ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.3K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
መጽሐፍን ሰጥቶኛል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥30 ሕፃኑም አለ «እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ፡፡ *"መጽሐፍን ሰጥቶኛል፥ ነቢይም አድርጎኛል"*፡፡» قَالَ إِنِّي عَبْدُ اللَّهِ آتَانِيَ الْكِتَابَ وَجَعَلَنِي نَبِيًّا

አምላካችን አላህ ለዒሣ ኢንጂልን ሰጥቶታል፦
57፥27 ከዚያም በዱካዎቻቸው ላይ መልክተኞቻችንን አስከታተልን፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሳንም አስከተልን፡፡ *"ኢንጂልንም ሰጠነው"*፡፡ ثُمَّ قَفَّيْنَا عَلَىٰ آثَارِهِم بِرُسُلِنَا وَقَفَّيْنَا بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ وَآتَيْنَاهُ الْإِنجِيل

ይህም ኢንጂል ኪታብ ሲሆን ዒሣ ሕፃን ሆኖ፦ "መጽሐፍን ሰጥቶኛል" በማለት ይናገራል፦
19፥30 ሕፃኑም አለ «እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ፡፡ *"መጽሐፍን ሰጥቶኛል"* ነቢይም አድርጎኛል፡፡» قَالَ إِنِّي عَبْدُ اللَّهِ آتَانِيَ الْكِتَابَ وَجَعَلَنِي نَبِيًّا

"ሰጥቶኛል" የሚለው ቃል "አታኒይ" آتَانِي ሲሆን አል-ገይቡል ማዲ ነው፥ ግን "ሠዩዑቲይ" سَيُؤْتِي ማለትም "ይሰጠኛል" በሚል አል-ገይቡል ሙስተቅበል ይመጣል። ለምሳሌ "ቃለ" قَالَ ማለት "አለ" ማለት ሲሆን አል-ገይቡል ማዲ ቢሆንም ግን "የቁሉ" يَقُولُ በሚል አል-ገይቡል ሙስተቅበል ሆኖ ይመጣል፦
33፥38 በትንሣኤ ወደ እኛ በመጣም ጊዜ፦ ቁራኛዬ ሆይ! «በእኔ እና በአንተ መካከል የምሥራቅና የምዕራብ ርቀት በኖረ ወይ ምኞቴ! ምን የከፋህ ቁራኛ ነህ» *"ይላል"*፡፡ حَتَّىٰ إِذَا جَاءَنَا قَالَ يَا لَيْتَ بَيْنِي وَبَيْنَكَ بُعْدَ الْمَشْرِقَيْنِ فَبِئْسَ الْقَرِينُ

የትንሳኤ ቀን አል-ገይቡል ሙስተቅበል ሲሆን ግን "ይላል" ለሚለው የገባው "ቃለ" قَالَ መሆኑ ግን "የቁሉ" يَقُولُ የሚለውን ለመግለጽ እንደመጣ አንባቢ ልብ ይለዋል፦
89፥24 «ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ መልካምን ሥራ ባስቀደምኩ ኖሮ» *ይላል*፡፡ يَقُولُ يَا لَيْتَنِي قَدَّمْتُ لِحَيَاتِي

እዚህ አንቀጽ ላይ ደግሞ "የቁሉ" يَقُولُ በሚል አል-ገይቡል ሙስተቅበል የመጣው፥ "ቃለ" قَالَ ደግሞ "አለ" ማለት ቢሆንም "ይላል" በሚል መጥቷል፦
5፥109 *"አላህ መልክተኞቹን የሚሰበስብበትንና «ምን መልስ ተሰጣችሁ?» የሚልበትን ቀን አስታውስ፡፡ «ለእኛ ምንም ዕውቀት የለንም አንተ ሩቆችን በጣም ዐዋቂ አንተ ብቻ ነህ» ይላሉ*፡፡ يَوْمَ يَجْمَعُ اللَّهُ الرُّسُلَ فَيَقُولُ مَاذَا أُجِبْتُمْ ۖ قَالُوا لَا عِلْمَ لَنَا ۖ إِنَّكَ أَنتَ عَلَّامُ الْغُيُوبِ

"የሚልበትን" ለሚለው የገባው "የቁሉ" يَقُولُ በሚል ሲሆን "ይላሉ" ለሚለው ግን "ቃሉ" قَالُوا ማለትም "አሉ" ነው፥ ልብ አድርግ አላህም መልእክተኞቹም የሚነጋገሩት በትንሳኤ ቀን መሆኑን። ስለዚህ በአላፊ ግስ የወደፊትን ግስ መግለጽ እንደሚቻል ሁሉ አላህ ለዒሣ ካደገ በኃላ የሚሰጠው ኢንጂል ለማመልከት በአላፊ ግስ ዒሣ "አታኒይ" آتَانِي ብሎ እንዲናገር አድርጎታል፦
3፥46 *«በሕፃንነቱ እና በጎልማሳነቱ ሰዎቹን ያነጋግራል፡፡ ከመልካሞቹም ነው» አላት*፡፡ وَيُكَلِّمُ النَّاسَ فِي الْمَهْدِ وَكَهْلًا وَمِنَ الصَّالِحِينَ

"ከህል" كَهْل ማለት "ብስለት"maturity" ማለት ሲሆን የጎልማሳነትን ጊዜ ያሳያል። ስለዚህ አላህ ለዒሣ ኢንጅልን የሰጠው በጎልማሳነቱ ጊዜ ነው። "አታኒይ" آتَانِي የሚለው "ይሰጠኛ" በሚል የመጣው ነው። የተሰጠው መጽሐፍ ኢንጅል እንደሆነ ደግሞ አምላካችን አላህ፦ "ኢንጂልን ሰጠነው" ይለናል፦
5፥46 በፈለጎቻቸውም ላይ የመርየምን ልጅ ዒሳን ከተውራት በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ ሲኾን አስከተልን፡፡ *"ኢንጂልንም በውስጡ ቀጥታና ብርሃን ያለበት በስተፊቱ ያለችውን ተውራትንም የሚያረጋግጥ ለጥንቁቆችም መሪና ገሳጭ ሲኾን ሰጠነው"*፡፡ وَقَفَّيْنَا عَلَىٰ آثَارِهِم بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ التَّوْرَاةِ ۖ وَآتَيْنَاهُ الْإِنجِيلَ فِيهِ هُدًى وَنُورٌ وَمُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ التَّوْرَاةِ وَهُدًى وَمَوْعِظَةً لِّلْمُتَّقِينَ

"መጽሐፍን ሰጥቶኛል" ብቻ ሳይሆን ያለው "ነቢይም አድርጎኛል" ነው፦
19፥30 ሕፃኑም አለ «እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ፡፡ *"መጽሐፍን ሰጥቶኛል፥ ነቢይም አድርጎኛል"*፡፡» قَالَ إِنِّي عَبْدُ اللَّهِ آتَانِيَ الْكِتَابَ وَجَعَلَنِي نَبِيًّا

"ጀዐለኒ" جَعَلَنِي በሚለው መነሻ ቅጥያ ላይ "ወ" وَ የሚል መስተጻምር "አታኒይ" آتَانِيَ የሚለውን አያይዞ የመጣ ሲሆን "ነቢይ" የሚሆነው ካደገ በኃላ እንደሚሆን ሁሉ መጽሐፍም የሚሰጠው ካደገ በኃላ ነው። ምነው ሳይጸነስም ነቢይ ሆነ የተባለም እኮ አለ፦
3፥39 እርሱም በጸሎት ማድረሻው ክፍል ቆሞ ሲጸልይ መላእክት፦ «አላህ በየሕያ ከአላህ በኾነ ቃል የሚያረጋግጥ ጌታም ድንግልም ከደጋጎቹ *"ነቢይም ሲኾን"* ያበስርሃል» በማለት ጠሩት፡፡ فَنَادَتْهُ الْمَلَائِكَةُ وَهُوَ قَائِمٌ يُصَلِّي فِي الْمِحْرَابِ أَنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكَ بِيَحْيَىٰ مُصَدِّقًا بِكَلِمَةٍ مِّنَ اللَّهِ وَسَيِّدًا وَحَصُورًا وَنَبِيًّا مِّنَ الصَّالِحِينَ

ያ ማለት የሕያ ሳይጸነስ በፊት ነቢይ ሆነ ማለትን እንደማያሲዝ ሁሉ በተመሳሳይ ዒሣም በሕጻንነቱ ነቢይ ሆነ መጽሐፍም ተሰጠው የሚለውን አያሲዝም።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የጨረቃ አቆጣጠር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥189 *ከለጋ ጨረቃዎች ይጠየቁሃል፥ እነርሱ ለሰዎች ጥቅም ለሐጅም ማወቂያ ጊዜያቶች ምልክቶች ናቸው በላቸው*፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْأَهِلَّةِ ۖ قُلْ هِيَ مَوَاقِيتُ لِلنَّاسِ وَالْحَج

የተቆጠሩ ቀኖች የያዘው 9ኛው ወር ረመዷን በመጣ ቁጥር የጨረቃ መታየት እና አለመታየት በፆም መጀመር እና መጨረስ ላይ የሚኖረውም አውንታዊ ተፅዖኖ ብዙ የክርስትና ዘላፊያን ሆኑ ኀያሲያን እንደ በቀቀን እየደጋገሙ መዝለፍና ኂስ መስጠታቸው አይቀሬ ነው። ይህንን ታሳቢና ዋቢ ባደረገ መልኩ ይህንን መጣጥፍ ለዚያ ምላሽ አቅርቤአለው። ግብጻውያን፣ ባቢሎናውያን፣ ሰመርያን፣ ሄለናውያን(ግሪኮች)፣ ሮማውያን፣ ዞራስተሪያን፣ ሂንዱ የየራሳቸው "የዘመን አቆጣጠር"calendar" ነበራቸው።
ይህ አቆጣጠራቸው ምንጩ "አል-ቀመርያ" ማለትም "የጨረቃ አቆጣጠር"lunar calender" እና "አሽ-ሸምሲያህ" ማለትም "የፀሐይ አቆጣጠር"solar calended" ናቸው። አምላካችን አላህ በተከበረ ቃሉ ፀሐይን እና ጨረቃን ለሰው ልጆች የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን መቁጠሪያ እንዳደረገ ይናገራል፦
6፥96 እርሱም ጎህን ከሌሊት ጨለማ ፈልቃቂ ሌሊትንም ማረፊያ *"ፀሐይንና ጨረቃንም ለጊዜ መቁጠሪያ አድራጊ ነው"*፡፡ فَالِقُ الْإِصْبَاحِ وَجَعَلَ اللَّيْلَ سَكَنًا وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ حُسْبَانًا ۚ ذَٰلِكَ تَقْدِيرُ الْعَزِيزِ الْعَلِيمِ
10፥5 እርሱ ያ ፀሐይን አንጻባራቂ ጨረቃንም አብሪ ያደረገ ነው፡፡ *የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን ታውቁ ዘንድም ለእርሱ መስፈሪያዎችን የለካ ነው*፡፡ አላህ ይህንን በእውነት እንጂ በከንቱ አልፈጠረውም፡፡ ለሚያውቁ ሕዝቦች አንቀጾችን ያብራራል፡፡ هُوَ الَّذِي جَعَلَ الشَّمْسَ ضِيَاءً وَالْقَمَرَ نُورًا وَقَدَّرَهُ مَنَازِلَ لِتَعْلَمُوا عَدَدَ السِّنِينَ وَالْحِسَابَ ۚ مَا خَلَقَ اللَّهُ ذَٰلِكَ إِلَّا بِالْحَقِّ ۚ يُفَصِّلُ الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ

የሥነ-ተረት ጥናት"mythology" እንደሚያትተው በተለይ በባቢሎናውያን "ሲን" የተባለው የጨረቃ አምላክ እና "ሻም" የተባለው የፀሐይ አምላክ ባልና ሚስት ተደርገው ይመለኩ ነው፤ "ሲን" ማለት "ጨረቃ" ማለት ሲሆን "ሻም" ደግሞ "ፀሐይ" ማለት ነው። ይህንን እሳቤ ቁርአን መንግሎ ይጥለዋል፤ መመለክ የሚገባው ፀሐይና ጨረቃን የፈጠራቸው አላህ ብቻ ነው፦
41፥37 ሌሊትና ቀንም፣ *"ጸሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፤ ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፤ ለዚያም ለፈጠራቸው አላህ ሰገዱ፤ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደሆናችሁ ለሌላ አትስገዱ"*። وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ

የዘመናችን የሥነ-ፈለክ ጥናት እንደሚያትተው የጨረቃ ፈለክ ምድራችንን በ 384,408 km በሆነ ዑደት”Revolution” ለመዞር የሚወስድባት ጊዜ 27 ቀናት ነው። አምላካችን አላህም በቁርኣን “ቀመር” قَمَر ማለትም “ጨረቃ” የሚለውን ቃል የተጠቀመው “27” ጊዜ ብቻ ነው። ጨረቃ ፕላኔታችንን በምእራባዊ አቅጣጭ 360 ድግሪ ለመዞር 19 ዓመት ይፈጅባታል።
የሚያስደምመው ነገር “ዓመት” የሚለው ቃል የተጠቀሰው “ሢኒን” سِنِين በብዜት 12 ጊዜ ወይም “ሠናህ” سَنَة በነጠላ 7 ጊዜ በጥቅሉ “19” ጊዜ ብቻ ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት የዓለማቱ ጌታ ነገርን ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ስለሆነ ነው፦
72፥28 እነርሱ ዘንድ ባለው ነገር እውቀቱ የከበበ እና * ነገሩንም ሁሉ “በቁጥር” ያጠቃለለ ሲሆን"* የጌታቸውን መልክቶች ያደረሱ መሆናቸውን ያውቅ ዘንድ ጠባቂ ያደርጋል። لِّيَعْلَمَ أَن قَدْ أَبْلَغُوا رِسَالَاتِ رَبِّهِمْ وَأَحَاطَ بِمَا لَدَيْهِمْ وَأَحْصَىٰ كُلَّ شَيْءٍ عَدَدًا

የእኛ አቆጣጠር የጨረቃ አቆጣጠር ነው፦
2፥189 *ከለጋ ጨረቃዎች ይጠየቁሃል፥ እነርሱ ለሰዎች ጥቅም ለሐጅም ማወቂያ ጊዜያቶች ምልክቶች ናቸው በላቸው*፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْأَهِلَّةِ ۖ قُلْ هِيَ مَوَاقِيتُ لِلنَّاسِ وَالْحَج

የለጋ ጨረቃ መታየት የጊዜ ማወቂያ ምልክት ነው። ነቢያችን”ﷺ” የአላህ ነብይ ስለሆኑ በዐቂዳህ እና በፊቅህ ጉዳይ ላይ የሚናገሩት ወሕይ ስለሆነ ስለ ጨረቃ እንዲህ ይሉናል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 6, ሐዲስ 2378
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"መቼም ቢሆን ለጋ ጨረቃ በረመዳን ወር ስታዩ ፆምን ጀምሩ፤ የሸዋል ለጋ ጨረቃ ስታዩ ፆማችሁን ጨርሱ፤ ሰማይ ደመናማ ሲሆንላችሁ ፆም ሰላሳ ቀን መሆኑን አጢኑ"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، - رضى الله عنه - قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِذَا رَأَيْتُمُ الْهِلاَلَ فَصُومُوا وَإِذَا رَأَيْتُمُوهُ فَأَفْطِرُوا فَإِنْ غُمَّ عَلَيْكُمْ فَصُومُوا ثَلاَثِينَ يَوْمًا ‏"
የጨረቃ አቆጣጠር በኢሥላም በግርድፉና በሌጣው ይህ ያክል ካየን ዘንዳ የጨረቃ አቆጣጠር በባይብልና በትውፊት እናያለን። የጨረቃ መታየት ለጊዜ ማወቂያ እንደሆነ መዝሙረኛው ይናገራል፦
መዝሙረ ዳዊት 104፥19 *"ጨረቃን ለጊዜዎች አደረገ"* ፀሐይም መግቢያውን ያውቃል።

በተለይ አይሁዳውያን የወር መባቻ ጠብቀው በዓላቸውን የሚያውቁበት ነው፤ የወር መባቻ የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "ቆደሽ" חֹ֫דֶשׁ ሲሆን ትርጉሙ "አዲስ ጨረቃ" ማለት ነው ፣ ይህም ቃል በባይብል 28 ጊዜ ተወስቷል፤ ዕብራውያን ወራቸውን ሆነ ዓመታቸውን የሚጀምሩ በለጋ ጨረቃ መታየት ነው፦
ዘኍልቍ 10፥10 ደግሞ በደስታችሁ ቀን፥ በበዓላታችሁም ዘመን፥ *"በአዲስ ጨረቃ" חָדְשֵׁיכֶם֒ ፥"* በሚቃጠል መሥዋዕታችሁና በደኅንነት መሥዋዕታችሁ ላይ መለከቶቹን ንፉ እነርሱም በአምላካችሁ ፊት ለመታሰቢያ ይሆኑላችኋል እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። NIV Bible
መዝሙር 81፥3 *"በአዲስ ጨረቃ" חָדְשֵׁיכֶם֒ ቀን"* በከፍተኛው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ፤ NIV Bible

በክርስትና ቀዳማይ የዘመን አቆጣጠር ከ 180 –222 ድኅረ-ልደት"A.D" ድረስ ለ 42 ዓመት የአሌክሳንድርያ ፓትርያርክ የነበረው ድሜጥሮስ የቀመረው ነው። ይህም የዘመን ቀመር "አቡሻኽር" ወይም "ባሕረ-ሐሳብ" ይባላል። "ባሕር" ማለት "ዘመን" ማለት ሲሆን "ሐሳብ" ማለት ደግሞ "ሒሳብ" "ቁጥር" "ኍልቅ" ማለት ነው። በዚህ የዘመን ቀመር ላይ ስለ "አዕዋዳት" ይናገራል፥ "አዕዋድ" ማለት "ዖደ" ማለትም "ዞረ" ከሚል የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን "ዙረት" ማለት ሲሆን በየጊዜው እየዞረ የሚመጣ ማለት ነው።
ዓውደ-ወርኅ በፀሐይ 30 ቀናት ሲሆን በጨረቃ 29 እና 30 ነው። ዓውደ-ዓመት በፀሐይ 365 ቀናት ሲሆን በጨረቃ 354 ቀናት ነው። በተጨማሪም መጽሐፈ ሲራክ ጨረቃም ለሁሉም የዘመን መለኪያ፣ ለዓለም ሁሉ ምልክት እና የበዓላት ምልክት እንደሆነች ይናገራል፦
መጽሐፈ ሲራክ 43÷6-7 *"ጨረቃም ለሁሉም የዘመን መለኪያ ናት፤ ለዓለም ሁሉ ምልክት ናት፤ በእርሷም ቀን ይለያል፤ በጨረቃም የበዓላት ምልክት ይታወቃል"*።

ታዲያ ጨረቃን ጠብቆ ፆም መያዝና መፍታት እንዲሁ በዓልን ማክበር ለምን ኂስ ይሰጥበታል? ተዉ እንጂ እግር እራስን ያካል እንዴ? ወርቁ ቢጠፋስ ሚዛኑ ጠፋ እንዴ? እውነቱ ቢጠፋባችሁስ ህሊናችሁ ጠፋባችሁ እንዴ? የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ ወይም ቅቤ አንጣሪዋ እያለሽ ጎመን ቀቃይዋን ምች መታት ይላል የአገሬ ሰው። ቅድሚያ እሥልምናን ለመዝለፍ ባይብላችሁን እና ትውፊታችሁን ጠንቅቃችሁ ዕወቁ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ረመዷን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥183 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *"ጾም በእነዚያ ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደ ተጻፈ በእናንተም ላይ ተጻፈ፥ ልትጠነቀቁ ይከጀላልና"*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

“ሰውም” صَوْم ወይም “ሲያም” صِيَام
የሚለው ቃል "ተሱም" يَصُمْ ማለትም "ታቀብ" ከሚል ትእዛዛዊ ግስ የመጣ ሲሆን "መታቀብ" ማለት ነው፥ ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን “ሰውም” صَوْم ወይም “ሲያም” صِيَام በግርድፉና በሌጣው ደግሞ "ጾም" ማለት ነው። አንድ ሰው ምንም ነገር ሳይቀምስ ሲቀር "ጾሙን ዋለ" ይባላል፥ ያ ማለት ከምግብና ከመጠጥ “ተከለከለ” አሊያም “ተቆጠበ” ማለት ነው። ጾም ማለት “መከልከል” ወይም “መቆጠብ” መሆኑን የምናውቀው የአለመናገር ተቃራኒ የሆነውን “ዝምታን” ለማመልከት “ሰውም” صَوْم የሚለው ቃል አገልግሎት ላይ ውሏል፦
19፥26 «ብይም፣ ጠጭም፣ ተደሰችም፡፡ እኔ ለአልረሕማን *"ዝምታን ተስያለሁ"*፤ ዛሬም ሰውን በፍጹም አላነጋግርም» በይ፡፡ فَكُلِي وَاشْرَبِي وَقَرِّي عَيْنًا ۖ فَإِمَّا تَرَيِنَّ مِنَ الْبَشَرِ أَحَدًا فَقُولِي إِنِّي نَذَرْتُ لِلرَّحْمَـٰنِ صَوْمًا فَلَنْ أُكَلِّمَ الْيَوْمَ إِنسِيًّا

መርየም “ሰውማ” صَوْمًا ማለትም "ዝምታ" ስትል ከንግግር መቆጠቧን ካመለከተ ጾም ማለት ከምግብና ከመጠጥ መከልከል እንጂ ከስጋ እና ከስጋ ተዋእፆ ከሆኑት እንቁላል፣ ወተት፣ አይብ እየተቆጠቡ ነገር ግን በእጅ አዙር የስጋ፣ የእንቁላል፣ የወተት ምትክ የሆኑትን ባቄላ፣ አተር፣ በቆሎ፣ ገብስ የመሳሰሉት በሳይክል ተዙሮ የማያልቀውን ቡፌ መብላት አይደለም። ጾም ከምግብና ከመጠጥ ብቻ ሳይሆን ከሚታይ፣ ከሚሰማ፣ ከሚታሰብ ነገር መቆጠብን እንደሚጨም በቋንቋ ሙግት አይተናል።

አምላካችን አላህ ጾምን መጾም ያለባቸው ያመኑትን ምዕምናን ብቻ መሆናቸው ለማመልከት፦ "እናንተ ያመናችሁ ሆይ" በሚል መርሕ ስለ ጾም ይናገራል፦
2፥183 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *"ጾም በእነዚያ ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደ ተጻፈ በእናንተም ላይ ተጻፈ፥ ልትጠነቀቁ ይከጀላልና"*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

"ከእናንተ በፊት በነበሩት" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት፥ ከእኛ በፊት የነበሩት ነቢያትና ተከታዮቻቸው ናቸው፦
42፥3 እንደዚሁ አሸናፊው ጥበበኛው አላህ *"ወደ አንተ ያወርዳል፡፡ ወደ እነዚያም ከአንተ በፊት ወደ ነበሩት አውርዷል"*፡፡ كَذَٰلِكَ يُوحِي إِلَيْكَ وَإِلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكَ اللَّهُ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
39፥65 ብታጋራ ሥራህ በእርግጥ ይታበሳል፡፡ በእርግጥም ከከሓዲዎቹ ትኾናለህ ማለት *"ወደ አንተም ወደ እነዚያም ከአንተ በፊት ወደነበሩት በእርግጥ ተወርዷል"*፡፡ وَلَقَدْ أُوحِيَ إِلَيْكَ وَإِلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكَ لَئِنْ أَشْرَكْتَ لَيَحْبَطَنَّ عَمَلُكَ وَلَتَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ

ስለዚህ ጾም የተደነገገው ከነቢያችን"ﷺ" በፊት በነበሩትም ነቢያት ጭምር ነው፥ "ኩቲበ" كُتِبَ ማለት "ተደነገገ" "ተደነባ" "ታዘዘ"prescribed" ማለት ነው። ጾም የምንጾምበትን ምክንያት ደግሞ ለማመልከት፦ "ተቅዋ ታገኙ ዘንድ ነው" ይለናል፦
2፥183 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *"ጾም በእነዚያ ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደ ተጻፈ በእናንተም ላይ ተጻፈ፥ "ልትጠነቀቁ ይከጀላልና"*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

"ተተቁን" تَتَّقُون ማለት "መፍራት" ማለት ነው። ጾም የምንጾምበት ምክንያቱ አንደኛውና ዋናው አምላካችን አላህ ስላዘዘን ሲሆን ሁለተኛውና ተከታዩ ምክንያት “ተቅዋ” ለማግኘት ነው፥ “ይከጀላልና” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ለዐለኩም” لَعَلَّكُمْ ሲሆን "ለዐለኩም" በሚለው ቃል ላይ መነሻ ቅጥያ ሆኖ የመጣው ቃል “ለዐል” لَعَلّ ነው። “ለዐል” ማለት “ዘንድ” so that” ማለት ሲሆን ምክንያታዊ መስተዋድድ ሆኖ የገባ ነው። ስለዚህ የምንጾምበት ምክንያት አካልን ከሚበላና ከሚጠና በመከልከል እራስን ሙሉ ለሙሉ ለዒባዳህ በመስጠት “አላህን ለመፍራት” ነው፥ የጾም ድባቡ እራሱ ተቅዋ ያዘለ ዘርፈ ብዙ የአምልኮ መርሃ-ግብር ነው። “ተቅዋ” َتَقْوَى ማለት “አላህ መፍራት” ሲሆን “ሙተቂን” مُتَّقِين ደግሞ አላህ የሚፈራው “ፈሪሃን” ነው።

በመቀጠል በሽተኛና መንገደኛ በፆም ወቅት መፆም እንደሌለበትና እንዴት ቀዳ ማውጣት እንዳለበት ይነግረናል፦
2፥184 የተቆጠሩን ቀኖች ጹሙ፡፡ *"ከእናንተም ውሰጥ “በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነ ሰው” ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን መጾም አለበት፡፡ “በእነዚያም ጾምን በማይችሉት ላይ ቤዛ ድኻን ማብላት አለባቸው፡፡ ቤዛን በመጨመር መልካምንም ሥራ የፈቀደ ሰው እርሱ ፈቅዶ መጨመሩ ለርሱ በላጭ ነው፡፡ መጾማችሁም ለእናንተ የበለጠ ነው፥ የምታውቁ ብትኾኑ ትመርጡታላችሁ"*፡፡ أَيَّامًا مَّعْدُودَاتٍ ۚ فَمَن كَانَ مِنكُم مَّرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَرَ ۚ وَعَلَى الَّذِينَ يُطِيقُونَهُ فِدْيَةٌ طَعَامُ مِسْكِينٍ ۖ فَمَن تَطَوَّعَ خَيْرًا فَهُوَ خَيْرٌ لَّهُ ۚ وَأَن تَصُومُوا خَيْرٌ لَّكُمْ ۖ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

የምንጾምበት ወር ደግሞ በረመዷን ወር ነው፦
2፥185 *"እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ ያ በእርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድ እና እውነትን ከውሸት ከሚለዩም ገላጮች አንቀጾች ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው"*፡፡ شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ ۚ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ ۖ وَمَن كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَرَ ۗ يُرِيدُ اللَّهُ بِكُمُ الْيُسْرَ وَلَا يُرِيدُ بِكُمُ الْعُسْرَ وَلِتُكْمِلُوا الْعِدَّةَ وَلِتُكَبِّرُوا اللَّهَ عَلَىٰ مَا هَدَاكُمْ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ
የወር ስሞች ቅደም ተከተል፡-
1ኛው ወር- ሙሐረም
2ኛው ወር- ሰፈር
3ኛው ወር- ረቢዑል-አወል
4ኛው ወር- ረቢዑ-ሣኒ
5ኛው ወር- ጀማዱል-አወል
6ኛው ወር- ጀማዱ-ሣኒ
7ኛው ወር- ረጀብ
8ኛው ወር- ሻዕባን
9ኛው ወር- ረመዷን
10ኛው ወር- ሸዋል
11ኛው ወር- ዙል-ቀዒዳህ
12ኛው ወር- ዙል-ሒጃህ ናቸው።
የተቆጠሩ ቀኖች የያዘው ረመዷን 9ኛው ወር ሲሆን ይህ ወር የሚጾምበት ምክንያት ቁርኣን ከጥብቁ ሰሌዳ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ የወረደበት ወር ስለሆነ ነው። ረመዷን የወር ስም እንጂ የጾም ስም አይደለም። “ረመዷን” رمضان‎ ማለት “ድርቀት” “ሞቃታማ” ማለት ነው።

ነገር ግን በክርስትና ያሉት ሰባቱ አፅማዋት ማለትም ፅጌ፣ ገና፣ ነነዌ፣ ሁዳዴ፣ ሰኔ፣ፍልሰታ እና እሮብና አርብ የቤተክርስቲያን መሪዎች ቀስ በቀስ በጊዜ ሂደት የደነገጓቸው ሰው ሠራሽ ሕግ እንጂ የመለኮት ትእዛዞች አይደሉም። የነነዌ ጾምም ለነነዌ ሰዎች ለሶስት ቀን የተሰጠ እንጂ አማኞች እንዲጾሙ የታዘዘበት አንቀጽ አይደለም።
በእርግጥም አላህ ለቀደሙት ነቢያት የጾም መርሕ ደንግጎ እንደነበር በተከበረ ቃሉ ነግሮናል። ነገር ግን የአላህ ጥንታዊ ነቢያት የተሰጣቸው ወሕይ የተዋቀረበት አንጓ፣ የተናገሩበት ቋንቋ፣ የመልዕክቱ ምጥቀት ሆነ የቃላቱ ልቀት በዘመናችን እንደሌሉ የታሪክ ምሁራን ያትታሉ፥ ምክንያቱም ከመለኮት የመጣውን እውነት ከሰው ትምህርት ጋር በመጨመር ቀላቅለውታል፤ ከመለኮት የመጣውን እውነት በመቀነስ ደብቀውታል። በዚህም ጾም መቼ እንደሚፃም፣ እንዴት እንደሚፆም፣ ለምን እንደሚፆም፣ ከምን እንደሚጾም ሥረ-መሠረታዊ ጭብጥ በባይብል የለም።

በቁርኣን ግን እነዚህ ምክንያቶች ተገልጸዋል። በጾም ማፍጠሪያ ጊዜ መብላት መጠጣት ብቻ ሳይሆን ከሃላል ጥንድ ጋር ተራክቦ ማድረግም ተፈቅዷል፥ መግሪብ አዛን ካለበት እስከ ፈጅር የኾነው ነጩ ክር የተባለው ብርሃን ጥቁሩ ክር ከተባለው ጨለማ እስከሚለይ ድረስ የፈለግነውን የምግብ አይነት እንድንመገብ አምላካችን አላህ ፈቅዶልናል፦
2፥187 *“በጾም ሌሊት ወደ ሴቶቻችሁ መድረስ ለእናንተ ተፈቀደላችሁ፡፡ እነርሱ ለናንተ ልብሶች ናቸው፤ እናንተም ለእነርሱ ልብሶች ናችሁ፡፡ አላህ እናንተ ነፍሶቻችሁን የምትበድሉ መኾናችሁን ዐወቀ፡፡ በእናንተም ላይ ተመለሰላችሁ፤ ከእናንተም ይቅርታ አደረገ፡፡ አሁን ተገናኙዋቸው፡፡ አላህም ለእናንተ የጻፈላችሁን ነገር ልጅን ፈልጉ፡፡ “ከጎህ የኾነው ነጩ ክርም ከጥቁሩ ክር ለእናንተ እስከሚገልጽላችሁ ድረስ ብሉ፤ ጠጡም”፡፡ ከዚያም ጾምን እስከ ሌሊቱ ድረስ ሙሉ"*፡፡ أُحِلَّ لَكُمْ لَيْلَةَ الصِّيَامِ الرَّفَثُ إِلَىٰ نِسَائِكُمْ ۚ هُنَّ لِبَاسٌ لَّكُمْ وَأَنتُمْ لِبَاسٌ لَّهُنَّ ۗ عَلِمَ اللَّهُ أَنَّكُمْ كُنتُمْ تَخْتَانُونَ أَنفُسَكُمْ فَتَابَ عَلَيْكُمْ وَعَفَا عَنكُمْ ۖ فَالْآنَ بَاشِرُوهُنَّ وَابْتَغُوا مَا كَتَبَ اللَّهُ لَكُمْ ۚ وَكُلُوا وَاشْرَبُوا حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَكُمُ الْخَيْطُ الْأَبْيَضُ مِنَ الْخَيْطِ الْأَسْوَدِ مِنَ الْفَجْرِ ۖ ثُمَّ أَتِمُّوا الصِّيَامَ إِلَى اللَّيْلِ ۚ وَلَا تُبَاشِرُوهُنَّ وَأَنتُمْ عَاكِفُونَ فِي الْمَسَاجِدِ ۗ تِلْكَ حُدُودُ اللَّهِ فَلَا تَقْرَبُوهَا ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ آيَاتِهِ لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَتَّقُون

አላህ የሚጾመውን ወንድ ባሪያውን “ሷኢሚን” صَّآئِمِين ሲላቸው የምትጾመውን ሴት ባሪያውን ደግሞ “ሷኢማት” صَّآئِمَٰت ብሎ ይጠራቸዋል። አላህ ሷኢሚን እና ሷኢማት ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሣሚሪይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

20:85 አላህም እኛም ከአንተ በኋላ ሰዎችህን በእርግጥ ፈትተን፤ *ሳምራዊውም* አሳሳታቸው አለው። قَالَ فَإِنَّا قَدْ فَتَنَّا قَوْمَكَ مِن بَعْدِكَ وَأَضَلَّهُمُ السَّامِرِيُّ

“ሣሚሪይ” سَّامِرِىّ በሙሳ ዘመን ለእስራኢል ልጆች በእሳት አቅልጦ ወይፈን የሰራላቸው ሰው ነው፦
20:85 አላህም እኛም ከአንተ በኋላ ሰዎችህን በእርግጥ ፈትተን፤ *ሳምራዊውም* አሳሳታቸው አለው። قَالَ فَإِنَّا قَدْ فَتَنَّا قَوْمَكَ مِن بَعْدِكَ وَأَضَلَّهُمُ السَّامِرِيُّ
20:87 ቀጠሮህን በፈቃዳችን አልጣስንም፤ ግን እኛ ከሕዝቦቹ ጌጥ፣ ሸክሞችን ተጫን በእሳት ላይ ጣልናትም፤ *ሳምራዊውም* እንደዚሁ ጣለ አሉት። قَالُوا مَا أَخْلَفْنَا مَوْعِدَكَ بِمَلْكِنَا وَلَـٰكِنَّا حُمِّلْنَا أَوْزَارًا مِّن زِينَةِ الْقَوْمِ فَقَذَفْنَاهَا فَكَذَٰلِكَ أَلْقَى السَّامِرِيُّ
20:95 ሙሳ *ሳምራዊው* ሆይ ነገርህም ምንድነው? አለ። قَالَ فَمَا خَطْبُكَ يَا سَامِرِيُّ

እሱም የሰራላቸው አንድ ወይፈን የሆነ ጥጃ ነው፦
20፥88 ለእነሱም አካል የኾነ *ጥጃን* ለእርሱ መጓጎር ያለውን አወጣላቸው፡፡ ተከታዮቹ «ይህ አምላካችሁ የሙሳም አምላክ ነው ግን ረሳው» አሉም፡፡ فَأَخْرَجَ لَهُمْ عِجْلًا جَسَدًا لَّهُ خُوَارٌ فَقَالُوا هَـٰذَا إِلَـٰهُكُمْ وَإِلَـٰهُ مُوسَىٰ فَنَسِيَ
7፥148 የሙሳም ሕዝቦች ከእርሱ መኼድ በኋላ ከጌጦቻቸው *ወይፈንን አካልን ለእርሱ ማግሳት ያለውን አምላክ አድርገው ያዙ፡፡ እርሱ የማያናግራቸው መንገድንም የማይመራቸው መኾኑን አይመለከቱምን?* አምላክ አድርገው ያዙት፡፡ በዳዮችም ኾኑ፡፡ وَاتَّخَذَ قَوْمُ مُوسَىٰ مِن بَعْدِهِ مِنْ حُلِيِّهِمْ عِجْلًا جَسَدًا لَّهُ خُوَارٌ ۚ أَلَمْ يَرَوْا أَنَّهُ لَا يُكَلِّمُهُمْ وَلَا يَهْدِيهِمْ سَبِيلًا ۘ اتَّخَذُوهُ وَكَانُوا ظَالِمِينَ

ይህን ትረካ በመጠኑም ቢሆን ከፔንታተች ጋር ይመሳሰላል፦
ዘጸአት 32፥7-8 ያህዌህም ሙሴን፦ ከግብፅ ምድር ያወጣኸው ሕዝብህ ኃጢአት ሠርተዋልና ሂድ፥ ውረድ። ካዘዝኋቸው መንገድ ፈጥነው ፈቀቅ አሉ፤ *ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ምስል ለራሳቸው አደረጉ፥ ሰገዱለትም፥ ሠዉለትም*፤፦ እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ *ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው አሉ* ሲል ተናገረው።
ዘጸአት 32፥20 *የሠሩትንም ጥጃ ወስዶ በእሳት አቀለጠው፥ እንደ ትቢያም እስኪሆን ድረስ ፈጨው፥ በውኃውም ላይ በተነው*፥ ለእስራኤልም ልጆች አጠጣው።

እዚህ ጋር የተሰራው ጥጃ አንድ ጥጃ እንደሆነ ይናገራል፤ ሰሪውም አሮን ነው ብሎ ያስቀምጣል፤ “ሣሚሪይ” سَّامِرِىّ በዕብራይስጥ “ሳንበርይ” זִמְרִי በአማርኛ “ዘንበሪ” የተባለው ሰው ነው፦
ዘኍልቍ 25፥14 ከምድያማዊቱም ጋር የተገደለው የእስራኤላዊው ሰው ስም *ዘንበሪ* ነበረ፤
ይህ ሆኖ ሳለ ሚሽነሪዎች ሁለት የተለያዩ ታሪኮችን በማታታት ቁርአን የታሪክ ግድፈት እንዳለበት ለማሳየት ሲያምታቱ ይገኛሉ። “ሳንበርይ” זִמְרִי ማለትም “ዘንበሪ” የተባለውን ስም “ሰማሪይ” שומרון‎ ማለትም “ሰማሪያ” ጋር ደባልቀው ቁርኣን፦ “በሙሳ ዘመን ጥጃ ሰራ የሚለው ግለሰብ የሰማሪያ ሰዎችን ነው” ብለው ለመጠምዘዝ ይሞክራሉ፤ በ 930 BC በአስሩ ነገድ ይኖር የነበረው ዘንበሪ የተባለው ንጉሥ ሳምርም ከሚባል ሰው በሁለት መክሊት ብር የሰማርያን ተራራ ገዛ፤ በተራራውም ላይ ሠራ፥ የሠራውንም ከተማ በተራራው ባለቤት በሳምር ስም ሰማርያ ብሎ ጠራው፦
1ኛ ነገሥት 16፥24 *ከሳምርም* በሁለት መክሊት ብር የሰማርያን ተራራ ገዛ፤ በተራራውም ላይ ሠራ፥ የሠራውንም ከተማ በተራራው ባለቤት *በሳምር* ስም *ሰማርያ* ብሎ ጠራው።

ከዚያ በኃላ ያሉ ሕዝቦች “ሳምራውያን” ሲባሉ ወንዱ “ሳምራዊ” ሴቷ “ሳምራዊት” ይባላሉ፦
ሉቃስ10፥33 አንድ *ሳምራዊ* ግን ሲሄድ ወደ እርሱ መጣ አይቶትም አዘነለት፥
ሉቃስ 17፥16 እያመሰገነውም በእግሩ ፊት በግንባሩ ወደቀ፤ እርሱም *ሳምራዊ* ነበረ።
ዮሐንስ 4፥9 ስለዚህ *ሳምራዊቲቱ*፦ አንተ የይሁዳ ሰው ስትሆን *ሳምራዊት* ሴት ከምሆን ከእኔ መጠጥ እንዴት ትለምናለህ? አለችው፤ አይሁድ *ከሳምራውያን* ጋር አይተባበሩም ነበርና።
ዮሐንስ 8፥48 አይሁድ መልሰው፦ *ሳምራዊ* እንደ ሆንህ ጋኔንም እንዳለብህ በማለታችን እኛ መልካም እንል የለምን? አሉት።

ይህንን እሳቤ ከያዝን ሳምራውያን ከጊዜ በኃላ የአስሩ ነገዶች መጠሪያ ሆነ፤ ሳምራውያን ቀልጠው የተሠሩትንም የሁለቱን እንቦሶች ምስሎች አደረጉ፥ የማምለኪያ ዐፀድንም ተከሉ፥ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ ሰገዱ፥ በኣልንም አመለኩ፤ የሰሯቸው አማልክት ብዙ ናቸው፦
2 ነገሥት 17፥16 የአምላካቸውንም የያህዌን ትእዛዝ ሁሉ ተዉ፥ *ቀልጠው የተሠሩትንም የሁለቱን እንቦሶች ምስሎች አደረጉ*፥ የማምለኪያ ዐፀድንም ተከሉ፥ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ ሰገዱ፥ *በኣልንም አመለኩ*።
2 ነገሥት 17፥29 *በየሕዝባቸውም አምላካቸውን አደረጉ፥ ሰምራውያንም በሠሩት በኮረብታው መስገጃዎች ሕዝቡ ሁሉ በሚኖሩበት ከተሞቻቸው አኖሩአቸው*።

ታዲያ ይህ ታሪክ በየትኛው ቀመርና ስሌት ነው ከቁርአን ጋር የሚመሳሰለው? ሲጀመር ከመነሻው “ሳንበርይ” זִמְרִי የተባለውን ስም እና “ሰማሪይ” שומרון‎ የተባለው ስም አንድ ነውን? ሲቀጥል በሙሳ ጊዜ የነበረው ሳንበርይ አንድ ግለሰብ ሲሆን ከይሁዳ ንጉሥ ከአሳ በኃላ አማልክት የሰሩት ሳምራውያን ደግሞ ሕዝብ ናቸው፤ ሲሠልስ ቁርኣን ልክ እንደ ዘጸአት በሙሴ ጊዜ ተሰራ የሚለን አንድ ጥጃ ነው፤ ነገር ግን በተቃራኒው ሳምራውያን የሰሩት የሁለቱን እንቦሶች ምስሎች ናቸው።
ጥያቄ፦ እስራኤላውያው በምድረ በዳ ያሉት የቱን ነው? “ከግብፅ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው” ወይስ “ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው” ?
ነህምያ 9፥18 ቀልጦ የተሠራውንም እምቦሳ አድርገው፡— *ከግብፅ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው* ባሉ ጊዜ፥ እጅግም ባስቈጡህ ጊዜ፥
ዘጸአት 32፥4 ከእጃቸውም ተቀብሎ በመቅረጫ ቀረጸው፥ ቀልጦ የተሠራ ጥጃም አደረገው፤ እርሱም፡— እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ *ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው*፡ አላቸው።

ዘንበሪ ይኖር የነበረው በማን ዘመን ነው? በሙሴ ወይስ በይሁዳ ንጉሥ በአሳ?
ዘኍልቍ 25፥14 ከምድያማዊቱም ጋር የተገደለው የእስራኤላዊው ሰው ስም *ዘንበሪ* ነበረ፤
1ኛ ነገሥት 16፥23 በይሁዳ ንጉሥ በአሳ በሠላሳ አንደኛው ዓመት *ዘንበሪ* በእስራኤል ላይ አሥራ ሁለት ዓመት ነገሠ። በቴርሳም ስድስት ዓመት ነገሠ።

አይ ሁለቱ የተለያዩ ሰዎች ናቸው ካላችሁ እንግዲያውስ ቁርአን እየነገረን ያለው በሙሳ ጊዜ ስለነበረ ክስተት እንጂ በሰማርያውን ስለተከሰተው ክስተት አይደለም።
ሁለት ክስተት በተለያዩ ጊዜ ሲከናወኑ ታሪኩ አንድ ነው ብሎ መደምደም ቂልነት ነው። ለምሳሌ በሉጥ ዘመን የነበሩ ሰዎች ወንድ ለወንድ ለተራክቦ ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል፦
ዘፍጥረት 19፥5-9 *ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት፤ በዚህ ሌሊት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው*። *ሎጥም ወደ እነርሱ ወደ ደጅ ወጣ መዝጊያውንም በኋላው ዘጋው*፤
እንዲህም አለ፦ ወንድሞቼ ሆይ፥ *ይህን ክፉ ነገር አታድርጉ፤ እነሆ፥ ወንድን ያላወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ላውጣላችሁ፥ እንደ ወደዳችሁም አድርጓቸው*፤ በእነዚህ ሰዎች ብቻ ምንም አታድርጉ፥ እነርሱ በጣራዬ ጥላ ሥር ገብተዋልና።

ይህ ድርጊት በመሳፍንቱ ዘመን የነበሩ ሰዎች ወንድ ለወንድ ለተራክቦ ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል፦
መሣፍንት 19፥22-25 ሰውነታቸውንም ደስ ባሰኙ ጊዜ ወስላቶች የሆኑ *የከተማው ሰዎች ቤቱን ከበቡ በሩንም ይደበድቡ ነበር፤ ባለቤቱንም ሽማግሌውን፦ ወደ ቤትህ የገባውን ሰው እንድንደርስበት አውጣልን፡ አሉት። ባለቤቱም ሽማግሌው ወደ እነርሱ ወጥቶ፦ ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህን ክፉ ነገር፥ እባካችሁ፥ አታድርጉ፤ ይህ ሰው ወደ ቤቴ ገብቶአልና እንደዚህ ያለ ኃጢአት አትሥሩ። ድንግል ልጄና የእርሱም ቁባት፥ እነሆ፥ አሉ፥ አሁንም አወጣቸዋለሁ፤ አዋርዱአቸው እንደ ወደዳችሁም አድርጉባቸው፤ ነገር ግን በዚህ ሰው ላይ እንደዚህ ያለ ኃጢአት አታድርጉ፡ አላቸው። ሰዎቹ ግን ነገሩን አልሰሙም፤ ሰውዮውም ቁባቱን ይዞ አወጣላቸው፤ ደረሱባትም፥ ሌሊቱንም ሁሉ እስኪነጋ ድረስ አመነዘሩባት፤ ጎህ በቀደደም ጊዜ ለቀቁአት*።

ያ ማለት ሁለት ተመሳሳይ ክስተት ግን በተለያየ ጊዜ የሆኑ ክንውኖች ናቸው ካላችሁ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን እሳቤ በዚህ መልክና ልክ ተረዱት።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
በአላህ ስም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

96፥1 *"አንብብ በዚያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም"*፡፡ اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ

አምላካችን አላህ በጂብሪል ለነቢያችን”ﷺ” “ኢቅራ” اقْرَأْ ማለትም “አንብብ” ወይም “አነብንብ” ብሎ አዟቸዋል፦
96፥1 *"አንብብ በዚያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም"*፡፡ اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ

“ቁርኣን” قُرْءَان የሚለው ቃል “ቀረአ” قَرَأَ ማለትም “አነበበ” ወይም “አነበነበ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “መነባነብ”recitation” ማለት ነው። “ኢቅራ” اقْرَأْ ትእዛዛዊ ግስ ሲሆን ቁርኣን ሲጀምር የሚነበበው "ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም" ነው፥ ከአንድ ሱራህ በስተቀር እያንዳንዱ ሱራህ ሲጀምር “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በኾነው” በሚል ነው። ይህቺ ሱራህ ሱረቱ "አት-ተውባህ" ናት። 9ኛው ሱራህ ተስሚያህ ባይኖራትም ሱረቱ አን-ነምል 27፥30 ላይ ይደግመዋል። ይህም ሱረቱ አት-ተውባህ የቁጣ ሱራህ ሆና ብትዘለልም ስትደመር ዘጠኝ የሆነችው ሱረቱ አን-ነምል ላይ ትገኛለች። 2+7=9 ይሆናል፦
27፥30 እርሱ ከሱለይማን ነው፡፡ እርሱም *"በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በኾነው"*፡፡ إِنَّهُ مِن سُلَيْمَانَ وَإِنَّهُ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ

አንድ ሱራህ ከሌላው ሱራህ የሚለየው “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” በሚል ቃል ነው፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 398
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *"ነቢዩ”ﷺ” ሁለት ሱራዎች አይለያዩ በመካከላቸው “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” የሚለው ቃል ወደ እርሳቸው ቢወርድላቸው እንጂ"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم لاَ يَعْرِفُ فَصْلَ السُّورَةِ حَتَّى تُنَزَّلَ عَلَيْهِ ‏{‏ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ ‏}

ያጅባል በጣም። "ቱነዘለ ዐለይሂ" تُنَزَّلَ عَلَيْهِ ማለትም "ወደ እርሳቸው ቢወርድላቸው" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيم ማለትም “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” ከአላህ ወደ ነቢያችን"ﷺ" እኛ እንድናነበው የወረደ ነው፦
29፥45 ከመጽሐፍ *ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ*፡፡ اتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِنَ الْكِتَابِ
18፥27 ከጌታህም መጽሐፍ *ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ*፡፡ وَاتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن كِتَابِ رَبِّك

"አንብብ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ስለዚህ "በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው" የሚለው እኛ እንድናነበው ከአላህ የወረደ ነው። "አንብብ በዚያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም" ብሎ ያ የጌታ ስም ደግሞ፦ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው" መሆኑን ነግሮናል። ክርስቲያን ፕሪንስ፦ "ቁርኣን የአላህ ንግግር ከሆነ አላህ ለምን "በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው" ይላል? "በእኔ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆንኩት" ለምን አይልም? የሚል የቂል ጥያቄ ይጠይቃል። እኛም መልሳችን እኛ ቁርኣንን ስንቀራ በጌታ ስም እንዴት እንደምናነብ ሲነግረን ነው። ፈጣሪ እራሱን በሦስተኛ መደብ አድርጎ መናገር የተለመደ ነው። ለምሳሌ፦ ፈጣሪ “የያህዌህን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ ያህዌህ ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና” ይለናል፦
ዘጸአት 20፥7 *የያህዌህን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ ያህዌህ ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና*።

"የያህዌህን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ ያህዌህ ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና" ብሎ የተናገረው ያህዌህ ከሆነ ያህዌህ ለምን በመጀመሪያ መደብ "የእኔን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ እኔ ስሜን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አላነጻውምና" ብሎ አልተናገረም? ብለን ጥያቄ ስናቀርብ "ያህዌህ እራሱ በሦስተኛ መደብ መናገር ሙሉ መብት አለው" የሚል መልስ ይሰጣሉ። እንግዲያውስ በሰፈራችሁ ቁና መስፈር ይሏችኃል እንደዚህ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የኢብራሂም መንገድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።

16፥123 *ከዚያም ወደ አንተ፦ "የኢብራሂምን መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን ተከተል! ከአጋሪዎቹም አልነበረም" ማለት አወረድን*፡፡ ثُمَّ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ أَنِ اتَّبِعْ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۖ وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِين

“ኢሥላም” إِسْلَٰم ማለትም “መታዘዝ” ወይም “መገዛት” ማለት ሲሆን አላህ ዘንድ ዕውቅና ያለ ሃይማኖት ኢሥላም ብቻ ነው፦
3፥19 *"አላህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት “ኢሥላም” ብቻ ነው"*፡፡ إِنَّ ٱلدِّينَ عِندَ ٱللَّهِ ٱلْإِسْلَٰمُ

አላህ ሰዎችን ሁሉ የፈጠረበት ሃይማኖት ኢሥላም ነው፦
30፥30 *"ፊትህንም ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት ያዟት፡፡ የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም፡፡ ይህ ቀጥተኛ ሃይማኖት ነው"*፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡ فَأَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا ۚ فِطْرَتَ اللَّهِ الَّتِي فَطَرَ النَّاسَ عَلَيْهَا ۚ لَا تَبْدِيلَ لِخَلْقِ اللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ቀጥተኛ" ለሚለው ቃል የገባው "ሐኒፋ" حَنِيفًا ሲሆን አላህ ሰዎችን ሁሉ የፈጠረበት ሃይማኖት ኢሥላም "ሐኒፋ" መሆኑን ያሳያል። አምላካችን አላህ ለኢብራሂም “አሥሊም” أَسْلِمْ ማለትም “ታዘዝ” ብሎ ሲለው እርሱም ለዓለማት ጌታ “አሥለምቱ” أَسْلَمْتُ ማለትም “ታዘዝኩ” አለ፥ ኢብራሂም ወደ ቀጥተኛው የተዘነበለ ሙሥሊም ነበረ፦
2፥131 *"ጌታው ለእርሱ "ታዘዝ” ባለው ጊዜ መረጠው፡፡ ለዓለማት ጌታ ”ታዘዝኩ” አለ"*፡፡ إِذْ قَالَ لَهُۥ رَبُّهُۥٓ أَسْلِمْ ۖ قَالَ أَسْلَمْتُ لِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
3፥67 *"ኢብራሂም ይሁዳዊም ክርስቲያንም አልነበረም፡፡ ግን "ወደ ቀጥተኛው የተዘነበለ ሙሥሊም ነበረ"፡፡ ከአጋሪዎችም አልነበረም"*፡፡ مَا كَانَ إِبْرَاهِيمُ يَهُودِيًّا وَلَا نَصْرَانِيًّا وَلَـٰكِن كَانَ حَنِيفًا مُّسْلِمًا وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

“ሙሥሊም” مُسْلِم የሚለው ቃል “አሥለመ” أَسْلَمَ ማለትም "ታዘዘ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ታዛዥ” ማለት ነው፥ አሁንም እዚህ አንቀጽ ላይ "ቀጥተኛ" ለሚለው ቃል የገባው "ሐኒፋ" حَنِيفًا ነው። "ሐኒፍ" حَنِيف ማለት "ቀጥተኛ" ማለት ሲሆን ለአላህ ቀጥ ያሉ "ቀጥተኞች" ደግሞ "ሑነፋ" حُنَفَاءَ ይባላሉ፦
22፥31 *"ለአላህ ቀጥተኞች በእርሱ የማታገሩ ሆናችሁ ከሐሰት ራቁ"*፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ከሰማይ እንደ ወደቀና በራሪ እንደምትነጥቀው ወይም ነፋስ እርሱን በሩቅ ስፍራ እንደምትጥለው ብጤ ነው፡፡ حُنَفَاءَ لِلَّهِ غَيْرَ مُشْرِكِينَ بِهِ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَكَأَنَّمَا خَرَّ مِنَ السَّمَاءِ فَتَخْطَفُهُ الطَّيْرُ أَوْ تَهْوِي بِهِ الرِّيحُ فِي مَكَانٍ سَحِيقٍ
98፥5 አላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ አጥሪዎች፣ *"ቀጥተኞች ኾነው ሊያመልኩት"*፣ ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ ዘካንም ሊሰጡ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ተለያዩ፡፡ ይህም የቀጥተኛይቱ ሃይማኖት ድንጋጌ ነው፡፡ وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ حُنَفَاءَ وَيُقِيمُوا الصَّلَاةَ وَيُؤْتُوا الزَّكَاةَ ۚ وَذَٰلِكَ دِينُ الْقَيِّمَة

ኢብራሂም እራሱ ሐኒፍ ሲሆን እርሱ የተጓዘበት መንገድ ደግሞ ሐኒፋ ነው፦
2፥135 አይሁድን ወይም ክርስቲያኖችን ኹኑ! ቅኑን መንገድ ትመራላችሁና» አሉም፡፡ «አይደለም *"የኢብራሂምን መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን እንከተላለን"*፤ ከአጋሪዎችም አልነበረም» በላቸው፡፡ وَقَالُوا كُونُوا هُودًا أَوْ نَصَارَىٰ تَهْتَدُوا ۗ قُلْ بَلْ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۖ وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

"ሚላህ" مِلَّة ማለት "መንገድ" ማለት ነው፥ ይህም የኢብራሂም መንገድ ሐኒፋ ነው፦
3፥95 «አላህ እውነትን ተናገረ፡፡ *"የኢብራሂምንም መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን ተከተሉ"*፡፡ ከአጋሪዎቹም አልነበረም» በላቸው፡፡ قُلْ صَدَقَ اللَّهُ ۗ فَاتَّبِعُوا مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِين
4፥125 *"እርሱ መልካም ሠሪ ኾኖ ፊቱን ለአላህ ከሰጠና የኢብራሂምንም መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን ከተከተለ ሰው ይበልጥ ሃይማኖቱ ያማረ ማን ነው? አላህም ኢብራሂምን ፍጹም ወዳጅ አድርጐ ያዘው"*፡፡ وَمَنْ أَحْسَنُ دِينًا مِّمَّنْ أَسْلَمَ وَجْهَهُ لِلَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ وَاتَّبَعَ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۗ وَاتَّخَذَ اللَّهُ إِبْرَاهِيمَ خَلِيلًا
6፥79 *«እኔ ለእዚያ ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረው አምላክ ቀጥተኛ ስኾን ፊቴን አዞርኩ፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም» አለ*፡፡ إِنِّي وَجَّهْتُ وَجْهِيَ لِلَّذِي فَطَرَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ حَنِيفًا ۖ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ
የኢብራሂም መንገድ ሐኒፋ ሲሆን አላማው ሁለንተናን ለአላህ መስጠት ነው፥ "የሰጠ" ለሚለው ቃል የገባው "አሥለመ" أَسْلَمَ ነው።
ነቢያችን"ﷺ" ወደ እርሳቸው ወሕይ ከመውረዱ ይህንን የኢብራሂም መንገድ ይተገብሩ ነበር፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 1 ሐዲስ 3
የምዕመናን እናት ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"ከወሕይ ጅማሬ ለአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ልክ እንደ ጎህ ንጋት ደማቅ ሆኖ በሰናይ ህልም ሁኔታ ነበር። ከዚያም የተማልሎ ውዴታ በእርሷቸው ላይ ነበር። በሒራእ ዋሻ ውስጥ ይገለሉ እና "ቀጥ ይሉ ነበር"። እርሳቸውም ቤተሰባቸውን ለማየት ከመፈለጋቸው በፊት ለብዙ ቀናት በተከታታይ አላህ ያመልኩ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ الْمُؤْمِنِينَ، أَنَّهَا قَالَتْ أَوَّلُ مَا بُدِئَ بِهِ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم مِنَ الْوَحْىِ الرُّؤْيَا الصَّالِحَةُ فِي النَّوْمِ، فَكَانَ لاَ يَرَى رُؤْيَا إِلاَّ جَاءَتْ مِثْلَ فَلَقِ الصُّبْحِ، ثُمَّ حُبِّبَ إِلَيْهِ الْخَلاَءُ، وَكَانَ يَخْلُو بِغَارِ حِرَاءٍ فَيَتَحَنَّثُ فِيهِ ـ وَهُوَ التَّعَبُّدُ ـ اللَّيَالِيَ ذَوَاتِ الْعَدَدِ قَبْلَ أَنْ يَنْزِعَ إِلَى أَهْلِهِ

"ቀጥ ይሉ ነበር" ለሚለው የግስ መደብ የገባው "የተሐነሱ" يَتَحَنَّثُ ሲሆን ኢብኑ ሐጀሩል አሥቀላኒ በፈተሑል ባሪ ፊ ሸርህ ሰሒሑል ቡኻርይ ሐዲስ 3 ላይ፦ "የተሐነሱ" يَتَحَنَّثُ ማለት "የተሐነፉ" يَتَحَنَّفُ ማለት ነው ብለው አስቀምጠዋል፦
قوله : ( فيتحنث ) ‏
‏هي بمعنى يتحنف ، أي : يتبع الحنفية وهي دين إبراهيم ، والفاء تبدل ثاء في كثير من كلامهم . وقد وقع في رواية ابن هشام في السيرة " يتحنف " بالفاء أو التحنث إلقاء الحنث وهو الإثم ، كما قيل يتأثم ويتحرج ونحوهما .

ልብ አድርግ የኢብራሂም መንገድ አላህ ሰዎችን ሁሉ የፈጠረበት ኢሥላም ነው፥ ሲቀጥል አላህ በኢብራሂም ዝርዮች ውስጥ ይመለሱ ዘንድ በአንድ አምላክ የማመን ቀሪ ቃል አድርጓል፦
43፥28 *"በዝርዮቹም ውስጥ ይመለሱ ዘንድ ቀሪ ቃል አደረጋት"*፡፡ وَجَعَلَهَا كَلِمَةً بَاقِيَةً فِي عَقِبِهِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

ነቢያችን"ﷺ" ደግሞ የኢብራሂም ዝርያ ናቸው። ከዚያ በኃላ አላህ ቁርኣንን በማውረድ "ቁል" قُلْ በሚል ትእዛዝ የኢብራሂምን መንገድ ቀጥተኛ ሲሆን መራቸው፦
6፥161 *«እኔ ጌታዬ ወደ ቀጥተኛው መንገድ ትክክለኛን ሃይማኖት "ቀጥተኛ" ሲኾን የኢብራሂምን መንገድ መራኝ፡፡ እርሱም ከአጋሪዎቹ አልነበረም» በል"*፡፡ قُلْ إِنَّنِي هَدَانِي رَبِّي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ دِينًا قِيَمًا مِّلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۚ وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ
10፥105 *"ፊትህንም ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ቀጥ አድርግ"*፡፡ ከአጋሪዎቹም አትሁን፡፡ وَأَنْ أَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

ይህ ዲን ሐኒፋ የሆነው ኢሥላም እንደሆነ እና ኢሥላም ማለት መታዘዝ ማለት እንደሆነ ከላይ አይተናል፥ ቁርኣን ደግሞ "ትእዛዝ" ሆኖ ወደ እርሳቸው ወርዷል፦
65፥5 *"ይህ "የአላህ ትእዛዝ ነው”። ወደ እናንተም አወረደው"*። ذَٰلِكَ أَمْرُ ٱللَّهِ أَنزَلَهُۥٓ إِلَيْكُمْ

ይህንን ትእዛዝ ተቀብለው የታዘዙ የመጀመሪያው ታዛዥ እርሳቸው ናቸው፦
6፥14 *«እኔ መጀመሪያ ትእዛዝን ከተቀበለ ሰው ልኾን ታዘዝኩ*"፡፡ ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትኹን ተብያለሁ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنِّىٓ أُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَسْلَمَ ۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ

“ትእዛዝን ከተቀበለ” የሚለው ይሰመርበት። "ትእዛዝን የተቀበለ" ለሚለው ቃል የገባው "አሥለመ" أَسْلَمَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፥ "አወል" أَوَّل ማለትም "መጀመሪያ" በአንጻራዊነት ደረጃ የመጣ ገላጭ ነው። እንግዲህ ቁርኣንን ተቀብሎ ከሠለሙት ሙሥሊሞች መጀመሪያ ነቢያችን"ﷺ" ናቸው ማለት ነው፦
6፥163 *"«ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም በማጥራት ታዘዝኩ፡፡ እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ» በል"*፡፡ لَا شَرِيكَ لَهُۥ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلْمُسْلِمِينَ
3፥20 ቢከራከሩህም፡- *"«ፊቴን ለአላህ ሰጠሁ፤ የተከተሉኝም ሰዎች እንደዚሁ ለአላህ ሰጡ»* በላቸው፡፡ فَإِنْ حَاجُّوكَ فَقُلْ أَسْلَمْتُ وَجْهِيَ لِلَّهِ وَمَنِ اتَّبَعَنِ

"ሰጠሁ" ለሚለው ቃል የገባው "አሥለምቱ" أَسْلَمْتُ ሲሆን እርሳቸው ቀጥሎ ተከታዮቻቸው ሁለንተናቸውን ለአላህ ያሠለሙ መሆናቸውን ፍንትው አርጎ ያሳያል። ነቢያችን"ﷺ" ከአላህ ወደ እርሳቸው በተወረደው ቁርኣን አምነዋል፥ ተከታዮቻቸውም እንደዚሁ አመኑ፦
2፥285 *"መልክተኛው ከጌታው ወደ እርሱ በተወረደው አመነ፡፡ ምእምኖቹም እንደዚሁ አመኑ"*፡፡ آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِ وَالْمُؤْمِنُون

"ሙዕሚኑን" مُؤْمِنُون ማለት አማኞች ማለት ነው። "ኢማን" إِيمَان ማለት "አመነ" آمَنَ ማለትም "አመነ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "እምነት" ማለት ነው። ቁርኣን ትእዛዝ ሆኖ ወደ ነቢያችን"ﷺ" ከመውረዱ በፊት ቁርኣንን ሆነ በቁርኣን ላይ እምነቱ ምን እንደሆነ ዐያውቁም ነበር፦
42፥52 እንደዚሁም *"ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲኾን መንፈስን (ቁርኣንን) አወረድን፡፡ መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም"*፡፡ ግን መንፈሱን ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው፡፡ አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ፡፡ وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ رُوحًا مِّنْ أَمْرِنَا ۚ مَا كُنتَ تَدْرِي مَا الْكِتَابُ وَلَا الْإِيمَانُ وَلَـٰكِن جَعَلْنَاهُ نُورًا نَّهْدِي بِهِ مَن نَّشَاءُ مِنْ عِبَادِنَا ۚ وَإِنَّكَ لَتَهْدِي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيم

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሡሑር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

"ሡሑር" سُّحُور ወይም "ሠሑር" سَّحُور ማለት ቋንቋዊ ፍቺው "ሠሐር" سَحَر ማለት ነው። "ሠሐር" سَحَر ማለት "የሌሊት መጨረሻ" ማለት ነው። "ሠሐር" سَحَر የሌሊት መጨረሻ በሚል ቃል ሦስት ጊዜ ቁርኣን ውስጥ መጥቷል፦
3፥17 ታጋሾች እውነተኞችም ታዛዦችም ለጋሶችና *"በሌሊት መጨረሻዎች"* ምሕረትን ለማኞች ናቸው፡፡ الصَّابِرِينَ وَالصَّادِقِينَ وَالْقَانِتِينَ وَالْمُنفِقِينَ وَالْمُسْتَغْفِرِينَ بِالْأَسْحَارِ
51፥18 *"በሌሊቱ መጨረሻዎችም"* እነርሱ ምሕረትን ይለምናሉ፡፡ وَبِالْأَسْحَارِ هُمْ يَسْتَغْفِرُونَ
54፥34 እኛ በእነርሱ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን ላክን፡፡ የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ እነርሱንስ *"በሌሊት መጨረሻ"* ላይ አዳንናቸው፡፡ إِنَّا أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ حَاصِبًا إِلَّا آلَ لُوطٍ ۖ نَّجَّيْنَاهُم بِسَحَرٍ

"ሡሑር" سُّحُور ማለት ሃይማኖታዊ ፍቺው ደግሞ በሌሊት መጨረሻዎች ከፈጅር አዛን በፊት ለጾም መያዢያ የሚበላ ምግብ ነው። ይህንን የሌሊት ምግብ መብላት የዚህችን ኡማ የጾም ሥርዓት ካለፉት አህሉል ኪታብ የሚለይበት ሥርዓት ነው፦
ሱነን ነሳኢ መጽሐፍ 22 , ሐዲስ 77
ዐምር ኢብኑል ዐስ እንደተረከው፦;"የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"በእኛ ጾም እና በአህሉል ኪታብ ጾም መካከል ያለው ልዩነት ሡሑር ነው"*። عَنْ عَمْرِو بْنِ الْعَاصِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ فَصْلَ مَا بَيْنَ صِيَامِنَا وَصِيَامِ أَهْلِ الْكِتَابِ أَكْلَةُ السُّحُورِ ‏

ሡሑርን መመገብ የሚኖረው ትሩፋት ረድኤታዊ በረከት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 30, ሐዲስ 32
አነሥ ኢብኑ ማሊክ ሰምቶ እንዳስተላለፈው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ሡሑርን ብሉ! በሠሑር ውስጥ በረከት አለና”*። قَالَ سَمِعْتُ أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ تَسَحَّرُوا فَإِنَّ فِي السَّحُورِ بَرَكَةً

"ተሠሐሩ" تَسَحَّرُوا የሚለው የግስ መደብ "ሠሑር" سَّحُور ከሚለው የስም መደብ የረባ ቃል ነው። አምላካችን አላህ፦ “መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፤ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ” ስላለን ሡሑርን መብላት ከነቢያችን"ﷺ" ያገኘነው ሱናህ ነው፦
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

ነቢያችን"ﷺ" የአላህ ነብይ ስለሆኑ በዐቂዳህ እና በፊቅህ ጉዳይ ላይ የሚናገሩት ሁሉ ወሕይ ነው። ኢሥላም ሰው ሠራሽ ሕግ ሳይሆን ዐቂደቱል ረባንያ ነው። ይህንን በቅጡ የማያውቁ ሰዎች፦ "የሙሥሊም ጾም ማለት ሌሊቱ ወደ መዓልት ተቀይሮ ሌሊቱ በሙሉ ሲበላ ይታደርና በመዓልት የሚተኛበት" ይመስለዋል። ይህ የተሳሳተ መረዳት ነው። ሙሥሊም መግሪብ አዛን ሲል ያፈጥራል እስከ ዒሻህ ሊበላ ይችላል። በዚህ ጊዜም ጾመኛ ማስፈጠር፣ ሰደቃ፣ ዳዕዋህ በማድረግ መሽጉል ነው። ዒሻህ ከተቆመ በኃላ ተራዊሕ ሶላት ይቀጥላል፥ ከዚያ ሶላቱል ለይል አለ። ይህ ሁሉ ዘርፈ-ብዙ እና መጠነ-ሰፊ አምልኮ ለምሳሌ ዚክር፣ ዱዓ፣ ቂርኣት፣ የሱናህ ሶላት ወዘተ.. ከተካሄደ በኃላ የፈጅር ሶላት አዛን ከማለቱ በፊት በሡሑር ይያዛል። ይህንን ካላወክ ቀረብ ብለክ አንድ ቀን ማየት ነው። በተለይ አውሮፓ አካባቢማ ጾሙ በጋ ላይ ከዋሉ ጾሙ 19-21 ሰአት ያክል ይጾማል። ከ 3-5 ሰአት ምግብ በማፍጠር የተበላው ቁጭ ብሎ ሡሑር የሚቀመሰው ለሱናው ያክል በወፍ በረር ነው። ይህንን የመለኮት ሕግና ሥርዓት የያዘው ጾም የምትተቹ አላህ ሂዳያህ ይስጣችሁ፥ ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተራዊሕ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

“ዒባዳህ” عِبَادَة ማለትም “አምልኮ” አላህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኝባቸው ሥስት ሸርጦች ኢማን፣ ኢኽላስ እና ኢቲባዕ ናቸው። “ኢቲባዕ” إتباع የሚለው ቃል “አትበዐ” أَتْبَعَ “ተከተለ” ከሚለው የመጣ ሲሆን “መከተል” ማለት ሲሆን ያለ ኢቲባዕ ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም። ኢቲባዕ ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው ብቻ ዒባዳህን መፈጸም ነው፦
7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ*፤ اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ
6፥106 *ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን ተከተል* ፡፡ اتَّبِعْ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ

“ተከተሉ” የሚለው ቃል “ኢተቢዑ” اتَّبِعُوا ሲሆን “ኢቲባዕ” إتباع ማለት እንግዲህ ከአላህ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደውን ብቻ መከተል ነው፤ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደው ደግሞ ቁርኣን እና ሰሒሕ ሐዲስ ነው።
“ቢድዓ” بدع ደግሞ “በደዐ” بدع ማለትም “ፈጠረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ኢብቲዳዕ” ابتداع ማለትም “ፈጠራ” ማለት ነው፤ ቢድዓ የኢቲባዕ ተቃራኒ ነው። ቢድዓ ማለት ከአምስቱ አሕካም ውጪ አዲስ ፈጠራ ማለት ነው፤ ስለ ቢድዓ ነቢያችን”ﷺ” እንዲህ ይሉናል፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 53, ሐዲስ 7
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ማንኛውም ሰው ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም”* عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ فِيهِ فَهُوَ رَدٌّ ‏”‌‏.‏
ሡነን ነሣኢ : መጽሐፍ 19, ሐዲስ 23
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሑጥባቸው ላይ እንደተናገሩት፦ *“አላህ የመራውን ማንም አያጠመውም፤ አላህ ያጠመመውን ማንም አያቀናውም። ከንግግር ሁሉ በላጩ የአላህ መጽሐፍ ነው፤ ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነው። ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው*። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ فِي خُطْبَتِهِ يَحْمَدُ اللَّهَ وَيُثْنِي عَلَيْهِ بِمَا هُوَ أَهْلُهُ ثُمَّ يَقُولُ مَنْ يَهْدِهِ اللَّهُ فَلَا مُضِلَّ لَهُ وَمَنْ يُضْلِلْهُ فَلَا هَادِيَ لَهُ إِنَّ أَصْدَقَ الْحَدِيثِ كِتَابُ اللَّهِ وَأَحْسَنَ الْهَدْيِ هَدْيُ مُحَمَّدٍ وَشَرُّ الْأُمُورِ مُحْدَثَاتُهَا وَكُلُّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلُّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ وَكُلُّ ضَلَالَةٍ فِي النَّارِ .

ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ከሆነ ካየን ቢድዓ የሚያራምድ ማንኛውም ሰው “ሙብተዲዕ” مبتدئ ይባላል።
ይህንን ለቅምሻ ያክል በወፍ በረር ካየን ዘንዳ ሚሽነሪዎች፦ “ተራዊሕ” تراويح‌‎ ማለትም “በረመዳን የሌሊት ሶላት” ነቢያችን”ﷺ” የማያውቁትና ያልሠሩት ነው ብለው ለሚቀጥፉት ቅጥፈት ምላሽ መስጠት ግድ ይላል፤ ስለ ተራዊህ ከነቢያችን”ﷺ” ሱናህ በቁና ማቅረብ ይቻላል፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 31, ሐዲስ 4
የነብዩ”ﷺ” ባልተቤት ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ *”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” በረመዳን ሌሊት ይጸልዩ ነበር”*። عَنْ عَائِشَةَ، رضى الله عنها زَوْجِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم صَلَّى وَذَلِكَ فِي رَمَضَانَ‏.‏
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 31, ሐዲስ 1
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ስለ ረመዳን እንደተናገሩት፦ *”ማንም በረመዳን ሌሊት በእምነት እና ከአላህ ወሮታ አገኛለው ብሎ ተስፋ አድርጎ ከቆመ ያለፈው ወንጀሉ ሁሉ ይቅር ይባልለታል”*። أَنَّ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ لِرَمَضَانَ ‏ “‏ مَنْ قَامَهُ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ ‏”‌‏.‏

አምላካችን አላህ፦ “መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፤ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ” ስላለን ተራዊሕ መልእክተኛው የነገሩን ነገር ስለሆነ ቢድዓ አይደለም፦
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አንዱ ተመላኪ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

ኢየሱስ ለሰይጣን፦ "ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና" ብሎታል፦
ማቴዎስ 4፥10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ *እርሱንም ብቻ አምልክ* αὐτῷ μόνῳ λατρεύσεις ተብሎ ተጽፎአልና አለው።

"አውቶ" αὐτῷ ማለት "እርሱ"him" ማለት ሲሆን ነጠላ ተውላጠ-ስም መሆኑ አንድ ነጠላ ማንነት ብቻ እንደሚመለክ ያሳያል፥ ከአንድ በላይ የሚመለኩ ማንነት ቢሆን ኖሮ "አውቶኢስ" αὐτοῖς ማለትም "እነርሱ"them" ይሆን ነበር። ይህ ጌታ አምላክ ለኢየሱስ የዳዊትን ዙፋን የሰጠው አብ ነው፦
ሉቃስ 1፥32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ *ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል*።

ይህ ጌታ አምላክ ከበጉ ማንነት በሰዋስው ተነጥሎ ተቀምጧል፦
ራእይ 21፥22 *"ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እና በጉ መቅደስዋ ናቸውና"* መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም።

ልብ አድርግ "ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ" እና "በጉ" ሁለት ማንነት እንደሆኑ ለማሳየት "ናቸው" በሚል የብዜት አያያዥ ግስ ተቀምጧል፥ በተጨማሪም "እና" በሚል መስተጻምር ተለይተዋል። ስለዚህ "ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ" እና "በጉ" ሁለት ማንነት ናቸው፥ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ አብ ከሆነ "በጉ" ደግሞ ኢየሱስ ነው። በጉ የሚታረድ ማንነት ስለሆነ ፍጡር ነው፦
ራእይ 5፥12 በታላቅም ድምፅ፦ *"የታረደው በግ"* ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል፥ አሉ።

መለኮት የሆነው ጌታ አምላክ ስጋ ስላልሆነ መቼም አይታረድም። እንደ ባይብሉ የታረደው በግ ሰው የሆነው ኢየሱስ ከሆነ ሰው አይመለክም፦
ራእይ 22፥3 *"የእግዚአብሔር እና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል"*፥ λατρεύσουσιν αὐτῷ ፊቱንም ያያሉ።

እግዚአብሔር እና በጉ ሁለት ማንነት መሆናቸው ለማሳየት አሁንም "እና" በሚል መስተጻምር ተለይተዋል። አሁንም "አውቶ" αὐτῷ ማለት "እርሱ"him" ማለት ሲሆን ነጠላ ተውላጠ-ስም መሆኑ አንድ ነጠላ ማንነት ብቻ እንደሚመለክ ያሳያል፥ ከአንድ በላይ የሚመለኩ ማንነት ቢሆን ኖሮ "አውቶኢስ" αὐτοῖς ማለትም "እነርሱ"them" ይሆን ነበር። "ያመልኩታል" እንጂ "ያመልኳቸዋል" አላለም፥ ይህ የሚመለክ እግዚአብሔር እንጂ በጉ አይደለም፦
ራእይ 7፥15 ስለዚህ *"በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አሉ፥ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ ያመልኩታል"*።
ራእይ 7፥17 በዙፋኑ መካከል ያለው *"በጉ እረኛቸው ይሆናልና"*።

ልብ አድርግ "አውቶ" αὐτῷ ማለትም "እርሱ"him" የሚለው ተክቶ የመጣው "እግዚአብሔር" የሚለውን ቃል ነው፥ "ያመልኩታል" የተባለው በግልጽና በማያሻማ "እግዚአብሔርን" ነው። በጉ ከእግዚአብሔር በሰዋሰው አቀማመጥ ተነጥሎ "እረኛቸው ይሆናልና" የተባለው።
አንዳንድ ቂሎች፦ "የእግዚአብሔር እና የበጉ ዙፋን አንድ ዙፋን ነው፥ ስለዚህ በጉ ይመለካል" ይላሉ፥ ለመሆኑ ሰለሞን የተቀመጠበት ዙፋን የማን ነው የእግዚአብሔር ወይስ የዳዊት? እስቲ እንመልከት፦
1ኛ ዜና 28፥5 *በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን* ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል።
1ኛ ዜና 29፥23 *"ሰሎሞንም በአባቱ በዳዊት ዙፋን ላይ ተቀመጠ"*፥ ተከናወነለትም፤ እስራኤልም ሁሉ ታዘዙለት።

የዳዊት ዙፋን የእግዚአብሔር ዙፋን ነው፥ ዳዊትም ሆነ ሰለሞን የተቀመጡት በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ነው። ታዲያ የእግዚአብሔር እና የዳዊት ዙፋን አንድ ስለሆነ ዳዊት ይመለካልን? እንደ ባይብሉ ኢየሱስም የተሰጠው ዙፋን የዳዊት ዙፋን ነው፦
ሉቃስ 1፥32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ *ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል*።

በእግዚአብሔር እና በበጉ ዙፋን ላይ ከኢየሱስ ጋር የሚቀመጡ አማንያንም ጭምር ናቸው፦
ራእይ 3፥21 እኔ ደግሞ ድል እንደ ነሣሁ *"ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ"*፥ ድል ለነሣው *"ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ"* ዘንድ እሰጠዋለሁ።

በዙፋኑ ላይ የሚቀመጡት አማንያንስ ይመለካሉን? ሲጀመር ኢየሱስ ዙፋኑን ከጌታ አምላክ በስጦታ ያገኘው ነው፥ ሲቀጥል እግዚአብሔር ለኢየሱስ የሰጠውን ነገር ሁሉ ለአማንያንም ይሰጣል፦
ሮሜ 8፥32 *"ከእርሱ ጋር ደግሞ "ሁሉን ነገር" እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?*

"ሁሉን ነገር" የሚለው ይሰመርበት። ለወልድ የተሰጠው "ሁሉ ነገር" እግዚአብሔር ከኢየሱስ ጋር ሁሉን ነገር ለአማንያን ይሰጣል። ለምሳሌ ሥልጣን፣ ፍርድ፣ ንግሥና፣ ዙፋን ወዘተ። ኢየሱስ ምንም የራሱ ነገር የለውም። ሁሉንም በስጦታ ያገኘው ነው፦
ሉቃስ 10፥22 *"ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል"*።
ዮሐንስ 17፥10 *"የእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው፥ የአንተውም የእኔ ነው"*፤ እኔም ስለ እነርሱ ከብሬአለሁ።

የኢየሱስ የሆነ ሁሉ ከአብ የተሰጠው ስለሆነ "የእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው" አለ፥ ግን የእግዚአብሔር የሆነ ሁሉ የኢየሱስ ስላልሆነ "የአንተውም የእኔ ነው" አለ እንጂ "የአንተ "ሁሉ" የእኔ ነው" አላለም። የአንተ ዙፋን የእኔ ነው ማለቱ ነው፥ የእግዚአብሔር ዙፋን የዳዊት ዙፋን ነው እንደማለት ነው። ከሌላ ማንነት ሥልጣን፣ ፍርድ፣ ንግሥና፣ ዙፋን እረ ሕይወትም ሳይቀር የተሰጠው ማንነት በፍጹም አይመለክም፦
ዮሐንስ 5፥26 አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ *"ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና"*።

ሕይወት አልባ የነበረውን የኢየሱስን ማንነት ሕይወት በመስጠት ወደ ህልውና ያመጣ ማንነት በእውነት ሊመለክ ይገባዋል።
ኢየሱስ የትምህርቱ ጭብጥ፦ “አላህ ጌታዬና ጌታችሁ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት” የሚል ነው፤ አምላካችን አላህም ኢየሱስ ተናገር ብሎ ያዘዘው ቃል “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” ማለትን ነው፦
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ
3፥51 *”አላህ ጌታዬና ጌታችሁ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት”* ፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» አላቸው፡፡ إِنَّ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ ۗ هَٰذَا صِرَٰطٌۭ مُّسْتَقِيمٌۭ

ስለዚህ አንድ ተመላኪ አለ እርሱም ኢየሱስን መልእክተኛ አድርጎ የላከ አላህ ብቻ ነው። እርሱም፦ "እኔን ብቻ አምልኩኝ" ይላል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አንዱ አምላክ እና በጉ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

አንዱ አምላክ አላህ ኢየሱስን ሲልከው፦ "ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ" እንዲል ነው፦
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

ነገር ግን ሰዎች ዛሬ ፍጡር የሆነውን ኢየሱስን ሲያመልኩ ይታያል። ይህ ስህተት ቢሆንም ኢየሱስ አምልኮ ይገባዋል ብለው ድምዳሜ ላይ ከአደረሳቸው አናቅጽ መካከል አንዱ እንይ፦
ራእይ 5፥13 *"በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው እና ለበጉ ይሁን ሲሉ ሰማሁ። አራቱም እንስሶች፦ አሜን አሉ፥ ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱለት"*።
καὶ πᾶν κτίσμα ὃ ἐν τῷοὐρανῷ καὶ ἐπὶ τῆςγῆς καὶ ὑποκάτω τῆςγῆς καὶ ἐπὶ τῆςθαλάσσης, καὶ τὰ ἐναὐτοῖς πάντα, ἤκουσαλέγοντας, Τῷκαθημένῳ ἐπὶ τῷθρόνῳ καὶ τῷ ἀρνίῳ ἡεὐλογία καὶ ἡ τιμὴ καὶἡ δόξα καὶ τὸ κράτοςεἰς τοὺς αἰῶνας τῶναἰώνων. καὶ τὰ τέσσαρα ζῷαἔλεγον, Ἀμήν: καὶ οἱπρεσβύτεροι ἔπεσανκαὶ προσεκύνησαν. 

እዚህ አንቀጽ ላይ "በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም" በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለአንድ አምላክ እና ለበጉ ቀርቧል። ግን "አምልኮ" ቀርቧል የሚል ሽታው የለም። ይልቁንም በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው እና በጉን ለመለየት "ካይ" καὶ ማለትም "እና" የሚል መስተጻምር ይጠቀማል። ሲጀመር ምስጋና የተገባው ማንነት ሁሉ አምልኮ ቀረበለት ብሎ መደምደም ስህተት ነው፥ ምስጋና የሚገባው ያህዌህ ቢሆንም ለቅኖች እና በግፍ መከራን የሚቀበል ሰው እግዚአብሔርን እያሰበ ኃዘንን ቢታገሥ ምስጋና ይገባቸዋል፦
መዝሙር 18፥3  *"ምስጋና የሚገባውን ያህዌህ እጠራለሁ"*፥ ከጠላቶቼም እድናለሁ።
መዝሙር 33፥1 ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ *"ለቅኖች ምስጋና ይገባል"*።
1ኛ ጴጥሮስ 2፥19  በግፍ መከራን የሚቀበል ሰው እግዚአብሔርን እያሰበ ኃዘንን ቢታገሥ *"ምስጋና ይገባዋልና"*።

በጉ ባለጠግነት ክብር ሕይወትም ተገባው ማለት ትህትና ተገባው ማለት ነው፥ ምክንያቱም ትሕትናና ባለጠግነት፣ ክብር፣ ሕይወትም ነው፦
ምሳሌ 22፥4  *"ትሕትና እና እግዚአብሔርን መፍራት ባለጠግነት ክብር ሕይወትም ነው*።

ክብር ለነገሥታት የሚሰጥ አንድ አምላክ ነው፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ ተብሏል፦
ዳንኤል 2፥37  አንተ፥ ንጉሥ ሆይ፥ የሰማይ አምላክ መንግሥትንና *"ኃይልን፥ ብርታትንና ክብርን የሰጠህ"* የነገሥታት ንጉሥ አንተ ነህ።
ሮሜ 13፥7 ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን፥ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ *"ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ"*።

እንግዲህ ክብርና ምስጋና የሚገባቸው እነዚህ አካላት እየተመለኩ ነው ብሎ መደምደም ቂልነት ነው። ሲቀጥል አንድ ነቢይ ከአንዱ አምላክ ጋር ምስጋና ክብር ተቀበለ ማለት ያን ነቢይ መመለክ ይገባዋል ብሎ ድምዳሜ ላይ መድረስ ከተቻለ ዳዊት ተመላኪ ነበር ማለት ነው፦
1 ዜና 29፥20 ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ፦ አምላካችሁን ያህዌህን ባርኩ፡ አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባታቸውን አምላክ ያህዌህን ባረኩ፥ *"ራሳቸውንም አዘንብለው ለያህዌህ እና ለንጉሡ ሰገዱ"*።

ጉባኤውን ሁሉ ራሳቸውንም አዘንብለው ለያህዌህ እና ለንጉሡ ሰገዱ ማለት ዳዊት ከያህዌህ ጋር ተሰግዶለታል። እና ዳዊት አምልኮ ተቀብሏልን? አይ፦ "ስግደት የአምልኮ ክፍል እንጂ ስግደት በራሱ አምልኮ አይሆንም፥ ለያህዌህ የባሕርይ ሲሆን ለዳዊት የጸጋ ነው" ከተባለ እንግዲያውስ ምስጋና ክብር የአምልኮ ክፍል እንጂ ምስጋና ክብር በራሱ አምልኮ አይሆንም፥ ለያህዌህ የባሕርይ ምስጋና ክብር ሲሆን ለበጉ የጸጋ ምስጋና ክብር ነው።
ሢሰልስ "ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱለት" ይላል፥ ሽማግሌዎቹም ወድቀው የሰገዱት ለአብና ለወልድ ቢሆን ኖሮ "ሰገዱላቸው" ይባል ነበር። ነገር ግን ሽማግሌዎቹም ወድቀው የሰገዱት ለበጉ ሳይሆን በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለእግዚአብሔር ነው፦
ራእይ 19፥4 ሀያ *"አራቱም ሽማግሌዎችና አራቱ እንስሶች በፊታቸው ተደፍተው በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለእግዚአብሔር፦ አሜን፥ ሃሌ ሉያ፡ እያሉ ሰገዱለት"*።
ራእይ 4፥10 *"ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ*።
ራእይ 11፥16 በእግዚአብሔርም ፊት በዙፋኖቻቸው የተቀመጡ *"ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር እየሰገዱ"*፡

ሲያረብብ በጉ መጥቶ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ከእግዚአብሔር መጽሐፍ መቀበሉ በራሱ በጉ እና በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው ሁለት የተለያዩ ምንነት እና ማንነት ናቸው፦
ራእይ 5፥7 *"መጥቶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠ ከዚያ ከቀኝ እጁ መጽሐፉን ወሰደው"*።
ራእይ 5፥13 *"በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው እና καὶ ለበጉ"* ይሁን ሲሉ ሰማሁ።

"ካይ" καὶ ማለት "እና" ማለት ሲሆን ይህ መስተዋድድ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው እና በጉን ሁለት ማንነቶች እንደሆኑ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው። በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው ምንነቱ ጌታ አምላክ መባሉ ኢየሱስ ደግሞ በግ መባሉ ሁለት ምነነቶች እንደሆኑ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፦
ራእይ 21፥22 *"ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እና በጉ መቅደስዋ ናቸውና"* መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም።

ልብ አድርግ "ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ" እና "በጉ" ሁለት ማንነት እንደሆኑ ለማሳየት "ናቸው" በሚል የብዜት አያያዥ ግስ ተቀምጧል፥ በተጨማሪም "እና" በሚል መስተጻምር ተለይተዋል። ስለዚህ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ" እና "በጉ" ሁለት ኑባሬ ናቸው። እንደ ባይብሉ በግ የሚታረድ ስጋ ስለሆነ ስጋ ደግሞ አምልኮ አይገባው። በነገራችን ላይ "በግ" የሚለውን ተርም እኛ ሙሥሊሞች አንቀበለም። ዋናው ነጥባችን ኢየሱስ አምልኮ አይገባውም ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዒሣ አይመለክም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

17፥81በልም *«እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»* وَقُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ ۚ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا

ሚሽነሪዎች እኛ ሙሥሊሞች ክርስትና ላይ ላስነሳነው ስሙር ሙግት የልብ ፍልጠት፣ የራስ ምታት፣ የሆድ ቁርጠት፣ የጎን ውጋት እና የእግር ቁርጥማት ይዟቸው እንደሆነ እልሃቸው ያሳብቅባቸዋል። 
ከእነዚህ ኃሳውያንና ነውጠኞች መካከል ክርስቲያን ፕሪንስ፦ “ዒሣ በቁርኣን ይመለካል” እያለ ቧጦና ሟጦ ያቅሙን ሲፍጨረጨር እናያለን፥ እስቲ ለዚህ ድምዳሜ አደረሰኝ ያለውን አንቀጽ በሰከነና በሰላ አእምሮ እንመልከት፦
9፥31 *ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊያመልኩ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን፣ ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፥ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም*፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው፡፡ اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا إِلَـٰهًا وَاحِدًا ۖ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ سُبْحَانَهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ

ክርስቲያን ፕሪንስ ይህንን አንቀጽ፦ "ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን ከአላህ እና ከመርየምን ልጅ ከአልመሲሕንም ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ" ብሎ ዒሣ ከአላህ ጋር እንደሚመለክ ለማሳየት ይሞክራል። እንደዛ ለማለት "አላህ" ከሚለው ቃል በፊት "ሚን ዱኒ" مِّن دُونِ ማለትም "ከ እና ሌላ" የሚለው መስተዋድድ የያዘ ቃል "ወ" وَ ከሚለው መስተጻምር በኃላ "ሚን ዱኒ" مِّن دُونِ የሚለው መስተዋድድ የያዘ ቃል ለዒሣ ገብቶ "ወሚን ዱኒል መሢሕ" وَمِّن دُونِ الْمَسِيح
መሆን ነበረበት። በጥቅሉ እንደ እርሱ ምኞት፦
اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّه وَمِّن دُونِ َالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَم
መሆን ነበረበት፥ ይህ ደግሞ አልሆነም። ለማንኛውም ተመሳሳይ ሰዋስው እስቲ እንመልከት፦
65፥4 *"እነዚያም ከሴቶቻቸው ከአደፍ ያቋረጡት ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሦስት ወር ነው፡፡ እነዚያም ገና አደፍን ያላዩት እንዲሁ፡፡ የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው ከእርግዝናቸውን እስከ መውለድ ነው፡፡ አላህንም የሚፈራ ሰው ከነገሩ ሁሉ ለእርሱ መግራትን ያደርግለታል፡፡ وَاللَّائِي يَئِسْنَ مِنَ الْمَحِيضِ مِن نِّسَائِكُمْ إِنِ ارْتَبْتُمْ فَعِدَّتُهُنَّ ثَلَاثَةُ أَشْهُرٍ وَاللَّائِي لَمْ يَحِضْنَ ۚ وَأُولَاتُ الْأَحْمَالِ أَجَلُهُنَّ أَن يَضَعْنَ حَمْلَهُنَّ ۚ وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَل لَّهُ مِنْ أَمْرِهِ يُسْرًا

"እነዚያም ከሴቶቻቸው ከአደፍ ያቋረጡት" وَاللَّائِي يَئِسْنَ مِنَ الْمَحِيضِ مِن نِّسَائِكُمْ
የተባሉት ያረጡ ሴቶች"Menopause" ምናልባት ካረገዙ ተብሎ ቢጠረጠር የዒዳህ ጊዜ ሦስት ወር ነው፥ “ዒዳህ” عِدَّة ማለት ሁለት ጥንዶች ከተጋቡ በኃላ ተራክቦ አድርገው ከዚያም አለመግባባት ቢፈጠር ፍቺ ለማድረግ ቢያስቡ ቅድሚያ ነፍሰ-ጡር መሆኗን ለማረጋገጥ የሚቆይበት የሦስት ወር ጊዜ ቆይታ ነው። በመቀጠል "ወ" وَ በሚል አያያዥ መስተጻምር በመጠቀም የዒዳህ ጊዜ ሦስት ወር የሚለው "እነዚያም ገና አደፍን ያላዩት" وَاللَّائِي لَمْ يَحِضْنَ
የተባሉትንም እንደሆነ ለማሳየት ገብቷል፥ "እነዚያም ገና አደፍን ያላዩት" የተባሉት ለዐቅመ-ሐዋ ደርሰው ተራክቦ አድርገው ግን የወር አበባ መምጣቱ ካልታየ ለእነርሱም የዒዳህ ጊዜ ሦስት ወር ነው።
በተመሳሳይ ሰዋስው፦ "ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ" اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ
ካለ በኃላ በመቀጠል "ወ" وَ በሚል አያያዥ መስተጻምር በመጠቀም "ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ" የተባለው በተጨማሪ "የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም" وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَم
እንደሆነ ለማሳየት ገብቷል።
ስለዚህ መልእክቱ፦ "እነዚያም ከሴቶቻቸው ከአደፍ ያቋረጡት እና እነዚያም ገና አደፍን ያላዩት ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሦስት ወር ነው" ማለት ከሆነ በተመሳሳይም፦ "ሊቃውንቶቻቸውን እና መነኮሳታቸውን የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ" ይሆናል።
ሁለተኛው ዒሣ ነቢይ እንደሚሆን በእናቱ አንቀልባ እያለ ተናግሯል፦
19፥30 ሕፃኑም አለ «እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ፡፡ *”መጽሐፍን ሰጥቶኛል፥ ነቢይም አድርጎኛል”*፡፡» قَالَ إِنِّي عَبْدُ اللَّهِ آتَانِيَ الْكِتَابَ وَجَعَلَنِي نَبِيًّا

ለማንም ነቢይ አላህ መጽሐፍንና ጥበብን ነቢይነትንም ሊሰጠውና ከዚያም ለሰዎች «ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ኾኑ» ሊል አይገባውም፦
3፥79 *ለማንም ሰው አላህ መጽሐፍንና ጥበብን ነቢይነትንም ሊሰጠውና ከዚያም ለሰዎች «ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ኾኑ» ሊል አይገባውም*፡፡ مَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُؤْتِيَهُ اللَّهُ الْكِتَابَ وَالْحُكْمَ وَالنُّبُوَّةَ ثُمَّ يَقُولَ لِلنَّاسِ كُونُوا عِبَادًا لِّي مِن دُونِ اللَّهِ

ሁልጊዜም ከአምልኮ ጋር በተያያዘ "ሚን ዱኒ" مِن دُونِ የሚለው መስተዋድድ የሚገባው ለአላህ ብቻ ነው፦
5፥116 አላህም፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! አንተ ለሰዎቹ፡- *እኔን እና እናቴን "ከአላህ ሌላ" አምላኮች አድርጋችሁ ያዙ ብላሃልን?»* በሚለው ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ قَالَ اللَّهُ يَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ أَأَنتَ قُلْتَ لِلنَّاسِ اتَّخِذُونِي وَأُمِّيَ إِلَـٰهَيْنِ مِن دُونِ اللَّه

እዚህ አንቀጽ ላይ ዒሣ እኔነቱ ከአላህ ሌላ ማንነት ሆኖ ቁጭ ብሏል። "ሚን ዱኒ" مِن دُونِ ውስጥ እርሱም እናቱም አልተካተቱም። ከዚያ ይልቅ ነቢይ እንደመሆኑ መጠን አላህ እንዲናገር ያዘዘው ቃል፦ "ጌታዬን እና ጌታችሁን አላህን አምልኩ" ነው፦
117 «በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል፦ *"ጌታዬን እና ጌታችሁን አላህን አምልኩ" ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም"*፡፡ በውስጣቸውም እስካለሁ ድረስ በእነርሱ ላይ መስካሪ ነበርኩ፡፡ በወሰድከኝም ጊዜ አንተ በእነርሱ ላይ ተጠባባቂ ነበርክ፡፡ አንተም በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ ነህ፡፡» مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَا أَمَرْتَنِي بِهِ أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ ۚ وَكُنتُ عَلَيْهِمْ شَهِيدًا مَّا دُمْتُ فِيهِمْ ۖ فَلَمَّا تَوَفَّيْتَنِي كُنتَ أَنتَ الرَّقِيبَ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنتَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ

ስለዚህ ዒሣ በቁርኣን ይመለካል ብሎ መዳከር ሰማይን እንደመቧጠጥ ነው አትልፋ፥ እንደ ጓያ ነቃይ የፍለፊቱን አትውሰድ! በጥልቀት አጥና። አየህ ሐሰት በእውነት ፊት እሳት የነካው ሰም፣ ጸሐይ ያየው ቅቤ፣ ነፋስ የጎበኘው አቧራ ይሆናል፦
17፥81በልም *«እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»* وَقُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ ۚ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሙግት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥125 *"ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃት እና በመልካም ግሳጼ ጥራ፡፡ በዚያችም እርሷ መልካም በኾነችው ዘዴ ተሟገቷቸው"*፡፡ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ቅን የኾኑትን ሰዎች ዐዋቂ ነው፡፡ ادْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ ۖ وَجَادِلْهُم بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِ ۖ وَهُوَ أَعْلَمُ بِالْمُهْتَدِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ተሟገቷቸው" ለሚለው ቃል የገባው "ጃዲልሁም" جَادِلْهُمْ ሲሆን "ጃደሉ" جَٰدَلُ ማለትም "ተሟገተ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ነው። "ጀደል" جَدَل ማለት "ሙግት"argument" ማለት ነው። "ዳዒ" دَاعِى ማለት "ጠሪ" ማለት ሲሆን "ደዕዋህ" دَعْوَة ማለት ደግሞ "ጥሪ" ማለት ነው። አንድ ዳዒ ዳዕዋው መልካም ሙግት መሆን አለበት፥ ይህ ሙግት መልካም ሙግት የሚሆነው በብልሃት እና በመልካም ግሳጼ ወደ አላህ ሰዎችን ሲጠራ ነው። "ሒክማህ" حِكْمَة የሙግት "ጥበብ" ሲሆን "መውዒዛህ" مَّوْعِظَة ደግሞ የሙግት "መርሕ" ነው። ለሙግት ጥበብ ዐቅል ወሳኝ ነጥብ ነው፥ “ዐቅል” عقل ማለት “ግንዛቤ”Metacognition” ማለት ሲሆን አላህ በቁርአን “ለዐለኩም ተዕቂሉን” لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُون ይለናል፦
2፥242 እንደዚሁ አላህ አንቀጾቹን *ትገነዘቡ ዘንድ* ለእናንተ ያብራራላችኋል፡፡ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمْ ءَايَٰتِهِۦ لَعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

ለሙግት መርሕ ደግሞ ነቅል ወሳኝ ነጥብ ነው፥ “ነቅል” نفل ማለት “ወሕይ” وَحْى ማለት ነው፤ ለዚህም አምላካችን አላህ፦ “አፈላ ተዕቂሉን” أَفَلَا تَعْقِلُون ይለናል፦
21:10 *ክብራችሁ በውሥጡ ያለበትን መጽሐፍ ወደ እናንተ በእርግጥ አወረድን፤ አትገነዘቡምን*? لَقَدْ أَنزَلْنَآ إِلَيْكُمْ كِتَٰبًۭا فِيهِ ذِكْرُكُمْ ۖ أَفَلَا تَعْقِلُونَ

የሙግት ነጥብ"premise" አቅርቦ ለመሞገትና ለመሟገት ዐቅልም ሆነ ነቅል ያስፈልጋል። ቁርኣንን ዳዕዋህ አድርጎ ለመሞገትና ለመሟገት ቁርኣን የወረደበትን ቋንቋ፣ ሰዋስው፣ ዐውድ፣ ተዛማች ቃላት(text) እና ሰበቡ አን-ኑዙል መረዳት ግድ ይላል። ሺዐህ የሚባሉት ራፊዳህ ቁርኣንን የሚተረጉሙበት መንገድ "ባጢን" ْبَاطِن ማለትም "ስውር ትርጉም"esoteric" ይባላል። ይህ አፈሣሰር ቁርኣን የወረደበትን ዐውድ፣ ቋንቋ፣ ሰዋስው፣ ተዛማች ቃላት(text) እና ሰበቡ አን-ኑዙል ያማከለ ሳይሆን “ተእዊል” تَأْوِيل ማለት “ትርጉም” በመስጠት መተርጎ ነው። ቁርኣን የወረደበትን ዐውድ፣ ቋንቋ፣ ሰዋስው፣ ተዛማች ቃላት(text) እና ሰበቡ አን-ኑዙል ያማከለ አፈሳሰር "ዛሂር" ظَّاهِر ማለትም "ግልፅ ትርጉም"exoteric" ይባላል።
የዛሂር አፈሣሰር የቁርኣንን መሠረትና ውቅር፣ ዋልታና ማገር፣ ጥልቀትና ስፋት፣ ድርና ማግ ለመረዳት ጉልህ ሚና አለው። የዛሂር አፈሣሰር አውታር፣ ምህዋር እና ምህዳር ዐረቢኛ ነው፥ ዐረቢኛ ለቁርኣን ግንባዜ እንደ እንሾሽላ መዋቢያ፣ እንደ ኩል መኳያ፣ እንደ ሽቶ ለመሸተት እና ለሙያዊ ቃላት ቅመራ ግብዐት ነው፦
43፥3 *እኛ ታውቁ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን አደረግነው*፡፡ إِنَّا جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

ለምሳሌ ባጢኒያህ “የድ” يَد ማለትም "እጅ" የሚለው ቃል ሁልጊዜ "ኃይል" በሚል ይተረጉሙታል፥ ግን "እጅ" የአላህን ህላዌ ባሕርይ ለማመልከት መጥቷል፦
38፥75 አላህም «ኢብሊስ ሆይ! *በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት* ከመስገድ ምን ከለከለህ? አሁን ኮራህን? ወይስ ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?» አለው፡፡ قَالَ يَٰٓإِبْلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسْجُدَ لِمَا خَلَقْتُ بِيَدَىَّ ۖ أَسْتَكْبَرْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ ٱلْعَالِينَ

“የደየ” ِيَدَىَّ ማለት ሙተና”dual” ነው፥ ይህንን ቃል “ኃይል” ብለን እንዳንተረጎግም ቋንቋው አይፈቅድልንም። ምክንያቱም ሁለት “ኃይል” የሚባል ቃል ትርጉም አልባ ነውና። ባይሆን የአላህ እጅ ከፍጡራን እጅ ጋር ሳናመሳስል መቀበል ነው፦
48፥10 እነዚያ ቃል ኪዳን የሚጋቡህ ቃል ኪዳን የሚጋቡት አላህን ብቻ ነው፡፡ *"የአላህ እጅ ከእጆቻቸው በላይ ነው"*፡፡ إِنَّ ٱلَّذِينَ يُبَايِعُونَكَ إِنَّمَا يُبَايِعُونَ ٱللَّهَ يَدُ ٱللَّهِ فَوْقَ أَيْدِيهِمْ 

የአላህ እጅ ከእጆቻቸው በላይ ነው ማለት የአላህ እጅ ከፍጡራን እጆች ተለይቶ የበላይ ነው ማለት ነው። ይህንን ያለ ተክይፍ፣ ያለ ተምሢል፣ ያለ ተዕጢል እና ያለ ተሕሪፍ የአላህ ንግግር ላይ በተቀመጠው መሠረት መቀበል ብቻ "ተፍዊድ" تفويض ይባላል። ተፍዊድ የቀደምት ሰለፎች የተረዱበትን "ቢላ ከይፈ" بلا كيف‎ ማለትም "ያለ እንዴትነት" መረዳት ነው። የሙዕተዚላህ አብነት"School of theology" ልክ እንደ ራፊዳህ ባጢን አፈሣሰር ቢኖራቸው የማቱሪዲያህ አብነት እና የአሽዐሪያህ አብነትሽ ከባጢንም ከዛሂርም አፈሣሰር ይጠቀማሉ።

ለኢሥላም ዘብ እና አበጋዝ የሆኑ ዐቃቢያነ ኢሥላም የሚባሉት ሙሥሊም ምሁራን ለኢሥላም ዐቅብተ እምነት የዛሂርን አፈሣሰርን ተመራጭ አርገው ሰሟገቱ ፍሬአማ ሆነዋል።
"ዐቅብተ እምነት" ማለት "የእምነት ጥበቃ" ወይም "የእምነት ዘብ" ማለት ነው፥ በዚህ መስክ የተሰማሩ ደግሞ ተባታይ ከሆነ "ዐቃቤ እምነት" አንስታይ ከሆነች "ዐቃቢት እምነት" ትባላለች። "ዐቃቢያን" ደግሞ የዐቃቤ ብዙ ቁጥር ነው። "አፓሎጄቲክስ"Apologetics" የሚለው የኢንግሊሹ ቃል "አፓሎጂአ" ἀπολογία ማለትም "መከላከል" ከሚለው ከግሪክ ኮይኔ ቃል የመጣ ነው። ለኢሥላም ዘብ እና አበጋዝ የሆኑ ሙሥሊሞች ዐቃቢያነ ኢሥላም ይባላሉ።
የዐውድ፣ የቋንቋ፣ የሰዋስው እና የተዛማች ሙግት አፈሣሠር “ተፍሢር ቢ አር-ረእይ” التفسير بالرأي‎ ወይም “አት-ተፍሢር ቢ አድ-ዲራያህ” التفسير بالدراية‎ ይባላል። በአል-በይዷዊይ የተዘጋጀው አንዋረል ተንዚል እና በኢማም ፈኽሩል ዲኑል ራዚ የተዘጋጀው መፋቲሑል ገይብ በዚህ አፈሣሠር ተመራጭ ነው።
የሰበቡ አን-ኑዙል አፈሣሠር ነቢያችን”ﷺ” እና ሶሓባዎች በአስተላለፉት መረዳት “አት-ተፍሢር ቢል መእሱር” التفسير بالمأثور‎ ወይም “አት-ተፍሢር ቢ አር-ሪዋያህ” التفسير بالرواية‎ ይባላል። በኢብኑ ጀሪር አጥ-ጠበሪ የተዘጋጀው ተፍሢሩል ጃሚል በያን እና በኢብኑ ከሲር የተዘጋጀው ተፍሢሩል ቁርኣን አል-ዚዙም በዚህ አፈሣሰር ተመራጭ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፈጣሪ ፆታ አለውን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

42፥11 *የሚመስለው ምንም ነገር የለም*፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِۦ شَىْءٌۭ ۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ

ፈጣሪአችን አላህ የሚመስለው ምንም ሆነ ማንም የለም፥ ፍጡራንም እርሱን አይመስሉትም፤ አላህም ከፍጡራን ጋር የማይመሳሰል የራሱ ስምና ባህርይ አለው፤ ይህንን ስምና ባህርይ ከፍጡራን ጋር ሳናመሳስልና ሳናወዳድር እራሱ ዕውቅና በመሰጠበት መሠረት እንቀበላለን፦
42፥11 *የሚመስለው ምንም ነገር የለም*፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِۦ شَىْءٌۭ ۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ
112፤4 *ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም*፡፡ وَلَمْ يَكُن لَّهُۥ كُفُوًا أَحَدٌۢ

አላህ ፈጣሪ ነው ፍጡርን አይመስልም ከተባለ ታዲያ ለምንድን ነው በቁርአን እራሱ "እርሱ" እና "አንተ" በሚል ተባዕታይ ፆታ የሚጠራው? ለሚለው ጥያቄ መልሱ አምላካችን አላህ ቁርኣንን ዐረቢኛ በማድረግ በዐረቢኛ ሰዋስው አውርዶታል፦
43፥3 *እኛ ታውቁ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን አደረግነው*፡፡ إِنَّا جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
12፥2 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው*። إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

"አን-ነሕው" النحو ማለት "ሰዋስው" ማለት ሲሆን "ጅንስ" جنس ማለት ደግሞ "ፆታ" ማለት ነው፥ የሰዋስው ፆታ በሁለት ይከፈላል፤ አንዱ "ሙዘከር" مذكر ማለትም "ተባታይ"masculine" ሲሆን ሁለተኛው "ሙዐነስ" مؤنث ማለትም "አንስታይ"feminine" ነው፤ ከዚህ ውጪ ልክ እንደ ኢንዶ-ኤሮፕያን ሰዋስው ግዑዝ ፆታ"neutral gender" የሚባል ዐረብኛ ሰዋስው ውስጥ የለም። ታዲያ ፆታ የሌላቸው ማንነት ሆነ ምንነት ምን ብለን እንጠራቸዋለን? ከተባለ አሁንም ለዐረቢኛው ሰዋስው መድረኩን መልቀቅ ነው። አሁንም በዚሁ የሰዋስው ሙግት ስንሄድ ከሁለቱም ማለትም ከሴትና ወንድ ፆታ ውጪ ያለ ማንነት ሆነ ምንነት ሲሆን "ሙፍረድ" مفرد ማለትም ነጠላ"singular" ከሆነ ተባታይ በሆነው በሦስተኛ መደብ “ሁወ” هُوَ ማለትም "እርሱ" የሚለውን እና በሁለተኛ መደብ “አንተ” أَنْتَ ማለትም "አንተ" የሚለውን ተውላጠ-ስም እንጠቀማለን።
ለምሳሌ "ዋሒድ" وَٰحِد ማለት "አንድ" ማለት ሲሆን ተዕባታይ መደብ ነው።
ከአንድ በላይ የሆነ ማንነት ሆነ ምንነት “ጀመዕ” جمع ማለትም "ብዜት"plurar" ከሆኑ አንስታይ በሆነው በሦስተኛ መደብ "ሂየ” هِيَ ማለትም "እርሷ" የሚለውን እና በሁለተኛ መደብ "አንቲ" أنتِ ማለትም "አንቺ" የሚለውን ተውላጠ-ስም እንጠቀማለን።
ለምሳሌ "ሰላሳህ" ثَلَٰثَة ማለትም "ሦስት" አንስታይ ናት፦
4፥171 *”እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ”*፡፡ .. *”«ሦስት ናቸው» አትበሉም”*፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ *”አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው”*፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ ۖ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ ۖ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ ۚ ٱنتَهُوا۟ خَيْرًۭا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا ٱللَّهُ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ سُبْحَٰنَهُۥٓ أَن يَكُونَ لَهُۥ وَلَدٌۭ ۘ لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًۭا

ልብ አድርግ አላህ አንድ ስለሆነ "ዋሒድ" ብለክ "ሁወ" እንጂ "ሂየ" አትልም። የሚያጅበው "ሰላሳ" ثَلَٰثَة በሚለው ቃል መጨረሻ ላይ "ታ" ة የሚባለው "ታእ-መርቡጧ" تاء مربوطة መሆኑ በራሱ ቃሉን አንስታይ ያደርገዋል። ለምሳሌ “መለክ” مَلَك ማለትም “መልአክ” በነጠላ ሙዘከር ነው፥ ነገር ግን በብዜት "መላኢካ-ህ" مَلَائِكَة ማለትም "መላእክት" ሙዐነስ ነው። "መላኢካ" በሚለው መድረሻ ቅጥያ ላይ ያለች "ታ" ة የምትባለው "ታእ-መርቡጧህ" ሙዐነስ ናት፥ ለዚያ ነው እዚህ አንቀጽ ላይ፦ "ናዘት" نَادَتْ ማለትም "ጠራች" የሚል ያለው፦
3፥39 እርሱም በጸሎት ማድረሻው ክፍል ቆሞ ሲጸልይ መላእክት፦ «አላህ በየሕያ ከአላህ በኾነ ቃል የሚያረጋግጥ ጌታም ድንግልም ከደጋጎቹ ነቢይም ሲኾን ያበስርሃል» በማለት *"ጠሩት"*፡፡ فَنَادَتْهُ الْمَلَائِكَةُ وَهُوَ قَائِمٌ يُصَلِّي فِي الْمِحْرَابِ أَنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكَ بِيَحْيَىٰ مُصَدِّقًا بِكَلِمَةٍ مِّنَ اللَّهِ وَسَيِّدًا وَحَصُورًا وَنَبِيًّا مِّنَ الصَّالِحِينَ

"ጠሩት" ለሚለው ቃል "ናዘት-ሁ" َنَادَتْهُ መሆኑን አንስታይ መሆኑን ያሳያል፥ "ቃለ" قَالَ ማለት "አለ" ማለት ሲሆን ተባዕታይ ነው፥ “ቃለት” قَالَت ደግሞ "አለች" ማለት ሲሆን አንስታይ ነው። ይህ ቃል ለመላእክት ጥቅም ላይ ውሏል፦
3፥42 *”መላእክትም ያሉትን”* አስታውስ፡፡ «መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሸ፡፡ አነጻሽም፡፡ በዓለማት ሴቶችም ላይ መረጠሽ፡፡» وَإِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَاكِ وَطَهَّرَكِ وَاصْطَفَاكِ عَلَىٰ نِسَاءِ الْعَالَمِينَ
"ያሉት" ለሚለው “ቃለት” قَالَت በሚል መምጥቷል፥ "ቃለ" በሚለው መድረሻ ቅጥያ ላይ ያለች "ታ" ت "ታእ-መፍቱሓህ" تاء مفتوحة የምትባለው ሙዐነስ ናት፥ ስለዚህ "ቃለት" የሚለው “ቃሉ” قَالُوا ማለትም "አሉ" ለማለት ተፈልጎ ነው፦
2፥30 ጌታህ ለመላእክት፡- «እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ፤» ባለ ጊዜ የኾነውን አስታውስ፤ *”እነርሱም”*፦ «እኛ ከማመስገን ጋር የምናጠራህ ላንተም የምንቀድስ ስንኾን በርሷ ውስጥ የሚያጠፋንና ደሞችንም የሚያፈስን ታደርጋለህን?» *”አሉ”*፡፡ አላህ «እኔ የማታውቁትን ነገር አውቃለሁ» አላቸው፡፡ وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي جَاعِلٌ فِي الْأَرْضِ خَلِيفَةً ۖ قَالُوا أَتَجْعَلُ فِيهَا مَن يُفْسِدُ فِيهَا وَيَسْفِكُ الدِّمَاءَ وَنَحْنُ نُسَبِّحُ بِحَمْدِكَ وَنُقَدِّسُ لَكَ ۖ قَالَ إِنِّي أَعْلَمُ مَا لَا تَعْلَمُون

እዚህ አንቀጽ ላይ "አሉ" ለሚለው “ቃሉ” قَالُوا ማለቱን አስተውል። መላእክት ፆታ የሌላቸው ሴትም ወንድም አይደሉም። ለምን በአንስታይ መደብ ተጠቀመ? ስልን መላእክት ብዙ ማንነቶች ስለሆኑ ሲሆን አላህ ደግሞ አንድ ማንነት ስለሆነ በተባታይ መደብ "እርሱ" "አንተ" "አለ" ተብሎ ተገልጿል።

እሩቅ ሳንሄድ በዐረቢኛ ድምጽ ያላቸው ተነባቢ ፊደላት”sound letters” 28 ሲሆኑ ከእነርሱ ውጥስ 14 ሐርፎች "ሑሩፉል ቀመሪያህ"lunar letters" ተባታይ ናቸው፣ እነርሱም፦
ء ﺏ ﺝ ﺡ ﺥ ﻉ ﻍ ﻑ ﻕ ﻙ ﻡ ﻭ ﻱ ه
የቀሩት 14 ሐርፎች "ሁሩፉ አሽ-ሸምሲያህ"solar letters" አንስታይ ናቸው፣ እነርሱም፦
ﺕ ﺙ ﺩ ﺫ ﺭ ﺯ ﺱ ﺵ ﺹ ﺽ ﻁ ﻅ ﻝ ﻥ
ያ ማለት አስራ አራቱ ቀመሪያህ ሙዘከር ስለሆኑ ወንዶች ናቸውን? አስራ አራቱ ሸምሲያህ ሙዐነስ ስለሆኑ ሴቶች ናቸውን? መልሱ አይ ይህ የዐረቢኛ ሰዋስው ላይ የተለመደ ነው። ፀሐይ "ሂየ” هِيَ ትባላለች፥ ጨረቃ ደግሞ “ሁወ” هُوَ ይባላል፤ እና ፀሐይ ሴት ጨረቃ ወንድ ነውን? ፀሐይ በአንስታይ መደብ ነው የተጠራችው፦
81፥1 *"ፀሐይ "በተጠቀለለች" ጊዜ"*። إِذَا الشَّمْسُ كُوِّرَتْ

"ተጠቀለለች" ለሚለው ቃል የገባው "ከወረት" كُوِّرَتْ የሚለው ሙዐነስ እንጂ "ከወረ" كُوِّرَ የሚለው ሙዘከር አይደለም፦
75፥8 *"ጨረቃም "በጨለመ" ጊዜ"*፡፡ وَخَسَفَ الْقَمَر

"ጨለመ" ለሚለው ቃል የገባው "ኸሠፈ" خَسَفَ የሚለው ሙዘከር እንጂ "ኸሠፈት" خَسَفَتْ የሚለው ሙዐነስ አይደለም።
ስለዚህ አላህ "አንተ" እና "እርሱ" ስለተባለ ፈጣሪ ፆታ አለው ብሎ መደምደም ስህተት ነው። ባይሆን በባይብል እግዚአብሔር ፆታ ከሌለው ወንድም ሴትም ካልሆነ ለምን "አንተ" እና "እርሱ" እንደሚባል የቤት ሥራ ሰጥተናችኃል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም