ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
እውነት ማን ነው?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

31፥30 ይህ *አላህ እርሱ እውነት ከእርሱም ሌላ የሚግገዙት ውሸት በመሆኑ* እና አላህም እርሱ የበላይ ታላቅ በመሆኑ ነው፡፡ ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْحَقُّ وَأَنَّ مَا يَدْعُونَ مِن دُونِهِ ٱلْبَٰطِلُ وَأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْعَلِىُّ ٱلْكَبِيرُ

ሚሽነሪዎች የራሳቸው መጽሐፍ ላይ ስለ ኢየሱስ አምላክነት በቂ መረጃ መስጠት ሲያቅታቸው ወደ ቁርአኑ መጡና፦ "አላህ እውነት ነው፤ ከአላህ ውጪ እውነት የለም፤ ስለዚህ በወንጌል ላይ ደግሞ ኢየሱስ በዮሐንስ 14፥6 "እውነት" ተብሏልና ኢየሱስ አምላክ ነው" የሚል ስሙር ሙግት ያቀርባሉ፤ ይህ ሙግት ውሃ ያነሳል ወይ? እስቲ በአፅንዖትና በአንክሮት ይህንን ሙግት ድባቅ እናስገባው፦

ነጥብ አንድ
"እውነት በቁርአን"
"አል-ሐቅ" الْحَقَّ በቁርአን ከተጠቀሱት የአላህ ስሞች አንዱ ነው፤ "አል" الْ በስም ላይ መነሻ ቅጥያ ሆኖ ሲመጣ “ማዕሪፋህ” معرفة ማለትም “አመልካች መስተአምር”definite article” ብቻ ሳይሆን "እጅግ በጣም" የሚል ትርጉም ይኖረዋል፤ አላህ በእርግጥም "እጅግ በጣም እውነት" ነው፦
31፥30 ይህ *አላህ እርሱ እውነት ከእርሱም ሌላ የሚግገዙት ውሸት በመሆኑ* እና አላህም እርሱ የበላይ ታላቅ በመሆኑ ነው፡፡ ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْحَقُّ وَأَنَّ مَا يَدْعُونَ مِن دُونِهِ ٱلْبَٰطِلُ وَأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْعَلِىُّ ٱلْكَبِيرُ
22፥62 ይህ *አላህ እርሱ እውነት በመሆኑ ከእርሱም ሌላ የሚግገዙት ነገር እርሱ ፍጹም ውሸት በመሆኑ* አላህም እርሱ የሁሉ በላይ ታላቅ በመኾኑ ነው፡፡ ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْحَقُّ وَأَنَّ مَا يَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ هُوَ ٱلْبَٰطِلُ وَأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْعَلِىُّ ٱلْكَبِيرُ
6፥62 ከዚያም *እውነተኛ ወደ ኾነው ጌታቸው ወደ አላህ* ይመለሳሉ፡፡ ንቁ! ፍርዱ ለእርሱ ብቻ ነው፡፡ እርሱም ከተቆጣጣሪዎች ሁሉ ይበልጥ ፈጣን ነው፡፡ ثُمَّ رُدُّوٓا۟ إِلَى ٱللَّهِ مَوْلَىٰهُمُ ٱلْحَقِّ ۚ أَلَا لَهُ ٱلْحُكْمُ وَهُوَ أَسْرَعُ ٱلْحَٰسِبِينَ

ከአላህ እውነተኛነት ጋር የሚነጻጸር እውነተኛ ነገር የለም፤ አላህ ፍፁም እውነት ሲሆን ፍጡራን ደግሞ አንጻራዊ እውነተኞች ናቸው፤ በእርግጥም አላህ እውነተኛው ንጉሥ፣ እውነተኛው ጌታ እና እውነተኛው አምላክ ነው፤ ከእርሱ ውጪ እውነተኛው ንጉሥ፣ እውነተኛው ጌታ እና እውነተኛው አምላክ የለም፦
20፥114 *እውነተኛው ንጉሥ* አላህም ከሓዲዎች ከሚሉት ላቀ፡፡ ወደ አንተ መወረዱም ከመፈጸሙ በፊት በማንበብ አትቸኩል፡፡ «ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትንም ጨምርልኝ» በል፡፡ فَتَعَٰلَى ٱللَّهُ ٱلْمَلِكُ ٱلْحَقُّ ۗ وَلَا تَعْجَلْ بِٱلْقُرْءَانِ مِن قَبْلِ أَن يُقْضَىٰٓ إِلَيْكَ وَحْيُهُۥ ۖ وَقُل رَّبِّ زِدْنِى عِلْمًۭا
10፥32 እርሱ *እውነተኛ ጌታችሁ* አላህ ነው፡፡ ከእውነትም በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ ምን አለ ከእውነት እንዴት ትዞራላችሁ? فَذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمُ ٱلْحَقُّ ۖ فَمَاذَا بَعْدَ ٱلْحَقِّ إِلَّا ٱلضَّلَٰلُ ۖ فَأَنَّىٰ تُصْرَفُونَ
28፥75 ከሕዝቦችም ሁሉ መስካሪን እናወጣለን፡፡ ያን ጊዜ *እውነተኛውም አምላክነት ለአላህ ብቻ መኾኑን ያውቃሉ*፡፡ ይቀጣጥፉት የነበሩትም ከእነርሱ ይጠፋቸዋል፡፡ وَنَزَعْنَا مِن كُلِّ أُمَّةٍۢ شَهِيدًۭا فَقُلْنَا هَاتُوا۟ بُرْهَٰنَكُمْ فَعَلِمُوٓا۟ أَنَّ ٱلْحَقَّ لِلَّهِ وَضَلَّ عَنْهُم مَّا كَانُوا۟ يَفْتَرُونَ

"ሐቅ" حَقَّ የተባሉት በቁርአን እንደየ አውዱ ለቁርአን እና ለመልክተኛው ይጠቀምበታል፤ ቁርአን ሐቅ ተብሏል፦
13፥1 አሊፍ ላም ሚም ራ ይህች አናቅጽ ከመጽሐፉ አንቀጾች ናት፡፡ ያም ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደው *እውነት* ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያምኑም፡፡ الٓمٓر ۚ تِلْكَ ءَايَٰتُ ٱلْكِتَٰبِ ۗ وَٱلَّذِىٓ أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ ٱلْحَقُّ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يُؤْمِنُونَ

ነብያችን”ﷺ” ሐቅ ተብለዋል፦
3፥86 ከእምነታቸው እና *መልክተኛውም እውነት መኾኑን ከመሰከሩ* የተብራሩ አንቀጾችም ከመጡላቸው በኋላ የካዱን ሕዝቦች አላህ እንዴት ያቀናል! አላህ በዳዮችንም ሕዝቦች አያቀናም፡፡ كَيْفَ يَهْدِى ٱللَّهُ قَوْمًۭا كَفَرُوا۟ بَعْدَ إِيمَٰنِهِمْ وَشَهِدُوٓا۟ أَنَّ ٱلرَّسُولَ حَقٌّۭ وَجَآءَهُمُ ٱلْبَيِّنَٰتُ ۚ وَٱللَّهُ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلظَّٰلِمِينَ

"ሷዲቅ" صَادِق የሚለው ቃል "ሐቅ" حَقَّ ለሚለው ተለዋዋጭ ሲሆን "እውነተኛ" ማለት ነው፤ "እውነተኛ" የተባሉት ደግሞ መርየም እና ምእምናንም ጭምር ናቸው።
መርየም፦
5፥75 የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ *እናቱም በጣም እውነተኛ ናት*፡፡ مَّا ٱلْمَسِيحُ ٱبْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌۭ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ ٱلرُّسُلُ وَأُمُّهُۥ صِدِّيقَةٌۭ
ምእምናን፦
49፥15 *ምእምናን* እነዚያ በአላህና በመልእከተኛው ያመኑት ከዚያም ያልተጠራጠሩት በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው፡፡ *እነዚያ እነሱ እውነተኞቹ ናቸው*፡፡ إِنَّمَا ٱلْمُؤْمِنُونَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ ثُمَّ لَمْ يَرْتَابُوا۟ وَجَٰهَدُوا۟ بِأَمْوَٰلِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ ۚ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلصَّٰدِقُونَ

ስለዚህ እውነት ወይም እውነተኛ የተባለ ሁሉ አምላክ ነው ብሎ ማለት ቂልነት ነው፤ "ኢየሱስ እውነት ነው" ከተባለ ነብያችን”ﷺ”፣ መርየም እና ምእምናን በተባሉበት ሒሳብና ስሌት እንጂ አላህ በተባለበት ቀመር አይደለም።
ነጥብ ሁለት
"እውነት በባይብል"
"እውነት" የሚለው ቃል በዕብራይስጥ ብሉይ ኪዳን "ኢመት" אֱמֶת ሲሆን በግሪክ አዲስ ኪዳን ደግሞ "አሌቴስ" ἀληθής ነው፤ ወደ ባይብሉ ከሄድን "እውነት" የፈጣሪ የእጆቹ ሥራ የሆነው የብስ ነው፦
መዝሙር 111፥7 *የእጆቹ ሥራ "እውነት" אֱמֶ֣ת እና ፍርድ ነው*፤
መዝሙር 95፥5 ባሕር የእርሱ ናት እርሱም አደረጋት፥ *የብስንም እጆቹ ሠሩአት*።

የብስ ማለትም ምድር እውነት ስለተባለ አምላክ ነውን? በተጨማሪ ሐናንያን እውነት ተብሏል፦
ነህምያ 7፥2 ወንድሜን አናኒንና የግንቡን አለቃ ሐናንያን በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኋቸው፤ *እርሱም "እውነተኛ" אֱמֶ֔ת ከሌሎቹም ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ*።
ትዕማር እውነት ተብላለች፦
ዘፍጥረት 38፥26 ይሁዳም አወቀ፦ ከእኔ ይልቅ እርስዋ *"እውነተኛ" צָֽדְקָ֣ה ሆነች*፤ ልጄን ሴሎምን አልሰጠኋትምና አለ። ደግሞም አላወቃትም።

አይ የብስ፣ ሐናንያን፣ ትዕማር እውነት የተባሉት በአንጻራዊ ነው ከተባለ ኢየሱስም እውነት የተባለው በአንጻራዊ ነው፤ ምክንያቱም ኢየሱስ የላከው እውነተኛ እንደሆነ ቃለ-ምስክርነቱን ሰጥቷልና፦
ዮሐንስ 7፥28 እንግዲህ ኢየሱስ በመቅደስ ሲያስተምር፦ እኔንም ታውቁኛላችሁ ከወዴትም እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፤ እኔም በራሴ አልመጣሁም ነገር ግን እናንተ የማታውቁት *የላከኝ "እውነተኛ" ἀληθινὸς ነው*፤
ዮሐንስ 8፥26 ስለ እናንተ የምናገረው የምፈርደውም ብዙ ነገር አለኝ፤ ዳሩ ግን *የላከኝ "እውነተኛ" ἀληθής ነው* እኔም *ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ አላቸው*።

በእርግጥም ኢየሱስ በጴንጤናዊውም በጲላጦስ ዘንድ መልካሙን መታመን ታምኖ የላከው የአንድ አምላክ ታማኝ እና እውነተኛ ምስክር ነው፤ ፍፁም እውነት ለሆነው ለአንዱ አምላክ ሊመሰክር ተልኳል፦
ራእይ 3፥14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ አሜን የሆነው፥ *የታመነውና እውነተኛው ምስክር*፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል፦
ዮሐንስ 18፥37 እኔ *ለ"እውነት" ἀλήθεια ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ* ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ *ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል* አለው።
1 ጢሞቴዎስ 6፥13 ሁሉን በሕይወት በሚጠብቅ በእግዚአብሔር ፊት፥ *በጴንጤናዊውም በጲላጦስ ዘንድ መልካሙን መታመን በመሰከረ* በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት አዝሃለሁ፤

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የሚያደርጉትን አያውቁምና

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

ኢማም ሙስሊም : መጽሐፍ 19, ሐዲስ 4417
አነሥ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ”
በሑድ ጦርነት የፊት ጥርሳቸው ተሰበረ፣ እራሳቸው ቆሰለ፤ ደም ከፊታቸው ይጠርጉ ነበር፤ እንዲህ አሉ፦ “ያ ህዝብ እንዴት ሊድን ይችላል ነብዩን እያቆሰለ እና ጥርሱን እየሰበረ ወደ አላህ ይፀልይለታል? በዚያን ጊዜ የላቀው እና ክቡሩ አላህ፦ 3፥128 “አላህ በእነርሱ ላይ ይቅርታ እስኪያደርግ ወይም እነርሱ በዳዮች ናቸውና እስኪቀጣቸው ድረስ ለአንተ ከነገሩ ምንም የለህም” የሚለውን አንቀጽ አወረደ። عَنْ أَنَسٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم كُسِرَتْ رَبَاعِيَتُهُ يَوْمَ أُحُدٍ وَشُجَّ فِي رَأْسِهِ فَجَعَلَ يَسْلُتُ الدَّمَ عَنْهُ وَيَقُولُ ‏”‏ كَيْفَ يُفْلِحُ قَوْمٌ شَجُّوا نَبِيَّهُمْ وَكَسَرُوا رَبَاعِيَتَهُ وَهُوَ يَدْعُوهُمْ إِلَى اللَّهِ ‏”‏ ‏.‏ فَأَنْزَلَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ ‏{‏ لَيْسَ لَكَ مِنَ الأَمْرِ شَىْءٌ‏}‏

ነብያችን”ﷺ” የጸለዩት ጸሎት ደግሞ ምን እንደሆነ ዐብደላህ ከእርሳቸው የሰማውን በሦስተኛ መደብ በሚቀጥለው ቁጥር እንዲህ ይነግረናል፦
ኢማም ሙስሊም : መጽሐፍ 19, ሐዲስ 4418
ለእኔ የአላህን መልእክተኛ”ﷺ” ስመለከት ታዩኝ የተናገሩትን ሰማዋቸው፦ ነብይ በህዝቡ ሲደበድቡት፣ ደም ከፊቱ ሲጠርግ፦ “ጌታዬ ሆይ ህዝቦቼን የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅርታ አድርግላቸው” አለ። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ كَأَنِّي أَنْظُرُ إِلَى رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَحْكِي نَبِيًّا مِنَ الأَنْبِيَاءِ ضَرَبَهُ قَوْمُهُ وَهُوَ يَمْسَحُ الدَّمَ عَنْ وَجْهِهِ وَيَقُولُ ‏ “‏ رَبِّ اغْفِرْ لِقَوْمِي فَإِنَّهُمْ لاَ يَعْلَمُونَ ‏”

አንዳንድ ቂል መሃይማን “ጌታዬ ሆይ ህዝቦቼን የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅርታ አድርግላቸው” የሚለውን ከዚህ ጥቅስ ጋር ለማዛመድ ሞክረዋል፦
ሉቃስ 23፥34 ኢየሱስም፦ *አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው* አለ።

የሚያጅበው ግን ይህንን ንግግር እንኳን ኢየሱስ ሊናገረው ይቅርና የሉቃስ ወንጌል ላይ ባሉት የግሪክ እደ-ክታባት ላይ ሽታው የለም። ይህንን የአዲስ ኪዳን ለዘብተኛ ምሁር ዶክተር ሄርማን እና ጽንፈኛ ምሁር ጀምስ ኃይት ተናግረዋል። NIV የግርጌ ማስታወሻ ላይም፦ “Luke 23፥34 some early manuscripts do not have this sentence” በማለት እርማችሁን እንድታወጡ አርድቷችኃል፦
https://youtu.be/eWiY32bb2K8


ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ውሸት ሲጋለጥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

17፥81 በልም *«እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»* وَقُلْ جَآءَ ٱلْحَقُّ وَزَهَقَ ٱلْبَٰطِلُ ۚ إِنَّ ٱلْبَٰطِلَ كَانَ زَهُوقًۭا

ሰው የሚዋሸት ከሁለት ነገር አንጻር ነው፥ አንዱ ባለማወቅ ሲሆን ሁለተኛው ሆን ብሎ ህሊናውን በመሸጥ ነው። እውነት ሲገለጥ ውሸት ይጋለጣል፥ እውነት ሲመጣ ውሸት ሁልጊዜ መቋቋው አይችልም። ውሸት በእውነት ፊት እሳት የነካው ሰም፣ ጸሐይ ያየው ቅቤ፣ ነፋስ የጎበኘው አቧራ ይሆናል። እውነትን በውሸት ላይ ስትጥለው ያፈራርሰዋል፥ ምክንያቱም ውሸትም መነሻም መድረሻም የለውምና እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነው፦
21፥18 በእርግጥ *እውነትን በውሸት ላይ እንጥላለን፡፡ አንጎሉን ያፈርሰዋልም፡፡ ወዲያውም እርሱ ጠፊ ነው፡፡ ለእናንተም ከዚያ ከምትመጥኑት ነገር ብርቱ ቅጣት አላችሁ፤ ወዮላችሁ*፡፡ بَلْ نَقْذِفُ بِٱلْحَقِّ عَلَى ٱلْبَٰطِلِ فَيَدْمَغُهُۥ فَإِذَا هُوَ زَاهِقٌۭ ۚ وَلَكُمُ ٱلْوَيْلُ مِمَّا تَصِفُونَ
34፥49 *«እውነቱ መጣ፤ ውሸትም መነሻም መድረሻም የለውም ተወገደ*» በላቸው፡፡ قُلْ جَآءَ ٱلْحَقُّ وَمَا يُبْدِئُ ٱلْبَٰطِلُ وَمَا يُعِيدُ

ይህንን ውሸት ለማጋለጥ እውነቱን እንግለጥ፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 63 ሐዲስ 75
ኑዐይም ኢብኑ ሐማድ እንደተረከው፤ ዐምር ኢብኑ መይሙን አለ፦ “በዘመነ-ድንቁርና ጊዜ ሴት ዝንጀሮ በብዙ ዝንጀሮዎች ተከባ አየው፤ ሕጋዊ ያልሆነ ተራክቦ አድርጋለች በሚል ምክንያት ሁሉም በድንጋይ ወገሯት፤ እኔም ከእነሱ ጋር ወገርኳት። حَدَّثَنَا نُعَيْمُ بْنُ حَمَّادٍ، حَدَّثَنَا هُشَيْمٌ، عَنْ حُصَيْنٍ، عَنْ عَمْرِو بْنِ مَيْمُونٍ، قَالَ رَأَيْتُ فِي الْجَاهِلِيَّةِ قِرْدَةً اجْتَمَعَ عَلَيْهَا قِرَدَةٌ قَدْ زَنَتْ، فَرَجَمُوهَا فَرَجَمْتُهَا مَعَهُمْ‏.‏

ቀጣፊዎች ይህንን ሐዲስ ይዘው፦ “ነብያችሁ”ﷺ” ዝንጅሮ ወግሯል” እያሉ ይቀጥፋሉ፤ ሲጀመር ይህንን ድርጊት አደረኩኝ እያለ ያለው ዐምር ኢብኑ መይሙን እንጂ ነብያችን”ﷺ” አይደሉም፤ ይህን የተናገሩት ነብያችን”ﷺ” ቢሆኑ ኖሮ ሐዲሱ በግልጽ “ቃለ ነብይ” ወይም “ቃለ ረሱል” ብሎ ይጀምር ነበር፤ የነብያችን”ﷺ ንግግር ሽታው እንኳን እዚህ ሐዲስ ላይ የለም።
ሲቀጥል ዐምር ኢብኑ መይሙን የተናገረው በዘመነ-ድንቁርና ጊዜ ማለትም ቁርአን ከመውረዱ በፊት የነበረውን የጨለማ ጊዜ በአውንታዊ ሳይሆን በአሉታዊ ለመግለፅ ነው።
እውነት ተገለጠ ውሸት ተጋለጠ፤ በልም እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነው፦
17፥81 በልም *«እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»* وَقُلْ جَآءَ ٱلْحَقُّ وَزَهَقَ ٱلْبَٰطِلُ ۚ إِنَّ ٱلْبَٰطِلَ كَانَ زَهُوقًۭا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የእስራኤል ሕዝብ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥78 *ከእነሱም እርሱ ከመጽሐፉ ያይደለ ሲኾን ከመጽሐፉ መኾኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙ ክፍሎች አሉ፡፡ እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልኾነ ሲኾን «እርሱ ከአላህ ዘንድ ነውም» ይላሉ፡፡ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑም በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ*፡፡ وَإِنَّ مِنْهُمْ لَفَرِيقًا يَلْوُونَ أَلْسِنَتَهُم بِالْكِتَابِ لِتَحْسَبُوهُ مِنَ الْكِتَابِ وَمَا هُوَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَقُولُونَ هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَمَا هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَيَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

ኢሳይያስ 53፥1-12 ዐውዱ የሚያወራው ስለ እስራኤል ሕዝብ ሆኖ ሳለ የክርስትናው ዓለም ግን ለኢየሱስ ስቃይ ነው በሚል እንደ ማስረጃ ይጠቀሙበታል። ነገር ግን የጥንት አይሁዳውያን እና የዘመኑ አይሁዳውያን እነዚህ ምዕራፍ "ስለ እስራኤል ሕዝብ የሚናገር ነው" ብለው ክፉኛ ይሞግታሉ። እስቲ ኢሳይያስ 53 ላይ ያሉትን አናቅጽ ጥርስና ምላሱን እየነቀስን እናስተንትን፦

አንቀጽ አንድ
የእግዚአብሔር ክንድ ተገልጦአል፦
ኢሳይያስ 53፥1የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? *የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?*

የእግዚአብሔር ክንድ በአሕዛብ ሁሉ ፊት ተገልጦአል፦
ኢሳይያስ 52፥10 *"እግዚአብሔር የተቀደሰውን ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ገልጦአል"*።

ያህዌህ ጥንት እስራኤላውያንን ከግብፃውያንም ባርነት በተዘረጋ ክንዱ ታድጓቸዋል፦
ዘጸአት6፥6 ስለዚህም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፦ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከግብፃውያንም ባርነት አወጣችኋለሁ፥ ከተገዥነታቸውም አድናችኋለሁ፤ *"በተዘረጋ ክንድ በታላቅ ፍርድም እታደጋችኋለሁ"*።
መዝሙር 77፥15 የያዕቆብንና የዮሴፍን ልጆች፥ *"ሕዝብህን በክንድህ አዳንሃቸው"*።

በተመሳሳይም የእግዚአብሔር ክንድ በአሕዛብ ሁሉ ፊት ተገልጦ ጥንት የእስራኤልን ሕዝብ እንደታደ በምርኮ ያሉትን እስራኤላውያን ይታደጋል፦
ኢሳይያስ 51፥9-10 *የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ፥ ተነሥ፥ ተነሥ፥ ኃይልንም ልበስ በቀድሞው ወራትና በጥንቱ ዘመን በነበረው ትውልድ እንደ ሆነው ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?ባሕሩንና የታላቁን ጥልቅ ውኃ ያደረቅኸው፥ የዳኑትም ይሻገሩ ዘንድ ጠሊቁን ባሕር መንገድ ያደረግህ አንተ አይደለህምን?*
ኤርምያስ 21፥4-5 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ *የባቢሎንን ንጉሥ በቅጥርም ውጭ የከበቡአችሁን ከለዳውያንን የምትወጉበትን በእጃችሁ ያለውን ዕቃ ጦራችሁን እመልሰዋለሁ፥ እነዚያንም ወደዚህች ከተማ ውስጥ እሰበስባቸዋለሁ። እኔም በተዘረጋች እጅና "በብርቱ ክንድ"፥ በቍጣና በመዓት በታላቅም መቅሠፍት እወጋችኋለሁ*።

አንቀጽ ሁለት
እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል፦
ኢሳይያስ 53፥2 *በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል። መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም*።

ከደረቅ መሬት ከግብጽ እንደ ቡቃያ የበቀለው የእስራኤል ሕዝብ ነው፦
መዝሙር 80፥8-11 *ከግብጽ የወይን ግንድ አመጣህ፤ አሕዛብን አባረርህ እርስዋንም ተከልህ። በፊትዋም ስፍራን አዘጋጀህ፥ ሥሮችዋንም ተከልህ ምድርንም ሞላች። ጥላዋ ተራሮችን ከደነ፥ ጫፎችዋም እንደ እግዚአብሔር ዝግባ ሆኑ። ቅርንጫፎችዋንም እስከ ባሕር፥ ቡቃያዋንም እስከ ወንዙ ዘረጋች*።
ሕዝቅኤል 19፥13 *አሁንም በምድረ በዳ፥ በደረቅና በተጠማች መሬት ተተከለች*።

መልክና ውበት፣ ደም ግባት የለውም፦
ኢሳይያስ 53፥2 *መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም*።

የእስራኤል ሕዝብ ግን ፊቱ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ፥ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጐሳቍሎአልና፦
ኢሳይያስ 52፥14 *ፊቱ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ፥ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጐሳቍሎአልና*።
ኤርምያስ 46፥12 አሕዛብ *ጕስቍልናሽን ሰምተዋል*፥ ልቅሶሽም ምድርን ሞልቶአታል።
ሕዝቅኤል 7፥3 *ጕስቍልናሽንም ሁሉ አመጣብሻለሁ*።
ሕዝቅኤል 7፥8 *ጕስቍልናሽንም ሁሉ አመጣብሻለሁ*።
መዝሙር 44፥25 *ነፍሳችን በመሬት ላይ ተጐሳቍላለችና*፥ ሆዳችንም ወደ ምድር ተጣብቃለችና።

መሢሑ ግን በትንቢት ውበቱ ያምራል እንጂ ይጎሳቆላል የሚል አንቀጽ የለም፦
መዝሙር 45፥2 *ውበትህ ከሰው ልጆች ይልቅ ያምራል*፤ ሞገስ በከንፈሮችህ ፈሰሰ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘላለም ባረከህ።
3፤ ኃያል ሆይ፥ *በቍንጅናህና በውበትህ* ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ።

አንቀጽ ሦስት-አምስት
የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፦
ኢሳይያስ 53፥3 *የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም*።

የእስራኤል ሕዝብ ሰዎች የሚንቁት ሕዝብም የሚጠላው ባሪያ ነው፥ ደዌውን እና ቍስሉን ባየ ጊዜ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ ወደ ንጉሡም ወደ ኢያሪም መልእክተኛን ላከ፤ እርሱ ግን ይፈውሳችሁ ዘንድ፥ ከቊስላችሁም ያድናችሁ ዘንድ አልቻለም፥ ይህ ሕዝብ ከሰውም የተጠላ ነበር፦
ኢሳይያስ 49፥7፤ የእስራኤል ታዳጊ ቅዱሱም፥ እግዚአብሔር፥ *ሰዎች ለሚንቁት ሕዝብም ለሚጠላው* ለገዥዎች ባሪያ እንዲህ ይላል፦ ስለ ታማኙ ስለ እግዚአብሔር ስለ መረጠህም ስለ እስራኤል ቅዱስ ነገሥታት አይተው ይነሣሉ፥ መሳፍንትም አይተው ይሰግዳሉ።
ሆሴዕ 5፥13 ኤፍሬምም *ደዌውን፥ ይሁዳም ቍስሉን* ባየ ጊዜ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ ወደ ንጉሡም ወደ ኢያሪም መልእክተኛን ላከ፤ እርሱ ግን ይፈውሳችሁ ዘንድ፥ *ከቊስላችሁም ያድናችሁ ዘንድ አልቻለም*።
ኤርምያስ 30፥12 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ *ስብራትህ የማይፈወስ ቍስልህም ክፉ ነው*።
ኤርሚያስ 22፥23 አንቺ በሊባኖስ የምትቀመጪ፥ በዝግባ ዛፍም ውስጥ ጎጆሽን የምትሠሪ ሆይ፥ ምጥ እንደ ያዛት ሴት *"ሕማም በያዘሽ ጊዜ"* እንዴት ታጓሪያለሽ!
ኢሳያስ 60፥15 ከሰውም ማንም እስከማያልፍብሽ ድረስ የተተውሽና *የተጠላሽ ነበርሽ*።

አንቀጽ ስድስት-ሰባት
በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፦
ኢሳይያስ 53፥7 ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ *ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም*።

በሸላቶቹም ፊት ዝም ያለ የባዘነ በግ የእስራኤል ሕዝብ ነው፥ ሸላቶቹም መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፥ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አጥንቱን ቈረጠመው፦
ኤርምያስ 50፥17 *እስራኤል የባዘነ በግ ነው፤ አንበሶች አሳደዱት፤ መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፥ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አጥንቱን ቈረጠመው*።
መዝሙር 44፥22 ስለ አንተ ሁልጊዜም ተገድለናል፥ *እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል*።

የእስራኤል ሕዝብ የደረሰበትን መከራ ለማሳየት የተሰጠ ፍካሬአዊ አነጋገር ነው፦
ኤርምያስ 30፥7 ወዮ! ያ ቀን ታላቅ ነውና፥ እርሱንም የሚመስል የለምና፤ *ያ የያዕቆብ መከራ ዘመን ነው*፥ ነገር ግን ከእርሱ ይድናል።
አንቀጽ ስምንት
በግዞት እና በፍርድ ተወሰደ፦
ኢሳይያስ 53፥8 በግዞት እና በፍርድ *"ተወሰደ" ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር "እርሱ" לָֽמוֹ እንደ ተወገደ* ከትውልዱ ማን አስተዋለ?

በሰቆቃ በባቢሎን ከሕያዋን ምድር ከከነዓን ተግዘው ስለ ቀድሞ ሕዝብ ይህኛው ሕዝብ ተመተው እንደተወገዱ ከትውልዱ ማን አስተዋለ? ማንም። "እርሱ" ብለው የተረጎሙት ቃል "ላሞው" לָֽמוֹ ሲሆን ትርጉሙ "እነርሱ" ማለት ነው እንጂ "ሁ" ה֚וּא ማለትም "እርሱ" ማለት አይደለም፦
ኢሳይያስ 48፥21 በምድረ በዳ በኩል *"እነርሱን"* לָ֑מוֹ በመራቸው ጊዜ አልተጠሙም፤ ውኃንም ከዓለቱ ውስጥ አፈለቀላቸው፥ ዓለቱንም ሰነጠቀ ውኃውም ፈሰሰ።
መዝሙር 99፥7 በደመና ዓምድም ተናገራቸው፤ ምስክሩንና የሰጣቸውን ትእዛዝ *"እነርሱን"* לָ֑מוֹ ጠበቁ።

ስለዚህ ዐውዱ ላይ ያለው የህማም ሰው ሕዝብ ነው እንጂ አንድ ግለሰብ አይደለም። "ሉጋህ" לֻקַּ֥ח ማለት "ተወሰደ" ማለት ነው። ከከነዓን ወደ ባቢሎን ተማርኮ መወሰዱን ያሳያል። "ስለ ሕዝቤ ኃጢአት" የሚለው ይሰመርበት። ስለ ቀድሞ ሕዝብ ይህ አዲሱ ሕዝብ ወደ ባቢሎን ተወስዷል፦
ኢሳይያስ 52፥5 *"ሕዝቤ በከንቱ ተወስዶአልና? לֻקַּ֥ח አሁን ከዚህ ምን አለኝ? ይላል እግዚአብሔር"*።

"ተወስዷል" ለሚለው መጠይቅ ግስ የገባው ቃል ልክ ከላይ እንዳለው "ሉጋህ" לֻקַּ֥ח ነው። ይህም በምርኮ መወሰድን ያመለክታል፦
ሕዝቅኤል 17፥12 እነሆ፥ *"የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ ንጉሥዋንና መኳንንቶችዋንም ማረከ፥ ወደ እርሱም ወደ ባቢሎን "ወሰዳቸው" וַיִּקַּ֤ח *።

አንቀጽ ዘጠኝ
ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፦
ኢሳይያስ 53፥9 *ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ፥ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር*።

የእስራኤል ሕዝብ ከክፉዎችም ከባቢሎናውያን ጋር በመቃብር ሆነዋል፥ ይህም መቃብር ምርኮ ነው፦
ሕዝቅኤል 37፥12 ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው፦ አዶናይ ያህዌክ እንዲህ ይላል፦ *"ሕዝቤ ሆይ፥ እነሆ፥ መቃብራችሁን እከፍታለሁ፥ ከመቃብራችሁም አወጣችኋለሁ፥ ወደ እስራኤልም ምድር አገባችኋለሁ"*።

ምርኮውን መቃብር እንዳለው እናስተውል፥ ከምርኮ ወደ እስራኤልም ምድር ከሰባ ዓመት በኃላ ገብተዋል።
ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር፦
ኢሳይያስ 53፥9 *ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር*።

የእስራኤል ቅሬታ ግፍን አይሠሩም፥ ሐሰትንም አይናገሩም፥ በአፋቸውም ውስጥ ተንኰለኛ ምላስ አይገኝም፦
ሶፎንያስ 3፥13 *የእስራኤል ቅሬታ ኃጢአትን አይሠሩም፥ ሐሰትንም አይናገሩም፥ በአፋቸውም ውስጥ ተንኰለኛ ምላስ አይገኝም*።

አንቀጽ አስር
የእስራኤል ሕዝብ ሕይወቱን ለኃጢአት መስዋዕት አርጎ ሰጥቷል፦
ኢሳይያስ 53፥10 *እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል*።

ከታች፦ "አባቶቻችን ኃጢአትን ሠሩ ዛሬም የሉም፤ እኛም በደላቸውን ተሸከምን" የሚል ቃል አለ፥ ለእውነት መሞት መስዋዕትነት ነው። ጳውሎስ፦ "የእኔ ሕይወት ይሠዋልና" ብሏል፦
2 ጢሞቴዎስ 4፥6 *በመሥዋዕት እንደሚደረግ፥ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና*፥ የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል።

የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ ነፍስ ነው፥ ይህ በምርኮ የተሰበረና የተዋረደ ነፍስ መሥዋዕት ነው፦
መዝሙር 51፥17 *የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፥ የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም*።

የእስራኤል ሕዝብ ሕይወቱን በምርኮ መስዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፦
ኢሳይያስ 53፥10 *እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል*።

ዕድሜውም ይረዝማል ማለት "የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናል" ማለት ነው፥ ዘሩን ያያል ማለት "እነርሱ ከነልጆቻቸው የእግዚአብሔር ቡሩካን ዘር ናቸውና በከንቱ አይደክሙም ለጥፋትም አይወልዱም" ማለት ነው፦
ኢሳይያስ 65፥22-23 ሌላ እንዲቀመጥበት አይሠሩም፥ ሌላም እንዲበላው አይተከሉም፤ *የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፥ እኔም የመረጥኋቸው በእጃቸው ሥራ ረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋልና*። *እነርሱ ከነልጆቻቸው የእግዚአብሔር ቡሩካን ዘር ናቸውና በከንቱ አይደክሙም ለጥፋትም አይወልዱም*።
አንቀጽ አስራ አንድ
ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል፦
ኢሳይያስ 53፥11 *ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል*፥ ደስም ይለዋል።

ያህዌህ የእስራኤል ሕዝብ የቈሰለውን ቁስል በፈወሰ ዕለት ብርሃን ያያል ማለት የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን፥ የፀሐይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይሆናል ማለት ነው፥ ከምርኮ በኃላ ደስ ይላቸዋል፦
ኢሳይያስ 30፥26 *እግዚአብሔርም የሕዝቡን ስብራት በጠገነ ዕለት፥ መቅሰፍቱ የቈሰለውንም በፈወሰ ዕለት፥ የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን፥ የፀሐይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይሆናል*።
ኢሳይያስ 9፥3 *ሕዝብን አብዝተሃል፥ ደስታንም ጨምረህላቸዋል፤ በመከር ደስ እንደሚላቸው፥ *ሰዎችም ምርኮን ሲካፈሉ ደስ እንደሚላቸው በፊትህ ደስ ይላቸዋል*።

ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፦
ኢሳይያስ 53፥11 ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ *ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል*።

ባሪያዬ የተባለው የእስራኤል ሕዝብ ነው፥ የሚያጸድቀውም በእውቀት በማስተማር ነው፦
ኢሳይያስ 52፥13 *እነሆ፥ ባሪያዬ በማስተዋል ያደርጋል፤ ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል፥ እጅግ ታላቅም ይሆናል*።
ኢሳይያስ 44፥21 *ያዕቆብ ሆይ፥ አንተም እስራኤል፥ ባሪያዬ ነህና ይህን አስብ፤ እኔ ሠርቼሃለሁ አንተም ባሪያዬ ነህ፤ እስራኤል ሆይ፥ በእኔ ዘንድ ያልተረሳ ትሆናለህ*።
ኢሳይያስ 49፥3 እርሱም፦ *"እስራኤል ሆይ፥ አንተ ባሪያዬ ነህ፤ በአንተም እከበራለሁ አለኝ"*።

ኃጢአታቸውን ይሸከማል፦
ኢሳይያስ 53፥11 ኃጢአታቸውን *ይሸከማል* יִסְבֹּֽל ።

"ወአዎኖታም" וַעֲוֺנֹתָ֖ם ማለት "ኃጢአታቸውን" ወይም "በደላቸውን" ማለት ነው። "ይስቦል" יִסְבֹּֽל ማለት "ይሽከማል" ማለት ነው። ይህ ይሸከማል የተባለው ደግሞ የእስራኤል ሕዝብ ነው፦
ሰቆቃው ኤርምያስ 5፥7 *"አባቶቻችን ኃጢአትን ሠሩ ዛሬም የሉም፤ እኛም በደላቸውን ተሸከምን" סָבָֽלְנוּ *።

"ሳባሌኑ" סָבָֽלְנוּ ማለት "ተሸከምን" ማለት ሲሆን ተሸካሚዎቹ በባቢሎን ምርኮ ያሉት ናቸው። "በደላቸውን" ለሚለው ቃል የገባው በተመሳሳይ "ወአዎኖቴም" עֲוֺנֹתֵיהֶ֥ם ነው። ሰቆቃ ማለት ስቃይ ማለት ነው፥ የእስራኤል ቅሬታ የእስራኤልንም ቤት ኃጢአት ተሸክሟል፦
ሕዝቅኤል 4፥4 *"አንተም በግራ ጐድንህ ተኛ የእስራኤልንም ቤት ኃጢአት አኑርባት፤ በምትተኛበትም ቀን ቍጥር ኃጢአታቸውን ትሸከማለህ"*።
4፥5 እኔም የኃጢአታቸውን ዓመታት ለአንተ የቀን ቍጥር እንዲሆንልህ ሦስት መቶ ዘጠና ቀን ሰጥቼሃለሁ፤ *"የእስራኤልንም ቤት ኃጢአት ትሸከማለህ"*።
ኢሳይያስ53፥6 እግዚአብሔርም *"የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ"*።

አንቀጽ አስራ ሁለት
ከኃያላን ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፦
ኢሳይያስ 53፥12 ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ *ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል*።

ኃያላን የተባሉት ከባቢሎን ምርኮ በኃላ የተነሱት ነገሥታት ናቸው፦
ዕዝራ 4፥20 *በኢየሩሳሌምም እጅግ ኃያላን ነገሥታት ነበሩ"*፥ በወንዝም ማዶ ያለውን አገር ሁሉ ይገዙ ነበር፤ ግብርንና ቀረጥን መጥንንም ይቀበሉ ነበር።

በትንቢቱ መሠረት የአምላክ ሕዝብ ከኃያላን ጋር ምርኮን ተከፋፍለዋል፦
ኢሳይያስ 9፥3 ሕዝብን አብዝተሃል፥ ደስታንም ጨምረህላቸዋል፤ በመከር ደስ እንደሚላቸው፥ *ሰዎችም ምርኮን ሲካፈሉ ደስ እንደሚላቸው በፊትህ ደስ ይላቸዋል*።

ስለ ዓመፀኞችም ማለደ፦
ኢሳይያስ 53፥12 ስለ ዓመፀኞችም *”ማለደ”*።

የማለዱት ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የተበተኑት ናቸው፥ ላስማርክኋችሁ ከተማ ወደ እግዚአብሔር ማልደዋል፦
ሶፎንያስ 3፥10 ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ *የሚማልዱኝ*፥ የተበተኑት ሴቶች ልጆቼ፥ ቍርባኔን ያመጡልኛል።
ኤርምያስ 29፥7 በእርስዋ ሰላም ሰላም ይሆንላችኋልና ወደ እርስዋ ላስማርክኋችሁ ከተማ ሰላምን ፈልጉ፥ *"ስለ እርስዋም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ"*።

ከላይ ከ 1-12 አናቅጽ ላይ ስለ እስራኤል ሕዝብ ሆኖ ሳለ ነገር ግን የአዲስ ኪዳን እደ-ክታባት አዘጋጆች ለኢየሱስ ስቃይ ትንቢት አድርገው መጠቀማቸው አያስገርምም። ምክንያቱም ይህ የተለመደ የማጣማም ሥራ ነው፥ ለምሳሌ ይህንን ጥቅስ እንመልከት፦
ሆሴዕ 11፥1-2 *እስራኤል ሕፃን በነበረ ጊዜ ወደድሁት፥ ልጄንም ከግብፅ ጠራሁት። አብዝቼ ብጠራቸው አጥብቀው ከፊቴ ራቁ፤ ለበኣሊምም ይሠዉ ነበር፥ ለተቀረጹ ምስሎችም ያጥኑ ነበር*።
ዘጸአት 4፥22 ፈርዖንንም፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ *እስራኤል የበኵር ልጄ ነው"*።

ልብ አድርግ ከግብፅ የተጠራው ልጅ አጥብቆ ከአምላክ ፊት የራቀ፤ ለበኣሊምም ይሠዋ የነበረ፥ ለተቀረጹ ምስሎችም ያጥን የነበረ የእስራኤል ሕዝብ ሆኖ ሳለ ግን የአዲስ ኪዳን እደ-ክታባት አዘጋጆች ለኢየሱስ ትንቢት ነው ይሉናል፦
ማቴዎስ 2፥14-15፤ እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና *ከጌታ ዘንድ በነቢይ፦ "ልጄን ከግብፅ ጠራሁት" የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብፅ ሄደ"*፥ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ።

እውነት ኢየሱስ አጥብቆ ከአምላክ ፊት የራቀ፤ ለበኣሊም ይሠዋ የነበረ፥ ለተቀረጹ ምስሎችም ያጥን የነበረ ነውን? በዚህ ቴኦሎጅን እንዴት ቶኦሎጃይዝ ማድረግ ይቻላል? ይህ እኮ ትንቢት ነው፥ ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፦
2 ጴጥሮስ 1፥20 ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ *በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም"*።

ብዙዎች ከመጽሐፉ ያይደለ ሲኾን ከመጽሐፉ መኾኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙ ክፍሎች እንደዚህ አይነቶቹ ናቸው፦
3፥78 *ከእነሱም እርሱ ከመጽሐፉ ያይደለ ሲኾን ከመጽሐፉ መኾኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙ ክፍሎች አሉ፡፡ እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልኾነ ሲኾን «እርሱ ከአላህ ዘንድ ነውም» ይላሉ፡፡ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑም በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ*፡፡ وَإِنَّ مِنْهُمْ لَفَرِيقًا يَلْوُونَ أَلْسِنَتَهُم بِالْكِتَابِ لِتَحْسَبُوهُ مِنَ الْكِتَابِ وَمَا هُوَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَقُولُونَ هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَمَا هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَيَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኢየሱስ ፍጡር ነው!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥47 ፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ *አላህ የሚሻውን ይፈጥራል*፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِى وَلَدٌۭ وَلَمْ يَمْسَسْنِى بَشَرٌۭ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ ٱللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَآءُ ۚ إِذَا قَضَىٰٓ أَمْرًۭا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

በሥነ-ኑባሬ ጥናት"ontology" ውስጥ መንስኤ"cause" እና ውጤት"effect" ድርና ማግ ናቸው። ለምሳሌ አናጺ መንስኤ እና ጠረጴዛ ውጤት ናቸው፤ አናጺን አናጺ አይሰራውም፤ ባይሆን አናጺውን ሌላ ኑባሬ ይሰራዋል፤ ፈጣሪ መንስኤ ሲሆን ፍጡር ውጤት ነው፤ አናጺን አናጺ እንደማይሰራው ሁሉ ፈጣሪን ፈጣሪ አይፈጥረውም፤ ስለዚህ ፈጣሪ መንስኤ የሌለው እና የመንስኤዎች ሁሉ መንስኤ ነው"Causeless Cause and the cause of the causes" እርሱ ይፈጥራል እንጂ አይፈጠርም፤ ፈጣሪና ፍጡር ሁለት ተቃራኒ ባሕርያት ያላቸው ናቸው።

በክርስትናው ኢየሱስ ፈጣሪና ፍጡር ነው የሚል ክፉኛ የተወሳሰበ ትምህርት አለ፥ በተቃራኒው በኢሥላም ደግሞ፦ "ኢየሱስ ፍጡር ብቻ ነው" የሚል ጥልልና ጥንፍፍ ያለ ትምህርት አለ። አምላካችን አላህ በማህጸን ውስጥ እንደሚፈልገው የሚፈጥርና የሚቀርጽ ነው፤ አንዳችን ነገር በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል፤ ዒሳንም በዚህ መልኩ ፈጥሮታል፦
3፥47 ፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ *አላህ የሚሻውን ይፈጥራል*፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِى وَلَدٌۭ وَلَمْ يَمْسَسْنِى بَشَرٌۭ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ ٱللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَآءُ ۚ إِذَا قَضَىٰٓ أَمْرًۭا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

አላህ ኢየሱስን ያለ ዘርዐ-ብእሲ ማለትም ያለ ወንድ ዘር ሁን በሚለው ቃል ፈጥሮታል ማለት ነው፤ ይህ ግልጽ እና ያልተዛባ ተስተምህሮት ነው፤ እስቲ የክርስትናውን ክፉኛ ውስብስብ አስተምህሮት ሞጋችና ጦማሪ እንደመሆኔ መጠን የሙግት ጦማርን ልጦምር።

"ኢየሱስ" የሚለው ስም የናዝሬቱ ኢየሱስ ከመፈጠሩ በፊት ብሉይ ኪዳን ላይ ያሉ ፍጡራን ሲጠሩበት የነበረ የፍጡር ስም ነው። የናዝሬቱ ኢየሱስ ከመወለዱ በፊት ይህ ስም ለራሱ ለኢየሱስ አገልግሎት ላይ የዋለበት ጥቅስ የለም፤ ከእርሱ በፊት ለእርሱ ለራሱ ስሙ አገልግሎት ላይ አልዋለም ከተባለ እራሱም የለም። ሲወለድ እንደ እስማኤል እና እንደ ሶምሶም በመልአክ የተሰየመ ነው ከተባለ ከጊዜ በኃላ የተጠራ ስም ሁሉ የፍጡራን ስም ነው።

ምን ስሙ ብቻ እራሱን ማንነቱ ማርያም ማህፀን ውስጥ መፈጠሩን በተለይ የክርስትና የዐቂዳህ መጽሐፍ የሆነው ሃይማኖተ-አበው ኢየሱስ ከመወለዱ በፊት በማህጸን ውስጥ የተፈጠረ "ፍጡር" ነው ይላል፦
1. ሃይማኖተ-አበው ዘመጠሊጎን 44፥3
ዘመጠሊጎን አለ፦
“ወለሊሁ ሐነፀ ሥጋሁ ውስጠ ከርሠ ድንግል ወኢተሳተፎ መኑሂ በፈጢረ ሥጋሁ አላ ለሊሁ ባሕቲቱ ፈጠሮ”

ትርጉም፦
"እርሱ ሥጋውን በድንግል ማሕፀን ፈጠረ፤ ሥጋውን በመፍጠር ማንም አጋዥ አልሆነውም፤ እርሱ እራሱ ፈጠረው እንጂ”

2. ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 124:19
ቄርሎስም አለ፦
"ንብሎ ፍጡረ እስመ ውእቱ ተወልደ በስጋ እምብእሲት"

ትርጉም፦
"ከሴት በሥጋ ስለተወለደ ፍጡር ነው እንላለን"

3. ሃይማኖተ-አበው ዘጎርጎርዮስ 35:6
ጎርጎርዮስም አለ፦
"ወዓዲመ ይትበሀል ፍጡረ በእንተ ዘኮነ ስጋ"

ትርጉም፦
"ስጋ ስለሆነ ፍጡር ይባላል"

"ፍጡረ" ማለት "ፍጡር" ማለት ነው። አንዱ እግዚአብሔር እንደ ተስፋው ቃሉ ከዳዊት ዘር ለእስራኤል መድኃኒትን ኢየሱስን ካለመኖር ወደ መኖር አመጣ፤ ይህም የተስፋ ቃል ኢየሱስ በማህፀን የተፈጠረ ፍጡር መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፦
ሐዋ ሥራ 13፥23 ከዚህም ሰው ዘር እግዚአብሔር እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም *ኢየሱስን አመጣ*።
ኢሳይያስ 49፥5-6 ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ እስራኤልንም ወደ እርሱ እንድሰበስብ ባሪያ እሆነው ዘንድ ከማኅፀን ጀምሮ *የሠራኝ* እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡— እርሱም፡— የያዕቆብን ነገዶች እንድታስነሣ ከእስራኤልም የዳኑትን እንድትመልስ ባሪያዬ ትሆን ዘንድ እጅግ ቀላል ነገር ነውና እስከ ምድር ዳር ድረስ መድኃኒት ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ፥ ይላል።

"ከማኅፀን ጀምሮ የሠራኝ" የሚለው ስለ ኢየሱስ መሆኑ የተለያዩ ጥንታዊ ማብራሪያ ማየት ይቻላል፤ ከዚህ መካከል ሃይማኖተ-አበው ላይ ቄርሎስ ነግሮናል፦
1. ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 76:19
ቄርሎስም አለ፦
"ወዓዲ ይቤ መድኅን በአፈ ዝንቱ ነብይ ኢሳይያስ በእንተ ልደቱ እምድንግል ወበእንተዝ ተፀነስኩ፤ እምከርሥ ከመ ዐቅም ምግባራተ ብዙኀ ወአቅም ነገደ ያዕቆብ ወአስተጋብእ ዝርዋነ እስራኤል ወበእንተዝ ግብር ተፈጥረ እምከርሰ ድንግል"

ትርጉም፦
"ዳግመኛም መድኅን ክርስቶስ ከድንግል ስለመወለዱ በኢሳይያስ አፍ "ብዙ ሥራ እሠራ ዘንድ የያዕቆብንም ወገን አጸና
ዘንድ አስራኤልንም አንድ አደርግ ዘንድ በማሕጸን ተፈጠርኩ አለ"

2. ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 76:21
ቄርሎስም አለ፦
"ወካዕበ ይቤ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር ዘፈጠረኒ እምከርስ እኩኖ ገብረ ለአስተጋብኦተ ሕዝበ ያዕቆብ ወለአንሥአተ እስራኤል እስመ ለሊሁ የአምረኒ"

ትርጉም፦
"ዳግመኛም የያዕቆብን ወገን አንድ ለማድረግ፤ እስራኤልን ለማዳን አገልጋይ እሆነው ዘንድ በማሕጸን የፈጠረኝ እግዚአብሔር እርሱ ይወደኛልና"

"ዘፈጠረኒ" ማለት "የፈጠረኝ" ማለት ነው። ኢየሱስ ማርያም ማህፀን ውስጥ የተፈጠረ ከሆነ በምን ተፈጠረ? ሁሉን ነገር በቃል የተፈጠረ ነው። ኢየሱስም ኹን በሚል ቃል ማህጸን ውስጥ የተፈጠረ ነው።
የክርስትና ውስብስብ ትምህርት ተመልሰው ይህ ድንግል ማርያም ማህፀን ውስጥ የተፈጠረው ስጋ አምላክ ነው፤ ይመለካል ይሉናል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 78፥31
ቄርሎስም አለ፦
“ወዓዲ ንቤ እስመ ሥጋሁ ለእግዚእነ ክርስቶስ አምላክ ውእቱ”

ትርጉም፦
"ዳግመኛ የጌታችን የክርስቶስ ስጋ አምላክ እንደሆነ እንናገራለን”

አንድ ኑባሬ ከተፈጠረ አምላክ አይሆንም። ምክንያቱም አምላክ ከጊዜ በኃላ አይሰራምና፦
ኢሳይያስ 43፥10 ከእኔ በፊት *አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይሆንም*።

አምላክ ካልሠሰራ በማህጸን የተሠራው ኢየሱስ ፍጡር ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፈጣሪ ፍጡር አይደለም!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

13፥16 *አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው*፤ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው፤ በል፡፡ قُلِ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ

አምላካችን አላህ የሁሉን ነገር ፈጣሪ ነው፥ አላህ በፈጣሪነቱ ላይ ፍጡርነት የሚባል የነውር እና የጎደሎ ባሕርይ የለውም። አላህ ሁለመናው ፈጣሪ ነው፥ ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው» ወዲያውም ይኾናል፦
13፥16 *አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው፥ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው"* በል፡፡ قُلِ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ
2፥117 ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ *ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው» ወዲያውም ይኾናል*፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ፈጣሪ እና ፍጡር ሁለት ተቃራኒ ባሕርይ ናቸው፥ "ኢየሱስ ማህጸን ውስጥ የተፈጠረ ፍጡር ነው" ስንላቸው፥ እነርሱም ቅብል አርገው፦ "አዎ! ኢየሱስ ፍጡርም ፈጣሪም ነው" ይሉናል፦
ሃይማኖተ-አበው ስምዓት 124:19
ቄርሎስም አለ፦
“ለሊሁ ፍጡር ወለሊሁ ፈጣሪ”

ትርጉም፦
“እርሱ ፍጡር ነው እርሱ ፈጣሪ ነው”

ይህንን ስብጥር እሳቤ አዕምሮአችሁ ይቀበለዋልን? "እርሱ ፍጡር ነው እርሱ ፈጣሪ ነው" ምን ማለት ነው? ሁሉን ቻይ እና ሁሉን የማይችል፥ ሁሉን ዐዋቂ እና ሁሉን የማያውቅ" ሁለት ባሕርይ እንዴት አንድ ላይ ይዋሕዳል? "አይ ፈጣሪ ፍጡር ሆነ" ብለውን አረፉት፦
ሃይማኖተ-አበው ዘአክርስቶዶሎስ 112:31
አክርስቶዶሎስም አለ፦
“ወፈጣሪ ኮነ ፍጡረ እንተ ይእቲ እምህላዌነ ድንግል ዘበአማን ማርያም”

ትርጉም፦
“ፈጣሪ ከእኛ ባሕረይ ከተገኘች በእውነት ድንግል ከምትሆን ከማርያም ፍጡር ሆነ”

እሰይ! ይቀጥሉና፦ "ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር አብን መስሎና አህሎ ከአብ ማንነትና ምንነት የተገኘ ነው" ይሉናል። አብ ማለት “አስገኚ” ሲሆን ወልድ ደግሞ “ግኝት” ነው። በ 325 ድኅረ-ልደት"AD" የተሰበሰበው የኒቅያ ጉባኤም፦
ግሪኩ፦ Φῶς ἐκ Φωτός, Θεὸν ἀληθινὸν ἐκ Θεοῦ ἀληθινοῦ,

ግዕዙ “ብርሃን ዘምብርሃን፤ አምላክ ዘምአምላክ”

ትርጉም፦
“ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፤ ከአምላክ የተገኘ አምላክ” ብሎታል።

አምላክ አምላክን ካስገኘ ሁለት አምላክ አይሆንም ወይ? አምላክ ተገኘ የሚለው ሲያስገርም አምላክ ተፈጠረ ደግሞ ያስደምማል፦
አማርኛ፦
ምሳሌ 8፥22 *እግዚአብሔር ከሁሉ በፊት ፈጠረኝ*፥ (1980 አዲስ ትርጉም)

ግዕዝ፦
ምሳሌ 8፥22 “ፈጠረኒ እግዚእ መቅድመ ተግባሩ”

ኢንግሊሽ፦
Proverbs 8፥22 “The LORD made me as he began his planning, (International Standard Version)

ዕብራይስጥ፦
ምሳሌ 8፥22 יְהוָה–קָנָנִי, רֵאשִׁית דַּרְכּוֹ: קֶדֶם מִפְעָלָיו מֵאָז.

ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
Proverbs 8፥22 κύριος ἔκτισέν με ἀρχὴν ὁδῶν αὐτοῦ εἰς ἔργα αὐτοῦ

በተለይ በግሪኩ ሰፕቱአጀንት”LXX” ላይ “ኪትዞ” ἔκτισέν ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ነው፤ በተመሳሳይ ዕብራይስጡ “ቃናኒ” קָ֭נָנִי ማለት “አስገኘኝ” ማለት ነው፤ ይህ ቃል ሔዋን “አገኘሁ” ብላ ለተጠቀመችበት የዋለው ቃል “ቃኒቲ” קָנִ֥יתִי ሲሆን ዳዊት ደግሞ ኲላሊቴን “ፈጥረሃል” ለሚለው የተጠቀመው “ቃኒታ” קָנִ֣יתָ ብሎ ነው፦
ዘፍጥረት 4፥1 ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር *አገኘሁ* קָנִ֥יתִי አለች።
መዝሙር 139፥13 አቤቱ፥ አንተ ኵላሊቴን *ፈጥረሃልና* קָנִ֣יתָ ፥
ዘዳግም 32፥6፤ ለእግዚአብሔር ይህንን ትመልሳለህ? የገዛህ አባትህ አይደለምን? *የፈጠረህ* קָּנֶ֔ךָ እና ያጸናህ እርሱ ነው።

የመጨረሻው ጥቅስ ላይ “የፈጠረክ” ለሚለው የገባው “ቃነካ” קָּנֶ֔ךָ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። እግዚአብሔር “የገዛህ አባትህ” መባሉ “አባት” ማለት ለእግዚአብሔር ፈጣሪ ማለት እንደሆነ ይህ ጥቅስ ያስረዳል።
እንግዲህ “መገኘት” እና “መፈጠር” ተለዋዋጭ ቃል ከሆነ ኢየሱስ ፍጡር እና ግኝት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል። ይህንን ጥቅስ ተሃድሶና እና ፕሮቴስታት ስለ ኢየሱስ አይደለም ብለው ሽምጥጥ አርገው ቢክዱም፤ ቀደምት ኦርቶዶክስ፣ካቶሊክ፣ አንግሊካን እና የኒቂያ ጉባኤ ስለ ኢየሱስ ፍጥረት ሳይፈጠር መወለዱን ያሳያል ይላሉ፤ በ 325 AD በኒቂያ ጉባኤ አርዮስንና አትናቲዎስ ኢየሱስ ፍጡር ነው ወይስ አይደለም ለሚለው ክርክራቸው ይህ ጥቅስ ነበር፤ አንዳንድ ኦርቶዶክሳውያንም ይህ ስለ ኢየሱስ አይደለም ብለው ሊያቅማሙ ሲሞክሩ አንድምታው ሆነ ሃይማኖተ-አበው አጋልጧቸዋል፤ ቄርሎስ በሃይማኖተ-አበው ላይ ለኢየሱስ ነው ይለናል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 76:12
ቄርሎስም አለ፦
“ተፈጥረ ጥበብ ዘውእቱ ቃል”

ትርጉም፦
*“ጥበብ ተፈጠረ ይኸውም ቃል ነው”*

ቄርሎስም አለ፦
“ወይእዜኒ ጥበብ ትቤ ፈጠረኒ እግዚእ መቅድመ ተግባሩ”

ትርጉም፦
*“ከፍጥረት አስቀድሞ የነበርኩኝ በቀድሞ ተግባሩ ጌታ ፈጠረኝ አለች”*

የመቃብያን ጸሐፊም ሰሎሞን በምሳሌ መጽሐፍ ላይ ስለ ኢየሱስ፦ “ዛሬም የሚታየው ሁሉ ሳይታይ ዛሬም የሚጠራው ስም ሁሉ ሳይጠራ ፈጠረኝ” ማለቱን ተናግሯል፦
3ኛ መቃብያን 4፥18 ሰሎሞን ፦ *“ዛሬም የሚታየው ሁሉ ሳይታይ ዛሬም የሚጠራው ስም ሁሉ ሳይጠራ ፈጠረኝ”* ብሎ ተናገረ፤

እንግዲህ አባት ማለት “አስገኚ” ወይም “ፈጣሪ” መሆኑን እንዲሁ ልጅ ማለት “ተገኚ” ወይም “ፍጡር” መሆኑን ካየን ዘንዳ ኢየሱስ በየትኛው መልኩ ፍጡር ነው።
የዓለማቱ ጌታ አላህ ጌታችሁ ነው፥ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው፤ እርሱን በብቸኝነት አምልኩት፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነውና፦
6፥102 ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ *ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ ۖ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ فَاعْبُدُوهُ ۚ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኢትዮጵያ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

9፥119 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ *ከእውነተኞቹም ጋር ኹኑ*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَكُونُوا۟ مَعَ ٱلصَّٰدِقِينَ

እውነተኛ ሰው በማስረጃ እና በዕውቀት ይናገራል፥ ከእውነተኞችም ጎን ይቆማል፦
2፥111 *እውነተኞች እንደኾናችሁ ማስረጃችሁን አምጡ* በላቸው፡፡ قُلْ هَاتُوا۟ بُرْهَٰنَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
6፥143 *እውነተኞች እንደሆናችሁ በዕውቀት ንገሩኝ* በላቸው፡፡ نَبِّـُٔونِى بِعِلْمٍ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
9፥119 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ *ከእውነተኞቹም ጋር ኹኑ*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَكُونُوا۟ مَعَ ٱلصَّٰدِقِينَ

ይህንን ከተረዳን ዘንዳ "ኢትዮጵያ" የሚለው ቃል "አይቲዮፒያ" Αιθιοπία ከሚል ሁለት የግሪክ ቃል የተዋቀረ ሲሆን "የተቃጠለ ፊት" ማለት ነው፥ "አይቶ" αιθω ማለት "አቃጠለ" ማለት ሲሆን "ኦፕስ" ωψ ደግሞ "ፊት" ማለት ነው። ይህ ቃል ከሳህራ በረሃ በስተደቡብ ላለው ማለትም ከግብጽ ወደ ደቡብ ለተገኘው የአፍሪካ ክፍል ሁሉ ቃሉ አገልግሎት ላይ ይውል ነበር። በዋናኝነት በሱዳን የነበረው የአይቲዮፒያ ሥርወ-መንግሥት ስያሜ ነው።
ብሉይ ኪዳን ላይ የነበሩት ነቢያት የዕብራይስጥ እና የዐረማይክ ተናጋሪዎች ነበሩ። በእነዚህ ቋንቋ አንድም ቀን "ኢትዮጵያ" የሚለው ቃል ተጠቅመው አያውቁም። ለምሳሌ መዝሙረኛው፦ "ኩሽ እጆችዋን ወደ አምላክ ትዘረጋለች" ይላል፦
መዝሙር 68፥31 መኳንንት ከግብፅ ይመጣሉ፤ *"ኩሽ" እጆችዋን ወደ አምላክ ትዘረጋለች"*።
יֶאֱתָיוּ חַשְׁמַנִּים, מִנִּי מִצְרָיִם; כּוּשׁ תָּרִיץ יָדָיו, לֵאלֹהִים.

ዕብራይስጡን ተመልከት "ኩሽ" כּ֥וּשׁ ነው የሚለው። "ኢትዮጵያ" ብለው በዐማርኛ የተረጎሙት በዕብራይስጡ "ኩሽ" כּ֥וּשׁ መሆኑን አስምርበት። የኩሽ መንግሥት ኑቢያ ውስጥ የነበረ ሲሆን ደቡብ ምስራቅ አፍሪካን እና ሳባ፥ ኤውላጥ፥ ሰብታ፥ ራዕማ፥ ሰበቃታ ናቸው። በአገራችን ሦስት የቋንቋ እና የዘውግ ቤተሰብ አሉ፥ እነርሱም ኩሸቲክ፣ ሴሜቲክ እና ኦሞቲክ ናቸው። ኩሸቲክ የሚባሉት ኦሮሞ፣ ሱማሌ፣ አፋር ወዘተ ናቸው። ሴሜቲክ የሚባሉት አማራ፣ ትግሬ፣ ጉራጌ ወዘተ ናቸው። ኦሞቲክ የሚባሉት ዳውሮ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ ወዘተ ናቸው።
ስለዚህ ባይብሉ ኩሽ ሲል ሴሜቲክን እና ኦሞቲክን ሳይሆን ከአገራችን ኩሸቲክን ከአገራችን ውጪ ሱዳንን፣ ኬንያን፣ ሳባ፥ ኤውላጥ፥ ሰብታ፥ ራዕማ፥ ሰበቃታ ናቸው።

በተለይ፦ "ኢትዮጵያ የቃል ኪዳን አገር ናት፥ ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት" ለምትሉ እርማችሁ አውጥታችሁ እውነቱን ቢመራችሁም ዋጡት። "ኢትዮጵያ የቃል ኪዳን አገር ናት" የሚል ባይብል ላይ አይደለም ፍንጭ ሽታውን አታገኙትም። "ኢትዮጵያ" የሚለው ቃል በነቢያቱ ዕብራይስጥ ላይ የለም። ቢኖር እንኳን ከሳህራ በረሃ በስተደቡብ ላለው ማለትም ከግብጽ ወደ ደቡብ ለተገኘው የአፍሪካ ክፍል ሁሉ እንጂ የአገራችንን ሴሜቲክ የሚባሉት አማራ፣ ትግሬ፣ ጉራጌ ወዘተ ወይም ኦሞቲክ የሚባሉትን ዳውሮ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ ወዘተ አያመለክትም።
ይሁን እንጂ "ኢትዮጵያ" የሚለው ቃል በኃላ ላይ ለአገራችን በሙሉ መጠሪያ ስም ሆኖ ማገልገል ጀምሯል። ያ ማለት ነቢያት ኩሽ ያሉት የእኛን አገር ነው ማለት አይደለም። አገሬን እወዳለው፥ አገር መውደድ እና መዋሸት ሁለት ለየቅ የሆኑ ተቃራኒ ነገሮች ናቸው። ከሥነ-ምግባር እሴት አንዱ ትክክለኛ ንግግር መናገር ነው፥ አንድ አማኝ ትክክለኛውንም ንግግር መናገር እና የሐሰትንም ቃል መራቅ አለበት፦
33:70 እላንተ ያመናችሁ ሆይ አላህን ፍሩ፤ *ትክክለኛውንም ንግግር” ተናገሩ*። يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَقُولُوا۟ قَوْلًۭا سَدِيدًۭا
22፥30 ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ፡፡ *ሐሰትንም ቃል ራቁ*፡፡ فَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلرِّجْسَ مِنَ ٱلْأَوْثَٰنِ وَٱجْتَنِبُوا۟ قَوْلَ ٱلزُّورِ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የዒሣ አፈጣጠር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥59 *”አላህ ዘንድ የዒሣ ምሳሌ እንደ ኣደም ብጤ ነው፡፡ ከዐፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለእርሱ «ኹን» አለው፤ ኾነም”*፡፡ إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ ٱللَّهِ كَمَثَلِ ءَادَمَ ۖ خَلَقَهُۥ مِن تُرَابٍۢ ثُمَّ قَالَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

ሰው የተፈጠረው ከምድር ነው። “ምድር” የሚለው ቃል ተክቶ የመጣ “ሃ” ْهَا ማለትም “እርሷ” የሚል ተውላጠ-ስም አለ፥ “ሃ” በሚለው ቃል ላይ “ሚን” مِنْ ማለትም “ከ” የሚል መስተዋድድ መነሻ ቅጥያ ሆኖ መጥቷል፦
20፥55 *ከእርሷ ከምድር ፈጠርናችሁ*፡፡ በእርሷም ውስጥ እንመልሳችኋለን፡፡ ከእርሷም በሌላ ጊዜ እናወጣችኋለን፡፡ مِنْهَا خَلَقْنَاكُمْ وَفِيهَا نُعِيدُكُمْ وَمِنْهَا نُخْرِجُكُمْ تَارَةً أُخْرَىٰ

ይህ የሚያሳየው ሰው የተፈጠረው ከምድር ነው፤ ምድር ለአካል መሰራት ግኡዝ ንጥረ-ነገር ነው። አላህ ምድርን ወደ እራሱ በማስጠጋት እልቅና ክብር ለመስጠት “አርዲ” أَرْضِي ማለትም “ምድሬ” በማለት በአገናዛቢ ተውላጠ-ስም ይናገራል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! *ምድሬ* በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ እኔንም ብቻ አምልኩኝ፡፡* يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّ وَاسِعَةٌ فَإِيَّايَ فَاعْبُدُونِ

ይህንን ከምድር የተፈጠረውን ሰው አላህ ሩሕ በመንፋት ሕያው አደረገው። “ሩሕ” رُوح ማለትም “መንፈስ” ማለት ሲሆን አላህ ግኡዛን ነገሮችን ሕያው የሚያደርግበት ንጥረ-ነገር ነው። አላህ ከምድር በተፈጠረው አካል ከመንፈሱ ሲነፋበት ያ ግኡዝ አካል ሕያው ሆነ፦
38፥72 *ፍጥረቱንም ባስተካከልኩ እና ከመንፈሴ በነፋሁበት ጊዜ* ለእርሱ ሰጋጆች ኾናችሁ ውደቁ» አልኩ፡፡ فَإِذَا سَوَّيْتُهُۥ وَنَفَخْتُ فِيهِ مِن رُّوحِى فَقَعُوا۟ لَهُۥ سَٰجِدِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ሩሕ” رُوح በሚለው ቃል ላይ “ሚን” مِنْ ማለትም “ከ” የሚል መነሻ ቅጥያ አለ፥ ይህ የሚያሳየው “ሩሕ” አካል ሕያው የሚሆንበት ንጥረ-ነገር መሆኑን ነው። “ከ”ምድር “ከ”መንፈስ የሚለው ቃላት ይሰመርበት። አላህ ምድርን ወደ እራሱ በማስጠጋት እልቅና ክብር ለመስጠት “አርዲ” أَرْضِي ማለትም “ምድሬ” በማለት እንደተናገረ ሁሉ በተመሳሳይም ሩሕን ወደ እራሱ በማስጠጋት እልቅና ክብር ለመስጠት “ሩሒ” رُّوحِى ማለትም “መንፈሴ” በማለት በአገናዛቢ ተውላጠ-ስም” ተናግሯል። ምድርም መንፈስም የሰው ምንነት ነው፥ አላህ ልክ ኣደምን ከዐፈር ሰርቶ ከመንፈሱ አካሉ ላይ ሲነፋበት ሰው እንደሆነ ሁሉ መርየም ውስጥ ያለውን አካል ከመንፈሱ ሲነፋበት ዒሣ ሰው ሆነ፦
21፥91 ያችንም ብልቷን የጠበቀቺውን *”በእርሷም ውስጥ ከመንፈሳችን የነፋንባትን”* እርሷንም ልጅዋንም ለዓለማት ተዓምር ያደረግናትን መርየምን አስታውስ፡፡ وَالَّتِي أَحْصَنَتْ فَرْجَهَا فَنَفَخْنَا فِيهَا مِن رُّوحِنَا وَجَعَلْنَاهَا وَابْنَهَا آيَةً لِّلْعَالَمِينَ

ኣደም እና ዒሣ አፈጣጠራቸው የሚያመሳስላቸው ለዚህ ነው፦
3፥59 *”አላህ ዘንድ የዒሣ ምሳሌ እንደ ኣደም ብጤ ነው፡፡ ከዐፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለ"እርሱ" «ኹን» አለው፤ ኾነም”*፡፡ إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ ٱللَّهِ كَمَثَلِ ءَادَمَ ۖ خَلَقَهُۥ مِن تُرَابٍۢ ثُمَّ قَالَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

“ኸለቀ” خَلَقَ ማለትም “ፈጠረ” በሚለው ግስ መዳረሻ ቅጥያ ላይ “ሁ” هُۥ ማለት “እርሱ” የሚል ተሳቢ ተውላጠ-ስም አለ፥ ይህም የስም ምትክ “ኣደም” ءَادَم የሚለውን የተጻውዖ ስም ተክቶ የመጣ ነው። “ከአፈር” ፈጠረው የሚለው ኣደምን እንጂ በፍጹም ዒሣን አይደለም። ይህንን ለመረዳት አንድ የሰዋስው ሙግት እናቅርብ፦
2፥45 *”በመታገስ እና በሶላትም ተረዱ፡፡ እርሷም በፈሪዎች ላይ እንጅ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት፡፡ وَاسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ وَإِنَّهَا لَكَبِيرَةٌ إِلَّا عَلَى الْخَاشِعِينَ

“ሃ” َّهَا ማለትም “እርሷ” የሚለው ተውላጠ-ስም ተክቶ የመጣው ምንን ነው? “መታገስ” የሚለው ቃል ወይስ “ሶላት” የሚለው ቃል? ስልን፤ መልሱ የቅርብ ቃል “ሶላት” ስለሆነ “እርሷ” የሚለው ተክቶ የመጣው “ሶላት” የሚለውን ቃል ነው። በተመሳሳይ የቅርብ ቃል “ኣደም” ስለሆነ “እርሱ” የሚለው ተክቶ የመጣው “ኣደም” የሚለውን ቃል ነው።
ኣደም እና ዒሣ የተመሳሰሉበት ነጥብ የተፈጠሩበት ንጥረ-ነገር ሳይሆን የተፈጠሩበት ሁኔታ ነው። ሁለቱም በታምር ኹን በሚለው ቃል መፈጠራቸው ነው። አላህ ኣደምን ከዐፈር ፈጥሮ ኹን እንዳለው እንደሆነ ሁሉ ዒሣን ከመርየም ኹን በማለት ፈጥሮታል፦
3፥47 *፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ዒሣ የተፈጠረው ኣደም ላመጣው ጦስ ገፈትና አበሳ ለመቅመስ ሳይሆን አራተኛውን የሰውን ፍጥረት ሊያሟላ ነው። አምላካችን አላህ ኣደምን ያለ ወንድና ሴት ፈጥሮ በተቃራኒው እኛ ደግሞ ከወንድና ከሴት ፈጥሮናል፥ ሐዋን ከወንድ ያለ ሴት ፈጥሮ ስለነበር የሐዋ አፈጣጠር ተቃራኒ ከሴት ያለ ወንድ ዒሣን በመፍጠር ፍጥረቱ ተሟልቷል። ለምን እኛን ልክ እንደ ኣደም ያለ ወንድና ሴት ከዐፈር አልፈጠረንም? መልሱ፦ "የአላህ ምርጫ ነው" ከሆነ እንግዲያውስ የሐዋም ሆነ የዒሣ አፈጣጠር የአላህ ምርጫ ነው፥ ለፍጡራን ግን በዚህ መልኩ ልፈጠር የማለት ምርጫ የላቸውም፦
28፥68 *ጌታህም የሚሻውን ይፈጥራል፤ ይመርጣልም፡፡ ለእነርሱ ለፍጡራን ምርጫ የላቸውም*፡፡ وَرَبُّكَ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ وَيَخْتَارُ ۗ مَا كَانَ لَهُمُ الْخِيَرَة

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሐያእ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

68፥5 *”አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ”*፡፡ وَإِنَّكَ لَعَلَىٰ خُلُقٍ عَظِيمٍ

“ሐያእ” حَيَاء ማለት “ጨዋነት” “እፍረት” “ዓይነ-አፋርነት” ማለት ነው፤ ሐያእ የኢማን አንዱ ቅርንጫፍ ነው፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 59
አቢ ሁራይራ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ኢማን ከሰባ በላይ ቅርንጫፎች አሉት፤ ሐያእ የኢማን ቅርንጫፍ ነው”*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الإِيمَانُ بِضْعٌ وَسَبْعُونَ شُعْبَةً وَالْحَيَاءُ شُعْبَةٌ مِنَ الإِيمَانِ ‏

ተወዳጁ ነቢያችን”ﷺ” ዓይነ-አፋ ነበሩ፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 6, ሐዲስ 20
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ *”የአንሷር ሴት ለነብዩ”ﷺ” “ከሐይድ መጨረስ በኃላ እንዴት ነው የምንተጣጠበው? ብላ ጠየቀች፤ እርሳቸውም፦ “ሽቶዋማ ቁራጭ ጨርቅ ከመስክ ጋር ውሰጂና ሦስት ጊዜ ሃፍረተ-ስጋን መታጠብ ነው” አሏት። ከዚያም ነቢዩ”ﷺ” አፍረው ፊታቸውን መለሱ፤ ስለዚህ እኔ ወደ እኔ አመጣኃትና ነብዩ”ﷺ” ምን እንዳሉ አስረዳኃት”*። عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّ امْرَأَةً، مِنَ الأَنْصَارِ قَالَتْ لِلنَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم كَيْفَ أَغْتَسِلُ مِنَ الْمَحِيضِ قَالَ ‏”‏ خُذِي فِرْصَةً مُمَسَّكَةً، فَتَوَضَّئِي ثَلاَثًا ‏”‌‏.‏ ثُمَّ إِنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم اسْتَحْيَا فَأَعْرَضَ بِوَجْهِهِ أَوْ قَالَ ‏”‏ تَوَضَّئِي بِهَا ‏”‏ فَأَخَذْتُهَا فَجَذَبْتُهَا فَأَخْبَرْتُهَا بِمَا يُرِيدُ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم‏.‏

ነቢያችን”ﷺ” ይህ ታላቅ ሥነ-ምግባር ሐያእ ያላቸው ነቢይ እና በሐያአቸውም ተከታዮቻቸው መልካም መከተል አላቸው፦
68፥5 *”አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ”*፡፡ وَإِنَّكَ لَعَلَىٰ خُلُقٍ عَظِيمٍ
33፥21 ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ *በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አላችሁ*፡፡ لَّقَدْ كَانَ لَكُمْ فِي رَسُولِ اللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِّمَن كَانَ يَرْجُو اللَّهَ وَالْيَوْمَ الْآخِرَ وَذَكَرَ اللَّهَ كَثِيرًا

”ጠባይ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ኹሉቅ” خُلُق ሲሆን “አኽላቅ” أخلاق ማለት ደግሞ ሥነ-ምግባር”ethics” ማለት ነው፥ ነቢያችን"ﷺ" የተላኩት ይህንን መልካም ሥነ-ምግባር ሊያሟሉ ነው፦
አል-አደቡል ሙፍረድ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 273
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“እኔ የተላኩትን መልካም ሥነ-ምግባርን ላሟላ ነው”*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ‏:‏ إِنَّمَا بُعِثْتُ لِأُتَمِّمَ صَالِحَ الأَخْلاق

"ተዝኪያህ" تَزكِية የሚለው ቃል “ዘካ” زَكَىٰ ማለትም “ጠራ” ከሚል የግስ መደብ የመጣ ሲሆን “መጥራራት” ማለት ነው፦
2፥151 በውስጣችሁ ከእናንተው የኾነን *በእናንተ ላይ አንቀጾቻችንን የሚያነብላችሁ እና "የሚያጠራችሁ"፣ መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራችሁ፣ ታውቁት ያልነበራችሁትንም ነገር የሚያሳውቃችሁ የኾነን መልክተኛ እንደላክን ጸጋን ሞላንላችሁ*፡፡ كَمَا أَرْسَلْنَا فِيكُمْ رَسُولًا مِّنكُمْ يَتْلُو عَلَيْكُمْ آيَاتِنَا وَيُزَكِّيكُمْ وَيُعَلِّمُكُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُعَلِّمُكُم مَّا لَمْ تَكُونُوا تَعْلَمُونَ

"የሚያጠራችሁ" ለሚለው ቃል የገባው "ዩዘኪይኩም" يُزَكِّيكُمْ መሆኑ ይህንን ታሳቢና ዋቢ ያረገ ነው። ተዝኪያህ ሦስት ደረጃዎች አሉት፥ እነርሱም፦
1ኛ. "ተዕሊም" تَعْلِيم‎ ማለትም "ትምህርት"
2ኛ. "ተርቢያህ" تربية ማለትም "እድገት"
3ኛ. "ተዕዲል" تَعْدِيل‎ ማለትም "ግብረገብ" ነው።
ነቢያችን"ﷺ" በሥነ-ምግባር እና በግብረገብ ሊያጠሩን የተላኩ ነቢይ ናቸው። የሥነ-ምግባር እና የግረገብ አስኳሉ ሐያእ ነው፥ ሐያእ ከኢማን ነው፥ ኢማን ደግሞ ወደ ጀነት ይመራል። ጸያፍ ነገር ከብልግና ነው፥ ብልግና ወደ እሳት ይመራል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 27, ሐዲስ 115
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ሐያእ ከኢማን ነው፥ ኢማን ደግሞ ወደ ጀነት ይመራል። ጸያፍ ነገር ከብልግና ነው፥ ብልግና ወደ እሳት ይመራል"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ الْحَيَاءُ مِنَ الإِيمَانِ وَالإِيمَانُ فِي الْجَنَّةِ وَالْبَذَاءُ مِنَ الْجَفَاءِ وَالْجَفَاءُ فِي النَّارِ ‏

አምላካችን አላህ ከእሳት ይጠብቀን፥ ጀነትን ይወፍቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አምልኮ ለማርያም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥116 አላህም፡- «የመርየም ልጅ ዒሣ ሆይ! አንተ ለሰዎቹ፡- *እኔን እና እናቴን ከአላህ ሌላ አምላኮች አድርጋችሁ ያዙ ብለሃልን?*» በሚለው ጊዜ አስታውስ ፡፡ وَإِذْ قَالَ اللَّهُ يَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ أَأَنتَ قُلْتَ لِلنَّاسِ اتَّخِذُونِي وَأُمِّيَ إِلَـٰهَيْنِ مِن دُونِ اللَّهِ

ዐበይት ክርስትና ማለት ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ እና አንግሊካን ኢየሱስን እና እናቱን ከአላህ ሌላ አምላክ አድርገው ይዘዋል። ቅድሚያ “አምላክ አድርጎ መያዝ” ምን ማለት ነው? አንድ ሰው አንድ ነገር አምላክ አርጎ ያዘ ማለት ለአምላክ የሚሰጠውን የአምልኮ ክፍል ለሌላ ማንነት ሆነ ምንነት መስጠትን ያመለክታል። ለምሳሌ አንድ ሰው ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ ያዘ ማለት ፍላጎቱን አምላኬ ብሎ ጠራ ማለት ሳይሆን ለአምላክ የሚሰጠውን የአምልኮ ክፍል ለፍላጎቱ ቅድሚያ ሰጠ ማለት ነው፦
25፥43 *ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን?* አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትሆናለህን? أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا

ሰዎች ከአላህ ሌላ አምላክ አድርገው የያዙት ዒሳን እና እናቱን ብቻ ሳይሆን የእርሱ ባሮች የሆኑትንም ጭምር ነው፦
18፥102 እነዚያ የካዱት *ባሮቼን ከእኔ ሌላ አማልክት አድርገው መያዛቸውን* የማያስቆጣኝ አድርገው አሰቡን? እኛ ገሀነምን ለከሓዲዎች መስተንግዶ አዘጋጅተናል። أَفَحَسِبَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ أَن يَتَّخِذُوا۟ عِبَادِى مِن دُونِىٓ أَوْلِيَآءَ ۚ إِنَّآ أَعْتَدْنَا جَهَنَّمَ لِلْكَٰفِرِينَ نُزُلًۭا

ይህንን ከተረዳን “ኢላሀይኒ” إِلَٰهَيْنِ ለኢሣ እና ለመርየም በሙተና የገባ ነው፥ በሙፍረድ ሲሆን ደግሞ “ኢላህ” إِلَٰه ማለትም “የሚመለክ” ማለት ነው። አምላካችን አላህም እያወቀ የትንሳኤ ቀን ዒሣን፦ "እኔን እና እናቴን ከአላህ ሌላ አምላኮች አድርጋችሁ ያዙ ብለሃልን" ብሎ ይጠይቀዋል፦
5፥116 አላህም፡- «የመርየም ልጅ ዒሣ ሆይ! አንተ ለሰዎቹ፡- *እኔን እና እናቴን ከአላህ ሌላ አምላኮች አድርጋችሁ ያዙ ብለሃልን?*» በሚለው ጊዜ አስታውስ ፡፡ وَإِذْ قَالَ اللَّهُ يَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ أَأَنتَ قُلْتَ لِلنَّاسِ اتَّخِذُونِي وَأُمِّيَ إِلَـٰهَيْنِ مِن دُونِ اللَّهِ

“አምልኮ” የሚለው ቃል “መለከ” ማለትም “ገዛ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ለምንነት መገዛት” ማለት ነው። ከሣቴ ብርሃን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት (2005) ገጽ 708)

አምልኮ በውስጡ ልመና፣ ስግደት፣ ስለት መሳል እጣን ማጨስ መስዋዕት ማቅረብ ይይዛል። “አምላክ” የሚለውም ቃል “መለከ” ከሚል ስርወ ቃል መምጣቱ አንባቢ ልብ ይለዋል። ሰውን በአካል ማየት፣ መስማት፣ መናገር እስከቻለ ድረስ ማነጋገሩ ተፈጥሯዊ ነው። ነገር ግን ሰው የሚያይበት አይን፣ የሚሰማበት ጆሮ፣ የሚናገርበት አፍ፣ የሚያውቅበት አንጎል በሞት ጊዜ ስለሚፈራርሱ አይሰማም፣ አይናገርም፣ አያይም፣ ዐያውቅም።
በክርስትና ማለትም ካቶሊክ፣ ኦርቶዶክስና አንግሊካል ወደ ማርያም ጥሪ፣ ልመና፣ መተናነስ፣ መጎባደድ ይደረጋል፣ ስለት መሳል፣ እጣን ማጨስ እና መስዋዕት ማቅረብ ይደረጋል። ታዲያ ማርያም በሌለችበት ይህን ማድረግ አምልኮ አይደለምን? አዎ ከተባለ እንግዲያውስ አግባብ አይደለም። አይ ከተባል ለምን ወደ ማርያም ይህ ሁሉ ይደረጋል? ማርያም በምኗ ትሰማለች? በምኗ ታያለች? በምኗ ታውቃለች? ሰውን የምትገናኝበት ህዋሳቷ አፈር ሆኖ የለ እንዴ? በሰው ልብ ያለውን መለኮት ካልሆነች እንዴት ታውቃለች? ከአላህ ሌላ ማንነት ሆነ ምንነት መለማመን፣ መጎባደድ፣ መተናነስ፣ መጥራት ሺርክ ነው። ምክንያቱም ሁሉንም ነገር በጊዜና በቦታ ሳይገደብ ማወቅ፣ ማየት እና መስማት የሚችል አንድ አምላክ አላህ ብቻ ነው፦
46፥5 *እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልስለት ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው*። وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّن يَدْعُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَن لَّا يَسْتَجِيبُ لَهُۥٓ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ وَهُمْ عَن دُعَآئِهِمْ غَٰفِلُونَ

ማርያም በሌለችበት እንዲህ ጸሎት፣ ስግደት እና መገዛት ይቀርብላታል፦
ዚቅ ዘየካቲት ኪዳነ ምህረት ገፅ 144
*“ብቻዋን ታላላቅ ብርሃናትን ለፈጠረች ለመድኃኒት ድንግል ማርያም ኑ እንስገድላት ለእርሷም እንገዛ”*
መጽሐፈ ሰአታት ገፅ 31
፦ *“በብርሃን ጌጥ ያጌጥሽ ወርቅ ዘቦ ግምጃን የተጎናፀፍሽ የዳዊት ልጅ እመቤታችን ተገዛንልሽ ለአንቺ እንገዛለን”*
፦ *“አደፍ ጉድፍ የሌለብሽ ብርሌ ካህናት የሚያሹትሽ የሽቱ ሙዳይ እመቤታችን ሆይ ተገዛንልሽ ለአንቺን ፈፅመን እንገዛለን”*
፦ *“የታተምሽ የውሃ ጉድጓድ የተዘጋሽ የተክል ቦታ የዳዊት ልጅ እመቤታችን ሆይ የነብያት ልጆቻቸው አንች ነሽና ተገዛንልሽ ለአንቺ ፈፅመን እንገዛለን”*
፦ *“በብርና በወርቅ የተሸለምሽ አዲስ የጣሪያ ዋልታ ሚስጥር ማደሪያ የዳዊት ልጅ እመቤታችን ሆይ ተገዛንልሽ ለአንቺ ፈፅመን እንሰግዳለን”*

በካቶሊክ ማርያም፦ “ሰማይ ላይ ኖራ በኃላ ስጋ የለበሰች አርያማዊት ማለትም ሰማያዊት ናት፤ ከዚያም ሞታ ሳትበሰብስ ተነስታ ወደ ሰማይ አርጋለች” ተብሎ ይታመናል፤ በኦርቶዶክስና በአንግሊካንም፦ “ሞታ ሳትበሰብስ ተነስታ ወደ ሰማይ አርጋለች” ተብሎ ይታመናል።
በ 375 AD የተነሱት ኮላደሪያን ክርስቲያኖች ማርያምን በግልጽ፦ “ቴአ” Θεία ማለትም “ሴት አምላክ” ብለው ይጥሩአት ነበር።
በ 431 AD የኤፌሶን ጉባኤ ማርያምን “ቴኦቶኮስ” Θεοτόκος ማለትም “የአምላክ እናት” ብለዋታል።
ካቶሊክ፣ ኦርቶዶስ፣ አንግሊካን ማርያምን በግሪክ “ኪርያ” κυρία ማለትም “ሴት ጌታ” ይሉአታል፣ “ኩርዮስ” κύριος ማለት “ወንድ ጌታ” ማለት ነው። በአገራችን ኦርቶዶክሶች ደግሞ “እግዚኢት” ትባላለች፥ “እግዚኢት” ማለት “ሴት ጌታ” ማለት ሲሆን “እግዚእ” ደግሞ “ወንዱ ጌታ” ማለት ነው፤ ኢየሱስን “እግዚኢነ” ማለትም “ጌታችን” እንደሚሉት ሁሉ ማርያም “እግዚኢትነ” ማለትም “ጌታችን” ይሉአታል። ከዚህ የበለጠ ማርያምን አምላክ አድርጎ መያዝ አለን? ይህ አምልኮ ካልሆነ ምን ይባላል?
ከአስራ አራቱ ቅዳሴ ሁለቱ ቅዳሴ ማለትም ቅዳሴ እግዚእ እና ቅዳሴ ማርያም ለኢየሱስ እና ለማርያም የሚቀርብ ቅዳሴ ነው። በዚህ ቅዳሴ ጊዜ ለኢየሱስ እና ለማርያም የመስዋዕት ቁርባን ይቀርብላቸዋል። ቁርባን የአምልኮ አስኳሉ ነው። ይህ ቁርባን ህብስትና ወይን መባ በማቅረብ፥ በከንፈር በማወደስ፥ ጧፍ በማብራት፥ ዕጣን በማጨስና በሰውነት በመቆም የመባ መስዋዕት፣ የከንፈር መስዋዕት፣ የመብራት መስዋዕት፣ የዕጣን መስዋዕት እና የሰውነት መስዋዕት ነው።

ቅዳሴው ሲጀምር ለኢየሱስ የሚቀርብ መስዋዕት ከሆነ እንዲህ ብሎ ይጀምራል፦
*"አኮቴተ ቁርባን ዘእግዚነ፣ ወአምላክነ፣ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ"*

ትርጉሙ፦ *"የጌታችን፣ የአምላካችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የቁርባን አኮቴት"*

ቅዳሴው ሲጀምር ለማርያም የሚቀርብ መስዋዕት ከሆነ እንዲህ ብሎ ይጀምራል፦
*"አኮቴተ ቁርባን ዘእግዚትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ-አምላክ"*

ትርጉሙ፦ *"የአምላክ እናት የጌታችን የድንግል ማርያም የቁርባን አኮቴት"*

"አኮቴት" የሚለው ቃል "አዕኮተ" ማለትም "አመለከ" "አመሰገነ" "አወደሰ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አምልኮ" "ምስጋና" "ውዳሴ" ማለት ነው። ለምሳሌ "አእኲትዎ ለአምላክ" ማለት "ለአምላክ አምልኮ አቅርቡ" ማለት ነው። ቅዳሴ እግዚእ እና ቅዳሴ ማርያምን ተመልከት።

ለኢየሱስ በወር ውስጥ ሦስት ቀን ማለት በ 6 ኢየሱስ፣ በ 27 መድኃኒያለም፣ በ 28 አማኑኤል፣ በዓለ ወልድ እየተባለ አኮቴተ ቁርባን ይቀርብለታል።
ለማርያም በወር ውስጥ ስድስት ቀን ማለትም በ 1 ልደታ ማርያም፣ በ 3 በአታ ማርያም፣ በ 6 ቁስቋም ማርያም፣ በ 10 ፀደንያ ማርያም፣ በ 16 ኪዳነ-ምህረት ማርያም፣ በ 21 ቅድስት ማርያም እየተባለ አኮቴተ ቁርባን ይቀርብላታል።
ነገር ግን እነዚያ ዱዓ ሲደረግላቸው የነበሩት አካላት ከአምላኪዎች ተቃራኒ በመሆን አምልኮ እንዳልተቀበሉ ይክዳሉ፦
19፥81 *ከአላህም ሌላ አማልክትን* ለእነርሱ መከበሪያ እንዲኾኑዋቸው *ያዙ*። وَٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ ءَالِهَةًۭ لِّيَكُونُوا۟ لَهُمْ عِزًّۭا
19፥82 ይከልከሉ፥ *ማምለካቸውን በእርግጥ ይክዷቸዋል፡፡ በእነሱም ላይ ተቃራኒ ይኾኑባቸዋል*። كَلَّا ۚ سَيَكْفُرُونَ بِعِبَادَتِهِمْ وَيَكُونُونَ عَلَيْهِمْ ضِدًّا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሰባው ሱባዔ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥78 *ከእነሱም እርሱ ከመጽሐፉ ያይደለ ሲኾን ከመጽሐፉ መኾኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙ ክፍሎች አሉ፡፡ እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልኾነ ሲኾን «እርሱ ከአላህ ዘንድ ነውም» ይላሉ፡፡ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑም በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ*፡፡ وَإِنَّ مِنْهُمْ لَفَرِيقًا يَلْوُونَ أَلْسِنَتَهُم بِالْكِتَابِ لِتَحْسَبُوهُ مِنَ الْكِتَابِ وَمَا هُوَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَقُولُونَ هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَمَا هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَيَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

ነቢዩ ዳንኤል የኢየሩሳሌም መፍረስ የሚፈጸምበትን ሰባውን ዓመት፥ ያህዌህ በቃሉ ለነቢዩ ለኤርምያስ የተናገረውን የዓመቱን ቍጥር በመጽሐፍ አስተዋለ፦
ዳንኤል 9፥2 እኔ ዳንኤል *የኢየሩሳሌም መፍረስ የሚፈጸምበትን ሰባውን ዓመት፥ እግዚአብሔር በቃሉ ለነቢዩ ለኤርምያስ የተናገረውን የዓመቱን ቍጥር በመጽሐፍ አስተዋልሁ*።

የባቢሎን ምርኮ 70 ዓመት የሚጀምረው በ 605 ቅድመ-ልደት"BC" የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ዮአኪንንን እና የከበረውንም የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ከእርሱ ጋር ባስወሰደ ጊዜ ነው፦
2 ዜና 36፥9-10 *"ዮአኪንም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የአሥራ ስምንት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወርና አሥር ቀን ነገሠ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ። ዓመቱ ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡከደነፆር ልኮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፥ የከበረውንም የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ከእርሱ ጋር አስወሰደ፤ ወንድሙንም ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ"*።

ከዚህ ከ 605 ጀምረን 70 ዓመት ስንቆጥር 535 ቅድመ-ልደት"BC" ይሆናል፥ ከዚያ በኃላ ነቢዩ ዳንኤል የዓመቱን ቍጥር በመጽሐፍ አስተዋለ። በዚህ ጊዜ ገብርኤል ለዳንኤል፦ "በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል" አለው፦
ዳንኤል 9፥24 ዓመፃን ይጨርስ፥ ኃጢአትንም ይፈጽም፥ በደልንም ያስተሰርይ፥ የዘላለምን ጽድቅ ያገባ፥ ራእይንና ትንቢትን ያትም፥ ቅዱሰ ቅዱሳኑንም ይቀባ ዘንድ *"በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል"*።

"ሱባዔ" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "ሻቡኢም" שָׁבֻעִ֨ים ሲሆን "ሳምንታት" ማለት ነው፥ "ሻቡአ" שְׁבוּעַ ማለት "ሳምንት" ወይም "ሰባት" ማለት ነው። "ሰባ ሱባዔ" ማለት "ሰባ ሳምንት" ማለት ነው፥ አንድ ሳምንት ሰባት ቀናት ናቸው። ስለዚህ 70×7= 490 ይሆናል። ይህ ሰባ ሱባዔ በዳንኤል ሕዝብ እና በቅድስት ከተማ ላይ የተቆጠረ ስሌት ነው። ይህ ሰባ ሱባዔ ለሦስት ይከፈላል፥ እነርሱም 7 ሱባዔ፣ 62 ሱባዔ እና 1 ሱባዔ ይሆናል። ይህ 7+62+1=70 ሱባዔ ይሆናል። እነዚህን ነጥብ በነጥብ እስቲ እንመልከት፦
ነጥብ አንድ
"ሰባት ሱባዔ"
ስለ ኢየሩሳሌምን መጠገን እና መሥራት ቃሉ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔ ይሆናል፦
ዳንኤል 9፥25 ስለዚህ እወቅ አስተውልም፤ *"ኢየሩሳሌምን ስለ መጠገን እና ስለ መሥራት ቃሉ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔ ይሆናል"*። ከዚያም በስድሳ ሁለት ሱባዔ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ጎዳና እና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።
וְתֵדַע וְתַשְׂכֵּל מִן-מֹצָא דָבָר, לְהָשִׁיב וְלִבְנוֹת יְרוּשָׁלִַם עַד-מָשִׁיחַ נָגִיד--שָׁבֻעִים, שִׁבְעָה; וְשָׁבֻעִים שִׁשִּׁים וּשְׁנַיִם, תָּשׁוּב וְנִבְנְתָה רְחוֹב וְחָרוּץ, וּבְצוֹק, הָעִתִּים.
English Standard Version
Know therefore and understand that from the going out of the word to restore and build Jerusalem to the coming of an anointed one, a prince, there shall be seven weeks. Then for sixty-two weeks it shall be built again with squares and moat, but in a troubled time.

የዕብራይስጡን ያመጣሁት ምክንያት 7 እና 62 ቁልጭ አርጎ ስለሚለይ ነው። "ሌ" לְ ማለት "ስለ" ማለት ነው፥ ስለ ኢየሩሳሌምን መጠገን እና መሥራት ቃሉ ወጥቷል። "ዳባር" דָבָ֗ר ማለት "ቃል" ማለት ነው። ይህ ቃል የወጣው ከፈጣሪ ሲሆን በነቢዩ ኤርሚያስ በኩል ነው፦
ኤርምያስ 29፥10 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ *"ሰባው ዓመት በባቢሎን በተፈጸመ ጊዜ እጐበኛችኋለሁ፥ ወደዚህም ስፍራ *"እመልሳችሁ"* הָשִׁיב֙ ዘንድ መልካሚቱን "ቃሌን" דְּבָרִ֣י እፈጽምላችኋለሁ።

"ቃሌ" ለሚለው ቃል የገባው "ዳባሪ" דְּבָרִ֣י ሲሆን "የዳባር አገናዛቢ መደብ ነው። "ሀሺብ" הָשִׁיב֙ ማለት "እመልሳለው" ማለት ሲሆን ዳንኤል ላይ "መጠገን" ለሚለው የገባው ቃል "ሀሺብ" הָשִׁיב֙ ነው፥ "ሀሺብ" הָשִׁיב֙ ማለት "ሹብ" שׁוּב "መመለስ" ማለት ነው፦
ኤርሚያስ 29፥14 ከእናንተም ዘንድ እገኛለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ምርኮአችሁንም *"እመልሳለሁ"* וְשַׁבְתִּ֣י ፥ ከአሕዛብም ሁሉ ዘንድ እናንተንም ካሳደድሁበት ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እናንተንም ለምርኮ ወዳፈለስሁበት ስፍራ "እመልሳችኋለሁ" הֲשִׁבֹתִ֣י ።

"እመልሳለሁ" ለሚለው ቃል "ሸብቲ" שַׁבְתִּ֣י የሚለው ቃል መግባቱ አስተውል። "እናንተንም ለምርኮ ወዳፈለስሁበት ስፍራ "እመልሳችኋለሁ" የሚለው ይህንኑ ታሳቢ ያረገ ነው።
ኢየሩሳሌምን "መሥራት" ለሚለው ቃል የገባው "ሊብኖውት" לִבְנ֤וֹת ሲሆን ይህም ቃል በኤርሚያስ በኩል ወጥቷል፦
ኤርምያስ 30፥18 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የያዕቆብን ድንኳን ምርኮ እመልሳለሁ፥ ለማደሪያውም እራራለሁ፤ ከተማይቱም በጉብታዋ ላይ *"ትሠራለች"* נִבְנְתָ֥ה ፥ አዳራሹም እንደ ዱሮው የሰው መኖሪያ ይሆናል።

"ኒብናታህ" נִבְנְתָ֥ה ማለት "ትሠራለች" ማለት ነው። እዚህ ጋር መያዝ ያለብን ነጥብ በነቢዩ ኤርሚያስ ስለ መመለስ እና ስለ መሥራት ቃል ከያህዌህ የመጣበት ጊዜ በ 586 ቅድመ-ልደት"BC" ነው። የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በ 605 ቅድመ-ልደት"BC" ዮአኪንን ማርኮ ከ 8 ዓመት በኃላ ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ የአሻንጉሊት መንግሥት አነገሠ፥ ሴዴቅያስ በነገሠ በ 11 ዓመት ኢየሩሳሌም አፈረሱ፦
2 ነገሥት 25፥2 *ከተማይቱም እስከ ንጉሡ እስከ ሴዴቅያስ እስከ አሥራ አንደኛው ዓመት ድረስ ተከብባ ነበር*።
2 ነገሥት 25፥8 *በባቢሎንም ንጉሥ በናቡከደነፆር በአሥራ ዘጠነኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በሰባተኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ባሪያ የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ*።
2 ነገሥት 25፥10 *ከዘበኞቹም አለቃ ጋር የነበረው የከለዳውያን ሠራዊት ሁሉ የኢየሩሳሌምን ቅጥር ዙሪያዋን አፈረሱ*።

8+11=19 ይሆናል። ከምርኮ መጀመር ከ 605 ላይ19 ዓመት ሲቀነስ 586 ይሆናል፥ 605−19=586 ይሆናል። በዚህ ጊዜ ኢየሩሳሌምን ስለ መጠገን እና ስለ መሥራት ቃሉ ወደ ኤርሚያስ መጣ፦
ኤርምያስ 1፥3 በይሁዳም ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮስያስ ልጅ እስከ ሴዴቅያስ እስከ *"አሥራ አንደኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየሩሳሌም እስከ ተማረከችበት እስከ አምስተኛው ወር ድረስ *"የእግዚአብሔር ቃል መጣ"*።

ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ቃሉ የመጣው ከተማይቱ በፈረሰችበት በ 586 ቅድመ-ልደት"BC" ነው። ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ቃሉ ከመጣበት እስከ አለቃው መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔ ይሆናል፥ ቅድሚያ ለምን 7 ሱባዔ እንደቀደመ እና እንደተቀመጠ የክርስትና ምሁራን አጥጋቢ መልስ የላቸውም። አንድ ሱባዔ 7 ዓመት ከሆነ 7 ሱባዔ 49 ዓመት ይሆናል። 7×7=49 ይሆናል። ከ 586 ቅድመ-ልደት"BC" 49 ዓመት ስንቆጥር 537 ይሆናል፥ 586-49= 537 ይመጣል።
በ 537 ቅድመ-ልደት"BC" እግዚአብሔር በኤርምያስም አፍ የተናገረው የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘንድ እግዚአብሔር የፋርስን ንጉሥ ቂሮስን አስነሣ፦
ዕዝራ 1፥1 *"በኤርምያስም አፍ የተናገረው የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘንድ በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት እግዚአብሔር የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አስነሣ"*።

ይህ የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ ከመወለዱ ከ 200 ዓመት በፊት ያህዌህ የሚቀባው መሢሕ እንደሆነ ተተንብዮለታል፦
ኢሳይያስ 45፥1 *"እግዚአብሔር፦ "ለመሢሑ לִמְשִׁיחוֹ֮ ለቂሮስ እንዲህ ይላል፦ "አሕዛብንም በፊቱ አስገዛ ዘንድ የነገሥታትንም ወገብ እፈታ ዘንድ፥ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹን በፊቱ እከፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያዝሁት"*።
"This is what the LORD says to his anointed, to Cyrus, whose right hand I take hold of to subdue nations before him and to strip kings of their armor, to open doors before him so that gates will not be shut: NIV

"መሺሆው" ִמְשִׁיחוֹ֮ ማለት "የእርሱ መሢሕ" ማለት ነው፥ ይህም የሚያሳየው አለቃው ቂሮስ የያህዌህ መሢሕ መሆኑን ነው። አለቃውም መሢሕም እርሱ ነው።
ነጥብ ሁለት
"ስድሳ ሁለት ሱባዔ"
ዳንኤል 9፥25 *ከዚያም በስድሳ ሁለት ሱባዔ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ጎዳና እና ከቅጥር ጋር ትሠራለች"*። וְשָׁבֻעִים שִׁשִּׁים וּשְׁנַיִם, תָּשׁוּב וְנִבְנְתָה רְחוֹב וְחָרוּץ, וּבְצוֹק, הָעִתִּים.

"ከዚያም" የሚለው ቅድመ ተከተል የጊዜ ሳይሆን የንግግር ቅድመ ተከተል ነው። "የጭንቀ ዘመን" የተባለው ምርኮ የሚጀምርበት ቀን ነው፥ ይህ ቀን የመዓት ቀን የመከራና የጭንቀት ቀን ነው፥ በዚህ የጭንቀት ዘመን ከተማይቱ የሚያስጨንቁአት ሁሉ ተጨንቃ አገኙአት፦
ሶፎንያስ 1፥15 ያ ቀን የመዓት ቀን የመከራና የጭንቀት ቀን፥ የመፍረስና የመጥፋት ቀን፥ የጨለማና የጭጋግ ቀን፥ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን።
ሰቆቃው ኤርምያስ 1፥1 አሌፍ። *"ሕዝብ ሞልቶባት የነበረች ከተማ ብቻዋን እንዴት ተቀመጠች"*!
ሰቆቃው ኤርምያስ 1፥3 ጋሜል። *"ይሁዳ ስለ መጨነቅና ስለ ባርነት ብዛት ተማረከች"*፤ በአሕዛብ መካከል ተቀመጠች ዕረፍትም አላገኘችም፤ *"የሚያስጨንቁአት ሁሉ ተጨንቃ አገኙአት"*።

"ይሁዳ ስለ መጨነቅና ስለ ባርነት ብዛት ተማረከች" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። በ 605 ቅድመ-ልደት"BC" ከተማይቱ ተማረከች፥ የጭንቀቱ ዘመኗ ጀመረ። ከ 605 ጀምረን 62 ሱባዔ ስንቆጥር 171 ቅድመ-ልደት"BC" ይሆናል። ቅድሚያ 62 ሱባዔ 434 ዓመት ነው፥ 62×7=434 ይሆናል።
እንግዲህ ከምርኮ 605 ጀምሮ 434 ዓመት ስንቆጥር 171 ቅድመ-ልደት"BC" ነው። 605-434=171 ይሆናል። በዚህ ጊዜ የተገደለ መሢሕ አለ፦
ዳንኤል 9፥26 *"ከስድሳ ሁለት ጊዜ በኋላ መሢሕ ይገደላል"*፥ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም።

ዳንኤል 9፥26 ላይ "ሰባት" የሚል ቃል የለም። የዕብራይስጡን ማየት ይቻላል። ስድሳ ሁለት ሱባዔ ሲያልቅ የተቀባው ሊቀ-ካህን ሣልሳዊ "አንያስ" ተገሏል፦
ዳንኤል 11፥22 የሚጐርፍም ሠራዊት ከፊቱ ይወሰዳል፥ እርሱ እና *"የቃል ኪዳኑ አለቃ ይሰበራሉ"*።

አንጥያኮስ ኤጴፋኔዎስ በ 171 ቅድመ-ልደት የተቀባው ሊቀ-ካህን ሣልሳዊ "አንያስን" አስገድሎታል። "ማሺአሕ" מָשִׁ֣יחַ ማለት "የተቀባ" ማለት ሲሆን ይህ ቃል 39 ጊዜ ብሉይ ኪዳን ላይ ለተለያየ ካህን፣ ንጉሥ እና ነቢይ አገልግሎት ላይ ውሏል፦
ዘሌዋውያን 4፥3 *የተቀባውም* הַמָּשִׁ֛יחַ ካህን በሕዝቡ ላይ በደል እንዲቈጠርባቸው ኃጢአት ቢሠራ፥ ስለ ሠራው ስለ ኃጢአቱ ነውር የሌለበት ወይፈን ለእግዚአብሔር ለኃጢአት መሥዋዕት ያቀርበዋል።

"ማሺአሕ" מָשִׁ֣יחַ የሚል ቃል በተገኘ ቁጥር ለወደፊት ከዳዊት ቤት ለሚመጣው ንጉሥና ነቢይ ነው ብሎ ማለት ቂልነት ነው። ኢንሻላህ ይቀጥላል......

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሰባው ሱባዔ

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥78 *ከእነሱም እርሱ ከመጽሐፉ ያይደለ ሲኾን ከመጽሐፉ መኾኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙ ክፍሎች አሉ፡፡ እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልኾነ ሲኾን «እርሱ ከአላህ ዘንድ ነውም» ይላሉ፡፡ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑም በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ*፡፡ وَإِنَّ مِنْهُمْ لَفَرِيقًا يَلْوُونَ أَلْسِنَتَهُم بِالْكِتَابِ لِتَحْسَبُوهُ مِنَ الْكِتَابِ وَمَا هُوَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَقُولُونَ هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَمَا هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَيَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

ነጥብ ሦስት
"አንድ ሱባዔ"
ዳንኤል 9፥27 *"እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል"*።

"እርሱም" የሚለው ተውላጠ-ስም "የሚመጣው አለቃ" የሚለውን ተክቶ የመጣ ተውላጠ-ስም ነው፦
ዳንኤል 9፥26 *"የሚመጣውም አለቃ ሕዝብ ከተማይቱን እና መቅደሱን ያጠፋሉ"*።

ይህም አለቃ አንጥያኮስ ኤጴፋኔዎስ ነው፥ አንጥያኮስ ኤጴፋኔዎስ 215 ቅድመ-ልደት ተወልዶ በ 175 ቅድመ-ልደት ንግሥናን ተቆናጠጠ። በመቀጠል በ 171 ቅድመ-ልደት ከብዙ ሄለናውያን አይሁድ ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ማለትም ለሰባት ዓመት አድርጓል፥ በሱባዔውም እኵሌታ ማለትም በሦስት ዓመት ተኩል በ 167 አጋማሽ ላይ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን አስቀርቷል። ይህንን ያስቀረው ለ ሦስት ዓመት ተኩል ነው፦
ዳንኤል 12፥11 *"የዘወትሩም መሥዋዕት ከቀረ ጀምሮ፥ የጥፋትም ርኵሰት ከቆመ ጀምሮ ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ቀን ይሆናል"*።

1290 ቀናትን በዓመት ሲሰላ 3 ዓመት ከ 6 ወር ይሆናል። 1290፥360= 3.59 ይሆናል፥ 1 ዓመት 360 ቀናት ስለምይዝ። ይህም 3.5+3.5= 7 ሱባዔ ይሆናል።
በዳንኤል አውራ ፍየል የተባለው የግሪኩ ንጉሥ በ 336 ቅድመ-ልደት የተነሳው ታላቁ እስክንድር ነው፦
ዳንኤል 8፥8 *አውራውም ፍየል ራሱን እጅግ ታላቅ አደረገ፤ በበረታም ጊዜ ታላቁ ቀንዱ ተሰበረ፥ ወደ አራቱም የሰማይ ነፋሳት የሚመለከቱ አራት ቀንዶች ከበታቹ ወጡ። አውራውም ፍየል ራሱን እጅግ ታላቅ አደረገ፤ በበረታም ጊዜ ታላቁ ቀንዱ ተሰበረ፥ ወደ አራቱም የሰማይ ነፋሳት የሚመለከቱ አራት ቀንዶች ከበታቹ ወጡ*።
ዳንኤል 8፥21 *አውራውም ፍየል የግሪክ ንጉሥ ነው፤ በዓይኖቹም መካከል ያለው ታላቁ ቀንድ መጀመሪያው ንጉሥ ነው። እርሱም በተሰበረ ጊዜ በእርሱ ፋንታ አራቱ እንደ ተነሡ፥ እንዲሁ ከወገኑ አራት መንግሥታት ይነሣሉ፥ ነገር ግን በኃይል አይተካከሉትም*።

ታላቁ ቀንዱ የተባለው የመጀመሪያው ንጉሥ እስክንድር በ 323 ቅድመ-ልደት በሞተ ጊዜ መንግሥቱ በአራት ጀነራሎቹ አራት መንግሥታት ሆነው ተከፋፈሉ፥ እነርሱም በካሳንደስ የሚመራ የግሪክ መንግሥት፣ በሊሲማኩስ የሚመራ የትሬስ መንግሥት፣ በቀዳማዊ ሰሎቂውስ የሚመራ የደማስቆ መንግሥት እና በበጥሊሞስ የሚመራ የግብጽ መንግሥት ናቸው። ከእነዚህ መንግሥታት መካከል በካሳንደስ ከሚመራ ከግሪክ መንግሥት አንድ ታናሽ ቀንድ ወጣ፥ ወደ ደቡብም ወደ ምሥራቅም ወደ መልካሚቱም ምድር እጅግ ከፍ አለ። እስከ ሰማይም ሠራዊት ድረስ ከፍ አለ፤ ከሠራዊትና ከከዋክብትም አያሌዎችን ወደ ምድር ጣለ፥ ረገጣቸውም፦
ዳንኤል 8፥9-10 *ከእነርሱም ከአንደኛው አንድ ታናሽ ቀንድ ወጣ፥ ወደ ደቡብም ወደ ምሥራቅም ወደ መልካሚቱም ምድር እጅግ ከፍ አለ። እስከ ሰማይም ሠራዊት ድረስ ከፍ አለ፤ ከሠራዊትና ከከዋክብትም አያሌዎችን ወደ ምድር ጣለ፥ ረገጣቸውም*።

ይህ ትንሽ ቀን የተባለው አንጥያኮስ ኤጴፋኔዎስ ነው፥ ይህ ንጉሥ ከእርሱም የተነሣ የዘወትሩ መሥዋዕት ተሻረ፥ የመቅደሱም ስፍራ ፈረሰ። ሠራዊቱም ከኃጢአት የተነሣ ከዘወትሩ መሥዋዕት ጋር ተሰጠው፤ እርሱም እውነትን ወደ ምድሩ ጣለ፥ አደረገም ተከናወነም፦
ዳንኤል 8፥11-12 *እስከ ሠራዊትም አለቃ ድረስ ራሱን ታላቅ አደረገ፤ ከእርሱም የተነሣ የዘወትሩ መሥዋዕት ተሻረ፥ የመቅደሱም ስፍራ ፈረሰ። ሠራዊቱም ከኃጢአት የተነሣ ከዘወትሩ መሥዋዕት ጋር ተሰጠው፤ እርሱም እውነትን ወደ ምድሩ ጣለ፥ አደረገም ተከናወነም*።
ዳንኤል 8፥23 *በመንግሥታቸውም መጨረሻ፥ ኃጢአታቸው በተሞላች ጊዜ፥ እንቆቅልሽን የሚያስተውል ፊተ ጨካኝ ንጉሥ ይነሣል። ኃይሉም ይበረታል፥ ነገር ግን በራሱ ኃይል አይደለም፤ በድንቅም ያጠፋል፥ ያደርግማል፥ ይከናወንማል፤ ኃያላንንና የቅዱሳንን ሕዝብ ያጠፋል*።

እንቆቅልሽን የሚያስተውል ፊተ ጨካኝ ንጉሥ አንጥያኮስ ኤጴፋኔዎስ ከ 171 ቅድመ-ልደት ጀምሮ እስከ 164 ቅድመ-ልደት ለ 6 ዓመት ከሦስት ወር ኃያላንንና የቅዱሳንን ሕዝብ አጥፍቷል፥ መቅደሱን አርክሳል፦
ዳንኤል 8፥13-14 ከቅዱሳኑም አንዱ ሲናገር ሰማሁ፤ ለተናገረው ለቅዱሱም ሁለተኛው ቅዱስ፦ *ስለ ዘወትሩ መሥዋዕት፥ መቅደሱና ሠራዊቱም ይረገጡ ዘንድ ስለሚሰጥና ስለሚያጠፋ ኃጢአት የሆነው ራእይ እስከ መቼ ይሆናል? አለው። እርሱም፦ እስከ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ማታና ጥዋት ድረስ ነው፤ ከዚያም በኋላ መቅደሱ ይነጻል፡ አለኝ*።

2300 ቀናት 6 ዓመት ከ 3 ወር ነው፥ 2300÷360=6.3 ይሆናል።
የሚመጣው አለቃ አንጥያኮስ ኤጴፋኔዎስ እና ከእርሱም ጋር ሠራዊቶች መቅደሱንም ግንቡንም አጥፍተዋል(አርክሰዋል)፥ የዘወትሩንም መሥዋዕት አስቀርተዋል፥ የጥፋትንም ርኵሰት አቁመዋል፦
ዳንኤል 11፥31 *ከእርሱም ጋር ሠራዊቶች ይቆማሉ፥ መቅደሱንም ግንቡንም ያረክሳሉ፥ የዘወትሩንም መሥዋዕት ያስቀራሉ፥ የጥፋትንም ርኵሰት ያቆማሉ"*።
ዳንኤል 9፥26 *"የሚመጣውም አለቃ ሕዝብ ከተማይቱን እና መቅደሱን ያጠፋሉ"*።

ይህ እንቆቅልሽን የሚያስተውል ፊተ ጨካኝ ንጉሥ አንጥያኮስ ኤጴፋኔዎስ የጥፋት ርኵሰት በቤተ መቅደሱ ያደረገው ዚየስ ኦሊምፒየስ የተባለውን ጣዖት አስገብተው የአሳማ ስጋ መስዋዕት በመሰዋት ነው። "ማጥፋት" ማለት "ማርከስ" ስለሆነ "የጥፋት ርኵሰት" ተብላል። መቅደሱ እና ሕዝቡ ስለሚያጠፋ ኃጢአት የሆነው ራእይ ለ 2300 ቀናት ወይም ለ ስድስት ዓመት ከ3 ወር ድረስ ነው፤ ከዚያም በኋላ መቅደሱ ይነጻል በተባለው መሠረት ይሁዳ መቃቤስ በሚባል መሪ በሚመራው በመቃብያን ቡድን በ 164 ቅድመ-ልደት ዚየስ ኦሊምፒየስ የተባለውን ጣዖት ከመቅደሱ አስወጥተዋል።
ማጠቃለያ
ከላይ ያለው የጥንቶቹ አይሁዳውያን ሆነ የአሁኖቹ አይሁዳውያን ግንዛቤ ነው። ነገር ግን ክርስቲያኖች በተለይ ፕሮቴስታንት፣ አድቬንቲስ እና የይሆዋ ምስክሮች በተቃራኒው የተረዱበት ነገር ይለያል። "ቃል የሚወጣበት" የሚለውን "አዋጅ"edict" በሚል ነው የተረዱት፥ እንደሚታወቀው ከምርኮ በኃላ አዋጅ በነገሥታት ታውኸዋል። እነርሱም፦
1ኛ. የቂሮስ አዋጅ ዕዝራ 1፥1 በ 539 AD
2ኛ. የዳርዮስ አዋጅ ዕዝራ 6፥12 በ 521 AD
3ኛ. የአርጤክስ አዋጅ ዕዝራ 7፥21 በ 457 AD
4ኛ. የአርጤክስ አዋጅ ነህምያ 2፥8፣18 በ 445 AD

ፕሮቴስታን 62 እና 7 ደምረው 69 ሱባዔን ከአራተኛው አዋጅ ለማስላት ይሞክራሉ። 69×7= 483 ይሆናል። ከአራተኛው አዋጅ ከ 445 ጀምረን 483 ዓመት ስንቆጥር 38 ድኅረ-ልደት ነው፥ 483-445= 38 ይሆናል። በእነርሱ ስሌት ዳንኤል ላይ የተጠቀሱት ሁለቱ መሢሖች ኢየሱስ ነው ይባልና፥ "ከ 62 እና 7 በኃላ መሢሕ ይገደላል" የሚለው ይዘን ከሄድን ከ 38 በኃላ ይገደላል ተብሎ እንደ እነርሱ እምነት ኢየሱስ የተገደለው በ 33 ድኅረ-ልደት ነው፥ ያ ማለት ኢየሱስ ከተገደለ በኃላ ከ5 ዓመት በኃላ መሢሕ ይገደላል ማለት ትንቢቱ ፉርሽ ይሆናል።

አድቬንቲስት 62 እና 7 ደምረው 69 ሱባዔን ከሦስተኛው አዋጅ ለማስላት ይሞክራሉ። 69×7= 483 ይሆናል። ሦስተኛው አዋጅ 457 ነው፥ ከ 457 ጀምረን 483 ዓመት ስንቆጥር 26 ድኅረ-ልደት ነው፥ 483-457= 26 ይሆናል። በእነርሱ ስሌት ዳንኤል ላይ የተጠቀሱት ሁለቱ መሢሖች ኢየሱስ ነው ይባልና፥ "ከ 62 እና 7 በኃላ መሢሕ ይገደላል" የሚለው ይዘው በዚህ ያሰሉታል።

የይሆዋ ምስክሮች 62 እና 7 ደምረው 69 ሱባዔን ከሦስተኛው አዋጅ ለማስላት ይሞክራሉ። 69×7= 483 ይሆናል። ሦስተኛውን አዋጅ 455 ያረጉትና ከ 455 ጀምረን 483 ዓመት ስንቆጥር 28 ድኅረ-ልደት ነው፥ 483-455= 28 ይሆናል። በእነርሱ ስሌት ዳንኤል ላይ የተጠቀሱት ሁለቱ መሢሖች ኢየሱስ ነው ይባልና፥ "ከ 62 እና 7 በኃላ መሢሕ ይገደላል" የሚለው ይዘው በዚህ ያሰሉታል።

የተቀረው 1 ሱባዔ ፕሮቴስታንት ወደ ፊት ሐሣዌ መሢሕ ሲመጣ የሚሆን ነው ሲሉ፣ አድቬንቲስት ደግሞ ከ 26 እስከ 33 ተፈጽሟል። በሱባዔ እኩሌታ በ 29 ተኩል ላይ ሲጠመቅ መስዋዕቱና ቁርባኑ ቀርቷል ይላል። የይሆዋ ምስክሮች እንዲሁ ከ 28 እስከ 36 ተፈጽሟል። በሱባዔ እኩሌታ በ 33 ድኅረ-ልደት ሲሰቀል መስዋዕቱና ቁርባኑ ቀርቷል ይላሉ።

ይህ የእነርሱ የተለያየ አመለካከት ነው። ነገር ግን 7 ሱባኤ ማለትም 49 ዓመት ለምን እንደተጠቀሰ መፍታት አልቻሉም፥ በግምት፦ "የመቅደሱ ግንባታ የወሰደበት ጊዜ ነው" በማለት ዕውር ድንብር መልስ ለመስጠት ይሞክራሉ። ነገር ግን የመቅደሱ ግንባታ የተጠናቀቀው በ 516 ቅድመ-ልደት ነው። ከመጀመሪያው ከቂሮስ አዋጅ ከ 539 እስከ የመቅደሱ ግንባታ መጠንናቀቅ 516 ድረስ 23 ዓመት እንጂ 49 ዓመት አይደለም፥ 539-516= 23 ዓመት ይሆናል።

በጥቅሉ የሰባ ሱባዔ ትርጉም ከላይ አይሁዳውያን ባስቀመጡት መልክ ካልሆነ የ 7 ሱባዔ ትርጉም ይዛባል።
ከክርስትና ብዙዎች ከመጽሐፉ ያይደለ ሲኾን ከመጽሐፉ መኾኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙ ክፍሎች እንደዚህ አይነቶቹ ናቸው፦
3፥78 *ከእነሱም እርሱ ከመጽሐፉ ያይደለ ሲኾን ከመጽሐፉ መኾኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙ ክፍሎች አሉ፡፡ እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልኾነ ሲኾን «እርሱ ከአላህ ዘንድ ነውም» ይላሉ፡፡ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑም በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ*፡፡ وَإِنَّ مِنْهُمْ لَفَرِيقًا يَلْوُونَ أَلْسِنَتَهُم بِالْكِتَابِ لِتَحْسَبُوهُ مِنَ الْكِتَابِ وَمَا هُوَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَقُولُونَ هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَمَا هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَيَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቀሪን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

15፥95 *"ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል"*፡፡ إِنَّا كَفَيْنَٰكَ ٱلْمُسْتَهْزِءِينَ

የአእምሮ ስንኩላን ከትልቅ እስለ ደቂቅ ያለ አንዳች ከልካይ የባልቴት የቡና ወሬ ሲነዙ ማየት ዐላዋቂነትን ከማሳበቅ ውጪ አንዳች የሚፈይዱት ነገር የለም። በኢሥላም ያሉ የመስኩ ሊሒቃን፦ “ውኃን ከጡሩ፥ ነገርን ከሥሩ” ይላሉና እኛም ከሥሩ ስለ ቀሪን የተነሳውን የወይዛዝርት የቡና ወሬ በትክክለኛ የአስተላለፍና የአስነዛዘር ሙግት እንሞግታለን። "ቀሪን" قَرِين የሚለው ቃል 8 ጊዜ በቁርኣን የተጠቀሰ ሲሆን "ጓደኛ" ማለት ነው፦
37፥51 ከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ ይላል፦ *"እኔ ጓደኛ ነበረኝ"*፡፡ قَالَ قَائِلٌ مِّنْهُمْ إِنِّي كَانَ لِي قَرِينٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ቀሪን" قَرِين የተባለበው ሰው ለሰው "ጓደኛ" በሚሆንበት ስሌት ነው። ስለዚህ "ቀሪን" ማለት "ሸይጧን" ማለት ሳይሆን "ጓደኛ" ማለት ብቻ ነው። ለምሳሌ ሥራችንን የሚመዘግቡ መልአክ "ቀሪን" قَرِين ተብለዋል፦
50፥23 *"ቁራኛውም መልአክ"* «ይህ ያ እኔ ዘንድ ያለው ቀራቢ ነው» ይላል፡፡ وَقَالَ قَرِينُهُ هَـٰذَا مَا لَدَيَّ عَتِيد

"ቀሪኑሁ" قَرِينُهُ ማለት "ጓደኛው" ማለት ነው። ሰው ለሰው ጓደኛ እንደተባለ ሁሉ ወይም ለአማንያን መልአክ ጓደኛ እንደተባለ ሁሉ ሸይጧን ለከሃድያን "ጓደኛ" ነው፦
43፥36 *ከአልረሕማን ግሣጼ ከቁርኣን የሚደናበርም ሰው ለእርሱ ሰይጣንን እናስጠጋለን፡፡ ስለዚህ እርሱ ለእርሱ "ቀሪን" ነው*፡፡ وَمَن يَعْشُ عَن ذِكْرِ الرَّحْمَـٰنِ نُقَيِّضْ لَهُ شَيْطَانًا فَهُوَ لَهُ قَرِينٌ
4፥38 እነዚያም ለሰዎች ይውልኝ ሲሉ ገንዘቦቻቸውን የሚሰጡ በአላህና በመጨረሻውም ቀን የማያምኑ ይቀጣሉ፡፡ *"ሰይጣንም ለእርሱ ጓደኛው የኾነ ሰው ጓደኛነቱ ከፋ!* وَالَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُمْ رِئَاءَ النَّاسِ وَلَا يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَلَا بِالْيَوْمِ الْآخِرِ ۗ وَمَن يَكُنِ الشَّيْطَانُ لَهُ قَرِينًا فَسَاءَ قَرِينًا

ልብ አድርግ "ጓደኛ" ለሚለው ቃል እዚህ ጋር የገባው "ቀሪን" قَرِين ነው። ለሰው ከሰው፣ ለሰው ከመልአክ እና ለሰው ከጂን ጓደኛ ሊኖረው ይችላል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 52, ሐዲስ 62
ዐብደላህ ኢብኑ መሥዑድ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ከእናንተ መካከል ማንም የለም ከጂን የሆነ ጓደኛ ቢኖረው እንጂ። እነርሱም(ሠሐባዎች)፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" ሆይ! እርስዎም ቢሆኑ? አሉ። እርሳቸውም፦ "እኔም ብሆን፥ ግን አላህ በእርሱ ላይ እረድቶኛል። በመልካም እንጂ እንዳያዘኝ አሥልሞታል"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ مَسْعُودٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ مَا مِنْكُمْ مِنْ أَحَدٍ إِلاَّ وَقَدْ وُكِّلَ بِهِ قَرِينُهُ مِنَ الْجِنِّ ‏"‏ ‏.‏ قَالُوا وَإِيَّاكَ يَا رَسُولَ اللَّهِ قَالَ ‏"‏ وَإِيَّاىَ إِلاَّ أَنَّ اللَّهَ أَعَانَنِي عَلَيْهِ فَأَسْلَمَ فَلاَ يَأْمُرُنِي إِلاَّ بِخَيْر

እዚህ ሐዲስ ላይ "ጓደኛ" ለሚለው ቃል "ቀሪን" قَرِين የሚለው ቃል መግባቱ አንባቢ ልብ ይለዋል። እዚሁ ሐዲስ ላይ "አሥለመ" َأَسْلَم ማለት ሁለት ትርጉም አለው፤ አንደኛ "ታዘዘ” ማለት ሲሆን የስም መደቡ "ሙሥሊም" مُسْلِم ማለት ነው፥ የእርሳቸው ጓደኛ ሙሥሊም ጂን እንጂ ካፊር ጂን አለሞሆኑን እንረዳለን። ሁለተኛ "ጠበቀ" ሲሆን የስም መደቡ "ሙሠለም" مُسَلَّم ማለትም "የተጠበቀ" ማለት ነው፥ እርሳቸው ከእርሱ እኩይ የተጠበቁ መሆናቸውን እንረዳለን።
ዋቢ ማብራሪያ፦ "ኢማም ነወዊ አል-ሚንሃጅ ሸርሕ ሰሒሕ ሙሥሊም መጽሐፍ 52, ሐዲስ 62 ተመልከት።

ጂን ደግሞ ልክ እንደ ሰው ነጻ ፈቃድ ያላቸው ፍጡራን ናቸው። “ጂን” جِنّ የሚለው ቃል “ጀንነ” جَنَّ ማለትም “ተሰወረ” ወይም “ተደበቀ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ስውር” ወይም “ድብቅ” ማለት ነው፥ “ጅኒ” جني ደግሞ የጂን ብዙ ቁጥር ነው። ጂኒዎች የተፈጠሩት ከሰው በፊት ከእሳት ነበልባል ነው፦
15፥27 *ጃንንም ከሰው በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው*፡፡ وَالْجَانَّ خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ مِن نَّارِ السَّمُومِ
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 55, ሐዲስ 78
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”መላእክት ከብርሃን ተፈጥረዋል፤ ጂንዎች ከእሳት ነበልባል ተፈጥረዋል፤ አደም ለእናንተ እንደተገለጸላችሁ ከሚጭለቀለቅ ሸክላ ተፈጥሯል”*፡፡ عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم‏ خُلِقَتِ الْمَلاَئِكَةُ مِنْ نُورٍ وَخُلِقَ الْجَانُّ مِنْ مَارِجٍ مِنْ نَارٍ وَخُلِقَ آدَمُ مِمَّا وُصِفَ لَكُمْ ‏.‏

ጂኒዎች የተፈጠሩበት ዓላማ የፈጠራቸው አላህ እንዲያመልኩ ነው፦
51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

ጂኒዎች እንደ ሰው ነጻ ምርጫ ያላቸው ፍጡሮች ናቸው፥ በነጻ ምርጫቸው ሙሥሊም አልያም ካፊር የመሆን ምርጫ አላቸው፦
72፥14 *«እኛም ከእኛ ውስጥ ሙስሊሞች አሉ፡፡ ከእኛም ውስጥ በዳዮች አሉ፡፡ የሰለሙም ሰዎች እነዚያ ቅንን መንገድ መረጡ፡፡»* وَأَنَّا مِنَّا الْمُسْلِمُونَ وَمِنَّا الْقَاسِطُونَ ۖ فَمَنْ أَسْلَمَ فَأُولَـٰئِكَ تَحَرَّوْا رَشَدًا

ከጂኒዎች መካከል አማንያን እንዳሉ ሁሉ ከሃድያንም አሉ፥ ከሃድያኑ "ሰይጣናት" ይባላሉ። “ሸይጧን” شَّيْطَان የሚለው ቃል “ሸጠነ” شطن ማለትም “ራቀ” ወይም “ተገለለ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “የተገለለ” ወይም “የራቀ” ማለት ነው፥ “ሸያጢን” شَيَاطِين ደግሞ የሽይጧን ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሰይጣናት” ማለት ነው። “ሸይጧን” ልክ እንደ “ሌባ” “ውሸታም” “ባለጌ” የባህርይ ስም እንጂ የተጸውዖ ስም አይደለም። ሸይጧን የሰውም የጂኒም አለ፦
6፥112 እንደዚሁም ለነቢያት ሁሉ *ከሰው እና ከጂን የኾኑን ሰይጣናት ጠላት* አደረግን፡፡ وَكَذَٰلِكَ جَعَلْنَا لِكُلِّ نَبِيٍّ عَدُوًّا شَيَاطِينَ الْإِنسِ وَالْجِن
114፥6 *«ከጂኒዎችም ከሰዎችም ሰይጣናት እጠበቃለሁ»* በል። مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ
23፥97 በልም *«ጌታዬ ሆ! ከሰይጣናት ጉትተጎታዎች በአንተ እጠበቃለሁ»* ፡፡ وَقُل رَّبِّ أَعُوذُ بِكَ مِنْ هَمَزَاتِ الشَّيَاطِينِ
7፥200 *ከሰይጣንም በኩል ጉትጎታ ቢያገኝህ በአላህ ተጠበቅ፡፡ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና*፡፡ وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ الشَّيْطَانِ نَزْغٌ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ ۚ إِنَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ