኛ ቀን ይገረዛል፦
ዘፍጥረት 17፥12 *የስምንት ቀን ልጅ ይገረዝ*፤ በቤት የተወለደ ወይም ከዘራችሁ ያይደለ በብርም ከእንግዳ ሰው የተገዛ፥ ወንድ ሁሉ በትውልዳችሁ ይገረዝ።

ኢየሱስም ስምንት ቀን ሲሞላው ተገርዟል፥ በማህጸን ከመረገዙ ማለትም ከመጸነሱ በፊት ስም እንደወጣለት ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ፦
ሉቃስ 2፥21 *"ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይጸነስ በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ"*።
ሮሜ 15፥9 *"ክርስቶስ ስለ እግዚአብሔር እውነት የመገረዝ አገልጋይ ሆነ"* እላለሁ።

ይህ የተገረዘውን ሕጻን በጌታ ፊት ያቆሙት ዘንድ ዮሴፍና ማርያም ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት፦
ሉቃስ 2፥24 *"እንደ ሙሴም ሕግ የመንጻታቸው ወራት በተፈጸመ ጊዜ፥ በጌታ ሕግ፦ የእናቱን ማኅፀን የሚከፍት ወንድ ሁሉ ለጌታ የተቀደሰ ይባላል ተብሎ እንደ ተጻፈ *"በጌታ ፊት ሊያቆሙት፥ በጌታም ሕግ፦ ሁለት ዋሊያ ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች እንደ ተባለ፥ መሥዋዕት ሊያቀርቡ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት"*።

አስቡት ፈጣሪ ጾታ ኖሮት፣ ወንድ ሆኖ፣ ተገርዞ፣ በጌታ ፊት ሊያቆሙት ሲወስዱት። አያችሁ የሁሉ ጌታ እና ሕጻኑ ሁለት የለያዩ ኑባሬ እንደሆኑ?
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጥር 6 ቀን በዓመት አንዴ "ግዝረተ ኢየሱስ" ተብሎ የተገዘረበትን ዓመታዊ ክብረ በዓል ትዘክራለች። "ግዝረት" ማለት የግዕዝ ቃል ሲሆን "ግርዘት"circumcision" ማለት ነው። ይህ ተቆርጦ የተገዘረው ሸለፈት ስጋ አምላክ ነው፥ ይመለካል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 78፥31
ቄርሎስም አለ፦
“ወዓዲ ንቤ እስመ ሥጋሁ ለእግዚእነ ክርስቶስ አምላክ ውእቱ”

ትርጉም፦
“ዳግመኛ የጌታችን የክርስቶስ ስጋ አምላክ እንደሆነ እንናገራለን”

"የክርስቶስ ስጋ አምላክ እንደሆነ እንናገራለን" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ያ የተገዘው ሸለፈት ስጋ አምላክ ከነበረ ዛሬ የት ይገኛል? አሁን ተሸልቶ አፈር ሆኖ ታመልኩታላችሁን? የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ፦
21፥22 *የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ*። فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ውይይት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16:125 ወደ ጌታህ መንገድ *በብልሃትና በመልካም ግሣጼ በለዘብታ ቃል ጥራ”፤ በዚያችም እርሷ መልካም በሆነችው “ዘዴ ተከራከራቸው”*፤ ٱدْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِٱلْحِكْمَةِ وَٱلْمَوْعِظَةِ ٱلْحَسَنَةِ ۖ وَجَٰدِلْهُم بِٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ ۖ وَهُوَ أَعْلَمُ بِٱلْمُهْتَدِينَ

"ውይይት" በተቃናቃኝ እና በአቀንቃኝ አሊያም በአውንታዊ እና በአሉታዊ አመለካከት ባላቸው ሰዎች መካከል የሚደረግ ሙግት ብቻ ሳይሆን ችግር ሲመጣ የመጣው ችግር ለማንበብ፣ ለመረዳት፣ ለመፍታት አይነተኛ ቁልፍ ነው፤ ማንኛውም ውይይት አላህ ይሰማዋል፣ ያውቀዋል፣ የቂያማ ቀን በቀኝና በግራ ያሉት መላእክትም ውይይታችንን ጽፈውት ያስጠይቀናል፦
9፥78 አላህ ምስጢራቸውን እና *ውይይታቸውን የሚያውቅ መኾኑን* አላህም ሩቆችን ሁሉ በጣም ዐዋቂ መኾኑን አያውቁምን? أَلَمْ يَعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ سِرَّهُمْ وَنَجْوَىٰهُمْ وَأَنَّ ٱللَّهَ عَلَّٰمُ ٱلْغُيُوبِ
43፥80 ወይም እኛ ምስጢራቸውን እና *ውይይታቸውን የማንሰማ መኾናችንን ያስባሉን? አይደለም፤ መልክተኞቻችንም እነርሱ ዘንድ ይጽፋሉ*፡፡ أَمْ يَحْسَبُونَ أَنَّا لَا نَسْمَعُ سِرَّهُمْ وَنَجْوَىٰهُم ۚ بَلَىٰ وَرُسُلُنَا لَدَيْهِمْ يَكْتُبُونَ

ስለዚህ ውይይት ለአላህ ውዴታ ተብሎ የሚቀርብ የማስተማሪያ ጥበብ እንጂ የሌላውን ሰው ሃሳብና ስሜት ለማብጠልጠል፣ ለማጠልሸት፣ ለማበሻቀጥ፣ ለማነወር፣ ተብሎ የሚደረግ ንትርክ ወይም እሰጣገባ አይደለም። ለውይይት ምህዳር የሚሆኑ ቅድመ-ሁኔታ እስቲ ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"ሥነ-እውነት"
የሥነ-እውነት ጥናት"metaphysics" ምሁራን እንደሚያትቱት እውነት አንድ ሲሆን ሁለት ገፅታዎች አሉት፤ አንዱ "ውሳጣዊ እውነታ"subjective truth" ሲሆን ለምሳሌ እኔ አሳ መብላት እወዳለው ብል፤ ሌላ ሰው አልወድም ብንል ሁለታችንም ትክክል ነን፤ ይህ "ውሳጣዊ እውነታ" ይባላል፤ ሁለተኛው ደግሞ "ውጫዊ እውነታ"objective truth" ሲሆን ለምሳሌ ቢጫ ቀለም በየትኛውም ቋንቋ ስሙ ይቀያየር እንጂ ቢጫ ቀይ፣ አረንጓዴ፣ ነጭ አይደለም፤ ይህ "ውጫዊ እውነታ" ይባላል፤ አንድ ሰው ይህንን እውነታ ሲቃረን ዕውቀት ጎድሎት በመሃይምነት እንዳለ ያሳብቅበታል። አምላካችን አላህ ከሰዎች ጋር ባለን መስተጋብር፦ "ትክክለኛውንም ንግግር” ተናገሩ" "ሐሰትንም ቃል ራቁ" ይለናል፦
33:70 እላንተ ያመናችሁ ሆይ አላህን ፍሩ፤ *ትክክለኛውንም ንግግር” ተናገሩ*። يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَقُولُوا۟ قَوْلًۭا سَدِيدًۭا
22፥30 ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ፡፡ *ሐሰትንም ቃል ራቁ*፡፡ فَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلرِّجْسَ مِنَ ٱلْأَوْثَٰنِ وَٱجْتَنِبُوا۟ قَوْلَ ٱلزُّورِ

እውነትን ለመግለጥ ሃሰትን ለማጋለጥ እውነቱ ምንድን ነው? ሃሰቱ ምንድን ነው? ብሎ መሞገት እንጂ እውነተኛው ማን ነው? ሃሰተኛው ማነው? ካልክ ሰውዬው ወደ ግትረኛነት ወይም ወደ መበሻሸቅ ይሄዳል፤ ስለዚህ ውይይት ለማድረግ ሃቅ መያዝ አይነተኛ ሚና ነው፤ አንድ ሰው እውነተኛ ለመሆን ማስረጃ ማቅረብ አለበት፤ ሁሌም ማስረጃ ከያዙ እውነተኞች ጋር መሆን አለብን፦
2፥111 *እውነተኞች እንደኾናችሁ ማስረጃችሁን አምጡ* በላቸው፡፡ قُلْ هَاتُوا۟ بُرْهَٰنَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
9፥119 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ *ከእውነተኞቹም ጋር ኹኑ*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَكُونُوا۟ مَعَ ٱلصَّٰدِقِينَ

የተሟላ ማስረጃ ማለት ደግሞ ከአላህ የሚመጣው የአላህ ንግግር ነው፦
6፥149 *የተሟላው ማስረጃ የአላህ ነው*፡፡ በሻም ኖሮ ሁላችሁንም ባቀናችሁ ነበር» *በላቸው*፡፡ قُلْ فَلِلَّهِ ٱلْحُجَّةُ ٱلْبَٰلِغَةُ ۖ فَلَوْ شَآءَ لَهَدَىٰكُمْ أَجْمَعِينَ
45፥6 *እነዚህ በአንተ ላይ በእውነት የምናነባቸው ሲኾኑ የአላህ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ከአላህና ከማስረጃዎቹም ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ*? تِلْكَ ءَايَٰتُ ٱللَّهِ نَتْلُوهَا عَلَيْكَ بِٱلْحَقِّ ۖ فَبِأَىِّ حَدِيثٍۭ بَعْدَ ٱللَّهِ وَءَايَٰتِهِۦ يُؤْمِنُونَ
ነጥብ ሁለት
"ሥነ-ዕውቀት"
"የሥነ-ዕውቀት ጥናት"epistemology" ምሁራን ዕውቀት በሁለት ይከፍሉታል፤ አንዱ "ውሳጣዊ ዕውቀት"Rational knowledge" ሲሆን ለምሳሌ ከውስጥ የሚመጣ እሳቤ፣ ፈጠራ፣ መፍትሔ ወዘተ "ውሳጣዊ እውነታ" ይባላል፤ ሁለተኛው ደግሞ "ውጫዊ ዕውቀት"Irational knowledge" ሲሆን ለምሳሌ ልምድ፣ ተሞርኮ፣ ሰርቶ ማሳያ ወዘተ "ውጫዊ ዕውቀት" ይባላል፤ ዕውቀት ለብዙ ነገር ማስረጃ ነው፤ እውነተኛ ሰው በዕውቀት ይናገራል፤ ያለ ዕውቀት አንድን እምነት መከተል ያስጠይቃል፦
6፥143 *እውነተኞች እንደሆናችሁ በዕውቀት ንገሩኝ* በላቸው፡፡ نَبِّـُٔونِى بِعِلْمٍ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
17፥36 *ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል*፡፡ መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም እነዚህ ሁሉ ባለቤታቸው ከእነርሱ ተጠያቂ ነውና፡፡ وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِۦ عِلْمٌ ۚ إِنَّ ٱلسَّمْعَ وَٱلْبَصَرَ وَٱلْفُؤَادَ كُلُّ أُو۟لَٰٓئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْـُٔولًۭا

አንድ ነገረኛ ወሬን ቢያመጣልን በስሕተት ላይ ሆነን ሕዝቦችን እንዳንጎዳ እና በሠራነው ነገር ላይ ተጸጻቾች እንዳንሆን በዕውቀት በተደገፈ ማስረጃ ማረጋገጥ አለብን፦
49:6 እላንተ ያመናችሁ ሆይ ነገረኛ *ወሬን ቢያመጣላችሁ” በስሕተት ላይ ሆናችሁ “ሕዝቦችን እንዳትጎዱ” እና በሠራችሁት ነገር ላይ “ተጸጻቾች” እንዳትሆኑ ”አረጋግጡ”*። يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِن جَآءَكُمْ فَاسِقٌۢ بِنَبَإٍۢ فَتَبَيَّنُوٓا۟ أَن تُصِيبُوا۟ قَوْمًۢا بِجَهَٰلَةٍۢ فَتُصْبِحُوا۟ عَلَىٰ مَا فَعَلْتُمْ نَٰدِمِينَ

ዕውቀት ከሰው ልጅ አዕምሮ ሲመጣ "ዐቅል" عقل ሲባል ወሕይ ሆኖ ወደ ነብያት ሲመጣ ደግሞ "ነቅል" نفل ይባላል፤ ለምሳሌ ቁርአን ከዕውቀት ጋርም የተዘረዘረ መጽሐፍ ነው፤ ነብያችን"ﷺ" የማያውቁት እና ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቃቸው አላህ ነው፦
7፥52 *ከዕውቀት ጋርም የዘረዘርነው የኾነን መጽሐፍ ለሚያምኑ ሕዝቦች መምሪያና እዝነት ሲኾን በእርግጥ አመጣንላቸው*፡፡ وَلَقَدْ جِئْنَٰهُم بِكِتَٰبٍۢ فَصَّلْنَٰهُ عَلَىٰ عِلْمٍ هُدًۭى وَرَحْمَةًۭ لِّقَوْمٍۢ يُؤْمِنُونَ
4፥114 *አላህም በአንተ ላይ መጽሐፍንና ጥበብን አወረደ፤ የማታውቀውንም ሁሉ ዐሳወቀህ*፡፡ የአላህም ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው፡፡ وَأَنزَلَ ٱللَّهُ عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحِكْمَةَ وَعَلَّمَكَ مَا لَمْ تَكُن تَعْلَمُ ۚ وَكَانَ فَضْلُ ٱللَّهِ عَلَيْكَ عَظِيمًۭا
55፥1-2 *አል-ረሕማን ቁርኣንን አሳወቀ*፡፡ ٱلرَّحْمَٰنُ عَلَّمَ ٱلْقُرْءَانَ
96፥5 *ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን*፡፡ عَلَّمَ ٱلْإِنسَٰنَ مَا لَمْ يَعْلَمْ

ነጥብ ሶስት
"ሥነ-አመክንዮ"
"የሥነ-አመክንዮ"Logic" ምሁራን "ሙግት"argument" በሁለት ይከፍሉታል፤ አንዱ "ስሙር ሙግት"valid argument" ሲሆን ይህ ሙግት በእማኝነትና በአስረጂነት ጠቅሶና አጣቅሶ መሟገት ነው፤ በትክክለኛው የአስተላለፍ ስልትና አወቃቀር ስለተዋቀረ የራሱ የሆነ መንደርደሪ፣ የሙግት ነጥብ"premise"፣ መደምደሚያ ያለው ነው፤ ዕውቀት ላይ የተመሰረተ ማስረጃ በአጽንኦትና በአንክሮት ለማዳመጥ ጥልና ጥንፍፍ ያለ መረዳት ነው፤ ይህን ሙግት አምላካችን አላህ መልካም ክርክር ይለዋል፤ ይህ ዘዴ ርቱዕ አካሄድ"optimistic approach" ነው፦
16:125 ወደ ጌታህ መንገድ *በብልሃትና በመልካም ግሣጼ በለዘብታ ቃል ጥራ”፤ በዚያችም እርሷ መልካም በሆነችው “ዘዴ ተከራከራቸው”*፤ ٱدْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِٱلْحِكْمَةِ وَٱلْمَوْعِظَةِ ٱلْحَسَنَةِ ۖ وَجَٰدِلْهُم بِٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ ۖ وَهُوَ أَعْلَمُ بِٱلْمُهْتَدِينَ
29፥46 የመጽሐፉን ባለቤቶችም በዚያች እርሷ *መልካም በኾነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ*፡፡ ከእነርሱ እነዚያን የበደሉትን ሲቀር፡፡ በሉም «በዚያ ወደኛ በተወረደው ወደናንተም በተወረደው አመንን፡፡ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን፡፡» وَلَا تُجَٰدِلُوٓا۟ أَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ إِلَّا بِٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ إِلَّا ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ مِنْهُمْ ۖ وَقُولُوٓا۟ ءَامَنَّا بِٱلَّذِىٓ أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَٰهُنَا وَإِلَٰهُكُمْ وَٰحِدٌۭ وَنَحْنُ لَهُۥ مُسْلِمُونَ

ሁለተኛው ሙግት ደግሞ "ስሁት ሙግት"Invalid argument" ሲሆን ይህ ሙግት ያለ ዕውቀትና ያለ መረጃ እውርር ድንብር የሆነ ፀለምተኛ ሙግት ነው፤ ሰው ሱሪ በአንገቴ ካለ ዓይን ያስፈጠጠ እውነት ዓይኔን ግንባር ያርገው ብሎ የጨባራ ለቅሶ ውስጥ እርርና ምርር ብሎ የሚንጨረጨረውና የሚንተከተከው በዚህ ሙግት ነው፤ ይህ አካሄድ ኢርቱዕ አካሄድ"pessimistic approach" ነው፦
22፥8 *ከሰዎችም ውስጥ ያለ ዕውቀት፣ ያለ ማስረጃም፣ ያለ አብራሪ መጽሐፍም በአላህ ጉዳይ የሚከራከር ሰው አለ*፡፡ وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يُجَٰدِلُ فِى ٱللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍۢ وَلَا هُدًۭى وَلَا كِتَٰبٍۢ مُّنِيرٍۢ

በድርቅና ያለ ዕውቀት፣ ያለ ማስረጃም፣ ያለ አብራሪ መጽሐፍም የሚከራከርን ሰው መሃይምነት ስላጠቃው መሃይማን በክፉ ሲያነጋግሩን በሰላም ውይይቱን መተው ነው፤ ምክንያቱም ወደ ብሽሽቅ ስለሚያስገባ ነው፤ ብሽሽቅ ውስጥ መልካም የሆነችውን ቃል ስለማንናገር ሰይጣን በመካከላቸው ያበላሻልና፦
7:199 “ገርን ጠባይ ያዝ”፤ በመልካምም እዘዝ “መሃይማንን” الْجَاهِلِينَ ተዋቸው። خُذِ ٱلْعَفْوَ وَأْمُرْ بِٱلْعُرْفِ وَأَعْرِضْ عَنِ ٱلْجَٰهِلِينَ
25:63 የአልረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ “በዝግታ የሚኼዱት”፣ “መሃይማን” الْجَاهِلُونَ በክፉ ባነጋገሩዋቸው ጊዜ፣ “ሰላም” የሚሉት ናቸው። وَعِبَادُ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلَّذِينَ يَمْشُونَ عَلَى ٱلْأَرْضِ هَوْنًۭا وَإِذَا خَاطَبَهُمُ ٱلْجَٰهِلُونَ قَالُوا۟ سَلَٰمًۭا
17:53 ለባሮቼም በላቸው፦ ያችን እርሷ “መልካም የሆነችውን ቃል ይናገሩ”፤ ሰይጣን በመካከላቸው ያበላሻልና፤ ሰይጣን ለሰው ግልጽ ጠላት ነውና። وَقُل لِّعِبَادِى يَقُولُوا۟ ٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ ٱلشَّيْطَٰنَ يَنزَغُ بَيْنَهُمْ ۚ إِنَّ ٱلشَّيْطَٰنَ كَانَ لِلْإِنسَٰنِ عَدُوًّۭا مُّبِينًۭا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አሐዳዊያን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤

21፥108 «ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ *”አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው”* ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም “ታዛዦች” ናችሁን?» *በላቸው*፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

በሥነ-መለኮት ጥናት ክርስትና፣ አይሁድ እና እስልምና አሐዳዊ ሃይማኖት"monotheistic Religion" ተብለው ይመደባሉ፤ ክርስቲያን፣ አይሁዳውያን እና ሙስሊም አሐዳውያን"Monotheism" ይባላሉ፤ ምክንያቱም ፈጣሪ በህላዌ ማለትም በምንነት አንድ ኑባሬ ነው ብለው ስለሚያምኑ ነው።

ነገር ግን የክርስትና አሐዳውያን በሥስት ዋና ዋና ክፍል ይከፈላሉ፤ እነርሱም፦
1ኛ አሓዳውያን“Unitarian” ሲሆኑ፤ “uni” ማለት "አንድ" ማለት ሲሆን ለእነርሱ አምላክ በምንነት እና በማንነት አንድ ስለሆነ አምላካቸውን “mono-une God” ይሉታል፤ እነዚህ የመጀመሪያ መቶ ክፍለ-ዘመን የኢየሱስ ቀዳማይ ተከታዮች ነበሩ።
2ኛ ደግሞ ክሌታውያ“Binitarian” ይባላል፤ “Bini” ማለት "ሁለት" ማለት ሲሆን ለእነርሱ አምላክ በምንነት አንድ ሲሆን በማንነት ደግሞ ሁለቱ አብና ወልድ ናቸው፤ አምላካቸውን “Bini-une God” ይሉት ነበር፤ ይህ ትምህርት ሁለተኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ላይ የዳበረ ትምህርት ነው።
3ኛ ሥላሴአዊያን“Trinitarian” ይባላሉ፤ “Tri” ማለት "ሶስት" ማለት ነው፤ ለእነርሱ አምላክ በምንነት አንድ ሲሆን በማንነት ሶስት ስለሆነ አምላካቸው “Tri-une God” ይባላል፤ ይህ በአራተኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ላይ የዳበረ ትምህርት ነው።

እንግዲህ አምላካችን አላህ ቁርአንን በነብያችን”ﷺ" ላይ ሲያወርድ የኢየሱስ ቀዳማይ ተከታዮች ትምህርት የያዙ ዩኒታሪያን በጥቂትም ቢሆኑ ነበሩ፤ አምላካችን አላህ እኛ እንዲህ እንድል አዞናል፦
3፥64 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! *በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ*፡፡ እርሷም *አላህን እንጅ ሌላን ላናመልክ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤ በላቸው*፡፡ እምቢ ቢሉም፡- *እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው*፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ تَعَالَوْا إِلَىٰ كَلِمَةٍ سَوَاءٍ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا اللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِ شَيْئًا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ ۚ فَإِن تَوَلَّوْا فَقُولُوا اشْهَدُوا بِأَنَّا مُسْلِمُونَ

የተውሒድ እሳቤ በእኛ እና በመጽሐፉ ባለቤቶች መካከል ትክክል የኾነች የጋራ ቃል ናት፤ ይህንን ጥሪ ያስተባበሉትን "እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ" እንላቸዋለን፤ ነገር ግን ጥቂት ቀጥተኛ አሐዳዊያን በእነርሱ ላይ ቁርአን በሚነበብላቸውም ጊዜ «በእርሱ አምነናል፡፡ እርሱ ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፤ እኛ ከእርሱ በፊት ሙስሊሞች ነበርን» ይላሉ፦
28፥52 እነዚያ ከእርሱ በፊት መጽሐፍን የሰጠናቸው እነርሱ *በእርሱ ያምናሉ*፡፡ الَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ مِن قَبْلِهِ هُم بِهِ يُؤْمِنُونَ
28፥53 በእነርሱ ላይ በሚነበብላቸውም ጊዜ «በእርሱ አምነናል፡፡ እርሱ ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፡፡ *እኛ ከእርሱ በፊት ሙስሊሞች ነበርን*» ይላሉ፡፡ وَإِذَا يُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ قَالُوا آمَنَّا بِهِ إِنَّهُ الْحَقُّ مِن رَّبِّنَا إِنَّا كُنَّا مِن قَبْلِهِ مُسْلِمِينَ

ልብ አድርግ "እኛ ከእርሱ ማለትም ከቁርአን መውረድ በፊት ሙስሊም ነበርን" ማለታቸው ምክንያታዊ ነው፤ ሙስሊም” مُسْلِم ትርጉሙ “አቢድ” عَابِدُ ማለትም “አምላኪ” አሊያም “ቃኒት” قَانِتِ ማለትም “ታዛዥ” ማለት ነው፦
21፥108 «ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ *”አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው”* ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም “ታዛዦች” ናችሁን?» *በላቸው*፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

ወደ ነብያችን የሚወርደው ቁርአን "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው” የሚል የተውሒድ ትምህርት ነው፤ አሁንም "ታዛዦች” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሙስሊሙን” مُّسْلِمُونَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ ከመጽሐፉ ሰዎች ቁርአንን ተገቢ ንባቡን ያነቡታል፤ እነዚያ በእርሱ ያምናሉ፤ በእነርሱ ላይ በተነበበ ጊዜ ሰጋጆች ኾነው በሸንጎበቶቻቸው ላይ ይወድቃሉ፤ "ጌታችን ጥራት ይገባው! እነሆ የጌታችን ተስፋ ተፈጻሚ ነው" ይላሉ፦
2፥121 እነዚያ መጽሐፉን የሰጠናቸው ተገቢ ንባቡን ያነቡታል፡፡ *እነዚያ በእርሱ ያምናሉ፤ በእርሱም የሚክዱ እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎቹ ናቸው*፡፡ الَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ يَتْلُونَهُ حَقَّ تِلَاوَتِهِ أُولَـٰئِكَ يُؤْمِنُونَ بِهِ ۗ وَمَن يَكْفُرْ بِهِ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْخَاسِرُونَ
17፥106 *ቁርኣንንም በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ኾነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፡፡ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው*፡፡ وَقُرْءَانًۭا فَرَقْنَٰهُ لِتَقْرَأَهُۥ عَلَى ٱلنَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍۢ وَنَزَّلْنَٰهُ تَنزِيلًۭا
17፥107 *«በእርሱ እመኑ ወይም አትመኑ»* በላቸው፤ እነዚያ ከእርሱ በፊት ዕውቀትን የተሰጡት *በእነርሱ ላይ በተነበበ ጊዜ ሰጋጆች ኾነው በሸንጎበቶቻቸው ላይ ይወድቃሉ*፤ قُلْ ءَامِنُوا۟ بِهِۦٓ أَوْ لَا تُؤْمِنُوٓا۟ ۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْعِلْمَ مِن قَبْلِهِۦٓ إِذَا يُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ يَخِرُّونَ لِلْأَذْقَانِ سُجَّدًۭا
17፥108 *ይላሉም «ጌታችን ጥራት ይገባው! እነሆ የጌታችን ተስፋ ተፈጻሚ ነው፡፡»* وَيَقُولُونَ سُبْحَٰنَ رَبِّنَآ إِن كَانَ وَعْدُ رَبِّنَا لَمَفْعُولًۭا
3:113 *የመጽሐፉ ሰዎች ሁሉ እኩል አይደሉም፤ ከመጽሐፉ ሰዎች ቀጥ ያሉ በሌሊት ሰዓቶች እነርሱ የሚሰግዱ ኾነው የአላህን አንቀጾች የሚያነቡ ሕዝቦች አሉ*፡፡ لَيْسُوا۟ سَوَآءًۗ مِّنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ أُمَّةٌ قَآئِمَةٌ يَتْلُونَ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ ءَانَآءَ ٱلَّيْلِ وَهُمْ يَسْجُدُونَ
ከመጽሐፉ ሰዎች በእርሱ በቁርአን የሚክዱ እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎቹ ናቸው፤ የመጽሐፉ ሰዎች ሁሉ እኩል አይደሉም፤ አብዛኛዎቻቸም አመጸኞች ናቸው፤ እነዚያ ከመጽሐፉ ሰዎች የካዱት በገሀነም እሳት ውስጥ ናቸው፤ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ እነዚያ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ ክፉ ናቸው፦
5፥59 «የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በአላህ እና ወደ እኛ በተወረደው በፊትም በተወረደው ለማመናችን *አብዛኞቻችሁም አመጸኞች ለመኾናችሁ* እንጅ ሌላን ነገር ከእኛ ትጠላላችሁን» በላቸው፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ هَلْ تَنقِمُونَ مِنَّا إِلَّا أَنْ آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْنَا وَمَا أُنزِلَ مِن قَبْلُ وَأَنَّ أَكْثَرَكُمْ فَاسِقُونَ
98:6 *እነዚያ ከመጽሐፉ ሰዎች የካዱት*፣ አጋሪዎቹም *በገሀነም እሳት ውስጥ ናቸው*፤ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ እነዚያ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ ክፉ ናቸው፡፡ إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ وَٱلْمُشْرِكِينَ فِى نَارِ جَهَنَّمَ خَٰلِدِينَ فِيهَآۚ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمْ شَرُّ ٱلْبَرِيَّةِ

ምክንያቱም ከመጽሐፋ ሰዎች አብዛኛውን በሃይማኖታቸው ወሰን በማለፍ በአላህም ምንነት ላይ "ሦስት ነው" በማለት ቀጥፈዋል፤ አላህ በአንድ ምንነቱ ላይ ሦስት ማንነት የሌለበት አንድ አምላክ ብቻ ነው፦
4፥171 እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! *በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ።….. « ሦስት ነው» አትበሉም وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው*፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ ۖ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ ۖ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ ۚ ٱنتَهُوا۟ خَيْرًۭا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا ٱللَّهُ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ

ከመጽሐፉን ባለቤቶችንም እነዚያን በአላህ ላይ በማጋራት የበደሉትን ሲቀሩ ለእነርሱ "በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው አመንን፤ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ለአንድ አምላክ ሙስሊሞች ነን" እንላለን፦
29፥46 የመጽሐፉን ባለቤቶችንም በዚያች እርሷ መልካም በኾነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ፡፡ *ከእነርሱ እነዚያን የበደሉትን ሲቀር*፡፡ በሉም *«በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው አመንን፡፡ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን*፡፡» وَلَا تُجَادِلُوا أَهْلَ الْكِتَابِ إِلَّا بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ إِلَّا الَّذِينَ ظَلَمُوا مِنْهُمْ ۖ وَقُولُوا آمَنَّا بِالَّذِي أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَـٰهُنَا وَإِلَـٰهُكُمْ وَاحِدٌ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ

ይህ መጣጥፍ የዩኒታሪያንን ተከታዮችን ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሀፍረተ ቢስነት ሲገን.pdf
1.3 MB
ከሰሞኑ ስለኩረጃ በማውራት ሲንቀበቀቡ የምናያቸው የፕሮቴስታንት ተርጓሚዎች ሲፈተሹ ..
___

@yahya5
ኢየሱስ ይመለካልን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥117 «በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል፦ *ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

“ዒባዳ” عبادة የሚለው ቃል “ዓበደ عَبَدَ “አመለከ” ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን “አምልኮ” ማለት ነው፤ አምልኮ የሚገባው አንዱ አምላክ አላህ ብቻ ነው፤ አላህ ዒሳን በል ብሎ ያዘዘው ቃል፦ “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” ማለትን ነው፦
5፥117 «በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል፦ *ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

ነገር ግን በተቃራኒው ክርስቲያኖች ኢየሱስን በቀጥታ ያመልካሉ፤ “አምልኮ” የሚለው ቃል በእብራይስጥ “አቫድ” עָבַד ሲሆን በግሪክ ደግሞ “ላትሬኦ” λατρεύω ነው፤ ይህም ለአንዱ አምላክ ብቻ በሙሉ ሁለንተና የሚቀርብ ልመና፣ ስእለት፣ማጎብደድ፣ መተናነስ፣ ስግደት፣ መገዛት ፣ አገልግሎት Adoration ነው። ኢየሱስ፦ አምልኩኝ ያለበት፣ ሀዋርያት እና ነብያት፦ ኢየሱስን አምልኩ ያለበት እና ሰዎች ኢየሱስን ያመለኩበት አንድ አንቀጽ የለም። ነገር ግን ኢየሱስ የሚመለክ መሆኑን የሚጠቁሙ ጥቅሶች አሉ ይላሉ፤ እውን ይህ ጥቅስ ኢየሱስ ይመለካል ይላልን? እስቲ ጥቅሱን እንየው፦
ዳንኤል 7፥13-14 በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ “የሰው ልጅ የሚመስል” ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት። ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ “ይገዙለት” δουλεύσουσιν ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም “ተሰጠው”፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።

ነጥብ አንድ
“የሰው ልጅ የሚመስል”
ዳንኤል በራእይ አራትም ታላላቅ አራዊት ከባሕር ሲወጡ አየ፤ እነዚህ አራቱ ታላላቅ አራዊት ከምድር የሚነሡ አራት ነገሥታት ናቸው፤ በራእይ ያየው “የሰው ልጅ የሚመስል” ደግሞ “የልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ” ነው፦
ዳንኤል 7፥27 መንግሥትም ግዛትም ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት *”ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ”* ይሰጣል፤ መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቶችም ሁሉ “ይገዙለታል* δουλεύσουσι ይታዘዙለትማል።
ዳንኤል 7፥18 ነገር ግን *”የልዑሉ ቅዱሳን”* መንግሥቱን ይወስዳሉ፥ እስከ ዘላለም ዓለምም መንግሥቱን ይወርሳሉ።
ዳንኤል 7፥22 *”በዘመናት የሸመገለው እስኪመጣ ድረስ፥ ፍርድም ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪሰጥ ድረስ”*፥ ቅዱሳኑም መንግሥቱን የሚወስዱበት ዘመን እስኪመጣ ድረስ አሸነፋቸውም።
ዘጸአት 19፥6 *”እናንተም የካህናት መንግሥት የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ”*። ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ቃል ይህ ነው።

የአይሁድ ኮሜንቴርይ፦ “የሰው ልጅ የሚመስል” የተባለው ዐውዱ ላይ የእስራኤል ሕዝብ ነው” ብለው የፈሠሩት። ዐውዱ ላይ የሰው ልጅ የሚመስል የልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ መሆኑን ፍትንው አርጎ ከዘጋ በኃላ ሌላ ትርጉም እንዳንሰጥ “የነገሩም ፍጻሜ እስከዚህ ድረስ ነው” በማለት ይቋጫል፦
ዳንኤል 7፥28 የነገሩም ፍጻሜ እስከዚህ ድረስ ነው።
ነጥብ ሁለት
“ተሰጠው”
ሙግቱን ጠበብ አድርገነው ዳንኤል ላይ “የሰው ልጅ የሚመስል” የተባለው ኢየሱስ ነው ቢባል እንኳን አሁንም ፍጡር ከመሆን የዘለለ ማንነት የለውም። ምክንያቱም በሃረጉ ውስጥ “ተሰጠው” የሚል ሃይለ-ቃል አለ፤ ሰጪው ደግሞ “በዘመናት የሸመገለው” አብ ነው፤ አንዱ አምላክ ለኢየሱስ የአባቱን ዙፋን ሰጥቶታል፦
ማቴዎስ 28፥18 ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ *ሥልጣን ሁሉ* በሰማይና በምድር *ተሰጠኝ*።
ሉቃስ 10፥22 *ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል*፥
ሉቃስ 1፥32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ *ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል*፤

ሰው እና የሰው ልጅ የተባለው ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ተለይቶ ፍጡር ነው፤ ታዲያ ይልቁንስ *ብስብስ የሆነ ሰው፥ ትልም የሆነ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ፊት ምንኛ ያንስ?
ዮሐንስ 13:31 ከወጣም በኋላ ኢየሱስ እንዲ አለ። *አሁን የሰው ልጅ ከበረ እግዚእብሔርም ሰለ እርሱ ከበረ*፤
ኢዮብ 25፥6 ይልቁንስ *ብስብስ የሆነ ሰው፥ ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ*!

የሰው ልጅ የሚመስል የሚባለው ኢየሱስ ነው ብንል እንኳን ኢየሱስ የሚመስለው አለ የሰው ልጅ የሚመስል ተብሏልና፤ ሰውን ይመስላል፤ ነገር ግን ነገር ግን ያ የሚመለከው አንዱ አምላክ የሚመስለው አለን? የለም፦
ኢዮብ 23:13 *እርሱ ግን ብቻውን ነው፤ እርሱንስ የሚመስለው ማን ነው?*

ነጥብ ሶስት
“ይገዙለት”
“ይገዙለት” ተብሎ በግሪክ ሰፕቱጀንት”LXX” ላይ የሰፈረው ቃል “ዱልኦስ” δοῦλος ነው፦
ዳንኤል 7፥14 ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ “ይገዙለት” δουλεύσουσιν ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም “ተሰጠው”፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።

“ይገዙለት” ተብሎ መገዛት የተገባው የሰው ልጅ የሚስመለው የልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ እንደሆነ ዐውዱ ላይ ፍንትውና ቁልጭ ብሎ ተቀምጧል፦
ዳንኤል 7፥27 መንግሥትም ግዛትም ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት “ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ” ይሰጣል፤ መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቶችም ሁሉ “ይገዙለታል* δουλεύσουσι ይታዘዙለትማል።

አይ የሰው ልጅ የሚመስል የተባለው ኢየሱስ ነው፤ “ይገዙለት” ማለት “ያመልኩት” ዘንድ ማለት ነው ብላችሁ ከፈሰራችሁት የማትወጡት ገደል ውስጥ ትገባላችሁ፤ እንግዲያውስ የሚመለኩ አበዛዛቸው፦
ኢየሩሳሌም፦
ኢሳይያስ 60:12 ለአንቺም “የማይገዛ” δουλεύσουσί ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፥ እነዚያ አሕዛብም ፈጽመው ይጠፋሉ።

ያዕቆብ፦
ዘፍጥረት 25፥23 እግዚአብሔርም አላት፦ ሁለት ወገኖች በማኅፀንሽ ናቸው፥ ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይከፈላሉ፤ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ “ይገዛል” δουλεύσει ።
ዘፍጥረት 27፥29 አሕዛብ “ይገዙልህ” δουλευσάτωσάν ሕዝብም ይስገዱልህ፤
ሮሜ 8፥12 ለእርስዋ፦ ታላቁ ለታናሹ “ይገዛል” δουλεύσει ተባለላት።

“እርስ በእርስ”፦
ገላትያ 5፥13 ነገር ግን በፍቅር እርስ በእርሳችሁ “አገልግሉ” δουλεύετε ። KJV

ልብ አድርጉ ሁሉም ጋር መገዛት ተብሎ በግሪኩ ኮይኔ የቀረቡት ቃላት አንድ አይነት ነው።

በተለይ የክርስትና የዐቂዳህ መጽሐፍ የሆነው ሃይማኖተ-አበው ስጋ ፍጡር ነው ይሉን እና ተመልሰው አምላክ ነው ይላሉ፦
ሃይማኖተ-አበው ዘመጠሊጎን 44፥3
ዘመጠሊጎን አለ፦ “ወለሊሁ ሐነፀ ሥጋሁ ውስጠ ከርሠ ድንግል ወኢተሳተፎ መኑሂ በፈጢረ ሥጋሁ አላ ለሊሁ ባሕቲቱ ፈጠሮ”
ትርጉም፦ ” እርሱ ሥጋውን በድንግል ማሕፀን ፈጠረ፤ ሥጋውን በመፍጠር ማንም አጋዥ አልሆነውም፤ እርሱ እራሱ ፈጠረው እንጂ”
ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 78፥31
ቄርሎስም አለ፦ “ወዓዲ ንቤ እስመ ሥጋሁ ለእግዚእነ ክርስቶስ አምላክ ውእቱ”
ትርጉም፦ ” ዳግመኛ የጌታችን የክርስቶስ ስጋ አምላክ እንደሆነ እንናገራለን”

ይህንን ህሊና ይቀበለዋል? ስጋው ምግብ ሲበላ የሚበላው ምግብ ሰውነት ሲሆን ይመለካልን? ሲከሳ ወይም ያ ምግብ ከሰውነት ሲወጣ አይመለክምን? ደሙ ስጋ ውስጥ እያለ የሚመለክ ሲፈስ የማይመለክ ነውን? ይህንን ውስብስብ ትምህርት እንኳን ልታስረዱን ይቅርና ለራሳችሁ አልገባችሁም። ኢየሱስ መመለክ የሚገባው እርሱ ሳይሆን የእርሱ አምላክ እንደሆነ በግልፅ ተናግሯል፦
ማቴዎስ 4፥10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ *እርሱንም ብቻ አምልክ* λατρεύσεις ተብሎ ተጽፎአልና አለው።

አንድ ነጠላ ማንነት”person” ብቻ የሚመለክ መሆኑን ለማሳየት “እርሱ” የሚለው ነጠላ ተሳቢ-ተውላጠ ስም እና “ብቻ” በሚል ገላጭ”adjective” የሚመለከው ለኢየሱስ ንግስና የሰጠው ጌታ አምላክ ብቻ መሆኑን ያሳያል፤ ይህ ጌታም አምላክ አንድ ጌታ ነው፤ ይህ አንድ ጌታ ለእስራላልውያን የመረጠውን ኢየሱስን የላከ ነው፦
ሉቃስ 1፥32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ *ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል*፤
ማርቆስ 12፥29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፦ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ *ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው*፥
ሐዋ ሥራ 3፥20 እንግዲህ *ከጌታ ፊት* የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ *የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ*፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ጥንታዊ ስም አሏህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

20፥14 *«እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ*፡፡ ሶላትንም በእርሷ እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ إِنَّنِىٓ أَنَا ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدْنِى وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ لِذِكْرِىٓ

“አሏህ” ٱللَّه የሚለው ስም 2699 ጊዜ በቁርአን የመጣ ሲሆን ትርጉሙ “የሚመለክ” ወይም “አምልኮ የሚገባው” ማለት ነው፦
Lane’s Arabic-English Lexicon by Edward William Lane (London: Willams & Norgate 1863)
አላህ ኢስሙል ዛት ማለትም የህላዌው ስም ነው፥ አምላካችን አላህ ጥንትም ሙሳን ሲያናግር የነበረው የሙሳ አምላክ አላህ እራሱ ነው፤ አላህ ለሙሳ፦ “እኔ አላህ እኔ ነኝ፥ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ” ብሎታል፦
20፥14 *«እኔ አላህ እኔ ነኝ፥ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ*፡፡ ሶላትንም በእርሷ እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ إِنَّنِىٓ أَنَا ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدْنِى وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ لِذِكْرِىٓ

አላህ ለሙሳ፦ “እኔ አላህ እኔ ነኝ፥ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ” ብሎ ከማለቱ በፊት «ሙሳ ሆይ» በማለት ጠርቶታል፦
20፥11 በመጣም ጊዜ «ሙሳ ሆይ» በማለት *”ተጠራ*፡፡ فَلَمَّآ أَتَىٰهَا نُودِىَ يَٰمُوسَىٰٓ

ይህንን ጥሪ ጠርቶ ያነጋገረው እራሱ እንደሆነ በመጀመሪያ መደብ ለነቢያችን”ﷺ”፦ “ጠራነው፥ ያነጋገርነውም ሲኾን አቀረብነው” በማለት ሙሴን የጠራው እርሱ እንደሆነ ይናገራል፦
19፥51 በመጽሐፉ ውስጥ *ሙሳንም አውሳ*፡፡ እርሱ ምርጥ ነበርና፡፡ መልክተኛ ነቢይም ነበር፡፡ وَٱذْكُرْ فِى ٱلْكِتَٰبِ مُوسَىٰٓ ۚ إِنَّهُۥ كَانَ مُخْلَصًۭا وَكَانَ رَسُولًۭا نَّبِيًّۭا
19፥52 ከጡር ቀኝ ጎን በኩልም *ጠራነው፥ ያነጋገርነውም* ሲኾን አቀረብነው፡፡ وَنَٰدَيْنَٰهُ مِن جَانِبِ ٱلطُّورِ ٱلْأَيْمَنِ وَقَرَّبْنَٰهُ نَجِيًّۭا

አምላካችን አላህ ለሙሳ "አላህ" ነኝ ብሎ እራሱ ማስተዋወቁ ካየን ዘንድ ለሙሳ እና ከእርሱ በኃላ ላሉት ነቢያት ያወረደው ወሕይ ሥረ-መሠረቱ በዘመናችን ስለሌለ በትክክል አሁን በአህሉል ኪታብ እጅ ያሉት ጋር አላህ የሚለውን ስም በግልጽ ማግኘት አልተቻለም። ነገር ግን "አላህ" የሚለውን ስም በእነርሱ ቅሪት ውስጥ ስለመኖሩ ፍንጭ የሚሰጡ አናቅጽ በፓሌዎ ዕብራይስጥ አነባነብ አለ። ፓሌዎ ዕብራይስጥ ማለት ከማሶሬት ዕብራይስጥ በፊት የነበረ እና ነቢያቱ ሲጠቀሙበት የነበረ ዕብራይስጥ ነው። ማሶሬት የሚባለው እደ-ክታብ በ 875 ድኅረ-ልደት"AD" ከመዘጋጀቱ በፊት ማሶሬት የሚባሉ የአይሁድ ግሩፕ ዕብራይስጥን ከዐረማይክ ጋር እየደባለቁ የጥንቱን የፓሌዎ ዕብራይስጥ በርዘውታል። "ማሶሬት" מֶסֹרֶת ማለት ቋንቋዊ ፍቺው "እስራት" ማለት ሲሆን ሃይማኖታዊ ፍቺው "ትውፊት" ማለት ነው።

በፓሌዎ ዕብራይስጥ "አ-ለ-ሀ" אלוה "አሌፍ-ላሜድ-ሃ" ነው።
"አሌፍ" א ሲነበብ "አ" እንጂ "ኤ" አይደለም።
"ላ" לו ሲነበብ "ላ" እንጂ "ሎ" አይደለም።
"ሀ" ה ሲነበብ "ሀ" ነው ግን የመጨረሻ ፊደል ላይ በሳድስ "ህ" ተብሎ ይሰክናል።
በፓሌዎ ዕብራይስጥ ሲነበብ "አ-ላ-ህ" ይሆናል።
በፓሌዎ ዕብራይስጥ ውስጥ "ኤ" የምትባል ኃምስ እና "ኦ" የምትባል ሳብዕ አናባቢ የለም። ስለዚህ "ኤ" እና "ሎ" የሚባለውም የማሶሬት ጭማሬ ነው።
ግዕዝ ሰባት አናባቢ አሉት፥ እነርሱም፦
ግእዝ "አ" ካዕብ "ኡ" ሣልስ "ኢ" ራብዕ "ኣ" ኃምስ "ኤ" ሳድስ "እ" እና ሳብዕ "ኦ" ናቸው።

በፓሌዎ ዕብራይስጥ ግን የዘር መነሻ ግእዝ "አ" ነው። የዘር ግንድ ራብዕ "ኣ" ነው። የዘር መዳረሻ ሳድስ "እ" ነው።
ይህንን ከተረዳን "አላህ" אלוה የሚለው ቃል በዕብራይስጡ ባይብል ውስጥ በቅሪት አለ፦
ኢዮብ 3፥4 ያ ቀን ጨለማ ይሁን፤ "አላህ" אֱל֣וֹהַּ ከላይ አይመልከተው፥ ብርሃንም አይብራበት።
ኢዮብ 5 ፥17 እነሆ፥ "አላህ" אֱל֣וֹהַּ የሚገሥጸው ሰው ምስጉን ነው፤ ስለዚህ ሁሉን የሚችለውን የአምላክን ተግሣጽ አትናቅ።
መዝሙር 139፥19 "አላህ" אֱל֣וֹהַּ ሆይ! አንተ ኃጢአተኞችን የምትገድል ከሆንህስ፥ የደም ሰዎች ሆይ፥ ከእኔ ፈቀቅ በሉ።
ታዲያ "አላህ" እኮ ማዕረግ ሆኖ እንጂ ስም ሆኖ አልመጣም የሚሉ ተከራካሪዎች አይጠፉም። ይህንን ለመረዳት ቅድሚያ ስለ ስም እንረዳ፦
ኤርምያስ 51፥57 መሳፍንቶችዋንና ጥበበኞችዋንም፥ አለቆችዋንና ሹማምቶችዋን ኃያላኖችዋንም አሰክራለሁ፥ ለዘላለምም አንቀላፍተው አይነቁም፥ ይላል *"ስሙ የሠራዊት ያህዌህ"* የተባለው ንጉሥ። וְהִשְׁכַּרְתִּי שָׂרֶיהָ וַחֲכָמֶיהָ פַּחוֹתֶיהָ וּסְגָנֶיהָ, וְגִבּוֹרֶיהָ, וְיָשְׁנוּ שְׁנַת-עוֹלָם, וְלֹא יָקִיצוּ: נְאֻם-הַמֶּלֶךְ--יְהוָה צְבָאוֹת, שְׁמוֹ.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ያህዌህ ጸባዖት ሴሙ" אֱלֹהֵי-צְבָאוֹת, שְׁמוֹ ማለት "ስሙ የሠራዊት ያህዌህ ነው" ተብሏል። በተመሳሳይ ሰዋሰው "አላህ ጸባዖት ሴሙ" אֱלֹהֵי-צְבָאוֹת, שְׁמוֹ ማለት "ስሙ የሠራዊት አላህ ነው" ተብሏል፦
አሞጽ 5፥27 ስለዚህ ከደማስቆ ወደዚያ አስማርካችኋለሁ፥ ይላል ያህዌህ *"ስሙ የሠራዊት አላህ ነው"*። וְהִגְלֵיתִי אֶתְכֶם, מֵהָלְאָה לְדַמָּשֶׂק: אָמַר יְהוָה אֱלֹהֵי-צְבָאוֹת, שְׁמוֹ

"የሰራዊት አላህ" የሚለው "የሰራዊት ያህዌህ" በሚለው ተለዋዋጭ ሆኖ መጥቷል። ብሉይ ኪዳን ለመበረዝ ተጠያቂዎቹ የማሶሬት ቡድን ናቸው። "አሏህ" በዕብራይስ ቁርኣን ላይ “ላሜድን” ל ተሽዲድ ስናደርገው “አሏህ” אללה‌‎ ሲሆን ከውስጡ ሁለት “ላሜድ” ל ነው፥ አንዱን ላሜድ ማሶሬቶች ቀንሰው "አላህ" אלוה አድርገው ከዚያም ሲያነቡ አጣመው "ኤሎሃ" ብለው አዛብተውታል። አሏህ የሚለው ስም ነቢያችን"ﷺ" ነብይ ሆነ ከመላካቸው በፊትና ቁርኣን ከመውረዱ በፊት በሴመቲክ ዳራ ደግሞ ከሁሉ በላይ የሆነው አንዱ አምላክ ሲጠራበት የነበረ ስም እንደነበር የተለያየ መድብለ-ዕውቀቶች"Encycolopedias" ሆኑ ታሪካዊ ፍሰቶች ያትታሉ፦
1. የሃይማኖት መድብለ-ዕውቀት 1987: “አላህ የሚለው ስም ስረ-መሰረት የጋራ በሆኑ በተለያዩ ጥንታዊ የሴም ቋንቋዎች ይገኛል” ገጽ 27.
Encycolopedia of religion 1987: “the orgin of Allah is found in a root common to various ancient semetic languages” p27.
2. የክርስትና መድብለ-ዕውቀት 2001: “ ቅድመ-ቁርኣን ዐረብ ተናጋሪ ክርስቲያንና አይሁድ እንዲሁ አላህ ለታላቁ አምላክ ይጠቀሙበት ነበር” ገጽ 101.
Encyclopedia of Christianity 2001: “before Quran Arabic-speaking Christians and Jews also refer to supreme God as Allāh” page 101.
3. የኢሥላም መድብለ-ዕውቀት 1913: “ዐረቦች ቅድመ-ነቢዩ ሙሃመድ በነበሩት ዘመናት አላህ የሚባል ታላቅ አምላክ ያመልኩ ነበር” ገጽ 302.
Encyclopedia of Islam 1913: “Before prophet Muhammad Arabian was worshiping supreme God who is Allah” page 302.
4. የብሪታኒካ መድብለ-ዕውቀት 1996: “ቅድመ-ቁርኣን በነበሩት ዐረቢያን መጽሐፍት ውስጥ አላህ የሚለው ቃል ይገኛል” ገጽ 106.
Encyclopedia of britannica 1996: “Before Quran The word Allah was in the Arabic books” page 106.

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ያህዌህ እና መሢሑ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥75 የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُل

“አል-መሢሕ” الْمَسِيح የሚለው የዐረቢኛው ቃል “መሠሓ” مسح ማለትም “አበሰ” አሸ” “ቀባ” ከሚል ሥርወ-ግንድ የተገኘ ሲሆን “የቀባ” አሊያም “የተቀባ” ወይንም “የሚያብስ” አሊያም “የታበሰ” ወይንም “የሚያሽ” አሊያም “የሚታሽ” የሚል ፍቺ አለው፤ ዒሣ ኢብኑ መርየም በሽተኞችን፣ ህሙማንን እና ሙታንን በማበስ፣ በማሸት እና በመቀባት ከበሽታቸው በአላህ ፈቃድ ያሽራቸው ስለነበረ እና በአላህ የተሾመ(የተቀባ) ነቢይ ስለሆነ “አል-መሢሕ” ተብሏል። አምላካችን አላህ በተከበረው ቃሉ በዘጠኝ አንቀፆች 11 ጊዜ ኢየሱስ መሢሕ መሆኑን ነግሮናል። ይህ መሢሕ አስተምረው ካለፉት መልእክተኞች አንዱ የአላህ ባሪያ ነው፦
5፥75 የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُل
4፥172 *"አልመሲሕ ለአላህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም"*፡፡ لَّن يَسْتَنكِفَ الْمَسِيحُ أَن يَكُونَ عَبْدًا لِّلَّهِ

"መሺአሕ" מָשִׁיחַ‎ የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "መሸሕ" מָשַׁח ማለትም "ቀባ" "አሸ" "ዳሰሰ" ከሚል ስርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የተቀባ"anointed one" ማለት ነው። ይህም ቃል በብሉይ ኪዳን ላይ ለተለያየ ካህን፣ ንጉሥ እና ነቢይ አገልግሎት ላይ ውሏል። ነገር ግን ቃል የተገባለት መሢሕ በትንቢት የተነገረለት ንጉሥና ነቢይ ነው፦
ዘፍጥረት 49፥10 በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፥ የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል፥ *"ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ"*፤ የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል።

"ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ" የሚለው ይሰመርበት። "ገዢ" ተብሎ የተቀመጠው የዕብራይስጥ ቃል "ሺሎሕ" שִׁיל֔וֹ ሲሆን "ሕጋዊ መብት ያለው ገዢ" ማለት ነው። ይህ ወደፊት የሚመጣው መሢሕ ከአንዱ አምላክ ከያህዌህ በማንነት ሆነ በምንነት ይለያል፦
ዘዳግም 6፥4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ *አምላካችን ያህዌህ አንድ ያህዌህ ነው*። שְׁמַע, יִשְׂרָאֵל: יְהוָה אֱלֹהֵינוּ, יְהוָה אֶחָד.
መዝሙር 2፥2 የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም *”በያህዌህ” יְהֹוָה እና "በመሢሑ" ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ”*።

ያህዌህ አንድ ነው፥ በያህዌህ እና በመሢሑ መካከል "እና" የሚለው መስተጻምር መግባቱ በራሱ ያህዌህ እና መሢሑ ሁለት ማንነትና ምንነት መሆናቸውን ቁልጭ እና ፍንትው አድርጎ ያሳያል፥ የሚመጣው መሢሑ ያህዌህ ሳይሆን የያህዌህ መሢሕ ነው። ያህዌህ ቀቢ መሢሑ ተቀቢ ነው፥ መሢሑ የያህዌህ ባሪያ ነው፦
ሕዝቅኤል 37፥24 *"ባሪያዬም ዳዊት ንጉሥ ይሆናቸዋል፤ ለሁሉም አንድ እረኛ ይሆንላቸዋል"* ፤ በፍርዴም ይሄዳሉ ትእዛዜንም ይጠብቃሉ ያደርጓትማል።
ሕዝቅኤል 37፥25 አባቶቻችሁም በኖሩበት ለባሪያዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድር ይኖራሉ፤ እነርሱና ልጆቻቸው የልጅ ልጆቻቸውም ለዘላለም ይኖሩባታል፤ *"ባሪያዬም ዳዊት ለዘላለም አለቃ ይሆናቸዋል"*።

"ዳዊድ" דָּוִ֔ד ማለት "የተወደደ"beloved one" ማለት ነው። "ዶውድ" דּוֹדָ֑ ማለትም "ወዳጅ" ለሚለው ቃል ገላጭ ሆኖ እንደሚገባ ሁሉ ከዳዊት ቤት የሚመጣው መሢሕም "ዳዊድ" ተብሏል እንጂ የእሴይ ልጅ ዳዊት ይመጣል ማለት በፍጹም አይደለም። ይህ የተወደደ መሢሕ የያህዌህ ባሪያ ከያህዌህ "እና" በሚል መስተጻምር አሁንም ተለይቷል፦
ሆሴዕ 3፥5 ከዚያም በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመልሰው *"አምላካቸውን እግዚአብሔርን እና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ"*፤ በኋለኛውም ዘመን ፈርተው ወደ እግዚአብሔርና ወደ በረከቱ ይመጣሉ።
ኤርሚያስ 30፥9 *"ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር እና ለማስነሣላቸው ለንጉሣቸው ለዳዊትም ይገዛሉ"* እንጂ ሌሎች አሕዛብ እንደ ገና አይገዙአቸውም።

እንግዲህ በብሉይ የተተነበየለት የሚመጣው መሢሕ "ባሪያ" "አለቃ" "እረኛ" እና "ንጉሥ" እንጂ ፈጣሪ ያህዌህ በፍጹም አይደለም። ይህንን መሢሕ ግን "ፈጣሪ አላህ ነው" ብሎ ማለት ኩፍር ነው፦
5፥72 *"እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ"*፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም