ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.3K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ጥያቄ፦ እስራኤላውያው በምድረ በዳ ያሉት የቱን ነው? “ከግብፅ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው” ወይስ “ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው” ?
ነህምያ 9፥18 ቀልጦ የተሠራውንም እምቦሳ አድርገው፡— *ከግብፅ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው* ባሉ ጊዜ፥ እጅግም ባስቈጡህ ጊዜ፥
ዘጸአት 32፥4 ከእጃቸውም ተቀብሎ በመቅረጫ ቀረጸው፥ ቀልጦ የተሠራ ጥጃም አደረገው፤ እርሱም፡— እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ *ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው*፡ አላቸው።

ዘንበሪ ይኖር የነበረው በማን ዘመን ነው? በሙሴ ወይስ በይሁዳ ንጉሥ በአሳ?
ዘኍልቍ 25፥14 ከምድያማዊቱም ጋር የተገደለው የእስራኤላዊው ሰው ስም *ዘንበሪ* ነበረ፤
1ኛ ነገሥት 16፥23 በይሁዳ ንጉሥ በአሳ በሠላሳ አንደኛው ዓመት *ዘንበሪ* በእስራኤል ላይ አሥራ ሁለት ዓመት ነገሠ። በቴርሳም ስድስት ዓመት ነገሠ።

አይ ሁለቱ የተለያዩ ሰዎች ናቸው ካላችሁ እንግዲያውስ ቁርአን እየነገረን ያለው በሙሳ ጊዜ ስለነበረ ክስተት እንጂ በሰማርያውን ስለተከሰተው ክስተት አይደለም።
ሁለት ክስተት በተለያዩ ጊዜ ሲከናወኑ ታሪኩ አንድ ነው ብሎ መደምደም ቂልነት ነው። ለምሳሌ በሉጥ ዘመን የነበሩ ሰዎች ወንድ ለወንድ ለተራክቦ ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል፦
ዘፍጥረት 19፥5-9 *ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት፤ በዚህ ሌሊት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው*። *ሎጥም ወደ እነርሱ ወደ ደጅ ወጣ መዝጊያውንም በኋላው ዘጋው*፤
እንዲህም አለ፦ ወንድሞቼ ሆይ፥ *ይህን ክፉ ነገር አታድርጉ፤ እነሆ፥ ወንድን ያላወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ላውጣላችሁ፥ እንደ ወደዳችሁም አድርጓቸው*፤ በእነዚህ ሰዎች ብቻ ምንም አታድርጉ፥ እነርሱ በጣራዬ ጥላ ሥር ገብተዋልና።

ይህ ድርጊት በመሳፍንቱ ዘመን የነበሩ ሰዎች ወንድ ለወንድ ለተራክቦ ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል፦
መሣፍንት 19፥22-25 ሰውነታቸውንም ደስ ባሰኙ ጊዜ ወስላቶች የሆኑ *የከተማው ሰዎች ቤቱን ከበቡ በሩንም ይደበድቡ ነበር፤ ባለቤቱንም ሽማግሌውን፦ ወደ ቤትህ የገባውን ሰው እንድንደርስበት አውጣልን፡ አሉት። ባለቤቱም ሽማግሌው ወደ እነርሱ ወጥቶ፦ ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህን ክፉ ነገር፥ እባካችሁ፥ አታድርጉ፤ ይህ ሰው ወደ ቤቴ ገብቶአልና እንደዚህ ያለ ኃጢአት አትሥሩ። ድንግል ልጄና የእርሱም ቁባት፥ እነሆ፥ አሉ፥ አሁንም አወጣቸዋለሁ፤ አዋርዱአቸው እንደ ወደዳችሁም አድርጉባቸው፤ ነገር ግን በዚህ ሰው ላይ እንደዚህ ያለ ኃጢአት አታድርጉ፡ አላቸው። ሰዎቹ ግን ነገሩን አልሰሙም፤ ሰውዮውም ቁባቱን ይዞ አወጣላቸው፤ ደረሱባትም፥ ሌሊቱንም ሁሉ እስኪነጋ ድረስ አመነዘሩባት፤ ጎህ በቀደደም ጊዜ ለቀቁአት*።

ያ ማለት ሁለት ተመሳሳይ ክስተት ግን በተለያየ ጊዜ የሆኑ ክንውኖች ናቸው ካላችሁ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን እሳቤ በዚህ መልክና ልክ ተረዱት።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
በአላህ ስም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

96፥1 *"አንብብ በዚያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም"*፡፡ اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ

አምላካችን አላህ በጂብሪል ለነቢያችን”ﷺ” “ኢቅራ” اقْرَأْ ማለትም “አንብብ” ወይም “አነብንብ” ብሎ አዟቸዋል፦
96፥1 *"አንብብ በዚያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም"*፡፡ اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ

“ቁርኣን” قُرْءَان የሚለው ቃል “ቀረአ” قَرَأَ ማለትም “አነበበ” ወይም “አነበነበ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “መነባነብ”recitation” ማለት ነው። “ኢቅራ” اقْرَأْ ትእዛዛዊ ግስ ሲሆን ቁርኣን ሲጀምር የሚነበበው "ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም" ነው፥ ከአንድ ሱራህ በስተቀር እያንዳንዱ ሱራህ ሲጀምር “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በኾነው” በሚል ነው። ይህቺ ሱራህ ሱረቱ "አት-ተውባህ" ናት። 9ኛው ሱራህ ተስሚያህ ባይኖራትም ሱረቱ አን-ነምል 27፥30 ላይ ይደግመዋል። ይህም ሱረቱ አት-ተውባህ የቁጣ ሱራህ ሆና ብትዘለልም ስትደመር ዘጠኝ የሆነችው ሱረቱ አን-ነምል ላይ ትገኛለች። 2+7=9 ይሆናል፦
27፥30 እርሱ ከሱለይማን ነው፡፡ እርሱም *"በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በኾነው"*፡፡ إِنَّهُ مِن سُلَيْمَانَ وَإِنَّهُ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ

አንድ ሱራህ ከሌላው ሱራህ የሚለየው “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” በሚል ቃል ነው፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 398
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *"ነቢዩ”ﷺ” ሁለት ሱራዎች አይለያዩ በመካከላቸው “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” የሚለው ቃል ወደ እርሳቸው ቢወርድላቸው እንጂ"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم لاَ يَعْرِفُ فَصْلَ السُّورَةِ حَتَّى تُنَزَّلَ عَلَيْهِ ‏{‏ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ ‏}

ያጅባል በጣም። "ቱነዘለ ዐለይሂ" تُنَزَّلَ عَلَيْهِ ማለትም "ወደ እርሳቸው ቢወርድላቸው" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيم ማለትም “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” ከአላህ ወደ ነቢያችን"ﷺ" እኛ እንድናነበው የወረደ ነው፦
29፥45 ከመጽሐፍ *ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ*፡፡ اتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِنَ الْكِتَابِ
18፥27 ከጌታህም መጽሐፍ *ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ*፡፡ وَاتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن كِتَابِ رَبِّك

"አንብብ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ስለዚህ "በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው" የሚለው እኛ እንድናነበው ከአላህ የወረደ ነው። "አንብብ በዚያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም" ብሎ ያ የጌታ ስም ደግሞ፦ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው" መሆኑን ነግሮናል። ክርስቲያን ፕሪንስ፦ "ቁርኣን የአላህ ንግግር ከሆነ አላህ ለምን "በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው" ይላል? "በእኔ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆንኩት" ለምን አይልም? የሚል የቂል ጥያቄ ይጠይቃል። እኛም መልሳችን እኛ ቁርኣንን ስንቀራ በጌታ ስም እንዴት እንደምናነብ ሲነግረን ነው። ፈጣሪ እራሱን በሦስተኛ መደብ አድርጎ መናገር የተለመደ ነው። ለምሳሌ፦ ፈጣሪ “የያህዌህን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ ያህዌህ ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና” ይለናል፦
ዘጸአት 20፥7 *የያህዌህን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ ያህዌህ ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና*።

"የያህዌህን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ ያህዌህ ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና" ብሎ የተናገረው ያህዌህ ከሆነ ያህዌህ ለምን በመጀመሪያ መደብ "የእኔን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ እኔ ስሜን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አላነጻውምና" ብሎ አልተናገረም? ብለን ጥያቄ ስናቀርብ "ያህዌህ እራሱ በሦስተኛ መደብ መናገር ሙሉ መብት አለው" የሚል መልስ ይሰጣሉ። እንግዲያውስ በሰፈራችሁ ቁና መስፈር ይሏችኃል እንደዚህ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የኢብራሂም መንገድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።

16፥123 *ከዚያም ወደ አንተ፦ "የኢብራሂምን መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን ተከተል! ከአጋሪዎቹም አልነበረም" ማለት አወረድን*፡፡ ثُمَّ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ أَنِ اتَّبِعْ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۖ وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِين

“ኢሥላም” إِسْلَٰم ማለትም “መታዘዝ” ወይም “መገዛት” ማለት ሲሆን አላህ ዘንድ ዕውቅና ያለ ሃይማኖት ኢሥላም ብቻ ነው፦
3፥19 *"አላህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት “ኢሥላም” ብቻ ነው"*፡፡ إِنَّ ٱلدِّينَ عِندَ ٱللَّهِ ٱلْإِسْلَٰمُ

አላህ ሰዎችን ሁሉ የፈጠረበት ሃይማኖት ኢሥላም ነው፦
30፥30 *"ፊትህንም ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት ያዟት፡፡ የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም፡፡ ይህ ቀጥተኛ ሃይማኖት ነው"*፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡ فَأَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا ۚ فِطْرَتَ اللَّهِ الَّتِي فَطَرَ النَّاسَ عَلَيْهَا ۚ لَا تَبْدِيلَ لِخَلْقِ اللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ቀጥተኛ" ለሚለው ቃል የገባው "ሐኒፋ" حَنِيفًا ሲሆን አላህ ሰዎችን ሁሉ የፈጠረበት ሃይማኖት ኢሥላም "ሐኒፋ" መሆኑን ያሳያል። አምላካችን አላህ ለኢብራሂም “አሥሊም” أَسْلِمْ ማለትም “ታዘዝ” ብሎ ሲለው እርሱም ለዓለማት ጌታ “አሥለምቱ” أَسْلَمْتُ ማለትም “ታዘዝኩ” አለ፥ ኢብራሂም ወደ ቀጥተኛው የተዘነበለ ሙሥሊም ነበረ፦
2፥131 *"ጌታው ለእርሱ "ታዘዝ” ባለው ጊዜ መረጠው፡፡ ለዓለማት ጌታ ”ታዘዝኩ” አለ"*፡፡ إِذْ قَالَ لَهُۥ رَبُّهُۥٓ أَسْلِمْ ۖ قَالَ أَسْلَمْتُ لِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
3፥67 *"ኢብራሂም ይሁዳዊም ክርስቲያንም አልነበረም፡፡ ግን "ወደ ቀጥተኛው የተዘነበለ ሙሥሊም ነበረ"፡፡ ከአጋሪዎችም አልነበረም"*፡፡ مَا كَانَ إِبْرَاهِيمُ يَهُودِيًّا وَلَا نَصْرَانِيًّا وَلَـٰكِن كَانَ حَنِيفًا مُّسْلِمًا وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

“ሙሥሊም” مُسْلِم የሚለው ቃል “አሥለመ” أَسْلَمَ ማለትም "ታዘዘ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ታዛዥ” ማለት ነው፥ አሁንም እዚህ አንቀጽ ላይ "ቀጥተኛ" ለሚለው ቃል የገባው "ሐኒፋ" حَنِيفًا ነው። "ሐኒፍ" حَنِيف ማለት "ቀጥተኛ" ማለት ሲሆን ለአላህ ቀጥ ያሉ "ቀጥተኞች" ደግሞ "ሑነፋ" حُنَفَاءَ ይባላሉ፦
22፥31 *"ለአላህ ቀጥተኞች በእርሱ የማታገሩ ሆናችሁ ከሐሰት ራቁ"*፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ከሰማይ እንደ ወደቀና በራሪ እንደምትነጥቀው ወይም ነፋስ እርሱን በሩቅ ስፍራ እንደምትጥለው ብጤ ነው፡፡ حُنَفَاءَ لِلَّهِ غَيْرَ مُشْرِكِينَ بِهِ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَكَأَنَّمَا خَرَّ مِنَ السَّمَاءِ فَتَخْطَفُهُ الطَّيْرُ أَوْ تَهْوِي بِهِ الرِّيحُ فِي مَكَانٍ سَحِيقٍ
98፥5 አላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ አጥሪዎች፣ *"ቀጥተኞች ኾነው ሊያመልኩት"*፣ ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ ዘካንም ሊሰጡ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ተለያዩ፡፡ ይህም የቀጥተኛይቱ ሃይማኖት ድንጋጌ ነው፡፡ وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ حُنَفَاءَ وَيُقِيمُوا الصَّلَاةَ وَيُؤْتُوا الزَّكَاةَ ۚ وَذَٰلِكَ دِينُ الْقَيِّمَة

ኢብራሂም እራሱ ሐኒፍ ሲሆን እርሱ የተጓዘበት መንገድ ደግሞ ሐኒፋ ነው፦
2፥135 አይሁድን ወይም ክርስቲያኖችን ኹኑ! ቅኑን መንገድ ትመራላችሁና» አሉም፡፡ «አይደለም *"የኢብራሂምን መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን እንከተላለን"*፤ ከአጋሪዎችም አልነበረም» በላቸው፡፡ وَقَالُوا كُونُوا هُودًا أَوْ نَصَارَىٰ تَهْتَدُوا ۗ قُلْ بَلْ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۖ وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

"ሚላህ" مِلَّة ማለት "መንገድ" ማለት ነው፥ ይህም የኢብራሂም መንገድ ሐኒፋ ነው፦
3፥95 «አላህ እውነትን ተናገረ፡፡ *"የኢብራሂምንም መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን ተከተሉ"*፡፡ ከአጋሪዎቹም አልነበረም» በላቸው፡፡ قُلْ صَدَقَ اللَّهُ ۗ فَاتَّبِعُوا مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِين
4፥125 *"እርሱ መልካም ሠሪ ኾኖ ፊቱን ለአላህ ከሰጠና የኢብራሂምንም መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን ከተከተለ ሰው ይበልጥ ሃይማኖቱ ያማረ ማን ነው? አላህም ኢብራሂምን ፍጹም ወዳጅ አድርጐ ያዘው"*፡፡ وَمَنْ أَحْسَنُ دِينًا مِّمَّنْ أَسْلَمَ وَجْهَهُ لِلَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ وَاتَّبَعَ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۗ وَاتَّخَذَ اللَّهُ إِبْرَاهِيمَ خَلِيلًا
6፥79 *«እኔ ለእዚያ ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረው አምላክ ቀጥተኛ ስኾን ፊቴን አዞርኩ፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም» አለ*፡፡ إِنِّي وَجَّهْتُ وَجْهِيَ لِلَّذِي فَطَرَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ حَنِيفًا ۖ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ
የኢብራሂም መንገድ ሐኒፋ ሲሆን አላማው ሁለንተናን ለአላህ መስጠት ነው፥ "የሰጠ" ለሚለው ቃል የገባው "አሥለመ" أَسْلَمَ ነው።
ነቢያችን"ﷺ" ወደ እርሳቸው ወሕይ ከመውረዱ ይህንን የኢብራሂም መንገድ ይተገብሩ ነበር፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 1 ሐዲስ 3
የምዕመናን እናት ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"ከወሕይ ጅማሬ ለአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ልክ እንደ ጎህ ንጋት ደማቅ ሆኖ በሰናይ ህልም ሁኔታ ነበር። ከዚያም የተማልሎ ውዴታ በእርሷቸው ላይ ነበር። በሒራእ ዋሻ ውስጥ ይገለሉ እና "ቀጥ ይሉ ነበር"። እርሳቸውም ቤተሰባቸውን ለማየት ከመፈለጋቸው በፊት ለብዙ ቀናት በተከታታይ አላህ ያመልኩ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ الْمُؤْمِنِينَ، أَنَّهَا قَالَتْ أَوَّلُ مَا بُدِئَ بِهِ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم مِنَ الْوَحْىِ الرُّؤْيَا الصَّالِحَةُ فِي النَّوْمِ، فَكَانَ لاَ يَرَى رُؤْيَا إِلاَّ جَاءَتْ مِثْلَ فَلَقِ الصُّبْحِ، ثُمَّ حُبِّبَ إِلَيْهِ الْخَلاَءُ، وَكَانَ يَخْلُو بِغَارِ حِرَاءٍ فَيَتَحَنَّثُ فِيهِ ـ وَهُوَ التَّعَبُّدُ ـ اللَّيَالِيَ ذَوَاتِ الْعَدَدِ قَبْلَ أَنْ يَنْزِعَ إِلَى أَهْلِهِ

"ቀጥ ይሉ ነበር" ለሚለው የግስ መደብ የገባው "የተሐነሱ" يَتَحَنَّثُ ሲሆን ኢብኑ ሐጀሩል አሥቀላኒ በፈተሑል ባሪ ፊ ሸርህ ሰሒሑል ቡኻርይ ሐዲስ 3 ላይ፦ "የተሐነሱ" يَتَحَنَّثُ ማለት "የተሐነፉ" يَتَحَنَّفُ ማለት ነው ብለው አስቀምጠዋል፦
قوله : ( فيتحنث ) ‏
‏هي بمعنى يتحنف ، أي : يتبع الحنفية وهي دين إبراهيم ، والفاء تبدل ثاء في كثير من كلامهم . وقد وقع في رواية ابن هشام في السيرة " يتحنف " بالفاء أو التحنث إلقاء الحنث وهو الإثم ، كما قيل يتأثم ويتحرج ونحوهما .

ልብ አድርግ የኢብራሂም መንገድ አላህ ሰዎችን ሁሉ የፈጠረበት ኢሥላም ነው፥ ሲቀጥል አላህ በኢብራሂም ዝርዮች ውስጥ ይመለሱ ዘንድ በአንድ አምላክ የማመን ቀሪ ቃል አድርጓል፦
43፥28 *"በዝርዮቹም ውስጥ ይመለሱ ዘንድ ቀሪ ቃል አደረጋት"*፡፡ وَجَعَلَهَا كَلِمَةً بَاقِيَةً فِي عَقِبِهِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

ነቢያችን"ﷺ" ደግሞ የኢብራሂም ዝርያ ናቸው። ከዚያ በኃላ አላህ ቁርኣንን በማውረድ "ቁል" قُلْ በሚል ትእዛዝ የኢብራሂምን መንገድ ቀጥተኛ ሲሆን መራቸው፦
6፥161 *«እኔ ጌታዬ ወደ ቀጥተኛው መንገድ ትክክለኛን ሃይማኖት "ቀጥተኛ" ሲኾን የኢብራሂምን መንገድ መራኝ፡፡ እርሱም ከአጋሪዎቹ አልነበረም» በል"*፡፡ قُلْ إِنَّنِي هَدَانِي رَبِّي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ دِينًا قِيَمًا مِّلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۚ وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ
10፥105 *"ፊትህንም ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ቀጥ አድርግ"*፡፡ ከአጋሪዎቹም አትሁን፡፡ وَأَنْ أَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

ይህ ዲን ሐኒፋ የሆነው ኢሥላም እንደሆነ እና ኢሥላም ማለት መታዘዝ ማለት እንደሆነ ከላይ አይተናል፥ ቁርኣን ደግሞ "ትእዛዝ" ሆኖ ወደ እርሳቸው ወርዷል፦
65፥5 *"ይህ "የአላህ ትእዛዝ ነው”። ወደ እናንተም አወረደው"*። ذَٰلِكَ أَمْرُ ٱللَّهِ أَنزَلَهُۥٓ إِلَيْكُمْ

ይህንን ትእዛዝ ተቀብለው የታዘዙ የመጀመሪያው ታዛዥ እርሳቸው ናቸው፦
6፥14 *«እኔ መጀመሪያ ትእዛዝን ከተቀበለ ሰው ልኾን ታዘዝኩ*"፡፡ ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትኹን ተብያለሁ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنِّىٓ أُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَسْلَمَ ۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ

“ትእዛዝን ከተቀበለ” የሚለው ይሰመርበት። "ትእዛዝን የተቀበለ" ለሚለው ቃል የገባው "አሥለመ" أَسْلَمَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፥ "አወል" أَوَّل ማለትም "መጀመሪያ" በአንጻራዊነት ደረጃ የመጣ ገላጭ ነው። እንግዲህ ቁርኣንን ተቀብሎ ከሠለሙት ሙሥሊሞች መጀመሪያ ነቢያችን"ﷺ" ናቸው ማለት ነው፦
6፥163 *"«ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም በማጥራት ታዘዝኩ፡፡ እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ» በል"*፡፡ لَا شَرِيكَ لَهُۥ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلْمُسْلِمِينَ
3፥20 ቢከራከሩህም፡- *"«ፊቴን ለአላህ ሰጠሁ፤ የተከተሉኝም ሰዎች እንደዚሁ ለአላህ ሰጡ»* በላቸው፡፡ فَإِنْ حَاجُّوكَ فَقُلْ أَسْلَمْتُ وَجْهِيَ لِلَّهِ وَمَنِ اتَّبَعَنِ

"ሰጠሁ" ለሚለው ቃል የገባው "አሥለምቱ" أَسْلَمْتُ ሲሆን እርሳቸው ቀጥሎ ተከታዮቻቸው ሁለንተናቸውን ለአላህ ያሠለሙ መሆናቸውን ፍንትው አርጎ ያሳያል። ነቢያችን"ﷺ" ከአላህ ወደ እርሳቸው በተወረደው ቁርኣን አምነዋል፥ ተከታዮቻቸውም እንደዚሁ አመኑ፦
2፥285 *"መልክተኛው ከጌታው ወደ እርሱ በተወረደው አመነ፡፡ ምእምኖቹም እንደዚሁ አመኑ"*፡፡ آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِ وَالْمُؤْمِنُون

"ሙዕሚኑን" مُؤْمِنُون ማለት አማኞች ማለት ነው። "ኢማን" إِيمَان ማለት "አመነ" آمَنَ ማለትም "አመነ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "እምነት" ማለት ነው። ቁርኣን ትእዛዝ ሆኖ ወደ ነቢያችን"ﷺ" ከመውረዱ በፊት ቁርኣንን ሆነ በቁርኣን ላይ እምነቱ ምን እንደሆነ ዐያውቁም ነበር፦
42፥52 እንደዚሁም *"ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲኾን መንፈስን (ቁርኣንን) አወረድን፡፡ መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም"*፡፡ ግን መንፈሱን ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው፡፡ አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ፡፡ وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ رُوحًا مِّنْ أَمْرِنَا ۚ مَا كُنتَ تَدْرِي مَا الْكِتَابُ وَلَا الْإِيمَانُ وَلَـٰكِن جَعَلْنَاهُ نُورًا نَّهْدِي بِهِ مَن نَّشَاءُ مِنْ عِبَادِنَا ۚ وَإِنَّكَ لَتَهْدِي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيم

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሡሑር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

"ሡሑር" سُّحُور ወይም "ሠሑር" سَّحُور ማለት ቋንቋዊ ፍቺው "ሠሐር" سَحَر ማለት ነው። "ሠሐር" سَحَر ማለት "የሌሊት መጨረሻ" ማለት ነው። "ሠሐር" سَحَر የሌሊት መጨረሻ በሚል ቃል ሦስት ጊዜ ቁርኣን ውስጥ መጥቷል፦
3፥17 ታጋሾች እውነተኞችም ታዛዦችም ለጋሶችና *"በሌሊት መጨረሻዎች"* ምሕረትን ለማኞች ናቸው፡፡ الصَّابِرِينَ وَالصَّادِقِينَ وَالْقَانِتِينَ وَالْمُنفِقِينَ وَالْمُسْتَغْفِرِينَ بِالْأَسْحَارِ
51፥18 *"በሌሊቱ መጨረሻዎችም"* እነርሱ ምሕረትን ይለምናሉ፡፡ وَبِالْأَسْحَارِ هُمْ يَسْتَغْفِرُونَ
54፥34 እኛ በእነርሱ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን ላክን፡፡ የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ እነርሱንስ *"በሌሊት መጨረሻ"* ላይ አዳንናቸው፡፡ إِنَّا أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ حَاصِبًا إِلَّا آلَ لُوطٍ ۖ نَّجَّيْنَاهُم بِسَحَرٍ

"ሡሑር" سُّحُور ማለት ሃይማኖታዊ ፍቺው ደግሞ በሌሊት መጨረሻዎች ከፈጅር አዛን በፊት ለጾም መያዢያ የሚበላ ምግብ ነው። ይህንን የሌሊት ምግብ መብላት የዚህችን ኡማ የጾም ሥርዓት ካለፉት አህሉል ኪታብ የሚለይበት ሥርዓት ነው፦
ሱነን ነሳኢ መጽሐፍ 22 , ሐዲስ 77
ዐምር ኢብኑል ዐስ እንደተረከው፦;"የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"በእኛ ጾም እና በአህሉል ኪታብ ጾም መካከል ያለው ልዩነት ሡሑር ነው"*። عَنْ عَمْرِو بْنِ الْعَاصِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ فَصْلَ مَا بَيْنَ صِيَامِنَا وَصِيَامِ أَهْلِ الْكِتَابِ أَكْلَةُ السُّحُورِ ‏

ሡሑርን መመገብ የሚኖረው ትሩፋት ረድኤታዊ በረከት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 30, ሐዲስ 32
አነሥ ኢብኑ ማሊክ ሰምቶ እንዳስተላለፈው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ሡሑርን ብሉ! በሠሑር ውስጥ በረከት አለና”*። قَالَ سَمِعْتُ أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ تَسَحَّرُوا فَإِنَّ فِي السَّحُورِ بَرَكَةً

"ተሠሐሩ" تَسَحَّرُوا የሚለው የግስ መደብ "ሠሑር" سَّحُور ከሚለው የስም መደብ የረባ ቃል ነው። አምላካችን አላህ፦ “መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፤ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ” ስላለን ሡሑርን መብላት ከነቢያችን"ﷺ" ያገኘነው ሱናህ ነው፦
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

ነቢያችን"ﷺ" የአላህ ነብይ ስለሆኑ በዐቂዳህ እና በፊቅህ ጉዳይ ላይ የሚናገሩት ሁሉ ወሕይ ነው። ኢሥላም ሰው ሠራሽ ሕግ ሳይሆን ዐቂደቱል ረባንያ ነው። ይህንን በቅጡ የማያውቁ ሰዎች፦ "የሙሥሊም ጾም ማለት ሌሊቱ ወደ መዓልት ተቀይሮ ሌሊቱ በሙሉ ሲበላ ይታደርና በመዓልት የሚተኛበት" ይመስለዋል። ይህ የተሳሳተ መረዳት ነው። ሙሥሊም መግሪብ አዛን ሲል ያፈጥራል እስከ ዒሻህ ሊበላ ይችላል። በዚህ ጊዜም ጾመኛ ማስፈጠር፣ ሰደቃ፣ ዳዕዋህ በማድረግ መሽጉል ነው። ዒሻህ ከተቆመ በኃላ ተራዊሕ ሶላት ይቀጥላል፥ ከዚያ ሶላቱል ለይል አለ። ይህ ሁሉ ዘርፈ-ብዙ እና መጠነ-ሰፊ አምልኮ ለምሳሌ ዚክር፣ ዱዓ፣ ቂርኣት፣ የሱናህ ሶላት ወዘተ.. ከተካሄደ በኃላ የፈጅር ሶላት አዛን ከማለቱ በፊት በሡሑር ይያዛል። ይህንን ካላወክ ቀረብ ብለክ አንድ ቀን ማየት ነው። በተለይ አውሮፓ አካባቢማ ጾሙ በጋ ላይ ከዋሉ ጾሙ 19-21 ሰአት ያክል ይጾማል። ከ 3-5 ሰአት ምግብ በማፍጠር የተበላው ቁጭ ብሎ ሡሑር የሚቀመሰው ለሱናው ያክል በወፍ በረር ነው። ይህንን የመለኮት ሕግና ሥርዓት የያዘው ጾም የምትተቹ አላህ ሂዳያህ ይስጣችሁ፥ ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተራዊሕ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

“ዒባዳህ” عِبَادَة ማለትም “አምልኮ” አላህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኝባቸው ሥስት ሸርጦች ኢማን፣ ኢኽላስ እና ኢቲባዕ ናቸው። “ኢቲባዕ” إتباع የሚለው ቃል “አትበዐ” أَتْبَعَ “ተከተለ” ከሚለው የመጣ ሲሆን “መከተል” ማለት ሲሆን ያለ ኢቲባዕ ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም። ኢቲባዕ ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው ብቻ ዒባዳህን መፈጸም ነው፦
7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ*፤ اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ
6፥106 *ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን ተከተል* ፡፡ اتَّبِعْ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ

“ተከተሉ” የሚለው ቃል “ኢተቢዑ” اتَّبِعُوا ሲሆን “ኢቲባዕ” إتباع ማለት እንግዲህ ከአላህ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደውን ብቻ መከተል ነው፤ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደው ደግሞ ቁርኣን እና ሰሒሕ ሐዲስ ነው።
“ቢድዓ” بدع ደግሞ “በደዐ” بدع ማለትም “ፈጠረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ኢብቲዳዕ” ابتداع ማለትም “ፈጠራ” ማለት ነው፤ ቢድዓ የኢቲባዕ ተቃራኒ ነው። ቢድዓ ማለት ከአምስቱ አሕካም ውጪ አዲስ ፈጠራ ማለት ነው፤ ስለ ቢድዓ ነቢያችን”ﷺ” እንዲህ ይሉናል፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 53, ሐዲስ 7
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ማንኛውም ሰው ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም”* عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ فِيهِ فَهُوَ رَدٌّ ‏”‌‏.‏
ሡነን ነሣኢ : መጽሐፍ 19, ሐዲስ 23
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሑጥባቸው ላይ እንደተናገሩት፦ *“አላህ የመራውን ማንም አያጠመውም፤ አላህ ያጠመመውን ማንም አያቀናውም። ከንግግር ሁሉ በላጩ የአላህ መጽሐፍ ነው፤ ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነው። ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው*። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ فِي خُطْبَتِهِ يَحْمَدُ اللَّهَ وَيُثْنِي عَلَيْهِ بِمَا هُوَ أَهْلُهُ ثُمَّ يَقُولُ مَنْ يَهْدِهِ اللَّهُ فَلَا مُضِلَّ لَهُ وَمَنْ يُضْلِلْهُ فَلَا هَادِيَ لَهُ إِنَّ أَصْدَقَ الْحَدِيثِ كِتَابُ اللَّهِ وَأَحْسَنَ الْهَدْيِ هَدْيُ مُحَمَّدٍ وَشَرُّ الْأُمُورِ مُحْدَثَاتُهَا وَكُلُّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلُّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ وَكُلُّ ضَلَالَةٍ فِي النَّارِ .

ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ከሆነ ካየን ቢድዓ የሚያራምድ ማንኛውም ሰው “ሙብተዲዕ” مبتدئ ይባላል።
ይህንን ለቅምሻ ያክል በወፍ በረር ካየን ዘንዳ ሚሽነሪዎች፦ “ተራዊሕ” تراويح‌‎ ማለትም “በረመዳን የሌሊት ሶላት” ነቢያችን”ﷺ” የማያውቁትና ያልሠሩት ነው ብለው ለሚቀጥፉት ቅጥፈት ምላሽ መስጠት ግድ ይላል፤ ስለ ተራዊህ ከነቢያችን”ﷺ” ሱናህ በቁና ማቅረብ ይቻላል፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 31, ሐዲስ 4
የነብዩ”ﷺ” ባልተቤት ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ *”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” በረመዳን ሌሊት ይጸልዩ ነበር”*። عَنْ عَائِشَةَ، رضى الله عنها زَوْجِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم صَلَّى وَذَلِكَ فِي رَمَضَانَ‏.‏
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 31, ሐዲስ 1
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ስለ ረመዳን እንደተናገሩት፦ *”ማንም በረመዳን ሌሊት በእምነት እና ከአላህ ወሮታ አገኛለው ብሎ ተስፋ አድርጎ ከቆመ ያለፈው ወንጀሉ ሁሉ ይቅር ይባልለታል”*። أَنَّ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ لِرَمَضَانَ ‏ “‏ مَنْ قَامَهُ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ ‏”‌‏.‏

አምላካችን አላህ፦ “መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፤ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ” ስላለን ተራዊሕ መልእክተኛው የነገሩን ነገር ስለሆነ ቢድዓ አይደለም፦
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አንዱ ተመላኪ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

ኢየሱስ ለሰይጣን፦ "ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና" ብሎታል፦
ማቴዎስ 4፥10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ *እርሱንም ብቻ አምልክ* αὐτῷ μόνῳ λατρεύσεις ተብሎ ተጽፎአልና አለው።

"አውቶ" αὐτῷ ማለት "እርሱ"him" ማለት ሲሆን ነጠላ ተውላጠ-ስም መሆኑ አንድ ነጠላ ማንነት ብቻ እንደሚመለክ ያሳያል፥ ከአንድ በላይ የሚመለኩ ማንነት ቢሆን ኖሮ "አውቶኢስ" αὐτοῖς ማለትም "እነርሱ"them" ይሆን ነበር። ይህ ጌታ አምላክ ለኢየሱስ የዳዊትን ዙፋን የሰጠው አብ ነው፦
ሉቃስ 1፥32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ *ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል*።

ይህ ጌታ አምላክ ከበጉ ማንነት በሰዋስው ተነጥሎ ተቀምጧል፦
ራእይ 21፥22 *"ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እና በጉ መቅደስዋ ናቸውና"* መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም።

ልብ አድርግ "ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ" እና "በጉ" ሁለት ማንነት እንደሆኑ ለማሳየት "ናቸው" በሚል የብዜት አያያዥ ግስ ተቀምጧል፥ በተጨማሪም "እና" በሚል መስተጻምር ተለይተዋል። ስለዚህ "ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ" እና "በጉ" ሁለት ማንነት ናቸው፥ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ አብ ከሆነ "በጉ" ደግሞ ኢየሱስ ነው። በጉ የሚታረድ ማንነት ስለሆነ ፍጡር ነው፦
ራእይ 5፥12 በታላቅም ድምፅ፦ *"የታረደው በግ"* ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል፥ አሉ።

መለኮት የሆነው ጌታ አምላክ ስጋ ስላልሆነ መቼም አይታረድም። እንደ ባይብሉ የታረደው በግ ሰው የሆነው ኢየሱስ ከሆነ ሰው አይመለክም፦
ራእይ 22፥3 *"የእግዚአብሔር እና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል"*፥ λατρεύσουσιν αὐτῷ ፊቱንም ያያሉ።

እግዚአብሔር እና በጉ ሁለት ማንነት መሆናቸው ለማሳየት አሁንም "እና" በሚል መስተጻምር ተለይተዋል። አሁንም "አውቶ" αὐτῷ ማለት "እርሱ"him" ማለት ሲሆን ነጠላ ተውላጠ-ስም መሆኑ አንድ ነጠላ ማንነት ብቻ እንደሚመለክ ያሳያል፥ ከአንድ በላይ የሚመለኩ ማንነት ቢሆን ኖሮ "አውቶኢስ" αὐτοῖς ማለትም "እነርሱ"them" ይሆን ነበር። "ያመልኩታል" እንጂ "ያመልኳቸዋል" አላለም፥ ይህ የሚመለክ እግዚአብሔር እንጂ በጉ አይደለም፦
ራእይ 7፥15 ስለዚህ *"በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አሉ፥ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ ያመልኩታል"*።
ራእይ 7፥17 በዙፋኑ መካከል ያለው *"በጉ እረኛቸው ይሆናልና"*።

ልብ አድርግ "አውቶ" αὐτῷ ማለትም "እርሱ"him" የሚለው ተክቶ የመጣው "እግዚአብሔር" የሚለውን ቃል ነው፥ "ያመልኩታል" የተባለው በግልጽና በማያሻማ "እግዚአብሔርን" ነው። በጉ ከእግዚአብሔር በሰዋሰው አቀማመጥ ተነጥሎ "እረኛቸው ይሆናልና" የተባለው።
አንዳንድ ቂሎች፦ "የእግዚአብሔር እና የበጉ ዙፋን አንድ ዙፋን ነው፥ ስለዚህ በጉ ይመለካል" ይላሉ፥ ለመሆኑ ሰለሞን የተቀመጠበት ዙፋን የማን ነው የእግዚአብሔር ወይስ የዳዊት? እስቲ እንመልከት፦
1ኛ ዜና 28፥5 *በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን* ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል።
1ኛ ዜና 29፥23 *"ሰሎሞንም በአባቱ በዳዊት ዙፋን ላይ ተቀመጠ"*፥ ተከናወነለትም፤ እስራኤልም ሁሉ ታዘዙለት።

የዳዊት ዙፋን የእግዚአብሔር ዙፋን ነው፥ ዳዊትም ሆነ ሰለሞን የተቀመጡት በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ነው። ታዲያ የእግዚአብሔር እና የዳዊት ዙፋን አንድ ስለሆነ ዳዊት ይመለካልን? እንደ ባይብሉ ኢየሱስም የተሰጠው ዙፋን የዳዊት ዙፋን ነው፦
ሉቃስ 1፥32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ *ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል*።

በእግዚአብሔር እና በበጉ ዙፋን ላይ ከኢየሱስ ጋር የሚቀመጡ አማንያንም ጭምር ናቸው፦
ራእይ 3፥21 እኔ ደግሞ ድል እንደ ነሣሁ *"ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ"*፥ ድል ለነሣው *"ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ"* ዘንድ እሰጠዋለሁ።

በዙፋኑ ላይ የሚቀመጡት አማንያንስ ይመለካሉን? ሲጀመር ኢየሱስ ዙፋኑን ከጌታ አምላክ በስጦታ ያገኘው ነው፥ ሲቀጥል እግዚአብሔር ለኢየሱስ የሰጠውን ነገር ሁሉ ለአማንያንም ይሰጣል፦
ሮሜ 8፥32 *"ከእርሱ ጋር ደግሞ "ሁሉን ነገር" እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?*

"ሁሉን ነገር" የሚለው ይሰመርበት። ለወልድ የተሰጠው "ሁሉ ነገር" እግዚአብሔር ከኢየሱስ ጋር ሁሉን ነገር ለአማንያን ይሰጣል። ለምሳሌ ሥልጣን፣ ፍርድ፣ ንግሥና፣ ዙፋን ወዘተ። ኢየሱስ ምንም የራሱ ነገር የለውም። ሁሉንም በስጦታ ያገኘው ነው፦
ሉቃስ 10፥22 *"ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል"*።
ዮሐንስ 17፥10 *"የእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው፥ የአንተውም የእኔ ነው"*፤ እኔም ስለ እነርሱ ከብሬአለሁ።

የኢየሱስ የሆነ ሁሉ ከአብ የተሰጠው ስለሆነ "የእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው" አለ፥ ግን የእግዚአብሔር የሆነ ሁሉ የኢየሱስ ስላልሆነ "የአንተውም የእኔ ነው" አለ እንጂ "የአንተ "ሁሉ" የእኔ ነው" አላለም። የአንተ ዙፋን የእኔ ነው ማለቱ ነው፥ የእግዚአብሔር ዙፋን የዳዊት ዙፋን ነው እንደማለት ነው። ከሌላ ማንነት ሥልጣን፣ ፍርድ፣ ንግሥና፣ ዙፋን እረ ሕይወትም ሳይቀር የተሰጠው ማንነት በፍጹም አይመለክም፦
ዮሐንስ 5፥26 አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ *"ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና"*።

ሕይወት አልባ የነበረውን የኢየሱስን ማንነት ሕይወት በመስጠት ወደ ህልውና ያመጣ ማንነት በእውነት ሊመለክ ይገባዋል።
ኢየሱስ የትምህርቱ ጭብጥ፦ “አላህ ጌታዬና ጌታችሁ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት” የሚል ነው፤ አምላካችን አላህም ኢየሱስ ተናገር ብሎ ያዘዘው ቃል “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” ማለትን ነው፦
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ
3፥51 *”አላህ ጌታዬና ጌታችሁ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት”* ፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» አላቸው፡፡ إِنَّ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ ۗ هَٰذَا صِرَٰطٌۭ مُّسْتَقِيمٌۭ

ስለዚህ አንድ ተመላኪ አለ እርሱም ኢየሱስን መልእክተኛ አድርጎ የላከ አላህ ብቻ ነው። እርሱም፦ "እኔን ብቻ አምልኩኝ" ይላል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አንዱ አምላክ እና በጉ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

አንዱ አምላክ አላህ ኢየሱስን ሲልከው፦ "ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ" እንዲል ነው፦
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

ነገር ግን ሰዎች ዛሬ ፍጡር የሆነውን ኢየሱስን ሲያመልኩ ይታያል። ይህ ስህተት ቢሆንም ኢየሱስ አምልኮ ይገባዋል ብለው ድምዳሜ ላይ ከአደረሳቸው አናቅጽ መካከል አንዱ እንይ፦
ራእይ 5፥13 *"በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው እና ለበጉ ይሁን ሲሉ ሰማሁ። አራቱም እንስሶች፦ አሜን አሉ፥ ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱለት"*።
καὶ πᾶν κτίσμα ὃ ἐν τῷοὐρανῷ καὶ ἐπὶ τῆςγῆς καὶ ὑποκάτω τῆςγῆς καὶ ἐπὶ τῆςθαλάσσης, καὶ τὰ ἐναὐτοῖς πάντα, ἤκουσαλέγοντας, Τῷκαθημένῳ ἐπὶ τῷθρόνῳ καὶ τῷ ἀρνίῳ ἡεὐλογία καὶ ἡ τιμὴ καὶἡ δόξα καὶ τὸ κράτοςεἰς τοὺς αἰῶνας τῶναἰώνων. καὶ τὰ τέσσαρα ζῷαἔλεγον, Ἀμήν: καὶ οἱπρεσβύτεροι ἔπεσανκαὶ προσεκύνησαν. 

እዚህ አንቀጽ ላይ "በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም" በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለአንድ አምላክ እና ለበጉ ቀርቧል። ግን "አምልኮ" ቀርቧል የሚል ሽታው የለም። ይልቁንም በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው እና በጉን ለመለየት "ካይ" καὶ ማለትም "እና" የሚል መስተጻምር ይጠቀማል። ሲጀመር ምስጋና የተገባው ማንነት ሁሉ አምልኮ ቀረበለት ብሎ መደምደም ስህተት ነው፥ ምስጋና የሚገባው ያህዌህ ቢሆንም ለቅኖች እና በግፍ መከራን የሚቀበል ሰው እግዚአብሔርን እያሰበ ኃዘንን ቢታገሥ ምስጋና ይገባቸዋል፦
መዝሙር 18፥3  *"ምስጋና የሚገባውን ያህዌህ እጠራለሁ"*፥ ከጠላቶቼም እድናለሁ።
መዝሙር 33፥1 ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ *"ለቅኖች ምስጋና ይገባል"*።
1ኛ ጴጥሮስ 2፥19  በግፍ መከራን የሚቀበል ሰው እግዚአብሔርን እያሰበ ኃዘንን ቢታገሥ *"ምስጋና ይገባዋልና"*።

በጉ ባለጠግነት ክብር ሕይወትም ተገባው ማለት ትህትና ተገባው ማለት ነው፥ ምክንያቱም ትሕትናና ባለጠግነት፣ ክብር፣ ሕይወትም ነው፦
ምሳሌ 22፥4  *"ትሕትና እና እግዚአብሔርን መፍራት ባለጠግነት ክብር ሕይወትም ነው*።

ክብር ለነገሥታት የሚሰጥ አንድ አምላክ ነው፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ ተብሏል፦
ዳንኤል 2፥37  አንተ፥ ንጉሥ ሆይ፥ የሰማይ አምላክ መንግሥትንና *"ኃይልን፥ ብርታትንና ክብርን የሰጠህ"* የነገሥታት ንጉሥ አንተ ነህ።
ሮሜ 13፥7 ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን፥ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ *"ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ"*።

እንግዲህ ክብርና ምስጋና የሚገባቸው እነዚህ አካላት እየተመለኩ ነው ብሎ መደምደም ቂልነት ነው። ሲቀጥል አንድ ነቢይ ከአንዱ አምላክ ጋር ምስጋና ክብር ተቀበለ ማለት ያን ነቢይ መመለክ ይገባዋል ብሎ ድምዳሜ ላይ መድረስ ከተቻለ ዳዊት ተመላኪ ነበር ማለት ነው፦
1 ዜና 29፥20 ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ፦ አምላካችሁን ያህዌህን ባርኩ፡ አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባታቸውን አምላክ ያህዌህን ባረኩ፥ *"ራሳቸውንም አዘንብለው ለያህዌህ እና ለንጉሡ ሰገዱ"*።

ጉባኤውን ሁሉ ራሳቸውንም አዘንብለው ለያህዌህ እና ለንጉሡ ሰገዱ ማለት ዳዊት ከያህዌህ ጋር ተሰግዶለታል። እና ዳዊት አምልኮ ተቀብሏልን? አይ፦ "ስግደት የአምልኮ ክፍል እንጂ ስግደት በራሱ አምልኮ አይሆንም፥ ለያህዌህ የባሕርይ ሲሆን ለዳዊት የጸጋ ነው" ከተባለ እንግዲያውስ ምስጋና ክብር የአምልኮ ክፍል እንጂ ምስጋና ክብር በራሱ አምልኮ አይሆንም፥ ለያህዌህ የባሕርይ ምስጋና ክብር ሲሆን ለበጉ የጸጋ ምስጋና ክብር ነው።
ሢሰልስ "ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱለት" ይላል፥ ሽማግሌዎቹም ወድቀው የሰገዱት ለአብና ለወልድ ቢሆን ኖሮ "ሰገዱላቸው" ይባል ነበር። ነገር ግን ሽማግሌዎቹም ወድቀው የሰገዱት ለበጉ ሳይሆን በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለእግዚአብሔር ነው፦
ራእይ 19፥4 ሀያ *"አራቱም ሽማግሌዎችና አራቱ እንስሶች በፊታቸው ተደፍተው በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለእግዚአብሔር፦ አሜን፥ ሃሌ ሉያ፡ እያሉ ሰገዱለት"*።
ራእይ 4፥10 *"ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ*።
ራእይ 11፥16 በእግዚአብሔርም ፊት በዙፋኖቻቸው የተቀመጡ *"ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር እየሰገዱ"*፡

ሲያረብብ በጉ መጥቶ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ከእግዚአብሔር መጽሐፍ መቀበሉ በራሱ በጉ እና በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው ሁለት የተለያዩ ምንነት እና ማንነት ናቸው፦
ራእይ 5፥7 *"መጥቶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠ ከዚያ ከቀኝ እጁ መጽሐፉን ወሰደው"*።
ራእይ 5፥13 *"በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው እና καὶ ለበጉ"* ይሁን ሲሉ ሰማሁ።

"ካይ" καὶ ማለት "እና" ማለት ሲሆን ይህ መስተዋድድ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው እና በጉን ሁለት ማንነቶች እንደሆኑ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው። በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው ምንነቱ ጌታ አምላክ መባሉ ኢየሱስ ደግሞ በግ መባሉ ሁለት ምነነቶች እንደሆኑ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፦
ራእይ 21፥22 *"ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እና በጉ መቅደስዋ ናቸውና"* መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም።

ልብ አድርግ "ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ" እና "በጉ" ሁለት ማንነት እንደሆኑ ለማሳየት "ናቸው" በሚል የብዜት አያያዥ ግስ ተቀምጧል፥ በተጨማሪም "እና" በሚል መስተጻምር ተለይተዋል። ስለዚህ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ" እና "በጉ" ሁለት ኑባሬ ናቸው። እንደ ባይብሉ በግ የሚታረድ ስጋ ስለሆነ ስጋ ደግሞ አምልኮ አይገባው። በነገራችን ላይ "በግ" የሚለውን ተርም እኛ ሙሥሊሞች አንቀበለም። ዋናው ነጥባችን ኢየሱስ አምልኮ አይገባውም ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዒሣ አይመለክም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

17፥81በልም *«እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»* وَقُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ ۚ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا

ሚሽነሪዎች እኛ ሙሥሊሞች ክርስትና ላይ ላስነሳነው ስሙር ሙግት የልብ ፍልጠት፣ የራስ ምታት፣ የሆድ ቁርጠት፣ የጎን ውጋት እና የእግር ቁርጥማት ይዟቸው እንደሆነ እልሃቸው ያሳብቅባቸዋል። 
ከእነዚህ ኃሳውያንና ነውጠኞች መካከል ክርስቲያን ፕሪንስ፦ “ዒሣ በቁርኣን ይመለካል” እያለ ቧጦና ሟጦ ያቅሙን ሲፍጨረጨር እናያለን፥ እስቲ ለዚህ ድምዳሜ አደረሰኝ ያለውን አንቀጽ በሰከነና በሰላ አእምሮ እንመልከት፦
9፥31 *ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊያመልኩ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን፣ ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፥ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም*፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው፡፡ اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا إِلَـٰهًا وَاحِدًا ۖ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ سُبْحَانَهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ

ክርስቲያን ፕሪንስ ይህንን አንቀጽ፦ "ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን ከአላህ እና ከመርየምን ልጅ ከአልመሲሕንም ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ" ብሎ ዒሣ ከአላህ ጋር እንደሚመለክ ለማሳየት ይሞክራል። እንደዛ ለማለት "አላህ" ከሚለው ቃል በፊት "ሚን ዱኒ" مِّن دُونِ ማለትም "ከ እና ሌላ" የሚለው መስተዋድድ የያዘ ቃል "ወ" وَ ከሚለው መስተጻምር በኃላ "ሚን ዱኒ" مِّن دُونِ የሚለው መስተዋድድ የያዘ ቃል ለዒሣ ገብቶ "ወሚን ዱኒል መሢሕ" وَمِّن دُونِ الْمَسِيح
መሆን ነበረበት። በጥቅሉ እንደ እርሱ ምኞት፦
اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّه وَمِّن دُونِ َالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَم
መሆን ነበረበት፥ ይህ ደግሞ አልሆነም። ለማንኛውም ተመሳሳይ ሰዋስው እስቲ እንመልከት፦
65፥4 *"እነዚያም ከሴቶቻቸው ከአደፍ ያቋረጡት ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሦስት ወር ነው፡፡ እነዚያም ገና አደፍን ያላዩት እንዲሁ፡፡ የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው ከእርግዝናቸውን እስከ መውለድ ነው፡፡ አላህንም የሚፈራ ሰው ከነገሩ ሁሉ ለእርሱ መግራትን ያደርግለታል፡፡ وَاللَّائِي يَئِسْنَ مِنَ الْمَحِيضِ مِن نِّسَائِكُمْ إِنِ ارْتَبْتُمْ فَعِدَّتُهُنَّ ثَلَاثَةُ أَشْهُرٍ وَاللَّائِي لَمْ يَحِضْنَ ۚ وَأُولَاتُ الْأَحْمَالِ أَجَلُهُنَّ أَن يَضَعْنَ حَمْلَهُنَّ ۚ وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَل لَّهُ مِنْ أَمْرِهِ يُسْرًا

"እነዚያም ከሴቶቻቸው ከአደፍ ያቋረጡት" وَاللَّائِي يَئِسْنَ مِنَ الْمَحِيضِ مِن نِّسَائِكُمْ
የተባሉት ያረጡ ሴቶች"Menopause" ምናልባት ካረገዙ ተብሎ ቢጠረጠር የዒዳህ ጊዜ ሦስት ወር ነው፥ “ዒዳህ” عِدَّة ማለት ሁለት ጥንዶች ከተጋቡ በኃላ ተራክቦ አድርገው ከዚያም አለመግባባት ቢፈጠር ፍቺ ለማድረግ ቢያስቡ ቅድሚያ ነፍሰ-ጡር መሆኗን ለማረጋገጥ የሚቆይበት የሦስት ወር ጊዜ ቆይታ ነው። በመቀጠል "ወ" وَ በሚል አያያዥ መስተጻምር በመጠቀም የዒዳህ ጊዜ ሦስት ወር የሚለው "እነዚያም ገና አደፍን ያላዩት" وَاللَّائِي لَمْ يَحِضْنَ
የተባሉትንም እንደሆነ ለማሳየት ገብቷል፥ "እነዚያም ገና አደፍን ያላዩት" የተባሉት ለዐቅመ-ሐዋ ደርሰው ተራክቦ አድርገው ግን የወር አበባ መምጣቱ ካልታየ ለእነርሱም የዒዳህ ጊዜ ሦስት ወር ነው።
በተመሳሳይ ሰዋስው፦ "ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ" اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ
ካለ በኃላ በመቀጠል "ወ" وَ በሚል አያያዥ መስተጻምር በመጠቀም "ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ" የተባለው በተጨማሪ "የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም" وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَم
እንደሆነ ለማሳየት ገብቷል።
ስለዚህ መልእክቱ፦ "እነዚያም ከሴቶቻቸው ከአደፍ ያቋረጡት እና እነዚያም ገና አደፍን ያላዩት ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሦስት ወር ነው" ማለት ከሆነ በተመሳሳይም፦ "ሊቃውንቶቻቸውን እና መነኮሳታቸውን የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ" ይሆናል።
ሁለተኛው ዒሣ ነቢይ እንደሚሆን በእናቱ አንቀልባ እያለ ተናግሯል፦
19፥30 ሕፃኑም አለ «እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ፡፡ *”መጽሐፍን ሰጥቶኛል፥ ነቢይም አድርጎኛል”*፡፡» قَالَ إِنِّي عَبْدُ اللَّهِ آتَانِيَ الْكِتَابَ وَجَعَلَنِي نَبِيًّا

ለማንም ነቢይ አላህ መጽሐፍንና ጥበብን ነቢይነትንም ሊሰጠውና ከዚያም ለሰዎች «ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ኾኑ» ሊል አይገባውም፦
3፥79 *ለማንም ሰው አላህ መጽሐፍንና ጥበብን ነቢይነትንም ሊሰጠውና ከዚያም ለሰዎች «ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ኾኑ» ሊል አይገባውም*፡፡ مَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُؤْتِيَهُ اللَّهُ الْكِتَابَ وَالْحُكْمَ وَالنُّبُوَّةَ ثُمَّ يَقُولَ لِلنَّاسِ كُونُوا عِبَادًا لِّي مِن دُونِ اللَّهِ

ሁልጊዜም ከአምልኮ ጋር በተያያዘ "ሚን ዱኒ" مِن دُونِ የሚለው መስተዋድድ የሚገባው ለአላህ ብቻ ነው፦
5፥116 አላህም፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! አንተ ለሰዎቹ፡- *እኔን እና እናቴን "ከአላህ ሌላ" አምላኮች አድርጋችሁ ያዙ ብላሃልን?»* በሚለው ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ قَالَ اللَّهُ يَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ أَأَنتَ قُلْتَ لِلنَّاسِ اتَّخِذُونِي وَأُمِّيَ إِلَـٰهَيْنِ مِن دُونِ اللَّه

እዚህ አንቀጽ ላይ ዒሣ እኔነቱ ከአላህ ሌላ ማንነት ሆኖ ቁጭ ብሏል። "ሚን ዱኒ" مِن دُونِ ውስጥ እርሱም እናቱም አልተካተቱም። ከዚያ ይልቅ ነቢይ እንደመሆኑ መጠን አላህ እንዲናገር ያዘዘው ቃል፦ "ጌታዬን እና ጌታችሁን አላህን አምልኩ" ነው፦
117 «በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል፦ *"ጌታዬን እና ጌታችሁን አላህን አምልኩ" ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም"*፡፡ በውስጣቸውም እስካለሁ ድረስ በእነርሱ ላይ መስካሪ ነበርኩ፡፡ በወሰድከኝም ጊዜ አንተ በእነርሱ ላይ ተጠባባቂ ነበርክ፡፡ አንተም በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ ነህ፡፡» مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَا أَمَرْتَنِي بِهِ أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ ۚ وَكُنتُ عَلَيْهِمْ شَهِيدًا مَّا دُمْتُ فِيهِمْ ۖ فَلَمَّا تَوَفَّيْتَنِي كُنتَ أَنتَ الرَّقِيبَ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنتَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ

ስለዚህ ዒሣ በቁርኣን ይመለካል ብሎ መዳከር ሰማይን እንደመቧጠጥ ነው አትልፋ፥ እንደ ጓያ ነቃይ የፍለፊቱን አትውሰድ! በጥልቀት አጥና። አየህ ሐሰት በእውነት ፊት እሳት የነካው ሰም፣ ጸሐይ ያየው ቅቤ፣ ነፋስ የጎበኘው አቧራ ይሆናል፦
17፥81በልም *«እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»* وَقُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ ۚ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሙግት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥125 *"ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃት እና በመልካም ግሳጼ ጥራ፡፡ በዚያችም እርሷ መልካም በኾነችው ዘዴ ተሟገቷቸው"*፡፡ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ቅን የኾኑትን ሰዎች ዐዋቂ ነው፡፡ ادْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ ۖ وَجَادِلْهُم بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِ ۖ وَهُوَ أَعْلَمُ بِالْمُهْتَدِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ተሟገቷቸው" ለሚለው ቃል የገባው "ጃዲልሁም" جَادِلْهُمْ ሲሆን "ጃደሉ" جَٰدَلُ ማለትም "ተሟገተ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ነው። "ጀደል" جَدَل ማለት "ሙግት"argument" ማለት ነው። "ዳዒ" دَاعِى ማለት "ጠሪ" ማለት ሲሆን "ደዕዋህ" دَعْوَة ማለት ደግሞ "ጥሪ" ማለት ነው። አንድ ዳዒ ዳዕዋው መልካም ሙግት መሆን አለበት፥ ይህ ሙግት መልካም ሙግት የሚሆነው በብልሃት እና በመልካም ግሳጼ ወደ አላህ ሰዎችን ሲጠራ ነው። "ሒክማህ" حِكْمَة የሙግት "ጥበብ" ሲሆን "መውዒዛህ" مَّوْعِظَة ደግሞ የሙግት "መርሕ" ነው። ለሙግት ጥበብ ዐቅል ወሳኝ ነጥብ ነው፥ “ዐቅል” عقل ማለት “ግንዛቤ”Metacognition” ማለት ሲሆን አላህ በቁርአን “ለዐለኩም ተዕቂሉን” لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُون ይለናል፦
2፥242 እንደዚሁ አላህ አንቀጾቹን *ትገነዘቡ ዘንድ* ለእናንተ ያብራራላችኋል፡፡ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمْ ءَايَٰتِهِۦ لَعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

ለሙግት መርሕ ደግሞ ነቅል ወሳኝ ነጥብ ነው፥ “ነቅል” نفل ማለት “ወሕይ” وَحْى ማለት ነው፤ ለዚህም አምላካችን አላህ፦ “አፈላ ተዕቂሉን” أَفَلَا تَعْقِلُون ይለናል፦
21:10 *ክብራችሁ በውሥጡ ያለበትን መጽሐፍ ወደ እናንተ በእርግጥ አወረድን፤ አትገነዘቡምን*? لَقَدْ أَنزَلْنَآ إِلَيْكُمْ كِتَٰبًۭا فِيهِ ذِكْرُكُمْ ۖ أَفَلَا تَعْقِلُونَ

የሙግት ነጥብ"premise" አቅርቦ ለመሞገትና ለመሟገት ዐቅልም ሆነ ነቅል ያስፈልጋል። ቁርኣንን ዳዕዋህ አድርጎ ለመሞገትና ለመሟገት ቁርኣን የወረደበትን ቋንቋ፣ ሰዋስው፣ ዐውድ፣ ተዛማች ቃላት(text) እና ሰበቡ አን-ኑዙል መረዳት ግድ ይላል። ሺዐህ የሚባሉት ራፊዳህ ቁርኣንን የሚተረጉሙበት መንገድ "ባጢን" ْبَاطِن ማለትም "ስውር ትርጉም"esoteric" ይባላል። ይህ አፈሣሰር ቁርኣን የወረደበትን ዐውድ፣ ቋንቋ፣ ሰዋስው፣ ተዛማች ቃላት(text) እና ሰበቡ አን-ኑዙል ያማከለ ሳይሆን “ተእዊል” تَأْوِيل ማለት “ትርጉም” በመስጠት መተርጎ ነው። ቁርኣን የወረደበትን ዐውድ፣ ቋንቋ፣ ሰዋስው፣ ተዛማች ቃላት(text) እና ሰበቡ አን-ኑዙል ያማከለ አፈሳሰር "ዛሂር" ظَّاهِر ማለትም "ግልፅ ትርጉም"exoteric" ይባላል።
የዛሂር አፈሣሰር የቁርኣንን መሠረትና ውቅር፣ ዋልታና ማገር፣ ጥልቀትና ስፋት፣ ድርና ማግ ለመረዳት ጉልህ ሚና አለው። የዛሂር አፈሣሰር አውታር፣ ምህዋር እና ምህዳር ዐረቢኛ ነው፥ ዐረቢኛ ለቁርኣን ግንባዜ እንደ እንሾሽላ መዋቢያ፣ እንደ ኩል መኳያ፣ እንደ ሽቶ ለመሸተት እና ለሙያዊ ቃላት ቅመራ ግብዐት ነው፦
43፥3 *እኛ ታውቁ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን አደረግነው*፡፡ إِنَّا جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

ለምሳሌ ባጢኒያህ “የድ” يَد ማለትም "እጅ" የሚለው ቃል ሁልጊዜ "ኃይል" በሚል ይተረጉሙታል፥ ግን "እጅ" የአላህን ህላዌ ባሕርይ ለማመልከት መጥቷል፦
38፥75 አላህም «ኢብሊስ ሆይ! *በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት* ከመስገድ ምን ከለከለህ? አሁን ኮራህን? ወይስ ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?» አለው፡፡ قَالَ يَٰٓإِبْلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسْجُدَ لِمَا خَلَقْتُ بِيَدَىَّ ۖ أَسْتَكْبَرْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ ٱلْعَالِينَ

“የደየ” ِيَدَىَّ ማለት ሙተና”dual” ነው፥ ይህንን ቃል “ኃይል” ብለን እንዳንተረጎግም ቋንቋው አይፈቅድልንም። ምክንያቱም ሁለት “ኃይል” የሚባል ቃል ትርጉም አልባ ነውና። ባይሆን የአላህ እጅ ከፍጡራን እጅ ጋር ሳናመሳስል መቀበል ነው፦
48፥10 እነዚያ ቃል ኪዳን የሚጋቡህ ቃል ኪዳን የሚጋቡት አላህን ብቻ ነው፡፡ *"የአላህ እጅ ከእጆቻቸው በላይ ነው"*፡፡ إِنَّ ٱلَّذِينَ يُبَايِعُونَكَ إِنَّمَا يُبَايِعُونَ ٱللَّهَ يَدُ ٱللَّهِ فَوْقَ أَيْدِيهِمْ 

የአላህ እጅ ከእጆቻቸው በላይ ነው ማለት የአላህ እጅ ከፍጡራን እጆች ተለይቶ የበላይ ነው ማለት ነው። ይህንን ያለ ተክይፍ፣ ያለ ተምሢል፣ ያለ ተዕጢል እና ያለ ተሕሪፍ የአላህ ንግግር ላይ በተቀመጠው መሠረት መቀበል ብቻ "ተፍዊድ" تفويض ይባላል። ተፍዊድ የቀደምት ሰለፎች የተረዱበትን "ቢላ ከይፈ" بلا كيف‎ ማለትም "ያለ እንዴትነት" መረዳት ነው። የሙዕተዚላህ አብነት"School of theology" ልክ እንደ ራፊዳህ ባጢን አፈሣሰር ቢኖራቸው የማቱሪዲያህ አብነት እና የአሽዐሪያህ አብነትሽ ከባጢንም ከዛሂርም አፈሣሰር ይጠቀማሉ።

ለኢሥላም ዘብ እና አበጋዝ የሆኑ ዐቃቢያነ ኢሥላም የሚባሉት ሙሥሊም ምሁራን ለኢሥላም ዐቅብተ እምነት የዛሂርን አፈሣሰርን ተመራጭ አርገው ሰሟገቱ ፍሬአማ ሆነዋል።
"ዐቅብተ እምነት" ማለት "የእምነት ጥበቃ" ወይም "የእምነት ዘብ" ማለት ነው፥ በዚህ መስክ የተሰማሩ ደግሞ ተባታይ ከሆነ "ዐቃቤ እምነት" አንስታይ ከሆነች "ዐቃቢት እምነት" ትባላለች። "ዐቃቢያን" ደግሞ የዐቃቤ ብዙ ቁጥር ነው። "አፓሎጄቲክስ"Apologetics" የሚለው የኢንግሊሹ ቃል "አፓሎጂአ" ἀπολογία ማለትም "መከላከል" ከሚለው ከግሪክ ኮይኔ ቃል የመጣ ነው። ለኢሥላም ዘብ እና አበጋዝ የሆኑ ሙሥሊሞች ዐቃቢያነ ኢሥላም ይባላሉ።
የዐውድ፣ የቋንቋ፣ የሰዋስው እና የተዛማች ሙግት አፈሣሠር “ተፍሢር ቢ አር-ረእይ” التفسير بالرأي‎ ወይም “አት-ተፍሢር ቢ አድ-ዲራያህ” التفسير بالدراية‎ ይባላል። በአል-በይዷዊይ የተዘጋጀው አንዋረል ተንዚል እና በኢማም ፈኽሩል ዲኑል ራዚ የተዘጋጀው መፋቲሑል ገይብ በዚህ አፈሣሠር ተመራጭ ነው።
የሰበቡ አን-ኑዙል አፈሣሠር ነቢያችን”ﷺ” እና ሶሓባዎች በአስተላለፉት መረዳት “አት-ተፍሢር ቢል መእሱር” التفسير بالمأثور‎ ወይም “አት-ተፍሢር ቢ አር-ሪዋያህ” التفسير بالرواية‎ ይባላል። በኢብኑ ጀሪር አጥ-ጠበሪ የተዘጋጀው ተፍሢሩል ጃሚል በያን እና በኢብኑ ከሲር የተዘጋጀው ተፍሢሩል ቁርኣን አል-ዚዙም በዚህ አፈሣሰር ተመራጭ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፈጣሪ ፆታ አለውን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

42፥11 *የሚመስለው ምንም ነገር የለም*፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِۦ شَىْءٌۭ ۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ

ፈጣሪአችን አላህ የሚመስለው ምንም ሆነ ማንም የለም፥ ፍጡራንም እርሱን አይመስሉትም፤ አላህም ከፍጡራን ጋር የማይመሳሰል የራሱ ስምና ባህርይ አለው፤ ይህንን ስምና ባህርይ ከፍጡራን ጋር ሳናመሳስልና ሳናወዳድር እራሱ ዕውቅና በመሰጠበት መሠረት እንቀበላለን፦
42፥11 *የሚመስለው ምንም ነገር የለም*፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِۦ شَىْءٌۭ ۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ
112፤4 *ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም*፡፡ وَلَمْ يَكُن لَّهُۥ كُفُوًا أَحَدٌۢ

አላህ ፈጣሪ ነው ፍጡርን አይመስልም ከተባለ ታዲያ ለምንድን ነው በቁርአን እራሱ "እርሱ" እና "አንተ" በሚል ተባዕታይ ፆታ የሚጠራው? ለሚለው ጥያቄ መልሱ አምላካችን አላህ ቁርኣንን ዐረቢኛ በማድረግ በዐረቢኛ ሰዋስው አውርዶታል፦
43፥3 *እኛ ታውቁ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን አደረግነው*፡፡ إِنَّا جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
12፥2 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው*። إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

"አን-ነሕው" النحو ማለት "ሰዋስው" ማለት ሲሆን "ጅንስ" جنس ማለት ደግሞ "ፆታ" ማለት ነው፥ የሰዋስው ፆታ በሁለት ይከፈላል፤ አንዱ "ሙዘከር" مذكر ማለትም "ተባታይ"masculine" ሲሆን ሁለተኛው "ሙዐነስ" مؤنث ማለትም "አንስታይ"feminine" ነው፤ ከዚህ ውጪ ልክ እንደ ኢንዶ-ኤሮፕያን ሰዋስው ግዑዝ ፆታ"neutral gender" የሚባል ዐረብኛ ሰዋስው ውስጥ የለም። ታዲያ ፆታ የሌላቸው ማንነት ሆነ ምንነት ምን ብለን እንጠራቸዋለን? ከተባለ አሁንም ለዐረቢኛው ሰዋስው መድረኩን መልቀቅ ነው። አሁንም በዚሁ የሰዋስው ሙግት ስንሄድ ከሁለቱም ማለትም ከሴትና ወንድ ፆታ ውጪ ያለ ማንነት ሆነ ምንነት ሲሆን "ሙፍረድ" مفرد ማለትም ነጠላ"singular" ከሆነ ተባታይ በሆነው በሦስተኛ መደብ “ሁወ” هُوَ ማለትም "እርሱ" የሚለውን እና በሁለተኛ መደብ “አንተ” أَنْتَ ማለትም "አንተ" የሚለውን ተውላጠ-ስም እንጠቀማለን።
ለምሳሌ "ዋሒድ" وَٰحِد ማለት "አንድ" ማለት ሲሆን ተዕባታይ መደብ ነው።
ከአንድ በላይ የሆነ ማንነት ሆነ ምንነት “ጀመዕ” جمع ማለትም "ብዜት"plurar" ከሆኑ አንስታይ በሆነው በሦስተኛ መደብ "ሂየ” هِيَ ማለትም "እርሷ" የሚለውን እና በሁለተኛ መደብ "አንቲ" أنتِ ማለትም "አንቺ" የሚለውን ተውላጠ-ስም እንጠቀማለን።
ለምሳሌ "ሰላሳህ" ثَلَٰثَة ማለትም "ሦስት" አንስታይ ናት፦
4፥171 *”እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ”*፡፡ .. *”«ሦስት ናቸው» አትበሉም”*፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ *”አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው”*፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ ۖ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ ۖ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ ۚ ٱنتَهُوا۟ خَيْرًۭا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا ٱللَّهُ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ سُبْحَٰنَهُۥٓ أَن يَكُونَ لَهُۥ وَلَدٌۭ ۘ لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًۭا

ልብ አድርግ አላህ አንድ ስለሆነ "ዋሒድ" ብለክ "ሁወ" እንጂ "ሂየ" አትልም። የሚያጅበው "ሰላሳ" ثَلَٰثَة በሚለው ቃል መጨረሻ ላይ "ታ" ة የሚባለው "ታእ-መርቡጧ" تاء مربوطة መሆኑ በራሱ ቃሉን አንስታይ ያደርገዋል። ለምሳሌ “መለክ” مَلَك ማለትም “መልአክ” በነጠላ ሙዘከር ነው፥ ነገር ግን በብዜት "መላኢካ-ህ" مَلَائِكَة ማለትም "መላእክት" ሙዐነስ ነው። "መላኢካ" በሚለው መድረሻ ቅጥያ ላይ ያለች "ታ" ة የምትባለው "ታእ-መርቡጧህ" ሙዐነስ ናት፥ ለዚያ ነው እዚህ አንቀጽ ላይ፦ "ናዘት" نَادَتْ ማለትም "ጠራች" የሚል ያለው፦
3፥39 እርሱም በጸሎት ማድረሻው ክፍል ቆሞ ሲጸልይ መላእክት፦ «አላህ በየሕያ ከአላህ በኾነ ቃል የሚያረጋግጥ ጌታም ድንግልም ከደጋጎቹ ነቢይም ሲኾን ያበስርሃል» በማለት *"ጠሩት"*፡፡ فَنَادَتْهُ الْمَلَائِكَةُ وَهُوَ قَائِمٌ يُصَلِّي فِي الْمِحْرَابِ أَنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكَ بِيَحْيَىٰ مُصَدِّقًا بِكَلِمَةٍ مِّنَ اللَّهِ وَسَيِّدًا وَحَصُورًا وَنَبِيًّا مِّنَ الصَّالِحِينَ

"ጠሩት" ለሚለው ቃል "ናዘት-ሁ" َنَادَتْهُ መሆኑን አንስታይ መሆኑን ያሳያል፥ "ቃለ" قَالَ ማለት "አለ" ማለት ሲሆን ተባዕታይ ነው፥ “ቃለት” قَالَت ደግሞ "አለች" ማለት ሲሆን አንስታይ ነው። ይህ ቃል ለመላእክት ጥቅም ላይ ውሏል፦
3፥42 *”መላእክትም ያሉትን”* አስታውስ፡፡ «መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሸ፡፡ አነጻሽም፡፡ በዓለማት ሴቶችም ላይ መረጠሽ፡፡» وَإِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَاكِ وَطَهَّرَكِ وَاصْطَفَاكِ عَلَىٰ نِسَاءِ الْعَالَمِينَ
"ያሉት" ለሚለው “ቃለት” قَالَت በሚል መምጥቷል፥ "ቃለ" በሚለው መድረሻ ቅጥያ ላይ ያለች "ታ" ت "ታእ-መፍቱሓህ" تاء مفتوحة የምትባለው ሙዐነስ ናት፥ ስለዚህ "ቃለት" የሚለው “ቃሉ” قَالُوا ማለትም "አሉ" ለማለት ተፈልጎ ነው፦
2፥30 ጌታህ ለመላእክት፡- «እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ፤» ባለ ጊዜ የኾነውን አስታውስ፤ *”እነርሱም”*፦ «እኛ ከማመስገን ጋር የምናጠራህ ላንተም የምንቀድስ ስንኾን በርሷ ውስጥ የሚያጠፋንና ደሞችንም የሚያፈስን ታደርጋለህን?» *”አሉ”*፡፡ አላህ «እኔ የማታውቁትን ነገር አውቃለሁ» አላቸው፡፡ وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي جَاعِلٌ فِي الْأَرْضِ خَلِيفَةً ۖ قَالُوا أَتَجْعَلُ فِيهَا مَن يُفْسِدُ فِيهَا وَيَسْفِكُ الدِّمَاءَ وَنَحْنُ نُسَبِّحُ بِحَمْدِكَ وَنُقَدِّسُ لَكَ ۖ قَالَ إِنِّي أَعْلَمُ مَا لَا تَعْلَمُون

እዚህ አንቀጽ ላይ "አሉ" ለሚለው “ቃሉ” قَالُوا ማለቱን አስተውል። መላእክት ፆታ የሌላቸው ሴትም ወንድም አይደሉም። ለምን በአንስታይ መደብ ተጠቀመ? ስልን መላእክት ብዙ ማንነቶች ስለሆኑ ሲሆን አላህ ደግሞ አንድ ማንነት ስለሆነ በተባታይ መደብ "እርሱ" "አንተ" "አለ" ተብሎ ተገልጿል።

እሩቅ ሳንሄድ በዐረቢኛ ድምጽ ያላቸው ተነባቢ ፊደላት”sound letters” 28 ሲሆኑ ከእነርሱ ውጥስ 14 ሐርፎች "ሑሩፉል ቀመሪያህ"lunar letters" ተባታይ ናቸው፣ እነርሱም፦
ء ﺏ ﺝ ﺡ ﺥ ﻉ ﻍ ﻑ ﻕ ﻙ ﻡ ﻭ ﻱ ه
የቀሩት 14 ሐርፎች "ሁሩፉ አሽ-ሸምሲያህ"solar letters" አንስታይ ናቸው፣ እነርሱም፦
ﺕ ﺙ ﺩ ﺫ ﺭ ﺯ ﺱ ﺵ ﺹ ﺽ ﻁ ﻅ ﻝ ﻥ
ያ ማለት አስራ አራቱ ቀመሪያህ ሙዘከር ስለሆኑ ወንዶች ናቸውን? አስራ አራቱ ሸምሲያህ ሙዐነስ ስለሆኑ ሴቶች ናቸውን? መልሱ አይ ይህ የዐረቢኛ ሰዋስው ላይ የተለመደ ነው። ፀሐይ "ሂየ” هِيَ ትባላለች፥ ጨረቃ ደግሞ “ሁወ” هُوَ ይባላል፤ እና ፀሐይ ሴት ጨረቃ ወንድ ነውን? ፀሐይ በአንስታይ መደብ ነው የተጠራችው፦
81፥1 *"ፀሐይ "በተጠቀለለች" ጊዜ"*። إِذَا الشَّمْسُ كُوِّرَتْ

"ተጠቀለለች" ለሚለው ቃል የገባው "ከወረት" كُوِّرَتْ የሚለው ሙዐነስ እንጂ "ከወረ" كُوِّرَ የሚለው ሙዘከር አይደለም፦
75፥8 *"ጨረቃም "በጨለመ" ጊዜ"*፡፡ وَخَسَفَ الْقَمَر

"ጨለመ" ለሚለው ቃል የገባው "ኸሠፈ" خَسَفَ የሚለው ሙዘከር እንጂ "ኸሠፈት" خَسَفَتْ የሚለው ሙዐነስ አይደለም።
ስለዚህ አላህ "አንተ" እና "እርሱ" ስለተባለ ፈጣሪ ፆታ አለው ብሎ መደምደም ስህተት ነው። ባይሆን በባይብል እግዚአብሔር ፆታ ከሌለው ወንድም ሴትም ካልሆነ ለምን "አንተ" እና "እርሱ" እንደሚባል የቤት ሥራ ሰጥተናችኃል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መርየም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥116 አላህም፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! አንተ ለሰዎቹ፡- *እኔን እና እናቴን ከአላህ ሌላ አምላኮች አድርጋችሁ ያዙ ብለሃልን?*» በሚለው ጊዜ አስታውስ ፡፡ وَإِذْ قَالَ اللَّهُ يَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ أَأَنتَ قُلْتَ لِلنَّاسِ اتَّخِذُونِي وَأُمِّيَ إِلَـٰهَيْنِ مِن دُونِ اللَّهِ

አላህ ዒሳን እዲናገር ያዘዘው ቃል፦ “አላህ ጌታዬ ጌታችሁ ነው፤ በብቸኝነት አምልኩት” የሚል ሲሆን ነገር ግን ነሳራዎች እርሱ እና እናቱን ከአላህ ሌላ አምላክ አድርገው ይዘዋል፤ “አምላክ አድርጎ መያዝ” ምን ማለት ነው? አንድ ሰው አንድ ነገር አምላክ አርጎ ያዘ ማለት ለአምላክ የሚሰጠውን የአምልኮ ክፍል ለሌላ ማንነት ሆነ ምንነት መስጠትን ያመለክታል፤ ለምሳሌ አንድ ሰው ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ ያዘ ማለት ፍላጎቱን አምላኬ ብሎ ጠራ ማለት ሳይሆን ለአምላክ የሚሰጠውን የአምልኮ ክፍል ለፍላጎቱ ቅድሚያ ሰጠ ማለት ነው፦
25፥43 *ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን?* አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትሆናለህን? أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا

ሰዎች ከአላህ ሌላ አምላክ አድርገው የያዙት ዒሳን እና እናቱን ብቻ ሳይሆን የእርሱ ባሮች የሆኑትንም መላእክት እና ነብያትንም ጭምር ነው፦
18፥102 እነዚያ የካዱት *ባሮቼን ከእኔ ሌላ አማልክት አድርገው መያዛቸውን* የማያስቆጣኝ አድርገው አሰቡን? እኛ ገሀነምን ለከሓዲዎች መስተንግዶ አዘጋጅተናል أَفَحَسِبَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ أَن يَتَّخِذُوا۟ عِبَادِى مِن دُونِىٓ أَوْلِيَآءَ ۚ إِنَّآ أَعْتَدْنَا جَهَنَّمَ لِلْكَٰفِرِينَ نُزُلًۭا ፡፡
3:80 *መላእክትንና ነቢያትንም አማልክቶች አድርጋችሁ እንድትይዙ* ሊያዛችሁ አይገባዉም፤ እናንተ ሙስሊሞች ከሆናችሁ በኋላ በክሕደት ያዛችኋልን? وَلَا يَأْمُرَكُمْ أَن تَتَّخِذُوا الْمَلَائِكَةَ وَالنَّبِيِّينَ أَرْبَابًا ۗ أَيَأْمُرُكُم بِالْكُفْرِ بَعْدَ إِذْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

ይህንን ከተረዳን “ኢላሀይኒ” إِلَٰهَيْنِ ለኢሳ እና ለመርየም በሙተና የገባ ነው፤ በሙፍረድ ሲሆን ደግሞ “ኢላህ” إِلَٰه ማለትም “የሚመለክ” ማለት ነው፣ “አምልኮ” የሚለው ቃል “መለከ” ማለትም “ገዛ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ለምንነት መገዛት” ማለት ነው። ከሣቴ ብርሃን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት (2005) ገጽ 708)

አምልኮ በውስጡ ልመና፣ ስግደት፣ ስለት መሳል እጣን ማጨስ መስዋዕት ማቅረብ ይይዛል። “አምላክ” የሚለውም ቃል “መለከ” ከሚል ስርወ ቃል መምጣቱ አንባቢ ልብ ይለዋል። ሰውን በአካል ማየት፣ መስማት፣ መናገር እስከቻለ ድረስ ማነጋገሩ ተፈጥሯዊ ነው፣ ነገር ግን የሚያይበት አይን፣ የሚሰማበት ጆሮ፣ የሚናገርበት አፍ፣ የሚያውቅበት አንጎል በሞት ጊዜ ስለሚፈራርሱ አይሰማም፣ አይናገርም፣ አያይም፣ ዐያውቅም።
በክርስትና ማለትም ካቶሊክ፣ ኦርቶዶክስና አንግሊካል ወደ ማርያም ጥሪ፣ ልመና፣ መተናነስ፣ መጎባደድ ይደረጋል፣ ስለት መሳል፣ እጣን ማጨስ እና መስዋዕት ማቅረብ ይደረጋል፤ ታዲያ ማርያም በሌለችበት ይህን ማድረግ አምልኮ አይደለምን? አዎ ከተባለ እንግዲያውስ አግባብ አይደለም፤ አይ ከተባል ለምን ወደ ማርያም ይህ ሁሉ ይደረጋል? ማርያም በምኗ ትሰማለች? ታያለች? ታውቃለች? ሰውን የምትገናኝበት ህዋሳቷ አፈር ሆኖ የለ እንዴ? በሰው ልብ ያለውን መለኮት ካልሆነች እንዴት ታውቃለች? ከአላህ ሌላ ማንነት ሆነ ምንነት መለማመን፣ መጎባደድ፣ መተናነስ፣ መጥራት ሽርክ ነው፤ ምክንያቱም ሁሉንም ነገር በጊዜና በቦታ ሳይገደብ ማወቅ፣ ማየት እና መስማት የሚችል አንድ አምላክ ብቻ ነው፦
46:5 *እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልስለት ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው*። وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّن يَدْعُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَن لَّا يَسْتَجِيبُ لَهُۥٓ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ وَهُمْ عَن دُعَآئِهِمْ غَٰفِلُونَ

ማርያም በሌለችበት እንዲህ ጸሎት፣ ስግደት እና መገዛት ይቀርብላታል፦
ዚቅ ዘየካቲት ኪዳነ ምህረት ገፅ 144
“ብቻዋን ታላላቅ ብርሃናትን ለፈጠረች ለመድኃኒት ድንግል ማርያም ኑ እንስገድላት ለእርሷም እንገዛ”
መጽሐፈ ሰአታት ገፅ 31
፦ “በብርሃን ጌጥ ያጌጥሽ ወርቅ ዘቦ ግምጃን የተጎናፀፍሽ የዳዊት ልጅ እመቤታችን ተገዛንልሽ ለአንቺ እንገዛለን”
፦ “አደፍ ጉድፍ የሌለብሽ ብርሌ ካህናት የሚያሹትሽ የሽቱ ሙዳይ እመቤታችን ሆይ ተገዛንልሽ ለአንቺን ፈፅመን እንገዛለን”
፦ “የታተምሽ የውሃ ጉድጓድ የተዘጋሽ የተክል ቦታ የዳዊት ልጅ እመቤታችን ሆይ የነብያት ልጆቻቸው አንች ነሽና ተገዛንልሽ ለአንቺ ፈፅመን እንገዛለን”
፦ “በብርና በወርቅ የተሸለምሽ አዲስ የጣሪያ ዋልታ ሚስጥር ማደሪያ የዳዊት ልጅ እመቤታችን ሆይ ተገዛንልሽ ለአንቺ ፈፅመን እንሰግዳለን”

ይህ አምልኮ ካልሆነ ምን ይባላል? አላህ የትንሳኤ ቀን ከእርሱ ሌላ አምልኮ የሚደረግላቸውን አካላት እንዲህ በማለት እያወቀ ይጠይቃቸዋል፦
25፥17 *እነርሱን እና ከአላህ ሌላ የሚግገዟቸውንም የሚሰበስብባቸውን እና «እናንተ እነዚህን ባሮቼን አሳሳታችሁን ወይስ እነርሱው መንገድን ሳቱ?» የሚልበትን ቀን አስታውስ*፡፡ وَيَوْمَ يَحْشُرُهُمْ وَمَا يَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ فَيَقُولُ أَأَنتُمْ أَضْلَلْتُمْ عِبَادِي هَـٰؤُلَاءِ أَمْ هُمْ ضَلُّوا السَّبِيلَ

ነገር ግን እነዚያ ዱዓ ሲደረግላቸው የነበሩት አካላት ከአምላኪዎች ተቃራኒ በመሆን አምልኮ እንዳልተቀበሉ ይክዳሉ፦
19፥81-82 *ከአላህም ሌላ አማልክትን* ለእነርሱ መከበሪያ እንዲኾኑዋቸው *ያዙ* وَٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ ءَالِهَةًۭ لِّيَكُونُوا۟ لَهُمْ عِزًّۭا ፡፡
ይከልከሉ፤ *ማምለካቸውን በእርግጥ ይክዷቸዋል፡፡ በእነሱም ላይ ተቃራኒ ይኾኑባቸዋል* كَلَّا ۚ سَيَكْفُرُونَ بِعِبَادَتِهِمْ وَيَكُونُونَ عَلَيْهِمْ ضِدًّا ፡፡
በካቶሊክ ማርያም፦ “ሰማይ ላይ ኖራ በኃላ ስጋ የለበሰች አርያማዊት ማለትም ሰማያዊት ናት፤ ከዚያም ሞታ ሳትበሰብስ ተነስታ ወደ ሰማይ አርጋለች” ተብሎ ይታመናል፤ በኦርቶዶክስና በአንግሊካንም፦ “ሞታ ሳትበሰብስ ተነስታ ወደ ሰማይ አርጋለች” ተብሎ ይታመናል።
በ 375 AD የተነሱት ኮላደሪያን ክርስቲያኖች ማርያምን በግልጽ፦ “ቴአ” Θεία ማለትም “ሴት አምላክ” ብለው ይጥሩአት ነበር።
በ 431 AD የኤፌሶን ጉባኤ ማርያምን “ቴኦቶኮስ” Θεοτόκος ማለትም “የአምላክ እናት” ብለዋታል።
ካቶሊክ፣ ኦርቶዶስ፣ አንግሊካን ማርያምን በግሪክ “ኪርያ” κυρία ማለትም “ሴት ጌታ” ይሉአታል፣ “ኪርዮስ” κύριος ማለት “ወንድ ጌታ” ማለት ነው። በአገራችን ኦርቶዶክሶች ደግሞ “እግዚኢት” ትባላለች፤ “እግዚኢት” ማለት “ሴት ጌታ” ማለት ሲሆን “እግዚእ” ደግሞ “ወንዱ ጌታ” ማለት ነው፤ ኢየሱስን “እግዚኢነ” ማለትም “ጌታችን” እንደሚሉት ሁሉ ማርያም “እግዚኢትነ” ማለትም “ጌታችን” ይሉአታል። ከዚህ የበለጠ ማርያምን አምላክ አድርጎ መያዝ አለን? ነሳራዎች ሆይ! ዒሳን በቀጥታ መርየምን ደግሞ በተዘዋዋሪ እያመለካችሁ ትገኛላችሁ፤ እናማ በእኛ እና በእናንተ የጋራ የሆነው ቃል አንድ አምላክ ብቻ ማምለክ የሚል ነውና ከአንዱ አምላክ ሌላ ከፍጡራን ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፦
3፥64 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! *በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ እርሷም አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው*፤ በላቸው፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ تَعَالَوْا إِلَىٰ كَلِمَةٍ سَوَاءٍ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا اللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِ شَيْئًا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ ۚ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አሽ-ሻም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

21፥71 *"እርሱን(ኢብራሂም) እና ሉጥንም ወደዚያች፤ በውስጧ ለዓለማት በረከትን ወደ አደረግንባት ምድር በመውሰድ አዳን"*፡፡ وَنَجَّيْنَاهُ وَلُوطًا إِلَى الْأَرْضِ الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا لِلْعَالَمِينَ

"አሽ-ሻም" اَلـشَّـام‎ ማለት በቋንቋ ደረጃ ከሄድን "አሽ-ሸማል" الشِّمَال ማለትም "ግራ" ማለት ነው፥ ለምሳሌ የአሽ-ሻም ተቃራኒ "አል-የመን" اَلْـيَـمَـن ማለት "አል-የሚን" الْيَمِين ማለትም "ቀኝ" ማለት ነው፦
50፥17 *"ሁለቱ ቃል ተቀባዮች መላእክት ከቀኝ እና ከግራ ተቀማጮች ኾነው በሚቀበሉ ጊዜ አስታውስ"*፡፡ إِذْ يَتَلَقَّى الْمُتَلَقِّيَانِ عَنِ الْيَمِينِ وَعَنِ الشِّمَالِ قَعِيدٌ
70፥37 *"ከቀኝ እና ከግራ ክፍልፍል ጭፍሮች ሲኾኑ"*፡፡ عَنِ الْيَمِينِ وَعَنِ الشِّمَالِ عِزِينَ

የጀነት ባለቤት "አስሓቡል የሚን" أَصْحَابُ الْيَمِين ማለትም "የቀኝ ጓድ" ሲባሉ የእሳት ባለቤት "አስሓቡ አሽ-ሻማል" أَصْحَابُ الشِّمَال ይባላል፦
56፥27 *"የቀኝም ጓዶች ምንኛ የከበሩ የቀኝ ጓዶች! ናቸው"*። وَأَصْحَابُ الْيَمِينِ مَا أَصْحَابُ الْيَمِينِ
56፥41 *"የግራ ጓደኞችም ምንኛ የተዋረዱ የግራ ጓዶች! ናቸው"*፡፡ وَأَصْحَابُ الشِّمَالِ مَا أَصْحَابُ الشِّمَالِ

እንግዲህ ቀኝ እና ግራ አንጻራዊ ንግግር መሆኑን ከተረዳን ነቢያችን"ﷺ" ከሚኖሩበት በስተ ግራ ያለችው አሽ-ሻም "ሡርያኒይ" سُرْيَانِي‎ ማለትም "ሶሪያህ" ስትሆን በስተ ቀኝ ያለችው አል-የመን ደግሞ "ሠበእ" ِِسَبَإٍ ማለትም "ሳባ" ናት። ነቢያችን"ﷺ" ስለ ሻም እና የመን እንዲህ ዱዓ አርገዋል፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 49, ሐዲስ 4334
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"አላህ ሆይ! እኛን በእኛ ሻም ባርክ! አላህ ሆይ! እኛን በእኛ የመን ባርክ!"*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ اللَّهُمَّ بَارِكْ لَنَا فِي شَأْمِنَا اللَّهُمَّ بَارِكْ لَنَا فِي يَمَنِنَا
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 15, ሐዲስ 32
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ ነቢዩም"ﷺ" አሉ፦ *"አላህ ሆይ! እኛን በእኛ ሻም እና በእኛ የመን ባርክ!"*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ اللَّهُمَّ بَارِكْ لَنَا فِي شَامِنَا وَفِي يَمَنِنَا‏

አምላካችን አላህ በሳባ አገር እና በሻም አገር መካከልም ቅጥልጥል ከተሞችን አድርጓል፦
34፥18 *"በእነርሱ እና በዚያች በውስጧ በረከትን ባደረግንባት አገር (በሻም) መካከልም ቅጥልጥል ከተሞችን አደረግን"*፡፡ በእርሷም ጉዞን ወሰንን፡፡ «ጸጥተኞች ኾናችሁ በሌሊቶችም በቀኖችም ተጓዙ» አልን፡፡ وَجَعَلْنَا بَيْنَهُمْ وَبَيْنَ الْقُرَى الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا قُرًى ظَاهِرَةً وَقَدَّرْنَا فِيهَا السَّيْرَ ۖ سِيرُوا فِيهَا لَيَالِيَ وَأَيَّامًا آمِنِينَ

“ቢላድ አር-ራፊደይን” بلاد الرافدين‌‎ የተባለው ቦታ በግሪክ “ሞሶፓታሚያ” μέσοποταμία ይባላል፤ “ሜሶ” μέσος ማለት “መካከል” ማለት ሲሆን “ፓታሞስ” ποταμός ደግሞ “ወንዞች” ማለት ነው፤ በሁለቱ ወንዞች በኤፍራጥስና በጢግሮስ ወንዞች መካከል ያለውን አገር ያመለክታል፤ ይህ ቦታ በጥንት ሰመርያንና አካዳውያን ሲሆኑ በአሁኑ ኢራቅ፣ ኩዌት፣ ምስራቃዊ ሶርያ እና ደቡብ ምስራቅ ቱርክ ናቸው። ከዚህ ቦታ ኢብራሂም በስደት ወደ ሻም መጥቷል፦
37፥99 አለም፦ *«እኔ ወደ ጌታዬ ኼያጅ ነኝ*፡፡ በእርግጥ ይመራኛልና፡፡» وَقَالَ إِنِّي ذَاهِبٌ إِلَىٰ رَبِّي سَيَهْدِينِ
29፥26 ሉጥም ለእርሱ አመነ፤ ኢብራሂም «እኔ ወደ ጌታዬ ተሰዳጅ ነኝ፡፡ እነሆ እርሱ አሸናፊው ጥበበኛው ነውና» አለም፡፡ فَآمَنَ لَهُ لُوطٌ ۘ وَقَالَ إِنِّي مُهَاجِرٌ إِلَىٰ رَبِّي ۖ إِنَّهُ هُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

አላህ ኢብራሂምን እና ሉጥን ከሞሶፓታሚያ ወደ ለዓለማት በረከትን ወደሆሃነችው ወደ ሻም ማለትም ወደ ከነዓን ምድር በመውሰድ አዳናቸው፦
21፥71 *"እርሱን(ኢብራሂም) እና ሉጥንም ወደዚያች፤ በውስጧ ለዓለማት በረከትን ወደ አደረግንባት ምድር በመውሰድ አዳን"*፡፡ وَنَجَّيْنَاهُ وَلُوطًا إِلَى الْأَرْضِ الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا لِلْعَالَمِينَ

ከዚያ ኢብራሂም ልጁ እና የልጅ ልጁን በሕግ አዘዘ፥ ያዕቁብም እንደዚሁ ልጆቹን አዘዘ፥ እርሱም፦ "ልጆቼ ሆይ! አላህ ለእናንተ ሃይማኖትን መረጠ፤ ስለዚህ እናንተ ሙስሊሞች ኾናችሁ እንጂ አትሙቱ" አላቸው፦
2፥132 *"በእርሷም በሕግጋቲቱ ኢብራሂም ልጆቹን አዘዘ፡፡ ያዕቁብም እንደዚሁ ልጆቹን አዘዘ፡፡ «ልጆቼ ሆይ! አላህ ለእናንተ ሃይማኖትን መረጠ፤ ስለዚህ እናንተ *”ሙስሊሞች”* ኾናችሁ እንጂ አትሙቱ» አላቸው"*፡፡ وَوَصَّىٰ بِهَآ إِبْرَٰهِـۧمُ بَنِيهِ وَيَعْقُوبُ يَٰبَنِىَّ إِنَّ ٱللَّهَ ٱصْطَفَىٰ لَكُمُ ٱلدِّينَ فَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُونَ
“ሙሥሊም” مُسْلِم የሚለው ቃል “አሥለመ” أَسْلَمَ ማለትም “ታዘዘ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ታዛዥ” ማለት ነው። የዕቁብ ከሻም ምድር ወደ ምስር ማለትን ወደ ግብጽ ምድር በልጁ በዩሱፍ ምክንያት ተጉዟል፦
12፥93 «ይህንን ቀሚሴን ይዛችሁ ሊዱ፡፡ *በአባቴ ፊትም ጣሉት የሚያይ ሆኖ ይመጣልና፡፡ ቤተሰቦቻችሁንም ሰብስባችሁ አምጡልኝ*» አላቸው፡፡ اذْهَبُوا بِقَمِيصِي هَـٰذَا فَأَلْقُوهُ عَلَىٰ وَجْهِ أَبِي يَأْتِ بَصِيرًا وَأْتُونِي بِأَهْلِكُمْ أَجْمَعِينَ
12፥99 በዩሱፍ ላይም በገቡ ጊዜ ወላጆቹን ወደ እርሱ አስጠጋቸው፡፡ «በአላህም ፈቃድ ጥብቆች ስትኾኑ *ምስርን ግቡ*» አላቸው፡፡ فَلَمَّا دَخَلُوا عَلَىٰ يُوسُفَ آوَىٰ إِلَيْهِ أَبَوَيْهِ وَقَالَ ادْخُلُوا مِصْرَ إِن شَاءَ اللَّهُ آمِنِينَ

“ሚስር” مِصْر ማለት ትርጉሙ “ከተማ” ማለት ሲሆን የግብጽ ስም ነው፥ የያዕቆብ ልጆች እዚች አገር ከተሙ። በመቀጠል አላህ ሙሳን በማስነሳት መጽሐፍን ሰጠው፤ ለእስራኤልም ልጆች መሪ አደረገው፤ “ከእኔ ሌላ መጠጊያን አትያዙ” አላቸው፦
17፥2 *ሙሳንም መጽሐፉን ሰጠነው፡፡ ለእስራኤልም ልጆች መሪ አደረግነው*፡፡ “ከእኔ ሌላ መጠጊያን አትያዙ” አልናቸውም፡፡ وَآتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ وَجَعَلْنَاهُ هُدًى لِّبَنِي إِسْرَائِيلَ أَلَّا تَتَّخِذُوا مِن دُونِي وَكِيلًا

ከዚያም አላህ የእስራኤልንም ልጆች ባሕሩን አሻገራቸው፡፡ ለእነርሱ በኾኑ ጣዖታት መገዛት ላይ በሚዘወትሩ ሕዝቦች ላይ አለፉም፦
7፥138 *የእስራኤልንም ልጆች ባሕሩን አሻገርናቸው፡፡ ለእነርሱ በኾኑ ጣዖታት መገዛት ላይ በሚዘወትሩ ሕዝቦች ላይ አለፉም*፡፡ «ሙሳ ሆይ፡- *ለእነርሱ አማልክት እንዷላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን*» አሉት፡፡ «እናንተ የምትሳሳቱ ሕዝቦች ናችሁ፤» አላቸው፡፡ وَجَاوَزْنَا بِبَنِي إِسْرَائِيلَ الْبَحْرَ فَأَتَوْا عَلَىٰ قَوْمٍ يَعْكُفُونَ عَلَىٰ أَصْنَامٍ لَّهُمْ ۚ قَالُوا يَا مُوسَى اجْعَل لَّنَا إِلَـٰهًا كَمَا لَهُمْ آلِهَةٌ ۚ قَالَ إِنَّكُمْ قَوْمٌ تَجْهَلُونَ

ሙሳም ለእስራኤልንም ልጆች፦ "ሕዝቦቼ ሆይ! ያችን አላህ ለእናንተ ያደረጋትን የተቀደሰችውን መሬት ግቡ" አላቸው፦
5፥21 *«ሕዝቦቼ ሆይ! ያችን አላህ ለእናንተ ያደረጋትን የተቀደሰችውን መሬት ግቡ፡፡ ወደ ኋላችሁም አትመለሱ፡፡ ከሳሪዎች ኾናችሁ ትመለሳላችሁና፡፡»* يَا قَوْمِ ادْخُلُوا الْأَرْضَ الْمُقَدَّسَةَ الَّتِي كَتَبَ اللَّهُ لَكُمْ وَلَا تَرْتَدُّوا عَلَىٰ أَدْبَارِكُمْ فَتَنقَلِبُوا خَاسِرِينَ

እነርሱም በምድረበዳ በአላህ ላይ በማመጻቸው የተቀደሰችው መሬት በእነርሱ ላይ አርባ ዓመት እርም ሆነች፡፡ በምድረ በዳ ተንከራተቱ፦
5፥26 *”እርስዋም የተቀደሰችው መሬት በእነርሱ ላይ አርባ ዓመት እርም ናት፡፡ በምድረ በዳ ይንከራተታሉ”*፡፡ «በአመጸኞችም ሕዝቦች ላይ አትዘን» አለው፡፡ قَالَ فَإِنَّهَا مُحَرَّمَةٌ عَلَيْهِمْ ۛ أَرْبَعِينَ سَنَةً ۛ يَتِيهُونَ فِي الْأَرْضِ ۚ فَلَا تَأْسَ عَلَى الْقَوْمِ الْفَاسِقِينَ

ከዚያም በሻም ምድር የሚኖሩትን ደካሞች የነበሩትን ሕዝቦችና በውስጧ በረከት ያደረገባትን የሻም ምድር ምሥራቆችዋንም ምዕራቦቿንም አወረሳቸው፦
7፥137 *"እነዚያንም ደካሞች የነበሩትን ሕዝቦች ያችን በውስጧ በረከት ያደረግንባትን ምድር ምሥራቆችዋንም ምዕራቦቿንም አወረስናቸው፡፡ የጌታህም መልካሚቱ ቃል በእስራኤል ልጆች ላይ በመታገሳቸው ተፈጸመች"*፡፡ وَأَوْرَثْنَا الْقَوْمَ الَّذِينَ كَانُوا يُسْتَضْعَفُونَ مَشَارِقَ الْأَرْضِ وَمَغَارِبَهَا الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا ۖ وَتَمَّتْ كَلِمَتُ رَبِّكَ الْحُسْنَىٰ عَلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ بِمَا صَبَرُوا ۖ
“መሥጂድ” مَسْجِد የሚለው ቃል “ሠጀደ” سَجَدَ ማለትም “ሰገደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መስገጃ” ማለት ሲሆን “ሡጁድ” سُّجُود ደግሞ “ስግደት” ማለት ነው። የጥንት ሰዎች መሥጂድ የሚሠሩት ድንኳን ነው። በመካህ የተመሠረተው የመጀሪያው መሥጂድ “አል-መሥጂዱል ሐረም” الْمَسْجِدِ الْحَرَام ማለትም “የተከበረ መሥጂድ” ሲሆን በሻም ምድር የተመሠረተው ሁለተኛው መሥጂድ ደግሞ አል-መሥጂዱል አቅሳ” الْمَسْجِدِ الْأَقْصَى ማለትም “የሩቅ መሥጂድ” ነው፦
17:1 ያ ባሪያውን *“ከተከበረው መስጊድ” ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ “ሩቁ መስጊድ”* በሌሊት ውስጥ ያስኼደው ጥራት ይገባው፤ ከታምራቶቻችን ልናሳየው አስኼድነው ፤ እነሆ እርሱ አላህ ሰሚው ተመልካቺው ነው። سُبْحَٰنَ ٱلَّذِىٓ أَسْرَىٰ بِعَبْدِهِۦ لَيْلًۭا مِّنَ ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ إِلَى ٱلْمَسْجِدِ ٱلْأَقْصَا ٱلَّذِى بَٰرَكْنَا حَوْلَهُۥ لِنُرِيَهُۥ مِنْ ءَايَٰتِنَآ ۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 45
አቢ ዘር ሰምቶ እንደተረከው፦ “እኔም፦ *”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በምድር ላይ መጀመሪያ የተመሠረተው የትኛው መሥጂድ ነው? አልኩኝ። እርሳቸውም፦ “አል-መሥጂዱል ሐረም” አሉ። እኔም፦ “ከዚያስ ቀጥሎ? ብዬ አልኩኝ። እርሳቸውም፦ “አል-መሥጂዱል አቅሳ” አሉ። እኔም፦ “በሁለቱ መካከል ምን ያህል የጊዜ ልዩነት አለ? ብዬ አልኩኝ። እርሳቸውም፦ “አርባ ዓመት” አሉ”*። قَالَ سَمِعْتُ أَبَا ذَرٍّ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ، أَىُّ مَسْجِدٍ وُضِعَ فِي الأَرْضِ أَوَّلُ قَالَ ‏”‏ الْمَسْجِدُ الْحَرَامُ ‏”‌‏.‏ قَالَ قُلْتُ ثُمَّ أَىٌّ قَالَ ‏”‏ الْمَسْجِدُ الأَقْصَى ‏”‌‏.‏ قُلْتُ كَمْ كَانَ بَيْنَهُمَا قَالَ ‏”‏ أَرْبَعُونَ سَنَةً،

“ፉሲዐ” وُضِعَ ማለት “ተመሠረተ” ማለት ነው፥ በሁለቱ መሣጂጅ መካከል ያለው የጊዜ ልዩነት 40 ዓመት ነው። እነዚህ መሣጂድ የተመሠረቱት በአደም ጊዜ ነው፥ በኢብራሂም ጊዜ ነው” የሚል ሁለት እይታ እንዳለ የመስኩ ልሂቃን ያትታሉ።
ከዚያም አምላካችን አላህ ዙሪያውን በባረክው በሁለተኛው የሩቁ መሥጂድ ለሱለይማንም ነፋስን በኀይል የምትነፍስ በትዕዛዙ ወደዚያች በእርሷ ውስጥ በረከትን ወደ አደረግንባት ሻም የምትፈስ ስትኾን ገራለት፥ ሱለይማን እዛው አቅሳ መስገጃው ላይ ሕንጻ አል-በይቱል መቅዲሥ ገነባ፦
21፥81 *”ለሱለይማንም ነፋስን በኀይል የምትነፍስ በትዕዛዙ ወደዚያች በእርሷ ውስጥ በረከትን ወደ አደረግንባት ምድር (ወደ ሻም) የምትፈስ ስትኾን ገራንለት”*፡፡ በነገሩ ሁሉም ዐዋቂዎች ነበርን፡፡ وَلِسُلَيْمَانَ الرِّيحَ عَاصِفَةً تَجْرِي بِأَمْرِهِ إِلَى الْأَرْضِ الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا ۚ وَكُنَّا بِكُلِّ شَيْءٍ عَالِمِينَ
34፥13 *”ከምኩራቦች፣ ከምስሎችም እንደ ገንዳ ከኾኑ ገበታዎችም፣ ከተደላደሉ ታላላቅ ድስቶችም የሚሻውን ሁሉ ይሠሩለታል”*፡፡ አልናቸውም፡፡ يَعْمَلُونَ لَهُ مَا يَشَاءُ مِن مَّحَارِيبَ وَتَمَاثِيلَ وَجِفَانٍ كَالْجَوَابِ وَقُدُورٍ رَّاسِيَاتٍ
አላህ ለሱለይማን ከጥንት በተመሠረተው መሥጂድ ላይ “መሐሪብ” እንዲሠራ ከጂኒዎች የሚሻውን ሁሉ እንዲሠሩለት ገራለት። እዚህ አንቀጽ ላይ “ምኩራብ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “መሐሪብ” مَّحَٰرِيب ሲሆን “አል-በይቱል መቅዲሥ” ٱلْبَيْت الْمَقْدِس ነው። “አል-በይቱል መቅዲሥ” ማለት “የተቀደሰ ቤት” ማለት ነው፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 1473
ዐብደላህ ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ሡለይማን ኢብኑ አቢ ዳዉድ በይቱተል መቅዲሥን ገንብቶ በጨረሰ ጊዜ አላህን ሦስት ነገሮች ጠይቋል። ፦ በፍርዱ የሚያስማማበትን ፍርድ ጠየቀ፥ ያም ተሰጠው።
፦ከእርሱ በኃላ ማንም የማይኖረውን ንግሥና።
፦ ሶላት ለማድረግ እንጂ ወደዚህ መሥጂድ የሚመጣውን ልክ እናቱ ስትወልደው ከኀጢአት ነጻ እንደሆነ እንዲሆን”*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، عَنِ النَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏”‏ لَمَّا فَرَغَ سُلَيْمَانُ بْنُ دَاوُدَ مِنْ بِنَاءِ بَيْتِ الْمَقْدِسِ سَأَلَ اللَّهَ ثَلاَثًا حُكْمًا يُصَادِفُ حُكْمَهُ وَمُلْكًا لاَ يَنْبَغِي لأَحَدٍ مِنْ بَعْدِهِ وَأَلاَّ يَأْتِيَ هَذَا الْمَسْجِدَ أَحَدٌ لاَ يُرِيدُ إِلاَّ الصَّلاَةَ فِيهِ إِلاَّ خَرَجَ مِنْ ذُنُوبِهِ كَيَوْمَ وَلَدَتْهُ أُمُّهُ

“ቢናእ” بِنَاء የሚለው ቃል “በና” بَنَىٰ ማለትም “ገነባ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ግንባታ” ወይም “ሕንጻ” ማለት ነው። ሡለይማን የገነባው ጥንት በተመሠረተው መሥጂድ ላይ ነው፥ እርሱ ገንቢ እንጂ መሥራች አለመሆኑ እሙልና ቅቡል ነው።

ከዚያ የእስራኤል ልጆች ሁለት ጊዜ አጠፉ፥ ከሁለቱ የመጀመሪያይቱ ቀጠሮ በመጣም ጊዜ ለአላህ የኾኑን ባሮች የብርቱ ኃይል ባለቤቶች የኾኑትን ናቡነደፆርን እና ሰራዊቱን በ 606 ቅድመ-ልደት”BC” ይህንን መሐሪብ ማለኪያ አጥፍተውታል፥ ይህ ተፈጻሚ ቀጠሮም ነበር፡፡ የኋለኛይቱም ጊዜ ቀጠሮ በመጣ ጊዜ መሥጂዱን በመጀመሪያ ጊዜ እንደገቡት ሊገቡ፣ ያሸነፉትንም ሁሉ ፈጽመው ማጥፋትን እንዲያጠፉ በ 70 ድህረ-ልደት”AD” የሮም ጦር የሆነው ጀነራል ቲቶ እና ሰራዊቱ ከበው አጥፍተዋል፦
17፥7 መልካም ብትሠሩ ለነፍሶቻችሁ መልካምን ሠራችሁ፡፡ መጥፎንም ብትሠሩ በእነርሱ በነፍሶቻችሁ ላይ ነው” አልን፡፡ *”የኋለኛይቱም ጊዜ ቀጠሮ በመጣ ጊዜ ፊቶቻችሁን ሊያስከፉ፣ መስጊዱንም በመጀመሪያ ጊዜ እንደገቡት ሊገቡ፣ ያሸነፉትንም ሁሉ ፈጽመው ማጥፋትን እንዲያጠፉ እንልካቸዋልን”*፡፡ إِنْ أَحْسَنتُمْ أَحْسَنتُمْ لِأَنفُسِكُمْ ۖ وَإِنْ أَسَأْتُمْ فَلَهَا ۚ فَإِذَا جَآءَ وَعْدُ ٱلْـَٔاخِرَةِ لِيَسُۥٓـُٔوا۟ وُجُوهَكُمْ وَلِيَدْخُلُوا۟ ٱلْمَسْجِدَ كَمَا دَخَلُوهُ أَوَّلَ مَرَّةٍۢ وَلِيُتَبِّرُوا۟ مَا عَلَوْا۟ تَتْبِيرًا

የመስኩ ምሁራም፦ “ፈኢዛ ጃአ” فَإِذَا جَآءَ ማለትም “በመጣ ጊዜ” የሚለው የጊዜ ተውሳ-ግስ ሙስተቅበል ሆኖ የወደፊቱ ያመለክታል” ይላሉ። እውነት ነው፥ “የኋለኛይቱ ቀጠሮ” የሚለው ኃይለ-ቃል በሌላ አንቀጽ የእስራኤል ልጆች ተበትነው ከነበሩበት አገራት አላህ እንደሚያመጣቸው ተናግሯል፦
17፥104 ከእርሱም በኋላ ለእሰራኤል ልጆች፦ *«ምድሪቱን ተቀመጡባት *”የኋለኛይቱም ቀጠሮ”* በመጣ ጊዜ እናንተን የተከማቻችሁ ስትኾኑ እናመጣችኋለን»* አልናቸው”። وَقُلْنَا مِنۢ بَعْدِهِۦ لِبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ ٱسْكُنُوا۟ ٱلْأَرْضَ فَإِذَا جَآءَ وَعْدُ ٱلْـَٔاخِرَةِ جِئْنَا بِكُمْ لَفِيفًۭا

ከተመለሱ በኃላ እስከ ትንሣኤ ቀን ክፉ ቅጣትን የሚያቀምሳቸውን አላህ በእነርሱ ላይ በእርግጥ ይልካል፦
7፥167 *ጌታህም እስከ ትንሣኤ ቀን ክፉ ቅጣትን የሚያቀምሳቸውን በእነርሱ ላይ በእርግጥ የሚልክ መኾኑን ባስታወቀ ጊዜ አስታውሳቸው፡፡ ጌታህ በእርግጥ ቅጣተ ፈጣን ነው”*፡፡ እርሱም በእርግጥ እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ وَإِذْ تَأَذَّنَ رَبُّكَ لَيَبْعَثَنَّ عَلَيْهِمْ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ مَن يَسُومُهُمْ سُوٓءَ ٱلْعَذَابِ ۗ إِنَّ رَبَّكَ لَسَرِيعُ ٱلْعِقَابِ ۖ وَإِنَّهُۥ لَغَفُورٌۭ رَّحِيمٌۭ

ኢንሻላህ ያንን ቀን አላህ ያምጣው! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሙሰዲቃን እና ሙሃይሚን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥48 *”ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ “አረጋጋጭ” እና በእርሱ ላይ “ተጠባባቂ” ሲሆን በእውነት አወረድን”*። وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ

አምላካችን አላህ በነቢያችን"ﷺ" ላይ ቁርኣንን በእውነት አወረደ፥ ከቁርኣን በፊት ተውራትንና ኢንጂልን ለሰዎች መሪ አድርጎ አወረዳቸው፦
3፥3 *”ከእርሱ በፊት ያሉትን የሚያረጋግጥ ሲኾን መጽሐፉን በአንተ ላይ ከፋፍሎ በእውነት አወረደ፡፡ ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል”*፡፡ نَزَّلَ عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَأَنزَلَ ٱلتَّوْرَىٰةَ وَٱلْإِنجِيلَ
3፥4 *”ከእርሱ በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ አወረዳቸው”*፡፡ مِن قَبْلُ هُدًۭى لِّلنَّاسِ

“የደይ” يَدَيْ ማለት “ፊት” ማለት ሲሆን “ኃላ” ለሚል ተቃራኒ ሆኖ የመጣ ነው፥ “ቀብል” قَبْل ማለት "ፊት" ማለት ሲሆን የየደይ ተመሳሳይ ትርጉም ነው። "የደይ-ሂ" يَدَيْهِ ማለት እና "ቀብሉ" قَبْلُ ማለት "ከበፊቱ" ማለት ነው፥ "ሂ" هِ ወይም "ሁ" هُ የሚለው ተሳቢ ተውላጠ-ስም ቁርኣንን ያሳያል። ከቁርኣን በፊት የወረዱትን ተውራትና ኢንጅልን ሊያረጋግጥ ቁርኣን ወርዷል። “ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። አምላካችን አላህ፦ “እመኑ” ያለን ከቁርኣን በፊት ባወረደው ወሕይ ነው፦
4፥136 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ እና በመልክተኛው፤ በዚያም በመልክተኛው ላይ ባወረደው መጽሐፍ፤ በዚያም *”ከበፊቱ ባወረደው መጽሐፍ እመኑ”*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ ءَامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَٱلْكِتَٰبِ ٱلَّذِى نَزَّلَ عَلَىٰ رَسُولِهِۦ وَٱلْكِتَٰبِ ٱلَّذِىٓ أَنزَلَ مِن قَبْلُ

“ከበፊቱ ባወረደው መጽሐፍ እመኑ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። እንግዲህ አምላካችን አላህ ተውራትና ኢንጅል የሚላቸው ወደ ሙሳ እና ወደ ዒሣ የወረዱትን ወሕይ ብቻና ብቻ ነው። አምላካችን አላህ ከራሱ የሚያወርደው ወሕይ እውነት ይለዋል፦
34፥48 ፦ጌታዬ *“እውነትን ያወርዳል”*፤ ሩቅ የኾኑትን ሚስጢሮች ሁሉ ዐዋቂ ነው *በላቸው*። قُلْ إِنَّ رَبِّى يَقْذِفُ بِٱلْحَقِّ عَلَّٰمُ ٱلْغُيُوبِ

ይህ ከአላህ የወረደውን እውነት የመጽሐፉ ሰዎች ከውሸት ማለት ከሰው ንግግር ጋር ቀላቅለውታል፦
3፥71 የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! *“እዉነቱን በዉሸት” ለምን ትቀላቅላላችሁ*? እዉነቱንም እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን ትደብቃላችሁ? يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ

ይህ የሰው ንግግር “ውሸት” ለምን ተባለ? ምክንያቱም የሰው ንግግር በእጆቻቸው ፅፈው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ብለው የቀጠፉት ጭማሬ ስለሆነ ነው፦
2፥79 *ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው*፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው፡፡ فَوَيْلٌۭ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ ٱلْكِتَٰبَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ ٱللَّهِ لِيَشْتَرُوا۟ بِهِۦ ثَمَنًۭا قَلِيلًۭا ۖ فَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ

እዚው ዐውድ ላይ ስንመለከት ከመጽሐፉ ሰዎች የአላህን ንግግር የሚሰሙ እና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ የሰው ንግግር በእጆቻቸው ፅፈው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ብለው በርዘውታል፦
2፥75 *ከእነርሱ የኾኑ ጭፍሮች የአላህን ንግግር የሚሰሙ እና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ “የሚለውጡት” ሲኾኑ ለእናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?”* أَفَتَطْمَعُونَ أَن يُؤْمِنُوا لَكُمْ وَقَدْ كَانَ فَرِيقٌ مِّنْهُمْ يَسْمَعُونَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ يُحَرِّفُونَهُ مِن بَعْدِ مَا عَقَلُوهُ وَهُمْ يَعْلَمُون

“የሚለውጡት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ዩሐረፉነሁ” يُحَرِّفُونَهُ ሲሆን “የሚበርዙት” ማለት ነው፤ “ዩሐረፉ” يُحَرِّفُ የሚለው አላፊ ግስ “ሐረፈ” حَرَفَ ማለትም “በረዘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ የሚበርዙት ፊደሉ “ሐርፍ” حَرْف ሲባል፥ በራዡ “ሙተሐሪፍ” مُتَحَرِّف ሲልባ፥ የመበረዙ ድርጊቱ ደግሞ “ተሕሪፍ” تَحريف ይባላል፤ ይህ ሙግት የሥነ-ቋንቋ ሙግት ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው።
በተጨማሪም ከቀደምት የነቢያችን”ﷺ” ቅርብ ባልደረባ ኢብኑ ዓባሥ”ረ.ዐ” የሱረቱል በቀራ 2፥79 አንቀጽን በሰሒሕ ሐዲስ ሲፈሥረው እንዲህ ይላል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 52, ሐዲስ 46:
ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ” ሲናገር፦ *ሙስሊሞች ሆይ ለምን የመጽሐፉ ሰዎችን ትጠይቃላችሁ? በተመሳሳይ መጽሐፋችሁ ከአላህ ዘንድ ለነቢዩ”ﷺ” የተወረደው ወቅታቂ መረጃ እና የምትቀሩት እያለ? መጽሐፋ አልተበረዘምን? አላህ ለእናንተ የመጽሐፉ ሰዎች በእጆቻቸው በርዘው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» እንደሚሉ አውርዷል*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ يَا مَعْشَرَ الْمُسْلِمِينَ، كَيْفَ تَسْأَلُونَ أَهْلَ الْكِتَابِ، وَكِتَابُكُمُ الَّذِي أُنْزِلَ عَلَى نَبِيِّهِ صلى الله عليه وسلم أَحْدَثُ الأَخْبَارِ بِاللَّهِ، تَقْرَءُونَهُ لَمْ يُشَبْ، وَقَدْ حَدَّثَكُمُ اللَّهُ أَنَّ أَهْلَ الْكِتَابِ بَدَّلُوا مَا كَتَبَ اللَّهُ وَغَيَّرُوا بِأَيْدِيهِمُ الْكِتَابَ، فَقَالُوا هُوَ مِنْ عِنْدِ اللَّهِ، لِيَشْتَرُوا بِهِ ثَمَنًا قَلِيلاً أَفَلاَ يَنْهَاكُمْ مَا جَاءَكُمْ مِنَ الْعِلْمِ عَنْ مُسَاءَلَتِهِمْ، وَلاَ وَاللَّهِ مَا رَأَيْنَا مِنْهُمْ رَجُلاً قَطُّ يَسْأَلُكُمْ عَنِ الَّذِي أُنْزِلَ عَلَيْكُمْ